አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

ከጉብኝቱ በኋላ በነበረን የእጅ ሥራ ክፍለ ጊዜ “ስለጉብኝቱ ጥያቄ ካላችሁ ጠይቁ!”
በተባልነው መሠረት፣ መሐሪ ቀድሞ እጁን አወጣና “ቲቸር እስረኞቹ ግን ለምን በሌሊት አያመልጡም?” ብሎ ጠየቀ፡፡ “ቲቸር” ምንም ምንም ሳትናገር ቁማ መሐሪን ስታየው ቆየች፤ እናም ረጋ ባለ ድምፅ እንዲህ አለች፣

ሌላ ጥያቄ ያለው?

ይኼ ሁሉ ነገር ሳያንሰን፣ አስተማሪያችን ሥሩ እያለች የምታዘው ነገር ሁሉ ያበሳጨን ነበር። እኔና መሐሪ አንድም ቀን የምታዘውን ሠርተን እናውቅም… ከሙቅና ከወረቀት ሰሃን ሥሩ አለችን ድፍን የከፍሉ ልጅ የወረቀት ሰሀኑን፣ ሰባት ቀን ያደረ ደረቅ ቂጣ አስመስሎ ሲመጣ(ደግሞ ሽታው ሲያስጠላ) ሁለታችን ብቻ ባዶ እጃችንን ቁልጭ ቁልጭ እያልን ተገኘን፡፡ ከሃያ ዜሮ ሰጠችን!! ከሃያ ዜሮም፣ ከሃያው ሃያም ስትሰጥ ፊቷ ላይ ምንም የተለየ ስሜት አይነበብም ነበር፡፡ የመሐሪን እናት ማሚ ስለሙቁ ስንነግራት ፈገግ ብላ “መሥራት ነበረባችሁ!” አለችን፡፡ ተባብረን ልናሳምናት ሞከርን፡፡

እንዴ ማሚ! ስንት ሕዝብ በሚራብበት አገር፣ በእርዳታ የሚገኝ ስንዴ ለእጅ ሥራ እያልን...

ትክ ብላ አየችንና “ወሬኞች!” ብላ ወደ ሥራዋ ሄደች፡፡ ፊቷ ላይ ግን ፈገግታ ነበር፡፡ማሚ ሁልጊዜ እኛ ጋር ስታወራ፣ ፊቷ ላይ ወይ ለይቶለት የማይፈነዳ፣ አልያም ለይቶለት የማይከስም፣ ልክ እንደጥዋት ጤዛ የተንጠለጠለ ውብ ፈገግታ ነበር፡፡ ፈገግታው ሁልጊዜ
ዓይኗ ላይ ነበር፣ ከእንድ ቀን በስተቀር፡፡

ከማረሚያ ቤት ጉብኝታችን የተመለስን ቀን፣ ማሚ ጋር ስላየነው ነገር ስናወራ መሐሪ ካለወትሮው ዝም ብሎ፤ እኔ ነበርኩ የባጥ የቆጡን የማወራው፡፡ ማሚ በጣቷ ጉንጩን ነካ እያደረገች “ምነው ለምቦጭህን ጣልክ?” ስትለው ነበር ዝም ማለቱ ትዝ ያለኝ!እንዳቀረቀረ ሹክሹክታ በሚመስል ድምፅ “ሚስቱን የገደለ ሰውዬ አዬን እዚያ ታስሯል!” አላት፡፡ ማሚ ኮስተር ብላ…

እ? አለች

እኔ ነበርኩ ወሬውን የጨረስኩት፡፡ ስለ ሰውዬው ነገርኳት፡፡ በተለይ ስለ ራሱ ሞላላነትና ስለ መላጣው …ስለ ሚስቱም ጉዳይ!

ማሚ መሐሪን ድንገት ወደ ራሷ ሳብ አድርጋ አቀፈችው፡፡ አጥብቃ አቀፈችው፤ እሱም ታፋዋን አቅፎ ቀሚሷ ውስጥ ተሸጎጠ እና እንዲህ አለች “ሕፃን ስለሆናችሁ እየቀለዱባችሁ ነው” ግን እንደዛም እያለች ማሚ ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው ከንፈሯ ይንቀጠቀጥ ነበር…መሐሪን ትንሽ ገፋ አደረገችውና፣ አፏን በመዳፏ አፍና ወደ ውስጥ እየተጣደፈች ገባች! ወደ መኝታ ቤቷ !
ሌላኛው ጠላታችን የሙዚቃ ትምህርት ነበር! ሙዚቃ አስተማሪያችን ከዓመት በፊት የትምህርት ቤታችን ሜዳ የሚጠበው ስፖርት አስተማሪ ነበር፡፡ የመኪና አደጋ ደርሶበት ግራ እግሩ በከባድ ጀሶ ተጠቅልሎ፣ በአንድ የብረት ምርኩዝ እየታገዘ መሄድ ከጀመረ
በኋላ ነው የሙዚቃ አስተማሪ የሆነው ድፍን መንፈቅ ዓመቱን ውጭ ሜዳ ላይ
እያስወጣ “ ተጫወቱ!” ይለንና አንዲት ዛፍ ሥር ተቀምጦ፣ ጥርሱን በቀጭን የወይራ እንጨት እየፋቀ ያየናል፡፡ የፈተና ቀን ሲደርስ ግን፣ “በየተራ ተማሪ ፊት እየወጣችሁ ዝፈኑ፣ ሀምሳ ማርክ አለው!” አለን፡፡ “እዚች አገር እንኳን እኛ፣ ዘፋኙ ራሱ ሃምሳ ማርክ አያገኝም!" እያልን አላገጥን እኔና መሐሪ። ብንደረግ ብንሠራ አንዘፍንም አልን፡፡ “ዝፈኑ ስትባሉ ማልቀስ ከፈለጋችሁ ጥሩ!” ብሎ ከሀምሳው ዜሮ አከናነበን፡፡

በኋላ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው እባክህ በሌላም መንገድ ቢሆን ፈትናቸው” ተብሎ በስም ጠሪያችን አማላጅነት ተለምኖና አዝኖልን (እኔ ግን ስጠረጥር ጎበዝ ነን በሚል ትዕቢት ተወጥረው የሙዚቃ ክፍለ ጊዜን እንደናቁ አስተነፍሳቸዋለሁ በሚል ቂም በቀል)
እያንዳንዱ ጥያቄ ዐሥር ነጥብ ያለው የቃል ፈተና ፈተነን፡፡

በገና ስንት ክር አለው …?

ባስብ ባስብ አልመጣልህ አለኝ፡፡ መቼም መንፈሳዊ ነገር ላይ ሰባት ቁጥር አይጠፋም ብዬ ሰባት አልኩ፡፡ፊቱ ላይ የነበረው ቁጣ በሆዱ ለሰባት ይቆራርጥህ!” የሚል አስመስሎት ነበር፡፡ ከፈተናው በኋላ እልህ ይዞን፣ ሰፈራችን ወደ አለው መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን መዝሙር ቤት ሄድን፡፡ መዝሙር ቤቷ በር ላይ ተቀምጦ ያገኘነውን ዘበኛ “በገና ስንት ክር አለው? “ስንለው፣ እኔ አላቅም! መሪ ጌታ ሲመጡ ጠይቁ ብሎ
በቆምንበት ረሳን ፡፡ በገናውኮ ከኋላው ነበር፡፡ እሺ! እንቁጠረው ስንል፣ መሪ ጌታ
ካልፈቀዱ አይቻልም ብሎ ጠመመ! በዚያው ረሳነው!

2ኛ እምቢልታ ከምን ያሠራል?

እምቢልታ ራሱ ምን እንደሆነ አላውቅም…እምቢልታ ማለት ብሎ በሚነጫነጭ ድምፅ በሰፊው እብራራልኝ፣ ያውም ያልጠየቀውን ነጋሪት ሁሉ ጨምሮ! “የሆነ ሆኖ አልመለስከውም” ከሚል መደምደሚያ ጋር፡፡ ስለ እምቢልታና ነጋሪት የዚያን ቀን
አውቅሁ!

3ኛ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅኝቶች ምን ምን ናቸው?

ትዝታ፣ ብዬ ጀመርኩ፡፡ ሌሎቹን ማወቅ አልቻልኩም፡፡ መምህሩ በስክርቢቶው ጫፍ ጢረጴዛውን ሲጠቀጥቅ ቆየና፣ ትክ ብሎ እየተመለከተኝ .. ሌላው ይቅር… ሰው እንዴት አምባሰል ይጠፋዋል? እንዴት ባቲ ይጠፋዋል? አላየንም ጎበዝ ተማሪ !" አለና ወደ ቀጣይ ጥያቄው አለፈ፡፡

4ኛ ሦስት የክር የሙዚቃ መሣሪያዎችን ጥቀስ (ይኼ ሰውዬ የሙዚቃ አስተማሪ ነው ወይስ የዳንቴል ሥራ?ክር ክር ብሎ ሊሞት ነው እንዴ! እያልኩ በውስጤ
ክራር ፣ በጎና ፣ ጊታር ተመስገን!” አለ፡፡ አነጋገሩ ያበሳጭ ነበር ፡፡ በጣም ያበሳጨኝና፣ ሰውየው ነገር መፈለጉ የገባኝ ከዚህ ሁሉ ጥያቄ በኋላ ወደመጀመሪያው ነገር ሲመለስ
ነበር፡፡

የምታውቀውን የአንድ ዘፈን አዝማች በዜማ አንጎራጉር አስተማሪ አይጥመድ! ከዛም ብሶቱን ተነፈሳት “ስማ! ጎበዝ ሁነህ ናሳ ብትቀጠር ፣ጨረቃ… ማርስ ብትረግጥ፣ ካለባህሪ ዋጋ የለውም፣ ዋናው ትሕትና ነው:: ይች አገር ገና
ከጥንት ከአክሱምና ከዛገዌ ዘመን
ጀምሮ፣ ስንት ሊቃውንት፣ ስንት ጠቢባን ነበሯት፣አሏትም፡፡አዋቂ ነጥፎባት
አያወቅም ትሕትና ነው ዋናው ትሕትና! እኔ ተፈሪ ሃያ ሦስት ዓመት ሳስተምር፣ ማንም
እከሌን ፈትን፣ እከሌን ፈተና ቀይርለት ብሎኝ አያውቅም…” ብሎ፣ ግማሽ ዛቻ… ግማሽ ፉከራ የቀላቀለ ረዥም ምከር ከመከረኝ በኋላ፣ መሐሪን ጠራው፡፡
መሐሪም የኔው ዕጣ ነበር ያጋጠመው፡፡ በሕይወት ዘመኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመቶው ሃያ ሦስት ያመጣሁበት ትምህርት ሆነ፡፡ የሚገርመው ነገር መሐሪ ከመቶው ሠላሳ አምስት ማምጣቱ ነበር እንዴት ሠላሳ አምስት ሰጠህ?” ብለው፡፡

“ዘፈንኩ!” አለኝ።

ከምርህ ነው? … "

ታዲያ! ጋሽ ዝናቡ እኔንም ማሚንም ከሚገለን ብዘፍን አይሻልም” ከዚያን ቀን ጀምሮ ለስንት ዓመት፣ እኔም ፍቅረኛው ሮሐም ምን እንደዘፈነ እንዲነግረን ብንጠይቀው፣ ብንለምነው ምስጢር ነው ብሎ ሳይነግረን ቀረ፡፡ ባሕሪው እንደዚህ ነው:: አንድ ነገር ምስጢር ነው ካለ፣ ለምን አይገድሉትም ትንፍሽ አይልም፡፡

በእነዚህ ይዞ ሟች ትምህርቶች ምክንያት፣ እኔና መሐሪ ተያይዘን ገደል ገባን! መብረቅ የወደቀብን ያህል ነበር የደነገጥነው! …ቀድሞ እንዴት እንዳልታየን አልገባኝም፡፡ እኔ እንኳን አራተኛ፣ አርባ አራተኛም ብወጣ “እሰይ ዋናው ጤና! የምትል እናትና አብርሃም ስትመለስ ታሳየኛለህ፤ እስቲ ሂድና ዕቁብ ከፍለህ ና!” በሚል አባት ተባርኪያለሁ፡፡ ለመሐሪ ነበር ሁለታችንም የደነገጥነው፤ እንዲያውም ያንን ካርድ ይዘን ስንመለስ፣ እንደፍጥርጥርህ ብዬው ወደ ቤቴ ልሄድ ነበር፡፡ መሐሪ ግን በቁጣ ቦግ ብሎ
እኔን አጋፍጠኸኝ ልትሄድ ነው እንዴ? አታስብም?” ሲለኝ፣ አሳዝኖኝ አብሬው መብረቅ ልመታ
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አራት


#በአሌክስ_አብርሃም

…መሐሪ ካርዱ ከእጁ አምልጦት ወደቀ! ጋሽ ዝናቡ ወንበሩን ማወዛወዙን አቆመና፣ እጁን ወደፊት ዘርግቶ “እስቲ አምጣው!?” አለ፡፡ ዓይኑን በወደቀው ካርድ ላይ ተከሎ፤ መሐሪ መንቀሳቀስ ስላልቻለ፣ እኔ ያለ የሌለ ድፍረቴን አሰባስቤ ካርዱን እነሳሁና፣ ደረጃውን ወጥቼ ሰጠሁት፡፡ ካርዱን አሰጣጤ ለሆነ ተናካሽ
እንስሳ ሥጋ እንደሚወረውር ሰው በጥንቃቄ ነበር!... ከእጄ እንዳይወስደው!

