አትሮኖስ
278K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
452 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አራት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ



#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


እንደርስበታለን ብለን ከገመትነው ስዓት በፊት ማታሩ ጆንግ ደረሰን፡፡ ስለ ቤተሰቦቻችን ምንም ዜና የለም። በተስፋ ከመጠበቅ እና ደህንነታቸውን ከመመኘት ውጪ ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም::

አማጺዎች ከ ማታሩ ጆንግ ሃያ ኪሎ ሜትር እና ከዛ በላይ በምትርቀው ሱምብያ ከተማ መሰፈራቸውን ሰማን። ቀጥሎ አማጺዎች ደብዳቤ እንደላኩና ደብዳቤው የነሱም መምጣት፤ ስለ
እኛ እየታገሉ እንደሆነ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚፈልጉ ያትታል። መልዕክተኛው ወጣት ነው፡፡ ሰውነቱ ላይ የአማጺዎችን ስም እና አጸርሆተ ቃል ማለትም (አአግ
አብዮታዊ የአንድነት ግንባርን ተነቅሷል። ከአውራ ጣቱ ውጪ ሁሉንም ጣቶቹን ቆርጠውበታል። አውራ ጣት በብዙ ሰወች
የተለመደ የፍቅር ምልክት ነበር።

መልዕክቱ እንደደረስ ሰዎች ወደ ጫካ መሸሸግ ጀመሩ። የካሊሎ ቤተሰብ ግን እንድንቆይ እና ስንቅ ይዘን እነሱን
እንድንከተል ጠየቁን። ቆየን፡፡
ያ ምሽት በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የከተማን ህይወት የሚሰጠው የሰዎች መኖር እና መንፈሳቸው እንደሆነ ተረዳሁ። የሰዎች አለመኖር ከተማውን አስፈሪ አደረገው። ድቅድቅ ጨለማ እና ከባድ ጸጥታ! የዶሮዎች እና የወፎች ዝማሬ
እንኳ የለም። ጨለማ ፈጥኖ መጣ፤ ጨረቃም የለችም። አየሩ ከብዷል፡፡ ተፈጥሮ ራሷ የሚመጣውን የፈራች ትመስላለች።

ሰዎች ለሳምንት ያህል ተሸሸጉ። አማጺዎች ግን አልመጡም።በኋላ ሌላ መልዕክተኛ ላኩ፡፡ መልዕክተኛው ታዋቂ የካቶሊክ ካህነ ነበር፡፡ ከማስፈራራት ውጪ ካህኑን ምንም አላደረጉትም።
ቃሉን ተቀብሎ ህዝቡ ወደ ጫካ ተመልሶ ገባ። አስር ቀናት አለፉ አማጺዎች ግን አልመጡም፡፡ ነዋሪው ወደ ከተማ መመለስ ጀመረ። ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ፤ ሰዎች ወደ ዕለት ተዕለት
ኑሯቸው ተመለሱ፡፡ አምስት ቀናት በሰላም አለፉ፡፡

በመጨረሻ አማጺዎች ሲመጡ ቀላል የተኩስ ድምጽ ሰማን፡፡
ጅኒ የር፣ታሉ፣ ካሎኮ፣ ገብሬላ፣ ካሊሎ እና እኔ ቤት ውስጥ ነበረን
"ሰማቹህ?” ብለው ጠየቁ። ወታደሮች ናቸው የተኮሱት ወይስ ሌላ አካል እያልን በማሰብ ደርቀን ቆምን።
ከደቂቃዎች በኋላ ሶስት ጊዜ ተተኮሰ። አሁን ሁላችንም ፈራን።ከተማው ጸጥ ረጭ አለ። ተኩሱ ሲቀጥል። ሁሉም ተደናገጠ።በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ሰዎች መጮህ እና ወደ ተለያዩ
አቅጣጫዎች መሮጥ ጀመሩ። ሰዎች ተገፋፉ፣ አንዱ በአንዱ ላይ ወደቀ የወደቁ ሰዎችን ረግጦ ያልፋል። እናቶች ልጆቻቸውን አጡ፤ ቤተሰብ ተለያየ፤ የከተማው ነዋሪዎች ለዘመናት
የለፉበትን ጥሪት ትተው ሮጡ። ልቤ በፍጥነት ይመታል።

ወደ ማታሩ ጆንግ ለመግባት ሁለት መንገዶች አሉ።የመኪና መንገድ እና በወንዙ በማቋረጥ :: አማጺዎች ግን በየብስ በኩል እያጠቁ ሲገሰገሱ ሰዎች ወደ ወንዝ እንዲሮጡ ተገደዱ። ብዙ
ሰዎች በፍርሃት ወንዝ ውስጥ ገቡ። እስኪደክማቸው ድረስ ዋኙ:: ወታደሮቹ በቁጥር መበለጣቸውን ሲያውቁ ቀድመው ነበር ከተማውን ለቀው የወጡት :: ህዝብ ሁሉ የተመመበት
አንድ ማምለጫ መንገድ ብቻ ነበር፡፡ ተከተልናቸው። መንገዱ ጭቃ ነበር፡፡ ጭቃ የያዛቸውን አካል ጉደተኞች ማንም
አልረደቸውም፡፡ ማንም ሊረደቸው የሚፈልግ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ አማጺዎቹ ወደ ሰው መተኮስ ጀመሩ። ሰው ከተማውን ለቆ እንዲወጣ አልፈለጉም። ነዋሪውን በተለይ
ሴቶችን እና ህጻናትን ምሽግ በማድረግ ከመከላከያ ጥቃት መዳን ይፈልጋሉ፡፡
እንደምንም ግን ወደ ማምለጫው መንገድ ስንዳረስ አማጺዎች ቀጥታ ወደ እኛ መተኮስ ጀመሩ። ሁሉንም የመሳሪያ አይነቶች ተጠቀሙ።ጥይት አዘነቡ፤ ሮኬት ና መትረየስ ተኮሱ ቦምብ ወረወሩ። እኛ ምንም አላመነታነም:: መያዝ የከፋ እንደሚሆን እናውቃለን፡፡ ከተያዝን እንመለመላለን : በጋለ ጩቤ አእግ
ብለው ደስ ያላቸው ቦታ ላይ ይጻፉብናል። ስለዚህ ማምለጥ ግድ ነው። ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ሳናርፍ በፍጥነት ሮጥን::
አማጺዎች ተስፋ ቆርጠው ወደ ማታሩ ጆንግ ተመለሱ። እኛ ግን መሮጣችንን ቀጠልን፡፡

ለብዙ ቀናት ስድስታችን ጅኒየር ታሎ ካሎኮ፣ ገብሬላ፣ ካሊ እና እኔ በቀጭን መንገድ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ መሃል ተጓዝን፡፡ሁላችንም ሃሳብ ላይ እንመስላለን። ማውራት የለም፤ መሄድ
ብቻ:: ስለ ቤተሰቦቼ ደግሜ ላያቸው እችላለሁ ብየ አሰብኩ፡፡ማልቀስ ፈለኩ በጣም ስለ ራበኝ ግን አቅም አልነበረኝም ::

በተተወ መንደር ውስጥ ባዶ መሬት ላይ ተኛን።በሚቀጥለው ቀን ሙዝ፣ብርቱካን እና ኮኮናት ዛፍ በሚገኝበት መንደር አለፍን፡፡ ሙዙ ጥሬ ስለሆነ ቀቅለን ነበር የበላነው። ከዛ ትንሽ ብርቱካን እና ኮኮናት በላን። በቂ ምግብ ግን ማግኘት
አልቻልንም። ከቀን ቀን ረሃባችን እየተባባሰ መጣ። ስለዚህ ወደ
ማታሩጆንግ ተደብቀን በመግባት ምግብ መግዣ ገንዘብ ማግኘት አለብን፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ አልነበረንም።

በመንገዳችን ጸጥ ረጭ ባለ በተከዳ ከተማ ስናልፍ አስክሬን፣የተበላሸ ምግብ ፣ የእንጨት ስራዎች፣ ልብስ እና ሌሎች
እቃዎች በየቦታው ወድቆ አየን። አስክሬን ተቆራርጦ እጅ፣ እግር እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በየቦታው ወድቋል። ይሄን ሳይ አዞረኝ፤ አቅለሸለሸኝ። የነ ካሊሎ ቤት በከተማ እንዳሉ ሌሎች
ቤቶች በሩ ተሰብሯል ተቃጥሏል። የጥይት ቀዳዳ በበሩ በኩል ሲታይ ስታር ቢራ እና ሲጋራ መጠቅለያ ደግሞ ድጃፍ ላይ ወድቋል።

ገንዘቡን ባስቀመጥኩት ቦታ ሳይነካ አገኘሁት። ገንዘቡን ካልሴ ውስጥ ከትቼ ወደ ረግረጉ ወረድን፡፡ አማጺዎች ባህር ዳርቻው አካባቢ ማማ ላይ ወጥተው ይጠብቁ ስለነበር መንፏቀቅ ነበረብን፡፡ ከመካከላችን አንድ ልጅ ትልቅ ቦርሳ አንግቶ ስለነበር ጠባቂዎች አይትውት ተኩስ ከፈቱ።ከጠባቂዎች እስክንርቅ
ድረስ በፍጥነት ሮጥን።አመሻሽ ላይ ብዙ ሰዎች ያሉበት መንደር ውስጥ ገባን፡፡
ገንዘብ ስለያዝን ምግብ ይሸጡልናል የሚል ተስፋ ነበረን።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ለክፉ ጊዜ ምግብ መቆጠብ ስለምንፈልግ አንሸጥም ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ያለ ምንም ምክንያት አንሸጥም አሉ። ራሳችንን ወቀስን፡፡ የጦርነት ወቅት እንዲህ ተለዋዋጭ
ነው። ማንም አይቆጣጠረውም፡፡ ነገሮችን በፍጥነት መረዳትና
የመትረፌያ መንገዶችን መቀየስ ነበረብን። ያን ምሽት አማራጭ
ስላልነበረን ሰዎች ወደ መኝታ ሲሄዱ ምግብ ሰርቀን በላን::

ምግብ እና ውሃ ሳናገኝ ብዙ ስለቆየን
ጉሮራችን ተንቃቃ፣ ሆድ ቁርጠትም ተሰማን። ከንፈራችን ተጣበቀ መገጣጠሚያችንም ዝሏል። ምግብ የት እንደምናገኝ ግራ ገባን። በመጨረሻ ረሃብ ወደ ማታሩ ጆንግ እንደገና
መለሰን።

የበጋ ወቅት ስለ ነበር ሳር ቅጠሉ ቢጫ ሁኗል። በሳር መሃል እየሄድን ድንገት አማጺዎች መጡብን። ገብሬላ ላይ ሽጉጥ ደቀኑ፤ እኔ ላይ ደግሞ ጩቤ ሰነዘሩ፡ "ደንግጧል" ብሎ ከት ብሎ
ሳቀ፡፡ አልፈን ወደመጣንበት መንደር መለሱን፡፡ አማጺዎቹ እጅጌ ጉርድ ቲሽርት፣ ጂንስ ጃኬት እና ሱሪ ለብሰዋል እና አዲዳስ ጫማም ተጫምተዋል። እጃቸው ላይ ውድ ስዐቶች አስረዋል።
ሁሉም በጉልበት የተቀሙ ወይም የተዘረፍ ናቸው።

ፈራሁ! እጆቼ እና እግሬዎቼ ተንቀጠቀጡ።አማጺዎች ትንሽም እንኳ ለመንቀሳቀስ ከሞከርን እንደሚገሉን ዝተዋል።ከጓደኞቼ እንዱ ወይም ወንድሜ ቢንቀሰቀስ ለማምለጥ ቢሞክርና ቢገሉንስ ብየ ሰግቻለሁ።

በአቅራቢያው ወዳለ መንደር ስንደርስ የመንደሩን ነዎሪዎች ሴቶች ህጻናት ሳይሉ ሁሉንም አሰለፉ። መጀመሪያ ካሊሎ
ቀጥሎ እኔን እና ሌሎች ወንዶችን መረጠው ወደ ፊት እንድንመጣ አዘዙ።
"ጠንካራ ወታደሮችን እንፈልጋለን” በማለት ጅኒየር
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አምስት


#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ


#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


በቡድን መሆናችን እንድንተጋገዝ እና ችግርን በጋራ እንድናልፍ ቢረዳንም ሰዎች እኛን ሲያዩ ይፈሩ ጀመር። በእኛ
እድሜ ያሉ ታዳጊዎች በአማጺዎች ተገደው ይገድሉ ያቆስሉ ነበር። ስለዚህ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመጠበቅ ሲሉ እኛን ለመጉዳት ጥረዋል። እኛም ጥግጥጉን ይዘን መንደሮችን ማለፍ
ጀመርን። የጦርነት አንዱ መዘዝ ይሄ ነው። ሁሉም ሰው መተማመን ያቆማል፣ ጸጉረ ልውጥ ሰው በሙሉ እንደጠላት
ይቆጠራል። የሚያውቁህ ሰዋች እንኳ ሲያቀርቡህ ሲያወሩህ በጥንቃቄ ነው::

በአንድ መንደር ስናልፍ ገብሬላን የምታውቅ ሴትዮ አክስቱ ወደ ሰላሳ ኪሎሜትር የምትርቅ መንደር ውስጥ እንዳለች ነገረችው: አቅጣጫውን ጠቁማን ጉዞ ጀመርን።

የአዝመራ ወቅት እየተቃረበ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ዝናብ ዘንቧል መሬቱ ረስርሷል፡፡ ወፎች በማንጎ ዛፍ ላይ ቤታቸውን ይሰራሉ፡፡ ጠዋት ጠዋት ጤዛ ይታይ ነበር። አጎቴ በዚህ ወቅት
ነው መሞት ምፈልገው እያለ ይቀልድ ነበር። ፀሐይ ቀድማ ወጥታ በሰማያዊው ሰማይ ላይ ትታያለች።

የካማቶር ነዎሪዎች ሁሉም ገበሬ ናቸው። ማገዝ የግድ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና ጋር ተገናኘን። የመጀመሪያ
ስራችን የነበረው ማሳ ማጽዳት ነበር፡፡ ቅጠላቸው የተቆላለፈ የወይን ዛፎችን መቁረጥ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ሶስት ስዓት የሚፈጀውን ሶስት ቀን ቆየንበት።
ከዛ ዘራን።

ለሶስት ወራት ያህል በካማቶር በእርሻ ስራ ላይ ብንቆይም ልለምደው አልቻልኩም። የተመቸኝ ከስዐት እረፍት ላይ ለዋና ወደ ወንዝ የምንወርድበት ጊዜ ብቻ ነበር። ስራው ለፍቶ መና
ነበር። ምክንያቱም አማጺዎች ሲመጡ ትተነው እንሮጣለን ሰብሉ በአረም ይዋጣል ወይም እንስሳት ይበላል::
አንድ የአማጺዎች ጥቃት ግን ይባስ ብሎ ከወንድሜ ጋር አለያየኝ። ትልቅ ወንድሜን ጅኒ የርን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት
ያን ጊዜ ነበር።

ጥቃቱ የደረሰው በአንድ ለሊት ድንገት ነበር። ስለ አማጺዎች መድረስ ምንም ወሬ አልተሰማም :: ከየት መጡ ሳይባል
መንደራችን ገቡ።

ከምሽቱ ሁለት ስዐት አካባቢ ህዝቡ የቀኑን የመጨረሻ ጸሎት እያደረገ ነበር። ኢማሙ ብዙ እንደሚቆይ ይታወቃል፡፡ በህዝቡ ፊት ለፊት ሁኖ ረዥም የሱራ ጸሎት ያደርሳል። የአማጺዎችን
መግባት ሲሰማ ከኢማሙ በስተቀር ሁሉም መስጊዱን ጥሎ ሄደ። አማጺዎች ኢማሙን ብቻውን አግንተው ህዝቡ በየት
በኩል እንደሄደ ጠየቁት፡፡አልመለሰላቸውም፡፡ እጁን እና እግሩን
አስረው አቃጠሉት።

የአማጺዎች ጥቃት ሲጀምር ጅኒ የር እና ጓደኞቼ ቤት ውስጥ ነበሩ። እኔ ግን ደጃፍላይ ነበርኩ። ድንገት ተኩስ ሲጀምር
ፌቴን ሳላዞር ሩጬ ጫካ ውስጥ ገባሁ።አንድ ዛፍ ስር ብቻየን
አደርኩ። ሲነጋ ካሎኮን አገኘሁት። መንደሩ መሃል ላይ የኢማሙ የተቃጠለ አስክሬን ተጥሏል፤ ቤቶች ተቃጥለዋል
ህይወት የሚባል የለም:: በጥቅጥቁ ደን መኋል ጅኒ የር እና ጓደኞቻችንን ፈለግን
ግን ልናገኛቸው አልቻልንም።
የምናውቃቸው ሰዎች አግኝተን ለሁለት ሳምንታት ያህል ከነሱ ጋር በረግረጉ አካባቢ ተደበቅን። ሁለት ሳምንት ሁለት ወር ሆነብኝ፡፡ ስለእነ ጅኒየር አስባለሁ። አምልጠው ይሆን? ሁሉንም እያጣሁ ነው፦ቤተሰቦቼን፣ጓደኞቼን። በፍርሃት ውስጥ መኖር ሰለቸኝ:: ሞትን የምጠብቅ መስሎ ተሰማኝ። መንደሩ መልቀቅ ሰላም ወደ ሚገኝበት መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ:: ቆረጥኩ። ካሎኮ ግን ፈራ፤ በረግረጉ መቆየትን መረጠ።

ጠዋት ሁሉንም ተሰናብቼ ወደ ምዕራብ መጓዝ ጀመርኩ።በኪሴ ከያዝኩት ያልበሰለ ብርቱካን ውጭ ሌላ ምንም
አልያዝኩም:: ለስድስት ቀናት ያገኘሁትን እየበላሁ ተጓዝኩ።
በስድስተኛው ቀን ሰው አገኘሁ፡፡ የአንድ ቤተሰብ አባላት እየዋኙ ነበር። ሰላምታ ሰጠኋቸው፡፡ አልመለሱልኝም። ልብሴን አውልቄ ወደ ወንዙ ገባሁ፡፡ " ከየት ነው የመጣሃው ወዴት እየሄድክ ነው?” ሲል ጠየቀኝ።
ከማታሩ ጆንግ ነኝ ወዴት እንደምሄድ ግን አላውቅም” ስል መለስኩለት። ቀጥየ "ወደ ቦንቴ ለመሄድ አቋራጩ መንገድ የቱ
ነው” ስል ጠየቁ፡፡ ቦንቴ ስላማዊ ቦታ ነው ይባላል። በባህሩ በኩል እንድሄድ እና ሰዎችን እንድጠይቅ ነገረኝ።

ብዙ የተቃጠሉ መንደሮችን እያለፍኩ ተጓዝኩ፡፡ በመንደሮቹ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች ከአዋቂ እስከ ህጻናት አየሁ።አይናቼን ለመጨፈን ሞከርኩ ግን አልቻልኩም። በመጨረሻ ደነዘዝኩ።

ብዙ ስጓዝ ውየ ራሴን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ መሃል አገኘሁት።ከቆምኩበት ጫካ
ሰማዩን እንዳላይ በረጃጂም ዛፎች
ቅርንጫፎች እና ቅጠሎች ተጋርድዋል፡ እንዴት እዚህ ጫካ እንደገባሁ እንኳ አላውቅም። ለሊቱ ሲቃረብ ረጂም ቅርንጫፍ ካለው አንድ ዛፍ ላይ ወጥቼ አደርኩ።

በሚቀጥለው ቀን ከጫካው ለመውጣት ወሰንኩ። በጉዞየ በአንድ ትልቅ አለት ላይ የሚወርድ ፏፏቴ አየሁ። በዳርቻው
ትንሽ ለማረፍ ወሰንኩ። ግን ብዙም አልቆየሁም። ወደ ሃሳብ ከምገባ ብየ ጉዞየን ቀጠልኩ። ቀኑን ሙሉ ተጓዝኩ። ዙሬ ዙሬ በመጨረሻ ራሴን ትናንት ማታ ካደርኩብት እዛው ቦታ ላይ
አገኘሁት፡፡ እንደጠፋሁ አመንኩ። ስለዚህ ራሴን ማደላደል አዲሱ ቤቴን ማመቻቸት ጀመርኩ። ቅርንጫፎች ላይ ቅጠሎችን
ጨመርኩ።አካባቢውን ዙሬ ቃኘሁ። ምንም እንኳ ብጠፋ እና ብቻየን ብሆንም ለጊዜው ይሄ ቦታ ሰላማዊ ነው።
የፏፏቴው ጥግ ባልበሰሉ ፍራፍሬዎች ተሸፍኗል። አንዱን ቆርጬ በላሁ። መራራ ነው:: ነገር ግን ረሃብ ያስታግሳል።
ስለዚህ ወደ አስራ ሁለት የሚሆኑ ፍሬዎችን በላሁ። ከተወሰኑ ስዓታት በኋላ ገላየን ለመታጠብ አሰብኩ። ልብሴ ቋሽሽዋል፣የሰውነቴም ሽታ ተቀይሯል። መጀመሪያ በንጹህ ውሃ ቀጥሎ
በእንዶድ ገላየን ታጠብኩ ልብሴንም አጠብኩ።

አስቸጋሪው ነገር ብቸኝነት ነበር። ብቻህን ስትሆን ብዙ ታስባለህ ላቸማሰብ ሞከርኩ ግን አልቻልኩም፡፡ ወደ ጭንቅላቴ የሚመጡትን ሁሉንም ሃሳቦች ለመከላከል ወሰንኩ ብዙውን
ጊዜየን ሃሳብን በመዋጋት ማለትም ስለ ወደፊት ህይወቴ ማሰብ፡
ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ የት ናቸው የሚሉ ሃሳቦችን በመሸሽ አሳልፍ ነበር።
ይሄን ሳደርግ ራሴ ከመቼውም በላይ የጠነከረ መስለኝ። ሃሳቦቹ በህልሜ ይመጣሉ በማለት መተኛት ፈራሁ::

በጣም ትንሽ እያለሁ አባቴ የሚለው አባባል ነበር " በህይወት እስካለህ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ እና መልካም ነገር እንደሚሆን ተስፋ አለ። እጣ ፈንታቸው መጥፎ የሆነ ደግ ጊዜ
የማይመጣለቸው ሰዎች ግን ይሞታሉ።”በጉዞየ ስለዚህ አባባል
አስብ ነበር፡፡ እነዚህ ቃላቶች ወደፊት እንድሄድ እንድገፋ አበረቱኝ፡፡

በረሃብ ደክሜ እያዘገምኩ ስሄድ በእኔ የእድሜ ክልል ያሉ ህጻናት አጋጠሙኝ። ስድስት ነበሩ፤ ከስድስቱ ሶስቱ አልሃጂ፣
ሙሳ እና ኬን ማታሩ ጆንግ በሚገኘው ሴንትያል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብረውኝ ተምረዋል። እጃችንን በመጨባበጥ ሰላም ከተለዋወጥን በኋላ ወደየት እየሄዱ እንደሆነ ጠየቅኳቸው፡፡ በቦንቴ ወረዳ ወደ ምትገኝ የል ወደ ምትባል ሰፈር እየሄዱ እንደሆነ እና የል በ ሴራሌዮን መከላከያ ኃይል የሚጠበቅ
አስተማማኝ ሰላም ያለበት አካባቢ እንደሆነ ነገሩኝ። ተከተልኳቸው::

እንደገና የሰባት ህጻናት ቡድን፡፡ ሰዎች እኛን ሲያዩ ይጮሃሉ ይሮጣሉ። እንደአውሬዎች ተቆጠርን፡፡ ቦታ የሚያመለክተን አቅጣጫ የሚጠቁመን ሰው አልነበረም። ከስድስት ቀናት ጉዞ
በኋላ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘን። የመንደሩ ሰው እኛን ሲያይ ሩጦ እንደጠፋ እሱ ግን መሮጥ እንደማይችል ነገረን። ከየት እንደመጣን እና ወዴት መሄድ እንደምንፈልግ ነገርነው፡፡
ለተወሰኑ ቀናት ከእሱ ጋር
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ስድስት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ


#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

የተጠጋጉ ጎጆ ቤቶችን ተመለከትን። ከመንደሩ ስንደርስ ማንም የለም። ከእኛ ተደብቀው ነበር። ብዙም ሳይቆይ አሳ አጥማጆች መጥረቢያ፣ ጦር እና መረብ ይዘው ወጡ። ምንም ማድረግ
አልቻልንም። ባለንበት ደርቀን ቆምን።
እንግዲያውስ "እባካችሁ እኛ ልንጎዳችሁ አልመጣንም፧ መንገደኞች ነን”ብለን ጮህን።አሳ አጥማጆች በሰደፍ መተው ጣሉን፡፡ ከበላያችን ላይ ተቀምጠው ካስሩን በኋላ ወደ አለቃቸው ወሰዱን። ብዙ ጥያቄዎች ጠየቁን። ከየት እንደመጣን፣ የት እንደምንሄድ እና
ለምን ይሄን አቅጣጫ እንደመረጥን ተጠየቅን፡፡ በመጨረሻ እጅ እና እግሮቻችንን ፈተው ከመንደራቸው አባረሩን። ጫማችንን ግን አልሰጡንም::

ብዙ ከተጓዝን በኋላ ነበር አሳ አጥማጆቹ ምን እንደቀጡን የገባን፡፡ ፀሐይ ስትወጣ 120 ዲግሪ ሆነ። ምንም ምንጠጋበት
ዛፍ እንኳ አልነበረም፡፡ ፀሐይዋ አሽዋው ላይ ስታርፍ በጣም ሞቀ፤ ግለት ሆነ። በባዶ እግር አሽዋ ላይ ተራመድን።
እግሮቻችንን ቆሰሉ። ደነዘዝን።በመጨረሻ አንድ ጎጆ ቤት ላይ ደረስን፡፡ ወደ ውስጥ ገብተን ተቀመጥን፡፡ የቤቱ ባለቤት ብዙም
ሳይቆይ መጣ። በሩ ላይ ቆሞ ተመለከተን እና ጉዳታችንን ሲያይ ፊቱን ዙሮ ሄደ፡፡

ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሳር ይዞ መጣ። እሳት አያያዘ ከዛ ሳሩን በጥቂቱ እሳቱ እንዲለበለብ ካደረገ በኋላ ሳሩን ወደ እግሮቻችንን አስጠጋው:: ሙቀቱ ስቃያችንን አስታገስልን።ቀጥሎ የተጠበሰ አሳ ሾርባ፣ ሩዝ እና ውሃ ይዞ መጣ እና
ፊታችን ላይ አስቀምጦ እንድንበላ ጠየቀን፡፡ እንደገና ወቶ ሄደ፤
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ተመለሰ። የምንተኛበትን ምንጣፍ አሳየን፤ ከመተኛታችን በፊት እግሮቻችንን የምንቀባው ቅባት ሰጠን።

በሚቀጥለው ቀን ስም አልባው እንግዳ ተቀባይ ሰው ምግብ ይዞልን መጣ። ፊቱ ላይ ያለው ፈገግታ እየተሻለን እንደሆነና እሱም ደስ እንዳለው ነገረን።

በጎጆው ለሳምንት ቆየን።እንግዳ ተቀባዩ ጥዋት እና ማታ ምግብ ይሰጠናል።ጥርሱ ነጭ በረዶ ይመስላል ከወገብ በላይ ሁሌም ራቁቱን ነው ልብስ አይለብስም።አንድ ቀን ስሙን ጠየቁት።ምን ይጠቅምሀል ብለህ ነው። እንደዚሁ ይሻለናል ለደንነታችን አለኝ።

በሚቀጥለው ቀን አመሻሽ ላይ ወደ ውቅያኖስ ይዞን ወረደ።እግራችንን እንድንነክር ነገረን።ጨዋማ ውሃ ከስቃይ እንደሚያስታግስ እና ከቲታኖስ እንደሚጠብቀን ገገረን።

በሁለት ሳምንት ውስጥ ከህመማችን አገገጀምን።አንድ ጠዋት ግን ሽማግሌ ሴትዮ ከእንቅልፋችን ቀስቅሳ መሄድ እንዳለብን ነገረችኝ።የአስተናጋቻችን እናት ነበረች።መንደሩ ስለኛ እንደሰማና ሊይዙን እየመጡ እንደሆነ ነገረችን።የተጠበሰ አሳ እና ውሃ ሰታን 'ልጆቼ መፍጠን አለባችሁ ጸሎቴ ከናንተ ጋር ነው" አለች።

ፈጥነን ከአሳዳጆቻችን ማምለጥ አልቻልንም አስራ ሁለት ነበሩ። አሸዋ ላይ ጥለው እጆቻችንን አሰሩ።ወደ መንደሩ መልሰው አለቃቸው ፊት አቀረቡን።

እናንተ ህፃናት ትናንሽ ሰይጣናት ሁናችኋል። አሁን ግን ወደተሳሳተ መንደር ነው የመጣችሁት አለ። እንደእናንተ ላለ ሰይጣኖች እዚህ ጋር ይበቃል።

ልብሳችሁን አውልቁ ብሎ አዘዘ አለ ስም አልባው አስተናጋጃችን እና እናቱ በ ህዝብ መሃል ነበሩ። በአለቃው መቆጣት ስለ እኛ ሲሳቀቁ እና ሲከፉ አየሁቸው። ልብሴን
ሲያወልቁ የራፕ ካሴት ከኪሴ ወደቀ። አለቃው ካሴቱን መረመረ እና የካሴት መጫወቻ እንዲመጣ አዘዘ፡፡
መጥቶ ሙዚቃው ተከፈተ። አለቃው ጠራኝ እና እንዴት እንደምንደንስ ማሳየት ጀመርኩ። ሞቴን ሳስብ መዳነስ ከበደኝ፤
ምቱም ጠፋብኝ፡፡ አለቃው ግን መረጋጋት ጀመረ። ልጆች መሆናችንን አወቀ። በድንገት ጓደኞቼ እንዲፈቱ አዘዘ። አለቃው ለህዝቡ ስህተት እንደሆነ እና ልጆች መሆናችንን እና ራሳችንን
ለማትረፍ እንደመጣን ተናገረ::
አለቃው ነጻ እንዳደረገን እና በፍጥነት አካባቢውን ለቀን እንድንወጣ ነገረን።

