አትሮኖስ
279K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
;
;
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


እስክንድር በምልክት አሳየው ። በዚያ ሁሉ ጠጪ መሐል ሁለት እጁን እኪሱ አድርጎ ፡ ሁሉንም በንቀት ዐይን እየተመለከተ ነበር ወደ ሽንት ቤቱ የሔደው ።

“ ቢራዋ ሥራዋን እየሠራች ነው ” አለ እስክንድር የአቤል አረማመድ እያየ ።

“ ግን ምን ይሻለዋል ?” አለ ሳምሶን " በአቤል ሁኔታ በማዘን ' “ አሁን በማዕረግ የሚመረቅ ይመስልሃል ? ” እስክንድር ገርሞት ሣቀ ። የሳምሶን ጥያቄ ግን ከቅን
መንፈስ የመነጨ ነበር ። አቤል የሚወደውም የሚያከብረውም በማዕረግ ተማሪነቱ ነው ። የአቤል የማዕረግ ተማሪነት በዩኒቨርስቲው ውስጥ በብዙ ተማሪዎች ዘንድ ይታወቃል
እንደ እስክንድር ጠጋ ብለው የማያውቁት አሁንም የዓመቱ የፕሬዚዳንት የከፍተኛ የማዕረግ ሽልማት ከአቤል እጅ አይወጣም የሚል ግምት አላቸው ። ሳምሶንም የመኝታ ክፍል ጓደኛው ቢሆንም ቅሉ በትምህርት ያን ያህል መድከሙን አያውቅም ነበር ።

“ እውነቴን ኮ ነው ። ምን ያሥቅሃል ?”

ማዕረጉ ቀርቶ በዚህ ዓመት መመረቁ ራሱ ነው እኔን የሚያጠራጥረኝ” አለው እስክንድር " በኀዘን ስሜት ፊቱ
ተለዋውጦ።

“ ያሳዝናል ! ግን ምን ታረገዋለህ! ” አለና ሳምሶን "ቢራውን ከጠርሙሱ ውስጥ እየጨለጠ ፥ “ በነገራችን ላይ መውደቂያችንን እናዘጋጅ እንጂ ! መቼም ዛሬ ወደ ካምፓስ አንገባም” አለው ።

እስክንድር የሳምሶን ሐሳብ ገባሁ ፤አንድ ሴሚስተር ሙሉ ታፍኖ የቆየ ስሜቴ ተነሣ ነገር ግን ኪሱ አስተ ማማኝ አልነበረም ።

“ እኔጋ በቂ ገንዘብ የለማ ! ” አለው ልመና በተቀላቀለበት ድምፅ ከልብ ተዝናንቶ ።

አቤልም እሺ የሚል አይመስለኝም ። ከአሁን በፊት ውጭ እድሮ አያውቅም ።
“ ምን ትቀልዳለህ ? ጭራሽ ? እምልህ ...”
“ አዎ ፡ ከእኔ ጋር ስንተዋወቅ ይኸው አራት ዓመት አለን አንድ ቀንም ኣድርጎት አያውቅም ።

እንግዲያው ዛሬ ድንግሉን ማስወሰድ አለብን ? ”አለ ሳምሶን ተንኮልም የፍቅር ስሜትም እየተሰማው ።

“ እዩዬ ! ተው እባክህ ! ” አለ እስክንድር ' በተዘበራረቀ ስሜት ።

“ ምናለበት ? አንተ ደሞ ! እንዲያውም ሴት ከቀመሰ የዐይኑ ፍቅር ይለቀው ይሆናል ። ገንዘብ እንደሆን እኔ ይዣለሁ ብዬሃለሁ ።

እስክንድር የሳምሶን ሁኔታ ራሱ እንግዳ ሆነበት ። ሳምሶን አብዛኛውን ጊዜ በኪሱ በርካታ ገንዘብ ይይዛል ። ወላጆቹ ደኅና ገቢ አላቸው ። አባቱ በአንድ ኢንተርናሽናል ድርጅት ውስጥ በጥሩ ደመወዝ ይሠራሉ ። በእናቱ ስም ደግሞ
መስጊድ አካባቢ የሰዓት መሸጫ ሱቅ አላቸው ። ወላጆቹ ለሳምሰን በወር ተቆራጭ ካደረጉለት ሃምሳ ብር ሌላ
ሊጠይቃቸው ብቅ ባለ ቁጥር አንድ ወይም ሁለት ባለ አሥር ኖት ሳያሽጉት አይመለስም ። ታዲያ ሳምሶን ይህን ሁሉ ገንዘብ ሲይዝ " ለመጠጥ ማጥፋት አይወድም። የሱ ገንዘብ የሚያልቀው በምግብ ነው ። መብላት ፡ ስፖርት መሥራት ግንባታ ብቻ ! በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ካሉት ምግብ ቤት ባለቤቶች ውስጥ እሱን የማያዉቅ የለም ። ዛሬ ገንዘቡን ለመጠጥና ለሴት ለማውጣት መዘጋጀቱ ነው እስክንድርን ያስገረመ።

“ እንዴት ነው ? ዛሬ ግንባታው ቀርቶ ለማፍረስ ነው መሰል የታጠቅከው ” አለው እስክንድር እየሣቀ ።

“አንዳንዴ ያስፈልጋል እባክህ ! ”
አሳላፊዋ አራት ጠርሙስ ቢራ ይዛ መጣች አንዱ ለራስዋ መሆኑ ነው ።

ቢራ እዚሁ ጓዳ መጥመቅ ጀመራችሁ እንዴ ? "
አላት እስክንድር ፡ ከታዘዘች መዘግየቷን ለመጠቆም ።

“ ቆየሁ እንዴ?አንድ ሰካራም ይዞ ሲነተርከኝ ነው” አለች ፥ ቢራውን እየከፈተች ።

“ አንቺው መጠጥ አቅርበሽለት አንቺው፡ሰካራም ትይዋለሽ ? በይ ነይ በይ ” አለና ሳምሶን ፡ ዳሌዋ ላይ ቸብ አደረጋት ቸብታው ጠንከር ያለ ስለ ነበር ዳሌዋን ለበለባት።

“ እንደዬ ! ታዲያ ዱላው ምንድነው ? ” አለች ተቆጥታ ዳሌዋን በእጅዋ እያሻሸች

ዝም በይና ቁጭ በይ ! ከፈለግኩ ጥርስሽን ነው የማረግፈው አላት ሳምሶን እንደ ልማዱ ።

እስክንድር ነገሩ ማየሉን ሲያይ ተደናገጠ

“ ኧረ እባክህ ! የማነህ ሒድና የሚስትህን ጥርስ አውልቅ " የእኔን የብርቅነሽን አይደለም። ስለ ቢራው እንደሆን ኬረዳሽ ! ” ብላው የከፈተችውን ቢራ ጥላ ተነሣች ብርቅነሽ አምርራ ልትሔድ ስትል'እስክንድር እጅዋን
ይዞ አባብሎ አስቀመጣት ።

“ አንቺ ደሞ እረፊ እንግዲህ ። እሱ ለጠዋታ ያህል ነው የነካሽ
እየተመናቀረች ከሳምሶን ርቃ እስክንድር ጎን ተቀምጠች ። ሳምሶንም ጥርሱን እያንቀጫቀጨባት ነበር ። በማይ
ረባ ነገር ተለካክፈው የጎሪጥ መተያየታቸው እስክንድርን
አስገረመው ።

“ ሁለታችሁም ዕረፉ ፡ ይሄ ቡና ቤት ነው በሰላም ጠጥተን መጫወት ነው የምንፈልገው ”አላቸው : ከግንባሩ ኮስተር ብሎ ፥ ግን በሆዱ እየሣቀ ።

የእስክንድር ሐሳብ እነሱጋ ረግቶ አልቆየም ። በድንገት አንድ ሐሳብ አእምሮውን ወጋው ።አቤል ወደ ሽንት
ቤት ከሔደ ቆይቷል ፤ግን አልተመለሰም ። እስክንድር ልቡ መጥፎ ነገር ጠረጠረና ድንገት ከተቀመጠበት ተነሣ ።

ምነው ?” አለው ሳምሶንም ፡ በሁኔታው ተደናግጦ ።

“ ምንም አይደለም ፥ መጣሁ ” ብሎ እስክንድር ወደ ሽንት ቤቱ ሄደ ። አቅለሽልሾት ይሆናል በሚል ግምት ሳምሶን ነገሩን ቸል አለው ።

እስክንድር ከመጸዳጃ ቤቱ አጠገብ ሲደርስ አቤል እጁን በኪሱ እንዳደረገ ግድግዳ ተደግፎ ቆሞ ነፋስ ሲቀበል አገኘው። ዐይኑ በርበሬ መስሏል ።አላፊ አግዳሚውን በንቀት ዐይን ነው የሚመለከተው።

ቴክሱ ምነው ? ”አለው እስክንድር ፥ ደህና መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ"

“ ወረፋ ሆኖብኝ ነው እባክህ ! ”

“ የሽንት ወረፋ ? በል እንግዲህ ጠብቅ ። ምን ታረገዋለህ ? ” ብሎት እስንድርን ወደ መጣበት ተመለሰ ።አቤል አንድ አደጋ ደርሶቀታል የሚል ሥጋት ስለ ነበር፡ በሰላም በማግኘቱ ልቡ ተረጋጋ ። ምንጊዜም አያምነውም አንድ ቀን በራሱ ላይ የሞት ቅጣት ይፈርዳል የሚል ፍራቻ አለው።

ወደ መቀመጫው ሲምለስ ብርቅነሽና ሳምሶን ተስማተው ጎን ለጎን ተቀምጠው ሲያወሩ አገኛቸው ።

ታረቃችሁ እንዴ ? ”

“ ዱሮስ መች ተጣላን ? አንተ ደሞ ” አለችና ብርቅነሽ ጠየቀችው፡ ፡

ቀድሞውንም ጸበኞች የሚገባበዙት መሐላቸው ገላጋይ ሲኖር ነው ። ብቻቸውን ሲሆኑ አንደኛው ዐቅሙን
ዐውቆ ወይም ጥቅሙን ከጉዳቱ አመዛዝኖ ጸባዩን ያሳምራል ? አለ እስክንድር በልቡ ።

“ ያንን ነገር “ኮ ለብርቅነሽ ነገርኳት” አለው ሳምሶን' ዓይኑን እስክንድር ላይ ተክሎ "

የቱን ነግር ? ”

የአቤልን ነዋ ! በቃ እሷ ይዛው ትደር ።

ሳምሶን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸውን አጫውቷት ከዚያው ቡና ቤት መኝታ እንድትይዝ ገንዘብም
ሰጥቷታል ።

“ አንተ ዛሬ የልጁን ድንግል ለማስወሰድ ታጥቀህ ተነሥተሃል ማለት ነው? ” አለ እስክንድር ጉጉቱ አስገርሞት እየሣቀ ።

“መሆን አለበት ብዬሃለሁ ። አድቬንቸር ነው
“ አንቺስ ? በነገሩ ተስማማሽ ? ” አላት እስክንድር ፊቱን ወደ ብርቅነሽ መልሶ።

ውይ በደስታ ነዋ ! እንዲያም ድንግል ወንድ ደርሶኝ አያውቅም ። ዕድሌ ሆኖ የተፈተነ ብቻ ነው የሚደርሰኝ።

ስትናገር ሣቅ ሃቅ ስለምትል የቀልዷን ይመስላል እንጂ ብርቅነሽ የምትናገረው የልቧን ነበር ። ወሲብ ጀማሪ ደርሷት
አያውቅም ። የልጅነት ባሏም ቢሆን ሁለተኛ ሚስቱ ነበረች ።ቡና ቤቱ ውስጥ የሥራ ጓደኞቾ፥ “ ዛሬ የአንዱን ጀማሪ ድንግል ወሰድን ” እያሉ ሲያወሩ ትቀናለች በዚህ ወሬ የተካነችው የቡና ቤቱ ባለቤት ነች የጥንት ዝናዋን ስታወራ ይሄ አርዕስት
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


በድንገት የተከሰተው አደጋ ክፉኛ ስላስደነገጠው ሻምበል ብሩክ ቀን እረፍት፤ ሌት እንቅልፍ፤ የሚባል ነገር አጥቶ እንደዚሁ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ከረመ፡፡ ለዚሁ ጉዳይ ሲልም ከመስሪያ ቤቱ የአስራ አምስት ቀን ፈቃድ ወሰደ፡፡ በዚህ ፈቃድ በወሰደበት ጊዜው
ውስጥ ደግሞ ብዙ መሯሯጥ ይጠበቅበታል፡፡መጀመሪያ ሆስፒታል የተኛች እናቷን ማረጋጋት አለበት :: ከዚያም ለወንድሟ በቂና አሳማኝ ምክንያት መስጠት ይጠበቅበታል ይህንን ሁሉ ሲያደርግ በሀሳብ የምትረዳውና ! አብራው የምትሯሯጠው! አዜብ ብቻ ነች፡፡ አዜብ ስለደረሰው አደጋ የትህትና አክስት እንዲያውቁት ፈልጋ ነበር፡፡

"አይሆንም ትርፉ ማስደንገጥ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ እነሱ ካወቁ ወሬው መዛመቱና፤ እናትዋ ጆሮ መድረሱ የማይቀር ስለሚሆን፤ በሚስጥር ቢያዝ ይሻላል” በማለት የተከራከረው ሻምበል
ነው፡፡ሻምበል ለእናቷ የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ እንዲሆን ሀሳብ
ሲያወጣና፧ ሲያወርድ፤ አዜብም እንደዚሁ ያሳምናታል ብላ ያሰበችውን ምክንያት ስትደረድር፤ ቆዩና ሁለቱም ይሆናል ባሉት ሃሳብ ላይ በጋራ ከተስማሙ በኋላ፤ ይህንኑ ሊያስረዳ ወደ የካቲት አስራ
ሁለት ሆስፒታል አቀና፡፡ ትህትና ከእናትዋ ጋር በአይነ ስጋ ከተገናኙ ሶስት ቀን ሆኗቸዋል፡፡ አንዱአለምም ድምጹ ከጠፋ ሳምንት አልፎታል፡፡በነገሩ እናት ግራ ተጋብታለች፡፡
"ልጆቼን ምን ነካብኝ?" በሚል ጭንቀት ተውጣለች፡፡ትናንትና ሆስፒታል መጥታ ያስተዳደረቻት ሰራተኛዋ ነበረች፡፡ ትህትና ከቤት ያለማደሯን ብቻ ነው የነገረቻት፡፡ በሽታዋን ማዳመጡን ትታ ልጆችዋን
እያብሰለሰለች፤ በሀሳብ እንደተዋጠች ነበር ሻምበል ብሩክ የደረሰው፡፡ብሩክን ስታየው በደስታ ልቧ ቀጥ አለች ::
"ትህትናዬስ ብሩኬ?" ከኪሱ አውጥቶ ይሰጣት ይመስል በጉጉት አይን አይኑን እያየች ጠየቀቸው፡፡ ሻምበል ብሩክ እንደማፈር ብሎ ሳቅ አለና፤ ተቅለሰለሰ፡፡ ለዘዴው...
“ምነው ብሩኬ በደህና ነው?" ከሁኔታው የከፋ ችግር እንደሌለ ተረድታለች፡፡
“ምንም ችግር የለም እማማ፡፡ ምን የኛ የወጣቶች ነገር...
የሚያሰጋ ነገር ያለመኖሩን ከሁኔታው ብትገነዘብም ምክንያቱን ለማወቅ
ቸኮለች፡፡
"ምንድነው እሱ ታዲያ?
ትህትና ምንም እንኳ እጮኛዬ ብትሆንም፤ ከትዳር በፊት እርግዝና ማለት፤ ትንሽ ያልተለመደ ስለሆነ... አንጠልጥሎ ተወው። ነገሩ ገባት
ከዚያ በላይ ልታስጨንቀው አልፈለገችም እሱ ግን ቀጠለ "ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ የቤተሰብን ክብር መንካት ነው የሚል እምነት አላት፡፡ ተመካከርንና ማህጸኗ እንዲጠረግላት አደረግን፡፡ አሁን
ራስ ደስታ ሆስፒታል ትንሸ እረፍት ትውለድ ስላሉኝ አስተኝቻታለሁ።"አለና አጭር ድራማውን አጠናቀቀ፡፡ እናት የልጇን አቋም በእርግጥ ታውቀዋለች፡፡
አባቷ ያሳደጋትም በዚያ እምነት ጸንታ
እንድትኖር ነውና፤ በወሰደችው እርምጃ የተቃወሞ ድምጽ አላሰማችም፡፡
ነገሩን ውስጥ ውስጡን ስታብላላ ቆየችና......
“ሻምበል አደራህን! ትሁቴ ህጻን ልጅ ናት።እንደታላቅ ወንድም ተንከባከባት፡፡ እሷ ምኑንም የማታውቅ አንድ ፍሬ
ልጅ ናት፡፡ ለመጠንቀቁም ቢሆን አንተ ትሻላለህ፡፡ እሷ ምኑን ታውቀዋለች ብለህ
ነው?" የአሁኑ ስህተት እንዳይደገምና፤ በሌላ ጊዜ ተጨማሪ ጉዳት
እንዳይደርስባት፤ ሻምበል ሃላፊነቱን እንዲወጣ በማሳሰብ፤ አደራዋን
አጠበቀች፡፡ እሱም ትህትና ከሆስፒታል እንደወጣች ይዟት እንደሚመጣ
ቃል ገባላት፡፡ በመጠኑም ቢሆን ልቧ ትንሽ እረፍት አገኘ፡፡
“የአንዱአለሜ ወሬስ ? ምነው ጭልጥ ብሎ ጠፋ?" አከታትላ ጠየቀችው፡፡
“እኔ ራሴ ካገኘሁት ሳምንት ሆኖኛል እማማ፡፡ ለፈተናው ዝግጅት ሸፍቷል፡፡ ዘንድሮ አንደኛ ካልወጣሁ ሰው አይደለሁም ሲል የፎከረውን ለመፈፀም ቆርጦ መነሳቱን ትህትና ነግራኛለች። ምንም አያስቡ፤ ፈተናውን እንደጨረሰ እንዲመጣ እነግረዋለሁ።” ምክንያቱ
ብዙ ባይዋጥላትም የሻምበልን የማፅናኛ ቃል ከማዳመጥ በስተቀር አማራጭ አልነበራትም፡፡ዝም አለች፡፡ ከዚያም ሻምበል በግማሽ ልቡ ሆኖ፤ የሆነ ያልሆነውን፤ ሲያወራት ከቆየ በኋላ፤ ተሰናብቷት ወደ ትህትና ሩጫውን ቀጠለ....
ትህትና የቀዶ ህክምና ከተደረገላት በኋላ በአንደኛ ማእረግ እንድትተኛ ያደረገው ሻምበል ብሩክ ነው፡፡ ሻምበል አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም ንጽህናው በተጠበቀና፤ ተጨማሪ በሽተኛ በሌለበት
አንደኛ ማእረግ ውስጥ እንድትተኛ የፈለገበት ዋናው ምክንያት፤
በሚተኙ በሽተኞች ስቃይ ተጨማሪ የአእምሮ መረበሽ ሊደርስባት ይችላል በሚል ፍራቻ ነው፡፡
ለቀዶ ጥገናው የተወጋችው ማደንዘዣ ስራውን በማጠናቀቁ ለአስቸኳይ ህክምናው በተሰጣት በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ከሰመመናዊ እንቅልፉ ነቃችና አይኗን ገለጥ አደረገችው፡፡ ጣሪያውን ተመለከተች፡፡ ዙሪያዋን ቃኘች
የት እንዳለች፤ ምን እንደሆነች፤ በፍጹም
አታውቀውም፡፡ የተወጋችው የእንቅልፍ
መርፌ ፤ በጥይት የቆሰለው ሰውነቷና
እንደ ጉድ የፈሰሰው ደሟ መላ
አካሏን ድቅቅ አድርጐታል፡፡ከግራ ጆሮዋ ጀምሮ ፊቷ በአጠቃላይ በፋሻ ተሸፍኗል፡፡በክንዷ ላይ የተሰካውን ግሉኮስ ተመለከተችው፡፡ ጠብ ጠብ... እያለ
ይወርዳል። እንደገና አይኗን ጨፈነች፡፡ትንሽ ቆየችና መልሳ ገለጠችው::
እንደገና በሀሳብ ባህር ውስጥ ገባች፡፡ ምን ነበር የሆነው ? የት ነው ያለችው? እዚህ ለምን መጣች? እሷ ማን ነች? ቆይ .. ቆ ይ.. ምን ነበር የሆነው ? የሆነ
ነገር ብዥ ፧ ብዥ አለባት እንዴ ?..
መርካቶ ውስጥ እንደሻውን... ከዚያ በኋላ እራሷን... እንዴ?
ምንድነው ነገሩ? እሷ ሞታለች አይደለም እንዴ? በሰማይ ቤት ነው ወይንስ በምድር ላይ ያለችው? በዚያች በተሰናበተቻት ምድር ላይ? በፍጹም ሊሆን አይችልም! እንቆቅልሹም ሊገባት አልቻለም፡፡ ከዚያም ፊት ለፊትዋ የተቀመጡትን ሰዎች ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው፡፡
ብዥ ፤ ብ ዥ ፤አሉባት አላወቀቻቸውም :: እነሱ በሀዘን ተውጠው አይን አይኗን ይመለከቷታል፡፡ እንደገና ትኩር ብላ ከመታሸግ በተረፈው በቀኝ አይኗ አየቻቸው፡፡ አሁንም አላወቀቻቸውም፡፡ እንቅስቃሴ የላትም፡፡እዚያ ከፊት ለፊቷ ሆነው በሀዘን ኩርምት ጭብጥ ብለው የተቀመጡትን ሰዎች በድጋሜ በጥንቃቄ ተመለከተቻቸው፡፡ የሆነ ምስል መጣላት፡፡
የምታውቀው ምስል በርቀት የምታውቀው ምስል.. አዎን
ታውቃቸዋለች እንጂ !! እንዴ..? በሚገባ ታውቃቸዋለች :: ቀስ ብላ በለሆሳስ ተጣራች "ብ..ሩ. ኬ..... አ . ዜ. ቢ . ና
እህህህ....." በዚህ ጊዜ አዜብ ቀስ ብላ ተነሳችና ሄዳ አጠገቧ ቆመች፡፡ ብሩክም አዜብን ተከትሎ ወደ አልጋው ተጠጋ፡፡ሻምበል እንደዚያ ሆና ሊያያት አልቻለም :: እንባው አመለጠውና ቀስ ብሎ ጉንጮቹን
እያቋረጠ ፈሰሰ፡፡
“እ ማ ዬ...ደ ህ...ና. ነች? ..አ.ን.ዱ.ዬስ..?"
"ሁለቱም በጣም ደህና ናቸው፡፡ ስለ እነሱ ምንም አታስቢ፡፡ እኛ አለን፡፡ አሁን ዋናው ማሰብ ያለብሽ ስለራስሽ ጤንነት ብቻ ነው እሺ?” አዜብ ነበረች፡፡
“እ..ሺ በደከመ ድምጽ፡፡
“ትሁት አዜብ የምትልሽን ስሚያት፡፡ስለ እማማ ምንም የሚያስጨንቅሽ ነገር የለም፡፡እሳቸው አንቺ ስለጠፋሽባቸው ነው ትንሽ ያሰቡት እንጂ በጣም ደህና ናቸው፡፡ ቶሎ ድነሽ ሄደሽ እንዲያዩሽ
በሃሳብና በጭንቀት ራስሽን መጉዳት የለብሽም፡፡ እሺ? አንዱ አለምም ድኗል ማለት ይቻላል፡፡ሰሞኑን መጥቶ ይጠይቅሻል እሺ?” ጉንጮቿን
እየዳበሰ፡፡
እሺ” አለች በድጋሜ፡፡ በዚያው ድክምክም ባለ ድምጿ። አሉኝ የምትላቸውና የምትተማመንባቸው ሁለቱ ጓደኞቿ፤ ደራሾቿ ፤ በዚህ በክፉ ቀን እንኳ ከጐኗ
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....በለሃጩ አጨማለቃት፡፡ራቁት ገላውን እራቁት ገላዋ ላይ እንደቁንቡርስ አንደባለለው፤ መላ ፊቷን በሚርገበገብ ከንፈሩና በምላሱ አልኮሰኮሰው፤ እጆቿንና እግሮቿን ከአልጋው ጠርዞች ጋር እንደተጠፈሩ አፍዋ በቡትቶ ታጭቆ እንደተጎስጎስ በተንጋለለችበት ጥያፌዋን፣ ምሬቷን ሰውነቷን እያወራጨች አሳየችው፡፡

ግድ አልነበረውም...