ከዘላለም የረዘመ ለሚመስል ጊዜ ካርዱን ሲመረምር ቆየቶ፣ በረዥሙ እህህ ብሎ
አቃሰተ እና እዚህ መርዶ ላይ የሚፈርም አባት አለኝ ብለህ አንከርፍፈህ መጣህ እ
" ብሎ በሚያስደነግጥ ፍጥነት ምንጥቅ ብሎ ሲነሳ፣ ሁለታችንም ወደኋላ ሸሸት አልን ጋሼ ተነሰቶ ሲሄድ ተቀምጦበት የበረው ወንበር፣ ከዚህ ጉድ ሩጦ ማምለጥ ፈልጎ አቅም ያነሰው ይመስል፣ ባለበት ሆኖ ወደ ኋላና ወደፊት ተራወጠ፡፡ ወንበሩ ላይ የነበረው በፈዛዛ ቀይ ጨርቅ ከረጢት የተቋጠረው የስፖንጅ ድልዳል ተንሸራቶ መሬት ላይ ወደቀ፡፡

መሐሪ በድንጋጤ የተሰነዘረበትን ቡጢ እንደሚከላከል ቦክሰኛ ፊቱን በቀጫጫ ክንዶቹ መህል ቀብሮ ነበር ወደ ኋላው የሸሸው::ያች አቋቋሙ እስካሁን እንደፎቶ ቁልጭ ብላ ትታየኛለች፡፡ ሸሽቶ ደግሞ ከእኔ ኋላ ነበር የተደበቀው፡፡ ጋሼ እቆምንበት ትቶን ወደ ውስጥ ሲገባ እንኳን፣ መሐሪ አላየውም!! ነገሩ ጸጥ ሲልበትና የጠበቀው ኩርኩም
ሲዘገይ፣ ቀስ ብሎ ከከንዶቹ መሀል ቀና አለ፡፡ የጋሼን አለመኖር ሲያይ፣ ድንገት “ማሚን ገደላት!” ብሎ ወደ ውስጥ ሮጠ!እኔ ባለሁበት አንዴ የግቢውን በር፣ አንዴ አባትና ልጅ ተከታትለው የገቡበትን የቤቱን ዋና በር እየተመለከትኩ እንደቆምኩ፣ ከውስጥ የሆነ ከባድ እቃ ሲወድቅና ሲሰባበር ሰማሁ፡፡ ምን እንደገፋኝ እንጃ በሩጫ ተከትያቸው
ገባሁ፡፡ ደመነፍሴ ጓደኛህን ታደግ ብሎ ገፍቶኝም እንደሆነ እንጃ:: ከዋናው ቤት ጋር ተያይዞ ወደተሠራው ኩሽና በሚወስደው በር ላይ ተቀምጦ የነበረው ተደራራቢ የአበባ ማሰቀመጫ፣ ወለሉ ላይ ወድቆ ብትንትኑ ወጥቷል፡፡ ጋሽ ዝናቡ ኩሽናው ውስጥ ገብቶ በዚያ ንጋሪትና እምቢልታ ቢጨመርበት የክተት ጥሪን በሚያስንቅ ድምፁ ማሚ ላይ ያንባርቅበታል …

“ለስሙ ሴት ነሽ! …እናት ነሽ! እዚህ ተጎልተሸ እየዋልሽ፣ አንድ ልጅ እንኳን እንድ ልጅ መቆጣጠር ያቃተሸ ዳሩ በልደትና ሰርግ ሰበብ ማን እየተኳኳለና እግሩን እያነሳ ይዙርልሽ? አራተኛ …አራተኛ … ምን ማለት ነው ይኼ? , እ? ….ዳሩ አራተኛ ይሁን አስራ አራተኛ አይገባሽ አንች .…አራተኛ .…” ማሚ ምን መዓት ወረደብኝ ብላ ነው መሰል
ድምፅዋ አይሰማም! ለነገሩ እንኳንስ እንዲህ ዓይነት ውርጅብኝ ፊት ቁማ መመላለስ ቀርቶ በሰላሙም ቀን ንግግሯ የተቆጠበ ነው !

መሐሪ፣ አባቱን ያረጋጋ መስሎት እንዲህ ሲል ሰማሁት “ጋሽ፣ አብርሽኮ አምስተኛ ነው የወጣው” ወደኋላዬ ልሮጥ ነበር፤ ምነካው… እንዴት በዚህ እሳት ውስጥ ስሜን ያንሳል? እያልኩ ሳስብ

“ኧረ? ይኼ ነው “ኤክስኪውዝህ?”… በማኀበር ነው የሞትነው በለኛ ?,ደሞ አብርሽ ይባልልኛል …ግም ለግም አብረህ አዝግም ምድረ ድኩማን! ጧ! “ ጥፊ መሆን አለበት!" እቆምኩበት ሁኜ ጉንጬ ሲግል ተሰማኝ፡፡ ስለዛች “ጧ” ከዚያ በኋላ ሁለታችንም አንስተን አናውቅም !

“አትምታው! …ልጄን አትምታው!! ..ጆሮውን ልታደነቆረው ነው እንዴ?” ከዚያም በፊትም ሆነ ከዚያም በኋላ ሰምቼው የማላውቀው የማሚ ቁጡ ድምፅ አንባረቀ!

“ይችን ይወዳል ዝናቡ! …ለኔ ነው ቢላ ያነሳሽው? …እኮ ለኔ? …ግደይውና ነይ አብረን እንኑር አለሽ? …ታዲያ መርዝ አይሻልሽም? እ!” እንደፈለክ በል! ብቻ ልጄን ትነካውና ውርድ ከራሴ …እስቲ አሁን ምናለ? አብሮት ከሚያጠናው ጓደኛው ጋር ትምህርት ከበዳቸው፣ እሱ ብቻ አይደለም …ይኼ ያስመታል?
ደግሞ ወደ ስድስት አልፈዋል …በቃ

“ፓ! አንችም ብሎ ማብራሪያ ሰጭ .
ወደ ስድስት አልፈዋል ትላለች እንዴ? በዚህ የሞተ ውጤት ከአምስት ወደ ስድስት ወድቀዋል ነው የሚባለው … ማለፍ ሁሉ ስኬት አይደለም ..ከገባሽ! እንዲያውም አብርሃም የሚባል ካንተ የባሰ እንቅልፋም! ሁለተኛ እዚች ቤት ድርሽ ይልና .

ተው እንጂ አልበዛም” አለች ማሚ

በዛ እንዴ? እንዴት ለልጅሽ ውድቀት ጠበቃ ትሆኛለሽ ?……እንዲያውም አሳይሻለሁ ብሎ ወደ ሳሎን በቁጣ ሲመለስ፣ እንደጨው ዓምድ ደርቄ በቆምኩበት ተገጣጠምን፡፡
በረንዳው ላይ ነው ያለው ብሎ አስቦኝ ሳለ፣ ሳሎን ውስጥ ስላገኘኝ ትንሽ እንደመደናገር አለውና በዚያው ድምፅ

ስማ አንተ ሁለተተኛ እዚህ ቤት አይህና ውርድ ከራሴ! … ሁለተኛ… ሂድ አሁን
ወጥቼ ወደ ቤቴ ተፈተለከሁ! የእውነት ምርር ያለ ድንጋጤና ሐፍረት ተሰምቶኝ ነበር !
እቤቴ እስክደርስ ኤልቆምኩም፡፡ እቤታችን በር ላይ ስደርስ የከሰል ምድጃ ላይ የተቀጣጠለ እሳት ይዛ ከቤት የምትወጣው እናቴ ጋር ልጋጭ ለትንሽ ተረፍኩ፡፡

ምን እያባረረህ ነው?' ብላ እንደ መሳቅም እንደ መደንገጥም አለች! ሁልጊዜ ሳኮርፍ
የምመናቀረው ነገር (እንደሷ አባባል) ያስቃታል! ለእናቴ የሆነውን ነገር አልነገርኳትም.. ጥያቄዋ ሲበዛብኝ ካርዴን ሰጥቻት “አምስተኛ ወጣሁ” አልኳት፡፡ ካርዱ እንዳይቆሸሽ፣
በሥራ የቆሸሽ እጁን ልብሷ ላይ ጠራረገችና ተቀብላኝ፣ አንዴ እንኳን ሳታየው እና እንኳን አምስተኛ ለምን መጨረሻ አትወጣም… እንዲህ እሳት ውስጥ እስክትማገድ ያመናቅራል እንዴ? ሳመኝ ና! ጎበዝ! ጎበዝ!" እያለች ካርዱን ጠረጴዛው ላይ አስቀምጣ እራሷ መጥታ አገላብጣ ሳመችኝ :: አባቴ ለምሳ እንደመጣ ፍልቅልቅ እያለች፣ ካርዴን
ልክ እንደምሳ አቀረበችለትና “አብርሽ አምስተኛ ወጣ!” አለችው፡፡

አምስት? . ብሎ በዛው ሌላ ወሬ ቀጠለበት እንደው ይኼን የጫማ ሶል በምን ብታጥቢው ነው እንዲህ የቆረፈደው?…ያልተላገ እንጨት ላይ ስራመድ የዋልኩ ነው የመሰለኝ ማታ በቅባት ካላሸሽልኝ፣ እግሬ ዋጋም የለው

“አንተ ደሞ! እስቲ ጎበዝ በለው :

እህ አልኩትኮ የኔ ልጅ ባይባልስ አገር ያወቀው አይደለም እንዴ …ማነው ስሙ
ይኼ የኛ ዕቁብ ሰብሳቢ ልጅ፣ ዘንድሮም ወደቀ መሰል፣ እዚያ ቦኖ ውሃው ግንብ ሥር ተቀምጦ ይነፋረቃል፡፡ ትምርቱስ ይከበደው መቼም ሰው እንዴት አሳምሮ ማልቀስ ያቅተዋል? " አባባ በቃ እንዲህ ነው።በራሱ ዓለም የሚኖር፡፡

የጋሽ ዝናቡ ነገር እንዲቹ ሲያብሰለስለኝ ዋለ! ወደማታ ላይ ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ታዲያ፣ የቤታችን በር ተንኳኳ፤ ጋሽ ዝናቡ ነበር: በጓሮ በር ወጥቼ ልሮጥ ሳስብ፣በተረጋጋ ድምፁ ከእናቴ ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ ስሰማ ተረጋጋሁ፡፡ እናቴ እንዲገባ ትለምነዋለች ረጋ ብሎ ወደ ቤት ገባ፡፡ ቡኒ የሱፍ ካፖርቱን እስከ አንገቱ ቆልፎ ለብሷል ጥቁር ቴክሳስ ባርኔጣውን በእጁ እያፍተለተለ …ቤታችን መሀል ላይ ቆመ! ረዥም ነው፡፡ አንገቴን ሳቀረቅር ተወልውሎ ከሚያብረቀርቅ ጥቁር ቆዳ ጫማው ጋር ተፋጠጥኩ፡፡

“ተቀመጥ! ጋሽ ዝናቡ፣ ምነው ከመሻ? በሰላም?” ሰላም ነው!ሰላም ነው አትጨነቂ! …ቀን ለምን ውጤታችሁ ዝቅ አለ ብዬ ልጆቹ ላይ አጓጉል ጮኸኩባቸው .…የኔን ነገር ታውቂው የለም … የኔውስ ለምዶታል አብርሃምን
አስደነገጥኩት መሰለኝ ይቅርታ ልጠይቅ ነው የመጣሁት …. አማልጅኝ እንግዲህ!” አለ።

እናቴ ወደኔ እያየች “ኧረ የታባቱ ደሞ ለሱ ይቅርታ! አንደኛ የሚወጡ ልጆች አምስተኛ ሲወጡ፣ ላይጮህባቸው ነበር ታዲያ ሲያርሱ ነው ሲያርሙ ዱላም ሲያንስ ነው ትንሽማ ቀበጥ ብለዋል …ተነስ አንተ!” አለችኝ በርግጌ ተነሳሁና
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አምስት


#በአሌክስ_አብርሃም

ለስላሳና ኬክ ጋብዘን፡፡ ስንወጣ ኬክ አስጠቅልሎ ለመሐሪ እያቀበለው “ለእናት ውሰድላት አለው፡፡

መሐሪ፣ ሮሐን አፈቀርኩ ሲል ቀድሞ በሐሳቤ የመጣው ታዲያ፣ ይኼው የጋሽ ዝናቡ ቁጣ ነበር፡፡ አራተኛ መውጣቱ ትልቅ ነገር ሆኖ፣ መላእክት እና ሰዎች ቢቧደኑ፣ መሀል ላይ የምትቆም ማሚንና ባለቤቷን ጋሽ ዝናቡን ቢለዋ ያማዘዘ፣ መሐሪ ከአንዲት ሴት ጋር ፍቅር ጀመረ የሚል ወሬ ጋሼ ጆሮ ሲደርስ፣ …ማሰቡ ራሱ አስፈርቶኝ ነበር! ቢሆንም ከመሐሪ ጎን ከመቆም ውጭ፣ ምናባቴ አማራጭ አለኝ ደግሞ ለከፋቱ ሮሐም ለመሐሪ
በፍቀር ክንፍ ብላ ተያይዘው ማበዳቸው እንዲያውም አንድ ቀን እኛ ቤት ነኝ ብሎ
ከሮሐ ጋር ማምሻቱ አስፈርቶኝ በቀጣዩ ቀን

