አትሮኖስ
274K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
436 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...«ለመሆኑ የትናንቱን ፖሊስ ፍንግል አርገኸው ነበር ለካ
የሮጥከው» አለኝ
«አዎን» አልኩት
«ተነስቶ ቢከተልህስ? እና ካንተ የፈጠነ ሯጭ ቢሆንስ? ወይም
ስትሮጥ ውጋትቢይዝህስ? ወይም ቢተኩስብህስ? ወይ ፊሽካ ቢነፋና
ሌሎች ፖሊሶች ከያለበት ወዳንተ ቢሮጡስ?»

«ታድያ እንዴት ማድረግ ነበረብኝ?» አልኩት
«አታውቅምን ?»
«አላውቅም»
«እንግዲያው ነገ ጧት በአስራ አንድ ተኩል ቤቴ ና....
ከዚያ በኋላ አራት ወር ሙሉ ጧት ጧት ካስራ አንድ ተኩል እስከ
አንድ ተኩል ድረስ የሚያውቀውን ሁሉ አስተማረኝ፡፡ ከሱ እኩል
ከሆንኩ በኋላ፣ አንድ ሌሊት ማጅራት መቺዎች የሚበዙበት
ሰፈር ወሰደኝና እኔ እንግዲህ አላግዝህም፣ ዝም ብዬ ማየት ነው።ይሄ የመጨረሻ ፈተናህ ነው አለኝ

አንድ ቦታ ስድስት ዱርዬዎች ከበቡና ማኑ «ወዲህ በኩል
ያሉት ሁለቱ የኔ ናቹው፣ አራቱን ውሰድ አለኝ በእንግሊዝኛ።
የኔን ሶስቱን አጋደምኳቸው፣ አንዱ ሸሸ። ፈተናዬን አለፍኩ

ግን አንድ ሌሊት አክስ ውስጥ ብቻዬን ስዘዋወር፣ ሶስት
አሜሪካኖች ግድግዳ ላይ ሲፅፍ ይዘውት፣ ሊደበድቡት እንደ ጀመሩ
ድንጋይ በመወርወር አስጥዬዋለሁ። ይህን የአምባጓሮ ችሎታውን ለምን ከነሱ ለማምለጥ አልተጠቀመበትም? ማወቅ ፈለግኩ፣ ግን አልጠየቅኩትም። ከፈለገ እሱ ራሱ እንደሚነግረኝ አውቃለሁ)

ማኑ አንድ ሊላ ነገር አስተኖሮኛል (አለ ባህራም) አየህ፣ ድሮ ሻህ ግርማ ሞገስ ያለው፣ ከነሲሩስ ከነዳርዮሽ የሚስተካከል ንጉስ
መስሎኝ ነበር። እና እየጠላሁትም አከብረው እፈራው ነበር። በማኑ
ቀልድ እየሳቅኩ በማኑ አይን ሳየው ግን ሽህ ምንም ግርማ ሞገስ የለውም። በነዳርዮሽ ዙፋን ላይ ተቀመጠ እንጂ፣ የነዳርዮሽ ደም ወይም ክብር ወይም ጀግንነት የለውም፡፡ የአንበሳ ቆዳ የለበሰ ውሻ ነው

ብኝ እሱን ተወው

አንድ ጊዜ የኮረምሻህር ወደብ ከተማ የሰራተኞች ማርበር
ሰላማዊ ሰልፍና ንግግር ለማድረግ በህግ ተፈቀደለት። የኛ ፓርቲ ላያግዛቸው ወስኖ፣ እኔና ማኑ በባቡር ሄድን፡፡ ስነ ስርአቱ
የሚካሄደው በታጠረ ኳስ ሜዳ ውስጥ ነበር። ቦታ ቦታችንን ይዘን
ንግግሩ የሚደረግበት ሰአት ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው፣ ብዙ ብዙ
ፖሊሶች በትልቁ በር ሲገቡ አየሁ። እንደገቡ ፊታቸው ያገኙትን
በዱላ መጨፍጨፍ ጀመሩ
ማኑን «እንሂድ?» አልኩት
«አንተ ሂድ አለኝ
«አንተስ?» አልኩት
«እኔ ደህና ቦታ እንድይዝና ካለቆቻችን ትእዛዝ ካልመጣ
በስተቀር እንዳልለቅ ታዝዣለሁ»
ይህን ጊዜ ሜዳውን ጩኸትና ትርምስምስ ሞልቶታል
“አለቆቻችን የተፈቀደላቸው መስሏቸው ነበር፡፡ ግን ፈቃዱ
ወጥመድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን እዚህ መቆም ምንም ጥቅም የለውም፡፡
«ና እንሂድ» አልኩት
«አልሄድም፡፡ ኮሙኒስት ነኝ። አለቆቼ ሽሽ ካላሉኝ ልሸሽ
አልችልም» አለኝ
«እዚህ መቆምህ ጥቅም የለውማ!» አልኩት
“ምን ታውቃለህ? ይልቅ ሂድ ፖሊሶቹ እዚህ ሊደርሱ ነው።
በወዲያ በኩል ዝለልና አምልጥ» አለኝ
«አንተ ካልሄድክ አልሄድም» አልኩት
«እኔ አለቆቼን እታዘዛለሁ። አንተም አለቃህን ታዘዝ፡፡ አለቃህ
እኔ ነኝ፡፡ በል አሁን ሂድ። ሂድ!» አለኝ ሄድኩ። አጥሩን ልዘል ስል ዘወር ብዬ አየሁት። ዙሪያውን
ፖሊሱና ሰዉ ሲተራመስ ሲከታከት፣ እሱ ሁለት እጆቹን ደረቱ ላይ አጣምሮ እንደ ሀውልት ቆሟል። በአጥሩ ዘለልኩ
ማኑ ፖሊሶቹ ደብድበውት ሶስት ሳምንት ሙሉ ሀኪም ቤት ተኛ
መሀል ጣቱ ተሰብሮ ቀረ። አሁን ሊያጥፈው ኣይችልም
ማኑ እንዴት ኮሙኒስት እንደሆነ ልንገርህ?
አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛ ነበረው። ጓደኝየው በጣም ጥሩ
ልጅ ነው:: ቆንጆ ቆንጆ ግጥሞችን ይደርሳል። ግን ድሀ ብጤ ነው።
ከዚህም በላይ እጅግ የተዋበ!

አንድ ቀን የዚህ ልጅ አባት ታሰሩ። በሽተኛ ሚስት፣ ስድስት
ትንንሽ ልጆች ኣሏቸው። እሱ የመጀመሪያ ልጃቸው ነው። አባትየው ታስረው ልጆቹ ምን ይብሉ? ልጁ ጨነቀው። ያባትየውን ጉዳይ የሚከታተለው የፖሊስ ሹም ቢሮ ሄደና እያለቀሰ የቤቱን ችግር ነገረው። ፖሊሱ ደግ ነበር። የልጁ ችግር ገባው። ጉዳዩ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ፣ አባትህን ዝም ብዬ ነፃ ብለቃቸው፣ የበላይ ሹማምንት ይቀጡኛል፡፡ ብቻ ለማንኛውም ዛሬ ማታ ለእራት ቤቴ ብቅ በልና እንመካከርበታለን» አለው
ሲመሽ ልጁ ፖሊሱ ቤት ሄደ፡፡ እራት ከበሉ በኋላ ፖሊሱ
ልጁን ያሻሽው ጀመር። ልጁ በመጀመሪያ ደነገጠ፤ በኋላ ተቆጣ::ይኸኔ የፖሊሱ ፊት ተለወጠ። ደግ የነበረው በሀይል ክፉ ሆነ፡፡ ረጋ ባለ ድምፅ ልጁን እንዲህ እላው
«አባትህ በኔ እጅ ነው:: ላስገድለውም እችላለሁ፣ ላሳስረውም እችላለሁ፣ ላስፈታውም እችላለሁ፡፡ ስለዚህ አባትህ ባንተ እጅ ነው
ማለት ነው:: እዚህ ከኔ ጋር ካደርክና ካስደሰትከኝ፣ ነገ አባትህ
ለምሳ ቤቱ ይመጣል፣ ተነገ ወዲያ መስሪያ ቤቱ ይሄዳል፣ በስህተት
መያዙን አስመሰክርለታለሁ፡ ቤቶችህ የሚበሉትን ያገኛሉ። እኔን
እምቢ ካልከኝ ግን አባትህ ወየውለት! ትንንሽ ወንድሞችህና
እህቶችህም ምን እንደሚውጣቸው አላውቅም፡፡ ባንተ አጅ ናቸው።
ሁሉም ባንተ እጅ ነው»
ልጁ እሺ እርስዎ እንዳሉኝ አደርጋለሁ አለ። አባትየው ተፈታ።
መስሪያ ቤቱም ተቀበሉት
ልጅየው ውርደቱን ተሸክሞ መጣና የተፈፀመበትን ግፍ
እያለቀሰ ለማኑ አጫወተው። ምን ባደርግ ይሻለኛል? አለው
አየሀ፣ ሲለያዩ ፖሊሱ ምን ብሎታል «እኔ የተገደልኩ ወይም
የተጎዳሁ እንደሆነ፣ ሁለት ሌሎች የፖሊስ ሹማምንት አሉ፤ ጓደኞቼ
ናቸው፡ ኣንተ እንደጎዳኸኝ ያውቃሉ፤
ስለዚህ አባትህን እነሱ
መልሰው ያሳስሩታል። ያን ጊዜስ አባትህን አያርገኝ፣ ቤቶችህን
አያርገኝ! ስለዚህ በኔ ላይ የበቀል ሀሳብ ባታስብ ጥሩ ነው።
ብሉታል። ልጁ ምን ይሁን? የተዋረደ ክብሩን ሊበቀል አልቻለም።
ግን ውርደቱ ሊረሳ የሚችል አይነት አይደለም። ልጁ አልቻለም።
በዛበት፡፡ ከሚችለው በላይ በዛበት፡ አበደ። አበደ በቃ! እብድ ሆነ።
ቤቶቹ በድህነታቸው ላይ ሀዘን ተጨመረጣቸው:: ደግሞስ ማን
ያውቃል? ኢራንም አንድ ታላቅ ደራሲ ባጭሩ ተቀጨባት ማለት
ይሆናል'ኮ
አይ ኢራን! ስንቱን ጉድ ትችያለሽ! ኢራን ውቢቱ! እንዴት
መሰለችህ! አቤት ህዝቡን ብታውቀው! ቋንቋውን ብትሰማው! አይ ህዝብ! እንደ ምንም ብዬ ከሻህና ከጋንግስተሮቹ ነፃ ባወጣው'ኮ የኢራን ህዝብ በደስታ ሊኖር የሚችል ህዝብ ነው። ክብሩን ልመልስለት ብችል፡ ማንንም ሳይፈራ ሰርቶ ለመብላት ቢችል፤ ህግ ካልጣስ ማንም ሊያስረው እንደማይችል እርግጠኛ ለመሆን ቢችል!
ሻህና አሜሪካኖቹ ሀብቱን ባይነጥቁት! ብቻዬን እንዳልመስልህ! በጭራሽ ብቻዬን አይደለሁም፡፡ እኔ ያየሁትን ያዩ፣ እንደኔ የሚቆረቆሩ፣ እንደኔ የተናደዱ፣ እንደኔ ደም ለማፍሰስ ዝግጁ የሆኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ኢራናውያን አሉ። አሉ! አሉ!
የሚመራቸውን ይጠብቃሉ! (አለ ባህራም)
ባህራምና እኔ ከተዋወቅን ጀምሮ እስከተለያየን ድረስ ስለኢራን
ያወራልኝ ነበር። ኢራን፣ ኢራን፣ ኢራን። አልሰለቸኝም ግን ይበዛብኝ ነበር። ይልቁንም የአገሩ መበስበስ ያንገሸግሸኝ ነበር፡፡ ሁሉ ነገር በጉቦ ነው። ፖሊሱ፣ ጃኛው፣ አስተማሪው ሳይቀር ጉቦ ይበላል።
#ምንዱባን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ዣቬር

መሴይ ማንደላይን ከቤቱ ውስጥ የሕክምና እርዳታ የሚሰጥ ክፍል ስለነበረው ፋንቲንን ወደዚያ አስወሰዳት:: የሕክምና እርዳታ የሚሰጡ ሴሮች አልጋ ላይ አስተኝዋት:: በኃይል አተኩሳለች:: ሕሊናዋን ሳታውቅ እንዲሁ እየቃዠች ጥቂት እንደቆየች እንቅልፍ ይዞአት ጭልጥ አለ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ከእንቅልፍዋ ነቃች
ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ አየች:: መሴይ ማንደላይን ጣራ ጣራውን እያየ ቆሞአል፡፡ ፊቱ በሀዘኔታ ተሞልቷል:: ከንቲባው ጣራውን ሳይሆን ግድግዳ
ላይ ከፍ ብሎ የተሰቀለወን መስቀል ነበር የሚያየው፡፡
ይህ ሰው መልአክ እንጂ ሰው አይመስላትም:: ሰውነቱ በብርሃን
የታነጸ መሰላት፡፡ መሴይ ማንደላይን እየጸለየ ስለነበር ጸሎቱን ላለማቋረጥ ሳትናገር ለረጅም ጊዜ አፍጥጣ አየችው:: በመጨረሻ ግን እየፈራች ቀስ
ብላ ተናገረች::

«ምን እየሠሩ ነው?»

መሴይ ማንደላይን ከዚህ ሥፍራ የፋንቲንን መንቃት እየተጠባበቀ
ለአንድ ሰዓት ያህል ቆሞአል፡፡ እጅዋን ይዞ የልብዋን አመታት ቆጠረ::
«አሁን ምን ይሰማሻል? ደህና ነሽ!»
«በጣም ደህና ነኝ:: እየበረታሁ ነኝ፤ እንቅልፍ ወሰደኝ» አለች ፋንቲን፡፡
«እንግዲያውስ ወደ ጥያቄሽ ልመለስና ምን ትሠራለህ ስላልሽው ስላንቺው ፈጣሪን በመማጠን ጸሎት እያደረስኩ ነበር፡፡»
ያን እለት ማታ ስለፋንቲን የሕይወት ታሪክ ሲጠይቅ አምሽቶ
በሚቀጥለው ቀን ያንኑ ቀጠለ፡፡ ምንም ነገር ሳይቀረው ስለፋንቲን ኑሮ ሁሉንም አወቀ፡፡
«ከመጠን በላይ ስቃይ ተቀብለሻል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ሀዘን አይግባሽ፡፡በዚህ ዓይነት ነው ሥጋ ለባሾች ወደ መስዋዕትነት የሚለወጡት:: ከዚህ
የተለየ መንገድ እንዳለው አላውቅም:: ይህ አንቺ ያለፍሽበት ምድራዊ ገሀነም ወደ መንግሥት ሰማይ የሚወስድ የመጀመሪያ እርምጃ ነው:: ከዚያ መጀመር ግዴታችን ነው::»
ይህን ካለ በኋላ መሴይ ማንደላይን በኃይል ተነፈሰ:: ፋንቲን ጥቂት ፈገግ ስትል ወላቃ ጥርስዋ ታየ::
መሴይ ማደላይን ወደ እነቴናድዬ ደብዳቤ ጻፈ፡፡ በደብዳቤው ፋንቲን
ያለባት እዳ አንድ መቶ ሃያ ፍራንክ እንደሆነ ገልጾ የላከላቸው ግን ሦስት መቶ ፍራንክ መሆኑን ይጠቅሳል፡፡ ብልጫ ገንዘብ የላከላቸው የፋንቲንን
ልጅ ይዘው ወዲያውኑ እንዲያመጡ ነበር:: የልጅትዋ እናት እንደታመመችና
ልጅዋን ለማየት እንደጓጓች ገልጾ ነበር ልጅትዋን ይዘው እንዲመጡ
የጠየቃቸው::
እነቴናድዬ ደብዳቤውና ገንዘቡ እንደደረሳቸው በጣም ተደነቁ::
«ሰይጣን» አለ ሚ/ር ቴናድዬ ለሚስቱ:: «ልጅትዋን አንሰጥም::
ምናልባት አንድ ቂል በውበትዋ ተማርኮ ይሆናል ይህን የመሰለ ደብዳቤ የሚጸፈው::»
ሰውየው ልጅትዋን በመላክ ፈንታ ሂሳቡን በጥንቃቄ አስልቶ ፋንቲን ያለባት እዳ አምስት መቶ ፍራንክ እንደሆነ ገልጾ የመልስ ደብዳቤ
ለመሴይ ማንደላይን ጻፈለት:: ተጨማሪው ሁለት መቶ ፍራንክ ልጅት በታመመች ጊዜ ለመድኃኒት የወጣ መሆኑን አስረድቶ ነበር የጻፈው።

መሴይ ማንደላይን ደብዳቤው እንደ ደረሰው ሦስት መቶ ፍራ
ላከላቸው:: ከገንዘበ ጋር ደግሞ በተቻለ ፍጥነት ኮዜትን ይዘው እንዲመ መልዕክት አከለበት፡፡
«በምንም መንገድ ልጅትዋን አንለቅም» አለ ማ/ር ቴናድዬ::
ፋንቲን በሽታዋ ጠናባት እንጂ ስላልተሻላት አልጋ ላይ ቆየች
መሴይ ማንደላይን በቀን ሁለት ጊዜ ይጠይቃታል፡፡ በጠይቃት
ቁጥር «ኮዜትን ቶሎ በዓይኔ የማያት ይመስሎታል?» ስትል ትጠይቀዋለች።
እርሱም ሲመልስ “ምናልባት ነገ! በማንኛውም ሰዓት ልትደርስ
ትችላለች» ይላታል፡፡
በዚህ ጊዜ የእናተዬዋ የገረጣ ፊት ወገግ ይላል::
«አዬ! እንዴት ደስ ባለኝ!» በማለት ትቆጫለች::
ሕመምዋ እያደር ጠናባት:: አንድ ቀን ሐኪሙ የሳምባዋን አተነፋፈስ
በማዳመጫ መሣሪያ ካዳመጠ በኋላ ራሱን ነቀነቀ::
«እየተሻላት ነው?» ሲል መሴይ ማንደላይን ጠየቀው::
«ዓይንዋን ለማየት የጓጓችላት ልጅ አላት አይደል!» አለ ዶክተሩ
«አዎን፡፡»
«እንግዲያውስ ቶሎ ብታስመጠላት ይሻላል፡፡»
መሴይ ማንደላይን በድንጋጤ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡
«ሐኪሙ ምን አለ?›› አለች ፋንቲን፡፡
መሳይ ማንደላይን ፊቱን ፈገግ ለማድረግ ሞከረ::
«ልጅሽን በቶሎ እንድናስመጣልሽና ይህም በሽታሽን ሊያቃል እንደሚችል ነው የነገረን» ካላት በኋላ ወደ ቢሮው ሄደ፡፡
መሴይ ማንደላይን ከቢሮው ውስጥ ቁጭ ብለ ሥራውን እየሰራ
ሳለ የፖሊስ አዛዥ ዣቬር ሊያነጋግረው እንደሚፈልግ ተገለጸለት።

«ይግባ! » አለ፡፡

ዣቬር ገባ፡፡
ለከንቲባው የአክብሮት ሰላምታ ሰጠ፡፡ ፊቱን ወደ መስኮት አዙሮ
ስለነበር ዣቬር ሲገባ የከንቲባውን ጀርባ ነው ያየው፡፡ መሴይ ማንደላይን ቀና ብሎ ሳያየው ወረቀት ማገላበጡን ቀጠለ፡፡

ዣቬር የክፍሉን ፀጥታ ሳያደፈርስ ቀስ ብሉ ወደፊት ተራመደ፡፡ ፊቱ
ላይ የቆራጥነት ብቻ ሳይሆን የድፍረትም ዓይን በግልጽ ይታያል፡፡ በመጨረሻ ከንቲባው ብዕሩን አስቀምጦ ቀና አለ፡፡
«ታዲያስ፣ ምንድነው ዣቬር? ምን አጋጠመህ?»
ዣቬር አሳቡን ለማሰባሰብ ብሎ ለአጭር ጊዜ ዝም አለ፡፡ ከዚያም
ድምፁን አለስልሶ ሀዘን በተሞላበት አንደበት «ክቡር ከንቲባ፤ አንድ ወንጀል ተሠርታል» አለ፡፡

«የምን ወንጀል?»
«አንድ ግለሰብ አንድን የመንግሥት ባለሥልጣን በስህተት ስለወነጀለ ራሱን ለማጋለጥ ይፈልጋል፡፡ እኔ ደግሞ አሁን የመጣሁት ሥራዬ
እንደመሆኑ መጠን ይህን ለማሳወቅ ነው::»
«ራሱን ለማጋለጥ የሚፈልገው ሰው ማነው?» ሲል መሴይ ማንደላይን ጠየቀው፡፡
«እኔ» አለ ዣቬር፡፡
«አንተ?»
«አዎን፤ እኔ!»
«ማንን በድለህ ነው ራስህን የምታጋልጠው?»
«ክቡርነትዎን፡፡»
መሴይ ማንደላይን ወንበሩን አስተካክሎ ተቀመጠ:: ዣቬር ሳይፈራ አሁንም በትህትና ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ክቡር ከንቲባ ፧ እኔ አሁን እርስዎን የምጠይቀው ላደረስሁት በደል
ከስራ እንዲያሰናብቱኝና ክስ እንዲመሠርቱብኝ ነው:: »
መሴይ ማንደላይን በጣም ተደንቆ ለመናገር እፉን ከፈተ:: ዣቬር
ቀድሞ ተናገረ፡፡
ስራህን ብቻ ልቀቅ ይሉኝ ይሆናል:: ግን ይህ ብቻ አይበቃም:: በገዛ
ፈቃድማ ሥራ ተመልቀቅ መቻል ክበር ነው:: ጥፋት ስላጠፋሁና በደል ስለሠራሁ ለፍርድ ቀርቤ መቀጣት አለብኝ:: ከስራም መባረር ይኖርብኛል
«እንዴ! በምን ምክንያት?»
«ክቡር ከንቲባ ጉዳዩን ሲያውቁት ይህን ጥያቄ አይጠይቁኝም::
ነገሩ ሁሉ ይገባዎታል፡፡
ዣቬር በኃይል ተነፈሰ፡፡ ሀዘን እየተሰማውና እያፈረ ንግግሩን ቀጠለ
«ክቡር ከንቲባ ከስድስት ሳምንት በፊት ያቺን ሴት በነፃ ከለቀቅዋት
በኋላ በጣም ተናድጄ ከስሽዎት ነበር፡፡»
«እኔን ነው የከሰስከው?»
«አዎን፤ ፓሪስ ድረስ ሄጄ ለፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክሴን አቀረብኩ
ብዙ ጊዜ የማይስቀው መሴይ ማንደላይን ከት ብሎ ሳቀ::
«የፖሊስን ሥልጣን ተጋፋ ብለህ ነው የከሰስከኝ?»
«የለም፧ የጥንት ወንጀለኛ ናቸው ብዬ ነው የከሰስክዎት፡፡»
ከንቲባው ደንገጥ አለ። እንዳቀረቀረ የቀረው ዣቬር ንግግሩን ቀጠሉ
«አልተጠራጠርኩም ነበር፡፡ ለብዙ ጊዜ ጥርጣሬ ነበረኝ፡፡ መልካችሁ
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በታደለ_አያሌው

...ረቂቋን የጆሮ ማዳመጫ አዉቆብኝ ኖሯል፤ መንጭቆ አወጣብኝ፡፡
ማደመጫዉን የያዘበትን እጁን ሳይ ተገለጠልኝ ባልቻ በአንድ ወቅት
ከፍተኛ የመንግሥት ደኅንነት ሹሞችን አጠቃላይ መገለጫቸዉን ለጥቂት
የሲራክ፯ አባላት በገለጸልን ጊዜ፣ ስለዚህ ሰዉ ልዩ ምልክት የነገረን አስታዉሼ ይኼን ሰዉ ገመትሁት አወቅሁት የቀለበት ጣቱ ከስሯ ጀምራ የለችም: በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ሰው
እጅ መግባቴን፣ አሁን አወቅሁ ሰዉዬዉ የሀገር ዉስጥ ደንነት ዋና መምሪያ ሹም መሆኑን አሁን ገና፣ ነገሮች ሁሉ ከተጨመላለቀ በኋላ ተረዳሁ። አጠመድሁ ስል እንደ ተጠመድሁ ያወቅሁት፣ አሁን ገና ሁለት እጆቹ ካነቁኝ፣ ድፍርስ ዓይኑ ካፈጠጠብኝ፣ ድርብርብ ጥርሱ ካገጠጠብኝ በኋላ ነበር። መጠርጠር አልነበረብኝም? ነበረብኝ።

«ላም ሆይ ላም ሆይ ሞኟ ላም ሆይ
ሣሩን አየሽና ገደሉን ሳታይ
እልም ካለው ገደል ወደቅሽብን ወይ

እያልሁ፣ መስኮት ቀርቶ ስንጥቅ እንኳን በሌለዉ አመዳም ግድግዳ ላይ
አፍጥጬ በራሴ አላገጥሁበት።

“ጥሩ” አለ የተገለበጠችዋን ወንበር አቃንቶ ራሱ እየተቀመጠባት
“እንተዋወቃ… ማን ብዬ ልጥራሽ?”

ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጭጭ አልሁበት።

“ኦ..ይቅርታ፤ መጀመሪያ ራሴን ማስተዋወቅ ይገባኛል ለካ። ኮሎኔል…"
ብሎ ስለራሱ ሊነግረኝ ሲጀምር ጆሮዬን ያዝሁበት ስሙን እንዲጠራብኝ
አልፈለግሁም አዉቄዋለኋ!

“ማ..ነ..ሽ?” አለኝ በዝግታ፣ በዚያች ኦና ቤት ዉስጥ ብቻ ለብቻ ሲከበኝ
ቆይቶ በዓይኔ እንኳን እንዳልላወስ ከግድግዳዉ ጋር እያጣበቀኝ
ወዲያዉኑ ጆሮዉን ወደ ከንፈሮቼ አምጥቶ ለረዥም አፍታ መልሴን መጠባበቅ ቢጀምርም፣ ትንፋሼን ሳይቀር ዋጥሁበት እንኳንስ ለኮሎኔ ይቅርና፣ ለገዛ እናቴ እንኳን እንዲህ ነዉ ብዬ የማፍረጠርጠዉ ማንነት የለኝ እኔ፡ ዉብርስት እባላለሁ የሲራክ አባል ነኝ የምል መስሎታል? አያዉቀኝማ! አ ያ ዉ ቀ ን ም! ሲራክ.፯ን ጨርሶ አያዉቀንም ማለት ነዉ። የሆነዉ ሁሉ ሆኖም፣ ኮሎኔሉ ከዚህ በላይ
ትዕግሥት የሚኖረዉ አይመስለኝም: ቀጣዩን ጥያቄዉንም እንደዚሁ
ተለሳልሶ እንደማይጠይቀኝ ቁልጭ ብሎ ታይቶኛል።

ስለዚህ አእምሮዬን ማሠራት አለብኝ፡

እኔ ስለማደርገዉ ሳወጣ ሳወርድ፤ እሱ ቀድሞኝ ጆሮዉን ከከንፈሮቼ አንስቶ ከንፈሮቹን ወደ ጆሮዬ አመጣብኝ፡ ይህም ሳያንስ የጥምቀትን ዉርጭ የሚያስመሰግን ቀዝቃዛ ትንፋሹን ለቀቀብኝ ፡ ከዚያ ምላሱን እና
የላይኛዉን ትናጋዉን በማጋጨት መሰለኝ፣ ሦስት ሰቅጣጭ ድምፆች
አከታትሎ አጮኸብኝ በምላስም ማጨብጨብ ይቻላል እንዴ?

“ጣ! ጣ! ጣ!”

ጣዉላ እና ጣዉላ ቢጋጭ ራሱ እንደዚህ መጮሁን እኔ እንጃ በቅጽበት አንድ ጎረምሳ እንደ ሳምሶናይት ያለ ትልቅ ቦርሳ ተሸክሞ ከተፍ አለለት የመጨረሻ ዕድል ሰጥቼሻለሁ፣ የምትነግሪኝ አለ? ማነሽ ለማለት በሚመስል ሁኔታ በጥልቀት ሲያስተዉለኝ ቆይቶ ወደ በሩ አመራ።
በሩን ከፍቶ እንደ መዉጣት ካለ በኋላ፦

“ቶሎ!” የሚል ትእዛዝ ሰጠዉ

“እሺ፤ እንደ ተለመደዉ” ሲል መለሰለት፣ ባለ ሳምሶናይቱ አናዛዥ። እኔና አናዛዡ ብቻ ቀረን፡ በሩን ቀጭ አድርጎ ቆለፈና መክፈቻዉን በኪሱ ወሽቆ ሳምሶናይቱን እዚያች ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጠ። እስኪከፍተዉ ድረስ እሱም ዓይኑን ከዓይኔ፣ እኔም ዓይኔን ከእጁ ላይ አልነቀልንም አንደኛዉን ኪስ ከፍቶ ዘረገፈዉ፡ ሰአሊ ለነ! ያላመጣዉ ምንም የስለት መሣሪያ የለም፡ ትንሿ የብረት መጋዝ ሳትቀር መጥታለች፡ ከሳምሶናይቱ
ሌላኛዉ ኪስም እንዲሁ መርፌዎች እና መርዝ የተሞሉ አራት ብልቃጦች ዘረገፈ፡ ይኼ ሁሉ ለኔ እንዳይሆን ብቻ! ነዉ?

