#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
...እንዲህ እንዳይመስሉሽ። ኸግር እስተራስሽ እያገላበጡ ነው ሚያዩሽ።ቄንጥ ሲያወጡ አይጣል ነው” ሲሉ መከሯት።
“እሚታዬ ልቤ ፈራ” አለቻቸው፣ እጆቿን እያፍተለተለች።
“ምን ሚያስፈራ ነገር አለ?” አሉ፣ ቆጣ ብለው። ለራሳቸው፣ እንደዛ
ቆፍጣና ምትመስለኝ ልዥ ምን ሆነች? ማታውቀው ቦታ ስለምትኸድ ነው? አሉና ለእሷ፣ “አብሬሽ ማዶል እንዴ ምመጣው? ንጉሥ የሆኑ እንደሁ ልዣችንን እንዳው ዝም ብለን ምንሰድ ይመስልሻል? ጐንደርንም ቢሆን አገላብጨ ነው ማውቃት። ጃንሆይ ሳይነግሡ በፊት... ነፍሳቸውን ይማርና ኸነእንኰዬ አባት ጋር ኑረናል። ጃንሆይ ኸነገሡ በኋላ አልኸድኹም እንጂ” አሏት።
“አብረሽኝ ምትመጪ ባትኾኚ ምን ይውጠኝ ኑሯል?” ብላ፣አንገታቸው ሥር ገብታ ሳይታሰብ ተንሰቀሰቀች። ውስጥ ውስጡን
ያስለቀሳት ግን ከጥላዬ መለያየቷ ነው።
“ደሞ ለክፉ ሆነ ለደግ ግዝየ ሚሆን ወልደልዑልን የመሰለ ወንድም አለሽ። ስንኳን ላንቺ ለእህቱ፣ አላየሽም እንዴ ላገር ሲተርፍ? አርከሌድስም አለ። ልዤ ነው ብዬ ማዶል ። አንቺም ብትሆኚ ታውቂያሽ እንዴት ብርቱና ታማኝ እንደሆነ። እንደ ኒቆላዎስስ ቢሆን... ጋሻና መከታ እንደሚሆንሽ አንቺም ታቂያለሽ” አሉ፡ ደረታቸውን መታ፣ አንገታቸውን ነቀነቅ አድርገው።
ምንጊዜም ቢሆን ስለሚወዱት ታናሽ ወንድማቸው ስለኒቆላዎስ
ሲያወሩ ደስ ይላቸዋል፤ ይኮሩበታል ። ቀጠለና፣ “አጎትሽ እሽቴም አለ። ደሞስ ያጎቶችሽ ልዦች ጌታ፣ አውሳቢዮስና፣ ነጮ አሉ ማዶል እንዴ? የወገን ጥላ አያሳጣኝ ማለት ነው” እያሉ እንባዋን በነጠላቸው ከፊቷ
ላይ ጠራረጉላት።
“ግና የቤተመንግሥት ወግ ኸየት አባቴ አውቄ?” አለች።
“አንቺ ደሞ ያልቸገረሽን። ወጉንስ እኼው እያስተማርሁ ማዶል
እንዴ? ሌላውን ደሞ ግዝየው ሲደርስ ትማሪያለሽ።”
“እሚታዬ፣ ቤተመንግሥት ልገባ?”
“ቤተመንግሥት ለመግባት ምን ያንስሻል? አጥንተ ጥሩ... ያውስ
የንጉሥ ዘር ማዶለሽ? አባትሽስ ቢሆኑ የደንብያው ባላባት የአቤቴ
ተክለሃይማኖት ልዥ ማዶለ? መልክስ ቢሆን ማን ደረሰብሽ? ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም ይላሉ፤ አንቺ ፈጅተሻል። ቅላትሽ እኮ የኔና የናትሽ ነው። እንዳባትሽ ጠይም ብትሆኚ ኑሮኮ ምን የመሰለች ጠይም አሳ መሳይ ትሆኚ ነበር። ምግባርና ብሩህ አይምሮም አክሎልሻል።
ለዝህም እኮ ነው ጃንሆይ የመረጡሽ። እቴ ኸንግዲህ ማቄን ጨርቄን የለም፤ መኸድ ብቻ ነው።”
“ልጄ ዕድል ነው። ተሰጥቶሽ ነው። ደግ ሁኖልሻል፤ ሁሉን
አብዝቶልሻል” አሏት፣ እስከዛ ድረስ እናታቸው የሚሉትንና
የሚያደርጉትን በፀጥታ ሲታዘቡ የቆዩት እናቷ።
“የምን ዕድል ነው ምትይ? ዕድል ከሰማይ ይወድቃል? እንዲሁ
ነው እንዴ ንጉሡ ልዣችንን ሊያገቡ የፈለጉ? ልዣችን ሚገባትን ነው ያገኘችው። በደም ግባቷ፣ በብሩህ አይምሮዋ፣ በመልካም ምግባሯና
ጎንበስ ቀና ብላ ስላስታመመቻቸው ነው ንጉሡ ለንግሥትነት የመረጧት፣ ንግሥትነት እንደሚገባት አይተው መዝነው ነው እንጂ እንደ መደዴው ለውበቷ ወይም እንደገበሬ ለሙያዋ ብቻ ብለው
አይደለም።” ዮልያና ልጃቸውን ቆጣ አሉ።
“መቸም ደመ ግቡ ሁሉ... ያስታመመ ሁሉ ንጉሥ ባል አያገኝም። እንዳው የዕድል ነገር ይገርማል። እኼን ማን አሰበው?” አሉ፣ የእናታቸውን አፍ ብዙም የማይዳፈሩት ወይዘሮ እንኰዬ።
“የኔ ልዥ ገና ንግሥት እሌኒን አረግሻለሁ” አሉ፣ አያትየው።
“እሳቸውን መሆን እንዴት ይቻለኛል?”
“አንቺ ደሞ... እሌኒን ትሆኛለሽ ስልሽ እኮ ልክ እንደሳቸው ሁኚ
ማለቴም ማዶል። እንዴት እንደምኖሪ ማወቅ ያንቺ ፈንታ ነው። ሁሉ እየቅል ነው።”
ለጊዜው የአያቷ ምክር በመጠኑም ቢሆን አረጋጋት።
በነጋታው መንገደኛ ናትና ጥሩ እንቅልፍ እንድታገኝ እናትና አያት
ትኩስ ወተት በማር አጠጥተው አስተኟት። እሷ ግን እንደ ትናንቱ
ሁሉ ዛሬም እንቅልፍ በዐይኗ ሳያልፍ ፍርሐት፣ ጥላዬን ለመጨረሻ ጊዜ ሳታየው የመሄድ ጭንቀት፣ ብሎም ቀስ እያለ ውስጧ እየተጫረ የመጣው ቤተመንግሥት የመግባት ጉጉት መሳይ ነገር ሲፈራረቁባት
ሌሊቱ እንደመንጋት አለ።
ዶሮ ሲጮህ ቀሰቀሷትና ተጣጠበች። ቁርስ ብዪ ብለው ሲያቀርቡላት ግን ተናነቃት። እናቷ፣ “ትንሽ አፍሽ አርጊ፤ ምንገድ ባዶ አፍ አይከድም” እያሉ ሊያግባቧት ሞከሩ። እሷ ግን እንኳን እናቷን፣
አባቷን፣ ወንድሟን፣ ጥላዬንና የቤት አገልጋዮቹን ቋራን ራሱን ጥላ መሄዱ ዳገት ሆነባት።
ዐይኗ እንባ አቀረረ።
የእናቷን ፊት የተጫጫነውን ሐዘን ስታይ፣ ዐይኖቿ ጥግ ተጠልሎ
የነበረው እንባዋ ወደ ጉንጮቿ ኮለል አለ። እናቷ እስከዛ ሰዐት አምቀውት የነበረውን እንባ እንደ ድንገተኛ ዝናብ አወረዱት። ጉልበታቸው ላይ ተደፍታ፣ “እነየ መተሽ አታይኝም?” ስትላቸው፣ ትከሻዋ ላይ ተደፍተው
እዬዬ ሲሉ እሷም ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።
አያትየው ልጃቸውን፣ “እንደማበርታት ጭራሽ ታባቢያታለሽ?” ብለው ቆጣ አሉና፣ ወለተጊዮርጊስን ትከሻዋን ነካ አድርገው፣ “ተይ እኮ የኔ ልዥ፣ በቅጡ እንዳልተኛሽ ስንኳ ያስታውቃል። ምንገደኛ ነሽ። ገና
ምንገዱ ሚያጠወልግሽ ይበቃል። ፊትሽን አታበላሺ። የቀባሁሽንም
ኩል እንባሽ አጠበው። በቃ እንድች ብለሽ እንዳታለቅሺ። በይ ነይ” አሉና ፊቷን በእጃቸው አባብሰው፣ እንደገና ሥር ኩል ዐይኗ ላይ አደረጉላት።
እንግዶቹ እህል አፋቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለመሄድ ወደ ውጭ ሲወጡ በአቅራቢያ ያለ ቤተዘመድ፣ የወለተጊዮርጊስን ጐንደር መሄድ የሰማ
ጎረቤትና ጓደኞቿ ተሰብስበዋል። ወለተጊዮርጊስ የአያቷን ረጅም የሐር ቀሚስ ለብሳ፣ ከቀሚሱ ሥር በሐር ክር ጫፉ የተጠለፈና ተረከዟን ጠበቅ አድርጎ የያዘ ሱሪ ታጥቃ፣ በአያቷ ወርቅ አሸግና ብቅ ስትል፣እንግዶቹ ትንግርት እንጂ እውን ሰው የሚያዩ አልመስል አላቸው።
ዘመድና ጎረቤት ግቢውን በዕልልታ ሲያደምቀው፣ የወለተጊዮርጊስ ጓደኞች ዐይናቸው እያየ በጓደኛቸው ሕይወት ውስጥ ያልገመቱት
ዓይነት ለውጥ መምጣቱ፣ ካጠገባቸው ተነስታ ለንግሥትነት መታጨቷ አስደነቃቸው። በዓመት መለወጫ ቀን አደይ አበባ እያስቀጠፈች፣ከቤት ቤት በድፍረት ይዛቸው እየዞረች፣ የምታስተባብራቸውና እንደ
መሪያቸው የሚቆጥሯት ጓደኛቸው ከመሃከላቸው በመለየቷ አዘኑ፤
በታላቁ ዕድሏ ቀኑ፣ ተደሰቱ። በዚኹም ድብልቅልቅ ስሜት መሃል ግን በመለያየታቸው አለቀሱ።
ግራዝማች የልጃቸውን ውበት ገና ያን ቀን ያዩ ይመስል ዐይናቸው
ውሃ አቆረ። እሷን ለመሰናበት ማልደው የመጡት ታላቅ ወንድሟ
ወልደልዑል፣ አጎቷ አርከሌድስ፣ የዮልያና ወንድም ኒቆላዎስ፣ አጎቷ
እሽቴና የአጎቷ ልጆች አውሳቢዮስ፣ ጌታና ነጮ በኩራት ተመለከቷት።
ንጉሥ ቤት ነውና የምትገባው በልባቸው ዙርያ የተስፋ ድር አደራችበት።
እናትና ልጅ በሠሩት ጥበብ ተደንቀው ዐይን ለዐይን ተያዩ።
አያትየዋ ያ ሁሉ እንባ ምልክት ስንኳ አልተወም፡፡ ድንቅ እኒያ
ደርሰው ትከሻ ሚሰጡ የጐንደር ወይዛዝርት እንግዲኽ ዐይናቸው
ይደፍርስ አሉ።
ለሱ አይቅርበት አሉ እናትየው፣ እንባቸውን በነጠላቸው እየጠራረጉ።
ጎረቤትና ቤተዘመድ ምርቃት ሲያዘንብላት፣ ዕልል ሲልላት፣ ጓደኞቿ የደስታ እንባ ሲራጩላት፣ ምቀኛው ግን፣ “ታመው የተኙ ግዝየ መዳኒት አርጋባቸው እንደሁ እንጂ ውነት አሁን ንጉሡ…” እያለ ወሻከተ።

#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ባህራም
ከቅርብ
ማክሰኞ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ ከምሳ በኋላ Le Monde ጋዜጣዬን ገዝቼ ካፌ ዶርቢቴል ገብቼ እንደ ልማዴ petit creme አዝዤ ካርታ የሚጫወቱት ሀበሾች አጠገብ ቁጭ አልኩ። ትንሽ ቆይቶ ባህራም መጣ፡፡ ሳየው የተለወጠ መሰለኝ፡፡ ልማዱ በፍጥነት እርምጃው ከተፍ ብሎ ሲያበቃ፣ ሀበሾቹን «እናትክን! ሀለላሴ ሙት! Je veux jouer
aux cartes.» («ካርታ አጫውቱኝ») ብሎ ቁጭ ማለት ነበር፡፡ ዛሬ ግን በቀስታ እርምጃ መጣ። እንደ ድሮው አልቀለደም፡፡ እንደ አጋጣሚ ለካርታ ጨዋታው አንድ ሰው ጎድሏቸው ስለነበረ «ባህራም! ና ካርታ እንጫወት አሉት
«ካርታ ጨዋታ አላሰኘኝም» አለና ዝም ብሎ ቁጭ አለ።
የተበሳጨ ይመስላል
«ምን ሆነሀል?» አለው ሉልሰገድ
«በፈተና ወደቅኩ» አለ
ሁሉም የሚሉትን አጡ
እንግዲህ በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲዎች ደምብ፣ አንድ ተማሪ የሰኔ ወር ፈተናውን የወደቀ እንደሆነ በእረፍት ጊዜው ሲያጠና
ይከርምና፣ በጥቅምት (ትምህርት ቤት ሲከፈት) እንደገና
ይፈተናል። ስለዚህ ተመስገን
«አይዞህ በጥቅምት ፈተና ታልፋለህ» አለው ባህራም አልተፅናናም፡፡ ሁሉም ዝም አሉ። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ።
ባህራም «ዘላለም ካርታ ጨዋታ ምን ያረጋል? እንውጣ ትንሽ
እንንሽርሽር» አለ። ማንም መልስ አልሰጠውም፡፡አብረውት
መውጣት ፈርተዋል። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ ለጨዋታው
ብቻ ሳይሆን ከባህራም ብስጭት ለማምለጥም ጭምር። ገባው::
ተነስቶ ብቻውን ወጣ፡፡ ተከትዬው ወጣሁ። ወደ መናፈሻው በኩል
እያመለከትኩ
«ወደዚያ እንሂድ?» አልኩት፡፡ መልስ ሳይሰጠኝ ወደዚያው
አመራ። ትንሽ እንደተራመድን
«ያውና ተካ። ወደኛ በኩል ይመጣል» አለኝ «አደራህን አብሮን እንዳይመጣ። ዛሬ እሱ ሁለት ቃላት ቢያናግረኝ አብዳለሁ»
«አትስጋ» አልኩት
ተካ አቆመንና በፈረንሳይኛ
«ከየት ነው የምትመጡት?» አለን
«አሁን ከየትም ብንመጣ ደንታ የለህ። ለምንድነው የምትጠ
ይቀን?» አልኩት በአማርኛ
«ከዶርቢቴል ነው የምትመጡት?» አለኝ ባማርኛ
«አዎን» አልኩት ባህራም እጁን ኪሱ ከቶ ወደዚያ ይመለከታል
«ወዴት ነው የምትሄዱት?» አለኝ ተካ
«ወዴትም፡፡ ምን ያረግልሀል?»
«ወደ ሲቴ ነው የምትሄዱት?»
«ምነው? ከኛ ጋር ሲቴ መሄድ አማረህ?»
«አይ! እኔ ለራሴ ከዛ መምጣቴ ነው። ቡና አምሮኛል»
«እንግዲያው ሂድና ቡናህን ጠጣ»
«ጋዜጣህን አሁን አታነበው እንደሆነ ስጠኝ»
ጋዜጣዬን ሰጠሁትና መንገዳችንን ልንቀጥል ስንል
«ይሄ አቃጣሪ ገንዘብ እንዳያጭበረብርህ ተጠንቀቅ» አለኝ
«ሂድ ቡናህን ጠጣ» እልኩት። ሄደ
እኔና ባህራም አንድ ቃል ሳንነጋገር መናፈሻው ደረስን፡፡ ዛፎች
ጥላ ስር አንድ አግድም ወምበር ላይ ቁጭ አልን ፈተና መውደቅ የተለመደ ነገር ነው:: በጥቅምት ታልፋለህ» አልኩት
በተገማመደ ፈረንሳይኛው፣ በወፍራም ልዝብ ድምፁ መናገር
ጀመረ መውደቄ አይደለም የሚያበሳጨኝ፣ አወዳደቄ ነው።
ትምህርቱን በደምብ ይዤዋለሁ። በምን እንደጣሉኝ ታውቃለህ?
በፈረንሳይኛዬ ጉድለት: አያስቅህም? ፈተናውን የወደቅኩት እኔ ራሴ ባልሆን ያስቀኝ ነበር
«እኔንና ፈረንሳዮቹን የክፍሌን ልጆች አስተያየን እስቲ፡፡
ትምህርቱን እኩል እናጠናቀው። ፈተና እንግባና ጥያቄው ይሰጠን።
መልሱን እኔም እነሱም እኩል እንወቀው። እነሱ ምን ያረጋሉ?
መልሱን በፍጥነት ይፅፋሉ፡ አሰካኩንና አገባቡን ያማርጣሉ፡፡
ጥቃቅኗን ነገር ጭምር ያስገቧታል፡፡ ሀያ ሀያ አንድ ገፅ ፅፈው ይወጣሉ፡፡ ያልፋሉ፡፡ እኔም መልሱን ከነሱ እኩል አውቀዋለሁ፡፡
ታድያ ፈረንሳይኛው ከየት ይምጣ? ከሱ ጋር ስታገል የጊዜዬን
ግማሽ አጠፋለሁ:: ለዚያውም አምጩ የማመጣው ፈረንሳይኛ አንካሳ ሽባ ስለሆነ፣ በደምብ የማውቀውን መልስ ልክ እንደማላውቀውና
በግምት ወይም በነሲብ እንዳገኘሁት ያስመስልብኛል። ዘጠኝ አስር ገፅ ፅፌ እወጣለሁ፣ በመጥፎ ፈረንሳይኛ፡፡ ትምህርቱን እያወቅኩት ፈተናውን እወድቃለሁ
«ፈረንሳዮች ደሞ ታውቃቸዋለህ። በቋንቋቸው የመጣ በጣም
አንጎለ ጠባብ ናቸው። ለምሳሌ አስተውለህ እንደሆነ በፍጥነትና ያለ ስህተት ያነጋገርካቸው እንደሆነ ያከብሩሀል፣ «Intelligentይሉሀል።
እየተንተባተብክ ያነጋገርካቸው እንደሆነ ግን ምንም ቁም ነገር
ብትናገር መሃይም ነህ ማለት ነው። በቋንቋህ ብታናግራቸው እንደ ቂል አፋቸውን ከፍተው እንደሚቀሩና፣ የነሱም ቋንቋ ላንተ ያንን ያህል እንግዳ እንደነበረ፣ የሚሉት ሁሉ «ዠቨሹቪ» ይመስልህ እንደነበረ፣ በስንት ልፋት በመጠኑ ልታውቀው እንደቻልክ፣ በቋንቋቸው መንተባተብ ስለቻልክም ሊያመሰግኑህ እንጂ ሊንቁህ
እንደማይገባቸው፣ ይህን ለመገመት ያህል ሰፊ አንጎል የላቸውም።ተራውስ ሰው እንዲህ ቢሆን አልፈርድበትም፡፡ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮቹ እንዲህ ሲሆኑ ግን በጭራሽ አይገባኝም፡፡ እንግዲያውኑ የነሱ ትምህርት የታል? እቺን ያህል ቀላል ነገር ማመዛዘን ካልቻሉ አንጎላቸውስ ትምህርታቸውስ ምን ትርጉም ይኖረዋል?
«እማናውቀው አገር መጥተን፣ በማናውቀው ቋንቋ
የማናውቀውን ህዝብ ባህልና ታሪክ ለመማር ስንታገል፣ ለምን
አስተያየት አያደርጉልንም?»
“ምን አይነት አስተያየት ሊያደርጉልን ይችላሉ?» አልኩት
«ፈረንሳይኛችን ትንሽ የተጣመመ እንደሆነ፣ የቋንቋውን መጣመም ችላ ብለው የፍሬ ነገሩን እዚያ መገኘት ለምን አያስቡልንም? አገራችን ስንመለስ በራሳችን ቋንቋ ነው የምንmቅመው፣ ስለዚህ ፈረንሳይኛውን አንደነሱ ቻልነው በመጠኑ ተንተባተብንበትስ ምን ያህል ልዩነት ያመጣል? እንግዳ ስንሆን፣ ፈረንሳይኛውን በሀያ ሶስት፣ በሀያ አራት፣ በሀያ አምስት
አመታችን ስንጀምረው፣ እንዴት ከናታቸው ጡት ጋር ሲጠቡት
ካደጉ ሰዎች እኩል ካልሆነ ተብለን እንቀጣበታለን? ቅጣት መሆኑ
ይታይሀል? ፍሬ ነገሩን እንደማውቀው ግልፅ ሳለ፣ የተጠቀምኩበት ፈረንሳይኛ የተቀመመ ፈረንሳይኛ ባለመሆኑ ፈተናዬን ስወድቅ፣አንድ አመት ሙሉ የለፋሁበትን ስከለከል፣ ይሄ ቅጣት ነው እንጂ ምንድነው? ፍትህ የሌለው ቅጣት
«አንድ አመት ምን ያህል እንደሆነ ይገባሀል? አስበው፡፡ የዘጠኝ
የአስር አመት ልጆች ሳለን ክፍል በመድገም አንድ አመት ብናጠፉ
ምንም አይደለም፡፡ በህያ ስድስት፣ በሀያ ሰባት አመታችን አንድ
አመት ማጥፋት ግን ሌላ ነገር ነው:: ምክንያቱም እነዚህ አመታት
ከሀያ አምስት እስከ ሰላሳ አምስት ሰፈር ያሉት አመታት የሌሎቹን አመታት ሶስት አራት እጥፍ ዋጋ አላቸው። አሁን ነው ህይወታችንን ለመጨረሻ የምንቀርፀው:: አሁን ነው ያለ የሌለንን ለሀገራችን ልናበረክትላት የሚገባን። አሁን ነው የኑሮ ስራችንን የምንመርጥበት የምንጀምርበት ጊዜ። አሁን ነው የኑሮ ጓደኛችንን
የምንመርጥበት፣ ትዳራችንን የምንቆረቁርበት ጊዜ፡፡ አሁን ነው።
አሁን! አሁን! አሁን ነው ልጅነትም የማያታልለን፣ እርጅናም የማይ
ጫጫነን፡፡ አሁን ነው ፍሬ ለመስጠት ዋጋ ለማስገኘት የምንችለው» ረጋ ባለ ድምፅ
«አሁን ነው ፈረንሳዮች "ለምን ቋንቋችንን ከኛ እኩል
አልቻላችሁም?' ብለው ወርቅማ አመታችንን የሚያጠፉብን

