አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወዲያነሽ


#ክፍል__ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በሐይለመለኮት_መዋል


....እናቴ አዘኔታ በሚታየበት ፊት ወደ እኔ መለስ አለችና ሞኝነትህ፣ ሞኝነትህ ነው ልጄ! 'አይዞሽ ግድ የለሽም' ብለህ ይዘሃት ና፡፡ እኔ እናትህ አሳምሬ እቀበልልሃለሁ። አትፍሪ! አትፍሪ ነዪና እንታረቅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ እኔና አንቺ እናትና ልጅ ነን፣ ልጄ ልጄ ብላሻለች” ብለህ አሳምረህ ንገርልኝ በማለት ያን በውስጤ ሲገላበጥ የዋለ ሥጋትና የመንፈስ ሽብር ገደለችልኝ
እናቴ ጋሻዬነህን ፍለጋ መልከት መልከት ስትል እንቅልፉ ሊጥለው ሲያንጎላጅ
አየችውና «አፈር በበላሁት! ልጄን! ልጄን! ያቺ እናትህ እንኳን አላየች!» ብላ
ካነሣችው በኋላ እግሩን እያንዘላዘለች ወደ የውብነሽ መኝታ ቤት ይዛው ገባች::
የእናቴ እግር ወጣ እንዳለ የውብነሽ ድንገት ብድግ ብላ አለቀ! ጨብጠኝ
ወዳ አይምሰልህ የግዷን ነው» ብላ ደስታዋን ገለጸችልኝ።

«አዎ ከእንግዲህ ደግሞ አንድ አስቸጋሪና የለየለት ግብግብ ብቻ ይቀረኛል» ብዬ መለስኩላት

የወዲያነሽ ምነው ቆየህ? ና እንጂ ጌታነህ! ቁርጤን ልወቅ? የምትል
መሰለኝ፡፡ ሰዓቴን ብመለከት ዐሥራ ሁለት ሰዓት አልፏል። እናቴ ከተቀመጠች
በኋላ ጥያቄና መልስ ቀጠለ። ከመጠን በላይ ተዝናናሁ፡፡ መላ አካላቴ
ተንፈላሰሰ፡፡ የወዲያነሽን ሥቃይና መከራ ባጭር ባጭሩ አንዲትም ሳላስቀርና
ሳልዘነጋ እንደ ተረት ነጋሪ አሳምሬ ወጣሁላት። የእኔንም ልፋትና ውጣውረድ
ሁሉ ገለጽኩላት፡፡ ንግግሬን እንደ ጀመርኩ ፊቷ ትንሽ በትንሽ ጠወለገ፡፡ እንባዋ
እየተሽቀዳደመ ሲወርድ ማዘንና መፀፀቷ ገባኝ። የእናቴ ርኅራኄና ገራገርነት እንደ ኮረብታ ጎልቶ ታየኝ፡፡ በኀዘን ጠውልጎ በእንባ የራሰውን ጉንጯን በማየቴ
በጣም ረካሁ፡፡ በሕዝብ ኃይል ሥልጣን እንደ ያዘ መንግሥት ደስ አለኝ።
የወዲያነሽም ድል ስታደርግ ወለል ብሎ ታየኝ፡፡

«አሠቃይቻታለሁ በቁሟ ቀብሪያታለሁ» አለችና ልቅሶዋን ቀጠለች።
«ያለፈው አልፏል ከነገ ጀምሮ ታርቃችሁ ተፋቀሩ እንጂ እሷ በበኩሏ ሁለንም
ነገር ይቅር ብላ ትታዋለች በጣም እኮ ነው የምትወድሽ» ብዬ ትካዜዋን ለማቅለል ሞከርኩ፡፡ ሙሉ ፈገግታዋ ሳይመለስ ለመሄድ ተነሣሁ፡፡ «ጋሻዬን አምጪልኝ የውብነሽ!» አልኳት፡፡

«አንት ጨምላቃ ጨመለቅ! እኔ እጅ ገብቶ ነው የምትወስደው?ባይሆን እንኳ ዋንየዋ ከመጣች በኋላ የሆነው ይሆናል!» ብላ ቱግ አለች። ልቤ ጮቤ ረገጠች፡፡ ተደሰትኩ እንጂ አልከፋኝም፡፡ የወሬ ሠንጋ ጥለን ስናወራርድ ሁለት ሰዓት ተኩል አለፈ። የውብነሽን ለብቻዋ ጠርቼ «ነገ አራት ሰዓት እንድትመጪ» አልኳትና «ደኅና እደሩ» ብዩ ወጣሁ፡፡

የቤቴን አጥር ግቢ ከፍቼ ስገባ የወዲያነሽ ጋቢዋን ለብሳና የሰበሰቡን አግዳሚ ተደግፋ ስትጠብቀኝ ደረስኩ እንደ ወትሮዋ ነቃ መብላት ስላልተቀበለችኝ
አእምሮዋ በሐሳብ ጉልበቷ በመቆም እንደ ተዳከሙ ገባኝ። እጅዋን ያዝ አድርጌ ዐይን ዐይኗን እያየሁ አመሸው እንዴ የወዲያ ደስ ይበልሽ! ደስ ብሎኛል
የሄድኩበት ጉዳይ ተሳክቷል» አልኩና በምሽቱ አየር የቀዘቀዙ ጉንጮቿን ሳምኳቸው፡፡

«እንኳን ደኅና መጣህ? እንኳን ደስ ያለህ? ጋሻዬስ? ከእጅህ ላይ ሳጣው ጊዜ አፌ ተሳሰረ» አለችና በልከኛው የመብራት ውጋጋን ውስጥ ትክ ብላ ተመለከተችኝ፡፡ ተያይዘን ከገባን በኋላ እንዴት ብዬ ልግለጽልሽ? እናቴ በጣም ተደሰተች። ምነው የዛሬዋ ዕለት የሁለትና የሦስት ቀን ያህል በረዘመች ! ስለ አንቺና እኔም አንዳችም ሳላስቀርና ሳልደብቅ ነገርኳት። በጸጸት ተቃጥላ እንባ በእንባ ሆነች። ርኅራኄዋንና የእናትነት ልባዊ ፍቅሯን ለማግኘት ችያለሁ፡፡በመጨረሻ ግን ጋሻነህን ልውሰድ ብዬ ብጠይቅ አፈን አስያዘችኝ፡፡ «እሷን እዚህ ይዘህ መጥተህ ይቅርታ አድርጊልኝ ብዬ ሳንታረቅና እንደ እናትና ልጅ ሳንሳሳም፣ ልጅ የሚሉ ነገር አልሰጥም ብላ ማለች» ብዪ ጋሻዬነህ የቀረበትን ምክንያት አብራራሁላት፡፡

የወዲያነሽ እውነት ስላልመሰላት «መቼ ሥራ አጡና! እንኳን ጥራትና አምጣት ሊሉህ ይቅርና ይህንኑ ዐይኗን እንዳታሳየኝ ብለውህ ይሆናል፡፡ ያንተን ሥራ መች አጣኋትና! ታዝናለች፣ ይከፋታል ብለህ ነው:: አትጨነቅ ቢከፋኝስ ምን እንዳላመጣ ነው? አጀብ እቴ ! ያም ሆነ ይህ እንኳን ደስ ያለህ» ብላ አሻግራ ስትመለከት «አምጪ እጅሽን፣ የወዲያነሽ ሙች! » ብዩ ለእውነተኛነቴ ማረጋገጫ እንዲሆን እጅዋን ስቢ ጠፋሁት፡፡

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ራት አቀረበች። ሆዴ በቀኑ ምግብ ደስታና ፈንጠዝያ በመጎሰሩ ምንም አላሰኘኝም፡፡ የወዲያነሽ «በቃኝ! በቃኝ!» እስከምትል ማጉረስ በመቻሌ እንደገና ደግሞ አጋጣሚው አስደሰተኝ። ከራት በኋላ ከቀኑ ወሬ ውስጥ ቀነጫጭቤ አወራሁላት። በጥርጣሬና በሥጋት ታፍኖ የነበረው አእምሮዋ ገለጥለጥ ስሳለላት ጥርጣሬዋ ከላይዋ ላይ በንኖ ጠፋ፡፡

«እኔ በበኩሌ ቂም የሚሉ ነገር አልያዝኩም፡፡ ላንተ ስል ሁሉንም ነገር ትቼዋለሁ፡፡ የፈራሁትና የሠጋሁት አሻፈረኝ ይላሉ ብዬ ነው እንጂ፣ እሺ ካሉንማ ምን ቆርጦኝ። ጫማቸው ላይ ወድቄ ይቅርታ አድርጉለኝ ብላቸው ምን ነውር አለበትና ነው?» በማለት እቅጩን ነግራኝ ወደ መኝታ ቤት ገባች። መላ ሰውነቴ ጥርስ አውጥቶ ሣቀ፡፡ ተከትያት ገባሁ። ምንጊዜም ከዚያ ቀደም ወስዶኝ በማያውቅ ሁኔታ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ፡፡ እውነተኛ ፍቅርና የሕሊና ጸጥታ ምንኛ ሰላም ይሰጣሉ!
የወዲያነሽ ቀኝ እጅዋን በብርድ ልብስ ውስጥ አሾልካ ግንባሬን
እየዳበሰች «እንዴ? የዛሬውስ እንቅልፍ ለብቻው ነው፣ ለጤና ያድርግልህ» ብላ በማያስደነግጥ ሁኔታ ባትቀሰቅሰኝ ኖሮ ተኝቼ አረፍድ ነበር። ከአንገቴ ቀና
ብዬ «ረፍዷል እንዴ? ስንት ሰዓት ሆነ?» አልኳት፡፡ ሰዓቷን አየት አድርጋ «ሦስት ሰዓት ከሐያ አምስት» ብላኝ ሄደች።