“ቶሎ ምረጭ፣ የቱ ላስቀድምልሽ?”

“እ?” አልሁት፣ ድምፄን ቢከዳኝ በቅንድብ ምልክት፡
“‹ለሞኝ ጉድኋድ አያሳዩትም፣ ቤት ነው ብሎ ራሱ ይገባበታል› ተብሎ ሲተረት ብሰማም፤ የቆንጆም ሞኝ እንዳለዉ ግን አቺን አሁን ገና አየሁ ገና በገዛ'ጅሽ ሰተት ብለሽ እንጦሮጦስ ትወርጃለሽ? ጅል!”

ደም የጠማዉ ነፍሱን በጥርሱ በኩል አሳየኝ፡፡ በኹለቱም ጎኗ ስለት ያላትን ቢለዋ እና ፒንሳ እያጋጨ ወደኔ መጣ፡ ሥራዉ የሰዎችን አካል እያፈረሰ የሚያናዝዝ ሰዉ መሆኑ ያስታዉቃል ለእንደ'ሱ ዓይነት ሰዎች ደግሞ ጥፍር መንቀል፣ የዉሃ ጥም እንደ መቁረጥ ያለ እርካታ ያመጣላቸዋል እንጂ እንዲች ብሎ አይስቀጥጣቸዉም፡ ለምደዉታል:
ርኅራኄ የሚባለዉን ነገር ከዉስጣቸዉ ጨልጠዉ ደፍተዉታል እንዲያዉም ብዙ ጊዜ የሚመረመረዉ ሰዉ ለሐቅም ሆነ ራሱን ለማትረፍ ሲል፣ ገና ሳይነኩት ቶሎ የተናዘዘ እንደሆነ በኃይል ይናደዳሉ ይባላል።

“ጅል ነሽ እንዴ ? ”

እንደ ቅድሙ ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጸጥ አልሁት።

ቁልቁል እያየኝ ከአጠገቤ ቆሞ ነበር። ወደ ኋላ የሚመለስ መስሎ፣ ከመሬቱ ጋር ደባለቀኝ፡ ምኔን በምኑ እንደ መታኝ እንኳን አላየሁትም። ብቻ ብዥ ጭልም ብሎብኝ ቆየሁ።

ነፍሴ ስትመለስ ብልቃጧን ሲያነሳ አየሁት በብልቃጧ ላይ የሰፈረዉን
ስም አሻግሬ ሳነበዉ ሪማሾ-ሚር (Himacio-mir) የሚባለዉ የሰመመን
መርዝ መሆኑን አወቅሁ። ከሚያስቃዠዉ ሰመመን በፊት ጡንቻ የሚያኮማትር እና ሽቅብ ሽቅብ የሚያስብል ንጥረ ነገሮችም አብረዉ እንደ ተቀበመሙበት አዉቃለሁ እሱን የተወጋ ሰዉ ታዲያ እንባ እንደ ዝናብ
እስኪወርደዉ ድረስ ያምጣል እንጂ ወጥቶለት የሚገላገለዉ ነገር
አይኖረዉም፡ ለማስመለስ ጫፍ ይደርስና ይመለሳል። ስለሆነም ጭንቁ አያድርስ ነዉ በጠባብ ጫማ ከመዋልም፣ ሽንት አቋርጦ ከመቋጠርም፣ ሚስማር ላይ ከመቀመጥም ሁሉ ይብሳል

መርፌዉን ተክሎ ሲሪንጁ እስኪሞላ ድረስ ብልቃጧን ምጥጥ አደረጋት።
ሲሪንጁ ጢቅ አለለት: ይኸኔ ጡንቻዎቼን ማነቃቃት ጀመርሁ። ከቀደመኝ አበቃልኝ፡ ልክ እጁን አንከርፍፎ ሲመጣ፣ የፈራሁ መስዬ አንድ ዓይኔን በእጆቼ ጨፈንሁ: ወደ ማጅራቴ መርፌዉን ሲሰድ እጁን
ለቀም አድርጌ ያዝሁትና፣ ፋታ ሳልሰጠዉ ጠምዝዤ ደረቱ ላይ ስካሁለት ዓይኔን እንኳን እስከማርገበግብ አልዘገየም፣ ትዉኪያ ሲያጣድፈዉ ልክ የገማ ጣት እንደ ጎረሰ ሰዉ፣ እንባዉ ዱብ እስኪል ድረስ ሽቅብ ቢለዉም ምንም አይወጣዉ። “ህእእእ!” ይላል በየቅጽበቱ፣ ስቃይ ብቻ! በዚያ ላይ የሠራ አካላቱ እየዛለበት መጣና፣ እንደ አሮጌ ጨርቅ እጥፍጥፍ ብሏል ጊዜ ኖሮኝ ባዘንሁለትማ ደስታዬ ነበረ ግን ለሐዘኔታ የሚሆነዉን ጊዜ የት ልዉለድለት? ይልቅ አሁኑኑ ማምለጥ አለብኝ፡፡ ባይሆን
እያመለጥሁ አዝንለታሁ
ያዉም ከቻልሁ ከኪሱ ባወጣሁት ቁልፍ በሩን ቀስ አድርጌ ከፍቼ አንገቴን ሳሰግግ
በአካባቢዉ ማንም የለም:: ቢሆንም ግን እርግጠኛ መሆን አልቻልሁም:
ያለሁት ዋነኛዉ ቤተ መንግሥት ዉስጥ ነዉ፡ ቤተ መንግሥትን ያህል ግቢ፣ በሚታዩና በሚዳሰሱ ወታደሮች ብቻ ይጠበቃል ማለት ጅልነት
ነዉ። በየሥርቻዉ ካሜራ፣ በየቦታዉ ረቂቅ ዳሳሾች መኖራቸዉ አያጠራጥርም።

“ህእእእ. አህክ እትፍ! ህእእእ አህክ እትፍ!” ይላል አሁንም፣አንጀቱ ከጉሮሮዉ ጫፍ እስኪደርስበት እየሳበዉ፡ ደም ከሚያስንቅ እንባ በቀር ሌላ ምንም ጠብ አይለዉም: መጨከን አለብኝ እንጂ፣ ሁኔታዉ አንጀት ይበላል ያሳዝናል። የሐፍረተ ሥጋዉን መሸፈኛ ብቻ ትቼለት
#ሳቤላ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...«ደኅና እኔ እጠራታለሁ » አለና ሚስተር ካርላይል በዚያ ግጥም ብሎ በሞላው ሕዝብ መኻል ዐልፎ ሔደ " በዚያ ሰዓት አንዲቷ የለንደን ተጫዋች አሳዛኝ
ዘፈን ስትዘፍን ስለነበር ተመልካቹ ሁሉም ሚስተር ካርላይልን በክፉ ዐይን ዐየው የሰውን መከፋት ችላ ብሎ አለፈና ከሳቤላ ፊት ቆመ።

"እኔ ደሞ ዛሬ ማታ ወደኔ ትመጣለህ ብዬ አላሰብኰም - በጣም ግሩም ዝግጅት አይዶለም ? እኔን መቸም እንዴት አስደሰተኝ መሰለህ » አለችው .

« እዎን በጣም ደስ የሚል ነው » አላት ፊቱን ጥቁርቁር እያደረገ
« አሁን ግን ስቤላ ( ሎርድ ማውንት እስቨርን እምብዛም ደኅንነት የተሰማቸው አልመሰለኝም " ስለዚህ ሠረገላውን ልከውልሻል »

« ምን ! አባባ ደኅና አይዶለም !! » አለች ከመናገሩ ቀጠል አድርጋ።

«ሳያማቸው አልቀረም ግን እስከዚሀም አይመስለኝም " ሆኖም ወደቤት እንድትመጭ ይፈልጉሻል : እየመራሁ ላሳልፍሽ ? »

«አየ አባባ ... ሁልጊዜ እንዳሰበልኝ አሁንኮ እንዳይሰለቸኝ ስለሠጋ ቀደም ብሎ ሊያላቅቀኝ ፈልጎ ነው " አመሰግናለሁ ... ሚስተር ካርላይል " እስከ ዝግጅቱ መጨረሻ እቆያለሁ »

« የለም የለም ሳቤላ ... እሱማ ስለ ባሰባቸው ነው የላኩብሽ» መልኳ ልውጥ ግንባሯ ቁጥር አለ ግን አልደነገጠችም « እሺ ጥሩ አሁን አዳራሹን አንዳንረብሽ ይህ የተጀመረው ዘፈን ያብቃና እወጣለሁ »

« ጊዜ ባታባክኝ ይሻላል ስለ አዳራሹና ስለ ሕዝቡ ምንም አታስቢ»

ወዲያው ተነሥታ ክንዷን ከሚስተር ካርላይል ክንድ ጣል አደረገች » እሱም ነገሩን ለሚስዝ ዲሊ ገጸላትና ሳቤላን እየመራ ይዟት ወጣ ተመልካቹ በግድ
በመጨነቅ መንገድ እየሰጠ አሳለፋቸው " ብዙ ሕዝብም በዐይኑ ተከተላቸው ከሁሉ የበለጠ የተቅበጠበጠችውና ለማወቅ የጓጓችው ግን ባርባራ ነበረች "
የት ሊወስዳት ነው ? » አለች ሳታስበው
« እኔ ምን ዐውቃለሁ ? » አለቻት ኮርነሊያ « ባርባራ ... ዛሬ ማታ መቁነጥነጥ አበዛሽሳ? ምን ነካሽ? ሰዎችወደዚህ የሚመጡት እኮ ሊያዳምጡ ሊመለከቱ
እንጂ እንደዚህ ሊቅበጠበጡ አይደለም »

የሳቤላ ካባ ከተቀለበት ወርዶ ተደረበላትና ደረጃውን ከሚስተር ካርላይል ጋር ወረደች " ሠረገላው እስከ በሩ ተጠጋላት ። ሠረገላ ነጂው መንገድ ለመጀመር
ልጓሙን ሳብ አድርጎ ተዘጋጅቶ ጠበቃት አንድ ሌላ አሽከር እመቤቲቱን ገና ሲያያት የሠረገላውን በር ከፈተላት ሰውየው ገና ሥነ ሥርዓት ያልተማረ አዲስ ገብ ገጠሬ ብጤ ነበር " ክንዷን ከሚስተር ካርላይል ክንድ አስለቅቃ ወዶ ሠረገላው ልትገባ ስትል ሰውየውን እያየች ትንሽ ቆም አለችና « አባባ በጣም አሞታል እንዴ ? » አለችው "

« አዎን እመቤቴ ሲያቃስቱ ለሰማቸው ያሳዝናሉ " አዩ አንጀት ሲበሉ ! ሰዎችማ ምናልባት ዛሬን ቢያድሩ ነው እንጂ አይተርፉም ይላሉ » አላት።

ምርር ብላ ጮኸችና ከመደንገጧ የተነሣ ልትወድቅ ስትል የካርላይልን ክንድ ግጥም አድርጋ በመያዝ ተረፈች ሚስተር ካርላይል ሰውየውን በቁጣ ገፈተረው ።ከዚያ ድንጋይ ንጥፍ መሬት ላይ በቁመቱ ቢዘርረውም አይረካም ነበር " በጣም
ተናድዶበታል "

«ምነው ሚስተር ካርላይል ለምን አልነገርከኝም ? » አለችው እየተንቀጠቀጠች "

« እኔስ አሁን በመናገርሽም በጣም አዝኛለሁ አሁንም አትደንግጪ ! ሁል ጊዜም እንዴት እንደሚነሣባቸው ታውቂያለሽ " የተለመደው በሽታ ተነሣባቸው
እንጂ ሌላ ምን ይሆናሉ ብለሽ ነው » በይ ይልቅ አሁን ግቢና እንሒድ ምንም ክፉ ነገር እንደማይጠብቀን አምናለሁ»

« አንተም አብረኸኝ ልትመጣ ነው ? »

«አዎን ብቻሽን እንዴት እሰድሻለሁ?» አላት እንዲቀመጥ ፈቀቅ አለችለት "

« ግድ የለም ተይው እኔ ከውጭ እቀመጣለሁ » አላትና በሩ ከተዘጋ በኋላ ከነጂው ጐን ተቀመጠ አሽከሮቼ ከኋላ ተቀመጡ " ሠረገላው ገሠገሠ " ሳቤላ
ከአንድ ጥግ ሽብልል ብላ ተቀምጣ ትንሠቀሠቅ ጀመር "

« ለፈረሶቹ አትዘንላቸው ቶሎ ቶሎ ንዳ አለበለዚያ ሳቤላ በሐሳብ ብቻ ትታመማለች » አለ ሚስተር ካርላይል

« ምስኪን ልጅ መከራዋ አላለቀላትም " ሌሊቱ ከመንጋቱ በፊት ከዚህ የከፋ ነገር ይጠብቃታል " እኔ ከዚህ ቤት ዐሥራ አምስት ዓመቴ ነው ። እሷን ገና ሕፃን ሳለች ጀምሬ ነው የማውቃት »

« ግን ኧርሉን በጣም የሚያሠጋቸው ነው ? »

« አዎን በጣም ታመዋል ሚስተር ዌይን ራይት በሽታው ወደ ልባቸው ተሸጋግሯል ሲሉ ሰምቻለሁ »
« ወትሮምኮ በሺታው ሲነሣባቸው እንዶዚህ ኃይለኛ ነው »

« ዐውቃለሁ የዛሬው ግን የተለየ ነው » ከዚህ ሌላ ዶግሞ » አለ ሠረግላ ነጅው በምስጢር አነጋገር « የሌሊት ወፎቹም በከንቱ አይዶለም የመጡት »

« የሌሊት ወፎቹ ? » አለ ሚስተር ካርላይል "

« አዎን " የነሱ መምጣት ሞት ሰተት ብሎ ወዶቤት መግባት መሆኑን የማያወላውል ምልክት ነው»
« ስለ ምንድን ነው የምታወራው ሚስተር ዌልስ?» አለው ሚስተር ካርላይል
« ዛሬ ቤቱን የሌሊት ወፎች ሲዞሩት አመሹ የት አባታቸው አስቀያሚዎች ናቸው " እኔማ አልወዳቸውም "

« የሌሊት ወፎች ኮ ሌሊት የትም መብረር ይወዳሉ ተፈጥሯአቸው ነው . . .

« ተፈጥሮአቸው ቢሆንም በመንጋ ሁነው እየበረሩ በመስኮት አይገቡም ዛሩ ማታ እመቤቴን ከሙዚቃው ትርዒት አድርሼ ተመለስኩ " ከዚያ ሚስዝ ሜሰን
እንደምትፈልገኝ ነገሩኝና እሷ ወደ ነበረችበት ወደ ቤተ መጻሕፍቱ ስገባ ከተከፈተው መስኮት ቁማ አገኘኋት » ብርድ ስለነበር ለምን መስኮት ከፍታ እንደ ቆመች ጠየቅኳት እሷም ቀረብ ብዬ
እንድመለከት ጠራችኝ እኔም ወደ መስኳቱ ጠጋ ብዬ ብመለከት
ብመለከት በሕይወቴ አይቸው የማላውቀው ጉድ አየሁ" በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የሌሊት ወፎች ዳመና መስለው ክንፎቻቸውን እያማቱ መጡብን ወደ ኋላችን ሸሸት ባንል ኖሮ ፊታችንን ይመቱን ነበር " ከየት እንደ ተጠራቀሙ አላውቅም ከአንድ ደቂቃ በፊት ከደጅ ሳለሁ ለምልክት እንኳን አልነበሩም "

እነዚህ የለሊት ወፎች ምን ነካችው ይህን የሚያህል ክምችት ባንድ ላይ ሆነው አይተህ ታውቃለህ ... ዌልስ ? አለችኝ ሚስዝ ሜሰን “ እኔም ኧረ የለም ደግሞ እንደዚህ ከሰው ሲጠጉም አይቸ አላውቅም እንደዚህ ሆነው ባያቸውም ደስ አይለኝም " ገዱ ደግ አይደለም የክፉ ነገር ምልክት ነው አልኳት ለካስ እሷም በምልክቶችና በሕልመች ከሚስቁት አንዷ ሆናለች በሳቅ ልትፈርስ
እርሶዎም እንደሚያውቁት እሷ እመቤት ሳቤላን ከድሮ ጀምራ ስታስተምር የኖረች ናት እነዚህ የተማሩ ሰዎች በምልክት በሕልም በቀላሉ አያምኑም »

ሚስተር ካርላይል አንገቱን ነቀነቀ

« እንዶዚህ በብዛት መምጣታቸው የምን ምልክት ነው ትላለሀ ... ዌልስ አለችኝ ሚስዝ ሚዞን እያሾፈችብኝ „ “ እኔ እንደዚህ ግጥም ብለው በብዛት ሲመጡ
አይቻለሁ አላልኩም ግን የሌሊት ወፎች እንደዚህ በብዛት ሆነው ወደ ቤት ሲገቡ ብዙ ጊዜ መታየታቸውንና ከገቡበት ቤትም ሰው እንደሚሞት የማያብል
የታወቀ ምልክት መሆኑን ሲነገር ሰምቻለሁ ' አልኳት “ ኧረ ሞትስ በዚህ ቤት አይምጣ” እያለች መስኮቱን ዘጋችው የጌቶች ነገር በሐሳቧ መጣባት መስኮቱ እንደ
ተዘጋ እነዚያ አስቀያሚ ፍጡሮች መስኮቱን በክንፋቸው ይጠፈጥፉት ጀመር ከዚያ ሚስዝ ሜሰን ለአንድ ሦስት ደቂቃ ያህል ስለሌላ ጉዳይ ስታነጋግረኝ ቆየችና ስታበቃ ወደ መስኮቱ ዞር ብዬ ብመለከት አንድም የሌሊት ወፍ አልነበረም“

« ደግሞ ካንዱ ቤት መስኮት ክንፎቻቸውን ሊያርገበግቡ ሔደው ይሆናላ» አለ ሚስተር ካርላይል በነግሩ ባለማመን ።
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

....ሚስጥሮቹን ሁሉ ነገረኝ፡ እኔም የእኔን ነገርኩት ብዙም ሳይቆይ ጥልቅ ፍቅር ውስጥ መሆናችን ይፋ ወጣ ስህተትም ቢሆን እንኳን መጋባት እንዳለብን አመንን፡ ከዚያ ወላጆቻችን እንደሚፈልጉት የእነሱ ግልባጭ ሳያደርጉን ከዚህ ቤትና ከወላጆቻችን ሕግ ማምለጥ አለብን ብለን ተነጋገርን፡.

“ታውቃላችሁ፣ ወላጆቼ አላማቸው አባታችሁን እናቱ ከእሷ በእድሜ አጅግ የሚበልጥ ሰው በማግባት ለሰራችው ኃጢአት እንዲከፍል
ሊያደርጉት ሁሉንም ነገር ሰጥተውት ነበር ያንን አምናለሁ: ባጧቸው ሁለት ልጆቻቸ
ምትክ እንደልጅ ነበር የሚቆጥሩት። ወደ ዩኒቨርስቲም አስገቡት: በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበር። ክሪስቶፈር አንተም ጉብዝናህን ከእሱ ነው የወረስከው: በሶስት ዓመት ተመረቀ በሶሰት አመቱ ከዩኒቨርስቲ ቢመረቅም የተመረቀበትን የማስተርስ ዲግሪውን አልተጠቀመበትም ምክንያቱ ደግሞ ዲግሪው ላይ
ያለው ትክክለኛ ስሙ ስለነበረና ማንነታችንን ከአለም ሁሉ መደበቅ ስለነበረብን ነበር። የኮሌጅ ትምህርት ውጤቱን መጠቀም ስላልቻልን በመጀመሪያዎ የጋብቻችን አመታት ነገሮች ከባድ ሆነውብን ነበር።”

መናገሯን ገታ አደረገችና መጀመሪያ ክሪስን ቀጥሎ ደግሞ እኔን ተመለከተች:: መንትዮቹን አቅፋ ጭንቅላታቸው ላይ ሳመቻቸው: ፊቷ በጭንቀት
ተኮማትሮና ቅንድቦቿ ተኮሳትረው ካቲ… ክሪስቶፈር… እንድትረዱኝ
የምጠብቀው እናንተን ነው: መንትዮቹ ገና ልጆች ናቸው: የኛ ነገር እንዴት እንደነበረ ለመረዳት ሞከራችሁ?”

“አዎ፣ አዎ፣” ሁለታችንም ጭንቅላታችንን ነቀነቅን።

እየተናገረች ያለችው የእኔን ቋንቋ ነበር የሙዚቃና የዳንስ ቋንቋ! የፍቅርና የሚያምሩ ቦታዎች ውስጥ ያሉ ቆንጆ ቆንጆ ፊቶች ታሪክ! ለካ ተረትም እውነት ሊሆን ይችላል።

በመጀመሪያ እይታ የተፈጠረ ፍቅር! እኔም የሚያጋጥመኝ እንደዚህ እንደሚሆን አውቃለሁ። ልጁ እንደ አባዬ ልብን የሚነካና የሚያንፀባርቅ ቁንጅና ያለው ይሆናል

“አሁን በደንብ አዳምጡኝ" አለች ቀስ ባለ ድምፅ ለስለስ ማለቷ ለምትናገራቸው ነገሮች ትልቅ ግምት እንድንሰጣቸው አደረገን: “እዚህ የመጣሁት አባቴ እንደገና እንዲወደኝ ለማድረግ የተቻለኝን ለመሞከርና በአባት ብቻ
የሚገናኘውን ወንድሙን በማግባቴ ይቅር እንዲለኝ ለማድረግ ነው አያችሁ፣
ልክ አስራ ስምንተኛ አመት እድሜዬ ላይ ስደርስ አባታችሁና እኔ ኮበለለን ከዚያ ከሁለት ዓመት በኋላ ተመልስን መጥተን ለወላጆቼ ነገርናቸው: አባቴ
እጅግ ተናድዶ በቁጣ አበደ በሸቀ ሁለታችንም ቤቱን ለቀን እንድንወጣ አዘዘ፡ በጭራሽ ተመልሰን እንዳንመጣ ነገረን በጭራሽ! ለዚያ ነው ከውርሱ
እንድሰረዝ የተደረግኩት አባታችሁም ጭምር ከውርስ ውጪ የሆነው አባቴ ለአባታችሁ ትንሽ ውርስ ሊሰጠው እቅድ ነበረው ትልቁ ድርሻ የእኔ ነበር ምክንያቱም እናቴ የራሷ ገንዘብ ነበራት በመጀመሪያ ደረጃም አባቴ ያገባት ከወላጆቿ ገንዘብ ወርሳ ስለነበረ ነው: በዚያ ላይ በልጅነቷ ቆንጆ ባትባልም መልኳ ደህና ነበር በዚያ ላይ ባለስልጣን የሚያስመስላት ቁመና ነበራት።

አይሆንም! ለራሴ በምሬት አሰብኩ. ያቺ አሮጊት አስቀያሚ ሆና ነው የተወለደችው!

“አሁን አባቴ እንደገና እንዲወደኝ ለማድረግ እዚህ መጥቻለሁ። አጎቴን በማግባቴ ይቅር እንዲለኝ አደርጋለሁ: ይህንን ለማድረግ ደግሞ የቅን፣ የትሁትና በደንብ የተቀጣ ልጅን ሚና መጫወት አለብኝ፡ የሚጠበቅብኝን ገፀ
ባህርይ ሚና መጫወት ሳልጀምር በፊት ሙሉ በሙሉ ራሴን በሆንኩበት ሰዓት ልትሰሙት የሚገባችሁን ነገር አሁን ማለት ስለፈለግኩ ነው:ስለዚህ ነው ይህንን ሁሉ የነገርኳችሁና በቻልኩት መጠን ታማኝ ልሆን
የቻልኩት መንፈሰ ጠንካራና በራሴ መቆም የምችል አይደለሁም። ጠንካራ የነበርኩት አባታችሁ ስለሚደግፈኝ ነበር አሁን እሱ የለም። ምድር ቤት አንደኛ ፎቅ ላይ ከትልቁ ቤተ መፃህፍት ባሻገር ባለች ትንሽ ክፍል ውስጥ
ፍቅሩን ያላሳያችሁ ሰው አለ እናቴን አውቃችኋታል፡ በትንሹም ቢሆን ምን እንደምትመስል አይታችኋታል። አባቴን ግን አልተዋወቃችሁትም። እና
ይቅርታ እስኪያደርግልኝና ከትንሽ ወንድሙ አራት ልጆች የመውለዴን ሀቅ እስኪቀበል ድረስ እንድታገኙት አልፈልግም።

“ለእሱ ይህንም መቀበል በጣም ከባድ ነው አሁን ግን አባታችሁ ስለሞተና ሞቶ በተቀበረ ሰው ላይ ቂም መያዝ አስቸጋሪ ስለሆነ፣ ለእኔ ይቅርታ ማድረግ ብዙም የሚያስቸግረው አይመስለኝም:"
ለምን እንደሆነ እንጃ አንድ ፍርሃት ተሰምቶኛል፡

“አባቴ እንደገና ኑዛዜው ውስጥ እንዲያስገባኝ የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ግዴታ ውስጥ ነኝ፡”

“መታዘዝና ክብር ከማሳየት በስተቀር ካንቺ ምን ሊፈልግ ይችላል?” አለ ክሪስቶፈር በትልቅ ሰው የአነጋገር መንገድ።
ሁሉም ነገር ለምን እንደሆነ
የተረዳ ይመስል ነበር፡ እናታችን ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ተመለከተችው እጆቿ ጉንጮቹን እየዳበሱ ደስ በሚል ሀዘኔታ አስተዋለችው: በቅርቡ የቀበረችው
ባሏ ትንሹ ምስል ነው ስለዚህ አይኖቿ በእምባ ቢሞሉ አይገርምም

“ምን እንደሚፈልግ አላውቅም: ነገር ግን ምንም እንድስራ ቢፈልግ ያንን አደርጋለሁ። እንደምንም ኑዛዜው ውስጥ ሊያስገባኝ ግድ ነው ለአሁኑ እንርሳው: እያወራሁ ሳለ ፊታችሁን እየተመለከትኡ ነበር።እስቲ የተናገረችው ሁሉ እውነት እንደሆነ እንዳይሰማችሁ። አባታችሁና እኔ ያደረግነው ነገር ከስነምግባር ያፈነገጠ ነገር አልነበረም: የሚፋቀሩ ጥንዶች
እንደሚያደርጉት በቤተክርስቲያን ነው የተጋባነው: ምንም ያልተቀደሰ የሚባል ነገር የለውም፡ እናንተም ከሰይጣን የተፈለፈላችሁ ወይም ክፉ አይደላችሁም ይህ አባታችሁ እንደሚለው የማይረባ ንግግር ነው። እናቴ እኔንና እናንተን የመቅጫ ሌላው መንገዷ ራሳችሁን የማይረባ አድርጋች
እንድታስቡ ማድረግ ነው:

“የህብረተሰቡን ህጎች የሚሰሩት ሰዎች እንጂ እግዚአብሔር አይደለ በሌሎች የአለማችን ክፍሎች የቅርብ ዝምድና ያላቸው ስዎች ተጋብተው ልጆች ይወልዳሉ: ይህም እንደ ትክክል ይቆጠራል፡ ለማህበረሰቡ
መገዛት ያስፈልገን ስለነበር፣ ያደረግነው ነገር ትክክል መሆኑን ለማሳት እየሞከርኩ አይደለም፡ ይህ ማህበረሰብ የቅርብ ዝምድና ያላቸው ወንድና ሴት ጋብቻ መፈፀም አይገባቸውም፣ ከተጋቡ የሚወልዷቸው ልጆች በአእምሮ
ሆነ በአካል እንከን ያለባቸው ይሆናሉ ብሎ ያምናል። ግን ማነው ፍፁም?