#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...ወጥመድ ውስጥ የገባ አይጥ ማምለጫ አጥቶ ይቅበዘበዛል፡፡ ከድመት ጥፍር ውስጥ የገባ ፍጡር ግን ይበልጥ ይጨነቃል፡፡
ማዳምና ሚስተር ቴናድዬ ምን ዓይነት ሰዎች ይሆኑ?
ምድባቸው እውቀት ኖሯቸው ግን ጊዜ ከጣላቸው ሳይሆን የተናቁ
ሆነው ጊዜ ካነሳቸው ሰዎች ውስጥ ነበር፡፡ ጊዜ ያነሳቸው ሰዎች ጥፋት ቢፈጽሙ የሠርቶ አደሩ ትጋት ወይም የቡርዣው ክብር የተጐናጸፉ ባይሆነም ስህተታቸው ጊዜ ከጣላቸው ሰዎች ላይ ተደፍድፎ እነርሱ
ከጥፋቱ ነፃ ይሆናሉ፡፡
ይህም በመሆነ ባልና ሚስት መደባቸው ከተናቁ ሰዎች መካከል
ቢሆንም ጊዜ ስለሰጣቸው ብቻ እንደ ትልልቅ ሰዎች ይከበራሉ:: ሴትዮዋ ጨካኝ፣ ሰውዬው በዋል ፈሰስ ዓይነት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሁለቱም ትንሽ ቀዳዳ ካገኙ ተንኮል ከመሥራት አይቆጠቡም:: እንደ ትል ከብርሃን ወደ ጨለማ፤
እንደ አባያ በሬ ወደፊት ከመራመድ ወደኋላ ማፈግፈግ፤ እንደ እባብ ከቀና አስተሳሰብ ተንኮል ወደ መሽረብ፤ ከሰፊው ጠባብ መንገድን የሚመርጡ
ዓይነት ሰዎች ናቸው::
የሚገርመው ግን ክፋት፧ ተንኮልና ምቀኝነት ለኑሮ መሳካት ዋስትና
ሊሆን ስለማይችል እነዚህ ሰዎች በሆቴል ቤታቸው ብዙም አልተጠቀሙም።
ፋንቲንን ያመስግኑና ሳያስቡት በድንገት ሃምሣ ሰባት ፍራንክ
አግኝተዋል፡፡ ይህን ገንዘብ በማግኘታቸው ሆቴል ቤታቸው ከመታሸግ ዳነ፡፡ግን አሁንም ቢሆን በሚቀጥለው ወር ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋቸው ስለነበር ሴትዮዋ የኮዜትን ጋቢና ቀሚሶች ወደ ገበያ ወስዳ ስልሣ ፍራንክ
ሽጠቻቸው፡፡ ገንዘቡ ሲያልቅ ኮዜትን ለነፍሳችን ብለው ያስጠግዋት እንጂ ጥቅም እንዳገኙባት ረስተው በጣም ጨከኑባት፡፡ የራስዋ የሆኑ ልብሶች
ተሽጠው የተቦጫጨቁትን የልጆቻቸው ውራጅ ኣለበስዋት:: ለውሻ እንደሚሰጥም አጥንት ከበላተኛ የወዳደቀ ትርፍራፊ አበልዋት:: ምድብዋ በር
ላይ ተኝቶ ዓይን ዓይን ከሚያይ ውሻና ከተመጋቢ እግር ስር ድምፅ እያሰማ ከሚሄድ ድመት ጋር ሆነ፡፡ ምግብ እንደ ውሻና ድመት በገበቴ መሣይ ነገር መሬት ተጣለላት::
እናትዋ አገርዋ ከገባች በኋላ ከእዚህ ግባ የማይባል ሥራ አገኘች፡፡በየወሩ ደብዳቤ ለእነሚስተር ቴናድዬ ጻፈችላቸው:: በደብዳቤዋ ከልጅዋ
ደኅንነት በስተቀር ሌላ የምትጠይቀው ነገር አልነበራትም፡፡ ባልና ሚስት
የመልስ ደብዳቤ ሲልኩ ኮዜት ተመችቶአት እንደምትኖርና ጤናዋም ደህና መሆኑን ገልጸው ነበር የሚጽፉላት::
ኣንዳንድ ልቦች በአንድ ጎናቸው ጥላቻን ካላቀፉ ፍቅር ብቻውን
መንተራስ የማይችሉ አሉ፡፡ መዳም ቴናድዬ የራስዋን ልጆች በጣም
ትወዳለች:: የልጆችዋ ፍቅር አዲስዋን ልጅ እጅግ እንድትጠላ አደረጋት፡፡ኮዜት ያለ አግባብ ስትነቀፍ፤ ስትገረፍ፤ ስትሰደብ፧ ስትመናጨቅና ስትጠላ
እኩዮችዋ የሆነ ሌሎቹ ሁለት ልጆች ሲታቀፉ፤ እሽሩሩ ሲባሉ፤
የማይገባቸውን ምስጋና ሲያገኙ በማየትዋ ነገሩ ሊገባት አልቻለም:: የሰው ልጅ ጭካኔ፤ የዚህ ዓለም ውጣ ውረድ፤ የእግዚኣብሔር ሽረትና ምህረት
ምን እንደሆነ ለማወቅ እድሜዋ አልፈቀደላትም::
ሴትዮዋ ትጨክንባታለች:: ኢፓኒንና አዜልማም ይጨክኑባታል፡፡ምናልባት የጭካኔው መጠን ይለያይ ይሆናል እንጂ በዚያ እድሜ ልጆች
ቤተሰቦቻቸው የሚፈጽሙትን ነው የሚከተሉት፡፡
ዓመት አለፈ፤ ሌላውም ተደገመ::
የሰፈር ሰዎች ምን ብለው ያወሩ ጀመር፧ «እነመዳም ቴናድዬ ምን
ዓይነት ርህሩህና ደግ ቢሆኑ ነው እባካችሁ:: እነርሱ ለራሳቸው ምስኪኖች ሆነው መጠጊያ የሌላትንና እናትዋ የጣለቻትን ልጅ ያሳድጋሉ::»
የዜት እናት ልጅዋን የረሳች መሰላቸው::
ዓመት እስከ ዓመት ቁመትዋ እየጨመረ ሲሄድ መከራዋና
ስቃይዋም እንዲሁ ጨመረ::
ኮዜት ሕፃን ሆና ሳለ የሁለቱ ልጆች ጥፋት ማስተባበያ ነበረች::
እያደገች ስትሄድ ማለት አምስት ዓመት ሳይሞላት የቤቱ አሽከር ሆነች::
ኮዜት ትላላካለች ፤ ቤት ትጠርጋለች፤ ግቢ ታጸዳለች ፤ እቃ
ታጥባለች ፤ ከባድ ነገር ትሸከማለች:: እናትዋ በየወሩ የምትከፍለውን ገንዘብ ባጓደለች ቁጥር ልጅትዋ የምትሸከመው ሸክም እየከበደ ይሄዳል::
እናትዋ የጥቂት ወሮችን ክፍያ አልላከችም::
እናት ከሦስት ዓመት በኋላ ወደ ሞንትፌርሜ ከተማ ብትመለስና
ልጅዋን ብታያት አታውቃትም፡፡ ያኔ ጥላት ስትሄድ ድምቡሽቡሽ ብላ
ንከሱኝ፣ ግመጡኝ ትል የነበረችው ልጅ በቁራና መንምና አጥንትዋ .
ገጥጦ ፣ ፊትዋ ገርጥቶ ሌላ ልጅ መስላለች፡፡ «እደለ ቢስ፣ ገዳፋ» እያሉ ነው ባልና ሚስት የሚጠርዋት::
እድልዋ ዝምተኛ እንድትሆን ፧ ችግርዋ ፉንጋ እንድትመስል
አድርጓአታል። ዓይኖችዋ ቢጎደጉዱም ከቦታቸው አልጠፉም፣ ሲያይዋቸው
ያስፈራሉ፡፡ ስቃይ እንዳንገበገባቸው ያስታውቃሉ፡፡ ትላልቅ ስለነበሩ ያዘሉትም የስቃይ መጠን ትልቅ ነበር::
ዓይኖችዋ እንባ አቅርረው፣ በክረምት ቡትቶ ለብሳ አፈር ላይ
ስትተኛና በበጋ ደባደቦ ለብሳ በጠራራ ፀሐይ ከቁመትዋ የሚበልጥ መጥረጊያ ይዛ ደጃፍ ስትጥርግ ማየት ልብ ላለው የሚዘገንን ትርኢት ነበር፡፡ ሆኖም
ሰዎች «እድለቢስ... ገዳፉ... እበይ» እያሉ ነበር የሚጠርዋት::
ጠዋት ጠዋት እየተባችና እየፈራች ሰውነትዋ ተንቀጥቅጦ በቅጡ
ሳይነጋ ነበር የምትነሳው:: ከሰፈር የምታመጣው ነገር ካለ የሰፈር ሰው ሳይነሳ ትሄድና እስኪነሱ ትጠብቃለች፡፡ከገበያም የምትገዛው እቃ ካላ
ገበያተኞች እቃቸውን ሳያወጡ እርስዋ ቀድማ ትገኛለች::
ደጉ ሰው
የዚያች ምስኪን ልጅ እናት ምን ሆነች? ሞንትፐርሜ ውስጥ ይኖሩ
የነበሩ ሰዎች ልጅዋን ከድታ እንደጠፋች ሲናገሩ ሰምተናል:: የት ነው ያለችው? ምን እየሠራች ነው?
ኮዜትን ከነማዳም ቴናድዩ ቤት ትታ ከሄደች በኋላ ትውልድ አገርዋ
በደህና ደርሳለች:: ከአሁን በፊት እንደተጠቀሰው IIመነ 1818 ዓ.ም. ነበር፡፡ፋንቲን ወደ ትውልድ አገርዋ የተመለሰችው አገሩን ለቅቃ በወጣች በአሥራ
ሁለተኛ ዓመትዋ ነበር፡፡ አገሩ በጣም ተለዋውጦ ነው ያገኘችው:: የእርስዋ ኑሮ እያቆለቆለ ሲሄድ የትውልድ አገርዋ ከተማ በጣም እያደገና እየተሻሻለ ሄድዋል፡፡ በመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት በተለይ ትልቅ መሻሻል ተገኝቶ
አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ተቋቁመዋል፡
በዚያ አገር ፋብሪካ ውስጥ ተመርተው የሚወጡ ዕቃዎች ዋጋ እጅግ የናረ ነበር፡፡ ነገር ግን ፋንቲን ወደ አገርዋ ስትመለስ ያ ሁናቴ ተለውጦ ነው የደረሰችው:: አንድ ያልታወቀ ሰው በ1815 ዓ.ም. መጨረሻ ገደማ
መጥቶ አስደናቂ የሆነ የፈጠራ ሥራ በመሥራቱ የፋብሪካ ውጤቶች ዋጋ ዝቅ ይላል::
ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሰውዬው ከመጠን በላይ ሀብታም
ይሆናል፡፡ ፋብሪካው ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሰዎች ደግሞ ጥሩ ደመወዝ ስለተከፈላቸው እነሱም የተሻሻለ ኑሮ መኖር ቻሉ፡፡ ሰውዬው ማን እንደሆነና
ከየት እንደመጣ ግን ማንም አያውቅም:: ወደ ከተማው ሲመጣ ምንም ገንዘብ ይዞ እንዳልመጣ ሁሉም የሚያውቀው ፥ነው:: ግን እርሱ በወጠነው
የፈጠራ አሳብ እርሱ ብቻ ሳይሆን አገሩ ሁሉ ከበረበት:: ወደዚያ ሲመጣ አለባበሱም ሆነ አነጋገሩ የጭቁን ሰው ነበር፡፡ በታኅሣሥ ወር ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ወደ ከተማው ሲገባ የለበሰው ልብስ የተቦጫጨቀ እግሩና እጁ

#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ”
የምርመራ ማዘዣዎችን ተቀብያት ስወጣ፣ ለአልትራሳውንድ ምርመራዉ ጨመር ያለ ዉሃ መጠጣቱ እንደሚጠቅመኝ ስለማዉቅ፣ ወደ ሆስፒታል
ስመጣ ጀምሬዉ ያጋመስሁትን ኹለት ሊትር ዉሃ እየተጎነጨሁለት
ወደ ቤተ ሙከራዉ ተመለስሁ። እንደ ፈራሁት ስዓቱ ሰዉ የማይበዛበት ሰዓት ሆኖ ይመስለኛል፣ የሚያማርር ወረፋ አልገጠመኝም። በመሆኑም፣
ደሜን ጨምሮ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ናሙናዎችን ሰጥቼ በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ዉጤት ደረስልኝ። ዉጤቴን ይዤ እንደገና ወደ ቀድሞዋ የልቤ ሰዉ፣ የአሁኗ ደግሞ ሐኪሜ ቢሮ ወጥሮ የያዘኝን ሽንቴን እንደ
ቆነጠጥሁ ተመለስሁ። ገለጥ አድርጌ እንኳን ወረቀቱን የማየት ሐሳብ ብልጭ አላለልኝም።
ሆስፒታላችሁ ብርሃናዊ አይደል እንዴ አንቺ፣ ፍጥነቱ!”
“ዉጤቱ ደረሰልን?”
“ይኼዉ” አልኋት፣ ጠረጴዛዋ ላይ እንደ ከባድ እቃ በኹለት እጄ
እያስቀመጥሁላት።
“ደፈንሽዉ ኣ?” አለችኝ፣ ትኩረቷን አድርጋበት ከነበረዉ ኮምፒዉተሯ
ወደ ዉጤት ወረቀቴ እያመጣችዉ።
“እረ እኔ ምኑንም አላየሁት”
ለመጨረሻ ጊዜ ሆዴን ሰረቅ አድርጋ አየችዉና ወረቀቱን ገለጠችዉ፡፡ድንገት ፊቷ እብጥ አለብኝ። ዉጤቱ ላይ ደስ የማይል ነገር እንዳገኘች ጠረጠርሁ። ቢሆንም ግን ራሷ እስከምትነግረኝ ድረስ ብጠብቅ ይሻላል ብዬ ያላየኋት መሰልሁ። እሷም ያልደነገጠች ለመምሰል የሆነ ያልሆነዉን ቀበጣጠረች፡፡ እንደገና በሚያደናግር ትኩረት አስተዋለችዉና ወደ አልትራሳዉንድ ክፍሉ እንድከተላት ነገረችኝ፡፡ ስንገባ ያገኘነዉን ራዲዮሎጂስት እንኳን በቅጡ ሰላም አላለችዉም። ቶሎ ብዬ ሆዴን ገልጬ አልጋዉ ላይ እንድንጋለል አዘዘችኝ፡፡ ለወትሮዉ በልዩነት የተማረዉ ባለሙያ ያለበትን አልትራሳዉንድ ይቅርና ተራ ነገርም ቢሆን
ሐኪም ያለሙያዉ ገብቶ አይፈተፍትም፡፡ እሷ ግን እጅግ ከመቻኮሏ የተነሳ እሱን ጨምራ በጥድፊያ ከፍ ዝቅ አደረገችዉ። የእዉር ድንብሯ ወጥቷል። ሌላዉ ቀርቶ ገና በመመርመሪያዉ (ultrasound probe)
እንኳን ሳይዳብሰኝ ነበር ዓይኖቿን ወደ ምስል መከሰቻዉ የተከለቻቸዉ።
ችኮላዋን በበጎ የተረዳት የክፍሉ ባለሙያ፣ ሳይቀየማት የሚደረገዉን ሁሉ አድርጎ የፅንሱን ጥላማ ገጽ ፊት ለፊታችን ባለዉ ዝርግ መከሰቻ አመጣልን። ይኼ ሁሉ ሲሆን የእሷን አድራጎት ብቻ ነበር የምከታተለዉ።
እስኪበቃት ድረስ እያጎላች እና እያሳነሰች ስትመለከተዉ ቆየች። እኔንም እንዳየዉ ጋበዘችኝ፡፡
አየሁት።
ችግር አለ። ከባድ ችግር!
“አይ፤ ያን ያህል እንኳን አንገት የሚያስደፋ አይደለም” አለችኝ፣
ከአልጋዉ ላይ እንድነሳ እየደገፈችኝ። ድንገት ሰዉነቴ እየከዳኝ፣ የበለጠ ድጋፍ እየፈለግሁ መጣሁ። ደግነቷ፣ እጇን አልከለከለችኝም።
“በእርግጥ የማልደብቅሽ ነገር ቢኖር፤ እኔም ልክ የላብራቶሪ ዉጤትሽን ሳየዉ ደንግጫለሁ። በዚያም ላይ ከእኔ ባልተናነስ ስለ ሁኔታዉ ልታወቂ እንደምትችይ ስለማዉቅ በማይመስልሽ ቃል አንቺን አልሸነግልሽም።እንኳንስ የሕክምና ሥነ ምግባር ለማገባት ላንቺ ለጓደኛዬ ይቅርና፣
ለታካሚዎቼ ሁሉ የሆነዉን በግልጽነት የማስረዳት ኃላፊነት አለብኝ። የምልሽ ይገባሻል መቼስ”
ጓደኛዬም ሐኪሜም በሆነችዋ ሸዊት ፊት፣ ግብኔ ብቻ ያልቀረ ለመምሰል ተጣጣርሁ። ጠንካራ ለመምሰል እየሞከርሁ የዉጤት ወረቀቱን እንድትመልስልኝ እና የሆነዉን ሁሉ በራሴ ዓይን እንዳየዉ እጄን ዘረጋሁላት። ሐኪሜ ለምን እንደዚያ እንደሆነች ገባኝ፡፡ ምክንያቱም የፎሊክ አሲድ መጠኑ ከሚጠበቀዉ መጠን እጅግ የወረደ ኖሯል።
እንደዚህ ሲሆን ደግሞ በፅንሱ ላይ የነርቭ ክፍተት የማስከተል ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን እንኳንስ ሥራዬ ብላ ያጠናችዉ እሷ ትቅርና፣ እኔ ዉብርስትም አዉቀዋለሁ። የፎሊክ አሲድ እጥረት ከተከሰተ፣ የነርቭ
ዘንግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በወቅቱ እንዳይዘጋ ያደርገዋል። በመሆኑም፣ የፎሊክ አሲድ እጥረት እንዳያጋጥም፣ እርግዝና ከመፈጠሩ አስቀድሞ ወይ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከተመረጡ ምግቦች፣ ወይ ደግሞ ሰዉ ሰራሽ እንክብሎችን መዉሰድ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ይኼዉ በእኔ የምርመራ ዉጤት ላይ እንደ ታየዉ፣ ልክ ያልሆነ ነገር በፅንሱ ላይ ይፈጠራል።
ምን ዋጋ አለኝ? አርፍጃለኋ!
“በእርግጥ ሌሎችም መነሻዎች ስላሉት፣ የፎሊክ አሲድ እጥረቱ ነዉ ይኼን ያመጣዉ ብሎ አፍን ሞልቶ መደምደም አይቻልም። ሆኖም እኔን ደጋግመዉ ከገጠሙኝ ዐሥር የፎሊክ አሲድ እጥረት ያየሁባቸዉ ነፍሰ
ጡሮች፣ ቢያንስ የስድስቱ ወደ ነርቭ ክፍተት ያደርሳል። የነርቭ ክፍተት ስልሽ የተለመዱትን፣ በተለይም ስፓይናቢፊዳ(አከርካሪው ላይ ያለው ነርቭ ወደ ውጭ መውጣት) ማለቴ ነዉ። ይኼ ደግሞ ያልሰለጠነ ሀገር በሽታ እየሆነ መጥቷል። ምክንያቱም የበለጸጉት ሀገራት ምግባቸዉን በጠቅላላ በፎሊክ እንዲበለጽግ ስላደረጉት፣ ብዙም አያጋጥማቸዉም። የእኛን ሀገር ግን አታንሺዉ”
“በናትሽ መፍትሔ አለዉ በዪኝ”
“ደግሞ በኛ ዘመን መፍትሔ የሌለዉ ነገር ምናለና ዉቤ”
“እኮ ምን?”
“በተአምር ታምኛለሽ?”
የጭንቅ ዝልዝል የተንጠለጠለበትን ፊቴን መለስሁላት።
“ተአምር?”
“አሁን አንዴ ፅንሱ ቅርጽ ይዟል። ተአምር ካልተፈጠረ በቀር፣ ሕጻኗ... በነገራችን ላይ ጾታዋን አልነገርሁሽም አይደል ቅድም? ሴት ናት። እና፤ከላብራቶሪም ሆነ ከአልትራሳዉንድ ባገኘነዉ ዉጤት መሠረት፣ በወሊድ ጊዜ ሊገጥሙን የሚችሉ የነርቭ ዘንግ ክፍተቶች ይኖራሉ፡፡ በተለይ
ስፓ ይናባይፊዳ የሚባለዉ ለብቻዉ ወይም ደግሞ ሀይድሮሴፋለስ(ጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር) ጭምር
ሊሆኑ ይችላሉ። ግን እንዳልሁሽ ነዉ፤ ተወልዳ በዓይናችን እስከምናያት ድረስ መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አንችልም”
“እንዲያዉ አይበልብኝና ይኼ ነገር እዉነት የሚሆን ከሆነ ምንድነዉ
የሚሆነዉ ግን?”
“እንደምታዉቂዉ፤ ለሐቅ የቀረበ ግምት እንጂ ፍጹም የሚባል ያለቀ
የደቀቀ ሐቅ የለም በሳይንስ፡፡ አንቺም ሐሳቤን የምትጋሪዉ ይመስለኛል።ሆኖም አብዛኛዎቹ የዚህ ክፍተት ተጠቂዎች የታወቁ ጉዳቶች ይገጥሟቸዋል። ለምሳሌ ሽንትና ሰገራ ያለመቆጣጠር፣ የእግርና የእጅ ሽባነት፣ የዓይን መንሸዋረር ወይ መጥፋት እና ሌሎችም ጭምር።እንዲያዉም አልፎ አልፎ የከፋዉ ሲመጣ፣ እነዚህ ያልሁሽ ሁሉም አንድ
ላይ የሚከሰቱበት አጋጣሚ ሁሉ አለ። ታዲያ እንዳልሁሽ፣ በኛ ዘመን
መፍትሔ የሌለዉ ችግር የለም። ቢፈጠርም እንኳን ሕክምና አለዉ”
“አለዉ?” አልሁኝ፣ ለእፎይታ ራሴን እያመቻቸሁ። አንደኛዬን ግልብ
ሆኜ የለ አሁንማ? አሁን መሳቅ አሁን ማልቀስ፣ አሁን ማመን አሁን
መካድ። ስስ ሆኛለሁ።
“አዎ። ቀዶ ጥገናም እኮ አለዉ። አንቺን መምከር ሳይገባኝም፣ ከዚህ በላይ መጨነቅ ግን አይኖርብሽም። ጭንቀት ራሱ ሌላ ጣጣ ስላለዉ፣ እዉነታዉን የምነግርሽ እንድትጨነቂበት ሳይሆን ለግልጽነት ብዬ ነዉ።
በዚያ ላይ አንቺ ጠንካራ ሰዉ መሆንሽን ለእኔ ለጓደኛሽ እንዲነግሩኝ አልጠብቅም። አዉቅሻለኋ!”
ቀዝቃዛ ትንፋሽ ተነፈስሁ። ገና ዛሬ፣ አሁን ገና የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጠርሁት። ወይ ስለ ንስሐ ምንም አላዉቅም፣ ወይ ደግሞ እግዚአብሔር ቂመኛ ነዉ
ስል አሰብሁ። እኔ የተማርሁት ሰዉ ፍጹም ተጸጽቶ ንስሐ ከገባ
ኃጢአቱ ሁሉ ፍጹም ይሰረይለታል የሚለዉን ነበር። ከእግዚአብሔር
ጋር የሚያደረገዉም እርቅ ፍጹም ይሆንለታል ሲባል አዉቃለሁ። ታዲያ እኔ ፍጹም የሆነ ጸጸት ተጸጽቼ ንስሐ አልገባሁም? ቀኖናዬንስ በሚገባ ወይስ እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ መሆኑን አላመንሁም?

#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
..ዳኞቹ ሁሉም ቀጠሮአቸውን ለማክበር ምንም እንቅፋት አልገጠማቸውም "አንድ ሰዓት ሲሆን ተከታትለው ደረሱ "
ቤቱ ሚስተር ካርላይልና እህቱ ቢቀመጡበትም አባታቸው ሚስተር ካርላይል ሲሞት በውርስ የደረሳት ሀብቷ በመሆኑ በስሟ ይጠራል "
ሚስ ካርላይል ' የጋያ መሳቢያ ውዥሞዎቻቸውንና የትምባሆውን ጢስ ባትወደውም አብራቸው ተቀመጠች " ልክ እንደነሱ የውይይቱ ዋና ተሳታፊ ሆነች "
እንደ አባቷ ሕግ ዐዋቂነቷ ይነገርላት ነበር " እውነትም በሕግ ነክ ጉዳዮች ፈጣን አስተዋይነትና ጥሩ አስተያየት ነበራት " ሁለት ሰዓት ሲሆን አንድ አሽከር ገብቶ
ሚስተር ካርላይልን «ሚስተር ዲል አንድ ጊዜ ዘልቀው ያነጋግሩኝ ይላል» አለው "
ሚስተር ካርላይል ተነሥቶ ወጣና አንድ የተከፈተ ፖስታ በእጁ ይዞ ገባ "
« ለግማሽ ሰዓት ያህል እንድለያችሁ የሚያደርገኝ አንድ አንስቸኳይ ጉዳይ ገጠመኝ " በጣም አዝናለሁ • ቢሆንም በተቻለ መጠን ቶሎ እመለሳለሁ » አላቸው።
«ማነው የላከብህ ? » አለችው ኮርኒሊያ ወዲያው ተቀብላ "
ምንም ሳይመልስላት አየት ሲያደርጋት «ምንም እንዳትጠየቁ» ማለት እንደሆነ አድርጋ ተረጐመችውና ዝም አለች " እሱም የጀመረውን በመቀጠል እስከዚያው ስለሕጉ ከኔ በበለጠ የሚያውቀው ዲል በውይይቱ ይጨመራችኋል እኔም ብዙ አልቆይም » አላቸውና ወጥቶ ወደ ዳኛው ሔር ዐጸድ ገሠገሠ ።
ጨረቃዋ እንዳለፈው ሌሊት ደምቃ ነበር " ከተማውን ከበስተኋላው ትቶ እነዚያን ቀደም ሲል የጠቀስናቸውን ቪላዎች አልፋችው ሔደ » በግራ በኩል በስተኋላው ወዶሚታየው ዱር ሳያስበው ተመለከተ " ጥንት በዚሁ አካባቢ ገዳም ነበረበት ስለሚባል ይህ ዱር የገዳም ዐጸድ እየተባለ ይጠራል " ዛሬ ግን ገዳም የነበሪ ለመሆኑ ከአፈ ታሪክ በቀር በዐይን የሚታይ ምንም ምልክት አልነበረበትም ።
ከዱሩ ውስጥ ጥቂት ገባ ብሎ አንድ ትንሽ ቤት አለ " የሪቻርድ ሔርን ሕይወት አደገኛ ሁኔታ ላይ የጣለው ግድያ የተፈጸመው ከዚሀ ቤት ውስጥ ነበር ሃልዮን ከሞተበት ወዲህ ቤቱን ማንም ደፍሮ ሊከራየው ወይም ሊኖርበት ስላቻለ ወና ሆኖ ቀርቷል።
ሚስተር ካርላይል ወደ ዳኛው ግቢ የሚያስገባውን በር ከፍቶ ግራና ቀኝ ተመለከተ " ነገር ግን ሪቻርድ ከዚያ ግድም መደበቁን የሚጠቁም አንድም በጆሮ የሚ
ሰማ ወይም በዐይን የሚታይ ምልክት አጣ » በመስኮት ስትመለከት የነበረችው ባርባራ በር ከፈተችለት
« እማማ በጣም ተሸብራለች »
አለችው በጆሮው ቀስ ብላ ገና ሲገባ "
« እስካሁን አልመጣም እንዴ ? » አላት
« ከሆነ እሺ እንግባ ከዚህ ቦታ አስክወጣ ድረስ በጣም ቸኩያለሁ ለመሆኑ ገንዘቡንስ የማገኝ ይመስልሃል ? »
« አዎን ታግኛለህ " ግን ሪቻርድ ... የዚያን አሳዛኝ ምሽት እውነተኛ ታሪክ ልታስረዳኝ መፈለግህን እኅትህ አጫውታኛለች " አሁን ከዚህ እንዳለን ብትነረኝ ይሻላል "
« አንተ እንድትሰማው የፈለገችው ባርባራ ናት " በበኩሌ አንተም ሆንክ ሌላ ሰው ቢሰማው የማገኘው ጥቅም የለም ምክንያቱም ካንተ ጀምሮ የሚያም
ነኝ ሰው አይኖርም " »
« ምናለ አንተ ነግረህ ሞክረኝ! ብቻ አጠር አርገው " »
« ካልክ እሺ " ከአደጋው በፊትም ቢሆን የሆሊጆንን ቤት አዘወትር ነበር !ቤተሰቦቼ ግን አልወደዱልኝም " አፊን ፍለጋ የምሔድ እየመሰላቸው ይቆጡኝ
ነበር እሷን መፈለጌ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል " አንድ ቀን ሆሊጆን ጠበንጃይን እንዳውሰው ጠየቀኝ ያንለት ማታ አፊን ማንም ይሁን ግድየለም አንድ ሰው
ፍለጋ ሔጄ ሳለ "
« እዚህ ላይ ሪቻርድ ... ለሐኪምህና ለጠበቃህ ጉዳይህን ጨርስህ ንገር » የሚል የጥንት አባባል አለ » በዚህ ረገድ ሊሞክርልህ የሚችል ነገር ሊኖር መቻል አለመቻሉን የምገመግመው አንተ አንድም ሳታስቀር ስትነግረኝ ብቻ ነው " አለበለዚያ ግን ከነጭራሹ ባልሰማው ይሻላል " በርግጥ የምትነግረኝን ምስጢር የመጠበቅ ኃላፊነት አለብኝ »
« መናገር ካለብኝማ ልንገርህ » አለ ሪቻርድ ምልስ ብሎ» «ልጅቷን እወዳት ነበር“ ራሴን እስክችል ለብዙ ዓመትም ቢሆን ጠብቄ ሚስት ላደርጋት ፍላጐት ነበረኝ " ነገር ግን አባቴ ሐሳቤን ስላልተቀበለ ቃል ልገባላት አልቻልኩም "
« ሚስት ? » አለው ሚስተር ካርላይል ጠበቅ አድርጎ "
« አዎን እየነገርኩህ »
« በል ቀጥል ...ሪቻርድ ፤እሷስ ትወድህ ነበር ? »
« ማረጋገጥ አልችልም » አንዳንድ ጊዜ የወደደችኝ ትመስልና በሌላ ጊዜ ደግሞ ተለውጣ አገኛታለሁ ሌታ ቀን ብጤ ነበረች የምመጣበትን ቀን ወስና ከዚያ
ውጭ እሷ ዘንድ እንዳልደርስ ከነገረችኝ በኋላ በቀጠረችኝ ቀን ደግሞ ሐሳቧን ለውጣ
ትመልሰኛለች » ብዙ ጊዜ ወደሱ ታደላ ነበር » እኔን እንዳልመጣ በምትወስናቸው ቀኖች ከሱ ጋር ታመሽ እንደ ነበር ደረስኩበት " ግን ከሱ ጋር ተገናኝተን አናውቅም»
« ግን ሪቻርድ . . . የሰውየውን ስም እኮ አልነገርከኝም »
ሪቻርድ ሔር በጥቁሩ አርቲፊሻል ሪዙ የሚስተር ካርላይልን ትከሻ እስኪታከክ ድረስ ወደ ጆሮው ጠጋ ብሎ በቀስታ « ያ እርጉም ቶርን ነዋ!»አለው "
« ቶርን ማን ነበር ? ሰምቸው አላውቅም » አለው ባርባራ የነገረቸውን አስታውሶ .
« ዌስት ሊን ውስጥ እሱን የሚያውቅ ሰው የነበረ አይመስለኝም " ከዌስት
ሊን ራቅ ብሎ ነበር የሚኖር » ሲመጣ ደግሞ እንዳይታይ ይጠነቀቅ ነበር " »
« ከአፊ ጋር ለመዳራት ? »
« አዎን ከሷ ጋር ለመዳራት ርቀት አያግደውም ነበር "ጭልምልም ሲል እየጋለበ ይመጣና ፈረሱን ከአንድ ዛፍ ላይ ያስራል አባቷ ከቤት ካለ ከዱሩ ከሌለ ግን ከቤት ውስጥ አንድ ሁለት ሰዓት ያህል አብረው ያመሹና እንዳመጣጡ ጋልቦ ይሔዳል።
« ወደ ዋናዉ ነጥባችን እንመለስ ሪቻርድ ... ወደዚያ ምሽት ታሪክ»
ሆሊጆን ጠመንጃው ተበላሽቶበት ስለነበር የኔን እንዳውሰው ለመነኝ ያን ለት ማታ አፊ እንድመጣ ቀጥራኝ ስለነበር ጠበንጃዬን ይዤ ወረድኩ አባቴ የምሔድበትን ሲጠይቀኝ ከቦሻሞ ዘንድ አልኩት ይህ ውሸቴ በጉዳዩ ምርመራ ጊዜ
« ሆሌጆን ጠበንጃው ተበላሽቶበት ስለ ነበር የኔን እንዳውሰው ለመነኝ"ያን ለወንጀለኝነቴ ማጠናከሪያ ሆኖ ተገኘ " ሁልጊዜ እንደማደርገው እንዳልታይ በዙሪያ መንገድ †ንከራትቼ ሃሊዮን ቤት ስዴርስ አፊ እየተጀነነች ወጣችና ልታስተናግደኝ እንደማትችል ነገረችኝ እሷና እኔ በዚህ ስንነጋገር ጠበንጃዬን እንደ ያዝኩ
ሎክስሌይ ባጠገባችን ሲያልፍ አይቶኝ ነበር ። እውነት ለመናገር ከሆነ እሷ ከምትረግጠው መሬት ጋር ሳይቀር ፍቅር ስለ ያዘኝ እንደ ፈለገችው ታዝብኝ ነበርና እንዳለችኝ ተሸነፍኩላት " ጠበንጃው የጐረሰ መሆኑን ነግሬ ሰጠኋት ተቀብላ በሯን ዘግታብኝ ገባች ። እሱ መኖሩን ብትክድም ቶርን ገብቶ ይሆናል ብዬ ስለ ጠረጠርኩ ከቤቱ ጥቂት ራቅ ብዬ ከዛፎቹ ውስጥ ተደበቅሁ ሎክስሌይ ሲመለስ እንደ ገና አየኝና ለምን እንደ ተደበቅሁ ቢጠይቀኝ በኔ ጉዳይ ምን አገባው ብዬ ምንም ላልመልስለት ከነበርኩበት ቦታ ራቅ ብዬ ሔድኩ"ያም ለወንጀለኝነቴ እንደ መረጃ ተቈጠረብኝ" ከዚያ በኋላ ኻያ ደቂቃ ቆይቶ በስተሆሊጆን ቤት በኩል ተኩስ ሰማሁ " የፀሐይ መግቢያ ላይ ስለነበር ' አንድ ከመሽ የመጣ ቆቅ አዳኝ ይሆኖል

