ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28 (2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም) *ሱራህ 19, አያህ 27* فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡ *ሱራህ 19, አያህ 28* يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ…
▶️ ሌሎች #በኦርቶዶክስ ያሉ #መጽሀፍቶች ደግሞ የተለያዩ #የዘር ግንድ ቆጠራዎችን ይጠቅሳሉ።
" #ድርሳነ #ጽዮን" የተባለው መጽሀፍ #የማርያም የዘር ሃረግን ሲገልጽ👇
ሜሊኪ። "የሐና(የእናቷ)
/ \ |
ሴም ሌዊ። ኤሊ
| |
ሆናሲን። ሜሊኪን
| |
ቀለምዮስን። ማቴን
| |
ኢያቄምን። ሐና
\ /
ማ ር ያ ም ን
ወለዱ ይላል[7]።

▶️ የማቲዎስ ወንጌል እንድምታ ደግሞ ከዚህ የተለየ ይገልጻል።
አኪም
|
ኤልዩድ
|
አልዓዛር
|
ቅዕራ
|
ኢያቄም ይላል[8]።

እንግዲህ እነዚህ #መጽሀፍት ደግሞ #በማርያም #አባት ቢስማሙም #በአያቶቻቸው ግን ፈጽሞ #አይስማሙም

▶️ የአንዳንድ ካቶሊካውያን አመለካከትም። << #ማርያም #ሰማያዊ #ፍጡር>> እንደሆነች ሲገልጹ ይህንንም ሀሳብ #የሰዓታት ጸሐፊና #የተአምረ #ማርያም ጸሐፊም በከፊል የሚቀበሉት ቢሆንም #ሃይማኖተ #አበው ግን በግልጽ ይህን ሃሳብ ያወግዘዋል። << እመቤታችን ከሰው የተለየች #ፍጥረት #ምድራዊት ያልሆነች ቀድሞ #በሰማይ #የነበረች #ሃይል(ፍጡር) ናት የሚል ቢኖር #ውግዝ ይሁን። በቅድስት መጽሀፍት እንደተጻፈው #ቅድስት ድንግል ማርያም #ከዳዊት#ከይሁዳ #ከአብርሃም ዘር እንደሆነች #በእውነት የሚያምን ግን #ከግዝት የተፈታ ይሁን>> ይላል[9]።

▶️ ማርያም ዘመዷ #ኤልሳቤጥ፣ እጮኛዋም #ዮሴፍ የነበረ ሴት እንደሆነች ሃገሯም #ናዝሬት #ገሊላ ሆኖ #ከዳዊት #ዘር እንደነበረች #መጽሀፍቅዱስ እየተናገረ #ሰማያዊ #ፍጡር #ናት ማለት " ህዝቤ #እውቀት #ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል/ሆሴ 4-6/። እንደሚለው #የእውቀት #ማጣት ይመስላል።
መጽሀፍቅዱስ የማርያም #አባት #ኢያቄም ሳይሆን < #ኤሊ> የተባለ #ሰው እንደነበር የሚገልጸው ፍንጭ አለ።
(በሉቃስ 3፥23)
ደግሞ #የማርያም #ገድሎች እንደሚሉት #ለእናት #ለአባቷ #አንዲት #ልጅ ሳትሆን #እህትም እንዳላት #መጽሀፍቅዱስ ይናገራል። 👇

<< ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ #የእናቱም #እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።>> {ዮሐ19፥25}።

<<ለዮሴፍ አባቱም #የማታን ልጅ #የያዕቆብ ልጅ (የማታን የልጅ ልጅ) ነው ብሎ #ማቲዎስ (በማቲ 1-16) #የዘር #ሐረጉን ሲቆጥር ወንጌላዊው #ሉቃስ ደግሞ #የማርያምን #የዘር ሃረግ ተከትሎ #በመቁጠር #የማርያም #አባቷ < #ኤሊ> እንደሆነ አስቀምጧል {ሉቃ 3-23}።

🔆 የዮሴፍ የዘር ሀረግ 🔆

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።

2፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ........
............................................

6፤ " እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።"...............................
............................................