በከርዳዳ ጺም የተሸፈነ ፊቱን ከፊቷ ላይ አንስቶ እስረኛው ምርኮኛው በሆነው ከስሩ በተንጋለለላት ገላዋ ላይ አንቀዋለሰው፣ አይን አዋጅ ሆነበት:: ..በደመነፍስ ያዳብሳት ጀመር፡፡ በል..በል የሚለውን ግፊት፤

ሂድ..ሂድ የሚለውን ስካር ሩጥ..ሩጥ የሚለውን እብደት ጥድፊያ አምቆ
መቆየቱ ጣፋጭ የስቃይ ስሜት ፈጠረለት፡፡ ከረሜላውን ከአፉ ከትቶ
ኮረሻሽሞ ጎረዳድሞ ከመዋጡ በፊት፣ የጎረሰውን ከረሜላ እየመላለሰ በመዳፉ
ላያ እየተፋ በስስት በስቃይ ስሜት እያየ ቀስቃዩ በሰቀቀኑ እንደሚደሰት ህፃን
የጓጓለትን የተንቀዋለለለትን ገላዋን ከስሩ አጋድሞ ተሰቃየ ለራቁት ገላዋ
ሳሳለት፡፡

ፂማም ፊቱን ወደ ደረቷ አስጠግቶ በጡቶቿ መሃል ወደቀ፡፡ሳያጎረድማት መጠጣት፤ ሳይኮረሽማት ላሳት፤ መልሶ ከአፉ አውጥቶ ተመለከታት::አውሬ ሆነች፡፡ ጥላቻዋ እየጨመረ. ምሬታ እየኮረረ. እልኋ እየጋመ በመጣ ቁጥር የልቡ ምት እየጨመረና ትንፋሹ እየተፋጀ መጣ ሰውነቱ በላብ አሙለጨለጨ ፊቱን ከጡቶቿ መሃል አውጥቶ ቁልቁል
አዘገመ...

ወገቧን ሰብቃ ሰደበችው ፧ ሽንጧን እያላጋች ረገመችው፧ ጭኖቿን
እያማታች ተፋችው

ደስታው ወሰን አጣ…

ጎንበስ ብሎ የሚወራጭ . አካሏን በለሀጩ በራሱ ከንፈሮቹ ተረከበው:: እንደ እንፋሎት የሚጋረፍ፡ ትንፋሹ ለስላሳ ቆዳዋን ፈጃት ፡ ለበለባት:: ህሊናቸውን መሳት የጀመሩ ደዳራ ጣቶቹ የሴት አካልዋን በጭካኔ አፍረጠረጡት፡፡

በሩ ተበረገደ፡፡

በጉልበቶቿ መሃል እንደተንበረከከ በድንጋጤ ፊቱን ወደጀርባው መነጨቀው የተመለከተውን አልወደደውም፡፡ በር ላይ በድን ይመስል የተገተረው ሰው የሚያየውን ትርዒት ለመረዳት ጊዜ ፈጀበት:: የሚመለከተው እየተገለጸለት ሲሄድ በእልህ ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡

“ጠርጥሬሃለሁ! አንት ውሻ ጠርጥሬሃለሁ!” አለ ማርቆስ በሩን
ለቅቆ ወደ ክፍሉ ከመግባቱ በፊት ከኮቱ ስር ሽጉጡን ላጥ አድርጎ አቀባብሎ
እላይዋ ላይ በተከመረባት ሰው ላይ እየደገነ። “እንዳትነቃነቅ... ከዚያ አልጋ
ላይ ለመውረድ ሞክርና እንደ ውሻ እገድልሃለሁ!” አለ ማርቆስ ሽጉጠን
እንደደገነ ወደ ስልኩ እያመራ፡፡ “ትንሽ ተነቃነቅና ምክንያት ስጠኝ ግንድህን አጋድምሃለሁ!” በቀኝ የያዘውን ሬድዮ ወደ አፉ ኣስጠግቶ ተናገረ።
“ሃሎ… ቆንጆዎቹ ቡድን ለ... አስቸኳይ ነው... ዜሮ አራት” ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አለ፡፡ “ቁጥር አንድ ጋር አገናኝኝ፡፡” የሬዲዮ መገናኛውን በግራው እንደጨበጠ በቀኙ የያዘውን ሽጉጥ እላይዋ ላይ በተከመረው ሰው
ላይ ደግኖ ተጠባበቀ፡፡ “ሃሎ …ዜሮ አራት በፍጥነት እፈልግሃለሁ… እዚሁ
ድረስ… ሌላ ሰው አይደለም አንተ ራስህ ተገኝታህ መመልከት አለብህ።”
አነጋግሮ ሊያበቃ ስልኩን ዘግቶ ሽጉጡን ወደፊት ኣስቀድሞ ወደ አልጋው
ተጠጋ፡፡

“ጉድህን እናየዋለን” አለ ማርቆስ ጺማሙን ሰውዬ በጥላቻ
እየተመለከተ፡፡

“ይቅርታ አድርግልኝ ማርቆስ፡፡ ሌላው ይቅር ልብሴን ልልበስ፡፡” አለ ሰውየው በጭኖቿ መሃል እራቁቱን እንደተንበረከከ በልምምጥ ፊት ማርቆስን እየተመለከተው፡፡

“ከማነው ሃጢያታችንን የምንሸሽገው? ለዓመታት አንዳችን የአንዳችንን ሃጢያት እንዳናይ የገዛ ሃጢያታችን እንዳይታይ ፊታችንን ስንመላለስ ቆይተናል፡፡ ከአሁን ወዲያ ግን ገበናችን መገለጥ አለበት፡፡
ከኃጢያታችን እራቁታችንን መተያየት አለብን። : እውነት ተሽፋፍና ተጀቧቡና አትኖርም፡፡ እራቁቷን ነው የምታምር፡፡” በዕልህ ተንቀጠቀጠ፡፡
“እራቁቷን!”

“ማርቆስ ልብህ ይራራ… ሁላችን እንሳሳታለን… ማረኝ፡”

"ማነው አውሬ… ለተናካሽ እውሬ የሚራራ? ቀሚሷን ገልበው እርቃኗን አንጋለው ለሚያረክሷት፣ ጭኖቿን በርግደው ሴትነቷን አጋልጠው ለባእድ
ለሚሽጧት አፍሪካ ርህራሄ አይኖራትም፡፡ ምህረት ምንድነው? በየዋህነት ለቸረቸራችሁ፣ በልበ ገርነቷ ለሽረሞጣችሁ፣ በድንግልናዋ ላቃጠራችሁ ምህረት ምንድነው? አፍሪካ መቼ ነው ቀሚሷን ዝቅ የምታደርግ፣ ጭኖቿን የምትሰበስብ፣ እፍረቷን የምትሸፍን? እናንተ ስትጠረጉ ብቻ ነው! ምህረት አያሻም! ራቁታችንን መተያየት አለብን!”

የክፍሉ በር ከጀርባው ሲበረገድ የተንበረከከው ጺማም ሰው ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የቢሮውን በር በርግዶ ሲገባ ብርጋድየር ጀኔራሉ ከጠረጴዛው ጀርባ እንደተቀመጠ አፍጥጦ ተመለከተው፡፡
“ያዝነው!” አለ ማርቆስ ትንፍስ ትንፍስ እያል፡፡
“ናትናኤልን?” አለ ጀኔራሉ የሰማውን ለማረጋገጥ፡፡
“አዎ፡፡” አለ ማርቆስ ጭንቅላቱን ነቅንቆ ፀጉሩን እየደባበሰ፡፡
“ብታምነኝም ባታምነኝም እራሴን እስከምጠላ ተስፋ ቆርጬ ነበር፡፡”

“እንዴት ያዝስከው? ማለቴ የት?” አለ ጀኔራሉ ማርቆስን ተቀመጥ ሳይለው በቆመበት እንዳፈጠጠበት፡፡

“ባቡር ላይ፡፡” አለ ማርቆስ ወደፊት ተራምዶ ወንበር ላይ እየተቀመጠ፡፡ “ዛሬ ማታ ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ ባቡር ላይ ሲሳፈር እዛ የመደብኳቸው ሁለት ሠራተኞቼ አይተውት አብረውት ተሳፍረዋል፡፡”

“ወደ ድሬዳዋ ተሳፍራል ነው የምትለኝ? ያዝኩት ያልከኝ መስሎኝ ነበር'ኮ፡፡” አለ ጀኔሪሉ ፊቱን አኮሳትሮ “መከታተሉ ምንድነው ትርጉሙ ለምን ቀጥታ አላስወገድከውም? "

“አታስብ... ከአዲስ አበባ እስከ ድሬዳዋ ያሉትን ጣቢያዎች በሙሉ በሰዎቻችን ሸኛቸዋለሁ፡፡”

“ባበሩ ሳያነሳ ለምን አልያዝከውም
“ጀኔራል ሰውየው ትኬት ሲቆርጥ ሰዎቻችን አላዩትም፡፡ ምናልባት
በሌላ ሰው እስቆርጦም ሊሆን ይችላል:: ድንገት ባቡር ላይ ሲሳፈር ያዩ ሠራተኞቼ ምርጫ ስላልነበራቸt ስልክ ደውለው ሲያስታወቀኝ ባበር ጣቢያ ውስጥ አስወጋጅ ሃያል ስላልነበረ ተከትለውት እንዲሳፈሩ አዘዝኳቸው።

ታዲያ ምኑን ነው ያዝኩት የምትለኝ?”

“ከዚህ ወድያ ሊያመልጥ አይችልም:: በየትኛውም ጣበያ ቢወርድ
ከማንም ጋር ከመገናኘቱ በፊት እንዲያስወግዱት ትዕዛዝ አስተላልፌአለሁ::”አለ ማርቆስ በፍጹም እርጋታ:: “በየጣብያው የሚጠባበቁት ሰዎች አሉ።

“አንተ ራስህ ለምን ድሬዳዋ በረህ አትጠብቀውም? የምልህ ይህን
ሰው አደገኛ ነው ጀኔራሉ ተረበሸ… “አንተ ራስህ ቀድመህ ብትጠበቀው
እመርጣለሁ:::”
“አንድ ሄሊኮፕተር እዛጋጅቼ እየተጠባበቅሁ ነው… ቀጥታ ወደ
ድሬዳዋ እንዳልበር ምናልባት በመሃል ሊወርድ ስለሚችል ባቡሩ እያንዳንዱን
ጣቢያ ሲያልፍ፡-የጣቢያው ያሉ ሰዎች የሬድዮ መልዕክት እያስተላለፉልኝ
እየጠበቅሁ ነው::”

“የት ነው ያለው ኣሁን?” አላ ጀኔራሉ በጉጉት፡፡
“ባቡሩ ናዝሬትን ማለፉን :: እንዳረጋገጥኩ ነው ወዳንተ የመጣሁት:: አላ ማርቆስ፡፡

ማርቆስ!” አለ ጀኔራሉ ፊቱ በጭንቀት ተወሮ፡፡ “ይህ አካሄድህ አላማረኝም እንበልና ይህ ሰው በሁለት ጣቢያዎች መሃል ከባቡሩ ቢዘል ምን ልታደርግ ነው? ከቦታው ላይ ምን ያህል ዘግይተህ እንደምትደርስ አታውቅም?”

“አብረውት የተሳፈሩት ሰዎች የነፍስ ወከፍ መሳሪያ የታወቁ ናቸው፡፡”

“የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ይታጠቁ እንጂ ለዚህ ሥራ የሰለጠነና የተዘጋጁ አይመስሉኝም። ተራ የክትትል አባላት ናቸው… አይደለም?” አለ ጀኔራሉ ጠረጴዛውን ቡጢ ደልቆ፡፡

“እርግጥ የክትትል ሠራተኞች ናቸው ግን”

ማርቆስ! ማርቆስ! ምን እየሰራህ ነው?
👍3
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


“ተቀመጪ እባክሽን” አላት ወፍራሙ የግል መርማሪ ዴሪክ ዊሊያምስ
በአንድ እጁ የእንኳን ደህና መጣሽን አቀባበል፣ በሌላኛውም እጁ ደግሞ
እንድትቀመጥ እየጋበዛት፡፡ ቆዳ ወንበሩ ላይ ያሉትን ወረቀቶችም ጠርጎ አነሳላት።

“የዛሬው ውሎሽ እንዴት ነበር ዶክተር ሮበርትስ?” ብሎ ደስ በሚል ስሜት ጠየቃት። ቅድም በስልክ ካወራት በኋላ ጥሩ ስሜት ውስጥ ነው የሚገኘው።

“በእርግጥ ውሎዬ አድካሚ ነበር” ብላ ኒኪ እውነቱን ነግራው ጣቶቿን ሞዠቀች። “በእውነቱ ሁለቱን ታካሚዎቼን እንደማላድናቸው ዛሬ ላይ ለማወቅ ችያለሁ።” ብላ መለስችለት፡፡ ለምን እንደሆነ ባይገባትም ከዴሪክ ዊሊያምስ የሆነ ነገሩ የደህንነት ስሜት እንዲሰማት ያደርጋታል፡፡ ማለትም ሌሎች እሷን ለማማለል የሚፈልጉ ሰዎች ከሚያደርጉት እንክብካቤ በተለየ መልኩ ቅልል ይላታል፡፡

“ሁለት ብቻ? ዕድለኛ ሰው ነሽ ባክሽ፡፡” ብሎ ወደ ጉዳያቸው ከመግባታቸው በፊት ዴስኩን ነፃ አደረገ፡፡ “ባይገርምሽ ሁሉም ደምበኞቼ ከብዙ ጊዜ አስቀድመው ነው ነገሮች የተዘበራረቀባቸው። አንቺን ሳይጨምር
ማለቴ ነው እንግዲህ።” ብሎ ከቀለደ በኋላ ፈገግ ሲል ኒኪም ፈገግ አለች፡፡

“እሺ ያገኘኸው አዲስ ነገር ምንድነው?” ኒኪ በጉጉት ተሞልታ “ስለ ባሌ ውሽማ ቢሆን ደግሞ ደስ ይለኛል” አለችው።

“ስለ እሷ አይደለም፡፡ ይቅርታ” ብሎ ሲመልስላት በጉጉት ተሞልቶ
የነበረው የኒኪ ፊት ዳመነ፡፡

“አሁን ገና አይደለም እንዴ ምርመራውን የጀመርነው? እመኚኝ የጣውንትሽን ጉዳይ በቅርቡ እንቋጨዋለን። ዛሬ ላንቺ የምነግርሽ ነገር” ብሎ በኩራት ተሞልቶ ከተመለከታት በኋላ “በእውነት እንደ ጅማሬ በጣም ቆንጆ የሆነ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ።” አላት፡፡

“እሺ እስቲ አስገርመኝ” አለችው ኒኪ የሚነግራትን ነገር ለማወቅ ጓጉታ፡፡

ዴሪክ ዊሊያምስ ጉሮሮውን አጥርቶ “አንቺ የሰጠሺኝን ነገሮችን በደንብ
አድርጌ ካነበብኩኝ በኋላ ጉዳዩን ከትሬይ ሬይሞንድ ለመጀመር ውሳኔ ላይ
ደረስኩኝ”

በዚሁ መሰረት ወደ ዌስትሞንት ሄዶ ምርመራውን ለመጀመር ሲል መርማሪ ፖሊስ ጆንሰንን እንዳገኘው፣ ጆንስን በዚያ ዘረኛ አመለካከቱን በሚያሳይ ሁኔታ የሬይሞንድን ቤተሰቦችም ሆነ በዙሪያቸው የሚገኙ የአደንዛዥ
ዕፅ አዘዋዋሪዎችን በጣም ተጭኖ
መረጃ እንዲነግሩት የጠየቃቸው መሆኑን እና ይሁን እንጂ ምንም ዓይነት መረጃ ሳያገኝ እንደሄደ፣ ይሄ ደግሞ ለእሱ ጥሩ ዕድልን እንዳመቻቸለት ካስረዳት በኋላ
ሲቪል መስሎ በመቅረብ መረጃዎችን እንዲሰጡት ሲጠይቃቸው ዕፅ
አዘዋዋሪዎቹ ልባቸውን ከፍተው መረጃዎቹን ወደሱ እንዳፈሰሱለት
ተረከላት፡፡ ኒኪ የዊሊያምስን ትረካ በጥሞና እያዳመጠችው ነበር፡፡ ዊሊያምስ ትረካውን አቋረጠና

“ትሬይ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀሙን ያቆመው ባለቤትሽን አግኝቶ ከታከመ
በኋላ ነበር። ማለቴ ሁለት ዓመት አልፎታል አይደል?” ሲል ጠየቃት፡፡”

“አዎ ልክ ነህ። በዶውግ እገዛ የተነሳ ነው ዕፁን መጠቀሙን ያቆመው::”
ብላ መለሰችለት፡፡

“ልክ ብለሻል” ብሎ ዊሊያምስ በመቀጠልም “ግን ነገሮች እንደዚህ በቀላሉ የሚተው አይደሉም። መጠቀም ከማቆሙ በፊት ትሬይ በተለይ የ ሄሮይን
አደንዛዥ ዕፅን ያዘዋውር ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን አዲስ የዲስሞርፊን
አይነት አደንዛዥ ዕፅን ማዘዋወር ጀመረ። ዕፁ በተጠቃሚዎቹ ላይ አደገኛ
አካላዊ እና አዕምሮአዊ ችግርን የሚያደርስ ነው። ተጠቃሚዎቹ ክሮክዲልዐብለው ነው የሚጠሩት” አላት፡፡

“ይህንን አደንዛዥ ዕፅ አውቀዋለሁ፡፡ የዶውግ ጓደኛ የሆነው ሀዶን ዶፎ
ወደ እነርሱ ክሊኒክ ለመታከም የሚመጡት ተጠቃሚዎች የሚወስዱት
ይህንን ዕፅ እንደሆነ እና አደንዛዥ ዕፁንም ሩሲያውያን እንደሚያመርቱት
ጭምር አጫውቶኛል።” አለችው ኒኪ፡፡
“ልክ ነሽ” አለና ኒኪ ስለ አደንዛዥ ዕፁ በማወቋ ትንሽ ተገረመ፡፡ “ትሬይ ለአንድ የሜክሲኮ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ነበር ይሠራ የነበረው። የአደንዛዥ ዕፁንም ገበያ ከሩሲያኖቹ ጋር እየተፎካከረ እንዲቀጥል አድርጎላቸው ነበር።
እነዚህ አብሯቸው ይሰራ የነበሩት ሰዎች አዲስ ህይወት መጀመሪያ ስለሚባል ነገር መስማት አይፈልጉም፡፡ እንዲያውም እሱ ሥራውንዐእንዲያቋርጥ በፍፁም የሚፈልጉ ሰዎች አይደሉም::”ፀ

“ግን እኮ እሱ እነዚህን ነገሮች ትቶ አዲስ ህይወት ጀምሯል እኮ!”ብላ ኒኪ ሙግቷን ቀጠለች እና “ዶውግ ከሱስ እንዲፈወስ ካደረገው በኋላ ትሬይ በሙሉ ተለውጧል። እኔም ቢሮዬ ውስጥ ሥራ ሰጠሁት።ትሬይ በየቀኑ ሰዓቱን አክብሮ በመገኘት ሥራውን በብቃት ሲወጣም ነበር”

“ይህ ቀን ቀን አንቺ ቢሮ ውስጥ ሲሰራ የነበረው ሥራው ነው፡፡” አላት፡፡እና ዊልያምስ በመቀጠልም “ባለቤትሽ የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኛን ከሱሱ በደንብ
አድርጎ እንዲላቀቅ የሚያደርግ ትልቅ ባለሙያ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ነገር
ግን የናርኮቲክ ቢዝነሱን አስመልክቶ ብዙ የሚያውቅ አይመስለኝም፤ ሌላኛው
ትሬይን ቀጥሮ የሚያሰራው ሜክሲኳዊ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ አለቃው
ስም ካርሎስ ዲ ላ ሮዛ ይባላል” አላት እና ኒኪን ቀጥ ብሎ እየተመለከተ

ስሙን ስትሰማ ፊቷ ላይ ለውጥ እንዳመጣ ለማጣራት ቢሞክርም ፊትዋ
ላይ የተለየ ነገር ማንበብ አልቻለም። ምክንያቱም ትሬይ ከጀርባ ሆኖ
አደንዛዥ ዕፅ ያዘዋውር ነበር የሚለው ሃሳብ በጣም አስደንግጧት ነበር፡፡

እና ይሄ ያልከው ሰው ነው ትሬይን የገደለው? ወይም ያስገደለው ብለህ
ታስባለህ?”