#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
የአያቶቻችን ቤት
ቀኑ እንዳንከፍት ከተከለከልነው መስኮትና ሙሉ በሙሉ ከሸፈነው ከባድና ትልልቅ መጋረጃዎች ጀርባ ደብዛዛ ብርሃኑን በማሳየት መንጋቱን እየነገረን ነው: ክሪስቶፈር እያዛጋና እየተንጠራራ አልጋው ላይ በመቀመጥ ወደ እኔ
እየተመለከተ “ሰላም ጨብራሪት” አለኝ፡ የእሱም ፀጉር ከእኔ በባሰ ተንጨባሮ ነበር ፀጉሩ ያምራል፡ እግዚአብሔር ለእኔና ለኬሪ ቀጥ ያለ ፀጉር ሰጥቶን ለኮሪና ለእሱ እንደዚህ አይነት የሚጠቀለል ጸጉር ለምን ሊሰጣቸው እንደመረጠ አልገባኝም: ድሮ የተጠቀለለውን ፀጉሩን ሲያበጥር አጠገቡ ተቀምጬ ፀጉሩ
ከእሱ ላይ ተነቅሎ እኔ ጭንቅላት ላይ እንዲሆን እመኝ ነበር።
ከተኛሁበት ተነስቼ ተቀመጥኩና ምናልባት አስራ ስድስት በአስራ ስድስት የሚሆነውን ክፍል ዙሪያውን ተመለከትኩት። ውስጡ ሁለት ትልልቅ አልጋዎች፣ ሰፊ የልብሰ ማስቀመጫ መሳቢያ፣ ትልቅ የልብስ ማስቀመጫ
ቁምሳጥን፣ ሁለት ትልልቅ ወንበሮች፣ በሁለቱ መስኮቶች መካከል ከትንሽ ወንበር
ጋር የተቀመጠ የመልበሻ ጠረጴዛ፣ በተጨማሪም በዙሪያው አራት ወንበሮች የተደረጉለት ትልቅ ጠረጴዛ ተጠቅጥቀውበት ክፍሉን ትንሽ አስመስለውታል።
በሁለቱ ትልልቅ አልጋዎች መካከልም መብራት የተቀመጠበት ሌላ ጠረጴዛ
አለ: በክፍሉ ውስጥ አራት መብራቶች አሉ ካረጁት ጥቋቁር ቁሳቁሶች ስር ድሮ በጣም የሚያምር እንደነበረ የሚያስታውቅ ወርቃማ መስመር ያለው ቀለሙ የደበዘዘ አሮጌ ቀይ ምንጣፍ ተነጥፏል። የአልጋ ልብሶቹ ወርቃማ ቀለም ያላቸው ወፍራሞች ናቸው: ግድግዳዎቹ ደብዛዛ ቢጫ የግድግዳ ወረቀት የተለጠፈባቸው ሲሆን ሶስት ስዕሎችም ተሰቅለውባቸዋል። ከስዕሎቹ መሃል ሰይጣኖች ምስኪን ነፍሳትን ሲበሉ የሚያሳየው አንደኛው ስዕል ልብ
ያስደነግጣል። ሰይጣኖቹ ራቁታቸውን የሆኑ ሰዎችን ሲያባርሩ ያለበት የስዕሉ
ክፍል ደማቅ ቀይ ቀለም ተቀብቷል። ነፍሳቱ እግራቸውን እያንፈራገጡ ቢሆንም በረጃጅም አንፀባራቂና ሹል ጥርሶች ከተሞላው የሰይጣናቱ አፍ
ማምለጥ አልቻሉም
ስዕሉን እየተመለከትኩ ሳለ ወንድሜ “ሲኦል ላይ እያፈጠጥሽ ነው? ይህንን ስዕል የሰቀለችው መልአክ የሆነችው አያታችን ራሷ መሆን አለባት አልታዘዝ
ካልን የሚጠብቀን ምን እንደሆነ ልታሳየን ፈልጋ ሳይሆን አይቀርም” አለ ወንድሜ የእውነትም ሁሉን ነገር ሳያውቅ አይቀርም ዶክተር ከመሆን ቀጥሎ የሚፈልገው አርቲስት መሆን ነው የውሀና የዘይት ቀለም በመጠቀም ሲስል እጅግ በጣም ጎበዝ ነው።
ከብዙ መገላበጥ በኋላ ኬሪና ኮሪ አንድ ላይ ነቅተው ማዛጋት ጀመሩ። አይኖቻቸውን አሸት አሸት አደረጉና እንቅልፍ ባልለቀቀው አይናቸው አካባቢውን ቃኙ፡ ከዚያ ኬሪ “እዚህ መሆን አልፈልግም” አለች።
አላስገረመኝም: ኬሪ አፍ ከመፍታቷ በፊትም እንኳን ሀሳቧን መግለፅ የምትወድ ናት አፏንም የፈታችው በዘጠኝ ወሯ ነበር፡ የምትወደውንና የምትጠላውን ታውቃለች: ለኬሪ መሀከል ላይ ብሎ ነገር የለም: ወይ ታች
ነው አለዚያም ላይ ነው፡ ላይ ሰማይ ጥግ፡ ስትደሰት በጣም የሚያምር የትንሽዬ ወፍ የሚመስል ድምፅ አላት፡ ችግሩ እንቅልፍ ካልወሰዳት በስተቀር ስትዘምር መዋሏ ነው። በዚያ ላይ ከአሻንጉሊቶቿ፣ ከሻይ ስኒዎቹና
ከሌሎችም ነገሮች ጋር ታወራለች ምርጫዋ ዝም ብሎ የተቀመጠና መልስ የማይሰጣትን ነገር ማዋራት ነው።
ኮሪ የተለየ ነው። ኬሪ ዝም ብላ ስትለፈልፍ እሱ ቁጭ ብሎ በእርጋታ ያዳምጣታል ወ/ሮ ሲምሰን ኮሪን “ቀስ እያለ ወደ ውስጥ የሚሰርግ የረጋ ውሀ
ነው" ስትለው ትዝ ይለኛል። ይህንን ስትል ምን ለማለት ፈልጋ እንደሆነ አሁንም አይገባኝም: ምናልባት ዝምተኛ ሰዎች ሌሎችን የሚያስገርምና ከላይ ከሚታየው ነገር ስር የሚገኝ ሚስጥራዊ አስተሳሰብ አላቸው ለማለት
ይመስለኛል፡
“ካቲ እዚህ መሆን አልፈልግም ስል ሰምተሸኛል?" አለችኝ ትንሽዋ እህቴ።ኮሪ ይህንን ሲሰማ ከአልጋው ላይ ዘሎ ወረደና ሮጦ ወደ እኛ መጣ ከዚያ
በፍርሃት አይኖቹን አፍጥጦ መንትያ እህቱን እቅፍ አደረጋት ከዚያ ረጋ ብሎ “እዚህ እንዴት መጣን?” ብሎ ጠየቀ፡
“ትናንት ማታ በባቡር ነው የመጣነው አታስታውስም?”
“አይ አላስታውስም”
“በጨረቃ በጫካ ውስጥ እየተራመድን ነበር፡ በጣም ያምር ነበር‥”
“ፀሀዩዋ የታለች? አልነጋም?”
ፀሀዩዋ ከመጋረጃዎቹ ጀርባ ተደብቃለች ያንን ለኮሪ ብነግረው በእርግጠኝነት መጋረጃውን ከፍቶ ወደ ውጪ ይመለከታል አንድ ጊዜ ውጪውን ካየ ደግሞ ውጪ መውጣት ይፈልጋል፡ ምን ማለት እንዳለብኝ አላወቅኩም።
የበሩን ቁልፍ ለመክፈት የሚሞክር የሆነ ሰው መልስ ከመስጠት አተረፈኝ። አያታችን በነጭ ፎጣ የተሸፈነ በምግብ የተሞላ ትልቅ ትሪ ይዛ ወደ ክፍሉ እየገባች ነበር። ትልልቅ ትሪዎችን እየተሸከመች ቀኑን ሙሉ ደረጃውን
ወደላይና ወደታች ስትወጣ እንደማትውል ኮስተር ባለ አነጋገር አስታወቀችን በተደጋጋሚ ከመጣች ሠራተኞቹ ሊያዩዋት ስለሚችሉ ምግብ የምታመጣልን
በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ተናገረች።
ትሪውን ትንሽዋ ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠች “ሳስበው hአሁን በኋላ የሽርሽር ቅርጫት እጠቀማለሁ” አለችን፡፡ የምግቡ ሀላፊነት የእኔ እንደሆነ ሁሉ ዞር ብላ ተመለከተችኝና “ይህንን ምግብ ቀኑን ሙሉ እንዲቆይ አድርጊ።ምግቡን ለሶስት ጊዜ ማለትም ለቁርስ፣ ለምሳና ለእራት እንዲሆን አድርገሽ
ከፋፍይ፡ ፍራፍሬዎቹን ደግሞ ከምግብ በኋላ መብላት ትችላላችሁ። እስከ ቀኑ መጨረሻ ድረስ ፀጥተኛና ጥሩ ልጆች ከሆናችሁ አይስክሬምና ኩኪስ
ወይም ኬክ አመጣላችሁ ይሆናል። ከረሜላ ግን በጭራሽ አይታሰብም።
አያታችሁ ካልሞተ በስተቀር ወደ ጥርስ ሀኪም መሄድ የማይታሰብ ስለሆነ ጥርሳችሁ እንዲቦረቦር ልናደርግ አንችልም:”
ክሪስቶፈር ልብሱን ለባብሶ ከመታጠቢያ ቤት ወጣና ምንም ሀዘን ሳይሰማት የባሏን ሞት ቀለል አድርጋ የምታወራውን አያታችንን አፍጥጦ እየተመለከታት
ነበር። ስለባሏ ሳይሆን ቻይና ውስጥ ባለ አንድ የአሳ ማርቢያ ውስጥ እየሞተ ስላለ አሳ የምታወራ ነው የምትመስለው: “ከበላችሁ በኋላ ደግሞ ጥርሳችሁን አጽዱ” ቀጠለች “ፀጉራችሁን በደንብ ማበጠር፣ ሰውነታችሁን ንፁህ ማድረግና ልብሳችሁንም በንፅህና መልበስ አለባቸሁ ፊታቸውና እጃቸው
የቆሸሸና ንፍጣም ልጆች አልወድም”
ይህንን ስትል የኮሪን አፍንጫ የመፀዳጃ ወረቀት በመጠቀም በጥድፊያ ጠረግኩለት ምስኪን ኮሪ አብዛኛውን ጊዜ ሀይለኛ ጉንፋን ስላለበት ንፍጡ
ይዝረበረባል እሷ ደግሞ አፍንጫው ላይ ንፍጥ የሚታይበት ልጅ አትወድም
“መታጠቢያ ቤቱን ስትጠቀሙ ስርዓት መያዝ አለባችሁ: ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ መታጠቢያ ቤት መጠቀም አይችሉም” አለች። ይህንን ስትናገር በተለይ እኔንና የመታጠቢያ ቤቱን የበር ጠርዝ ተደግፎ የቆመውን ክሪስቶፈርን
እየተመለከተች ነበር።
ጉንጮቼ ሲግሉ ታወቀኝ! ምን አይነት ልጆች እንደሆንን ነው የምታስበው?ቀጥሎ ከዚህ በኋላ ደጋግመን የምንሰማውን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ነገረችን፡
“አስታውሱ እግዚአብሔር ሁሉንም ያያል፡ ከጀርባዬ የምትሰሩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይመለከታል! እኔ ባልቀጣችሁ እግዚአብሔር ይቀጣችኋል”
ከቀሚሷ ኪስ ወረቀት አወጣችና “በዚህ ወረቀት ላይ እኔ ቤት ውስጥ እስካላችሁ ድረስ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ህጎች ሁሉ ተጽፈዋል። አለች ከዚያ ወረቀቱን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ እንድናነባቸውና በቃላችን እንድናጠናቸው እንደሚገባ አዝዛን ፊቷን አዙራ ልትሄድ ካለች በኋላ...
ተመልሳ ገና ወዳልከፈትነው ልብስ ማስቀመጫ ሳጥን አመራች።

#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
እንደ ሄሪ ማርክስ አይነት እድለኛ ሰው የለም፡፡
እና ሁል ጊዜ እድለኛ እንደሆነ ይነግሩት ነበር፡ ምንም እንኳን አባቱን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ያጣ ቢሆንም ደከመኝ ሰለቸኝ በማይሉ ብርቱ እናቱ እጅ በማደጉ እድለኛ ነው፡፡ እናቱ የፅዳት ሰራተኛ ናቸው አገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በገባችበት በዚያ ቀውጢ ወቅት እንኳን ስራቸውን አላጡም ነበር፡፡ የሚኖሩት እዚህ ግባ በማይባል ኮንዶሚኒየም
ውስጥ ቢሆንም በችግር ጊዜ የሚረዳዱ ጥሩ ጎረቤቶች አሏቸው: ሄሪ ከችግር የማምለጥ እድልና ክህሎት ነበረው፡፡ እሱና የትምህርት ቤት ጓደኞቹ
ረብሸው ሲገረፉ የአስተማሪው አርጩሜ እሱጋ ሲደርስ ይሰበር ነበር፡ ሄሪ ከፈረስ ወይም ከጋሪ ላይ ሲወድቅ ፈረሶቹ ሳይረግጡት በስልት ያሳልፋቸዋል፡፡
ለውድ ጌጣጌጥ ፍቅር ስላለው ነው ሌባ የሆነው፡፡
በጉርምስናው ወቅት በየወርቅ ቤቱ እየተዘዋወረ ዕንቁዎችን መመልከት
ይወድ ነበር፡ እነዚህ እንቁዎች የሚመስጡት ስለሚያምሩ ብቻ ሳይሆን በመጻሕፍት ላይ እንደሚያነበው የሀብታም ምልክት ስለሆኑም ጭምር ነው፡
አንድ ቦታ ረግቶ መስራት ስለማይወድ አንድ ወርቅ ሰሪ ጋ በተቀጠረ በስድስት ወሩ ስራውን ለቀቀ፡፡ ሰዓት መጠገንና የጋብቻ ቀለበቶች ማስፋት ስራም እንዲሁ አስጠላው፡ ነገር ግን የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮችን ለይቶ
የማወቅ ችሎታ አዳብሯል፡፡
ሬቤካ ሞግሃም ፍሊንትን የተዋወቃት በፈረስ እሽቅድድም ቦታ ላይ ሲሆን የአንዱ ተወዳዳሪ ደጋፊ ነው ብላ አስባለች ሬቤካ ቀውላላ፣አፍንጫዋ አለቅጥ የረዘመ መልከ ጥፉ ሴት ናት፡ ራሷ ላይ በደፋችው ቆብ ላይ ላባ ሰክታለች፡፡ አጠገቧ ያሉት ወጣት ወንዶች ከምንም ሳይቆጥሯት ሄሪ
ስላናገራት በጣም ነው በሆዷ ያመሰገነችው::
እሷን ለመተዋወቅ የጓጓ እንዳይመስል መግባባቱን በዚያው ቀን ማድረግ አልፈለገም፡፡ በሌላ ቀን ስዕል አዳራሽ ስታገኘው ደስ ብሏት ከዚህ ቀደም በደምብ እንደምታውቀው ሁሉ ሰላምታ ሰጠችውና ወስዳ ከእናቷ ጋር
አስተዋወቀችው፡፡
እንደ ሬቤካ ያሉ እመቤቶች ሲኒማ ወይም ምግብ ቤት ያለ አጃቢ
አይሄዱም፡፡ ብቻቸውን የሚሄዱ የደሃ ልጆች ናቸው፡፡ የሬቤካ እናትና አባት የሄሪን የቤተሰብ ሁኔታ ማጣራት አልደፈሩም፡፡ ቤተሰቦቹ ዮርክሻየር ውስጥ የገጠር ቤት፣ ስኮትላንድ ውስጥ የትግል ትምህርት ቤት እንዳላቸው፣ አካል
ጉዳተኛ እናቱ ደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ እንደሚኖሩና በንጉሠ ነገሥቱ አየር ኃይል ውስጥ ለሹመት መታጨቱን ሲነግራቸው እውነት ነው ብለው ተቀብለውታል።
ሄሪ በከፍተኛው መደብ ህብረተሰብ ዘንድ ውሸት ማውራት እንደሚብስ አውቋል።
በዚህ አይነት ሄሪ ከሬቤካ ጋር ጓደኝነት ከመሰረተ ሶስት ሳምንት
ሞላው፡፡ አንድ ቀን አንድ ፓርቲ ይዛው ሄደች፡፡ እዚያም ክሪኬት ሲጫወት ዋለና ከተጋበዘበት ቤት ገንዘብ ሰረቀ፡ ጋባዦቹም እንግዶቻቸውን ማሳጣት
ስላልፈለጉ ለፖሊስ ሳያሳውቁ ቀሩ፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ አንድ ዳንስ ምሽት ላይ ወስዳው ኪስ ሲያወልቅና የሴቶችን ቦርሳ እየከፈተ ሲበረብር አመሸ፡፡ ሬቤካ
ቤተሰቦቿን ልታስተዋውቀው የወሰደችው ጊዜ እንኳን ገንዘብ፣ ከብር የተሰሩ ቢላዎችንና ከወርቅ የተሰሩ የቀሚስ ማያያዣዎችን መንትፏል፡
በሱ አመለካከት ከሀብታሞች መስረቅ እንደ ጥፋት አይቆጠርም፡
እነዚህ ሃብታሞች የሰበሰቡት ሃብት አይገባቸውም ባይ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ህይወታቸውን በሙሉ የአንድ ቀን ስራ እንኳን ሰርተው አያውቁም፡፡ ከነዚ ሰዎች ገንዘብ መስረቅ ናዚዎችን እንደመግደል ይቆጠራል እንደወንጀል
ሳይሆን ለህዝብ እንደሚሰጥ አገልግሎት።
ይህን የስርቆት ተግባር ከጀመረ ሁለት አመት ያህል ሆኖታል፡ ነገር
ግን በዚህ ከቀጠለ አንድ ቀን መያዙ እንደማይቀር ተገንዝቦ ሌላ ስራ
መፈለግ ሲያስብ ጦርነቱ ከተፍ አለለት፡
ምንም ቢሆን በመደበኛ ወታደርነት መቀጠር አይፈልግም፡፡ አሸር ባሽር
ምግብ፣ ዩኒፎርምና ወታደራዊ ስነ-ስርዓት የእሱ ዕጣ ክፍሎች አይደሉም ሆኖም የአየር ኃይል ዩኒፎርም ይማርከዋል፡፡ አይሮፕላን አብራሪ መሆን ይፈልጋል፡፡ እንዴት እንደሚፈፅመው ባያውቅም ያደርገዋል፡፡ እሱ እንደሆነ
እድለኛ ነው፡፡
ሬቤካን ርግፍ አድርጎ ከመተዉ በፊት እሷን ተጠቅሞ አንድ ሁለት
የሀብታም ቤት መዝረፍ ፈልጓል፡፡
ሰር ሲሞን ሞንክፎርድ የተባሉ ሀብታም የመጽሐፍ አሳታሚ ቤት
ለግብዣ ተጠርተው ሄዱ፡ ሄሪ ክብርት ሊዲያ ሞስ ከተባለች እመቤት ጋር ወሬ ጀመረ፡፡ እመቤቲቷ ብቻዋን ስለነበረች ለአንድ ሃያ ደቂቃ ያህል
አጫወታትና ወደ ሬቤካ ዞረ፡ ከዚያም ጊዜው አሁን ነው ብሎ በመገመት ተንቀሳቀሰ፡፡
ሁለቱን ወይዛዝርት ይቅርታ ጠየቀና ከዳንሱ አዳራሽ ወጣ
የሚቀጥለው ፎቅ ላይ ወጣና ኮሪደሩን ይዞ ሄደ፡፡ ኮሪደሩ መጨረሻ አንድ ትልቅ መኝታ ክፍል አገኘ፡፡ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል አንድ ሰው ‹‹ምን ነበር?›› አለው፡፡
‹‹እዚህ ነው?›› ብሎ ጠየቀው
‹‹ምኑ?››
‹‹መፀዳጃ ቤቱ?››
ወጣቱ ሰው ከቁጣው መለስ አለና ‹‹አሃ ገባኝ፤ መፀዳጃ ቤቱ ኮሪደሩ
ጥግ ነው የሚገኘው›› አለው፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለሁ፡››
‹‹ምንም አይደል››
ሄሪ ወደ መፀዳጃ ቤቱ እየሄደ ‹‹በጣም የሚያምር ቤት ነው›› አለው ወጣቱን፡፡
‹‹አዎ›› አለና በደረጃው ወርዶ ሄደ ወጣቱ፡
ሄሪ በእፎይታ ፈገግ አለ፡፡ ወጣቱ ሰው መሄዱን አረጋገጠና ወደ
መኝታ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፡
መኝታ ቤቱ የእመቤት ሞንክፎርድ ሲሆን የመልበሻ ክፍልም እንዳለው
ሄሪ ተመለከተ፡ ቀጥሎ ደግሞ የወንድ መልበሻ ክፍል አለ፡፡ ሀብታም ባልና ሚስቶች የየራሳቸው መኝታ ክፍል አላቸው፡፡ ይህም የሆነው ከሰራተኛው
መደብ ያነሰ ወሲባዊ ፍላጎት ስላላቸው ይሆን?› ሲል አሰበ፡፡
ሄሪ የሰር ሲሞን መልበሻ ክፍል ገባና የኮሞዲኖውን መሳቢያ ከፈተው፡፡መሳቢያው ውስጥ በተለያዩ ጌጣጌጦችና አምባሮች የተሞላ ከቆዳ የተሰራ
የጌጣጌጥ ማስቀመጫ ሳጥን አገኘ፡፡ ብዙዎቹ ጌጣጌጦች ተራ ቢሆኑም ከነዚያ ውስጥ ግን ከወርቅ የተሰሩ የእጅ አምባሮች ላይ አይኑ አረፈ፡ አምባሮቹን
ኪሱ ጨመራቸው፡፡ ከጌጣጌጥ ሳጥኑ ቀጥሎ ውስጡ ሃምሳ ፓውንድ የያዘ የቆዳ የኪስ ቦርሳ አገኘ፡፡ ከቦርሳው ውስጥ ሃምሳ ፓውንድ ወሰደ፡፡ ብዙ ሰዎች ሃያ ፓውንድ ለማግኘት ከሁለት ወር ያላነሰ ከባድ የፋብሪካ ስራ
መስራት ያስፈልጋቸዋል፡፡
በየሄደበት ያገኘውን ሁሉ አይሰርቅም፡፡ የተወሰነ ዕቃ ብቻ መስረቅ ጥርጣሬ ይፈጥራል። ሰዎች ዕቃ ጎድሎ ሲያዩ ጌጣጌጡን ሌላ ቦታ እንዳስቀ
መጡት ወይም ቦርሳ ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ እንደነበራቸው ማስታወስ ስለሚያቅታቸው ስርቆት ተፈፅሟል ብለው ለፖሊስ ሪፖርት አያደርጉም፡፡
መሳቢያውን ዘጋና እመቤት ሞንክፎርድ መኝታ ክፍል ዘው አለ፡፡
የያዘውን ይዞ ለመውጣት ቢመኝም ትንሽ ደቂቃዎች እመቤቲቱ ክፍል
ቢያጠፋ ወደደ፡፡ ሴቶች ከባሎቻቸው የተሻለ ጌጣጌጥ ይኖራቸዋል፡፡ እመቤት
ሞንክፎርድ ደግሞ ዕንቁ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ሄሪ ደግሞ ዕንቁ ነፍሱ ነው፡፡
የምሽቱ አየር ምቹ በመሆኑ መስኮቶቹ በሙሉ ተከፍተዋል፡ በቀጥታ መልበሻ ክፍል ውስጥ ገባና ጌጣጌጡ ያለበት ኮሞዲኖጋ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ሁሉንም መሳቢያዎች ሲከፋፍት የተለያዩ የጌጣጌጥ ሳጥኖች እና ትሪ ሙሉ
ጌጣጌጥ አገኘ፡፡ የበር መከፈት ድምፅ ለመስማት ጆሮውን ቀስሮ እያንዳንዱን የጌጣጌጥ ሳጥን ፈተሸ፡፡