ኧረ አንት ልጅ ሥርዓት ያዝ ጋሽ ቢሰማ ስለው ….በቁጣ ቱግ ብሎ…

“የራሱ ጉዳይ ነው! ከፈለገ ቤቱን ለቅቄለት እወጣለሁ!እለኝ፡፡ በውስጤ እሱንኳን ተወው! ያንን ቤት ለቆ ከወጣ የሚወጣው ነፍስህ ነው!” እያልኩ ዝም አልኩ፡፡ መሐሪ ባለችው ትርፍ ሰዓት ሁሉ ከሮሐ ጋር ተያይዘው የት እንደሚሄዱ እንጃ፣ መጥፋት ሆነ ሥራቸው፡፡ ሊያመሽ ከፈለገ ብቻ እየተጣደፈ “እናንተ ቤት ነኝ ይለኝና ነብሱን ስቶ ወደ ሮሐ ይበራል! ታዲያ ጋሽ ዝናቡን እየፈራሁም ቢሆን፣ ለጓደኛዬ ለመሐሪ ግን ልቤ በደስታ ይፈነጥዝ ነበር፡፡ ከሮሐ ጋር አብረው ሳያቸው፣ ልጁን እንደዳረ አባት ሐሤት አደርጋለሁ፡፡ ደግሞ ሲያምሩ፣ ከዓይናቸው የሚረጨው የፍቅር ብርሃን ድምቀቱ ሰው ፍቅር ለምን ያዘህ? አይባልም፡፡ሰው ላፈቀርካት ሴት ለምን ልብስህን ጣልክ? አይባልም እንዲያው ቀንበር ጠቦኝ እንጂ… እንደ ሮሐ ሥጋም በነፍስም ሲበዛ ውብ የሆነች ልጅ ያፈቀረ ጓደኛዬን፣ ባለፉበት ሁሉ ከፊታቸው ቀድሜ ያውም እንደ ንጉሥ ሰልፍ ነጋሪትና እንቢልታ አስይዤ “ይች ምናላት በደንብ እበዱ ወፎች ከበላያችሁ ያርግዱ ተማሪዎች በዙሪያችሁ ተኮልኩለው በፍቅራችሁ መልካም መዓዛ ይታወዱ …" እያልኩ ማወጅ ያምረኛል! ውብ ልጅ ነበረች ሮሐ ፈረንጅ የመሰለች” ይሏታል ፈረንጅ አትመስልም! ለኔ ቅላቷ በፈረንጅ ቀለም ላይ ትንሽ ጠይምነት ጠብ ተደርጎበት የተሰራ ለስላሳ ፍካት ነው፡፡
ልክ ወተት ላይ ቡና ጠብ እንደሚደረገው፡፡ ውብ ነበረች፣ ውብ፡፡ በዚያ የውብ ቆዳ መደብ ላይ፡ ምንኛ ዓይንን ተጠበበት የምለው፣ ዓይኗ ሲያርፍብኝ ነው፤አፍንጫን አንደም
አድርጎ አሳካው የምለው ከዓይኖቿ መሃል እስከ ላይኛው ከንፈሯ የተዘረጋ ቀጭን የገነት መንገድ አስመስሎ ቢያሰምረው ነው …የታችኛው ከንፈሯ ትንሽ ወደ ታች ወረድ ብሎ ቀበጥ አኩራፊ አስመስሏታል፡፡ የደላው ሰውነት አላት፡፡ ከረዥም ሉጫ ጸጉር ጋር ውብ ነበረች ሮሐን ለዐሥረኛ ክፍል ተማሪ ይኼ ሁሉ ውበት አልበዛም?እላለሁ እንዳንዴ ባየኋት ቁጥር፣ ስሙ ለተጠራ የዘራፊዎች መንደር፣ ያውም በጨለማ ወርቅ
ተሸከማ የምትሄድ ምስኪን ትመስለኛለች፡፡ ከመሬት ተነስቼ ሰዎች የሚጎዷት ይመስለኛል፡፡ መሐሪ ጋር በፍቅር አበዱ! እኔም ከዚያ ዝናቡ ከሚባል ሰውዬ ዶፍ ላስጥላቸው ራሴን ዣንጥላ እድርጌ ከበላያቸው ዘረጋሁ!!

አስባለሁ፤ሁልጊዜ አስባለሁ!… አእምሮዬ እንደ እስፖንጅ መጦ የያዘው ትላንታችንን፣ ፈሳሽ ትዝታ አድርጎ እየጨመቀ፣ ዙሪያዬን በጨቀየ ነበር ይከበዋል! ኤልረሳም፣ ያየሁ
የስማሁትን ነገር አልረሳም፡፡ ሰዎች ነገሬ ብለው የማይመለከቷቸውን ነገሮች እንኳን
ጨምድዶ ከያዘ የማይለቅ ተፈጥሮ ነው ያለኝ፡፡ ቆይቶ ይኼ ተፈጥሮዬ ከኋላዬ እየተከተለ የእኔኑ ጀርባ የሚገርፍ የእሳት ጅራፍ እየሆነ ሲያሰቃየኝ ብጠላውም፣ ልላቀቅ ያልቻልኩት መከራ እንደሆነ ይከተለኛል፡፡ እንደመርሳት ምን ፈውሽ አለ?!

ድንገት ካለምንም ምክንያት (ከመሬት ተነስቶ እንደሚሉት) በተቀመጥኩበት የሚያናውዝ ትውስታ እንደደራሽ ጎርፍ እያላጋ ወደራቀ ጊዜ ይወስደኛል፡፡ ዛሬዬን አጣጥሜ መኖር አልቻልኩም፡፡ ትዝታው ከአእምሮዬ አልፎ ሰውነቴንም ስለሚያዝለኝ ልወደውም፡፡ ትዝታ ግን ታሪክ ነው? በታሪክና በትዝታ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? ትዝታ
ታሪክ ከሆነ፣ ለምንድነው ሰዎች ታሪክ አውርተው ሲጨርሱ ከድካም ይልቅ በወኔ የሚሞሉት? አስባለሁ ወደኋላ ተመልሸ አስባለሁ፣ ወደ ልጅነታችን …

እኔና መሐሪ የ3 ከፍል ተማሪዎች ሆነን አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡ አልረሳም፡፡ ከትምህርት ቤት ሰፈራችን እስከምንደርስ ድረስ መንገድ ላይ የምናደርጋቸውን ነገሮች አንድ በአንድ አስታውሳለሁ፡፡ ቦርሳችንን በጀርባትን አዝለን መንገድ ለማቋረጥ ግራ ቀኝ እንመለከትና፣
የመኪናዎቹን ርቀት ገምቼ ለመሻገር መንገድ ስጀምር፣ መሐሪ ልብሴን አንቆ ወደኋላ ይጎትተኛል ይኼ ነገሩ ያበሳጨኛል፡፡ እሱ ደግሞ ድፍረቴ ያበሳጨዋል …እንነዛነዛለን

ገና የትና የት ያለ መኪና የምትፈራው፣ አንተ የገጠር ሰው ነህ እንዴ?”

“የትናየት እይደለም …እውር ነህ አታይም? ..አጠገባችን ደርሶ ነበር”

ነዳጅ ማደያው አጠገባችን ነው …እዛጋ ነበር መኪናው ትንሽ ብንጠብቅ ምን ትሆናለህ…ትሞታለህ?” መሐሪ መኪና ይፈራ ነበር።

እና ቆሜ ላድርልህ ነው? ከፈለክ አንተ ቆመህ እደር…ምናይነቱ ነው?!' በቆመበት ትቼውመንገዱንም በፈጣን ሩጫ ሳቋርጥ፣ ከባዱን የቦርሳውን ማንገቻ ግራና ቀኝ ደረቱ ላይ እንቁ፣
መገዱን ወዲያና ወዲህ እያየ በሩጫ ይከተለኛል፡፡ ቦርሳው ሁልጊዜ ከባድ ነው።የማያጭቀው፣ የማያዝለው ነገር የለም፡፡ ድንገት ዝናብ ቢጥል እያለች፣ ማሚ ጃኬት አጣጥፋ ታስገባለታለች… “ውሃ ደግሞ ጥሩ ነው ቶሎ ቶሎ ጠጣ” ትልና ክዳን ባለው ትልቅ የፕላስቲክ ኮዳ ሞልታ ታሸክመዋለች፡፡ አንድም ቀን ግን ጠጥቶት አያውቅም አንዳንዴ መንገድ ላይ እንረጭበታለን፡፡

ጋሽ ዝናቡ በተራው “አረፍ ስትል አትራገጥ…እንብብ!”ብሎ የሆነ መጽሐፍ ሸክሙ ላይ ይጨምርለታል፡፡ ያኔ ነው ከበደ ሚካኤል የሚባሉ ደራሲ መኖራቸውን ያወቅነው።አንዳንዴ የቦርሳው ክብደት ስለሚያደክመው “አግዘኝ!” ይለኛል፡፡ ሂድ ወደዚያ! ኩሊ
መሰልኩህ እንዴ” እያልኩ…ቦርሳችንን እንቀያየራለን፡፡ እየተነጫነጭኩም ቢሆን ሸከምን መሸከሜ አይቀርም፡፡ ታዲያ ሸክሙ ሲበዛብን (መቸስ ጋሽ ዝናቡን ማስቆም የማይታሰብ ነው) ማሚን አሳምነን ጃኬትና ውሃውን ለማስተው ተከራከርናት ፤ እየተቀባበልን
“እንዴ ማሚ አማርኛ መጽሐፍ አለ”
“እንግሊዝኛ መጽሐፍ ትተን መሄድ አንችልም …”
“ሒሳብ መጽሐፍ ይዘን ካልሄድን አስተማሪያችን ያብዳል …ምን እንደሚያክል ደግሞ
በዛ ላይ ደብተር! ተባብረን ስናጣድፋት፣ አንዴ እኔን… አንዴ መሐሪን እየተመለከተች ፊቷ ላይ ለይቶለት የማይፈነዳ ሳቅ እንዳረበበ እንደፈለጋችሁ አታድርቁኝ ኋላ ግን ብላ እጅ ሰጠች፡፡ከመሐሪ ቦርሳ ጃኬትና ውሃ ቀነስን፡፡ መንገድ ላይ ቀላሉን ቦርሳ ወደ
ላይ እያጓንን በመያዝ ድላችንን አጣጣምናት፡፡

መሐሪ ዕድለኛ ልጅ አልነበረም፡፡ በጭራሽ ዕድለኛ ልጅ አልነበረም፡፡ የዚያኑ ቀን
ከትምህርት ቤት ስንመለስ፣ ሰማዩን ቀዶ የተዘረገፈ የሚመስል ድንገተኛ ዶፍ ወረደ፡፡እቤት ስንደርስ ውሃ ውስጥ ነክረው ያወጧት ድመት መስለን ነበር፡፡ በተለይ መሐሪ ለአንድ ሳምንት የቆየ ትክትክ ሲያጣድፈው ከረመ ማሚ ከመጀመሪያው ይበልጥ የከበደ ባለወፍራም ገበር ጃኬት ገዝታ፣ መሐሪ ቦርሳ ውስጥ ጠቀጠቀችው፡፡ ዓመቱን
ሙሉ ያ ጃኬት ከቦርሳው ተለይቶ አያውቅም ነበር፡፡

መንገዱን ከተሻገርን በኋላ እየተነጫነጨ፣ “መገጨት ከፈለክ ራስህ ተገጭ አያገባኝም” ይላል፡፡ ከዋናው መንገድ ወደ ቤታችን ወደሚወስደው የኮረኮች መንገድ መገንጠያ ድረስ ተኮራርፈን በእግሮቻችን መንገድ
👍4
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ስድስት


#በአሌክስ_አብርሃም

ሳሌም፣ እኔና መሐሪን ገና ከሩቅ ስታየን፣ በሚቅጨለጨል ሳቋ ታጅባ ወደኛ ትሮጣለች፡፡ እናቷ ቀስ!.…ቀስ!” እያለች በዓይኗ ትከተላታለች፡፡ በየተራ እንስማታለኝ፡፡ መሃላችን ገብታ በማይገባን ቋንቋ ትኮላተፋለች፡፡ እጅና እጇን ይዘን ኦፕ! ኦፕ! እያለች ወደ እናቷ እንወስዳታለን፡፡ እንዳንዴ ትተናት ወደቤታችን ስንሄድ፣ ካልወሰዳችሁኝ ብላ መንገዱ ላይ በደረቷ ተኝታ ታለቅስ ነበር::

እኔና መሐሪ ለውዝ አሰፍረን በየኪሳችን እንይዝና፣ ለሳሌም እናካፍላታለን፡፡ ለለውዙ አንከፍልም፡፡ ለጋሽ ዝናቡ እንዳትናገር አስጠንቅቀን በዱቤ እንወስዳለን፤ ያው ቅዳሜ ልብስ ለማጠብ እነ መሐሪ ቤት ስትመጣ ማሚ “ምን ይሻላቸዋል? እነዚህ አንበጣ የሆኑ
ልጆች እያለች ትከፍላለች፡፡ ሳሌምን የዱቤ ለውዝ አስለምደናት፣ ገና ሲሰፈር መሬት
ላይ በቂጧ ዝርፍጥ ትልና ቀሚሷን ዘርግታ ታመቻቻለች፡፡ ለውዙን እንደ ዶሮ ጥሬ ቀሚሷ ላይ እንስትንላታለን፡፡ በትንንሽ እጆቿ እየለቀመች ትቆረጥማለች አንዳንዴ አንዲት የለውዝ ፍሬ ታመልጣትና፣ ያችን ለመያዝ ስትነሳ፣ የቀሚሷ ላይ በሙሉ መንገዱ
ላይ ይበታተናል፡፡ ብዙ ጊዜ ለውዟን ከያዘች ቻው ስንላት እንኳን ቀና ብላ አታየንም፤ ሐሳቧ ለውዙ ላይ ነው… “አንቺ! ቻው በያቸው እንጂ?” ትላለች እናትየዋ በሐፍረት፤ ሚስኪን የገጠር ሴት ናት፡፡

እየተሳሳቅንና ለውዛችንን እየቆረጠምን፣ ወደ ቤታችን እናዘግማለን፡፡ ለውዝ አበላላችን በራሱ ትንሽ ትርኢት ይመረቅበት ነበር፡፡ ገለባውን አራግፈን ወደላይ እንወረውርና፣ አፋችንን ከፍተን እንጠብቀዋለን…ብዙውን ጊዜ ብንካንበትም አልፎ አልፎ ግን
ከጥርሳችን ጋር እየተጋጨ አልያም አፋችን ስቶ መሬት ላይ ይወድቃል፡፡ አንስተን መብላታችን አይቀርም፡፡ ብዙ ጊዜ የሚስተው መሐሪ ነበር፡፡ ጥርሳም ስለሆንከ ነው እለዋለሁ፡፡ መላፋት እንጀምራለን፡፡ እንዲህ ነበር ደርሶ መልሳችን!

አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስንመለስ፣ የኢየሩስ ጉሊት ባዶ ሆኖ አገኘነው፡፡
የምትቀመጥበት ድንጋይ ብቻ ነበር ያለው፡፡ የት ሄደው ነው? ተባብለን አለፍን፡፡ በቀጣዩም ቀን ባዶ ነበር፡፡ በሦስተኛው ቀን መሐፊ እቤቷ ሄደን እንያት አለኝ፡፡ ደብተሬን አስቀምጨ ተመለስኩና፣ መሐሪን ስጠራው “ማሚ ነገ ቅዳሜ እንያትና፣ ካልመጣች ትሄዳላችሁ” ብላለች” እለኝ፡፡ ረቡዕ፣ ሐሙስና ዓርብ መሆን አለባቸው ቀናቱ
ምክንያቱም በቀጣዩ ቀን ማሚ እንዳለችው ጥድቄ እነመሐሪ ቤት መጥታ ነበር፡፡ ገና በጧቱ መሐሪ እቤታችን መጣና፣ ሁልጊዜ ሲጨነቅ እንደሚያደርገው እጁን እያፍተለተለ
“ባሏ ደብድቧት ነው የጠፋችው?” አለኝ፡፡

“ማን?

“ጥድቄ”

“መጣች እንዴ?” አልኩት …

"ጧት መጣች፤ ልብስ ልታጥብ፡፡ ማሚ ግን እንዲህ ሁነሽማ እታጥቢም! ምናምን ብላት ቁጭ ብለው እያውሩ ነው፡፡ እንዳለ ፊቷ በሞላ እባብጧል፡፡ በቢለዋ ሊያርዳት ነበር፤ አምልጣ ጎረቤት ቤት ተደበቀች

አረ!?”

ራሷ ናት ለማሚ እያለቀሰች የነገረቻት፡፡ ፊቷ ሁሉ እንዳለ አባብጧል…ጥርሴ ተነቃንቋል ብላለች!” መሐሪ ሊያወራ በፍጥነት ነበር፡፡ ልክ እሱ ራሱ ሲደበደብ አምልጦ በሩጫ የመጣ ዓይነት፡፡ ሁልጊዜም ሲጨነቅ ወይ ሲፈራ፣ እንደዚህ ነው አወራሩ፡፡ ተያይዘን
ወደቤታቸው ሄድን:: ገና በሩ ላይ ስንደርስ ሳሌም ኦፕ! ኦፕ! እያለች ወደኛ ሮጠች!
ጥድቄ ዓይኗ ሁሉ አባብጦ ከንፈሯ ደም አርግዞ ከልብስ ማጠቢያው አጠገብ ባለ
አግዳሚ የድንጋይ ወንበር ላይ፣ ከማሚ ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠው ነበር፡፡

ማሚ በጣም ከመበሳጨቷ የተነሳ፣ ከመሐሪ ጋር ተከታትለን ስንገባ፣ እንደወትሮው ስላም እንኳን አላለችኝም፡፡ በየመሀሉ እየደጋገመች “ወይ ጥጋብ! ወይ ጥጋብ! ወይ ጥጋብ!” እያለች ከድምፅዋ እኩል ቸብ ቸብ እያደረገች ታጨበጭባለች፡፡ እንዲህ
እንደተቀመጡ ጋሽ ዝናቡ ነጭና ጥቁር መስመር ያለበት በልኩ የተስፋ የሜዳ አህያ ቆዳ በሚመስል ዥጉርጉር የሌሊት ልብሱ ላይ፣ ከጥጥ የተሠራ ነጭ ጸጉራም ካፖርት ደርቦ እየተንጠራራ ከቤት ወጣና በረንዳው ላይ ቆሞ አዛጋ፡፡ ሲያዛጋ ድምፁ በሌሊት ከሩቅ የሚስማ የጫካ እንሰሳ ዓይነት ድምፅ ይመስል ነበር፤አዋአዋዋአዋአዋአዋአዋአዋእዋእዋ!
“ጎሽ! ተነስቷል” አለች ማሚ ! እሱን እየጠበቁ ነበር
ማሚ ወደ በረንዳው መጣች፡፡ እኔና መሐሪ ደረጃው ላይ ተቀምጠን ከህጻኗ ጋር እየተጫወትን ስለነበር፣ እንድታልፍ ጠጋ አልንላት፡፡ እዚያው ደረጃው ሥር እንደቆመች ጋሽ ዝናቡን ሽቅብ እያየች፣

“ይኼ ባለጌ የሠራውን አየህ?” አለች።

“ማነው” አሉ ኮስተር ብሎ፡፡

ወደ ጥድቄ እየጠቆመች ባል ተብየው ነዋ!” አለች፡፡ጋሽ ዝናቡ ጥድቄን ገና ያኔ ያያት ይመስል ደህና አደርሽ?” አላት::

ከተቀመጠችበት ተነስታ ጎንበስ ቀና እያለች እግዚሃር ይመስገን! ጋሽ ደህና አደሩ” አለች።

እንዲህ ሕግ ባለበት አገር፣ እንደ እባብ ቀጥቅጦ ቀጥቅጦ፣ ጎረቤትኮ ነው ነብሷን ያተረፈው:: ነይ ወደዚህ አሳይው!” አለች፤ ማሚ፡፡ እንደዚህ ቀን ስትበሳጭ አይቻት አላውቅም፡፡ ጥድቄ ቀረብ አለች፤ ስትራመድ ታነከስ ነበር…

“አንድ ነገርማ አድርግ ዝናቡ እንዲህ ዓይነቱን ጥጋበኛማ “ሀይ!” ካላሉት፣ ነገ ተነስቶ ሰው ይገድላል፣ የምታረገውን አርግ በቃ!” ጋሽ ዝናቡ፣ ማሚ ተማምናበት የሆነ ውለታ ስለጠየቀችው ይሁን ወይም በጕዳዩ አዝኖ፣ ብቻ ፊቱ ላይ የሆነ ኩራትና ወንድነት
እንዣበበት፡፡

ፊቷን በትኩረት ከተመለከተና ምን ልሁን ብሎ ነው እንዲህ ያደረገሽ?” አለ፡፡

“ጥጋብ ነው ጋሸ

“ምንድነው ጥጋብ? በደንብ ንገሪኝ አለ ጋሼ ችሎት ላይ እንደተሰየመ ዳኛ ነበር
አነጋገሩ፡፡
ለኔ የነገርሽኝ እንድ ባንድ ንገሪው አትፍሪ እሱ መላ አያጣም” አለች ማሚ፡፡ ብስጭት ብላ ነበር ።

ንገሪኝ አትፍሪ! አለ ጋሼ ጋሽ ዝናቡና ማሚ በአንድ ጉዳይ ላይ እንዲህ
ተስማምተው ሲያወሩ ሳያቸው፣ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡

እኔ ሰይጣን ይላካቸው ጠላት፣ ምናባቴ አውቄ.. እዚህ ፈረንጆቹ ቤት ውስጥ ያሉ
ሁለት ፈረንጆች፤ምን ፈረንጅ ናቸው አማረኛውን ሲያቀላጥፉት ያዩ እንደሆነ፣ ለጉድ ነው ጋሽ፣ እኔም እንደነሱ አይፍታታልኝ:: መጡና ባል አለሽ ወይ? አሉኝ፡፡ አዎ! ስላቸው ጊዚ
ባለቤትሽ ቤት በሚኖርበት ቀን ሁለታችሁንም እናነጋግራለን፣ እቤትሽ ውሰጅን አሉ:: እኔ ደሞ መቼም ደሀ ጉጉ ነው፣ እርዳታ ይሰጣሉ ሲባል ሰምቼ፣ አዝነውልኝ ሊሰጡኝ ይሆናል ብያለሁ፣ በኋላ ማክሰኞ አመሻሹ ላይ ተቃጥረን ሦስት ሁነው እቤቴ መጡ፡፡
መጡና 'ይችን ልጃችሁን ፈረንጅ አገር ልከን እናስተምራት፣ ለሷም ለእናተም ጥሩ ነው:: አሉ”

“አሃ …ማደጎ” አለ፤ ጋሽ ::

“ማደጎ ይሁን? ምን ይሁን? ምናባቴ አውቄ ብለው፡፡ ከመሬት ተነስተው ከፈቀዳችሁ እንውሰዳት፤ እዚህ መንገድ ለመንገድ ከምትበላሽ አሉ እንጅ! …ኋላ እንደው እንዲህ ሲሉ ነጥቀው የወሰዱብኝ መሰለኝ አንዘፈዘፈኝ፤ ጋሽ! አንዘፈዘፈኝ !ሌላ ምን ተስፋ አለኝ
ምን የዓይን ማረፊያ አለኝ … ልጄን አቅፌ ውጡልኝ ከዚህ ቤት ብዬ ኡኡ! አልኩ፡፡
አስቡበት ብለው ወጥተው ሄዱ …
እሽ! " አለ፣ ጋሽ ብዙም የገረመው አይመስልም፡፡
“ፈረንጆቹ ወጣ እንዳሉ፣ ባለቤቴም ከተል ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡ ካለወትሮው እስከ እኩለ ሌሊት አምሽቶ፣ ስክር ብሎ መጣ፣ መጣና የልጄን ዕድል ልታበላሽ ደህና እግዜር ያያትን፤ ትሄዳለች፤ እኔ አባቷ ፈቅጃለሁ፤ ፈረንጅ አገር በአውሮፕላን ሽው! …እዚህ ማስክ የለም! ጭርንቁስ.…እከካም! ትሄዳለች” አለኝ፡፡ ልጄን ሊነጥቁኝ ሲማከሩብኝ ያመሹ
መሰለኝ ጋሸ፡፡ ሰካራም ነው፡፡ አንድ
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሰባት


#በአሌክስ_አብርሃም

...ማሚና ኢየሩስ ተያይዘው ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ፣ ጋሽ ዝናቡ በረንዳው ላይ ባለው ተወዛዋዥ ወንበር ላይ ተቀምጦ በዝምታ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ሲወዛወዝ ቆየና፣ ረጋ ባለ ድምፅ፣

“መሐሪ ቦርሳዬን ኣቀብለኝ” አለ፡፡

ሁል ጊዜ ሥራሲሄድ የሚያንጠጥለሰውን ቡናማ የቆዳ ቦርሳ ከፍቶ ወረቀቶች፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መድሐፍና እና ጥቁር ብድር አወጣ፡፡

ልጅቱን ጥራት አለው መሐሪን በአገጩ ወደገባችበት እየጠቆመ ፡፡ ማሚና ትድቄ
ተያይዘው መጡ።

"የባለቤትሽ ስም ማነው?"

ጋንጩር ነው እንጂ ምን ስም አለው ብላ በብስጭት ከተናገረች በኋላ፣ ማሚ በከንዷ ግሸም ስታደርጋት ተረፈ! ተረፈ መርጊያ ምን ይተርፋል ይኼ ጦሱ ነው የተረፈን አለች

“ከዚህ በፊት ደብድቦሽ አልያም ሰድቦሽና እስፈራርቶሽ ያውቃል …”

ስድብና ማስፈራርያማ ስንቁ ነው…ምሳና ራቴ … ድንገት ያሰረችውን ሻሽ ከራሷ ላይ መንጭቃ ፈታችና የተጎሳቆለ ጸጉሯን ከጆሮዋ በላይ ገለጥ ገለጥ አድርጋ …"ይኼው የዛሬ ዓመት በቡና ስኒ ወርውሮ የፈነከተኝ፡ ሐኪም ዘንድ ሄጄ ተሰፍቼ ነው!እስካሁንም ቅዝቃዜ
ሲሆን ያመኛል ፡ ያዞረኛል” አለች፡፡ ማሚ አዲስ የሰማችው ነገር ስለሆነ ተንጠራርታ ጠባሳውን አየችና ወይ ጥጋብ!" ብላ በብስጭት ተነፈሰች፡፡

ጋሽ ዝናቡ ጥድቄን የተለያየ ነገር እየጠየቀ፡ አንድ ገጽ ከግማሽ የሚሆን የክስ ማመልከቻ ፅፎ ጨረሰና ጉሮሮውን ጠርጎ በጎርናና ድምፁ አነበበላት፡፡ “በተደጋጋሚ በሚያደርስብኝ
አካላዊ ጥቃት የእኔም ሆ የልጄ ሕይዎት አደጋ ላይ በመውደቁ እያለ፣ እንብቦ ሲጨርስ ጥድቄ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ወረቀቱ ግርጌ ላይ በጣቷ አስፈርሟት፡፡
መፅሀፍቱን ወደ ቦርሳው ጨማመረና፡ ለራሱ በሚመስል ድምፅ “በቃ! ሰኞ ክስ እንመሰርታለን አለ።

ማሚ ወደኋላ ቀረት አለችና ጋሽ ዝናቡን

“ቡና ላፍላ እንዴ? አለችው።

"እሽ" አለ ሁለቱም ንግግራቸው ለስለስብሎ ነበር
በስንተኛው ቀን እንደሆነ እንጃ፣ የጥድቄ ባል ታሰረ ብሎ መሐሪ ነገረኝ፡፡ ለሁኔ ግን መልኩን እንኳን ከማላውቀው ሰውዬ እስር በላይ፣ እስካሁን ውስጤ የቀረው ማሚ
ከጥድቄ ጋር ፍርድ ቤት ሂዳ ያየችውን ስታወራ ጣል ያደረገችው ነገር ነበር፡፡ ባልየው ችሎት ገብቶ ዳኛው ፊት ሲቆም፣ መርፌ ቢወድቅ በማያሰማው የችሎቱ ጸጥታ ውሰጥ አባባ ባቦ የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ሳሌም ነበረች

ዐመሉ ውሻ ነው እንጂ፤ ማታ ሲገባ ለልጁ በኪሱ ዳቦ ሳይዝ አይገባም ነበር አለች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጥድቄና ሳሌም እነ መሐሪ ሴት እቃ ቤት” የምንላት፡ በዋናው ቤት ኋላ ባለች ሰርቪስ ቤት ውስጥ መኖር ጀመሩ፡፡ ይኼንንም ሐሳብ ያመጣው መሐሪ ይሁን እንጂ ሙግቱ ላይ ነበርኩበት፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እኔና መሐሪ አገር ምድሩ ያውቃው ዳኛ፡
ጋሽ ዝናቡ ፊት በድፍረት ቁመን የራሱን ቤት ለአንዲት ደሀ ያካፍል ዘንድ የሞገትንበት፣ ሞግተንም ያሸንፍንበት ፋይላችን ነበር፡፡ ዝም ብሎ ሲሰማን ቆየና

“ጥሩ ጠበቃ ወጥቷችሁ የለም እንዴ ጃል” ብሎ ፈቀደ፡፡ ያኔ ሳሌም ዕድሜዋ ከሁለት ዓመት አለፍ ቢል ነበር፡፡ ሲበዛ ሁለት ዓመት ከአምስት ወር!