“ይህንን እንኳ በእርግጠኝነት ልመልስልሽ ያስቸግረኛል ግን ሊሆን የማይችልበት ምክንያት የለም ብዬ እገምታለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ አንቺ እንደነገርሽኝ ከሆነ ትሬይ ይህንን ስራውን ለማቆም ሙከራ ካደረገ ሊያስገድሉት ይችላል እላለሁ፡፡ ዴላ ሮዛ ዌስት ሞንት ውስጥ በጣም ትልቅ አሳ ሊሆን ይችላል” ብሎ ዊልያምስ ገለፃውን በመቀጠልም “ነገር ግን በአለም ዙሪያ ከሚገኙ ታላላቅ አደንዛዥ እጽ አምራቾች እና አዘዋዋሪዎች አንጻር ሲታይ እሱ ትንሽዬ የጥብስ አሳ ነው፡፡”

“የ ዴ ላ ሮዛ አለቃ እጅግ በጣም አደገኛ ሰው ነው፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ነገሩ ገራሚ ነገር የሚታይበት፡፡” አላት፡፡
“የዚህ እጅግ በጣም አደገኛ አለቃ ስም ማን ይባላል?” ብላ ኒኪ ጠየቀች፡፡

“ዶክተር ሮበርትስ ብታምኚኝም ባታምኚኝም ይህንን ሰው በሆነ መልኩ
የምታውቂው ሰው ነው፡፡ ሉዊስ ዶሚኒኩ ሮድሪጌዝ ይባላል።” ኒኪም ግንባርዋን ቋጥራ ስሙን የት እንደምታውቀው እያሰበች ቆየች።

“አኔ ቤታማን የምትባለው የአንቺ ታካሚ የዚህ ሰው ሚስት ናት” ካላት በኋላ ዊልያሚስ ላፕቶፑን አዙሮ የጎግል ኢሜጅ ላይ ያገኘውን የአንድ መልከ መልካም ዳር ዳሩ ላይ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ጥቁር ሉጫ ጸጉር እና ጠንቃቃ አይኖች ያሉትን የላቲን ተወላጅ ፎቶ አሳያት፡፡
ኒኪም ግራ እንደተጋባች “ሚስተር ዊልያምስ የተሳሳትክ ይመስለኛል
ወይንም ደግሞ እንድትሳሳት ሆነሃል የአኔ ባለቤት እኮ የሪል እስቴቶችን
ገንብቶ የሚሸጥ የቢዝነስ ሰው ነው፡፡” አለችው፡፡

“ዴሪክ ብለሽ ጥሪኝ እባክሽን” ብሎ አስታወሳት እና በመቀጠልም “ምንም
ነገር አልተሳሳትኩም ሉዊስ ሮድሪጌዝ አኔ ቤታማንን ያገባት የዛሬ ስምንት አመት ኮስታሪካ ውስጥ ቀለል ባለ ሰርግ ነው ካላመንሽኝ የምስክር ወረቀታቸውን ኮፒ ላሳይሽ እችላለሁ እኔ ይህ ጉዳይ የሳበኝ ከዚህ በፊት ከሉዊስ ሮድሪጌዝ ጋር የሚገናኝ ስራ ሰርቼ ስለነበር ነው ጉዳዩም አንዲት ሜክሲኮ ውስጥ የጠፋች ወጣት ሴትን አስመልክቶ ነው፡፡ በይፋ ባይሆንም ሁሉም ሰዎች ወጣቷ ልጅ በሰው እንደተገደለች
👍61
#የወዲያነሽ


#ክፍል__ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በሐይለመለኮት_መዋል


....እናቴ አዘኔታ በሚታየበት ፊት ወደ እኔ መለስ አለችና ሞኝነትህ፣ ሞኝነትህ ነው ልጄ! 'አይዞሽ ግድ የለሽም' ብለህ ይዘሃት ና፡፡ እኔ እናትህ አሳምሬ እቀበልልሃለሁ። አትፍሪ! አትፍሪ ነዪና እንታረቅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ እኔና አንቺ እናትና ልጅ ነን፣ ልጄ ልጄ ብላሻለች” ብለህ አሳምረህ ንገርልኝ በማለት ያን በውስጤ ሲገላበጥ የዋለ ሥጋትና የመንፈስ ሽብር ገደለችልኝ
እናቴ ጋሻዬነህን ፍለጋ መልከት መልከት ስትል እንቅልፉ ሊጥለው ሲያንጎላጅ
አየችውና «አፈር በበላሁት! ልጄን! ልጄን! ያቺ እናትህ እንኳን አላየች!» ብላ
ካነሣችው በኋላ እግሩን እያንዘላዘለች ወደ የውብነሽ መኝታ ቤት ይዛው ገባች::
የእናቴ እግር ወጣ እንዳለ የውብነሽ ድንገት ብድግ ብላ አለቀ! ጨብጠኝ
ወዳ አይምሰልህ የግዷን ነው» ብላ ደስታዋን ገለጸችልኝ።

«አዎ ከእንግዲህ ደግሞ አንድ አስቸጋሪና የለየለት ግብግብ ብቻ ይቀረኛል» ብዬ መለስኩላት

የወዲያነሽ ምነው ቆየህ? ና እንጂ ጌታነህ! ቁርጤን ልወቅ? የምትል
መሰለኝ፡፡ ሰዓቴን ብመለከት ዐሥራ ሁለት ሰዓት አልፏል። እናቴ ከተቀመጠች
በኋላ ጥያቄና መልስ ቀጠለ። ከመጠን በላይ ተዝናናሁ፡፡ መላ አካላቴ
ተንፈላሰሰ፡፡ የወዲያነሽን ሥቃይና መከራ ባጭር ባጭሩ አንዲትም ሳላስቀርና
ሳልዘነጋ እንደ ተረት ነጋሪ አሳምሬ ወጣሁላት። የእኔንም ልፋትና ውጣውረድ
ሁሉ ገለጽኩላት፡፡ ንግግሬን እንደ ጀመርኩ ፊቷ ትንሽ በትንሽ ጠወለገ፡፡ እንባዋ
እየተሽቀዳደመ ሲወርድ ማዘንና መፀፀቷ ገባኝ። የእናቴ ርኅራኄና ገራገርነት እንደ ኮረብታ ጎልቶ ታየኝ፡፡ በኀዘን ጠውልጎ በእንባ የራሰውን ጉንጯን በማየቴ
በጣም ረካሁ፡፡ በሕዝብ ኃይል ሥልጣን እንደ ያዘ መንግሥት ደስ አለኝ።
የወዲያነሽም ድል ስታደርግ ወለል ብሎ ታየኝ፡፡

«አሠቃይቻታለሁ በቁሟ ቀብሪያታለሁ» አለችና ልቅሶዋን ቀጠለች።
«ያለፈው አልፏል ከነገ ጀምሮ ታርቃችሁ ተፋቀሩ እንጂ እሷ በበኩሏ ሁለንም
ነገር ይቅር ብላ ትታዋለች በጣም እኮ ነው የምትወድሽ» ብዬ ትካዜዋን ለማቅለል ሞከርኩ፡፡ ሙሉ ፈገግታዋ ሳይመለስ ለመሄድ ተነሣሁ፡፡ «ጋሻዬን አምጪልኝ የውብነሽ!» አልኳት፡፡

«አንት ጨምላቃ ጨመለቅ! እኔ እጅ ገብቶ ነው የምትወስደው?ባይሆን እንኳ ዋንየዋ ከመጣች በኋላ የሆነው ይሆናል!» ብላ ቱግ አለች። ልቤ ጮቤ ረገጠች፡፡ ተደሰትኩ እንጂ አልከፋኝም፡፡ የወሬ ሠንጋ ጥለን ስናወራርድ ሁለት ሰዓት ተኩል አለፈ። የውብነሽን ለብቻዋ ጠርቼ «ነገ አራት ሰዓት እንድትመጪ» አልኳትና «ደኅና እደሩ» ብዩ ወጣሁ፡፡

የቤቴን አጥር ግቢ ከፍቼ ስገባ የወዲያነሽ ጋቢዋን ለብሳና የሰበሰቡን አግዳሚ ተደግፋ ስትጠብቀኝ ደረስኩ እንደ ወትሮዋ ነቃ መብላት ስላልተቀበለችኝ
አእምሮዋ በሐሳብ ጉልበቷ በመቆም እንደ ተዳከሙ ገባኝ። እጅዋን ያዝ አድርጌ ዐይን ዐይኗን እያየሁ አመሸው እንዴ የወዲያ ደስ ይበልሽ! ደስ ብሎኛል
የሄድኩበት ጉዳይ ተሳክቷል» አልኩና በምሽቱ አየር የቀዘቀዙ ጉንጮቿን ሳምኳቸው፡፡

«እንኳን ደኅና መጣህ? እንኳን ደስ ያለህ? ጋሻዬስ? ከእጅህ ላይ ሳጣው ጊዜ አፌ ተሳሰረ» አለችና በልከኛው የመብራት ውጋጋን ውስጥ ትክ ብላ ተመለከተችኝ፡፡ ተያይዘን ከገባን በኋላ እንዴት ብዬ ልግለጽልሽ? እናቴ በጣም ተደሰተች። ምነው የዛሬዋ ዕለት የሁለትና የሦስት ቀን ያህል በረዘመች ! ስለ አንቺና እኔም አንዳችም ሳላስቀርና ሳልደብቅ ነገርኳት። በጸጸት ተቃጥላ እንባ በእንባ ሆነች። ርኅራኄዋንና የእናትነት ልባዊ ፍቅሯን ለማግኘት ችያለሁ፡፡በመጨረሻ ግን ጋሻነህን ልውሰድ ብዬ ብጠይቅ አፈን አስያዘችኝ፡፡ «እሷን እዚህ ይዘህ መጥተህ ይቅርታ አድርጊልኝ ብዬ ሳንታረቅና እንደ እናትና ልጅ ሳንሳሳም፣ ልጅ የሚሉ ነገር አልሰጥም ብላ ማለች» ብዪ ጋሻዬነህ የቀረበትን ምክንያት አብራራሁላት፡፡

የወዲያነሽ እውነት ስላልመሰላት «መቼ ሥራ አጡና! እንኳን ጥራትና አምጣት ሊሉህ ይቅርና ይህንኑ ዐይኗን እንዳታሳየኝ ብለውህ ይሆናል፡፡ ያንተን ሥራ መች አጣኋትና! ታዝናለች፣ ይከፋታል ብለህ ነው:: አትጨነቅ ቢከፋኝስ ምን እንዳላመጣ ነው? አጀብ እቴ ! ያም ሆነ ይህ እንኳን ደስ ያለህ» ብላ አሻግራ ስትመለከት «አምጪ እጅሽን፣ የወዲያነሽ ሙች! » ብዩ ለእውነተኛነቴ ማረጋገጫ እንዲሆን እጅዋን ስቢ ጠፋሁት፡፡

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ራት አቀረበች። ሆዴ በቀኑ ምግብ ደስታና ፈንጠዝያ በመጎሰሩ ምንም አላሰኘኝም፡፡ የወዲያነሽ «በቃኝ! በቃኝ!» እስከምትል ማጉረስ በመቻሌ እንደገና ደግሞ አጋጣሚው አስደሰተኝ። ከራት በኋላ ከቀኑ ወሬ ውስጥ ቀነጫጭቤ አወራሁላት። በጥርጣሬና በሥጋት ታፍኖ የነበረው አእምሮዋ ገለጥለጥ ስሳለላት ጥርጣሬዋ ከላይዋ ላይ በንኖ ጠፋ፡፡

«እኔ በበኩሌ ቂም የሚሉ ነገር አልያዝኩም፡፡ ላንተ ስል ሁሉንም ነገር ትቼዋለሁ፡፡ የፈራሁትና የሠጋሁት አሻፈረኝ ይላሉ ብዬ ነው እንጂ፣ እሺ ካሉንማ ምን ቆርጦኝ። ጫማቸው ላይ ወድቄ ይቅርታ አድርጉለኝ ብላቸው ምን ነውር አለበትና ነው?» በማለት እቅጩን ነግራኝ ወደ መኝታ ቤት ገባች። መላ ሰውነቴ ጥርስ አውጥቶ ሣቀ፡፡ ተከትያት ገባሁ። ምንጊዜም ከዚያ ቀደም ወስዶኝ በማያውቅ ሁኔታ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ፡፡ እውነተኛ ፍቅርና የሕሊና ጸጥታ ምንኛ ሰላም ይሰጣሉ!
የወዲያነሽ ቀኝ እጅዋን በብርድ ልብስ ውስጥ አሾልካ ግንባሬን
እየዳበሰች «እንዴ? የዛሬውስ እንቅልፍ ለብቻው ነው፣ ለጤና ያድርግልህ» ብላ በማያስደነግጥ ሁኔታ ባትቀሰቅሰኝ ኖሮ ተኝቼ አረፍድ ነበር። ከአንገቴ ቀና
ብዬ «ረፍዷል እንዴ? ስንት ሰዓት ሆነ?» አልኳት፡፡ ሰዓቷን አየት አድርጋ «ሦስት ሰዓት ከሐያ አምስት» ብላኝ ሄደች።

በመስኮቱ በኩል የገባው የረፋዷ ፀሐይ ጮራ ክፍሉን አወግጎታል።
ተጣጥቤና ለባብሼ ለመቀመጥ ቸኮልኩ፡ ሠራተኛይቱ ያመጣችልኝ ሽግ ያል ውሃ ደህና አዝናናኝ፡፡ ጊዜው በመገሥገሡ ተደሰትኩ በእናቴ ፊት «የሚያስከብረኝን» ልብስ ለብሼ ስጨርስ አራት ሰዓት ተኩል አለፈ፡፡

የወዲያነሽ ከፊት ለፊቴ ቆም አለችና ምን ዓይነት ልብስ ልልበስ? እስኪ ንገረኝ?» ብላ ዐይኖቼን በዐይኖቿ አቆላመጠቻቸው ደረቷ ላይ ዠቅ
ያለውን ሐብልና መስቀል እየተመለከትኩ «መጨነቅና መጠበብ አያስፈልግም የአንቺ መጎናፀፊያና ግርማ ሞገስሽ የሰው ልጅነትሽ ብቻ ነው። የሐር ድርብና የወርቅ ቁርጥራጭ አይደለም፡፡ ይህን የአጣና ያአገኘ የመለያ ምልክት በግብግብ
እናስወግደዋለን። ደስ ያለሽን ልበሽ?» አልኳት። ባለ ወይን ጠጅ ጥለት ኩታና ቀሚስ ለብሳ፣ ተረከዘ
አጭር ጫማ ተጫምታ ጸጉሯን በቀላሉ ጎነጎነችው፡፡

ምንም እንኳ ቀደም ሲል በሕወይቷ ላይ በደረሰው ተደጋጋሚ ችግርና የሕሊና
ሥቃይ የተነሣ አካላቷ ሲፈካና ሲጠወልግ፣ ሲከሳና ሲኮስስ ቢኖርም፣ የወዲያነሽ በአሁኑ ጊዜ በምቹ ቦታ ላይ በቅላ በማለፊያ ዳስ ላይ እንደ ተንሰራፋች የወይን
ተክል ሐረግ ቀስ በቀስ አምሮባታል።

የችግርና የሠቀቀን ኑሮ ያሟሰሰው ለዛና ዛላዋ፣ ውበትና ደም ግባትዋ
እንደገና እንደ ሐምሌ ጎርፍ እየሞላ፣ እንደ መስከረም ወንዝ እየጠራ፣ እንደ ጥቅምት አዝመራ አሺቷል። ከአገርና ከሕዝብ መኻል በተለይ ተመርጣ የምትጠቀስ ልዩ ቆንጆ ባትሆንም የወዲያነሽ የምትኮክብ የውበት ጉልላት
ሆነች። ጠበብ ካለው ግንባሯ ግርጌ ከቅንድቦቿ ድባብ ሥር ያሉት ተንተግታጊ ውብ ዐይኖቿ ከሥጋ ቅምር ሳይሆን ከሚጨበጥ ንጥረ ብርሃን የተሠሩ መሰሉ፡፡
👍51
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...ሁለት ዓመታት እንደ ዋዛ አለፉ። በነዚህ ሁለት አመታት ውስጥ የአማረችና የጌትነት ግንኙነት ደረጃ በውል አልታወቀም። አማረች በሁለተኛው አመት መጀመሪያ ላይ የእናቷን ቡናማ ቀለም ያላት ዳትሰን መኪና
ይዛ መምጣት ጀመረች። ይሄ ሁኔታ ደግሞ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት ይበልጥ አጎላበትና ድህነቱ ተፅእኖ ያሳድርበት ጀመር፡፡ በልቡ የተሰማውን ስሜት በአንደበቱ ለመግፅ ከአቅም በላይ መንጠራራት እየመሰለው ፈራት፡ የግንኙነት ደረጃቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ እሷ እንድትነግረው ፈለገ፡፡ እሷ ደግሞ ግፊቱ ከሱ እስከሚመጣ ድረስ ጠበቀችው፡፡
ሁለቱም ከሱ ይምጣ ከሷ ይምጣ ሲባባሉ ጊዜው ነጎደ። አማረች በቤት ውስጥ መነጫነጭ ጀመረች፡፡ እሷ ስትበሳጭ እናቷ አብረዋት ጭንቅ ጥብብ ይላሉ፡፡ “ምን ሆነሻል ልጄ?እስቲ የሆንሽውን ንገሪኝ?" ይሏታል።
ምክንያቱን እሷም በውል አታውቀውም፡፡ ይሄ ንጭንጫ ከጌትነት ጋር ስትገናኝ ድራሹ ይጠፋል፡፡ ደስተኛ ሆና አብራው ትቆያለች። ከሱ ስትለይ ደግሞ ያው ፀባይዋ ተመልሶ ይመጣል። ቀስ በቀስ ፍቅር እንደጀማመራት ተረዳች። ሲሽሻት በዘዴ የቀረበችው እሷ ትሁን እንጂ አፍ አውጥታ አፈቀርኩህ ብላ ለመጠየቅ ተቸገረች። ሴት ልጅ ለፍቅር ስትጠየቅ እንጂ ስትጠይቅ አልተለመደምና እንዴት አድርጋ ስሜቷን እንደምትገልጽለት
ከመጨነቅ የተነሳ የሌለባትን ፀባይ ማሳየት ጀመረች።

ዩኒቨርሲቲው ሊዘጋ ተቃርቧል። ጌትነትና አማረች ፈተና ጨርሰው
ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ ትምህርት ቤት ከተዘጋ ደግሞ በየቀኑ መገናኘት ሊቀር ነው። አልፎ አልፎ ስልክ መደዋወሉ ብቻ ብዙም ፋይዳ የለውም፡፡ በየግላቸው በናፍቆት ሲጠበሱ መክረማቸው ነው፡፡
ቢያንስ ዐይን ለዐይን እየተያዩ ረሃባቸውን ለመወጣት ሰበባቸው ትምህርት ቤት ነበረችና መዘጊያዋ ሲደርስ ሁለቱም ተጨነቁ፡፡ በተለይ አማረች ይሄው ለተወሰነ ጊዜ የመለያየቱ ነገር በይበልጥ አስጨንቋት ሙሉውን ሌሊት በሀሳብ ስትገላበጥ አነጋች፡፡ ጌትነትን ወኔ ለማላበስ ምን ማድረግ እንዳለባት ዕቅድ ስታወጣ ፕሮግራም ስትነድፍ አደረች።

"ጌትሽ ትምህርት ቤት ከመዘጋቱ በፊት በፈተና ሲጨነቅ የከረመ አእምሯችንን ትንሽ ለማዝናናት ወደ ላንጋኖ ብንሄድ ምን ይመስልሃል?' ከፊቷ ፈገግታ ባይጠፋም በልቧ እምቢ ብሎ እንዳያሳፍረኝ አምላኬ አደራህን እያለች ነበር፡፡

ያንን ከአማረች የተሰነዘረ የተቀደሰ ሃሳብ ሲሰማ የጌትነት ልብ በደስታ
ወከክ አለች። በተለይ የሀብታም ልጅ መሆኗን እየተረዳ ከመጣ በኋላ "እንድታስጠናኝ እንጂ እኩያህ ነኝ ወይ? እንዴት ያለአቅምህ ትንጠራራለህ? የሳቀና የተጫወተ ሁሉ አፈቀረ ማለት አይደለም የድሃ ልጅ!"ብላ ቅስሜን ብትሰብረውስ? የሚል ፍርሃት ሸምቅቆ ይዞት ነበር። ተንቀዥቅዦ ውርደት ከመቅመስ ይልቅ የሷን ፍላጎት ከሷ ከመጠበቅ ውጪ
አማራጭ የለውም ብሎ ወስኖ በነበረበት ሰዓት ይሄንን ሲመኘው የኖረውን ሰናይ ሃሳብ ስታቀርብለት አላንገራገረም፡፡

"ደስታውን አልችለውም አማረች ግን መቼ?" አላት፡፡ቅዳሜ ዕለት የዋና ልብስ እንዳትረሳ!... "
ቅዳሜ ከጠዋቱ ሁለት ስዓት ላይ ለገሀር እንዲጠብቃት ተቀጣጠሩ
ቅዳሜ ላንጋኖ ደርሰው ተዝናንተው በእለቱ ወደ አዲስ አበባ ሊመለሱ
እንደማይችሉ የታወቀ ነው። ነገሩ አዳር እንዳለበት በልቡ ገመተና ለማንኛውም ብሎ ለእህቱ ነገራት፡፡


"ዘይንዬ ነገ ወደ ላንጋኖ ሳልሄድ አልቀርም ምናልባት ካደርኩ ከጎረቤት የሚያስተዳድርሽ ሰው ልፈልግ?" አላት፡፡
"ወንድም ጋሼ ለምን አብሬህ አልሄድም?” አለችው፡፡ ደንገጥ አለ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እህቱ ያቀረበችለትን ጥያቄ ላለመቀበልና ለመዋሸት ተገደደ::“ዘይንዬ ጉዞው ከመስሪያ ቤታችን ሰራተኞች ጋር ስለሆነ አይመችም::
በሌላ ጊዜ ፕሮግራም ይዘን እንሄዳለን እሺ?" አለና ተለማመጣት::"እሺ ወንድም ጋሼ ለእትዬ ጤናዳም እነግራቸውና ከሎሚ ጋር አብሬ አድራለሁ" የዕድሜ አቻ የጎረቤታቸውን ልጅ ማለቷ ነው፡፡

በከፍተኛ የንፋስ ሞገድ የታጀበ ውርጭ እንደ ጅራፍ እየተጋረፈ ይዘንባል። የብዙዎቹን ሰዎች ጃንጥላ የሚገለብጥ የሚያፏጭ ንፋስ ከታክሲ ላይ ወርዶ እየሮጠ ሄደና ከአንድ ህንፃ ስር ተጠለለ፡፡ ከቀጠሮው በፊት ስላሳ ደቂቃ ቀድሟል፡፡ የቀጠሮው ሰዓት ሊደርስ አምስት ደቂቃ ሲቀረው
ዐይኖቹን አሻግሮ ወረወረና ከወዲያ ማዶ ብቅ ባለችው ቡናማ ዳትሰን መኪና ላይ አሳረፋቸው። አማረች ከቀጠሮው በፊት አምስት ደቂቃ ቀደም ብላ መድረሷ ነበር። እየሮጠ ሄደ። ተገናኙ። ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጡ። "ጎበዝ ሰዓት አክባሪ!" የጋቢናውን በር እየከፈተችለት በቀጠሮ አክባሪነቱ አድናቆቷን በፈገግታ ገለፀችለት፡፡

“አመሰግናለሁ" እሱም እየሳቀ ነበር፡፡ መቼም አማረች የጨዋታ ቅመም ነች፡፡ እንኳንስ ወደ ሽርሽር ቦታ ለመዝናናት እየሄዱ ይቅርና በአስጨናቂው ጥናት ላይም ቢሆን አፍ ታስከፍታለች። በተለይ የዛሬው ጉዞ የረጅም ጊዜ ጓደኝነታቸው ወደ ላቀ ደረጃ የሚሸጋገርበት አጋጣሚ ነውና
ፍፁም ነፃነት እንዲሰማው የተቻላትን ሁሉ ለማድረግ ወስናለች። ጉዞ ተጀመረና ቀስ እያሉ እየተዝናኑ አዋሳ ደረሱ። አዳር በቀለ ሞላ ሆቴል ነበር። ራታቸውን በልተው ሲጨዋወቱ አመሹ :: የተያዘው አልጋ
ሁለት ነው፡፡

“አንድ አልጋ ይበቃናል ለምን ለሁለት አልጋ ይከፈላል የሚል የተቀደሰ ሃሳብ ያቀረበ አልነበረም" መኝታ ክፍላቸው ጎን ለጎን ቢሆንም በመካከሉ የግንብ ግርዶሽ አለ፡፡ በይሉኝታና በፍራቻ ግርዶሽ ላይ የግንቡ ግርዶሽ ተጨምሮበት ለሊቱን ሙሉ ተለያይተው ማደራቸው ነው፡፡
የቅርብ ሩቅ... በመንፈስ እሱ ወደ እሷ እሷም ወደ እሱ እየሄዱ ቢፈላ
ለጉም ሃሳባቸውን በግልፅ አውጥተው መነጋገር አልቻሉምና መድረሻቸውን ያላወቁ መንታ መንገድ ላይ የቆሙ መንገደኞች ሆኑ። በስሜትዐረጅም ርቀት የተጓዙ ነገር ግን በይሉኝታ ልጓም ተሽብበው የተያዙ ተፈላላጊዎች። አማረች የዛሬው ግብዣዋ የሽርሽር ብቻ ሳይሆን የፍቅር ግብዣንም የሚያጠቃልል መሆኑን ከሁኔታዎች ይገነዘባል የሚል እምነት ነበራት፡፡ እሱ ደግሞ ይቺ ቆንጆ የሀብታም ቤተሰብ ልጅ በትምህርት ቤት ውስጥ በተመቻት ጊዜና ቦታ ሁሉ እየተገኘ የሚያስጠናትን እንደ ውለታ ቆጥራ ያንን ውለታ ለመክፈል የጋበዘችው እንጂ የፍቅር ግብዣ ጭምር መሆኑን አላወቀምና ፈራት፡፡ እሱ እንደሚያስበው በፍቅር አስባው ካልሆነ ሊያስቀይማት ሊጣላት ነው ማለት ነው፡፡ ይህንን ደግሞ
አልፈለገውም፡፡ ዐይኖቹ ያንን ልብ የሚያጠፋ ውበቷን በቅርበት እያስተዋሉ እንዲያደንቁ፣ ጆሮዎቹ ያንን የማይጠገብ ጨዋታዋን እንዲያደምጡ፣ አፍንጫው ያንን ጣፋጭ መአዛዋን ያለምንም ገደብ እያጣጣመ በሀሴት ይሞላ ዘንድ የተፈቀደለት ሰው ነውና ቢያንስ ቢያንስ ሌላው ባይሳካለት እንኳ እሷነቷን ጥሬ ጓደኛነቷን ላለማጣት ራሱን ቆጠበ፡፡ ሲያያት
ምራቁን የሚውጠው ወንድ ሁሉ ያልተፈቀደለትን እሱ ተፈቅዶለታል።
ይሄ ሁሉነቷ ገደብ ያልተደረገበት ሰው ነውና ከራሷ እስካልመጣ ድረስ ተሽቀዳድሞ ነገር ማበላሸት ይሆናል በሚል ፍራቻ ዝምታን መርጧል።
👍4
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...«እየው» አሉት ወደ ጆሮው ጠጋ በማለት «እሙዬን ራሴን አሞኛልና
መድሃኒት ግዢልኝ ብዬ ወደ ከተማ ልልካት ነው። እሷ ከሄደች በኋላ የምነግርህ ነገር አለኝ። በል ቶሎ ተኛ፡፡» አሉት እያዋከቡት።

