#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
ከሁለት ወራት በኋላ
...በቤቨርሊ ሪል ስቴት ውስጥ ከሚገኘው የግሬቸን እና አዳም አድለር ቤት
ውስጥ ኒኪ ለሁለት ወራት አብራቸው ቆይታለች፡፡ ቤታቸው ብዙ የእንግዳ
ክፍሎች አሉት። ቤቱ በጥይት ከደረሰባት ቁስል ለማገገም የሚመች ነው።ደልቀቅ ያለ እና በደስታ የተሞላ ቤት ነው። ልጆች የሚሯሯጡበት፣ በሳቅ እና በአብሮነት የሚኖርበት ቤት ስለሆነ ቀለል ብሏታል። ምክንያቱም የኒኪን የማያቋርጡ ሀሳቦች ወደ ሌላ ቀለል ወዳሉ አቅጣጫዎች ማስቀየስ የሚችል ቤት ነው።
“በህይወት አለሽ እኮ ኒክ” እያለች ግሬቸን ሁልጊዜ ኒኪን ታበረታታለች፡፡
“ከሞት ተርፈሻል እኮ፤ ለዚህ ደግሞ የሆነ ምክንያት ሊኖረው ይችላል።”
“አልተረፍኩም ባይሆን ህይወቴን አንድ ሰው አትርፎልኛል። ያውም በአንድ ዘረኛ በወንድነቱ የሚመካ እና ሴቶችን በሚንቅ ሰው እና በጣም አታላይ በሆነ..” ብላ መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰንን የምትገልፅበት ቃላት አጣች። ኒኪ ስለ ጆንሰን ስታስብ በጣም ትናደዳለች። ንዴቷ በቀጥታ በእሱ ላይ ሳይሆን በራሷ ላይ ነው:: ምክንያቱም እሱን በተሳሳተ መንገድ ነው ያሰበችው፡፡ ሌሎችንም ሰዎች ደግሞ ባልተገባ መንገድ ነበር በበጎ መልኩ ስታስብላቸው የነበረው:: ይሄንን ያለፈ ጊዜ ስህተቷን ስታስብ ነው እንግዲህ ሀይለኛ ንዴት የሚይዛት።
“እሱን እኔ አላውቅም” ብላት ግሬቸን በመቀጠልም
እጨነቃለሁ። ኒኪ ለወደፊት ህይወትሽ ምን አስበሻል? እኛ እንወድሻለን እና
ለእኔ ግን ህይወትሽን ያተረፈልኝ ጥሩ ሰው ነው:: ስለ አንቺ ህይወት
የፈለግሽውን ጊዜ ያህል እዚህ ከእኛ ጋር ብትኖሪ ደስተኛ ነን። ነገር ግን ዕድሜ ዘመንሽን ሙሉ እዚህ ወንበር ላይ ተቀምጠሽ ጋዜጣ እያነበብሽ ብቻ
እንድትኖሪ አንፈልግም”
በግሬቸን ምክር መሰረት ሎስ አንጀለስ ውስጥ የምትሠራበትን የቴራፒ
ፍቃዷን መልሳለች፡፡ የሴንቸሪ ሲቲ ቢሮዋን የኪራይ ውልንም አቋርጣለች።
በተጨማሪም ደግሞ ቤንትውድ ውስጥ የሚገኘውን የእሷን እና የሟች ባሏን
ዶውግ ቤት ለሽያጭ አቅርባለች፡፡
የሆነ ጠዋት ላይ ግሬቸን ለልጆቿ ምግ እየቋጠረችላቸው አጠገቧ ለምትገኘው ኒኪ ይህንን አለቻት ኒኪ አንቺ ሀብታም፣ ቆንጆ፣ ጤነኛ እኛ የተማርሽ እኮ ነሽ፤ በዚያ ላይ ደግሞ ወጣት ነሽ ብላ ጉሮሮዋን አጥርታ ኒውዩርክ ሄዳ እንደ አዲስ ኑሮዋን እንድትጀምር እንደ ሁልግዜውም ሁሉ ሙግቷን ጀመረች፡፡
“ወጣት አይደለሁም” አለች ኒኪ፡፡
“መቼስ ከዚህ በኋላ ዕድሜ ዘመንሽን