15፤ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም #ማታንን ወለደ፤ ማታንም #ያዕቆብን ወለደ፤

16፤ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ #ዮሴፍን ወለደ።
▶️ ዘካርያስ #በቤተ መቅደስ #ምድብ ተራ (ሰሞን) ደርሶት #በእግዚአብሄር ፊት #በክህነት #በቤተ መቅደስ ውስጥ በሚያገለግልበት ጊዜ #ዩሐንስም እንደሚወለድ #መልአክ ተገልጦ ሲያነጋግረው #የአሮንን #ቡራኬ እንዲያሰማቸው ህዝቡ #በውጭ #በአደባባይ ይጠባበቅ ነበር እንጂ ከእነርሱ ጋር #አንድም #ሰው እንዳልነበረ #መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል {ሉቃ 1፥21፣ ዘሁ 6፤ 24-26}። እንዲሁም #መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል #በ6ኛው ወር #ማርያም ወደ ነበረችበት #በገሊላ አውራጃ ወደነበረችው #ናዝሬት #ከተማ ቤቷ ድረስ ሄዶ #አበሰራት እንጂ #በቤተ መቅደስ እንዳልነበረ #ቃሉ ይናገራል {ሉቃ 1፥26}።

▶️ ናዝሬት #ከተማ ደግሞ #ከገሊላ ባህር በስተ #ምዕራብ 25 ኪ.ሜ ርቃ #በዛብሎን ነገድ ድርሻ ውስጥ #የተመሰረተች የሃገሩ #ጠረፍ ከተማና #ዝቅተኛ #ግምት ይሰጣት የነበረች #ከተማ ስትሆን {ዩሐ 1፥47} #ቤተመቅደሱ የነበረው ደግሞ #በኢየሩሳሌም ሆኖ #በይሁዳ አውራጃ #በዮርዳኖስ ወንዝ #ወደጨው #ባህር ከሚገባበት #በምዕራብ 30 ኪ.ሜ #ከታላቁ #የሜድትራኒያን #ባህር 50 ኪ.ሜ ርቃ #በተራራ ላይ የምትገኝ #ከተማ ነች። በመሆኑም #ገብርኤል ሲያበስራት #ማርያም የነበረችው #በኢየሩሳሌም #ቤተ መቅደስ ሳይሆን #በቤቷ በተናቀችው #ከተማ #በናዝሬት ውስጥ ነበረች። ጌታ #ኢየሱስም በዚህ #ስፍራ #አደገ {ሉቃ 2፤ 39-40 ፣ 51}።

▶️ ከናዝሬት እስከ #ቤተልሔም #በእግር ቢያንስ 3 ቀን ያክል ያስኬዳል። #ከቤተልሔም እስከ #ኢየሩሳሌም ድረስ ያለው #ርቀት ደግሞ 8 ኪ.ሜ ነው። ስለዚህ #ማርያምና #ዮሴፍ ለቆጠራ ወደ #ኢየሩሳሌም በመሄድ እስከ #ቤተልሔም 3 ቀናት ያክል ተጉዘው #በመንገድ ላይ #ማርያም #የመውለጃዋ ሰዓት ቢደርስባት በዚያው በአንድ #ከብቶች #በረት ውስጥ #ክርስቶስን ወልዳዋለች። በተወለደ #በ8 ቀኑ እንደ #መልአኩ አጠራር <ኢየሱስ> ተብሎ ሲጠራ #ለ40 ቀናት ያክል #የመንጻት #ወራታቸውን በዚያው ፈጽመው {ዘሌ 12፤ 2-8፣ ዘሌ 5፥11} #ከ8.ኪሜ ጉዞ ቡኋላ ወደ #ኢየሩሳሌም #ቤተመቅደስ አደባባይ ደርሰዋል። #በጌታ #ህግ የታዘዘውን ሁሉ ከፈጸሙ ቡኋላ #በገሊላ አውራጃ ወዳለች #ናዝሬት #ከተማቸው ተመልሰዋል {ሉቃ 2፥39}[2]።

▶️ በገሊላ #አውራጃ #በቃና #መንደር #ሠርግ በነበረበት ሰዓት #ማርያም ለሰርግ ቤቱ #ዘመድ እንደመሆኗ መጠን #በአስተናጋጅነት ስታገለግልና #የጓዳው #ወይን በማለቁ #ኢየሱስን ጠርታ የመጀመርያውን #ተአምር ሲያደርግ የምናነበው #ዘመዶቻቸው #ለናዝሬት ከተማ በቅርብ እንደነበሩ ያሳያል። #ኢየሱስም የራሱና የቤተሰቦቹ #አገር #ናዝሬት መሆኑን ጠቅሷል {ሉቃ 4፤ 16-30}። #ናዝራዊ መባሉም ለዚሁ ነው {ማቴ 2፥23፣ 1፥47}። #የይሁዳ ሰዎች #በገሊላ #አውራጃ የሚኖሩ አይሁዶች #ከአህዛብ ጋር ካላቸው #ግንኙነት ሳቢያ #የአይሁድ #ህግ የሚጠበቅባቸውን እንደማያሟሉ በመግለጽ በተለይም #የናዝሬት ነዋሪዎችን ይጠሏቸው ነበር {ማቴ 4፥15፣ ዩሐ 1፤ 45-46}። ይህም ሆኖ #ከማርያም ማንነት ሳይሆን #እግዚአብሔር #በጸጋው በዚህ በተናቀው #በገሊላው #ናዝሬት ትኖር የነበረችውን #ልጃገረድ #ተስፋ የተሰጠው #የመሲሁ #እናት እንድትሆን መረጠ!።

