#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስሞንት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ካርለት የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የሥራ ፈቃዷን ልትጨርስ የቀራት አንድ ሳምንት ብቻ ነው ከዚህ በፊት ከአንድም ሁለት ጊዜ፡
የጥናት ፈቃዷን አራዝማለች" ዘመናዊው ሕይወቷን በመዘንጋት ለሐመሩ ንጹሕ ሕይወት ረክታለች" ዛሬ የሐመር ሕዝብ ለሷ የለንደን
ሕዝብ ነው።
ከእንግዲህ ወዲያ ካርለት ኢትዮጵያዊት ነች" ለንደን
የሥጋ ዘመዶቿ፣ ሐመር ደግሞ የመንፈስ ወዳጆቿ የሚገኙበት ነው" በዚህ ቀን ካርለት ከከሎ ጋር ስለ ማኅበረሰቡ የወደፊት ዕጣ
ተነጋግረው ነበርu ካርለት፣ «ሐመሮች በእርግጥ የሚያውቁት ራሳቸውን ነው ከነሱ ውጭ ያለው ዓለም ምን እንደሚመስል
አያውቁም። ይሁን እንጂ ከዓለማችን ውጭ በራሳቸው ደሴት
ተጠልለው ዝንተ ዓለም መኖር አይችሉም" ተወደደም ተጠላ
በክልላቸው ሳይንስ የፈጠራቸው ተሽከርካሪዎችና በራሪዎች
ያልፋሉ። ስለ እነሱ ሌላው ሲያውቅ፣ እነሱም ስለ ሌላው ለማወቅ መቻል አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ድልድይ የሐመር ወጣቶች ሲሆኑ፣ የዘመኑን ትምህርት መቅሰም መቻል አለባቸው» ብላ ነገራዋለች" ከሎም ሐሳቧ የሱም እምነት እንደሆነ አረጋግጦላታል"
ካርለት፣ ሐመርን ለመልቀቅ የተወሰኑ ቀናት ሲቀራት ሆዷ
ተሸበረ ተጨነቀች" የገርሲ፣ ፌጦ፣ ኩንኩሮ፣ ጨዋንዛ፣ ግራር ዘንባባ፣ አጋም፣ ጠዬ፣ አንቃ፣ ሌሊሚ፣ ጨውሊምባ፣ ሾላ፣ ዋንዛ፣
እንኮይ...ደኑ የአሰሌ፣ የካራ ሰንሰለታማ ተራራ፣ የላላ፣ የሻንቆ፣የወሮ…መንደር፤ የሐመር ልጃገረድ፣ ጐረምሳ፣ አዛውንት፣
ሽማግሌ፣ ባልቴት ቀብራራው ደልቲ ገልዲ በአእምሮዋ እንደ
ፔንዱለም ባለማቋረጥ እየተመላለሱ (ጨክነሽ ጥለሽን ልትሄጂ እያሉ፣ ልቧን አንጠለጠሉባት።
ካርለት ቀሪውን ጊዜዋን ከብቱን፣ ሰውን፣ ጫካውን ፎቶ ስታነሣ ሰነበተች። ልቧ ግን እንደ ታረደ ዶሮ እየተነሣ ፈረጠባት ስትመጣ
ዳር ዳር ቆመው የተመለከቷት ሐመሮች የጕዞዋን ዜና ሲሰሙ
ሕሊናቸው ኩምሽሽ ብሎ ዓይናቸው በእንባ ሲሞላ ተመለከተች ስትቀርባቸው ሊወጓት ቀንዳቸውን ያዞሩባት የነበሩት ከብቶች
ጠረኗን እየፈለጉ ተጠግተው እጆቿን ላሷት።
ካርለት በሕይወቷ እንዲህ ልብ ሰራቂ የሆነ የሰውና የተፈጥሮ ፍቅር አጋጥሟት አያውቅም። ስለዚህ፣ ልቧ ደረቷን ሲረግጥ፣
ሕሊናዋ አነባ! ዓይኖቿም አለቀሱ።
ካርለት ሐመርን ልትለቅ አንድ ቀን ሲቀራት የኢቫንጋዲ ጭፈራውን ለመካፈል አሸዋማ፣ ገላጣና ዙሪያውን በለመለሙ የሐመር እፅዋት ተከቦ ፍቅር እየተቦካ ወደሚጋገርበት፣ ንብ አበባ
ወደምትቀስምበት፣ አዕዋፍና ሰዎች ጥዑም ዜማቸውን ወደሚያዜሙበት፣ የእፅዋት፣ የአራዊት፣ የአዕዋፍ፣ የሰው ዳንኪራ
ወደሚረገጥበት ስፍራ ተጓዘች።
ካርለት በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት ሁሌም እንደምታደርገው
ጀግናውን በዓይኖቿ አማተረች" ጀግናው እየዘለሉ አየሩን ከሚቀዝፉት ጐረምሶች መካከል የለም ካርለት፣ «አምላኬ!» ብላ፣
እንደ መኪና ጎማ ተነፈሰች" በጭንቀት ዓይኖቿ ሲቅበዘበዙ ግን ደልቲ ገልዲ ካለወትሮው ተክዞ፣ ራቅ ብሎ ቆሞ አየችው" ጀግናውን ተክዞ አይታው አታውቅም። ቀጭኔ፣ አንበሳ...የገደሉት አነጣጣሪ
ዓይኖቹ ቦዘው ስታይ ሰውነቷ ተዝለፈለፈባት። ጭንቀት ያዘለው ዶፍ
ዝናብ ሊያለብሳት መጣሁ ወረድሁ እያለ አጕረመረመባት። ካርለት
በደመ ነፍስ ወደ እሱ እየተንቀሳቀሰች፣ «ምን ሆኖ ይሆን?» ብላ ራሷን ጠይቃ ፊት ለፊቱ ሄዳ ቆመች።
«ካርለት» አላትና ዝም ብሎ ዓይን ዓይኗን ተመለከተ
«ምን ሆንክ ደልቲ?» ብላ ጠየቀችው።
ዝም ብሎ ዓይኖቹን ከሷ ላይ አንሥቶ ወደ ጨረቃዋ ወረወራቸው" ካርለት ዘለሽ እቀፊው እቀፊው አሰኛት።
ካርለት» አለ ደልቲ ዓይኖቹን ሳያወርድ።
«አቤት» አለችው:
ደልቲ ገልዲ ግን ዝም አለ ተመልሶ።
እንደ ባልጩት ድንጋይ እያብለጨለጨ የተከፋፈለው የጭኑና
አጁ ጡንቻ፣ ሣንቃው ደረቱ፣ የሚንቦገቦጉት ትናንሽ ዓይኖቹ በጨረቀዋ ብርሃን ካርለት ስታይ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት
መላ አካሏ እሳት ላይ የወደቀ ቋንጣ ይመስል ኩምትርትሩ ወጣ"
«ወይ አምላኬ፣ ምናለ የልቡን በነገረኝ፤ ምናልባት
መለያየታችን አስጨንቆት ይሆን? መቼም ማለት የፈለገው ነገር አለ
ከአንደበቱ እንዳያወጣው ግን እየተናነቀው ነው» ብላ አሰበች"
ይህን ስታስብ፣ «ካርለት መሄድሽ ነው?» የሚል ከደልቲ ጕሮሮ አፈትልኮ ወጣ"
«አዎ መሄዴ ነው» አለች ካርለት፣ «ምን ሊለኝ ይሆን አምላኬ» ብላ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተችው» ደልቲ ግን አሁንም ጸጥ አላት።
«ትወደኝ ነበር?» ብላ የሞኝ ጥያቄ ጠየቀችው ደልቲ ግን ትክ ብሎ አይቷት፣ «አይ» አላት፣ በምፀት" ካርለት መልሱ ከልቡ እንዳልሆነ በሚገባ ተረዳች" ካርለት ያኔስ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆነች ጀግናው እንደገና ጣላት። ስለዚህ፣ እጇን ሰዳ እጁን ያዘችውና ወደ
ሰንበሌጡ ይዛው ገባች“ ከዚያ ጭፈራው በዓይነት በዓይነት ቀጠለ ዳንኪራው ተመታ። አሁንም እንደ ባለፈው ተመልካች በሌለበት የተፈጥሮ አዳራሽ ትርዒታቸውን ለራሳቸው አሳዩ። ዳንኪራው ግን
እንዳለፈው ተስፋ ሰጪ ሳይሆን ለየት ያለ፣ የሰቀቀን፣ የኃዘን፣
የህምታ ውዝዋዜ ሆነ።
በነጋታው ፀሐይ ከወደቀችበት ተነሥታ ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ ካርለት ዕቃዎቿን በስቴሽን ዋገን መኪናዋ ላይ ከከሎ ጋር አስተካክለው ጭነው እንደ ጨረሱ ሐመሮች ከየመንደሩ ተሰባስበው
ሴቶቹ ደረታቸውን እየደቁ ሲያለቅሱ፣ ወንዶቹ በርኮታቸው ተቀምጠው ተከዙ። ካርለት ዓይኗ በእንባ ሊጠፋ ተቃረበ" የሁለት
ዓለም ዘመዳሞች ሲለያዩ አምርረው አዘኑ"
ካርለት፣ ከሎ ሆራና ጎይቲ በሽማግሎች ተመርቀው፣ ጀርባቸው በከብት እበት ከተቀባ በኋላ ሦስቱም መኪና ውስጥ ገብተው መኪናዋ ተንቀሳቅሳ አቧራው ሲነሣ የሐመር ጭንቅላቶች ወደ መሬት
አቀረቀሩ" ካርለት ትንሽ ከተጓዘች በኋላ ኢቫንጋዲ የጨፈረችበትንና
የቦረቀችበትን የሐመር ጫካ ለመሰናበት መኪናዋን አቁማ ስትወርድ፣ ከሎና ጎይቲም አብረው ወረዱና እንባቸውን አወረዱ..
ወፎች ግን እየዘመሩ፣ ቱር እያሉ እየበረሩ፣ እየተዳሩ ምግባቸውን መፈለጋቸውን አላቆሙም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዋናው የመኸር ወቅት የሐመር የተፈጥሮ ውበትና ልምላሜ የክቱን አውጥቶታል" እፅዋት ለምልመው አብበዋል የከስኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ሆኖ ይፈሳል። የቡስካ ተራራ አሁንም ከቦታው ሳይንቀሳቀስ የሐመሮች የታሪክ ሐውልት ሆኖ ፈገግታውን በልምላሜ ያሳያል"
ከአሰሌ ሰንሰለታማ ተራራዎች እስከ ኬንያ ጠረፍ፣ ከኤርቦ እስከ አሪ ማኅበረሰብ የሐመሮች ዘፈንና ዳንኪራ አሁንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ያስተጋባል። የሐመር ተፈጥሮ ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ከድንቢጥ ወፍ እስከ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ፣ ከትል እስከ ተሳቢው
ዘንዶ ከከብት እስከ ሚዳቋና ድኩላ ይፈነጭበታል"
ሁሉም የተፈጥሮ ድምፁን ባሰማ፣ እንቅስቃሴ ባደረገ ቁጥር ውብ የሙዚቃ ቅማሬ ከጋራ ጋራ፣ ከቋጥኝ ቋጥኝ ይስተጋባል" የሐመር ምድር ለሚመጡትም ለሚሄዱትም ሁሌም ያው ነው" መለምለም፣ ማበብ፣ መጠውለግ፣መድረቅ..ተልሶ ደግሞ መለምለም።
ደልቲ ገልዲን መኪናዋ የሚወዳቸውን ጭና በአራት እግሯ ከቡስካ በስተጀርባ ተሠውራበታለች መዝናኛዎቹ፣ መደሰቻዎቹን
ሌባዋ ይዛ በአቧራ ደመና ገብታ ጠፍታበታለች" ደልቲ አሁን ሁለት እግር ያለው ከሌላ ፍጡር ያልተለየ መሆኑን ሳይረዳ አልቀረም
የጎሽን ጀርባ በአንድ ምት ብቻ አከርካሪውን አድቅቆ
የሚያንበረክከው አንበሳ መጨረሻ የዝንብ መዝናኛ መሆኑ የማይቀር እውነት መሆኑን ደልቲ የግድ ሊመለከተው፣ ሊደርስበት ነው"

👍28❤3