ሙሉ ብቻሽን መኖር አትፈልጊም?” አለቻት።
አልፈልግም ብለሽ ነው?' ብላ ኒኪ ለራሷ አሰበችና የክርስትና ልጇ ሉቃስ ብስክሌቱን በግቢያቸው በሚገኝ ሣር ላይ በደንብ ሲያሽከረክር አይታው ፈገግ አለች። ዞር ብሎም ሲያያት አውራ ጣቷን ከፍ አድርጋ አድናቆቷን ገልፃለት ወደ ጋዜጣ ንባቧ ተመለሰች፡፡
ዛሬ ሀዶን ዶፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ችሎት ላይ ይቀርባል፡፡ አቃቤ ህጉ፣ ዶፎ የሉዊስ ሮድሪጌዝን የኮርዲል ዕፅ ትርፍ 90 ከመቶውን ለበጎ አድራጎት
ክሊኒካቸው እንደተሰጠ በማስመሰል ገንዘቡን ለሮድሪጌዝ ሲያስተላልፍ
ቆይቷል በሚል ክሱን ያቀርብበታል። በዚህም ልክ እንደ ባይደኖቹ ሁሉ ብዙ
ሚሊዮን ዶላሮችን ማግኘት እንደቻለ ያትታል። ዊሊ ደግሞ ይህንን የአደንዛዥ ዕፅ ገንዘብ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅት በሽያጭ ማዕከሎቹ እና በሚወደው የእግር ኳስ ክለቡ (Ram) ሥር በህገወጥ መንገድ ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ሚስቱ ቫለንቲና ደግሞ ከአደንዛዥ ዕፅ አምራች ከበርቴዎች ጋር ከአሥርት አመታት በላይ አብራቸው ስትሰራ ቆይታለች።የጠፉ ሰዎች አፈላላጊ በጎ አድራጎት ድርጅቷም በህገወጥ የወሲብ ንግድ እና ሰዎችን በህገወጥ በማዘዋወር የተጨማለቀ ገንዘብ ስታገኝ እንደነበረ ከጋዜጣው ላይ ለማንበብ ቻለች::
ከዚህም በላይ ደግሞ ቫለንቲና ባደን አዕምሮዋ ትክክል ያልሆነች ሴት
እንደሆነች ጭምር ጋዜጣው ከዘገበ በኋላ ምናልባትም በእህቷ መሰወርም
እጇ ሊኖርበት እንደሚችል ጋዜጣው ያስቀምጣል። ለቤተሰቦቿ ቅርብ የሆኑ
የበፊት ዘመዶቿ እንደተናገሩት ከሆነ ደግሞ ቫለንቲና በጣም በቁንጅና
በምትበልጣት መንትያ እህቷ ማሪያ ላይ በጣም ትቀና እንደነበር ነው።የቫለንቲና ችሎት ምናልባትም በቅርብ ወራት ላይጀመር ይችላል፡፡ ከዊሊ
ግድያ በኋላ እክስናርድ ውስጥ በሚገኘው የሳይካትሪስት ሆስፒታል ገብታ ህክምናዋን በመከታተል ላይ ትገኛለች፡፡
ዊሊያም ትክክል ነበር ማለት ነው እያለች ኒኪ ሀዘን ውስጥ ሆና ማሰብ ጀመረች። እና ከሉዊስ ሮድሪጌዝ ጋር ስላላት ግንኙነት እንዲሁም ደግሞ በከተማው ስላለው የሙስና ሁኔታ አስቀድሞ ያወቀው ዊሊያምስ ቢሆንም ሚዲያው ግን ለኤፍ.ቢ.አይ ነበር ዕውቅናውን የሰጠው፡፡ ቻርሎቴ ክላንሲም ብትሆን በይፋ በሰው መገደሏን ያሳወቀው ኤፍ.ቢ.አይ ነበር፡፡
ምስኪን ዊሊያምስ” ብላ ኒኪ አሰበች እና “እንዴት ግን በህይወትም ሳለህ እና ሞተህም ቢሆን ዕውቅናን ሊነፍጉህ ቻሉ?”