#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ሦስት ወራት አለፈ" ካርለት በሐመር ቆይታዋ ብዙ ልምድ አካበተች ያልጠበቀችውንም እርካታ አገኘች ካርለት ከሎን ወደ ዲመካ፣ ቱርሚና ጂንካ ከተማ ሲሄዱ እግረ መንገዷን መኪና ማሽከርከር ስላስለመደችው መረዳዳት
ጀምረዋል" ካርለት በሐመር ኑሮዋ ዕቃዋን፣ ገንዘቧን ለማስቀመጥ የምትተማመነው በመኪናዋ ውስጥ ነው፤ በተለይም ሙዚቃ ለማዳመጥ መኪናዋ ከፍተኛ ጥቅም ትሰጣታለች" በነዳጅ በኩል እስከዚያ ወቅት ድረስ ችግር አላጋጠማትም፤ ካስፈለጋት ግን ጂንካ ከተማ ናፍታ ማግኘት እንደምትችል ተረድታለች።
የሐመር ሰማይ ጥርት ያለና አልፎ አልፎ ብን ያለ የጥጥ ባዘቶ መሳይ ዳመና ይታይበታል” የዝናቡ ወቅት፣ እምብዛም የሚያስተማምን ባይሆንም፣ ድንገት እያጓራ የሚያጋሽብ ጥልመት ዳመና ከታየ «አህያ» የማይችለው ዝናብ፣ መዓቱን ያወርደዋል" በዚህ
ወቅት የዕጽዋት ቅጠሎች እንደ በረዶ ብን ብን እያሉ ሲወድቁ ከብቶች ጅራታቸውን ሸጒጠው፣ ጆሮአቸውን ይጥላሉ።
በዚህ ወቅት፣ የከሰኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ዛፍ ቅጠሉን እያተራመሰ፣ ባሕርይውን ይቀይርና በመደንፋት፣ እየተነሣ ይፈርጣል"
በዚያን ጊዜ ከሰኬ ወንዝና የሐመር ማኅበረሰብ፣ ከብቱ፣ ፍየሉ፣ ይኰራረፋሉ «አትድረስብኝ» አንመጣብህም ይባባላሉ"
አንድ ጊዜ፣ ካርለትና ከሎ መዝነቡን ሳያውቁ ከጂንካ ወደ ሻንቆ ሲሄዱ፣ ከሰኬ ወንዝን በመኪና ገብተው ሊሻገሩ ሲሉ መኪናዋ
በአሸዋው ተያዘች እነሱም ከመኪናቸው ወርደው በዶማና አካፋ
ለማውጣት ሲሞክሩ «ፉ..ፉ..ፉ.» የሚል ድምፅ ሰሙ። ቀና ሲሉ ደረቱን ገልብጦ፣ የሚጣደፍ ደራሽ ውኃ ተመለከቱ። ካርለትና ከሎ ብርክ ይዟቸው እንደ ሕፃን ልጅ ተንቦራቹ። ውኃው ግን ገሰገሰ ካርለትና ከሎ ዳር ላይ ሊደርሱ ሲሉ ውኃው ሲያጠናግራቸው
ተንገዳገዱ፤ ሳያስቡት እጅ ለእጅ መያያዛቸው ግን በጃቸውና ለትንሽ
አመለጡ። ደራሽ ውኃው መጀመሪያ መኪናዋን እያነቃነቀ ፈተሻት፣
ቀጥሎ በጎኗ፣ ከዚያም በጭንቅላቷ አቆማት።
«አምላኬ!» አለች፣ ካርለት መኪና የሚያገለባብጠው ውኃ እነሱን ቢያገኝ እንዴት ብትንትናቸውን እንደሚያወጣቸው እያሰበች።
ዛፉ «ቋ..ቀሽ.."ቀሽቀሽ...» ይላል፤ ግንድና ቅጠሉ ብቅ–ጥልቅ ይጫወታሉ፤ ውኃው፣ ሣር ቅጠሉን ያግበሰብሳል" መኪናዋ ጎማዋ ሲታይ ቆይታ በጎኗ ተጋደመች። ደራሽ የውኃ ሙላቱ ግን ለማንም
በሚያስገርም ሁኔታ እየቀነሰ፣ እየቀነሰ መጣና ጸጥ አለ። ካርለትና
ከሎ መኪናዋን ማውጣት ባለመቻላቸው፣ በየቦታው የተገነደሰውንም
ግንድ ለብቻቸው ማነቃነቅ የማይሞከር በመሆኑ፣ የሻንቆን መንደር
ኗሪ በእግር ሄደው ጠርተው፣ በስንት ችግር መኪናዋን ሊያወጡ
ቻሉ" ስለዚህ፣ ሐመር ላይ ዝናብ ሲዘንብ ከስኬ ሰው፣ ከብት፣ መኪና ሳይቀር ስለሚወስድና ስለሚያሰምጥ ምሱን አያጣም፤ ከብቱን፣ አራዊቱን፣ ሰውን...ድንገት ጠልፎ በመዋጥ የቆየ ልምድ አለው። ካርለትና ከሎ በቆይታቸው የተለያዩ ዕጽዋትንና ጥቅማቸውንም ተረድተዋል። ወንዴና ሴቴ ቃጫ ለገመድና ቤት ሥራ፣
ጠዬ ለዱላ፣ ሌልሜ ለቤት ሥራ፣ ፌጦ ለመፋቂያ፣፣ ኩንኩሮ ለተለያየ ጥቅም፣ ፊላና ሰንበሌጥ ለቤት ሥራ እንደሚውሉ ተረድተዋል።
በተረፈ ጨው ሊንባ፣ እንኮይ፣ ዘምባባ፣ አጋም፣ ጨዋንዛ፣ ግራር
ወዘተ የሐመርንና የአጐራባቾችን መሬቶች አስውበው ሲመለከቱ፣
ከመንፈስ እርካታው በተጨማሪ አንዳንዶቹን መጠቀም ችለዋል።
ካርለትና ከሎ ሻንቆ፣ ላላ፣ ወሮ፣ ዴንባይቴ፣ ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዴ...መንደሮች ሲዘዋወሩ ከማኅበረሰቡ
አባላት ጋር ከሚገናኙበት አንዱ ሸፈሮ ቡና (የቡና ገለባ) የሚፈላበት
ወቅት ነው። የሐመር ቡና የሚፈላው በጀበና ሳይሆን በትልቅ እንስራ ነው ቡናው የሚጠጣው ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ ረፋዱ ድረስ
ሲሆን፣ ያደረሰው ሁሉ መጠጣት ይችላል። አንድ ጊዜ ታዲያ፣ ካርለትና ከሎ ሻንቆ መንደር ለመጀመሪያ
ጊዜ ቡና ሊጠጡ ሄደው፣ ኦይጊ የተባለችው የመንደሩ ኗሪ ቤቷ ለመጡት እንግዶች በሾርቃ ከትልቅ ቅል ላይ በተከፈለ መጠጫ
ለሁሉም እንግዳ ስታድል፣ ለሁለቱም ሰጠቻቸው" ካርለት አንዱን
ሾርቃ እንደምንም ጨርሳ ‹ተገላገልኩ› ብላ፣ ሾርቃውን ለአይጊ አቀበለቻት በሐመር ባህል ሾርቃውን ቡናውን ለምትቀዳው ካቀበሉ
ድገሚኝ እንደማለት በመሆኑ፣ ኦይጊ ቡናውን በሾርቃ ሞልታ ለካርለት ሰጠቻት፤ «አምላኬ!» አለች ካርለት የመጀመሪያው ቋቅ
ሊላት ደርሶ፣ ሁለተኛውን ስታስታቅፋት።
ካርለት፣ ቡናውን መጠጣት ከበዳት። ቁጭ አድርጋ ትታ
እንዳትሄድ፣ ባህሉን መናቅ እንዳይሆንባት ሠግታ ስትጨነቅ ቡናውን
በያዘው ሾርቃ ላይ ዝንቦች እየገቡ ተንሳፈፉ። ካርለት፣ «ጥሩ አጋጣሚ» ብላ፣ እየሣቀች፣ «ዝንብ ገባበት» በላቸው አለችው ከሎን!
«ድፊው» ይሉኛል ብላ። እነሱ ግን፣ «ጠጭው ምንም አይልሽም፣
ይሄ የወተት እንጂ፣ የቆሻሻ ዝንብ አይደለም» አሏት። ካርለት፣ ሌላ አማራጭ ስላልነበራት የሚንሳፈፉትን ዝንቦች «እፍ» እያለች
ቡናውን ጠጥታ ጨረሰች።
ካርለት በሐመር ኑሮዋ በጣም የከበዳት ችግሯ ግን የሐመሮች የጊዜ ዕውቀት አለመኖር ነው። ካለፕሮግራሟ በተለይ በገበያ ቀን ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ቀይአፈርና ጂንካ በመኪናዋ እንድትወስዳቸው
ይጠይቋትና መኪናዋ ውስጥ ዱቄት፣ ፍየል፣ በግ፣አረቄ፣ ማርና ቅቤ
ሰለሚጭኑ ሁሌ ትሳቀቃለች" አንዳንዴም አፍ አውጥታ! «አልሄድም» ትላለች።
ካርለት ምግብ፣ ደብዳቤ፣ መጽሔት፣ ከቤተሰብ ጋር የስልክ ግንኙነት ለማድረግ አዲሳባ ስትሄድም በጕዞው ከሎ ሆራ መኪና
ማሽከርከር ቢረዳትም ወንዝ እየሞላ፣ ጭቃ ሲይዛቸው ትማረራለች።
ካርለትና ከሎ ወደ አዲሳባ ሲሄዱ አልፎ አልፎ የሚላኩት መልእክት የተወሰነ ሲሆን አቡጀዲ፣ የላስቲክ ጫማ፣ ሸፈሮ ቡና
ሽጉጥ መሳይ መድኃኒት «ቴትራሳይክሊን ወይም ክሎሮፌኒኮል”ዋነኞቹ ናቸው"
ካርለት ሐመር ሦስት ወር ቆይታ አዲሳባ እንደሄደች፣ ከስቲቭ ጋር ተገናኙ። ስለ ሐመር ሕይወቷ፣ ስላየቻቸው ነገሮች፣ ስላጋጠማት ችግርና ስለ ወሰደችው የመፍትሔ እርምጃ አጫወተችው
ስቲቭ ከነገረችው ሌላ፣ ካርለት አንገቷና እጇ ላይ ያለውን ነገር ከማየቱም ባሻገር፣ ሳታቋርጥ ስታክ ተመለከታት» ከዚያም፣ «የኔ
ፍቅር፣ ይህን ያህል ለምን ራስሽን ለችግር ታጋልጫለሽ?» አላት
ስቲቭ"
«ችግር ስትል ምን ማለትህ ነው?»
«ይህ ደረሰብኝ እያልሽ ያወራሽኝ ሁሉኮ ጋሪ ላይ የተጫነ ጭነት ሳይሆን፣ አንች የተሸከምሽው ችግር ነው?» አላት"
«ስቲቭ፣ አንድ ሰው የምኖረው ትርጕም ያለው ሥራ ለመሥራት ነው ካለ፣ ሕይወቱም ትርጕም ያለው ይሆናል" ሌላው ደግሞ
(ምኖረው ለመሞት ነው› ካለ በውስጡ እውነትነት አለው” ሕይወቱ ግን፣ ትርጕም አልባ ይሆንበታል"
«ማንኛውም አጋጣሚ በየግላችን አእምሮ አመዛዝነን፣ መክረን፣
እናወጣ እናወርደዋለን፣ ቀጥሎ ጥሩ ወይም መጥፎ ትርጕም እንሰጥና ተግባሩ ላይ ያን አጋጣሚ እንጠላዋለን ወይም እንወደዋለን።
«አንዱ መኖርን ጥሩ ሥራ ለመሥራት እንደሆነ ተረድቶ ሲጥርI ሌላው ደግሞ መኖሩ ለመሞት መሆኑን አውቆ ተስፋው ይኰሰምናል"

#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ
ከአዲስ አበባ ፍልውሃ በታች ከማህተማ ጋንዲ መንገድ መስመር ከብሔራዊ ስታዲዬም ብዙም ሳይርቅ ከግዮን
ከኢትዮጵያ ከሒልተን
ሆቴል... ለሚመጡ እንግዶች አመች የሆነው የ“ጎጆ” ምግብ ቤት ግቢው በመኪና ተጣቧል።
ቢኤም ደብሊው መኪና በዘበኛው መሪነት ቦታዋን ይዛ እንደቆመች ሁለቱ እንግሊዛውያን ወደ ምግብ ቤቱ አመሩ። እሷ ቀደም እሱ ደግሞ ከኋላዋ ተከትሏት ሲገባ እንደ ቀልድ ቁመናዋን አስተዋለ: ፀጉሯ አጠር ከማለቱ ሌላ ስትሄድ የሚደንሰው ዳሌዋ አለ
'' የለም' »አስኝቶ የሚያወራርደው ወገቧ
ያው ነው።ስትጠመጠም እንደ ላስቲክ እየተሳሳበ በሰራ አካላቱ የሚስለከለከው አካሏ ለውጥ የለውም። ልክ እንደ ዛሬ ሁለት ዓመት ከስድስት ወሩ ነው ጥቁር ቲሽርት እንደ ወትሮው ሁሉ ጂንስ ሱሪ ለባብሳለች።ወገቧና አንገቷ ልብሷ አልደረሰበትም:
የሴት እምብርት ሲያይ ጎሮሮውን እንዳነቁት ሁሉ አይኑ የሚፈጠው ስቲቭ አጎጠጎጤ ጡቷን ደረቱ ላይ አስደግፋ ለጠጥ ብላ
ሽቅብ ተስባ ስትስመው እንደ ህፃን ልጅ በእቅፉ አልሞላ ስትለው እቅፉን ጠበቅ አድርጎ እንደ ቄጤማ አካሉ ላይ የለጠፉት ትዝ
አለው።
ገባ ብለው ክፍት ቦታ ሲያማትሩ አስተናጋጁ በስተግራ በኩል ግድግዳው ጥግ ባዶ ቦታ አሳያቸው።
የሲሊን ዲዮን ዜማ በለሆስታ ይሰማል ካርለት ድምፀ መረዋ ካናዳዊት አቀንቃኝ ስሊን ዲዮን ኒወርክ “ብራንድ ዌይ
ዳንሰሮች ጋር አይኖቿዋን እያስለመለመች, እግሮችዋን መሬት
ለመሬት እየሳበች ወለሉ ላይ እየተኛች...በለበሰችው ጃፖኒ እርቃን የሆነውን ትከሻዋን እየላሰች ስትዘፍን ስላየቻት ይበልጥ ወዳታለች::
እና! ገና "ከመግባታቸው በፊት የምትወደውን ዜማ ስትሰማ የደስታ ስሜት ተሰምቷታል።
አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ይዞላቸው መጣ: ሁለቱም
ዝርዝሩን ተቀበሉና በፀጥታ አንብበው ካዘዙ በኋላ ጨዋታቸውን ሊጀምሩ ሲሉ
“የሚጠጣስ?” አይኖቹን ግራና ቀኝ እያዟዟረ ጠየቀ
አስተናጋጁ።
“ማርቲኒ” አለችው ካርለት
“ነጭ ወይንስ ቀይ ማርቲኒ” የሾለ ፊቱን ወደ ፊት አስግጎ ጠየቃት።
ነጭ ይሁንልኝ አለችው። አስተናጋጁ ለጨዋታ
መጣደፋቸውን ተረድቶ ይቅርታ በሚጠይቅ አስተያየት ስቲቭን
እያየ አገጩን ሽቅብ ሰበቀ።
“ብሳክ ሌብል” አለው።
ካርለት ቦርሳዋን ወንበሩ ላይ አንጠልጥላ ፈገግ እያለች።
“እሺ ስቲቭ! ስትለው ስቲቭም ወንበሩ ላይ ጠረዼዛው እያስጠጋ ፈገግ ብሎ አንገቱን ወዘወዘ ደህና ነኝ ለማለት።
“…ኢንግላንድ መልም ጊዜ አሳለፍሽ?
“ከናቴ ከጓደኞቺ ጋር በመገናኘቴ ደስ ብሎኛል። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ግን ደስተኞች አይደሉም:: ሁሉም ያለሙትን ህይወት
መኖር የቻሉ አልመሰለኝም። ከጎይቲና ከከሎ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜም ባመዛኙ እንግዳ ለሆነባቸው ስልጣኔ እያንዳንዷ እንደ ህፃን
ልጅ ማስረዳቱ አድካሚ ቢሆንም ወድጄዋለሁ:
“ጥናቴን በተመለከተ ማንቸስተር ያቀረብሁት ዝግጅት ለአማሪዬና ስብሰባ ተሳታፊዎቼ ጥሩ ስሜት የፈጠረ በመሆኑ ደስ ብሉኛል። ከዚህ ተጨማሪ ከማንቸስተር ዩንቨርስቲ አዳራሽ ስንወጣ ብዛት ያላቸው የ" ጋርዲያን የሄራልድ ትሪቡን…
ጋዜጠኞች ለኔ ለጎይቲና ለከሎ ያቀረቡልን ጥያቄ የሰጠነው መልስ በቤቱ ውስጥ የነበረው የመግባባትና የማድነቅ እንድምታ ስቃይን እሚያስረሳ ነበር። “በተለይም ሴቶችን አስገድዶ መድፈርና
የወሲብ ብዝበዛ በሐመር ምድር የተወገዘና የማይፈፀም ፀያፍ ጉዳይ
መሆኑን ላስረዳቸውና ጎይቲ “ሴትን ያለፍቃዷ ማን ያስቸግራታል ደሞ." ያለችው ስሜታዊ አባባል ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው ውስጥ
ዋናው ነበር።
“በተረፈ ለአንድ ሳምንት ስፔን ለአንድ ሳምንት ደግሞ
ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሄጄ ነበር: እንደ ማይክል ጃክሰን በዚች ፕላኔት ካለው ወፈ ሰማያት ህዝብ መሀከል የማደንቀው ሁለት ሰው ነው:: ማንዴላንና ማር ትሬዛን ብዬ ባልደመድምም በደረጃ ከማይክል አስተያየት የማላርቀውን ማንዴላንና የሱን አመራር
በቅርብ ለማየት እድል ለማግኘቴ የተደሰተሁ ሲሆን በጆሀንስበርግ ሰሜን ማዕክል ብራምፎንቴን በሚገኘው ዊትስ ዩንቨርስቲ የአባቴ ስራዎች በመታሰቢያነት ሲቀርቡ ንግግር ማድረግ መቻሌሞ ጥሩ አባት ሞቶም የደስታ ምንጭ እንደሚሆን ለማመን ችያለሁ።
የነፃነት ረጅም ጉዞ በሚል
ርዕስ በ1994 ዓ.ም
በማክዶናልድ አሳታሚ ኩባንያ በኔልስን ማንዴላ የታተመው የ ባለ 617 ገጽ መጽሐፍም በመርፌ ቀዳዳ የሚታይን ብርሃን ተከትሎ
ከፀሐይ አካል መድረስ መቻሉን የተማርኩበት ነበረ።
“የፍቅር ህይወቴን በተመለከተ ግን እግሮቼ ሁለት መሰላል ላይ ናቸው:: ባል የማግቢያዬ ልጅ የመውለጃዬ ጊዜ እያለፈ
መሆኑን ሳስብ አንጀቴ በሃዘን መኮራመቱ ባይቀርም የሰለጠነው
ዓለም ለፍቅር ቀረቤታ ያለው አነስተኛ ግምት የመመዘኛ ዝባንዝንኬው በተፈጥሮው ዓለም ደግሞ ህይወቱን ላልኖረው ሰው
ያለው አስቸጋሪነትና የፍቅር አለመጣጣም... ለጊዜው መምረጥ ከሚያስቸግር ሁኔታ ላይ እንደጣለኝ ነው የምረዳው።
“እዚህ ላይ ግን ልገልፅልህ የምወደው እንደማንኛውም
ሰው መጭው ህይወቴ ምን መምሰል እንዳለበት ሳስብ ብዥ ብዥ እያለ የሚታየኝ ህልም አስጨናቂና አሳሳቢ ቢሆንም ከምንም በላይ
የምፈልገው በአባቴ የሰው ልጅ ሕይወት ምርምር ጎዳና መጓዝንና ለሙያዬ መሉ መስዋዕትን መክፈል ስለሆነ መፅናኛዬ ሚዛኍን
የደፋ ነው፡፡ ስለዚህ ደስተኛነቴ አሁንም ከቁጥጥሬ አልወጣም ብላ
ፈገግ አለች::
ስቲቭ ሃሣቧን ያዝኩት ሲል ወዲያ ስታላጋው ወዲህ
ስታጋጨወ ቆይታ እንደ ጥሩ ተውኔት ጨዋታውን ባላሰበው መንገድ ደመደመችበት።
ለጥቂት ጊዜ ሁለቱም በየግል ሃሣባቸው ተውጠው እንደቆዩ ፈጣኗ ካርለት ከነበረችበት የሃሣብ ግልቢያ ድንገት ልጓሟን ስባ የስቲቭን ቀኝ እጅ በቀኝ እጅዋ ቀስ ብላ ጫን አድርጋ
ሳታስደነግጠው ሳታሽብረው ሃሣቡን ሳታምታታበት ትክ ብላ
መረጋጋቱን ካስተዋለች በኋላ፡-
“ስቲቭ! አንተስ ከተለያዬን በኋላ ጥሩ ጊዜ አሳሰፍክ?"
አለችው።
ዘናና ፈገግ ብሎ “በስራዪ ብዙም ውጥረት አልነበረኝም የዲፕሎማት ትልቁ ሥራ ግንኙነት መፍጠር፤ የአገሪቱን
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አዝማሚያ መከታተል፤ ተስፋን መመገብ ገደብ አልባ የሆነ ቃል ኪዳን መግባት በመሆኑ በፈቀደልኝ የጉዞ ፍጥነት እያሽከረከርኩ ስራዬን ለመወጣት ሞክሬያለሁ፡ የኢትዮጵያ ኑሮ ግን ከብዶኛል" አላት
እንዴት? የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ!" አለችው ውስጡን
ጠልቃ ለመመልከት አይኖቹን እየፈለገች።
ካርለት የሰዎችን አይን በማየት ስለ ሁኔታዎች ምንነት ለማወቅ እንደሚቻል በስነ ልቦናዊ ትምህርቷ ታውቃለች። አንድ ሰው ያስጨነቀው ነገር ትዝታውን• ፍቅሩን ጥላቻውን... ሲገልፅ
የአይኖቹ ኳሶች የት እንደሚሆኑ ወዴት እንደሚዞሩ ከስነ አዕምሮ
ባለሙያዋ እናቷ ተምራለች። ሌላው ቀርቶ እውነትና ውሸት አባባልን የአይንን እንቅስቃሴ አይታ በከፊል መግለጽ ትችላለች።
ከዚህ በተጨማሪም የአንድ ሰው አመለካከቱ በመስማት ወይንም በማየት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ከአገላለፁ በመረዳት አይኑና ሃሣቡ ከሚሰጣት ግንዛቤ ግንኙነቷን ለመመዘንና ለመለካት
አትቸገርም። ለዚህም ካርለት ስቲቭ ሲያወራት አይኖቹን ትፈልግ ነበር: ኋላ ግን አይኑን በአይኗ ያዘችው እንቅስቃሴዋንም
አስተከለችና፡-
"...የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ? አለችው ደግማ ስቲቭ
በአፍንጫው ጫን አድርጎ ተነፈሰና፡-

#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
...በሙዚቃው ደነስኩ.. ውልቅልቅ እስክል ውስኪውን አንጠፍጥፌ ጠጣሁ"..አዎ አውቃኛለች... ፈፅሞ አልረሳችኝም...ከሁሉም ያስደሰተኝ ደግሞ ‹‹ቀናህ!!!›› የምትለዋ ቃል ነች...ምክንያቱም ቅናት እነጠቃለሁ ብሎ ከመፍራት ጋር ወይም ከመሠሠት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስሜት ነው።ፍርሀትም ስስትም ምንጫቸው ፍቅር ነው...እርግጠኝነት ከጎደለው ፍቅር።እና ታፈቅረኛለህ እያለችኝ ነው?ግን እንዳዛ ስላሰበች ለምንድነው እንደዚህ የፈነጠዝኩት? የእውነት እያፈቀርኳት ይሆን እንዴ ? እንዴ ከነጠላ ስሞ ሌላ ስለእሷ ምንም የማላውቃትን ሴት እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? ግን እኮ ፍቅር የኋላ ታሪክን አጥንቶ የወደፊት መድረሻን ገምቶ አሁን የቋሙበትን ድልዳል በሚዛን መዝኖ የሚገባበት የምክንያትና ውጤት ቁርኝት ማሳያ አይደለም..?ፍቅር ጨርቁን እንደጣለ ዕብድ ነገረ ስራው ቅፅበታዊና ተአምራዊ ነው።ስለዚህ ሳላቃትም በፍቅሯ ብወድቅ የሚደንቅ አይደለም!ግን ዕድሜዋ ጉዳይስ? ቢያንስ 10 አመት ትበልጠኛለች? እርግጥ በዕድሜ ሰላሳም ሀምሳም የምትበልጠውን እንስት ማፍቀር የተለመደ ነው?ቢሆንም ግን ቢገለበጥ ነበር የሚያምረው ..እኔ 10 አመት ብበልጣት።
ወየጉድ አሁንኮ ነገረ ስራዬን ላየ የመጀመሪያ የፍቅር አይነጥላዬን ገና እየገለጥኩ ያለው ጀማሪ አፍቃሪ ነው የምመስለው ፤ግን እኔ ቢያንስ አምስት አጫጭር ጣፍጭ ለወግ የሚበቁ እና አንድ ረጅም የተወሳሰበ ልቤንም ቅስሜንም አብሮ እንቅሽቅሽ አድርጎ የሠበረ.. በአለንጋ ተደጋግሞ በመገረፍ የተነሳ ትላልቅ ተጠላላፊ ሰንበር እንደተጋደመበት ጀርባ የእኔም ልብ በዛ ፍቅር ምክንያት ዙሪያ ጥምጥም የዞረበት ጠባሳ የተጋደመበት ሆኗል...
"ያ ፍቅር ህይወትን አስተምሮኛል ?ያ ፍቅር ደስታን አሳይቶኛል...?ያ ፍቅር ዘመዶቼን አሳጥቶ የከተማ ስደተኛና ምፅተኛ አድርጎኛል...ያ ፍቅር በራስ መታመኔን እንቅሽቅሽ አድርጎ የህይወት መስመሬን ከላይ ወደታች ገለባብጦታል…ያ ፍቅር ዛሬ ቢቋረጥም ግን ትዝታ ብቻ ሆኖ የቀረ እንደይመስላችሁ፡፡ ዛሬም ጣጣው እያደነኝ ነው...፡፡
እስከህይወቴ ፍፃሜ እንደተጣባኝ የሚዘልቅ ይመስለኛል። ...ይሄው ስድስት አመት ሞላኝ ባዶ ሆኜ መኖር ከጀመርኩ ...እና አሁን የማፍቀር ስሜት ሲሰማኝ የተገረምኩት ለዛ ነው።እውነት እርቃን ገላዋን ስላሳየችኝ ...ተዳፍኖ የኖረው የወሲብ ስሜቴ ስለተወጣጠረ ነው የተምታታብኝ። ግን አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከለል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል፤ ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ...የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር እስከ እርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች ስለሆን ይሆናል።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል..ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር ከቃላት ልውውጥ እና ከአይን መሠራረቅ ላያልፍ ይችላል፤ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቋረጥ ይችላል..እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ አለ?።
ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ ስላለቀ ነው ብለን መደምደም አንችልም... አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው ጉዞቸውን በተለያየ ጎዳና ሊቀጥሉ የሚገደዱባቸው አያሌ አጋጣሚዎች አሉ። ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።
ወይ ጉድ ..በዚህች እንግዳ ሴት የተነሳ የፍቅር ኤክሰፐርት መሆን ዳዳኝ እኮ….ጠርሙሶ ውስጥ ያለችውን መጠጥ እያወዛወዝኩ ከሆቴል ወጣሁና በእኩለ ለሊት ወደቤቴ ገባሁ፡፡በፀጥታ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ….፡፡ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ፡፡
ጥዋት
..ከእንቅልፌ ባንኜ አይኖቼን ብገልጥም ቀልጠፍ ብዬ ከአልጋዬ መውረድ አልቻልኩም። ብነሳም ምን አልባት ምሳዬን ሰርቼ ከመብላት ውጭ ሌላ የምሄድበት ቦታ የለም ።ምሳ ደግሞ አላሰኘኝም፡፡ ምን አልባት ቁርሴን ከጋሽ ሙሉአለም የተሠጠኝን ቋንጣ ፈርፍር በደንብ ስለበላሁ ይሆናል። ተንጠራራሁና ከኮመዲኖዬ ላይ rich Dad poor Dad የሚለውን መፅሀፍ አነሳሁና ማንበብ ጀመርኩ .. አንድንም አባት የሌለው ሰው ሁለት አባቶች ያሉት ሰው የፃፈውን መፅሀፍ ለማንበብ መቋመጡ የሚገርም ነው። ብቻ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሁለት ገፅ ሳላነብ ስልኬ ጠራ አነሳሁና አየሁት..፡፡
የማላውቀው ቁጥር ነው ፡፡ላንሳው ልተወው ተወዛገብኩ።በስተመጨረሻ አነሳሁት
‹‹ሄሎ»
"ሄ...ሎ"ጥፍጥ ያለ የህፃን ድምፅ...ደነገጥኩ፡፡
‹‹ሄሎ..ሄሎ ..ማን ልበል?"
«ተአምል...ነኝ»
"ተአምር"የተኛሁበት የእንጨት አልጋ ከስር እርብራብ ተቀንጥሶ ይዞኝ ወደታች እየሰመጠ መሠለኝ...፡፡ስልክ ባልያዘው ቀኝ እጄ ፍራሹን ጨምድጄ ያዝኩ....፡፡እለተ መፅአት የፊታችን እሁድ መሆኑን ተረጋገጠ የሚል አዎጅን አስከትሎ የነጋሪት ጉሰማ ብሰማ ራሱ እንዲህ ሰማይ ምድሩ አይዞርብኝ፡፡
ልጅቷ ኩልትፍትፍ ባለ ድምፅ ንግግሯን ቀጠለች
"አዎ ተአምል...ል..ጅህ"
ይሄ መቼስ ተአምር ነው....፡፡ ተአምር አሁን ስምንት አመቷ ነው።በአካል ከተያየን 6 አመት አልፎናል።ማለቴ ቀጥታ በአካል ያየዋት አቅፌ የሳምኮት :ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ስታለቅስ ያባበልኮት የዛሬ ስድስት አመት ገና ክፉና ደጉን በቅጡ መለየት ባልቻለችበት ጊዜ ነው። ለዛውም እንደአባትና እንደልጅ እኮ አይደለም እንደ እህቴ ልጅ...እንደአጎቷ ሆኜ..፡፡ለምን እንደዛ ሆነ የእውነትም አጎቷ ስለሆንኩ፤ እንደዛም ስለመሰለኝ...፡፡ከዛ ወላጆቾ የውጭ ፕሮሰስ ጀምረው ስለነበር ተአምር ዲ.ኤን. ኤ ምርመራ ማድረግ ግዴታ ሆነ …ተመረመረች...ውጤቱ ለቤተሠብ በሀይለኛ መብረቅ የመመታት ያህል ድብ እዳና አስደንጋጭ ነበር... ልጅቱ የእህቴ ባል አይደለችም?
‹‹እንዴት ሆኗ...?"የህግ ሚስቱ እኮ ነች…፡፡››
"በተክሊል ነው እኮ የተጋብት"ብዙ ብዙ ተባለ... እኔ የምገባበት ጠፋኝ..ጠጋ አልኩና
በወቅቱ"ምስር ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ?››ብዬ ጠየቅኳት።
"አንተም እንደሌላው እንዴት ሆነ ብለህ ትጠይቀኛለህ?"
‹‹ምን ማለት ነው ?እንዴት አልጠይቅሽም?"
‹‹ያደረከውን ታውቃለህ ብዬ ነዋ ?››