“ምንድነው እሱ?» አላቸው አስራት ዓይኑን ዓይናቸው ላይ ትክል አደርጎ።
«ብኋላ እነግርህ የለ! አሁን ተኛ፣» አሉትና ወደ ጓዳ ገባ ብለው ጋቢ
አምጥተወ ሰጡት፡፡ በል ቶሎ በል!ካሉ በኋላ አሁንም ወደ ጆሮው ጠጋ ብለው «እሙዬ ምን ሆንክ ታለችህ ድንገት ቁርጠት ተነሳብኝ ብለህ ቅልስልስ እያልክ ንገራት።
አሉት ጣደፍ ጣደፍ እያሉ።
አስራት ግራ እየገባው ጋቢውን ለብሶ ቁጭ ብሎበት በነበረ መደብ ላይ ጥቅልል ብሎ ተኛ፡፡ በጆሮው ግን የእናቱን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ያዳምጣል፡፡
የሔዋን እናት የአስራትን አተኛኘት ካረጋገጡ በኋሳ ወደ ጓሮ ዞሩ። ልክ እንደ ታመሙ" ሁሉ ሰውነታቸውን ድክምም፤ ዓይናቸውን ቅዝዝ፣ ፊታቸውንም
ጭምድድ አድርገው ከሔዋን አጠገብ ደረሱና በቀስታ እየተቀመጡ «እንዴት ይሻለኛል
እሙዬ ስላልተቀሳቀስኩበት ነው መሰለኝ ይኸ ራሴ ተነሳና ይፈልጠኝ ጀመር ያንን ኪኒንና የምትሉትን ነገር ግዛልኝ ልለው ወደ ቤት ብገባ አስራቴ ደሞ ሆዴን አመመኝ ብሎ ተኝቶ አገኘሁት።
አሉና ኧረ እዲያ» በማለት ብስጭትና ምሬታቸውን ለመግለፅ ሞከሩ።

«አመመሽ እማ?» አለቻቸው ሔዋን ሁኔታቸውን ሰለል እያደረገች፡፡ብታይ ጦሩን ይዞ ሽቀሽቀኝ፡፡ አሏት ራሳቸውን በሁለት እጃቸው ይዘው
ወደ መሬት በማጎንበስ።
«ምን ዓይነት ኪኒን ይሆን?»
«ይኽ እምብሮ ነው ምንትስ የምትሉት!
«አስፕሪን ይሆናል::»
«ይሆናላ! እኔ አላቀው፡፡ እንዳንዴ ሲያመኝ ይኸው አስራቴ ነበር
የሚገዛልኝ። እንግዲህ አባታችሁ እስከሚመጣ ልጠብቅና የሚያውቀው ተሆነ ይገዛልኛላ::"» አሏት በግማሽ ልባቸው ወደ ሔዋን ወረቀቶች ዓየት እያረጉ፡፡
«እኔ እገዛልሻለሁ እማ!» አለቻቸው ሔዋን።
«አዬ...ልጄ! መንገዱ ይርቅሻል። የኛ ሰፈር ደሞ ገጠር አይሉት ከተማ አጉል ነው።ከሱቅ እስቲደርሱ ድረስ ያለው መንገድ መች ቀላል ነውና።ክ
«ግድየለም እማ! መግዣውን ስጪኝ፡፡» አለቻቸው።
«ተበረታሽ ደግ የኔ ልጅ!» ብለው ከተቀመጡበት ተነሱና ነይ ቤት
እሰጥሻለሁ፡፡» እያሉ ወደ ቤት አመሩ፡፡ አስራት ጥቅልል ብሎ እንደተኛ ነው፡፡
የእናቱንና የሔዋንን ወደ ቤት መግባት እውቆ የሚደረገውን ለመከታተል ጆሮውን አቁሞ ሳለ ሔዋን ተናገረችው።
«አመመህ እንዴ አስራት!»
«አረ ቁርጠት ሊገለኝ ነው፡፡» አላት ገልበጥበጥ እያለ።
የሔዋን እናት ፈጥነው ወደ ጓዳ ገብተዋል። «ቆይ ተኔ መድሃኒት
እንሰጥሀለን፡፡ እስከዚያው ቻለው፡፡» እያሉ ይዘው የመጡትን ገንዘብ ለሔዋን ሰጧት፡፡ ተቀብላቸው ከቤት ስትወጣ እስከ ውጭ ድረስ ሸኟት፡፡
ጥቂት ርምጃዎች እስክትራመድ ድረስ በዓይናቸው ሲከታተሏት ከቆዩ በኋላ ፊታቸውን ወደ ግቢው በር ምልስ አድርገው እስከ ቁርጭምጭሚታቸው ይደርስ
የነበረ የአበሻ ቀሚሳቸውን እስከ ጉልበታቸው ድረስ ሰቀሰቁና ወደ ቤት ሳይገቡ ወደ ጓሮ
በሚወሰደው መተላለፊያ መንገድ ሮጡ። ከቦታው ሲደርሱ የሔዋንን የወረቀት አቀማመጥ ልብ ብለው ተመለከቱ፣ወረቀቷን ሲመልሱ
አቀማመጡ እንዳይጠፋባቸው ተጠነቀቁ። ከዚያም የጻፈችባትን ወረቀት ከማስደገፊያዋ ደብተር
ውስጥ ቀስ ብለው መዝዘው አወጧትና አሁንም በሩጫ ወደ ቤት ገሰገሱ።
“እስቲ ተነስ እስራቴ! አሉት ቶሎ ቶሎ እየተነፈሱ።
አስራት ከተሸፈነበት ገለጥ ብሎ ከፊትለፊቱ የቆሙ እናቱንና በእጃቸው የያዝዋትን ወረቀት እየተመለከተ «ምንድነው?» ሲል ጠየቃቸው፡፡
«ቶሎ ተነስ! እሙዬ የጣፈችው ወረቀት ነው፡፡ ሳትመጣብን አንብበውና ከአስተቀመጠችበት ቦታ ልመልስ አሉት በተቻኮለ አነጋገር፡፡
አስራት ከተኛበት ቀና ብሎ ወሪቃቱን ተቀበለና አየት ሲያዩርግ ግጥም ደረድርበታለች፡፡ ከግጥሙ ዳርና ዳር ደግሞ የተለያዩ ቃላት ተሞነጫጭረውበታል።
አስቹ ሆዴ፣ የኔ ምስኪን.. ወዘተ የሚሉ፡፡ ወደ ዋናው ግጥም ከመግባቱ በፊት እነዚህን ቃላት አየት አየት ሲያደርግ ለካ ለሔዋን እናት ዘግይቶባቸው ኖሯል፡፡

“አንብበው እንጂ! አቃተህ እንዴ?» ሲሉ ጮሁበት፡፡ አስራት ግጥሞቹን ማንበብ ጀመረ።
እናቱም፣ ጀሮአቸውን አቁመው ያዳምጡ ጀመር።

«የኔ ሆድ አስቻለው አንተ የኔ ከርታታ!
ላመንከው ለመሞት የማታመነታ።
እመጣለሁ ብለህ ሄደህ እንደዋዛ፣
አንተም በዘያው ቀረህ የኔም አሳር በዛ፡፡
በእርግጥ ባትኖር እንጂ ፍጹም በሕይወት፣
አይጨክንም ነበር አስቹ የአንተ አንጀት።

የበላክን አውሬ ምነው ባገኘሁት፣
በውስጡ ባገኝክ እኔም በበላሁት።
ደምህን ከደሜ አጥንቴን ከአጥንትህ፤
አገናኝህ ነበር ነፍስ እንዲዘራብህ፡፡

የሳምከው ከንፈሬ ደርቋል እንደ ኩበት፤
እህል ውሃ ጠልቶ አንተ የሌለህበት፡፡

እንደው ሂጂ ሂጂ ብረሪ ይለኛል፣
እልም ያለው ገደል ባህሩ ይታየኛል።
ዛሬ ነገ አልኩ እንጂ ልቤ እየዋለለ፣
ስሜቴስ ይጮሀል በርቺ በርቺ እያለ።
ይጎነትለኛል የናፍቆት ሰቀቀን፣
አንተን ካላገኘሁ አይቀርም አንድ ቀን።»
«ኧ! ኧ! እስቲ እስቲ ድገመው!» አሉ የሔዋን እናት አሁንም ጆሮአቸውን ወደ አስራት ጣል አድርገው:: ዓይናቸው ፍጥጥ ማለት ጀምሯል፡፡
አስራት ቀስ ረጋ ብሎ ደግሞ አነበበላቸው: አንብቦ ከጨረሰም በኋላ እናቱ የሚሆኑትን ለማየት ቀና ብሎ በስጋት ዓይን ያያቸው ጀመር።
የሔዋን እናት ድንገት ጥርሳቸውን ግጥጥ፣ ፊታቸውን ክፍት አደረጉና
እንባቸውን እያዘሩ "እክክክክ..እክክክክ...እክክክክ" አሉ አንዳች የሀዘንና የስጋት
ስሜት ውስጣቸው ገብቶ በረብራቸውና፡፡ቀጠሉ አሁንም እጆቻቸውን በነጠላ ላይ ሸፍነው በወገባቸው ላይ በማሳረፍ ቀሚሳቸው በአየር ተንሳፎ
እስኪገለብ ድረስ በቆሙበት ላይ ወደ ግራ ቀኝ እየተወዛዙ «አንቲ» አሉ የጥሪ ያህል በረዘመ ድምፅ።
ሟቿን የአስቻለውን እናት መጥራታቸው ነው።«የጠጡት ጥዋ የለም? የካደሟት አድባር የለችም? የሳሙት ቤተክሲያን የለም፣? አረ አንድ በሉኝ! ኧረ በውቃቢዎ! ድረሱልኝ! ኧረ ልጆዎ ልጄን በላብኝ! ኧረ ልጄን አስመነነብኝ! ኧረ ምን አባቴን ልሁነው! እያሉ ዓይንና አፍንጫቸውን በነጠላቸው
እየጠራረጉ ልክ ሞታ ቀብረዋት ሀዘናቸው ገና እንዳልወጣላቸው አይነት ወያኔ ልጄን ወይኔ ልጄን እመዬ ምን ላርግሽ? እንደው ምን ልሁንልሽ? ልጄ! ልጄ! ልጄ! አሉ በተከታታይ።
“ምነው እማዬ! ምን ሆንሽ?» አላቸው አስራት ደንግጦ ።
በቃ እኮ እንግዲህ እኔም ልጄ በህይወት አለች ብዬ ተስፋ አላደርግም አንተም እህት አለችኝ ብለህ አታስብ! ልጂ ማምለጧ ነው። እሙዩ ተእንግዲህ ሰው አልሆነችም በቃ በቃ! በቃ በቃ! እህህህ።
«አረ ምንም አትሆን እማ»
«ኧረ ወዲያ አስራቴ በቃ ቁርጡን ነገረችን እኮ! በቃ ተናዘዘች እኮ!
«እሙዬ ገደል መግባቷ ነው እኮ! እ፤ህህህህህህ…"
«እንጠብቃታለና»
«አየየ... ጥበቃ! አየየ... ጥበቃ ዋልኝ! የሷ ነገር ተእንግዲህ ከበቃ
እኔም አብሬ ወደ ገደል ነው! እኔም ከእሷ ጋር ወደ ባህር ነው እህህህህህ» አስራት
👍8
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....“ግዝየ እኛ ነን።”

ጥላዬ፣ በወርቅ ያሸበረቀችው ቁስቋም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ሲገባ በቤተክርስቲያኗ ውበት ተማረከ። በአጥሩ ግንብ ማማር ተደነቀ።ፀሐይዋ አለዚያን ቀን እንደዚያ አብርታ የማታውቅ መስላ ታየችው።ቆም ብሎ ሁሉን በዓይኑ ቃኘ።

ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ከሞተ በኋላ፣ ምንትዋብን የማግኘት ፍላጎቱ
ቢበረታም አስራ ዐራት ዓመት ሙሉ ቆርጦ አለመነሳቱ ኅሊናውን
ሲቆጠቁጠው ቆይቶ፣ የኢዮአስን ሞትና የመንግሥቱን ማብቃት ሲሰማ አላስችል ብሎት ወደ ጐንደር አቀና።

ከአብርሃም ቤት ወጥቶ ቁልቁል ሲወርድ፣ የተጫጫነው ትካዜ፣ ገና ከደብረ ወርቅ ሲነሳ ምንትዋብ ላይ የደረሰው ድርብ ሐዘን፣ የጐንደር መበጥበጥ፣ የሃገሩ መረበሽ የልብ ስብራት የፈጠረበት መሆኑ ቀርቶ ዛሬ ቁስቋም ግቢ ውስጥ ሲቆም፣ ድንገት ሰላምና መረጋጋት በማግኘቱ ያችን ሰዐት ለዘላለም ለማቆየት የፈለገ ይመስል እዚያው ያለበት ቦታ
ቆሞ ቀረ።

ውስጡ የተቀጣጠለው የተስፋ ስሜት ያቺ ደማቅ ፀሐይ ከረጨችው ብርሃን ጋር ተዋሕዶ ልቡን አሞቀው። ለጊዜው እዚያ ቦታ ላይ ለምን እንደተገኘ ረስቶ፣ ሄዶ መሳለም ብሎም ጸሎት ማድረስ እንዳለበት ዘንግቶ ከቆመበት አልንቀሳቀስ አለ። ቁስቋምን በምናቡ ብራና ላይ
ሣላት። ቀደም ብሎ ጐንደር እንዲመጣ በሮብዓም ግብዣ ሲቀርብለት አለመቀበሉ የሚያየው ውበትና ታሪክ ተካፋይ ሳያደርገው በመቅረቱ ተቆጨ። አንዲት መነኩሴ እጅ ሲነሱት ደንገጥ ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው።
ምን ያህል ጊዜ እዚያ እንደቆመ ባያውቅም ወደ ቤተክርስቲያኗ በዝግታ አመራ። በወንዶቹ መግቢያ በኩል ሄዶ በሩን ተሳለመ። ቆም ብሎም
ዳዊቱን ከማኅደሩ አውጥቶ ደገመ።

ሲጨርስ፣ ዙርያውን ተመለከተ። ወደ ቤተመንግሥት የሚመራው
ሰው በዓይኑ ፈለግ ፈለግ አደረገ። ወደ መጣበት ሲመለስ፣ አንድ ቄስ
ከግቢ ሊወጡ ሲሉ አያቸውና “አባቴ!” ብሎ አስቆማቸው። እንዲባርኩት ከተጠጋቸው በኋላ፣ ወደ “እቴጌ ቤተመንግሥት በየት ነው ምሄድ?” ሲል ጠየቃቸው።

ቄሱም፣ “በዝያ በወንዶቹ መግቢያ በኩል ሲኸዱ ዘበኞቹን ያያሉ።
እነሱ ያሳይዎታል” ብለውት ተሰናበቱት።

ተመልሶ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ወንዶች መግቢያ አመራ። በስተጀርባ በኩል ቁልቁል ሲወርድ፣ ቄሱ እንዳሉት በግንብ የታጠረው በር ላይ ዘበኞች ቆመዋል። ትኩር ብለው ያዩታል። ራቅ ብሎ እጅ ነሳና፣ “እቴጌ
ዘንድ ጉዳይ ነበረኝ። ስሜ ሥሙር ነው። ኸነማይ ነው የመጣሁት።
የእቴጌ ዘመድ ነኝ።” ብሎ የያዘውን የተጠቀለለ ዕቃ አሳያቸው።

ዘበኞቹ፣ ጉዳዩ ምን እንደሆነ ደግመው ደጋግመው ከጠየቁት በኋላ፣እንዲጠብቅ ነግረውት አንደኛው ወደ ውስጥ ገባ። ጥቂት ቆይቶ አንድ ያደገደገ አስተናጋጅ መጥቶ ማን እንደሆነና ጉዳዩ ምን እንደሆነ አጥብቆ ከጠየቀው በኋላ ሄደ። ጥላዬ እንደገና ዘለግ ላለ ተጨማሪ ጊዜ ከጠበቀ በኋላ፣ አስተናጋጁ ተመልሶ መጥቶ እንዲከተለው በእጁ
ምልክት ሰጠው።

ግቢው ውስጥ ሲገባ፣ የምንትዋብ ቤተመንግሥት ከፊት ለፊቱ ገዝፎ ታየው። በስተቀኙ ያለው የጸሎት ቤቷን እያደነቀ ሲሄድ ግቢው ውስጥ ያለው የሰው ብዛትና ጫጫታ ገረመው። ሕፃናት ከወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ። “ኸነዝኸህ ውስጥ የልዥ ልዧቿ አሉበት መቸም”
ብሎ ወደፊት ሲመለከት ወይዛዝርትና ባለሟሎች ከወዲያ ወዲህ ይዘዋወራሉ። አስተናጋጁ በዝምታ ሲመራው ድንገት ግዙፍ የሆነ ግንብ ሲያይ ዝናውን የሰማው “ሽናዋ” የግብር አዳራሽ መሆኑ ገባው።የግንቡ ማማር ከፀሐይዋ ብርሃን ጋር ተደምሮ ዓይኑን አጭበረበረው።ምንትዋብን ራሷን እንደዛ ገዝፋ ያያት መሰለው።

ስለ ምንትዋብ ሲያስብ፣ ምን እንደሚጠብቅ ማወቅ አልቻለም።
ልጄ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ሞቶ፣ ቤተመንግሥት ሁለት ተከፍሎ ብሎም ፍርክስክሱ ወጥቶ፣ ወጣቱ ንጉሠ ነገሥት አድያም ሰገድ ኢዮአስ በሻሽ ታንቆ ተገድሎ፣ ሬሳው ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ፣ መሣፍንት በየበኩላቸው
ተቆራቁሰው፣ ሃገር ተተራምሶ፣ ወንድሟ ወልደልዑልና ዘመዶቿ አንድ በአንድ ሞተው፣ እሷ ቤተመንግሥቱን ጥላ ወጥታ ምን ልትመስል እንደምትችል መገመት ተሳነው። ቁስቋም ግቢ ውስጥ ሲገባ ተሰምቶት የነበረው የመንፈስ መነቃቃት ከውስጡ ሊተን ቃጣው።

አስተናጋጁ፣ በሽናዋ አዳራሽ በስተቀኝ በኩል ወዳለው እንቁላል
ግንብ ወደሚወስደው ደረጃ ሲወጣ ተከትሎት ወጣ። ቁና ቁና ተነፈሰ።ጉልበቱ ላለበት። ዕድሜው እንደገፋ ቢያውቅም አሁን በቅጽበት ጨምሮ የሸመገለ መሰለው። ደረጃውን ሲጨርሱ፣ ላብ አሰመጠው።በፍጥነት ግንባሩን ያራሰውን ላብ በኩታው ተም ተም አደረገው። እጁ
ውስጥ ሊንቆረቆር የሚታገለውን ላብ እጀ ጠባቡ ላይ ጠራረገው። በርላይ ሲደርሱ ቆም ብሎ ኩታውን አስተካከለ።
ግራና ቀኝ ያደገደጉ አስተናጋጆች ቆመዋል። አስተናጋጁ እርሱን
ለእነሱ አስረክቦ ወደኋላ ሲቀር፣ አንደኛው እልፍኝ አስከልካይ እጅ
ነስቶ “ይግቡ” አለና ቀደም ብሎ ገብቶ እጅ ነስቶ፣ “እቴጌ እንግዳው መጥተዋል” ብሎ አስቀደመው

ጥላዬ፣ ልቡ ከታች ምላሱ ካላይ ጉሮሮውን የዘጉበት መሰለው።

ምንትዋብ፣ ቀይ ከፋይ የለበሰ ሰፊ ወንበር ላይ ተቀምጣለች።
የለበሰችው ረጅምና ባለቀይ ጥበብ ቀሚስ ላይ የደረበችው በወርቅ ያጌጠው ሰማያዊ ካባ ልዩ ድምቀት ሰጥቷታል። ሹሩባዋ ላይ ሸብ ያደረገችው ነጭ ሐር ሻሽ ግርማ ሞገስ አክሎላቷል።

ጥላዬ፣ ልቡ ቷ አለበት፤ ሰውነቱ ራደ። ግርማ ሞገሷ አስፈራው።

ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። ያ በር ላይ ሲደርስ ሊያጥለቀልቀው የቃጣው
ላብ ፊቱ ላይ ክልብስ አለበት።

“ይቀመጡ” ብላ፣ ፊት ለፊቷ ያለ ወንበር በእጇ አሳየችው።

በእጁ ግንባሩን አሻሽና በጨርቅ የተጠቀለለውን ብራና ከብብቱ
ስር አውጥቶ፣ የተሸፈነበትን ጨርቅ ከላዩ ላይ አንስቶ እንደገና ለጥ ብሎ እጅ ነሥቶ፣ ሲሰጣት ምንትዋብ ተቀበለችው። ዕንጨት ላይ የተወጠረውን ብራና ስታየው ከዓመታት በፊት መነኩሴው ይዘውት መጥተው የነበረው ዓይነት የራሷ ምስል ነው።

“እርስዎን ደሞ ማን ላከዎት?” አለችው።

“ማነም አላከኝ። ዛሬስ ራሴ መጣሁ።”

“ሥሙር ማለት እርስዎ ነዎት?”

“እርስዎ አያስታውሱኝም። ግዝየውም ርቋል። የባላምባራስ ሁነኝ ልዥ ... ጥላዬ ነኝ።”

“ባላምባራስ ሁነኝ የቋራው ... የሳቸው ልዥ ... ጥላዬ?” ብላ የሷ
ያልመሰላት ድምፅ ከውስጧ ሲወጣ ተሰማት።

“አዎ... የቋራው ... ጥላዬ።”

ምንትዋብ ደነገጠች፤ ምላሷ ተቆለፈ። ከጥቂት ዝምታ በኋላ
እንደምንም ብላ፣ “ኧረ... በቁስቋሟ ተቀመጥ እንጂ!” አለችው፣ ወንበር እያመለከተችው።

ተቀመጠ።

ሁለቱም በዝምታ ተያዩ።

“ለካንስ አንተ ኑረኻል ካንዴም ሁለቴ ምስል ስትልክ የነበርኸው።
ለመሆኑ እስተዛሬ የት ነበርህ?”