በየጊዜው የኤል.ኤ.ፒ.ዲ ሪፖርተሮች በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ድረስ ገብተው
ዜና ስለሚሰሩበት በእያንዳንዱ የከተማዋ ጋዜጦች ብቻ ሳይሆኑ እያንዳንዱ
የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን የአዕምሮ ሀኪሞችንና ሌሎችንም በዚህ ጉዳይ ላይ
የጠለቀ አስተያየት የሚሰጡ ሰዎችን ቃለ መጠየቅ እያደረጉ ላለፉት ሁለት
ወራት የከተማውን እና መላውን የሀገሪቱን ህዝብ በሙሉ ከሐሜት እና ከቢዝነስ ዜናዎች ውጪ ትኩረቱን በዚህ ላይ እንዲያደርግ አድርጎት ነበር፡፡
ዛሬ ላይ ደግሞ ሀዶን ችሎት ላይ ቀርቦ ሲወጣ በቴሌቪዥን ስታየው ፊቱ
ላይ የሚታየው ነገር ዕድሜው በ10 ዓመት የጨመረ ስላስመሰለው ኒኪ
አዘነችለት። እርግጥ ነው እሱ እሷን እና ዶውግን አታሏቸዋል። እነርሱንም
ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ለጋሶችን እንዲሁም ደግሞ በየጊዜው በውድ ዋጋ
በአደንዛዥ ዕፅ ጉዳት የተነሳ አንጎላቸው ቀዶ ጥገና የሚሰራላቸውን ሰዎች
ጭምር ነው ያታለለው፡፡
ሮድሪጌዝ ከሚቆርጥለት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች የሚመጣጠን
ገንዘብ ከእነዚህ ታካሚዎቹ ሲያገኝ ነው የኖረው:: ምን ይሄ ብቻ እነዚህ
በየመንገዱ ላይ ክሮክዲል የሚጠቀሙ ደሀ ታካሚዎቹን የሚያክምበት
ክሊኒኩ ከዚህ በኋላ በሰዎች ዘንድ አመኔታን እንዲያጣ በማድረጉ እነዚህ
ገንዘብ የሌላቸው በአደንዛዥ ዕፅ የተጎዱ ሰዎች የት ሄደው ሊታከሙ ይችላሉ? እነዚህ ሁሉ ነገሮች እውነታ ቢሆኑም በእውነታዎች ላይ ተመስርተን ብቻ ለሰዎች ያሉንን የበፊት ስሜቶቻችንን ልናስወግዳቸው አንችልም። ይህም ስለሆነ ዶውግ ባሏ በላይዋ ላይ ከሌላ ሴት ጋር ሄዶባት እና ያቺን ሌንካ የተባለች ሴትን ማስረገዙን አውቃም እንኳን ቢሆን አሁንም ትወደዋለች፡፡ ጉድማን ባልጠበቀችው እና ይሆናል ብላ ባልገመተችው አንፃር ተገኝቶ መጥፎ ፖሊስ መሆኑን እንዲሁም ደግሞ ለእሷ ያስብላት የነበረውን ዊሊያምስን መግደሉን እያወቀችም ቢሆን አሁንም ለእሱ ጥሩ ነገር አላት።ሀዶንም ቢሆን የባሏን ውሽማ ማንነት እያወቀ ቢዋሻትም እንዲሁም ደግሞ አሁን ላይ ያወቀቻቸውን ዘግናኝ ወንጀሎችን ከዕፅ አምራች ከበርቴዎች ጋር መሥራቱን አውቃ እንኳን ለእሱ ያላት ስሜት ሙሉ በሙሉ አልጎሽም።
በጠዋት ላይ በዚህ አይነት ስሜት ውስጥ በነበረችበት ሁኔታ ላይ ነበር እንግዲህ ጓደኛዋ ግሬቸን አዳም ዛሬ ቀኑን ሙሉ ቀረፃ ላይ ነው፤ ስለዚህ ልጆቹን ይዤ ወደ
አንቲንግዶን ቦታኒካል ጋርደን ይዤያቸው ለመሄድ አስቤያለሁ። መቼስ ሦስቱን ልጆቼን ብቻዬን አልችላቸውም እና አብረሽኝ ትሄጂያለሽ?” ያለቻት::
ኒኪም “እኔ እንኳን እቤት ብቆይ እና እረፍት ባደርግ

👍2
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....አስቻለውን የማገናኛውም ቀን ተወሰነ በማግስቱ ሰዓቱ ደግሞ ምግብ ተሰራርቶ ካለቀ በኋላ ወደ ሰባት ወይም ስምንት አካባቢ፡፡ በሚገናኙም ጊዜ የሔዋንን ልቦና ማደነጋገሪያ ዘዴ ተፈጠረ ከዚህ በኋላ ነበር ታፈሡ ወደ አስራ ሁለት ሰአት አካባቢ ወደ ቤቷ የተመለሰችው.