#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
ብዙ ፍላጎቶች አሏት..ለዛውም ያልተገሩ ፍላጎቶች ።አንደኛውን ለማሟላት በቀኝ ትጓዛለች ..ሌላው ደግሞ ወደግራ ያስፈነጥራታል...እንዲሁ የፍላጎቶቾን ጭራ ተከትላ ከግራ ቀኝ ስትላጋ ትከርምና በስተመጨረሻ እራሷ ከራሷ ትጠፋለች‹‹...የት ነው ያለሁት?ምን እየሠራሁ ነው? ምንድነበር የምፈልገው?››የአንድንም መልስ መመለስ አትችልም.... ፍፅም ድንዛዜ ውስጥ ትገባለች።ነፍሷ በማጥ ተይዛ እዛው ጭቃ ውስጥ መውጣት አቅቷት የምትንቧጫረቅ ይመስላታል..‹‹.ጭቃ ውስጥ ገብቼ እንደዚህ እየዳከርኩ ያለሁት እኔ ነኝ ሌላ ሰው?›› ግራ ይገባታል...እራሷው ከእራሷ ትጠፋለች።አንድ ሰው እራሱ ጠፊ እራሱ ደግሞ ፈላጊ ሲሆን የሚፈጠረው ነገር?
ለሊቱ በመከራ ነው የነጋላት..ምን አልባትም በህይወቷ ካጋጠሟት እጅግ አታካችና ደባሪ ለሊቶች ውስጥ አንዱ ነው….አስራአንድ ሰዓት ከሆነ በኃላ ክፍሏ ውስጥ መቆየት አልቻለችም ፡፡ መኝታዋን ለቃ ወረደችና ቁምሳጥኗን ከፋፍታ ፊት ለፊት ያገኘቻውን ልብስ ያለምንም ማሰብ ለባበሰችና ስልኳንና የቃልን ላፕቶፕ በቦርሳዋ ከተተች፡፡ ከክፍሏ ይዛ ወጣች…በሩን ስትዘጋና ስትከፍት እናቷን እንዳትቀሰቅስና እሄዳለሁ አትሂጂም የሚል አተካራ ውስጥ ላለመግባት ብላ በጥንቃቄና በፀጥታ ወደታች ወረደች ፡፡ የሳሎኑን በራፍ ከፍታ ወጣች... ግቢው ውስጥ የለሊቱን መንጋት የሚያበስሩ ባለ ብዙ ቀለም ማራኪ ወፎች ከአንዱ ዛፍ ወደሌላው ዛፍ እየተሸጋገሩ ሲዘምሩ ከሚሰማው ተፈጥሮዊ ዝማሬ በስተቀር ሙሉ አካባቢው ፀጥ ያለ ነው፡፡ወደ ዘበኛው ቤት ሄደችና በስሱ አንኳኳች‹‹…..ማነው….?››የሚል ሻካራ ድምጽ ከውስጥ ተሰማ፡፡
‹‹ድምፅህን ቀንስ እኔ ነኝ?››
‹‹እትዬ ልዩ ምነው?››የ50 አመቱ ጎልማሳ እሷን የ23 አመቷን ልጅ እትዬ እያለ ሲጠራት ሁሌ እንዳስፈገጋት ነው…ብዙ ጊዜ ልዩ ብቻ ብሎ እንዲጠራት ነግራውም አስፈራርታውም ነበር..እሺ ይላል እንጂ በተአምር ተሳስቶ ልዩን ከእትዬ ነጠሎ ጠርቷት አያውቅም.. አሁንማ እሷም ለመደችው …
‹‹ድምፅ ቀንስ እኮ አልኩህ…ፈልጌህ ነው?››
‹‹እሺ እሺ..›› እየተደናበረ ወጣ፡፡››
‹‹ምነው…? ፈለግሺኝ….?››
‹‹መኪና ይዤ ልወጣ ነው፡፡››
‹‹ከማ ጋር?››
‹‹ከአንተ ጋር ››
‹‹ምን አልሺኝ እትዬ?››
‹‹ብቻዬን ነዋ…እዚህ አካባቢ በዚህን ሰዓት አብሮኝ ሊሄድ የሚችል ሰው ይታይሀል?..አሁን ክፈትልኝ…እስከዛ ሞተር ላሙቅ ››እለችውና መኪኖች ወደሚቆሙበት ስፍራ ሄደች…
ሶስት ሚኪኖች በተርታ ተጠጋግተው ቆመዋል፡፡ዝም ብላ የእናቷን ሰማያዊ ኮሮላ መኪና ውስጥ ገባች፡፡ያው በእነሱ ቤት ልምድ መኪኖች ግቢ ውስጥ ከገቡ በኃላ ቁልፋቸው አይነቀልም..ምን አልባት ኢመርጀንሲ ተፈጥሮ ቢፈለጉ ገና ቁልፉን ከቤት ወይም ከሹፌሮች ጋር ከመፈለግ መንዳት የሚችል ሰው ወዲያው ገባ ብሎ ይነዳቸዋል..ይህ ህግ የወጣው በእሷ ምክንያት ነው..፡፡ያው በተለያ ሰበብ ሁሌ አደጋ ስለማያጣት…ሹፌር ፍለጋና ቁልፍ ፍለጋ ህይወቷንም ጭምር ሊያሳጣት የደረሰ አጋጣሚ ተከስቶ ስለነበር ይሄ ውሳኔ ተወሰነ..እና ይሄው ዛሬ ለራሷ ረዳት…፡፡
ላፕቶፑን ያለበትን ቦርሳዋን ከጎኗ አስቀመጠችና ቁልፉን አሽከርክራ ሞተሩን አስነሳችው.‹‹.መቼስ እማዬ የመኪናውን የሞተር ድምፅ ሰምታ በመንቃት መጥታ እንደማትቀውጠው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››አለች
ዘበኛው በራፉን በልቅጦ ከፈተና እየተጎተተ ወደእሷ መጣ….. በአሳዛኝ ሁኔታ እየተቅለሰለሰ‹‹እትዬ ልዩ ግን አትዬ እንዴት እንደሚቆጡኝ እየታየኝ ሆዴ ተሸብሮብኛል…. ሊያባርሩኝ ሁሉ ይችላሉ፡፡›› አላት፡፡
ኪሷ ገባችና ድፍን ሁለት መቶ ብር በማውጣት በእጁ አስጨበጠችው… ‹‹ከሰደበችህ በዚህ ቻለው…ከባረረችህ ግን ደውልልኝ እኔ አስቆማታለሁ…›› አለችው፡፡
በደስታ ተፍለቅልቆ‹‹እሺ የእኔ ደግ..ይሁን እችለዋለሁ…በይ ሂጂ›››አለታ
መኪናውን አስነሳችና ግቢውን ለቃ ወጣች….መንገዱ ነፃና ምንም አደናቃፊ ስለሌለበት 25 ደቂቃ ነው የፈጀባት፡፡በራፉ ላይ ደርሳ የመኪናዋን አፍንጫ የግቢ በራፋቸው ላይ አስደግፋ አቆመች ..ሰአቷን ስታይ ሰውነቷ ቀዘቀዘ.. ‹‹በዚህ ሰዓት ለምን መጣሁ? ምንድነው የማደርገው..?›› ግራ ገባት…፡፡
‹‹በዚህ ለሊት እንደመርዶ ነጋሪ የሰው በራፍ አላንኳኳም፡፡የራሱ ቤት እንኳን ቢሆን የራሱ ጉዳይ….የኪራይ ቤት ለዛውም አሮጊት…..ምን አለ የዛን ቀን ስልክ ቁጥሩን ተቀብዬው ቢሆን.. አሁን ደውልለትና ቀጥታ መጥቶ ይከፍትልኝ ነበር….ከዛ ይሄንን ላፕቶፕ አፍንጫው ላይ ወርውሬለት የመኪናዬን መሪ ወደኃላ አዙሬ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይሄን ሰፈር እለቅ ነበር…ከህይወቴ እስከመጨረሻ አሽቀንጥሬ እወረውረውና ከእነመፈጠሩም እረሳው ነበር፡፡››ስትል አብሰለሰለች፡፡
የመኪናዋ መሪ ላይ ተደፍታ እነዚህንና መሰል ሀሳቦች እያሰበች ሳለ ባልገመተችው ሁኔታ የግቢው ትንሿ በራፍ ከውስጥ መንጓጓት ጀመረች…..ነቃ አለችና, ከተደፋችበት ተነሳች፡፡ በራፉ ተከፍቶ ነጭ በነጭ የለበሰች አንድ ሰትዬ ወጡ …አሮጊቷ የቃል አከራይ ናቸው፡፡አለባበሳቸውን ብቻ አይቶ ወደቤተክርስቲያን ሊሄዱ እንደሆነ መናገር ይቻላል…ከወጡ በኃላ ባልተለመደ ሁኔታ መኪና በራፋቸውን ታኮ መቆም እንዳስገረማቸውም እንዳስደነገጣቸውም ከሁኔታቸው መገመት ይቻላል፡፡…ልዩ ያንን ስለተረዳች ፈጠን ብላ ገቢናውን ከፈተችና በመውረድ ወደ እሳቸው ተጠጋች፡፡
‹‹ደህና አደሩ ማዘር …የቃል ጓደኛ ነኝ፡፡››
‹‹እ…የበቀደሞ ልጅ ነሽ;››
‹‹ቆቅ አሮጊት ናቸው››ስትል አሰበች… እንዲህ በፍጥነት ያውቁኛል ብላ አልገመተችም ነበር፡፡
‹‹አዎ..አውቀውኛል››
‹‹ታዲያ ሰላምም አይደለሽ…?ገና ለሊት ነው እኮ፡፡››
‹‹‹አዎ ከቃል ጋር 12.30 የሆነ ቦታ ለመሄድ ተቀጣጥረን ነበር …ሳላስበው ትንሽ ቀደም ብዬ መጣሁና ማንኳኳት ደበረኝ፡፡››
‹‹እና አትደውይለትም ነበር?››
‹‹ሞክሬ ነበር..ዘግቶታል መስለኝ አይሰራም››ውሸት መቼስ የተካነችበት ነው..ከልጅነቷ ጀምሮ በብቃት የምትሰራቸው ሶስት ነገሮች ሌብነትና ቅጥፈት እና ወሬ(የሰው ሚስጥር)ማነፍነፍ ናቸው…፡፡
‹‹ግቢያ ….በራፍን ልክፈትልሽና ሚኪናዋን ታስገቢያት?››
የበቀደምለታው ግልምጫ ከዛሬው መሽቆጥቀጥ ጋር አመዛዝና ፈገግ አለች፡፡በቀደም የዱርዬ ገፀ ባህሪ ተላብሳ ነው ፊታቸው የተጋረጠችው ዛሬ ደግሞ የሞጃ ልጅ .ስለዚህ አይፈረድባቸውም፡፡
‹‹…ግዴለም ማዘር እርሶ ይሂዱ እኔ ከፍቼ አስገባዋለሁ››አለቻቸው፡፡
‹‹እሺ ልጄ.ደህና ዋይ ..››.ብለው በራፍን ለቀውላት ወደፊት መራመድ ሲጀምሩ የእሳቸውን ቀልብ ምትማርክበት የሆነች ሸር ነገር ብልጭ አለችላት…ኪሷ ገባችና ድፍን ሁለት መቶ ብር አወጣች፡፡
‹‹ማዘር.. ››
‹‹አቤት ልጄ›› ባሉበት ቆሙና ፊታቸው ወደ እሷ አዞሩ..ሮጣ ሄደችና ተጠጋቻቸው.
.‹‹‹ይቅርታ ይቺን ሙዳይ ምፅዋት ውስጥ ያስገቡልኝና..ያሰበችው ይሳካላት ብለው ይፀሉልኝ፡፡››
ፊታቸው ሲፈካ በግልፅ ይታያታል…‹‹ልጄ ይሳካልሽ…. ተባረኪ… ወይ አንቺም እንደቃልዬ ነሽ መሰለኝ..ለመሆኑ ስምሽ ማነው?››ሲሉ ጠየቋት፡፡

#ህያብ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በኤርሚ
"ህያብ ያለፈ ታሪክሽ ምንም ይሁን ምን አንቺን ከማፍቀር ሊያቆመኝ አይችልም። የኔ ቆንጆ የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ?"
"ዮኒ.." ተርበተበትኩ... ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ፈገግ ብሎ እያዬን ነው። ፈገግታው ውስጥ ሁሉም ነገር ሰላም ነው የሚል መልዕክት ያነበብኩ መሰለኝ••• አበባውን ተቀበልኩ
ከዮኒ ጋር ህልም የሚመስሉ ሁለት ሳምንታትን አሳለፍን። ሁሉም ነገር በጣም ደስ የሚል ነበር እያንዳንዷን ቀን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍናት።
ጎንደርን ለቆ ወደ አዲስ አበባ የሚሄድበት ቀን ደረሰ እኔና ቢን ቀድመን ለመሰናበት አገኘነው።
ካፌ ተገናኝተን ሞቅ ያለ ወሬ እያወራን በመሀል ቢኒ
"ይህን ሁሉ ጊዜ አስለፍተሀት አንድ ወርም ሳይቆይ ልትሄድ ነው?" አለው።
"በልፋት እንኳን ከኔ የበለጠ የለፋች አይመስለኝም ሀሀሀሀ ስቀልድ ነው። ይሄን የመሰለ ፍቅር ትቼ መሄዴ ሳያስከፋኝ ቀርቶ መሰለህ በእርግጥ መጀመሪያ ወድጄና ፈቅጄ እንደውም በጣም ፈልጌው ነበር ዝውውር የጠየኩት" ያልሰማሁት አዲስ ነገር ሆነብኝ
"አንተ ጠይቀህ ነው እንዴ የተዘዋወርከው" ግርም ብሎኝ ጠየኩት
"አዎ ለዚህ ዝውውር እስከ ጥግ ለፍቻለሁ አሁን ግን አልፈልገውም ነበር ግን ምንም ማድረግ አልችልም" እዝን ብሎ አንገቱን ደፋ
"ለምን ነበር ዝውውሩን የጠየከው" ቢኒ ጣልቃ ገባ
"በሷ ምክንያት ነዋ" እጄን በእጁ እያጠላለፈ "ያን ሁሉ ነገር ሰማሁ ምንም ብሰማ እንኳን ላንቺ ያለኝ ፍቅር ሊቀንስ አልቻለም ጭራሽ የማላውቀው ስበት ወዳንቺ ይገፋኛል። መቋቋም አቃተኝ ስራዬ ላይ ሳይቀር ተፅዕኖ ፈጠረብኝ እናም መሸሽን መረጥኩ እና ዝውውር ጠየኩ"
"የዚህ አመት ትምህርት ሲያልቅ እመጣ አይደል ከእናቴ ውጪ የሚቀበለኝ ሰው አለ ማለት ነው" መሄዱ ሀዘን እንዳይለቅብኝ መልካም መልካም ነገሮችን ለማውራትና ለማሰብ ሞከርኩ
"እስከዛው አደራ የምለው ላንተ ነው ቢኒያም.... ናፍቆት ናፍቆት እያለች ትምህርት ላይ እንዳትዘናጋ ደግሞ በስልክም እናወራለን" ቢኒ በአንገት ንቅናቄ እሽታውን ገለፀ።
ፍቅሬን ሞቅ ባለ ስንብት ወደ አዲስ አበባ ሸኘነው።
እኔ ልሁን እሱ ይሁን ማን እንደተቀየረ ባይገባኝም ከቢኒ ጋር እንደድሯችን ልንሆን አልቻልንም ሳገኘው ሳወራው የሆነ ክፍተት እንዳለ ይሰማኛል። መጥፎ ስሜቶች አብረውኝ እንዲቆዩ አልፋግም እሱን ለማውራት ወሰንኩ
"ቢን ግን የተፈጠረ ችግር አለ ማለቴ ምንም እንደድሮው ልንሆን አልቻልንም እኮ ያጠፋሁት ጥፋት አለ እንዴ"
"ኖ ህያብ ምንም አላጠፋሽም እኔ ነኝ በራሴ ችግር ምክንያት ነው አንቺም ለይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ አላወኩም.... "
"እና ችግሩን ንገራታ መፍትሄው እኮ በሷ እጅ ነው" የቢኒ ጓደኛ ሀብታሙ ከየት መጣ ሳይባል አጠገባችን ተገኝቷል
"እየውልሽ ህያብ ቢኒ ባንቺ ምክንያት ሀገ..." ንግግሩን ሳይጨርስ የቢኒ እጅ አፉ ላይ አረፈ እና እንቅ አድርጎ ያዘው ትንሽ ከታገሉ በኋላ ለቀቀው
"ባለፈው እንደነገርኩህ ነው ወይ ንገራት ካለዛ እኔ እነግራታለሁ"
" ቢኒ ምንድነው ማወቅ ያለብኝ ነገር አለ" ቢኒ ግራ ገብቶት አንዴ እሱን አንዴ እኔን ያያል።
"አቦ ዝም ብለህ እኮ ነው የምታካብደው" ሀብታሙ በንዴት እየተወናጨፈ ትቶን ሄደ
"ቢን ንገረኝ ምንድነው ከኔ የምትደብቀው ነገር አለ እንዴ"
"አይ ህያብ ለመደበቅ አይደለም እነግርሻለሁ ምን መሰለሽ ግን.... እ...እ....እ ማለቴ እኔ ካንቺ..... ማለቴ ....አንቺን.... "
እኔ ቢኒያም ነኝ ልተርክላቹ
ከመጀመሪያ ጀምሮ ምን እንደተፈጠረ ልንገራችሁ። ህያብን አፈቅራታለሁ አጠገቤ እያለች የማንም ሳትሆን በየቀኑ አብሪያት ስሆን ስንተቃቀፍ ስናወራ አብረን ስንበላና ስንጠጣ ጭንቅላቴ የሚያስበው ጓደኛዬ እንደሆነች ቢሆንም ይህ ልቤ ግን ሁሉን ነገር ፍቅር ብሎ ይወስደው ነበር። ሁሉም ነገር የገባኝ ህያብን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ሳያት ነው። መቋቋም አቃተኝ
ከዮኒ ጋር ካወራን በኋላ እሷ ያለምንም ጥርጥር የሱ እንደምትሆን አመንኩ በዛው ልክ ደግሞ ህያብን ላጣት እንደሆነ እና መቼም የኔ እንደማትሆን ተረዳሁ.... አለ አይደል በቃ ሳስብ የኖርኩት የዮኒ ብልግና የሆነ ቀን አንገሽግሿት እሱን መፈለጓን ለማቆም የምትወስን..... ከዛ የኔ የምትሆንበት ሰፊ እድል.....
በነዛ ሁሉ ጊዜያቶች ለራሴ ስነግረው የነበረው ህያብ መቼም ቢሆን ከዛ ባለጌ ዮኒ ጋር ልትሆን እንደማትችል እና የኔ እና የኔ ብቻ እንደምትሆን ነበር። ሁኔታዎች ግን ባላሰብኩት መንገድ ድብልቅልቃቸው ወጣ ህያብን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ላያት ሆነ።
ለዶርም ጓደኞቼ ህያብም ሆነ ማንም ቢጠይቃቸው ቤተሰብ ጋ እንደሄድኩ እንዲነግሩ አስጠንቅቄ ከሀብታሙ ጋር አዲስ አበባ አክስቱ ቤት ሄድን። ሀብታሙ ከስር ከመሰረቱ ለሷ ያለኝን ፍቅር ያውቃል እንድቀርባትም ያደፋፈረኝ እሱ ነበር ለዛም ነው ብቻዬን ልሂድ ስለው አይሆንም ብሎኝ አክስቱ ጋር በነፃነት መሆን እንደምንችል አሳምኖኝ አብሮኝ የመጣው
ለቀናት ጠጣሁ ሰከርኩ በእብደት አለም ውስጥ ዋዠኩ። መርጋጋት የሚባለው ነገር ከኔ በእጥፍ እራቀ። ሁኔታዬ ያሳሰበው ሀብትሽ ከቀናት በኋላ መጠጥ ከሚባል ቦታ እንዳልደርስ በግድ ከለከለኝ
ወደምጠጣበት ቦታ ለመሄድ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ጫማዬን እያሰርኩ ፊት ለፊቴ መጥቶ ቆመና "ምን እየሆንክ ነው በዚህ ሁኔታህ ህያብን የምታገኛት ይመስልሀል። ቢኒያም እንደዚህ እየሆነ መሆኑን የምታውቅ መሰለህ.... እሷማ የምታውቀው ቢኒ እንደታላቅ ወንድም የምታየው ጓደኛዋ እንደሆነ ነው። ንገረኝ እስኪ በማን ላይ ነው የተናደድከው ህያብ ላይ ነው?"
"አይደለም" አልኩት አንገቴን እንደደፋሁ
"በፍቅር ነው?"
"አይደለም እሷን በማፍቀሬማ ደስተኛ ነኝ"
"በራስህ ነው?"
"አዎ ምክንያቱም እስከዛሬ ያመንኩበት ሁሉ ገደል ገባ"
"ይህ እንዳይሆን ማድረግ የምትችለው ነገር ነበር?"
"አላውቅም ምን ላደርግ እችላለሁ መጀመሪያ ነግሪያት ቢሆን የምትወደው ጓደኛዋ ለመሆን አልችልም ነበር። መሀል ላይ ደግሞ ያመንኩት የሱ ነገር ስልችቷት እኔን እንደምታይ ነበር። አሁን ደግሞ ረፍዷል እና በራሴ የትኛውን ነገር አላደረክም ብዬ ልናደድበት?"
"ጥያቄዬን በጥያቄ ሳይሆን በቀጥታ መልስልኝ በራስህ ነው የተናደድከው?"
"አይደለም" አልኩት
"በዮኒ ነው?"
"አይደለም"?
" እና በማን ነው"?
"አላውቅም" አልኩት እውነት ግን በማን ነው የተናደድኩት
"እሺ ለምንድነው እንደዚ እየሆንክ ያለኸው"
"ትቀልዳለህ እንዴ ህያብ የኔ ስለማትሆን ነዋ! በናትህ አሁን መጠጣት ነው የምፈልገው" አልኩት ወሬውን ጨርሶ ዞር እንዲልልኝ በማሰብ
"እንደዚህ መሆንህ ህያብን ያንተ እንድትሆን ያደርጋታል?"
"አያደርጋትም" ከፊት ለፊቴ ዞር አለና ከኮመዲኖ ላይ ቁልፍ እነሳ ከዛ ቀጥታ ወደበሩ አመራ እና ቁልፉን እያሳየኝ
"ስለዚህ በማን እንደተናደድክ አታውቅም ግን ምስኪኑን ጨጓራህን በመጠጥ እያነደድከው ነው ቢያንስ ለጨጓራህ በጠዋት እየተነሳሁ እስከማታ በመጠጥ የማነድህ በዚህ ሰው ተናድጄ ነው ብለህ አንድ ምክንያት ንገረው። ህያብ ደግሞ ከእጅህ ወጥታለች ስለዚህ ሁኔታዎችን አምነህ ተቀበል ወይም ያንተ የምትሆን ከሆነ ያንን ጊዜ ጠብቅ.... ወደራስህ ተመልሰህ ጠብቀኝ ምግብ ይዤ እመጣለሁ" በሩን ቆልፎብኝ ሄደ
ያለሁበት አንድ ክፍል ቤት ሌላ መውጫ የለውም ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና አልጋ ላይ ወጥቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ።

#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹ፀባይ ይኑርሻ..››እያለ ወደእሷ ተጠጋና የሆኑ አንድ ሶስት ቁልፎችን ጫን ጫን ሲያደርጋቸው የለበሰችው ልበስ በመፈታታት ወለሉ ላይ ዝርግፍ ብሎ ወደቀ…እርቃኗን ቀረች፡፡
‹‹እንዴ..!!!››በድንጋጤ በርግጋ የእጇን መዳፎች በማነባር ቶሎ ብላ ብልቷ ላይ ከደነችው--ለካ መለመላዋን ነው ይዟት የመጣው…..ዘግይቶ ነው ይሄን የተረዳችው፡፡
‹‹ልቀቂው ….በጣም እኮ ነው የምታምሪው››
‹‹ሂድ እዛ…ሌላ ቀለል ያለ ሚለበስ ነገር የለህም..?››
‹‹የለኝም…››
ቶሎ ብላ አልጋ ላይ ወጣቸና አንሶላ የመሰለውን ጨርቅ ይሁን ልስልስ በረት ያለየችውን ልብስ ገልጣ ገባች
‹‹እኔም አብሬሽ ልተኛ…?››
በመለማመጥ ጠየቃት…
‹‹ከውስጥ ሳትገባ..ከላይ ከሆነ ተኛ››
እሱ ‹‹እሺ ››ብሎ የሜትር ያህል ርቀት በማሀላቸው ትቶ እንዳለችው ከላይ ተኛ
‹‹ምን እያደረግኩ ነው..?እስቲ አንድ ሴት ለዛውም ልጃገረድ ነኝ ብላ በአካባቢዋ ባሉ ወጣቶች ላይ ጉራዋን የምትነዛ እንዴት ለመጀመሪያ ቀን የመጣችበት ለዛውም በጥልቀት እኳን የማታውቀው የወንድ ቤት ውስጥ ዘላ ከመግባቷ አልጋ ላይ ትወጣለች…ይሄ ቅብጠት ነው ጅልነት….?ወይኔ ይሄ ግራ አጋቢ ፍጡር ምን አስነክቶኛል….?››ስትል አጉረመረመች፡፡
ደግሞ እሺ አልጋ ላይ መውጣቷ ሳያንስ እሱም ከጎኗ እንዲተኛ መፍቀዷ የዋህነትቷ ውጤት እንደሆነ እና ቆይቶ የሚያፀፅት ስህተት እንደሚያሰራ እንዲሁ ታወቃት….?
‹‹በጣም ቆንጆ እኮ ነህ….?ቆንጆ ና የምትገርም ፍጡር ››ይህን የተናገረችው እሷ እሯሷ መሆኗን ማመን አልቻለችም… ‹‹በቃ ለይቶልኛል…››አለች በውስጧ፡፡
‹‹አፍቅረሺኛል ማለት ነው.?›› እሱ ደግሞ ጭራሽ የዲፕሎማሲ ቃና በሌለው ጥሬ ንግግሩ ፀፀቷን አናረው፡፡
‹‹ኸረ በፍጽም… ባፈቅርህስ ምን ታደርግልኛለህ..?ሰው አይደለህ አላገባህ…››የገዛ ልቧ ግን ሰው ሆነ ሌላ ፍጡር ዋናው ማፈቀርሽ ነው እያላት ነው…
‹‹ሰው ባልሆንስ ከተመቸውሽ ብታገቢኝ ምን አለበት.?››
‹‹ምንም የለበትም …ግን ያው ባገባህስ ምን ዋጋ አለው ብዬ ነው.?››
‹‹እንዴት.? ››
‹‹እንትንህ እኮ ባቄላ ነው የምታህለው..ለእኔ ተፈጥሮ የሚስማማ ሆኖ አይደለም የተፈጠረው……እና ምንም ማድረግ አልችልም››
‹‹እንዴ ግን እንደዚህ እየተናገርኩ ያለሁት እኔው ነኝ…››ስትል የራሷን ባህሪ ባለማመን ጠየቀች..ለነገሩ እውነቷን ነው በጊዜው ተደብቆ የሚያዳምጣት ሰው ቢኖር እኮ በቃ የአራት አምስት አመት አሪፍ ልምድ ያለት ባልቴት ነው የምትመስለው…በአዲሱ የባህሪ ለውጧ እራሷን ከፉኛ ታዘበች፡፡
‹‹እና ታዲያ ወደውስጥ እንዳልገባ ለምን ከለከልሺኝ.?››
‹‹ዝም ብዬ ነዋ››
‹‹ዝም ብለሽ ከሆነማ ልግባ ..››ከእሷ አንደበት የሚወጣውን መልስ ሳይጠብቅ ተስፈንጥሮ ከውስጥ ገባ…ግን ሰውነቱ ከሰውነቷ ለማስጠጋት አልደፈረም ….ድርጊቱን ችላ አለችና…
‹‹ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ.?››ስትል የሁለቱንም ትኩረት ወደሌላ አቅጣጫ ዘወረችው፡፡
‹‹ጠይቂኝ››
‹‹እዚህ ማለት ከራስህ ወገን ሚስት አላገባህም.?››
‹‹እኛ ጋር ማግባት የሚባል ነገር የለም..ቃሉም አይታወቅም….››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው የምትኖሩት . .?እንዴትስ ነው የምትዋለድት.?››
‹‹የምንኖረው ያው ሁለታችንም እራሳችንን ችለን ነው..ሴቷም ሆነች ወንድ ራሳቸውን ችለው ነው የሚኖሩት…ግንኙነትም ለመፈፀም በሁለቱ ፃታዎች መሀከል በእለቱ ያለ ስሜት ብቻ ነው ወሳኙ…
ለመውለድ ግን እዚህ እንደእናንተ በአጋጣሚ ወይም ሁሉም እንደፈለገው አይደለም የሚወልደው….
‹‹እና እንዴት ነው.?››ጠየቀችው ገርሟት
‹‹በአመት ስንት አዲስ ልጅ መወለድ አለበት.? የሚለውን የሚወስኑት የማህበረሰቡ የበላይ ጠባቂዎቹ ናቸው፡፡በተወሰነው ቁጥር መሰረት መውለድ የሚፈልጉ ሴቶች ይወዳደራሉ…..ከዛ እድሉ ቀንቶቸው የተመረጡት ሴቶች ከተመረጡ ወንዶች ጋር ግንኙነት በመፈፀም አርግዘው ይወልዳሉ..
የተወለደውን ማሳደጉ የሁሉም ኃላፊነት ነው ..በእናት እና ልጅ መካከል ያለው ቁርኝት እንደእናንተ አይደልም …እናት ትወልዳለች ከዛ ታስረክባለች..መውለድ ማለት ለማህበረሰቡ የተለየ አስዋፅኦ ማበርከት ማለት ነው እንጂ እናትም ሆነች አባት በሚወለደው አዲስ ልጅ ላይ የተለየ ኃላፊነትም ሆነ የተለየ መብት የላቸውም…››
‹‹ይገርማል…..ግን ደስ አይልም ..ልክ እንደ ማሽን ነው የምታስቡት ››
‹‹ብለሽ ነው ?ታዲያ እንደእናንተ የሰው ልጆች በስሜት መሞላትና በሆነ ባልሆነው መሳቀቅና ማልቀስ ይሻላል?
‹‹ቆይ ግን ይሄ ቦታ የት ነው ሚገኘው ?ምድር ላይ ነው?››አዲስ ርዕስ ከፈተች፡፡
አይ ከምድር በጣም ቅርብ የሆነ በመጠን ግን ከመሬት በጣም የሚያንስ ራሱን የቻለ ፕላኔት ነው፡፡
‹‹ስሙ ምን ይባላል?››
‹‹እኛ ኬድሮን እንለዋለን…የዕውቀት ምድር ማለት ነው ››
‹‹በእኛ በሰው ልጆችስ ስያሜው ምንድን ነው?››
‹‹አይ በሰው ልጆች አይታወቅም…››
‹‹እንዴት አይታወቅም ?ከምድር በጣም ቅርብ ነው አላልክም?››
‹‹ነው፡፡ ግን እራሳችንን ከጥቃትና ከውድመት ለመታደግ ባለን ለዘመናት በዳበረ እውቀትና ጥበብ አማካይነት ለእይታ እንዲሰወር አድርገነዋል..ለክ ቅድም ስትመጪ ከተማው ሙሉ በሙሉ ከእይታሽ ተሰውሮ እንደነበረ ሁሉ የእኛ ፕላኔት ምድር ላይም ሆነ ማርስ ላይ ሆነሽ እስከአሁን በተፈጠሩት በማንኛውም መሰሪያ ሊታይ የማይችል የተሰወረ እንዲሆን አድርገናል፡፡የሰው ልጅ ምደር ብቸኛዋ ህይወት የምታኖር ፕላኔት እንደሆነች ነው የሚያውቀው...ግን ደግሞ እኛ የምድር አፍንጫ ስር በማርስና በመሬት መካከል ተሰንቅረን ለአመታት በስኬት እየኖርን ነው፡፡ደግሞም አስፈላጊ ሲሆን ምድር ገብተን ብዙ ቡዙ ተልኮዎችን ፈፅመን ኮሽ ሳይል እንመለሳለን፡፡››
‹‹ወደፊትስ…?.››
‹‹ወደፊት እንግዲህ አናውቅም…በቴክኖለሎጂ ፍጥነት የሰው ልጅ መቼም ከእኛ የተሻለ መራቀቅ ላይ ይደርሳሉ ብዬ አላስብም››
‹‹ግን የእኛ ምድር ትለያለች አይደል?››ስትል ጠየቀችው፡፡
✨ይቀጥላል✨