በመስኮቱ በኩል የገባው የረፋዷ ፀሐይ ጮራ ክፍሉን አወግጎታል።
ተጣጥቤና ለባብሼ ለመቀመጥ ቸኮልኩ፡ ሠራተኛይቱ ያመጣችልኝ ሽግ ያል ውሃ ደህና አዝናናኝ፡፡ ጊዜው በመገሥገሡ ተደሰትኩ በእናቴ ፊት «የሚያስከብረኝን» ልብስ ለብሼ ስጨርስ አራት ሰዓት ተኩል አለፈ፡፡

የወዲያነሽ ከፊት ለፊቴ ቆም አለችና ምን ዓይነት ልብስ ልልበስ? እስኪ ንገረኝ?» ብላ ዐይኖቼን በዐይኖቿ አቆላመጠቻቸው ደረቷ ላይ ዠቅ
ያለውን ሐብልና መስቀል እየተመለከትኩ «መጨነቅና መጠበብ አያስፈልግም የአንቺ መጎናፀፊያና ግርማ ሞገስሽ የሰው ልጅነትሽ ብቻ ነው። የሐር ድርብና የወርቅ ቁርጥራጭ አይደለም፡፡ ይህን የአጣና ያአገኘ የመለያ ምልክት በግብግብ
እናስወግደዋለን። ደስ ያለሽን ልበሽ?» አልኳት። ባለ ወይን ጠጅ ጥለት ኩታና ቀሚስ ለብሳ፣ ተረከዘ
አጭር ጫማ ተጫምታ ጸጉሯን በቀላሉ ጎነጎነችው፡፡

ምንም እንኳ ቀደም ሲል በሕወይቷ ላይ በደረሰው ተደጋጋሚ ችግርና የሕሊና
ሥቃይ የተነሣ አካላቷ ሲፈካና ሲጠወልግ፣ ሲከሳና ሲኮስስ ቢኖርም፣ የወዲያነሽ በአሁኑ ጊዜ በምቹ ቦታ ላይ በቅላ በማለፊያ ዳስ ላይ እንደ ተንሰራፋች የወይን
ተክል ሐረግ ቀስ በቀስ አምሮባታል።

የችግርና የሠቀቀን ኑሮ ያሟሰሰው ለዛና ዛላዋ፣ ውበትና ደም ግባትዋ
እንደገና እንደ ሐምሌ ጎርፍ እየሞላ፣ እንደ መስከረም ወንዝ እየጠራ፣ እንደ ጥቅምት አዝመራ አሺቷል። ከአገርና ከሕዝብ መኻል በተለይ ተመርጣ የምትጠቀስ ልዩ ቆንጆ ባትሆንም የወዲያነሽ የምትኮክብ የውበት ጉልላት
ሆነች። ጠበብ ካለው ግንባሯ ግርጌ ከቅንድቦቿ ድባብ ሥር ያሉት ተንተግታጊ ውብ ዐይኖቿ ከሥጋ ቅምር ሳይሆን ከሚጨበጥ ንጥረ ብርሃን የተሠሩ መሰሉ፡፡
👍51
#የወዲያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...አስታውሳለሁ ግን እኮ ታዲያ...” ብዩ ሙሉ ሐሳቤን ሳልገልጽላት ዝም አልኩ።የዝምታዬ መነሾና ጥጥር ምክንያት ግን አዲሱ እኔ በመሆኑ እሷ ልታውቀው
አትችልም፡፡

«ና በል እንሒድ ቶሉ እንመለሳለን» አለችና ተነሣች። የእኔ ጉዳይ
በእርሷና በእናቴ መካከል ተመክሮበት ያለቀ በመሆኑ እንግዲህ አደራሽን እንደዚያቹ እንደ ምክራችን አድርገሽ ንገሪው፡፡ እኔና አንቺ እንደ ተባባልነው
ቢሆን ይሻላል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ እኔ ደኅና አድርጌ እነግረዋለሁ፤ አደራሽን አደራችሁን» ብላ እናቴ በዐይኗ ሸኘችኝ፡፡ «ሂዱ» የምትለን ወደ እኔ ቤት መሆኑን አወቅሁ፡፡ የወዲያነሽን ለመጠበቅ ቆምኩ። «ሂዱ እንጂ ምን ቀረህ?
እናቷ እኮ ነኝ! ሌላ እናት ያላት መሰለህ? አይዞህ! ለሌላ ሰው አልሰጥብህም፣ እሷም በጀ አትልም» ብላ ስቃ አሣቀችኝ፡፡ የወዲያነሽ እናቴን በዐይኗ እየጠበቀች 'የሂዱ' ምልክት በጣቷ አሳየችኝ። ምርቱን እንደከተተ ሰው ተደስቼ ወጣሁ፡፡ወደ እኔ ቤት የመሄዱን ነገር ሰርዘን መኪና ውስጥ ተቀመጥን።

«አባቴ ስለ አንተና ስለ የወዲያነሽ ምንም ነገር ፈጽሞ እንዳልሰማና እስከ ዛሬም እንዳላወቀ ታውቃለህ:: ምስጢሩን የቀበርነው ሁላችንም ስለ ፈራነው ነው»
በማለት ንግግሯን ጀመረች፡፡ ጠንቃቃነቴንና ለጉዳዩ ያለኝን ከፍተኛ ግምት በግልጽ ለማስረዳት «አንቺና እማማስ ብትሆኑ ካባረራችኋት በኋላ ስለ እርሷ ምን የምታውቁት ነገር ነበር? ምስጢሩ ያልተነዛው ከእርሷ ጋር በመባረሩና እስር ቤት
በመውረዱ ነበር» ብዩ ተራ ለቀቅሁ፡፡

«ነገሩን በብልሃትና በዘዴ ካላስኬድነው በስተቀር ከአባታችን ጋር ብዙ ንትርክና ጭቅጭቅ እንደሚነሳ የታወቀ ነው፡፡ እኛ ግን ስለ ነገሩ ፍንጭ አግኝቶ
እንዲጠራጠር በማድረግ ጉዳዩን ለመጀመር አስበናል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ አንተም እኛም ጥሩ ጥሩ ሽማግሌዎች መርጠን...» ብላ ሳትጨርስ «የብልሃቴ አቀነባባሪ እኔ ነኝ፡፡ የአዲሱ ሕይወቴ ጎዳና ቀያሽና ደልዳይ ራሴ ነኝ።
እያስፈልግም፡ በቃኝ! አባቴንም እንደ እናቴ በማስማልና በፍርሃት
እየተርበደበድኩ በመጠጋት የሚለኝንና የሚወስንብኝን ሁሉ አቀርቅሬ በመስማት ዕድል ለሚሏት አጋጣሚ ነገር አልንበረከክም! መጠራጠር ማለት ስለ አንድ ነገር ቢያንስ በጥቂቱ ማወቅ ወይም መገመት ማለት ነው። የትላንቱን ስሕተቴን ዛሬና
ነገ መድገም የለብኝም፡፡ አታስቡ! እኔ ለአባቴ የራሴ ዝግጅት አለኝ፡፡ በቀጥታ ቀርቤ ፊት ለፊት አስረዳዋለሁ፡፡ ለጥያቄዎቹም መልስ እሰጣለሁ» በማለት ጣልቃ
ገብቼ ተናገርኩ። ድንገት ደሟ ፈላና «ከንትርክና ብዙ ጣጣን ከሚያስከትል ጭቅጭቅ ይልቅ መግባባት ይበልጣል። በንትርክና በአሻፈረኝ ባይነት የምታገኘው
ድል አድራጊነት ሁሉ እስከ መጨረሻው አያረካህም፡፡ አባቴ በመጀመሪያ ጋሻዬነን አይቶ ከተደሰተና የሐሳቡ አቅጣጫ ካማረ ሁሉም ነገር ይሳካልናል።
የወዲያነሽንና የአንተን ግንኙነት፣ የደረሰባትን መከራና ሥቃይ ሁሉ ቀስ በቀስ እተርክለታለሁ፡፡ ልቡ ካዘነና መንፈሱ በርህራሄ ከተነካ፡ በሉ ሂዱና አምጧት ይላል” ብላ ነገሯን ልታራዝም ስትል «አይቻልም! ማን አስተርጓሚ አደረገሽና!
መሸሸግም ሆነ መደበቅ የለበትም፡፡ አልለማመጥም:: እጅግ አርኪው ድል አድራጊነትም ከትግልና ከሥቃይ በኋላ የሚገኝ ድል አድራጊነት ነው፡፡ እኔና
የወዲያነሽ ጋሻዬነህን አስከትለን ባንድ ላይ እንቀርባለን፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት “እንቺም ሆንሽ እናቴ አንዲት ቃል መናገርም ሆነ ማሰማት የለባችሁም፡፡ በምንቀርብበት ቀን እንግዶች ቢኖሩም ባይኖሩም ግድ የለኝም። እንዲያውም ወሬው እንዲስፋፋና እንዲዛመት ብዙ ሰዎች ቢኖሩ በጣም ጥሩ ነው:: በዚህ ብትስማሙ ተስማሙ፡ አለበለዚያ ግን የማደርገውንና የማላደርገውን እኔ ራሴ አውቃለሁ፡፡ እኔ የምፈልገው እንዲያውቅ ብቻ እንጂ እንዲስማማ ወይም መርቆ
እንዲቀበለን አይደለም፡፡ ከባለቤቴ ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ አስተያየትም ሆነ ሌላ ሐሳብ እንዲያቀርብ አይደለም» በማለት ቀጥ እንዳለ አቀበት ስትፈራው የቆየችውን ጉዳይ አውላላ ሜዳ አደረግሁላት፡፡ በእኔ ላይ የነበራት ግምትና አስተሳሰብ ሁሉ ነፋስ እንደ መታው ልም ዱቄት ተበተነ፡፡በሁለታችን መካከል በጣም ግዙፍ የሆነ የሐሳብ ልዩነት ተፈጠረ፡፡ በእኔ ላይ የሐሳብ በላይነት ለማግኘት ባለመቻሏ ተከዘች። ምክራቸውንና መላቸውን ሁሉ ባለምቀበሌ ንዴቷ ናረ። የመዥገር ሞት ያህል አላሳዘነችኝም፡፡ ቁርጡን ለማወቅ
የጓጓው አእምሮዋ ራሱ የዘጋውን የዝምታ በር ከፈተው፡፡ «እኔ እና የግሌን የአቀራረብ መንገድና ሐሳብ አዘጋጃለሁ እንጂ የእናንተን አልቀበልም ማለትህ ነው?» ብላ ሁኔታዬንም አብራ ለመረዳት ፊቷን ወደ እኔ አዞረች፡፡