አባቴ ጎበዝ አናጺ ነበር፣ ከአናጺነት የካኪ ቱታው ውጭ የክት ልብስ ሲለብስ ይጨንቀዋል፡፡ በተለይ ጋቢ ሲለብስ አንዴ ከትከሻው እየጠንሸራተት፣ ሌላ ጊዜ መሬት ለመሬት እየተጎተተ ያስመርረው ነበር፡፡ የፈለገ ቢዘንጥና ቢታጠብ፡ ልብሱ ላይ የተለጠፈ፣ አልያም ጸጉሩ ላይ የተሰካ አንዳች የእንጨት ፍቃፋቂ አይጠፉም፡፡ ብዙ ማውራትና ብዙ መቀመጥ አይሆንለትም፡፡ በሕይወቱ ዘለግ ያለ ነገር አወራ ከተባለ፣ ወይ
ስለዕቁብ ነው፣ ካልሆነም ስለ እንጨት እና ሚስማር መወደድ ነው:: ዘወርወር ያለ ዉሬ በቀላሉ የሚረዳ ሰው አልነበረም። ነገሩ ሁሉ አጭርና ቀጥ ያለ ነው። ይኼንን ነገሩን እኔ ብወድለትም፣ እናቴ ግን ሁልጊዜ ምን ቢያደርጉት ይሻላል ይኼ ሰው ነገር መዘንኮር እያለች ትበሳጫለች፡፡
ታዲያ እንደ ሁልጊዜው በእናቴ እስገዳጅነት ጧት ተነስቶ ቤተክርስቲያን ደረስ ብሎ መመለሱ ነበር፡፡ በር ላይ ቁሜ እጁን እያስታጠብኩት ነው፣

ከሰብከቱ ሁሉ የማይዋጥልኝ፣ ይኼ ክርስቶስ አናጢ ነበር የሚሉት ነገር ነው ..
ታዲያ ቢሆን እና ምንህ ተነካ ሥራህን ተሻማህ!?…ሆ” አለች እናቴ፡፡

እኔ ምኔ ይነካል እንደው የመምሬ አፈወርቅ ነገር ቢገርመኝ ነው እንጅ!”
እሳቸው አልጻፉት መጽሐፉን ነው የሰበኩት!” አባቴ ዝም ብሎ ቆየና ድንገት
ክርስቶስ መምህር ነበር ሲሉን አይደለም እንዴ፤ ይኼው ቄስና መምህሩን ሁሉ
የምንፈራና የምናከብር

እና አለች እናቴ ሐሳቡ ኤልያያዝ ብሏት፡፡

“አናጢ ነበር ካሉ፣ ለምን አናጢ አያከብሩም ታዲያ? መምሬ አፈወርቅ ራሳቸው የሚያከራዩትን ሁለት ክፍል ቤት የሠራሁበትን የላቤን ዋጋ እስካሁን መች ከፈሉኝ? እንግዲህ በክርስቶስ አምሳል መዶሻ ያነሳውን የመንደርሽን አናጢ ካላከበርሽ፣ ክርስቶስንስ መች ታከብሪያለሽ! መስቀል ላይ ስላልቸነከሩኝ ነው እንዴ? ይሄው የዕቁብ ከፍይ ጎደለብኝ

እናቴ ዝም አለች፡፡ ይኼኛው ዝምታዋ የኩርፊያ ነው፡፡ በዝምታዋና በዝምታዋ መካከል ያለውን ልዩነት፣ ፊቷን እንኳን ባላይ መለየት እችላለሁ፡፡ እንዴት እንደሆን እንጃ፤ ወሬ ለማስቀየር ይሁን፣ አልያም በአባቴ ብስጭት ንዴቷን እኔ ላይ ለመወጣት፣ “ምናለ እንዲያው እሁድ እንኳን ቤተክርስቲያን ብትስም፣ ይኼው መሐሪን እንኳ ስሞ ሲመለስ
አገኘነው የተባረከ ልጅ አለች፡፡ መሐሪ ለምን ቤተክርስቲያን እንደሚሄድ ስለማውቅ፣ሳቄን አፍኜ ዝም አልኩ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሰበብ ወጥተው ከሮሐ ጋር እሁድ እሁድ ጧት ይገናኛሉ፡፡ ዛሬም አብረው ነው ያገኟቸው…

አባቴ ድንገት “አብራው የነበረችው ልጅ የግርማ ልጅ አይደለችም እንዴ?” ብሎ ጠየቀ።

ብትሆንሳ ታዲያ? አብረው ነው የሚማሩት?” እናቴ ስለተበሳጨች ንጭንጭ ብላለች፡፡

እሱማ ..እንዲያው ግን፣ የግርማ ልጅና የዝናቡ ልጅ አብረው ሳይ

ነሽ እቴ …የማያሳስበው ያሳስብሃል”

“ግርማ ጥሩ ሰው ነበር …ሆቴሉን በጠገንኩ ቁጥር አክብሮ ክፍያውስ ቢሆን፡ ከጥሩ ሰው ልጅ ጋር መግጠም ጥሩ ነው” አለ አባቴ፡፡ የሮሐ አባት ጋሽ ግርማ ከተማው ውስጥ የታወቀ ሀብታም ነው::ወደኋላ ክብልስ የሚል ጸጉር ያለው፣ የህንድ የፊልም አክተሮች የመሰለ፣ ፈገግታ ከፊቱ የማይጠፋ ሰውዬ፡፡ የነዳጅ ማደያ እና ትልቅ ሆቴል አለው::
ከሁለት ዓመት በፊት በሆነ ጉዳይ ተከሶ ፍርድ ቤት ይቀርባል ፡፡ጉዳዩ በትክክል ምን እንደሆን እንጃ፤ ከመንግሥት ጨረታ ጋር የተያያዘ ነገር ነው ሲሉ ነው የሰማሁት

ዳኛው ጋሽ ዝናቡ ነበር፡፡ እንግዲህ እንደሚወራው፤ ጋሽ ግርማ ነገሩ አላምር ሲለው፤ ከክሱ ነፃ ለመውጣት ሲል ለጋሽ ዝናቡ ጠቀም ያለ ብር ጉቦ ለመስጠት አማላጅ ይልካል፡፡ ጋሽ ዝናቡ አማላጁንም ጋሽ ግርማንም ጠራርጎ እስር ቤት አስወረወራቸው።ጭራሽ የሮሐን አባት፣ በተከሰሰበትም ጒዳይ የሁለት ዓመት እስር አከናንቦት፣ ፍርዱ ወደ ገንዘብ ተቀይሮለት ነው የተፈታው ይባላል። ሮሐና መሐሪ ታዲያ የአባቶቻቸውን ታሪክ
ለአባቶቻቸው ትተው የጦፈ ፍቅር ውስጥ አሸሼ ይላሉ!

ሮሐ አባቷ ለመሐሪ ቤተሰቦች ያለውን ጥላቻ ስትገልጽ ታዲያ፣ እየሳቀች እንዲህ ትላለች
“መሐሪ እኛ ቤት ሽማግሌ ቢልክ፣ ዳዲ ገና ሊያገባኝ የጠየቀው የጋሽ ዝናቡ ልጅ መሆኑን ሲያውቅ፣ ሁሉንም ነው የሚረሽናቸው ሂሂሂሂ፡፡ እኛም እንዲህ ነበር የምናስበው:: ጋሽ ዝናቡ መሐሪ ሴት ማፍቀር ብቻ ሳይሆን የጋሽ ግርማን ልጅ ማፍቀሩን ቢሰማማ

ለዚያም ነበር ያንን ሁሉ ጊዜ
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ስምንት


#በአሌክስ_አብርሃም

ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል አልፈን ለማትሪክ የምንዘጋጅበትን መጽሐፍና፣ያለፉ ዓመታት
ተፈታኞችን የፈተና ወረቀቶች ሰብስበን እንሙት ባልንበት ክረምት ታዲያ፣ ይሆናል
ብለን ያላሰብነው፣ የልብ ምታችንን ቀጥ አድርጎ ሊያቆም የሚችል፣ ድንገተኛ ነገር
ተፈጠረ (የሰው ልብ አቻቻሉ )

ትምህርት ቤት ለክረምት ከተዘጋ በኋላ፣ በተለይ ቅዳሜ ቅዳሜ ሄኖክ የሚባል አብሮን የሚማርና ሮሐን ክፉኛ ይከጅል የነበረ ልጅ፣ ተስፋ ቆርጦ ይሁን አልያም እሷን ባላገኛትም እንኳን፣ ጠረኗ ቤቴን ይሙላው ብሎ …ብቻ ለጥናት በሚል ሰበብ፣ የተከራያትን አንዲት ክፍል ቤት ለመሐሪና ሮሐ ይለቅላቸውና ዓለማቸውን ሲቀጩ ይውላሉ፡፡ የዓለም ቀጨታው ከመሳሳም አያልፍም” ቢልም ወዳጄ መሐሪ … ነፍሴ እሺ ብላ አታምንም ነበር፡፡ እንዲያው ይሁንልህ በሚል ቸልተኛ መሸነፍ አምኘለት እናልፈዋለን፡፡

ታዲያ ሲመሻሽ ሄኖክን ለቤቱ አመስግነን ሮሐን በአሳቻ መንገዶች እያቆራረጥን
እስከቤቷ አቅራቢያ ሸኝተን (የት ዋልሽ ስትባል የት እንደምትል እንጃ ወደ ቤታችን
እናዘግማለን፡፡ መሐሪና ሮሐ ሁልጊዜ ከዚህ ቤት ሲወጡ ዝምተኛና አንገታቸውን የደፉ የሚሆኑበት ነገር አለ፥ ምን ሆናችሁ አልልም፡፡ በሌለሁበት ጉዳይ መተፋፈሩ እኔም ላይ ተጋብቶ አፌን ይዘጋኛል፡፡ ወደ ቤት ስንመለስ በመንገዳችን፣ መሐሪ ዓይኔ ቀላ እንዴ? ከንፈሬ አበጠ እንዴ? - ጸጉሬ እንዴት ነው? የሚሉ አንዳንድ ወላጅ ሊያውቃቸው የማይገቡ ነገሮችን ማድረጉን ሊጠቁሙ የሚችሉ ምልክቶችን ተባብረን አሻራ እናጠፋለን፡፡ እቤት የሚጠብቀው ሣር ቅጠሉን የሚጠራጠር የዳኛ ዓይን ነው!