ከዚያ ሁላችንንም አቅፋ እየሳቀች በግማሽ ደግሞ እያለቀሰች ነበር። “አያታችሁ ልጆቻችን ቀንድ ኖሯቸው፣ ጀርባቸው ጎብጦ፣ መንታ ጭራ ኖሯቸው እግራቸው ላይ ሸኮና ኖሮ እንደሚወለዱ ይተነበይ ነበር እንደ እብድ ሊረግመን እየሞከረ ነበር። የተረገምን እንድንሆንና ልጆቻችን ትክክለኛ ቅርፅ ያላቸው እንዳይሆኑ ይፈልግ ነበር ግን የተነበያቸው ነገሮች ሁሉ እውነት ሆኑ? ራሷም በከፊል እብድ የሆነች ትመስል ነበር። “በጭራሽ!” የራሷን ጥያቄ
መለሰች። ለመጀመሪያ ጊዜ ልወልድ ስል አባታችሁና እኔ ትንሽ ተጨንቀን ነበር፡ ሌሊቱን ሙሉ እስኪነጋ ድረስ በሆስፒታሉ ኮሪደሮች ላይ ሲንጎራደድ
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


የደማውን እጇን በውሃ አጣጥባ በፎጣ አድርቃ በፋሻ አሰረችው:፡
ለምንድነው የፈራሁት? ስትል ራሷን ጠየቀች አይገድለኝ፤ ሊከለክለኝም
አይችልም፤ እድሜዬ ከ21 አመት በላይ ነው! ይህም አገር ነፃ አገር ነው! በማለት ራሷን ለማሳመን ሞከረች፡፡

ይህም ሆኖ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም፡

ጠረጴዛው ላይ የገበታ እቃዎች ደረደረችና ሰላጣ አጠበች፡፡ መርቪን ስራ ወዳድ ቢሆንም እቤቱ የሚመጣው በሰዓቱ ነው፡፡ በሙያው ኢንጂነር ሲሆን ከአይሮፕላን ሞተር መዘውሮች ጀምሮ እስከ ማቀዝቀዣ ሲስተሞችና የመርከብ መፍቻዎች ድረስ ያሉትን ዕቃዎች የሚያመርት ፋብሪካ ባለቤትና ጥሩ የቢዝነስ ሰው ነው፡፡ መርቪን የአይሮፕላን ሞተሮች መስራት ከጀመረ
ጀምሮ ነው ገንዘብ በሻንጣ መቁጠር የጀመረው፡፡ የመዝናኛ አይሮፕላን ማብረር የጊዜ ማሳለፊያው ሲሆን ለዚህም ሲል ትንሽ አይሮፕላን ገዝቷል።
መንግስት አየር ኃይል ሲያቋቁም የአይሮፕላን ሞተር መስራት ከሚችሉት ጥቂት ሰዎች ውስጥ መርቪን አንዱ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህማ መርቪን ያለ
እረፍት ይሰራል፡፡

ዳያና ሁለተኛ ሚስቱ ስትሆን የመጀመሪያ ሚስቱ ሁለቱን ልጆቹን ይዛ ሌላ ሰው አግብታ ከሄደች ሰባት ዓመት ሆኗታል፡ መርቪንም ፊርማውን ቶሎ ቀደደና ዳያናን ላግባሽ ብሎ ጠየቃት፡፡ መርቪን ፈርጠም ያለና ኪሱ ረብጣ ገንዘብ ያለው ከመሆኑም በላይ ዳያናን ከማፍቀርም አልፎ ያመልካት
ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የጋብቻ ስጦታ ብሎ ያበረከተላት የአልማዝ ሀብል ነበር፡፡

የአምስት ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን ሲያከብሩ ግን ስጦታ ብሎ
ያበረከተላት የልብስ ስፌት መኪና ነው፡፡ የስፌት መኪናውን ሲሰጣት ትዳሯ እንዳበቃለት ተገነዘበች፡፡ መኪና መንዳት ስለምትችል የራሷ መኪና እንዲኖራት ትመኝ ነበር፤ መርቪን ደግሞ የመግዛት አቅም አለው፡፡ አምስት ዓመት ሙሉ አብረው ሲኖሩ ልብስ ሰፍታ እንደማታውቅ እንኳን
አልተገነዘበም፡፡

ባሏ እንደሚወዳት ብታውቅም እሱ ግን ከሚስትነቷ ውጭ ትኩረት
አይሰጣትም፡፡ እቤት ውስጥ ሚስት የምትባል ሴት እንዳለች፣ ቆንጆ
እንደሆነች፣ በሴትነቷ የሚጠበቅባትን ማህበራዊ ህይወት የማታጓድል፣ምግቡን ሰራርታ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ የምትጠብቅ፣ አልጋም ላይ ፈቃደኛ
የሆነች ሴት አለችው ታዲያ ሚስት ከዚህ በላይ ምን ይጠበቅባታል በእሱ አስተሳሰብ፡፡ ስለምንም ነገር አማክሯት አያውቅም እሷ የቢዝነስ ሰው ወይም ኢንጂነር ባለመሆኗ በሱ ቤት አንጎል የላትም፡፡ ከሷ ይልቅ ፋብሪካው ውስጥ ካሉት ሰዎች ጋር ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦችን ይለዋወጣል፡ በሱ አመለካከት መኪና ለወንዶች፣ የስፌት መኪና ደግሞ ለሴቶች ነው፡፡

መርቪን ከልጅነቱም ጮሌ ነበር፡ አባቱ የማሽን ኦፕሬተር ነበሩ¨
መርቪን በማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ፊዚክስ ያጠና ሲሆን ለማስተርስ ዲግሪው እንዲያጠና በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ዕድል ቢያገኝም እሱ ግን የትምህርት ሳይሆን የተግባር ሰው በመሆኑ በአንድ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ውስጥ የዲዛይን መምሪያ ውስጥ ተቀጠረ፡፡ በዓለም ላይ በፊዚክስ መስክ የሚደረጉትን
ግስጋሴዎች የሚከታተል ሲሆን ከአባቱ ጋርም ስለነዚህ ነገሮች ይወያይ ነበር፡ ከዳያና ጋር ግን እንደዚህ አይነት ነገር መነጋገር ሲያልፍም አይነካካውም::

እንደ ዕድል ሆኖ ዳያና ፊዚክስ ባለበት ድርሽ ብላ አታውቅም፡፡
አይገባትም፡፡ እሷን የሚጥማት ሙዚቃ፣ ስነጽሑፍ ከፍ ካለም ታሪክ ብቻ ነው:፡ መርቪን ደግሞ ከፊልምና ከዳንስ በስተቀር ሌላው አይጥመውም፡፡ስለዚህ እነሱን የሚያነጋግር ነገር የለም ማለት ነው:

ልጅ ቢኖራቸው ኖሮ ነገሮች ይለዋወጡ ነበር፡፡ መርቪን ከመጀመሪያ ሚስቱ ሁለት ልጅ ስለወለደ ሌላ ልጅ አይፈልግም፡፡ ዕድሉን ቢሰጣት ልጆቹን ማቅረብ ትፈልግ ነበር፤ በየት በኩል? የልጆቹ እናት ከአባታቸው ጋር የነበራት ጋብቻ ያፈረሰው በዳያና ምክንያት መሆኑን በመናገር የልጆቹን
አዕምሮ ስለመረዘች ደመኛ አድርገዋታል፡፡ ታዲያ የእናትነት ፍላጎቷን የምትወጣው ሊቨርፑል ውስጥ በምትኖረው እህቷ መንታ ልጆች ነው፡፡

ክፋቱ አሜሪካ ከሄደች ልጆቹ እንደሚናፍቋት ጥርጥር የለውም፡፡

መርቪን ከከተማው ነጋዴዎችና ባለስልጣናት ጋር ስለመሰረተ በፊት በፊት እቤት በጋበዛቸው ቁጥር እነሱን ማስተናገድ
ያስደስታታል፡ ለጥሩ ልብስ ያላት ፍቅር ከፍተኛ ሲሆን ልብስም
ያምርባታል፡ ነገር ግን ህይወት ማለት ከመልበስም በላይ መሆኑን
ትረዳለች፡

የሚያውቋት ሴቶች መጠጥ የማያበዛ፣ ታማኝ፣ ደግ ባልና ጥሩ
መኖሪያ ቤት ስላላት ዕድለኛ ናት ብለው ያምናሉ፡ ሆኖም እሷ ደስተኛ
አይደለችም፡፡ የማታ የማታ ግን ማርክ የተዘጋ ልቧን ከፈተው፡፡
የመርቪን መኪና ግቢ ሲገባ ሰማች፡፡ የመኪናው ድምጽ የለመደችው ቢሆንም ዛሬ ግን የአውሬ ድምጽ መሰላት፡፡

መጥበሻውን ምድጃው ላይ ስትጥድ እጇ ተንቀጠቀጠ፡፡ መርቪን ወደ ማድ ቤት ገባ፡ ባሏ ነፍስ የሚያስት ቁመና ያለው ሲሆን በጥቁር ፀጉሩ ላይ ጣል ጣል ያደረገበት ሽበቱ የተለየ ግርማ ሞገስ ሰጥቶታል፡፡ ቁመቱ ሎጋ
ሲሆን እንደ ጓደኞቹ ቀፈታም አይደለም፡፡ ኩራተኛም ባይሆን ዳያና በጥሩ ልብስ ሰፊ የተሰፋ ሱፍ ልብስና ውድ ሸሚዞች እንዲለብስ አድርጋዋለች፡፡

ዳያና መጨነቋን ከፊቷ ላይ አንብቦ ምንድን ነው ነገሩ ብሎ
ይጠይቀኛል ብላ ሰግታለች።

መጥቶ ከንፈሯን ሲስማት ሀፍረቷን ውጣ እሷም ሳመችው፡፡ አንዳንድ
ጊዜ እቅፍ አድርጎ በእጁ የቂጧን ፍንካች ሲደባብስ ይሟሟቁና ወደ መኝታ ቤት ሲሮጡ ምድጃው ላይ ያለው ምግብ አርሮ ይጠብቃቸዋል አሁን አሁን ግን እንዲህ አይነት ነገር እምብዛም አያደርጉም፡፡ ዛሬም ከወትሮው የተለየ አይደለም፡፡ እንደ ነገሩ ሳም አደረጋትና ዞር አለ፡፡
ኮቱን፣ ሰደርያውንና ክራቫቱን አውልቆ የሸሚዙን እጀታ ጠቀለለና ፊት መታጠቢያው ላይ ፊቱንና እጁን ታጠበ፡፡ የትከሻው መስፋትና የክንዱ መፈርጠም ለጉድ ነው፡
አሁን አልነግረውም አለች በልቧ፡
ጋዜጣ እያነበበ ስለሆነ ከቁብም አልቆጠራት፡፡

ድንቹ ምድጃው ላይ ሲንጨረጨር ሻይ ጥዳ ዳቦውን ማርጋሪን ቀባች:
የእጇን መንቀጥቀጥ ባሏ እንዳያውቅባት ለመደበቅ እየሞከረች ነው መርቪን
‹‹ስራ ቦታ ውስጥ አንድ በጥባጭ ሲበጠብጠኝ ዋለ›› አላት ሰሃኑን ፊቱ ስታስቀምጥ።

‹እኔ ምን ቸገረኝ ታዲያ አለች በሆዷ እኔ እንደሆነ ከዚህ በኋላ
በቅተኸኛል፡፡› ለምን ሻይህን አፈላውልህ?›

‹‹ደሞዝ እንድጨምርለት ጠየቀኝ፣ እኔ ደግሞ ለመጨመር ዝግጁ
አይደለሁም›› አላት፡፡

ዳያና ፍርሃቷን ዋጥ አድርጋ ‹‹አንድ የምነግርህ ነገር አለ›› አለች:
የተናገረችውን ነገር መልሳ ብትውጥ ወደደች፤ ግን አንዴ አምልጧታል፡

‹‹ጣትሽ ምን ሆነ?›› ሲል ጠየቃት በፋሻ የታሰረውን ጣቷን አይቶ፡

ይህ ጥያቄ ትንሽ ከጭንቀቷ መለስ አደረጋት ‹‹ምንም›› አለች ወንበሩ
ላይ ዘፍ እያለች ‹‹ድንች ስቆርጥ ቢላ ቆረጠኝ›› ብላ ሹካና ማንኪያዋን አነሳች፡:

መርቪን ምግቡን ስልቅጥ አድርጎ በላና ‹‹ከዚህ በኋላ ሰው ስቀጥር
መጠንቀቅ አለብኝ: ችግሩ ጥሩ ባለሙያዎችን ማግኘት በአሁን ጊዜ
አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ ነው፡››

ስለ ስራው ሲናገር አስተያየት እንድትሰጥ አትጠበቅም፡፡ ሀሳብ የሰጠች እንደሆን ይገላምጣታል፡፡ እሷ እንደሆን ለእሱ ለማዳመጥ ብቻ የተፈጠረች ፍጡር ናት፡፡
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

ከሎ ሆራ ልቡን የሰረቀችውን የሐመር ውብ ለማግኘት ብዙ መድከሙ
አልቀረም።ካርለትም ብትሆን የሐሳቡን መናወጥ
ስላጤነችና ለጥናቷም እገዛ ይኖረዋል ከሚል እምነት በመነሣት ያችን ውብ ኮረዳ ማፈላለጉ ላይ አልሰነፈችም ሻንቆና ላላ መንደር
አለመኖሯን ግን ሁለቱም በየፊናቸው አረጋግጠዋል።

እንደ ተለመደው ከሎ ሆራና ካረለት በየመንደሩ በመዞር
ለማጠናከር ሲንቀሳቀሱ፣ ከዲመካ ከተማ ወደ አምስት ኪሎ ሜትር
እራቅ ብላ ከምትገኘው ኮረብታማ መንደር ወሮ ሄዱ"ከዚያ እንደ ደረሱ ወንዶች ወደ ወንዝ፣ ሴቶችም እርሻና ማሳ ጥበቃ ሄደው ስለነበር፣ መንደሯ ውስጥ ያገኙት የሚያላዝኑ ውሾችንና አሮጊቶች
ብቻ ነበር። መሸትሸት ሲል ግን ከብትና ኗሪው ከየውሎው ወደ
መንደሯ መጠረቃቀም ጀመረ።

ይህ ትዕይንት ለካርለት እንግዳ አልነበረምና ከመንደሯ ወጣ ብለው የአካባቢውን ውበት ሲቃኙ፣ ከሎ ደንገጥ ብሎ ዓይኑን ወደ አንድ አቀጣጫ ደገነ" አንዲት ልጃገረድ ስታርስበት የዋለችበትን ሞፈርና ቀንበር ከበሬዎች ጫንቃ ስታላቅቅ፣ ከበስተኋላ ተመለከቱ"።
እግርቿ ግጥም፣ ዳሌዎ ኮራ ከወገቧ ሰርጎድ ያለችውን ኮረዳ ሁለቱም ከበስተኋላዋ በማየት ብቻ ማንነቷን አወቁ" ልጅቷ በሬዎቹን
ፈትታ ዘወር ስትል፣ ሁለቱም ዓይናቸው እሷ ላይ ነው" ኮረዳዋ አንዳችም የመደነጋገር ሁኔታ ሳታሳይ ፈገግ ብላ በዚያ ኰራ ባለው አረማመዷ ወደነሱ ሄደች"።

ከሎ ምራቁን ቶሎ ቶሎ ከማንጐራጐጭ በስተቀር የሚመለከተው ልጅቷን ነው" ካርለት ደግሞ በተመስጦ የምትከታተለው እሱን ነው"

በልጅነቷ ወንድና ሴት ተቃቅፈው አልጋ ላይ ሲተኙ የሚያደርጉትን ለማወቅና ብዙ ጊዜ ለማየት ትጓጓ ነበር" ነፍስ ካወቀች
ጊዜ ጀምሮ የምትተኛው በግል መኝታ ቤቷ ሲሆን፣ አንድ ቀን ታዲያ የናቷ ጓደኛና ባሏ በእንግድነት እቤታቸው ይመጣሉ" እንዳጋጣሚ ሆኖ ለእንግዳ የተዘጋጀው የመኝታ ከፍል ተይዞ ስለነበር እንግዶች
ካርለት መኝታ ክፍል እንዲያድሩ ተደረጉ፣ እሷ ከወላጆቿ መኝታ ቤት ካለው ትንሽ ክፍል እንድትተኛ ይደረጋል" ካርለት ግን
እንቅልፍ ከመተኛት ይልቅ አንድ ለብዙ ጊዜ ለማወቅ ትጓጓ የነበረውን ሁኔታ ለመፈጸም አሰበች" እናም፣ የቆየ የልጅነት ፍላጎቷን ለማሟላት እንግዶች እሷ ከምትተኛበት ክፍል ገብተው ከመተኛታቸው በፊት አልጋው ሥር ገብታ ተደበቀች" ባልና ሚስቱ
በመጠጥ ኃይል ሞቅ ብሏቸው ነበርና እየተሣሣቁ ተደጋግፈው ገብተው አልጋ ላይ እንደ ወጡ ተያያዙ"

ካርለት የአልጋ ላይ ጨዋታቸውን ሁሉ ልቅም አድርጋ ሰማች"ከዚያ በኋላ ሰዎቹ ሲተኙ፣ ወላጅ እናቷ ካርለት ከተኛችበት ከፍል
ልታያት ስትገባ ድንግጥ አለች ቀስ አድርጋ እጇን ልጇ አልጋ ላይ ስትጭን ጨርቅ ብቻ ሆነባት በድንጋጤ ጮኸች። አባት፣ እንግዶች
ሳይቀሩ እየተሯሯጡ ሲመጡ የለችም ቤቱ ቢታሰስ፣ ብትፈለግ
በቀላሉ ልትገኝ አልቻለችም" በጨረሻ ግን አልጋ ስር እንደ ውሻ ተጠቅልላ ተገኘች" እና ዛሬም እንደ የዛኔው እንዲታወቅባት
ስላልፈለገች የኮረዳዋንና የከሎን ሁኔታ በጥንቃቄ መከታተል ቀጠለች።

ከሎና ካርለት ከልጅቱ ጋር ፊትና ኋላ ወደ መንደሩ እንደ ደረሱ፣ከልጅቷ መኖሪያ ቤት ትይዩ ድንኳን ለመትከል እንደ ፈለገች ለከሎ
ሆራ ሆነ ብላ አማከረችው «ኢህ» ብሎ ፈቃደኛነቱን ገለጸላት ለነገሩማ እንሂድ ብትለውስ መቼ በጄ ይል ነበር።

ከሎ፣ ስለ ብዙ ነገር እንዳላወጣ እንዳላወረደ አሁን የሚፈልገውና የሚያየው ውብ ልጅ ነው  የሐመሯን ኮረዳ" አጠገቧ
ካለው ድንኳን ውስጥ ሆኖ እሩቅ ያለች ይመስል አለማት" ከሎ ሴት
አያውቅም ለማለት አይቻልም" በተለይ በገንዘብ የሚገኘውን የስሜት እርካታ በሚገባ ያውቀዋል" የሴት ጓደኛም ለመያዝ ብዙ
ሞካሮ ነበር" ግን፣ ከሙሉ ስሜቱ እንዲህ እንደ አሁኑ ነፍሱ ምንጥቅ እስክትል ወዶ አያውቅም"

ልጃገረዷ ደግሞ በሕይወቷ እንደ ወንድ ጓደኛ ግንኙነት
የጠገበችው የለም። ከሚጠይቋት ወንዶች ውስጥ ከመረጠቻቸው ጋር
ብቻ ተዝናንታለችI ዕድሜ ለሐመር ደንና ጫካ።

እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ልጃገረዷ ወላጆቿን በሥራ በመርዳት ስታገለግል ቆይታ ለምሽት ጭፈራው መሰናዳት ጀመረች"የጐረምሶችን ጩኸት እንደ ሰማች ከጓደኞቿ ጋር ለመደነስ ስትሄድ፣እነ ከሎ ተመለከቷት" አባቷ እንዳያገኛት ተጠንቅቃ አለፈች።

ልጃገረድ በኢቫንጋዲ (የምሽት ጭፈራ) መካፈሏን ባህሉ የሚፈቅድ ቢሆንም ወደ ጭፈራ ቦታ ስትሄድ ግን አባትየው ሳያይ
ሲሆን፣ ከጐረምሳ ጋር ስትዳራ ካገኘም አባት ተኵሶ ጐረምሳውን
እስከመግደል ድረስ መብት አለው" ይህ መብት እንጂ ያደርጋል ማለት ግን አይደለም። ስለዚህ፣ ለደንቡ ያህል ጭፈራውም ሆነ
ድሪያው አባት በማያየው መንግድ እንዲሆን ልጃገረዶች የራሳቸውን
ጥናቃቄ ይወስዳሉ"
በአጋጣሚ ግን እሷ ባህሉ ያደገችበት ሆነና ብትጠነቀቅም፣ አባቷ
ግን ከሌሎች የሐመር ወንዶች ለየት ያለ ነው።
በኢቫንጋዲ ጭፈራ ልጃገረዷ ኮከብ ደናሽ ስትሆን፣ የክልሉ ጎረምሶች
በፍቅር ሲያጫውቷትና ወደ ጫካ ሄድ መለስ ስትል ከሎን ግን ለዳንስ ሳትጋብዘው ቀረች። ወደ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የወንዶች ድምፅ ተሰማ። በመንገድ ላይ የሚያልፉ
ገበያተኞች እግረ መንገዳቸውን ለጭፈራ ሲመጡ የተለመደ ነበርና
ጨዋታው ቀጠለ። ካርለት አሁንም ክትትሏን እንደ ቀጠለች ነው" ጭፈራው ደመቀ፣ ውዝዋዚው ጦፈ፣ ከዚያ የመጨረሻው የዳንስ
ስልት ጊዜ እነ ካርለት የሚከታተሏት ኮረዳ ከአንድ መልከ መልካም ሸበላ ጋር መርፌና ክር ሆኑ ካርለት ያ ሰው ማን እንደሆነ ለመገመት ጊዜ አልፈጀባትም። መጀመሪያ እዳልነበረ እርግጠኛ ነች። ከገበያ ከተመለሱ መንገደኞች ጋር እንደ መጣ አወቀች" ደልቲና ኮረዳዋ
ወደ ጫካው ሲሠወሩ፣ ከሎና ካርለት ተፋጠጡ።

ውቢቷ ልጃገረድ ጎይቲ አንተነህ ትባላለች። በሐመርኛ ጎይቲ ማለት መንገድ ሲሆን፣ የስሟ ትርጓሜ ከመንገደኛ የተወለደች ለማለት ነው" ካርለትና ከሎ የሐመርኛ ቋንቋ አቀላጥፎ የሚናገ
ረውንና በአኗኗሩም ሆነ በአለባበሱ ሐመር የሆነው የጎይቲ ወላጅ አባት ጠዋት ከከብቶች በረት ሲመለስ፣ እንግዶች ከቤቱ ፊት ለፊት
ድንኳን ተክለው አየ አንተነህ (ጋልታምቤ) እንግዶቹን አንዳየ በጨዋ መልክ ሰላምታ ከሰጠ በኋላ፣ ጨዋታ ቢጤ ጀማመሩ።
የመጡበትን ጉዳይና ማንነታቸውን ከገለጸለት በኋላ፣ «ሸፈሮ ቡና
እንጠጣ» ብሎ፣ ወደ ቤቱ ይዟቸው ገባ።

ቡናውን ያፈላችውና የምትቀዳው ውቧ ልጃገረድ ጎይቲ አንተነህ ከአባቷ ፊት በጣም ጨዋና ረጋ ያለች ናት ካርለትና ከሎ በጣም
ጠባብ ወደ ሆነው የጎጆው በር በየተራ ገብተው ከተነጠፈው ቁርበት
ላይ እንደ ተቀመጡ፣ ጎይቲ በሾርቃ ሞልታ ሸፈሮ ቡናውን ለካርለት
አቀበለቻት ቀጥላ ለከሎ ስትሰጠው በአጋጣሚ እሷን እሷን እያየ ነበር እሷ ደግሞ ሾርቃውን የያዘ መስሏት ስትለቅለት ከመሬት
ወርዶ ተሰበረ። ሁለቱም በጣም ደነገጡ" ካርለት ድንገተኛ ሣቅ አፈናት፤ የልጃገረዷ አባትና ሌሎች ሁለቱ ሐመሮች ግን ጸጥ ብለው ሁኔታውን አረጋጉ።

ቡናው የውኃ ጥምን ስለሚከላከል ማንኛውም ሐመር በየመንደሩ
ቡና በእንስራ ተጥዶ፣ ሁለትና ከሁለት በላይ ሾርቃ ሳይጠጣ ከመንደሩ የሚርቅ የለም" አንተነህ ይመር ጎይቲ (ሴት ልጁ) ቡናውን
አጠጥታ ስትጨርስ፣ «ረሃብ፣ ችግር ከሐመር ምድር ይራቅ ከብቶች ይጥገቡ፤ ንቦች አበባ ይቅሰሙ፤ ሰማዩ ውኃ ያውረድ ፍቅር ሰላም ለሐመር ሕዝብ ቦርጆ ያውርድ አንቺም ተባረኪ የተባረh ባልና ትዳር ይስጥሽ፤ ሁላችሁም ተባረኩ» ብሎ ሸፈሮ ቡናውን ወደ አራቱም አቅጣጫና ወደ ጎይቲ፣ «ፕስስ...» አለና አማተበ።
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ


ጆሮዎቹ ላይ ሉቲ አንጠልጥሏል ጥቁር ቆዳው ላይ አልፎ
አልፎ ቡግር መሣይ ነጠብጣቦች ይታያሉ: አገጩ ጠበብ ብሎ
ቁጥርጥር ያሉት ፂሙ ፀጉሮቹ አልፎ አልፎ ጉች ጉች ብለዋል።

አይኖቹ ቦዘዝ ብለው የጭካኔ የእንቢተኝነት... እይታ ይታይባቸዋል። ሶራ የኮንችትን አያት ፎቶ ግራፍ ሲመለከት ቆይቶ ሲጋራውን አቀጣጥሎ ወደ መቀመጫው ተመለሰ።

ኮንችት ከወደ ውስጥ በሩን ከፍታ ብቅ ስትል ቤቱ በምግብ ሽታ ታፈነ። ከዚያ የተጣጠፉ የጠረዼዛ ልብሶችን እያነጣጠፈች
ሰሃን ማንኪያ ሹካ እየደረደረች።

“ወንድ አያቴ ሴት አያቴን በፍቅር ልቧን ጠምዝዞ የጣላት እንዴት እንደሆነ ልንገርህ" አለችው ሙሉ ለሙሉ በፈገግታ ወደ
እሱ ዞራ።

የጡቶችዋ ጎንና ጎኖች ታዩት፡ ጫፋቸው ደግሞ ጋዋኗን ወጠር አድርጎት ተመለከተ። ሰርጓዳ እምብርቷን አይቶ ዝቅ ሲል
ደግሞ ነጭ ፓንቷን አየ የታባክ ተመለስ እንደተባለ ሁሉ እንደመርበትበት ብሎ

“ምን አልሽኝ?" አላት:

“ሴት አያቴ በወንዱ አያቴ ፍቅር እንዴት እንደወደቀች
ልንገርህ"

“እሽ በምናቸው ነው?''

በዝምታው ነው” አለችው።

“ዝምታው!” ተደንቆ አያት:

አዎ!

ዝምታው” አለችውና ቀኝ እግሯን አንዱ ወንበር
ላይ አስቀምጣ ሙሉ ለሙሉ ለስላሳ ጭኗን እያሳየችው ስታየው፡-

“አልገባኝም” አላት ግራ ትከሻውን ሰብቆ። እሷም ጠረጴዛው ላይ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ማዘጋጀቷን እያረጋገጠች፡-

“አዝናለሁ! እይታ እንጂ ማብራሪያ ሊገልፀው አይችልም:: ዝምታ ግን የሴት አያቴን የፍቅር ልብ ማሸነፉ እውነት ነው"
ብላው ወደ ጓዳ ገባች::

ሶራ ምክንያቷን ለመስማት ጆሮዎቹን እንዳቆመ ጠበቃት።የበሰሉና  የቆርቆሮ ምግቦችን እየደረደረች በመካከሉ ቀና ብላ አይታው፡-

“እዚህ ገባ ስትል መታጠቢያና መፀዳጃ ታገኛለህ። በኔ በኩል
አስፈላጊውን ሁሉ እዘጋጅቼ የጨረስሁ ይመስለኛል" ብላ አንድ የቲማቲም ቁራጭ በሹካዋ አንስታ ዋጠች።

ሶራ ወደ ጠቆመችው ክፍል ገብቶ ተጣጥቦ ወጣ፡

የስፔን ባህላዊ ምግብ ጃፓሾ ፒላ... ክሪም በእንቁላል ከወይን ጋር ጠረዼዛው ላይ ተደርድሯል።

“ቦና ፔቲ" አለችው ኮንችት እንብላ ለማለት በፈረንሳይኛ።

"ሳቅ ብሎ “ሜርሲ” አላት: ፈረንሳይኛ, እንግሊዘኛ መቻሏ አስተሳሰቧ በአመለካከቷ አድማስ መጨመር የሚኖረው ጠቀሜታ ታየው:: የአስተሳሰብ ብስለት ከሚያመጡ ምክንያቶች አንዱ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ መሆንና ሌላውን ለማንበብ መቻል እንደሆነ ያውቃል።

ይህን እያሰበ የሚፈልገውን ከአነሳ በኋላ አንገቱን አቀርቅሮ ሲበላ ቆየና ቀና ሲል እሷ ሰሃን ላይ ምንም ምግብ የለም።

“አትበይም?'' አላት ወደ ምግቡ በቢላዋው እየጠቆመ፡

አይኖችቿን በልጠጥ አድርጋ አመሠግናለሁ: ደስ ሲለኝ ብዙ አልበላም" አለችው።

“ለቅርፅሽ እንዳይሆን ፈገግ ብሉ ጠቃት:

“ለዚያ ቢሆን ከልቤ ነው የምጨነቀው:"

“ለምን?”