ጥላዬ ፈገግ ብሎ ዝም አለ። ከመምጣቱ በፊት ሊላት በሐሳቡ
ያወጣው ያወረደው፣ ያለመውና የተመኘው ሁሉ ከጭንቅላቱ ብን
ብሎ ጠፍቷል። የቀረው ዝምታ ብቻ ብዙ ሐሳቦችን፣ በርካታ
ትዝታዎችንና ስሜቶችን የያዘ ከንግግር የላቀ ዝምታ። ለዚህ ቀን
ምን ዓይነት ቃላት ይበቁ ነበር? በዚያ ሁሉ የሐሳብ ውዥንብር ውስጥ አንድ ነገር ከአእምሮው አልወጣ አለ ንግሥታዊ ግርማ ሞገሷ።አፍዝ አደንግዝ የያዘው ይመስል አፉ ተሳሰረ። ስትናገር ደንገጥ ብሎ መስማት ጀመረ።

“ዛዲያ እስተዛሬ እንደዝኽ መምጣት እየቻልህ ስለምን ይኸን ያህል ግዝየ ቆየህ? እኔኮ ኸቋራ ኸወጣሁ ዠምሮ የት እንደደረስህም አላውቅም
ነበረ። ቤተመንግሥት እኮ እንዲህ ኸዘመድ እንደልብ ሚያገናኝ ቦታ
ማዶል ። እንደዝህ ስጎዳ ስለምን አልጠየቅኸኝም?”
👍8
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ዣቬር ምልክት ሲሰጣቸው ብዙ መሣሪያ የያዙ ፖሊሶች ከክፍሉ
ውስጥ ገቡ፡፡ ሽፍቶቹን ያዝዋቸው: ክፍሉ ውስጥ በርቶ የነበረው ሻማ
አንድ ብቻ ስለነበር ክፍሉ ውስጥ ሰው ሲበዛ ጊዜ ብዙ ጥላ በማጥለሉ እየጨለመ ሄደ።

«ሁሉንም በብረት ሰንሰለት እጆቻቸውን እሰሩ» በማለት ዣቬር አዘዘ

«በሉ ወደዚህ ኑ» የሚል ቀጭን የሴት ድምፅ ተሰማ፡፡ ሚስስ
ቴናድዬ ነበረች፡፡ ባልዋ ከለበሰችው ሰፊ ካባ ስር ተሸሽጓል፡፡

ጠንቀቅ በሉ!» ስትል በመጮህ ተናገረች::

ሽፍቶቹ በሙሉ ያለማንገራገር እጆቻቸውን ሰጥተው ሲጠፈሩ
በማየትዋ «ፈሪ ሁሉ!» ስትል አጉረመረመች፡፡

ዣቬር ፈገግ አለ፡፡ ሚስስ ቴናድዬ ወደነበረችበት አመራ፡፡

«አይጠጉኝ፧ ከዚህ ቶሎ ቢወጡ ይሻላል» ስትል በማንጓጠጥ
ተናገረች::«እምቢ ካሉ ዋጋዎን ነው የምሰጥዎት::»

«ደፋር» አለ ዣቬር፡፡ «እመቤቴ እንደ ወንድ ጢም አብቅለዋል፤ እኔ
ደግሞ እንደ ሴት ጥፍር አሳድጌአለሁ» ሲል አሾፈባት።

ዣቬር እየተጠጋት መጣ፡፡ አጠገብዋ አንዳንዴ ልጆችዋ አንዳንዴም ራስዋ የምትቀመጥበት ድንጋይ ነበር፡፡ ዘልላ ሄዳ ያንን ድንጋይ አነሳችና
ዣቬርን ለመምታት ወረወረችው:: ዣቬር ጎንበስ በማለት ራሱን አዳነ፡፡ድንጋዩ ከግድግዳ ጋር ሄዶ ተላተመ:: የግድግዳው ቀለም ፈራርሶ ወለሉን ሞላው:: ድንጋዩ ሲመለስ እየተንከባለለ ከዣቬር እግር ስር ደረሰ።

ዣቬር ወደ ባልና ሚስቱ ሄደ:: በአንድ እጁ የሴትዮዋን፤ በሌላ እጁ የወንዱን ትከሻ ጨምድዶ ያዘ፡፡

«መሣሪያ አምጡ» ሲል ጮኸ፡፡

ወዲያው የብረት ማሠሪያ መጥቶ ሁለቱ ሰዎች ተቀፈደዱ። የራስዋና
የባልዋ እጆች መቀፍደዳቸውን ባየች ጊዜ «ወይኔ ልጆቼ» በማለት ከጮኸች ኋላ ከመሬት ላይ ተዘረረች፡፡

«በእድላቸው ያድጋሉ» ሲል አፌዘባት::

ሦስቱ ፊታቸውን በከሰል ያጠቆሩና ሦስቱ ፊታቸውን በጨርቅ የሸፈኑ ሽፍቶች እጃቸው ታስሮ ቆመዋል::

«ፊታችሁን እንደሽፈናችሁ ቆዩ» አለ ዣቬር፡-

እያንዳንዳቸውን በስም እየጠራ አንዱን «እንደምን አመሸህ»፣ ሌላውን ጤና ይስጥልኝ»፤ ሌላውን ደግሞ «ብርቱም አልሰነበትክ» በማለት
ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ገና ከክፍሉ ሲገባ አንገቱን ደፍቶ ቆሞ
የነበረው እስረኛ ታወሰው::
«እስረኛውን ፍቱት» ሲል አዘዘ፡፡ «ከዚህ ቤት ደግሞ አንድ ሰው .
እንዳይወጣ?»
ይህን እንደተናገረ ከወንበሩ ላይ ሄዶ ቁጭ አለ፡፡ ከኪሱ ወረቀትና
ብዕር አውጥቶ ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ፡፡ ቀና ብሉ «እያየ እስረኛውን ወደዚህ አምጡት» አለ፡፡
ፖሊሶቹ በዓይን ፈለጉት::
«ምነው፤ ምን ያንቀረፍፋችኋል? የት አለ ሰውዬው?» ሲል
ጮኸባቸው::
እስረኛው አባባ ሸበቶ ከዚያ አልነበረም፧ ወጥቶ ሄዷል፡፡
በሩ ላይ ፖሊስ ቆሞአል፡፡ የነበሩበት ክፍል ፎቅ ቤት ነው:: ታዲያ የት ሄደ? መስኮቱ አጠገብ ፖሊስ አልነበረም:: ትርምሱ ሲበዛ ቀደም ሲል እነቴናድዬ ለማምለጫ ባዘጋጁት የገመድ መሰላል አድርጎ ሾልኮአል። የፖሊሶቹ ዓይን አርፎ የነበረው ሽፍቶቹ ላይ ነበር፡፡

«ጋኔላም!» አለ ዣቬር በጥርሶቹ መሀል፤ «ጥሩ ምስክር ይሆነን
ነበር፡፡»

በሚቀጥለው ቀን ማታ አንድ ልጅ በኃይል እያፏጨና እየዘመረ
በመንገድ ላይ ሲጓዝ ከአንድ ነገር ጋር ይጋጫል፡፡ የተጋጨው ከሴት ጋር ነበር፡፡ ለመውደቅ እንደ መንገዳገድ ይልና ወደኋላ ዞር ብሎ ይመለከታል::

«ምነው! ትልቅ ውሻ መስሎኝ ነበር፡፡»

አሮጊትዋ ገንፍላ ከተኛችበት ብድግ አለች፡፡

«የተረገምክ» አለች ፤ «ከድካም ብዛት ሰውነቴ ባይከዳኝ ምን
እንደማደርግህ አውቅ ነበር፡፡»
ልጁ ኣሁን ትንሽ ራቅ ብሎ ነበር የቆመው፡፡

«ፕስ... ፕስ...» በማለት ካሽሟጠጣት በኋላ «በካልቾ ማቅመሴ አልተሳሳትኩም ፤ አበጀሁ፤ አበጀሁ» ሲል ተናገራት፡፡
ሴትየዋ ከተቀመጠችበት ብድግ አለች፡፡ ልጁ ሮጦ ሸሽ፡፡ እርሱን ለመያዝ ስትሮጥ መብራት ከነበረበት ደረሰች፡፡ የፊትዋ መሸብሸብና የወገብዋ መጉበጥ በግልጽ ታየ:: ልጁ ራቅ ብሎ ቆሞ አጤናት።

«እኔ የምወደው መልክ የለሽም» ብሎአት እያዜመ መንገዱን ቀጠለ፡፡ የቤት ቁጥር 50-52 ስለደረሰ ቆመ፡፡ በሩ መቆለፉን ሲያይ በእርግጫ መታው
አመታቱ የልጅ ሳይሆን የአዋቂ ነበር፡፡ ለካስ መንገድ ተኝታ
ያያት ሴት ትከተለው ኖሮ ከነበረበት ደረሰች::

ምንድነው ነገሩ እባካችሁ? ያ ከበሩ ላይ የቆመው ማነው? የእግዜር ያለህ በሩን እየሰበሩት ነው፤ ሌቦች ከቤቴ ሊገቡ ነው» ስትል ጮኸች፡፡

ልጁ በር መደብደቡን ቀጠለ፡፡ ሴትዬዋ ትንፋሽ አጥሮአት መተንፈስዋ በግድ ሆነ፡፡

«የአሁነስ ዘረፋ ዓይን በዓይን ሆነ እንዴ?» ብላ ከጠየቀች በኋላ ልጁን አተኩራ ስትመለከተው ማን እንደሆነ አወቀችው፡፡

«እንዴ! ያ ርኩስ፤ ያ ሰይጣን ነው እንዴ!»

«ጉድ ፈላ! አሮጊትዋ ናትና» አለ ልጁ ወደኋላ እየሸሸ፡፡ «ዘመዶቼን
መጠየቅ መጥቼ እኮ ነው::»

«ከዚህ ማንም የለም፤ አንተ ጋኔል» አለች ሴትዬዋ ጥላቻዋን ከፊትዋ ላይ ለማሳየት እየሞከረች::

«አይ ምን ይላሉ እርስዎ ደግሞ፤ ታዲያ አባቴ የት ሄደ?»

«ላ ፎርስ ከተባለ ሥፍራ፡፡»
«እናቴስ?»
«ሳን ላዛር፡፡»
«እሺ፧ እህቶቼስ?»
«ሌ ማደለኔ ሄደዋል፡፡»
ልጁ ጆሮውን አከክ እያደረገ ሴትዮዋን ቀና ብሎ አያት:: ሴትዮዋ እነቴናድዬ ይኖሩበት የነበረው ቤት ጠባቂ ነበረች፡፡

«እንዴት ይሆናል?» ሲል ራሱን ጠየቀ።

ከዚያም ፊቱን አዙሮ ቀደም ሲል ያዜመው የነበረውን ዜማ እያዜመ
መንገዱን ቀጠለ፡

ቅዱስ ዴኒስና ከፕሎሜ
ጎዳና ያስ ቤት

ኢፓኒን

ማሪየስ ባጠመደው ወጥመድ ፍርድ ሲገለባበጥ አየ:: የፖሊሱ
አዛዥ እስረኞቹን ይዞ ወጣ፡፡ ማሪየስም ከነበረበት ክፍል ወዲያው ሄደ፡፡ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ገደማ ሆኖአል፡፡ ወደ ጓደኛው ቤት አመራ፡፡ ከጓደኛ
ው ከኩርፌይራክ ቤት እንደደረሰም ከእርሱ ጋር ለማደር እንደመጣ ገለጸለት፡፡ ኩርፌይራክም ከመሬት ላይ ፍራሽ አነጠፈለት::

በሚቀጥለው ቀን በጠዋት ከቤቱ ተመልሶ ያለበትን ቤት ኪራይ
ክፍሎ ቤቱን ለቀቀ፡፡ እቃውን በጋሪ አስጭኖ ከኩርፌይራክ ሰፈር ሄደ፡፡

ዣቬር የልጁን ስም ረስቶ ከቤቱ አገኘው እንደሆነ ብሉ ቢመጣ
አጣው:: ማሪየስን ለማግኘት ብዙ ሞከረ ፤ ግን አልተሳካለትም:: ምናልባትም ልጁ የሚደርሰውን አደጋ ላለማየት ብሎ በመፍራት ከአገር የጠፋ መሰለው::

ማሪየስ ግን ባየውና በተሰጠው ፍርድ እጅግ ተረብሾ ነበር፡፡ ሁሉም
ነገር ጨለመበት:: የሚያየው የወደፊት ተስፋ ከፊቱ ራቀ፡፡ ልቡ የተሰቀለላት ልጅና አባትዋ ድንገት እንደ ብርሃን ብልጭታ ብቅ ብለው እንደገና ተሰወሩበት:: የእርሱ የወደፊት ተስፋ እነዚህ የማይታወቁ ፍጡሮች ነበሩ፡፡
ልቡ በልጅትዋ ፍቅር ታውሮአል፡፡ «ሂድና ፈልጋት» ብሎ ስሜቱን
ቢገፋፋውም ዓይኑ ማየት ስላልቻለ እንዲያው ዝም ብሎ መረበሽ፤ መጠበብ፤
መጨነቅ ሆነ፡፡ ቀቢጸ ተስፋ ተጠናወተው:: ተስፋ የተለየው ሕይወት ጨለማ ስለሆነ ፀሐይ ወጥቶ ሳለ ምድር ጨለመችበት:: ዓይኖቹ የፍቅር ረሃብተኞች ቢሆኑም ለማየት የፈለጉትን ባለማግኘታቸው ከማየት ተቆጠቡ::ጀሮዎቹ ለመስማት የፈለጉትን ድምፅ ባለመስማታቸው ሌላ ነገር ከመስማት አፈገፈጉ፡፡ ልቡ የፈለገውን ሳያገኝ ሲቀር የፍላጎቱ መጠንና ግለት እየጎላ
👍20
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳምንቶች ሁለት ሦስቱ ሲያልፉ ጉዳዮች ደግሞ ከወደፊት ይልቅ የኋሊት
የሚሠግሡ መሰሉ የፍራንሲዝ ሌቪሰን ጉዳይ ፈቀቅ አልል አለ ባለ ዕዳዎቹም ፍንክች አላሉም ሰው እንዳያየው በሚስተር ካርላይል ዝግ ሠረገላ እየሆነ ሦስት ጊዜ ሌቪሰን ፖርክ ቢመላለስም ሰር ፒተርም እንደ ባለ ዕዳዎቹ ድርቅ አለ አንድ ጊዜ ለአንድ ዕዳ አንዲከፌል የሰጠውን ገንዘብ ለቪሰን ተቀብሎ ሳይከፍል ለራሱ
ማጥፋቱን ስለ ደረሰበት ፡ ሰር ፒተር በጣም ተናደደና ምንም ማድረግ እንደ ማይችል ነገረው " ሌቪሰን ወደ ነበረበት ወዶ አውሮፓ ከመመለስ በቀር ሌላ ተስፋ
እንደሌለው ተረዳ ።

ሰር ፒተርም የሱ ብጤ ከንቱዎች የተጠራቁሙበት እዚያው ስለሆነ፤ከሁሉ
ፍራንሲዝ ሌቪሰን የተሻለ የሚስማማው ወደዚያው ቢመለስ መሆኑን ነገረው
ሊሔድ ሲነሣ ሰር ፒተር የአንድ መቶ ፓውንድ ኖት አውጥቶ ወደሱ ሲመጣ ላወጣው ወጭ መተኪያ ብሎ ሰጠው ። አበሉንም እንደማያቋርጥበትም ገለጸለት ።

“ ዛሬ ከሰር ፒተር ጋር እንዴት ሆናችሁ ? አለው ሚስተር ካርላይል ማታ
ከራት ላይ እንደ ነበሩ ።

“ መቸም ምንም አይል” አለው ፍራንሲዝ ሌቪሰን ' “ ከሱ ጋር ምንም ያህል
ነገር አልፈጸምኩም " እነዚህ የዱሮ ሰዎች ጉዳዮችን ቶሎ አይቆርጡም " ጊዜ መውሰድ ደስ ይላቸዋል "

ከኢስት ሊን ለመውጣት ስለ አልፈለገና እውነቱን ቢናገር ደግሞ የማይሔድ
በት ምክንያት ስላልነበረው ያልሆነ መልስ ነገረው ።
በመሻሻል ፈንታ በፍጥነት እየባሰ የሔደው ደግሞ የሳቤላ ቅናት ነበር ። ባርባራን በየዕለቱ ከሚስተር ካርላይል ጋር ስትገናኝ ታያለች ካፒቴን ሌቪሰን ነገሩን እየተከታተለ የተመለከተውን እያጋነነ እየተነተነ ይነግራታል ። ሳቤላ በዚህ ጊዜ ራሷንና በዙሪያዋ ያሉትን ሁሉ ትጠላ ጀመር በባሏ ላይ አደገኛ የሆነ ጥላቻ ጠነሰሰች ጥንስሱም እየፈላ መጣ ካፒቴን ሌቪሰን ከሰር ፒተር ዘንድ በሔደበት
ቀን በሠረገላ ሆና በዌስት ሊን ስታልፍ ባሏና ባርባራ በጣም የጠበቀ ጫወታ እንደያዙ አገኘቻቸው " እነሱ ግን ሠረገላዋ ባጠገባቸው ዐልፎ ሲሔድ ልብ ብለው አላዩትም ።

በበነጋው ጧት የጆስቲስ ሔር ቤተሰብ ቁርስ ላይ እንደ ተቀመጡ ፖስተኛኛውን ሲመጣ አዩትና ባርባራ በመስኮቱ ዘልቃ አንድ ደብዳቤ ተቀበለችው "

“ ከማን የተላከ ነው ?” አላት አድራሻው ለሱ ባይሆንም የማንኛውንም ደብዳቤ ይዘት ለማወቅ ጉጉት የነበረው አባቷ ።

“ ከአን ነው ... አባባ” አለችው ደብዳቤውን ከጐኗ በማስቀመጥ "

“ ታዲያ ለምንና ምን ብላ እንደ ጻፈችው ከፍተሽ አታይውም ?”

“ እከፍተዋላሁ " ለእማማ ሻይ ልቀዳላት ብዬ ነው „”

ባርባራ ሻዩን ለናቷ ሰጥታ ፖስታውን ስትከፍተው፡አንዲት ትንሽ የታጠፈች
ወረቀት ከጭኗ ላይ ወደቀች : ደግነቱ ግን አባቷ ከቡናው ስኒ እንዳቀረቀረ ስለ ነበር ወረቀቲቱን አላያትም ሚስዝ ሔር ግን አይታ ነበር "

“ባርባራ አንድ ነገር ጣልሽ"

ባርባራም ወረቀቲቱን አይታ ስለ ነበር ቀስ አድርጋ ሳትታይ ያዘቻት ።
“ አንቺ የኔ ልጅ ኧረ አንድ ነገር ከጭንሽ ላይ ወይቀ ”
“አንቺ እናትሽን አትሰሚያትም እንዴ?

"ምንድነው የጣልሽው? አላት አባቷ"

ባርባራ ፊቷ በድንጋጤ እንደ ቀላ ከተቀመጠችበት ተነሣችና ልብሷን አራገፈች “ምንም ነገር የለም... አባባ ” አለችው " ከዚያ ከቦታዋ ተመልሳ ከተቀመጠች በኋላ እናቷን ዝም እንድትል በዐይኗ ገረመመቻት "

ባርባራ የእኅቷን ደብዳቤ አንብባ ማየት የሚፈልግ እንዲያየው ጠረጴዛው
ላይ አኖረችው ።

አባትየው ቶሎ አነሣና ከተመለከተው በኋላ እያልጐመጐመ ከጠረጴዛው ላይ
ጣለው "

“ ዱሮውንም ከአን ደብዳቤ ምንም አይገኝም ። እስኪ አንድ ስኒ ቡና ጨምሪልኝ ' ባርባራ ። ”

በመጨረሻ ዳኛው ቁርሱን በልቶ ካበቃ በኋላ ወደ አትክልቱ ቦታ ለመንሸራሸር ወጣ ። ሚስዝ ሔር ባርባራን ቀና ብላ አየቻት "

“ ልጄ ... ምን አድርጌሽ ነው እንደዚያ ተቆጥተሽ ያየሺኝ ? ከጭንሽ ላይ
የወደቀውስ ምን ነበር ? እኔማ ከአን ደብዳቤ የወደቀ መስሎኝ ነው ።

“ እሱስ ነው ፤ከአን ፖስታ ነው የወደቀው ። አባባ ግን ሁሉን ነገር እኔ ልየው እያለ መጠየቅ ይወዳል አን ለማንም ሳይሆን ለኔ ብቻ በተለየ ወረቀት አብራ ትጽፍልኛለች " ምናልባት ከዚህ አብራ ከአንድ ፖስታ ከምትልካቸው ትናንሽ ደብዳ
ቤዎች አንዱ ሊሆን ይችላል

“ ባርባራ አባትሽ ላንቺ የሚጻፉትን ደብዳቤዎች ማየት አይችልም የምት
ይው ደስ አይለኝም ።”

“ የምትይው እውነት ነው ... እማማ ። እሱ ግን ትንሽ ልብ ቢኖረው እኔና አንም ስለየግላችን የመጻጻፍ ነጻነት ሊኖረን እንደሚገባ ማወቅ አለበት " እሱ በሆነው ባልሆነው ጥልቅ ማለት አያስፈልገውም ነበር

ባርባራ ወድቃ የነበረችውን ወረቀት አውጥታ “እማማ ... ስለ ሪቻርድ
ነው” አለቻትና አነበበችላት
“ ከሪቻርድ ቀንም ስምም የሌለው ማስታወሻ ደረሰኝ እኔም በጽሑፉ ነው ያወቅሁት አሁን የተወለደችው ጨረቃ ስትደምቅ ስለሚመጣ ከአፅዱ እንድትጠብቂው ሲመጣ ምልክት ያሳይሻል” ይላል የአን ወረቀት "

ሚስዝ ሔር ፊቷን ለጥቂት ደቂቃዎች ሸፍና ቆየች።

ግን እኮ ... እማማ ለመምጣት ሙከራው ለሱ አደገኛ ነው'' አለቻት

“ በሕይወት መኖሩን ማወቅሳ ! ስለ አደጋው እስካሁን የጠበቀው አምላክ
ይጠብቀዋል ይልቅስ ልጄ
እሷን ወረቀት አጥፊያት ''

« በፊት አርኪባልድ ካርላይል ያንብበወና ኋላ አጠፋታለሁ "

“ እንግዲያውስ ዛሬ ፌልግሽ አሳይው።እሱን ካላጠፋሽ ልቤ አያርፍልም"

ባርባራ ሚስተር ካርላይልን ፍለጋ ወደ ዌስትሊን ብትዘልቅ ወደ ሊንበራ መጓዙን ሚስተር ዲል ነግራት ከዚያ ወደ ቤቷ ተመልሳ ሲያልፍ እንድታገኘው ከበር
ስትጠብቅ አመሸች " ሲቀር ጊዜ በሌላ በኩል አድርጐ ወደ ቤት ዐልፎ ይሆናል
በማለት ወደ ኢስት ሊን ሔደች " እዚያ ስትደርስ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተደወለ

ሚስተር ካርላይል አሁን ነጻ ነው ወይስ ሥራ ይዟል ?

«ሚስተር ካርላይል
አልገቡም እሜቴ ና ሚስ ካርላይልም ራት እየጠበቋቸው ነው ” አለና በሩን የከፈተው አሽከር እንድትገባ ጠየቃት " እሷ ግን ገብታ ለማነጋገር አላሰኛትም ነበርና ተመልሳ ሔደች "

በመስኮት ቁማ የባሏን መምጣት ስትጠብቅ የነበረችው ሳቤላ ባርባራን ወደ ቤት ስትመጣና ተመልሳ ስትወጣ አየቻት ወዲያው ደግሞ በሩን የከፈተላት አሽከር ሳቤላ ወደ ነበረችበት ክፍል ገባ
“ ያቺ ሚስ ሔር አይደለችም እንዴ ? አለችው " ናት . .
እመቤቴ ጌቶችን ነበር የፈለገች " እኔ እንኳን የእርስዎን መኖር ነግሬአት ነበር ግን ለመግባት አልፈለገችም :

ሳቤላ ምንም ሳትመልስ ዝም አለች " ፍራንሲዝ ሌቪሰን በአስተዛዛኝነት
መልኩ ሲያያት አየችው " እጆቿን እስኪያማት ድረስ እያፋተገች ወደ መስኮቱ ተመለሰች "

ባርባራ እያዘገመች ቁልቁል ስትወርድ ሚስተር ካርላይል ቶሎ ቶሎ እየተራመደ! አሻቅቦ ወደ ቤቱ ሲመጣ ተገናኙና ሲጨባበጡ ሳቤላ አየቻቸው "

“ ከቢሮህ መጥቸ አጣሁህ ፤ ይኸውልህ ይህ ወረቀት ከሪቻርድ ደረሰኝ "ብላ ያችን ቁራጭ ወረቀት ሰጠችው "

ሚስተር ካርላይል ወረቀቲቱን ተቀብሎ ሲያነብ ባርባራ ተጠግታ ስትመለከተው እነሱን ደግሞ በቅናት የተንገገበችው ሳቤላና በተንኮል የተመረዘው ካፕቴን ሌቪሰን በመስኮት ዘልቀው ከሩቅ ይመለከቷቸው ነበር ኮርኒሊያ ካርላይል
አየቻቸው
👍18
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

“ደህና እደሪ ካተሪን፡ በጣም ጥሩ እህትና ለመንትዮቹም እናት ነሽ. ግን በጣም ቀሽምና ጥሩ ያልሆንሽ ሌባ ነሽ" አለኝ።.

እያንዳንዱ የክሪስ የእናታችንን ክፍል መጎብኘት የተደበቀውን ገንዘባችንን መጠን አሳደገው ነገር ግን ግባችን የሆነው አምስት መቶ ዶላር ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ይወስዳል አሁን እንደገና በጋ መጣ: አሁን አስራ አምስት አመት ሆኖኛል። መንትዮቹ በቅርቡ ስምንት አመት ይሆናቸዋል። በቅርቡ ነሀሴ ሲመጣ የታሰርንበት ሶስተኛ አመት ይሆናል። ሌላ ክረምት ከመግባቱ በፊት ማምለጥ አለብን፡ ኬሪን ስመለከተው ፍዝዝ ብሎ አደንጓሬዎች ይለቅማል። ምክንያቱም የመልካም ዕድል ጥራጥሬ ስለሆኑ ነበር በአዲሱ አመት መጀመሪያ ትንንሾቹ ቡናማ አይኖች ውስጡን እንዳያዩት ብሎ አይበላቸውም ነበር አሁን ግን እኔና ክሪስ እያንዳንዱ አደንጓሬ የአንድ ቀን ሙሉ ደስታ ይሰጣል ብለን ስለነገርነው ይበላል እኔና ክሪስ እንደዚህ አይነት ተረቶች እየፈጠርን እንዲበሉ እናደርጋለን፡ ወለሉ ላይ ይቀመጥና ጊታሩን አንስቶ
አይኖቹን የካርቱን ፊልም ላይ ይተክላል። ኬሪ በቻለችው መጠን ወደሱ
ተጠግታ ቲቪውን ሳይሆን የሱን ፊት እየተመለከተች ትቀመጣለች።

"ካቲ" አለች በዚያች እንደ ወፍ በመሰለች ድምፅዋ

“ኮሪ ደህና አይደለም፡”

“እንዴት አወቅሽ?”