▶️ ወደ ዋናው #ሃሳብ ስንመለስ #በኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #ማርያም ትኖርበት ስለነበረችበት #ስፍራ #ሁኔታ በዋናነት 2 አመለካከት አለ።
አንደኛው #በናዝሬት #በዮሴፍ ቤት ነበረች የሚሉና ሌሎች ደግሞ #ከቤተ መቅደስ ዘንድ ነበረች የሚሉ ሲኖሩ ሁለቱን #አስታራቂ #ሃሳብ አለን ያሉ ደግሞ ሌላ 3ኛ ሃሳብ የሚያቀርቡ አሉ[3]። ሃሳባቸውም፦

<<አንዳንዶች #ከዮሴፍ ቤት አንዳንዶች #ከቤተ መቅደስ ይላሉ ግን #አይጣላም ሁሉም ተደርጓል #ከድናግለ እስራኤል ጋር #ውሃ ልትቀዳ ሄዳ #ውሃ #ቀድታ ስትመለስ #የተጠማ #ውሻ አገኘችና #በጫማዋ ቀድታ #አጠጣችው
ይህን ያዩ ሌሎች #ሴቶች በዚህ ወራት አምላክ #ከድንግል #ይወለዳል የተባለው ከአንቺ ይሆንን? ብለው ዘበቱባት። ወዲያው #መልአኩ መጥቶ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት ዝም ብላ ሄደች። ከቤትም ደርሳ ውሃውን ስታወርድ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት ይህ ነገር ደጋገመኝ #ከቤተመቅደስ ሄጄ ልረዳው ብላ #ከደናግለ #እስራኤል ጋር ተካፍላ እያስማማች የምትፈትለው #ሐርና #ወርቅ ነበር። ያንን ይዛ ሄደች #ከቤተ #መቅደስ ተቀምጣ #ሐርና #ወርቁን እያስማማች ስትፈትል #መልአክ መጥቶ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት እፎኑ ይከውነኒ ዝንቱ እንዝ ኢያአምር ብእሴ - #ወንድ #ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል? አለች። እኔ ይህን አላደርገውም #እንደምን #ይሆናል ስትለው ነው ከዚህ ቡኋላ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላእሌኪ - ቅዱስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #በአንቺ ላይ #ይመጣል አላት። ይኮነኒ በከመ ትቤለኒ (እንደ ቃልህ ይሁንልኝ) አለችው። ይህን #ቃሏን ምክንያት አድርጎ #በማህጸኗ ተቀርጾአል[4]>> ብለው ያቀርባሉ።

▶️ የዚህ #ተረት #ፈጣሪ #በመጽሐፍ ቅዱስ #በዮሴፍ ቤት #ናዝሬት #ከተማ ነበረች የሚለውን #የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ #ገለጻ በመተው ሌላ #ያልነበረና የሌለ #ታሪክ ጽፏል። ይህ ደግሞ በቃሉ ላይ #አመጽና #መሸቃቀጥን ያመለክታል። አዎን ቅዱስ #ገብርኤል #ማርያምን ሲያበስራት #በእጮኛዋ #ዮሴፍ ቤት #በናዝሬት ከተማ ነበረች እንጂ #ቤተ መቅደስ ወይም #በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ አልነበረችም #ወቅቱና #ሁኔታውም አይፈቅድም {ሉቃ 1፥26}።

▶️ አንዳንዶችም #በቤተ መቅደስ ነበረች የሚለውን #አባባል #መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ብለው #በመቃወም #ማርያም የነበረችው #በቤተ መቅደስ #ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ሳይሆን #በቤተ መቅደሱ ግቢ #በማህደረ #ደናግል ውስጥ ትኖር ነበር የሚሉ አሉ። ነገር ግን #ሄሮድስ በሰራው #ቤተ መቅደስ #አደባባይ ጊቢ ውስጥ ይኖሩና ቆመው #ለአፍታ ያህል ይጸልዩ የነበሩት #አሮጊቶችና #መበለቶች እንደነ #ሃና #የሳሙኤል እናት {1ኛ ሳሙ 1፥9 እና አሮጊቷ ሃና} ሉቃ 2፤ 36-38} እንጂ #ደናግል ወጣት #ሴቶች በጭራሽ አይገቡምና ይህም #ጥናቱ ያላላቀ #ጅምር #አንካሳ #ሃሳብ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ ፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ 1 ዲድስቅሊያ 44።