#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
...በሱስ እና በወንጀል ወደ ተጨማለቀ የህይወት ማጥ መግባት ቁልቁለትን ተንደርድሮ የመውረድ ያህል ቀላልና አዝናኝ መሰል ነው ከአዙሪቱ መውጣት ግን ቀጥ ያለ ሰማይ ጠቀስ አቀበትን የመውጣት ያህል ፈታኝና ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ቢሆንም አሸናፊዎች በጥረታቸው ያሳኩታል፡፡
የዛሬው ቀን ለትንግርት ልዩ ነው፡፡ የክርስቲያኖችን ገና.. የሙስሊሞችን መውሊድ... የደርግን መስከረም 2፣ የወያኔን ግንቦት 2ዐ፣የኢትዮጵያውያንን እንቁጣጣሽ ዓይነት ነው፡፡ ሦስት ዓመት ከተንቦጫረቀችበ የሕይወት አዘቅት ወጥታ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር የምትንደረደርበት የዳግም ውልደት ቀን፡፡ ይህንን የመሸጋገሪያ ቀን ደግሞ በልዩ ሁኔታ ልታከብረው ወስናለች፡፡ሳሪስ የሚገኘዉ ባለ ሦስት ክፍል ቤቷ በልዩ ሁኔታ አምሯል፡፡ ይሄንን ቤት ውጭ የሚገኙት ሁለት
ወንድሞቿና አንድ እህቷ አዋጥተው ነው የገዙላት፡፡ እናትና አባቷ ሳይቀሩ የሚኖሩት ካናዳ ነው፡፡ ከቤተሠቡ ውስጥ ብቸኛዋ አገር ቤት ኗሪ እሷ ነች፡፡ ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያን ለቃ እነሱ ጋር እንድትመጣ ጨቅጭቀዋታል፤ ለምነዋታልም፡፡ ግን አልተሳካላቸውም፡፡ ይሄ ሁኔታ ደግሞ አሜሪካን እንደምድራዊ ገነት በሚያስብና በእውኑም በህልሙም ምድሪቷን ለመርገጥ በሚኳትን ሸፋታ ልብ ካለው ትውልድ መከከል ተፈጥራ አብራ እየኖረች የተለየ እምነት መያዟ ከእሷ በስተቀር ሰሚውን ሁሉ ያስገርማል ፡፡
‹‹ይህቺ መስኮት እንደሌለው ቤት በመከራ የምታፍን ነጻነት አልባ ሀገር ....››
‹‹ይህቺ ጥቂቶች ድራማ የሚሰሩባት..ብዙሀኑ በፍዘት የሚመለከቱባት ሀገር.... >>
‹‹ይህቺ በተረት የተሞላች...የምንቸገረኝ ሀገር.....>>
‹‹ይህቺ ማማት እንጂ ..አብሮ መስራት የማይሳካላቸው ጭንጋፍ ልጆች የሞሉባት ሀገር...>>
‹‹ይህቺ ባለውለታዎቾን የማታከብር... ባንዳዎችን የምትሾም የሽፍቶች ሀገር....››
‹‹ይህቺ ነበርኝ እንጂ አለኝን የማታውቅ ሀገር....>>
‹‹ይህቺ ዘረኞች የወረሯት...የጎጠኞች ሀገር...>>
‹‹ይህቺ ......>>በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ የቅርቧ ሰዎች ወደ ስደቱ ዓለም እንድትበር ለማበረታቻ የተሰነዘረላት ‹‹..ብትሄጂ ተገላገልሽ እንጂ ምንም አታጪም›› የሚለውን ሀሳብ ለማስረገጥ ከተነገሯት ንግግሮች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ያሉት ነገር ሁሉ ትክክል ቢሆንም ባይሆንም…ለእሷ ግን ከሀገር ለቆ ለመሰደድ ምክንያት አይሆናትም..… እሷ በቃ የሀገሯ ቋሚ ልጅ ነች፡፡ሀገሯ ለእሷ ተመቸቻትም ጐረበጠቻትም በቃ ሀገሯ ነች፤ልትከዳትም.. ልትሸሻትም አትሻም…. ‹‹ሀገሬ ብቻ እኮ አይደለችም ለእኔ ያልተመቸችኝ ..እኔስ ለሀገሬ መች ተመቸዋት?›› የሚል አባባል አላት፡፡በዚህ ምክንያት ዛሬም በውጣ ውረድ ህይወት እየተርገበገበችም ቢሆን ይሄው እዚሁ አለች፡፡ የሀገሯ እንብርት የሆነችው አዲስአበባ ላይ፡፡ የዛሬውን ልዩ ቀኗን ከወዳጆቿ ጋር ልታከብር እየተዘጋጀች፡፡
ሳሎኑ መሀከል ባለ ጠረጴዛ ላይ ሦስት ነጫጭ ሻማዎች ሳይለኮሱ ይታያሉ፣ደብዛዛ ሰማያዊ ቀለም የተቀባው የሳሎኑ ግድግዳ መስኮቱ ላይ ከተዘረጋው መጋረጃ ጋር ስምምነት ፈጥሯል፣ ሻማዎቹ የተቀመጡበትን ጠረጴዛ ስድስት በሚሆኑ በምርጥ ባለሙያ መሠራታቸው በሚያስታውቁ ደረቅ ወንበሮች ዙሪያውን ተከቧል፤በአንድ ጥግ ማዕዘን ላይ መካከለኛ መጠን ኖሮት ሠማያዊ ጨርቅ በለበሰ ጠረጴዛ ላይ የተለያዩ የወጥ ዓይነቶች የያዙ ሣህኖች.... የተቆረጠ እንጀራ ይዞ በነጭ ዳንቴል የተሸፈነ ትሪ.... ኩኪሶችና ብስኩቶች ሲገኙ፣ከአንድ ጥግ ደግሞ የተለያዩ መጠጦች የያዙ ጠርሙሶች ተደርድረዋል፡፡ለግብዣው የተጠሩት ሁሴን፣ ሰሎሞንና ሌሎች ሁለት የቡና ቤት ጓደኞቿ ናቸው፡፡ ድግሱ ግን አስር ያህል ሰዎችን ዘና ባለ ሁኔታ የማስተናገድ አቅም አለው፡፡
የሶኒ ምርት ከሆነው ቴፕ ሪከርደር በስሱ የተለቀቀው የአስቴር አወቀ ዘፈን ለቤቱ
ተጨማሪ ድባብ ለግሶታል፡፡ ግንባሯን ቀና አድርጋ የግድግዳ ሠዓቷን ተመለከተች፡፡ ስድስት ሠዓት ሊሞላ አስር ደቂቃ ነው የቀረው፡፡ የእንግዶቹ መምጫ ሰዓት ደርሷል፡፡
ሁለቱ ሴት ጓደኞቿ እቤቷን ቢያውቁትም ሠሎሞንና ሁሴን ግን ፍፁም አያውቁትም፡፡
ቤት እንዳላት እንኳን ያወቁት ከሦስት ቀን በፊት ስለ ዛሬው ቀን ዝግጅት ስትነግራቸው ነበር፡፡
ሁለቱም በአግራሞት ነበር ያፈጠጡባት፡፡እንደመሠሎቿ በምትሠራበት ቡና ቤት ውስጥ ምትኖር ነበር የሚመስላቸው፡፡ ሌላው ይቅር ለዓመታት አንሶላ የተጋፈፋት... ደጋግሞ ጠረን የተጋራት ሁሴን እንኳን ግምት አልነበረውም፡፡ ትንግርት በሌሎች ነገሮች ግልፅ የመሆኗን ያህል የግል ህይወቷን በተመለከተ ለማንም በጣም ድብቅ ነች፡፡
በተሠጣቸው ምልክት ታግዘው በመጀመያ
ቤት የደረሱት ሁሴንና ሠሎሞን ነበሩ፡፡
ሠሎሞን ጥቁር ሱፍ ከነጭ ሸሚዝና ቀይ መደብ ካለው ክራባት ጋር ለብሷል፡፡ አለባበሱ የቦርጩን መጠን አተልቆበታል፡፡ ሁሴን
እንደወትሮው ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው፡፡ ሠማያዊ ጅንስ ሱሪ ነጣ ካለ ሹራብ ጋር ለብሶ ከታች ስኒከር ጫማ ተጫምቷል፡፡ሁለቱም ፊት ለፊታቸው
ለተገተረችው ትንግርት ሠላምታ መስጠት ዘንግተው የቤቱን ዙሪያ ገባ በአግራሞት ይቃኙ ጀመር፡፡የቤቱ ስፋትና ጥራት ብቻ ሳይሆን የትንግርት ከወትሮ የተለየ አለባበስ ጭምርም
ነበር ያፈዘዛቸው፡፡ እሷ የሆነ ገፀ ባህሪ ተላብሳ የምትተውንበት ቲያትር ቤት የገቡ ነው የመሠላቸው፡፡ ተረከዟ ድረስ የሚረዝም..
ባማረ ጥልፍ ያሸበረቀ የአገር ባህል ቀሚስ ለብሳ ነጭ አንገት ልብስ አንገቷ ላይ ጣል አድርጋለች፡፡
ድሮም የፈረስ ጭራ የሚመስለው ፀጉሯ ሹርባ ተሠርቶ ጀርባዋ ላይ ተነጥፏል፡፡
‹‹እውነትም ትንግርት ነሽ›› ሁሴን ነበር ተናጋሪው፡፡ በዝግታ እርምጃ ወደ እሷ ተጠግቶ ደረቱ ላይ ልጥፍ አድርጎ እያቀፋት፡፡
‹‹በዶላር ነበር እንዴ ስትሰሪ የከረምሽው?›› እጁን ለሠላምታ እየዘረጋላት ሠሎሞን እደዛ ያላት፡፡
‹‹አይ..በዩሮ ነው፡፡ ለማንኛውም ቁጭ በሉ፡፡›› በማለት ወደ ወንበሩ መርታ አስቀመጠቻቸው፡፡ በዛው ቅፅበት ሌሎች ተጋባዥ እንግዶቿም እጅ ለእጅ ተያይዘው ገቡ እና ተቀላቀሏቸው፡፡ ጨዋታው ደራ፣ ሳቁ ደመቀ፤ ሁሉም የምርጫቸውን እያነሱ ምሳቸውን ተመገቡ፡፡ ያሻቸውንም የመጠጥ ዓይነት እየመረጡ መጎንጨት ጀመሩ፡፡ ሻማዎቹ ተለኮሱ፡፡ እቤቱ
ደመቀ፡፡ ትንግርት በመሀከል ጨዋታቸውን
አቋረጠቻቸውና በተቀመጠችበት ሆና ንግግሯን ጀመረች፡፡ እንግዶቿም በፀጥታ ያዳምጧት ጀመር፡፡
‹‹ጥሪዬን አክብራችሁ እቤቴ ስለመጣችሁ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ቀን ለእኔ ልዩ ነች፡፡ ልክ የዛሬ አምስት ዓመት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዲግሪ ስመረቅ የተሠማኝን ዓይነት የደስታ ስሜት ነው ዛሬም እየተሰማኝ ያለው›
‹‹በዲግሪ ስመረቅ ...?›› ሠሎሞን ነበር ፡፡
‹‹አዎ ምነው በሶስዮሎጂ ተመርቄያለሁ፡፡ ያንን ያህል እኮ ትልቅ ነገር አይደለም፡፡ እና ወደ ነገሬ ልመለስና ባለፉት ሦስት ዓመታት የቡና ቤት ሕይወቴ ሁለተኛ ዲግሪዬን ስማር እንደቆየሁና ዛሬ በእናንተ ፊት የምረቃ በዓሌን እያከበርኩ እንዳለሁ አርጋችሁ ቁጠሩት፡፡ እውቅና የሚሠጠኝ አካል ባይኖርምC ብዙ ተዓምር የሚያሠኙ የሕይወት ውጣ ውረዶችን አሳልፌያለሁ፡፡ መዓት ዓይነት ወንዶች
አጋጥመውኛል፡፡ ልምዱ የሌለው ጀማሪ….ያጎበደደ ሽማግሌ… አምስት አስር ልጆች ያሉት ባለትዳር... በስንፈተ ወሲብ የሚሰቃይ ጎልማሳ…ከወሲብ ጥማቱ በቀለሉ የማይረካ ጎረምሳ፣ደግ፣ንፉግ፣ተጫች፣ ዝጋታም፣ተደባዳቢ፣ኧረ ስንቱ…፡፡

#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁንገመቹዋቤ
‹‹አሁን አልነግርህም...ግን ለወራት ያስብኩበት አንድ ነገር አለ፡፡››
‹‹እኮ ንገሪኛ?››
‹‹አይ መጀመሪያ ከእሷ ጋር ልነጋገር…ግን አንተ ምንም አታስብ እሷን በምንም ዘዴ ቢሆን በምንም አሳምናታለሁ..በእኔ ጣለው…ትሄዳለች፡፡››
‹‹አንቺስ?››
‹‹ጋሼ እኔ እዚሁ ነኝ…የግል ኮሌጆች ምዝገባቸው ለወራት የሚዘልቅ ነው…ጊዜ አለን…ለማንኛውም ብሩ አንተው ጋር ይቀመጥ..ልመዘገብ ስሄድ እወስደዋለሁ›› ብላ ነበር ብሩን መልሳለት የወጣች፡፡
ሳባ በደንብ ትዝ ይላታል..በዛን ቀን ማታ እራት ተበልቶ ቡና ተጠጥቶ እንዳለቀ የሚፈልገውን ነገር ለአባታቸው አቀራረቡና ተያይዘው ወደመኝታ ቤታቸው ሄዱ፡፡ክፍላቸውን ዘጋግተው አልጋቸው ላይ ወጡና ወሬ ጀመሩ፡፡
‹‹ሳቢ አርብ ነው ወይስ ሰኞ የምትሄጂው?››አለቻት ስንዱ
ሳባ ግራ በመጋባት‹‹የት ነው የምሄደው ?›ስትል መልሳ ጠየቀቻት፡፡
‹‹አዲስ አበባ ነዋ….ምዝገባው እኮ ከአርብ እስከ ማክሰኞ ነው፡››
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ?የምን ምዝገባ ነው?ዕድሜ ልኩን ወጥ እየወጠወጠና ልብሶቼን እያጠበ፤ንፍጤን እየጠረገና ለሀጬን እያበሰ ያለእናት ያሳደገኝን አባቴን እግር አልባ ሆኖ አልጋ ላይ ቀርቶ እያየሁ፤ እኔ ገና ለገና ነገ ባለድግሪ ለመሆን ብዬ ጥዬው የምሄድ ይመስልሻል…?እንደውም ስለትምህርት ሲጠራ እንዴት እንደሚቀፈኝ ብታውቂ ››
‹‹እንዴት ?ለምንድነው ትምህርት ሊቀፍሽ ሚችለው?›
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..?እንደአንቺ ማትሪክ ሳይመጣልኝ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ አባቴ ልሸኝሽ ብሎ በዛን ጊዜ አዲስ አበባ ይሄድ ነበር?.ባይሄድ ደግሞ ለዛ አደጋ ይጋለጥና እንደዛ ኩሩና ሀገር የማይበቃው የነበረው አባቴ እንዲህ ተቆራምዶ ቤት ይቀር ነበር…?››
‹‹ምን ነካሽ…..ያ የእግዚያብሄር ፍቃድ ነው፡፡ ደግሞ አባታችን በህይወት ስለተረፈልንና ዛሬም በእጆቹ እየዳበሰን ስለሆነ... ዛሬም በአንደበቱ እየመከረንና እየገሰፀን ስለሆነ ማመስገን ነው ያለብን፡፡ዛሬም ስለነጋችን እየተጨነቀና
መንገድ እያሳየን በመሆኑ እድለኞች ነን፡፡ከእሱ ጋር በመኪና ውስጥ የነበሩት ሰዎች እኮ ግማሹ ወዲያው ነው የሞቱት፡፡››
‹እሱስ እውነትሽን ነው…ተመስገን ነው…አባቴን ባጣ ምን ይዉጠኝ.ነበር?ግን አትልፊ…እኔ የትም አልሄድም፡፡››
‹‹ቆይ ጋሽ በአምላክ.. ለእኔም አባቴ እንደሆነ ታምኛለሽ?››
‹‹ምን ማለትሽ ነው…በጣም እንጂi አንቺ እኮ እህትና ወንድም ስለሌለኝ በውስጤ የነበረውን ቁጭትና ሀዘን ያጠፋሺልኝ ምርጥ እህቴ ነሽ››
‹‹ይሄን በመስማቴ ተደስቼያለሁ..ታዲያ አሁን ዩኒቨርሲቲ ብትገቢ እኔ.አንቺ እዚህ ሆነሽ ከምትንከባከቢው በታች ትንከባከበዋለች ብለሽ ታስቢያለሽ?››
‹‹በፍፁም… እንደውም እሱን በመንከባከብ አንቺ ከእኔ የተሻልሽ ነሽ፡፡››
‹‹እና ታዲያ በእኔ እምነት ይኑርሻ፡፡››
‹‹ባንቺ እምነት ሳይኖረኝ ቀርቶ እኮ አይደለም፡፡አመታቱ ረጅም.መሆናቸው አሳስቦኝ ነው..አራት አመት…››
‹‹አራት አመት ምን አላት? አርባ አመትስ ቢሆን?››
‹‹ምን ነካሽ አንቺም እኮ የራስሽ ህይወት አለሽ…ችላ ብለሽ ልታልፊው የማትችይው የስራ ዕድል ሊያጋጥምሽ ይችላል..?ልታፈቅሪ ትችያለሽ…ባል ማግባትም ልትወስኚ ትችያለሽ…አንቺ ባትፈልጊ እንኳን ቤተሰቦችሽ ሊያስገድዱሽ ይችላሉ፡፡ያኔ እንዴት ሊሆን ነው…?ትምህርቴን ለሁለተኛ ጊዜ መልሼ ላቋርጥ ነው…?፡፡የማልወጣውን ነገር መነካካት አልፈልግም፡፡ግድ የለም ይቅርብኝ፡፡እዚሁ የተዘጋውን የአባቴን ሱቅ ከፍቼ እሱን እየሰራው ብንከባከበው ይሻላል፡፡››
‹‹አይ እንደዛ ማደርገው እኔ ነኝ፡፡አንቺ ወደ ትምህርትሽ ነው የምትሄጂው፡፡ ብታፈቅሪስ ላለሽው ቆየሁኮ አፍቅሬያለሁ፡፡››
‹‹ባክሽ ቀልዱን አቁሚ፡፡››
‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም ..እውነቴን ነው፡፡››
‹‹እንዴ አንቺ…?ከመቼ ጀምሮ...?ትራሷን ከፍ አደረገችና ከአንገቷ ቀና ብላ አፋጠጠችባት››
‹‹ቢያንስ ሶስት አመት…፡፡››
‹‹አንቺ ሶሰት አመት ሙሉ አፍቅረሽ ለእኔ ሳትነግሪኝ..?እኔ እኮ በህልሜ ያናገረኝን ወንድ ማንነት ሳይቀር ነው የምነግርሽ፡፡››
‹‹እንደምታስቢው ለመናገር ቀላል አልነበረም፡፡››
‹‹…እውነትሽን ነው ቀላል አልነበረም….?››ሳባ ተበሳጨች… ከዛ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ትራሷን ወደታች አወረደችና ብርድ ልብሱን ተከናንባ ተኛች፡
‹‹እንዴ ጥለሺኝ እየተኛሽ ነው…?ማን ነው ያፈቀርሺው ብለሽ አትጠይቂኝም?››
‹‹ምን ሊያደርግልኝ… ሶስት አመት ሙሉ የደበቅሺኝን ዛሬ ብሰማው ምን ይረባኛል… ?.እንደውም ከማያምነኝ ሰው ጋር መተኛት አልፈልግም፡፡›› ብላ ነበር መኝታዋን ለቃ በመውረድ ከላይ ያለውን አልጋ ልብስ ገፋ ስሊፐሯን ተጫምታ ከክፍሉ ለመውጣት ወደበራፍ መራመድ የጀመረች...ለመክፈት እጇን ወደ እጀታው ስትዘረጋ ከስንዱ አንደበት እጅግ አስደንጋጭ መንፈሰን የሚያርድና የሚያደነዝዝ ቃል ነበር የወጣው ፡፡
‹‹ያፈቀርኩት አባትሽን ነው፡፡››
በቆመችበት ደንዝዛ ለደቂቃዎች ቆመች...እንደምንም ፊቷን አዞረችና
‹‹አልሰማሁሽም››ነበር ያለቻት፡፡እውነታው ግን የተናገረችውን ሶስት ቃላት በትክክል ሰምታለች…ግን.አልገባትም.ወይም.ሊታመን የሚችል ዜና ሆኖ አላገኘችውም፡፡
‹‹አዎ ለዛ ነው ሶስት አመት መሉ ሳልነግርሽ በውስጤ አፍኜ የኖርኩት..አባትሽን ስላፈቀርኩ በራሴ አፍሬያለሁ፡፡››
‹‹ቀስ ብላ እግሮቿን እየጎተተች ወደውስጥ ተመለሰችና አልጋ ልብሱን እንደተከናነበች አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡በሰማችው ዜና ደስታ ይሰማት ወይስ ሀዘን ማወቅ አልቻለችም…..አባቷን እኩያዋ የሆነች ልጅ ለዛውም አብራት የምትኖር የገዛ ጓደኛዋ ስታፈቅረው ፡፡
‹‹እርግጠኛ ነሽ ግን?››
‹‹እስከ ዛሬ አመት ማለቴ ጋሼ አደጋ እስኪደርስበት ድረስ እርግጠኛ አልነበርኩም…እንዲሁ ውስጤ የተፈጠረ ቅዠት አድርጌ በማሰብ ራሴን በመገሰፅ ነገሮችን አዳፍኜ መቀጠልን ነበር የወሰንኩት፡፡ጋሼ የተጎዳ ጊዜ ግን በተለይ ዜናውን ፖሊሶች ደውለው ሲነግሩኝ የተሰማኝ ስሜት፤የፈራሁት ፍርሀት፤ላፈቀርሽውና ህይወትሽን ሳይቀር ልትሰጪው ፍቃደኛ ከሆንሺለት ሰው ውጭ ለሌላ ሰው የሚሰማሽ እንዳልሆነ ገባኝ..እውነትም አፍቅሬዋለሁ ብዬ ሙሉ በሙሉ የደመደምኩት የዛኔ ነው››
በወቅቱ ሳባ ምንም ልትላት አልቻለችም….
‹‹ምነው አላመንሺኝም አይደል..?አልፈርድብሽም እኔ ለራሴ የልቤን ጩኸት አምኖ ለመቀበል አመታት ከወሰደብኝ አንቺ እንዴት እንዲህ በፍጥነት ትረጂዋለሽ ብዬ አስባለሁ?፡፡››
‹‹አይደለም እኮ …ማለት አባዬ ለአንቺም እንደአባትሽ ነው፤ለእሱ ካለሽ ክብርና መውደድ የተነሳ ምን አልባት ተምታቶብሽ እንዳይሆን ብዬ ነው እኮ…?›
‹‹ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር እኮ..ግን አይደለም..ጋሼ አባቴ ሳይሆን ባሌ እንዲሆን ነው የምፈልገው፡፡›
‹‹አባዬ እኮ 42 አመቱ ነው ፤ከአንቺ በ22 ዓመት ይበልጣል፡፡››
‹‹አውቃለሁ… ግን ያ ግድ አይሰጠኝም..››
‹‹እሺ አሁን ያለበት ሁኔታስ…?››
‹‹እሱም ጉዳዬ አይደለም…እኔን የሚያስጨንቀኝ ብቸኛው ምክንያት አንቺ ስለነገሩ ምን ታስቢያለሸ ?የሚለው ነው…፡፡››
‹‹እኔ ደግሞ ምን?››