የዛሬው የድግስ ሽርጉድም የዚሁ ዕቅድና ፕሮግራም እንዱ አካል
መሆኑ ነው የሔዋን ህልም ግን የታፈሡን ልብ የባሰ አሸበረውና በባሰ ስጋት ውስጥ ገባች ይቺ ልጅ የዋህ ናትና አምላኳ ምን እየነገራት ይሆን? በማለት፡፡
ያም ሆኖ የድግሱ ስራ ቀጠለ፡፡ በያይነቱ ተካፋፍለው ይሰሯቸው የነበሩ የወጥ ዓይነቶች ሁሉ ደረሰ ቤት ተወለወለ፡፡ ተስተካከለ፡፡ ጊዜውም ደረሰ፡፡ ልክ ከቀኑ ሰባት ሠዓት ተኩል፡፡
የሚመጡትን እንግዶች በውል የምታውቅ ታፈሡ ብቻ ናት፡፡ ትርፌም ዋናው እንግዳ አስቻለው መሆኑን ታውቃለች፡ ታፈሠ ትናንት ማታ በሆነ ሰበብ ወደ ውጭ ጠርታ ለሔዋን ፍንጭ እንዳትሰጥ አስጠንቅቃ የአስቻለውን መምጣት በጆሮዋ ሽክ ብላታለችና፡፡ ሔዋን ግን ምንም ዓይነት ፍንጭ አልነበራትም፡፡ እሷ የምትጠብቀው የማታውቃቸውን የታፈሡን እንግዶች ብቻ ነው። ነገር ግን በዚያ ሠዓት ይመጣል ብላ ያላሰበችው ነው፡፡ ነገር ግን
ድንገት ከሁሉም ቀድማ ዓይኗን ወደ ውጭ በር ጣል ስታደርግ
የምታውቀውና የምትናፍቀው
ነገር ግን በዛ ሰዓት ይመጣል ብላ ያላሰበችው እንግዳ ብቅ ሲል አየችው።በልሁ ቡላማ ሱሪ በነጭና ሰማያዊ ቡራቡሬ
ሽሚዝ ለብሶ ነጣ ያለ ጃኬቱን ትከሻው ላይ አንጠልጥሎ
በፍጥነት ርምጃ እየገሰገሰ ወደ ታፈሡ ቤት መጣ፡፡
«እንዴ! ታፈሠዬ! ባልሁዩ መጣ!» አለች ሔዋን በልሁን ፍልቅቀቅ ብላ
እያየችና ጆርዋን እነታፈሡ ለሚሰጧት መልስ አቁማ::
«መጣ?» ብላ ታፈሡ ቶሎ ብላ ወደ በሩ በመራመድ ላይ ሳለች በልሁ ወዲያው ከች አለ።
«ታዲያስ! እንደምናችሁ?» እያለ እንደ አዲስ ሊስማት ወደ ታፈሡ
ተጠጋ::
«እንኳን ደህና መጣህ በልሁዬ?» አለች ታፈሡም አንገቱን እቅፍ
አድርጋ እየሳመችው፡፡
«ሔዩ?» አለ በልሁ ወደ ሔዋን እየተመለሰ::
«አቤት በልሀዬ!»
ደጋግመው ተሳሳሙ:: በልሁ ልክ እንደ ታፈሡና ሔዋን ትርፌንም
ከሳማት በኋላ ወዲያው ንግግር ጀመረ፡፡ የሮጠና የቸኮለም ይመስል እንደ ማለክለክ ይቃጣዋል፡፡ «እንዴት ነው፣ አዲስ ስሜት አይነበብብኝም?»
«ይመስላል፡፡ ግን ምንድነው?» አለችው ታፈሡ ዓይኖቿ በፍርሀት
እየተርገበገቡና ልቧ ከወትሮው እጥፍ እየመታ»
«አስመራ ደርሼ መጣሁ፡፡»
«እ» አለች ታፈሡ የደነገጠች መስላ ለመታየት እየሞከረች፡፡
«አስቻለውን እግኝቼ ይዤው መጣሁ፡፡»
በልሁና ታፈሡ እርስ በርስ የሚተያዩ ይምሰሉ እንጂ በዓይናቸው ሰረቅ እያረጉ በማየት የሚሰልሉት የሔዋንን ስሜት ነው::
ሔዋን የበልሁን
አስቻለውን እግኝቼ ያዤው መጣሁ የሚል ቃል ስትሰማ ልከ ሳያስብ
ሳይጠረጥር በኃይለኛ ጥፊ ድንገት ጆሮውን እንደተመታ ሰው ሰማይና ምድሩ ተቀላቀለባት፡፡ ዓይኗ ፈጠጠ፡፡ ጥርሷ ገጠጠ፡፡ አፏም ያለ ፍላጎቷ ቧ ብሎ
ተከፈተ፡፡ በአጠቃላይ የአንጎሏ የማሰብ ሥርዓት ተዛባ፡፡ በድን ሆነች፡፡
በልሁ ለጥያቄ ፋታ በማይሰጥ ፍጥነት ቶሎ ቶሎ ይናገር ጀመር ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ
አስቻለው በድንገተኛ አደጋ ምክንያት አንዳንድ የአካል ጉዳቶች ደርሰውበታል፡፡ በእጅና በእግሩ ላይ የፕላስቲክ ልጣፎች
ይታያሉ፡፡ ለጊዜው የሚሄደውም በክራንች ነው፡፡ ፊቱም ላይ ትንሽ
ተጎድቷል:: ነገር ግን የፕላስቲክ ቆዶ ጥገና በተባለ የህክምና ጥበብ በአጭር ጊዜና በአስተማማኝ ሁኔታ ሁሉም ነገር ወደነበረበት ሁኔታ እንደሚመለስ
ሀኪሞች አረጋግጠውልናል፡፡ አለና አሁንም ፈጥኖ በመቀጠል «ልብ በሉ! በዚሁ የህክምና ጥበብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ህክምናውን በተሟላ የሰውነት ስጋ ላይ ማድረግ ስለማይቻል አስቻለው በጣም በጣም እንዲከሳ ተደርጓል፡ለህይወት ማቆያ ብቻ እንጂ በቂ ምግብ አይወስድም፡፡ የመክሳቱም ምክንያት ይኸው ብቻ ነው፡፡ ከስቶ ስታዩት ሌላ ነገር መስሏችሁ እንዳትደነግጡ፡፡ እሺ!»