ባጭሩና በቀላሉ ”አዎ” አልኩና ተጨማሪ ምክንያትና ማብራሪያ
ለማቅረብ ስዘጋጅ «በቃኝ አያስፈልገኝም! አልሰማም ቀኙን ሲያሳዩህ ግራ ግራውን ትመርጣለህ፡፡ እኔን ያናደደኝ ያንተ እምቢታና የመጣው ይምጣ ባይነት ሳይሆን በዚሀ ይሻላል በዚያ፡ ይኸ ያዋጣል ያኛው ይበልጣል እያልኩ ከእናቴ ጋር
ስነታረክና ስከራከር መሰንበቴ ነው» ብላ ፊቷን አዞረች።

አልደነገጥኩም፡፡ «የአንቺም ይሁን የእናቴ ርዳታ እያስፈልገኝም፡፡ ጥገና እና ድረታ አልፈልግም፡ ጥገና አይዋጥልኝም! ጥገና ማለት ውስጠ ሰባራ ማለት ነው፡፡
ከሆነላችሁ እናንተም ተደርባችሁ በጥያቄና መልስ አዋከቡኝ! ዝግጁ ነኝ። ነገር ግን እኔ በማልገኝበት ወቅት አባቴን እንድትለምኑልኝና እኔን፣ ባለቤቴንና ልጄን ዝቅ አድርጋችሁ እንድትለማመጡልኝ አልፈልግም፡፡ እኔ ራሴ ባለጉዳዩ ፍላጎቴንና ውሳኔዩን ለማስረዳት በሚገባ ዝግጁ ሆኛለሁ» ብዬ ፋታ ሰጠሁ፡፡

«አያዋጣም እንጂ ቢያዋጣማ ጥሩ ነው:: ለፍተህ ለፍተህ እዚህ ከደረስክ በኋላ እንዴት እንዲህ በቀላሉ ትገነፍላለህ?» ብላ ራሷን ነቀነቀች።

«በቃኝ ነው የምልሽ! በሐሳቤና በእምነቴ እንድትስማሚ አላስገድድሽም። የገዛ መብቴን አልመፀወትም:: የሕሊናዬን ቁስል የማድንበትን መድኃኒት ቀስ በቀስ እያወቅሁ ነው:: ከአባቴ መሠረተቢስ እምነት ጋር እንድጋጭና እንድታተር
እንጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ አንገቴን ሰብሬ የሚኖረው የሚያቀርበውን
ዝባዝንኪ ሐሳብ ሁሉ ያለ አንዳች ክርክር እንድቀበል አልፈልግም! ጨቋኝ ግዴታውን አልቀበልም:: ሐሳባችሁንም ሰርዙ። ከዚህ አሁን ከነገርኩሽ አፈጻጻም ውጪ አንዳችም የምቀበለውና የምስማማበት ሐሳብ ስለ ሌለ ነገር ሳናንዛዛ ወደ ቤት እንግባ» አልኩና ለጠላቱ የመጭረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጥ
ሰው የማያወላዳውን ነገርኳት። ለወለላ ገሥግላ ፊት ዛቀች!

ያለውን ይበል ብላ እንዴት አታስብም? እንዴት አይገባህም? ነገሩን ረጋ ብለህ ተመልከተው፡ ራስህን ብቻ አትውደድ፡ ይኸማ ይበጣበጡ' ይጣሉ፡ ይጋደሉ ማለትህ እኮ ነው? ስንትና ስንት ዓመት ሙሉ ምስጢሩን ደብቀህ
ከኖርክ በኋላ አሁን በመጨረሻ ጣጣን አመጣህ። ለካስ በጄም በግሬም ገብተህ የተለማመጥከኝ እንዲህ ለመሆን ኖሯል? አሁን አንተ በምትለው ሁኔታ ከሆነ
አገር ምድሩን እንደሚበጠብጥ አውቃለሁ፡፡ እናቴ ግን ያን ሁሉ አድራጎት ያደረገችው ላንተው ስትል እንደነበር ታውቃለህ» ብላ ፊት ለፊት ወደ ጨለማው
👍3
#የወዲያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ሰኞና ማክሰኛ ተከታታዮቹም ቀናት በየተራ አልፈው ቅዳሜ ደረሰ፡፡ሁላችንም በሐሳባችን እንደ ጸናን ሰነበትን

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ዘጠኝ ተኩል ገደማ ላይ ደርሶ ብርድ ብርድ ስላለኝ ፀሐይ ለመሞቅ ምድረ ግቢው መኻል ተቀመጥኩ በየወዲያነሽ አእምሮ ውስጥ
ያለው ጥያቄ ሳይመለስ በመሰንበቱ ሥጋቷ አልተወገደም፡፡ በአንዲት ትንሽ ነጭ ፎጣ ብርጭቆ እየወለወለች ዝግ ብላ መጣችና “አሁን ነው እንዴ የምንሄደው? እ...!» ብላ ንግግሯን በጥያቄ አንጠለጠለችው::

«አንቺና ጋሻዬነህ የምትሄዱት ሌላ ጊዜ ነው:: ቀኑን እኔና አንቺ
እንወስነዋለን፡፡ ዛሬም ሆነ ነገ የምሄደው እኔ ነኝ። ከነዚያ ከተከለከሉ መጻሕፍት አንብባ የነገረችሽን የእስረኛዋን ጓደኛሽን የምክር ቃላት አትርሺ፡ መብት
የሚገኘው በትግል ነው፡፡ ጨቋኞች በሰላምና በውዴታ መብት እይሰጡም ብላ
ነግራኛለች አላልሽም? እኔና አንቺም» ብዬ ዝም አልኳት። ከጀመርኩት አርእስት ውጪ «አዎ እውነትህን ነው: ከመንገድ ሲገቡ ያላሰቡትን ያልሰሙትን ነገር ተናግሮ ክፉም ደግም መስማትና መናገር ለእርሳቸውም ሆነ
ለእኛ ነገር ማበላሸት ነው» ብላ የብርጭቆይቱን ጥራት ለማረጋገጥ ትክ ብላ ተመለከተቻት ንግግሯን ሰምቼ ዝም ስላልኩ ወደ ቤት ገባች፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አባቴን እንኳን ደኅና” መጣህ ለማለት ወደ ወላጆቼ ቤት ገሠገሥኩ፡፡