የዚያን ቀን ቅዳሜ ማታ መሐሪ፣ “ግባና ሰላም ብለሃቸው ትሄዳለህ ብሎ ገፋፍቶኝ
(ሁልጊዜ ራሳቸው ቤት ውስጥ ብቻውን መግባት ለምን እንደሚፈራ አይገባኝም) …ወደ ቤታቸው ተያይዘን ገባን፡፡ ጋሽ ዝናቡ በረንዳው ላይ ተቀምጦ መጽሐፍ ያነብባል፡፡
መጽሐፉን አጠፍ አድርጎ ጎረምሶች ከየት ነው” አለ።

እግራችንን እናፍታታ ብለን .” አልኩ (ተከላካይ ጠበቃ ይመስል የምፈጥነው ነገር አለ)

"ሙሉ ከሰዓት እግር ስታፍታቱ …መልካም ዝም ተባባልን፡፡

እንግዲህ ወደ መጨረሻው መጀመሪያ እየቀረባችሁ ነው፣ ዝግጅት እንዴት ነው?
“ያው …" መሐሪ ተንተባተስ ድንገት ጋሽ ዝናቡ ሂዱ እስቲ ወንበር ይዛችሁ ኑ!” አለ፡፡ የየራሳችንን ወንበር ይዘን መጠንና፣ ፊት ለፊቱ ተቀመጥን፡፡ ተጨንቀናል። ጋሽ ዝናቡ ቁጭ በሉ አለ ማለት፣ ልክ አሰተማሪ ውጣ ተንበርከክ እንደሚለው ዓይነት፣ የቅጣት ስሜት ያለው ነገር ነው፡፡

እና እግር ማፍታታቱ የት የት ወሰዳችሁ?” አለን ድንገት፡፡ እኔና መሐሪ ተያየን
አብርሃም” አለኝ (የማሪያምን ብቅል ፈጭቻለሁ ብል ደስታዬ)

"አቤት ጋሸ”

“መሐሪ ወንድምህ ማለት ነው፤ እናንተ አሁን ጓደኛ አትባሉም፣ ለኛም ቢሆን ከመሐሪ ለይተን የማናይህ ልጃችን ማለት ነህ፣ የመሐሪ ነገር የእኔን ያህል የእናቱን ያህል ሊያሳስብህ ይገባል፡፡ እፈለጋችሁበት ስትሄዱ፣ የት ወጣህ? የት ገባህ? የማንለው ለምን ይመስልሃል? ስላደገ ችላ ብለን ነው? አይደለም! አንተን ስለምናምንህ፣ ጥሩ ልጅ ስለሆንክና፣ መጥፎ ቦታ ሲውል ዝም ብለህ እንደማትመለከተው ስለምናምን ነው፡፡
ይገባኛል ጓደኝነታችሁ፣ እርስ በርስ ነገሮችን የምትሸፋፍኑት ነገር፥ ግን ደግሞ
ከሪያሊቲው ብዙ መራቅ የለባችሁም፡፡” ብሎ ተራ በተራ አዬንና

ስለ ሮሐ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ፡፡” አለን:: የመሐሪ ጉሮሮ ገርገጭ ሲል ሰማሁት፡፡ ምራቁን ሳይሆን ሰላሳ ሁለት ጥርሱን ባንዴ የዋጠው ነበር የሚመስለው፡፡
“ሮሐ ኧረ ሮሐን አናውቃትም …ማናት? …” ብዬ ወደ መሐሪ ስዞር፣ አንገቱን ደፍቶ
መሬት መሬቱን ይመለከታል ፡፡

“መሐሪ እናተ ቤት ነኝ እያለ፣ የት ያመሽ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ ከመጀመሪያው
አውቃለሁ ኢትስ ኦኬ” አሁን ልወቅሳችሁ አልያም ልከሳችሁ አይደለም ዕድሜያችሁ ነው፡፡ ሰው እናትና አባቱን ይተዋል…” ይላል መጽሐፉም አይደለም እንዴ መሐሪ እሁድ ጧት ቤተክርስቲያን ስትሄድ እንደዛ ሲሉ አልሰማህም?…” እለና ሃሃሃሃ ብሎ ሳቀ፡፡አሳሳቁ የመሐሪን የእሁድ ጧት ጉዳይ እንዳወቀ የሚያሳብቅ ዓይነት ነበር፡፡ “ሕፃን አይደላችሁም፤ በመደባበቅ ጫካ ለጫካ በመሄድ፣ የጥናት ጊዚያችሁን ማባከን የለባችሁም ያውም ባለቀ ሰዓት ትምህርት ዋናው ጉዳይ ነው፡፡ ትምህርት!
ትምህርት! ባለማመን ቀስ ብዬ የጋሽ ዝናቡን ፊት ስመለከተው ዓይን ለዓይን
ተገጣጠምን፡፡ መልሼ አቀረቀርኩ ፡፡

“መሐሪ”

“እቤት ጋሽ”

“ስሚመቻት ቀን አምጣትና ከእኔም ከእናትህም ጋር እስተዋውቀን፡፡ ከዚህ በኋላ ጢሻ ለጢሻ እየዞራችሁ ጊዚያችሁን ስማይረባ ድብብቆሽ እንዳታሳልፉ፡፡መገናኘት ሲኖርባችሁ እዚሁ ትምጣ

“ማን መሐሪ ተንተባተበ፡፡

“ከዚህ ሳምንት እንዳያልፍ! አሁን ሂዱ” ማሚን እንኳን ገብቼ ሰላም ሳልላት በቀጥታ ከበረንዳው ወደ ቤቴ ሮጥኩ፡፡

መንገድ ላይ ለራሴ እንዲህ እያልኩ ነበር፡፡ “ከስብከቱ ሁሉ የማይዋጥልኝ ይኼ ሰው እናትና አባቱን ይተዋል የሚሉት ነገር …አሁን ጋሽ ዝናቡ ልተውህስ ቢሉት የሚተው ሰው ነው ?
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ዘጠኝ


#በአሌክስ_አብርሃም

ጋሼ መቀለድ ሁሉ
ጀመረኮ” ስንላት “ይኼ ስራው ኮስታራ አደረገው እንጂ፣ ድሮማ ጥርስ አያስከድንም ነበር አለን፡፡ መሐሪ ታዲያ ከዚያ በኋላ በሆነ ነገር ሲጨናነቅ “ሳቃቸውን ድሮ ጨርሰው እኛ ያጨናንቀናል” ይላል፡፡

ጋሽ ዝናቡ ለምሳ ወደቤት ካልተመለሰ፣ በቀን አንዴ እየደወለ እሺ! ጥናት እንዴት
ነው?” እያለ ይሰልለናል፡፡ ያን ሰሞን ሥራ ይበዛበት ስለነበር (ተዘዋዋሪ ችሎት የሚባል ነገር) ብዙ ባያገኘንም አምሽቶ ሲመጣ፣ በቀጥታ ወደ ከፍላችን ብቅ ይልና በሩን ያንኳኳል፡፡ እንደማሚ በርግዶ አይገባም፣ እንዲያውም ወደ ውስጥ አይገባም እንዴት እየሄደ ነው?” ይለናል፡፡ አፋችን እየተንተባተበና ቃላት አፋችን ላይ እየተጋጩ “ጥሩ ነው! ምንም አይል፡፡” እንላለን፡፡ “አይዞን!” ብሎ ተመልሶ ይሄዳል፡፡ ዓርብ ዓርብ ታዲያ
እዚያዉ በር ላይ እንደቆመ ዋሌቱን ከኋላ ኪሱ ያወጣና፣ ድፍን አምሳ ብር መዞ በሩ ሥር የቆመች የመጽሐፍ መደርደሪያ ጫፍ ላይ አስቀምጦልን ይሄዳል፡፡ ብዙ ጊዜ ሮሐንን እንጋብዝዎታለን፡፡ በተረፈው ለሳሌም እና ለማሚ ኬክ እንገዛላቸዋለን፡፡ ሁለቱም ኬክ ይወዱ ነበር፡፡ ማሚ ኬክ በኛ ጊዜ ቀረ …እያለች፣ ሳሌም ነገም ኬክ እንበላለን እያለች ትዝታና ተስፋን ዛሬ ላይ እንጋብዛለን፡፡

ሮሐ ቅዳሜ ቅዳሜ እነ መሐሪ ቤት መምጣት ከጀመረች ሰነባብታ ነበር፡፡ ጋሽ ዝናቡ ወታደራዊ ትዕዛዝ መሠረት በስንት ክርከርና ፍርሃት (መሐሪ አይሆንም ብሎ በኔው ውትወታ) አምጥተን ካስተዋወቅናት በኋላ፤ ከእኛም በላይ ቤተኛ ሆና ቁጭ አለች፡፡
“በምን ቀን ነው ያስተዋወቅናትም እስከምንል፡፡ በተለይ ማሚ ልክ እንደ ልጇ ሚስት ነበር አቀባበሏ፡፡ ታዲያ መሐሪን ለብቻው እንደዚህ ስለው ሚስት ናትና ይለኛል፡፡ማሚም ፊት ይሁን ጋሽ ዝናቡ ፊት፣ ሮሐ በመጣች ቁጥር ግን ሁልጊዜ ያፍራል። ፍቅረኛው እቤቱ መምጣቷ ብዙ ምቾት የሰጠው አይመስለኝም ፡፡ እውነቱን ለመናገር
እኔም የሮሐ ነገር ምቾት ነስቶኝ ነበር፡፡

እስተዳደጓ ይሁን አልያም ተፈጥሮዋ፣ ሮሐ ፍርሃት የሚባል ነገር ያልፈጠረባት ልጅ ነበረች፡፡ ከልክ ያለፈ ነጻነቷም በመሸማቀቅ ጭብጦ ላከልነው ለእኔና መሐሪ በቀላሉ የሚለመድ ነገር አልሆን ብሎ ተቸግረን ነበር፡፡ መሐሪ ወላጆቹ ባሉበት ሮሐን ፈጽሞ አጠገቡ እንድትቀመጥ አይፈልግም፡፡ ሮሐ ደግሞ ጎኑ ከመቀመጥ አልፋ ክንዱን ትከሻው
ላይ ጣል ታደርጋለች፡፡ ጋሽ ዝናቡ ፊት ጭምር እንደዚያ ታደርጋለች፡፡ መሐሪ ታዲያ ክንዷ ባረፈበት ቁጥር፣ ዝንብ እንዳረፈበት ፈረስ ሰውነቱን እያነዘረ ክንዷን ሊያባርረው ይታገላል፡፡ አቤት ያ ትዕይንት እንዴት እንደሚያዝናናኝ፡፡

አንድ ቀን ማትሪክ ወስደን ዕረፍት ላይ በነበርንበት ሰሞን፣ ሮሐ እነመሐሪ ቤት መጥታ ሰብሰብ ብለን እናወራለን፡፡ ልክ እንደ ጓደኛዋ ነበር ጋሽ ዝናቡን የምታወራው፡ስትጠራው ሁሉ “አንተ” እያለች ነው፡፡ ድንገት “ጋሺ ማሚ ጋር እንዴት ተገናኛችሁ ግን አለችው፡፡ እንዲሁ አለችው፡፡ እኔና መሐሪ ተሳቀን ልንሞት፡፡ መሐሪ በቀስታ አመልካች ጣቱን ከጆሮው በላይ ራሱ ላይ ሰክቶ እንደቡለን መፍቻ እያዞረ አሳየኝ፣ የማታል እንዴ?” ማለቱ ነበር: ትከሻዬን ሽቅብ ሰበቅኩና ሳቄን አፍኜ ዝም አልኩ፡፡ ተነሽና ከዚህ ቤት ውጭ ቢላትስ እያልኩ ሳስብም ነበር: ጋሽ ዝናቡ ግን፣ ከት ከት ብሎ ስቆ ራሷ ትንገርሽ እኔ እርጅናው ነው መሰል ነገር እየረሳሁ ነው? አላት

በእነዚያ ወራት ያ በጋሽ ዝናቡ የቁጣ መንፈስ የተሞላ ሰፊ ግቢ፣ የጥሩ ቤተሰብ ድባብ አርብቦበት ነበር፡፡ የተቋጠረው የጋሸ ፊት እነመሐሪ ግቢ እንደልጅ ተንቀባራ ባደገችው
ሳሌም የልጅነት ቡረቃ ተፈቶ ዘና ሲል አይቸዋለሁ በሮሐ ግዴለሽ ወሬ ሳይወድ በግዱ የተለጎመ አፉ ተፈቶ ሲያወራ ታዝቢያለሁ! “ጋሼ ይኼኮ በቃ የሥራ ጐዳይ ነው አጋጣሚ ነው …ለምን ከአባባ ጋር አትታረቁም ትለዋለች፡፡ ጋሽ ዝናቡ እየሳቀ አባትሽ ከሕግ ጋር እንጂ መች ከእኔ ጋር ተጣላ” ይላታል።

“ዋትኤቨር ብትታረቁ ይሻላችኋል …እዚች ጠባብ ከተማ ውስጥ በተገናኛቹ ቁጥር
ከምትገለማመጡ፡፡ ጋሽ እያያት ይስቃል፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ጋሽ ለእኔና መሐሪ ሮሐ
ጥሩ ልብ ያላት ልጅ ናት፤እንዳታስቀይሟት ብሎን አረፈው፡፡ መሐሪስ እሽ፣ እኔ ምን
ቤት ነኝ እያልኩ ተገረምኩ፡፡ አድናቆቱ ወደማሚም ተጋብቶባት ነበር ሮሐዬ ድንጋይ የምታናግር ተጨዋች አሉ እንጅ የኛ ዝጎት፣ ማልጎምጎም ብቻ፤ ወይ ፈታ ብለው አያወሩ " አለች ወደኔና መሐሬ እያየች፡፡ ሮሐ ታዲያ ኧረ ጋሽ እንደምታካብዱት አይደለም፣ ደስ የሚል ፈታ ያለ ሰው ነው ትለናለች! እኔና መሐሪ በአንድ አፍ ያልተያዘ … ብለን እንሳሳቃለን:: የዚያ ሰሞን የአስራ ሁለተኛ ክፍል የአማርኛ። ላይ የነበረ ጥያቄን እያስታወስን፡