“ቅጥነት ውበት መሆኑን ገና በመዋለ ህናት እያለሁ
ስለማውቅ" ፈገግ አለች
ጭኖቹ ላይ ያስቀመጠውን “ናፕኪን' አንስቶ አፉን እያበሰ፤

“አዎ! ሴት ልጅ ቀጠን ስትል ውበቷ ይፈካል" ሲል
አቋረጠችውና፡-

“ወንድም ቢሆን ዘርጠጥ ከሚል ከወደ ሆዱ ሰብሰብ ሲልና ትከሻው ሲሰፋ ለሴት ልጅ የደረት ላይ ዋና አመች ይሆናል" ብላ ፈገግ ስትል ሶራ ደነገጠ። ከደረቱ ይልቅ ሆዱ አብጧል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆን
ኖር እንዴት አማረብህ?”
የሚያሰኘው ውፍረቱ ያኔ አሳፈረው፡

ሆዱ ወደ ውስጥ ሊሸልገው ሞከረ:: ህሊናው ግን “ዘገየህ”ብሎ አሾፈበት: ቅርዑን ጠላው።

መብላቱንም አቆመ።

“ምነው?” አለችው ኮንችት በመገረም እያየችው።

ምኑ?" አላት ስሜቱን ለመደበቅ እየጣረ።

“ሀሳብ የያዘህ ትመስላለህ?"

ደህና ነኝ" አለና ዘና ብሎ ቁጭ አለ።

ኮንችት ከተቀመጠችበት ተነስታ ሶፋው ላይ እግሮችዋን አጣጥፋ ቁጭ ስትል ተነስቶ ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ገባ።

ውሃውን ከፍቶ ጎረድ  ያለ  አፍንጫውን ቦግ ቦግ ያሉ
አይኖቹንን ጠይም ፊቱን ተመልክቶ ጎንበስ ብሎ ሆዱን አየው:በሁለት እጁ ሆዱን ከፍሉ የተከመረውን ትርፍ በጥላቻ ተመልከቶ
"ቆርጦ መጣል ነበር ብሎ ተመኘና ፊቱን በውሃ አበስ አበስ አድርጎ ወጣ።

“ሆዴን እንዴት ጠላሁት መሰለሽ አላት ወደ መቀመጫው እየሄደ።

“ዘገየህ” አለችው ዘና ብላ፡

“ለምኑ? አላት ፈገግ ብሎ።

“ግልፅነት ይጎድልሃል አንደ የሚያስጨንቅህ ነገር
እንደነበር ስለተረዳሁ ስጠይቅህ ደበቅኸኝ፡ አሁን ግን ሳልጠይቅህ
ነገርኸኝ... ደካማነት ነው" አለችውና፡-

“ሆድህን ግን ለምን ጠላኸው?''

“...ለዋና ስለማይመች" አላት።

“ባለህ እንኳ የምትኮራ መሆን አለብህ። ለውበትና ለጤንነት መስተካከል ሽንቃጣነት ምርጫህ ካልሆነ ለሴት ብለህ አካላዊ ለውጥ መፈለግ የለብህም: ሴት ልጅ በባህር ውስጥ ጠልቃ የፍቅር ሉል

ማውጣት በአስተሳሰብ በስለት ወይንም በሌሎች የራሷ ምክንያት
የምትፈልገውን ለመምረጥ እምትቸግር አይደለችም ግን አንድ ነገር አትጣ” ስትለው

“ምን?” አላት ፈጠን ብሎ።

"ለሴት ልጅ ቅርፅ ብቻ ወሳኝ አይደለም፡ ህሊናዊ ይዘትንም የመፈተሽ ተፈጥሮአዊ ፀጋ አላት። ብቻ የሚፈቀር ነገር አትጣ።
ይዘቱም ቅርፁም ባዶ ከሆነባት እንደ ሎጥ ሚስት ገትራህ ፊቷን ሳታዞር ትሄዳለች አለችና ራሷን ሶፋው ላይ አስተኝታ ሳቀች::
ክሊሊሊ..ሊ እያለ የሚያስተጋባው ሳቋ በውስጡ አንዳች ስሜት
ፈጠረበት:: ሳቋ የተለመደ አይነት አይደለም። ግን የሚያውቀው
እንዲያውም ሲያዳምጣቸው ስሜቱን ከሚያዝናኑት ሙዚቃዎች እንደ አንዱ ቆጠረው:

“እኔ እንደምገምተው" ብላ እግሮችዋን ፈርከክ አድርጋ
የእግሮችዋን ጣቶች በእጆችዋ ጣቶች እየደባበሰች ሳለች ነጩን ፓንት እንደገና አየው።

“በአዳምና ሔዋን ዘመን ፍቅርን የጀመረችና የሰጠች ሔዋን ናት: አዳም በእግዚአብሔር ስም ዳቦዋን ቆረሰው፤እና አብረው ተካፍለው በሉት፤ አጣጣሙት:: ከዚያን ጊዜ ወዲሆ ሴት ልጅ
በወንድ አካል ጠልቃ የፍቅር ሉል ለማውጣት የምትፈልገው አንድ
ነገር ብቻ ነው” አለችው።

“ምን?” ሲላት ኮንችት ፈገግ ብላ፦

ጊዜ አነስተኛ ጊዜ" አለችው።

“እንዳባባልሽ እንግዲህ ፍቅርን የፈጠረች ሴት ናት ማለት ነው ሲል።

“የፈጠረች የሚለውን የጀመረች ካልነው እውነተኛው  መላምት ይህ ይመስለኛል" አለችው

"ወንዶችስ?”

ወንዶችማ ሲበዛ ስሜታዊ ናችሁ: ወደ ስር ለመጥለቅና የፍቅር ሉል ለማግኘት የዋና ስልት የላችሁም:: ላይ ለላይ ያዝ ለቀቅ ማረጉን ትመርጣላችሁ: ይህ ደግሞ የተፈጥሮ ችግራችሁ ነው:
ጥልቁን የፍቅር ሉል የምትፈልጉት በሆዳችሁ እንጂ በልባችሁ
አይደለም

ሶራ ፀጥ ብሎ ማሰቡን መረጠ፡

'ውብ... ለስላሳ... አስተሳስብ በሳል. ሞልቃቃ...' እያለ ስለሷ
ሲያስብ በተከፈተው ጭኗ እንደገና አየው። ነጭ ፓንቷን…

💫ይቀጥላል💫
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ቀኑ ጭፍግግ ያለው ነው።እቤት ተቀምጬ ከግድግዳዬ ባሻገር ካሉት ጋሽ  ሙሉአለም ጋር  የተለመደውን የአያትና የልጅ ወሬ  ማውራት በጣም ፈልጌ ነበር ...ግን   ዛሬ ዝም እንዳሉ ነው...አንዳንዴ  እንዲህ ያደርጋቸዋል፡፡

ዝምታቸው ሶስት አራት ቀን ባስ ሲልም እስከ ሳምንት ይዘልቃል።እናም በዚህ ሁለት ቀን እየሆነ ያለው እንደዛ ነው።ያ ደግሞ ለእኔ ድብርት ይለቅብኛል። እና አሁን ለዚህ ነው እቤቴን ለቅቄ የወጣሁት። የስራ ሰዓት እስኪደርስ ሁለት ትርፍ ሰዓት አለኝ፡፡
.አይገርምም በዚህ ድህነቴ ይሄ ሁሉ ትርፍ ሰዓት ..
ኑሮዬ የሚያሻሽል መአት ነገር ልሰራበት እችል ነበር...ለምሳሌ ጀብሎ ሆኜ ሲጋራና መስቲካ ባዞር የተወሰኑ ብሮች በእርግጠኝነት አገኝ ነበር....ሊስትሮም ሆኜ ጫማ ብጠርግም እንደዛው...ግን ሰነፍ ነኝ ወይም ግብዝ ነኝ ..ዲግሪ ተመርቄ እንዴት ሊስትሮ? እንዴት ጀብሎ ?ግን ባለዲግሪ ሆኜ አስተናጋጅ መሆን ከቻልኩ ጀብሎስ መሆን ምኑ ይከብዳል? ዛሬ ደገሞ ምን አይነት ሀሳቦች ናቸው በአዕምሮዬ የሚራወጡት ?
ምንአልባት እንዲህ ምነጫነጨው ልጄ ናፍቃኝ ይሆናል..ድምፆን ከሰማው ሶስት ቀን አለፈኝ..ወይ ጉድ ለአመታት ረስቼት እንዳልነበር አሁን  እንዲህ ታሪክ ይቀየር..?.በሀሳብ ስናውዝ አንድን መኪና እንዳልገጨው ስለፈራሁ ፊት ለፊቴ ካገኘሁት ካፌ ዘው ብዬ ገባሁ እና በቅርብ ያገኘውት ጠረጰዛ ላይ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩ።

ማኪያቶ አዝዤ ለመጠጣት እያማሰልኩ ፊት ለፊቴ ያለው ቴሌቪዥን የሚያሰራጨውን ፕሮግራም  እያየሁ ነው.፡፡:ፕሮግራሙ የተደገመ ይላል፡፡ምንአልባት ከሶስት ወይም ከአራት ቀን በፊት የተከናወነ ክንውን መሰለኝ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጡ .››ይላል፡ከዚህ በፊት በቴሌቭዝን የማውቃቸውም ፤በጦርነቱ ምክንያት በየፌስቡኩ ምስላቸውና የጀግንነት ስራቸው ያነበብኩላቸው ጉምቱ የሀገሪቱ የጦር ጄኔራሎች አሉበት.፡፡እኔም እንደወትሮው የቴሌቭዝን ፕሮግረሞች በተሰላቸ መንፈስ  ሳይሆን በተነቃቃ ስሜት ነበር ስከታተል የነበረው..
የማዕረግ እድገቱ ኮረኔሮችን እና ጀኔራሎችን ያከተተ ነው..የፈረጠሙና የገዘፍ የጦር ሹሞቹን ብርጋዴር ጄኔራል፤ሜጄር ጀኔራል.፤ሌፍተራን ጄኔራል እያሉ ትከሻቸወ ላይ ማዕረጉን የሚያሳይ ኮኮብ ሲያስሩላቸው ደስ ይላል፤ይነሽጣልም፡፡፡ምን አለበት እኔም ባለፈው ምልመላ ብመዘገብና ወታደር ብሆን በዚህ ህይወት ከመርመጥመጥ አይሻልም ነበር? ብዬ እራሴን ጠየቅኩ ፡፡ጥያቄዬ አግባብ ነው ወይስ አልፎ ሂያጅ ግልብ ስሜት የፈጠረው..?መልስ ከማግኘቴ በፊት በመሀከል ነጎድጎድ ተንጓጓ፤ ፍንጥቅጣቂና ዝብርቅርቅ ቀለማት በአካባቢዬ ተረጩ፤  መብረቅ  በድንገት ወደቀ…ከመቀመጫዬ ተነሳሁ ወደእስክሪኑ አፈጠጥኩ አዎ እራሷ ነች..፡፡
ኮረኔል ዜናወርቅ ይግዛው  ወደ ብርጋድር ጀኔራልነት ተሸጋግረዋል፡፡በዛ በእውቅ ቀራፂ በአመታት ጥረትና  ልፋት የተቀረፀ የሚመስለው የታነፀና የተገናባ ሰውነቷ ላይ ያንን ባለግርማ ሞገሱ የመከላከያ ልብስ ስትለብስበት ዋው…ጠቅላይ ሚስቴሩ ፊት ቆማ ቆፍጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠች…ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደጆሮዋ ጠጋ ብለው የሆነ ነገር እያንሾካሾኩላት ማዕረጉን በትከሻዋ አጠለቁላት.
እንደ አጀማማሯ ሰላምታ  ሰጥታ  ከመድረኩ ስትወርድ ጋዜጠኛ ተቀበላት፡
‹‹ብርጋዴር ጀኔራል እንኳን ደስ ያሎት››
‹‹እንኳን አብሮ ደስ ያለን?››
‹‹ሴት ሆኖ እዚህ ትልቅ ክብር ያለው ወታደራዊ ማዕረግ ላይ በመድረሶት ምን ተሰማዎት?››
‹‹ያው ይሄ ማዕረግ በደም እና በላብ ነው የሚገኘው…ደምና ላብ ደግሞ የወንድም ሆነ የሴት ጠረኑም ቀለሙም አንድ ነው…በአጠቃላይ ሴት ስለሆንኩ ሳይሆን ስለሚገባኝ ያገኘሁት ማዕረግ ስለሆነ ደስ ብሎኛል፡፡››

ጋዜጠኛው ያልጠበቀውን መልስ ማግኘቱ በሁኔታው ያስታውቃል፡፡
‹‹ምስጋና የሚያቀርብለት ሰው ወይም አካል ካለ እድሉን ልስጦት›የሚል የተለመደ የመዝጊያ ሀሳብ አቀረበ
‹‹የእውነት  ወታደር እንድሆን እና ህልሜን እንድኖር የረዳኝን ተቋሜን አመሰግናለሁ….ሀገሬንም እንደዛው…በደሜ ቁስሏን አጥባለሁ.. በአጥንቴ በጀርባዋ የተሸከመችውን ችግሯን አክላታለሁ የሚል አላማ ነበረኝ ያንንም ያደረኩ ይመስለኛል….ወደፊትም በተለየ መልኩ ተመሳሳዩን ማድረጌን ኦቀጥላለሁ…አመሰግናለሁ፡፡›› ብላ ከእስክሪኑ ወጣች…እኔም ኪሴ ገብቼ የጣጣሁበትን የማኪያቶ ሂሳብ ጠረጳዛ ላይ አስቀመጥኩና ለብቻዬን እየለፈለፍኩ ወደቤት ተመለስኩ ተንቆራጠጥኩ ..ጨጓራዬን ለበለበኝ..ምን አስዋሻት?.የጄኔራሉ ውሽማ እንደሆነች ነበር የነገረቸኝ…?ታዲያ አሁንስ ስለአለመሆኗ ምን መረጃ አለኝ ?ብዬ እራሴን ጠየቅኩ.፡፡ውሸቷን ነዋ ውሸቷን…..ቅምጡ እንደሆነች እኮ ነበር የነገረችኝ….ስራ እንደሌላትም ነግራኝ ነበር…፡፡እንደእብድ በግትልትል ሀሳቦች ሰክሬ ቀባጠርኩ፡፡

ዘንድሮ ምን ውስጥ ነው የገባሁት…?የጄኔራል ቅመጥ አፈቀርኩ ብዬ ስሰጋና ስሸማቅ ጭራሽ እራሷ ጀኔራል…ለመሆኑ ስንት አመቷ ነው…?ስትታይ እኮ ሰላሳም የሞላት አትመስልም..መቼስ በሰላሳ አመት እዚህ ደረጃ ደርሳ እኔን አታሳቅቀኝም..እኔም እኮ ሰላሳ ሊሟለኝ ሁሉት አመት ያልሞላ ጊዜ ነው የቀረኝ…ይሄው ታዲያ እኔ ያለሁበትን እና እሷ ያለችበትን እዩት..
ግን ግላዊ ህይወቷ እንዴት ነው….?ለምን እንደዛ ታደርጋለች..?እንዴት እኔን መረጠችኝ…?ንቃኝ ነው አምናኝ…?
ግን እኮ እስከዛሬ ሶስት ለሚሆኑ ቀናቶች አብረን ተጫወትን አብረን አንድ አልጋ ላይ ተኛን እንጄ ምንም በመሀላችን የተፈጠረ አካላዊ ንክኪ ሆነ ፍቅራዊ ድርድር የለም፡፡..ዝም ብዬ ነወ የምቀባጥረው...እሷ እኔን የምትፈልገኝ ለመደበሪያ ነው..ካላባት ትልቅ ሀላፊነት እና የስራ ጫና ዘና ለማለት እና የህወትን ሌለኛውን ጀርባ ለማየት ስትፈልግ ይሆናል እንደዛ የምታደርገው….ኡኡ ላብደ ነው..፡፡ልብሴን ቀየርኩና ከቤት ወጣሁ ፡፡ሰዓቱ ስለደረሰ ወደስራ ነው የገባሁት..ከአንገት በላይ የግድ ስለሆነብኝ ብቻ ስራዬን መሰራት ጀመርኩ፡፡

ማታ አራት ሰዓት አካበቢ የደንበኞችን ትዕዛዝ ለመተግበር ከአንዱ ጠረጴዛ ወደሌላው ጠረጴዛ ስመላለስ አይኔ አንድ ነገር አየ..ጄኔራሏ እንደተራ ሰው ጅንስ ሱሪ ለብሳ ኮፍያ ያለው ቢጃማ ጃኬት አድርጋ ኮፊያውን ጭነቅላቷ ላይ ደፍታ  በአይኖቿ ጥቁር መነፅሯን ሰክታ ልክ የሰፈር ማጅረት መቺ መስላ ሚሪንዳ ቶኒኳን  ትጠጣለች፡ ፡ተንደርድሬ ስሯ ደረስኩና ጠረጴዛውን ተደገፍኩ…. አይኖቾ ላይ አፈጠጥኩባት ….ተረጋግታ ቀስ ብላ መነፅሯን አወለቀችና በፈግታ አየችኝ...ምለው ነገር ስለጠፋኝ ካጎነበስኩበት ቀና አልኩና ፊቴን ዞሬ ከመቀመጫዋ ራቅኩ…ተመልሼ ወደእዛ አልሄድኩም… .በጣም ተበሳጭቼባተለሁ፡፡
እንዲያ በተወጠረ ስሜት ላይ ሆኜ ሰዓቱ እንደምንም ገፋ፡፡ ተስተናጋጆችም አንደ በአንድ እያሉ ወጥተው አለቁ… ፡፡እሷም ምን ጊዜ እንደወጣች፤ወደየት እንደወጣች  ባላያሁበት የጊዜ ቀፅበት ከእይታዬ ተሰወረች …ሂሳብ አሰረክቤና  አንገቴን አቀርቅሬ በተከፋ ስሜት ወደቤት ሄድኩ..በራፍን ከፍቼ ገባሁ፡፡

‹‹አንተ ቀልማዳ መጣህ?››አያቴ ናቸው፡፡

ውይ ተመስጌን አያቴ መናገር ጀመሩ…

‹‹አዎ አያቴ..ግን ቢያዩ ድክም ብሎኛል››መናገር በመጀመራቸው በጣም ደስ ቢለኝም እኔ ደግሞ በተቃራኒዊ በዚህ ወቅት ምንም አይነት የመናገር አፒታይት የለኝም.፡፡ጥልቅ ምስጠት ውስጥ ገብቼ በሀሳብ መንቦራጨቅ ነው ያማረኝ፡፡
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_አስራ_አንድ


...ደግመን ልንበድላት አይገባም የዱላን ፍቅር አሳይዋት እሷም ተተወሰነ ጊዜ በኋላ ፍርሃቱ ይወጣላታል!"

"እእ! እሽ ዛሬስ እኛም አስበናታል ና እንጂ አንተስ
ተጫዋት?"

አለሁ የት እሄዳለሁ  አዳሬ ተዚሁ ነው" ብሎ ደልቲ
ከበርኮታው ላይ ተነሳ ጎረምሳው ደግሞ የባራዛ አርጩሜውን ወደ
ደበቁበት ጉቶ ሄዶ ሶስት ለበቆችን አነሳ ደልቲም ከወንዶች ግማሽ ክብ ሰልፍ ገብቶ ወገብ ለወገብ ተያያዘ

አንዱ ጎረምሳ አንደ መፎከሪያ በርኮታውን በቀኝ እጁ ይዞ የመፎከሪያ በሬውን ጥንካሬና ውበት የጓደኝነታቸውን ምሥጢር
ሲደረድር ሁለት ልጃገረዶች አንባራቸውን እያፋጩ: ከፊት ለፊቱ ቆመው ሲያሞጋግሱት ቆይቶ እያቀነቀነ መዝለልና መጨፈር ጀመረ
ከዚያ የእድሜ ጓደኞቹ ተቃቅፈው ሄደው በቃህ ብለው በትህትና
ጠይቀው አጅበው ተሰልፉ አስገቡት ወዲያው ግን
ጧ ጧ፥ጣጣ.ጣ… የሚል ግርፊያ ተሰማና ልጃገረዶች እያውካኩ፥ ብትን ብለው ሲስቁ ቀጭን የሲቃ ልቅሶ ከመካከላቸው ተሰማ"

ያች ባለጌ ናት! አለ ደልቲ ንድድ እያለው"

ኮቶ ምን አደረኩት ..." ካርለት እንባዋ እየረገፈ ሰውነቷ
እየተንቀጠቀጠ፥ ኮቶን ተጠምጥማ ጠየቀቻት ለበለባት የተገረፈችው
ቦታ ሰንበሩ ጀርባዋ ላይ እንደ እባብ ተጋድሞ ቆጠቆጣት እንባዋ
እርግፍ እርግፍ አለ

"ኮቶ ለምን ገረፉኝ ..." አለቻት ህቅ ብላ እያለቀሰች,

"ይእ! ካርለቴ ደንብ ነው ብየሽ! ዘመድሽኮ ነው፤ “ለምን ተኔ ጋር አትደንሽም ብሎ ነው የመታሽ ሄደሽ አብረሽው ደንሽ
ይልቅ  ታለበለዚያ ይደግምሻል"" ስትላት ካርለት ቦታውን ለቃ
ልትሄድ አሰበች ህሊናዋ ተሟገተ

"ኮቶ ለምን እገረፋለሁ!- እኔ'ኮ መመታት አለመድሁም?" ብላ
በቀላው ዐይኗ ትክ ብላ አየቻት

"ይእ!  ስንወለድ እኮ እኛም አለመድነውም ትርጉሙን
ስናውቅ ማድረግ ያለብን ነው ብለን ስናምን ልባችን ደንድኖ ለመድነው አንችስ ሰው መስለሽኝ ስትመጭ የካሮ አፈር  ፈጭተሽ መች ትቀቢ ነበር ቆዳ መልበስ:
በእግር መሄድ እንጨት
መልቀም የተማርሽው እዚህ አይደል ግርፊያም የሚለመደው ስትደፍሪ ነው
የፍቅር ማባያ ይሆንሻል
የተማርሽው እዚህ አይደል
ስትገረፊ መጀመሪያ እንደቃሪያ ያቃጥልሻል ቀጥሎ የፍቅር ማባያ ይሆንሻል በመጨረሻ ደግሞ የሚለበልበው ቃሪያ
ያምርሻል! አይዞሽ የኔ እህት ያን ጊዜ እንደ ሱስ በልቦናሽ
ውል እያለ አምጭ አምጭ' እያለ ተሐመር አንበሶች ክርን ስር ያልወሰውስሻል
ከዚያ ትለምጅዋለሽ" ብላ ደረቷ ላይ አስጠግታ አግባባቻት,

"እሽ ኮቶ ካርለት በጽሞና ስታዳምጣት ቆይታ እንባና ሳቋ ተቀላቀለባት

"እሽ! ዓላማ ታውቂያለሽ ኮቶ" አለቻት  ትክ ብላ በጨረቃ  ብርሃን እያየቻት

"ይእ! ኢላማ ማለትሽ ነው  ማነጣጠሪያ የዓልሞ ተኳሽ
መለያ ነው ኢላማ ተሆነ "

"ልክ ነሽ! የአነጣጠርኩት: ዓልሜ የምመታው ኢላማ አለኝ ኮቶ! ስለዚህ

"ይእ! አይ ካርለቴ መቼም የአንች ነገር እንደ እርጎ ዝንብ ወንዶች መዋያ ጥብሉቅ ማለት ስትወጂ  እስቲ እንደ ሴት ኢላማሽ
ልጅ መውለድ: ለባል ታዛዥ ለመሆን ይሁን የአባት ደንብ ለማክበር ይሁን ኢላማሽ!"

"እንደንስ ኮቶ!  ዳንስ አማረኝ ግርፊያ ፈለግሁኝ... ንኪው ልቤን የፍርሃት እርግጫውን አቆመ
አደፋፈርሽው አስተማርሽው ህዋን የሰው ልጅ በእግሩ ሲረግጥ እኔም በጭንቅላቴ
የመሬትን እንብርት  እነካዋለሁ…ቃሪያውን እየበላሁ ጥቅምና
ጉዳቱን ለሌላው አሳያለሁ  እነ ዲያና ፎሲ ከጉሬላ ጋር ቅጠል በልተውስ ኖረው የለ

"ይእ!- ካርለቴ!" ወዘወዘቻት ትከሻዋን"

"ደህና ነኝ ኮቶ"

"እየቃዠሽ! ቢጫ ሐሞት እንደሚያስተፋ ወባ እንደያዘው ሰው

"የለም ደህና ነኝ ቃል ኪዳን ነው ኮቶ ሰው ለመሆን፥
ጠንካራ ሰው!... በተሰጠኝ የሰውነት ክፍል ሁሉ ተጠቅሜ ከቦርጆ
ወቀሳ ለመዳን ባህሉ ተጠየቀኝ ለዓላማዬ ስል እኔም የእባብንም
አንገት አንቄ ጥርሶቹን ላይ መርዛም ነው የሚባለውን እባብ ጥቅምና
ጉዳቱን ጉሮሮውን ፈልቅቄ ላይ ተገርፌ፥ አልቅሼ: ቧጥጬ ባህሌን ጥሼ ባህል ላሳውቅ ኮቶ!"

"ይእ!  መንደር እንሂድ ካርለቴ?"z

"ተይኝ!  ትንሽ ጊዜ ብቻዬን ተይኝ!  እሽ?"

"ይእ! እሽ " ኮቶ ሄደች ዝምታ ፀጥታ ህሊናን
እንዳይደነብር  እንደሚያረጋጋ ተከብቶች ከአባቷ ከመንደሯ…
ተምራለችና ሄደች
ካርለት ራሷን ከፈተችው... ወደ ራሷ ገባች ... የላላውን
አጠባበቀች የተወጠረውን አላላች የአበጠውን አፈረጠች የቆሸሸውን አፀዳች ካርለት እንደ አዳኝ ውሻ ዐይኗን ጠበብ አድርጋ ደልቲን አየችው አያያትም" ወደ ዳንሱም ልትጋብዘው አትችልም፤ ዳንሱ
እንደገና ተጋጋለ

"ይእ! ካርለቴ ነይ ጋብዥው የገረፈሽን?" ብላ ኮቶ ጠራቻት ወገባቸውን ተቃቀፉ ከዚያ በቄንጥ እንደ ፔንዱለም ፊትና ኋላ
ተወዛወዙና ሶሰት ጊዜ ዘለል: ወዝወዝ… ብለው ሾረው ሄደው ሁለት
ጎረምሶችን ጋበዙ"

የገረፋት ጎረምሳ ካርለት ስትጋብዘው እየሰገረ ሄዶ የካርለትን ጭኖች እንደ መሮ እየሰረሰረ ገብቶ: በእጆቹ ቀጭኑን ወገቧን
ጨምድዶ አሻት ጎረምሳው ሳያቋርጥ እየሰረሰራት ጭኖችዋን በስቶ
ገባ "የት ሊደርስ ነው?" እያለች ሸሸችው እሱ ግን
ወገቧን የጨመደደበትን እጁን እየወጠረ ሲጠጋት ቆየና ከገለዋ ተጣበቀ
የሚታሸው አካሏ የአምቦ ውሃ እንደጠጣ ሰው አስገሳት እሷም
ሰረሰረችው፥ ወዘወዘችው.

ካርለት ያላየች መስላ ደልቲን አየችው ደስ ብሎታል እሷም ደስ አላት ደልቲ አልቀናም ቅናት ባህል እንጂ ተፈጥሯዊ
እንዳልሆነ አሰበች ጭፈራው ቀጠለ ጨዋታው ደመቀ።

"ኮቶ!"