ባለፈው ጊዜ ወላጆቼን ለመጠየቅ ስሔድ ይጨመድደኝ የነበረው
ሥጋትና ፍርሃት እንዲሁም የሕሊና ረብሻ እጅግ በጣም ተቀነሰ። እረጋገጤ ደልዳላ ከመሆኑም በላይ ቀና ብዬ ተራመድኩ፡፡ ዱሮ ደረጃውን የምወጣው አንድ
በአንድ ሲሆን ዛሬ ግን ሁለትና ሦስቱን በአንድ ጊዜ አጠቃለልኩት። ደረጃውን
ጨርሼ ፊቴን ወደ በሩ መለስ ሳደርግ የብዙ ሰዎች ድምፅ ሰማሁ፡፡ ወደ ውስጥ ለመዝለቅ የነበረኝ ድፍረት ከፍ አለ። እቤቱ ውስጥ ለነበሩት ሁሉ ጎንበስ ብዬ
እጅ ነሣሁ፡፡ ከዚያም በቀጥታ ወደ አባቴ ሄድኩና እጅ ነሥቼ ጨበጥኩት።
«እንኳን ደኅና ገባህ! የሄድክበት ሁሉ ቀናህ! » አልኩና አንገቴን በትሕትና ሰበር አድርጌ ከፊቱ ገለል ብዬ ቆምኩ፡፡
እንኳን ደኅና ቆያችሁኝ አዎ ደኅና ደርሼ መጣ። ሁሉም ደህና
ቆየኝ። ክብሩ ይስፋ!ና! እዚች አጠገቤ ና አጠገቡ የነበረውን ወንበር በጣቱ አሳየኝ። እንኳን በደህና ገቡ ለማለት ያመጡትንና ሌሎችንም እንግዶች አንድ
በአንድ አየኋቸው፡፡ በሰዎች ላይ የሚታየው ፈገግታና የአቀማመጣቸው ሁናቴ
የተለያየ በመሆኑ አባቴን በተለያየ የአስተሳሰብ ደረጃ እንደሚመለከቱት ያስታውቃል። አንዳንዱ ውስጣዊ ጭንቀት አስገድዶት በግድ ፈገግ ብሏል።
ለማስደሰትና በግድ ለመደሰት ብሉ በደረቅ ፈገግታ ፊቱን ያጨማደደም አለ።የአንዳንዶቹን ፊት ደግሞ የበታችነት ስሜት ስለተጫነው ፊታቸው ከልቅሶ በኋላ የሚታይ ፊት እንጂ ለደስታ የቀረበ ገጽታ አይመስልም፡፡

ሁለትና ሦስቱን እንደ አባቴ የቅርብ ጓደኞች ስለምመለከታቸው በእነርሱ ላይ የነበረኝን ጥላቻ ለመርሳትም ሆነ ለማሻሻል ያለኝ አቅም በጣም አነስተኛ ነበር። ሕሊናዬ ዘወትር ይበቀላቸዋል፡፡ ወረቀት እያገላበጡ የሚዶልቱት ሁሉ ትውስ ሲለኝ፡ የሰውን ሕልውና አርደውና አወራርደው የሚገድሉ ይመስሉኛል።
ክርክርና ወሬ ሲጀምሩ ማንም በአጠገባቸው እንዲያልፍ ስለማይፈልጉ ዓለምን
የተንኮል ገበያ እንጂ የመልካም ምግባር አደባባይ እንድትሆን የሚያስቡ አይመስሉም፡፡ እናቴ እንኳን ደበቅ እያለች «መጡ ደግሞ እነ ጋጠው ገሽልጠው»
ትላቸው ነበር፡፡

ለእኔም እንደ እንግዶቹ ጠላ ደረሰኝ፡፡ ከዚህም ከዚያም የሚመጣውን ወሬ እየሰማሁ ጠላዬን ሁለት፣ ሦስት ጊዜ አስሞላሁ፡፡ እንግዶቹ አንድና ሁለት እየሆኑ ተራ በተራ እጅ እያነሡ ሄዱ።

እናቴና የውብነሽ ከአሁን አሁን ተናግሮ ጉድ ይፈላ ይሆን በማለት
በአስጨናቂ ሐሳብ እንደሚሠቃዩ ስጋታቸው በየፊታቸው ላይ ይታወቃል፡፡ ከእኔ ጋር ማዶ ለማዶ መፋጠጡን ስለ ጠሉት ሁለቱም ወደ ማድ ቤት ወረዱ፡፡

እኔና አባቴ በጣም በመጠነኛ መግባባት ስለ ጭሰኛ' ስለ ግብር' ስለ ሲሶና እርቦ ስለ ገሚስና ከአሥር አንድ፣ እንዲሁም ስለ ሕግና ስለ እኔ የልጅነት ዓመታት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት እንደነገሩ አወራን። ከዚያ በኋላ
ግን፡ እነዚያ ለሁለት ሳምንት የተለዩት የወንጀለኛ መቅጫና የፍትሐ ብሔር ሕግ መጻሕፍት ትዝ ስላሉት «ትንሽ ሥራ አለብኝ፡ ከእናትህና ከአጎትህ ጋር ተጫወት» ብሎኝ ወደ መኝታ ቤት ገባ።

ከአባቴ ጋር ተዝናንቼ ሳወራና ስጫወት በመልሶቼም እየተማመንኩ ስመልስ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር፡፡ አባቴ ገባ ከማለቱ እኅቴና እናቴ ተካ አሉ።
የፌሩት ጉዳይ ባለመነገሩ የሁለቱም ፊት ፈገግታ አጋተ። ሩብ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አባቴ እንደገና ተመልሶ መጣ። ኖር ብለን ተቀበልነው። እምብዛም
ሳይጠጋ ቆም አለና እነዚያን በዕድሜና በክርክር ጽሑፍ ንባብ የተዳከሙ ዐይኖቹን በግራ እጅ ጣቶች እያሻሸ ሳልነግርህ እንዳትሄድ ብዬ ነው የተመለስኩት ዘንድሮስ በጣም ጎብዘሃል አሉ፡፡ መቼ እንደሆነ አላውቅም፡ አንድ ወዳጂ ሰዉ ጋር መንገድ ላይ አየሁት ብሉ ነገረኝ። አዎ ምንም ይሁን ምን እያደር ልብ
ሲገዙ ነው የሚታወቀው» አለና የቤቱን ግድግዳ ባይኑ ዞረው፡፡ የእናቴን የየውብነሽ ልብ በፍርሃት ተበዝብዞ ፊታቸው ድንጋጢ በሚያሯሩጠው ደም ጢም
ኣለ።

ከተቀመጥኩበት ተነሥቼ «ምን ነገሩሁ? ምን አሉህ?» አልኩና የሰማውን ለመስማት ጓጓሁ። «እሱስ ይሁን፡ እንዲያው እስከ ዛሬ ለምን ደብቀሽኝ ብዬ ነው:: ነገ እነግርሃለሁ፡፡ አበጀህ! ጠላትም ወዳጅም ደስ አይበለው ብሎ ለመመለስ ሲጀምር «አሁኑኑ ብትነግረኝስ?» አልኩት፡፡

«ነገም እኮ ሩቅ አይደለም። ነገ ይሻላል» ብሎ ሊገባ ሲል «እኔም ብዙ ነገር እነግርሃለሁ» አልኩና እኔም ነገሩን ችላ አልኩት፡፡ እናቴ በፍርሃትና በጥርጣሬ እየዋለለች «ምን ሰምቶ ይሆን? ምን ነግረውት ይሆን ጌታዬ?» አለች
ከንፈሯ ሥር በሚንደፋደፉ ቃላት።

«ነገ በአንድ ላይ እንሰማዋለን» ብዬ ሊንቀሳቀስ የነበረውን ነገር እንዳጠፋ ልጅ ኮረኮምኩት፡፡ ነገሩ ሁለት ቤት ያለው ሆነና ራቴን በልቼ ወደ ቤቴ ተመለስኩ።

የዕለቱን ወሬ ለመስማት በከፍተኛ ጉጉት የምትጠባበቀዋ የወዲያነሽ፣ ከልጅዋ ጋር ስታወራ ደረስኩ እና ከጎኗ ተቀመጥኩ፡፡ ከእኛ ራቅ ብሎ በብረት
ምድጃ ውስጥ የተንተረከከው የከሰል ፍም የቢቱን አየር አሙቆታል። በወላጆቼ ቤት ስላጋጠመኝ ነገር አንድ በአንድ ጠየቀችኝ፡፡ የየወዲያነሽ ነገር ስለሆነብኝ ደከመኝና ታከተኝ ሳልል መለስኩላት፡፡ «እኛንስ መቼ ነው የምትወስደንና እጅ
ነሥተን፤ ጫማ ስመን፤ የሚሉንን የሚሉን?» አለችና የመንፈስ ጭንቀት ስለ ተሰማት አቀረቀረች። «በክብርና በይፋ ነው ይዤሽ የምቀርበው! ይህቺ የማከብራትና የምወዳት ባለቤቴ ናት ብዬ የምናገረውና የማስረዳው እኔ ነኝ፡፡በመለማመጥና በማጎብደድ ሳይሆን አባቴ በመሆኑና ለወላጅነቱ ክብር ብቻ ብዩ ያውም ክብረ ሕሊናሽን በማይነካ ሁኔታ እጅ ትነሺ ይሆናል» ብዬ አገጫን ይዤ አበረታታኋት።

«አንተ እንዳልከ! እኔ እንዲሁ ነው የምቀባጥረው» ብላ፤ ረጋ ባለ
እረማመድ ወደ ጓዳ ገባች፡፡ በውስጧ ፍርሃት እንደልቡ ይጨፍራል፡፡ከሠራተኛይቱ ጋር ራት አቀረቡ፡፡ መብላቴን ሳልናገር ደስ ይላት ዘንድ ዝግ ብዬ በላሁ። ጋሻዬነህ እንኳ ወግ ደርሶት «በእማምዬ ሞት፡ በእኔ ሞት» እያለ ደጋግሞ አጎረሰኝ፡፡ ዕለታዊ ድርጊት የአካባቢ ቅጂ ነው፡፡
👍3
#የወዲያነሽ


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...አረ የምን አጥር መዝለል አጥር የምታዘልልና ጥቅጥቅ ባለ ጨላማ የምታስሮጥ ዘንካታ አለችኝ አልኩና እናቴና የውብነሽን አየኋቸው።ክፉኛ ደንግጠዋል።