በጉዞየ ከሚረብሽኝ አንድና ዋናው ነገር ጉዞው የት እና መቼ እንደሚቋጭ አለማወቄ ነው፡፡ ይሄ ጥያቄ አዕምሮየን፣ ሰውነቴን እና ስሜቴን በጉዞየ ሁሉ ሲጎዳ ቆይቷል። በህይወቴ ምን እንደምሰራ ወደ የት እንደማመራ አላውቅም:: በየጊዜው እንደገና እንደምጀምር ይሰማኛል። አሁን የህይወቴ ዋና አላማ መትረፍ
ብቻ ነው። ለትንሽ ጊዜም ቢሆን እራሳችንን በምግብ እና በንጹህ
ውሃ ለማስደስት እንሞክር ነበር። በተለያዩ ስሜቶች ከመዋለል መከፋት ቀላል ነበር፡፡ ወደፊት መግፋት እንዳለብኝ አወቅኩ።
የባሰ አለ ብየ ስላሰብኩ አልተካፋሁም።

ጉዞችን ደመና እንደሽፈናት እና ለመውጣት እንደምትፍጨረጨር ጨረቃ መስሎ ታየኝ፡፡ ጨረቃዋ በመጨረሻ ትወጣለች ለሊቱንም ሙሉ ብርሃንዋን ትሰጣለች::

አንድ ቀን ሰኢዱ ”ብዙ ቀን ሰዎች ሊገድሉን ሲመጡ አይኖቼን ጨፍኜ ሞትን ጠብቄለሁ። እስከአሁን አልሞትኩም::
ሞትን በተቀበልኩ ቁጥር ግን አንድ አካሌ እንደሞተ ይሰማኛል። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሙሉ ለሙሉ እንድምሞት ይሰማኛል። ያኔ
ባዶ ስውነቴ ብቻ አብሮችሁ ይጓዛል። ከአሁኑ በላይ ዝምተኛ ይሆናል" አለ። አይኖቼ እንባን አቀረሩ፤ ግንባሬም ሞቀ። የሰኢዱ ን ቃላቶች እያሰብኩ እስኪነጋ ድረስ መተኛት አልቻልኩም::

ጉዞችን አስቸጋሪ ቢሆንም አንዳንዴ ለትንሽ ደቂቃ ቢሆንም መዝናናት እንሞክራለን። አንድ ቀን አንድ መንደር ስንደርስ ሰዎች ለአደን እየተዘጋጁ ነበር። አብረናቸው እንድናድን ጋበዙን፡፡ ከአደን በኋል ምግብ ለሚያዘጋጁ ሴቶች ውሃ በመቅዳት አገዝን፡፡

ምሽት ላይ ሁሉም መንደርተኛ ወደ መንደሩ ተመለሰ፡፡ምግቡ ወደ መንደሩ አደባባይ ወጣ፡፡ ለሁሉም በስሃን ታደለ።
ከምግቡ በኋላ ከበሮ መምታት ተጀመረ:: ሁላችንም እጅ ለ እጅ ተያይዘን ክብ ሰርተን በጨረቃ ብርሃን መዳነስ ጀመርን።
በመሃል የት እንደመጣን ስለእኛ ታሪክ እንድናካፍል ተጠየቅን፡፡ቆይቶ ዳንሱ ቀጠለ።

ሲነጋ ውሃ እና መንደርተኛው የሰጠንን የተጠበሰ ስጋ ይዘን ጉዞችንን ቀጠልን፡፡ "የአባቶቻችሁ አምላክ ይከተላቹህ" ብለው ሸኙን።

ፀሐይዋ ስታዘቀዝቅ ወደ አንድ ልዩ መንደር ደረስን። መንደር ለማለት ይከዳል:: አንድ ትልቅ ቤት አንድ ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ ደግሞ ጭስ ቤት ብቻ ነበር የሚገኘው:: አማጺዎች በቀላሉ
ሊይዙት የሚችሉት ሰፈር" ብሎ ጅማህ ሳቀ።

ሰው መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሰፈሩን ሙሉ ዙረን አየነው:: የወይራ ዘይት ሲመረት እንደነበር ምልክቶች አሉ።
ወንዙ ላይ ሳር የበቀለብት ታንኳ አለ። ወደ ትልቁ ቤት ተመልሰን ይዘነው የመጣነውን የተጠበሰ ስጋውን እና ውሃ አስቀመጥን።
ብዙም ሳይቆይ መሸ እና ከጓደኞቼ ጋር ተኛን፡፡ የሊሊቱ አጋማሽ እስከሚደርስ ግን እንቅልፍ አልወሰደኝም። ሴት አያቴን
አስታወስኩ:: "እንደ እሳት እኮ ነው ያደግከው: ስም የወጣልህ ቀን እንደ ትናንት ትዝ ይለኛል" ትላለች :: ሰፊ ድግስ ተደግሶ በግ ዶሮ ታርዶ ከተበላ ከተጠጣ በኋላ ኢማሙ ፊት ቀርቤ "ኢስማኤል ተብሎ ይጠራ እንዳለ እና ታዳሚው እንዳጨበጨበ ከዛም ጭፈራ እልልታ እንደነበረ ትነግረኛለች...

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሰባት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ


#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


ጥዋት ስንነሳ ስጋው ተበልቶ አገኘን። ማን እንደበላው ግራ ገባን። መጀመሪያ ራስ በራሳችን ተጠቋቁመን ነበር። በኋል ግን ውሻ ሆኖ አገኘነው አልሀጂ በጣም ተናዶ ውሻውን ካልደበደብኩ ብሎ ተከላከልነው፡፡ ውሃችንን ይዘን ጉዞችንን
ቀጠልን፡፡ ቀትር ላይ ያገኘነውን ፍራፍሬ ለመብላት ሞከርን።እስከ ማታ ድረስ በመካከላችን ምንም አይነት ንግግር
አልነበረም። ምሽት ላይ ለማረፍ ወሰን።

አልሃጂ "ውሻውን መግደል ነበረብኝ" አለ።

ለምን? አልኩ እኔ

እኔን ተከትሎ “ምን ትርጉም አለው? የሱ መሞት ምን ያደርግናል" አለ ሞሪባ፡፡
አልሃጂ " ያለንን ብቸኛ ምግብ ነዋ የበላብን። ጥሩ ስጋ ይሆን ነበር።
"አይመስለኝም! ደግሞ ማዘጋጀቱ አስቸጋሪ ይሆን ነበር አልኩ።

ሙሳ ደግሞ ውሻውን ቢገድለው ኖሮ እበላው ነበር አለ። አባቴ ማሌዥያውያን ውሻ እንደሚበሉ ነግሮኛል።አልሃጂ ገድሉት ቢሆን ንሮ በልቼ እሞክረው ነበር። አባቴን እንደገና ሳገኘው የውሻ
ስጋ እንደሚጥም እና እንደማይጥም እነግረው ነበር አለ፡፡ጉዞችንን ማታ ለማድረግ ወሰን፡፡ ቀን ምግብ እንፈልጋለን
ተራ ይዘን እንተኛለን፡፡ ማታ ጨረቃዋ ምትከተለን ይመስላል።ሲነጋ ትጠፋ እና በሚቀጠለው ቀን እንደገና መታ መንገዳችንን ትመራለች።
አንድ ቀትር ላይ ኦና በሆነ መንደር ዉስጥ ምግብ ስንፈልግ ቁራ ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ ከሰማይ ወደቀ። አልሞተም ነገር ግን መብረር አልቻለም፡፡ ያልተመደ ነገር ነበር፤ ምግብ ግን ፈልገን ነበር። ላባዋን ስንነጭ ሞሪባ ምን ቀን እንደሆነ ጠየቀን። ማንም ሚያውቅ አልነበረም::

"ዛሬ የባዕል ቀን ነው" አለ ኬን እየሳቀ፡፡ "የፈለጋችሁትን ቀን ልትሰይሙት ትችላላችሁ::"
" የቁራው መውደቅ የእርግማን ምልክት ነው መብላት የለብንም" አለ ሙሳ።

"እንግዲህ የእርግማን ምልክት ከሆነ እኛም እርጉማን ነን፡፡ ስለዚህ በደንብ አድርጌ ነው ምበላው:: የፈለከውን ማድረግ ትችላላህ" አለ ኬን፡፡
ብዙም ሳይቆይ ማታ ሆነ፡፡ ከባድ ጸጥታ! ንፋሱ እና ደመና አንድ የሚጠብቁት ነገር ያለ ይመስል መንቀሳቀሳቸውን
አቆሙ:: ለሊቱ በጣም ጨለማ ነበር። ጫካ ላይ አልነበርንም ጨለማው ግን ለመተያየት አስቸጋሪ ነበር። ሶስት ሰዎች ወደ እኛ ሲመጡ አየን፡፡ በዛፎች መሃል ተደብቀን ማየት ጀመርን።እኛ በመጣንበት አቅጣጫ ሄዱ፡፡ ከተደበቅንበት እየተጠራራን መውጣት ጀመርን። ሰኢድ ግን ሊነሳ አልቻለም። በፍርሃት ደነዘዘ ሊንቀሳቀስ አልቻለም:: በመጨረሻ ኬን ተሸክሞት ድልድዩን ተሻገርን፡፡
ድልድዩን እንደተሻገርን ሰኢድ አስነጠሰ፡፡ ኬን አስቀመጠው እና አስታወከ፡፡ በኋላ " መናፍስት ነበሩ አይደል ማታ ያየናቸው" አለ፡፡
ሁላችንም ተስማማን፡፡

“ራሴን ስቼ ነበር። አሁን ደህና ነኝ እንሂድ" አለ፡፡ እኩለ ቀን ሲሆን አንድ ትልቅ መንደር ደረስን። ገበያ ነበር የሚመስለው:: ሰዎች ያዜማሉ ይጨፍራሉ ልጆች ውርውር
ሲሉ የምግብ ሽታ:: ወደ መንደር ቀስ ብለን ገብተን እንጨት ላይ ተቀመጥን።
ሰዎች አዩን አንዳንዶቹ ከዚህ በፊት የምናውቃቸው ይመስላሉ::
እጃቸውን እያውለበለቡ ሰላም አሉን፡፡ አንድ ሴት ወደ እኛ መጥታ አውቅሃልሁ አለችኝ፡፡ አኔ ግን ላውቃት አልቻልኩም::
ጅኒየር እኔን እየፈለገ መጥቶ እንደነበረ እና እናቴን አባቴን እና ትንሽ ወንድሜን ከሚቀጥለው መንደር እንዳየቻቸው
ነገረችኝ፡፡ ከዛ መንደር ብዙ የማታሩ ጆንግ ሰው አለ እናንተም ዘመዶቻችሁን ልታገኙ ትችላላችህ አለች ወደ ጓደኞቼ ፊትዋን
ዙራ።

ወዲያው ለመሄድ ፈልጌ ነበር ነገር ግን በቀጣዩ ቀን ለመሄድ ተስማማን፡፡ በዛ ላይ ሰኢድ እረፍት ያስፈልገዋል::
ወደ ወንዝ ወርደን ዋኘን ድብብቆሽ ከተጫወትን በኋላ ድስት ሙሉ ሩዝ ሰርቀን በላን፡፡

ያን ምሽት መተኛት አልቻልኩም::

አልሃጂ "ውሾቹ ቀሰቀሱኝ” አለ

እኔ እንኳን ከመጀመሪያው አልተኛሁም አልኩ፡፡

ቤተሰቦችህን ለማየት ጓጉተሃል አይደል አለ አልሃጂ። "እኔም አለ እየሳቀ፡፡ ውሻወቹ ጩሀት ግን አልተለየብሁም?”
ትንሽ ቆይቶ መንደርተኛው ነቃ:: እኔ እና አልሃጂ ሁሉንም ከእንቅልፍ ቀሰቀስና ቸው:: ሰኢድ ሊነሳ አልቻለም:: "ተነስ
መሂድ አለብን" እያልን በጣም አንቀሳቀስነው። ሊነሳ ግን አልቻለም:: እንደገና ራሱን ስቶ ይሆን አልን። አንድ ትልቅ ሰው መጥቶ ውሃ አፈሰሰበት። ሰዒድ አልተንቀሳቀስም። ሰውየዋ
ፊቱን አዙሮ ትንፋሹ አዳመጠ። ቀስ ብሎ " ከዚህ መንደር የምታውቁት ሰው አለ ብሎ ጠየቀን፡፡ አናውቅም ብለን መለስን።
ኬንን ወስዶ በጆሮው አንድ ነገር ነገረው:: ኬን ማልቀስ ጀመረ። ሰዒድ ጥሎን እንደሄደ አወቅን፡፡ ሁሉም ማልቀስ ጀመሩ እኔ ግን ለደቂቃዎች ደንዝዥ ነበር። ኬን እና ትልቁ ሰውየ የመቃብር ሳጥን አምጥተው የስዒድን አስክሬን ሳጥኑ ውስጥ አስገቡ።በነጭ አንሶላ ተጠቅልሎ በእንጨት ሳጥን ውስጥ ከጠረጴዛ ላይ
ተቀመጦ ጸሎት ማድረግ ተጀመረ። ሰሙን እየጠራ ጸሎት ማድረግ ሲጀመር እንባየ ከፊቴ ላይ ኮለል ብሎ መፍሰስ ጀመረ።የስዒድን ትቶን መሄድ ማመን አልቻልኩም፡፡ ራሱን እንደሳተ
እና እንደሚመለስ ለማስብ ስጀምር ወደ መቃብር አስገቡት።እንባየ መሬት ላይ ተንጠባጠበ።

ከቀብር ስነ ስርዐቱ በኋላ ብቻችንን ቀረን። አንድ ነገር እንደሚጠብቅ ሰው ለስዓታት በመቃብሩ ቦታ ተቀመጥን። በጣም ልጆችን ነበርን። ከኬን በስተቀር ከአስራ ሶስት አመት በታች! ኬን ሶስት አመት ይበልጠናል። ምሽቱ ሲቃረብ
ከመቃብር ስፍራው ተንቀሳቀስን።

ሰዒድ ያለው አንድ ነገር ትዝ አለኝ " አንድ አካሌ እንደሞተ ይሰማኛል ::"

ሲነጋ የቀብር ስነ ስርዐቱ እንዲፈጸም የረዱንን አመስገን።ከመካከላቸው አንድ "የት እንዳረፈ ሁሌም ታውቃላችሁ አለ"።
በስምምነት ራሳችንን ነቀነቅን፡፡ ወደዚህ መንደር የመመለስ እድላችን አንስተኛ ነው:: ነገን አናውቅምና። ጓደኛችንን ጥለነው እየሄድን ነው" እናቴ እንደምትለም "የዚህ አለም ጊዚያዊ ሩጫውን ጨረሰ”::

ለሊቱን ሙሉ በጸጥታ ተጓዝን። ለትንሽ ደቂቃ ስናርፍ ሞሪባ ራቅ ብሎ ከተቀመጠ በኋላ ማልቀስ ጀመረ። ራሱን ለመቆጣጠር በቅጠሎች መጫወት ጀመረ።ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ጉዟችንን ቀጠልን።

"መንደሩ ስንደርስ እናቴን ጥብቅ አድርጌ ነው ማቅፋት” አለ አልሃጂ።

ሁላችንም ሳቅን፡፡

ወደ መንደሩ ስንቃረብ ቤተሰቦቻችንን እንደምናገኛቸው ተሰማኝ፡፡ ፈገግታየ አልተቋረጠም። የቡና ዛፎች ደኑን መተካት ጀምረዋል። በቡናው ተቃራኒ መለስተኛ የሙዝ እርሻ አለ፡፡ ከኛ
ተሻግሮ አንድ ሰው ያልበሰለ ሙዝ ሲቆርጥ አገኘነው::

ሰላም ዋሉ?" አለ ኬን።

ሰውየው ጎር ጋስሙ ይባላል። ወንደላጤ ነው:: ሰዎች ትልቅ ሰው አይደል ለምንድን ነው የማያገባው:: የግድየለሽ ኑሮ
የሚኖረው" ይላሉ። ምንም መልስ አይሰጥም::

ጋስሙ ፈገግ አለ። ያዙ አለን ሙዝ።

“አባትህ እና እናትህ ሁሌም ስለ አንተ ያወራሉ ይጸልያሉ” አለ ወደ እኔ ዙሮ።" አሁን ሲያዩህ በጣም ነው ደስ ሚላቸው" አለኝ።መንደሩ ተራራ ላይ ነው አለኝ እና መሮጥ ጀመርኩ። መንገዱ አዙሪት ነበር፡፡ ጫፍ ላይ ስንደርስ ደክሞን ተቀመጥን፡፡

ከተራራው ስወርድ የጥይት ተኩስ ተሰማ።ሰዎች መጮህ ማልቀስ ጀመሩ:: ሙዙን ጥለን በዛፎች መሃል ተሸሸግን።

በመጨረሻ አቆመ ሁሉም ነገር ጸጥ ረጭ አለ። ጋስሙን ወደ መንደሩ መሄድ እንደምፈልግ ስነግረው እጆቼን ያዘኝ፡፡ እጄን አስለቅቄ ወደ ታች ሮጥኩ፡፡ መንደሩ ስደርስ ሁሉም ነገር ተቃጥሏል። የት ጀምሬ እንደምፈልጋቸው
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ስምንት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ


#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

..ለቀናት የተጓዝን ይመስለኛል። ሁለት ስዎች ድንገት ግንባራችን ላይ መሳሪያ ደቅነው ተንቀሳቀሱ እስከ ሚሉን ድረስ
ምንም አላስታውስም:: ከባድ መሳሪያ AK 47፣03 እና HPG ይዘው በሁለት ረድፍ ነዱን:: ፊታቸው በጣም ጥቁር ከመሆኑ የተነሳ ክስል የተቀቡ ነበር ሚመስለው። ቀይ በርበሬ በሚመስሉ
አይኖቻቸው አፈጠጡብን። በመንገዳችን የደንብ ልብሳቸው በደም የተጨማለቀ አራት ሰዎች መሬት ላይ ወድቀዋል። ፊቴን
ለማዞር ስሞክር ራሱን የተመታ ሌላ ሰው ተመለከትኩ።አጥወለወለኝ፡፡ ሁሉም ነገር በዙሪያዬ ሲሽከረከር፤ ሲዞርብኝ አንዱ ወታደር ተመለከተኝ። የውሃ ዕቃውን አውጥቶ ትንሽ ከተጎነጨ በኋላ የቀረውን ፊቴ ላይ ደፋብኝ፡፡

“ትለምደዋለህ ፤ ሁሉም ሰው በመጨረሻ ይለምደዋል” አለ።

የተኩስ ድምፅ ድንገት አካባቢውን አናወጠው። ወታደሮቹ ስድስታችንን ይዘው ተንቀሳቀሱ፡፡ የወታደር ጀልባ ከመተረጊስ ጋር የሚንሳፈፍበት አንድ ወንዝ ደረስን :: በወንዙ ዳርቻ የአስራ
አንድ ፣ አስራ ሁለት አመት የሚሆናቸው ታዳጊ ወታደሮች አስክሬን ወድቋል:: ፊታችን አዙረን ጉዞችንን ቀጠልን። የተኩሱ ድምጸ እየጨመረ መጣ፡፡ ወደ ጀልባው ስንወጣ ተኩሱ ወደ እኛ
ተቃረበ። ሮኬት ይወረውራሉ፤ የወንዙ የላይኛው ክፍል በተኩስ ተናወጠ፡፡ እሳት ላይ እንደተጣደ ወሃ ወንዙ በጥይት ናዳ ፈልቶ ይፈለቀለቃል:: የወታደር ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጀልባዎች እየሮጠ ወደ ወታደሮቹ መተኮስ ጀመረ:: ከእኛ ጀልባ ካሉት ወታደሮች አንዱ ተኩሶ ሰውየውን ጣለው:: ጀልባዎቹ ወደ ታች ሲወርዱ ዘለን ወጣን፡ ወታደሩ ጦር ወደ ሰፈረበት የል ወደ ሚባል መንደር ይዞን መራን። ከአስር ቤቶች በላይ ያሉበት ትልቅ
ሰፈር ነው። አብዛኞቹ ቤቶች በወታደሮቹ የተያዙ ናቸው።ወታደሮቹ እኛ በገባንበት በወንዝ ዳርቻ በኩል ካሉት ዛፎች
በስተቀር በአካባቢው ያሉ ዛፎችን ቆርጠዋል። ከድንገተኛ ጥቃት
ራሳቸውን ለመታደግ እንዳደረጉት አስረዱን::

በመጀመሪያ በዚህ በ የል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ደህንነት ያገኘን መስሎን ነበር። መንደሩ ሞቅ ደመቅ ያለ ሳቅ
እናጨዋታ የሞላበት ነበር፡፡ አዋቂዎች፣ የታጠቁ እና ያልታጠቁ የመንደሩ ሰዎች ስለ አየር ንብረት፣ ስለ አዝመራ እና ስለ አደን ያወራሉ። ስለ ጦርነቱ ግን ምንም ማውራት አይፈልጉም አያወሩም፡፡ በመጀመሪያ ሰዎች ለምን እንደዚህ እንደሚሆኑ አልገባኝም ነበር፡፡ ቀስ በቀስ የሰዎች ፈገግታ ስለ ምንም ነገር
መጨነቅ እንደሌለብኝ እምነት አሳደረብኝ፡፡ የሰፈሩ ቀልብ ግን
ያለ አባት እና እናት በቀሩ ልጆች የደበዘዘ ይመስላል።እድሜቸው ከስድስት እስከ አስራ ስድስት የሚሆኑ ወደ ሰላሳ
የሚጠጉ ልጆች ነበሩ። አንዱ እኔ ነበርኩ። ልጅነታችን ለጊዜው ችግር ይግጠመው ወይም ሙሉ ለ ሙሉ እንሰረቅ አናውቅም።

ተሰርቶ ባላላቀ የጡብ ቤት ውስጥ ከሌሎች ልጆች ጋር ማደር ጀመርን። ወታደሮቹ ከእኛ ራቅ ብሎ ባለ አንድ ትልቅ ቤት ውስጥ ፊልም ያያሉ፣ሙዚቃ ያደምጣሉ፣ ይስቃሉ ማሪዋና ያጨሳሉ
ሽታው ስፈሩን ሁሉ ያዳርስ ነበር። ቀን ቀን ከህዝቡ ጋ ተደባልቀው ምግብ እየሰሩ ያሳልፋሉ። ኬን እና እኔ ውሃ በመቅዳት ስሃን በማጠብ እናግዝ ነበር። ሌሎቹ ጓደኞቻችን ሽንኩርት ከተፋ እና መሰል የማዕድ ቤት ስራዎችን ይረዱ ነበር፡፡ ሙሉ ቀን በስራ መጠመዴን ወደድኩት፥
ወንዝ መውረድ፣ መመለስ እና ስሃን ማጠብ፡፡ ከባድ ራስ ምታት
ከሚያስከትልብኝ ሃሳቦች መራቂያ መንገዱ ይሄ ብቻ ነበር።
እኩለ ቀን ሲሆን ሁሉም ስራ አልቆ ምግብ ይቀርባል። ወላጆች ደጃፍ ላይ ተቀምጠው የልጆቻቸውን ፀጉር ይሰራሉ፣ ሴቶች ይዘፍናሉ ወንዶች ደግሞ ኳስ ይጫወቱ ነበር። ደስታው ጫጫታው ከወንዙ ባሻገር ሳይሰማ አይቀርም። በዚህ መንደር ህይወት በፍርሃት አይኖርም፡፡

የኳስ ጨዋታው በማጊቦ የነበረውን የሊግ ጨዋታ አስታወሰኝ፡፡ የእኔ ቡድን ማለትም እኔ እና የተወሰኑ ጓደኞቼ ያሸነፍንበት የዋንጫ ጨዋታ ትዝ ይለኛል። ወላጆቼ ጨዋታውን ለመመልከት ታድመው ነበር፡፡ ጨዋታው ሲጠናቀቅ እናቴ ኩራት እና ደስታ በተደባለቁበት ስሜት ፊቷ በርቶ ተነስታ አጨበጨበች፡፡ አባቴ ደግሞ እኔ ወዳለሁበት ከመጣ በኋላ ራሴን
አሻሽቶ ቀኝ እጄን ወደ ላይ በማንሳት አሸናፊነቴን አወጀ፡፡ ለጁንየርም ተመሳሳይ አደረገ። እናታችን ቀዝቃዛ ውሃ በኩባያ
አመጣችልን። ደስታው የልብ ምቴን ጨመረ፤ ሰውነቴ በላበት ተጠመቆ ነበር። ከጨዋታው በላይ የአባቴ እና እናቴ ደስተኛ መሆን ደስታየን ጨመረው፡፡

አሁን ግን ራሴን ከጨዋታው አገለልኩ። ከቤቱ ጀርባ ተቀምጨ የራስ ምታቴ እስኪበርድ ድረስ ሰማዩን ስመለከት
ቆየሁ፡፡ የራስ ምታት በሽታ ማይግሬን እንደሚያሰቃየኝ ለማንም አልተናገርኩም፡፡ የወታደሮቹ ሐኪም ጠዋት ጠዋታ ልጆችን ስብስቦ ጉንፋን እና ሌሎችን በሽታዎች እንደተሰማቸው ጠይቆ ህክምና ይሰጣል፡፡ አንድም ቀን ግን ቅዥት ወይም የራስ ምታት በሽታ ማይግሬን የሚያስቃየው ልጅ ካለ ብሎ ጠይቆ አያውቅም!ማታ አል ሃጂ፣ ጁማህ፣ ሞሪባ እና ኬን በትናንሽ የአለት
ድንጋዮች ገበጣ ሲጫወቱ ነበር። ሙሳ በሰፈሩ ታዋቂ ለመሆን ብዙም ጊዜ አልፈጀበትም። ልክ እንደ ዛሬው ሙሳ ሁሌም ማታ ማታ ለሰፈሩ ልጆች ተረት ተረት ያወራል። እኔ ግን በቤቱ ጥግ
ላይ ቁጭ ብየ ጥርሴን ነክሼ ስቃየን ውጭ አያቸዋለሁ። በአይነ ህሊናየ የእሳት ነበልባል፤ በመንገዴ ያየሁዋቸው አስቃቂ ነገሮች በጨረፍታ እና የህጻናት እና ሴቶች መራራ ጩኸት ይመጣል።ጭንቅላቴ እንደ ደወል ሲደበደብ በዝምታ አለቅሳለሁ። አንዳንዴ የራስ ምታት በሽታው ማይግሬኔ ሲበርድልኝ ለአፍታ ቢሆንም እንቅልፍ ይወስደኛል። ብዙም ሳልቆይ በቅኝዥት እባንናለሁ።
አንዴ ጭንቅላቴ ላይ በጥይት ሲመታ በህልሜ አየሁ። በደም ተጨመለቄ ወድቄለሁ ሰዎች ግን በጥድፊያ ያልፉኛል። ዉሻ መጥቶ ደሜን ይልሳል። ላባርረው ብፈልግም አቅም አልነበረኝም
መንቀሳቀስም አልቻልኩም። በመጨረሻ የፈራሁትን ነገር ከማድረጉ በፊት ከእንቅልፌ ባነንኩ። ከዛ በኋላ የቀሪውን ለሊት መተኛት አልቻልኩም:: አልቦኝም ነበር።

አንድ ቀን የመንደሩ ሁኔታ ድንገት ተለወጠ። ወጥረት ሆነ የውጥረቱ ምክንያት ባይታወቅም አንድ ከባድ
ነገር እንደሚከተል መገመት ይቻላል። በመንደሩ የሚገኙ ሁሉ ወታደሮች የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው ትጥቃቸዉ
አሟልተው ተሰበሰቡ፡፡ “ተጠንቀቅ” “አሳርፍ” “ተጠንቀ “አሳርፍ” :: ከአል ሃጂ ጋር ውሃ ለመቅዳት ወንዝ ስወርድ ነው
የአሰልጣኙን ድምፅ የሰማሁት። ስመለስ ልምምድ አብቅቶ መቶ አለቃ ጃባቲ በወታደሮቹ ፊት ቁሞ ይናገራል። ለምሳ
እስከሚለቀቁ ድረስ ለስዐታት ንግግር አደረገ። መቶ አለቃ በሚናገርበት ወቅት የዕለት ተዕለት ስራችንን እየሰራን ምን
እንደሆነ በልጅ አዕምሮችን ለመረዳት እንሞክር ነበር።

ማታ ወታደሮቹ ጠበንጃዎችን ሲያጸዱ ፤ አልፎ አልፎ ወደ ሰማይ በመተኮስ አሳለፉ። ህጻናት ተኩሱን ሲስሙ ወደ ወላጆች እቅፍ ሮጡ። ወታደሮቹ ገሚሶቹ ሲጋራ ማሪዋና ሲያጨሱ የቀሩት ቁማር ሲጫወቱ እና ፊልም ሲያዩ ለሊቱ ተቃረበ።
መቶ አለቃ ጃባቲ ቤቱ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብሎ መፅሐፍ ያነብ ነበር።ቀና ብሎ አያይም። ቢጮሁ ቢያፏጩ ቀና ብሎ አያይም።ያለ ወትሮው ፀጥታ ሲሰፍን ድምጸ ሲጠፋ ግን ቀና ብሎ አካባቢውን ይቃኛል። ወደ እሱ ስመለከት አይናችን ተጋጨ እና ወደ እሱ እንድመጣ ጠራኝ፡፡ ቁመቱ ረጂም፣ ፀጉሩ የሳሳ፣ አይኖቹ ትልልቅ እና ጉንጩ ወፍራም ነበሩ። ዝምተኛ ነገር ግን በዝምታው
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ዘጠኝ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