ፊቱን ወደ ውጭ በር መለስ ሲያደርግ አስቻለውና አጃቢዎቹ
ተከታትለው ብቅ ሲሉ አያቸው፡፡ ወዲያው ደግሞ «ያው አስቻለው እየመጣ ነው፡፡ ወጣ በሉና በእልልታ ተቀበሉት፡ : » አላቸው፡፡
በእርግጥም ሰዎች አስቻለውን አጅበው ከውጭ በር ላይ ደርሰዋል፡፡
ታፈሡና ትርፌ እልልታውን እያቀለጡ ወደ እንግዶቹ ሮጡ፡፡ ሔዋን ግን ከቆመችበት ንቅንቅ አላለችም፡፡ እንደ እንጨት ደርቃ ቀረች፡፡ በልሁ ከተናገረው ቃል እንዱንም አልተረዳችም፡፡ ቀድሞ ነገር ጆሮዋ እንኳ ስለመስማቱ ማንም እርግጠኛ አይደለም፡፡
«ሔዩ» ሲል ጠራት በልሁ ሁኔታዋን ተጠራጥሮት ለመሰለል ያህል፡፡ሔዋን ልክ እንደ አእምሮ ዘገምተኛ ሰው የቴለና የጀለ በሚመስል ድምጽ «እ» አለችው በደመ ነፍስ፡፡
ብቅ ብለሽ አስቻለውን አትቀበይውም እንዴ?»
ሔዋን ግን አሁንም ዝም፡፡ በልሁ ራሱ ክንዷን ያዝ አድርጎ የመጎተት
ያሀል ወስዶ በር ላይ ቢያደርሳትም ከዚያ ማለፍ አልቻለችም፡፡ እንዲያውም
የቤቱን በር የግራ በኩል መቃን ሙጥኝ አለች፡፡ ዓይኗ ከውጭ ከሚመጡት ሰዎች ላይ አልተነቀለም፡፡ ታፈሡና ትርፌ አስቻለውን በመሳም ላይ ናቸው፡፡
ነገር ግን ምን እየተደረገ እንዳለ ለሔዋን አይታዉቃትም፡፡ የአስቻለው አጃቢዎች ካሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌና መርዕድ ሌላ ሦስት የቀድሞ የስራ
ባልደረቦቹ ናቸው ከአስቻለው ጋር
ስድስት ታፈሡና ትርፌ ሴጨመሩ
ስምንት ሆነዋል፡፡ ለሔዋን ግን የሰዎቹ ብዛት አንድ ከተማ ነዋሪ
በሙሉ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣ
መስሎ ነው የሚታያት ሰዎች ስለመሆናቸው እንኳን በውል አይታወቃትም በሰመመን ውስጥ
የሚታይ የአንዳች ፍጡራን
ትርምስምር መሰለዠሎ እንጂ፡፡ በህልም ይሁን በእውን ባለየላት ሁኔታ ሰው ሊመስላት ያልቻለ አንድ ፍጡር በክራንች የሚጎተት መስሎ ይታያታል ጤነኛው እግሩ እንኳ በውል እግር አይመስልም፡ ሱሪው ብቻ ይወዛወዛል፡፡
የፈቱም አጠቃላይ ገፅታ አስፈሪ ጭምብል ያጠለቀ መሰላት ሰው ስለመሆኑ እንኳ እርግጠኛ ሳትሆን
አስቻለው አጠገቧ ደረሰ።
«ሔዩ» አላት አስቻለው ከጤነኛውም ከጉዳተኛውም ዓይኖቹ እንባውን እያፈሰሰ፡፡ ለሔዋን ግን ድምጹ እንኳ የሰው አልመሰላትም፡፡ ስልል ያለና
በጣም የደከመ ነው፡፡ መልስ ሳትሰጠው ፍጥጥ ብላ ብቻ ትመለከተው ጀመር፡፡
«አላወቅሽኝም ሔዩ?»
