ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ መጽሀፍ ቅዱስ #የእስራኤል #ዜግነት ያላት #እስራኤላዊት#በገሊላ ናዝሬት ከተማ ትኖር የነበረች #አይሁዳዊት ወጣት ሴት እንደነበረች ይናገራል [ሉቃ 1፥26] እንዲሁም #ከዳዊት #የዘር #ግንድ የተገኘች መሆኗንም ይናገራል [ማቴ 1፥17 ፣ ኢሳ 11፥1 ፣ ሐዋ 13፥22]።

▶️ ዘመዷ #ኤልሳቤጥ ስትሆን ምን አይነት #ዝምድና እንደነበራቸው ግን በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም [ሉቃ 1-36]። ስለማርያም #ቤተሰቦች #የእነማ ልጅ እንደሆነች፣ የትና መቼ #እንደተወለደች፣ የት #እንዳደገች #መጽሀፍ ቅዱስ አላማው ስላልሆነ የተወሰነ #ፍንጭ ከመስጠት በስተቀር ምንም #አይናገርም
#መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም #ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ #ካበሰራት ቡሀላ እንኳ " #ከመውለዷ ጋር በተያያዘ ካልሆነ በቀር #ሰፋ ያለ መረጃ የለም።

▶️ እንደዛ ሆኖ ሳለ #መጽሀፍቅዱስ #ዝም ያለበትን ነገር #ዝም ማለት ሲገባቸው #የመጽሀፍቅዱስን አላማ ሳይገነዘቡ #ግምታዊ #ሃሳቦችን በመስጠት #የተጻፉና #በየአደባባዩ የሚሰበኩ መጽሀፍት #ጥቂቶች አይደሉም።
<< ድንግል ማርያም #ኢትዮጽያዊት ነች>> ብለው በድፍረት የጻፉም እንዳሉ ይታወቃል።
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ ድሮም ፍለጋቸው እናቱ #ማርያምን ሳይሆን #የተወለደውን #የአይሁድ #ንጉስ ነው {ማቴ 2፥2፣ 11}። #ሄሮድስም #ህጻኑን #ለመግደል አቅዶ እንደተነሳና #ህጻኑን ግን እንዳላገኘው ያሳይና ወዲያውም ወደ 30 ዓመት #ዕድሜው ተምዘግዝጎ ወደ #አገልግሎቱና #ዋና ወደ ሆነው #ሰፊ #ክፍል ውስጥ ይገባል። ▶️ በሉቃ 1፥26፣ እስከ 2፥52 ብንመለከትም #መልአኩ #ገብርኤል #ማርያምን #ትጸንሻለሽ ብሎ ከገለጸ…
▶️ በዩሐ ወንጌል 2፤ 1-11 #ማርያም የተጠቀሰችበትን #ዋና #ምክንያት ብናይ #ኢየሱስ #የምልክቶችን #መጀመሪያ "በቃና ዘገሊላ" #ተአምር እንዳደረገና #ክብሩን እንደገለጸ #ደቀመዛሙርቱም #በእርሱ #ለመጀመሪያ ጊዜ #እንዳመኑ ለማሳየት #ታሪኩን ከስር #በመጀመር በአንድ ወቅት #በገሊላ አውራጃ #በቃና ሠርግ እንደነበርና <እናቱም በዚያ ነበረች> በማለት እግረ መንገዷን ተጠቅሳ #በድግሱ ስነ ስርዓት ላይ #የወይን #ጠጅ ማለቁንና #ማርያምም #የወይኑ ማለቅ #እንዳሳሰባትና ለእርሱ #እንደገለጸችለት ጠቅሶ ከዚያም #ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ #መለኮታዊውን #ተአምር #እንዳደረገ ሁሉም #በእርሷ ሳይሆን #በእርሱ እንዳመኑ <... በእርሱ አመኑ> በማለት ጠቅሶ #የማርያምን #ሁኔታ ይተወዋል።
▶️ ኤልሳቤጥ በጸነሰች #በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል #ልጅ #የመውለድ #መልእክት ይዞ ወደ እሷ መጣ። በዚህ ጊዜ #መልእክቱ የመጣው #በገሊላ አውራጃ ከምትገኝ #በናዝሬት ከተማ ለምትኖርና ስሟ #ማርያም ለምትባል #ድንግል ልጃገረድ ነበር። #ማርያም #ከይሁዳ ነገድ #ከዳዊት ትውልድ የሆነች #አይሁዳዊት #ድንግል ነበረች (ኢሳ 7፥14)። #በናዝሬት ከተማ #በአናጺነት ሙያ ለሚተዳደር #ዮሴፍ ለተባለ #ሰው የታጨች ስትሆን (ማቴ 13፥55) ሁለቱም ድሆች ነበሩ (ሉቃ 2፥24 ፣ ዘሌ 12፥8)።

▶️ ከሉቃስ ወንጌል #ምዕራፍ 1፤ 26-33 #የቅዱስ ገብርኤልን #ሰላምታ በደንብ ስንመለከተው #ማርያም ለጊዜው #እንደፈራችና #ግራ እንደተጋባች ያስረዳል። <<ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው>> አላት። #መልአኩ #ሠላምታ ሊሥጣት የመጣው ለምንድን ነው?? #ጸጋ የሞላባትስ በምን #መንገድ ነው? #እግዚአብሔር #ከእሷ ጋር የሆነውስ #እንዴት ነው??..

▶️ የማርያም #ምላሽ #በእግዚአብሄር ፊት #ትሁትና #እውነተኛ እንደነበረ ያሳያል። ከቶውንም #ከመልአክ ጋር እንደምትነጋገርና #ከሰማይ ልዩ #ጸጋዎችን እንደምታገኝ አልጠበቀችም። #የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #የሉቃስ ወንጌል #አንድምታው እንደሚለው <<ማርያም #የኢሳያስን #ትንቢት የሆነውን ኢሳ 7፥14 ስታነብ ያቺን #ሴት ምነው እኔ #በሆንኩ አላለችም። እንደውም ምነው #ከጊዜዋ ደርሼ #ወጥቼ #ወርጄ አገልግያት በማለት #ታስብ እንደነበር ይገልጻል[1]። እንዲህ አይነት #ሁኔታዎች እንዲፈጸምላት የሚያደርግ #ምንም የተለየ ነገር አልነበራትም። አንዳንድ የስነ መለኮት #አስተማሪዎችም እንደሚናገሩት <<ማርያም #ከሌሎች አይሁዳውያን #ሴቶችና #ልጃገረዶች #የተለየች ብትሆን ኖሮ <<መልካም እንግዲህ #ጊዜው #ደርሷል! እስከአሁንም #ስጠብቀው ቆይቻለሁ! ትል ነበር። ነገር ግን #በፍጹም አላለችም[2]!!! ሁሉ ነገር ለእሷ #አዲስና #አስደናቂ #ዱብእዳ ስለነበረ ግራ #ተጋብታለች#ፈርታለች#ደንግጣለችም <<ይህ እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው?>> በማለትም አስባለች። #ቅዱስ ገብርኤልም #አትፍሪ በማለት #የማረጋጋት ተግባር ሲያከናውን ይታያል።

▶️ ከዚያም #መልአኩ ገብርኤል #መልካሙን #ዜና ያበሰራት #ኢየሱስን (አዳኝ፣ መድኃኒት) ማቲ 1፥21 ብላ የምትሰይመውን #መሲህ እንደምትወልድ ነበር። በመቀጠልም #መልአኩ የኢየሱስን #አምላክነትና #ሰብአዊነት አስረግጦ በመንገር #የምትወልደው #ልጅ ታላቅ እንደሆነና እንደሚሆን እንጂ በእርሷ ታላቅነት ላይ አላተኮረም {ሉቃ 1፥31}።

▶️ የሚወለደው ህጻን(ኢየሱስ) #ንጉስ ሆኖ #የዳዊትን #ዙፋን በመውረስ #ለዘላለም በእስራኤል ላይ #ይነግሳል#እግዚአብሔር #ከዳዊት ጋር የገባውን #ቃል #ኪዳን (2ኛሳሙ 7) እና ለእስራኤል #ህዝብ የሰጠውን #የመንግስት የተስፋ #ቃሎች #እያመለከተ ነበር {ኢሳ 9፤1-7፣ 11-12 ፣ 61 ፣ 66፣ ኤር 33}።
▶️ ዘካርያስ #በቤተ መቅደስ #ምድብ ተራ (ሰሞን) ደርሶት #በእግዚአብሄር ፊት #በክህነት #በቤተ መቅደስ ውስጥ በሚያገለግልበት ጊዜ #ዩሐንስም እንደሚወለድ #መልአክ ተገልጦ ሲያነጋግረው #የአሮንን #ቡራኬ እንዲያሰማቸው ህዝቡ #በውጭ #በአደባባይ ይጠባበቅ ነበር እንጂ ከእነርሱ ጋር #አንድም #ሰው እንዳልነበረ #መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል {ሉቃ 1፥21፣ ዘሁ 6፤ 24-26}። እንዲሁም #መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል #በ6ኛው ወር #ማርያም ወደ ነበረችበት #በገሊላ አውራጃ ወደነበረችው #ናዝሬት #ከተማ ቤቷ ድረስ ሄዶ #አበሰራት እንጂ #በቤተ መቅደስ እንዳልነበረ #ቃሉ ይናገራል {ሉቃ 1፥26}።

▶️ ናዝሬት #ከተማ ደግሞ #ከገሊላ ባህር በስተ #ምዕራብ 25 ኪ.ሜ ርቃ #በዛብሎን ነገድ ድርሻ ውስጥ #የተመሰረተች የሃገሩ #ጠረፍ ከተማና #ዝቅተኛ #ግምት ይሰጣት የነበረች #ከተማ ስትሆን {ዩሐ 1፥47} #ቤተመቅደሱ የነበረው ደግሞ #በኢየሩሳሌም ሆኖ #በይሁዳ አውራጃ #በዮርዳኖስ ወንዝ #ወደጨው #ባህር ከሚገባበት #በምዕራብ 30 ኪ.ሜ #ከታላቁ #የሜድትራኒያን #ባህር 50 ኪ.ሜ ርቃ #በተራራ ላይ የምትገኝ #ከተማ ነች። በመሆኑም #ገብርኤል ሲያበስራት #ማርያም የነበረችው #በኢየሩሳሌም #ቤተ መቅደስ ሳይሆን #በቤቷ በተናቀችው #ከተማ #በናዝሬት ውስጥ ነበረች። ጌታ #ኢየሱስም በዚህ #ስፍራ #አደገ {ሉቃ 2፤ 39-40 ፣ 51}።

▶️ ከናዝሬት እስከ #ቤተልሔም #በእግር ቢያንስ 3 ቀን ያክል ያስኬዳል። #ከቤተልሔም እስከ #ኢየሩሳሌም ድረስ ያለው #ርቀት ደግሞ 8 ኪ.ሜ ነው። ስለዚህ #ማርያምና #ዮሴፍ ለቆጠራ ወደ #ኢየሩሳሌም በመሄድ እስከ #ቤተልሔም 3 ቀናት ያክል ተጉዘው #በመንገድ ላይ #ማርያም #የመውለጃዋ ሰዓት ቢደርስባት በዚያው በአንድ #ከብቶች #በረት ውስጥ #ክርስቶስን ወልዳዋለች። በተወለደ #በ8 ቀኑ እንደ #መልአኩ አጠራር <ኢየሱስ> ተብሎ ሲጠራ #ለ40 ቀናት ያክል #የመንጻት #ወራታቸውን በዚያው ፈጽመው {ዘሌ 12፤ 2-8፣ ዘሌ 5፥11} #ከ8.ኪሜ ጉዞ ቡኋላ ወደ #ኢየሩሳሌም #ቤተመቅደስ አደባባይ ደርሰዋል። #በጌታ #ህግ የታዘዘውን ሁሉ ከፈጸሙ ቡኋላ #በገሊላ አውራጃ ወዳለች #ናዝሬት #ከተማቸው ተመልሰዋል {ሉቃ 2፥39}[2]።

▶️ በገሊላ #አውራጃ #በቃና #መንደር #ሠርግ በነበረበት ሰዓት #ማርያም ለሰርግ ቤቱ #ዘመድ እንደመሆኗ መጠን #በአስተናጋጅነት ስታገለግልና #የጓዳው #ወይን በማለቁ #ኢየሱስን ጠርታ የመጀመርያውን #ተአምር ሲያደርግ የምናነበው #ዘመዶቻቸው #ለናዝሬት ከተማ በቅርብ እንደነበሩ ያሳያል። #ኢየሱስም የራሱና የቤተሰቦቹ #አገር #ናዝሬት መሆኑን ጠቅሷል {ሉቃ 4፤ 16-30}። #ናዝራዊ መባሉም ለዚሁ ነው {ማቴ 2፥23፣ 1፥47}። #የይሁዳ ሰዎች #በገሊላ #አውራጃ የሚኖሩ አይሁዶች #ከአህዛብ ጋር ካላቸው #ግንኙነት ሳቢያ #የአይሁድ #ህግ የሚጠበቅባቸውን እንደማያሟሉ በመግለጽ በተለይም #የናዝሬት ነዋሪዎችን ይጠሏቸው ነበር {ማቴ 4፥15፣ ዩሐ 1፤ 45-46}። ይህም ሆኖ #ከማርያም ማንነት ሳይሆን #እግዚአብሔር #በጸጋው በዚህ በተናቀው #በገሊላው #ናዝሬት ትኖር የነበረችውን #ልጃገረድ #ተስፋ የተሰጠው #የመሲሁ #እናት እንድትሆን መረጠ!።

▶️ ወደ ዋናው #ሃሳብ ስንመለስ #በኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #ማርያም ትኖርበት ስለነበረችበት #ስፍራ #ሁኔታ በዋናነት 2 አመለካከት አለ።
አንደኛው #በናዝሬት #በዮሴፍ ቤት ነበረች የሚሉና ሌሎች ደግሞ #ከቤተ መቅደስ ዘንድ ነበረች የሚሉ ሲኖሩ ሁለቱን #አስታራቂ #ሃሳብ አለን ያሉ ደግሞ ሌላ 3ኛ ሃሳብ የሚያቀርቡ አሉ[3]። ሃሳባቸውም፦

<<አንዳንዶች #ከዮሴፍ ቤት አንዳንዶች #ከቤተ መቅደስ ይላሉ ግን #አይጣላም ሁሉም ተደርጓል #ከድናግለ እስራኤል ጋር #ውሃ ልትቀዳ ሄዳ #ውሃ #ቀድታ ስትመለስ #የተጠማ #ውሻ አገኘችና #በጫማዋ ቀድታ #አጠጣችው