የሰባት አመት ልጅ እያለሁ የሼክስፒር ቃለ ተውኔትን ለማቅረብ ወደ ከተማ አዳራሽ እሄድ ነበር፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ
አዋቂዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ። ረጂም ጣውላ ወንበር ላይ ተቀምጠው ውይይታቸው ሲያልቅ የሼክስፒር ቃለ ተውኔትን እንዳቀርብ እጠራለሁ። አባቴ ጸጥታ እንዲሰፍን እና
ተውኔቱ እንዲጀምር ደመቅ አርጎ ያነጥሳል። እጁን አጣምሮ ከደማቅ ፈገግታ ጋር ፊት ለፊት ይቀመጥ ነበር። ወንበር ላይ እወጣና ረጂም ዱላ እንደ ሰይፍ በመጠቀም እጀምራለሁ።
ከጅሊየስ ቄሳር “ጓደኞቼ፣ ሮማዊያን፣ የሃገሬ ልጆች እስኪ ጀሮችሁን ስጡኝ፡፡ ብየ እጀምራለሁ። አዋቂዎች የሚወዷቸው
ስለነበሩ ብዙ ጊዜ ማክቤዝ እና ጅሊየስ ቄሳርን ነበር ማቀርበው።የእንግሊዝኛ ቋንቋን የመናገር ችሎታየ የዳበረ እና ጥሩ የሆነ ስለሚመስለኝ በከፍተኛ ጉጉት እና ደስታ ነበር ማቀርበው::

ወታደሮቹ በእኩለ ለሊት ሲገሰግሱ ነቅቼ ነበር። የኮቴቸው ድምጸ በሙሉ መንደሩ አስተጋባ። ቀኑን ሙሉ ጆሮዎየ ላይ
ሲያቃጭልብኝ ዋለ። አስር ወታደሮች ሰፈሩን እንዲጠብቁ ከእኛ ጋር ቀሩ። በየምድብ ቦታቸው ቀኑን ሙሉ ሲጠብቁ ዋሉ። ምሽቱ ፥ሲቃረብ ወታደሮቹ ወደ ሰማይ በመተኮስ እና የመንደሩ ሰዎች
ወደ “ቤት እንዲገቡ” እንዲሸሸጉ በማዘዝ የስዓት እላፊ አወጁ።ያን ምሽት ሙሳ ተረት አላወራም ሞሪባም ከልጆች ጋር ገበጣ አልተጫወተም፡፡ በዝምታ ጀርባችንን ለግድግዳው ሰጠን
ተቀምጠን የተኩስ እሩምታ ሲዘንብ ከርቀት እናዳምጥ ነበር።ለሊቱ እስኪገባደድ የመጨረሻ ስዓት፤ ጨረቃ በጉም መሃል አልፋ ፊቷን በክፍቱ የቤታችን መስኮት እስከምታሳይ እና
በአውራ ዶሮ ጩኅት ለሊቱ እስከሚባረር ድረስ ተኩሱ ቀጠለ።

ፀጠዋት ከፀሐይዋ መውጣት ጋር መመለስ የቻሉ የተወሰኑ ወታደሮች ብቻ ወደ መንደር መጡ። የተወለወለ ኮሬ ጫማቸው በጭቃ ተበላሽቷል። ፈንጠር ፈንጠር ብለው መተማማኛ የመሰላቸውን መሳሪያቸውን አቅፈው ተቀምጠዋል። ብሎኬት ላይ ተቀምጦ የነበረ አንድ ወታደር እጁን በራሱ ላይ ጭኖ
ተርገፈገፈ። ተነስቶ መንደሩን ዙሮ ወደነበረበት ተመለሰ።በተደጋጋሚ እንደዚህ ሲያረግ ቆየ። መቶ አለቃ ጃባቲ ሬዲዮ ላይ መልዕክት ሲያስተላልፍ ከቆየ በኋላ ሬዲዮውን ወረውሮ ወደ ቤቱ ገባ። መንደርተኛው ምንም አላወራም:: ዝም
ብሎ የወረደውን መዓት ታዘበ።

እኩለ ቀን ሲሆን ከሃያ የሚበልጡ ወታደሮች ወደ መንደሯ መጡ። መቶ አለቃ ሲያቸው ማመን አልቻለም ተገረመ ተደሰተ ብዙም ሳይቆይ ቁጥብ ሆነ። ወታደሮቹ ራሳቸዉን እንደገና ካዘጋጁ በኋላ ወደ ጦር ሜዳ ወረዱ። ምንም መደበቅ አላስፈለገም ጦርነቱ ቅርብ ነው። ብዙም ሳይቆይ የተኩስ እሩምታ መስማት ጀመርን። መንደሩን የሚጠብቁት ወታደሮች ወደ ቤት እንድንገባ አዘዙን። ተኩሱ ከወፎችን እና ዶሮዎች ጩኅት ጋር እስከ ምሽት ድረስ ቀጠለ። ለሊት ጥይት ለማምጣት እና ለአጭር ረፍት ጊዜ ወታደሮች እየሮጡ ወደ መንደር መጡ። የቆሰሉ ወታደሮች በፋኑስ የታገዘ ቀላል ቀዶ ጥገና ቢደረግላቸውም አብዛኞቹ ይሞታሉ። ወታደሮቹ የሞቱ ጓዶቻቸዉን ወደ መንደር
አያመጡም። ምርኮኛዎችን አሰልፈው ግንባራቸውን በጥይት በመምታት ይገድሉዋቸዋል።

ጦርነቱ ለቀናት ቀጠለ።ወታደሮች ቀስ በቀስ ቁጥራቸው እየቀነሰ ሄደ፡፡ ወታደሮቹ እረፍት አጡ ፤ ኮሽ ካለ የመንደሩ ሰዎች
ላይ ሳይቀር መተኮስ ጀመሩ:: መቶ አለቃዉ የመንደሩን ነዋሪዎች ወደ አደባባይ ወጥተው እንዲሰበስቡ ትዕዛዝ ሰጠ።
“ጫካው ውስጥ ህይወታችንን ሊያጠፉ ዕድላችንን ሊያበላሹ የሚጠብቁ ወታደሮች ተዋግተናቸዋል። በቁጥር ግን ይበልጡናል። መንደሩን በሙሉ ከበው አሉ። ይሄን መንደር እስከሚይዙ ድረስ ተስፋ አልቆርጥም:: የእኛን ምግብ እና መሳሪያ የራሳቸው ማድረግ ይፈልጋሉ።” ብሎ ንግግሩን ገታ አደረገና ቀስ ብሎ እንደገና ቀጠለ። አንዳንዶቻችሁ ከዚህ የምትገኙት ወላጆቻችሁን ቤተሰቦቻችሁን ስለገደሉባችሁ ነው፡፡ ሌሎች ደግሞ አስተማማኝ መጠጊያ መሸሸጊያ ነው ብላችሁ ነው:: እንግዲህ ከዚህ በኋላ
አስተማማኝ አይደለም:: ለዚህ ነው ጠንካራ ወንዶችን ታደጊዎችን የምንፈልገው:: እነዚህን እንድታግዙን የሰፈሩን ሰላም እና ደህንነት እንድንጠብቅ
እንፈልጋለን። መዋጋት ወይም ማገዝ ካልፈለጋችህ ምንም አይደል፡፡ ነገር ግን ቀለብ አይሰፈርላችሁም በመንደሩም መቆየት አትችሉም። መሄድ ትችላላችሁ ከዚህ የምንፈልጋቸው ምግብ
በማብሰል መሳሪያ በማዘጋጀት ጥይት በማቀበል የሚረድን የሚዋጉ ናቸዉ። ለምግብ ማብሰል በቂ ሴቶች አሉ። ስለዚህ ብቁ የሆኑ ታዳጊ ወንዶች እና ወጣቶች ነው እነዚህን አማጺዎች
እንዲዋጉ ምንፈልገው:: አሁን ነው የወላጆቻችሁን ደም የምትመልሱት፤ ሌሎች ልጆችንም ወላጆቻቸውን ከማጣት
ማስቀረት የምትችሉት::” ትንፋሽ ወሰደ። “ ነገ ጠዋት ሁላችሁም ከዚህ ቦታ እንድትሰለፉ ለተለያዩ ስራዎች ሰዎችን
እንመርጣለን።” አደባባዩን ለቆ ሲሄድ ጠባቂዎቹ ተከተሉት።

ለተወሰነ ጊዜ ደርቀን ባለንበት ቁመን ቀረን። ከዛ የስዓት እላፊው ሲቃረብ ወደየ ምኝታ ቦታችን ተበተን። ቤት ውስጥ
ጁማህ፣ አል ሃጂ ሞሪባ፣ ሙሳ እና እኔ ምን ማድረግ እንዳለብን ድምጻችንን ቀንሰን ተወያየን፡፡

“አማጺዎች ከዚህ መንደር የሆነ ማንም ሰው ጠላት ወይም ስላይ ነው ብለው ስለሚገምቱ ሁሉንም ይገድላሉ። ይሄን
ነው ያለው አምሳ አለቃው።” አለ አል ሃጂ የገጠመንን ኣጣብቂኝ ለማስረዳት ሲሞክር። ሌሎቹ ወንዶች ከተጋደሙበት ስጋጃ ተነስተው ውይይቱን ተቀላቀሉ። አል ሃጂ ቀጠለ “የሚሻለው ለጊዜውም ቢሆን ከዚህ መቆየት ነው።” ሌላ ምርጫ
አልነበረንም። መንደሩን ለቆ መሄድ ማለት መሞት ማለት ነው::

“አዳምጡ! ይህ ከመቶ አለቃ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ ሁላችሁም አሁንኑ ወደ አደባባይ በመውጣት ተሰብሰቡ።” ብሎ በድምጽ ማጉያ ለፈለፈ። ተናግሮ ሳይጨርስ አደባባዩ በሰዎች ሞላ፡፡
ሁሉም ሰው ለደህንነቱ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚወስነውን ይህን ጊዜ በጉጉት ይጠብቅ ነበር። ከአዋጁ በፊት ከጓደኞቼ ጋር ኩሽና ቤቱ ውስጥ ተቀምጬ ነበር። ፊታቸው ባዶ ምንም ስሜት የማይታይበት አይናቸው ግን በሃዘን ገርጥቶ ነበር። አይን ለ አይን ላያቸው ብሞክርም ፊታቸውን አዞሩ። ቁርሴን ለመብላት ብሞክርም ፍርሃት የመብላት ፍላጎቴን ነጥቆኛል።

በሰልፍ መሃል ቦታ ስናገኝ የተኩስ እሩምታ አየሩን ተቆጣጠረው:: ከዚያ ከተኩሱ የሚከብድ ጸጥታ ሆነ።

መቶ አለቃ ለሁሉም ለመታየት ከተደረደረ ጡብ ላይ ወጣ።አጥንት ከሚሰብር ዝምታ በኋላ ወደ ወታደሮቹ እጁን
አመለከተ:: ወታደሮቹ የአንድ ወጣት እና ሌላ ታዳጊ አስክሬን ከፊታችን አስቀመጡ፡፡ የመንደሩ ነዋሪዎች ነበሩ። ልብሳቸው በደም ተጠምቋል አይናቸው እንደተከፈተ ነው፡፡ ሰዎች ፊታቸውን ለማዞር ሲሞክሩ ትንንሽ ልጆች ማልቀስ ጀመሩ።መቶ አለቃው ጉሮሮውን አጥርቶ መናገር ጀመረ፡፡እነዚህን አሰቃቂ አስክሬን በተለይ ልጆች ባሉበት
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስር

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

...በር ላይ ቆመ። ፈገግ ብሎ መሳሪያውን ካነሳ በኋላ ወደ ስማይ ብዙ ተኮሰ። መሬት ላይ ወደቅን። ስቆ ወደ ውስጥ ገባ። ተነስተን ወደ ህንጻው ገባን። ሀምሳ አለቃው በቤቱ ጀርባ ወዳለ ክፍል
መራን። ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ታዳጊዎች ነበሩ።

አንድ ፊሽካ ባንገቱ ላይ ያንጠለጠለ ነገር ግን መለዮ ያልለበስ ወታደር AK-47 ካለበት ሳጥን በማውጣት አንድ አንድ ለሁላችን አደለን። ወደ እኔ ሲደርስ ቀና ብየ ላየው ስላልቻልኩ ራሴን ቀና
አድርጎ ነበር የሰጠኝ። እጆቼ ይንቀጠቀጡ ነበር።

“ሁላችሁም በሁለት ነገሮች ትመሳሰላላችሁ” አለ ወታደሩ።
“ስው ቀና ብላችሁ አይን ለአይን ማየት አትችሉም እና መሳሪያ መያዝ ያስፈራችኋል። ራሳችሁ ላይ የተደቀነ ይመስል ትንቀጠቀጣላችሁ። ይሄ መሳሪያ ከእንግዲህ የናንተ ነው።እንዴት መያዝ እንዳለባችሁ ከአሁኑ ተማሩ። ለዛሬ ይበቃል”አለ ወታደሩ።

ያ ለሊት በድንኳኔ መግቢያ ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ቆምኩ።ጓደኞቼ መጠው ያወሩኛል ብየ ስጠብቅ ነበር። ማንም ከድንኳኑ
አልወጣም:: እጄን ራሴ ላይ ጭኜ ተቀመጥኩ። የራስ ምታቴ ያን ምሽት ጠፋ።

ከእኔ ጋር ድንኳን የሚጋሩት ሼኩ እና ጆሲያህ ደወል እስከ ሚደወል ንጋት 12 ስዓት ድረስ ተኝተው ነበር።ለስልጠና
መነሳት ነበረብን። ኑ እንሂድ” ብየ ቀስ አድርጌ ልቀሰቅሳቸው ሞከርኩ። ወደ ሌላ ጎናቸው እየተንከባለሉ ከእንቅልፋቸው ሊነሱ አልቻሉም፡፡ ከዛ ሰሌኑን አንስቼ መትቼ አስነሳሁዋቸው።

አዲስ የወታደር ጫማ፣ ሱሪ እና ዝንጉርጉር ቲሸርት ተስጥቶን ልምምዳችን ጀመርን። ሱሪ ስቀይር ወታደሩ ወደ እኔ
መጥቶ አሮጌውን ሱሪ ወደ እሳት ጨመረው። አሮጌው ሱሪ የራፕ ካሴቴን ይዞ ስለነበር ወደ እሳቱ ሩጬ ላተርፈው ሞከርኩ።ካሴቱ ግን መቃጠል ጀምሯል። አይኔ እንባ አቀረረ።

ወደ ጎን ረድፍ ሰርተን እግራችን ከፍተን እጃችንን አጣምረን መጠበቅ ጀመርን። አንዳንድ ወታደሮች ከጦር ሜዳ ተመልሰው የጦር መሳሪያቸውን አስተካከሉ ጥይቶችን በጎናቸው ባለ
ከረጢት ያዙ። አንዳንዶቹ ልብሳቸው እና ፊታቸው ደም ይታይበታል። ቁርሳቸውን በፍጥነት በልተው ተመለሱ::

ሼኩ እና ጆሲያህ ከእኔ ጎን ነበሩ። አንድ ድንኳን መጋራታችን እንደ ትልቅ ወንድም እንዲሰማኝ አድርጓል። በልምምድ መሃል
እኔን ያያሉ፤ ከአሰልጣኝ በላይ እኔ የማደርገውን ያደርጉ ነበር፡፡አሰልጣኙ ራሱን አስር አለቃ ጋዳፊ ብሎ ነበር ያስተዋወቀን ከመቶ አለቃ ጃባቲ እና ከሃምሳ አለቃው ጋር ሲነጻጸር በእድሜ
ያንሳል፤ ራሰ በራ መሆኑ እና ኮስታራ ፊቱ ግን ትልቅ ሰው ያስመስለዋል ::

መጀመሪያ በህንጻው ዙሪያ ለተወሰነ ደቂቃ ሮጥን። ቀጥሎ በዱር ውስጥ አድብቶ መግባት ተማርን። ዛፎ ላይ መውጣት መውረድ፣ ድምጸ ሳናሰማ መንቀሳቀስ እና ተመልሶ ወደ ነበሩበት
ሩጦ መመለስ በተደጋጋሚ ሰራን። አስር አለቃ ጋዳፊ ብዙ አይናገርም:: “መጥፎ አይደለም”፣ “መጥፎ” እና “ፍጥነት” ብቻ
ይል ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ በምልክት ይጠቀማል። ወደ ጫካው ከገባን
በእጃችን እንቅስቃሴ መግባባት እንዳለብን ነገረን። “ቃላት ተናገራችህ ማለት ግንባራችሁን ለጥይት አሳልፋችሁ ሰጣችሁ ማለት ነው” ይላል፡፡ በስልጠና መሃከል ቁርስ እንድንበላ አንድ ደቂቃ ብቻ ይሰጠናል። በመጀመሪያ ቀን ብዙ ሳንበላ ነበር ምግቡ የተነሳው። ከሳምንት በኋላፀ በፍጥነት መብላት ለመድን።
ከስዓት AK-47 ያደለንን አስር አለቃ ፊት ለፊት ገጥመን ተሰለፍን። የእኔ ተራ ሲደርስ አፍጥጦ አየኝ እና ከእንጨት ሳጥን ውስጥ መሳሪያ አውጥቶ ደረቴ ላይ አስታቀፈኝ፡፡ መሳሪያየን
ይዥ ወደ ሰልፉ ተመለስኩ፡፡ እጆቼ ይንቀጠቀጡ ነበር፡፡ በእጆቼ
ይዤው እንኳ ላየው ፈራሁ። እኔ ማውቀው በቅርቅሃ ሚስራ የአሻንጉሊት ሽጉጥ ነበር። እኔ እና ጓደኞቼ ከቅርቅሃ ሰርተን በቡና ማሳ ወይም በግንባታ ላይ ባሉ ቤቶች መሃል እንጫወት ነበር። አሁን የዕቃ ዕቃ ጨዋታ አይደለም የእውነት AK-47 ይዘናል። ለጊዜው ያለ ጥይት መሳሪያውን ይዘን መሮጥ መንከባለል ተማርን። ቀጥሎ ወደ ሙዝ ማሳ በመውረድ ሙዙን በሰንጢ መውጋት ጀመርን፡፡ “ሙዙን እንደ ጠላት ተመልከቱት።ወላጃችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን እንደገደሉት አማጺዎች” አስር አለቃ ጮኸ። “ቤተሰቦቻችሁን የገደለን ሰው እንደዚህ ነው ምትወጉት?” እንደዚህ ነው ብሎ እየጮኸ መውጋት ጀመረ።

መጀመሪያ ሆዱን፣ ከዛ አንገቱ ላይ፣ ልቡን” እያለ ቀጠለ። እኛም በንዴት ስሜት ሙዙን መውጋት ቀጠልን:: ምሽት ላይ አልሞ መተኮስ ሰለጠን። ሼኩ እና ጆሲያህ መሳሪያቸውን ለማንሳት
አቅም አልነበራቸውም:: አስር አለቃ ከፍ ያለ ኩርሲ ነገር ሰጣቸው እና ልምምዳቸውን ቀጠሉ። በመጨረሻ መሳሪያ ፈቶ መጠገን እንደይዝጉ ዘይት መቀባት ተማርን፡፡ ያ ምሽት ሁላችንም ደክሞን ስለነበር በቀጥታ ወደ ምኝታችን አመራን።

ሼኩ እና ጆሊያህ ቀን የሰሙትን “አንድ ሁለት” “ፓው ፓው ቡም” ድምጾች በእንቅልፍ ልባቸው ይሉ ነበር።

እሁድ ጠዋት ነበር አስር አለቃ ያን ቀን ስልጠና እንደሌለ እና እንድናርፍ ሲነገረን፡፡ “ሃይማኖተኛ ከሆናችሁ ማለት
ክርስቲያን ከሆናችሁ ዛሬ አምላካችሁን የማምለኪያ ቀን ይሁናችሁ ፤ ምን አልባት ሌላ ጊዜ ላይኖራችሁ ይችላል። ሂዱ”

የወታደር ልብሳችንን እንደለበስን ወደ መንደሩ አደባባይ ወጣን። ኳስ መጫወት ስንጀምር መቶ አለቃ ከቤቱ ደጃፍ ወጥቶ
ሊቀመጠ ነበር። ጨዋታውን አቁመን ለመቶ አለቃ ሰላምታ ሰጠን። “ጨዋታችሁን ቀጥሉ። አሁን የምፈልገው ወታደሮቹ ኳስ ሲጫወቱ ማየት ነው።” ብሎ ባርጩሜ ላይ ተቀመጦ
ጅሊየስ ሲዘር (ቄሳር) ን ማንበቡን ቀጠለ ::

ኳስ ጨዋታው ሲበቃን፤ ለመዋኘት ወሰን እና ወደ ወንዝ ወረድን። ፀሐይማ ቀን ነበር፡፡ ወደ ወንዝ ስንወርድ ሰዉነታችን
ላይ የነበረው ላብ እየደረቀ ነበር። ለተወሰኑ ደቂቃዎች ከተንቦጫረቅን በኋላ በሁለት ቡደን ተከፍለን መወዳደር
ጀመርን።

እንሂድ ጓዶች: በዓሉ አብቅቷል።” ብሎ አስር አለቃ ከወንዙ ዳር ሁኖ ጮኸ። ጨዋታውን አቁመን አሱን ተከትለን
ወደ መንደራችን ሄድን።

መንደር እንደደረስን መሳሪያችንን እንድጠግን ትዕዛዝ ተሰጠን። መሳሪያችንን እያጸዳን የወገብ እና የጀርብ ቦርሳ ተሰጠን። ጥይቶችንን የፈለግነውን ያህል እንድንወስድ ተነገረን።
መሸከም ከምንችለው በላይ ከሆነ በፍጥነት መሮጥ እንደማንችል
ነገረን። ከአል ሃጂ እና ከእኔ በስተቀር ሌሎች ደስተኛ ነበሩ።ፀተጨማሪ ልምምድ የሚሄድ ነበር የመሰላቸው። አል ሃጂ መሳርያውን አጥብቆ ያዘ።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_አንድ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

“ተነሱ ወታደሮች” አለ አስር አለቃ፡፡ የደንብ ልብሱን ለብሶ ሙሉ ትጥቁን ታጥቆ ነበር የመጣው። በተጠንቀቅ ተሰልፈን ነበር። አረንጓዴ ከረባት ሰጠን እና “ይሄን ከረባት ያላደረገ ወይም እንደ እኔ አይነት ባርኔጣ ያላደረገ ካያችሀ ተኩሳችሁ ምቱት” አለ በጩኸት። አሁን ለስልጠና እንደማንሄድ ለሁሉም
ግልጸ ነው። “አሁን ዘና በሉ፤ ከተወሰኑ ከደቂቃዎች በኋላ ጉዞ እንጀምራለን።”

አስር አለቃ ትቶን ሄደ፡፡ መሬት ላይ ተቀመጥን፤ ሁላችንም በየግል ሃሳባችን ተውጠን ነበር፡፡ሼኩ እና ጆሲያህ ከጎኔ
ተቀምጠዋል ፤ አይናቸው ውሃማ ነበር የተከፉ ይመስላሉ።ማድረግ የምችለው ራሳቸውን እያሻሽሁ አይዙዋችሁ ማለት ብቻ ነበር። ተነስቼ ወደ አል ሃጂ እና ሌሎች ጓደኞቼ ሄድኩ። ምንም
ቢፈጠር አንድ ላይ ለመሆን ተስማማን።

ወጣት ወታደር የፕላስቲክ ቦርሳ ይዞ ወደ እኛ መጣና ክኒን የሚመስል ነጭ ነገር ስጠን፡፡ “አስር አለቃ ተጨማሪ ሃይል
ይሰጣችኋል ፦ያበረታችኋል” ብሏል አለ። ክኒኖቹን ከወሰድን በኋላ መንቀሳቀስ ጀመርን። መሳሪያችንን ይዘን አዋቂ
ወታደሮችን ተከትለን መራመድ ጀመርን። ምሽት ላይ እንመለሳለን ተብሎ ስለታሰበ ምግብ እና መጠጥ አልያዝንም፡፡
ጫካው ውስጥ ብዙ ኩሬዎች አሉ።” አለ መቶ አለቃ:: ብዙ ምግብ እና ውሃ ይዞ ከመምጣት ጥይት እና መሳሪያ መሸከም
ይሻላል ለማለት ይመስላል :: “በብዙ ጥይቶች ውሃ እና ምግብ ማግኘት እንችላለን። ምግብ እና ውሃ ብንዝ ግን እስከ ማታ እንኳ አያቆየንም::” አለ አስር አለቃ መቶ አለቃ ጃባቲ የጀመረውን
ሃሳብ ሲያስረዳ፡፡

ሴቶች እና ትልልቅ ሰዎች ቤታቸው ደጃፍ ሁነው ስንሄድ ይመለከቱ ነበር። አንድ ህጻን የት እንደምንሄድ ምን እንደሚገጥመን ያወቀ ይመስል ስቅ ስቅ ብሎ አለቀሰ።ፀሐይዋ አንፀባራቂ ከመሆኗ የተነሳ ጥላችን መሬት ላይ ይታይ ነበር።

በህይወቴ እንደዛን ቀን መንቀሳቀስ ወደ ማንኛውም ቦታ ለመሄድ ፈርቼ አላውቅም። አይኖቼ እንባ ሲያቀርሩ ለመዋጥ እታገል ነበር። መሳሪያየም አጥብቄ ያዝኩ።

ወደ ጫካው አንድ ክፍል ስንገባ መሳሪያችንን እንደብቸኛ የጥንካሬ ምንጭ ይዘን ነበር። በጥንቃቄ በቀስታ ነበር የምንተነፍሰው። መቶ አለቃ በሚመራው ረድፍ ነበርኩ። እጁን
ወደ ሰማይ ሲያነሳ ጉዟችንን ገተን ቆምን። ቀስ አድርጎ እጁን ሲያወርድ በአንድ እግራችን ሸብረክ ብለን ከተቀመጥን በኋላ አካባቢን ቃኘን። ወዲያው ተነስተን ረግረጋ ጥግ እስክንደርስ ድረስ በፍጥነት መንቀሳቀስ ጀመርን። ረግረጉ ላይ መሳሪያችንን አስተካክለን ጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጀን።
በዝምታ እንደ አዳኝ አድፍጠን ጣታችንን ቃታ ላይ አሳርፈን ጠበቅን፡፡ ፀጥታው ግን አስጨነቀኝ።

አማጺዎች በረግረጉ በኩል ሲያልፉ በአካባቢው የነበሩ ትናንሽ ዛፎች ተንቀሳቀሱ። ገና አይታዩም መቶ አለቃ ግን “ሳዛችሁ ተኩሱ” አለ። ከደቂቃዎች በኋላ የተወሰነ ቡድን ሲመጣ
አየን። እጃቸውን አንስተው ተጨማሪ ታጣቂዎችን ጠሩ።አንዳንዶቹ እንደ እኛ ታዳጊዎች ነበሩ። መቶ አለቃ RPG
እንዲተኮስ አዘዘ፡፡ የአማጺዎች አዛዥ ግን ለመተኮስ ስንዘጋጅ ድምፅ ስምቶ ስለነበር ወታደሮቹን “በማፈግፈግ!” “ሸሹ”
“አምልጡ” አለ። ስለዚህ ፈንጁ የተወሰኑትን ብቻ ነበር ያገኘው።
ከፍንዳታው በኋላ በሁለቱም በኩል የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ።

መሳሪያየን ፊት ለ ፊት ደቅኜ ደርቄ ቀረሁ፡፡ መተኮስ አልቻልኩም። ጠቋሚ ጣቴ ደነዘዘ፡፡ ጫካው ይዞርብኝ ጀመር።
የምወድቅ ስለመሰለኝ ከጎኔ የነበረውን የዛፍ ግንድ በአንድ እጄ ያዝኩ። ማስብ አልቻልኩም ግን ከሩቅ ተኩስ ይሰማኛል ፤ ሰዎች በስቃይ እየጮሁ ይሰማኛል። ቅዥት በሚመስል ስሜት ውስጥ
እያለሁ የደም ርጭት ፊቴን መታኝ፡፡ ደሙን ከፊቴ ላይ እያበስኩ አንድ ወታደር ወደ እኔ ሲመጣ አየሁ::