«ሔዋን አሁንም ዝም፡፡»
«ሳሚው እንጂ ሔዩ!» አለች ታፈሡ አስቻለውን ደገፍ አድርጋ ከጎኑ በመቆም በአሁን ሠአት ከታፈሡ በኩል ለቅሶ የለም። በሔዋን አኳሀን ደንግጣ ሁለመናዋ ደርቋል፡፡ በልሁም ሆነ ሌሎቹ በትኩረት የሚከታተሉት
የሔዋንን ስሜት ነው፡፡ ያሰጋቸውም የልብ ህመምተኛ መሆኗ ነው፡፡
ሔዋን አሁንም በዚያ በተረበሽ ስሜት ውስጥ ሆኗ ልትገደል የተከበበች አውሬ ይመስል ዓይኗን በሁሉም ላይ ከማንከራተት በስተቀር ምላሽ መስጠት አልቻለችም አስቻለው ራሱ «ቀድም የፈራሁት ይሄን ነበር
ዘመዶቼ! አለና እያለቀሰ ፈቱን በሔዋን ትክሻ ላይ አሳረፈው፡፡ እዚያው ላይ ተደፍቶ ይንሰቀሰቅ ጀመር፡፡

👍7
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
የአዳራሹ በሮች ወለል ብለው ተከፈቱ ወርቅማው ብርሃን ደረጃዎቹን አጥለቀለቃቸው » ሁለት የወንድ አሽሮች ከበሩ ቆሙ አንዱ ከነበረበት ሲቆም
ሌላው ወደ ሰረገላው ተጠጋና ሳቤላን ደግፎ ሲያወርዳት ፒተር መሆኑን 0ወቀችው » ምን ያደርጋል ፒተር እንደምነህ ? " የማትው ነገር ! ለጊዜው የምትናገረውም ጠፋት ድንግርግር አላት ድምጿም ድክምክም አለ "
“ ሚስዝ ካርላይል ከቤት አሉ ?” አለች "
“ አዎን አሉ "
ወዲያው ጆይስ ልትቀበላት ወደፊት ቀረበችና “ማዳም ቬን ይመስሉኛል ? አለቻት " " በዚህ በኩል ይምጡ ” አለቻት በአክብሮት።
ሳቤላ ግን ዕቃዋን ያወረደው አሽከር በትክክል መግባታቸውን የምትመለከት መስላ ከኮሪደሩ ቆም ብላ ጠበቀች " ዋናው ሐሳቧ ግን ጆይስ ወደ ሚስተር ካርላይልና ሚስዝ ካርላይል ዘንድ የምታስገባት ስለ መሰላት ጥቂት 0ረፍ ለማለት ነው » ጆይስ ግን እሳት ይነድበት ከነበረው ሳሎን አስገብታ ሳሎንዋ እሱ መሆኑን ነግራ “ መኝታዎን እስካሳይዎ ድረስ ምን ልዘዝልዎ ? አለቻት
“አንድ ስኒ ሻይ” አለች ሳቤላ " ጆይስ ሻይ እንዲዘጋጅ አዘዘችላትና ሔዶች" ሳቤላም ልቧ እየመታ ዱሮ የራሷ ከነበረው ክፍል ዐልፋ ወደ ፎቅ ወጡ " የበፊቱ
መኝታ ቤቷና መልበሻ ክፍሏ ተከፍተው ስለ ነበር በናፍቆት አየቻቸው " ወደ ሌላ ባለቤት ከመዞራቸው በቀር ውበታቸውና ያማረ ዝግጅታቸውን ሁሉ አልቀነሱም "የነበሩት ጌጦቻቸው አልተነኩም ። ከሶፋው ላይ አንድ መጽሐፍ እና አንድ ያንገት መደረቢያ » አልጋው ላይ ተቀይሮ የተጣለ የመስለ አንድ የሐር ቀሚስ ይታያሉ " ቀጠለችና ዱሮ ሳቤላ ሙሽራ ሁና ወደ ኢስት ሊን በመጣች ጊዜ ' ሚስ ኮርኒሊያ በኋላ ለቃው ወደ ምድር ቤት እስክትወርድ ድረስ ይዛው ወደ ነበረው ክፍል ጆይስ ፊት ፊት አየመራች ሳቤላ እየተከተለች ገቡ " ዕቃውን ከጋሪው ያወረደውና አንድ ረዳቴ ሆነው አስገቡት " ጆይስ የሚያስቀምጥበትን አሳየችው " ሰውየው ጓዟን አደራጅቶ የታሰሩትን ሳጥኖች ፈትቶ ወጣ " ሳቤላ እንደ ሐውልት ድርቅ ብላ ቁማ ቀረች " ልብሷን ለመቀየር እንኳን አልሞከረችም "