አባቴ፡ በንቀትና በችላ ባይነት እግሮቹን ከዘረጋ በኋላ አይሄሄ
ለጉራማ ማን ብሎህ! ማን ይችልህና! ቆየት ብለህማ እንደ እስክንድር በባለ ክንፍ ፈረስ ጋልቤያለሁ ሳትል ትቀራለህ? ዛሬስ ብለህ ብለህ ይሉኝታውንም እርግፍ አድርህ ትተህዋል! ሲሉ ሰምተሃል መሰል ደግሞ አጥር የምታዘልል አለች ወግ ነው! አታደርገውም እንጂ የወንድ ልጅ ሙያ ነው። ተከሶና ተታኮሶ
ቆንጆን ነጥቆ ማምጣት በእኛ ጊዜ ቀረ፡፡ ይቺን እናትህን ስንቱ ጎበዝ ጎረምሳ የትልልቅ ሰው ልጅ ነበር የከጀላት። እኔ አባትህ ግን እሳት የላስኩ፡ እሳት የጎረስኩ ስለ ነበርኩ፡ የሚያይብኝን ሁሉ በቁሙ አጭረቀርቀው ነበር። እከሌ እኮ
ቀና ብሉ አያት፡ አነጋገራት፡ በቤቷ አጠገብ አለፈ ሲሉ የሰው እንደሆነ እማኝ በሌለበት ቦታ ጠብቄ በጆሮ ግንዱ ነበር የማጮህበት። በዚህ ዐይነት አንድ
ዙር የዝናር ጥይት ነበር የጨረስኩት። የኋላ ኋላ ግን ተንቀባርሬ፡ ኮርቼ ስሜን
አስጠርቼና አስከብሬ ወሰድኳት» አለና የተናገረውና ያስታወሰው ሁሉ እውነት መሆኑን ለማስመስከር እናቴን በኩራት አያት፡፡

«በእናንተ የወጣትነት ዕድሜ ያገለገለው ጥይትና ዛሬ በእኛ ጊዜ ያለው ጥይት ልዩነት አለው። የምናነጣጥረውና የምንተኩሰውም በልዩ ዘዴና አኳኋን ነው:: ለልዩ ድልና ለአዲስ ዓላማ ነው፡፡ የእናንተ ትግልና የኑሮ ጎዳና አንድ ቢበዛም ሁለት እንጂ ከዚያ በላይ አይወጣም፡፡ ዛሬ ላይ ቆመን ከትላንትና የተሻገሩልንን ልዩ ልዩ የሚታዩና የማይታዩ ነገሮች በመዋጋትና በመለወጥ ላይ
ነን። የትላንትናን ጥሩ ጥሩ ነገሮች ለወደፊት እያስተላለፍን መጥፎ መጥፎውን እየነቀልን ለማንጓለል ተሰናድተናል፡፡ እያንጓለልም ነው። የእኔን የኑሮ ጦርነት ድሉች ስትሰማ ትደነቃለህ። አሁን ለጊዜው መድፍና መትረየስ ያለበት እንዳይመስልህ?» ብዬ አእምሮዬ ውስጥ ካካበትኩት ሓሳብ ውስት በጭቄ
እንደቀልድ አሰማሁት።

«ጉድ ነው! ዛሬስ እዚሁ እፊቴ ቁጭ ብሎ ማይጨው ዘመትኩ ሊል ነው። ደርሶ ባለ ጦርነት መቼ የታወጀው ጦርነት ነው በል? እዚህ በያባሕር ዛፎች ውስጥ መሽጋችሁ እንዴ!» አለና ጎላ ያለ የፌዝ ሣቅ ስቆ ዝም አለ።

እኔ የማቀርብልህና የማብራራልህ አንተ እምታነበውን የነጋሪት ጋዜጣ ዐይነት ሳይሆን ሌላ ያውም ልዩ ሕዝባዊ ነጋሪት ጋዜጣ አለኝ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕሊናዩ ጓዳ ውስጥ ያስቀመጥኩትን ዐዋጅ በይፋ አሰማሃለው። መስማት ብቻ
ሳይሆን በተጨባጭ እያየህ፣ ትዳስሳለህ!» ብዬ አእምሮውን ለማወቅ ያህል ዝም አልኩ፡፡
«እኔ አባትህ አሁንም ቢሆን ጀግና ነኝ፡፡ የምርበተበትና የምፈራ

አይምሰልህ፡፡ አንተ ዐዋጅ የምትለው የመንደሩን አሉባልታና ወሬ እንዳይሆን ይዘኸው ና። የፈለግኸውን ይዘህ ብትመጣ እያብራራሁ እሸነሽንልሃለሁ። ጦርነት በምትለው የወሬ ዘመቻ ላይ ጀብዱ ሠርተህ ከሆነም እሽልምሃለሁ። ለሞየትም ዝግጁ ነኝ» በማለት ከነትምክህቱ ተኮፈሰ በንግግራችን ወቅት አነጋገሬ ሁሉ
ፍራቻ ስላልተጠናወተው ራሴን ዛሬስ በርትተሃል፡ በዚህ አያያዝ መግፋትና መቀጠል ነው» አልኩት። አጎቴና እናቴ አፍላፍ ገጥመው የስጋት ወሬያቸውን
ይሰልቃሉ፣ እነርሱንም ስጋት ይድሳቸዋል። ወደ እኛ ዞር እንዲሉ በማለት ድምፄን ከፍ አድርጌ ትላንትና ማታ እኮ እነግርሃለሁ ብለህ የተለያየነው በቀጠሮ ነው። በትላንትና ውስጥ ሆነን ነገ የምንለው ዛሬን ነው። እዚህም
የረጂም ጊዜ ቀጠሮ መስጠት ደስ ይልሃል እንዴ?» ብዬ ዐመድና ቅንቅኗን እንደምታራግፍ ዶሮ እጆቼን ዘርግቼ ተንጠራራሁ።

ያለቦታው ያነሳሁት ሐሳብና
ቃል ራሴን መልሶ ቅር አሰኘኝ፡፡ እሱም በትዝብት ገረመመኝ፡፡ «
ይኸነዬ ጨንቆህ ነው። ቡቡ ነህ! ብኩን ነህ አላልኩህም? ወኔህ በቀላሉ ይቀልጣል፡፡ በል ልገላግልህ! ቀኛዝማች ጥበበ ሥላሴን ታውቀው የለ? እሱ ታድያ ልጅህ መኪና ገዝቷል እንዴ? ሲነዳ አየሁት፥ ብሎ ነገረኝ፡፡ ነገሩ በጣም የሚያስደንቅ ባይሆንም
ባቄላ የምታህል ልብ በመግዛትህ ደስ ስላለኝ ነው:: እጎንህም ሰው ነበር አለኝ መሰለኝ። ይኸው ነው ሌላ አይምሰልህ፡ ወይም የተውሶ መኪና ስትነዳ አይቶህ ይሆናል፡፡ ደኅና ጓደኛ ማበጀትም እኮ ቁም ነገር ነው» ብሎ ተነሣ፡፡
የተውሶ አይደለም፤ እኔው ራሴ ገዝቻለሁ» ብዩ እኔም ቆምኩ፡፡ «ደግ አድርገሃል፣ እንግዲህ ቀስ በቀስ ሰው ልትሆን ነው፡፡ በርታ! እኔ ደግሞ በበኩሌ
ያሰብኩትን በቅርቡ እነግርሃለሁ፡፡ ደግሞ ምንድነው እያልክ ስትጨነቅ እንዳትሰነብት የሌላ አይምሰልህ። ጉልቻን የመሰለ ነገር የለም፡፡ የደኅና ሰው ዘር፣
የጨዎ ልጅ ማግባትም እኮ ማንም ተመኝቶ የማያገኘው ትልቅ ማዕረግ ነው»
ብሉ ወደ መኝታ ቤት ለመግባት መንገድ ሲጀምር «በል ከእነሱ ጋር ተጫወት አደራችሁን እንቅልፌን ሳልጨርስ እንዳትቀሰቅሱኝ» ብሎ ገባ፡፡

የእኅቴና የአናቴ አንጎል ሲጨነቅበት አድሮ የዋለበት ጉዳይ በዚህ ሁኔታ በማለፉ በልባቸው እፎይ አሉ። ኣባቴ በወጣትነቱና በጐልማሳነቱ ብዙ ያየና ያሳለፈ በመሆኑ የእኔን ከቤት መውጣት እንደ አንድ ትልቅ ኃጢአትና በደል አልቆጠረውም፡፡ 'ወንድ ልጅና አንበሳ የትም ሄዶ የትም ገብቶ ማደር አለበት”
የሚለው አነጋገሩ እኔን በቸልታ የማያው ምክንያት ነበረች።