ፀሐዮዋ የመሳሪያ ጫፍ እና ወደ እኛ የሚመጡ ጥይቶችን ታሳይ ነበር። ጆሲያህን መፈለግ ጀመርኩ፡፡ ጆሲያህን ግን መድፉ አግንቶት ነበር፡፡ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሰውነቱ በደም ተጨማልቆ አገኘሁት። እጆቹን ትክሻየ ላይ እንዳደረገ
መንቀሳቀስ አቆመ። አይኖቹን ዘግቼ መሬት ላይ አሳረፍኩት።ከጎኔ የሆነ ሰው እንደቆመ ይሰማኝ ነበር። አስር አለቃ ነበር።
“ዝቅ በል” “ተኩስ” አለኝ። ፊት ለ ፊት ሙሳን አየሁት ጭንቅላቱ በደም ተሸፍኗል እጆቹ ግን ዘና ያሉ ይመስላሉ።ወደ ረግረጉ ስዞር አማጺዎች እየሮጡ ነበር። ድንገት መሳሪያየን አንስቼ ተኮስኩ።
አንድ ሰው ገደልኩ፡፡ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ ያየሁት እልቂት በጨረፍታ በአዕምሮየ ይመላለስ ጀመር። የሁለት ጓደኞቼ ሞት ውስጤን እየረበሸኝ ነበር የምተኩሰው። ብዙ ሰው ገደልኩ።
እንድናፈገፍግ ትዕዛዝ እስከሚሰጠን ድረስ መተኮሴን አላቆም ኩም ነበር።
የተሰው ጓደኞቻችንን መሳሪያ እና ጥይት ከወሰድን በኋላ ከዛው ጫካ ትተናቸው መጓዝ ጀመርን፡፡በዱር መሃል ቀስ ብለን
አድብተን ለተወሰነ ሜትሮች ከተጓዝን በኋላ ለሌላ የደፈጣ ውጊያ ተዘጋጀን። አሁንም አድፍጠን ጠበቅን፡፡ ጊዜው በምሽት እና ለሊት መሃል ነበር። አንድ ድንቢጥ ወፍ መዘመር ብትጀምርም
ሌሎች ሊከተሉዋት አልቻሉም:: እሱዋም አቆመች፤ ለሊቱ በፀጥታ ተዋጠ፡፡ ከአስር አለቃ ጎን ነበርኩ፡፡ አይኖቹ ከተለመደው
በላይ ቀልተዋል። የሚመጡ ሰዎችን ኮቴ ስንሰማ በተጠንቀቅ መጠበቅ ጀመርን። የተወሰኑ ታጣቂዎች ከቁጥቋጦ በመውጣት በዛፎች መሃል ራሳቸውን ከለሉ። ወደ እኛ ሲቀርቡ መተኮስ
ጀመርን። ፊት ለ ፊት የነበሩት ተኩሰን ከጣልነው በኋላ ሌሎቹን በረግረጉ በኩል ከተከተልናቸው በኋላ ጠፉን። ብዙ
አማጺዎችን ገደልን። ደማቸው የረግረጉን ውሃ ወደ ደም ለወጠው። አስክሬናቸውን
መሳሪያዎችን ወሰድን፡፡

አስክሬናቸውን አልፈራሁም ነገር ግን ተፀየፍኳቸው።በእግሬ አገላብጬ G3 መሳሪያ፣ ጥይቶች እና ሽጉጥ አገኘሁ::
ሽጉጡን አስር አለቃ ለራሱ አደረገ።ሟቾቹ አንገታቸው እና እጃቸው ላይ ጌጣ ጌጦች አድርገው ነበር። አንዳንዶቹ ከአምስት
በላይ የወርቅ ስዓቶችን እጃቸው ላይ አስረው ነበር። አንድ ፀጉሩ ያልተበጠረ ታዳጊ ደግሞ 'All eyes on me “ሁሉም አይኖች ወደ እኔ( ይመለከታሉ)” የሚል Tupac Shakur ቱፓክ ሻኩር ቲሸርት ለብሶ ነበር፡፡ የተወሰኑ አዋቂ ወታደሮች እና ጓደኞቼን ሙሳ እና ጆስያህን አጥተናል። ተረት አዋቂው ሙሳ አልፏል።
አጫዋቻችንን፥ ቀልድ አዋቂ እና ተረት ነጋሪው አሁን በምንፈልገው ጊዜ የለም! ተነጥቀናል። ጆስያህቱ ያኔ ከእንቅልፉ ባልቀስቅሰው እና የመጀመሪያው ስልጠና ቢያልፈው ዛሬ ባልዘመተ ነበር።

አመሻሽ ላይ መንደራችን ደርሰን የጦር መጋዝኑን ግድግዳ ተደግፈን ተቀመጥን፡ መንደሩ ጸጥታ ወርሶት ነበር። ጸጥታው
ያስፈራን ይመስል መሳሪያዎቻችንን ማፅዳት ዘይት መቀባት እና መገጣጥም ጀመርን። አዳዲስ መሳሪያዎችንን ወደ ሰማይ በመተኮስ ስንሞክርም ነበር። መክሰስ መብላት ብፈልግም አልቻልኩም ውሃ ጠጣሁ ግን ምንም አልተሰማኝም። ወደ ድንኳኔ ስገባ ከስሚንቶ ግድግዳ ጋር ተጋጪቼ ጉልበቴ ደማ።
አሁንም ምንም አልተሰማኝም ደንዝዥ ነበር፡፡ መሳሪያየን ድንኳኔ መውጫ ላይ አድርጌ በጀርባየ ተንጋልየ ተኛሁ።
አዕምሮየ ባዶ ሆነ፤ ምንም አይነት ሃሳብ ስሜት አልነበረኝም፡፡
በተዓምር እስክተኛ ድረስ የድንኳኑን ጣራ አንጋጥጬ ለደቂቃዎች አየሁ። በህልሜ ጆስያህን ከዛፍ ጉቶ ላይ ላነሳው ስሞክር አንድ ሰው ከበላየ ላይ ወጣብኝ። ግንባሬ ላይ መሳሪያ ሽጉጥ ደቀነ። ወዲያው
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ሁለት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


ቀኖቼን በወታደራዊ ስራዎች ተጠምጄ ባሳለፍኩ ቁጥር የራስ ምታቴ እየተሻለኝ መጣ፡፡ ቀን ቀን ኳስ መጫወት ትቼ ጥበቃ
ላይ እሰማራለሁ። ነጩን ክኒን በብዛት አዘውትሬ እወስድ ነበር።
ክኒኖቹ ሱስ ሁነውብኛል። ብዙ ኃይል ይሰጡኛል። መጀመሪያ አብዝቼ የወሰድኩ ቀን በጣም አልቦኝ ሁሉንም ልብሶቼን አውልቄ ነበር። ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል፤ ዕይታየ ደበዘዘ ብዥታ
ለደቂቃዎች ያህል መስማትም አልቻልኩም። ያለ ምንም ስራ
መንደሩን እዞረዋለሁ፤ እረፍት የለኝም ብዙ ኃይል ይሰማኛል ነገር ግን ደንዝዣለሁ ስሜት አይሰማኝም፡፡ ክኒኑን አብዝቼ
መውሰዴን ቀጠልኩ።ምንም ነገር አይሰማኝም ብዙ ኃይል ከማግኘት እና ለሳምንት እንቅልፍ ካለመተኛት በስተቀር። ማታ ማታ ፊልም እናያለን። የጦርነት ፊልሞች፥ራምቦ፣ ፈርስት ብለድ፣ ራምቦ ሁለት፣ ኮማንዶ እና ሌሎች በጄነሬተር ወይም በመኪና ባትሪ በመታገዘ እንመለከት ነበር። ሁላችንም እንደ
ራምቦ መሆን እንፈልግ ነበር። እሱ ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች ለመተግበር እንጓጓ ነበር።

ምግብ፣ መድሃኒት፣ ጥይቶች እና ጋዝ እያለቀብን ሲመጣ በከተማ፣ በገጠር መንደሮች እና በጫካ ውስጥ የሚገኙ
በር የአማጺዎችን ካምፖችን መውረር ጀመርን። ያልታጠቁ ሰዎች የሚገኝባቸውን ሌሎች መንደሮችን በማጥቃት ወታደሮችን መለመልን፡፡

“መልካም ዜና ደርሶናል ከመልዕክተኞቻችን የተወሰኑ አማጺዎችን ለመግደል እና በመጀመሪያም የእኛ የሆነውን ቁሳቁሳቸውን ለመውሰድ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ከዚህ እንቀሳቀሳለን” አለ መቶ አለቃ አዋጁን ሲነግር። ፊቱ ላይ ልበ ሙሉነት ይነበባል። ግንባራችን ላይ አረንጓዴ ጨርቅ አስረን
ነበር ታዳጊዎች ይመሩ ነበር። ምንም አይነት ካርታ ምንም አይነት ጥያቄም አልተነሳም:: ቀጣይ ትዕዛዝ እስከሚሰጠን ድረስ እንዲሁ መንገድ እንድንከተል ነበር የተነጋገርነው ሰርዲን ለመብላት እና ነጩን ክኒን ለመውሰድ ከቆምንበት ውጭ ለብዙ ሰአታት
ያለማቋረጥ ተጓዝን፡፡ ክኒኖቹ ብዙ ኃይል
ከመስጠታቸውም በላይ ደፋር አደረጉን፡፡ የሞት ሃሳብ በጭራሽ ወደ አዕምሮዬ አልመጣም፡፡ መግደል ግን ውሃ እንደመጠጣት ቀላል ሆነ። የመጀመሪያውን ሰው ስገድል ብቻ ልቤ ተነክቶ ነበር። ከዛ በኋላ ግን ምንም አይነት ሃዘን ፀፀት አልተሰማኝም::
ከበላን በኋላ መድሃኒቱን ወስደን አዋቂዎች ለተወሰነ ደቂቃ እረፍት እስኪወስዱ ዙሪያውን ለጥበቃ እንሰማራለን። ከ አልሃጂ ጋር ነበርኩ፡፡ የጥይት መያዣውን በፍጥነት መቀየርን
እየተወዳደርን ነበር።

“ቆይ አንድ ቀን ልክ እንደ ራምቦ ብቻየን አንድ ሙሉ መንደር እቆጣጠራለሁ” አል ሃጂ ፈገግ እያለ እቅዱን ነገረኝ።

ልክ እንደ ኮማንዶ ፊልም የራሴ ባዙቃ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ። ያምራል።” አልኩ እና አንድ ላይ ሳቅን፡፡

ወደ አማጺዎች ካምፕ ከመግባታችን በፊት መንገዳችን ቀይረን በጫካው ውስጥ በመጓዝ አሰሳ አናደርጋለን፡፡ ካምፑ ዕይታችን ውስጥ ከገባ በኋላሸ ከበባ እናደርግ እና የመቶ አለቃን ትዕዛዝ
እንጠብቃለን። አማጺዎች ከአንዱ ወደ አንዱ ይንቀሳቀሳሉ ፣ሌሎቹ ግድግዳ ተገድፈው ሲቀመጡ እንደእኛ ያሉ ታዳጊዎች ደግሞ ይጠብቃሉ:: አማጺዎችን ባየኋቸው ቁጥር ደሜ
ይፈላል፤ እናደዳለሁ። አማጺዎቹ ቤተሰቤን ያጣሁበትን መንደር አውድመው ካርታ የተጫወቱት ይመስሉኛል። ስለዚህ መቶ አለቃ ትዕዛዝ ሲሰጥ የቻልኩትን ያህል እተኩሳለሁ። ንዴቴ አይወጣልኝም! ከተኩስ በኋላ ወደ ካምፑ እንገባለን፡፡ የቆሰሉትን
እንገድላለን ፤ ቤት ውስጥ ገብተን ጋዝ፣ አደንዛዥ እፆች፣ ጫማ፣የእጅ ስዓቶች፣ ሩዝ፣ ዓሳ፣ ጨው እና ሌሎች ነገሮችን
እንሰበስባለን።ያልታጠቁ ሰዎችን (ሲቪል) ሰብስበን የዘረፍነውንእንዲሸከሙ እናደርጋለን።

“እኛ” መቶ አለቃ ወደ እኛ እየጠቆመ ” ልንጠብቃችሁ ነው እዚህ ያለነው። ምንም አይነት ጉዳት እንዳይደርስባችሁ የምንችለውን እናደርጋለን።” አለ ወደ ያልታጠቁት ሰዎች እየጠቆመ።
“የእኛ ስራ ጥብቅ ነው፤ ሃገራቸውን ለመጠበቅ ምንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ ጎበዝ ወታደሮችም
አሉን። እኛ እንደ አማጺዎች አይደለንም። እነዛ ነፍስ ገዳዮች ያለ ምንም ምክንያት ሰው ይገድላሉ፤ ሁሉንም ሰው በጅምላ
ይጨፈጭፋሉ። እኛ ግን የሃገራችንን ለመጠበቅ፤ አገራችን ከእነሱ ክፋት እና ጥፋት ለማዳን ስንል ብቻ እንገድላቸዋለን።ስለዚህ ለእነዚህ የሃገራችሁ ጠባቂዎች ክብር ስጡ” ብሎ መቶ አለቃ ረጂም ንግግር አደረገ። ንግግሩ ሁለት ዓላማ ነበረው።
አንዱ በሲቪሎች ስለ እኛ ጥሩ አመለካከት እንዲኖራቸው ማድረግ ሲሆን ሌላው ደግሞ የእኛን ሞራል መገንባት ነበር።ጠበንጃየን ይዤ ቁሜለሁ። ልዩ የመሆን ስሜት ተሰማኝ፣የተፈላጊነት ፤ አንድ ትልቅ እና ጥብቅ ነገር ተሳታፊ መሆን እና ከአሁን በኋላ ደግሞ ከማንም አልሸሽም።ሽጉጤ አለኝ አስር አለቃ ሁልጊዜ እንደሚለው “ ይሄ መሳሪያ በዚህ ጊዜ የሃይላችሁ ምንጭ ነው:: ይጠብቃችኋል! እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ ካወቃችሁ ደግሞ የምትፈልጉትን ሁሉ ይሰጣችኋል።
መቶ አለቃ ንግግሩን ለማድረግ ምን እንደገፋፋው አላስታውስም። ብዙ ነገሮች ያለ ምንም ምክንያት ወይም ማብራሪይ ይሰሩ ነበር። አንዳንዴ ፊልም እያየን መሐል ላይ ድንገት ለጦርነት እንድንቀሳቀስ እንጠየቃለን። ከስዓታት በኋላ እንዳልተፈጠረ ከማስታወቂያ በኋላ እንደተመለስ ፊልሙን ካቆምንበት
እንቀጥላለን። ሁሌም ውጊያ ላይ ነን ወይ የጦርነት ፊልም እየተመለክትን ነው ወይ ደግሞ አደንዛዥ ዕፅ እየወሰድን ነው።
ብቻችን የምንሆንበት የምናስብበት ምንም አይነት ጊዜ የለም::እርስበርሳችን ስናወራ የምናወራው ስለተመለከትነው የጦርነት ፊልሞች እና መቶ አለቃ፣ አስር አለቃ ወይም ከእኛ አንዳችን ስለፈፅምነው ጀብድ ብቻ ነበር። ከዛ ውጭ ሌላ አለም ያለ አይመስለንም ነበር።

ከመቶ አለቃ ንግግር በኋላ ተራ በተራ ምርኮኞችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደልን። አማጺዎችን ስንገድል የቤተሰቦቻችን ገዳዮች የተበቀልን ይመስለን ነበር። በፍጥነት የመግደልም ውድድር
ነበር፡፡እኔ አንዱን ምርኮኛ በፍጥነት ስለገደልኩ ተጨበጨበልኝ።ትልቅ ገድል እንደፈፀምኩ ተሰማኝ ። ለእኔ እና ኬን ታናሽ መቶ አለቃ እና ታናሽ ሐምሳ አለቃ የሚል ማዕረግ በቅደም ተከተል
ተሰጠን። ደስታችንን አደንዛዥ ዕፅ እና የጦርነት ፊልም በማየት ገለፅን፡፡

የግሌ ድንኳን ነበረኝ እንቅልፍ ስሌለኝ ተኝቼበት አላውቅም።አንዳንድ ቀን በውድቅት ለሊት ለስለስ ያለው ንፋስ ላንሳ የሚባል ጓደኛየን ዝማሬ ያስታውሰኛል። ዛፎቹ የእሱን ዝማሬ
ሚያንሾሻሽኩ ይመስላሉ:: ትንሽ ካዳመጥኩ በኋላ ደጋግሜ
እተኩስ እና ድምጹን አስወግዳለሁ ።

በምርኮ ይዘን ወደ ዋና ማዕከላችን የቀየርነው መንደር እና በጉዞችን የምናድርባቸው ጫካዎች ቤቴ ሆኑ፡፡ የጦር ጓዶቼ ቤተሰቤ ! መሳሪያዬ የፈለኩትን ማገኝበት እና ጠባቂየ ሲሆን
መግደል ወይም መገደል ደግሞ የምኖርበት ህግ ወይም ደንብ ሆነ። ሃሳቤ ከዚህ በላይ አይሻገርም። ከሁለት አመታት በላይ ተዋጋን መግደል የሌተ ቀን ተግባራችን ሆነ፡፡ ለማንም አላዝንም:: እንደልጅ ሳልኖር ልጅነቴን ሳላውቀው ሳላጣጥመውም ነጎደ። የቀን እና ለሊቱን መፈራረቅ ማውቀው በፀሐይ እና
ጨረቃ መውጣት ወይም መጥለቅ ብቻ ነው። እሁድ ይሁን አርብ ግን አላውቅም::

ህይወቴ ጤናማ ይመስለኝ ነበር። ጥር 1996 አስራ አምስት አመት ሲሞላኝ ግን ይሄ መቀየር ጀመረ

አንድ ቀን ሃያ የሚሆኑ የጦር ጓዶቼን ይዤ ጥይት ለማግኘት ባውያ ወደ ምትባል
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ሶስት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


መሳሪያየን አንግቼ ከኬን እና አል ሃጂ ወደ ከተማው ገባን።በከተማው ያሉ ግንብ ቤቶች ከእኛ ከተማ እና እስከ አሁን
ካየሁቸው መንደሮች ካሉ ቤቶች ትልቅ ናቸው፡፡ በዙሪያ ብዙ የማላውቃቸው አይቻቸው የማላውቅ ሰዎች አየሁ፡፡ ራሳችንን ዝቅ እያደረግን ሰላምታ ከተሰጣጣን በኋላ ጁማህን መፈለግ
ጀመርን። ፊቱን ወደ ጫካው ያዞረ ጡብ ቤት ደጃፍ ላይ ዥዋዥዌ ላይ ተቀምጦ ነበር። ከጎኑ መሳሪያ ነበር። ቀስ ብለን ወደ እሱ ስንጠጋ ፊቱን አዞሮ አየን።

ከባድ መሳሪያ ይዘህ ነው ምትዞረው ማለት ነው?” ብሎ አል ሃጂ ቀለደ።

“እንግዲህ ምን ታረገዋለህ! ከ AK ከፍ እያልኩ ነው” ብሎ መለሰ።ሁላችንም ሳቅን።

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ እንደምንመለስ ነግረነው ጥይት እና ምግብ ልንጭን ወደ መጋዝን ሄድን።መጋዝን እያለን አዛዣችን፥ መቶ አለቃ “ዛሬን ከዚህ እደሩ፤ እራት ተዘጋጅቷል” እንዳለ ነገረን፡፡ አልራበኝም፡ ስለዚህ ኬን እና አል ሃጂ ወደ እራት
ሲሄድ እኔ ተለይቼ ወደ ጁማህ ተመልሼ ሄድኩ። ማውራት ከመጀመሩ በፊት ለደቂቃዎች ዝም ብለን ተቀመጥን፡፡

ነገ በጥዋት ለውጊያ ስለምወጣ ከመሄዳችሁ በፊት አላይህም” ብሎ ዝም አለ እና መሳሪያውን እየነካካ ቀጠለ:
የዚህን መሳሪያ ባለቤት ገደልኩት።
ብዙዎቻችንን ከገደለ በኋላ ነበር የደረስኩበት። ከዛ በኋላ ነበር እኔ የያዝኩት ”ብሎ ፈገግ አለ፡፡ እጃችንን አጋጨንና ሳቅን።ወዲያውኑ እንድንሰበሰብ ተጠራን:: ተሰባስቦ መጫወቻ እና
የአዛዦችን መተዋወቂያ ማህበራዊ ፕሮግራም ነበር። ጁማህ መሳሪያውን በአንድ እጁ ከያዘ በኋላ በሌላ እጁ ጫንቃየ ላይ አድርጎ አቅፎኝ ወደ መሰብሰቢያው ሜዳ ሄድን።ኬን እና አል
ሃጂ ከዛው እያጨሱ ነበሩ። መቶ አለቃም በቦታው ነበር። ትንሽ ፈንጠዝያ ነበር። የመቶ አለቃ ጓደኞች አብዛኞቹ ማለትም ሃምሳ አለቃ ማንሳራይ እና አስር አለቃ ጋዳፊ ሙተዋል። እሱ እንዴት
እንደተረፈ አይታወቅም። በተዕምር ምኑም ሳይነካ የለአንዳች ጠባሳ ተርፎ ሌሎች ሃይለኛ እና ታዛዥ ጓዶችን በሞቱ ጓደኞቹ ምትክ ለማፍራት በቅቷል።መቶ አለቃ ጋር ስለ ሼክስፔየር ማውራት ፈልጌ ነበር። ነገር ግን እሱ በማስተባበር ፤ ሰላም በመስጠት ተጠምዶ ነበር። በመጨረሻ እኔ ፊት ለ ፊት ሲደርስ
እጄን ጥብቅ አርጎ ያዘና “ማክቤዝ አይበገርም፧ ታላቁ የብሪያም ጫካ ዶንከን ኮረብታ እስኪደርስ ድረስ ማክቤዝ እጅ አይሰጥም አለ።

ጮክ ብሎ ”ልለያችሁ ነው ጓዶች” አለ። እጅ ከነሳን በኋላ እጁን እያውለለበ ሄደ። እኛም መሳሪያችን ከፍ አድርገን በጩኸት
ሰላምታችን ገለጸን። መቶ አለቃ ከሄደ በኋላ የሴራሊዮንን ብሄራዊ መዝሙር መዘመር ጀመርን። “ከፍ አድርገን
እናከብርሻለን፤ የነጻ ህዝቦች ሃገር፤ ጥልቅ ነው ለአንቺ ያለን ፍቅር” ለሊቱን ሙሉ ስንጫወት ስናወራ አሳለፍን።
ከመንጋቱ በፊት ጁማህ እና የተወሰኑ ወታደሮች ለውጊያ ሄዱ። አል ሃጂ፣ ኬን እና እኔ በሚቀጥለው ጥየቃ ብዙ
እንደምንጫወት ቃል ገብተን ተሰናበትነው:: ጁማህ ፈገግታ ካሳየን በኋላ መሳሪያውን ጠበቅ አድርጎ ከያዘ በኋላ ወደ ጫካው ገባ፡፡

ከትንሽ ስዓታት በኋላ አንድ ትልቅ መኪና ወደ መንደር መጣ፡፡ ዩኒሴፍ UNICEF የሚል ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ የለበሱ
አራት ሰዎች ከመኪናው ወርደው ወደ እኛ መጡ። አንድ ነጭ እና ቆዳዋ ነጣ ያለ ምንአልባት የሊባኖስ ሰው እና ሌሎቹ የሃገሩ ሰዎች ሴራሊዎናውያን ናቸው:: ጦርነቱን ያዩ አይመስሉም የተመቻቸው ነበሩ። ወደ መቶ አለቃ ተልከው የመጡ ይመስላሉ። እሱም ሲጠብቃቸው ነበር፡፡ ቤት ደጃፍ ተቀምጠው ሲያወሩ ከማንጎ ዛፍ ስር ተቀምጠን መሳሪያችንን
እየወለወልን እናያቸው ነበር። በኋላ መቶ አለቃ ከሁለቱ የውጭ ሃገር ሰዎች ጋር እጅ ተጨባበጠ፡፡ ጠባቂው ወደ እኛ መጣ እና እንድንሰለፍ ነገረን። ሰፈሩን እየዞረ ከ “ መቶ አለቃ የመጣ ትዕዛዝ ነው!” ትዕዛዝ መቀበል እና የታዘዝ ነውን መፈፀም ለምደናል። ወደ ጎን መስመር ሰርተን መጠበቅ ጀመርን።

መቶ አለቃ ከፊታችን ቁሞ ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠን፡፡ ሌላ ግዳጅ እየጠበቅን ነበር፡፡ “አሳርፍ” ብሎ ቀስ ብሎ መራመድ
መቃኘት ጀመረ፡፡ እንግዶቹ ከጀርባ ነበሩ።
“ስጠቁም ወደ ጠባቂየ በመሄድ ትሰለፋላችሁ ገብቷችሃል።”ሲል “አዎ! አለቃ” ብለን ጮህን፡፡

“አንተ፣ አንተ.....” መቶ አለቃ እየመረጠ እስከ ሰልፉ መጨረሻ ደረሰ፡፡ መቶ አለቃ እኔን ሲመርጠኝ አትኩሬ ተመለከትኩት።
እሱ ግን አላየኝም:: አል ሃጂም ተመረጠ። ኬን ግን ትልቅ ስለሆነ አልተመረጠም:: “መሳሪያችሁን የጥይት ካዝና አወላልቃችሁ መሬት ላይ አስቀምጡ” የሚል ትዕዛዝ ከመቶ አለቃ ሰጠ፡፡ መሳሪያችንን አወላልቀን መሬት ላይ አስቀመጥን።መቶ አለቃን ተከትለን እንግዶች ወደ የመጡበት ገልባጭ መኪና ሄድን። መቶ አለቃ ፊቱን ወደ እኛ ሲያዞር ቆምን “ ጎበዝ ጀግና
ወታደር ነበራችሁ! ታውቃላችሁ የዚህ ወንድማማችነት እና ሃገርን የማዳን ጥሪ አካል እንደነበራችሁ። ከእናንተ ጋር ሃገሬን
በማገልገሌ ክብር ይሰማኛል። ኮርቼባችዋለሁ። አሁን ስራችሁ
እዚህ ጋ ያበቃል። ልለቃችሁ ይገባል። እነዚህ ሰዎች ትምህርት ቤት ያስገቧችኋል፤ ሌላ መልካም ህይወት እንዲኖሩዋችሁ ይረድዋችኋል።” ይሄን ብቻ ነበር ተናግሮ ትቶን ሄደ:: ቀጥሎ
ፍተሻ ነበር። ሰንጢ እና ቦምብ ይዤ ስለነበር መፈተሽ አልፈለኩም፡ ፈታሹን ብትነካኝ እገልሃለሁ ብየ ዛትኩበት። ከእኔ
ጎን ወደ አለው ቀጠለ።

ምን እየሆነ እንዳለ አልገባኝም? መቶ አለቃ ለእነዚህ ሰዎች ለምን አሳልፎ ሊሰጠን እንደወሰነ አልገባኝም። ጦርነቱ እስኪበቃ ድረስ የምንቀጥል መስሎን ነበር፡፡ ግን ያለምንም ማብራሪያ
ተወሰድን፡፡

መኪና ውስጥ የደንብ ልብሳቸው ንጹህ እና መሳሪያቸው አዲስ የሆነ ሶስት ፖሊሶች ነበሩ። ፖሊሶቹ ከገልባጩ ወርደው እኛ እንድንወጣ ጠቆሙን። ወጥተን ሁለት አግድም ወንበሮች
ላይ ፊት ለ ፊት ተቀመጥን። ፖሊሶች መውረጃው ላይ ተቀመጥን።

አል ሃጂ እና እኔ በመገረም በብስጭት ተያየን። የት እንደሚወስዱን እንኳ አናውቅም። ለስዓታት ተጓዝን። ያለምንም ስራ ቁጭ ብሎ መጓዙ አድካሚም
አሰልቺም ነበር፡፡ መኪናውን ጠልፎ ወደ ባውያ ለመመለስ አሰብኩ። መሳሪያውን ለመንጠቅ ስዘጋጅ መኪናው ለፍተሻ
ፍጥነቱን ቀንሶ ፖሊሶቹ ወረዱ።
መቀመጥ ስላልቻልኩ በጉዞ በሙሉ እረፍት አልነበረኝም ያቁነጠንጠኝ ነበር። የፍተሻ ጣቢያዎች ስንደርስ ትንሽ ፈታ እል ነበር። በመጨረሻ ፍተሻ ጣቢያ ያገኘናቸው ወታደሮች የሚያምር ደንብ ልብስ የለበሱ መሳርያቸው አዲስ ነበር።

በኮሮኮንች መንገድ የመጨረሻ ፍተሻ ጣቢያውን አልፈን እንደሄድን የተጨናነቀ የአስፓልት መንገድ ደረስን። ዙሪያውን
መኪኖች በተለያየ አቅጣጫ ሲጓዙ አየሁ፡፡ በህይወቴ የዚህን ያህል ብዙ መኪኖች አይቼ አላውቅም፡፡ መርሰዲሶች፣ቶዮታዎች፣ማዝዳዎች፣ቼርቮያለ ትዕግስት ሲያጮሁ ሙዚቃ ሲያጫውቱ ነበር፡፡ የት እንደምንሄድ አሁንም አላውቅም ነገር ግን Freetown ፍሪታውን የሴራሊዮን ዋና ከተማ እንዳለን
አውቂያለሁ።ለምን እንደሆነ ግን አላወቅኩም፡፡

ውጩ እየጨለመ ነው። መኪናችን በዝግታ ወደ ተጨናነቀው መንገድ ሲገባ የመንገድ መብራቶች ተራ በተራ
እንደፍንጣቂ ነገር ቦግ ቦግ እያሉ መብራት ጀመሩ። የሱቆች እና
የመጠጥ ቤት መብራቶች ሳይቆጠር ብዙ መንገድ መብራቶች ከተማዋን አንቆጥቁጠዋታል። የከተማዋ ፎቆቹም በብዙ ብርሃን የተንቆጠቆጡ ናቸው። ለተወሰኑ ደቂቃዎች በፍጥነት
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_አራት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


“ኑ ወደ ማዕድ ቤት ትንሽ ምግብ ያስፈልጋችኋል።” አለ ሴራሊዮናዊው የዩኒሴፍ ሰራተኛ፡፡ ተከተልነው።

በማዕድ ቤቱ ውስጥ አግድም ወንበርአ ላይ ከሌሎች ልጆች ጋር ተቀመጥን። ሩዝ በጎድጓዳ ስሃን ቀረበልን፡፡ እሱን ያለምንም
ፋታ መብላት ጀመርን። አል ሃጂ ከየት ናችሁ ብሎ እስከሚጠይቅ ድረስ ምንም አላወራንም: አል ሃጂ ሲጠይቃቸው
ደስተኛ አልነበሩም:: ማነህ አንተ? ያንተን ጥያቄ ልንመልስ ነው የመጣነው?” ሲል አል ሃጂ ተነስቶ ገፈተረው። ልጁ ተነስቶ
ሊደባደብ ሲል አንድ ሰው ተዉ ልጆች!” አለ።

ቦምብ አውጥቼ ይሄ የመጨረሻችሁ እንዲሆን ነው የምትፈልጉት ወይስ ጥያቄውን ትመልሳላችሁ?” አልኩ፡፡

ከኬኖ ወረዳ ነው የመጣነው”
“አልማዝ ከሚገኝበት አካባቢ?” አለ አል ሃጂ።
“ከጦሩ ጋር ነው ወይስ ለአማጺዎች ነው የተዋጋችሁት?”
ምኔ አማጺ ይመስላል? ለጦሩ ወግኜ ነው የተዋጋሁት።
አማጺዎች መንደሬን አቃጥለው ወላጆቼን ገለዋል፤ አንተ ግን እነሱን ትመስላለህ።”

በአንድ ወገን ነዋ የተዋጋነው” አለ አል ሃጂ። ተቀመጥን።ቦምቡን እንደያዝኩት ነበር። ፊቴን ወደ ማዕድ ቤቱ ያመጣን
ሰውየ አዙሬ “ መቶ አለቃ ለምን ለእነዚህ ያልታጠቁ ሴታ ሴት ሰዎች አሳልፈው እንደሰጡን ታውቃለህ?” ብየ ጠየቅኩት።
በፍርሃት ርዶ፣ በላብ ተጠምቆ ሊመልስ ሲል አንዱ ልጅ “ እሱ ያልታጠቀ ነው ሌሎች ልጆችን እንጠይቃቸው”አለ። ማቡ ይባል ነበር በኋላ ጓደኛሞች ሁነናል፡፡ ተነስተን ቤት ደጃፍ ላይ ወደ ተቀመጡት ታዳጊዎች ሄድን፡፡

“ጓዶች አዛጋችሁ ለምን ለእነዚህ ሰዎች እንደሰጡዋችሁ ታውቃላችሁ?” ብሎ አል ሃጂ ጠየቀ። ዝም አሉ፡፡ “ኣትሰሙም
እንዴ?