ጥያቄ ቁጥር 7. ያልተያዘ.........
ሀ መያዝ አለበት

ሊ ግልግል ያውቃል

ሔ መያዙ አይቀርም

መ. ሁሉም መልስ ነው፡፡ ይች 'ለ' የሆነች ልጅ ጋሽ ዝናቡን “ዘና ያለ ሰው ነው” አለችን።

የዚያ አዚማም ግቢ ሌላዋ ድምቀት ሳሌም ነበረች፡፡ ማሚና ጋሽ ዝናቡ አንድ መሐሪን ብቻ ወልደው የረሱትን የልጅ ሳቅ እንደገና እያስታወስች፣ በትዝታ የምታነጉዳቸው ውብ ፍጥረት። ግቢው ውስጥ ቢራቢሮዎችን ተከትላ ስትቦርቅ ጋሽ ዝናቡ የሚወዛወዝ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ በፈገግታ ይመለከታታል ማሚ ብቅ እያለች ቀስ እንዳትወድቂ
ቃቢዳ ትላታለች፡፡ ቃቢዳ ነበር የምትላት፡፡ ሳሌም የምትበላው ከመሐሪ ፣
የምትቀመጠው ከመሐሪ ጋር፣ የመሐሪ ነገር ሞቷ ነበር፡፡ እኔና መሐሪ የአሥራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስንወስድ ፈረንጆቹ ቤት” በተቋቋመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሆና ነበር…ሰማያዊ አጭር ባለማንገቻ ቀሚስ፣ ጉልበቷ ድረስ የሚደርሰ ነጭ ካልሲ ለብሳ፣ ገና በዚያ ዕድሜዋ ወገቧ ላይ የደረሰ ጥቁር
ጸጉሯ ቁጥርጥር ተሠርቶና ጫፉ ላይ በቀይ ቢራቢሮ ቅርፅ ባላት የፀረር ማስያዣ ተይዞላት(ማሚ ነበረች ብዙ ጊዜ የምትስሠራት) ቀተራመደች ቁጥር እንደ ጅራት እየተወዛወዘ፣ ስትሄድና ስትመጣ እስካሁን ዓይኔ ላይ አለች፡፡

እስከ ዛሬ እንደ ሳሌም ዓይነት ቆንጆ ሕፃን አይቼ አላውቅም፤ ስለምወዳትም እንደሆን እንጃ፡፡ በዚያ ላይ አፏ ዝም የማይል ፈጣንና ወሬኛ ነበረች፡፡ ስታድግ ምኞቷ ዶክተር መሆንና መሐሪን ማግባት እንደሆነ ለማሚ ነግራታለች፡፡ ካቶሊኮች ትምህር ቤት ከገባች በኋላ ግን፣ ምኞቶቿ ወደ ሦስት ከፍ ብለው ነበር ዶክተር መሆን ፣መሐሪን ማግባትና የካቶሊክ መነኩሌ መሆን፡፡ ሮሐ ይኼን ስትሰማ እየሳቀች “ይች ካሁኑ ቁልት ያደረጋት
ልጅ መሐሪን ማሚ እንኳን እንደሷ የት ወጣህ? የት ገባህ? አትለውምኮ እኔን ስታይ እንዴት ፊቷ እንሚቀያየር ትላለች፡፡

አረ ሕጻን አይደለችም እንዴ! ምን ታውቃለች? ይላል መሐሪ።
አንዳንዴ ሮሐና ሳሌም ይከራከራሉ …ሮሐ ድምፅዋን ቀንሳ (ማሚ እንዳትሰማት)
ሳሌም፣ መሐሪ የኔ ባል ነው፣ ይዤው እሄዳለሁ እሺ?” ትላታለች።

ኧረ ባክሽ! የኔ ባል ነው …ብትፈልጊ ሌላ ሰው አግቢ”

ሌላ ሰው የለም

“ይኼው አብርሽን አግቢ” ትልና ወደ እኔ ትጠቁማታለች በሐፍረት ዓይኔን የማሳርፈበት ይጠፋኛል፡፡ ሮሐ እንደ ቀልድ በጀመረችው ክርክር እንደ ትልቅ ሰው በሳሌም ትበሳጫለች፡፡

አንቺ ሕፃን ነሽ …ባል ምን ያደርግልሻል?” ትላታለች ፍጥጥ ብላ፡፡

ያስጠናኛል፣ የቤት ሥራ ይሠራልኛል፣ኬክ ይገዛልኛል .…አንችስ ባል ምን ያደርግልሻል?” ይች ሕፃን አይደለችም ትላለች ሮሒ

"ቅድም ሕፃን ነሽ አላልሽም? …ሂሂሂ”
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስር


#በአሌክስ_አብርሃም

ከቤታችን እስከዚህ ግቢ በተዘረጋችው
አቧራማ መንገድ ላይ የታተሙት የጫማዬ ዳናዎች ቢቀጣጠሉ ሰው አልረገጣቸውም ብለው ካስተማሩን ፕላኔቶች አንዱን ነክተው በተመለሱ፤ ግን ከመንገዱ ይልቅ ልቤ ላይ ነበር እያንዳንዱ እርምጃዬ በጋለ ብረት ማኅተሙን የተወው፡፡

ጋሽ ዝናቡ በደስታ ሁለት እጆቹን በሰፊው ዘርግቶ እፊቱ ያገኛትን ማሚን ቢያቅፋት (አፈሳት ቢባል ይሻላል) በቁሟ እጥፍጥፍ ብላ እንደ ከረባት በሰፊው ደረቱ ላይ ተቀመጠች፡፡በዚያ ሰዓት እፊቱ የኤሌክትሪክ ምሰሶም ቢያገኝ የሚያቅፈው ይመስለኛል።
መሐሪን አቅፎ ግንባሩን ጸጉሩን ሳመው::መሐሪን እንዳቀፈው እኔንም ጎትቶ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምታሳድር ዶሮ ግራና ቀኝ አቅፎ ሰፊ ደረቱ ላይ ለጠፈን፡፡ በረዥሙ ተንፍሶ ለቀቀንና ትክ ብሎ እያየን፣ ልክ ሴቶች እንደሚያለቅሱ ጠይም ፊቱ ላይ እንባው
ድንገት እየፈሰስ ችፍርግ ባለዉ ፂሙ መሃል ሰረገ፡፡ መሐረሙን አውጥቶ ዓይኑን
ጢረገና፣ ሶሪ ብሉን ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ማሚ እንደ ፎካሪ ሳሎኑ ውስጥ እየተንራደደች ደጋግማ በየተራ ጉንጫችንን አገላብጣ እየሳመች “የኔ አንበሶች እንዲህ ነዋ! እንደ ዛሬም
ኮርቼ አላውቅ ትላለች፡፡

ጋሽ ዝናቡ ፊቱ በደስታ እንደተጥለቀለቀ ተመልሶ መጣና “ሮሐ እንዴት ሆነች?” አለ ስሪ ፖይት ቱ አለ መሐሪ፡፡

እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት …ዋናው ያችን በር አልፎ ሙግባቱ ነው

የማትሪክ ውጤት ተነግሮ ነበር፡፡ እኔም መሐሪም አራት ነጥብ አምጥተን ዩኒቨርስቲ እንኳን የረገጠ ተማሪ በሌለበት ሰፈር ታሪክ ተባለልን፡፡ ገድላችን ከላይ እስከታች ተወራ፡፡ ጠባብ ከተማችን ሐውልት አታቆምልን ነገር ቸገራት እንጂ ስማችን አየሩን ሞላው እነዚያ መንትያ የሚመስሉት ልጆች ነቀነቁት” ተባለ፡፡ ይኼ የዳኛው የዝናቡ ልጅ እና በቀደም ቆርቆሮ ሲጠግን ከጣራ ላይ የወደቀው አናጢ ልጅ፣ ሁለቱም አራት ነጥብ
(እባቴ ከአስራ አምስት ቀን በፊት ከመሰላል ላይ ወድቆ እግሩን ወለም ብሎት እቤት ውሎ ነበር፡፡ ይኼም ወሬ ሁኖ ምልክት ሆነ)
መሐሪ ጋር ተያይዘን ወደ እኛ ቤት ሄድን፡፡ እቤት ስንደርስ፣ እናቴ ደስ ብሏት በእልልታ
ተቀበለችን፡፡ ቀድማ ሰምታ ነበር፡፡ ወሬው ቀድሞን ነበር፡፡ አገላብጣ ስማን ስታበቃ
ወደኔ ዞር ብላ ታዲያ አሁን ዩንበርስቲ ሌላ አገር ልትሄድ ነው? ብላ ጠየቀችኝ፡፡
ድምፅዋ ውስጥ እንባ የሚያቀባብል ሊተኮስ የተዘጋጀ ለቅሶ ነበር፡፡ አባቴ ጋደም ባለበት ና ሳመኝ ና የኔ ግስላ! …” ብሎ ሳመኝ፡፡(መሐሪ ከዚያች ቀን በኋላ ለሳምንት ግስላው እያለ ያበሽቀኝ ነበር፡፡ አባባ ታዲያ እየሳመኝ እዚያው ላይ እቁቡን ተቀብሎ ስለሚገዛልኝ ምን የመሰለ ልብስ” ነገረኝ፡፡ እናም በዚያው የዕቁብ ወሬ ሊጀምር ዳር ዳር ሲል፣ እናቴ
ገስጻ ወደ እኔ ውጤት መለሰችው፡፡ አይ አባባ! በጣም እኮ ነው የምወደው እንደው ዩኒቨርስቲ ስለ ዕቁብ የሚያጠና ራሱን የቻለ የትምህርት ክፍል በኖረና፤ አጥንቼ በከተማችን ትልቁን እቁብ በመሠረትኩለት እስከምል፣ በጣም ነው የምወደው አባባን፡፡ በምድር ላይ ተስፋ የሚያደርገው ብቸኛ ነገር ቢኖር ዕቁብ ነው! ልጀ ተምሮ ይጦረኛል የሚል ተስፋ እንኳን ያለው አይመስለኝም!! አሁን ራሱ ልጅህ አራት ነጥብ አመጣ ከሚለው ዜና ይልቅ፤ ልጅህ ዕቁብ ደረስው ቢሳል፣ የእግሩን ወለምታ ረስቶ ዘሎ ሳይቆም
ይቀራል? …እባባና ዕቁብ !

ውጤታችንን ስለማን ልክ በአስራ አምስተኛ ቀኑ፣ ማሚና ጋሽ ዝናቡ ድል ያለ ድግስ ደግሰው፣ ከመንደሩ ሰው እስከ ትምህርት ቤት አስተማሪዎቻችን ጓደኞቻችን ድረስ ጠሩ፡፡ ከተማው ውስጥ ያለ ጠበቃና ዳኛም አልቀረም፡፡ እንዲያውም ጋሽ ዝናቡ ሮሐን
እንዲህ አላት እሽ ካለና ከመጣ ለአባትሽ ይኼን መጥሪያ ስጭው' ብሎ የሮሐ አባት እንዲገኝ ጥሪ ላከለት፡፡ “ቢመጣም ባይመጣም እኛ እንቀውጠዋለን አለች ሮሐ፡ ጋሸ ታዲያ ፈገግ ብሎ “ እብድ የሆንሽ ልጅ፤ ወይ መጥሪያውን መሰጠት እንዳትረሸ

እሰጠዋለሁ፣ ብቻ የፍርድ ቤት መጥሪያ መስሎት አባቴን ካገር እንዳታስጠፋው ጋሽ?”

“ሀሀሀሀሀሀሀሀ” ብሎ ሳቀ ጋሼ፡፡ ከዚያ በፊትም ከዚያ በኋላም እንደዚያ ሲስቅ
አላየሁትም፡፡

የድግሱ ቀን፣ ነጫጭ የፕላስቲክ ወንበሮች ግቢውን በመደዳ ሞልተው ሲታይ፣ የግቢው ጥርሶች ይመስሉ ነበር፡፡ ያ ፈዛዛ ግቢ የሚስቅ ዓይነት፡፡ በቤቱ በረንዳ ላይ ትልልቅ ድምፅ ማጉሊያዎች ግራና ቀኝ ቆመው ግቢው ላይ የሰፈረውን የዝምታ አጋንንት ሊያባርሩ ከባሕላዊ እስከ ዘመናዊ ዘፈን ይረጫሉ ከበረንዳው ሥር ተቀጣጥለው የተቀመጡና ነጭ ጨርቅ የለበሱ ረዣዥም ጠረጴዛዎች ላይ የተደረደረው ምግብ፣ እንኳን ቢበሉት እያነሱ ቢደፉት የሚያልቅ አይመስልም፡፡ ከጠረጴዛዎቹ እለፍ ብሎ በቀይ የፕላስቲክ ሳጥን በብዙ መደዳ ቢራ ተከምሯል ..