“ ሌላ ምን የማደርግልሽ ነገር አለ ?” አለቻት ጆይስ »
ከመድረሷ ጀምሮ እንዳትታወቅ መሥጋት የጀመረችው በተለይም የጆይስን ንቁ ዐይን በጣም ስለ ፈራች ነበርና ቶሎ አንድትወጣላት ብላ ምንም እንደማትፈልግ ነገረቻት
“ የምትፈልጊው ነገር ቢኖር ደውይ ሐና የምትፈልጊውን ትታዘዛለች " ብላት ወጥታ ሔደች " በሩ እንደገና ሲከፈት ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ቆቧን አውልቃው ነበር » ቶሎ አለችና አንሥታ እንደገና ከራሷ ላይ ደፋችው በሩን የከፈተችው ጆይስ ነበረች "
“ ብቻሽን ወደታች ለመውረድ መንገዱ ይጠፋሽ ይሆን ማዳም ? አለቻት።
“አይጠፋኝም" አለች ሳቤላ "ወይ ጉድ ሳቤላ ኢስት ሊን ገብታ መውጫና መግቢያ ሊጠፋት !
ወይዘሮ ሳቤላ ቀስ ብላ ልብሷን ቀየረች ምንም ቢሆን የባለቤቶቹን ዐይን
ማየቱ ላይቀርላት ጊዜ መውሰድ ጥቅም እንደሌለው ተሰማት " በተፈጥሮም ሆነ በጥበብ ኃይል ፍጹም ተለውጣ ሌላ ስለ መሰለች የመታወቅ ሥጋቷ እንኳን ይህን ያህል አልነበረም ይሁንና እንባዋ አንድ ጊዜ ከፈነዳ ጨርሳ ከራሷ ቁጥጥር ውጭ
እንደምትሆንና ነገሩ ሁሉ እንደሚበላሽ አሰበች " ገንፍሎ የመጣባትን የትዝታና የሆድ ብሶት ስሜት በብዙ ትንንቅ ገታችው " በርግጥ ዓለሟን አይታ ወደ አደገችበት የትዳርን ክብር የባልን ፍቅር ወደ አጣጣመችበት ቤቷ ወደ ኢስት ሊን እንዲሁ ሁና መመለስ መራር ፈተና ነው አስጨናቂ የመንፈስ ሽብር ነው " አሁን ግን
ከመቻል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም ስለዚህ ራሷን ተቆጣጥራ የተደቀነባትን ፈተና
ተቀብላ ለመቻል ትዕግሥትንና ብርታትን ለማግኘት ከአልጋዋ ጎን ተንበርክካ ጸለየች።
ከዚህ በላይ ለመቆየት
ምክንያት አልነበራትም
ስለዚህ ጧፍ እያበራች ደረጃውን ወርዳ ወደ ሳሎኑ አመራች ስትገባ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቷል " የሻይ ማቅረቢያው ከጠረጴዛው ተቀምጦ የሻዩ ጀበና ይንሿሿል ።
ሻይዋን አሰናድታ የራቧን ያል በላች የተለያዩ ሐሳቦች በአእምሮዋ ይመላለሱባት ጀመር ።ልጆቹ ከየትኛው ክፍል ይሆኑ ? ሚስተርና ሚስዝ ካርላይል ራት
እየበሉ ይሆን ? ደወሎች አሁንም አሁንም ሲደወሉ አሽከሮች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ትሰማለች " እሷም በልታ አበቃችና ደወለች።
አንዲት አለባበሷ የጸዳ ነቃ ያለች ግንባረ ፍት ልጅ መጣችና ዕቃውን
አነሣች ጆይስ እንዳለችው የሳሎኑ ሠራተኛ ያስተማሪቱ ተላላኪ የተባለችው ሐና ነበረች " ሳቤላ ብቻዋን እንደተቀመጠች አንድ ድምፅ ሰማች ከመደንገጧ