ከግማሽ ሰዓት በኋላ የባጥ የቆጡን አወራርቼ «ደኅና እደሩ» ብዩ ወጣሁ፡፡ የቤቱን ዙሪያ ቆም ብዬ ተመለከትኩት። የትዝታ ጥላ እንጂ የሕልውና አለኝታ አልሆንልህ አለኝ፡፡ ቤቴ ስገባ ጉልላትና የወዲያነሽ ፊት ለፊት
ተቀምጠው መጽሐፍ ያነብባሉ፡፡ ሰላምታ አቅርቤ ከጉልላት ጐን እንደ ተቀመጥኩ ሁለት ሰዓት ሙሉ አንተን ስጠብቅ ቆየሁ፡ ቀጠሮዬን ረሳኸው እንዴ» ብሎ
ከአንገት በላይ ኩርፈያው አሳየኝ። መለስ ብዬ ሳይ የወዲያነሽ ቆማለች፡፡ «እረ በይልኝ! ምነው ምነው የኔ እመቤት» አልኳት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከወንበር ላይ
የምትነሣው እንደ ዱሮው በዝቅተኛነት መንፈስ ባለመሆኑ አልከፋም።

ጉልላት የት እንደ ዋልኩ ለማወቅ ከአንገት በላይ አፈጠጠብኝ። የነገሩን አቅጣጫ ቶሎ ለመቀየር በሁለት ሰዓት ውስጥ ስንት ኩባያ ሻይ አስቀዳህ? ብዬ ስለ በረዶ ተጠይቆ ስለ ድንጋይ እንደሚያስረዳ መምህር ነገሩን አምታታሁበት።

«ካልክስ አሁንም ተጥዶልኛል፡፡ ይኸኔ ፈልቷል» ብሎ የወዲያነሽን
መለስ ብሉ በእዎን በይልኝ ተመለከታት፡ በሁለቱ መካከል ያለው መግባባት ከፍ ያለ በመሆኑ እንቅስቃሴዎቹን ሁሉ እንደ እጅ ጣቶቿ ታውቃቸዋለች። የወዲያነሽ
ወዲያውኑ ብር ብላ ሄዳ ሻይ ይዛ በመመለስ አጠገቡ ቆም ብላ ትከሻውን ተመረኮዘች። የየወዲያነሽን የእርግዝና መጠን ወደ ጐን እየተመለከተ «ወንድ
ከሆነ የክርስትና አባቱ እኔ መሆን አለብኝ» አለና ከቀረበለት ሻይ ላይ ፉት አለ፡፡ «ሴት ከሆነችሳ?» አልኩት።

«ሴት ከሆነችማ ለማን ልበልህ? ለዚያች እኔና አንተ ለምናውቃት ሊ....ብሎ» በርግጠኛነት ምራቁን ዋጠ፡ የምንነጋገረው ስለ እርሷ መሆኑን በማወቅ በመጠኑ አፍራ ተቅለሰለሰች።
👍4
#የወዲያነሽ


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ዳፈና ውስጥ ተጎልቶ እየተቆሰቆሰ የሚበራ የማገዶ ብርሃን እንደሚጠባበቅ ሰው ሕሊናዬ በተመስጦና በጉጉት የሚጠባበቀው እሑድን እንጂ
ረቡዕንና ሐሙስን አልነበረም፡፡ እያንዳንዷ ቀን በዕጥፍ እየተቀመጠለች ብታጥር
ባልጠላሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ ረቡዕና ሐሙስ እንዲሁም ዓርብ ተራ በተራ አለፉ፡፡የሕሊናዬ ጠቅላላ ዝግጅት ለእሑድ ትንቅንቅ ክተት አለ። የትግልና የቁም ነገር
ንፁህ ምርቴን የምሰበስብበት ዕለት እሑድ በመሆኑ ያ አብሮ አደጌ ፍርሃት በቁሜ እንዳያበክተኝ በማለት ተጨማሪ የክርክርና የሙግት ሸንጎ በራሴ ውስጥ
አዘጋጀሁ፡፡

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የሁለት እምነቶች የጦፈ ግጭት የሚደረግበት ዋዜማ ነበር፡፡ ምድረ-ግቢው መኻል ዕንጨት ወንበር ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ከአባቴ
ጋር በማደርገው የአስተሳሰብ ጦርነት ላይ የሚገጥመኝ የመጨረሻ ውጤት ምን ይሆን እያልኩ ሳሰላስል እቆይና «ውጣልኝ! ውጣ! አሰዳቢ! ውርደተኛ ይዘሃት ገደል ግባ!» ብሎ የጮኸብኝ እንደሆነ ምን እመልስለታለሁ? በማለት ዝግጅቴን ለማጠናከርና ራሴን ለመፈተሽ ሀ ብዬ ነገሩን ወጠንኩ፡ ድንገት ከወንበሬ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሣሁና ያስፈለገውን ይበል፥ ይራገም! ያውግዝ! ፍትሐ ብሔሩን
እየጠቀሰ ከሚመካበት የንብረቱ ውርስ ላይ ይንቀለኝ! ይሰርዘኝ! እኔ ግን ከወሰንኳት ሐሳቤ ላይ እንዲት ጋት እንኳን ወደኋላ አልነቃነቅም፡፡ አላፈገፍግም፡፡ወደፊት መሸከም የሚገባኝን የኃላፊነት ቀንበር መሸከም አለብኝ፡ በዚያው አንፃር
ደግሞ የተገዢነትንና የባርነትን ቀንበር መሰባበርና ማነኳኮት ይጠበቅብኛል፡፡እኔው አነጣጥሬ እኔው ቃታ መሳብ ይኖርብኛል! ስለ የወዲያነሽ ሰብአዊ እኩልነት ስለ ሁለታችን የሕሊና ነጻነት ስል የሚያጋጥመኝን ችግርና ማናቸውም ተቃውሞ ሁሉ እቋቋመዋለሁ፥ እደመስሰዋለሁ» ብዩ የአባቴን የሕሊና ምስል ፊት
ለፊት አቁሜ በቁጣ አፈጠጥኩበት ደመናው ውስጥ ድብብቆሽ ስትጫወት የቆየችው ፀሐይ የእኔን ቁጣና የሕሊና ረብሻ የፈራች ይመስል ደመና ውስጥ
ጠልቃ ቀረች፡፡ እኔም ወደ ቤት ገባሁ። ወዲያ ወዲህ ብመለከት ሰው በማጣቴ በቀጥታ ወደ መኝታ ቤት ዐለፍኩ፡፡ የወዲያነሽ የቀኝ እጅዋን ተንተርሳ ዐይኗን
ለእንቅልፍ ሳይሆን ለዕረፍት እንገርባዋለች። በንጹሕ የምንጭ ውሃ ላይ የምትሯሯጥ የውሃ እናት እንደሚመለከት ልጅ አሽቆልቁዬ አየኋት። ደርባባ ዝምታዋ የተንጣለለ ውበት ወለደ። አልጋው ጠርዝ ላይ ጋደም እንዳልኩ
እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ኻያ ደቂቃ ያህል እንደ ተኛሁ ባንኜ ነቃሁ። በደመና ተሽፍና የነበረችው ፀሐይ መጥለቋን የተረዳሁት ክፍሉ ውስጥ በተተካው ድንግዝግዝ
ጨለማ ነበር። ዟ ብዩ አልጋው ላይ እንደ ተንጋለልኩ የወዲያነሽ ከያዘችው የጠርሙስ ውስጥ ውሃ እየቀነሰች ግንባሬ ላይ አንጠባጠበች።
በሐሳብ መጠመዱን አውቃ በሰበቡ አናጥባ ልትገላግለኝ ነበር፡፡ ከአልጋው ላይ ዘልዩ ትልቁ ክፍል ገባሁ፡፡ ተከትላኝ ገብታ አንድ ቦታ ላይ ቆማ እየዞረች
በምሮጥበት አቅጣጫ ሁሉ ረጨችብኝ፡፡ ሣቋ ሙዚቃዬ ነው። በናትሽ ቆይ በሞቴ ተይ! እባክሽ በሰበስኩ?» እያልኩ ክፍሉን ከአራት ጊዜ በላይ ዞርኩት።
ሰው ይመጣል ብለን ሳንጠረጥር የውብነሽ ድንገት መጥታ በመካከላችን ድንቅር
አለች።

«ኧረ በገላጋይ! ለእኔ ስትይ? ለእኔ ስትይ የዛሬን?» ብላ ጠርሙሱን
ተቀበለቻት። ከውሃው ቀነስ አድርጋ እጅዋ ላይ ስታቁር አይቼ «በቃ! አንቺ ደግሞ የምን ጭማሪ ነሽ» ብዩ ካንገት በላይ ተቆጣሁ፡፡ «ታዘብኩህ! ይኸን ያህል ታደላለህ?» ብላ እያሣቀች ተቀመጠች፡፡ ከጥቂት እንቶ ፈንቶ ወሬ በኋላ «እንግዲህ ነገ ያው ነው:: በእኔ በኩል የተለወጠና የሚለወጥ ነገር የለም» አልኳት
ምናልባት ያመጣችው አዲስ ወሬና ሐሳብ እንዳለ ለማወቅ፡፡ «እናታችን እንደሆነ ከአሁኑ መርበትበት ይዛለች፡፡ የቤቱ ዕቃ ሁሉ ያነቅፋታል። ነጋ ጠባ
ያቃዠኛል ነው የምትለው፣ እኔ እንጃላት» አለችና የትካዜዋን መጠን በወኪልነት
“ለማስረዳት የተላከች ይመስል የሚያሳዝን ባዶ ትካዜ ተከዘች። «ያለቀለት ጉዳይ ነው! ቃዠችም አለመችም አቀራረቤ አይለወጥም» በማለት ውክልናዋን እንደ ጨው አሟሟሁት። ነገሩን ቀዝቀዝ ባለ ሁኔታ የተመለከትኩት ለማስመሰል
«ይልቅስ መትተው ከማይመቱት ጋር ስለምፋጠጥ ምናልባት ተበሳጭቶ የተናደደ እንደሆነ በዚያ በከዘራ እንዳያንቆራጥጠኝና አሳሬን እንዳያስጨልጠኝ በአካባቢው ያለውን በትር ሁሉ ደብቂልኝ፡፡ ስለ ሌላው አትሥጊ» ብዬ የእሑዱን ተራ ሥጋቴን ለፍሥሐም ይሁን ለኀዘን ገለጽኩላት፡፡