“በቃ አወቅኩ”

“አመመኝ ብሎ ነግሮሻል?”

“ማለት የለበትም”

“እና ምን ተሰማሽ?”

“እንደ ሁልጊዜው”

“እንደ ሁልጊዜው እንዴት ነው?”

“አላውቅም”

"አዎ! መውጣት አለብን፣ በፍጥነት!

በኋላ ላይ መንትዮቹን አንድ አልጋ ላይ አደረግኳቸው: ሁለቱም እንቅልፍ
ሲወስዳቸው ኬሪን አንስቼ ወደ አልጋችን እወስዳታለሁ ለአሁን ግን ለኮሪ
እህቱ አጠገቡ ሆና መተኛት በጣም የሚመች ነው: “ሮዝ አንሶላ አልወድም።”
አለች ኬሪ ተኮሳትራ “ሁላችንም ነጭ አንሶላ ነው የምንወደው: ነጩ አንሶላ
የታለ?”

እኔና ክሪስ ነጭ ከሁሉም ቀለማት ይልቅ ተስማሚ ነው ብለን የተናገርንበት
ቀን ፀፀተኝ። ካቲ እናታችን በአብዛኛው ጥቁር ቀለም ያላቸውን ቀሚሶች
የምትወደው ለምንድነው? ጠየቀች ኬሪ ሮዙን አንሶላ አንስቼ በነጭ እስክቀይረው እየጠበቀች።

“እናታችን ፀጉሯ ቢጫና የፊቷ ቀለም ነጣ ያለ ነው፡ እና ጥቁር ቀለም ደግሞ
የበለጠ ቆንጆ ያደርጋታል።

“ጥቁር አትፈራም?”

“ጥቁር ቀለም በትልልቅ ጥርሶቹ የማይባላ መሆኑን ለማወቅ ስንት አመት
መሆን ነው ያለብሽ?”

“እንደዚህ አይነት የሞኝ ጥያቄዎችን ማወቅ የምችልበት በቂ እድሜ ሲኖረኝ::

“ግን ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ያሉት ጥቁር ጥላዎች ሁሉ የሚያበራ፣
ሹል ጥርሶች አሏቸው::” አለ ኮሪ ሮዙ አንሶላ እንዳይነካው እየሸሸ።

“አሁን ተመልከቱ” አልኩ የሆነ ዘዴ እየፈጠርኩ እንደሆነ ጠርጥሮ ክሪስ
በሚስቁ አይኖቹ እያየኝ ነው: “እናንተ ቆዳችሁ አረንጓዴ፣ አይናችሁ
ወይንጠጅ፣ ፀጉራችሁ ቀይ እንዲሁም በሁለት ጆሮዎች ፋንታ ሶስት ጆሮዎች
ከሌሏችሁ በስተቀር ጥቋቁሮቹ ጥላዎች የሚያበራ ሹል ጥርስ አያወጡም::እንደዛ ከሆነ ብቻ ነው ጥቁር የሚያስፈራው:”

ዘና አሉ‥ ከዚያ ነጭ አንሶላቸውንና ነጭ ብርድ ልብሳቸው ውስጥ ገቡና
ወዲያው እንቅልፍ ወሰዳቸው ከዚያ ገላዬንና ፀጉሬን ለመታጠብና ልብሴን ለመቀየር ጊዜ አገኘሁ: ጣራው ስር ወዳለው ክፍል ሮጥኩና መስኮቶቹን ከፋፈትኳቸው፡ ቀዝቃዛ አየር ገብቶ ክፍሉን እንዲያቀዘቅዘውና ጠውልጌ
ከምቀመጥ የመደነስ ፍላጎት እንዲሰማኝ ፈልጌያለሁ ንፋሱ ወደ ክፍሉ መግቢያ የሚያገኘው በክረምት ብቻ የሆነው ለምንድነው? ለምን አሁን በጣም በምንፈልገው ጊዜ አይመጣም?

እኔና ክሪስ ሀሳቦቻችንን፣ ተስፋዎቻችንን፣ ጥርጣሬዎቻችንንና ፍርሀቶቻችንን
አንንነጋገራለን ችግር ሲያጋጥመኝ ዶክተሬ ነው: እንደመታደል ሆኖ
የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ከባድ አይደሉም ወር ሲመጣ የሚያጋጥመኝ
ቁርጠትና የወር አበባዬ በፕሮግራሙ መሰረት አለመምጣቱ ብቻ ነበር።
ለዚህም ዶክተሬ የሚጠበቅ እንደሆነ ይነግረኛል። እኔ በረባው ባልረባው ጥንቃቄ የማደርግ አይነት ስለሆንኩ ውስጣዊው ማሽኔም ይህንኑ ይከተላል።

ስለዚህ አሁን በመስከረም አንድ ምሽት እኔ ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ
ሆኜ ክሪስ ሊሰርቅ ሄዶ የሆነውን ነገር ልክ ክሪስ የነበረበት ቦታ እንደሆንኩ
አድርጌ መፃፍ እችላለሁ: ስለዚህ የተለየ ወደ እናታችን ክፍል የተደረገ ጉዞ
በዝርዝር ነግሮኝ ነበር።
እንደነገረኝ መሳቢው ውስጥ ያለው መፅሀፍ ሁልጊዜ ይስበው ነበር ማረከው፣በኋላ ግን አስጥሞታል። ልክ እንደኔ ለምሽቱ የፈለገውን በቂ ገንዘብ ካገኘ በኋላ ልክ በማግኔት እንደተሳበ አይነት ወደዛ ጠረጴዛ ሄደ።

እሱ እያወራልኝ እኔ ግን በአንድ እይታ እያንዳንዱ ፎቶግራፍ ለዘለአለም
ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ እያለ ለምን እሱ ደጋግሞ ይመለከተዋል? እያልኩ
ከራሴ ጋር እያወራሁ ነበር:

“እዚያ ቆሜ በየጊዜው የተወሰኑ ገፆች ላይ የተፃፈውን እያነበብኩ ነበር” አለኝ እና ስለ ትክክልና ስህተት ስለሚባሉ ነገሮች እያሰብኩና ስለ ተፈጥሮ፣ ደስ ስለሚያሰኘው እንግዳ ጥሪዎቹ እየተገረምኩና ስለእኛ ህይወት ሁኔታዎች
እያሰላሰልኩ ነበር ስላንቺና ስለኔ እያሰብኩ ነበር፡ እነዚህ ለእኛ የማበቢያችን
አመታት መሆን ይገባቸው ነበር። በማደጌና በእኔ እድሜ ላይ ያሉ ወንዶች
ፈቃደኛ ከሆኑ ሴቶች ሊያገኟቸው የሚችሉ ነገሮችን ስለማሰብ ጥፋተኝነትና እፍረት ይሰማኛል። እና እዚያው ቆሜ ባላገኝሽ እያልኩ ስመኝ አዳራሹ ውስጥ ወደ ክፍሉ እየቀረበ የሚመጣ ድምፅ ሰማሁ። ማን እንደሆነ ታውቂያለሽ እናታችንና ባሏ እየተመለሱ ነበር። በፍጥነት መጽሀፉን ቦታው ላይ መለስኩና ቀጥሎ ትልቁ አልጋው አጠገብ ያለው የእናታችን ልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ ተደበቅኩ: ከገባች አታየኝም ብዬ አሰብኩ። ግን ልታየኝ እንደምትችልም ተጠራጥሬያለሁ። ነገር ግን ይህንን እያሰላሰልኩ
ድንገት በሩን ሳልዘጋ መርሳቴን አስታወስኩ።

የዚያን ጊዜ ነው የእናታችንን ድምፅ የሰማሁት። “የእውነት ባርት? አለች
ወደ ክፍሉ ገብታ መብራት እያበራች። “ብዙ ጊዜ የኪስ ቦርሳህን መርሳትህ
ግዴለሽነትህን ያሳያል”

“ተመሳሳይ ቦታ ስለማላስቀምጠው ነው የምረሳው:” ሲል መለሰላት።እቃዎችን ሲያንቀሳቅስ መሳቢያዎችን ሲከፍትና ሲዘጋ ይሰማኛል። ከዚያ “እዚህኛው ሱሪ ኪስ ውስጥ እንደተውኩት እርግጠኛ ነኝ ... ካለ መንጃ ፈቃዴ የትም መሄድ አልችልም::” አለ

“በአነዳድህ ላይ ቅሬታ የለኝም፧ ግን በዚህ ምክንያት እንደገና ልንዘገይ ነው ምንም ያህል በፍጥነት ብትነዳ የመጀመሪያው ክፍል ያመልጠናል” አለች
እናታችን

“ሄይ!” አለ ባሏ ድምፁ ውስጥ መደነቅ ይሰማኛል። ምን እንዳደረግኩ አስታውሼ በውስጥ አቃሰትኩ ቦርሳዬ ይኸው ኮመዲኖው ላይ: እዛ ላይ ማስቀመጤን አላስታውስም ሱሪው ውስጥ እንደነበረ መማል እችላለሁ” አለ

“መሳቢያው ውስጥ ደብቆት ነበር” ክሪስ አብራራልኝ፡ “ሸሚዞቹ ስር ተቀምጦ ጰነው ያገኘሁት: የተወሰኑ ገንዘቦች ወስጄ ከዚያ አስቀምጬው ያንን መፅሀፍ እሱ እያወራልኝ እኔ ግን በአንድ እይታ እያንዳንዱ ፎቶግራፍ ለዘለአለም ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ እያለ ለምን እሱ ደጋግሞ ይመለከተዋል? እያልኩ
👍511
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወሮበሎቹ የሚፈልጉትን ማግኘታቸው አያስደስተውም የሉተር ዕቅድ ቢጨናገፍ ደስታው ነበር፡፡ ነገር ግን ሉተር ጎርዲኖን ካላስለቀቀ ኤዲ ካሮል አንን ማግኘት አይችልም፡፡

ካሮል አንን በእጄ ካስገባሁ በኋላ ጎርዲኖ መያዙ አይቀርም  ሲል አሰበ፡ ይህ ግን የሚሆን አልመሰለውም፡፡ ጎርዲኖ በዚህ ጊዜ ውስጥ ርቆ
ሊሄድ ይችላል፡ ሌላው አማራጭ ሉተር ካሮል አንን በመጀመሪያ በእጁ
እንዲያስገባለት መደራደር ቢሆንም ሉተርን ለማስገደድ ምንም ማስፈራሪያ የለውም፡ ሉተር በአንፃሩ ካሮል አንን ይዟል፡

ወዲያው አንድ ሃሳብ ብልጭ አለበት፡፡ ጎርዲኖ በእኔ እጅ እኮ ነው ያለው፤ እሱን እንደማስፈራሪያ መጠቀም እችላለሁ› አለ፡፡ እነሱ ካሮል አንን ይዘዋል፧ እሷን ለማግኘት ከእነሱ ጋር መተባበር አለብኝ፤ ነገር ግን ጎርዲኖ በዚህ አይሮፕላን ላይ ነው ያለው፡፡ እሱን ማግኘት ከፈለጉ ከእኔ ጋር
መተባበር ይኖርባቸዋል
ሁሉም ነገር በእነሱ እጅ አይደለም ሲል በአዕምሮው አውጠነጠነ።

ስለዚህ የድርድሩን መዘውር በእጁ ማስገባት የሚችልበት መንገድ
ይኖር እንደሆን ማሰብ ጀመረ፡፡

አንድ መንገድ ይኖራል።

ለምንድን ነው እነሱ በመጀመሪያ ጎርዲኖን የሚወስዱት? ልውውጡ
መሳ ለመሳ ነው መከናወን ያለበት፡፡›

ከዚያም ንዴቱን ውጦ በጥልቅ ማሰብ ጀመረ፡

‹እንዴት ነው ልውውጡ ሊከናወን የሚችለው?

ጎርዲኖን ሊወስዱ በሚመጡበት ጀልባ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው።
ለምን አይሆንም?  ሲል ከራሱ ጋር ተሟገተ፡፡ እሷን ያገቷት ከቤታቸው ብዙም ባልራቀ ቦታ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህም  ቦታ አይሮፕላኑ ከሚያርፍበት ቦታ ብዙም እንደማይርቅ ገምቷል፡፡ ምናልባትም ከአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦታ እሷ እስከታሰረችበት ቦታ ድረስ የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ሊሆን ይችላል፡ ይሄ ደግሞ ሩቅ አይደለም፡፡

ኤዲ ባሰበው እቅድ ሉተር የሚስማማ ከሆነ ጓደኞቹን በስልክ ሊያናግር
የሚችለው አይሮፕላኑ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ቦትውድ (ካናዳ) ላይ ሲደርስ ይሆናል፡፡ ከቦትውድ ቀጥሎ አይሮፕላኑ የሚያርፈው ከሰባት ሰዓት ጉዞ በኋላ ማለትም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ሼዲያክ ላይ ነው: ወሮበሎቹ ደግሞ
በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ እዚያ ቦታ ላይ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው::

ኤዲ ካሮል አንን አስቀድሞ በእጁ ሊያስገባ እንደሚችል ሲያስበው ደስታውን መቆጣጠር አቃተው፡ የሉተርንም ጎርዲኖን የማስለቀቅ ጥረት
ሊያመክን እንደሚችል ትንሽ እድል እንዳለ ሲያስበው ደግሞ ተጨማሪ
ደስታ ፈጠረለት፡፡ ይሄ ደግሞ በስራ ባልደረቦቹ በኩል ጀግና ያስብለዋል፡
እነዚህን ነፍሰ ገዳይ ወሮበሎች መያዝ ከቻለ ጓደኞቹ ቀደም ብሎ ለፈጸመው ክህደት ምህረት ያደርጉለታል፡፡
መለስ ብሎ ሲያስበው ደግሞ ብዙ ተስፋ ማድረግ እንደሌለበት ገባው፡፡
ይሄ ሁሉ ገና ሀሳብ ነው፡፡ ሉተርም ባሰበው እቅድ አልስማማም ሊል ይችላል ኤዲ ያቀረበውን እቅድ ወሮበሎቹ የማይቀበሉ ከሆነ አይሮፕላኑን
የተባለው ቦታ እንደማያሳርፍ ያስጠነቅቃል፡ ነገር ግን ወሮበሎቹ የኤዲን
ማስፈራሪያ ከባዶ ዛቻ እንደማይዘል መገመት አያቅታቸውም፡፡ ኤዲ ሚስቱን ለማዳን ሲል የተባለውን ሁሉ እንደሚፈፅም ያውቃሉ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን
ሰው በእጃቸው ከማስገባት ውጭ ምንም ፍላጎት የላቸውም፡፡ እኔ ከነሱ
በላይ የተቸገርኩ ስለሆንኩ አቅመ ቢስ ነኝ ሲል አሰበ፡፡ ይህም ወደ ቀድሞው መከፋት ወሰደው፡፡

ሆኖም ኤዲ ያሰበውን ለሉተር ለመንገር ሰውዬውን ለመፈተን አሰበ፡፡
ቢያንስ ሰውዬውን ጥርጥርና ጭንቀት ውስጥ መክተት ይችላል፡፡ ምናልባት ሉተር የኤዲን ማስፈራራት አምኖ ላይቀበል ይችላል፡ ግን እንዴት እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹ኤዲ ውሸቱን ነው› ለማለት ወኔ ይጠይቃል፡፡ ሉተር ደግሞ ፈሪ እንደሆነ ታይቷል፤ በተለይ አሁን፡፡

ኤዲ ያሰበውን ለመሞከር ቆረጠ፡፡ ከሉተር በኩል ሊመጣ የሚችለውን
ተቃውሞ ለመመከት የሚያስችል ምላሽ አስቀድሞ መቀመር አለበት፡፡

ሉተር እንቅልፍ ካጡት ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በእንግዳ መቀበያው አንድ ጥግ ቁጭ ብሎ ብቻውን ዊስኪውን ይጨልጣል፡፡አይሮፕላኑ የፈጠረበት የሆድ መታወክ አሁን ስለቀነሰለት ፊቱ ፈካ ብሏል መጽሔት እያነበበ ነው፡፡ ኤዲ አጠገቡ ሄደና ጀርባውን ነካ አደረገው፡፡ ሉተር ኤዲን ሲያይ ደንገርገር አለው፤ ፍርሃት ብጤም ስለተሰማው ጠብ ጠብ ሸተተው፧ ኤዲም ‹‹ሚስተር ሉተር ካፒቴኑ ሊያናግርህ ይፈልጋል›› አለው፡፡

ሉተር ስጋት ገባው፡፡ ከተቀመጠበት አልነሳ ሲል ኤዲ ተነስቶ የጭንቅላት ምልክት አሳየው፡፡ከዚያም ሉተር መጽሔቱን አስቀመጠና የመቀመጫ ቀበቶውን አላቆ ተነሳ፡፡

ኤዲ ሉተርን ወደ ማብረሪያው ክፍል ሳይሆን ወደ መጸዳጃ ቤት ወሰደው፡፡፤

መጸዳጃ ቤቱ በትውከት ሽታ ታውኳል፡፡ እንደ እድል ሆኖ አንድ ሰው እጁን እየታጠበ ስላገኘ ኤዲ መጸዳጃ ክፍሉ ውስጥ እንዲቆይ ለሉተር የእጅ ምልክት ሰጠውና እሱ ማበጠሪያ አውጥቶ እያበጠረ ጠበቀው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እጁን የሚታጠበው ተሳፋሪ ከመጸዳጃ ክፍሉ ወጥቶ ሄደ፡፡ ኤዲም የሰውየውን መውጣት ተከትሎ ሉተር ያለበትን መጸዳጃ በር ቆረቀረ ሉተርም ‹‹ምን ፈለግህ?›› ሲል አምባረቀ፡፡
‹‹አፍህን ዝጋና አዳምጥ›› አለው፡፡ ኤዲ ከሉተር ጋር ጠብ ለመፍጠር አላሰበም፡፡ ሉተር ግን ጠብ ጠብ ብሎታል፡፡ ‹‹እዚህ አይሮፕላን ላይ ምን
እንደምትፈልጉ ደርሼበታለሁ ዕቅዳችሁን አውቄዋለሁ አሁን  የእቅድ
ለውጥ አድርጌያለሁ፤ እኔ አይሮፕላኑን የማወርድበት ቦታ ላይ ካሮል አንን
በጀልባ ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ›› አለው፡፡ሉተር አፉን በንቀት ሸረመመና ‹‹አንተ ጥያቄ ማቅረብ እኮ አትችልም የተባልከውን ማድረግ እንጂ›› አለው፡፡

ሉተር እንዲህ አይነት መልስ ይሰጣል ብሎ ኤዲ አልገመተም፡
‹‹እንግዲያውስ ስምምነታችን እዚህ ላይ አብቅቷል›› አለው ኤዲ፡
ሉተር መጨነቁን ፊቱ እያሳበቀበት ነው፡፡ ‹‹አንተ እኮ ምርጫ የለህም፧
ስለዚህ አፍንጫህን ተይዘህ አይሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ
ያቺን ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታክል ሚስትህን ማስመለስ ትፈልጋለህ፧
ስለዙህ አፍንጫህን ተይዘክ
አውሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ አለብህ››

‹‹እውነት ነው፡፡ ነገር ግን…›› ኤዲ ራሱን እየነቀነቀ ‹‹አላምናችሁም›› አለው ሉተርን «እንዴት አምናቹሀለው እኔ እናንተን አምኜ ሁሉን ነገር አድርጌ ብትከዱኝ እድሌን ማበላሸት የለብኝም።አዲስ ድርድር
እንድናደርግ እፈልጋለሁ፡፡››

የሉተር የመንፈስ ብርታት አሁንም ፍንክች አላለም፡:
አዲስ ስምምነት የለም›› አለ ፈርጠም ብሎ፡፡

አሁን ኤዲ ሉተርን የሚያንበረክክበትን ነገር መዘዘ ‹‹እሺ እንግዲያው
ወህኒ ትወርዳለህ›› አለው፡፡

ሉተር የንዴት ሳቅ ሳቀና ‹‹ምንድን ነው የምታወራው?›› ሲል ጠየቀ
ኤዲ አሁን ጥንካሬ ገባው፡፡ በአንጻሩ ሉተር ደግሞ ደካማ ሆኗል፡ለካፒቴኑ ሁሉን ነገር እነግረውና በሚቀጥለው የአይሮፕላን ማረፊያ ከተማ ላይ ለፖሊስ እንሰጥሃለን፡፡ ፖሊስ እዚያ ቦታ ላይ እንዲጠብቅህ በመገናኛ ሬዲዮ እንነግራለን፡፡ ካናዳ ውስጥ እስር ቤት ትወረወራለህ ጓደኞችህ ሊያድኑህ አይችሉም፡፡ ሰው በማገት፣ በባህር ላይ ውንብድናና በመሳሰሉት ወንጀሎች ትከሰሳለህ፡፡ እስር ቤት ውስጥ ትበሰብሳለህ›› አለው።

በመጨረሻ ሉተር መርበድበድ ጀመረ ‹‹ሁሉም ነገር በዕቅዱ መሰረት
እየተፈጸመ ነው›› ሲል የኤዲን ሀሳብ ተቃወመ ‹‹አሁን እቅዱን መለወጥ
አይቻልም፤ ጊዜ የለም፡፡››
👍17
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት 


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ካርለት ከዳንሱ ቦታ ራቅ ብላ ጀግናዋን በአይኖቿ
ስትፈልገው በጆሮዋ ስልምልም የሚያደርግ የሙዚቃ ቃና ሰማች።
እንግዳ ነው ያ ሙዚቃ ለጆሮዋ! ሳባት ሙዚቃው
ተጎተተችለት: ቃናው ጆሮዋን እየላሳት ወደ ውስጧ ዘለቀ የህሊናዋን ጓዳ! የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው። አሻት፤ ዳሰሳት…..እሷም
አንኳኳ የሆሊናዋን ጓዳ የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው አሻት፤ ዳሰሳት
ሁለመናዋን ነካካው
አንሸራተታት ደመቅ
ደመቅመቅ... የሚለው ዜማ ፍል ውኃ ውስጥ እንደገባች ሁሉ ቁልቁል እየፈሰሰ ሰውነቷን አጋላት ደስ አላት ሰውነቷ ሲግል‥. ጡቶችዋ ግን ተቆጥተው ቆሙ፤ ዳሌዋ አኩሩፎ አበጠ ፤ ጭኗ አዝኖ ለሰለሰ… ሙዚቃና ልብ ወለድ ጽሑፍ ካለ እሳት ሰውነቷን ሲያጋግሉት ደስ ይላታል... የረሳችው ስሜት
ፈረሰኛው አረፋ እንደሚያስደፍቀው ወራጅ ወንዝ ሞተሯን አሽከረከረው፤ አቃሰተች ያኔም ስርቅርቁ ዜማ በጆሮዋ መግባቱን
አላቆመም:

እየቀረበች ስትሄድ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ወይሳውን እየነፋ ጥዑም ዜማ የሚያወጣውን ጀግና አየችው። የሙዚቃው
ቅላፄ እንደ “ቤቶሆቨን ሞዛርት ሲንፎኒ" ቃናው እየቆዬ ጣማት።እሰይ እሱ ነው ብላ አጉተመተመች..

ከዚያ ዱካዋን አጥፍታ በሙዚቃው ስልት እርምጃዋን አስተካክላ ተጠጋችው፡
ባለወይሳው አይኖቹ ከጨረቃና ከዋክብቱ ጋር ይጫወታሉ ቅላፄው
ወዲያና ወዲህ ይመላለሳል። ሙዚቃው እንኳን ሌላውን ራሱንም
መስጦታል። እውነተኛ የኪነ ጥበብ ሥራ ውጤት ስቃይና ደስታዋ፤ሐዘንና ትካዜዋ. እፍታውን ቀማሹ ጣዕሙን አስተካካዩና ፈጣሪው
ያኔው ነውና ወይሳው ደልቲን መስጦታል! ወጥሮታል...