የተነሣ ልቧ ደረቷን ሰንጥቆ የሚወጣ መስሎ ዘለለ ኤሌክትሪክ የነዘራት ይመስል ከተቀመጠችበት ወንበር ብድግ አለች ።
ነገሩ ማንንም የሚያስደነግጥ አልነበረም የሰማችው ድምፅ የልጆች ንግግር ነበር የልጆቿ!ምናልባት ልጆቹን ወደ እሷ ዘንድ እያመጧቸው ይሆን ? ከጭንቀቷ የተነሣ እንደ ወናፍ ከፍ ዝቅ የሚለው ደረቷን በእጀዋ ድግፍ አድርጋ ያዘችው"
እሱስ ከክፍል ክፍል ሲተላለፉ ኖሯል የስማቻቸው ድምፆቹ ቀስ በቀስ ጠፉ።ምናልባትም ራት በልተው ወደ መኝታቸው እየሔዱ ይሆናል አዲሱን ሰዓቷን አየች"
አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር የዱሮውን በዚህኛው ለውጣዋለች ከድሮዎቹ ጥቃቅን ጌጦች ሁለት ብቻ አስቀርታ ሌሎቹን ወደ ኢስት ሊን ካመጣቻቸው እንዳይታወቁባት ፈርታ በመሸጥ ወይም በመለወጥ ጨርሳቸዋለች " ያስቀረቻቸው ሁለት
ጌጦችም አንድ በትንሹ የተሠራ የናቷ ምስል ነው "
ሌላው እሷና ፍራንሲዝ ሌቪሰን መጀመሪያ ሲገናኙ በድንገት የተሰበረው ትንሽ የወርቅ መስቀል ነው እንደ
ሚታወሰው ይህ ባለ ሰባት አረንጓዴ ዕንቁ ቀለበት የናቷ ስጦታ ነበር ሁለቱን ነገሮች ከሷ ልትለያቸው አልፈለገችም ስለዚህ በጥንቃቄ አሽጋ ማንም በቀላሉ አንዳያያቸው ከልብስ ሳጥኗ ውስጥ በሥር አስቀመጠቻቸው » አሁን ሰዓቷን እንዳየች ወዲያው ፒተር ገባ።
ወደ ላሎን መሔድ ትችያለሽ ?” አላት
ምናልባት አልደከመሽ እንደሆነ እሜቴ ሊያነጋግሩሽ ይፈልጋሉ አላት። ዐይኗ ጭጋግ ለበሰ ያ መራራ ስዓት ደረሰ ሚስተር ካርይልን ፊት ለፊት
ልትግናኘው ነው " ፒተር ከፍቶ በያዘው መዝጊያ ዐልፋ ሔደች » ፊቷና ከንፈሮቿ 0መድ እንደ ለበሱ ተሰማት ፊቷን ከሰውየው ፊት ዘወር አደረገችው "
ሚስዝ ካርላይል ብቻቸውን ናቸው ? አለችው ዋናው ጥያቄዋ ግን የሚስተር ካርላይልን መኖር ለማወቅ ነበር።
" ብቻቸውን ናቸው " ጌታዬ ዛሬ ከውጭ ራት አለባቸው ባልሳሳት አንቹ ማዳም ቫይን መሰልሺኝ ?አላት በእንግሊዝኛው አባባል መምጣቷን ሊነግር የሳሎኑን የመዝጊያ እጀታ እንደ ጨበጠ »
አሷም በፈረንሣዊኛው አጠራር “ ማዳም ቬን ” ብላ አረመችው።
“ ማዳም ቬን መጥተዋል
አለ ፒተር እንግዳይቱን ወደ
ውስጥ እንድትገባ በእጁ አመለከታት ባርባራ በቀንዲሉ ብርሃን ፊት ለፊት ተቀምጣለች አንድ ጊዜ ሳቤላ ከባሏ ጋር ሁና ከቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ባርባራን አይታት ነበር “ ማን መሆንዋን ሚስተር ካርላይልን ጠይቃው ባርባራ ሔር ናት ያላት ጊዜ ከነበረችበት ሁኔታ የጨመረች አትመስልም በዚያን ጊዜ ባርባራ ሔር
ነበረች «ዛሬ ባርባራ ካርላይል ሆናለች " ያን ጊዜ ሳቤላ ካርላይል የነበረችው ደግሞ ዛሬ ያ ሁሉ ተገላብጦ ሳቤላ ቬን ሆናለች "

👍11