"ዬ ሳቀች ከትከት ብላ ቀጣዩ ዳንስ እስኪጀመር
ቦታቸው ሲመለሱ

"ምን ሆንሽ ካርለቴ?" አለቻት

ሃሣቧን ሳትጨርስው  ደልቲ እጅዋን ያዝ አድርጎ
ከሴቶች መሐል ጠራት የሆነ ነገር እንደ ፍላፃ ተወርውሮ ስሜቷን
አጋጋለው" ፈገግ አለችለት ለስሜቷ-ለደልቲ…

ከዚያ በኋላ ብዙ አልተነጋገሩም ቀስ ቀስ እያሉ ፈንጠር ፈንጠር ብለው ጨረቃን አሹፈውባት ሰማይ ይግቡ መሬት ጠፉ….የኢቫንጋዲ ጭፈራው ግን ቀጥሏል ወደፊትም ለቀናት: ለዓመታት ይቀጥል ይሆናል ከዚያ ግን ይሸነቆራል
ወይንም ለዘመናት
ጥቅም፥ ገንዘብ‥ የተባለው ቆሻሻ ስልክልክ ብሎ ገብቶ ይበክለዋል ደስታም ጥቁር ከል ለብሳ: ተስፋ ቆርጣ: መባዘኗን ትጀምራለች
ካልያም አንድዬ አንች ከርታታ ተዛሬ ጀምሮ መባዘንሽ ያቆማል'
ብሎ ይጠራታል… እግዚኦ ያች ቀን ምናለ ባትደርስ! እግዚኦ!…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቀትር ነው፤ የፀሐይዋ ሙቀት አሸዋው ላይ ነጥሮ እንደ ሐይቅ
ማዕበል እየተንቀሳቀሰ ከርቀት ጀምሮ ይታያል በዚያ አይነቱ ሐሩር የዛፍ ጥላ ህይወት አዳኝ ነው" የሐመር ወንዶች በእንዲህ ዓይነቱ ሙቀት ወቅት ዛፍ ጥላ ሥር ይሄዱና ሲጫወቱ: ሲወያዩ
ቆይተው አሸዋውን ይደለድሉና በበርኮታቸው ጭንቅላታቸውን ደገፍ
አድርገው እረፍት መውሰድ የተለመደ ነው

የሐመር ህይወት የሆነው ከስኬ ወንዝ ከጥም አርኪነቱ ሌላ ከለላ ችግርን መፍቻ በከብት ዝላይ ወቅት የልጃገረዶች መገረፊያ
መጋጌጫ… ማረፊያ ነው ለሰውም ለከብቱም ጫርጫር ሲደረግ ውስጡ ውኃ ይፈልቃል ላዩ መኝታ ይሆናል መወያያ መድረክም  ነው ሐመሮች የከስኬ ናቸው ከስኬም የነሱ ነው ያጌጡበታል
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
.እንሂድ ወዳላት ቦታ ለመሄድ ብዙም ደስተኛ እንዳልሆነች በመገመት‹‹አዎ ምነው…?አባቴ እዛ ነው የሚኖረው ..በየሳምንቱ በዚህን ሰአት ይጠብቀኛል..ባይሆን ከዛ መልስ አንቺ የፈለግሽው ቦታ እንሄዳለን፡፡›አላት፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም..እንዲሁ ያልጠበቅኩት ቦታ ስለሆነ ነው››ብላ በምትሄድበት ቦታ እንዳልተከፋች ተናገረች…እውነታው ግን እንደዛ አልነበረም፡፡
ከዛ በመሀላቸው ዝምታ ሰፈነ›…የሆነ ነገር ይናገራል ብላ ብትጠብቅም ለረጂም ደቂቃ ዝም አለ፡፡እሱ በጥልቀት ስለእሷ እያሰበ ነው…እሷ ከጠበቀችውና ከምታውቃቸው ወንዶች ሁሉ የተለየ ሆኖ እንዳገኘችውና በዛም እየተደመመችበት ሁሉ አሱም እጅግ ገራሚ ሴት ሆና አግቷታል…..የሌብነት ታሪኳ ግራ አጋብቶት ሳያበቃ አሁን መኝታ ቤቱ ገብታ የሰራችው ስራ ከግምቱ ውጭ ነው የሆነበት ‹‹ይህቺ ልጅ በህይወቴ የተከሰተችው በድንገgትና በአጋጣሚ ነው ወይስ ሆነ ተልዕኮ ኖራት አቅዳና አልማ?››ሲል እራሱን ጠየቀ..ቃል የተመረቀው በኮምፒተር ኢንጂነሪንግ ነው፡፡በስራው በጣም የተመሰገነ እና ፕሮፌሽናል ባለሞያ ነው፡፡ስልኩ ላይ አንድ እራሱ የሰራው አፕ አለ..ባለበት በ10 ሜትር ያለ ካሜራ መኖሩን ምልክት የሚሰጥ አፕ ነው…ለረጅም ጊዜ የለፋበትና ሚኮራበት ስራው ነው…ከስድስት ወራ በላይ ሙከራ ላይ የቆየና መቶ ፐርሰንት ሙከራውን አልፎ አሁን ለሽያጭ ሊያቀርበው ድርድር ላይ ይገኛል፡፡እና ልዩ መኝታ ቤቱ ከገባችበት ከደቂቃዎች በኃላ ይሄ አፕ ካንቀላፋበት ነቅቶ ድምፅ ሲያሰማው ማመን አቅቶት ክፉኛ የደነገጠው ለዛ ነው፡እዛ እሱ ቤትም ሆነ በጊቢው ምንም አይነት የካሜራ ዘር አንደሌለ እና ኖሮም እንደማያውቅ እርግጠኛ ነው፡፡ለማንኛውም ወደቤቱ ሲመለስ ያረጋግጣል .ለምን አለማ እንዳስቀመጠችውና እሱስ ምን እንደሚያደረግ ያስብበታል.
‹‹ምነው ዝም አልክ ፈራህ እንዴ ?››ስትለው ነበር ከሀሳቡ የባነነው፡
‹‹ለምንድነው የምፈራው?››
‹‹አይ…ምን አልባት የተሰረቀ  መኪና ውስጥ ያስገባሁህ መስሎህ …እንዳልታሰር ብለህ ፈርተህ እንደይሆን ?››
የማሪያምን ብቅል የበላ ይለፈልፋል ነው የሚባለው አይደል..የራሷ ክፉ ስራ ደጋግሞ ያስለፈልፋት ጀመር.
‹‹በፍፅም እንደዛ አላሰብኩም….››አለ ፍርጥም ብሎ፡
‹‹ብታስብም እኮ በቂ ምክንያት አለህ..ግን ማረጋግጥልህ መኪናዋ የራሴው ነች .. ማለቴ የእኔ እንኳን አይደለችም የእናቴ ነች፡፡››
‹‹ገባኝ….››
‹‹ግን ትገርማለህ…እንዴት ነው ስሜትህን እንደዚህ ማመቅ የምትችለው?›› አለችው፡፡
‹‹እኔ ስሜቴን ማመቅ..?እንዴት እንዳዛ ልትይ ቻልሽ…?››አላት በውስጡ‹‹እኔም በአንቺ ሚስጥራዊ ደርጊቶች ተገርሜያለሁ››ሲል አሰበ
‹‹እኔን በተመለከተ እስከአሁን ያየሀቸው ነገሮች ድርጊቶቼ  የተለመዱ እና ዝም ብለህ የምታልፋቸው ናቸው ማለት  ነው…? ምንም አያስደንቁህም…? የማወቅ ጉጉትህን አይቀሰቅሱም..? እና ምንም ጥያቄ የለህም….?››
‹‹ስለአንቺ  በጥልቀት  ለማወቅ ሁኔታዎችን እየገመገምኩ ነው..ማለት እንዳልሽው ከድርጊቶችሸ በፍቃድሽ ከምታደረጊያቸው ነገሮች በመነሳትና   እነሱን በመገጣጠም…ግን ጥያቄ ልጠይቅሸ አለሰብኩም.. ማለት ምንም ጥያቄ የለኝም››እውነቱን ነገራት፡፡
‹‹ማለት ጥያቄ ካልጠየቅከኝ እንዴት ታውቀኛለህ?››
‹‹ጥያቄ በመጠየቅ የሆነ ስውን በጥልቀት መረዳት እኮ አድከሚው መንገድ ነው…አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽ ለዛ መልስ ትሰጪኛለሽ…ግን ደግሞ መልስሽ ውስጥ ተደብቀው የሚወለዱ ሌሎች ጥያቄዎች ይፈልቃሉ…. መልስ ጥያቄ ..መልስ… ነገሩ ሁሉ  አዙሪት ነው የሚሆነው…..››አለ….ወደቤቱ ሲመለስ ሰለሚጠብቀው እሱን ለመሰል ስለተደበቀ ካሜራ እያሰበ፡፡
‹‹እሺ እራሴ እየጠቅኩ እራሴ ልመልስ..?›››
ዝም አላት.እሷ ማውራቷን ቀጠለች፡፡
‹‹ለምን ሌባ ሆንኩ…?መስረቅ ስለሚያስደስተኝ  ወይ  የመስረቅ በሽታ ስላለብኝ…መልሱ ሁለተኛው ነው፡፡የስርቆት በሽታ አለብኝ፡፡አስቂኝ ነው አይደል?፡፡ግን በሚገርም ሁኔታ  ይሄን በሽታ ደበሪ ነው፡ አወቃላሁ ደባሪነቱ የሚገለፅልኝ ግን  ካደረኩት በኃላ ነው ፤እንደ መጠጥ ወይም ሲጋራ ሱስ በለው..አንድ የሀሺሽ ሱሰኛ ፊት ለፊቱ ሀሺሽ ሲያይ እንደሚያቅበጠብጠው ሁሉ እኔም የሚሰረቅ ነገር በአቅራቢያዬ ካለ እንደዛ ነው ሚያደርገኝ፡፡ ምንም ያህል ብጥር እራሴን ወደኃላ መግታት አልችልም፡ ሆን ብዬ እኮ አይደለም ማለቴ እቅድ ወጥቼ ልስረቅ ብዬ በፍፅም ሰርቄ አላውቅም፡፡ የማደርጋቸው ነገሮች በሁኔታዎች ውስጥ ነው የሚከሰቱት፡፡ለምሳሌ ፀጉር ቤት ፀጉሬን ለመሰራት ሄጄ ተሰርቼ ከጨረስኩ በኃላ  ሂሳብ 200 ብር ከሆነ ሀምሳ ብር ጨምሬበት 250 ብር ከፍልን ባለሞያዎ ስትፍነከነክ አዘናግቼ የ25 ብር ማበጠሪያ ሰርቄ ቦርሳዬ ውስጥ ደብቄ ወጣለሁ፡፡››
‹‹እንደዛ ካደረግሽ በኃላ ምን ይሰማሻል?›ሲል የትዝብት ሳይሆን የሀዘኔታ በሆነ ድምፅ ጠየቃት፡፡ንግግሯን ከስሜቷ ጋር አንድ ላይ አጣምሮ ሲመዝነው ምንም አይነት ውሸት የሚመስል ነገር ሊያገኝበት አልቻለም…
እሷ ቀጠለች‹‹በወቅቱማ  አሷ ዞር እስክትል መጠበቁ…. .ማዘናጋቱ …ሌሎች ተስተናጋጆች እንዳያዩኝ መጠንቁ ከዛ ፐርፌክት በሆነ ታይሚንግ ማበጠሪያውን ባርሳዬ ውሰጥ ከትቼ ምንም እንዳልተፈጠረ በፈገግታ ሁሉንም ተሰናብቼ መውጣቱ በጣም ደስ የሚል እርከታ ነው የሚሰጠኝ..ችግሩ አካባቢውን ለቅቄ ትንሽ ራቅ ካልኩ በኃላ ነው.፡፡
ስሜቴ ሁኑ በአንዴ ዘጭ ይላል፡፡.ለምንድነው እንዲህ ያደረኩት.?አሁን ይሄ ማበጠሪያ ምን ይረባኛል..?ብያዝስ ምንድነበር የምለው.?እኚህንና ሌሎች መሰል ጥቄዎችን እየጠየቅኩ በጣም አዝናለሁ፡፡ አንዳንዴም ስቀስቅ ብዬ አለቅሳለሁ፡፡ .እራሴን እጠየፋለሁ፡፡ ለምሳሌ እንዳልኩህ የሰረቅኩት ማበጠሪያ ከሆነ ፀጉሯ የተንጨፈረረ የጎዳና ለማኝ ፈልግና የመኪናዬን መሰኮት ዝቅ አድርጌ ወረውርላታለሁ….ካልሆነም ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ እጥለዋለሁ…ስልክ ከሆነ ደግሞ  ብዙውን ጊዜ መልሰው ስለሚደውሉ የሆነ ቦታ አስቀምጥላቸዋለሁ.ሄደው ይወስዳሉ.. አንዳንዱ ደግሞ  ሊሳደብ ሲፎክር እልክ ይይዘኝና ዝም ብዬ ለአንዱ የሰፈር ጎረመሳ ሸልመዋለሁ...ብቻ አንድም ቀን የሰረቅኩት ነገር ትንሽ እንኳን አጓጉቶኝ ተጠቅሜበት አላውቅም…. ምክንያም ምሰርቃቸው ነገሮች ሁለ ቤቴን ያጨናንቁ ተራ ቁሶች ናቸው.ቢሆንም ግን እቃዎቹን አለመጠቀሜ እኔን ንፁህና ስራዬንም ልክ አያደርገውም፡፡...ያው ሰርቃለሁ ማለት ሌባ ነኝ..ሌላ ምንም ማስተባበያ ሊሰጥበት የሚችል ጉዳይ አይደለም…፡፡
‹‹ግን ተይዘሽ አታውቂም.?››
‹‹አንድ አራቴ››
‹‹ታዲያ እንዴት ተወጣሽው.?››
‹‹ሶስቱን ከተሰራቂዎቹ ጋር ተደራድሬ ብር ሰጥቼያቸው ለቁኝ፣አንዱ ግን ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ አንድ ቀን አሳደረኝ፡፡›
‹‹እንዴት ?ልትደራደሪው አልቻልሽም ነበር?››
‹‹እንደውም መስረቄ ሳይሆን ለመደራደር ሞከሬ ነበር ይበልጥ ያበሳጨው... ሰውዬው ለካ ፖሊስ ነበር››
‹‹‹በተሰቀለው..ታዲያ በመጨረሻ እንዴት ሆንሸ?›
#ህያብ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በኤርሚ



#ከጊዜያት_በኋላ

"ንገሪኝ እስኪ ህያብ ሀኪም እንዲያይሽ ባትፈልጊም ህመምሽን ለኔ ንገሪኝ ዝምምም ብዬ እሰማሻለሁ። ስለ ልጅሽ ስለ ዮኒ ስለተፈጠረው ሁሉንም ንገሪኝ" ሶስት ወራትን በዝምታ ስለዚህ ነገር ሳያነሳብኝ ሳላወራው በየጊዜው የአእምሮ ህመሜ እየተነሳ ከኔው እኩል ሲሰቃይ አሳልፈናል። ትዕግስቱ እንክብካቤው ፍቅሩ ድሮ ከማውቀው የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግን ምን ዋጋ አለው ፍቅር አንዳንዴ ፍትሀዊ አይደለም ቢሆንማ ኖሮ የማፈቅረው ዮኒን ሳይሆን ቢኒን ነበር። ወደ መኝታ ቤት ሄድኩ... ተከተለኝ... በሩን ከፍቼ ገባሁና ቤቴ ሄደን ካመጣናቸው እቃዎች መሀል አነስተኛውን ሻንጣዬን አወረድኩት... ከፈትኩት... ውስጡ ያለው ሁሉም የልጄ ማስታወሻ ነው። ለአዲስ አመት የሳለችልኝን አበባ አገኘሁት... እሱን አቅፌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ

"የኔ ልጅ... የኔ እንቁ... ናፈቅሽኝ እኮ" ቢኒ አጠገቤ ብርክክ ብሎ ትከሻዬን ያዘኝ ከዛም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ። ህመሜ ሳይነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አረጋጋሁና ከእቅፉ ወጥቼ ከመፅሀፍ መሀል አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አወጣሁት... ከባዱን መርዶ ያረዳኝን... መራራውን እውነታ የጋተኝን ደብዳቤ አወጣሁና ለቢኒ ሰጠሁት። ግራ በተጋባ ፊት ካየኝ በኋላ ከፈተው... ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ እያንዳንዱን ቃል እንደ ውዳሴ ማርያም የሸመደድኩትን ደብዳቤ እሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነበው ከፈተው... እንዲህ ነው የሚለው...

"ማሚ ከበደል ሁሉ የቱ እንደሚከፋ ታውቂያለሽ... አባቴ የምትይው ሰው በስሜት ጦዞ ጭንሽን ሊከፍት ሲታገል ማየቱ...... ማም እውነቱ ይገልሻል አውቃለሁ ...ግን እንደዛ ጠንካራ ስነ ልቦና እንዲኖራት አድርገሽ ያሳደግሻት ልጅሽ ለምን ራሷን አጠፋች? የሚለው ጥያቄም ይገልሻል። ማም እውነቱን እወቂው..... መጀመሪያ የውሸት ቆይቶ ደግሞ የእውነት አባት የሆነኝ ዮኒ የውሸት አባቴ እያለ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ደፍሮኛል። ታስታውሻለሽ ያኔ ፔሬድ አሞኝ ነው ብዬሽ የተኛሁ ጊዜ... ለመጀመሪያ ጊዜ የደፈረኝ ቀን ነበር። አንቺ ውስጥ እያለሽ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ፊቴን አዙሬበት ነበር አይደል? ከዛ አንቺ ወጣሽ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ 'በሶስተኛው ቀን መድገም አለብን ካላዛ ተደፍነሽ ትቀሪያለሽ' አለኝ። እናም በሶስተኛው ቀን መኝታ ቤቴ ድረስ መጣ... መከላከል ደከመኝ እና በዝምታ አየሁት ሳይራራልኝ እላዬ ላይ ጨፍሮ ሄደ... ያንኑ ድርጊቱን የአባትነት እውነታው እስከሚታወቅ ድረስ ደጋገመው። በተለይ ፊልድ መውጣትሽ ለሱ ምቹ ሁኔታ ለኔ ደግሞ ስቃይን ፈጠረ

ካንቺ ፊት ላይ የየሁትን ደስታ እኔ ጋር ፈልጌ አጣሁት። ማም እንዴት ልደሰት... አባቴን አገኘሁ ብዬ እንዴት ደስ ይበለኝ...? አባትነቱን እኮ ጭኔ መሀል ቆፍሮ ቀብሮታል። እናም አባቴ አይደለም ሊሆንም አይችልም ብዬ በዝምታ ተሸብቤ ቁጭ ብዬ እያለ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። በየጊዜው እየመጣ ይቅርታ ብሎኝ 'አደራ ለናትሽ እንዳትነግሪያት' ከሚለኝ ከህሊናቢሱ አባቴ የስምንት ሳምንት ነብሰ ጡር እንደሆንኩ ሆስፒታል አረጋገጥኩ። ያኔ በራሴ ላይ ወሰንኩ... ታሪክ ራሱን አይደግምም... ማም አንቺ አባት እንደሌለኝ እያሰብሽ ወልደሽ እሳደግሺኝ... የኔ ልጅ አባት ግን አባቴ ነው... እናም በራሴ ላይ እና ባልወለድኩት የአባቴ ልጅ ላይ የሞት ፍርድ ወሰንኩ።

ማሚዬ ለኔ ስትይ ጠንክረሽ ኑሪ እወድሻለሁ።
እድለቢሷ ልጅሽ"

ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ ቢቆይም እንባ ከአይኖቹ እየወረደ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል።

"ይህን ደብዳቤ ሳገኘው ቢኒ ጊዜው ረፍዷል... የልጄ ገዳይ አጠገቤ አልነበረም... ትቶኝ ሄዶ ነበር... ፈለኩት በየሆስፒታሉ በየሆቴሉ ግን አጣሁት... ባገኘው በአደባባይ ስጋውም ዘልዝዬ ለአሞራ እሰጠው ነበር"። እያለቀሰ መጥቶ አቀፈኝ ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን...።

"እባክሽ አንድ ነገር እሺ በይኝ የስነልቦና ሀኪም ይይሽ እባክሽ ለኔ ስትይ" ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ቢጨቀጭቀኝም እምቢ ነበር መልሴ

"እሺ ደስ ያለህ ሀኪም ጋ ውሰደኝ"

።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።። ።።።

የስነ ልቦና ህክምናዬን ከጀመርኩ አንድ ሳምንት ቢያልፈኝም ለዶክተሬ ምንም የነገርኩት ነገር አልነበረም። የሆነ ቀን ግን ልክ ከዚህ በፊት ያለውን ታሪክ እንደሚያውቀው ሁሉ

"ዮኒን ብቻ ጥፋተኛ አድርጌ እንዳልፈርድ የሚያደርገኝ እንደዚህ ያሳመመኝ ብዙ ፀፀት ውስጤ አለ። ብዙ ቢሆን ኖሮ.... ብዙ.... ብዙ....

•ከመጀመሪያው ታሪኬን ነግሬው ቢሆን ኖሮ

•ስራ ስራ ማለቴን ትቼ ለልጄ ጊዜ ሰጥቻት ቢሆን ኖሮ

•እንደዛ ሆና እያየኋት ትንሽ እንኳን ለምን አልተጠራጠርኩም... አሁን እኔ ዶክተር እባላለሁ...

ከሁሉም በላይ ፀፀቱ በልቶ ጨረሰኝ... መገጣጠሚያ አጥንቴ እስከሚታይ ከሳሁ... ጠቆርኩ... ታመምኩ... አበድኩ ...ግን ትርጉም አልነበረውም... እኝህ ሁሉ የኔን እንቁ አይመልሱልኝም ባዶ... አንተስ የኔን እንቁ ትመልስልኛለህ? አየህ እዚህ መጥቼ መፋጠጣችንም ትርጉም የለውም ባዶ..." አልኩት። ዝምምም ብሎ ካየኝ በኋላ ከወንበሩ ተነስቶ መጥቶ ፊት ለፊቴ ሶፋ ላይ ተቀመጠ

ከስድስት ወራት ያላሰለሰ የህክምና ክትትል በኋላ ወደራሴ ተመለስኩ ወደ ስራየም ጭምር። ከቢኒ ጋር ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ጀመርኩ... ህይወት ድጋሚ ቀጠለች። ያለፈው ባይረሳም ህመሙ ቀንሷል... የልቤ በልቤ ተቀብሮ መሳቅ ቻልኩ።

ከቢኒ ጋ ልንጋባ ነው ማለትም ከሁለት ወር በኋላ እንጋባለን። ለፊርማው እንጂ የምንኖረው አንድ ቤት የምንተኛው አንድ አልጋ ላይ ከተጋባን ቆይተናል ለማለት ነው። ልንጋባ መሆኑን ያወቀው ሀብታሙ ካለበት ሀገረ አሜሪካ የሚያምር ቬሎና ሱፍ ልኮልናል። ለቢኒ ሚዜ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ።

የሆነኛው ሌሊት ላይ ተኝቼ ልጄን በህልሜ አየኋት... ብቻዋን አይደለም ዮኒ ሲደፍራት "ድረሽልኝ" እያለች ስትጮህ... ጮኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ... አጠገቤ የተኛው ቢኒ ጩኸቴ አስደንግጦት

"ምንድነው ፍቅር አይዞሽ ቅዠት ነው" አለና እቅፉ ውስት ከተተኝ... እኔ ግን የበቀል ጥሜ ድጋሚ አንሰራራ... እፈልገዋለሁ እናም እገለዋለሁ... እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

ለቀናት በሀሳብ ተብሰከሰኩ እናም ወሰንኩ ይህን ነገር ከስሩ መንግዬ መጣል ይኖርብኛል። ተቆርጦ ባቆጠቆጠ ቁጥር ህመሙ እየባሰ ነው የሚሄደው ስለዚህ እ ገ ለ ዋ ለ ው

#አሁን

ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም... ፍቅርን እንጂ።
እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው...

መፃፍ ጀመርኩ

"አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል።
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ያ ማለት ታዲያ ኬድሮን ሁሌ መልካም ስራና የሚያስመርቅ ተግባር ብቻ ትሰራለች ማለት አይደለም፡፡ሲመጣባትና በተለይ እንድትበሳጭ ካደረጓት ሰይጣን እንኳን ሊያስበው የማይችል ክፉ ስራና አስደናጋጨ ተንኮል ባለቤት ነች፡፡

የእሷ እኩዮች ሆኑ በዕድሜም ሆነ በአካል ዘለግ የሚሉ ልጆች ጋር ተጣልታ እጇን ሰንዝራ በጥፊ ከመታቻቸው የሆነ ነገራቸው ለሳምንት ይጣመማል…በዛ የተነሳ የማንኛውም ወላጅ ቀዳሚ ምክር ‹‹እባካቹ ከዛች ግማሽ ጋንኤል ከሆነች ልጅ  ጋር አትጋጩ›› የሚል ነው፡፡ትልልቅ ሰዎችንም ካበሳጯት የሆነ ነገር አድርጋ ሳትበቀላቸው በምህረት የምታለፈው ነገር አይኖራትም፡፡ ስትበሳጭ የሰውነቷ የቆዳ ቀለምና ከአይኖቾ የሚፈልቁት ብርሀን የተለዩና አስፈሪ ይሆናሉ፡፡
10   አመቷ ላይ ነው፡፡ከምሸቱ 12 ሰዓት አካባቢ ከብቶቾን ከፊት እየነዳች ወደ ሰፈር እንደደረሰች ወደ ቤታቸው መጠምዘዣ  ኩርባ ላይ  ባለ አንድ የግንድ ጉማጅ ላይ አንድ ልጅ ተቀምጦ አንገቱን አቀርቅሮ እንባውን ወደምድር ያንጠባጥባል…ልጁ በዕድሜ በሁለት አመት ቢበልጣትም ጓደኛዋና የሰፈሯ ልጅ  ነው፡፡ድባለ  ይባላል፡፡ገና ከሩቅ እንዳየችው ነው ሰላም እንዳልሆነ የተረዳችው… በእጇ አንጣልጥላ የያዘቻቸውን አምስት የሚሆኑ አንድ ላይ የታሰሩ አሳዎችን እያማታች ከብቶቹን ወደቤታቸው እንዲገቡ መንገዱን አስያዛቻቸው ወደ እሱ አመራች..ደርሳ  ከጎኑ ተቀመጠች፡፡እና ሳታስበው እንባ አውጥታ አብራው ማልቀስ ጀመረች..ገልመጥ ብሎ አያትና

‹‹አንቺ ደግሞ ምን ሆነሽ ነው?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ምንም አልሆንኩ ላግዝህ ብዬ ነው››

‹‹ምን ማለት ነው… በለቅሶ ማገዝ አለ እንዴ?››

‹‹ታዲያ በምን ላግዝህ?