📚፤ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ፤ <ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን 3ኛ ዕትም፡ ብራና ማተሚያ ድርጅት፤ አ.አ፥ ገጽ 18፡ 1995 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፡ "ፍትሐ ነገስት ንባቡና ትርጓሜ፤ አንቀጽ 1፤ 13፡ ገጽ 23፤ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፡ 1990 ዓ.ም።

[2] 📚፤ ኢንተርናሽናል መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፤ የሉቃስ 2፥4 እና 22 ማብራርያ፡ ገጽ 1531-1532፡ 1993 ዓ.ም።

[3] 📚፤ አባ ቤተማሪያም እና መዘምራን ሞገስ ዕቁባ ጊዮርጊስ፤ "አምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምስል ሥነፍጥረት አንድምታ"፤ አክሱም ማተሚያ ቤት፤ አክሱም፡ ገጽ 36፤ 1991 ዓ.ም።

📚፤ አስረዳ ባያብል (ሊቀ ጠበብት)፤ "ማህሌተ ጽጌ ትርጓሜ"፤ አ.አ፡ ገጽ 80፤ 1998 ዓ.ም።

[4] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ "ውዳሴ ማርያም ንባቡና አንድምታው" ዘሰንበተ ክርስቲያን፤ ገጽ 210፥ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1983 ዓ.ም።

(7.4▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
〽️ 1ኛ፦ በቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል ማለትም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚቀመጠው ታቦት ብቻ ነበር። እዛ ውስጥ ለአገልግሎት የሚገባውም ሊቀ ካህኑ ብቻ ሆኖ እሱንም በአመት 1 ቀን በማስተሰርያ ቀን ስለራሱና ስለህዝቡ መስዋዕትን ይዞ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን ሊቀ ካህኑ በተገቢው መመሪያና ሁኔታ መሰረት አለባበሱን አስተካክሎና ተቀድሶ ነው የሚገባው። ይህን ሁሉ ሳያሟላ አንዲት ነገር ብቻ እንኳን ቢስት ይቀሰፍና ይሞታል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ አይደለም ለመኖር በአመት አንድ ጊዜ እንኳን ለመግባት ይህን ሁሉ መስዋዕት የሚጠይቀውን፤ በዛ ስፍራ ነው ማርያም የኖረችው ማለት ለማመን አዳጋች አይሆንምን? ለዛውም ሴት⁉️

〽️ 2ኛ፦ ሴት ቤተ መቅደስ ስትገባ የታየው የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ነው⁉️

〽️ 3ኛ፦ በሰለሞን ቤተ መቅደስ ሴቶቹ ከአደባባዩ ውጭ ባለው ዓምድ እንደ ሃና ሲጸልዩ እንጂ ውስጥ ቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሲገቡ የታየው የት ጋር ነው⁉️

〽️ 4ኛ፦ ማርያም ትኖር በነበረችበት ዘመን የነበረው የሄሮድስ ቤተ መቅደስ ሲሆን የትኛዋም ሴት በቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል መግባት አይችሉም ነበር። ሴቶች የሚቆሙበት ራሱን የቻለ የሴቶች አደባባይ ነበረው። ይህ ከሆነ ታድያ ማርያም በቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ነው የኖረችው የሚለው ታሪክ ከየት የመጣ ነው⁉️

〽️ 5ኛ፦ አሁንም ድረስ እንኳን ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የትኛዋም ሴት በቤተ መቅደስ እንዲገቡና በመቅደስ ውስጥ እንዲጸልዩ ለአፍታ እንኳ አለመፍቀዷን የራሷ ስርዓት ይደነግጋል። ይህ ከሆነ ታድያ ቤተ ክርስቲያኗ ከራሷ ስርዓት ውጪ ያመጣችው ተረት ምንጩ ከየት ነው⁉️

〽️ 6ኛ፦ ማርያም በቤተ መቅደስ ነው የኖረችው የሚለውን ታሪክ ስለቤተ መቅደሱ ሁኔታ ምንም እውቀት ከሌለው ከቁርዓን ኮርጆ ማምጣት ለምን አስፈለገ⁉️