ካርለት ደልቲን በሚጫወተው የሙዚቃ ቃና ተመስጦ በማየቷ ይበልጥ ወደደችው፡ ደልቲ
ለስሜቱ ታማኝ ነው አይቀጥፍም አያስመስልም...
ስርቅርቁ የሙዚቃ ቃና
የሚንቆረቆረው ለህሊናው እርካታ ነው::

ካርለትን የሙዚቃው ስልት አቅም አሳነሳት: ሁለመናዋ
እንቅስቃሴ ፍጥነቱን ስለጨመረ ደካከመች: ስሜቷን አፋጭቶ
ሃይሏን መልሶ ለመሳል አጋዥ ያስፈልጋታል
ባለወይሳው ያን ሰው አጥታው ከርማለች! አሁን ግን አጠገቧ ነው።

እጆችዋ ትከሻው ላይ አረፉ። ባለወይሳው ስርቅርቅ ዜማውን አቁሞ ቀና ብሎ አያት። ቆዳዋ ተገልቧል፣ ከርቀት ጠቆር
ብለ የታየው አካሏ ቁልቁል ወደሱ ሲመጣ እየጎላ ታየው። የራቀው
ሽለቆ ቀረበው።

ንጥት ያለው ገላዋ  በተለይም ጭኗን ትክ ብሎ እያዬ፡ “ካርለትት አላትና አይኖቹ ሳቁ። ሃይል ያጣችው ካርለት
የተሸበሸበ ርጥብ ከንፈሯን ለጠጥ አርጋ ደካማ ፈግታዋን አሳየችው።

ባለወይሳው አስተውሎ አያት ውስጧንም አየው
የተቀጣጠለውን ስሜቷን ነካው፡

ጭኖቹ ላይ ያለውን ወይሳ አንስቶ ለጨረቃ ሰጣት!
ጨረቃም ወይሳውን ተቀብላ እየነፋች ጥዑም ዜማዋን ማንቆርቆር ጀመረች። በጨረቃ የሙዚቃ ቃና ደልቲ ቀኝ እጁ እየተንከላወሰ ወደ
ነጩ ጭኗ ገባ። ነዘራት
በሽተኛዋን! “በሽታውን የደበቀ..." እንዲሉ እሷም ሃኪሟን ረዳችው የሚያቃጥላትን የሚቆረጥማትን እጁን
በእጅዋ ይዛ አሳየችው።
ጆሮ ግንዱን ፀጉሩን
ማጅራቱን...እየደባበሰች የእርዳኝ ጥሪዋን አሰማችው። ሀኪሟ በስሜቷ እሱም ተሽፈነ። ለጋራ በሽታቸው ግን የሚበጀውን ያውቃል። ስለዚህ ማገገሚያ ቀንዱን አቁሞ ይዞ ከተቀመጠበት ተነሳ።

ሙዚቃው ይስረቀረቃል! ዳንሱ ጦፏል... ጨረቃ
ታዜማለች ! ቅጠሉ እስክስታ ይወርዳል! ነፋሱ አታሞውን
ይደልቃል... ጥቁርና ነጭ ቀለሙ ማራኪ ዜብራም ያናፋል...

ኮንችት ጭፈራውን በጉጉት እያየች እንደቆየች ስለ ነገው
ጉዟቸው ካርለትን ለመጠየቅ ፈልጋ አጣቻት የኩችሩ መንደር ኗሪ
ጥበቃውን አላቆመም። ነጩ እባብና ሎካዬ ግን አልመጡም። ኮንችት
በየዋህነታቸው ብታዝንም ማድረግ የምትችለው ባለመኖሩ በዝምታ
ሁኔታውን ስትከታተል ሰነበተች። የመቆያ ፈቃዷ  እያለቀ ነው:: ስፔን ስትመለስ ብዙ ልትሰራ አስባለች በተለይ ስለ ኢትዮጵያ  ስለ ኩጉዩ፡ ከመሄዷ በፊት ግን ሐመርን ኤርቦሬን ከካርለት ጋር በሷ
መኪና ለማየት ተስማምታለች ጉዞዋን በተመለከተ ግን ከካርለት
ጋር መነጋገር ያለባት ቁም ነገር ነበር።

ኮንቺት ካርለትን ስታጣት ደልቲን በጨረቀዋ ብርሃን  ፈለገችው የለም:

ካርለት የሄደችው እሱ ዘንድ ይሆን?' አብረው ሆነው
ለማየት ጓጓች: ፍቅር ሲለዋወጡ እንዴት ይሆን?' ለማስብ ሞከረች:: መልሳ ደግሞ ሃጢያት እንደሰራች ሁሉ አስበችው አፈረች። ሆኖም ግን አልቻለችም ጉጉቷ ጨመረ።

በዚህ መካከል ድክምክም ያለውን የወይሳውን ድምፅ
ኮንችት ከርቀት ሰማችው። በድፍረት ሄደች  ወደ ጫካው! ድንገት ግን ክው ኦለች ! ባለበት የሚሰግር
ዜብራ አየች ፈራችው
ዜብራውን ይጋልባል ... በስሜት ተውጣ አይኖችዋን ጨፈነች:
"...የፍቅር እንጥሌን ሌሎች ተንጠራርተው ሲያጡት የነካው እሱ ብቻ ነው" ኮንችትን የነገረቻት ትዝ አላት።

“ዋው! ጎመጀች በዜብራው
ግልቢያውን አሰጋገሩን
አደነቀችው። ወደደችው ያን ስሜት ሰላቢ ጥዑም ዜማ... ፈውስ ሰጭ ዳንኪራ… ንፁህ የጫካ ፍቅር... ማራኪ ተፈጥሮ ተጋግዘው እንግዳዋን መልሀቋን አስጥለው በጉጉት ገተሯት!  ተጣራች በሲቃ ሶራ ግን አልሰማትም! ኤጭ! ብላ ከንፈሯን ጣለች። ጎደሎነት
ተሰማት ያማራትን የዜብራ ግልቢያ ግን የሚያቀምሳት አጣች.የጎመጀችለትን ያጣችው ኮንችት አዘነች። ...ዛፉ ቅጠሉም አዘነላት ላልተጠራችው ተመልካች!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

“እ. እ..." አቃሰቱ እምቡዋ እ. እ" ሳግ ተናነቃቸው
ህፃናት ወጣቶች አዛውንቶች ኦሞ ወንዝ ዳር ጫካ ተሰባስበው እንግዶች በእንጨቷ ታንኳ ኦሞን ሲያቋርጡ አያቸው።

ኮንችት እጅዋን አውለበለበችላቸው “ቻው... ባባይ... አለቻቸው። ዝም አሉ ኩዩጉዎች የነሱ የጥልቅ ፍቅር መግለጫቸው ዝምታ ነው። ሳግ ያበት “እ... እ..." እሚያሰኝ ከጥጃዋ በሃይል እንደተነጠለች ላም የሚያንሰፈስፍ ዝምታ! “እ. እ. እምቡዋ.. እያሰኘ የማይፈስ እንባ የሚያስነባ, የማይገልፁት ግን የሚታይ
የሚነካ... የመለየት ጭንቀት የሚታይበት ስሜት..

“እወዳችኋለሁ! ከናንተ በመለየቴ አዝናለሁ. ምንጊዜም አልረሳችሁም..." ኮንችት በስፓኒሽ ለመግለፅ ለፈለፈች¦ ምላሽ ግን
አልነበረም። “ፀጥታ ብቻ! ለኩዩጉዎች የመለየትን መጥፎነት የሚገልፅ ቋንቋ የላቸውም ካለ ዝምታ በቀር።

ኮንችት አነባች::
የካርለትን ትከሻ ተደግፋ አነባች አለቀለች  ሌሎች ግን ዝም ረጭ ብለዋል  እንደ ሌሎች ወንዞች
የማይጮኸው የማይደነፋው.
የኩዩጉዎች ህይወት የመልክ ማያ መስታዋታቸው የሆነው የኦሞ ወንዝም በዝምታ ድባብ እንደ ተዋጠ
ነው: ወፎች ግን ይበራሉ ያዜማሉ! እዕዋት ያሽበሽባሉ...

“እሷ ሄደች በሉ
ሉካዬንና የሰላም አድባራችን
የነበረውን ነጩን እባብ እንጠብቅ ! ተከፍተን ታዩን መምጣቱን እንዳይተዉት እንዝፈን እንጫወት.."
ሽማግሌዎች ለኩችሩ መንደር ህዝባችው ተናገሩ ኮንችት ካርለት ከሎ ሶራ… ኦሞን ከተሻገሩ በኋላ ዞር ብለው አዩ: ኩዩጉዎች የሉም!.ሲደልቁ ግን ይሰማል ለዚህች ተለዋዋጭ ዓለም ለረጅም ጊዜ አልቅሶና አዝኖስ መኖር እንዴት ይቻላል!
👍263👎1🥰1😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


"እግዜር ይስጥህ እንኳን እቤትህ ቁጭ ብለህ ጠብቀህ ልዩ ጥዬሽ ገዳም ልገባ ነው አላልከኝ...ድፍረት ኖሮህ አይን አይኖቼን እያየህ እንደዛ ብትለኝ …የሆነ ቢላዎ ፈልጌ ልብህ ላይ ሽጪ እዚሁ ነበር የማስቀርህ...›ስትል ዛተች..ዛቻዋ ከልቧ ነበር.አድራሻው የማይታወቅ ገዳም ገብቶ ለዘላለም ከምታጣው እዚሁ በገዛ እጇ ገድላው አልቅሳ ከቀበርረችው በኃላ ምርጥ በተባለ እምነ በረድ ሀውልት አሰርታለት በየቀኑ መቃብሩ ጋር እየሄደች ሰታወራው መዋል  ይሻላት ነበር፤

አእምሮውን ሳት እንዳደረገው ትኩስ እብድ በቤቱ ወዲህ ወዲያ በመዟዟር ነበር ቀበጣጥረው

ፓስታውን በእጇ ይዛ እጆቾን ከደቡብ ወደሰሜን እያወናጨፈች አንዴ መኝታ ቤት ደግሞም ሳሎን እየተመላለስች ነው‹‹....አረ እያበድኩ ነው መሰለኝ...››አለችና የሳሎኑን በራፍ በርገዳ ወጣች…

...ሮጣ አሮጌቷ ቤት በረንዳ ላይ እራሷን አገኘችው ።ለማንኳኳት እንኳን ትእግስቱ አልነበራም፡፡ በራፍን በርግዳ ገባች፡፡ አሮጊቷ ተቀምጠውበት ከነበረው ግዙፍ ሶፋ  ቀልጠፍ ብለው ተነስተው ቆሙ..ልክ የሆነ ወንጀል ሰርተው በተደበቁት ድንገት ፓሊስ ቤታቸውን ከፍቶ ፊት ለፊታቸው እንደቆመ ነው ሁኔታቸው..

"ቃልዬ የት ነው?እንዴት እንዲህ ይሰራኛል?እርሶ እንደማፈቅረው አያውቁም?"
ቀስ ብለው ካሉበት ተንቀሳቅሰው ቀረቧት ፤ክንዷን ያዙና ወደራሳቸው በመጎተት እቅፋቸው ውስጥ አስገቧት። የምትፈልገው ይሄንን ነበር..መንሰቅሰቅ ጀመረች..እምባዋ ከጀርባቸው ላይ እያረፈ ወደታች ሲንኳለል ይታያታል…ቢያንስ ለ10 ደቂቃ በቆሙበት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቆዩ ።ከዛ አሮጊቷ ቀድሞ ደከማቸው.. እየጎተቱ ወስደው ሶፋ ላይ አስቀመጧትና  ከጎኗ ተቀመጡ።


‹‹እማማ ልጆት አይደለ እንዴት ዝም ይሉታል?››

"ልጄ ወደእግዚያብሄር ቤት ልሄድ ነው ሲለኝ እንዴት ብዬ አትሂድ አይሆንም እለዎለሁ?"

"እኔስ ፍቅር አሲይዞኝ እንዴት ይሄዳል?  ...እሺ አሁን ምንድነው የማደርገው ?ዛሬ እኮ አይኔን በጨው ታጦቤ ልነግረው ነበር  ..እጮኛዬ እንዲሆነኝ ቀለበት ላስርለት ነበር እኮ... በመዳፏ ጨምድዳ የያዘቻቸውን ሁለት ቀለበቶች ወደ ፊትለፊት ዘርግታ እርስ በርስ በማቅጨልጨል አሳየቻቸው

"ልጄ አልሆነማ ምን ይደረግ...?እሱ የእግዚያብሄር ሙሽራ ብሆን ይሻለኛል አለ?በውሳኔው ጣልቃ መግባት ከእግዜሩም መቀያየም ነው።"አሏት ልስልስ እና ድክም ባለ ድምፀ፡፡

‹‹አልገባዎትም ...በጣም እኳ ነው ያፈቀርኩት...እንሂድ ቢለኝ ምን አለበት..?ያለምንም ማቅማማት አብሬው ሄድ ነበርእኮ"

በእንባ የተዳረሰ ፊታቸውን በከፊል ፈገግ አድሮገው"አይ ልጄ ቢጨንቅሽ እኮ ነው... ገዳም   ፊልም ቤት አይደል አብረን እንግባ የሚልሽ።"

ትከሻዋ ላይ ጣል ያደረጉትን እጃቸውን መንጭቃ ወረወረችና ከተቀመጠችበት ተነሳች..."ይሄ እውነት አይደለም..ቃል አሁን መጥቶ እቤት ይጠብቀኛል ..አዎ እየጠበቀኝ ነው...›በማት ወደውጭ መራመድ ጀመረች....

‹‹አይ ልጄ እግዚያብሄር ይሁንሽ ከማለት ውጭ ምን አረጋለሁ? "አሉ አልመለሰችላቸውም.. ተንደርድራ ቃል ቤት ደረስች …ሙሉ በሙሉ ተበርግዶ እንደተከፈተ ነበር።

‹‹አዎ ቃል ተመልሶ መጥቶል..ቃልዬ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ እየጠበቀኝ ነው።አዎ እኔሞ አብሬው ከጎኑ እተኛለሁ...እቅፍ አድርጌው ከንፈሩን ስማለሁ ...እና የፈለገውን ነገር ቢጠይቀኝ በደስታ እሺ እለዋለሁ ...እናም ደግሞ ይሄንን ቀለበት ጣቱ ላይ አጠልቅለትና የዘላለም ባሌ እንዲሆን እጠይቀዋለሁ..እርግጠኛ ነኝ እሱም እሺ ብሎ ሌለኛውን ቀለበት ጣቴ ላይ ያጠልቅልኛል።›› ...ይሄን ሁሉ እየለፈለፈች የሳሎኑ በራፍ ጋር ቆማ የሚብረከረከውን ጉልበቷን ባለመተማመን ጉበኑን ጨምድዳ ይዛ ወደ ውስጥ ባዶውንና ኦናውን ሳሎን አያየች ነው...መቀባጠሯን ሳታቋርጥ ወደ ውሰጥ ገባችሁ ልብን በሚቆራርጥ ፍራቻና አጥንትን በሚከታትፍ ሰቃይ የመኝታ ቤቱን በራፍ ገፋ አደርጋ በመክፈት አይኖቾን ወደውስጥ ላከች  ..ሁሉ ነገር ጥላው እንደወጣችው ነው ...ቃል የለም...ወደ ሳሎን ተመለሰች...ቃል ሰርቶላት የደረደራቸው ምግቦች አጠገብ ተቀመጠች።እጆን ወደምግብ ዘረጋች...ልክ ምግብ ለሳምንት በልቶ እንደማያውቅ ሰው (እርግጥ ቃልን ለማግኘት ስትቆነጃጅ ጊዜ ስላላገኘች ከነጋ ምግብ አልበላችም።)እየተስገበገበች መብላት ጀመረች።ሲበቃት ደረቷ ጠቅላላ በወጥ አጨመላልቃዋለችሁ ...የሀገር ባህል ቀሚስ ላይ ወጥ  ነክትቶ... ይባስ ብላ በወጥ የተጨማለቀ አጇን ጠረገችበት 27 ሺ ብር የወጣበት ልብስ ግማሽ ቀን እንኳን ሳይለበስ ድራሹ ጠፋ...‹‹የት አባቱ ቃልዬም ጠፋቶል እንኳን ልብስ ›አለችና የውስኪ ጠርሙሱንና አንድ ብርጭቆ ይዛ መሬት ያዘች።እዛው ሳሎን የቀኝ ግድግዳውን  ተደግፋ በላይ በላይ እየቀዳች መጋት ቀጠለች...ሩብ ያህሉን እንዳጋመሰች ጊፍቲ ትዝ አለቻት።ተንበርክካ በእንፉቅቅ እየሄደች ስልኳን ካስቀመተችበት አነሳችና ከፈተችው …በርከት ያሉ የተደወሉ ስልኮችና ሚሴጆች አሉ...ምን ያህል እንደደነዘዘቸ ማስረጃው   ይሄ ሁሉ ተደውሎ ስልኩ ሲንጫረር አለመስማቷ ነው...ከሙዚቃው ጋር ደርባ ስትሰማ የቆየችው  ሙዚቃ መስሏት ይሆናል..አሁንም ቢሆን  ማን እንደደወለላት ለማየት  ደንታ አልነበራም።ስልኳን ፈለገችና ደወለችላት… አነሳችው፡፡

"ሄሎ ልዩ "
‹‹አቤት››
‹‹ እቤተ እንድትመጪ እፈልጋለሁ›

‹‹የት ቤት  ነው የምመጣው..?ምን ሆነሻል?››
‹‹ቃል እቤት ነይ..…አሁኑኑ››
‹ልዩ ምን ሆነሻል ቃል ሰላም አይደለም?››
‹‹አለም ተገለባብጧል ..የገሀነም በሮች ተከፍተዋል….ምትመጪ እንደሆነ ነይ››ጆሮዋ ላይ ጠረቀመችባ፡፡ሰከንድ  ሳትቆይ ጊፍቲ መልሳ ደወለችላት.. ስልኳን ሙሉ በሙሉ አጠፋችው፡፡ ውስኪዬን እየተጋተች ሀሳቦን ወደመቃዠቱ ገባች …..

ገዳም ገባ አሉኝ -ደብረሊባኖስ
ነፍስ እየገደሉ- ይማራል ወይ ነፍስ?
ነፍስ እየገደሉ -ከተማረ ነፍስ
እኔም ያው ሞትኩልህ....አንተም ተቀደስ።

የትና መቼ  እንደሰማችው የማታውቀው ዘፈን ግጠም ከነዜማው በአእምሮዋ እያንቃጨለ አስቸገራት፡፡

የሠው ልጅ 70 ትሪሊዬን ከሚሆኑ ህውሶች ተዋቅሮ የተገነባ ፍጡር ነው ።በአሁኑ ጊዜ የአለም ህዝብ ቁጥር 7ቢሊዬን ገደማ ነው። .ይሄ ሁሉ ህዝብ አንድ ላይ ተጨፍልቆ ከአጥናፍ አለም አንፃር ከህዋስ ያለፈ ቦታ የለውም።ግን ደግሞ ታአምር የሚያሰኘው አንድ ነጠላ ሰው አጥናፍ አለምን የሚያስስ ሰፊና ጥልቅ የሆነ  ከመጠኑ ቢሊዬን ጊዜ በላይ የሚገዝፍ  በአዕምሮው ማሽንነት የሚፈጠረ ተስፍፊና ተስፈንጣሪ ምናብ ባለቤት ነው።ሰው...ገራሚ ፍጡር ነው።ለዚህም ነው መሠለኝ ሩሚ "አፅናፍ አለም በሙሉ በውስጥህ ስላለ ብቸኝነት ፈፅሞ አይሰማህ "ያለው።ከዝንት አለም ውስጥ ተመዘን ወጥተን ወደህይወት ለመምጣት በእናትህ ቅድስ ማህፀን ውስጥ ገብተን ተብላልተንና በቅርፅና በመጠን ተስተካክለን መውጣት የግድ ይላል።ይሄ ብቸኛው መንገድ ነው።እንደ ሙሀመድ ነብይ..እንደ እየሱስ የእግዚያብሄር ልጅ ፤እንደ ቡድሀ ታላቅ መንፈሳዊ መገለጥ ላይ የደረስንና  የበራልን ብንሆንም እንኳን ሌላ መንገድ የለም። ሌላው ደግም በዚህ ምድር ቆይታ ላይ ሳለን አነዳንዶቻችን በእግዜያብሄር መንግስት እናምናለን?በዛም አሻግረን ወደ ገነትስ መግባት እንሻለን?ከዚህ በሚቃረን መልኩ ግን ከሞት መዳፍ ለማምለጥ ሰንጥርና ስንለፋ ይታያል?ሞት ማለት እኮ በሚመጣው አለም ወደሚጠብቀህ የዘላለም መኖሪያ ሾልከህ ምትሄድበት ብቸኛው በራፍ
👍8010👏4🤔2🥰1
#ተአምረተ_ኬድሮነ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹እኮ የምታደርጉትን ነገር አቁሙ ነው እያልንሽ ያለነው  ..በግልጽ እንንገርሽ  መሰለኝ….እርሱ መዳን አይችልም ማለት መዳን የለበትም …..እሱ ከዳነ  እኛ እንጠፋለን ማለት-ነው….ስለዚህ  እረዳሽንም አረዳሽንም እሱን ለመግደል የምናደርገው ጥረት አናቆምም….እኛ በራሳችን ማድረግ  ዳግመኛ  መሞከር ያልፈለግነው  የፖሊሶች አይን እየተከታተለን ስለሆነ ነው፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ አሁን የተመረዘበትን መድሀኒት የሰጣችሁት እናንተ ናችሁ….?››

‹‹እሱን ማወቅ ምን ይጠቅምሻል….?›.›

‹‹አይ እሱማ ምን ይጠቅመኛል..እንዲሁ ተገርሜ እንጂ››

‹‹ምንም የሚገርም ነገር የለም..አሁን ባቀረብንልሽ ሀሳብ
ትስማሚያለሽ ወይስ አትስማሚ..

….?››ይጠይቃታል ሰሎሞን ተብዬው….

ወዲያው  አዕምሮዋን አሰርታና የነገሮችን አካሄድ በፍጥነት በመተንበይ ‹‹አረ  እኔ ምን አገባኝ… እናንተ ለራሳችሁ ሰው ያላሰበችሁ እኔ ምን አስጨነቀኝ..እስማማለሁ…››ብላ ትመልሳለች ሰሚራ፡፡

እነሱም ካሰቡት በጣም በፍጥነት  ስለተስማማችላቸው ተደሰቱ..

‹‹አሪፋ…በጣም ጥሩ ውሳኔ ነው››ሰላም፡፡ 

ሰሎሞን  ‹‹እንግዲህ ስንት ቀን እንጠብቅሽ….?››

ሰሚራ ‹‹አንድ ሶስት ቀን እፈልጋለሁ››

‹‹ሶስት ቀን አይበዛም››

ኮስተር ብላ ‹‹ሰው ለመግደል እኮ ነው እየተስማማን ያለነው ..ሰው ለመግደል ሶስት ቀን እንዴት ሆኖ ነው የሚበዛው….?››

ሰሎሞንም በአሪፍ መስመር  እየሄደ ያለው ጠቃሚ ስምምነት ላለመበረዝ  ለስለስ ብሎ‹‹ያው ሞት አፍፍ ላይ ያለ ሰው ለመግዳል ብዙም አይከብድም  ብዬ ነዋ…በተለይ ላንቺ››

‹‹ላንቺ ስትል …….?ስታየኝ ገዳይ እመስላለሁ….?›› መለሰች ሰሚራ ኮስተር ብላ ፡፡

‹‹አይ አረ በፍጽም እንደዛ ማለቴ ሳይሆን የህክምና ዕወቀቱ ስላለሽ..የትኛው መድሀኒት ሰውዬውን በቀላሉ ሊገድለው ይችላል የሚለውን በደንብ ስለምታውቂ ብዬ ነው፡፡››

‹‹እንዳልከው መግደሉ ቀላል ነው..ግን ግድያውን ማንም  ሊደርስበት የማይችል እና  ፖሊስም በምርማራም ሊያረጋግጠው የማይችል መሆን አለበት››

‹‹አየሽ እኔ ቀልቤን በጣም ነው የማምነው…ገና እንዳየውሽ ለዚህ ስራ እንደምትረጂን እርግጠኛ ሆኜ ነበር..እሷ ግን አይሆንም ብላ በጣም ስትከራከረኝ  ነበር የሰነበተችው….እንድረታት አደረግሸኝ …ጀግና ሴት ነሽ..ስራውን በጥንቃቄ እና በፍጥነት ስሪልን እንጂ 100 ሺ ብር ቦነስ አለሽ››ሰሎሞን በፈገግታ ተሞልቶ   አሞገሳት፡፡

‹‹ችግር የለም..ባይሆን እድር ከሌላችሁ እድር ግቡ….››
‹‹ለእሱ አታስቢ›› ብለው  በደስታ ተሰናብተዋት በፈገግታ እደታጀቡ ይሄዳሉ፡፡

ሰሚራ እነሱ እደወጡ ነበር ምን ማድረግ እዳለባት ማሰብ የጀመረችው‹‹…ሰው እዚህ ድረስ መጨካከን የጀመረው መቼ ነው…….?›› ለዛውም በቤተሰብ ደረጃ…እራሷን በድንጋጤ የጠየቀችው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር… ‹‹…ምን ቢያደርጋቸው ነው የራሳቸውን ሰው እንዲህ ለማስገደል የሚጥሩት..….?››ሰው ሰውን  ከሞት ለማትረፍ‹‹…..የሰውን ህይወት ለማስተካከል ይለፋል ገንዘብን ይከሰክሳል እንጂ እንደነዚህ  የራስ ሰውን ለመግደል ምን አነሳሳቸው...….?