እኅቴና ባለቤቴ ወሬ ሲያወሩ እኔ በዝምታ ወደ ውስጤ ሠረግሁ። በልቤ ውስጥ የተከሰከሰው የሐሳብ እቃቅማ ወጋኝ፡፡ ጋሻዬነህና ሠራተኛችን ከእኔ
አቅራቢያ ተቀምጠው ተረት ትተርትለታለች፡፡ የስድስቱም ተበሉና ያንዷ የሞኝ፤ ልጅ ብቻ ቀረ። ዝም ስለምትል ነው እንጂ ሞኝ አልነበረችም። ከዚያ በኋላ
የሰባቱንም ጡት ጠብቶ ሰባት ቀንድ አወጣ» አለችው ሁላችንም ካንገት በላይ እንቶፈንቶውን ሁሉ እያወራን ቤት ያፈራውን ተጋበዝን። የውብነሽን ለመሸኘት እንደ ወጣሁ በዚያው ወደ ጉልላት ቤት ጐራ ብዬ ስጫወት አመሽሁ። የውሳኔ ማሻሻያም ሆነ የሐሳብ ለውጥ አላደረግንም፡፡ ዝግጅቱ ተጠናቆ የሕሊና ጦርነት ክተት ታውጇል። የሚቀጥለው ተግባር ነፃነት ወይም ሞት ብቻ ነው። ነፃነት ግን ይቀድማል። ማታ የወዲያነሽን ጸጥታ እንዳልነሣ ሹልክ ብዩ ገብቼ ተቀመጥኩ።
መደበኛው አንጎሌ ብቻ ሳይሆን መላው አካሌ ሆኖ የሚያስብና
የሚያሰላስል፡ ምክንያት የሚያቀርብና የሚከራከር መሰለኝ፡፡ ሰካራም ባለቤት
በታላቅ ሥጋት እንደምትጠባበቅ ሴት ብቻዬን ተጎለትኩ። ይህን ረጂም ሌሊት ልገፋው የምችለው በንባብ ነው ብዪ ንባብ ቀጠልኩ። ደፋ ቀና እያልኩ ሁለት ሰዓት ያህል ጠረጴዛው ላይ ተኛሁ፡፡በየዕንጨቱ ስንጣቂ ጭላንጭል እየሾለካ
ሚገባው ቀዝቃዛ አየር ነቃ እንድል አስገደደኝ። ቀልቤን ሰብስቦ ያለማቋረጥ ሁለት ሰዓት ያህል ካነበብኩ በኋላ በስተምሥራቅ በኩል ያለውን መስኮት ከፍቼ
አካባቢውን ቃሁት። ጭልምልምታዉ ሙልጭ ብሉ ስላልጠራ ድፍርሱ ብርሃን
ዋና ትንቅንቅ ላይ ነበር። በጋቢዩ ውስጥ መጽሐፌን ደረቴ ላይ ለጥፌ የመስኮቱን ደፍ ተደግፌ ቆምኩ። አጥቢያ ኮከብ ልክ የቀኗ ሁለት ሰዓት ፀሐይ መዳረሻ ላይ
ደርሳ ትንተገተጋለች። ቀስ በቀስ ምሥራቃዊው አድማስ ከዳር እስከ ዳር ግምጃ ለበሰ። ከተራራው በስተጀርባ ያደባችው ፀሐይ ጮራዋን ሽቅብ ወደ ሰማይ
ሰደደችው። አሞሮችና ወፎች ከዚህም ከዚያም መብረር ጀመሩ፡፡ ከየአቅጣጫው
ሲያደነቁሩኝ ያደሩት አውራ ዶሮዎች ዐልፎ ዐልፎ መኮኮል ቀጥለዋል፡፡ ከንጋቱ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ሞላና እሑድ ሆነ።

በማለዳው ቀዝቃዛ ጭጋግማ አየር ውስጥ የጋለ የብረት አሎሎ መስላ የምትታየዋ ፀሐይ ብቅ አለች፡፡ ደመና በማይታይበት
ሰማይ ላይ የወጣችው ጀንበር በየደቂቃው ኃይልና ግለት ትጨምር ይመስል ድምቀቷና ብርሃኗ አየለ። እንዲያ እንዲያ ስትል በባዶ ዐይን ከምትታይበት
ሁኔታ ዐልፋ ተንተግታጊ ደረጃ ላይ ደረሰች። እንደ ወህኒ ዘበኛ ከወዲያ ወዲህ በማለት ላይ እንዳለሁ የወዲያነሽ አጠገቤ መጥታ ቆመች። «እስኪ አሁን እንኳ ትንሽ ጋደም በል፤ ደግ አይደለም እኮ! በኋላ እኮ ይደነዝዝሃል! ይደብተሃል»
👍4🤔1
#የወዲያነሽ


#ክፍል_አርባ_ሶሰት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ስደበኝ! ወይ መቆየት! አሁንሜ ብለህ ብለህ ስለ ሕጉ አስተያየት ሰጪና እርማት አቅራቢ ሆንክ! ስንት ሊቃውንት የደከሙበትንና ያረቀቁትን ሕግ አንተ ስላቃለልከው አይቀልም።
መንገርስ ልክ ልክህን እነግርህ ነበር፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል ይልቅ ወሬሀን ጠርቅ!".ብሎ የሚሆነውን እያሳጣው በቅምጡ ተቁነጠነጠ፡፡ ሕሊናው ጉዳዩን ቢረዳም
በፈቃደኛነት እንደማይረታ፣ በጨቋኝነት የተሞላ ሕሊናው በቀላሉ እጁን እንደማይሰጥ አወቅሁ፡፡ ቢሆንም የእኔ ሕሊናና ወኔ እየሞቀና እየጎለመሰ ሲሔድ
ያ በከንቱ ግብዝነት የተወጠረው የእርሱ ሕሊና ግን ቁልቁል ሲሟሽሽ ታየኝ።

በዚሀ ልጅ እናት ላይ..» በማለት እንደገና ቀጠልኩ፡፡ «በከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የመኻል ዳኛ ሆነህ አምስት ዓመት እስራት ፊርደሀባት ነበር፡፡ በሕይወቷ ውስጥ አምስት ዓመት ብቻ ሳይሆን የሕይወቷ ብዙ
ክፍል እንዲበላሽና እንዲሰናከል ተደርጓል። ወደ ዋናው ፍሬ ነገር ልመለስና በሕግና በእውነት» ስም በተቋቋሙት ፍርድ ቤቶቻችሁ ወንጀለኛ እያላችሁ ከምትፈርዱባቸው ንጹሐን ሰዎች ይልቅ በእናንተ እጅግ ጉልህ በሆነ ጥፋትና በሚጨበጥ ኃጢኣት ወንጀለኛ በሆናችሁት ሰው በላ ሰዎች የተሞላ ነው:: ወደ ልጄ ጉዳይ ልመለስና፣ ይህ ልጅ በዕጓለ ማውታ፣ እናቱ ወህኒ ቤት ውስጥ እየማቀቀች ሳይተያዩና ሳይገናኙ በጠቅላላው አምስት ዓመት ተለያይተው ቆይተዋል፡፡ እዚህ ላይ ነበር ምስጢሩ የራሱን ጉድጓድ ቆፍሮ የራሱን ሕይወት
የሸሽገው:: ያን ሁሉ ስቃይና ችግር የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ» ብዩ በልበ ሙሉነት እንደገና ተዝናናሁ፡፡

አባቴ ስቅላት እንደ ተፈረደበት ሰው ወዙ ደረቅ። እርሱ በተደፈርኩ
ባይነት፣ እናቴና እኅቴ በድንጋጤ እንደ ተጨነቁ እኔም የዓላማዬን መጨረሻ ለማሳመር ሳሰላስል በቤቱ ስጥ ጊዜያዊ ጸጥታ ሰፈነ። የአባቴን ሕሊና ለማንበርከክ፣ ሲጨቁነኝና ሲያፍነኝ የኖረውን የበላይነቱን ለመሰባበር እእምሮዬ
ሙሉ የማጥቃት ዝግጅቱን ቀጠለ።

«ልጨርስልሃ?» አልኩት የሐሳቤን ደጀን ካጠናከርኩ በኋላ፡፡
«ደግሞ ምን ቀረህ? ምን ቀረኝ ልትል ይሆን?»
«እኔ የማሳይህና የማሳውቅህ ወርቁን ብቻ ሳይሆን የወርቁንም ማዕድን ጭምር ነው::
“ይኻ ሁሉ ዝብዝብ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?»
«ባጭሩ ላስረዳህ እችላለሁ፡ የዚህ ልጅ እናት የወዲያነሽ አሸናፊ ያን ሁሉ መከራና ሥቃይ ካሳለፈች በኋላ እንደገና ከእኔ ጋር ትገናኝተን በአሁኑ ጊዜ እጅግ የማከብራትና የምወዳት ባለቤቴ ነች!! »