‹‹በምንም .. ማንም ሊያግዘኝ አይችልም…››

‹‹እሺ ምን እንደሆንከ ንገረኝ?››

‹ምን ያደርግልሻል፤እዚህ እየጠበቅኩ ያለሁት አንቺ እስክትመጪ ነበር…ነገ ወይም ተነገወዲያ ልንሄድ ነው…..ጓደኛዬ ስለሆንሽ ልሰናበትሽ ነው›

ደንግጣ..‹‹እንዴ ወዴየት ነው ምትሄደው?››

‹‹ጊንር አካባቢ ወደሚገኝ ገጠር …አያቶቼ ጋር››

‹‹ለምን? ትምህርትስ?››

‹‹እኔም ወንድሞቼም አቋርጠን ነው የምንሄደው››

‹‹ቤተሰቡ ጠቅላላ ነው የሚሄደው እንዴ?››

‹‹አዎ… ከአባቴ በስተቀር…››

‹‹ከአባቴ በስተቀር ማለት ? አባትህስ ለምን?››

‹‹እሱ ሌላ ሚስት እዚህ አግብቷል…ጥሎን ከቤት ከወጣ ብዙ ቀን ሆነው ..ብንጠብቀው ብንጠብቀው ሊመጣ አልቻለም…እናቴ እናንተን የማኖርበት ገንዘብ የለኝም..ስራም ማግኘት ስለማልችል.ወደ ቤተሰቦቼ ይዣችሁ እሄዳለሁ ›› አለችኝ፡

‹‹እና በጣም አዝነሀል?›

‹‹በጣም እንጂ ..እኔ እዛ ገጠር ክረምት  ቤት ሲዘጋ ለተወሰነ ጊዜ መሄድ ነው ደስ የሚለኘ እንጂ ሁሌ እዛ መኖር አልፈልግም..እኔ እዚህ መኖር ነው የምፈልገው..አንቺ ትናፍቂኛለሽ›አላት እየነፈረቀ…፡፡

‹‹አንቺ ትንፋቂኛለሽ›› ሲላት ትኩር ብላ አይኖቹን አየቻቸው… ሀዘኑን ከውስጡ ማንበብ ስለቻለች…ልትገልፀው የማትችለው ስሜት ተሰማት… ከተቀመጠችበት ግንድ መቀመጫ ዘላ በመውረድ..‹‹ና እንሂድ›› አለችው…፡፡

‹‹ወደ የት?››

‹‹ወደ እናንተ ቤት››

‹‹ምን እንሰራለን …በጣም እኮ ነው የሚደብረው ..እማዬ የቤት እቃዎቻችንን ለጎረቤት እየሸጠች ነው..ይዘን የምንሄደውን ደግሞ እያሳሰረች ነው…››

‹‹እዚህ መቅረት ምትፈልግ ከሆነ ተከተለኝ›› አለችውና እርምጃዋን ወደእነሱ ቤት አስተካክላ እርምጃዋን ቀጠለች...እያቅማማ ተከተላት... እንደደረሱ እውነትም እቤቱ በኮተታ ኮተት ተሞልቶ ተተረማምሶል .. ሁለት ወንድሞቹ በሀዘን ኩርምትምት ብለው በቤቱ አንድ ጥግ ከላ አግዳሚ ወንበር ላይ ሲቀመጡ… እናትዬው ፈንጠር ብላ ኩርሲ ላይ ተቀምጣ ትተክዛለች፡፡

ኬድሮን ዝም ብላ በራፉን አልፋ ወደ ውስጥ ገባችና ወደ ድብአለ  እናት ተጠጋች… በእጇ ያንጠለጠለችውን አምስት አሳዎች ዘረጋችላት፡፡ሴትዬዋ ግራ ገብቷት አንዴ አሳዎቹን አንዴ   ኬድሮንን እያየች ለደቂቃዎች ቆየች፡፡

‹‹ተቀበይኝና ለልጆችሽ ጥበሺላቸው…ደግሞ ድብአለ  ወደ ጊንር መሄድ ሰለማይፈልግ እኔ እንድትሄዱ አልፈቅድላችሁም››
የድባአለ  እናት ፊቷ የቆመችው የ10 አመት ልጅ ዝም ብላ ልጅ ብትሆን ኖሮ በዚህ ንግግሯ በጥፊ ጆሮ ግንዷን አቅልጣ ከቤቷ  ገፍትራ ታባርራት ነበር….አረ የ10 አመት ብቻ ሳይሆን አንድ የ19 ዓመት የጎረቤት ልጅ እንዲህ ብስጭትጭት ባለችበት ጊዜ በዚህ አይነት ድፍረት  እየተውረገረገች መጥታ አሁን እሷ ያለችውን ብትላት ጉሮሮዋን አንቃ ከልጆቾ ጋር በመተባበርም ቢሆን  ንዴቷን እንደምትወጣበት እርግጠኛ ነች….ኬድሮንን ግን እንደዛ ልተደፍራት አልፈለገችም ..አላደረገችውም፡፡

‹‹ኬድርዬ ያልገባሽ ነገር አለ፡፡››

‹‹አስረጂኛ..››

ምን ብላ ትንገራት…. አንዴ እሷን አንዴ ልጆቹን  እያየች ግራ ስትጋባ…ልክ ከእኩያው ጋር ሚስጥር ማውራት እንደፈለገ ትልቅ ሰው‹‹ልጆችሸን ከቤት አስወጪያቸው.. ምን ይሰራሉ?›› አለቻት ፡፡

‹‹ልጆች ተነሱ ውጨ ተጫወቱ አንዴ ላውራት››ትዕዛዞን ተቀብላ አስተላለፈች፡፡

ድባአለን  ጨምሮ የሰባት አመትና የ10 አመት  ወንድሞቹ  እቤቱን ለእናታቸውና ለኬድሮን ጥለው ወጡ የእናቷ እኩያ የሆነችውን ትልቋን ሴትዬ ፊት ለፊት እያየቻት፡ኬድሮን እነሱ በለቀቁበት ቦታ ተቀመጠችና‹እሺ ንገሪኝ ›አለቻት፡፡
ምን መሰለሽ ኬድርዬ…እዚህ ሀገር ይዞኝ የመጣው ባለቤቴ ነው…አሁን ደግሞ እሱ ከእኛ ጋር የለም ፤ስለዚህ እዚህ ሆኜ ደግሞ ልጆቼን ማስተዳደር አልችልም››

‹‹የድባአለ  አባት ለምን ጥሎሽ ሄደ?››

‹‹እንዴት ብዬ ልንገርሽ የትልቅ ሰው ጉዳይ ነው፡፡››

‹‹ሌላ ሴት ወሽሞ ጥሎኝ ሄደ ላለማለት አፍረሽ ነው..የትልቅ ሰው ወሬ ምትይው?››

ሴትዬዋ አንገቷን በእፍረት አቀረቀረችና‹አዎ ምን ታርጊዋለሽ ..እኔ ልጆቼንና ትዳሬን እያልኩ ጉስቁል አልኩበትና  ጠላኝ መሰለኝ ሌላ ወዶ ሄደ››

‹‹ግን ብዙ ጊዜ ስትጨቀጭቂውና ስታበሳጪው አይቼለሁ››

‹‹ብጨቀጭቀውስ ለኑሮችን መሻሻል ብዬ ነው…እንዲህ ከሶስት ልጆቹ ጋር እርግፍ አድርጎ ጥሎኝ ይሄዳል፡፡15 ዓመት በትዳር ማሳለፍ እንዲህ ቀልድ ነው…?››

‹‹እኔ እንዲመለስ አደርጋለሁ…አንቺ ግን ፀባይሽን ታስተካክያለሽ… እርምጥምጥ የምትይውን ነገርም ታስተካክልሽ›› 

‹‹አይ ያከተመ ነገር እኮ ነው… እሺ አይልሽም እኔም ደግሞ እቃዎቼን ሁሉ እኮ ግማሹን ሸጬያለሁ፡፡››
እሱን ለእኔ ተይልኝ…እንቺ ወይም ባልሽ አሳዝናችሁኝ አይደለም… ለጓደኛዬ ለድብአለ  ብዬ ነው…
ብዙም ሳይመሳላት ‹‹ካልሽ እሺ ሞክሪ ›አለቻት፡፡

ቀጥታ ወደቤቷ ሄዳ እናቷን ካገኘችና ከብቶቹ ወደበረትና በጎቹንም ወደጉሮኗቸው መግባታቸውን ካረጋገጠች በኃላ ልክ አንድ ሰዓት ከሩብ አካባቢ ሹልክ ብላ ድብአለ  አባት ገብቶበታል ወደተባለው ቤት ነው ያመራችው…ስትሄድ ምን እንደምታደርግና እንዴት አድርጋ ከአዲሷ ሚስቱ አለያይታ ወደቤቱ እንዲመለስ እንደምታሳምነው ወይም እንደምታስገድደው ምንም አይነት እቅድ አልነበራትም፡፡
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ለሁለት ወራት ድምፅዋን አልሠማም፡፡ አልደወለችለትም፡፡ ምንም አይነት አዲስ ጽሁፍም አላከችለትም፡፡ እሷ ልታገኘው ካልፈለገች እሱ ሊያገኛት የሚችልበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ ይሄ ሁኔታ ሁሴንን እጅግ ሲያስጨንቀውና ሲያበሳጨው ነው የከረመው፡፡ ዛሬ ግን በሀሳብ የሚያባክነው ጊዜ አላገኘም፤ውጥረት ላይ ነው ያለው፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ በዋቤ ሸበሌ ሆቴል የሚስጥር የግጥምና የአጫጭር ልብ ወለድ መጽሐፍ ይመረቃል፡፡

ሁሴን፣ሠሎሞን እና ትዕንግርት ነገሮችን ሁሉ በታቀደላቸው ዕቅድ መሠረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከወዲህ ወዲያ ይሯሯጣሉ፡፡

‹‹አሁን ምን ቀረ?›› ሠሎሞን ነው የጠየቀው፡፡

‹‹ምንም ... የእንግዶቹ መምጣት ብቻ..፡፡›› ሁሴን መለሰ፡፡

‹‹የሚዲያ ሠዎችስ .. ያረፍዱ ይሆን?›

‹‹ኧረ ደርሰዋል...ሆቴል ሻይ ቡና እያሉ ናቸው፡፡››

‹‹በትክክልም መድረስ አለባቸው፡፡ ይሄን የመሠለ ግራ የገባው ታሪክ ለመዘገብ የማይጓጓ የወሬ ሠው የት ይገኛል ብለህ ነው?››ሰሎሞን ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹እስቲ ዛሬ እንኳን ስድብህን ዋጠው፡፡›› አለው ሁሴን እንደመበሳጨት ብሎ

<እንዴ  ቁጭ ብላችሁ ታወራላችሁ እንዴ......? እንግዶች እኮ መምጣት ጀምረዋል፡፡ ውጭ ናቸው›› ትንግርት ነች በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ እየገባች የምታወራው፡፡

‹‹በቃ የቀረን ነገር የለም ... ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡ ዘና የሚያደርጉን ሙዚቃኞች ከነ ሙዚቃ መሳሪያቸው መጥተዋል፡፡ ዝግጅቱን በንግግር የሚከፍቱልን የክብር እንግዳችን የደራሲን ማህበር ፕሬዘዳንትም በሠዓቱ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ሠጥተውናል፡፡
ለእድምተኞች ከመጽሐፍ በመቀንጨብ የሚያነቡ ሠዎችም ተመድበዋል፡፡ ያው እንደተነጋገርነው በመጀመሪያ አንቺ ታነቢያለሽ ሌላውን እኔ ጨምራለሁ፡፡ ይሄ ቀፈታም
ኢንጂነር እንደሆነ አይኖቹ ብር ላይ የሚገኝ ቁጥር እንጂ ፊደል ማንበብ ካቆሙ ዘመናት አልፈዋል፡፡ ስለዚህ የእሱ ኃላፊነት እንግዶች በስርዓት መስተናገዳቸውን መቆጣጠር ነው፡፡›› ንግግሩን ገታ አደረገና አይኖቹን ሠሎሞን ላይ ተክሎ ንግግሩን ቀጠለ ‹‹ደግሞ ዛሬ እንዴት ነው አለባበስህ? ሚስትህን ጥለህ ከቤት ስትኮበልል ወጣት የሆንክ መሰለህ
እንዴ?>>

‹‹ሰውዬ እንደውም ዛሬ ከዕድምተኞቹ ውስጥ አንዷን ምርጥ ካገኘሁ መጥበሴ አይቀርም፡፡›› አለው ሠሎሞን፡፡

‹‹ምን አልባት ከአስተናጋጆቹ መካከል ከሆነ እስማማለሁ፡፡ ዝግጅቱን ለመታደም ከሚመጡት ውስጥ ግን ላንተ ነፍስ የምትስማማ የምትኖር አይመስለኝም፡፡ ደራሲ ወይም ገጣሚ አፍቅረህ ልታብድ ነው...እስቲ በእኔ ይብቃ››ተሳሳቁ!!

‹‹ግን ዛሬም አትመጣም ማለት ነው?! >> ትንግርት ነበረች ጠያቂዋ፡፡ መልሱን ከሁሴን አንደበት ለመስማት በጉጉት ስሜት አይኖቿን እያቁለጨለጨች፡፡

‹‹በቃ ስለ እሷ እያወራችሁ ስሜቴን አታደፍርሱት፡፡ እንዲያውም ሠዓቱ ደርሷል በራፉን ክፈቱና እንግዶችን ወደ ውስጥ አስገቧቸው፡፡››

ሠሎሞን ተንደርድሮ በሩን ከፈተና ውጭ የተጠራቀሙትን እንግዶች ወደ ውስጥ እንዲገቡ ይጋብዛቸው ጀመር፡፡ ጋዜጠኞችም ከካሜራ ባለሞያቸው ጋር እየተንጋጉ ገቡ፡፡ በ3ዐ ደቂቃ ውስጥ ከተጠሩት ሠዎች
አብዛኞቹ ስለተገኙ ፕሮግራሙን ለማስጀመር ሁሴን ወደ መድረኩ ማይኩን በቀኝ እጁ የተወሰኑ ወረቀቶችንና በእለቱ ለምረቃ የተዘጋጀውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ በግራ እጁ ይዞ ወጣ፡፡መድረኩ ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ከሩቅ እንዲነበብ ታስቦ በባነር ላይ የተጻፈ ፅሁፍ ተለጥፏል፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡

የመፅሀፍ ምረቃ በዓል

የመፅሀፍ አይነት፦ የግጥምና አጫጭር ልቦለድ መድብል

ርዕስ፦ የጨረቃ ፍካት

ደራሲ፦ ምስጢር በለጠ

አሳታሚ፦ ፍካት ማተሚያ ቤት

የታተመበት ቀን፦ ሠኔ 2ዐ ቀን 2007 ዓ.ም.

ሁሴን ከአትሮኖሱ ጀርባ ቆሞ ጉሮሮውን ጠራረገና ንግግሩን ጀመረ፡፡ ከተለያዩ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ጣቢያ የመጡ ጋዜጠኞች ካሜራቸውንና መቅረፀ ድምጻቸውን በዙሪያው ቀሠሩ፡፡

‹‹ክቡራንና ክብርት የጥበብ አፍቃሪዎች

በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ከጥበብ ማዕዱ ለመቋደስና የደስታችን ተካፋይ
ለመሆን እዚህ ስለተገኛችሁ በደራሲዋ እና በራሴ ስም የከበረ ምስጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡በማስከተልም ስለደራሲዋ
አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮች መናገር እፈልጋለሁ›› መጽሀፉን አነሳና ወደ ታዳሚው
በማሳየት ንግግሩን ቀጠለ፡፡

‹‹ይሄ መጽሐፍ
ሠባት አጫጭር ልብ ወለድ እና ሠላሳ የተመረጡ ግጥሞች የተካተቱበት ባለ ሁለት መቶ ሃያ ገጽ መጽሐፍ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል አራቱ አጭር ልብ ወለዶች እና ሃያ የሚሆኑት ግጥሞች በተለያየ ጊዜ በፍኖተ ጥበብ ጋዜጣ ላይ ለህትመት የበቁና በአንባቢ
ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው፡፡ለዚህም
የጋዜጣው አንባቢ የሆናችሁ መመስከር ትችላላችሁ፡፡ ሌሎቹ ግን በደራሲዋ የቀረቡ ከዚህ በፊት ያልተነቡ አዳዲሶች ናቸው፡፡

የመሸጫ ዋጋው ሰላሳ ሁለት ብር ነው፡፡ ዋጋው ካለው የወረቀት ውድነትና ይሄን ተከትሎ አሳታሚ ድርጅቶች ከሚጠይቁት ዋጋ አንፃር ተሠልቶ የተተመነ ስለሆነ ተመጣጣኝ ነው ብለን እናስባለን፤ ስለ መጽሐፉ ይሄን ያህል ካልኩ ስለ ደራሲዋ ደግሞ ጥቂት ነገር ማለት ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ደራሲዋ አሁን በመሀከላችን... >> ንግግሩን አቋረጠና ወደ ውስጡ ትንፋሹን ደጋግሞ ሳበ፡፡ እንደ ማሳል አለና በተንቀረፈፈ ሁኔታ ንግግሩን ቀጠለ ፡፡

‹‹...አሁን በመሀከላችን የለችም፡፡ ማለቴ እዚህ ዝግጅት ላይ እንድትታደምና የድካሞን ውጤት፤ የዘራችውን ዘር ፍሬ እንድታጣጥም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም በአካል አላውቃትም፤ መኖሪያ ቤቷን፣ ስልኳን፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥሯን አላውቅም፡፡ ላውቅ ያልቻልኩትም እኔ ማወቅ ስላልፈለግኩ ሳይሆን እሷ እንዳውቅ ስላልፈለገች ነው፡፡››

ከእድምተኞች አካባቢ ጉምጉምታ በዛ፣ የጋዜጠኞች ጆሮ ይበልጥ ተቀሠረ፣ካሜራዎቻቸውን ከወዲያ ወዲህ በፍጥነት ማሽከርከር ቀጠሉ፡፡ ብዛት ያላቸው ሠዎች በተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልካቸው ሳይቀር ንግግሩንም ሆነ የዝግጅቱን ድባብ በተቻላቸው መጠን በመቅረፅ ላይ ናቸው፡፡‹‹... ያው እንዳልኳችሁ ምስጢር ከሁለት ዓመት ለበለጠ ጊዜ የፍኖት ጥበብ ጋዜጣ ቋሚ አምደኛ ነች፡፡ ጽሁፎችን የምትልከው በፖስታ ቤት በኩል ሲሆን አድራሻዋን ግን አትፅፍም፡፡ ጽሁፎቿ በጣም ማራኪ ብስለት ያልተለያቸውና ዘና የማድረግ ደረጃቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ዛሬም ድረስ የእሷ አድናቂ እንድሆን ተገድጄያለሁ፡፡ በነገራችን ላይ በግል ስልኬም ትደውልልኛለች፤ እውነቴን ነው የምላችሁ መፃፍ ብቻም ሳይሆን ማውራትም ትችልበታለች፡፡ የምትጠቀመው ስልክ የሕዝብ ነው አንድ ቀን ከልደታ፣ በሌላ ሳምንት
ከመገናኛ፣ ሲያሰኛት ከሳሪስ አካባቢ ባለ የሕዝብ ስልክ ነው የምትደውልልኝ፡፡ ከምታስቡት በላይ ግራ አጋቢ የሆነች ፍጡር ነች፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ ላገኛት እንደምፈልግ ነግሬያት ብማፀናትም ጥያቄዬን ልትቀበል አልቻለችም፡፡

በመጨረሻ እሷን ከተደበቀችበት ጉድጓድ እንዴት አድርጌ ለማውጣት እችላለሁ? ብዬ ሳስብ የፃፈቻቸውን ፅሁፎች የማሳተም ሃሳብ በአዕምሮዬ ተሠነቀረና አማከርኳት፤ ነገሩ ግን እንደገመትኩት አልሆነም፡፡ ጽሁፎቿን የማሳተም ፍላጎት እንደሌላትና እኔ ማሳተም ከፈለኩ ግን እንደማትቃወመኝ እናም ውክልናውንም እንደምትሠጠኝ ነግራኝ ከዛ አልፎ ግን ከእኔ ጋር ለመገናኘት ለጊዜው ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት አረዳችኝ፡፡ እንዳለችውም ውክልናውን በፖስታ ቤት ላከችልኝ..
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ማታ ቤት ገብታም ስለሴትዬዋ ማሰቧን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ወንድ ብትሆን "ፍቅር ያዘኝ እንዴ?ብላ ራሷን መጠራጠር ትጀምር ነበር...ሴትዬዋ የማሳጅ ቤት ባለቤት መሆኗን ከቢዝነስ ካርዷ ብትረዳም ‹‹የፈለገችኝ ለሌላ ስራ ቢሆንስ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት።

እንደምንም ራሷን   ተቆጣጠረችና አራት ቀን በመቆየት በአምስተኛው ቀን ደወለችላት፡፡

"ሳባ  እባላለሁ...በቀደም  ለታ  ቢዝነስ  ካርድሽን  ሰጥተሽኝ  ነበር..."ብላ.ቦታውንና ሁኔታውን ልትዘረዘርላት ስትጀምር አቋረጠቻት

"አውቄሻለሁ...ስለደወልሽ ደስ ብሎኛል..." የሚል መልስ ሰጠቻት
ትብለጥ፡

"አመሰግናለሁ"

"እሺ.ተገናኝተን.እናውራ፡

"ይቻላል"

"መቼ ይመችሻል?"

"ያው ያንቺን አላውቅም እንጂ እኔ ዛሬ እሁድ ስለሆነ  ይመቸኛል...ካልሆነ ግን በማንኛውም ቀን ከ11.30 በኃላ መሆን ይችላል።››

"ግድ የለም ይመቸኛል...ሰፈርሽ የት ነው፡፡"

"ላንቻ....ግሎባል አካባቢ፡፡"

‹‹በቃ ስምንት ሰዓት መኪና ልክልሻለሁ...ቁጥርሽን እሰጠዋለሁ… ይደውልልሻል።"
‹‹እረ  አያስፈልግም  ቦታውን  ንገሪኝና  በላዳ  መጣለሁ፡፡"አለቻት  ያልጠበቀችውን ነገር በመስማቷ ግራ ተጋብታ፡፡

"አይ እሱ  አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም...ቻው በቃ፡፡ ስምንት ሰአት ይመጣልሻል፡፡ በኃላ እንገናኝ።››ስልኩ ተዘጋ።

ይበልጥ ገረማት። ለእሷ እቤት  ድረስ  መኪና? መደመም  ውስጥ  የሚከት  ነው፡፡ቢሮዋ እንኳን ጉዳይ እንድታስፈፅም የሆነ ቦታ ሲልካት..አለቃዋ ቀብረር ብሎ‹‹እስከ እዛ በታክሲ ሄደሽ ..ከዛ በእግር ተሻግረሽ ወደዚህ ተጠምዝዘሽ ከዛ ሌላ ታክሲ ተሳፍረሽ....›› ብሎ ነው የሚያዛት። አሁን ግን መኪና ከሹፌር ጋር ለዛውም ቤቷ ድረስ?ለዛውም ለራሷ ጉዳይ፡፡

‹‹ይሄ  ነገር  የእውነት  ህይወቴን   የሚቀይር   አጋጣሚ   ይሆን   እንዴ?..›› ስትል አሰበችና ሰዓቷን ተመለከተች …5 ሰዓት ሆኗል።ፒጃማዋን አውልቃ ልብስ ቀየረችና ቦርሳዎን ይዛ አንድ ክፍል  ቤቷን  ቆልፋ  ግቢውን  ለቃ  ወጣች። ያመራችው እዛው ሰፈር ወደሚገኝ አንድ ፀጉር ቤት ነው።‹‹አዎ የተለየ ሰው ጋር ለተለየ አገጣሚ የተለየ ሆኜ መሄድ አለብኝ፡፡"ብላ ወስናለች፡፡ባላት ሶስት ሰዓት ወስጥ በተቻላት እና አቅሟ በፈቀደላት መጠን አምራና ዘንጣ የሚላክላትን ሹፌር መጠበቅ እንዳለባት ተሰምቷታል። ዝግጅቷን ጨርሳ 10  ደቂቃ  ያህል  እንኳን ሳታርፍ ነበር ስልኳ ያንጫረረው። ስልኳ እጇ ላይ ስለነበረ ፈጥና አነሳችው።

‹‹ሄሎ፡፡››

‹‹የእኔ እመቤት ጤና ይስጥልኝ፡፡ ደምሳሽ እባላለሁ፤አንቺን ወደ ቤት ለመውሰድ ተልኬ ነበር?››

‹‹ወደ ቤት?›› አለች ደንግጣ...የደነገጠችበት ምክንያት ፈፅሞ ቤት  የሚባል በምናቧ ስላልነበረ ነው... የጠበቀችው ሆቴል ወይም ካፌ..ወይም የሆነ  መዝናኛ ቦታ ነበር፡፡"

ደዋዩ  ፀጥ  ስትልበት  ግራ  ተጋብቶ "ምነው  እመቤቴ  ችግር  አለ.እንዴ?"ሲል ጠየቃት።
"እረ ምንም ችግር የለም...በቃ እየወጣሁ ነው"
"ግሎባል ጋር ቆሚያለሁ አቅጣጫውን ንገሪኝና ልቅረብልሽ"

"ቅርብ ነኝ ...እዛው እመጣለሁ"ብላ ስልኩን አቋረጠችና ቤቱን በመዝጋት ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ እንግዳና የማይገመቱ ነገሮች ናቸው እየገጠሟት የነበረው፡፡ ደግሞ የሹፌሩ ትህትና "ማን ነች ብላ ብትነግረው ነው እንዲህ እመቤቴ እያለ ቅንጥስጥስ የሚለው?" በማለት እያጉረመረመች ዋናው አስፓልት ላይ ወጣች። ወደ ግሎባል ተጠጋች፡፡ ወዲህ ማዶም ሆነ ወዲያ ማዶ ምንም መኪና አይታያትም...ስልኳን አወጣችና ደወለች፤ከአጠገቧ ከ5 ሜትር ርቀት አካባቢ በእጅ ምልክት ሲሰጣት አየችው፡፡ሰውዬውን ከዚህ በፊት አይታዋለች፤ በቀደም ከሴትዬዋ ጋር የእሷ ጋርድ ሆኖ ቢሮዋ ድረስ መጥቶ ነበር፡፡ የመኪና በራፍ ይዞ ቆሟል፡፡መጥታ እስክትገባ እየጠበቀ ነው፡፡ ትህትናው ከሰውነት ግዝፈቱና ከመወጣጠሩ ጋር ፈፅሞ አብሮ የማይሄድ ነው የሆነባት።መኪናዋ እጅግ ዘመናዊ ከመሆኗ የተነሳ ከዚህ በፊት እንኳን ልትቀመጥበት በአስፓልቱ ላይ እራሱ ሲነዳ የምታየው በጣም አልፎ አልፎ ነው።ለዛ ነው ገና ከቤቷ ቅያስ ወጥታ አስፓልቱን እንደያዘች አይኗ የገባው የመጀመሪያው መኪና ቢሆንም  ለእኔ የተላከ ይሆናል ብላ ስላልገመተች ትኩረት ያልሰጠቸው፡፡ እየፈለገች የነበረው ሌላ ቪታራ ወይም ቪትስ አይነት መኪና ነበር።

በደመነፍስ እየተንሳፈፈች ሄደችና ተጠጋችው፡፡በአንድ እጅ የመኪናውን በራፍ እንደያዘ ጎንበስ ብሎ በሌላ እጅ ወደውስጥ እንድትገባ አመለከታት.. ገባች። የመኪናው መቀመጫ ራሱ የተለየ ነው። ሁሉ ነገሩ የተሟላለት የሀብታም ወንደላጤ ሳሎን ነው የሚመስለው፡፡ ዙሪያውን የተገጠገጠው በሚያብረቀርቅ ቡኒ ቆዳ የተለበጠው ምቹ መቀመጫ ፊት ለፊት የሚታየው አነስተኛ ፍሪጅ፤ ከዛ ከፍ ብሎ ዘመነኛ የፈረንጅ ክሊፕ እያጫወተ ያለ ቲቪ...ሁሉም  ያምራል።‹‹አሁን ይሄን ያለው ሰው ቤት ምን ያደርግለታል?››። ስትል  በውስጧ እያልጎመጎመች ፈራ ተባ በሚል ስሜት ኮርነር ላይ ሄደችና ተቀመጠች።

ሹፌሩም ‹‹እመቤቴ የሚጠጣ ነገር ከፈለግሽ ፍሪጅ ውስጥ አለልሽ ፤ሌላ የሚያስፈልግ ነገር ካለ ጠይቂኝ›› አለና በራፉን ዘግቶ በፊት ለፊት ዞሮ ሄደና የሹፌሩን ቦታ ይዞ ማሽከርከር ጀመረ፡፡...ትንሽ  እንደተጓዙ  በእሷ  እና  በእሱ መካከል  ያለውን  ክፍተት  በተንሸራታች ጥቁር መስታወት  ዘጋው። ተንፈስ  አለች.. የተሻለ ነፃነት ተሰማት፡፡ ከ20 ደቂቃ በሀሳብ የሚያናውዝ ጉዞ በኋላ ካዛንቺስ ደረሱ፡፡ ከስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ቢሮ ቀጥሎ ባለው ቅያስ ተጠምዝዞ ገባና የተወሰነ ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ አንድ ግዙፍ ግቢ ውስጥ ይዟት በመግባት ጋራዥ  አቁሞ በፍጥነት ዞሮ በመምጣት በክብር እንዳስገባት በክብር እጇን ይዞ አወረዳት፡፡ እየመራት ወደ ግዙፉ ቪላ ቤት ይዟት ገባ። በእውነት መኖሪያ  ቤት  ሳይሆን የነገስታት የእልፍኝ አዳራሽ  ነው ሚመስለው፡፡ድባቡ ያስፈራል፤ በራፉን አልፈው ወደውስጥ አንድ ሶስት እርምጃ ዘልቀው እንደገቡ  የሆኑ  ደልደል  ያለች ነጭ ሽርጥ ያደረገች ሴትዬ  ከግራ  በኩል  ካለው  ኮሪደር  ድንገት ወጣችና.