“ማንም እንዲያስቸግረን አንፈልግም” አለ በሸካራ ድምጸ።በዛ ላይ ላልታጠቀ ተራ ሰው ጥያቄ መልስ መስጠት አንፈል
ግም።”

“ተራ ሰው ሲቪል አይደለንም! አለ ማቡ በቁጣ።” ተራ ያልታጠቀ ሰው ካለ እናንተ ናችሁ። መለዮ እንኳን ያልለበሳ
ችሁ። ምን አይነት ወታደር ነው መለዮ ማይለብሰው ባካችሁ?!”

“ለአማጺዎች ነው የተዋጋ ነው፤ ጦሩ ጠላታችን ነው።ለነጻነት ነው የተዋጋነው! ጦሩ ቤተሰቤን ገድሏል መንደሬንም
አፍርሷል፡፡የጦሩን አባላት ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እገላለሁ”ብሎ ተነሳ።

“አማጺዎች” ብሎ ማቡ ጮኸ። ሰንጢዎቻችን አውጥተን ተፋጠጥን፡፡ እንደገና ጦርነት! ፈረንጆቹ ቦታ ስለቀየርን ከጦር ቀጠና ስለተገለልን ብቻ ደህና የምንሆን መስሏቸዋል።አዕምሮችን የተበረዘ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ መሆናችንን አላወቁም! አሁን በቀላሉ እንደማናገግም ይገባቸዋል።

ቦምብ ወረወርኩ ግን ዘገየ፡፡ ድብድቡ ቀጠለ አንዳንዶቻችን ሰንጢ ይዘን ሌሎች በባዶ እጅ መታገል ጀመርን። አንዱን እግሩን ወጋሁት ሌላው እኔን ሊወጋ ሲል አል ሃጂ ቀድሞ ከጀርባ ወጋው፡፡ የጮኸ ወይም ያለቀስ የለም ሁላችንም ለምደነዋል በዛ ላይ አደገኛ ዕፅ ወስደን ነበር፡፡ ፖሊሶቹ “አቁሙ አቁሙ” እያሉ
ወደ እኛ መጡ፡፡ከአገላገሉን በኋላ የወደቀውን ሊያነሱ ሲጎነበሱ ገፍትረን ጥለን መሳሪያቸውን ቀማን። ማቡ ተኩሶ የተወሰኑትን ገደለ ሌሎችን ደግሞ አቆሰለ፡፡ አማጺዎች ከእኛ ወገን ሁለት
ታዳጊዎችን ገደሉ፡፡ ፖሊስ ወደ ሰማይ ቢተኩስም መታገል አላቆምንም:: ስለዚህ በጉልበት ለያዩን መሳሪያ ድቅነው
አቆሙን። አምቡላንስ እየጮኸ መጥቶ የተጎዱትን ወሰደ።ስድስት ታዳጊዎች ሲሞቱ ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ ብዙዎች
ቆሰሉ።

በማቡ ጀብድ ተገረምን፤ማዕድ ቤት ተመልሰን ስለእሱ ነበር የምናወራው። አንዱን ልጅ አይኑን መትቶት ልጁ ቡጢ ሊመልስ ቢፈልግም ማቡን ማየት አልቻለም። ድብድብ ረብሻው ለእኛ
ጨዋታ ነበር። ከማዕድ ቤት አውጥተው ወሰዱን። የጦር መኪና እየጠበቀን ነበር፡፡ “ወደ ጦርነቱ ሊመልሱን መሆን አለበት::” አለ አል ሃጂ። ዝም ብለን ብሔራዊ መዝሙሩን መዘመር ጀመርን::ወደ ጦርነቱ አልመለሱንም ነገር ግን ቤኒን ቤት ወደ ሚባል ሌላ የማገገሚያ ማዕከል ነበር የወስዱን፡፡ ለምን ወደ እዚህ ቦታ
እንደመጣን አሁንም አላወቅኩም፡፡ G3 ሽጉጤ፣ የጦርነት ፊልም እና የምወስደው ክኒን ትዝ ይለኛል። ከሁሉም በላይ መቶ
አለቃ “ከአሁን በኋላ ያገኘነውን አማጺ እንገላለን፧ ምህረት ምርኮኛ የሚባል ነገር የለም”የሚለው ንግግር ወደ አዕምሮየ
ይመላለስ ነበር።

ባልታጠቀ በሲቪል መታዘዝ ያበሳጫል፡፡ ድምጻቸውን መስማት እንኳ አልፈልግም:: ለቁርስ እንኳ ሲጠሩን ሳጥን ያገኘሁትን ነገር በቡጢ እመታለሁ። ከመመገብ ውጭ የታዘዝነውን አንፈፅምም ነበር።
እንቢተኛ ነበርን! ቁርስ ሻይ እና ዳቦ፣ ምሳ እና እራት ደግሞ ሩዝ እና ሾርባ እንበላ ነበር። መሳሪያችን እና አደገኛ ዕፅ ከእኛ
ጋር ስላልነበር ደስተኞች አልነበርንም።

ተደጋጋሚ የጤና ምርመራ እና የምክር አገልግሎት በነርሶቹ እና ሌሎች ሰራተኞች ይደረግልን ነበር፡፡ አንወደውም ነበር፡፡ ገና
ሲጀምሩ ያገኘነውን እቃ እንወረውራለን እንደበድባቸዋለን።ከምግብ በኋላ ያለምንም ምክንያት እንደባደብ ነበር። ሰራተኞቹ ምንም ብናደርግ እነሱን እንኳ ብንደበድባቸው አያዝኑብንም።
“የእናንተ ጥፋት አይደለም እንደዚህ ልታደርጉ የቻላችሁት”ብለው ፈገግታ ያሳዩናል።በእኛ ተስፋ ላለመቁረጥ የተስማሙ ይመስላሉ።

የራስ ምታት ማይግሬን እንደገና ተንስቶ ያሰቃየኝ ጀምሯል። አንጥረኛ በመዶሻ ራሴን የሚቀጠቅጥ ይመስለኛል።
አንዳንድ ቀን ራሴን መቆጣጠር ከብዶኝ መሬት ላይ እንከባለላሁ:: አል ሃጂ ደግሞ የቤቱን ምሰሶ በመደብደብ ሆስፒታል ገብቶ ነበር፡፡ ቆይቼ እኔም ራሴን ስቼ ሆስፒታል ገባሁ:: ሰውነቴን ሙሉ ያመኝ ነበር፤ ጉሮሮየ ደርቆ የማጥወልወል ስሜት ይሰማኝ ነበር። ነርሷ ፈገግታ እያሳየች ወደ እኔ አልጋ መጥታ መርፌ ወጋችኝ። አካሌ ተዳክሞ ተኛሁ።
በሚቀጥለው ቀን ከሆስፒታል ወጣሁ። ነርሷ ውሃ በደንብ ጠጣ አለች::

አንዳንዴ ከማጥወልወል ስሜት እና ድንገት እራስን ስቶ ከመውደቅ ባለፈ ከሁለት ወር በኋላ በአብዛኛው እየተሻለን
መጣ፡ የጦርነቱ መጥፎ ትዝታዎች ትርፍ ጊዜ ስለነበረን ወደ አዕምሮዋችን እየመጣ ያስጨንቀን ነበር። ይሄን ለማስረሳት ይመስላል ትምህርት ትጀምራላችሁ ተብለን የትምህርት
መሳሪያዎች ተሰጠን። ደብተር፣ እስክርቢቶ እና እርሳስ ከተሰጠን በኋላ ከሰኞ እስከ አርብ ከአራት ስዓት እስከ አስራ ሁለት ስዓት ትምህርቱ እንደሚሰጥ ተነገረን።ወዲያው ግን የተሰጠንን የትምህርት መሳሪያዎች አቃጠልን።
እንደገና ተሰጠን። እንደገና አቃጠልነው፡፡

አንድ ቀን ቀትር ላይ የማገገሚያው ሰራተኛች የተወሰነ የትምህርት መሳሪያዎች ደጃፍ አስቀምጠው ሂዱ። ማቡ የትምህርት መሳሪያዎችን አየና ለምን አንሸጠውም የሚል ሃሳብ
አመጣ። “ማን ይገዛናል? ሰዎች ይፈሩናል? አለ አንድ ታዳጊ ልጅ፡፡ “የሚረከበን ነጋዴ እንፈልጋለን” አለ ማቡ። በፕላስቲክ ቦርሳ ተሸክመን ቅርብ ወደ ሚገኝ ገቢያ ወስደን ለአከፋፋይ
ሸጥነው:: “ብዙ ገንዘብ ነው ያገኘነው” አለ ማቡ። ምሳ እንዳያመልጠን ወደ ማዕከሉ ቶሎ ተመልሰን። ከምሳ በኋላ ማቡ ድርሻችንን አከፋፈለ። ግማሾቹ ኮካ ኮላ፣ ከረሜላ እና ሌሎች ነገሮች ሲገዙ ማቡ፣ አል ሃጂ እና እኔ ደግሞ ለሽርሽር ወደ ፍሪ ታውን ለመሄድ አቀድን።

ጥዋት ቶሎ ቶሎ በላይ በላይ ቁርሳችንን ከበላን በኋላ አንድ በ አንድ ሾልከን ከመመገቢያ አዳራሹ ወጣን። ከውጭ ከተገናኘን በኋላ አውቶብስ መጠበቅ ጀመርን።

“ከተማውን ታውቁታላችሁ? ከዚህ በፊት ወደ ከተማው

ሂዳችሁ ታውቃላችሁ?”
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_አምስት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

...ቅጠሎቹ አረንጓዴ ሲሆኑ ግንዱ ግን በጣም አርጅቷል። “ይሄን ስንነግራቸው ማንም አያምነንም” አለ አል ሃጂ።

የእራት ስዓት እየደረሰ ስለነበር ወደ ማዕከል መመለስ ነበረብን፡፡ ያን ምሽት ጓደኞቻችን ስለ ረጃጂም ህንጻዎች :
መኪናዎች እና ገበያው ነገርናቸው፡፡ ሁሉም ደስ ብሏቸው ማየት ፈለጉ። ማዕከሉም ይሄን በመረዳት በሳምንት አንድ ቀን የሽርሽር ፕሮግራም ተያዘልን፡፡

ቀስ በቀስ ወደ ትምህርት ተመለስን። ቀለል ያለ የትምህርት ስርዓት ነበር፡፡ ለሂሳብ መደመር፣ማባዛት እና ማካፈል ስንማር እንግሊዝኛ ደግሞ ምንባብ ማንበብ፣ ቃላቶችን ትርጉም ማወቅ
እና የእጅ ጽሁፍ እንማራለን። ብዙም አንከታተልም ; ትኩረታችን በትንሽ ነገር ይሰረቃል። በእርሳስ እንወጋጋላን
እንደባደባለን። “የናንተ ጥፋት አይደለም
ወደፊት ትስተካከላላችሁ' ይለናል መምህሩ።

ከምሳ በኋላ የጠረጴዛ ቴንስ ወይም እግር ኳስ እንጫወት ነበር። ለሊት ግን አስጨናቂ ነበር። በቅዥት እንባንናለን፣ በላብ እንጠመቃለን፣ ጩኸት እና ግድግዳ መደብደብ ነበር። ሰራተኞቹ
ይህን ስለሚያውቁ ጥበቃ ያደርጉልን ነበር።

የሴራሊዮን ዝናባማ ወቅት ከግንቦት እስከ ጥቅምት ሲሆን ሐምሌ፣ ነሐሴ እና መስከረም ደግሞ ከባድ ዝናብ ይኖራል።
ዝናቡ አንዳንዴ የጦርነቱን መጥፎ ትዝታዎች ይቀሰቅስብኛል።
የሰለጠንኩበት ቦታ እና የሞሪባ ሞት ትዝ ይለኛል። ሞሪባ በተኩስ እሩምታ ሲገደል መቅበር ቀርቶ ማልቀስ እንኳ አልቻልንም። አንድ ዛፍ ላይ አስጠግተነው በአፉ ደም እየደፈቀ ትተነው ሄድን።

ሲነጋ ሰራተኛዋ ብርድ ልብሱን መልሳ እያለበሰችኝ “ያንተ ጥፋት አይደለም በፍጹም! አይዞህ ትረሳዋለህ ይሻልሃል”
ትለኛለች፡፡

አንድ ቀን ረፋድ ላይ ቴንስ ስንጫወት የግቢው ሰራተኞች በሙሉ ይመለከቱን ነበር። አንድ ሰው ከኋላ ትከሻዬ ላይ ሲነካኝ ተሰማኝ ። ነርሷ ነበረች ። ነጭ ደምብ ልብስ እና ነጭ ኮፍያ ለብሳለች። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ፊት ለ ፊት ሳያት። ነጭ ጥርሷ ከጥቁር እና አንጸባራቂ ቆዳዋ ጋር ተጣምሮ ልዩ ውበት
ሰጥቷታል። ስትስቅ ደግሞ የበለጠ ውበቷ ይፈካል። ረዥም ናት፤ ትልልቅ አይኖች አሏት፡፡ ጠርሙስ ኮካ ኮላ ሰጥታኝ በሚያስፈልግህ ጊዜ ና እና እየኝ” ብላ ፈገግታ ሰጥታኝ ሄደች::
ከአል ሃጂ ጋር ጨዋታውን ትተን ወደ ውጭ ወጣን እና ኮካውን መጠጣት ጀመርን። “ወዳሃለች” እያለ አል ሃጂ ሊቀልድብኝ ሞከረ። ምንም አላልኩም::

እህ ትወዳታለህ እንዴ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡
“ እኔ አላውቅም:: ትልቅ ናት በዛ ላይ ነርሳችን ናት” አልኩ።
ማለት ሴቶችን ትፈራለህ?” አለ
“አንተ እንደምታስበው ወዳኝ አይመስለኝም” ብየ አል ሃጂን
ተመለከትኩት። የምለውን ነገር እያዳመጠ ይስቃል።

ኮካውን ጠጥተን እንደጨረስን አል ሃጂ ሄደ እኔ ግን ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ወሰንኩ፡፡ በሩ ስደርስ ነርሷ ስልክ እያወራች አየኋት። እንድገባ እና እንድቀመጥ በእጇ ምልክት አሳየችኝ።
ወዲያው ስልኳን አቁማ ፈገግታ እያሳየችኝ ወንበሯን ወደ እኔ
አቀረበች፡፡ ስለ ጦርነቱ ጥያቄ ልትጠይቀኝ እንደሆነ ገመትኩ።
እሷ ግን በተረጋጋ መንፈስ “ ስምህ ማነው” ብላ ጠየቀችኝ፡፡ገረመኝ! ስሜን እንደምታውቀው እርግጠኛ ነበርኩ። “ስሜን ታውቂዋለሽ” ብየ በቁጣ መለስኩ።
“ ምን አልባት ላውቀው እችላለሁ ግን ስምህን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ?” አለች አይኗን እያፈጠጠች::

እሺ እሺ እስማይል” አልኩ፡፡

“ጥሩ ስም” አለች እራሷን እየነቀነቀች፡፡ “ የእኔ ስም አስቴር ነው። ጓደኛሞች እንሁን።”

“እርግጠኛ ነሽ ከእኔ ጋር ጓደኛ መሆን ትፈልጊያለሽ” አልኳት::ለተወሰነ ጊዜ ካሰበች በኋላ “እርግጠኛ ላልሆን እችላለሁ” አለች።

ምን ማለት እንዳለብኝ ስላላወቅኩ እና ማንንም ስለማመን ለተወሰነ ጊዜ ዝም አልኩ። እንዴት መትረፍ እና እራሴን
መንከባከብ እንዳለብኝ ብቻ ነው ነበር የተማርኩት። እንደ መቶ አለቃ ጃባቲ ያሉ ያመንኳቸው የታዘዝኳቸው ሰዎች እንኳ
ሰዎችን በተለይ አዋቂዎችን እንድጠራጠር አድርገውኛል::
የሰዎችን ሃሳብ መጠራጠር ከጀመርኩ ቆይቻለሁ። ሰዎች ጓደኛ የሚሆኑት አንዱ ሌላው ላይ ጥቅም ለማግኘት ነው ብየ አስብ ነበር፡፡ ስለዚህ ለነርሷ ምንም መልስ አልሰጠኋትም።

“ያንተ ነርስ ነኝ በቃ ይሄ ነው። ከእኔ ጋር ጓደኛ መሆን ከፈለክ ልትጠይቀኝ እና ላምንህ ይገባል” አለች። ተመሳሳይ ሃሳብ
ስለነበረን ፈገግ አልኩ። ፈገግታህ ያምራል” አለች። አፍሬ ቁጥብ ሆንኩ።
“ከከተማ እንዳመጣልህ የምትፈልገው ነገር አለ?” ብላ ጠየቀችኝ፡፡ መልስ አልሰጠሁም::

“ለዛሬ ይበቃናል” አለች፡፡

ከተወሰነ ቀን በኋላ ነርሷ ስጦታ ሰጠችኝ። የተጠቀለለ ነገር ነበር ምን ይሆን እያልኩ መክፈት ጀመርኩ። ልክ እንዳየሁት በደስታ ተነስቼ አቀፍኳት። “ጓደኛ ካልሆን ለምን ይሄን ማዳመጫ እና ካሴት አመጣሽልኝ? ራፕ ሙዚቃ እንደምወድ እንዴት አወቅሽ?”

“እባክህ ተቀመጥ” አለች። የጆሮ ማዳመጫውን አደረኩ
D.M.C የዲ.ኤም.ሲ ሙዚቃ ነበር የምሰማው “It's like that and that the Way it is...” እንደዛ ነው እንደነገሩ” ራሴን ማንቀሳቀስ ጀመርኩ።አስቴር የጆሮ ማዳመጫውን ከጆሮዬ አውጥታ “አንተ ሙዚቃ ስታዳምጥ እኔ ልመረምርህ ነው”
አለች። ተስማማሁ። ምላሴን ፣ አይኔን አየች ከዛ እግሬን ስታይ ጠባሳ ነበረኝ። “ይሄ ጠባሳ እንዴት ወጣብህ?”

“በጥይት ተመትቼ ቆስየ ነው” እላለሁ በቀላሉ።

ፊቷ በሃዘን ተሞላ “ምን እንደሆንክ ምን እንደሚሰማህ ከነገርከኝ መድሃኒት ላዝልህ እችላለሁ” አለች። ሁሉንም
ነገርኳት፡፡ እንዴት በጥይት እንደተመታሁ፣
ስንት ጊዜ እንደተመታሁ እና ከዛ ምን እንዳደረኩ ነገርኳት። ልነግራት ግን
ፈልጌ አልነበረም፡፡ አስቃቂውን የጦርነቱን ክስተት ስነግራት መጠየቅ ታቆማለች ብዬ እንጂ። እሷ ግን በጥንቃቄ ታዳምጣለች። የትናንቱን ታሪኬን ማስታወስ ስጀምር አንገቴን ደፋሁ።

በበጋ ወቅት ስለነበረው ጦርነት ነገርኳት። ምግብ እና ጥይት ያጠረን አስቸጋሪ ወቅት ነበር። ሌላ መንደር ማጥቃት ነበረብን።ከትንሽ ስለላ በኋላ የሶስት ቀን ጉዞ ወደ ሚጠይቅ አንድ ሰፈር ሄድን። እቅዳችን ምግብ እና ጥይት ይዞ መምጣት ሳይሆን የምናጠቃውን ሰፈር ወደ ዋና ማዕከል መቀየር ነበር። ያለን
መሳሪያ እና ምግብ ይዘን ወጣን። ቦታው ደርሰን ለደፈጣ ውጊያ ስንዘጋጅ መንደሩ ባዶ መሆኑን ተገነዘብን። ከስዓት በኋላ
አምስት ታጣቂዎች መጥተው ባልዲ ይዘው ወደ ወንዙ ወረዱ..ገና መጠርጠር ስንጀምር ከኋላ ተኩስ ተከፈተብን። ለሊቱን ሙሉ ተታኮስን፡፡ አምስት ሰዎች ሞቱብን፣ የተረፍነውንም ተከተሉን። መቶ አለቃ ጠንክሮ ከመዋጋት ሌላ አማራጭ
እንደለለን ነገረን። ሌላ መንደር ለመሄድ በቂ ምግብ ወይም ጥይት የለንም፡፡ይሄን ጦርነት ካላሸነፍን ጫካው ውስጥ
መንከራተት ከዛም ማለቃችን ነው:: ስለዚህ ወደ ማጥቃት ገብተን መጀመሪያ ከሞቱት መሳሪያ አገኘን እና ተበተን::
በሁለተኛው ዙር እንደገና ተሰባስበን ማጥቃት ጀመርን::በመጨረሻ ከጠላቶቻችን በላይ ሐይል አግኝተን መበተን ቻልን:: የተኩስ እሩምታው በረደ፡፡ መንደሩ በእኛ ቁጥጥር ውስጥ ሆነ::
በድንገት ጥይቶችን በምሰበስብበት ወቅት የጥይት ዝናብ ወረደብን።

ሶስት ጊዜ እግሬ ላይ ተመትቼ ራሴን ስቼ ወደቅኩ። ሁለቱ ጥይቶች ገብተው ወጥተዋል አንዱ ግን እግሬ ውስጥ ቀረ::
በሚቀጥለው ቀን ስነቃ እግሮቼ ላይ ምስማር የተተከለ ይመስላል።
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ስድስት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


ይሄን ነግሬያት ከሆስፒታሉ ለመውጣት ተነሳሁ። አስቴር ግን “በኮንናውት ሆስፒታል ሙሉ ምርመራ እንድታደርግ
ሁኔታዎችን አመቻቻለሁ።” ብላ ላፍታ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ ሙዚቃ ማዳመጫው ከእኔ ጋር ይቆይ ሌሎች እንዲቀኑብህ
እና እንዲሰርቁህ አያስፈልግም፡፡ በፈለከው ቀን መጥተህ ማዳመጥ ትችላለህ። ሁሌም እኔ ከዚህ ነኝ” አለች። ሙዚቃ ማዳመጫውን ወርውሬ ወጣሁ።

አንድ ቀን ከስዓት አስቴር ከስራ እረፍት ብትሆንም ከሁለት ሌላ ሰዎችጋር በነጭ ቶዮታ መጣች። አንዱ ሰው ሹፌር ሲሆን
ሌላው ግን የ ጦርነት ጋር የተገናኙ ህጻናት ወይም Children Associated with War የመስክ ሰራተኛ ነበር። ድርጅቱ ከ ዩኒሴፍ እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚሰራ የካቶሊክ ድርጅት ነበር።

“ ወደ ሆስፒታል ሂደን ከተመረመርክ በኋላ ከተማ ሽርሽር ትሄዳለህ።” አስቴር በደስታ ምን ትላለህ ብላ ጠየቀችኝ፡፡

“እሺ” ብየ ተስማማሁ። ደስ ብሎኛል።”ጓደኛየ አል ሃጂ መምጣት ይችላል?” ብየ ጠየቅኩ።

“ይችላል” ስትል እንደምጠይቃት የጠበቀች ይመስላል።ወደ ፍሪ ታውን መንቀሳቀስ ስንጀምር የመስክ ሰራተኛው
“ ስሜ ለስሊ ይባላል፤ ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል” ብሎ ተዋወቅን።ወደ መሐል ከተማው ስንደርስ አስቴር እጆቿን እየጠቆመች ፖስታ ቤት፣ ሱቆችን፣ የተባባሩት መንግስታት ድርጂት
ህንጻዎችን እና የጥጥ ዛፉን አሳየችኝ። በከተማው ሁሌም እደነቃለሁ። በስራ የተጠመዱ ሰዎች ሲጣደፉ ሲወጡ ሲወርዱ የነጋዴዎች የግዙኝ ጩኧት ደግሞ ልዩ ድምፅ ይሰጣል።

ዶክተሩ የቆሰለ ወይም በጥይት የተወጋ ሰውነቴን እየነካ እና እየጨበጠ “የሚሰማህ ነገር አለ” እያለ ደጋግሞ ይጠይቀኝ ነበር፡፡መናደድ ስጀምር ጨርሰሃል አለኝ፡፡ ልብሴን ለብሼ አስቴር ፣
ለስሊ እና አል ሃጂ ወደ ሚገኙበት መቆያ ክፍል ሄድኩ::ተያይዘን ወደ ገበያው ሄድን። አስቴር ለ አል ሃጂ የስፖርት
ማሊያ ስትገዛለት ለስሊ ደግሞ ለእኔ የ ቦብ ማርሌን ኤክሶዶስ (ስደት) የሚለውን አልበም ገዛልኝ፡፡ አል ሃጂ ማሊያውን
ወዲያው ለበሰው:: ማሊያው የሃገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቃላማ ማለትም አረንጓዴ፣ ነጭ እና ሰማያዊ ቀለማቶችን ይዟል።
አስቴር ለሁላችንም ኮካ ኮላ ገዛችልን። ለስለ እኔ እና ሌሎች ልጆችን ለማገዝ እንደተመደበ እና ዋና ስራው እኛ ከማገገሚያው በኋላ ለሚኖረን ህይወት ነገሮችን ማመቻቸት ነው።

በሚቀጥለው ቀን ወደ ከተማ ተመልሰን እኔ ሆስፒታል ሄድኩ። አስቴር ራሴን እያሻሸች “ መልካም ዜና ነው። ውጤትህ
መጥቷል። ዶክተሩ ለክፉ የሚሰጥ ህመም እንደሌለብህ አረጋግጧል። ለበለጠ እርግጠኝነት የተወሰኑ መድሃኒቶችን ትወስድ እና ዳግም ምርመራ ይደረግልሃል” አለች። ምንም
አላልኩም ! እሷ ግን ካሴት እና ማዳመጫውን ሰጠችኝ። አስቴርን እየለመድኳት ስመጣ ስለ ብዙ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡በተለይ ግን ስለ ሙዚቃ ቦብ ማርሌ እና ራን ዲ.
ኤም.ሲ፡፡ ለስሊ በሳምንት ሁለት ጊዜ ይመጣ ነበር። ስለ ራስ ተፈሪያኒዝም ማውራት ይወዳል። እኔም #የኢትዮጵያ ታሪክ ደስ ይለኛል በተለይ ንግስት ሳባ እና ንጉስ ሰለሞን የተገናኙበት ታሪክ
ይገርመኛል። የተጓዙት ረዥሙ ጉዞ ፣ የመረጡት ቦታ እና ለመድረስ ያሳዩት ፅናት ሁሌም ይገርመኛል። ከህይወቴ ጋርም ለማገናኘት እጥራለሁ፡፡ የእኔ የህይወት ሩጫ እንደ እነሱ ትርጉም ያለው እና ደስታ የሞላበት እንዲሆን እመኛለሁ።

አንድ ምሽት አስቴር ቤቷ ወሰዳ እራት ጋበዘችኝ፡፡ ከእራት በኋላ ወደ ከተማ ወጥተን መናፈስ ጀመርን። ራውዶን መንገድ ጫፍ ወዳለ የባህር ዳርቻ ሄድን። ጨረቃ በድምቀት ወጥታ ነበር እና ደርቻው ላይ ሁነን መመልከት ጀመርን፡
ልጅ እያለሁ በጨረቃ ውስጥ የተለያየ ቅርፆችን እንመለከት እንደነበር ለ
አስቴር ነገርኳት። ገረማት። ጨረቃዋን እያየን የያዘችው ቅርፅ ምን እንደሆነ መገመት ጀመርን።

ልጅ እያለሁ አያቴ አስተውሎ ለሚያይ እና ለሚያዳምጥ ሰው ሰማይ ይናገራል ትል ነበር፡፡ በሰማይ ሁሌም የጥያቄዎቻችን
መልስ እና የነገሮች ምክንያት ይገለፃል። የእያንዳንዱ ስቃይ፣ ጉዳት፣ ደስታ እና ግራ መጋባት መንስዔ ይነገራል፡፡” ያ ለሊት ሰማዩ እንዲያወራኝ ፈለኩ።

ከአምስት ወር የቤኒን ማገገሚያ ቆይታ በኋላ አንድ ቀን ዓለት ድንጋይ ላይ ተክዤ ተቀምጬ እያለሁ አስቴር አየችኝ። ምንም
ሳትናገር መጥታ ከጎኔ ተቀመጠች። በሰለለ ድምፅ “ ከዚህ በኋላ የምኖርለት ምክንያት ያለ አልመስለኝ እያለ ነው” አልኩ።” ቤተሰብ የለኝም። እኔ ብቻ ነው የቀረሁት። የልጅነት ታሪኬን እንኳ የሚናገር የለም::”

አስቴር እጆቹዋን ወደ እኔ ልካ ጎትታ አስጠጋችኝ እና አቅፋ
“እኔን እንደ ቤተሰብህ አስበኝ፤ እንደ እህት ” አለች:: ግን እህት እኮ የለኝም”
አሁን አለህ፡፡ የአዲስ ህይወት ገፀ በረከት ነው። የተለያዩ የቤተሰብ አባላትን ማፍራት ትችላለህ።” ብላ አየችኝ፡፡

“እሺ! እህቴ መሆን ትችያለሽ ለጊዜው።”

“ይሁን ስለዚህ ነገ ጊዚያዊ እህትህን ለማየት ትመጣለህ አይደል።”

“እሺ!”