ይቀጥላል
👍9912👏2👎1🔥1😁1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ትንግርት ያታሰረችበት ክፍል ሌሎች አራት ሴቶቸ አብረዋት ታስረዋል፡፡አንድ የ18 ዓመት ወጣት ...ሁለቱ ከ25-30 የሚገመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ከሁለቱ አንደኛዋ ቀጫጫ ቢጤ ስትሆን ስትታይ የቢሮ ሰራተኛ ነገር ትመስላለች.. ሌላኛዋ ግን ደልደል ያለች የተንጨፈረረ ፀጉር ያላት ወንዳወንድ ነገር ነች …አራተኛዋ 4ዐ ዓመት የሚጠጋት ገዘፍ ያለች ሴትዬ ነች፡፡ከእሷና ከልጅ እግሯ ወጣት በስተቀር ሌሎቹ እስር ሲታሰሩ ዛሬ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ከሁኔታቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡

‹‹አቦ አትቆዝሙብን ...እስቲ ወሬ አምጡ ..እናውራ፡፡ ካለዛ የእስር ቤት ተባዬች ደማችንን ሲመጡን በዝምታ ምናዳምጣቸው ከሆነ ስቃዩ ከፍተኛ ነው ሚሆንብን..፡፡ወሬ ግን ማደንዘዣ ነው ..ቀልባችን ወደ ወሬው ከላክን እነሱ ደማችንን ብቻ ነው ሚመጡት፡፡ ካለዛ
ደማችንንም ቀልባቸንንም ምጥጥ ነው የሚያደርጉት፡፡›› ቀጫጫዋ ወጣት ተናገረች

‹‹ተስማምተናል..…እስቲ ከተማሪዋ እንጀምር ..ምን አጥፍተሸ ታሰርሽ?››

‹‹ምንም?›› አለች ፈራ ተባ እያለች፡፡

‹‹ባክሽ አትሽኮርመሚ.. ዝምብለውማ አምጥተው እዚህ አያጉሩሽም... የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነሽ አይደል?››ትልቋ ሴትዬ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ... ዋናው ግቢ ነው የምማረው..የሶስተኛ አመት ተማሪ ነኝ፡፡››

‹‹የየት ሀገር ልጅ ነሽ…?››

‹‹የደብረማርቆስ፡፡››

‹‹እሺ ምን ሰርተሸ ታሰርሽ?››

‹‹ፖሊሶቹ ጭፈራ ቤት ለሊት ይዘውኝ፡፡››

‹‹አቦ አትፎግሪ.…ፋራ አረግሺን እንዴ ?››አለቻት ወንዳወንዷ ወጣት፡፡

‹‹እሱማ ዕቃ ይዘውብኝ ነው ፡፡››

‹‹የምን ዕቃ?››

‹‹ሀሽሽ ሚሉትን ዕፅ….፡፡››

‹‹ሀሽሽ !!አይ የዘንድሮ ተማሪ ስትጦዢ ይዘውሽ ነዋ?››

‹‹ወላዲቷን እኔ ነክቼውም አላውቅ ..፡፡ጓደኞቼ ናቸው ቦርሳሽ ውስጥ አስቀምጪልን ፤ የስጦታ ዕቃ ነው አሉኝ፤እውነት መስሎኝ እሺ አልኳቸው፤ከዛ ስንዝናና ስንጠጣ ቆይተን ከሰከርን በኋላ ወደ ጓሮ ይዘውኝ ሄደው ቦርሳዬን ተቀብለው ከውስጡ ያስቀመጡትን ቆንጥረው ወስደው የተቀረውን እዛው በመመለስ የራሴኑ ቦርሳ ለእኔው ካስያዙኝ በኃላ እነሱ እየተቀባበሉ ሲያጬሱ በስካር መንፈስ ናውዤ ቢሆንም በድርጊታቸው ግራ ገብቶኝ ስገረምባቸው ድንገት ከየት እንደፈለቁ
ያላወቅናቸው ፖሊሶች መጥተው ከበቡን..ከዛም አፈሱንና ሲፈትሹን እነሱ ምንም አልተገኘባቸው እኔ ቦርሳ ውስጥ ግን ተገኘ‹‹ካመጣሽበት ጠቁሚ፡፡ ››ተብዬ ይሄው ታስሬያለሁ፡፡

‹‹እና ጓደኞችሽ ምን አሉ?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንጃላቸው...ምናቀው ነገር የለም መሰለኝ ያሉት..ለዛም መሰለኝ የለቀቋቸው፡፡››

‹‹ታዲያ ምን ይሻልሻል?››

‹‹እንጃልኝ…እቤተሰቦቼ ከሰሙ በቃ ማጣፊያዬ ነው የሚያጥርብኝ... አባቴ ቀጥታ ይገድለኛል..፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ ፖሊሶቹ በዛ ሰዓት እንዴት ሊገኙ ቻሉ?›› ትንግርት ነች ግልፅ ስላልሆነላት የጠየቀችው፡፡

‹‹እሱማ ከመካከላችን ሜሪ የሚሏት የዱከም ልጅ በጣም የሚወዳትን ተማሪ ፍቅረኛዋን ችላ ብላ ትልቅ ሀብታም ሰውዬ ጋር ነበር ስትጨፍር ያመሸችው.. ልጁ መጥቶ አብራው ወደ ካምፓስ እንድትመለስ ሲለምናት ነበር..እሷ ግን አልሰማህም ነፍስያዬን ማስደሰት እፈልጋለሁ አለችው፤እያለቀሰና እየፎከረ ነበር ጥሏት የሄደው.....እሱ ይመስለኛል ለፖሊሶች የጠቆመው፡፡››

‹‹እናንተ ፖሊስ እጅ ስትወድቁ ሰውዬው አብሮችሁ ነበር?››

‹‹ነበር ግን ፖሊሶቹ ምንም አላሉትም አልፈተሸትምም..የሚያውት መሰለኝ… ሳስበው ሳስበው ዕፁን እራሱ ለእነሚሪ ያመጣላቸው እሱ ይመስለኛል፡››

‹‹በይ ነገ ይሄንን ሁሉ ለፖሊሶቹ በዝርዝር ንገሪያቸው..ሀሽሽ አለመጠቀምሽንም በምርመራ ማረጋገጥ የሚችሉ ይመስለኛል፡፡››
‹‹እስቲ እግዜር ቢረዳኝ እሞክራለሁ፡፡››ብላ መነፍረቅ ጀመረች፡ሁሉም አባበሏት..ስትረጋጋ ቀጣዩን ባለታሪክ ለማዳመጥ ተዘጋጁ፡፡ቀጣዪ ባለተራ በዕድሜ ከሁሉም አንጋፋ የሆነችው ሴትዬ ነበረች‹‹እሺ ያንቺስ ታሪክ?›› ቀጫጫዋ መጠየቅ ጀመረች፡፡

‹‹የእኔ እንኳን ከበድ ይላል..ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ተፈርዶብኝ ወደ ወህኒ መውረዴ አይቀርም፡፡››

‹‹እንዴ !!!እራስሽ ወንጀለኛ እራስሽ ዳኛ ሆነሽ አረፍሺው ?ለማንኛውም እስኪ እንስማው?››

‹‹የባሌን እንትን የማስወገድ ሙከራ አድርጌ ነው፡፡››

‹‹እንትን ምንድነው?››ነገሩ ግራ ገብቷት ጣልቃ በመግባት ሳታስበው ጥያቄ የሰነዘረችው ትንግርት ነበረች፡፡

<< የሚመጠጠው ጀላቲ››አሾፈችባት ወንዳወንዷ፡፡

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ባክሽ ሽሮ መብያውን ማለቷ ነው?››ቀጫጫዋ እስረኛ አስረዳቻት፡፡

‹‹በስመአብ ...!!!የባልሽን?››ተማሪዋ ጠየቀች... ሰቅጥጧት፡፡

ትንግርትም...የሴትዬዋ ጭካኔ አንዘርዝሯት‹‹ምነው አንደኛውኑ ብትገይው?››አለቻት፡፡
‹‹ጠላትን ለመበቀል ግድያ የመጨረሻው ቀሺሙ ዘዴ ነው?››መለሰች፡፡

‹‹እንዴት?››ግራ ገብቷት፡፡

‹‹ገደልኩት ማለት እኮ ገላገልኩት ማለት ነው ፤ከሞት በኃላ ፀፀት የለ.... መከራ የለ….ምን ይቀርበታል፡፡ ስለፅድቅና ኩነኔው እንደሆነ ማን እርግጠኛ መሆን ይችላል፡፡እንደውም እኔ ነኝ መከራውን የምቀበለው..እሱን የሰላም ዕንቅልፉ ወደሚያገኝበት ስፍራ ሸኝቼ እራሴን

ለዕድሜ ልክ የእስር ስቃይ አሳልፌ ሰጣለሁ..?ምን በወጣኝ፡፡እኔም እሰቃያለሁ እሱም በቁሙ እየኖረ ይሰቃይ...>>
‹‹ሰማንሽ ...እስቲ ያረግሺውን በዝርዝር አስረጂን?››

‹‹ባሌ ቀለም ቀቢ ነበረ፡፡ ከዛሬ ሁለት አመት
በፊት አንድ ፎቅ ሲቀባ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ
መሰላል አንሸራቶት ይፈጠፈጥና የቀኝ እግሩ
ስብርብሩ ይወጣል ይታያችሁ.. እኔ እና ታናሽ
እህቴ በኪራይ ቤት እሱ በሚያመጣው ገቢ
ነበር የምንተዳደረው፡፡እሱ ስብርብሩ ወጥቶ
ቤት ሲቀር የሆነ ነገር ማድረግ የሚጠበቀው
ከእኔ ነው፡፡እራሳችንን መቀለብ ብቻ ሳይሆን
እሱንም አሳክሞ ማዳን የእኔ ኃላፊነት ስለነበር መጣር ጀመርኩ፤ብዙ ነገር ለመስራት ሞከርኩ… ሰው ቤት ፅዳት..ቀን ስራ
ያልሞከርኩት ነገር የለም ፡፡ግን ሁሉም ከልፋት
በስተቀር ለቤተሰቡ የሚበቃ ጠብ የሚል ገንዘብ ሊያስገኝልኝ አልቻለም፡፡ቀለባችንን ችዬ የቤት ኪራይ ከፍዬ ከዛ ተርፎኝ እሱን
ለማሳከም አቅም አነሰኝ…እግሩ ከህክምና እጦት የተነሳ የተነፋፋ ቆሰለ ..ትል ሁሉ ማፍራት ጀመረ፤ምን ላድርግ ?ተሳቀቅኩ፡፡ ሲቸግረኝ ሌላ ዘዴ ቀየስኩ፡፡››

‹‹ምን ዓይነት ዘዴ?››

‹‹የለሊት ስራ ... ፋብሪካ ውስጥ አገኘሁ ብዬ አስወራሁ?››

‹‹ሳታገኚ?››

‹‹ስራውንማ አግኝቼያሁ ...ግን ፋብሪካ ውስጥ አልነበረም፤ ሽርሙጥና ነበር ለመስራት የወሰንኩት፡፡››

ቀጫጫዋ በገረሜታ‹‹ባል እያለሽ?››አለቻት ፡፡

‹‹ባሌማ እኮ ….ዓይኔ እያየ የተሰባበረ እግሩ ከህክምና እጦት የተነሳ መትላት ጀመረ፤ምንበላው አጣን፣የቤት ኪራይ መክፈል አቃተን፣እህቴም ትምህርቷን ልታቋርጥ ጫፍ ደረሰች..እና ምን እንዳደርግ ትጠብቂያለሽ…?

አንዳንዴ ይህቺ አስቀያሚ ህይወት ሁሉንም በራፎች ትከረችምብሽና አዋራጅ እና አስቀያሚ የሆነውን ጭላንጭል የዕድል ቀዳዳ ብቻ ትተውልሻለች፡፡››
‹‹እሺ ቀጥይ ባክሽ፡፡››አለቻት ትንግርት ታሪኳ አጓጉቷት፡፡
👍609👏1😢1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ባለፋ ሶስት ወር ውስጥ ተሰምቷት የማያውቅ ደስ የሚልና የሚያፅናና ስሜት ተሰማት…..እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ግዙፉ መስታወት ፊት ቆማ የለበስችውን ቢጃማ በቁሟ አወለቀችና እዛው ከእግሯ በታች ወለሉ  ላይ  ረገጠችው…መላ  እሷነቷን  በፅሞና  ተመለከተች…. ፀጉሯ በዛ ርዝመቱና ብዛቱ ጭብርር ብሎ ከመንግስት ተሰውሮ ዋሻ ውስጥ ለአመታት ተደብቆ የኖረ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ….አማላይ  የነበረው  የሠውነቷ ቅርፅ አሁንም እንዳለ ቢሆንም የሰውነቷ ክብደት ግን በተጋነነ ሁኔታ መቀነሱ ወደፊት ወጥተው በጉልህ የሚታዩት አጥንቶቾና  ወደ  ውስጥ  ጎድጉደው  ጭል ጭል የሚሉ አይኖቾ ምስክር ናቸው፡፡ከሁሉም በላይ ያስደነገጣት  ግን  የብልት ፀጉሯ ነው…ከስራዋ ባህሪ አንጻር ለአመታት በሶስት ቀን አንዴ ስትላጭ የኖረች ሴትዬ  ለወራት  ችላ  የተባለው  የብልቷ  ፀጉር  በአስፈሪ  ሁኔታ   አድጎና ተንጨፍርሮ እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ በመሀከል ስንጥቅ መኖሩን እራሱ በእጅ ዳብሰው ካልበረበሩት ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ አስደነገጣት….
….የቀኝ አጇን  ዘረጋችና  አንገቷን  ጠምዝዛ  ብብቷን  ተመለከተች  ..ተመሳሳይ ነው፡፡ በፀጉር ከመሸፈኑም በተጨማሪ ሽታ ከሩቁ ይገፋተራል፡፡ይሄ ሁኔታ ደግሞ ይበልጥ አስገረማት፡፡
‹‹ለምንድነው ግን በቁማችንም እያለን ጭምር ለጥቂት ቀናት ትኩረታችንን ከራሳችን ላይ ስናነሳ እንዲህ በፍጥነት የምንሸተው..?››ስትል ጠየቀች፡፡መልሱን ለመመለስ ግን ብዙም አላስቸገራትም፡፡  ምክንያቱም ከማሳጅ ስራዋ ጋ ተያይዞ ከወሰደቻቸው ኮርሶች አንደኛው የሰው ልጅ አመጋገብ ስርዓት በተመለከተ ነበር ፡፡ ከሺ አመታት በፊት የሞቱ ሰዎች መቃብር ተቆፍሮ ሲገኝና የጥርሳቸው ጤንነትና ጥንካሬ ሲፈተሸ አሁን ካለው የሰው ልጅ ጋር የማይነፃጸር እጅግ ንጹህና ጠንካራ  እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ምክንያቱም ደግሞ አመጋገባችን ሆኖ ነው የተገኘው፡፡አሁን አብዛኛው ምግቦች ከኬሚካል ጋ ንክኪ ያላቸው… ስኳርነት የበዛባቸውንና  ጤንነትን ሳይሆን ጥፍጥና መሰረት ያደረጉ ናቸው…ስለዚህ እነዚህ ገብተው ተፈጥአዊ ሰውነታችንን በክለዋል….በዛ ላይ ምንቀባቸው ቅባቶች የምንረጫቸው ሽቶዎች፤ የምንታጠብበት ሳሙና በጠቅላላ እንዲህ በቀናት ውስጥ በቁማቸንን እንድንሸት ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ለመረዳት ብዙ ምርምርም አያስፈልግም፡፡ ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና የቁም ሳጥኗን ኪስ ከፈተችና  የፀጉር  መላጫ ማሽኗንና መቀስ አውጥታ በመያዝ ወደ ሻወር ቤት ተመለሰች፡፡ምንም ማሰብ እና መጨነቅ አላስፈለጋትም፡፡ከፀጉሯ ጀመረች…..ከርዝመቱ ወጥራ ወደፊት እየያዘች…..ወገብ ላይ ትጎምደው ጀመር፡፡ ወለሉ በተንጨባረረ እና በተቆጣጠረ
ፀጉር ተሞላ፡፡ ባለከመከም ጎፈሬ ሆነች፡፡በመስታወቱ የተለየች አይነች እስከዛሬ እሷ ራሷ ማታውቃት አይነት ሳባን ተመለከተች፡፡መቀሷን አስቀመጠችና ማሽኗን አመቻቸችና ወደብልቶ ጎንስ ብላ እግሯን ፈርከክ በማድረግ ታጭደው ጀመረ…..ሁሉን ነገር ጨርሳ ሰውነቷን  ታጥባና  ፀድታ ከሻወር ለመውጣት ከ2 ሰዓት በላይ ነው የፈጀባት፡፡
ከዛ ወደመኝታዋ ተመልሳ የተወሰነ እረፍት አደረገች.. ከተኛበት  ብንን  አለችና ስልኳን አነሳች፡፡ እንዲህ አይነት ጥንካሬ እና ፍላጎት በደቂቃ ውስጥ ከየት እንዳመጣች አታወቅም፡፡ደወለች..ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ዶክተር››

‹‹ሳባ ለመሆኑ በህይወት አለሽ…?ምን ነካሽ…?ሌላ ሌላው ይቅር እሺ ህክምናሽን ግን እንዴት ታቋርጪያለሽ…ያልተመቸሽ ነገር ካለም እኮ ተነጋግረን ማስተካከል እንችል ነበር..››
‹‹ምን አልተመቻትም ብለህ አሰብክ…ያደረኩት ነገር አግባብ ነበር እንዴ?›ስትል መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ከህክምናሽ ጋር ምን አገናኘው..ምን አልባት በእኔ ህክምናውን መከታተል የሚከብድሽ ከሆነ እኮ በሀገሪቱ ያለሁት የስነ-ልቦና ሀኪም እኔ  ብቻ አይደለሁም
… ተነጋግረን ሁኔታዎችን መስመር ማስያዝ እንችል ነበር››

‹‹ኖኖ ዶክተር እንደዛ አስቤ አይደለም…እኔ እንደውም አንተ ካላከምከኝ ማንም ሊያክመኝ አይችልም››አለችው፡፡
የተናገረችው ትክክል ይሁን አይን እራሷም እርግጠኛ አይደለችም…እርግጥ ከእሱ ውጭ በሌላ ሀኪም መታከም አትፈልም….ደግሞም በእሱም ቢሆን መታከሙን የምትችል መስሎ አልተሰማትም፡፡ህመሟ አካላዊ ቢሆን ችግር የለውም፡፡ ጉበቷ ወይም ኩላሊቷ ቢሆን ወይም ማህፀኗን አሟት ልብሶቾን አወላልቃ እግሮቾን አንፈርክካ መላ ሚስጥሯን ለእሱ  ማሳየት  ቢሆን  ምንም  አይመስላት ነበር፡፡…..እሱ ፊት ስትቀርብ ከኤፍሬም  ጋር  በገዛ  ምርመራ  ክፍሉ  የሰራችው ነውር ነው ትዝ የሚለው የገዛ ወንድሙን ስታማግጥበት…ዝግንን አላት፡፡
‹‹እና ታዲያ ለምን እራስሽን  ሰወርሽ….?እንዴት  እዲህ  ይጠፋል…..?ደግሞ ለህክምና ፋይል ላይ ያስመዘገብሽ መረጃ በጠቅላላ የተሳሳተ ነው….አድራሻሽን ጭምር  ..አንድ ትክክል የሆነው ስልክ ቁጥርሽ ቢሆንም እሱንም ጠርቅመሽው ይሄው ስንት ወር፡፡››

ደስ አላት…ስለእሷ እንዲህ ሲጨነቅና ሲብሰለሰል መክረሙ ደብዝዞ እና ሊከስም ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረ ተስፋዋ በጥቂቱም ቢሆን ቢል ቢል እያለ  እንዲነቃቃ ተጨማሪ ነዳጅ ሆኖ ሲያነቃቃት ተሰማት፡፡
‹‹እና አሁን እንዴት ነሽ…?የት ነሽ..?ሀገር ውስጥ ነሽ?››

‹‹አዎ እዚሁ ነኝ፡፡››

‹‹እና እንዴት ነሽ?፡፡››

‹‹እኔ እንጃ ..ምን ላይ እንደሆንኩ አላውቅም…እንዴት እንደሆንኩ አላውቅም….. መኖሬን እራሱ አላውቅም….ለምን አሁን አንተ ጋ እንደደወልኩም አላውቅም….
››አለችው፡፡

ከንግግሯ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ካገኛት እጅጉኑ የከፋ እንደሆነ ወዲያው ተረዳ….ስለእሷ ሲያስብና   ሲጨነቅ   የከረመው   ግን ከዚህም የከፋ ነገር ላይ እራሷን ትጥላለች ብሎም ጭምር ስለሰጋ ነበር…እራሱን ያጠፋ ሰው ዜና በሶሻል ሚዲያም ሆነ በሜን እስትሪም ሚዲያ ሲሰማ ደንግጦ በንቃት ዜናውን እስከመጨረሻው ለማየት ሲጥር የነበረው እሷን አስቦ ነው፡፡አሁን  ግን በከፋ ሁኔታ ላይም ሆና ቢሆን በህይወት መኖሯ ብቻ አስደሰተው፡፡
‹‹አይዞሽ ይሄ በማንኛውም ሰው ላይ በሆነ ጊዜ ላይ የሚከሰት ነው..አንቺ ደግሞ ከዕድሜሽ በላይ ብዙ ነገር ያየሽና ብዙ ነገር ምታውቂ ጠንካራ ልጅ ነሽ...እኔም ደግሞ በፈለግሽኝ ጊዜና መንገድ ከጎንሽ ነኝ፡፡››
‹‹አንተ ከጎኔ መሆንህን በመስማቴ ተደስቼያለሁ…አመሰግናለሁ፡፡››

‹‹እና መች ብቅ ትያለሽ?›

‹‹እኔ እንጃ››አለችው የምትለው ግራ ገብቷት…

‹‹እኔ  እንጃ  ማለት  ምን  ማለት  ነው…ህክምናው  ቢቀር  አንኳን  ናፍቀሺኝል… ሆስፒታል መምጣት ካስጠላሽ የፈለግሺው ቦታ መገናኘት እንችላለን፡፡››
‹‹ካልክ ነገ ስንት ሰዓት ይመችሀል?››

‹‹እንቺ የሚመችሽን ሰዓት ነገሪኝ እኔ ፕሮግራሜን አሬንጅ ማድረግ እችላለሁ›› እሷን ከማግኘት የሚቀድምበት ምንም ጉዳይ የለውም፡፡
‹‹በቃ 10 ሰዓት እንገናኝ..››

ደስ አለው….‹‹እሺ የት እንገናኝ?›› ነገረችው
‹‹ችግር  የለም….እንገናኛለን…››

‹‹እሺ ዶ/ር ….አመሰግናለሁ››
👍697👏4🥰2