〽️ 7ኛ፦ ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ውስጥ በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ ዩሐንስም እንደሚወለድ መልአክ ተገልጦ ሲያነጋግረው የአሮንን ቡራኬ እንዲያሰማቸው ህዝቡ በውጭ በአደባባይ ይጠባበቅ ነበር እንጂ ከእነርሱ ጋር አንድም ሰው እንዳልነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል {ሉቃ 1፥21፣ ዘሁ 6፤ 24-26}። ሰው ያልነበረው ታድያ በቤተ መቅደስ ውስጥ እንደፈለጉ መግባት ስለሚቻል ከዛም አልፎ መኖር ስለሚቻል ነውን⁉️

〽️ 8ኛ፦ ማርያም በቤተ መቅደስ ነው የኖረችው የሚለው ታሪክ ውስጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መልካሙን ዜና (ኢየሱስን እንደምትወልድ) ያበሰራት እዛው በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንዳለች እንደሆነ ይተርካል። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ መልአኩ መልካሙን ዜና ይዞ ሲመጣ ስለማርያም አጠቃላይ ሁኔታ እንዲህ ያስነብበናል።

<<በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል #ናዝሬት ወደምትባል ወደ #ገሊላ #ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።>> {ሉቃ 1፤ 26-27}።

ቃሉ መልአኩ መልካሙን ዜና ይዞ የመጣው ማርያም ወደ ነበረችበት በገሊላ አውራጃ ወደነበረችው ናዝሬት ከተማ ቤቷ ድረስ እንጂ በቤተ መቅደስ እንዳልነበረ በግልጽ ይነግረናል። ታድያ የቱ ነው መታመን ያለበት⁉️

ናዝሬት ከተማ ቤተ መቅደሱ የነበረበት ስፍራ ይሆንን⁉️ እንዳንል እንኳን ናዝሬት ከተማ ከገሊላ ባህር በስተ ምዕራብ 25 ኪ.ሜ ርቃ በዛብሎን ነገድ ድርሻ ውስጥ የተመሰረተች የሃገሩ ጠረፍ ከተማና ዝቅተኛ ግምት ይሰጣት የነበረች ከተማ ነች {ዩሐ 1፥47}።
ቤተመቅደሱ የነበረው ደግሞ በኢየሩሳሌም ሆኖ በይሁዳ አውራጃ በዮርዳኖስ ወንዝ ወደጨው ባህር ከሚገባበት በምዕራብ 30 ኪ.ሜ ከታላቁ የሜድትራኒያን ባህር 50 ኪ.ሜ ርቃ በተራራ ላይ የምትገኝ ከተማ ነች። ከናዝሬት እስከ ቤተልሔም በእግር ቢያንስ 3 ቀን ያክል ያስኬዳል። ከቤተልሔም እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ያለው ርቀት ደግሞ 8 ኪ.ሜ ነው።

ስለዚህ ማርያም በገሊላ አውራጃ ወደምትገኝ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ ነበር የኖረችው (በጊዜውም የነበረችው) እያለ በቤተ መቅደሱ (በኢየሩሳሌም) ነው ማለት ያላዋቂ ፍልስፍና አያስብልምን⁉️ በሁለቱ መካከል ያለውንስ ርቀት እንዴት ያዩታል⁉️

〽️ 9ኛ፦ በቅድሚያ እርስ በእርስ ተስማሙ። ማርያም የኖረችው የት ነው⁉️ በናዝሬት በዮሴፍ ቤት⁉️ በቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን⁉️ በሁለቱም⁉️ ወይስ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ጊቢ⁉️

〽️ 10ኛ፦ ማርያም በዮሴፍ ቤት ናዝሬት ከተማ ነበረች የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ገለጻ በመተው ሌላ ያልነበረና የሌለ ታሪክ(በሁለቱም ኖራለች የሚለውን) መጻፍ ለምን አስፈለገ⁉️ ይህ በቃሉ ላይ አመጽና መሸቃቀጥ አይደለምን⁉️

〽️ 11ኛ፦ ሄሮድስ በሰራው ቤተ መቅደስ አደባባይ ጊቢ ውስጥ ይኖሩና ቆመው ይጸልዩ የነበሩት አሮጊቶችና መበለቶች ብቻ ሆነው ሳለ ማርያም በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ሳይሆን በቤተ መቅደሱ ግቢ በማህበረ ደናግል ውስጥ ነበር የኖረችው ማለት የእውቀት ማጣት አይደለምን⁉️