በሚቀጥለው ቀን አስቴር ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ጎብኚዎች እንዳሉ ነገረችኝ። ሰራተኞቹ የተሰጥዎ ውድድር እንድናደርግ ጠየቁን፡፡ የምንችለውን ማንኛውንም አይነት ነገር እንድናቀርብ
ነበር የተፈለገው።

ሬጌ ሙዚቃህን ለምን አትዘፍንም” ብላ አስቴር ሃሳብ አቀረበች።

• የሼክስፒርን ቃለ ተውኔትን ባቀርብስ”

“እሺ ትንሽ ሙዚቃ ብትጨምር ጥሩ ይመስለኛል” አለች

እጆችዋን ትከሻየ ላይ አደርጋ። ወድጃታለሁ ግን መውደዱን አላሳያትም:: ስታቅፈኝ ቀስ ብየ ከእቅፏ እወጣለሁ፡፡ ስትሄድ ግን አያታለሁ። ከትምህርት በኋላ ሩጬ እሷን ላይ እሄዳለሁ።ጓደኞቼ ማቡ እና አል ሃጂ “ የሴት ጓደኛህ መጣች እስማኤል” እያሉ ይቀልድብኛል፡፡

ጎብኚዎቹ ከ አውሮፓ ኮሚሽን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጂቶች የተውጣጡ ናቸው። ሙሉ ልብስ ከነከራባቱ ለብሰዋል። እርስበርሳቸው
ስላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ማዕከሉን እየዞሩ ቃኙ። በኋላ ለተሰጥኦ ውድድሩ በሚገባ ወደ ተዘጋጀው ወደ ምግብ አዳራሽ ገቡ። የማዕከሉ ዳሬክተር አቶ ካማራ የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ
በኋላ ውድድሩ ቀጠለ። ተረቶች፣ አስፈሪ ታሪኮች እና የባህል ጭፈራዎች ቀረቡ። እኔ ከጁሊየስ ቄሳር የተወሰነ ቃለ ተውኔት
ካቀረብኩ በኋላ አንድ የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ተጫወትኩ።ሙዚቃው ስለ አንድ ታዳጊ ወታደር ትንሳኤ ሲሆን በአስቴር
የሞራል ድጋፍ እራሴ የፃፍኩት ነው::

ከውድድሩ በኋላ በማዕከሉ ታዋቂ ሆንኩ። የማዕከሉ ዳሬክተር አቶ ካማራ ቢሯቸው ጠርተው “ አንተ እና ጓደኞችህ የእውነት ጎብኚዎችን አስደምማችኋል። አሁን ታዳጊዎች ማገግም እንደሚችሉ አውቀዋል።” አሉ። ወደፊት እንደገና የማቅረብ እድሉ እንዳለኝ ሳውቅ በጣም ደስ አለኝ፡፡ አቶ ካማራ ደግሞ ከእኔ
በላይ በከፍተኛ ስሜት ላይ ነበሩ።

የማዕከሉ ቃል አቀባይ ብትሆን ምን ይመስልሃል?” ብለው ጠየቁኝ፡፡
“ምን! ምንድን ነው ምሰራው ወይም የምናገረውስ?”አልኩ።

“ በመጀመሪያ ስለ ታዳጊ ወታደሮች ዝግጅት በሚኖርበት ጊዜ የምታነበውን ነገር እንፅፍልሃለን። ስራውን ከለመድከው በኋላ ፀ የምታቀርበውን ንግግር እራስህ ልታዘጋጅ ትችላለህ” አሉኝ::
ሳምንት ሳይቆይ በታዳጊ ወታደርነት እና እንዴት መቆም አለበት በሚሉ ሃሳቦች ላይ ንግግር አደረኩ። “ማገገም እንችላለን ብየ እራሴን ምሳሌ በማድረግ ህፃናት ከችግሩ መውጣት
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ሰባት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


“ደህና ነህ?” ብየ ጠየቅኩት::

ደህና ነኝ ብሎ ራሱን እያሻሸ ይቅርታ ይሄን ነገር እንደገና ስላነሳሁት እንደሚያስከፋህ ይገባኛል ግን እውነቱን መናገር አለብኝ” አለ። ክፍሉን እየዞረ የቅርብ ቤተሰቦችህን ማግኘት አልቻልንም። ስለዚህ አሳዳጊ ቤተሰብ ልንፈልግልህ ነው።
እንደሚስማማህ ተስፋ አለኝ፡፡ ሌላ ሃሳብ አለህ?”

“አዎ!” ብየ አባቴ ከጦርነቱ በፊት በዚህ ከተማ የሚኖር አንድ አጎት እንዳለኝ ይነግረኝ እንደነበር ነገርኩት።

ስሙ ማን ነው?”

“ቶሚ ይባላል እና አባቴ አናፂ እንደሆነ ነግሮኝ ነበር” ብየ መለስኩ።

“ምንም ቃል አልገባልህም፤ ግን የቻልኩትን እሞክራለሁ።በቅርብ እንገናኛለን” ብሎ ዝም ካለ በኋላ ትከሻየን እየነካካ “ ጥሩ እየሰራህ እንደሆነ ሰምቻለሁ። በርታ”አለኝ። ለስሊ በሰጠሁት ትንሽ መረጃ አጎቴን ከትልቅ ከተማ መሐል ያገኘዋል ብየ ተስፋ
አልታጣኩበትም ነበር። ለስሊ ከሄደ በኋላ ወደ አስቴር ሄድኩ።ለአስቴር ከ ለስሊ ጋር ስለበረን ቆይታ እና አጎቴን ያገኘዋል ብየ
እንደማልጠብቅ ነገርኳት። “ አይታወቅም! ሊያገኘው ይችላል” ” አለች::

አንድ ቀን ቅዳሜ ከስዓት ይመስለኛል ከአስቴር እና መሐመድ ጋር እየተጫወትኩ እያለ ለስሊ እየሳቀ መጣ። ጉድፈቻ የሚወስደኝ ቤት አግንቶልኛል፤ ልቀላቀል ነው ብየ ገመትኩ። ከማህበረሰቡ ጋር “መቀላቀል” ይሉታል ታዳጊ ወታደር የነበሩ ልጆችን ከ ዘመዶቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎች ጋር ሲያገናኙ።

“ምንድን ነው መልካሙ ዜና?”ለስሊ ዜናውን ለመስማት ፤ጉጉቴን ፊቴን ላይ እያነበበ ወደ በሩ ተመልሶ በሩን ከፈተው።
አንድ ረጂም ሰውየ ገባ፡፡ ከአባቴ ትንሽ ጠቆር ያለ ፈገግታው ግን ደመቅ ያለ ሰው ነበር።

“አጎትህ ነው አለ ለስሊ በኩራት።

' እንዴት ነህ ልጄ እስማየል? አለ ሰውየው:: ጎንበስ ብሎ በረጅም እጆቹ ጠበቅ አርጎ አቀፈኝ፡፡ ምን አልባት እያስመስለ ቢሆንስ ብየ አሰብኩ። ለቆኝ አለቀሰ። ሲያለቅስ እውነትም ዘመዴ
እንደሆነ አመንኩ፡፡ ምክንያቱም የእውነት ነበር ያነባው፤ በሃገራችን ባህል ወንዶች እምብዛም አያለቅሱም::

“ይህን ሁሉ ጊዜ መጥቼ ስላላየሁህ ይቅርታ አድርግልኝ:: ከዝች ቀን በፊት መጥቼ አይቼህ ቢሆን ንሮ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር። አሁን ያለፈው አልፏል። ዛሬ መጀመር እንችላለን። ስለ አጣሃቸው ቤተሰቦችህ በጣም አዝኛለሁ መፅናናተትን እመኝልሃለሁ። በርታ። ለስሊ ሁሉንም ነግሮኛል።” ለስሊን በአክብሮት አይን እየተመለከተ ቀጠለ “ ከዚህ ጨርሰህ ስትወጣ ከእኔ ጋር መጥተህ መኖር ትችላለህ። ልጄ ነህ! ብዙ የለኝም ግን የምታድርበት ቦታ፣ምግብ እና ፍቅር እስጥሃለሁ።” አለ።

ተነስቼ አጎቴን አቀፍኩት፤ እሱም አቅፎ ግንባሬን ሳመኝ፡፡ትንሽ ዝም ብለን ከቆየን በኋላ “ብዙ መቆየት አልችልም ከከተማ
ውጭ የጀመርኩት ስራ አለ። ለጊዜው ቅዳሜ እና እሁድ እየመጣሁ እጠይቅሃለሁ። አንተም ስትችል አንድ ቀን መጥተህ ቤቴን ታያልኛለህ:: ልጆቼን እና ባለቤቴን ቤተሰቦችህን ትተዋወቃለህ” አለ፡፡

“ጋሼ ከዚህ በኋላ ስለዚህ ልጅ ደህንነት እነግርዎታለን” አለ ለስሊ።

አመሰግናለሁ” አለ አጎቴ።

አጎቴ ስንሸኘው አባትህን ነው የምትመስለው ፤አስተዳደጋችንን አስታወስከኝ። እንደ አባትህ አስቸጋሪ
እንደማትሆን ግን ተስፋ አለኝ” አለ እየሳቀ። እኔም ሳቅኩ።

ስንመለስ አስቴር የቦብ ማርሌን ሙዚቃ ከፈተች እና አብረን ማዜም ጀመርን። “Three Little Birds” ሶስት ትናንሽ ወፎች “Dont Woy about a thing” ስለ ምንም ነገር አትጨነቅ
"Cause every little thing gonna be all right...."
ምክንያቱም ሁሉም መልካም ይሆናል

አጎቴን ስለማግኘቴ ለ አል ሃጂ እና ማቡ ልነግራቸው ፈለኩ ግን እነሱ ቤተሰብ ስላላገኙ ተሰማኝ።

አጎቴ ቃሉን ጠብቆ ቅዳሜ እና እሁድ እየመጣ ይጠይቀኝ ጀመር። ስጦታ ያመጣልኛል፣ ስለ አስተዳደጉ ይነግረኛል ስለ አባቴም ይጠይቀኝ ነበር። አንዴ አባቴ ስለነገረኝ አንድ የልጅነት ትውስታቸው ነገርኩት። አባቴ እና አጎቴ ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲወርዱ ድንገት የንብ ቀፎ ያንቀሳቅሱ እና ንቦቹ ይከተሏቸዋል። አባቴ አጭር ስለነበር አብዛኛው ንብ ከአጎቴ ራስ
ላይ ነበር፡፡ ሩጠው ወንዝ ውስጥ ቢገቡም ጠብቆ ሊለቃቸው አልቻለም:: ስለዚህ ከውሃው ወጥተው ወደ መንደር ሲሮጡ ንቦቹን ወደ ሰፈር ይዘዋቸው መጡ።

“አዎ አስታውሳለሁ፡፡ ሁሉም ሰው ንቦቹን ወደ መንደር ይዘናቸው ስለመጣን አዝኖብን ነበር። መሮጥ የማችሉትን
ሽማግሌ ሰዎች እና ትንንሽ ህፃናትን ንቡ ነድፏቸው ነበር።አባትህ እና እኔ ግን በር ዘግተን አልጋ ስር ተደብቀን በሰዉ
እንስቅ ነበር” ብሎ ሲስቅ አብሬው ሳቅኩ፡፡

አንድ ቀን አጎቴ ቤተሰቦቹን ሊያስተዋውቀኝ ወደ ቤቱ ወሰደኝ::
ፍንትው ያለ ፀሐያማ ቅዳሜ ነበር። ኒው ኢንግላንድ ቬል New England Vile ውስጥ ነው የሚኖረው፡ውብ ከተማ ነበር። ቤቱግን መብራት ሆነ የቦንቧ ውሃ የለም። ወደ ደጁ ስንጠጋ የአጎቴ
ባለቤት ወጣች:: ፊቷ ያበራ ነበር፡፡ አጥብቃ አቀፈችኝ፡፡ ለቀቀችኝ እና ካየችኝ በኋላ ጉንጨን ቆንጥጣ “ እንኳን ደህና መጣህ ልጅ አለች:: አጠር ያለች ጥቁር ፣ ክብ ፊት እና አይኖቿ ጎላ ጎላ ያሉ ሴትዮ ነበረች። አባቴ የራሱ ልጆች አልነበሩትም ግን የቤተሰብ ልጆችን እንደራሱ አድርጎ ያሳድግ ነበር፡፡ አራት ነበሩ፦ አሌ
ትልቁ ሲሆን፣ ማቲልዳ፣ ኮና እና ሶሞ ይከተላሉ፡፡ የሚሰሩትን ስራ አቁመው መጥተው ሰላም አሉኝ፡፡ “ሌላ ወንድም ማግኘት ደስ ይላል” አለ አሌ እያቀፈኝ፡፡ ከተዋወቅን በኋላ ከአክስቴ እና ከአጎቴ በስተቀር ሁሉም ወደ ስራቸው ሄዱ። አክስቴ የምግብ አይነት እያመጣች ትደረድራለች፦ ሩዝ፣ አሳ፣ ሾርባ፣ አትክልት
ሌሎች ምግቦች። ሆዴ እስከሚነፋ ድረስ ብዙ በላሁ። ከምግብ በኋላ አጎቴ የአናፂ መሳሪያዎችን እና መስሪያ ቦታውን
አስጎበኘኝ፡፡

“ አናፂ መሆን የምትፈልግ ከሆነ ረዳቴ ልትሆን ትችላለህ። ግን እንደ አባትህ ትምህርት ቤት መግባት የምትፈልግ
ይመስለኛል” ሲል ፈገግ አልኩ። አሌ ተመልሶ መጣና አጎቴን ከእኔ ከእሱ ጋር ኳስ እንዲጫወት ፍቃድ ጠየቀ፡፡ አጎቴም እሱ ከፈለገ እሽ አለ፡፡ እኔ እና አሌ ተያይዘን ብሮክፊልድስ Brookfields ወደ ሚባል አካባቢ ሄድን።

“ወደ እኛ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል:: የእኔን ክፍል መጋራት እንችላለን” አለኝ፡፡ በእድሜ ከእኔ ይበልጠኛል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም አጠናቋል። ደስተኛ ፣ ስርዓት ያለው እና ተናጋሪ ነው። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት አንዲት ቆንጆ ልጅ ወደ እኛ እጇን ታውለበልባለች። ማናት ብየ ከ መጠየቄ በፊት አሌ የአጎታችን ልጅ ናት ከመንገዱ ማዶ ከጉድ ፈቻ አሳዳጊዎቿ ጋር ነው የምትኖረው፡፡ አሚናታ ትባላለች ትተዋወቃላችሁ” አለኝ፡፡አሚናት የአባቴ ሁለተኛ ወንድም ልጅ ነች።
ኳስ ጨዋታውን እየተመለከትን የእኔ ልብ ግን የነበረው ይኖራል ብየ አስቤው የማላውቀው ቤተሰብ መገኘት ላይ ነበረ።
ደስተኛ ነበርኩ። ስንመለስ አጎቴ ወደ ማዕከሉ ሊመልሰኝ እየጠበቀኝ ነበር። እጄን ይዞ አውቶብስ ጣቢያው እስከምንደርስ ድረስ ምንም አላልኩም:: አውቶብስ ጣቢያው ስንደርስ ሌላ ጊዜ
በእራስህ ልትጎበኘን ከፈለክ ብሎ ገንዘብ ሰጠኝ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ለስሊ ወደ ማህበረሰቡ እንደምቀላቀል ነግሮኝ ነበር፡፡ ከአጎቴ ጋር ነው የምኖረው ሁለቱ
ሳምንቶች ቤኒን ቤት ካሳለፍኩት
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ስምንት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

....ብዙ የጦርነት ታሪክ እያዳመጡ መኖር
ይከብዳል። እኔ የራሴ አንድ አስቸጋሪ፣ አስጨናቂ እና በየ ጊዜው የሚጎዳ ታሪክ አለኝ፡፡ ለምንድን ነው ግን እሷ ይህን የምትሰሪው? ለምንድን ነው ግን እነሱ ይሄን የሚሰሩት? በየፊናችን የሄድን ይመስለኛል። ለመጨረሻ ጊዜ ያየኋት ጊዜ ነው። እወዳታለሁ ግን አልነገርኳትም::

አጎቴ በእጆቹ አንስቶ መኪና ውስጥ አስገባኝ፡፡ “ እንደ አለቃ (ሊቀ መንበር) ነው የምቀበልህ። አለቅነትህ ዛሬ ይጀምራል” አለኝ። አራቱ የአጎቶቼ ልጆች አሌ እና ሶስቱ ሴቶች ማቲልዳ፣
ኮና እና ሶሞ ተራ በተራ እያቀፉ ሳሙኝ። ፊታቸው በፈገግታ በራ። “እርቦሃል አይደል፤ እንኳን ደህና መጣህ በማለት ቆንጆ ዶሮ ወጥ ሰርቼለሁ” አክስቴ፡፡ እውነትም ቆንጆ ነበር። ታፋጭ!
እጄን እየላስኩ ነበር፡፡ ከምግብ በኋላ ምኝታ ቤቱን አሌ አሳየኝ።መሬት ላይ ነበረ ምተኛው። ምንጣፍ፣ አንሶላ እና ብርድ ልብስ የት እንዳለ አሳየኝ፡፡ ወደ ደጃፍ ስወጣ አጎቴ ከተማውን ታውቀዋለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “ብዙም አለመድኩትም” አልኩ።

“አሌ ያስጎበኝሃል። ካልሆነ ደግሞ በራስህ እየጠፋህ እየተገኘህ ልታጠናው ትችላለህ። ከተማው ለማውቅ ጥሩ ነው::”

ከአጎቴ ጋር መኖር ከጀመርኩ ከአንድ ወይም ሁለት ቀናት በኋላ አሌ ሸሚዝ፣ ቀበቶ እና ከሙሉ ልብስ ጋር የሚለበስ ጫማ ሰጠኝ:: “ ጨዋ መሆን ከፈለክ እንደ ጨዋ ልበስ” ብሎ ሳቀና ቀጠለ፡፡ “ሚስጥር ነው:: ዛሬ ማታ ጭፈራ ቤት ልወስድህ እፈልጋለሁ:: ትንሽ ዘና ትላለህ:: አጎቴ ወደ ምኝታ ከሄደ በኋላ
እንወጣለን::”

ማታ ከቤት ሾልከን ወደ መጠጥ ቤት ሄድን። ከአሌ ጋር ስንሄድ ትምህርት ቤት እያለሁ የሄድኩባቸው የጭፈራ ምሽቶች
ትዝ አሉኝ፡፡ ረጂም ጊዜ ነው ግን የጭፈራ ምሽቶቹ ስያሜዎችን አይረሱኝም፡፡ Back to School” ወደ ትምህርት ቤት
እንመለስ፣ “Pens down” ብዕራችንን እንጣል፣ “Bob Marley Night የቦብ ማርሌ ምሽት እና ሌሎችም ነበሩ። አውራ ዶሮ እስከሚጮህ ድረስ እንጨፍር ነበር። ያኔ በጣም ደስተኛ ነበርኩ።

“ደርሰናል” አለ አሌ። ብዙ ወጣቶች ወደ ጭፈራ ቤቱ ለመግባት ሰልፍ ይዘው ነበር፡፡ ወንዶቹ በደንብ የተተኮስ ሱሪ
እና ሸሚዝ ለብሰዋል፡፡ ሴቶቹ ደግሞ ቆንጆ አበባ ቀሚስ ከረጂም ተረከዝ ጫማ ለብሰው ከአንዳንድ ወንዶች በላይ ረዝመው ይታዩ ነበር። ከንፈሮቻቸውን ደማቅ ቀለም ተቀብተዋል። አሌ ደስተኛ
ሁኖ ከሰልፉ ፊት ካሉት ሰዎች ጋር ያወራ ነበር። ስንገባ ሙዚቃ እስከአንቃሩ ተከፍቶ ነበር። አሌን ተከትየ ጠረጴዛ አግንተን አንድ ከፍ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥን።

“ ወደ ዳንስ መድረኩ ልሄድ ነው” ብሎ ተነሳ፡፡ ብዙም ሳይቆይ በህዝቡ መሐል ተሰወረ። ለደቂቃዎች ሳስብ ከዛ ብቻየን ስደንስ ከቆየሁ በኋላ ድንገት አንድ በጣም ጥቁር ሴት አንስታ ወደ ዳንስ
መድረኩ መራችኝ። አብረን ከምቱ ጋር መደነስ ጀመርን።በሙዚቃው መሐል አንድ ከእኔ ተለቅ ያለ ልጅ ጎትቶ ወሰዳት።

“ አማላይ ነህ አየሁህ እኮ” አለ አሌ ከአጠገቤ ቁሞ። እየሳቀ ነበር። እኔ ምንም አላረኩም:: ከእኔ ጋር መደነስ ፈልጋ ነው።አልኩ

እውነት ምንም ሳትል ሴቶች ወደ አንተ ይመጣሉ” ብሎ ቀለደ፡፡ ለሊቱን ሙሉ ደነሰን አጎቴ ከመንቃቱ በፊት ተመለስን።

ከተወሰኑ ምሽቶች በኋላ ብቻየን ወደ መጠጥ ቤቱ ሂጂ ልጂቱን አገኘኋት። ስሟ ዘይናብ እንደሆነ ነገረችኝ፡፡

“ባለፈው ስለሆነው ነገር ይቅርታ አድርግልኝ” አለች።ወንድሜ ወደ ቤት መሄድ ፈልጎ ነው እና ከእሱ ጋር መሄድ
ነበረብኝ፡፡ ካልሆነ ወላጆቼ ይጨነቃሉ።”

ልክ እንደ እኔ እሷም ብቻዋን ነበረች።

ለሶስት ሳምንታት ያህል አብረን ከቆየን በኋላ ብዙ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረች፡፡ ከየት እንደመጣሁ? ክፍለ ሃገር ማደግ
እንዴት እንደሆነ? ክፍለ ሃገር ብዙ የፍሪ ታውን ሰው የሚጠቀምበት ቃል ሲሆን ገጠሬነትን ከኋላ ቀርነት እና ስርዓት
ማጣት ጋር አያይዞ ይገልፃል። ምንም ልነግራት አልፈለኩም ስለዚህ ተወችኝ። በቃ ከ ፍሪታውን ሴቶች ጋር የነበረኝ የፍቅር ታሪክ ይሄው ነው። ስለ እኔ ማወቅ ይፈልጋሉ እኔ ደግሞ ታሪኬን ለመንገር ዝግጁ አልነበርኩም። ምንም አይደል። ብቻየን መሆኔን ወድጀዋለሁ።

ለስሊ ሊያየኝ መጣ፡፡ እንዴት እንደሆንኩ እና ምን እየሰራሁ እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ ከትንሽ የራስ ምታት በስተቀር ደህና
እንደሆንኩ ነገርኩት። ማስታወሻ ደብተር ነገር አውጥቶ ፃፈ። “አንድ ስራ አለ ላንተ: በጣም አስፈላጊ ነው::”

ሁሌም የመልካም ዜና አብሳሪ ነህ” አልኩት።

“ ጠቃሚ ነው:: ሁለት ልጆችን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኒው ዮርክ አሜሪካ በመላክ የህፃናት ህይወት
በሴራሊዮን ምን እንደሚመስል ለማስረዳት ታስቧል። ስለዚህ
ቃለ መጠይቅ እየተደረገ ነው:: አቶ ካማራ አንተ ቃለ መጠይቅ እንድታደርግ ጠቁመው ነበር። ከፈለክ ይሄ አድራሻው ነው።አለና ሲፅፍበት የነበረውን ወረቀት ከማስታወሻው ገንጥሎ ሰጠኝ፡፡ “አብሬህ እንድሄድ ከፈለክ ቢሮ ና። ለቃለ መጠይቁ

የሚመጥን ልብስ ለብሰህ ና እሺ” ብሎ ሄደ::

የቃለ መጠይቁ ቀን ሲደርስ ግን እንደነገሩ የ አዘቦት ልብስ ለበስኩ። ስኒከርስ ፣ ጂንስ ሱሪ እና ረጅም እጅጌ ቲ ሸርት ለብሼ ሄድኩ። ለማንም የት እንደምሄድ አልተናገርኩም። ለአሌ
ልነግረው አሰብኩ ግን መናገር ከጀመርኩ ስለ ራሴ ከሚያውቀው አጎቴም ከነገረው በላይ ልነግረው ስለምችል ብየ ፈርቼ
ተውኩት።

ጠያቂው አትኩሮ ተመለከትኝ እና ቀስ ብሎ በእንግሊዝኛ

“ስምህ ማነው” ብሎ ጠየቀኝ።

“እስማየል” አልኩ።

ለምን አንተ ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሂዶ በዚህ ሃገር ስላሉ ህፃናት ችግሮች ለመናገር ትክክለኛው ሰው ነኝ ብለህ ታስባለህ?”