#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ጥያቄዋ እሱን በጣም ነበረ ያሳቀቀው ፤ ወዲያው ነበር ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ በመነሳት ወደእሷ የተጠጋው፡፡ከዛ ከጎኗ ተቀመጠና ወደራሱ ስቦ አቀፋት..በዛ ልስልስና ጣፋጭ አንደበቱ‹‹እንደውም በጣም የምወድሽማ አሁን ነው፡፡በጣም እኮ ነው የምታሳዝኚኝ፡፡አንቺ ብቻ ነሽ እኮ ያለሺን፡፡እንዴት አንቺን ላለመወደድ እችላለሁ?ከአንቺ ውጭ እኮ ምንም ነገር የለኝም፡፡››ብሎ በመረረና በጠነከረ ንግግር ስለፍቅሩ ጥልቀት አስረዳት፡፡
በጣም ነበር ያሳዘናት‹‹አንተም እነአባቢን ተከትለህ ጥለኸኝ ሄደህ ቢሆን ኖሮ ምን እሆን ነበር….?››አለችው ፡፡ያንን ስትለው መላ ሰውነቷ በፍራቻ እየተንቀጠቀጠባት እንደነበረ ትዝ ይላታል፡፡ናኦል ከገቡበት ከጨላማ ውስጥ ከሚመዘዝ የትዝታ ጉዞ በከፊልም ቢሆን እንዲወጡ ፈለገና የጫወታቸውን ርዕስ ቀየረ፡፡‹‹በቃ አሁን ልደሽን እናክብር….››አላት
‹‹ልደቱ የእኔ ብቻ ነው እንዴ…?የሁለታችንም እኮ ነው፡፡››
‹‹ታውቂያለሽ እኔ ልደቴን ማክበር እንደማልወድ››
‹‹እንዳልክ እሺ… ግን መጀመሪያ የእኔን ሻማ እንለኩስና የእነአባቢን የሙት አመት መታሰቢያ እናክብር››ብላ መለሰችለት፡፡
እሱ ግን‹‹አይ ልደቱም ሀዘኑም የእኛው አይደል ..ሁለቱንም ሻማዎች አንድ ላይ እንለኩሳቸው››አላት
አልተከራከረችውም‹‹ ክብሪቱን የት አደረከው?››
ከኪሱ ውስጥ ፈልጎ አወጣና ሰጣት ..ጫረችና የመጀመሪያውን የራሷን ሻማ በመለኮስ አባቷ መቃብር ላይ በማንጠባጠብ እረሱን ችሎ እንዲቆም አደረገች፡፡ከዛ ሌለናውን ሻማ ከወንድሟ እጅ ተቀበለችና ለኩሳ ወደግራዋ ዞራ እናቷ መቃብር ላይ በተመሳሳይ መልኩ አስቀመጠች፡፡በመቀጠል የራሷን የተቀዳደደ የጃኬት ኪስ ፈተሸችና ሁለት ብስኩት አወጣች፡፡ወደ ወንድሟ በስስት እያየች‹‹ወንድሜ ለልደቴ ሻማ ስለለኮስክልኝ አመሰግናለው .. ለእንተም መልካም ልደት ይሁንልህ..ለእኔ ስትል አብረኸኝ ስለተወለድክ አመሰግናለው፡፡››አለችውና ከኪሷ ያወጣችውን ብስኩት እጁ ላይ አደረገች፡፡
ትዝ ይላታል በጣም ነበር ደስ ያለው፡፡ያንን ብስኩት መያዟን አያውቅም ነበር፡፡ሳንቲሙን ከየት አግኝታ? መቼ ገዝታ? እንዴት ከእሱ ደብቃ ይዛ እንደመጣች አያውቅም፡፡እሱም ግን ሊያስደምማት ለሳምንት ሲያስብበት ነበረ፡፡እጁን ወደኪሱ ሰደደና አንድ ቸኮሌትና አንድ ጦር ማስቲካ በማውጣት .‹‹እህቴ እንኳን ተወለድሽ..ደግሞ ልደቱን የሚያከብር ሰው ስጦታ ይቀበላል እንጂ ስጦታ አይሰጥም›› ብሎ እጆ ላይ አስቀመጠላት፡፡
ኑሀሚ ቸኮሌትና መስቲካውን በጣም እንደምትወደው ያውቃል፡፡ ወላጆቻቸው በህይወት እያሉ እናትዬው የመስቲካ ሱሰኛ አባትዬው ደግሞ የቸኮሌት ሱሰኛ አድርገዋት ነበር፡፡ያኔ በሰላሙ ጊዜ በቀን ሁለቴ ወይም ሶስቴ ሰበብ እየፈጠረች ታለቅስ ነበር፡፡ለቅሶዋን ምታቆመው ደግሞ ወይ ቸኮሌት ወይም ደግሞ መስቲካ ሲሰጣት ብቻ ነበር፡፡ይሄም በደንብ ስለሚታወቅ ቀደም ተብሎ ይገዛና ተደብቆ ይቀመጥላታል፡፡ …..እና በወቅቱ የወንድሟ ስጦታ እናትና አባቷን በአንድ ላይ በጥልቀት እንድታስታውስ ነበር ያደረጋት፡፡ መልካቸው ብቻ ሳይሆን ጠረናቸውም ነበር ትዝ ያላት፡፡
‹‹ወንድሜ በጣም ነው ያስደሰትከኝ፡፡አንተ ስላለህልኝ በጣም እድለኛ ነኝ፡፡›› አለችው፡፡
‹‹እህቴ ስናድግ የቸኮሌት ፋብሪካ ይኖረኛል፡፡እና ያንን ፋብሪካ ላንቺ ስል ነው የምከፍተው፡፡ሁል ጊዜ የፈለግሽውን ያህል ቸኮሌት መብላት እንድትቺይ እፈልጋለሁ፡፡››ሲል ከጥልቅ ልቡ የመነጨውን ምኞቱን በፍቅር እና በስስት አይን አይኗን እያየ ነበር ቃል የገባላት፡፡ወደእዚህ አሁን ወዳለችበት ደቡብ አሜሪካ ከመምጣቷ በፊት ወንድሟ የዛን ጊዜ በልጅነታቸው ቃል የገባላትን ቸኮሌት ፋብሪካ ለመገንባት ማሽኑ የሚተከልበትን ዌርሀውስ ማስገንባት ጀምሮ ነበር፡፡ምን አልባት እስከአሁን አጠናቆትም ሊሆን ይችላል፡፡በጣም የሚያሳዝነውና መራሩ ሀቅ ግን ቸኮሌት ፋብሪካው ተተክሎ ማምረት ቢጀምር እንኳን እህቱን ማብላት አይችልም፡፡እህቱን በሰው ሀገር ምድር ላይ በሞት መነጠቋን ካወቀ ፋብሪካውን ያቃጥለዋል፡፡በዛ እርግጠኛ ነች፡፡
በወቅቱ በዛ የልጅነት ጊዜያቸው በወላጆቻቸው መቃብር ስር ስለቸኮሌት ፋብሪካው ቃል ሲገበላት‹‹ወንድሜ ቸኮሌት ፋብሪካ ለመክፈት እኮ ብዙ ብር ነው የሚያስፈልገው…ሀብታም መሆን አለብህ..ያ እንዴት ሊሆን ይችላል? ፡፡››ብላ ነበር የጠየቀችው፡፡
ወንድሟ እጆቹን ዘርግቶ ግራና ቀኝ ትከሻዋን በመያዝ ትኩር ብሎ አይኖቹን አይኖቾ ላይ ተክሎ‹‹አዎ ሀብታም መሆን አለብኝ፡፡እኔ ብቻ ሳልሆን አንቺም ሀብታም መሆን አለብሽ፡፡ለእኛ ሀብታም መሆን የግድ ነው፡፡እኔ ላንቺ ስል ሀብታምና ብዙ ብር ያለው ሰው መሆን እፈልጋለሁ፡፡አንቺም ለእኔ ስትይ እንደዛው ሀብታም መሆን አለብሽ፡፡››ነበር ያላት
‹‹እንዴት ግን..?ትምህርታችንን ከሶስተኛ ክፍል እንዳቋረጥን ነው፡፡ሳንማር እንዴት ነው ሀብታም ልንሆን የምንችለው?››
‹‹እንችላለን፡፡ማለቴ ሳይማሩ ሀብታም መሆን የሚቻል ይመስለኛል፡፡ያለበለዚያ ቡዙ የተማሩ ሆነው ምንም ብር የሌለቸውና አንዳንድ ያልተማሩ ሰዎች ደግሞ ሀብታሞች ሆነው አናገኝም ነበር፡፡አዎ እንዴት እንደሆነ ለጊዜው ባላውቅም ሳይማሩም ሀብታም መሆን እንደሚቻል እርግጠኛ ነኝ፡፡››አላት፡፡
አዎ..የወደፊት ህልማቸውን በተመለከተ ወንድሟ የሚያወራው ነገር በጣም መሳጭ እና አጓጊ ሆኖ ነበር ያገኘችው፡፡ቢሆንም ግን እንዴት ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል በወቅቱ ምንም ፍንጭ አልታያትም፡፡ግን ደግሞ የወንድሟን ንግግር የሞኝ ቅዠት አድርጋም አልወሰደችውም፡፡ ወንድሟን አይደለም በዛን ጊዜ አሁንም ታምነዋለች፡፡ከፍቅር የመነጨ እምነት፡፡
እርግጥ እሷም ከእሱ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ሀሳብ ሁሌ በውስጧ ታሰላስል ነበር፡፡ስታድግ የተወለዱበትንና ያደጉበትን የወላጆቾን ቤት መልሳ መግዛት የዘወትር ምኞቷ ነበር፡፡አዎ በወቅቱ እቤቱን የአባታቸው የልብ ጓደኛው በነበረ ሰው ባለቤትነት ተይዟል፡፡ ወላጆቻቸው ሞተው ወር እንኳን ሳይሞላው ነበር ከመሟቱ በፊት ለስራ ብሎ ብዙ ሚሊዬን ብር ተበድሮኛል ብሎ የተናገረው፡፡ብዙም ሳይቆይ የተናገረውን የሚያረጋግጥለት ሰንድ አቀረበ፡፡ከዛ በቀላሉ በፍርድ ቤት ከሶ ወላጆቻቸው ሞተው በተቀበሩ በሶስተኛው ወር እቤቱን ተረክበ፡፡ለእነሱ ቀርቦ የሚከራከርላቸውም ሆነ ወስዶ የሚያሳድጋቸው አንድም ዘመድ መቅረብ ስላልቻለ …ሰውዬው ጎዳና ጣላቸው የሚለውን የሰው አፍ ብቻ በመፍራት ወስዶ ለማደጎ ቤት አስረከባቸው፡፡ኑሀሚ በዛ ጮርቃ እድሜዋ ላይ ሆና እንኳን ያ ሁሉ የተወሳሰበ ቲያትር መሰል አሻጥር ፈፅሞ አይዋጥላትም ነበር፡፡ያንን ቤት በጣም ትወደዋለች፡፡ልጅነቷ ያለው እዛ ቤት ውስጥ ነው፡፡ሳቅና ደስታዋ እዛ ቤት የሆነ ቁምሳጥን ወይም የኮመዲኖ ኪስ ውስጥ የተቆመለፈበት ነበር የሚመስላት፡፡እና አንድ ቀን ተሳክቶላት ያንን ቤት ማስመለስና የራሳቸው ማድረግ ብትችል እናትና አባቷንም በከፊልም ቢሆን ከሞት አለም ማስመለስ እንደሆነ አድርጋ ነበር የምትቆጥረው ፡፡ዘወትር ትንሽ በከፋት ቁጥር የሚተኙበትን መኝታ ቤት ትዝ ይላታል፤እናቷ ምግብ የምታበስልበት ኪችን ሙሉ ስዕሉ በአእምሮዋ ይመላለስባት ነበር፡፡አባቷ በእረፍት ቀኑ ቢጃማ ለብሶ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ሲያነብ …እሷ ድክ ድክ እያለች ከሳሎን መጥታ ታፋው ላይ በመቀመጥ ከኪሱ ስልኩን አውጥታ ጌም ስትጫወት….

#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ስራው "የፍቅርና የጋብቻ አማካሪነት ነው።የተማረው ፍልስፍና ነው።ሁለተኛ ዲግሪውን ግን አሜሪካ ሄዶ በስነልቦና መስራት ችሏል፡፡በፍቅርና ጋብቻ አማካሪነት የሰራውም እዛው አሜሪካ ነው….ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ሶስት አመት ተቀጥሮ ሰርቶል፡፡አሜሪካዊያኑ በፍቅርና በጋብቻ ጉዳይ ችግር ሲያጋጥማቸው ባለሞያ ጋር መሄድና ድጋፍ ማግኘት ባህላቸው ነው፡፡በመጀመሪያ ወደትዳር ከመግባታቸው በፊት ማድረግ ስለሚገባቸው ስነልቦናዊ ቅድመ ዝግጅት ለማወቅ ባለሞያው ጋር ይሄዳሉ..ትዳር ውስጥ ገብተው ችግር ሲያጋጥማቸው…እርስ በርስ ያለው ተግባቦታቸው አመርቂ ካልሆነ…የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት የሚያጨቃጭቃቸው ከሆነ…የወሲብ አለመጣጣም በመሀከላቸው ካለ ብቻ ማንኛውንም ችግር በመሀከላቸው ከተፈጠረ ወደ ጋብቻ አማካሪ ሄዶ ሞያዊ ምክር መጠየቅና ከዛም የሚሰጣቸውን ምክርና ትዕዛዝ ለየብቻም ሆነ አንድላይ በመተግበር ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ጥረት ያስቀናል፤ሌላው ይቅር ጋብቻቸው እንደማይሰራ እርግጠኛ ከሆኑ እንኳን ጤናማና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዴት መለያየትና ጓደኛሞች ሆኖ መቀጠል እንደሚችሉ ምክር ለማግኘት ተያይዘው ወደ ጋብቻ አማካሪ ቢሮ ይሄዳሉ..ይህ ጉዳይ በጣም ነበር የሚያስገርመው፡፡በተለይ በመሀከላቸው ልጆች ካሉ ለየብቻ ሆነው እራሱ
የልጆቻቸውን ስነልቦና ጠብቀው እንዴት ተግባባተው ማሳደግ እንዳለባቸው ዝርዝር መመሪያ ከአማካሪዎች በመስማት ያንን ሳያዛንፉ በመተግበር የልጆቻቸውን ደስታ ሆነ የእነሱን ሰላም ይጠብቃሉ፡፡ያም ሆኖ ግን ምንም እንኳን በስራው በጣም ደስተኛና ጥሩ ገቢ የሚያገኝበት ቢሆንም ከአምስት አመት በኃላ ጠቅልሎ ወደሀገሩ ተመለሰ….ሲሄድ መቼም ላይመለስ ነበር…..ሀገር ቤት ባሉ ነገሮች ጠቅላላ ተስፋ ቆርጦ ነበር…ግን እንዲመለስ የሚያስገድደው ቁራጭ ምክንያት አገኘ……እና ተመለሰ፡፡
ሰለሞን ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሰ መጀመሪያ ተቀጥሮ ለመስራት ስራ ለማፈላለግ ሞክሮ ነበር….።አስቴር ግን የራሱን ስራ መጀመር እንዳለበት በተደጋጋሚ ጊዜ ግፊት ስታደርግበት እራሱን ከተበታተንበት ሰበሰበና እና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ በላዩ ላይ ዘጋና ስብሰባ ተቀመጠ።አስቴር የልጅነት ጓደኛው እናም ደግሞ ፍቅሩ ነች…ወጣት ሲሆኑ ደግሞ እህቱ ሆነች…እስከአሁንም እህቱ ሆና ቀረች..እሱ በልቡ ተመልሳ ፍቅሩ እንድትሆን ነው የሚመኘው….አላማውም እቅዱም ያ ነው..እሷ ግን ያንንን መስመር ጠርቅማ ዘግታበት አባቱን አባቷ እናቱን እናቷ አድርጋ ለእሱ ደግሞ እህቱ ሆናለች፡፡
ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የሚያውቃት፡፡ ገና ሰባት ወይ ስምንት አመቱ ላይ…የእናቷን ጠርዙ የነተበ የቀሚስ ጫፍ በትናንሽና ለስላሳ እጆቾ ጨምድዳ ይዛ ስርስሯ ኩስ ኩስ እያለች ስትመጣ ነበር የሚያውቃት…የዛን ጊዜውን የልጅነት መልኳን አሁንም በአእምሮው ሰሌዳ ላይ በጉልህ ተስሎ ይገኛል..በአጭሩ ተቆርጦ እርስ በርሱ ተጠቅልሎ የተንጨፈረረ ወርቃማ ፀጉር…ጎላ ጎላ ብላው በፍርሀት የሚንካባለሉ አይኖች…በእንባና በአቧራ ብራብሬ የሆነ አሳዛኝ ፊት….ልክ የግቢው አጥር ተከፍቶላቸው የፊትለፊቱን ትልቁን የሳሎን በራፍ አልፈው ወደጓሮ ሲዞሩ ከኃላ ተከትሎቸው ይሄዳል…እናትዬውን ተከትላ ማድቤት ስትገባ ተከትሏቸው ይገባል…
‹‹የእኔ ልጅ፣ እስኪ እኔ ስራዬን ልስራበት አንቺ ከሰሎሞን ጋር አብራችሁ ተጫወቱ››እያለች እናትዬው ታባብላታለች…እሷም የእናትዬውን ልመና ተቀብላ ከእሱ ጋር ለመጫወት ፍቃደኛ እንድትሆን በአይኖቹ ጭምር ይለማመጣታል….የተቋጠረ ግንባሯን ሳትፈታ በቀሰስተኛ እርምጃ ወደእሱ ትጠጋለች…በደስታ አጇን አፈፍ አድርጎ ይይዛትና እየጎተተ ወደትልቁ ቤት ይዞት ይሄዳል…ከታላቅ እህቱ ጋር በጋራ ወደሚኖርበት መኝታ ክፍላችው ይዞት ይገባል፣..ያሉትን መጫወቻዎች ሁሉ ከየመደርደሪያዎቹን ከየአልጋ ስሩ እየጎተተ ያወጣና ፊት ለፊቷ ወለሉ ላይ ይቆልላል፣ለእሱ የሰለቹትን መጫወቻዎች ለእሷ ብርቅ ነበሩ….እናትዬው እነሱ ቤት በተመላላሽነት በሳምንት ሶስት ቀን ትሰራለች፡፡እና እነዛን ሶስት ቀናት በናፍቆትና በፍቅር ነበር የሚወዳቸው… ሳምንቱን ሙሉ ለምን እንዳማይመጡ ይገርመው ነበር..ከዛ አባቱ እሱን አንደኛ ክፍል አስመዝግቦ ትምህርት ሲያስጀምረው ለእሷም እንደዛው ደብተርና ዩኒፎርም ገዝቶ እሱ የሚማርበት ትምህርት ቤት እናቷ እንድታስመዘግባት አደረገ…አንድ ትምህርት ቤት አንድ ክፍል መማር ጀመሩ…ይሄ ደግሞ የሚገናኙበትን የቀን ብዛትና አጋጣሚ አሰፋው…..ጓደኝነታቸው አብሮ ዕቃ ዕቃ ከመጫወት የተጀመረ ….ከዛ ኤለመንተሪ ጀምረው እስከ ሀይ እስኩል በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ነው የተማሩት።
የተወሰኑ ክፍሎችን አንድ ክፍል ጥቂት ክፍሎችን ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይም አብረው ተቀምጠው የመማር አጋጣሚዋች ነበሯቸው።ስለዚህ እሷ ልክ አብረውት እንደተወለድ ወንድሞቹ እና እህቱ እድሜ ልኩን ነው የሚያውቃት፡፡
ፍቅር የጀመሩት 8ተኛ ክፍል ሲማሩ ነው።በወቅቱ እሱ 8ተኛ ቢ ሲማር እሷ ደግሞ 8ተኛ ኤፍ ክፍል ነበረች።ግን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ወደት/ቤት ሲሄድና ወደሰፈር ሲመለሱ ተጠራርተውና ተጠባብቀው ነበር።እና አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲወጡ እየጠበቀችው ነበር።አብረው ወደቤት መመለስ ቢጀምሩም ግን አንደበቷ እንደተቆለፈና እንደተበሳጨች ነበር...ምን እንደሆነች ቢጠይቃትም በቀላሉ ልትነግረው አልቻለችም..በኋላ በስንት ጭቅጭቅ ከቦርሳዋ አንድ ወረቀት አውጥታ ሰጠችው።ምንድነው? ብሎ በጉጉት ተቀብሎ አነበበው።
አስቴርዬ የእኔ ቆንጆ..የፍቅርሽ ፍላፃ ልቤ ላይ ነው የተሰካው….እስካሁን ሰንኮፉን
አልነቀልኩትም…ያልነቀልኩት ሲሰካብኝ ከነበረው ጊዜ በላይ ስነቅለው ያመኝ ይሁን በሚል ስጋት ነው…….ምን አልባት አንቺው በትንፋሽሽ አዘናግተሸ በልስልስ እጆችሽ ቀስ ብለሽ ብትነቅይልኝ መልካም ይሆን ይመስለኛል፡፡፡አንቺ እኮ ከአለም ሴቶች ጭምር ተወዳዳሪ
የሌለሽ ውብ ነሽ።እኔ አፍቃሪሽ በአንቺ ፍቅር መንገላታት ከጀመርኩ አመታት አልፈዋል።ግን እስከዛሬ ስቃዬን በውስጤ አፍኜ ህመሜን የቻልኩት ከጓደኛዬ ከሰለሞን ጋር ግንኙነት ያላችሁ ስለሚመስለኝ ነበር።ግን በቀደም ወኔዬን አሰባስቤ ስጠይቀው ጓደኛሞች ብቻ እንደሆናችሁ ነገረኝና ነፍሴን በሀሴት አስጨፈራት።እና ውዴ አንቺስ ምን ትያለሽ...
?መልስሽን በጉጉት እጠብቃለሁ... የአንቺው አፍቃሪ መስፍን ጋዲሳ›› ይል ነበር።
አነበበውና ግራ የመጋባትና የመደነጋገር ስሜት ተሠማው..በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው በቀደም በብዙ ጓደኞቻቸው መካከል ስለፍቅር አንስተው ሲያወሩ መስፍን እንደቀልድ ‹‹አስቴርና ሰለሞን ፍቅረኛሞች ናቸው›› አለ ወዲያው ሰለሞን ከአፉ ተቀበለና
‹‹እውነት አይደለም እኔና አስቴር ፍቅረኛሞች ሳንሆን ጓደኛሞች ነን ››ብሎ መልስ ሰጠ ።ነገሩ በዚህ ተደመደመ።ደብዳቤውን ባነበበበት ወቅት ግን መሠፍን ሆነ ብሎ ለገዛ የግል ጥቅሙ ጥያቄውን ጠይቆት እንደነበረና እሱንም ማኖ እንዳስነካው ገባውና በጅልነቱ ተበሳጨ።
ግን ደግሞ የአስቴር ወቅታዊ ኩርፊያ አልገባውም ነበር።‹‹መስፍን ደብዳቤ ለፃፈላት እኔን ለምን ልታኮርፈኝ ቻለች?››እራሱን ጠየቀ
"እና እኔ ምን አጠፋው..የምታኮርፊኝ?"ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡

#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
እድላዊት
"የባሰ አለና አገርህን አትልቅ" እንደሚባለው እድላዊት ከወ/ ሮ በሰልፏ ሞት ጋር የተቃጠረች ይመስላል፡፡
ሳይሞቱ ቀድሜ ልውጣ ማለቷ በአካል ባትነሳም በመንፈስ ተነስታ ጉዞዋን ማሰቧ ፤ አፈር ሳታለብሽኝ ፤ ጥለሽኝ ልትሄጅ ነው? ያሏት፡፡ ወ/ሮ በሰልፏ ፤ ከህሊና የማይወጣ ጥያቄ አሳደረባት፡፡
እድላዊት ግን አፈር ሳታለብሳቸው አልሄደችም ነበር፡፡ አንዴ ያደላትን የስቃይና የመከራ ፅዋ ተቀብላ የወ/ሮ በሰልፏን ተስካር አወጣች፡፡ ሁሉን ነገር ምላድ ምላድ አሰያዘች፡፡ ልብሶቿን አጣጥባ ተነሳች፡፡
"አሁን ባዶሽን አትሄጅም"፡፡ ስንቅ አሰናድተሽ ነገ እሸኝሻለሁ ብሎ አስቀራት፡፡ እሸ ብላ ቀረች፡፡
ስንቅ ለማሰናዳት አልፈለገችም፡፡ ግን ደግሞ ፀበል አለመሔዷን እንዲነቃባት አትፈልግም፡፡ ትንሽ ዳቦ ቆሎ መሳይ አዘጋጀች፡፡ በነጋታው ጠዋት ከአቶ አርምዴ ጋር ተነሳች፡፡
አንዳንዴ እየተነጋገሩ ፤ አንዳንዴ የመለያየታቸው ነገር እያሳሰባቸው ፤ ለየብቻቸው ፣ በየራሳቸው ሃሳብ እየነጎዱ ሳይታወቃቸው ሸንኮራ ዮሐንስ ደረሱ፡፡
የሸንኮራ ዮሃንስ ፀበል ከመዲናችን አዲስ አበባ በ144 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ሚያዝያ 15/1654 ዓ/ም ገደማ ፀበሉ ለአባ ካሳ እንደተገለፀላቸው ይነገራል፡፡
ይህ ፀበል አይነ ስውር የሚያበራ ፤ ለምፅን የሚያነፃ ፤ ኤች አይቪን የሚፈውስ ፤ የአጥንት ካንሰርን ነቅሎ የሚጥል ፤ በአጠቃላይ ሰው ሰራሽ ይሁን ተፈጥሯዊ በሽታዎችን የሚፈውስ ለመሆኑ ብዙዎች ድነዋል፡፡ ተፈውሰዋል ፣ ምስክርነታቸውንም ተናግረዋል ፡፡
"የት አካባቢ ይሻልሻል"? አላት፡፡ ቤት ሊያሲዛት ፈልጎ ፤ አቶ አርምዴ፡፡
እድላዊት ሸንኮራን አልፋ ለመሄድ እንጅ ቤት ለመያዝ አልፈለገችም፡፡
"አሁን ቤት አልይዝም ወደ ፀበሉ ልሂድና ስመለስ እይዛለሁ፡፡አይታወቅም ወይም የማቀው ሰው ላገኝ እችላለሁ፡፡ ለእኔ ምንም አታስብ ፤ በቃ አንተም ተመለስ፡፡ ስራህን ትተህ ነው የመጣኸው፡፡ ላደርክልኝ ውለታና እገዛ እግዚአብሔር ሁሉንም እሱ ይክፈልልኝ አመሰግናለሁ" አለች፡፡ የሃዘን ስሜት በውስጧ እየተሰማት፡፡
አይ! እድል እኔ ምን አላደረግሁልሽም፡፡ ትንሽ ስንዴ ነገር ሸጥ እንኳን አድርጌ ፤ እንዳላዘጋጅልሽ ለመሄድ ቸኮልሽ፡፡
ለስምንት ዓመት አብራው የኖረችው የሟች እህቶቹ ምትክ እድላዊት ልትለየው በመወሰኗ ፤ የወንድ አንጀቱ እንደወላድ ተላወሰ፡፡ በአይኖቹ እንባው ግጥም አለበት፡፡
እድላዊት ከሞት አፋፍ ላይ ያተረፋትን አርምዴን መለየት አቃታት፡፡ ሆድ ባሳት፤ አለቀሰች፡፡ አርምዴ ያወራውን የሰማች አትመስልም፡፡
በፊቱ ላይ የወረደውን እንባ ጠራረገ፡፡ እድል ይበቃል አስካሁን ስታለቅሽ የኖርሽው፡፡ በትንሹም ፣ በትልቁም ማልቀስ ጥሩ አይደለም፡፡ የባሰ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለማፅናናት ሞከረ፡፡
እዚህ ከቆየሽ ተመልሸ አይሻለሁ፡፡ ሰባት መቶ ብር ለአንድ ነገር ይሆንሻል ብሎ ሰጣት፡፡ እግዚአብሔር ከአንች ጋር ይሁን፡፡ ብሏት ተሰነባብተው አቋርጦት ወደ ነበረው ስራው ተመለሰ፡፡
ከተሰነባበቱ በኋላ፤ አቶ አርምዴ ከአካባቢው ዞር እስከሚልላት ድረስ ፀበልተኛ መሰለች፡፡ ከአካባቢው እስኪሰወር ጠብቃ ወደ ሸንኮራ ባልጭ የሚወስደውን የፈረስ ጋሪ ተሳፈረች፡፡
ሰው እያባረረ የሚከተላት መሰላት፡፡ ከፈረስ ጋሪ እንደወረደች ከባልጭ ሞጆ የሚያደርሳትን ያዘች፡፡
እድላዊት አሁንም መነሻዋን እንጅ መድረሻዋን አታውቅም፡፡ ሞጆ መነሃሪያ ደረሰች፡፡ ከተሳፈረችበት ባስ ወርዳ ልብስ የያዘችበትን ፌስታል አንጠልጥላ ስራ ፈላጊዎች ወደ ሚቀመጡበት አካባቢ አመራች፡፡
አዳማ ናዝሬት አዳማ ….እያለ ይለፈልፋል፡፡ ጆሯዋ ጥልቅ አለ፡፡ ሃሳቧን ሰርዛ አዳማ ናዝሬት የሚለውን ሚኒባስ ተሳፍራ ጉዞዋን ወደ አዳማ ናዝሬት አደረገች፡፡
እረዳቱ ውረዱ አለ፡፡ መነሃሪያ ደርሰው፡፡ እድላዊት ሞጆና አዳማ የሚራራቁ መስሏት ውረዱ ሲባል አላመነችም ነበር፡፡
ከሞጆ እስሯ ተቀምጦ የመጣ አንድ መልከ መልካም ፍሪዛም ወጣት ሲወርድ ለመጠየቅ እየፈራች አንተ አንተ…..ብላ ሳትጨርስ ሳይሰማት ጥሏት ወረደ፡፡
እድላዊት ያላት አማራጭ ወርዳ መጠየቅ ሆነ፡፡ ፌስታሏን አንጠልጥላ ወረደች፡፡
የአዳማ መነሃሪያ ደላሎች እንደተገለበጠ የንብ ቀፎ ከበቧት፡፡ እያዋከቡ አንዱ ደላላ የትነሽ ? ድሬ ከሆንሽ አንድ ሰው የቀረው ነው፡፡ አሁን ልንወጣ ነው ነይ፡፡ ያንጠለጠለችውን ፌስታል የመዝረፍ ያህል ነጥቋት ሄደ፡፡
ሁለተኛው ደላላ ደግሞ የት ነሽ ? አሰላ ከሆንሽ ባይሞላም አሁን ይወጣል፡፡ ነይ እያለ እጇን እየጎተተ ወደ አሰላ በሚሄደው አውቶቢስ ውስጥ አስገባት፡፡ የአውቶቢሱን በር ዘግቶባት ወረደ፡፡
እድላዊት ወዲያና ወዲህ ሲያዋክቧት ቀልቧ ተገፏል፡፡ አፏን በፕላስተር የታሸገች መስላለች፡፡ ይህ ሁሉ ትእሪት ሲካሄድ የምትሄድበትን አልተናገረችም ነበር፡፡
"አንች እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ? ያልሞላ መኪና ውስጥ እቃሽ እኮ ተጭኗል፡፡ አሁን ልንወጣ ነው ነይ፡፡
የዘጋባትን በር ከፍቶ ይዟት ሄደ፡፡ ፌስታሏን ወስዶ የጫነባት ደላላ፡፡ እኔ ነኝ ፣ እኔ ነኝ የምጭነው፡፡ ግብግብ ተፈጠረ፡፡ ከአሰላው ደላላ ጋር፡፡
የድሬው አሸንፎ መኪናው ውስጥ ጎትቶ አስገባት፡፡ ገና መቀመጫ ሳይሰጣት የአውቶቢሱን በር ዘግቶ ተንቀሳቀሰ፡፡ እድላዊት እኔ አልሔድም ፣ እቃየን ስጠኝ፡፡ አውርደኝ ብትልም የሚሰማት አላገኘችም፡፡
"ሂጅ እዛጋ ክፍት ወንበር አለ፡፡ ተቀመጭ" አላት እረዳቱ፡፡
ግራ የገባት ከርታታዋ እድላዊት ተቀመጭ ከተባለችበት ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡ ከአንገቷ አቀርቅራ መኪናው ወንበር ላይ ተደገፈች፡፡ ለተሳፋሪ እንቅልፍ የወሰዳት መሰለች፡፡ የመውደቂያዋ ቦታ አሳስቧታል፡፡ ተጨንቃለች ፣ ሆዷ ተርፏ ተርፏ ይላል፡፡
አይኖቿ እንባ አቅረዋል፡፡ ምነው አምላኬ የት ልታደርሰኝ ነው?፡፡ መድረሻየን አላውቀውም፡፡
አንተን አምኘ ነው፡፡ እንግዴህ እንደፍቃድህ አድርገኝ እያለች ፈጣሪዋን እያለቀሰች ተማፀነችው፡፡
የራሳቸውን ሃሳብ እያወጡ እያወረዱ ስለስራ ያስባሉ፡፡ ከስሯ የተቀመጡት ወ/ሮ ዘነቡ፡፡ እድላዊት ለምን አቀርቅራ እንደምታለቅስ ግራ ገብቷቸዋል፡፡
"ምነው ልጄ ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው ? አሏት፡፡
"አይ! ምንም አልሆንኩም፡፡ አይኔን አሞኝ ነው አለች፡፡ ለራሷ ማልቀሷ ቢታወቃትም ፤ ስታለቅስ ግን ሰው የሰማት አልመሰላትም ነበር፡፡
"እና ማልቀሱ ጥሩ እኮ አይደለም፡፡ የባሰ ያምሻል አሉ፡፡ የእውነት አይኗን የታመመች መስሏቸው፡፡
ወ/ሮ ዘነቡ እድላዊትን በአለባበሷና በአነጋግሯ የገጠር ልጅ ለመሆኗ አልተጠራጠሩም ነበር፡፡
"እና አሁን የት ነው የምትሄጅው? አሏት ወ/ሮ ዘነቡ፡፡
እድላዊት የምትሄድበትን ቦታ አታውቅም፡፡ መጠጊያና ማረፊያ ለማግኘት ግን ሁሉንም አፍረጥርጣ መናገር የግድ ሆነባት፡፡
"የምሄድበትና መውደቂያዬን ባውቅማ ምን ያስለቅሰኝ ነበር፡፡ ያለማወቄ ነው እንጅ አለች፡፡ እንባዋ ሳያቋርጥ ግራና ቀኝ ጉልበቶቿ ላይ እየተንጠባጠበ፡፡
ከቤተሰቦቿ ጠፍታ መሆን አለበት ብለው ጠርጥረዋል ወ/ሮ ዘነቡ፡፡ ደግመው "ከየት ነው የመጣሽው? ታዲያ አሏት፡፡
"ከሸንኮራ ጅማ ነው የመጣሁት፡፡ ቤተሰቦቼን በህፃንነቴ ሞተውብኛል፡፡ ከዘመዶቼ ጋር አልስማማ ብዬ ጠፍቼ ነው፡፡