«የወላዲተ አምላክ ያለህ! ምን? ምን አልክ አንተ!?» ብሎ እንደ ብራቅ ጮኸ፡፡ «የወዲያነሽ ሚስቴ ነች፡፡ የምንኖረውም አብረን ነው!» ብዩ በተመሳሳይ ጩኸት መለስኩለት፡፡

ከመቀመጫው ላይ በቁጣ ተነሥቶ «ውጣ! ውጣልኝ! ቅሌታም ክብረ ቢስ! ዘር አሰዳቢ! እንዴት አንተ! መድኃኒ ዓለም ያዋርድህ! ኧረ ሂድልኝ! አረ
ውጣልኝ! ክብረ ቢስ ዘር አሰዳቢ!» ካለ በኋላ ማንቁርቱን የታነቃ ያህል ድምፁ እየሰለለ «አንዳንድ ያልተባረካ ሽንት ይኸው ነው! ያህያ ሥጋ...» ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ፊቱ ፍም መስሎ ተጨማደደ፡፡ ጭንቅላቱ ላይ በመሸጎሪያ እንደ ተመታ ሰው መኻል አናቱን በቀኝ እጁ መዳፍ ጫን ብሉ አቀርቅሮ ተቀመጠ።
እውነት በዙሪያው ተጎማለለች! ከአጭር የዝምታ ቆይታ በኋላ ዐይኑ ቀይ ሽንኩርት መስሎ እንደ ሰካራም ተግተርትሮ ተነሣና «ሰበብ አትሁንብኝ! ካህያህም ከውርንጭላህም ጋር ገደል ግባ!! » ብሎ ወደፊት ራመድ አለ።
አልተነቃነቅሁም፡፡ አልተጠጋም፡፡ ነገር እንደሚያጣራ ሰው ከወደ ትከሻው ሰገግ ብሎ አንገቱን ሰብሮ ቆመ፡፡ በቁጣ የታግለበለበው ደሙ በግንባሩ ላይ አሽቆለቆለ። ፊቱ የጋለ የመቆስቆሻ ብረት መሰለ። እህቴና እናቴም ቁንጢጥ እንደ ተጠሩ
ሕፃናት ተርበተበቱ። ጋሻዬነህ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ጨምድዶ ያዘኝ።

ልጄን በተዝናና ወኔ አቅፌ «አዎ ብትወዱም ብትጠሉም የወዲያነሽ ባለቤቴ ናት! ሕዝብ አሕዛብ እንዲሰማና እንዲያውቅ አደርጋለሁ፡፡ የሀብታምና
የከበርቴ ልጅ ብትሆን ኖሮ ይህ ሁሉ የተቃለለውና የተዋረደው አጥንቷ ልዩ ስምና ክብር ይሰጠው ነበር። እንኳን እናንተ እኔ ራሴ የገፈፍኳትንና የነጠቅኋትን
መብትና ነጻነት ታገኛለች፡፡ ይህ የውዴታ ጉዳይ አይደለም። ጤዛ የምታህለዋን ጣጣ ስትፈሩ ተራራ የሚያህል መከራ ይጠብቃችኋል። አሁንም በድጋሚ የማረጋግጥልህ የወዲያነሽ የምወዳት ባለቤቴ ናት:: የአብራኬ ክፋይ! የጋሻዬነህ
እናት ናት!» ብዩ ተጎማለልኩ።

«በሕግ! በሕግ አምላክ ውጣልኝ! ዛሬ ጉድ ይፈላል! አስወጡልኝ
ብያለሁ!» ብሎ ተመልሶ ተቀመጠ የትንሽ ትግል ፍጻሜና የአነስተኛ ፍልሚያ መደምደሚያ ሆነ፡፡
ጋሻዬነህን ይዤ ወደ ውጭ ስወጣ የወዲያነሽ ከምድር ቤቱ በር አጠገብ ከለል ብላና ዐይኗን በድንጋጤ በሰፊው ከፍታ «ምናሉህ? የእኛ ነገር እንደምን
ሆነ? ፍሬ ነገሩ አይሰማም እንጂ ስትጫጨሁ ነበር» ብላ ፍርሃት በተጠናወተው መልስ ጠባቂ ስሜት ጠየቀችኝ፡፡ ሁሉም ነገር እንዳሰብኩትና እንደ ፈለግሁት
ሆነ። ፍርሃትንና የበታችነትን እንዲሁም የሕሊና ባርነትን ተቋቁሜያቸዋለሁ፡፡
እንዲያውም እየደመሰስኳቸው ነው። አትፍሪ! እኒ ምንጊዜም ቢሆን አብሬሽ አለሁ። የሚለያየን ምንም ኃይል አይኖርም፡፡ የእኒንና የአንቺን ዘላቂ አንድነት የሚጠሉና የሚቃወሙ ሁሉ ጠላቶቻችን ናቸው። እንዳንቺ በመከራ ማጥ ውስጥ የሚሠቃዩና የተበደሉ ሁሉ አብረውን ይቆማሉ፡፡ በአባቴ ቤት ብቻ ሳይሆን በመሰሎቹ ፊት ሁሉ እየቆምን ማንነታችንን እናስመሰክራለን። ይህ ከትልቁ
ዓላማና ረጂም ግብግብ ውስጥ ቅንጣቱ ቢሆንም ከእኛ ጋር ላለችውና ወደፊት ይበልጥ እየደመቀች ለምታይለው እውነት አንድ ርምጃ ነው:: ነይ እንሒድ!
ከእንግዲህ እኔና አንቺ የምናጠቃውም ሆነ የምንከላከለው በአንድነት ነው» ብዩ ቀኝ እጅዋን ይዤ ከምድር ቤት ወጣን።

እባክህ ይቅርብህ! በዘመድና በሽማግሌ ይሁን። በዚሁ ወደ ቤታችሁ ሒዱ» ብላ የውብነሽ በተሰበረ ሕሊና ለመነችኝ፡፡
ፊቴን በቁጣ ከሰከስኩና "የመጣንበትን ጉዳይ ከፍጻሜ ሳናደርስ አንሔድም። ከእንግዲህ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አንመለስም። እንደ ዛፍ ቀጥ
እንጂ እንደ ምድር እንቧይ አፈር መሳስ የለም፡፡ ይዣት እገባለሁ። የዛሬዋን ዕለት ዕቅዴን ከፍጻሜ አድርሼ በሙሉ የሕሊና ነጻነትና ድል እንመለሳለን ዕቅዱን ነገርኳት አመዳይ እንደ መታው እህል ገረጣች።

የወዲያነሽ የንግግራችን ጠቅላላ ይዘት ስላልገባት የውብነሽ ምንድነው የምትልህ?» ብላ ትኩር ብላ አየችኝ:: አቅጣጫችሁን ለውጡ፡፡ መሬት ሳሙ፡ ጫማ ላሱ ነው የምትለን፡፡ እኔ ግን መሽቆጥቆጥ ይበቃናል፡ ለሥቃይሽና ለበታችነትሽ የማብቂያ ድንበር እንሠራለታለን፡፡ የራሣችንን መብት በትግል
ማሳወቅ እንጂ መለመንና ማጎብደድ የለብንም። የሚበድሉንና የሚጨቁኑንን
ሁሉ እውነትን ይዘን እንጋፈጣቸዋለን እላለሁ:: እኔ የአንቺን የየወዲያነሽን ያህል
ያልተበደልኩና ያልተጨቆንኩ ብሆንም በአዕላፋት የጠላት ሠራዊት መካከል አንዱን ብቻ መግደል ጠላትን ድል ”ማድረግ አይደለም። ቢሆንም » ብዬ ገና
1👍1
በማለቱ እንዳይብስበት ፈራሁና ከፊቱ ዘወር ብዬ ሁኔታውን በቅርበት እከታተል ጀመር፡፡ «አ..ት.ጠ.ጋ..ኝ!» አለ ከሩቅ የሚሰማ በሚመስል ድምፅ
እዚያው የቆምኩ መስሎት። ዐይኑ እንደ በፊቱ ወደ በዶው ግድግዳ ማተኮሩን ስመለከት
ውልብ ማለቴን እንጂ እኔን ሊያየኝ እንዳልቻለ ወዲያው ገባኝ፡፡ አባቴ : ከመቼውም ይልቅ ደም ብዛቱ መጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሶ ዳዊት ሲያነብ በኖረባት ክፍል ውስጥ ዐይኔ እያየው መታወሩን ተገነዘብኩ። እጅግም ሳይቆይ
አቅም የከዳው ግዙፍ ሰውነቱ ሽምድምድ አለና እንደ ተደገፈ ተዝለፍልፎ እዚያችው ከድንኳ አልጋ ላይ ወደቀ።

በሦስተኛዉ ቀን ቀብሩ ላይ ተገኘሁ፡፡

💫ተፈፀመ💫

#የወዲያነሽ በዚህ ሁኔታ ተፈፅሟል እንዴት አገኛችሁት አስተያየታችሁን እንደተለመደው ታች ባለው አድራሻ አሳውቁኝ እኔ በሌላ ድርሰት እመለሳለሁ አመሰግናለው።

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍3