#የወዲያነሽ
፡
፡
#ክፍል__ሰላሳ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በሐይለመለኮት_መዋል
....እናቴ አዘኔታ በሚታየበት ፊት ወደ እኔ መለስ አለችና ሞኝነትህ፣ ሞኝነትህ ነው ልጄ! 'አይዞሽ ግድ የለሽም' ብለህ ይዘሃት ና፡፡ እኔ እናትህ አሳምሬ እቀበልልሃለሁ። አትፍሪ! አትፍሪ ነዪና እንታረቅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ እኔና አንቺ እናትና ልጅ ነን፣ ልጄ ልጄ ብላሻለች” ብለህ አሳምረህ ንገርልኝ በማለት ያን በውስጤ ሲገላበጥ የዋለ ሥጋትና የመንፈስ ሽብር ገደለችልኝ
እናቴ ጋሻዬነህን ፍለጋ መልከት መልከት ስትል እንቅልፉ ሊጥለው ሲያንጎላጅ
አየችውና «አፈር በበላሁት! ልጄን! ልጄን! ያቺ እናትህ እንኳን አላየች!» ብላ
ካነሣችው በኋላ እግሩን እያንዘላዘለች ወደ የውብነሽ መኝታ ቤት ይዛው ገባች::
የእናቴ እግር ወጣ እንዳለ የውብነሽ ድንገት ብድግ ብላ አለቀ! ጨብጠኝ
ወዳ አይምሰልህ የግዷን ነው» ብላ ደስታዋን ገለጸችልኝ።
«አዎ ከእንግዲህ ደግሞ አንድ አስቸጋሪና የለየለት ግብግብ ብቻ ይቀረኛል» ብዬ መለስኩላት
የወዲያነሽ ምነው ቆየህ? ና እንጂ ጌታነህ! ቁርጤን ልወቅ? የምትል
መሰለኝ፡፡ ሰዓቴን ብመለከት ዐሥራ ሁለት ሰዓት አልፏል። እናቴ ከተቀመጠች
በኋላ ጥያቄና መልስ ቀጠለ። ከመጠን በላይ ተዝናናሁ፡፡ መላ አካላቴ
ተንፈላሰሰ፡፡ የወዲያነሽን ሥቃይና መከራ ባጭር ባጭሩ አንዲትም ሳላስቀርና
ሳልዘነጋ እንደ ተረት ነጋሪ አሳምሬ ወጣሁላት። የእኔንም ልፋትና ውጣውረድ
ሁሉ ገለጽኩላት፡፡ ንግግሬን እንደ ጀመርኩ ፊቷ ትንሽ በትንሽ ጠወለገ፡፡ እንባዋ
እየተሽቀዳደመ ሲወርድ ማዘንና መፀፀቷ ገባኝ። የእናቴ ርኅራኄና ገራገርነት እንደ ኮረብታ ጎልቶ ታየኝ፡፡ በኀዘን ጠውልጎ በእንባ የራሰውን ጉንጯን በማየቴ
በጣም ረካሁ፡፡ በሕዝብ ኃይል ሥልጣን እንደ ያዘ መንግሥት ደስ አለኝ።
የወዲያነሽም ድል ስታደርግ ወለል ብሎ ታየኝ፡፡
«አሠቃይቻታለሁ በቁሟ ቀብሪያታለሁ» አለችና ልቅሶዋን ቀጠለች።
«ያለፈው አልፏል ከነገ ጀምሮ ታርቃችሁ ተፋቀሩ እንጂ እሷ በበኩሏ ሁለንም
ነገር ይቅር ብላ ትታዋለች በጣም እኮ ነው የምትወድሽ» ብዬ ትካዜዋን ለማቅለል ሞከርኩ፡፡ ሙሉ ፈገግታዋ ሳይመለስ ለመሄድ ተነሣሁ፡፡ «ጋሻዬን አምጪልኝ የውብነሽ!» አልኳት፡፡
«አንት ጨምላቃ ጨመለቅ! እኔ እጅ ገብቶ ነው የምትወስደው?ባይሆን እንኳ ዋንየዋ ከመጣች በኋላ የሆነው ይሆናል!» ብላ ቱግ አለች። ልቤ ጮቤ ረገጠች፡፡ ተደሰትኩ እንጂ አልከፋኝም፡፡ የወሬ ሠንጋ ጥለን ስናወራርድ ሁለት ሰዓት ተኩል አለፈ። የውብነሽን ለብቻዋ ጠርቼ «ነገ አራት ሰዓት እንድትመጪ» አልኳትና «ደኅና እደሩ» ብዩ ወጣሁ፡፡
የቤቴን አጥር ግቢ ከፍቼ ስገባ የወዲያነሽ ጋቢዋን ለብሳና የሰበሰቡን አግዳሚ ተደግፋ ስትጠብቀኝ ደረስኩ እንደ ወትሮዋ ነቃ መብላት ስላልተቀበለችኝ
አእምሮዋ በሐሳብ ጉልበቷ በመቆም እንደ ተዳከሙ ገባኝ። እጅዋን ያዝ አድርጌ ዐይን ዐይኗን እያየሁ አመሸው እንዴ የወዲያ ደስ ይበልሽ! ደስ ብሎኛል
የሄድኩበት ጉዳይ ተሳክቷል» አልኩና በምሽቱ አየር የቀዘቀዙ ጉንጮቿን ሳምኳቸው፡፡
«እንኳን ደኅና መጣህ? እንኳን ደስ ያለህ? ጋሻዬስ? ከእጅህ ላይ ሳጣው ጊዜ አፌ ተሳሰረ» አለችና በልከኛው የመብራት ውጋጋን ውስጥ ትክ ብላ ተመለከተችኝ፡፡ ተያይዘን ከገባን በኋላ እንዴት ብዬ ልግለጽልሽ? እናቴ በጣም ተደሰተች። ምነው የዛሬዋ ዕለት የሁለትና የሦስት ቀን ያህል በረዘመች ! ስለ አንቺና እኔም አንዳችም ሳላስቀርና ሳልደብቅ ነገርኳት። በጸጸት ተቃጥላ እንባ በእንባ ሆነች። ርኅራኄዋንና የእናትነት ልባዊ ፍቅሯን ለማግኘት ችያለሁ፡፡በመጨረሻ ግን ጋሻነህን ልውሰድ ብዬ ብጠይቅ አፈን አስያዘችኝ፡፡ «እሷን እዚህ ይዘህ መጥተህ ይቅርታ አድርጊልኝ ብዬ ሳንታረቅና እንደ እናትና ልጅ ሳንሳሳም፣ ልጅ የሚሉ ነገር አልሰጥም ብላ ማለች» ብዪ ጋሻዬነህ የቀረበትን ምክንያት አብራራሁላት፡፡
የወዲያነሽ እውነት ስላልመሰላት «መቼ ሥራ አጡና! እንኳን ጥራትና አምጣት ሊሉህ ይቅርና ይህንኑ ዐይኗን እንዳታሳየኝ ብለውህ ይሆናል፡፡ ያንተን ሥራ መች አጣኋትና! ታዝናለች፣ ይከፋታል ብለህ ነው:: አትጨነቅ ቢከፋኝስ ምን እንዳላመጣ ነው? አጀብ እቴ ! ያም ሆነ ይህ እንኳን ደስ ያለህ» ብላ አሻግራ ስትመለከት «አምጪ እጅሽን፣ የወዲያነሽ ሙች! » ብዩ ለእውነተኛነቴ ማረጋገጫ እንዲሆን እጅዋን ስቢ ጠፋሁት፡፡
ከጥቂት ቆይታ በኋላ ራት አቀረበች። ሆዴ በቀኑ ምግብ ደስታና ፈንጠዝያ በመጎሰሩ ምንም አላሰኘኝም፡፡ የወዲያነሽ «በቃኝ! በቃኝ!» እስከምትል ማጉረስ በመቻሌ እንደገና ደግሞ አጋጣሚው አስደሰተኝ። ከራት በኋላ ከቀኑ ወሬ ውስጥ ቀነጫጭቤ አወራሁላት። በጥርጣሬና በሥጋት ታፍኖ የነበረው አእምሮዋ ገለጥለጥ ስሳለላት ጥርጣሬዋ ከላይዋ ላይ በንኖ ጠፋ፡፡
«እኔ በበኩሌ ቂም የሚሉ ነገር አልያዝኩም፡፡ ላንተ ስል ሁሉንም ነገር ትቼዋለሁ፡፡ የፈራሁትና የሠጋሁት አሻፈረኝ ይላሉ ብዬ ነው እንጂ፣ እሺ ካሉንማ ምን ቆርጦኝ። ጫማቸው ላይ ወድቄ ይቅርታ አድርጉለኝ ብላቸው ምን ነውር አለበትና ነው?» በማለት እቅጩን ነግራኝ ወደ መኝታ ቤት ገባች። መላ ሰውነቴ ጥርስ አውጥቶ ሣቀ፡፡ ተከትያት ገባሁ። ምንጊዜም ከዚያ ቀደም ወስዶኝ በማያውቅ ሁኔታ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ፡፡ እውነተኛ ፍቅርና የሕሊና ጸጥታ ምንኛ ሰላም ይሰጣሉ!
የወዲያነሽ ቀኝ እጅዋን በብርድ ልብስ ውስጥ አሾልካ ግንባሬን
እየዳበሰች «እንዴ? የዛሬውስ እንቅልፍ ለብቻው ነው፣ ለጤና ያድርግልህ» ብላ በማያስደነግጥ ሁኔታ ባትቀሰቅሰኝ ኖሮ ተኝቼ አረፍድ ነበር። ከአንገቴ ቀና
ብዬ «ረፍዷል እንዴ? ስንት ሰዓት ሆነ?» አልኳት፡፡ ሰዓቷን አየት አድርጋ «ሦስት ሰዓት ከሐያ አምስት» ብላኝ ሄደች።
በመስኮቱ በኩል የገባው የረፋዷ ፀሐይ ጮራ ክፍሉን አወግጎታል።
ተጣጥቤና ለባብሼ ለመቀመጥ ቸኮልኩ፡ ሠራተኛይቱ ያመጣችልኝ ሽግ ያል ውሃ ደህና አዝናናኝ፡፡ ጊዜው በመገሥገሡ ተደሰትኩ በእናቴ ፊት «የሚያስከብረኝን» ልብስ ለብሼ ስጨርስ አራት ሰዓት ተኩል አለፈ፡፡
የወዲያነሽ ከፊት ለፊቴ ቆም አለችና ምን ዓይነት ልብስ ልልበስ? እስኪ ንገረኝ?» ብላ ዐይኖቼን በዐይኖቿ አቆላመጠቻቸው ደረቷ ላይ ዠቅ
ያለውን ሐብልና መስቀል እየተመለከትኩ «መጨነቅና መጠበብ አያስፈልግም የአንቺ መጎናፀፊያና ግርማ ሞገስሽ የሰው ልጅነትሽ ብቻ ነው። የሐር ድርብና የወርቅ ቁርጥራጭ አይደለም፡፡ ይህን የአጣና ያአገኘ የመለያ ምልክት በግብግብ
እናስወግደዋለን። ደስ ያለሽን ልበሽ?» አልኳት። ባለ ወይን ጠጅ ጥለት ኩታና ቀሚስ ለብሳ፣ ተረከዘ
አጭር ጫማ ተጫምታ ጸጉሯን በቀላሉ ጎነጎነችው፡፡
ምንም እንኳ ቀደም ሲል በሕወይቷ ላይ በደረሰው ተደጋጋሚ ችግርና የሕሊና
ሥቃይ የተነሣ አካላቷ ሲፈካና ሲጠወልግ፣ ሲከሳና ሲኮስስ ቢኖርም፣ የወዲያነሽ በአሁኑ ጊዜ በምቹ ቦታ ላይ በቅላ በማለፊያ ዳስ ላይ እንደ ተንሰራፋች የወይን
ተክል ሐረግ ቀስ በቀስ አምሮባታል።
የችግርና የሠቀቀን ኑሮ ያሟሰሰው ለዛና ዛላዋ፣ ውበትና ደም ግባትዋ
እንደገና እንደ ሐምሌ ጎርፍ እየሞላ፣ እንደ መስከረም ወንዝ እየጠራ፣ እንደ ጥቅምት አዝመራ አሺቷል። ከአገርና ከሕዝብ መኻል በተለይ ተመርጣ የምትጠቀስ ልዩ ቆንጆ ባትሆንም የወዲያነሽ የምትኮክብ የውበት ጉልላት
ሆነች። ጠበብ ካለው ግንባሯ ግርጌ ከቅንድቦቿ ድባብ ሥር ያሉት ተንተግታጊ ውብ ዐይኖቿ ከሥጋ ቅምር ሳይሆን ከሚጨበጥ ንጥረ ብርሃን የተሠሩ መሰሉ፡፡

👍5❤1