.."እመቤቴ እንኳንም በሰላም መጣሽ"በሚል ቃል የታጀበ በሞቀ ፈገግታ ካመጣት ሹፌር ተቀብላት ወደ ውስጥ ይዛት ዘለቀች፡፡ሹፌሩ ቀኝ  ኃላ ዞሮ ተመልሶ ወጣ፡፡

ሴትዬዋ እየመራች ወስዳ ግዙፉ እና ባለግርማ ሞገሱ ሶፋ ላይ እንድትቀመጥ ካደረገች በኋላ"የሚጠጣ ምን ላምጣ?"ስትል ከአንገቷ ጎንበስ ብላ በትህትና ጠየቀቻት፡፡

‹‹አይ ግድ የለም…ምንም አያስፈልግም፡፡››ስትል መለሰችላት፡፡

‹‹አንድ ነገርማ ያዢ"

‹‹እንግዲያው ውሀ ይሁንልኝ›› አለች።እውነት ውሀ ጠምቷት ሳይሆን በህይወቷ እንዲህ አይነት ግራ የገባው ነገር ገጥሟት ስለማያውቅ በደመነፍስ  ነው ያዘዘችው።
//
ከ10 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ ሴትዬዋ በቀደም ካየቻት የተለየች ሆና መጣች፡፡ የሆነ የደቡብ አፍሪካ ወይም የታንዛኒያ የባህል አምባሳደር ነው የምትመስለው…ከላይ ከሻሽ አስተሳሰሯ እስከ ተጫማችው ጫማ ልዩ ኦሪጅናል አፍሪካዊ መስላ ነው የጠበቀቻት፡፡ ያው የሴትየዋ አለባበስ ለሳባ አዲስ ሆነባት እንጂ ለእሷ የተለመደና በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን የምትጠቀምበት ነው፡፡፡የሞቀና የጋለ ሰላምታ ሰጥታት ከተቀመጠችበት ሶፋ ላይ ልክ ለረጅም አመት እንደምታውቃት ታላቅ እህቷ አንድ እጇን ትከሻዋ ላይ ጥላ በፍቅርና በፈገግታ   እያወራቻት ወደሚቀጥለው ክፍል
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

አማዞን ደን ኮሎንቢያ ግዛት
ጫካውን እየሰነጠቁ ከአውሬውና ከነፋሳት ጋር እየተጋፉ መጓዝ በጀመሩ አራት ቀን ሆኗቸዋል፡
በጉዞቸው ከዛፍ ዛፍ ሲንጠለጠል አንድ ገራሚ እንስሳ አየች፡፡ትንሽ ነው፡፡ ድመት ነው የሚመስለው፡፡ ግን ጸጉር የለበሰ በመሆኑ ከመጠኑ ገዝፎ እንዲታይ እረድቶታል፡፡ ዝንጀሮም አንበሳም ይመስላል፡፡ከዚህ በፊት በምስል ላይ ፎቶውን እንኳን አይታ አታውቅም፡፡
‹‹ምንድነው ይሄ እንስሳት?››ቁራኛዋን ካርሎስን ጠየቀችው፡፡
‹‹እ ታማሪን ወይም ሮሳሊያ ይባላል፡፡ወይም በቀላሉ ወርቃማው አንበሳ ይሉታል፡፡››

‹‹አዎ እውነትም ወርቃማው አንበሳ፡፡ፀጉሩ እኮ ወርቅ መሳይና አብረቅራቂ ነው…ትክክለኛ ስሙ ይሄኛው ነው፡፡››
‹‹አዎ ዝርያው የዝንጀሮ ቢሆንም እንደምታይው ግን አንበሳ ነው የሚመስለው፡፡የዚህ ፕሪሜት ልዩ ቀለም ምናልባትም በጠንካራ የፀሐይ ብርሃን ጥምረት እና በአመጋገቡ ውስጥ በሚገኙ የካሮቲኖይዶች ብዛት ላይ የተመሠረተ ነው የሚል መላምት አለ።እንደምታይው አስደናቂ ገጽታ አለው: ወፍራም፤ ለስላሳ፤ ደማቅ ቀይ ፀጉር፤እንዲሁም ጥቁር ፊት እና ትልቅ ቡናማ አይኖች ያሉት አስደማሚ ፍጡር ነው››
‹‹ስላየሁት ደስ ብሎኛል፡፡የማልሞት ቢሆን ኖሮ እዚህ መጥቼ ስላየሁት እያንዳንዳንዱ ድንቅ እና አስደሳች ነገር… ስለእንስሳቱና ስለጥቅጥቁ ዳን… ስለሚንዠቀዠቀው የአማዞን ወንዝ ለወንድሜም ለጓደኞቼም በደስታ እንግራቸው ነበር..ግን ምን ዋጋ አለው….››ከገባችበት ጊዜያዊ የደስታ ስሜት ወጣችና ሀዘን ውስጥ ገባች፡፡
‹‹አይዞሽ …እሰክአሁን በህይወት አለሽ ..ለጊዜው ያ በቂ ነው፡፡››አላት፡፡

‹‹እንዳልክ ይሁንልህ››አለችውና ዝምታ ውስጥ ገባች፡፡
እኩለ ቀን ላይ ኣማዞን ወንዝን ታካ የተመሰረተች የደቡብ ኮለምቢያ የጠረፍ ከተማ ከሆነችውና 35 ሺ ኑዋሪዎች ከሚኖሩባት ላቲሲያ ከተማ ደረሱ፡፡ይህቺ ከታማ ሶስት ሀገሮች ማለት ፔሩ ኮሎቢያን ብራዚል የሚገናኙባት ነጥብ ከሆነችው ትሬስ ፎረንቴራስ ትንሽ ወደላይ ፈቅ ብላ ምትገኝ በዓሳ ምርቷ የታወቀች እጥር ምጥን ያለች ከተማ ነች፡፡የኮሎምቢያ መንግስት ግዙፍ የሆነ የዓሳ ምርቱን ከአካባቢው እየሰበሰበ በጀልባ በመጫን ወደ ማአከላዊ የሀገሪቱ ስፋራዎች የሚጫንባት ወሳኝ ከተማ ነች፡፡ከታማዋን በሩቅ ሲያዮት እና ጉዞቸውንም በዛ አቅጣጫ ሲያቀና ቀጥታ ወደከታማው ዘልቀው ሚገቡ መስሏት ተደስታ ነበር፡፡የዛም ምክንያቱ ህዝብ ያለበትና የመንግስት ተቋማት ሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ላይ ከደረሰች በተቻላት መጠን ለማምለጠ ትሞክራለች፤ያ ከሆነ ደግሞ ጥረቷ የመሳካት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ስሌቱን ስለሰራች ነው፡፡ይሁን እንጂ አጋቾቻ
የገመተቻቸውን ያህል ጥንቃቄ አልባ አልነበሩም፤በዛም ምክንያት ወደከታማዋ አልገቡም፡፡ይልቅስ ከተማዋን በቅርብ ርቀት ታካ አማዞን ጉያ ውስጥ ተወሽቃ ከምትገኝ ነባር ጎሳዎች ወደሚኖሩባት ወደአንድ መንደር ነው ጎራ ያሉት፡፡

‹‹እርግጠኛ ነኝ ይሄ የመጨረሻ የጉዞ መዳረሻችን ነው፡፡››ካርሎስን ነው የምትጠይቀው፡፡
‹‹አይመስለኝም..ግን የተወሰኑ ቀናትን እዚህ የምናርፍ ይመስለኛል››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹በሩቅ ወደምትታየው ከተማ ምንገባ መስሎኝ ነበር››
‹‹እ..ወደ ላቲሲያ ማለትሽ ነው..ወደእዛ አለመግባታችን ጥሩ ነው…ለአንቺ ምንም ሚጠቅም ነገር አይገኝበትም…ከኑዋሪዎቹ ከግማሽ በላይ የእኛ ሰውዬ ሰዎች ናቸው››

ተስፋ ቆረጠችና… ዝም አለች፡፡..የቡድኑ ሰዎችን ለመቀበል ሶስት የሆኑ የመንደሩ ሰዎች መጡና አወሯቸው፡፡ ከተወሰኑት ጋር የሞቀ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ አንድ ወለሉ በአየር ላይ የተንጠለለ በስሩ ውሀ የሞላበት በጣውላ እርብራብ የተሰራ የሳር ክዳን ቤት ከፊት ለፊታቸው ይታያል፡፡ወደዛው መጓዝ ጀመሩ፡፡ቤቱ ሰፋ ያለ ግን ደግሞ እቃ አልባ ነበር፡፡ቁራኛዋ ሰንሰለቱን ከላዩ ላይ አላቀቀና ለብቻዋ ተወላት፡፡ሁሉም በተርታ መቀመጫ ይዘው ተቀመጡ…ምግብ ቀረበላቸው፡፡ ሁሉም ተርበው ስለነበር የምግብ አይነቱ ሳያስጨንቃቸው በፍቅር በሉ ፡፡የሚጠጣ ነገር ቀረበላቸው…ጠንከር ያለ የአልኮል መጠጥ ነው፡፡እሷ መጠጣት አልፈቀደችም፡፡፡ውሀ ቀረበላት፤እሱን ጠጣች፡፡የምግብ ስርአቱ ካለቀ በኃላ እሷን እዛው ቤት ውስጥ ተዋትና ከውጭ ቆልፈውባት ወጥተው ሄዱ፡፡

ቤቱን ክፍት ትተውት ቢሄዱም ወደምትሄድበት ቦታ የላትም፡፡መቼስ በቃ ተመልሰሽ ሂጂ ቢሏት እንኳን የአራት ቀን መንገድ በእንደዛ አይነት ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ከጇጓርና ከአናኮንዳ ጋር እየታገለች…አረንጎዴ መርዛማ እንቁራሪቶችና ሰውነት ላይ ከተጣበቁ ማይላቀቁ ጉንዳኖችን ተቋቁማ ወደኃላ ተመልሳ ፔሩ ገባለው የሚል ግምት የላትም፡፡እርግጥ ወደፊት ቀጥላ በአምስት ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ከምትታየው ላቲሲያ ከተማ ልትሄድ ትችላለች፡፡ግን ሙሉ ከተማው የራሳቸው የጋንግስተሮቹ ግዛት እንደሆነ ካርሎስ በግልፅ ነግሯታል...ምክሩን ችላ ብላ ብትሄድና ምንም አይነት የመንግስት ተቋም ሆነ የሚታደጋት ተቋም በቦታው ባይኖርስ…?፡፡ጠቅለል አድርጋ ስታስበው ከዚህ አሁን ካለችበት ስፍራ አምልጦ ነፃ መውጣት የማይተገበር ምኞት ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
ደክሞት ስለነበረ እቤቱ ውስጥ ያለች አንድ መተኛ ፍራሽ ነገር ላይ ሄዳ ጋደም አለች፡፡፡ሰውነቷን በቀላሉ እንዳሳረፈችው አእምሮዋን ልታሳርፍ አልቻለችም፡፡ በእነዚህ ሰዎች እጅ ከገባች ቀን ጀምሮ እንዲህ ለብቻዋ በመሆን ጥቂት ሳዕታትን ባገኘች ቁጥር ወዲያውኑ ሀሳቧ በሮ ወንድሟ ጋ ነው የሚሄደው፡፡የትናንት ትዝታዋ ጋር ነው የሚለጠፈው፡፡ናኦል ይሄኔ ለአራት ቀን ድምፆ ሲጠፈበት እና ስልኳም አልሰራ ሲለው የሚያደርገው ጠፍቶት መስሪያ ቤቷ ሄዶ እህቴን ውለዱ እያለ እያስጨነቃቸው አንደሚሆን ገመተች..ብቻ በዛ ችኩል ባህሪው የሆነ ሰውን ውለዷት ብሎ አፍንጫ እንዳይሰብር ነው የሰጋችው፡፡ምን አልባትም ምስራቅ ጋር ሊሄድ እንደሚችል ገመተች፡፡እንዲህ አይነት ጭንቅ ውስጥ ሲገባ ከምስራቅ ቀድሞ ወደአእምሮ የሚመጣ ሌላ የተሻለ የሚቀርባቸውና የሚረዳቸው ሰው እንደሌለ ታውቃለች፡፡እሷም በእሱ ቦታ ብትሆን እንደዛ ነው የምታደርገው፡፡

ከምስራቅ ጋር በወዳጅነት መቀራረብ ብቻ ሳይሆን የስራ ባለደረባም ሆነው እንደሀለቃና ምንዝር ለረጅም አመት ሰርተዋል፡፡ለዛውም በሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት፡፡እርግጥ እሷም ሆነች ወንድሟ ቀጥታ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ተወዳድረው አይደለም የተቀጠሩት፡፡በወቅቱ ለእዛ የሚያበቃ እድሜ ላይም ሆነ ሁኔታ ላይ አልነበሩም፡፡ ..የእዛ መስሪያ ቤት አባል የሆኑት በእሷ በኩል ተመልምለው ..በእሷ ጥረት ወደስልጠና እንዲገቡ ተደርገው…በእሷ በኩል ተልዕኮ እየተሰጣቸው ነው፡፡ከዛ ብዙ ብዙ የሚባል ተልዕኮዎችን ተወጥተዋል…ለሀገር የሚጠቅሙ አንዳንዴም የተሳሳቱ ሰራዎችን ሰርተዋል፡፡ ያኔ እዛ በረንዳ ላይ ረዳት አልባ በነበሩበት ጊዜ ካገኘቻቸው በኋላ እንዴት እንደመለመለቻቸው ትዝ አላት፡፡
ኢትዬጵያ/አዲስ አበባ
አንድ ቀን አስራሁለተኛ አመታቸው ላይ ከምስራቅ ጋር በተዋወቁ በሁለተኛው ቀን በየእለቱ ለደምበኞች ጫት የማመላለስ ስራ ሰርተው ከጨረሱ በኃላ ምስራቅ እመጣለሁ ብላቸው ስለነበረች ቦታቸው ላይ ቁጭ ብለው እየጠበቋት ነበር፡፡ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ ምስራቅ እንዳለችው መጣች፡፡ ከመቀመጫቸው ተነስተው በፈገግታ ተቀበሏት፡፡ይዛ የሄደችው አንድ ፔስታል ቢሆንም አሁን ግን ሌላ አንድ ጥብሰቅ ያለ እቃ የታጨቀበት ፔስታል ይዛ መጥታለች፡፡
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ይህቺን ፀሀፊ ልጅ ወዶታል…እሷ እራሷ የመጀመሪያ ደንበኛው ከመሆኗም በላይ ሌላ ደንበኛ አገኝታለታለች፡፡ስልኩን አወጣና ደወለ……አስቴር ጋር…

‹‹እሺ ወንድሜ ደህና ነህ?››

‹‹አለሁልሽ…የላክሻት ልጅ መታለች ልልሽ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ነው …ተስማማችሁ?››

‹‹አዎ ጎበዝ ልጅ ትመስላለች››

‹‹ጎበዝ?››

‹‹አዎ ምነው?››

‹‹አይ በአንድ ቀን እንዴት ጎበዝ መሆኗን አወቅክ ?ብዬ ገርሞኝ ነዋ››

‹‹ማለቴ እንዲሁ  ሳያት ተግባቢና ቀልጣፍ ነገር ነች ልልሽ ነው››

‹‹ወንድሜ ፍቅር እንዳይዝህና እንዳትጎዳብኝ…ልጅቷ ፍቀረኛ አላት››

‹‹አይዞሽ አታስቢ አውቃለው፣በዛ ላይ እኔ ማፈቀሪያ ጭንቅላቴ የተበላሸብኝ ሰው ነኝ….››

‹‹ምኑ ነው ምታውቀው?››

‹‹እንዳላት ነዋ››

‹‹ከምኔው?››

‹‹ውይ ኪያ ደግሞ ….በቃ ቻው ማታ ቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ወንድሜ››በተንከትካች ሳቅ አጅባ ስልኩን ዘጋችው፡፡

////
ወላጇቾ ብቻ ሳይሆኑ ያደገችበትና የእድሜዋን ግማሽ የኖረችበት እቤቷም ጭምር ናፈቃት‹‹ ቤት ማለት..ግን ምን ማለት ነው?ስትል እራሷን ጠየቀችና መልሱን ከአእምሮዋ ውስጥ በርብራ ለማግኘት አይኖቾን ጨፍና ማሰላሰል ጀመረች

‹‹አዎ እቤት ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የሚታነፅ የሰው ልጅ መጠለያ ነው።ያንን ህንፃ ከመጠለያነት ወደ ቤትነት የሚቀይረው ግን የታነፀበት ማቴሪያል ጥራትና ውበት አይደለም...ውስጡ ያሉት  ዘመናዊ የቤት እቃዎች እና ውድነትም አይደለም። ህንፃው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነትና የፍቅር ትስስር መጠን ነው ህንፃውን እቤት የሚያደርገው።ለዚህ ነው ከኖርኩበት የተንጣለለ ቪላ ይልቅ አሁን እየኖርኩበት ያለሁት ባለ ሁለት ክፍል ጎስቋላ ቤት የተሻለ የሚሞቀውና የሚደምቀው
››መልሱን ለራሷ ሰጠች፡፡ ቀኑን እንዲሁ በሀሳብና በትካዜ ጊዜውን ብታሳልፍም ሲመሽ ግን ሁሉ ነገር የተለየ ሆነ፡፡

ማታ የቤተሰቡ አባል ጠቅላላ ተሰብስበው በሞቅ ደስታ ከወትሮ በተለየ ድግስ መሰል እራት ቀርቦ በመጎራረስ ከበሉና ቡናም ተጠጥቶ ከተነሳ በኃላ በፀሎት ሽንት ቤት ለመሄድ እንድምትፈልግ ለለሊሴ ነገረቻት…ያሰበችው እሷ ደግፋ እንድትወስዳት ነበር…በተቀራራቢ እድሜ ስለሚገኙ እቤት ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ እሷን ማዘዝ ወይም ትብብር መጠየቅ ቀላል ይላታል፡ ….ለሊሴ ግን እንዳሰበችው አላደረገችም….
‹‹ወንድሜ በፀሎትን ሽንት ቤት ትወስዳታላህ?››ብላ ስትጠይቀው ክው ነበር ያለችው….እሱ አንደበት አውጥቶ ፍቃደኝነቱን ሳይናገር በቀጥታ ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳና ወደእሷ በመሄድ ልክ ትናንት ለሊት እንዳደረገው ከስር ሰቅስቆ ልክ እንደህፃን ልጅ አቀፋት….እንዲህ አይነት ሁኔታ በህይወቷ ገጥሞት ስለማያውቅ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እፍረትም ተሰማት…‹‹.ወላጆቹ እንዲህ ሲያቅፈኝ ምን ይላሉ ?››የሚለው ሀሳብ አእምሮዋ ተሰነቀረና ያንን ለማጣራት እይታዋን በቤቱ ዙሪያ ስትሽከረከር ሁሉም በራሳቸው ጫወታ ተመስጠው እርስ በርስ እያወሩ እየተሳሳቁ ነው……አንከብክቦ እንዳቀፋት ይዟት ወጣ
..ቀጥታ ሽንት ቤት ወሰዳና ወደውስጥ አስገብቶ አቆማት…ልክ እንደሌሊቱ ውሀ በሀይላንድ ከቧንቧው ቀድቶ አመጣላትና የሽንት ቤቱን መጋረጃ ወደታች መልሶ ‹‹ስትጨርሺ ጥሪኝ
››ብሎ ከአካባቢው ዞር አለ፡፡

የሽንት ቤት ጣጣዋን ከጨረሰች በኋላ ቀጥታ ወደቤት አይደለም ይዞት የገባው፡፡ልክ እንደለሊቱ ወንበር አመቻችቶ ስለነበር ተሸክሞ ወስዶ አስቀመጣት….‹‹ቀኑን ሙሉ ተኝተሸ ስለዋልሽ አሁን ትንሽ ንፍስ ይንካሽ››

‹‹አዎ ትክክል ነህ፣በዛ ላይ ጨረቃዋም ናፍቃኝ ነበር፡፡››
እሱም ለራሱ መቀመጫ አምቻችቶ ከፊት ለፊቷ እየተቀመጠ‹‹ከጨራቃዋ ጋር ወዳጅ ናችሁ እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አዎ ለዛውም የእድሜ ልክ››

‹‹ያን ያህል ብቸኛ ነሽ ማለት ነው?››

‹‹እንዴት ከጨረቃ ጋር ለመወዳጀጀት ብቸኛ መሆን የግድ ነው እንዴ?››

‹‹አይ የግድ ባይሆንም ከልምዴ ስነሳ ብዙውን ጊዜ ከጨረቃዋ ጋር ለረጅም ጊዜ የማውጋት ልምድ ያላችው እንቅልፍ አልባ ብቸኛ ሰዎች ናቸው……በተለይ በፍቅር የተሰበሩ››

‹‹እንዴ በፍቅር የተሰበሩ ነው ያልከው..አይ እንደዛ እንኳን አይደለም…..ባይሆን እንዳልከው ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ በሚፈጠር ብቸኝነት ብንለው የተሻለ ነው..የፍቅር ጉዳይማ ቢሆን በምን እድሌ..ፍቅር እኮ በጣም ምርጥ ነገር ነው፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ… ፍቅር በጣም ወሳኝ ስሜት ነው….አንድ ሰው ሩሚን ‹‹ፍቅር ምንድነው?››ብሎ ጠየቀ።ሩሚም ..‹‹ፍቅር ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጉሙን ልታውቅ የምትችለው ውስጡ መጥፋት ስትችል ነው።›› ብሎ መለሰለት…..፡፡

‹‹አዎ ትክክለኛ አባባል ይመስለኛል….ፍቅር የምትተነትነውና የምታወራው ነገር አይደለም፣ፍቅር ኖረህ የምታጣጥመው የተቀደሰ ስሜት ነው….በፍቅር መጥፋት ጥሩ አባባል ነው››

‹‹አይ ጥሩ…ለማንኛውም ለደቂቃም ቢሆን እስቲ ከጨረቃዋ ጋር ብቻችሁን ልተዋችሁ…. መጣሁ›› ብሎ ተነስቶ ወደቤት ገባ..እሷ አይኖቾን ወደላይ አንጋጠጠች…ሰማዩ ጥርት ብሎ ይታያል ፡፡ጨረቃዋ ሙሉ ክብ ሆና ደፍናለች..ዙሪያዋን የተበተኑና ከዋክብቶች ብልጭ ድርግም እያሉ ይታያሉ…አናትና አባቷ ትዝ አሏት..ይሄኔ የእሷን መጥፋት ምክንያት በማድረግ የመጨረሻውን ጥል እየተጣሉና የመጨረሻ የተባለውን አንጀት በጣሽ ስድብ
እየተደሰዳደብ እንደሆነ በምናቧ አሰበችና ሙሉ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለባት..ሰውነቷ ሲሸማቀቅ ደግሞ የእግሯ ሆነ የፊቷ ጥዝጣዜ ህመም ተቀሰቀሰባት….
ድንገት የሰማችው ድምፅ ነው ከሀሳቧ ያባነናት…..ያልገመተችውን ነገር ነው እያየች ያለችው..ፊራኦል ፊት ለፊቷ ቅድም የነበረበት ቦታ ቁጭ ብሎ ክራር እየከረከረ የሙሀመድ አህመድን የትዝታ ሙዚቃ ያንቆረቁራል….ፍዝዝ ብላ በፍፁም ተመስጦ ታዳምጠው ጀመር፡፡
ስንቱን አስታወስኩት…ስንቱን አስብኩት ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት
አንዴ በመከራ …አንዴ በደስታዬ ስንቱን ያሳየኛል ..ይሄ ትዝታዬ

በድምፁ ድንዝዝ ብላ ጠፋች………… የትናንቱ ፍቅር ….ጣሙ ቁም ነገሩ ምነው ያስተዋሉት ያዩት በነገሩ
ሁሉም እንደገና ኑሮን ቢያሰላስል አይገኝም ጊዜ ያኔን የሚመስል፡፡

ዘፈኑን ሲጨርስ‹‹አንተ..አንድ ሺ አመት በዚህ ምድር ላይ ኖረህ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ያለውን ጊዜ ናፍቀህ የምትተክዝ እድሜ ጠገብ አዛውንት ነው የምትመስለው፡፡››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡

‹‹ያን ያህል?››

‹‹አዎ …ድምፅህ በጣም ግሩም ነው….ሙዚቃ ትሰራለህ እንዴ?››

‹‹አይ ያን ያህል እንኳን ሰራለሁ ማለት አልችልም …በፊት በፊት ቀበሌ ኪነት ከጓደኞቼ ጋር እሞክር ነበር አሁን ከህይወት ሩጫ ጋር አብሮ አልሄድ አለኝና ተውኩት፣እንዲህ አንደዛሬው ጨረቃዋ ሙሉ ስትሆን እንዲህ እቀመጥና ለእሷ አዜምለታለው፡፡››

‹‹እንዴ..ለእኔ የዘፈንክልኝ መስሎኝ ውስጤ በደስታ ተፍነክንኮ ነበር ..ለካ ለጨረቃዋ የተዘፈነውን ዘፈን ነው ሳይፈቀድልኝ የሰማሁት…..››

‹‹አይ እንደዛ አንኳን ለማለት አልችልም…የዛሬው ዘፈን ቀጥታ ላንቺ ነው..ምስጋናና ይቅርታ ለመጠየቅ፡ ብዬ ነው የዘፈንኩት፡፡››

‹‹አልገባኝም..ይቅርታውስ ለምን ?ምስጋናውስ?፡፡››

‹‹ይቅርታው ገና ስትመጪ ጀምሮ በሙሉ ልቤ ስላልተቀበልኩሽና ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ እንደሸክም ስለቆጠርኩሽ…ምስጋናው ዛሬ እናቴንም ሆና መላ ቤተሰብን አንበሽብሸሽ በማስደሰትሽ…..››
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

"አንች ጠጭ ጠጭ ምንም አይልሽም ብለሽኝ አሁን እኮ አዞረኝ" አለች፡፡ ለጓደኛዋ መቅደስ፡፡

"አንዱን ቢራ ጨረሽው እንዴ? ትገርሚያለሽ እንደለስላሳ ነው ስልሽ እንደለስላሳ ጨለጥሽው፡፡ በይ አሁን ቀስ ብለሽ አንድ ድገሚና ከዚያ በኋላ ይበቃሻል፡፡ ለነገሩ ቢራ አንድ ስለማይጠጣ ነው እንጅ በአንድ ቢበቃሽ ጥሩ ነበር፡፡

"አሁን አመመኝ እያልኩሽ ድገሚና ጠጭ ትይኛለሽ ? ብላ ብትኮሳተርም መድገሟ አልቀረም ሁለተኛ ቢራዋን አስከፈተች፡፡

በስካር መንፈስ ምሽቱ ወደ ቀን ተቀይሮበታል፡፡ አይመሽም እንዴ? ሆቴሉ አይዘጋም? ይላል ፤ ተመስን በውስጡ ፡፡

"ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝተህ ታውቃለህ"? እንዴ አለው ያሬድ፡፡

"ከሴት ጋር መተኛት አይደለም ለመተኛትም አውርቼ አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን ብተኛ ምን እሆናለሁ፡፡

"እና የትኛዋ ትሻልሃለች"?፡፡

"የሽሃረግ ትሻለኛለች ፤ እሽ ካለች፡፡

"እሽ ፤ እንጠይቃታለን ግን እንደ ገጠር ሴት ዝም ብለው እሽ አይሉም፡፡ ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡

"ለብር ችግር የለም፡፡ ብቻ እሽ አሰኝልኝ ፡፡

ያሬድ መቅደስን ለብቻዋ ጠርቶ ለማነጋገር ፈልጓል፡፡ ከመቀመጫው ተነሳ፡፡ መቅደስን ጠራት፡፡ ከሰው ጋር እንዴ? ብሎ ጠየቃት፡፡

"እኔ ከሰው ጋር ነኝ፡፡ የሽሃረግ ደግሞ እንደዚ አይነት ስራ ሰርታ ስለማታቅ አትወጣም አለችው፡፡

ደግሞ የከተማ ሴት እንደ ገጠር ነው እንዴ? በገንዘብ እሽ አትልም? ፡፡

"እሱማ ልክ ነህ ፤ እሷ ግን ስለማትሰራ ነው፡፡

ጓደኛየ ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝቶ አያውቅም፡፡ ዛሬ ምን እንደነካው እንጃ በየሽሃረግ አብዷል አላት፡፡

ብቻ ከእሷ ለመስማት እሽ ካለች እጠይቃታለሁ፡፡ ብላ ልጠይቃት እየፈራች ቢሆንም ተጠጋቻት፡፡ የሽሃረግ የጠጣችው የሐረር ቢራ አስክሯታል፡፡ ወደ ኋላ ያሰረችውን ሐር የሚመስለውን ፀጉሯን ለቃዋለች፡፡

ታዲያ አይኗን ሸፍኖት ትንሽ ትንሽ ነበር ፊቷ የሚታየው፡፡

መቅደስ የጠጣችው ቢራ እሷንም ሞቅ አድርጓት ስለነበር የሽሃረግን ሳትፈራ ስሟን አቆላምጣ የሺዬ ያሰውዬ ፎንቅቄያለሁ እያለ ነው አለቻት፡፡

"የቱ ነው"? አለች፡፡ ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገለጥ እያደረገች፡፡

ቢራ ከጋበዙሽ አንደኛው ፡፡ ያ የፂሙ አሪዝ የሚያምረው ሰውዬ፡፡ ደግሞ ሴት የሚባል አውጥቶ አያውቅም፡፡ ቢራ እራሱ የተማከራችሁ ይመስል እንደ አንችው ዛሬ ነው ፤ የጀመረው አለቻት፡፡

"አንች በምን አወቅሽ ዛሬ ቢራ መጀመሩን ?፡፡

አብሮት ያለው ጓደኛው ነው የነገረኝ፡፡

"እኔ እንደዚህ አይነት ስራ እንደማልሰራ እያወቅሽ ፤ ለምን ትጠይቂኛለሽ"? አለች፡፡ ውስጧ ፍራት ፍራት እየተሰማት፡፡

እሱንማ አውቃለሁ፡፡ ግን አንች እስከመቼ ድረስ ነው? ወንድ የማትፈልጊው ፤ የጠየቀሽን ሁሉ አልፈልግም እያልሽ፡፡ ላይፍሽን በአሁን ሰዓት ካልተጠቀምሽበት መቼ ልትጠቀሚበት ነው?፡፡ ደግሞ ጊዜሽ ካለፈ ወዲያ ማንም ሊጠይቅሽ አይደለም ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ይልቁንም ዛሬ እትዬም ስለሌለች አብረሽው እደሪ አለቻት፡፡

እሳትን በእሳት እንደ ሚባለው ሴትን በሴት አሳምኖ በቁጥጥር ስር ማድረግ በሴቶች የተለመደ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

ጊዜሽ ካለፈ ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ያለቻት ህሊናዋን በመርፌ የተወጋች ያህል ተሰማት፡፡ በትካዜ ተዋጠች፡፡ መጀመሪያም ልቧን በአይን አፋርነቱና በጉንጩ ላይ መስመር ሰርቶ በወረደው አሪዛም ፂሙ አሸፍቶ የወሰደባት ተመስገን እንኳን ለሴት ልጅ ለወንድ ልጅ ያማልል ነበር፡፡

"እትየ ስትመጣ ካልነገርሽብኝ እኔም ወድጀዋለሁ"፡፡ አለቻት የልብ ትርታዋ ከመጠን አልፎ ቁና ቁና እያስተነፈሳት፡፡

አልነግርብሽም፡፡ ደግሞ እኔ የምናግረው ጣቱን የሚጠባ ህፃን አደረግሽኝ እንዴ ብላት "በይ አሁን
ሰውም ስለሌለ እንዘጋጋና እኔም ሰው እየጠበቀኝ ነው እንተኛ አለቻት፡፡

"እምቢ ሳትል አትቀርም አለ ፤ ያሬድ፡፡

የከተማ ሴት ገንዘብ ነው የሚፈልጉት አላልከኝም" እንዴ አለ ፤ ተመስገን፡፡

የዚች የተለየ ነው እባክህ ብሎ ሌላም ደግሞ ሳይናገር መቅደስ ጠጡና ተነሱ ልንዘጋ ነው አለች፡፡

ተመስገን መሸ እንዴ? አለ፡፡

አልታወቀህም እንዴ? ከመምሸቱም ሊነጋ ተቃርቧል፡፡ እንዴውም የእኛ ብቻ ነው፡፡

ያልተዘጋው እንጅ የሁሉም ሆቴሎች ተዘግተዋል አለች ፤ መቅደስ፡፡

"እሽ ፤ እንነሳለን ግን የሽሃረግ ምን አለችሽ"? አለ

መቅደስ በስንት ልመና እሽ አስብያታለሁ፡፡ አሁንም እየፈራች ስለሆነ እናንተ ተነሱና አልጋ ቤት ጠብቁኝ፡፡ እኔ ይዣት እመጣለሁ አለች፡፡

ተንገዳገደ፡፡ ደግፎት ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡

መቅደስ ሆቴሉን ዘጋግታ ከጨረሰች በኋላ፤ የሽሃረግን የሆቴሉ ዘበኛ እንዳያያት ወደ ሽንት ቤት የሚሄዱ አስመስላ ወደ እነ ያሬድ አልጋ ቤት አስገባቻት፡፡ ያሬድ ለሚተኛበት ሌላ አልጋ ከፍታለት አብሯት ወደ ሚያድረው ሰው ጋር ተመለሰች ፡፡

ለተመስገን ችግር የሚያጋጥምህ ከሆነ እዚህኛው አልጋ ቤት ነው የምተኛው፡፡ ነገ በጥዋት ወደ አቶ ላንቻ ቤት እንሄዳለን ብሎት ሁለተኛ ወደ ያዘው አልጋ ሄዶ ተኛ፡፡

የመኝታው በር ተዘጋ፡፡ ልብሳቸውን አወላለቁ፡፡ ከአሁን በፊት እንደሚተዋወቁ ፍቅረኛ ተቃቀፉ፡፡ ታምሪያለሽ ፤ አንተም ታምራለህ፡፡ ብቻ የሚል ቃል ተነጋግረው በለበሱት ብርድልብስ ውስጥ ከንፈር ለከንፈር ተፈላልገው ተገናኙ፡፡

የሁለቱም የሰውነት ሙቀት ጨመረ፡፡ ሳይታወቃቸው የተመስገን እግሮች በየሻረግ እግሮች ውስጥ ተጠላለፉ፡፡ በስካር መንፈስ ጉዳያቸውን ከፈፀሙ በኋላ ሁለቱም እራሳቸውን ሳቱ፡፡ መተቃቀፉና መሳሳሙ ቀረ፡፡ ድጋሜም አልተገናኙም፡፡ የለሊቱ ጨለማ ለቆ የቀኑ ብርሃን ተተካ፡፡

ያሬድ እሱም በስካር መንፈስ የመኝታ በሩን ከፍቶ እንደ ገባ ጫማውን እንኳን አላወለቀም፡፡ የወደቀበትን አያውቀም፡፡ ስካርና እንቅልፉን አሳልፎ ከተኛበት መኝታ ላይ ባነነ፡፡ ጫማውን ሳያወልቅ በመተኛቱ ተገረመ፡፡እንደዚህ እራሴን እስከምስት ድረስ ሰክሬ ኖሯል፡፡ ወይ ነዶ የሰውዬው ልጅ እያለ ተነሳ፡፡ በሩን ከፈተ፡፡ ሌሊቱ ነግቶ ቀን ቀን እየሸተተ ነው፡፡

የስካር ፊቱን ታጠበ፡፡ ልቡ አቶ ላንቻ ጋር ለመሄድ ተቻኩሏል፡፡ የአልጋው በር አልተዘጋም፡፡ ገርበብ ብሏል፡፡ ሳይዘጉት ይሆን እንዴ? የተኙት እያለ ገርበብ ያለውን በር ከፈት አድርጎ ገባ፡፡

የሽሃረግ ከተኛችበት ስትነሳ ከማታውቀው ሰው ጋር ተኝታ የንፅህና ክብሯን በመስጠቷ የሞት ያህል ተሰምቷታል፡፡ በሁለት እጆቿ እራሷን ደግፋ ከአንገቷ ወደ መሬት አቀርቅራ ከመኝታው ላይ ተቀምጣለች፡፡ የተፈጠረውንና ያደረገችውን ሁሉ ለማስታወስ እየሞከረች ከህሊናዋ ጋር እየተሟገተች ሳለ ያሬድ በር ከፍቶ ገባ፡፡ ካቀረቀረችበት ቀና አለች፡፡ ከያሬድ ጋር አይን ለአይን ተጋጩ፡፡ ያሬድ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ ድንጋጤ ተሰማው፡፡

የሽሃረግን ደጋግሞ አትኩሮ ተመለከታት፡፡ ማታ በዲም ላይትና በፌር ቅባት ህንዳዊ መስላ የታየችው የፊት ላይ ቅባት ተወግዶ የኢትዮጵያዊነት ደም ግባቷ ተመልሷል፡፡ የጠይም ለግላጋ ቆንጆ መሆኗን በደንብ ይታያል፡፡ የሚያውቃት የሚያውቃት መሰለው፡፡

ተመስገን የት እንደ ሄደ እንኳን አልጠየቃትም፡፡ ወደ ተቀመጠችበት መኝታ ተጠጋ፡፡

ምነው? የማውቅሽ መሰለኝ፡፡ ግን ስምሽ ትክክለኛ የሽሃረግ ነው? አላት፡፡

የሽሃረግ ጭንቅላቷን በመጥረቢያ እንደተመታች ያህል ባለችበት ክው ብላ ቀረች፡፡ ያሬድን አፍጣ ፣ ደግማ ፣ ደጋግማ አየችው፡፡

"የየየየየየየየየየየየየ..ታ...ውቀኛለህ"?  አለች፡፡ አፏ እየተንተባተበ፡፡
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

ሁሴን ወደዩኒቨርሲቲው  ከተመለሰ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ…
አላዛር እንደተለመደው  ስራ ውሎ ቤት እንደገባ  በራፉ ከልክ በላይ ተቆረቆረ..በድንጋጤ ሄደና ከፈተው፡፡ሰሎሜ ነች..፡፡አይኖቾ በለቅሶ ብዛት ደም ለብሰዋል፡፡በዛ ላይ አባብጣለች፡፡ወደውስጥ ጎትቶ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ‹‹ምን ሆንሽ?››ሲል ጠያቃት..ልትመልስለት ሞከረች ግን ሳግ እየተናነቃት ማውራት አልቻለችም፡፡ተንደርድራ ሄዳ ሶፋው ላይ ወጥታ እጥፍጥፍ ብላ ተኛች፡፡ለምን እንደዚህ እንደሆነች በደንብ ያውቃል፡፡ቢሆንም አሳዘነችው፡፡ቢቻለው ይሄንን ጉዳይ እሷን ቅንጣትም ሳያሳዝን በፀጥታ ማጠናቀቅ ነበር ምኞቱ…ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም‹‹ካለመስዋዕትነት የሚገኝ ውጤት የለም››ብሎ በማሰብ እራሱን ለማፅናናት ሞከረ፡፡በጣም አሳዘነችው፡፡በዝግታ ሄዶ ፈራ ተባ እያለ ስሯ ተቀመጠ፡፡

‹‹ሶል ምን ሆንሽ?››

‹‹ያ ደደብ..ቺት ሲያደርግብኝ ነበር ለካ፡፡››

‹‹እንዴ ማን?›

‹‹እስራኤል ነዋ.. ሌላ ማን ይሆናል?››

‹‹እንዴ ገና ከመጀመሪያችሁ..አረ የተሳሳተ ወሬ ደርሶሽ እንዳይሆን?››ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን  እውነተኛ ሙሉ  ታሪኩን  ቢያውቅም በማስመሰሉ ቀጠለበት፡፡

‹‹ኸረ ባክህ…››አለችና ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከጃኬቷ ኪስ ውስጥ ፎቶዎችን አወጣችና ጠረጴዛው ላይ ዘረገፈችለት፡፡

ልክ ፎቶውን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየው በማስመሰል በመደነቅና  በመገረም እያቀያየረ ይመለከታቸው ጀመር፡፡

‹‹ልጅም አለው ማለት ነው?›

‹‹አይገርምም..ምን አይነት ጅል ኖሪያለው?››

‹‹እንዴ አንቺ እንዴት ልታውቂ ትችያለሽ?››

‹‹አይደል …ልስልስ ብሎሰ ሲቅለሰለስ እኮ መላአክ ነው የሚመስለው፡፡.

ፎቶውን እንዴት እንዳገኘችው በደንብ እያወቀ‹‹ለመሆኑ ይሄን መረጃ እንዴት አገኘሽው?››ሲል ጠየቃት፡፡

..ካፌ አስተናጋጅነት ስራ ጀምሬለሁ አላልኩህም…ሽፍቴን ጨርሼ ወደቤት ለመምጣት ታክሲ እየጠበቅኩ ሳለሁ ነው የሆነ ህፃን ልጅ  የሰጠኝ…የሆነች ሴት ነች የላከችልሽ››ነው ያለኝ…በወቅቱ ግራ ተጋብቼ ስለነበር ከዛ በላይ ማጣራት አልቻልኩም፡፡››

‹‹እራሷ ሚስቱ ትሆናለች፡፡››

‹‹አዎ መሰለኝ ከፎቶው ጋር አብሮት የሆነ ማስታወሻ ነበረበት

..‹እባክሽ የልጄ አባት ባሌን ተይልኝ……ትዳራችንን አትበጥብጪ› ይላል››

‹‹ይገርማል…ታዲያ እሱን አላናገርሽውም?››

‹‹ምን አባቱና ነው የማናግረው…..ወዲያውኑ ነው ስልኩን ብላክ ሊስት ውስጥ የጨመርኩት ፣  ብቻ እግዜር ነው የተፋኝ፡፡››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ምን እንዴት አለው..?አንድ ተጨማሪ ወር ቆይተን ቢሆን ኖሮ ሌላ ነገር ውስጥ ልንገባ እንችል ነበር››

‹‹ሌላ ነገር ማለት?››

‹‹አንተ ደግሞ በረዶ ነጭ ነው ካለሉህ አይገባህም….››አለችው በብስጭት፡፡
በረጅሙ ተነፈሰ….‹‹አለመነካካታችሁም አንድ ነገር ነው…አይዞሽ ቀስ እያልሽ ትረሺዋለሽ››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡

‹‹አይ አካላችን አለመነካካቱን አትይ …ልባችን ተነካክቶ ነበር..በተለይ ልቤ ልቡ ላይ ተለጥፎ ነበር….ልብን ከተለጠፈበት መንጭቀህ ስታላቅቀው ደግሞ ተቦጭቆ የሚቀር ነገር አለ..የሚቆስልና የሚቆጠቁጥ…ያማል…..››
ጭንቅላቷን እያሻሸ‹‹አይዞሽ…!!.››አላት፡፡

‹‹አላዛር››ስትል ድንገት ጠራችው፡፡

‹‹ወዬ ሰሎሜ››

‹‹ቆይ እኔ አስጠላለሁ እንዴ?››

‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው?››

‹‹ጓደኛዬ ከሆንክ በታማኝነት መልስልኝ..እኔ አስጠላለሁ ወይ?››

‹‹አንቺ ማለት ድቅድቅና ጭለማ በሆነ  አለም ውስጥ ቦግ ብለሽ በድምቀት የምታበሪ ጨረቃ ነሽ…አንቺ ውብ ካልሆንሽ..ውብ ሚባል ነገር ጭራሽ በዚህ አለም የለም ማለት ነው››አላት ከአንጀቱ፡

‹‹አንተ ደግሞ ከፊክሽን ያነበብከውን ውብ የፍቅር ውዳሴ አሰማኝ አላልኩህም እኮ….ንፅህ ስሜትህን ነው የጠየቅኩህ››

‹‹እኔም የነገርኩሽ ስለአንቺ የሚሰማኝን ነው..ፊክሽን ማንበብ እንደማልወድ ደግሞ ታውቂያለሽ፡፡››

‹‹ታዲያ እንደምትለው ከሆነ ..ለምን ፍቅርን በተመለከተ ስኬታማ መሆን አቃተኝ..?››

‹‹አንቺ ብቻ እኮ አይደለሽም ..እኛም ጓደኞችሽ እስከአሁን ይሄነው የሚባል የፍቅር ታሪክ የለንም፡፡ያ ማለት ወደፊት አይኖረንም ማለት አይደለም….ከፊታችን ገና ብዙ ብሩህ እድሎችና ተስፋዎች እንዳሉን አምናለው፡፡ደግሞ እንዳትረሺ ውቧች ሁሉ  ሁሌ  በፍቅር ውጤታማ መሆን አለባቸው የሚል ህግ የለም ፡፡ .››

‹‹ይሁን እስኪ እንደአፍህ ያድርግልን…..ምን አልባት ሁለችንም ጓደኛሞች ልጆች ሆነን ጀምሮ ተንኮል ስንሰራ ስላደግን የሆነ ሰው ‹ፍቅር  በልባችሁ አይደር…ካደረም አይሰንብት› ብሎ እረግሞን ይሆናል….›› ብላ  ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቆመች፡፡

‹‹ምነው ልትሄጄ ነው እንዴ?››

‹‹እና ልደር?››

‹‹ምን ችግር አለው…?

‹‹በል ይሄን ያህል ካለቃቀስኩብህ ይበቃኛል ..አመሰግናለው..ትንሽ ቀለል ብሎኛል››

‹‹በይ እሺ ደህና እደሪ››አለና በራፉ ድረስ ሸኛት፡፡በራፉን እንደከፈተ ቆሞ በራፏን ከፍታ እስክትገባ  ተመለከታት…ከዛ በእፎይታ እና በእርካታ በራፉን ዘጋና ወደመኝታው አመራ፡፡
////
አላዛር እና ሰሎሜ ለሁሴን ምርቃት ለመሄድ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ያልገመቱት አስደንጋጭ እና ያልተጠበቀ ግን ደግሞ አስደሳች ተብሎ ሊታሰብ የሚችል ዜና ደረሳቸው፡፡
መጀመሪያ ለአላዛር  ነው መልእክት የተላከለት፡፡
ሰሎሜ እና አላዛር ወንድሜ እኔን ለማስመረቅ ወደእኔ ለመምጣት ምታደርጉትን ዝግጅት አቁሙ..አስፈላጊ አይደለም፡፡ልትልክልኝ ያሰብከውን  ገንዘብም አትላክልኝ …እስከዛሬ ከበቂ በላይ ረድተኸኛል…አመሰግናለሁ፡፡ለምን እንደዛ እንዳልኩህ  ዝርዝር ምክንያቱን ሰሞኑን ኢሜል አደርግልሀለው፡፡››ይላል፡፡
ገና ሰሞኑን ጠብቆ ኢሜል እስኪልክለት መጠበቅ አልችልም.፡፡ለምን እንደዛ እንዳላቸው ለማወቅ..ስልክ ደወለለት …አይነሳም፡፡ደጋግሞ መከረ…፡፡በማግስቱ እንደውም ጭሩሱን ስልኩ አይሰራም ፡፡ጥሪ አይቀበልም ይላል፡፡
ለሰሎሜም ሁኔታውን ነግሯት አብረው መጨነቅ ጀመሩ፡፡
እሷም ከእሱ በላይ ተጨንቃ

‹‹ታዲያ ምን ይሻላል ትላለህ?››ስትል ጠየቀችው ፡፡

‹‹እኔ እንጃ …ምን አልባት እኛን ማስቸገር ከብዷት እንዳይሆን››

‹‹ይመስለኛል…ማለቴ አንተን ማስቸገር ከብዶት ነው የሚሆነው››ስትል በሀሳቡ ተስማማች፡፡

‹‹ምን ማለት ነው..?ጓደኛቹ አይደለን እንዴ..?በእንደዚህ አይነት ጊዜ ከጎኑ ካልሆን ጥቅማችን ምኑ ላይ ነው፡፡››ተበሳጨ፡፡
‹‹ያው ሁሉም ጓደኛ እኮ አንተ እንደምታደርገው አያደርግም››

‹‹እንዴት? ››

‹‹እኛ እርስ በርስ ጓደኛሞች ብቻ አይደለንም የእድሜ ልክ ትስስር ያለን ወንድምአማቾች ነን››

‹‹ይሄ ገለፃ አሌክስንም ያጠቃልላል?››ሲል መልሶ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

ፊቷ ቅይርይር አለ…አሌክስ የሚባለውን ስም መስማት የማትፈልገው ስም ከሆነ ከራርሟል ፡፡መኮሰታተሯን አይቶ‹‹እሺ አትበሳጪ..እንዳልሺው ሊሆን ይችላል፡፡አሁን ዋናው ነገር  ምን እናድርግ የሚለው ነው?›› ሲል ምክረ ሀሳቧን ጠየቀ፡፡

‹‹እኔም ግራ ገባኝ እኮ…፡፡›

‹‹ዝም ብለን  ወደ ጎንደር እንሂድ እባክሽ››ሲል ቅፅበታዊ ውሳኔውን ነገራት፡፡

‹‹መቼ….?››

‹‹በቃ ነገ እንዘገጃጅና ተነገ ወዲያ እንሂድ፡፡››

‹‹ግን አውቀሀል… ለምርቃቱ ገና አስር ቀን ይቀረዋል…ደርሰን እንመለሳለን ወይስ  እንዴት እናደርጋለን?››
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////

ሚካኤል ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊ ጋር ሚስጥራዊ ስብስባ እያደረገ ነው፡፡እኚን ባለስልጣን ለማግኘትና ለማናገር በጣም ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፏል …በጣም ብዙ ገንዘብም ከስክሷል፡፡

‹‹እሺ አቶ ሚካኤል እንዳገኝህ ያሳመነን ወዳጄ ትልቅ ባለውለታዬ ነው ..ምን እንዳደርግልህ ነው የምትፈልገው?፡፡››ሲል ቦርጫቸውን እሻሹ ጠየቁት፡፡

‹‹ያው ጫፉን ያውቁታል ስለአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱን ሰምቼለው…አባትህ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሰው ነው፡፡ምን እንድረዳህ እንደፈለክም ያልገባኝ ለዛ ነው፡፡ታውቃለህ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ፍርደኛ ቀጥታ ፋይሉ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ጋር ነው ሚላከው..እሳቸው ሲፈርሙበት የሞት ቅጣቱ ተፈጻሚ ይሆናል…እስከዛው በእስር ይቆያል…ማንም ሰው ምንም ማድረግ አይችልም፡፡››

‹‹አውቃለው…..የእኔ ፍላጎት የሞት ፍርድ ተፈፃሚ እስኪሆንበት ያለው የማረሚያ ቤቱ አያያዝ እንዲሻሻልለት ለመጠየቅ ነው፡፡››

‹‹አዎ አንተን ለማግኘት ከመምጣቴ በፊት ስለአባትህ አጠቃላይ ሁኔታ በመጠኑ ለማጣራት ሞክሬ ነበር፡፡አሁን የታሰረው ጥብቅ በሆነ  ጥበቃ ለብቻው መሆኑን ገልፀውልኛል፡፡››አሉን ፊትለፊታቸው የተቀመጠውን የውስኪ ብርጭቆ አንስተው ተጎነጩና መልሰው አስቀመጡት፡፡

ሚካኤልም ‹‹አዎ ያስጨነቀኝ እኮ ያ ነው፡፡››ሲል መለሰላቸው፡፡

‹‹ያ ለምን እንደሆነ መቼስ ታውቃለህ፡፡አባትህ ከሌሎች በእስር ቤት ካሉ ታራሚሆች ጋር በማሰር ከማረሚያ ቤቱ ለማምለጥ ሞክሮ አንድ የፖሊስ አባልና ሁለት እስረኛ ሞተዋል፡፡የዛ ኦፕሬሽን ዋናው ማስተር ማይንድ እና መሪ ደግሞ አባትህ ነበር…ያ ውሳኔ የተወሰነበት ከዛ ክስተት በኋላ ነው፡፡ለፖሊስ መገደል ምክንያት መሆን ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አይከብድህም››

‹‹አዎ አውቃለው…ግን እኮ በጣም ተቀጣ..እዛ ጨለማ ክፍል በሰንሰለት ተጠፍሮ መኖር ከጀመረ ስድስት ወር አለፈው፡፡እሺ ብቻውን ይታሰር….ቢያንስ ከጨለማ ክፍል የሚወጣበትና  ከሰንሰለት እስርም የሚገላገልበት እድል ቢኖር፡፡ዋናው ከሰው እንዳይቀላቀልና ተመሳሳይ አይነት የማምለጥ ሙከራ እንዳይሞክር አይደል››ሲል በንግግሩ ቃናም በአይኖቹም ተማፀናቸው፡፡

‹‹ይመስለኛል ..ያም ብቻ አይደለም..በእሱ ምክንያት የሞተው ፖሊስ በወህኒ ቤት ውስጥ በፖሊስችም ሆነ በእስረኞች በጣም ተወዳጅ ስለነበረ….በጓደኞቹ ዘንድ ከፍተኛ ብስጭት ፈጥሯል….እና አንድም በጣም እንዲቀጣ ይፈልጋሉ በሌላ ጎኑም በተግባሩ በተበሳጩ ሰዎች ጥቃት እንዳይደርስበትም ስጋት ስላለ መጠበቅ ይፈልጋሉ፡፡››

‹‹‹አውቃለሁ…ያ ጉዳይ በመፈፀሙ እኔም ከፍተኛ ልብ ስብራት ደርሶብኛል ፣ የሞች ፖሊስ ቤተሰቦች አግኝቼ ለማነጋገር ሞክሬለው፡፡ባለቤቱንና አንድ ልጁን ወዲው ነበር ያገኘዋቸው….እና ምንም እንኳን እሱን መልሼ ላመጣላቸው ባልችልም በኑሮ ግን እንዳይቸገሩ የተቻለኝን እያደረኩ ነው፡፡ለሚስቱ ስራ እንድታገኝ አድርጌለው….የልጁንም ትምህርት ቤት ክፍያ  እና አንዳንድ ወጪዎች እየከፈልኩ ነው….ምንም ሆነ ምንም ወደፊትም ያንን ማድረጌን አላቋርጥም፣እባኮት እርሶ በተቻሎት መጠን ይርዱኝ…ምንም አይነት ቤተሰብ እንዳይጠይቀውም ስለተከለከለ እኔ እንኳን ካየሁት ስድስት ወር አልፎኛል…››

‹‹በእውነት እያደረከው ስላለ ነገር ምስጋና ይገባሀል..ትልቅ ሰው ነህ!!እንግዲህ እንዲህ እናድርግ….አንድ አስር ቀን ስጠኝ  እና ሁኔታውን በተሻለ ሁኔታ ላጥና..ከዛ ሌሎች ጓደኞቼንም ቢሆን አስቸግሬ ማድረግ የምችለውን ነገር ላስብበትና መልሰን እናውራበት››

‹‹በእውነት በጣም ነው የማመሰግነው…..ምን አልባት ጓደኞቾትን ሲያስቸግሩ የሚያስፈልግ ነገር ካለ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አሟላለሁ…፡፡››ሲል ቃል ገባ፡፡

‹‹ችግር የለም… የሚስፈልግ ነገር ካለ አሳውቅሀለው….እነደነገርኩህ አንተን እንድረዳህ የጠየቀኝ ሰው በጣም ወዳጄና ባለውለታዬ ነው…..እና በእኔ አቅም ማድረግ የምችለውን ነገር ሁሉ እንደማደርግና የአባትህን በእስር ቤት ውስጥ ያለውን አያያዝ ለማሻሻል ጥረት እንደማደረግ ልገልጽልህ አፈልጋለው…በተለይ አባትህን የመጠየቅ  መብትህን መልሰህ እንድታገኝ ማድረግ ምችል ይመስለኛል፡፡››

‹‹አመሰግናለው..ስልኮትን በጉጉት ጠብቃለው፡፡›› በዛው ተለያዩ
////
ፀአዳ  በአራተኛው ቀን ስሜቷን አብርዳ….መረበሿን አረጋግታ ልጇን ይዛ መጣች፡፡ከዶዶላ ተመልሳ አዳማ እስክትገባ ስልኳን አልከፈተችም ነበር፡፡ቤቷ ደርሳ አረፍ እንዳለች ከፈተችና ለአዲስ አለም ደወለችላት፡፡

አዲስአለም ከሰላምታ ሳይሆን ከስድብ ነው የጀመረችው‹‹አንቺ ቅሌታም…..ጤነኛ ነሽ ግን?››

‹‹ቀስ …ይሄ ሁሉ ቁጣ ናፍቆት ነው ወይስ ሌላ ምክያት አለው?፡፡››

በስድቧ ገፋችበት ‹‹ወሬኛ ነሽ እሺ…..ለመሆኑ አሁን የት ነሽ?››

‹‹ቤቴ ነኛ››

‹‹ማለት እዚህ አዳማ?››

‹‹አዎ..ምነው ሌላ ቦታ ቤት አለኝ እንዴ?››

‹‹እኔ ምን አውቅልሻለው….ግን ሳስበው በቅርብ አዲስአበባ ላይ ቤት የሚኖርሽ ይመስለኛል….በቃ ጠብቂኝ አሁኑኑ መጣሁ…፡፡››

‹‹ኸረ እኔ ራሴ መጣለሁ…፡፡››

‹‹መጣው እኮ አልኩሽ፡፡››ስልኩን ጠረቀመችባት፡፡

‹‹ዛሬ ልትደበድበኝ ሁሉ ትችላለች››ስትል አሰበችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤቱን ማስተካከል ጀመረች ..ተዘግቶ ስለከረመ እምክ እምክ ይላል…መስኮቱን ከፋፈተች…ሰንደል ለኮሶችና በየኮርነሩ ላይ ሰካካች… ቡና ለማፍላት ሲኔ ደረደረች፣ከሰል በማቀጣጠል ላይ እያለች አዲስ አለም መጣች፡፡

ጠየቀቻት ካሰበችው ጊዜ በጣም ፈጥና በመምጠቷ ተገርማ‹‹እንዴ ..!!ስትደውይልኝ መንገድ ላይ ነበርሽ እንዴ?››ስትል ….፡፡
ልትስማት ስትጠጋት ወደኃ ሸሸቻትና ገፍትራት ወደቤት ገባች….ፀአዳማ እያቀጣጠለች የነበረውን ከሰል ትታ ከኃላ ተከተለቻት፡፡

‹‹ምስር የታለች?››

‹‹ጎረቤት ልትጫወት ሄዳለች››

‹‹ቆይ አንቺ ግን ያምሻል..?እንዴት አንድ ነር ሳትነግሪኝ ብን ብለሽ ትሔጃለሽ…እሺ መሄዱንስ ሂጂ እንዴትሰ ስልክሽን ትዘጊያለሽ?››

‹‹ስልኬ እኮ ተበላቶብኝ ነው››

‹‹አረ ባክሽ..አሁን እኔን የምትሸውጂኝ ይመስልሻል?››

‹‹‹እሺ በቃ ማንንም ለማውራት ጥሩ ሁኔታ ላይ አልነበርኩም…በፀጥታ ማሰብ ነበር የፈለኩት..በዛ ላይ አንቺ የሰርግና የመልስ ግርግር ላይ ስለሆንሽ ልረብሽሽ አልፈለኩም››

‹‹ወይ ረበሺኝ እኮ..እኔን ብቻ ሳይሆን ባሌንም ጭምር ነው በደንብ የረበሺን፡፡››

‹‹እንግዲህ አዝናለው…..በጣም ይቅርታ›

‹‹ደግሞ ሰውዬሽ..አብዶልሻል….››

‹‹የቱ ሰውዬ?››ግራ በመጋባት ጠየቀች፡፡

‹‹ስንት ሰውዬ ነው ያለሽ…?ዘሚካኤል ነዋ..ከደበቅሺበት  ውለጂያት ብሎ ሊያንቀኝ››

‹‹እንዴ ደወለልሽ እንዴ?››
ምን ይደውልልኛል…በዛን ቀን ልክ ያንቺ መልእክት ደርሶኝ እሱን ከሚካኤል ጋር አንብበን እየተገረምን ሳለ ቤት ድረስ መኪናውን እያከነፈ መጣና ሰፈሩን በመኪናው ክላክስ አደበላለቀው…ምን ሆኖ ነው ብዬ ስወጣ መኪና ውስጥ አስገባኝና ከሰፈር ይዞኝ ሄደ….››ብላ የዛን ቀን የሆነውን በዝርዝር ተረከችላት፡፡›

ፀአዳ በሰማችው ነገር በጣም ተገረመች‹‹ፈፅሞ እንደዛ ያደርጋል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር…ግፋ ቢል ደውሎ የሆነ ነገር ይልሻል ብዬ ነው ያሰብኩት፡፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..?ልጁ እኮ ጨርቁን ጥሎልሻል››

‹‹ማለት?››

‹‹አፍቅሯሻል እያልኩሽ ነው››

‹‹እኔ ፍቅር አልፈልግም››

‹‹እና ወሲብ ነው ምትፈልጊው?