“ከክፍለ ሃገር ነው የመጣሁት:: በጦርነቱ የተጎዳ ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ የተሳተፍኩ እና በህፃናት ማገገሚ ያለፍኩ ነኝ፡፡ በቃለ
መጠየቁ ከተሳተፉት የከተማ ልጆች በላይ የተሻለ ግንዛቤ አለኝ፡፡ እኔ አልፌበታለሁ። እነሱ ግን እዛ ሄደው ምን ሊሉ ይችላሉ? ከዜና የበለጠ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም::” ፈገግ ብሎ
የሚያየኝ ጠያቂ ትንሽ አበሳጭቶኛል።

“ሌላስ ምን ትላለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡

“ምንም! ለምንድን ነው ምትስቅብኝ?” ብየ መልሼ ጠየቁኩት::

“አሁን መሄድ ትችላለህ” አለ ሰውየው አሁንም እየሳቀ።

ተነስቼ ወጣሁ። በኋላየ በሩ እንደተከፈተ ትቼው ወደ አሳንሰሩ ሄጄ ቆምኩ አልተከፈተም። ለቃለ መጠየቁ የመጡት
ልጆች ሳቁብኝ። ትንሽ ቆይቶ አንድ ሰው መጣና ግድግዳው ላይ ቁልፍ ተጭኖ ከፈተልኝ፡፡ ቁጥር ተጫነልኝ እና እጁን
በማውለብለብ ተሰናበተኝ፡፡ አሳንሰሩ መንቀሳቀስ ሲጀምር የምይዘው አጣሁ ወዲያው ግን ከወለል ደረስኩ። ከህንጻው
ወጥቼ ቅርጹን መመርመር ጀመርኩ። ለመሐመድ አግኝቼ ልነግረው ጓጓሁ።

ቀስ ብየ የሚያልፉትን መኪናዎች እያየሁ መጓዝ ጀመርኩ፡፡ብዙ መኪናዎች፣ የጦር መኪና እና የሃገሪቱን ባንዴራ እላያቸው
ላይ ያደረጉ መርሰዲስ መኪኖች ተከታትለዉ በፍጥነት አለፉ።ቤት ስደርስ በብዙ መኪኖች ታጂቦ የሚልፈው የተከበረ ሰው ማነው ብየ አሌን ጠየቁኩት። ቲጃን ከባህን ይባላል። አዲሱ ፕሬዝደንት ነው አለኝ፡፡ የሴራ ሊዮን ህዝቦች ፓርቲ የሚባለው ፓርቲው ግንቦት 1996 ምርጫ አሸንፎ ሃገሪቱን ከ ሰምንት
ወራት በፊት ጀምሮ እየመራ እንደሆነ ነገረኝ።

አንድ ጥዋት አቶ ካማራ ወደ አጎቴ ቤት መጣ። ከቀናቶች በፊት
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


አክስቴን ተሰናብቼ መኪና ውስጥ ዘልዬ ገባሁ እና የይለፍ ወረቀት (ፓስፖርት) ለማግኘት በረርን፡፡ የከተማው ሰው ሁሉ
ፓስፖርት አውጥቶ ከሃገር ለመኮብለል የወሰነ ይመስላል። ብዙ ሰው ነበር። አቶ ካማራ ግን ቀጠሮ ስላስያዘ ገብተን ፎቶ፣
አስፈላጊ መረጃዎችን አስገባን እና ክፍያ ፈፅምን። ፓስፖርቱ ከአራት ቀን በኋላ እንደሚደርስ ለአቶ ካማራ ነገሩት።

“የመጀመሪያው ደረጃ ተጠናቋል፤ አሁን ቪዛ ማግኘት አለብን።” አለ አቶ ካማራ ከዛም ከፓስፖርት ቢሮ ወጣን፡፡

ማታ ቤት ስመለስ አጎቴ ቤት ነበር ሰላምታ ስሰጠው ፈገግ ብሎ
“ምን እየተካሄደ እንደሆነ ልትነግረኝ ትችላለህ” አለ። በዝርዝር ኒው ዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሂጄ ስለ ጦርነቱ እና በህፃናት ላይ ስለ ሚያደርሰው ተፅዕኖ ንግግር ላደርግ
እንደሆነ ነገርኩት። አጎቴ ብዙም አላመነም። “ሰዎች ብዙ ጊዜ
እንደዚህ አይነት ተስፋ እየስጡ ሌሎችን ያታልላሉ። ልጄ ተጠንቀቅ! ተስፋህን ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ብቻ እንዳትጥል!”
አለኝ::

ጥዋት ወደ ስራ ከመሄዱ በፊት “የአሜሪካው ጉዞ ዘግጅት እንዴት ነው?!”ብሎ ይቀልዳል።
አቶ ካማራ ገበያ ይዞኝ ሄደና የልብስ ሻንጣ እና የተለያዩ አይነቶች ልብሶች፦ ረጂም እጅጌ ሸሚዝ፣ ጨርቅ ሱሪ እና ባህላዊ ልብሶች ገዛልኝ፡፡ ለአጎቴ አሳየሁት ግን ትሄዳለህ ብሎ ሊያምን
አልቻለም:: “ትንሽ ቀየር ብትል፤ ቢያምርብህ ብለው ነው” ብሎ
ይቀልድብኛል።

አንዳንዴ አጎቴ እና እኔ ከስራ በኋላ ዘወር ዘወር እንላለን። እንደት እንደሆንኩ
ይጠይቀኛል። ደህና እንደሆንኩ
እነግረዋለሁ። ረጂም እጆቹን ትክሻዬ ላይ ያደርግ እና ወደ እሱ ያስጠጋኛል። አንዳንድ ነገሮችን ልነግረው ፈልጌ ቃላቶችን እንዳጣሁ የሚውቅ ይመስለኛል፡፡ እንደዛ ነው ሚሰማኝ፡፡ ከአጎቴ ልጆች ጋር ወደ ጫካ ሂደን እንጨት ስንለቅም አዕምሮዬ ባለፈው
ያየሁት እና የተሰራው በማስታወስ ይዋዥ ቃል።

ሰኞ ጥዋት ዶ/ር ታምባ የተባለ ሰው በአሜሪካን ኢምባሲ እንዳገኘው ተነግሮኛል። ወደ ኢምባሲው ሲሄድ የከተማው ቀስ በቀስ መንቃት ይሰማኝ ነበር። በከተማው ሙሉ የሚሰማው
ማህል ከተማ ያለው የመስጊድ የጸሎት ጥሪ፣ የአዟሪዎች የግዙኝ ተማፅኖ፣ የመኪና ረዳቶች ጥሪ “ሉምሌ፣ሉምሌ” ወይም ኮንጎ ሰፈር። በጣም በጥዋቱ ብደርስም ብዙ ሰዎች ኢምባሲ በር ላይ
ተሰልፈዋል። ፊታቸው የተቆጣ ሰው ይመስላል። ፍርድ ትሞታለህ ወይም ትኖራለህ የሚል ፍርድ የሚጠብቁ ነው
ሚመስሉት፡፡ ምን እንደማደርግ አላውቅም ነበር። ዝም በዬ ሰልፉን ጠብቄ ተሰለፍኩ። ከአንድ ስዓት በኋላ ዶ/ር ታምባ ከአንድ ልጅ ጋር መጣ እና እንድከተለው ጠየቀኝ። ልጁም ቀድሞ
ወታደር እራሱን አስተዋወቀ “ቤህ እባላለሁ። አብረን ስለምንሄድ ደስ ብሎኛል” ብሎ እጄን ጨበጠ። የአጎቴ መልስ ትዝ አለኝ ልጄ ተጠንቀቅ! ተስፋህን ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ብቻ እንዳትጥል”

ከሚያማምሩ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጥን ቃለ መጠየቁን መጠባበቅ ጀመርን፡፡ አንድ ነጭ ሴትዮ በግልፅ መስታውት ጀርባ ቁማ በድምፅ ማጉያ “
ለምን አላማ ነበር ወደ አሜሪካ የምትጓዘው?” ብላ ጠየቀች፡፡

የእኛ ተራ ሲደርስ ከመስታውቱ ጀርባ ያለችው ሴትዮ ፓስፖርታችንን ይዛ ነበር፡፡ ወደ እኔ አላየችም ይልቅ የፓስፖርቴን ገጾች ትገልጥ ነበር። መስኮቱ ለምን እንደዚህ የሰው ንክኪ እንዳይኖር ታስቦ እንደተሰራ ገረሞኝ እመለከት ነበር።

“በድምፅ ማጉያ ተናገር” አለች እና “ለምን አላማ ነበር ወደ አሜሪካ የምትጓዘው?” ብላ ጥያቄዋን ጀመረች::
“በህፃናት ላይ ስለ ሚያደርሰው ተፅዕኖ” ብየ ገለጸኩ::
“ጉባኤው የት ነበር?”
“ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኒው ዮርክ ከተማ
“ወደ ትውልድ ሃገርህ ለመመለስህ ዋስትናህ ምንድን ነው?እያሰብኩ ነበር “ንብረት አለህ፣ መመለስህን ሊያረጋግጥ
የሚችል የባንክ ተቀማጪስ አለህ?”
ተናደድኩ። በዚህ ሃገር ስላለው የህዝብ ኑሮ የምታውቂው ነገር አለ? ብዬ ልጠይቃት አስብኩ። ቀና ብላ ብታየኝ ኖሮ ይሄን ጥያቄ አትጠይቅም ነበር። በእኔ እድሜ ያለ ማንኛውም የሃገሬው ሰው የባንክ ሂሳብ መኖር አይደለም እስከ ጪራሹ ህልሙም የለውም:: ዶ/ር ታምባ በጦርነት የተጎዱ ህጻናት ተራድኦ
ድርጅት ሊቀ መንበር እንደሆነ እና አብሮን እንደሚሄድ፣ጉባኤው ሲያልቅ ወደ ሴራሊዮን እንደሚመልሰን አስረዳት።
ሴትዮዋ የመጨረሻ ጥያቄ ጠየቀች: “ አሜሪካ የሚኖር የምታውቀው ሰው አለ?”

“ማንም የለም። ከዚህ ሃገር ወጥቼ አላውቅም እንዳውም በዚህ ከተማ እንኳ የመጀመሪያየ ነው” አልኩ። ፓስፖርቴን
ዘግታ ነጥላ አስቀመጠችው።

ውጭ ዶ/ር ታምባ ቪዛ እንዳገኘን እና ፓስፖርታችንን ነገ እንደሚወስድ ነገረን፡፡ በመጨረሻ መንገደኛ መምስል ጀመርኩ፡፡
በቀኝ እጄ ሻንጣየን ይዣለሁ ፤ ቡናማ ባህላዊ ሱሪ እና ሽሚዝ ለብሼ ነበር። ከአሌ ክፍል ስወጣ አጎቴ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ነበር።

“ወደ አየር መንገድ እየሄድኩ ነው” አልኩ ፈገግ ብዬ፡ አጎቴ እንደሚቀልድብኝ አውቅ ነበር፡፡አዎ! አሜሪካ ስትደርስ ደውልልኝ፡፡ አይ መች ስልክ አለኝ፡፡በል በአሚናታ ቤት ደውልልኝ መጥታ ታገኘኛለች” ብሎ አጎቴ
ፈገግ አለ።

“እሽ እደውላለሁ” ብየ በፈገግታ መለስኩ።

“ልጆች ኑ ወንድማችሁን ተሰናበቱት። የት እየሄደ እንደሆነ አላውቅም ግን ይቅናህ እንበለው” አለ አጎቴ። ማቲልዳ፣ ኮና እና
ሶሞ ባልዲ እንደያዙ ወደ ደጃፍ መጡ። ውሃ ሊቀዱ ሊሄዱ ነበር፡፡ አቀፉኝ እና በመንገዴ እንዲቀናኝ ተመኙ። አክስቴ ጪስ ጪስ እንደሸተተች ከኩሽና ቤት መጥታ አቀፈችኝ። “ የትም ብትሄድ ቤትህን ጠረን መሽተት አለብህ። ይሄ ላንተ የምሰጥህ ሽቶየ ነው”አለች በፈገግታ:: አጎቴ ተነስቶ አቀፈኝ እጆቹን ትክሻየ ላይ አድርጎ “መልካም ምኞቴ ካንተ ጋር ነው። በኋላ ለእራት እጠብቅሃለሁ” ብሎ ወደ ደጃፍ ወጣ፡፡

ስለ ኒው ዮርክ ያለኝ አመለካከት የሚመነጨው ከራፕ ሙዚቃዎች ነበር። ሰዎች መንገድ ላይ የሚታኮሱበት እና ምንም እንዳልተፈጠረ የሚመስሉበት፣
ማንም የማይጓዝበት ይልቅ በስፖርት መኪኖች ለጭፈራ እና ለሁከት የሚሄድበት ቦታ አድርጌ ነበር በአዕምሮዬ የሳልኩት። እንደዚህ አይነት የእብድ ቦታ መገኘት አልፈልግም። ሃገር ቤት በቅቶኛል::

ጆን ኤፍ ኬኔዲ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ስንደርስ ጨልሞ ነበር። 4፡30 ነበር። ዶር ታምባን ለምን በጠዋት እንደጨለመ
ጠየቅኩት።” (Winter ) በጋ ስለሆነ” አለኝ። “አሃ”ብየ ራሴን ነቀነቅኩ ግን በጠዋት መጨለም የሚለው ነገር ሊገባኝ
አልቻለም:: Winter ዊንተር የሚለውን ቃል በሼክስፔየር ጹሑፎች አውቀዋለሁ ግን ትርጉሙን እንደገና ማየት ያለብኝ
ይመስለኛል።

ዶ/ር ታምባ ፓስፖርታችንን ይዞ ሄደ እና ከኢምግሬሽን ሰዎች ሁሉንም ነገር አስረድቶ አለፈ። ሻንጣችንን አገኘን ወደ
ተንሸራታች በሮች አመራን። ዶ/ር ታምባ ውጭ ነበር። ባህ እና እኔ በተንሸራታች በሩ ስናልፍ በጣም ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበለን።ቆዳየ ሲኮማተር ይሰማኛል፣ ፊቴ ሊሰማኝ አልቻለም፣ እና ጆሮዬ
ተቆርጦ የወደቀ ይመስላል፣ እጣቶቼን አመመኝ ጥርሴም ተንቀጠቀጠ። ንፋሱ በሱሪየ እና ሸሚዜ አልፎ ገብቷል፤ ምንም
የለበስኩ አልመስለኝ አለ፡እየተንቀጠቀጥኩ ነበር። በህይወቴ
እንደዚህ በርዶኝ አያውቅም። ሰው እንዴት ነው ከዚህ ሃገር የሚኖረው? ብዬ አሰብኩ፡፡ ዶ/ር ታምባ ታክሲ ይዞ እኔ እና ባህን አስገባን እና ለሹፌሩ ወረቀት ላይ እያነበበ ወደ የት መሄድ እንደሚፈልግ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሀያ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

...በቀጣዩ ቀን ጠዋት አንድ ደረጃ ወርዶ ወደ ሚገኘው ካፍቴሪያ ሄድኩ። ከሃያ ሶስት ሃገራት የተወጣጡ ሃምሳ ሰባት ህጻናት ቁርስ ሊበሉ እና የተባበሩት መንግስታት የመጀመሪያ አለም
አቀፍ የህጻናት ፓርላማን ለማስጀመር እየተጠባበቁ ነበር::ከሊባኖስ፣ ካምቦዲያ፣ ኮሶቮ፣ ብራዚል፣ ኖርዌይ፣ የመን፣ሞዛምቢክ፣ ፍልስጤም (ፓላስታይን)፣ ጓቲማላ፣ አሜሪካ (ኒው
ዮርክ)፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ፔሩ፣ ሰሜን አየር ላንድ፣ ህንድ፣ ፓፕዋ ኒው ጊኒ፣ ማላዊ እና ሌሎች ሃገራት የተውጣጡ ህጻናት ነበሩ።ባህ እና ዶ/ር ታምባን እየፈለኩ እያለ አንዲት ነጭ ሴት ወደ
እኔ መጣችና እራሷን አስተዋወቀችኝ፡፡

“ክርስቲን እባላለሁ ከኖርዌይ ነው የመጣሁት” ብላ እጇን ለሰላምታ ዘረጋች::

“እስማይል ከ ሴራሊዮን” ብየ እጇን ጨበጥኳት። ወረቀት አወጣች እና ስሜን ደረቴ ላይ ለጥፋ የቁርሱን ሰልፍ
እንድቀላቀል ካደረገች በኋላ ፈገግ እያለች ወደ ሌሎች ህጻናት ሄደች፡፡ በሰልፉ የተከተልኳቸው ሁለት ታዳጊዎች ሰምቸው
በማላውቅ ባዕድ ቋንቋ ያወሩ ነበር። እነሱ የሚፈልጉትን ያውቁ ነበር፡፡ እኔ ግን ምን እንደምፈልግ ወይም የምግቦቹ ስሞች ምን እንደሚባል እውቀቱ አልነበረኝም፡፡ በቆይታየ ሙሉ ግራ ተጋብቼ ነበር። “እንደነሱ” እያልኩ አዛለሁ ወይም ሌሎች ሳህን ላይ ያየሁትን አነሳ ነበር።

ከቁርስ በኋላ ሁለት ህንጻዎች አልፈን ወደ መሰብሰቢያው ህንጻ ሄድን። አሁንም በረዶ ይዘንብ ነበር፡፡ አፍንጫዬ፣ ጆሮዬ
እና ፊቴ ከአሁን ካሁን ወደቀ ብዬ በምሰጋበት፤ በዚህ ቀፋፊ ብርድ
ባለበት ሃገር እማ መኖር የለብኝም አልኩ ለራሴ።

በመጀመሪያው ቀን ስለ እየራሳችን አወራን አንዱ ስለ አንዱ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ነበር ወደ ጉባኤው የመጡት።
ሌሎቹ ደግሞ ወደ ጎረቤት ሃገር መቶ ኪሎ ሜትሮችን ካቁረጡ በኋላ ነበር በረራ ማድረግ የቻሉት። በደቂቃዎች ውስጥ ክፍሉ አስቸጋሪ የልጅነት ጊዜ ያሳለፍን ታዳጊዎች ተሰበሰብንበት
መሆኑን ተረዳን፡፡ ከትውውቅ በኋላ አስተባባሪዎች ስለ ራሳቸው ነገሩን፡፡

አብዛኞቹ አስተባባሪዎች በተለያዩ ተራድኦ ድርጅቶች የሰሩ ናቸው፡፡ አንድ አጠር ያለች ፣ ረጅም ጥቁር ፀጉር እና ጎላ ጎላ
ያለ አይን ያላት ሴት ግን “ እኔ ተረት ነጋሪ ነኝ” አለችን። ስሟ ሎራ ሲም ነበር ሁኔታዋ ገርሞኝ በትኩረት አዳምጣት ነበር።
እጆቿን እየተጠቀመች እያንዳንዱን ቃል ረግጣ በአፅንኦት ትናገር ነበር፡፡ ንግግሯን ከመጨረሷ በፊት የእሷን ስልጠና
ለመውሰድ ወሰንኩ፡፡ ታሪካችንን እንዴት በሚመስጥ እና ተፅዕኖ በሚፈጥር መልኩ መናገር እንዴት እንደምንችል
አስተምራችኋለሁ አለች፡፡ ኒው ዮርክ ከተማ ተወልዳ ያደገች አንዲት ነጭ ሴት እንዴት ተረት አዋቂ እንደሆነች ገርሞኛል።

ያን ቀን ሎራ አይኗ ባህ እና እኔ ላይ አርፎ ነበር። የሳሳ ቲሸርት እና ሱሪ ለብሰን ማሞቂያው አካባቢ ኩርምት ብለን
ተቀምጠን ነበር፡፡ ብርድ አጥንታችን ሰርስሮ ሳይገባ አልቀረም፡፡አሁንም አሁንም ያንቀጠቀጠን ነበር። በምሳ እረፍት ስዓት ሎራ ወደ እኛ መጥታ
ብርድ የሚከላከል ጀኬት አላችሁ?” ብላ
ጠየቀችን።ራሳችንን እየወዘወዝን እንደሌለን ነገርናት። ምሽት
ላይ ጃኬት፣ ኮፍያ እና ጓንት ይዛልን መጣች፡፡ ደስ አለኝ። አሁን ከተማውን ዘወር ዘወር ብዬ መመልከት እችላለሁ። ከአመታት በኋላ ሎራ ጃኬቷን ልትሰጠኝ ብትል ግን አልተቀበልኩም::
የሴት ጃኬት ስለነበር! ያኔ ግን የወንድ ይሁን የሴት ጉዳይህ አልነበረም እያለች ትቀልድብኛለች።

ባህ እና እኔ ከስራ ጋር እየተቀራረብን መጣን። እንዳንዴ በጣም ልጅ ሁኜ የሰማኋቸውን ተረቶች ትነግረናለች::
ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ባሻገር ያለች አንዲት ነጭ ሴት እንዴት የሃገሬን ብሎም የጎሳየን ወግ እና ታሪክ እንዳወቀች እንቆቅልሽ ይሆንብኝ ነበር። ከአመታት በኋላ ደግሞ እናቴ ሆነች። እጣ ፈንታ ወይስ አጋጣሚ? አንድ ተረት አዋቂ እና የወግ ባህል ካለው ማህበረሰብ የወጣ ልጅ ተረት አዋቂ የሆነች እናት በኒው
ዮርክ ሲያገኝ::

ኒው ዮርክ በገባሁ በሁለተኛው ቀን ወደ አጎቴ ደወልኩ።አሚናታ ነበር ያነሳችው። “እስማኤል ነኝ። አጎቴን ማግኘት
እችላለሁ?ብየ ጠየቅኩ።
“ላምጣቸው ከሁለት ደቂቃ በኋላ ደውል” ብላ ዘጋችው።ደውልኩ። አጎቴ ሲያነሳው “ ኒው ዮርክ ከተማ ነው ያለሁት”
አልኩት።
“እንግዲህ አምንሃለሁ።ሰሞኑን እኮ አላየሁህም።” ብሎ ፈገግ አለ፡፡ መስኮት ከፍቼ የኒው ዮርክ ን ጫጫታ አሰማሁት።
አይ ፍሪ ታውን አይመስልም፡፡ እና እንዴት ነው?” በጣም ይበርዳል” ስለው መሳቅ ጀመረ።

ምናልባት የምዕራቡ አለም አቀባበል ይሆናል። ስትመለስ ሁሉንም ነገር ትነግረኛለህ። ወደ ውጭ መውጣት ከሌለብህ አትውጣ::

እሱ ሲያወራ በቤቱ ግቢ የሚያልፈውን ኮረኮች መንገድ አስታወስኩ። የአክስቴ ሾርባ ውል አለብኝ፡፡

ጠዋት ጠዋት በረዶ የተከመረበትን መንገድ አቋርጬ ሂጄ ጉባኤውን እታደም ነበር። ችግራችንን ያሳለፍነውን ሰቆቃ
ስለ ልጆች በተለይዩ ሃገራት ያሉ ህጻናት
ስለሚገጥሟቸው ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው እንወያይ ነበር። ከረጅም ውይይት በኋላ ግን ፊታችን ወደፊት
የሚመጣውን ደስታ በማሰብ እና በተስፋ ይበራል፡፡ ለችግሮች መፍትሄ ስናቀርብ እና ዓለም እንዲያውቀው ስናደርግ ደግሞ ጉዳታችንን ያከምን ወደ በጎ የቀየርን ይመስላል።

በሁለተኛው ቀን ማታ የማሊው ማዱካ እና እኔ በምዕራብ በኩል በአርባ ሰባት ማዞሪያ ስንራመድ ሳናስበው ወደ ታይምስ አደባባይ እየተጠጋን ነበር። ህንጻዎችን እና የሚጣደፈውን ሰው
በማየት ተጠምደን እያለ ብዙ ብርሃን አየን፡፡ በትላልቅ እስክሪኖች የተለያዩ ማስታወቂያዎች ይቀርቡ ነበር። በምስል የተደገፈ ሙዚቃ እና ብዙ ቁጥሮችም ይዞሩ ነበር። ሁሉም በጨረፍታ
ታይቶ በፍጥነት ይቀየራል። በምናየው ነገር ተገርመን ለደቂቃዎች ገረን ቆምን :: ብርዱ እንኳን አልተሰማንም። ልብስ
ቤቶች እና ሌሎች ሱቆችን በመስኮት አፍጠን ስናይ የሚያብረቀርቁ
ህንጻዎች እና የመኪኖች ድምፅ ደግሞ ህልም እስኪመስለን ቀልባችንን ገዛ፡ ወደ ሆቴል ስንመለስ ለሌሎች ልጆች ያየነውን
ነገርናቸው:: ከዛን ቀን በኋላ ሁላችም ምሽት ምሽት ታይምስ አደባባይ እንድንሄድ ተደረገ።
ማዱካ እና እኔ ከቡድን ጉብኝት በፊት አንዳንድ ቦታዎችን ጎብኝተናል በሮክፌለር ፕላዛ የተዋበ ግዙፍ የገና ዛፍ፣የመላዕክት ቅርጻ ቅርጸ እና ብዙ ሰዎች የበረዶ ሸርተቴ ሲጫወቱ ተመልክተናል። በበረዶ ሸርተቴ ሰዎች በተደጋጋሚ እምቧለሌ ሲዞሩ ማዱካ እና እኔ ግን ሰዎች ምን እንዳስደስታቸ አልገባነም፡፡ የአለም ንግድ ማዕከልንም አይተናል፡፡ አንድ ቀን
በባቡር ስንሄድ ማዱካን “እንዴት ነው ሁሉም ሰው ዝምተኛ የሆነው” ብዬ ጠየቁኩት፡፡ ባቡሩን ዞሮ ቃኘና “ እንደ እኛ ሃገር የህዝብ ማመላለሻ አይደለም” አለ። እያንዳንዱን ነገር በአዕምሮዬ ለመያዝ እና በኋላ ለአጎቴ፣ ለአጎቴ ልጆች እና ለመሐመድ ለመንገር እታገል ነበር፡፡ ያምኑኛል ብየ አልጠበቅኩም::

በጉባኤው መጨረሻ ቀን እያንዳንዱ ህጻን ስለመጣበት ሃገር እና ስላሳለፈው ሁኔታ ንግግር እንዲያደርግ ተደረገ።
ዲፐሎማቶች እና የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ነበሩ። ሙሉ ልብሳቸውን ለብሰው በስርዓት ተቀምጠው በጥሞና ያዳምጡን
ነበር፡፡ ከፍሪ ታውን ይዠው የመጣሁት የተጻፈ ንግግር ቢኖርም ከልቤ ለመናገር ወሰንኩ። ስላሳለፍኩት ጊዜ እና ስላለኝ ተስፋ በአጭሩ ተናገርኩ:: ተስፋዬ ጦርነት እንደሚያበቃ ሲሆን ይሄ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሀያ_አንድ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

አንዳንዴ ማታ ማታ ለቤተሰቦቼ መሐመድን ጨምሮ (አሁን ከእኛ ጋር ነው የሚኖረው) ስለ ጉዞዬ እነግራቸው ነበር።
ሁሉንም ነገር አስረዳቸው ነበር፡፡ አየር ማረፊያውን፣ አውሮፐላኖቹን በአውሮፐላን መስኮት አሻግሮ ደመናን ማየት የሚሰጠውን ስሜት ሳይቀር እነግራቸው ነበር፡፡ ስነግራቸው የናፍቆት ስሜት ይሰማኝ ነበር። በአምስተርዳም አየር ማረፊያ እግረኛ መንገድ ስንቀሳቀስ ብዙ ነጮች ቦርሳቸውን እየጣሉ እና በተለያየ አቅጣጫ ሲሯሯጡ ትዝ ይለኛል።
ስለተዋወቅኳቸው ሰዎች፣ ስለ ኒው ዮርክ ረጃጂም ፎቆች፣ ስለ ስስ በረዶቿ እና ሰዎች መንገድ ላይ እንዴት እንደሚሰዳደቡ ሳይቀር ነገርኳቸው።

“የሚገርም ጉዞ ነው” ይላል አጎቴ፡አንዳንዴ በእውኑ አለም የሌለ አዕምሮዬ ውስጥ ለእኔ ብቻ የተከሰተ ይመስለኝ ነበር።

መሐመድ እና እኔ በኤድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገና ትምህርት ጀመርን። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሁኜ ጠዋት ትምህርት ቤት ስሄድ ትዝ ይለኛል። የወደቁ የማንጎ ቅጠሎችን የሚጠርጉ መጥረጊያዎች ድምፅ እና የደነበሩ ወፎች ጫጫታ ታጅበን ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ ትዝ ይለኛል።ትምህርት ቤቱ በጨቃ ጡብ እና ቆርቆሮ የተሰራ ትንሽ ህንፃ ሲኖረው ህንፃው በር አልነበረውም:: ከጥበቱ የተነሳ ሁሉንም ተማሪ መያዝ አይችልም ነበር። ብዙ ክፍለ ጊዜ ውጭ በማንጎ
ዛፍ ስር ጥላ ነበር የምንማረው:: መሐመድ በ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የነበረውን የትምህርት መሳሪያ እጥረት በደንብ ያስታውሳል። ብዙ ጊዜ ደግሞ መምህራን በእርሻ ያግዝ እንደነበር ይነግረኛል። ዘር በመዝራት፣ በመኮትኮት እና
በማጨድ ያግዝ ነበር። አብዛኞቹ መምህራን ኑሮቸውን በእርሻ ይደጉሙ ነበር። ብዙ ባወራሁት ቁጥር ብዙ ነገር እንደዘነጋሁ ማወቅ ጀምሬለሁ፡፡ ተማሪነትን ክፍል ውስጥ መቀመጥ፣
ማስታወሻ መያዝ፣ የቤት ስራ፣ ጓደኛ መያዝ እና ብሽሽቁን ሁሉ ረስቼዋለሁ ። አሁን ግን እንደገና ወደዛ ለመመለስ ጓጉቻለሁ:: በፍሪ ታውን የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ግን ሁሉም ተማሪዎች ከእኔ እና መሐመድ እርቀው ነበር የተቀመጡት::በአንዴ የምንገድላቸው ነበር የመሰላቸው። እንዴት እንደሰሙ
ባላውቅም ታዳጊ ወታደሮች እንደነበርን አውቀዋል፡፡በጦርነቱ ልጅነታችንን ብቻ አይደለም ያጣነው ስማችንም ከዚህ ስቃይ እና መከፋትን ካተረፍንበት መጥፎ ገጠመኝ ጋር እንዲጠራ ሁኖ ጠልሽቷል።

ቀስ ብለን ነበር ቤት ምንመለሰው። ቀስ ብሎ መራመድ ለማሰብ፤ ህይወት ወደየት አቅጣጫ እየተጓዘ እንደሆነ
ለመገምገም እድል ስለሚሰጥ ደስ ይለኝ ነበር። ህይወቴ ካለፈው እንደማይብስ እርግጠኛ ነበርኩ። እሱም የመፅናኛ እና ፈገግታየ ምንጭ ነበር። ቤተሰብ የአንድ ቤተሰብ አባልነትን ገና እየተለማመድኩ ነው፡፡ ለሰዎችም መሐመድ ጓደኛየ እንደሆነ መናገር ስለ ጀመርኩ ብዙ ማብራራት አይጠበቅብኝም።
ያለፈውን ታሪኬን መርሳት እንደማልችል አውቃለሁ። ነገር ግን ስላለፈው ማውራት ማቆም እና ዛሬን በአዲስ ህይወት መኖር
እፈልጋለሁ።

እንደተለመደው በጠዋት ነበር የተነሳሁት። ተነስቼ በቤታችን ጀርባ የሚገኝ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጨ
የከተማውን መንቃት እጠብቃለሁ። ግንቦት 25, 1997 የተኩስ እሩምታ ሰማሁ።ከተማዋ ከተለመደው ድምፅ ወጥታ በተኩስ እሩምታ ደነቆረች። የተኩስ እሩምታ በሃገሪቱ የህዝብ መወሰኛ ሁሉንም ከእንቅልፍ ቀስቀስ። እኔም ደጃፍ ላይ ወደ ነበረው አጎቴ
ምክር ቤት አካባቢ ነበር የሚሰማው።የተኩስ እሩምታው
ምን እየተካሄደ እንደለ አላወቅንም። ወታደሮች ግን በፓዲባ መንገድ ሲሯሯጡ የጦር መኪኖች ሲንቀሳቀሱ አይተናል። የተኩስ እሩምታው እየጨመረ ሌሎች የከተማውን ክፍሎች እያካለለ ነበር የቀጠለው:: የከተማው አዋቂ ስዎች ደንግጠው በፍርሃት እየረዱ በራቸው
ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል። መሐመድ እና እኔ ተያየን። ወደሱ ተጠጋሁ።

ረፋድ ሲሆን ማዕከላዊ እስር ቤት ተከፍቶ እስረኞች ተለቀቁ። ከእስር ከመውጣታቸው በተጨማሪ አዲሱ መንግስት ለእስረኞች መሳሪያ አደለ። አንዳንዶቹ በቀጥታ ወደ ፈረዱባቸው ዳኞች እና ጠበቆች በመሄድ እነሱን እና ቤተሰቦቻቸውን ገደሉ ቤታቸውንም
አቃጠሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ወታደሮች ቀድሞው የጀመሩትን ዘረፋ ተቀላቀሉ:: የሚቃጠሉ ቤቶች ጪስ አየሩን ሞልቶ ከተማዋን በጭጋግ ሸፈናት::