#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
==================
ተው በአያትህ አትፍረድ…ማንኛውም በቃኝ መመልኮስ ፈልጋለው ብሎ እራሱን ከአለም ለመለየት የወሰነ ሰው ማድረግ ያለበት ልክ እሷቸው እንዳደረጉት ነው፡፡የምልኩስና ህይወትን ለመንፈሳዊ መንገድ ራስን አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ከአለም ሆነ ከገዛ ዘመድ ምንም ነገር አለመጠበቅ ነው፡፡ከዛም አልፎ ለአለምም ሆነ ለገዛ ዘመድ ምንም አይነት ኃላፊነት አለመቀበል ማለት ነው፡፡አንድ ሰው ከመለኮሰ ልጄ ለምን ሳይጦረኝ ወንድሜ ለምን ሳይጠይቀኝ ብሎ የመጠየቅም ሆነ የመውቀስ መብት የለውም..በዛውም ልክ እናቴን መጦር ነበረብኝ..ወንድሜን መርዳት ይጠበቅብኛል..የልጅ ልጆቼን መንከባከብ የእኔ ኃላፊነት ነው ከሚለው ማህበራዊ ኃላፊነቶችም ራሱን ነፃ ማድረግ አለበት፡፡
ሙሉ ትኩረቱ መንፈሳዊ ብልፅግና እራስን ማጎልበት ላይ መሆን አለበት፡፡ለዘመዱም ሆነ ለመላ አለሙ እኩል ፀሎት ማድረግ ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ስለክርስቶስ ፍቅር መትጋት ፤ዳቢሎስ ለመጥላትና ለመርገም ግን ጊዜ ከማባከን መቆጠብ ነው ከእነሱ የምጠበቀው…ምክንያቱም በአንድ ንፅህ ልብ ፍቅርና ጥላቻ እውነትና ሀሰት ክፋትና መልካምነት ተጎራብተው መኖር አይቻላቸውምና፡፡ሁለቱንም አቻችሎ እያኖረ ያለ ልብ የመንፈሳዊ ሰው ልብ ሊባል አይችልም፡፡እና በአያትህ ውሳኔና ድርጊት ቅንጣት ያህል ቅሬታ እንዳያድርብህ ..እንደውም በተቃራኒው በረከታቸው እንዲጠብቅህ ብቻ ነው መመኘት ያለብህ››
‹‹ትክክል ነሽ እቴቴ…ለማንኛውም አንቺን ደጋግሜ አመሰግናለሁ››
‹‹እኔም አመሰግናለው ልጄ….ይሄ ፀባይህ መቼም እንዳይቀየር .አሁን ምን ማድረግ እንዳለብህ የምትወስነው አንተ ነህ…እንደእኔ እንደእኔ ኮሌጅ ገብተህ የሙያ ትምህርት ለመማር በመወሰንህ በጣም ጥሩ ነው…ሞያ ያለው ሰው ወድቆ አይወድቅም…ቢያንስ የሆነ ተባራሪ ስራ ሰርቶ ወይም የሆነ ነገር ጠጋግኖ የእለት ጉርሱን ያገኛል..ቀስ እያልክ ደግሞ በሂደት የራስህን ድርጅት የማቋቋም እድልም ይኖርሀል….እና እኔ እናትህ ሁሌም በውሳኔህ አብሬህ ነኝ፡፡››
‹‹አቴቴ አታስቢ ከሰሎሜና ከአላዛር ጋር ተነጋግረን ወስነናል…የሆነ ሞያ እንማራለን ››
‹‹ጎሽ ልጄ እንደዛ ነው…ሰሎሜንም ስለምትንከባከባት አመሰግናለሁ››
‹‹እንዴ እቴቴ እህቴ አይደለችም እንዴ?››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…እንደውም ትልቁ ላመሰግንህ የሚገባው እሷን በተመለከተ ነው…እናንተ ላትሰሙ ትችላላችሁ ፡፡ከጎረመሰችና ለአቅመ አዳምና ሄዋን ከደረሳችሁ በኃላ የሰፈሩ ሰው በሰበብ አስባብ እያደረገ…‹‹ይሄ ጎረምሳ ልጇን አስረግዞ ጉድ ያደርጋታል….››ሲሉኝ፡፡‹‹እንዚህ ልጆች እንዳይሳሳቱና አጉል ችግር ውስጥ እንዳይከቱሽ›› እያሉ ሲመክሩኝ፡፡እኔ ግን ከልጄ ይልቅ በአንተ ላይ ሙሉ እምነት ነበረኝ…አለማየሁማ እኔ እናቱን እንዳፍርና አንገቴን አንቄ እራሴን እንዳጠፋ አያደርገኝም….የገዛ እህቱን የሆነ ነገር አድርጎ የሰፈርተኛውን ሟርት እውን በማድረግ እኔ እናቱን ወደመቃብር አይልከኝም››የሚል ፅኑ እምነት ነበረኝ፡፡እናም ቤተክርስቲያን ስሄድ ጌታ ሆይ ለሁለቱም ልጆቼ ልቦና ስጥልኝ ብዬ ከመፀለይ ውጭ በእናንተ ላይ ምንም አይነት ተፅእኖም ሆነ ክትትል አድርጌ አላውቅም ፤ወደፊትም ስለማምናችሁ ስጋት የለብኝም…እና ለዚህም አመሰግናለው፡፡
አለማየሁ አቴቴ ስለእሱና ስለሰሎሜ እያንዳንዱን ቃላት ከአንደበታቸው አውጥተው በተናገሩት ቁጥር ከልቡ የተወሰነ አካሉ እየተሸራረፈ ሲረግፍ ይታወቀው ነበር..በቃ የአላዛር የእንጀራ እናት ከቀናት በፊት የሰነጣጠቀችው ልቡን አሁን ሙሉ በሙሉ ተሰባበረ፡፡ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለቱም የፍቅር ክንፎቹ ተቆርጦ ሲወድቅበት ..መቋቋም ከሚችለው በላይ ፍፅም ተስፋ መቁረት ውስጥ ነው የገባው፡፡‹‹እቴቴ ..ይሄን ሁሉ ሰቀቀን ስላሳለፍሽ ቅርታ….አይዞሽ አታስቢ …እኔ ልጅሽ ነኝ ልጅሽም እንደሆንኩ እቀጥላለሁ፡፡››ሲል ነበር በደመነፍስ ቃል የገባላቸው፡፡
በዚህ ሁኔታ ነበር ሁለቱም ተመሰጋግነውና ተላቅሰው ከቤተክርሰቲያን የተመለሱት፡፡
ከዛ በኃላ ግን አለማየሁ ሁሉም ነገሩ ነው የተመሰቃቀለበት፡፡ማትሪክ ውጤት አይቶ ዩኒቨርሲቲ መግባት እንደማይችል ያወቀ ሰሞን እንኳን እንዲህ መላ ነገሩ አልተተረማመሰም፡፡ከአላዛር እንጀራ እናት በተለያየበት ቀንም የተወሰነ የሚመረኮዘው ተስፋ ነበርው…ከቴቴ ጋር ካወራ በኃላ ግን በቃል ታስሮል….ከሚወዱትና ከሚያከብሩት ሰው አንደበት የወጣ ቃል ደግሞ ከፖሊስ ካቴና የጠበቀ ቀፍድዶ የሚያስር ነው፡፡አሁን ለአስራዘጠኝ አመት ሲንከባከበውና ሲፋለምለት ከነበረው የፍቅር ሀዲድ ተገፍትሮ ወጥቷል…፡፡የሰሎሜን ፍቅር ከልቡ አውጥቶ በአንደበቱ ማወጅ አይችልም…፡፡እንደዛ ካደረገ እናቷን ማሳዘን አንገት ማስደፋት እንደሆነ ገብቷታል፡፡ከሁለት አንዱን መምረጥ ያለበት ጊዜ ላይ እንደሆነ አውቆል፡፡
ልክ የሀይስኩል ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቀ. ለሰሎሜ ያለውን ፍቅር ለማፈንዳትና እሷን ከተቀናቃኞቹ ሁሴንና አላዛር ፈልቅቆ ራሱ ለማድረግ የአመታት እቅድ ነበረው…ያ ቀን እስኪደርስ በመመኘት ብዙ ቀን እንቅልፍ አጥቶል፡፡ በስንት ጣር ቀኑ ሲደርስ ግን እናቷ ያልጠበቀውን ዱብ እዳ ነገሩት፡፡እሱ እንደውም ይሰጋ የነበረው እንዲህ አይነት ነገር ተፈጥሮ ከሰሎሜ ፍቅር ይነጥለኛል ብሎ ሳይሆን ከአስካለ ጋር የነበረው የድብቅ ፍቅር ሰሎሜ ጆሮ ገብቶ እሷን ያሳጣኝ ይሆን ብሎ ነበር፡፡
ግን ይሄው ጨርሶ ባልጠበቀው መንገድ አሳዳጊ እናቱ እቴቴ እሱና ሰሎሜ በእህት እና ወንድም ስሌት እንዲቀጥሉ እንጂ ፍቅር የሚባል ነገር በመሀከላቸው እንዲበቅል ምንም ፍላጎት እንደሌላቸውና እንደውም እስከሞት ሚያደርስ ሀዘን ላይ እንደሚጥላቸው ግልፅ ባለ አማርኛ ነገርውታል፡፡
እሱ ብቻ ሳይሆን የገዛ ጓደኞቹ አላዛርና ሁሴንም እንደሚያፈቅሯትን በቅርብ በማንኛውም ጊዜ ፍቅራቸውን እንደሚናዘዙላት ያውቃል፡፡ለዚህ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ሶስቱም እሷን እንደሚያፈቅሮት ስለሚያውቁና እርስ በርስም ለዘመናት ሲነጋገሩና ሲወያዩ በመኖራቸው…‹‹.ስንጠይቃት ለየት ያለ ዝግጅት አዘጋጅተን..ሶስታችንም በአንድ ቃል..ሰሎሜ እኛ ሶስቱ ጓደኞችሽ አንቺን ከልጅነታችን ጀምሮ እናፈቅርሻለኝ… ሶስታችንም የእኛ እንድትሆኚ እንፈልጋለን፡፡አንቺ ከሶስታችንን ማንን ትመርጫለሽ…?በውሳኔሽ እንስማማለን፡፡አስበሽበት ከሶስታችን ማንኛችንን እንደምትመርጪ አሳውቂን ››ብለው ሰርፕራይዝ ሊያደርጓትና የመምረጡን እድል ለእሷ ሊሰጡ ገና ዘጠነኛ ክፍል እያሉ ነበር ቃል የተገባቡት፡፡
እና ከእቴቴ ጋር ከማውራቱ ከሳምንት በፊት በሁሴን ሽኝት ላይ ይሄንን ጉዳይ አንስተው ደግሞው ተነጋገርውበት ነበር፡፡ሁሴንም‹‹በቃ አንድ ሴሚስተር ተምሬ ከጨረስኩ በኃላ በሴሚስተር ዝግ ስመጣ እንደተባባልነው እናዳርጋለን›› ብሏቸዋል…እነሱም በሀሳቡ ተስማምተው ነበር፡፡ እስከዛ ማንም አፈቅርሻለው ብሎ እንዳይነግራት ተማምለው ከእንደገና ቃላቸውን አድሰው ነበር፡፡እና በዚህ ሁሉ ውይይትና ንግግር ሰሎሜ አሱን እንደምትመርጥ ከእነሱ በላይ ሰባና ሰማኒያ ፐርሰንት እድል እንዳለው ያምን ነበር..እንደዛ እንዲያስብ ያደረገው ደግሞ ከጓደኝነታቸውም በላይ እንደእህትና ወንድም አንድ ቤት በመኖራቸው..ቀን ብቻ ሳይሆን ምሽትም ለሊትም አንድ ቤት ውስጥ ስለሚሆኑ …ታፋው ላይ ያለውን ጠባሳ ስለምታውቅና ከጡቷ ዝቅ ብሎ ያለውን የማሪያም ስሞሽ ሰልሚያውቅ…ጭምር ነበር የእሷ ተመራጭ እሱ እንደሚሆን እርግጠኛ የሆነው፡፡

#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
///
ከሰርግ ግርግሩ በኋላ አዲስ አለምና ሚካኤል ወደመኝታ ቤታቸው ገብተው ልጃቸውን መሀል አድርገው ተኝተዋል፡፡
‹‹አረ እስኪ ዛሬ እንኳን ከመሀል አስወጪው››አላት
‹‹ምነው በልጅህ መቅናት ጀመርክ እንዴ?››
‹‹አዎ …አይገርምሽም ለካ ወንድ ልጅ ለአባቱ የመጀመሪያው ጣውንት ነው..አሁን አይደል ያወቅኩት….በይ አሁን ከመሀል አውጪው››አለ እየሳቀ፡፡
አዲስ አለም ቅዱስን ከመሀከል በማውጣት ከእሷ ጎን አስተኛችውና ‹‹እንዲህ አይነት ነጭናጫ መሆንህን ባውቅ ኖሮ መቼም አላገባህም ነበር›› አለችው።ሚካኤል ነፃ እጁን በዳሌዋ ላይ አሳርፎ ወደ እቅፍ ጎተታት። ጥንካሬውን ተቋቁማ ከእቅፉ ለማምለጥ ታገለቸው….በቀላሉ ልታሸንፈው አልቻለችም፡፡ ከተኛበት ተነሳና ጭና መሀከል ገባ…
ያልተጠበቀ አስደሳች የፍቅር ጊዜ አሳለፉና ሁለቱም ደክሟቸው በየፊናቸው ተዘረሩ ..ከተወሰነ እርፍትና መረጋጋት በኃላ
‹‹ያለፍቃዴ እንደደፈርከኝ ቁጠረው…ለእኔ መልአክ ለመሆን፣ ልትወደኝና፣ ልታከብረኝ ከዛም አልፎ ልትታዘዘኝ ቃል ገብተሀል …ይህንን በአንድ ቀን ልትረሳው አትችልም፡፡ምነው ረሳሀው እንዴ ?››አለችው፡፡
‹‹አንቺም እኮ እንደሙሽርነትሽ የሚጠበቅብሽን ነገር አላገኙሁብሽም››
‹‹አንተ ..ደግሞ ምንድነው ፈልገህ ያጣህብኝ?››
‹‹ድንግልናሽን?››
‹‹አንተ የተረገምክ …እሱንማ ተስገብግበህ ከ5 ኣመት በፊት ቀርጥፈህ በላኸው …አሁን ከየት ላምጣልህ…የፋብሪካ ውጤት አይደል አላሳበይደው?››
‹‹እንዴ …የእውነትሽን ነው…?ዘንግቼው እኮ ነው…..እኔው ነበርኩ የወሰድኩት?››አላት እየሳቀ…
‹‹አንተ ገና ይሄንን ልጅ እኔ ነኝ የወለድኩት?ማለትህ አይቀርም…››ሳቀች፡፡
‹‹አይ እሱን እንኳን አልልም..በልጄ ቀልድ የለም?››
‹‹እና በሚስት ነው ቀልድ ያለው››
‹‹በሚስት ሳይሆን በድንግልና….አንቺ ቀልዱ ቀልድ ነው…..ፀዲ ግን እንዴት ነው?››
‹‹ማለት?››
‹‹ማታ ከዘሚካኤል ጋር ተያይዛ እንደሄደች አልተመለሰችም….ሰርጉ ላይ ሁሉ ስትንሾካሾኩ ነበር..ምን እየተካሄደ ነው?››የቆረቆረውን ነገር ጠየቃት፡፡
‹‹ለእኔም ጓደኛዬ እንደሆነች ሁሉ ለአንተም ጓደኛህ ነች…ደውለህ ጠይቃት››
‹‹ሞክሬ ነበር ስልኳ አይሰራም››
‹‹አንተ…ተአምር ተፈጥሮ ከአመታት በኃላ ከወንድ ጋር ተያይዛ ብትወጣ ልትረብሻት ትደውልላታለህ?፡፡››አለችው በመገረም፡፡
‹‹መደወል አልነበረብኝም እንዴ?››አለ ደንግጦ፡፡
‹‹አልነበረብህም..ለማንኛውም ወንድምህ ቀልቡን ጥሎባታል››
‹‹እንዴት እንዴት ሆኖ…?.ማለት ትናንት ሰርግ ላይ ሲገናኙ ሁለተኛ ቀናቸው አይደል….?.››
‹‹አንዳንድ ፍቅር እንደዛ ነው…..››
‹‹ፍቅር አለሺው…ብቻ እወነቱን ንገረኝ ካልሽ በጣም ፈርቼለው››
‹‹ምን ያስፈራሀል?››
‹‹ፀዲ በመጀመሪያ ፍቅረኛዋ ምን ያህል እንደተጎዳችና ስንት መከራ እንዳሳለፈች በደንብ ታውቂያለሽ..ዳግመኛ ተመሳሳይ አይነት ስቃይ ላለማሳለፍ ለአመታት ከወንድ እርቃ ነው የኖረችው….እና አሁን እንዳልሺው ከዘሚካኤል ጋር የተጀመረ ነገር ካለ መጨረሻው ጥሩ እንደማይሆን እኔም አንቺም እናውቃለን፡፡››
‹‹እንዴት …?››
‹‹ምን እንዴት አለው…?የዘሚካኤልን ፀባይ የምታውቂው ነው››
‹‹ተው እንጂ ከወንድምህ ከተለያየህ እኮ 7 አመት አልፏሀል…በዚህ ሁሉ አመት ውስጥ ምን አይነት ሰው እንደሆነ ልትገምት አትችልም፡፡››
‹‹ለረጅም ጊዜ አብሬው ባልኖርም…በየሚዲያውና በየጋዜጣው ስለእሱ የሚባልውናና የሚፃፈውን ተከታትዬ እንደማነብ ታውቂያለሽ….ከአንድ ሴት ጋር አንድ ወር እንኳን ቆየ ሲባል ሰምቼ አላውቅም፡፡››
‹‹አይዞህ አትፍራ…እንደሰጋሀው ከእሱ ጋር እንኳን ዘላቂ ግንኙነት ባይኖራትም የተዳፈነውን እና ያረጀውን ስሜቷን ቢያነቃቃላት ቀላል ነገር አይደለም፡፡››
‹‹ማለት?፡፡››
‹‹ምን መሰለህ…ፀዲ የመጀመሪያ ፍቅረኛዋ ጋር ፍቅር የሰራችው መቼ ነው… በ17 አመቷ….በዛ ጊዜ እሷም ሆነች ፍቅረኛዋ በጣም ልጆች ከመሆናቸው በተጨማሪ ልምድ አልባዎች ነበሩ…ምን አልባት በየዋህነት ተቃቅፈው ሲተሸሹ ነው በድንገት ግንኙነት የፈፀሙትና እሷ ያረገዘችው፡፡እንደነገረችኝ ከሆነ ያ የሆነው ለአንድ ቀን ብቻ ነው፡፡ያ ማለት ስለመሳሳም….ስለወሲብ …ጣዕም ምንም የምታስታውሰውና የምታውቀው ነገር የለም፡፡‹‹ማያውቁት ሀገር አይናፍቅም፡፡ ይባል የለ፤ እሷ እንደዛ የሆነባት ይመስለኛል፡፡ታዲያ አሁን ከማንጋ ነው የተገናኘችው? ከኤክስፐርት ጋር‹‹….እንዴ….እንዲህ ነው ለካ….ብላ እራሷን እንድትጠይቅ ካደረጋት በቂ ነው….እርግጠኛ ነኝ ደግሞ እሷም አንተ ያስብከውን ነገር ታስባለች…ወንድምህ ሴት አንደማያበረክት….ፍቅር ሳይሆን ወሲብ አሳዳጅ እንደሆነ ታውቃልች..ያ ማለት ከእሱ ጋር ዘላቂ ነገር እንደማይኖራት ቀድማም ስለምታስብ ያን ያህል አትጎዳም፡፡
‹‹የእኔ ባለቤት…..ኤክስፐርት እኮ ነሽ..አሁን አረጋጋሺኝ››አለና ከንፈሯን ሳማት፡፡ተቃቅፈው ተኙ..በጣም ደክሟቸው ስለነበረ በፍጥነት ነው በእንቅልፍ የተሸነፉት፡፡
///
ልክ ሀይሌ ሪዞርት ደርሶ መኪናውን እዳቆመ‹‹በቃ አሁን እኔ ልሂድ››አለችው፡፡
‹‹እንዴ በፍፅም ..ክፍሌ አስገብተሸኝ ነው ምትሄጂው››አላት፡፡
‹‹ለምን ክፍልህ ማስገባት ብቻ …አባብዬህ አስተኝቼህ ብሔድ አይሻልም?››አላገጠችበት፡፡
‹‹አዎ ይሻላል..ልብ አድርጊ ቃል ገብተሻል››
‹‹ምንድነው ቃል የገባሁት?››
‹‹..ቀኑን ሙሉ ከእኔ ስትደበቂና ስትሸሺ የዋልሺው ሳየንስ..አሁን አታበሳጪኛ ››ብሶቱን ቀሰቀሰችበት፡፡
‹‹ከአንተ አልተደበቅኩም ነበር››አለችው፡፡
አገጯን ይዞ ፊቷን በትኩረት እየተመለከተ ‹‹ምን አይነት ጫዋታ ነው የምትጫወቺው?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹መጀመሪያ በጣም እስክግል ድረስ ትጠጊኛለሽ… ከዛ ትሮጪያለሽ። ››
ፊቷ ቀላ…ቃል እንኳን መናገር አቅቷት…አይኖቾን አፍጥጣ ልምምጥ በመሰለ
አስተያት እየተመለከተችው ነው፡፡እሱ ንግግሩን ቀጠለ‹እንግዲህ እኔን ለመግፋት ጠንክረሽ መጫወትሽን አቁሚ››ብሎ ከንፈሩን ወደከንፈሯ በጣም አስጠጋ፡፡ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ እጆቿን ጠንካራ ጡንቻዎች ላይ ዘረጋች። እጆቹ ወገቧ ላይ ተጣበቁ፣ ወደእቅፉ እየተጣደፉች ተሳበች፣ ሙቀቱ እንደኤሌክትሪክ ንዝረት በመላ ሰውነቷ ተሰራጨ፡፡
በተስፋ መቁረጥ‹‹ሙሉ ትኩረትህን አልፈልግም››አለችው፡፡ ነገር ግን
ከአንደበቷ እየሾለኩ የሚወጡ ቃላቶቹ እስትንፋስ የሌላቸው እና የማያሳምኑ ነበሩ፣ በወጥመድ እንደተያዘች እና ክንፏ እንደተነቃቀለ ወፍ ደካማና በቁጥር ስር እንደዋለች አምናለች፡፡ ለበርካታ ደቂቃዎች እዛው ከመኪና ሳይወርዱ ሲሳሳሙና ሲላላሱ ቆዩ…ከዛ ጎትቶ ከመኪናው አወረዳት…ክንዷን ይዞ ወደመኝታ ክፍሉ ሲመራት ሳትቃወም ተከተለችው፡፡ልዩና ዘመናዊ ክፍል ነው ይዞት የገባው እሷ ግን ቀልቧ ሁሉ እሱ ላይ ስለነበር ለሌላው ነገር ግድ አልነበራትም፡፡
በራፉን መልሶ ዘጋና እዛው መሀል ወለል ላይ እንደቆመች ይስማት ጀመር…እንደምንም ከንፈሯን አላቀቀችና‹‹ የእኔ ቤት ከዚህ ብዙም የራቀ አይደለም… አስራአምስት ደቂቃ ቢወስድብኝ ነው።›› አለችው፡፡