አንድ ሰው በሬዲዩ ወጥቶ ራሱን አዲሱ የሴራ ሊዮን ፕሬዝደንት እንደሆነ አወጀ:: ስሙ ጆኒ ፖል ኮሮማ ሲሆን የአብዮታዊ ጦር ኃይሎች ምክር ቤት መሪ እንደነበር ተናገረ። ምክር ቤቱ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠውን ፕሬዝደንት
ቲጃን ከባህን ከስልጣን ለማስወገድ በጦር መኮንኖች የተመሰረተ ነበር።
የኮሮማ መፈንቅለ መንግስቱን ለማካሄድ እንዳቀረበው ምክንያት መጥፎ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር እንደሆነ እና ሁሉም ሰው ወደ ስራ እንዲወጣ ምክር ሰጠ።

ከንግግሩ ጀርባ ግን የተኩስ እሩምታ እና የተቆጡ ወታደሮች ሲሳደቡ ሲጨፍሩ ይሰማል።

ምሽት ላይ በሌላ አዋጅ አማጺዎች እና ጦሩ የሲቪሉን መንግስት “ለሃገር ጥቅም” ሲባል ለመገልበጥ እንደተቀናጁ
በሬድዮ ተነገረ። አማጺዎች እና ጦር ግንባር የነበሩ ወታደሮችከተማውን ማጥለቅለቅ ጀመሩ፡፡ ሃገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስርዓት አልበኝነት ገባች። እየሆነ ያለው ሁሉ አላማረኝም:: ጠላሁት ወደ ቀድሞ ህይወቴ መመለስ አልችልም:: አሁን ግን በህይወት የማመልጥ አልመስልህ አለኝ፡፡

አማጺዎች እና ወታደሮቹ የባንክ ካዝናን መስበር፣ ፈንጅ ማፈንዳት፣ ሰዎችን አስቁሞ መበርበር መዝረፍ ጀመሩ::
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና የዮኒቨርሲቲ ግቢዎችን ተቆጣጠሩ። ደጅ ተቀምጦ ከመመልከት በስተቀር ምንም
የሚሰራ ነገር የለም:: አጎቴ የጀመረውን ቤት ለመጨረስ ወሰነ።በጠዋት ጀምረን እስከ ረፋድ ድረስ መስራት ጀመርን። የተኩስ እሩምታው ከቀን ቀን እየባሰ ከቤት መውጣት አስፈሪ እየሆነ መጣ፡፡ በጀምላ ብዙ ሰዎች ተገደሉ። ስለዚህ ብዙም ሳንቆይ ስራውን አቆምነው።

የታጠቁት ኃይሎች በከተማው ሱቆች እና ገበያ የሚገኘውን ምግብ በጉልበት ነጥቀው ወሰዱ። ከውጭ የሚመጣው ምግብ እና ከክፍለ ሃገር ወደ ከተማ የሚገባው ምግብ ቆሟል። ሎራ
ገንዘብ ትልክልኝ ስለነበር የቆጠብኩት ትንሽ ገንዘብ ነበረኝ ። ወደ ከተማው ወጥቼ ሩዝ፣ ደሮ፣ አሳ እና ሌሎች የታሸጉ ምግቦችን ለመግዛት ወሰንኩ፡፡ ወደ ገበያ መሄድ ግን አደጋ ነበረው። የበፊት
የጦር ሜዳ ጓደኞቼን ቢገኙኝ እና ከጦርነቱ እራሴን ማግለሌን

ቢያውቁ ይገሉኛል። ቤት መቀመጥ ደግሞ አልችልም ምግ መፈለግ ይኖርብኛል።

አንድ ድብቅ ገበያ እንዳለ እና የተለያዩ የማይገኙ የምግብ አይነቶች ለተራው ህዝብ እንደሚሸጥ ሰማን፡፡ ዋጋው ገበያ
ከመደበኛ ዋጋ ሁለት እጥፍ ቢሆንም ከአደጋ ያተርፋል።በጠዋት ማንም አንዳያየን አንገታችንን ደፍተን ወደ ገበያው
አመራን። ሩዝ፣ የወይራ ዘይት፣ ጨው፣ አሳ ገዝተን ልንወጣ ስንል መኪና እና ወታደሮች ዘለው ወረዱ። ወደ ህዝቡ
በመጠጋት የማስጠንቀቂያ ተኩስ ወደ ሰማይ ተኮሱ። በድምጸ ማጉያ አዛዡ የምግብ ዘምቢላችንን መሬት ላይ እንድናስቀምጥ እና እጃችንን ራሳችን ላይ እንድናስቀምጥ ትዕዛዝ ሰጠ።በድንጋጤ ለመሮጥ የሞከረች አንዲት ሴት ግንባሯ በጥይትተመታ:: ሁሉም ሰው ተረበሸ። እኛም ምግባችንን ይዘን ሮጥን።

ወደ ዋናው መንገድ ስንደርስ “ግድያ ይቁም” የሚል መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች አየን፡፡ ነጭ ቲሸርት እና ራሳቸው ላይ ነጭ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሀያ_ሁለት

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

ሰዎች በፍጥነት እየሮጡ በእኛ በኩል መጡ። ከኋላ ወታደሮች ያባሯቸው ነበር፡፡ እኛም ከፊት መምራት ጀመርን። መሐመድ እና እኔ በውስጥ ለውስጥ መንገዶች ሩጠን በታጠረ መንገድ
ደረስን። ታጣቂዎች አካባቢውን ይጠብቁ ነበር። ምሽት እስኪሆን የውሃ መውረጃ ቦይ ውስጥ ለስድስት ስዓታት ተንጋላን ተኛን።

ከሞት ለመትረፍ በለሊቱ መንቀሳቀስ ሳይሻል አይቀርም ብለን ነበር እስኪመሽ ፀየቆየነው:: ከእኛ ጋር የተወሰኑ ሰዎች ነበሩ:: ሰማያዊ ቲ ሸርት ያደረገ እና ግንባሩን እያለበው በተደጋጋሚ
የሚጠርግ ተማሪ፣ በፍርሃት የምትንቀጠቀጥ በሃያዎቹ
የምትገኝ ሴት እና ቲ ሸርቱ በሌላ ሰው ደም የተጨማለቀ ፂማም ሰውየ አብረውን ነበሩ። በጣም አዝኛለሁ መጥፎ ስሜትም
ተሰምቶኛል ግን ጦርነት እንደማያቁት እንደ እነዚህ ሰዎች አልፈራሁም። አጎቴ እንዳይጨነቅ ብቻ ነበር ሃሳቤ። የፍርድ ቀንን እንደመጠበቅ ምሽቱ በጣም ራቀብን። በመጨረሻ ቀስ ብሎ
እየጨለመ ድንግግዝ ካለ ብኋላ ሙሉ ጨለማ ሆነ ምሽት ገባ።

አጎቴ አይኖቹ እንባ አዝለው ደጃፍ ተክዞ ተቀምጦ አገኘሁት። ሲያየኝ ከተቀመጠበት ዘሎ ተነስቶ አቀፈኝ። በእቅፉ ውስጥ እንዳለሁ ከዚህ በኋላ ወደ ከተማ መሄድ እንደለለብን ነገረን።
አማራጭ ግን አልነበረንም! ምግብ ለማግኘት መውጣት ነበረብን፡፡

ተኩሱ ለተከታታይ አምስት ወራት የከተማው የማጀቢያ ድምፅ እስኪመስል ቀጠለ፡፡ ጠዋት ቤተሰቦች ደጃፍ ላይ
ተቀምጠው ይመለከታሉ። ታጣቂዎቹ ሲዘረፉ፣ ሲገድሉ እና ሴቶችን ሲደፍሩ ከልካይ አጡ። በሚቃጠሉ ቤቶች የፌዝ ሲስቁ ይስማል።አንድ ምሽት ጎረቤታችን ሬዲዮ ከፍቶ መንግስትን የሚወነጅል ጣቢያ ያዳምጣል። ወዲያው ገልባጭ መኪና ሙሉ ወታደር መጣና ቤታቸው ፊት ለፊት ቆመ፡፡ ሰውየውን፣ባለቤቱን እና ልጆቹን አውጥተው ተኩሰው ገደሏቸው::

ለሶስት ሳምንታት ያህል ከቤት መውጣት ፈራን፡፡ ቆይቶ ግን ተኩሱም እብደቱም ተለመድ፡፡ ተባራሪ ጥይት ሊገድላቸው
ቢችልም ሰዎች ግን የቀን ተቀን ንሮቸውን ቀጠሉ፡፡ ህጻናት ምን እንደተተኮስ በመገመት ይጫወታሉ። AK47 G3 HPG ወይም መትረጊስ እያሉ ይገምታሉ። ከመሐመድ ጋር አለት ላይ ዝም ብለን ተቀምጠን እናስባለን። ከጦርነቱ ለማምለጥ የተጓዝነው
ረጅሙን መንገድ አስታውስኩ። ረጅም መንገድ ብንጓዝም አሁን ጦርነቱ ደርሶብናል።

ኒው ዮርክ ካለችው ሎራ ጋር ለአምስት ወራት ያህል መገናኘት አልቻልኩም። ከዛ በፊት በየጊዜው ደብዳቤ እንለዋወጥ
ነበር። ደህና እንደሆነችና ራሴን እንድጠብቅ ትነግረኛለች።ደብዳቤዎቿ ለስራ ከምትንቀሳቀስባቸው የተለያዩ ሃገሮች ነበር የሚመጡት። ልደውልላት ብፈልግም አልቻልኩም። የሴራሊዮን ቴሌ ኮም ሴራ ቴል ስራ አቁሟል። በየቀኑ የስዓት እላፊ እስከሚደርስ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለን ከተማውን እንመለከታለን።
ተረት ማውራት፣ ቀልድ እና መዚቃ ከቆሙ ቆይተዋል። ነገሮች ብለን ተስፋ ብናደርግም በተቃራኒው ሁኔታው
እየባሰበት ነበር የሚሄደው:: አጎቴም አመመው። በቅርብ ከሚገኘው ሱቅ ማስታገሻ ብገዛለትም ህመሙ እየበረታበት መጣ፡፡ አክስቴ ሳሊ በግድ ልታበላው ብትፈልግም ይተፋዋል።
ሁሉም ሆስፒታሎች እና መድሃኒት ቤቶች ተዘግተዋል።በከተማ የሚገኙ ዶክተሮች እና ነርሶችን ማፈላለግ ጀመርን።
አብዛኞቹ ሃገር ለቀው ተሰደዋል፡፡ ሃገር ለቀው ያልወጡት ደግሞ ከቤት ,መውጣት ይፈራሉ፡፡ አንድ ምሽት አጎቴ በሽታው ባሰበት ሰውነቱ እተንቀጠጠ እኔን ተመለከተኝ። ተስፋው ተሟጦ ማለቁ ከአይኖቹ ይታያል። ከንፈሩ የሆነ ነገር ሊናገር ተንቀጥቅጠው
ቆሙ። አጎቴ አረፈ። ደነገጥኩ። እንዴት ነው ለባለቤቱ ምነግራት?! እሷ እኮ ውሃ እያሞቀችለት ነበር። ትንሽ ቆይታ
ውሃውን ይዛ መጣች እና ከሁለታችን ላይ ለቀቀችብን። የባሏን ህልፈት ማመን አልቻለችም:: የኔ የምላቸውን ሰዎች እንዳጣሁ ነው።

ቤቱ በለቅሶ ተደባለቀ። የአጎቴ ልጆች ከእንግዲህ ማን ሊንከባከበን ነው? እንዴት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እንዴት ይሄ
ይሆንብናል ይሄዳል ? እያሉ ያለቅሱ ነበር።

የአጎቴ ቀብር በሚቀጥለው ቀን ተፈፀመ። አስቸጋሪ ወቅት ቢሆንም ብዙ ሰዎች በቀብሩ ቦታ ተገኙ። አክስቴ መምጣት
ብትፈልግም አልቻለችም:: ከቤት ከመውጣታችን በፊት ተዝለፍልፋ ወደቀች። በመቃብሩ ቦታ ኢማሙ ሱራ ካደረሰ በኋላ አጎቴ ግብአተ መሬቱ ተፈፀመ። ሰዎች ወዲያው ወደ ቤታቸው
ተበተኑ። መቃብሩ ጎን ተቀምጩ አጎቴን አወራሁት። አጎቴ “የሚረዳህ ሰው ስላላገኘን ይቅርታ” አልኩ። በጣም እንደምወደው እና አድጌ እንዲያየኝ እፈልግ እንደነበር እንደሚያውቅ ተስፋ
አደረኩ፡፡ እጆቼን አፈር ጨብጬ አለቀስኩ።

የአጎቴ ቀብር ከተፈፀመ ከተወሰኑ ቀኖች በኋላ ሎራን በስልክ ማግኘት ቻልኩ፡፡ ኒው ዮርክ መምጣት ከቻልኩ እሷ ቤት ማረፍ እንደምችል ጠየቅኳት፡፡ እሽ አለች።
በሃሳቤ ይታየኛል” አልኳት። ጊኒ
ጊኒ ኮናክሪ ስደርስ እንደምደውልላት ነገርኳት፡፡ ኮናክሪ የጊኒ ዋና ከተማ ስትሆን በጊዜው ጊኒ ብቸኛዋ ሰላማዊ ጎረቤት ሃገር እና ብቸዋ ከሴራ ሊዮን መውጫ በር ነበረች:: መውጣት ነበረብኝ፡፡ ከቆየሁ ተመልሼ ወታደር እሆናለሁ ወይም እምቢ ብየ የቀድሞ ጓደኞቼ ይገድሉኛል። አገግመው የነበረ አንዳንድ ጓደኞቼ እንደገና ወደ ጦር ተቀላቅለዋል።

በደረቅ ለሊት ፍሪ ታውንን ለቅቄ ወጣሁ። ከመሐመድ በስተቀር መሄዴን
ለማንም አልተናገርኩም:: አክስቴ
ከተፅናናች በኋላ የእኔን መሄድ እንደሚነግራት ከመሐመድ
ተነጋግረናል። ከባሏ ሞት በኋላ ጀርባዋን ለአለም እና በአለም ለሚኖር ሁሉ ሰጥታለች፡፡ ህዳር 1 1997 ነበር የወጣሁት።ሳይነጋ መውጣት ነበረብኝ፡፡ በለሊት መጓዙ ከ ደህንነት አንፃር
የተሻለ ነበር። ግማሾቹ ታጣቂዎች ተኝተዋል የቀሩት ወታደሮች ደግሞ በለሊት ከሩቅ ማየት ይከብዳል። የተኩስ እሩምታው ፀጥ ረጭ ባለው ከተማ ይስተጋባል። ብርድ አየር እየመታኝ የሽተተ አስክሬን እና ባሩድ እያሸተትኩ መጓዝ ጀመርኩ። ለመሐመድ ስደርስ አሳውቅሃለሁ ብየ ተጨባበጥን። ትክሻየን መታ መታ ከማድረግ ውጪ ምንም አልተናገረም::

የተወሰኑ ልብሶቼን የያዘ አንድ ትንሽ ቆሻሻ ሻንጣ ብቻ ነበር የያዝኩት:: ትልቅ እና የሚስብ ሻንጣ መያዝ ለአደጋ ያጋልጣል።
ታጣቂዎች ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ጠቃሚ ነገር እያሸሽህ ስለሚመስላቸው ሊተኩስብህ ይችላሉ። መሐመድን ትቼ ጎህ ሳይቀድ ፈጠን ብየ መጓዜን ቀጠልኩ፡፡ ጨለማው ግን ያስፈራል።
የስልክ እንጨት ተደግፌ ተነፈስኩ። ራሴን ማበረታታት ጀመርኩ:: መውጣት አለብኝ ካልሆነ ወደ ጦሩ መመለሴ ነው።
ይሄን ማሰብ እንኳ አልፈልግም፡፡ የመኪና ድምፅ ስሰማ ቶሎ ብየ ወደ ቦይ ነገር በመግባት ተደበቅኩ፡፡ በመንገድ ላይ ብቸኛው ሲቭል እኔ ነበርኩ፡፡ የፍተሻ ጣቢያዎችን አንዳንዴ ቦይ ውስጥ
በጉልበቴ እየዳሁ ወይም በቤቶች ጀርባ ተደብቄ አለፍኩ። በሰላም ወደ አንድ አሮጌ የአውቶብስ ጣቢያ ደረስኩ። ብዙ ሰዎች ነበሩ።በሰላሳዎች የሚገኙ ወንዶች፣ ሴቶች እና ህፃናት። በአውቶብስ
ውስጥ መጨረሻ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ። ሹፌሩ እየዞረ ሂሳብ
ከተቀበለ በኋላ ጉዞ ጀመረ፡፡ መንገዱ ለብዙ አመታት አገልግሎት ውጭ ስለነበር አውቶብሱ ከቅጠል እና ቅርንጫፍ
ጋር እየተላተመ በዱር ውስጥ የሚሄድ ነበር የሚመስለው። ጎህ እስኪቀድ ቀስ ብሎ ነበር የተጓዘው:: አንድ ቦታ ላይ ሁላችን ወርደን መኪናው አንድ ዳገት መውጣት ነበረበት፡፡ ሁላችንም
ዝም ብለን ፊታችን በፍርሃት ከብዶ ነበር፡፡ ወደ አውቶብሱ ተመልሰን ከገባን በኋላ
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሀያ_ሶስት(የመጨረሻ ክፍል)

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


አስር ስዓት ሲሆን አውቶብሱ ካምቢያ ከምትባል ከተማ አደረሰን። የመጨረሻ ፌርማታው ነበር። ፍሪ ታውንን ለቀን
ከመጣን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳፋሪዎቹ ፊት ተፈታ። ግን ብዙም አልቆየም! ድንበር ለማለፍ ክፍያ ስንጠየቅ የሁሉም ፊት መልሶ ተኮማተረ አጉረመረምን፡፡ ሁሉም ሰው ከካልሲው
ውስጥ፣ ከውስጥ ሱሪ እና ከረባት ሳይቀር የተረፈ ገንዘብ ካለ ፈለገ። ሶስት መቶ ሊዮንስ (የሴራሊዮን ገንዘብ) ነበር
የተጠየቅነው:: አንድ ሰው ከገዛ ሃገር ለቆ ለመውጣት ለምንድን ነው ሚከፍለው? አሰብኩ ግን መከራከር አልችልም:: ከፈልኩ:: የይለፍ ወረቀቱ ላይ ማህተም እንደተደረገልኝ ወዲያው ወደ ጊኒ
ደንበር ተሻገርኩ። ዋና ከተማዋ ኮናክሪ ለመድረስ ደግሞ ገና ብዙ መንገድ ይቀረኛል። ወደ ከተማው የሚወስድ አውቶብስ ለማግኘት ቶሎ ቶሎ መራመድ ጀመርኩ። ጊኒ ውስጥ የሚነገር
የትኛውንም ቋንቋ መናገር አልችልም ምን ማድረግ እንዳለብኝም አላሰብኩበትም ነበር። ትንሽ አስጨነቀኝ ግን ከሃገሬ በህይወት መውጣቴ ትልቅ ነገር ነው::
ኮናክሪ የሚሄድ አውቶብሶች የጊኒ ወታደሮች ባቆሟቸው ኬላዎች በኩል ነበር የሚቆሙት፡፡ በኬላዎቹ ተጠግተው
በፈለጉት መጠን የጊኒን ገንዘብ የሚመነዝሩ ሰዎች ነበሩ።

ወታደሮቹ ይሄን ጥቁር ገበያ የሚከላከሉ መስሎኝ ነበር ግን ግድ አይሰጣቸውም:: ገንዘቤን ቀይሬ ወደ ኬላው ተጠጋሁ። ደንበሩ ላይ ያሉ ወታደሮች ወይ እንግሊዝኛ መናገር አይችሉም ወይ
ደግሞ እንደሚችሉ ማሳወቅ አይፈልጉም:: መሳሪያቸውን ብቻ
በተጠንቀቅ ይዘዋል፡፡ ቀና ብየ ማየት አልፈለኩም። ከዚህ በፊት ወታደር እንደነበርኩ እና አሁን ግን ትቼው እሸሸሁ መሆኑን ማሳበቅ አልፈለኩም::

አውቶብሱን ለማግኘት ጥቁር ቡናማ የሆኑ የጣውላ ቤቶችን ማለፍ ነበረብኝ። ውስጥ ወታደሮች የሰዎችን ሻንጣ ይበረብራሉ።ሰዎች ደግሞ መረጃዎቻቸውን ለሃላፊዎች ያሳያሉ። የእኔ ተራ ሲደርስ ወታደሮቹ ሻንጣየን ከፍተው በውስ ጡ ያለውን ሁሉ መሬት ላይ ዘረገፉት። ብዙ እቃ ስላልነበረኝ ለመሰብሰብ እና መልሶ ለመክተት ብዙም አያስቸግርም፡፡ ሁለት ቲ ሸርት፣ ሁለት
ዉስጥ ሱሪ እና ሶስት ጥንድ ሱሪዎች ብቻ ነበሩ::

ከጣውላ ቤቱ ስወጣ መረጃዎቼን ማሳየት ነበረብኝ፡፡ ብዙ ጠረጴዛዎቹ እና ወታደሮች ደግሞ የማንጎ ዛፍ ስር ነበሩ።
መሳሪዎቻቸው ወንበራቸው ላይ ወይም የአንዳንዶቹ ጠረጴዛዎቹ ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ለማን ማሳየት እንዳለብኝ
አላውቅም::

አንድ ወታደር ወደ እሱ እንደሄድ ምልክት አሳየኝ። እጁን ዘረጋ እና የይለፍ ወረቀቴን ተቀበለኝ። ወታደሩ በማይገባኝ አንድ
ቋንቋ ተናገረ።የይለፍ ወረቀቴን የደረት ኪሱ ውስጥ አስገባው እና እጁን ጠረጴዛ አድርጎ አትኩሮ ተመለከተኝ። አቀረቀርኩ
ወታደሩ አገጩን ቀና አደረገኝ፡፡ የይለፍ ወረቀቴን ከኪሱ አውጥቶ መረመረ። አይኑ ቀላ ፊቱ ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር።
እጁን አጥፎ ተደላድሎ ተቀመጠ። ፈገግ አልኩ እሱም ሳቀ።በቋንቋው የሆነ ነገር አለና እጁን እንደገና ጠረጴዛው ላይ አደረገ።ፈገግታው እየጠፋ ሄደ፡፡ የተወሰነ ገንዘብ እጁ ላይ አስቀመጥኩ።
የይለፍ ወረቀቴን ከኪሱ አውጥቶ ሰጠኝ እና በሩ እንዳልፍ ጠቆመኝ፡፡

ብዙ አውቶብሶች ስለነበሩ ወደ ኮናክሪ ለመሄድ አውቶብስ መያዝ እንዳለብኝ አላውቅም ግራ ገባኝ፡፡ ሰዎችን ለመጠየቅ ብሞክርም ማንም ሊረዳኝ አልቻለም:: የማውቀው ፈረንሳይኛ
ቃል bonjour ቦንጁር ብቻ ነበር፡፡

ግራ ገብቶኝ ቁሜያለሁ አንድ አልፎ ሂያጅ በኪሮ ቋንቋ ሲያጉረመርም ሰማሁትና “ ጤና ይስጥልኝ” ብየ ወደ ኮናክሪ
የሚወስደው አውቶብስ የትኛው እንደሆነ ጠየቅኩት። እሱም ወደ ዛው እንደሚጓዝ ነገረኝ እና ወደ ከአፍ እስከ ገደፉ ጢም
ብሎ የሞላ አውቶብስ ውስጥ ገባን፡፡ በየ ሃምሳ ሜትሩ ወደ አስራ አምስት የሚጠጉ ኬላዎች ላይ ወታደሮች ነበሩ እና ወታደሮቹ ምህረት የለሽ ነበሩ። ወታደሮቹ መክፈል የማችሉትን እየደበደቡ
ከአውቶብሱ ያወርዷቸዋል። እኔ ግን እድለኛ ነበርኩ። ከአጠገቤ የነበረው ሰውየ ልጅ ስለመሰልኳቸው ብዙ ኬላዎችን በነፃ አልፌያለሁ። የእሱን መረጃ ያያሉ እና የሁለታችንንም እሱን
ያስከፍላሉ፡፡ ሰውየው የገባው አይመስለኝም:: ገንዘብ ጉዳዩ አይደለም ኮናክሪ መግባት ብቻ ነበር የሚፈልገው:: የመግቢያ ክፍያው ሶስት መቶ ሊዮንስ እንደሆነ ሰዎች ሲያወሩ ሰማሁ።
መቶ ሊዮንስ ብቻ ነበር የቀረኝ፡፡ ምንድን ነው ማደርገው? ብየ ማሰብ ጀመርኩ። ይሄ ሁሉ መንገድ የመጣሁት ለከንቱ ነው? ወደ ፍሪ ታውን መመለስ እንኳ ብፈልግ የምመለስበት ገንዘብ የለኝም:: አይኖቼ እንባ አቀረሩ። ተረበሽኩ ከዚህ መውጫ መንገዱ አልታይህ አለኝ፡፡ አንድ የይለፍ ወረቀቱ የተመታለት ሰው ከኬላ ወደ አውቶብስ ሲመለስ ሻንጣውን ጥሎ አየሁ። የተወሰነ ካመነታሁ በኋላ እድሉን ልጠቀምበት ወሰንኩ። ሰልፉን ትቼ ሻንጣውን ይዤ ተከልኩት:: አውቶብስ ውስጥ ገብቼ መጨረሻ ወንበር ላይ ተደብቄ ተቀመጥኩ። አውቶብሱ ቀስ ብሎ ከወጣ በኋላ ፍጥነቱን ጨመረ። በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሃገሪቱ
ገባሁ በኋላ ግን ችግር ይሆናል፡፡

አውቶብሱ ወደ ኮናክሪ ሲደርስ መጨነቅ ጀመርኩ። ከደረስኩ በኋላ ምን እንደማደርግ አላውቅም:: የሴራሊዮን አምባሳደር ስደተኞች በጊዜዊነት ግቢው ውስጥ እንደሚያሳድር ሰምቻለሁ
ግን ኢምባሲው የት እንደሆነ እንኳ አላውቅም:: ጃሎህ ከሚባል
ፉላኒ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ አርብቶ አደር ጎሳ) ጋር ነበር የተቀመጥኩት። ጃሎህ ፍሪ ታውን እንደኖረ ነገረኝ፡፡ ስለ ጦርነቱ እና በሃገሪቱ ላይ ስላስከተለው ጉዳት አወራን። በኋላ ስልክ ቁጥሩን ሰጠኝ እና ከተማዋን ስንቀሳቀስ እርዳታ ካስፈለገኝ እንድደውልለት ነገረኝ። ማደሪያ እንደሌለኝ ልነግረው ፈለኩ ግን
ቀድሞኝ ወረደ። አብሮኝ የመጣውን ሴራ ሊዮናዊ ፈለኩ ግን ላገኘው አልቻልኩም። ከደቂቃዎች በኋላ አውቶብሱ ግዙፍ
መናሃሪያ ውስጥ ገባ። ወጥቼ ሁሉም ሲሄድ ተመለከትኩ። ተነፈስኩ እና እጆቼ ራሴ ላይ ጭኜ ወደ አግድም ወንበር ሂጄ
ተቀመጥኩ። ፊቴን በእጆቼ ሸፍኜ “ለሊቱን ሙሉ ከዚህ መቀመጥ አልችልም” ብየ ለራሴ አጉረመረምኩ።

ብዙ ታክሲዎች ነበሩ እና አውቶብሱ መናሃሪያ የደረሱ ሰዎች ሁሉ ይዟቸዎል። እኔም ብቸኛ ሚሄድበት የጠፋው እንግዳ
መስየ መታየት ስላልፈለኩ አንዱ
ታክሲ ውስጥ ገባሁ። ሹፌሩ በፈረንሳይኛ ሲናገር ወዴት እንደምሄድ እየጠቀኝ እንደሆነ ገመትኩ። ሴራ ሊዮን ቆንስላ አ ኢምባሲ” ብየ ነገርኩት።በመስኮት ስመለከት የመብራት ምሶሶዎች ላይ የመንገድ መብራቶቹ ተንበርግገው
ተንጠልጥለዋል። ብርሃናቸው ከጨረቃ ብርሃን ሳይበልጥ አይቀርም። ታክሲው ኢምባሲው ፊት ለፊት ቆመ እና የምፈልገው ቦታ ይዞኝ እንደመጣ
ለማረጋገጥ ወደ አረንጓዴ፣ ነጭ እና ሰማያዊ ባንዴራ ጠቆመኝ፡፡ራሴን በማወዛወዝ ትክክል እንደሆነ ከገለፅኩለት በኋላ ከታክሲው ወረድኩ
በኤንባሲው በር ላይ ጠባቂዎቹ በኪሪዎ የይለፍ ወረቀቴን እንዳሳይ ጠየቁኝ፡፡ አሳየኋቸው እና ወደ ግቢው እንድገባ ፈቀዱልኝ::

በግቢው ውስጥ ከሃምሳ በላይ ሰዎች ሲኖሩ እንደእኔ መጠጊያ ያጡ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ አብዛኖቹ ትራስ ብቻ አድርገው ተጋድመዋል። ጓዛቸውን ወይም ሻንጣቸውን ከጎናቸው አስቀምጠዋል። ሰዎቹ ማታ ማታ ከዚህ የሚያድሩ ሲሆን ቀን ቀን ወደ ውጭ ይወጣሉ። ጥግ ላይ ቦታ አገኘሁ እና መሬት ተቀምጨ ጀርባየን ወደ ግድግዳው አስጠጋሁ። ስዎቹን ሳይ
ከጦርነቱ ለማምለጥ ያለፍኩባቸው ሰፈሮች ትዝ አሉኝ።