ጋሽ ዝናቡ እዲስ ጥቁር ሙሉ ልብስ ለብሶና፣ ጥቁር የቴክሳስ ባርኔጣውን አናቱ ላይ ደፍቶ፤ በእንግዶቹ መሀል እየዞረ፣ ብሉልኝ ጠቱልኝ ይላል፡፡ ማሚ በበኩሏ እንደዛን ቀን አምራ አይቻት አላውቅም ከወትሮው ረዘም ያለ ሹል ተረከዝ ያለው ደማቅ ቀይ ጫማ
ለረዥም ቅዱ ጉልበቷ ድረስ የሚዘልቅ ቀይ ቀሚስ ለብሳ በተጋባዥ መካከል
ትውረገረጋለች፡፡ ሰርግ ነበር የሚመስለው::ሳሌም ከኋላዋ ማሰሪያ ያላት ነጭ ቀሚስ ለብሳ እንደ ትንሽ ነጭ ቢራቢሮ በሰው መሀል እየተሸሎከለከች መሐሪ በሄደበት ትከተለዋለች፡፡ ማረፊያዋም መነሻዋም መሐሪ ነው፡፡ ሮሐ ታዲያ ዛሬ እንኳን ብትፋታው ምናለበት” ትላለች፡፡

ከሳምንት በፊት መሐሪ ማሚን “ይኼ ነገር ግን አልሰፋም” ብሏት ነበር፡፡ ለድግሱ ስትሯሯጥ፤ “ዝም በል ወደዛ! ይኼን የፈዘዘ ግቢ ምን ምክንያት አግኝቼ ባጫጫስኩበት ስል ነው የኖርኩት፣ ገና ስትዳሩ " ብላ የሁለታችንንም ትከሻ ቸብ አደረገችና ሂሂሂ እያለች ወደ ሥራዋ ተመለሰች፡፡ እንዳለችውም ከማጫጫስ አልፎ በምግብና በመጠጥ፣በዘፈንና በዳንስ ግቢው አበደ፡፡ በዚያ ምሽት የእኔና መሐሪ ስም እየተነሳ ጀብዷችን ሲወሳ አመሸ፡፡ ዕድሜ ከተጫጫናቸው የፊደል አስተማሪያችን ከመምሬ
ምስሉ ጀምሮ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል መምህራኖቻችን ድረስ “የቀለም ብልቃጥነታችንና ያነገይቱ ኢትዮጵያ በተስፋ የምትጠብቀን ወጣቶች መሆናችንን መሰከሩ፡፡ እንኳን እኛ
አጉል ወጣቶች፣ ዓለም ለምኔ ብሎ ለነፍሱ ያደረ ሰው እንኳን ቢሆን፣ በእንደዚህ ዓይነት አጋጣሚ ህዝብ ፊት ሲሞካሽና ሲደነቅ ሁለት ጭልፋ ኩራት፣ አንድ የሾርባ ማንኪያ መታበይና፣ ግማሽ የሻይ ማንኪያ ትዕቢት የተቀላቀለበት ፅንስ ልቡ ውስጥ መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ደረቴ ሲነፋፋ ይሰማኝ ነበር፡፡ እንዲያው ድንገት ትን ብሎኝ ብሞት፣ አገሪቱ
አብራኝ ድፍት ብላ የምትቀር፣ ከኔ ሌላ ሰው የሌላት መሰለኝ፡፡
ይባስ ብሎ በዚህ ስሜት ላይ ጋሽ ዝናቡ ሁለት የቢራ ጠርሙዞች ይዞ ወደኔና መሐሪ መጣና ደሽ ደሽ እያደረገ ከፍቶ ለዛሬ ብቻ ዋ!” ብሎ ከማስጠንቀቂያ ጋር ሰጥቶን እየሳቀ ሄደ፡፡ እኔም መሐሪም ከዚያ በፊት አልኮል ቀምሰን አናውቅም፡፡ የመጀመሪያችን ነበር፡፡
ሮሐ ጋሽ ዝናቡ ገና ከመሄዱ እንደመደነስ እያደረጋት መጣችና ሄይ ዐይኔ ነው ወይስ ጋሽ ዝናቡ ቢራ ሰጣችሁ” አለችን፡፡ ሁለታችንም ጠርሙዛችንን ከፍ አድርገን ችርስ አልናት፡፡ ፍልቅልቅ እያለች ጠብቁኝ አለችና፣ በሰው መካከል እየተሽለኮለከች ሂዳ ወዲያው ተመለሰች፡፡ ከላይ የምትደርበውን ጃኬት በእጇ ይዛ ነበር፡፡ አጠገባችን ደርሳ ለልጥ ስታደርገው ግን፣ አንድ ጠርሙዝ ውስኪ ነበር “ጋሼ እንዳያየን ደብቄውኮ ነው፣ እንቀምቅመው በቃ” ብላ ሳቀች

“ኖ” አለ መሐሪ
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

....ደግሞ ተጠርቶ ያልመጣው ማን አባቱ ስለሆነ ነው ?…የሱ አሮጌ ሆቴል እና አሮጌ ነዳጅ ማደያና …አሮጌ መኪናና
አሮጌ ምናምን የሚገርመኝ መሰለው እንዴ? መሐሪ ነኝ መሐሪ ዝናቡ አውላቸው .. ሐሳቡን ሳይጨርስ ወደ ሮሐ ዞሮ…
እንዲህ ለብሰሽ…ምን ለብሰሽ ተራቁተሸ የመጣሽው ሳይጨርሰው ጋሽ ዝናቡ ከየት እንደመጣ ሳላየው ድንገት ደርሶ የመሐሪን ክንድ አፈፍ እደረገውና ግማሽ መግፋት በተቀላቀለበት ማባበል ወደ ቤት ሊወስደው ሲሞክር ጭራሽ ወደ ጋሽ ዝናቡም ዙሮ፣

ጋሼ ቆይ አትግፉኝ፡ አሁን ሕፃን ልጅ አይደለሁም፤ የዚችን አባት ጠርተኸዋል አይደል? ማንን መናቁ ነው ያልመጣው እኛ የታሰረው በራሱ ጥፋት እንጅ ጋሼ መሐሪን እየገፋ ወደ ቤት ወሰደው፡፡ ሳሌም ተጨንቃ ከኋላ ከኋላቸው የመሐሪን ቲሸርት ይዛ ተከትላቸው ገባች ፡

ሮሐ ግራ በመጋባት ትንሽ ቆማ ሲገቡ አየቻቸውና ድንገት ፊቷን አዙራ ወደ ግቢው በር በቁጣ አመራች፡፡ የውስኪውን ጠርሙስ ግቢው ጥግ ችፍርግ ብለው ወደበቀሉት አበቦች ወርውራ፣ ከሩጫ በማይተናነስ እርምጃ ወደ ውጭ ስትገሰግስ ተከትያት ሮጥኩ፡፡
“ሮሐ! ትንሽ ጠጥቷል የሚናገረውን አያውቅም”

“እም ፋይን!” ዝም ብዬ ከጎኗ መራመድ ቀጤልኩ፡፡ ከግቢው እንደወጣን ኮረኮንቹ
አላራምዳት ስላለ፣ ጫማዋን አውልቃ በእጇ አንጠለጠለችውና በባዶ እግሯ መንገድ ጀመረች፡፡ ስትራመድ ትንሽ ትንገዳገድ ነበር፡፡ ብዙ ጠጥታለች፡፡ የተቀባችው ሽቶና ከሰውነቷ ላይ የሚተነው የአልኮል ሽታ ያፍናል፡፡ ምን እንደምላት ግራ እንደገባኝ ከንዷን
ያዝ አድርጌ አስቆምኳት፡፡ እንባዋ ተዘረገፈ !

“ስቱፒድ ነገር ነው!”

እሺ! ነገ ሁሉንም ነገር እንነጋገራለን፣ መንገዱ በጠርሙዝ ስብርባሪና በምናምን የተሞላ ነው፣ አሁን ከቤት የሆነ ጫማ ላምጣልሽ ፕሊስ”
አሁን ገና ያየችው ይመስል ወደ ባዶ
እግሯ አቀርቅራ ተመለከተች፣ የእግሮቿን ጣቶች አንቀሳቀሰቻቸው፡፡ አቧራማው ኮረኮንች ላይ አርፈው ግቢው አጥር ላይ በተተከለው ቀይ መብራት የደመቁት ውብ እግሮቿ፣ ደማቅ ቀይ የጥፍር ቀለም ከተቀቡ ረዥም ጣቶቿ ጋር፣ በብዙ ጭንቀት የተነሳ የሆነ የጥፍር ቀለም ማስታውቂያ ውብ ፎቶ እንጂ
ሕያው እግር አይመስሉም ነበር፡፡
ሳሎን ሶፋው ሥር ፍላት ጫማ አስቀምጨረ ነበር፡፡ ካላስቸገርኩህ አቀብለኝ?” አለችኝ፡፡
የቆመችበት ትቻት ወደ ግቢ ሮጥኩና ጫማውን ይዠ ስመለስ፣ ልክ የተተከለች ይመስል ሳትንቀሳቀስ እዛው ጋ ቁማ አገኘኋት፡፡ ጫማውን ለማድረግ አንድ እግሯን ስታነሳ፣ ክፉኛ ተንገዳገደች፡፡ በርከክ ብዬ በእጄ ትከሻዬን ተደግፋ የአንድ እግር ጫማዋን እንዳጠለኵላት፣ ሳቅ ስምቼ ዞርኩ፡፡ መሐሪ ነበር ከኋላው ሳሌም ተከትለዋለች፡፡

በማላጋጥ አጨበጨበ እና፣ ወገቡን በሁለት እጁ ይዞ ቁሞ፣ ባለጌ ጓደኛህ በደንብ ብልግናው እንዲጎላ እስከ መንበርከከ የሚደርስ ጨዋነት እያሳየህ ነው ….? ጥሩ ነው ምድረ ኢዲየት!' ሂድ እቤቷ አዝለህ አድርሳት! አባቷ ለሚድራት ሀብታም አዝለህ አድርስለት… አቃጣሪ” ብሎኝ ጀርባውን አዙሮ ወደግቢው ተመለሰ፡፡ ሳሌም ተከትላው ከሥር ከሥሩ ትሮጣለች፡፡

ለምን እንደሆነ ባይገባኝም፣ እስካሁን ያልተነቀለ ቅሬታ በዚያች ቅጽበት ልቤን ወግቶኝ ቀረ፡፡ ስካር ቀድሞ ውስጣችን የሌለ ነገር ይፈጥራል ወይ? ወይንስ ያለውን ነው የሚያጎላው? እያልኩ እብሰለሰላለሁ፡፡ ስካሩም ሳይሆን ይኼ የሴትና የወንድ ጉዳይም ሳይሆን፣ መሐሪ ድምፅ ውስጥ የሰማሁት ንቀት አመመኝ፡፡ ጨለማ ውስጥ አጭር ቀሚስ
የለበሰች ፍቅረኛው እግር ሥር ተንበርክኬ ጫማ ማጥለቄ በሄኖክ እንደቀናው
አላስቀናውም፡፡ (አውቀዋለሁ ሙሉ ዘመናችንን ጓደኞች ነን) እንደወንድ አይደለም ያየኝ እንደ አሽከር ነው እንደ አሽከር አይደለም… እንደ አቃጣሪና በመሃላቸው ክፍተት ለመፍጠር እንደምሞክር እኩይ ገፀባህሪ ዓይነት ነው ያየኝ፡፡ ለሆነ ሰው ሮሐን አዝዬ
አድራሽ፤ ድምፁ ውስጥ አንዳች ቦታዬን ደረጃዬን የሚጠቁም ትዕቢተኛ ቃና ነበር
ጓደኛ አልነበርንም!! ለሚያነክስ ሰው ምርኩዝ አብሮት ዘላለም ቢቆይ ጓደኛው ሆነ ማለት አይደለም፡፡ በመሐሪ የተጎዳ ሥነ ልቦናውን እደግፍ ዘንድ፣ ምርኩዙ ሆኜ የኖርኩ ሰው ነበርኩ፡፡ ፍቅረኛው ግኡዝ ምርኩዙን ነው ተደግፋ ያገኛት፤ ሰክሮ ነው ብዬ ማድበስበስ እልቻልኩም፡፡

ሁለቱም አስጠሉኝ፡፡ ሮሐም መሐሪም መሀል መንገድ ላይ ጥያት መመለስ ግን
አልፈለኩም፡፡ ሁልጊዜ የምንሸኝባት ቦታ ግዙፉ ባለ ሁለት ፎቅ ቤታቸው ፊት ለፊት
ያለች አሳቻ ጨለማ ድረስ ሸኝቻት ልመለስ ስል፣ ክንዴን ይዛ ወደ ራሷ
ሳበችኝና፣ አቅፋ ጉንጨን ሳመችኝ! አሳሳሟ ድምፅ፣ ሙቀትና ኃይል ያለው ነበር፡፡ ልክ ማኅተም ወረቀት ላይ እንደሚመታው ዓይነት ነበር ከንፈሮቿ ከጉንጬ ጋር የተጋጩት፡፡ ምናልባት
ስለሰከረች ሚዛኗን መጠበቅ አቅቷትም እንደሆን እንጃ፡፡ ስመለስ ወደነመሐሪ ቤት
አልገባሁም …ጭፈራና ጩኸት ከውስጥ ይሰማል፡፡ እንደዋልኩበት ቤት ሳይሆን ልክ እንደማላውቀው ምንድነው እዚህ ግቢ ውስጥ ዛሬ ያለው? ብሎ እንደሚያልፍ መንገደኛ አልፌ ወደ ቤቴ ሄድኩ፡፡ ገና ትላንት መሐሪ እዚሁ ነው የምታድረው፣ እቤት ንገራቸው ብሎኝ ስለነበር እንደማድር ለእናቴ ነግሪያት ነበር፡፡

በነገራችን ላይ ስደርስ፣ ቆሜ ወደ ሰማይ አንጋጠጥኩ፡፡ ሰማዩ የዘመናት ጥላሸት ተሸክሞ እንደ ረገበ አሮጌ የማዳበሪያ ኮርኒስ የተቆዘረ ዥንጉርጉር ሆዱን አንጠልጥሎታል! አልፎ አልፎ ከሚያስተጋባው ጉርምርምታ ጋር ተዳምሮ አንዳች እንግዳ ፍጡር ሊወልድ
የሚያምጥ ነፍሰጡር ፍጥረት ይመስል ነበር! “አህያ የማይችለው ዝናብ መጣ ይላሉ በመንገዱ ከሚያልፉ ሰዎች መሃል አንዲት አሮጊት፣ ጨለማው ከባድ ስለነበር
ከቆምኩበት ሁኜ ሰዎቹ የለበሱት ነጠላ በድንግዝግዙ ሲንቀሳቀስ እንጂ መልካቸውን ማየት አልችልም ነበር፡፡ እንደገና ወደ ሰማይ ፊቴን አንጋጠጥኩ፡፡ ደመናው በሆነ ሹል ነገር ወጋ ቢያደርጉት፣ ውሃ ሳይሆን ጥላሸት የሚያዘንብ ነበር የሚመስለው !
ወደ ቤት ገባሁ፡፡ እናቴ ለአባባ ስለ ድግሱ ድምቀት እያወራችለት ነበር፡፡ እግሩን ክፉኛ ስለታመመ አልሄደም፡፡ ከፊቱ ማሚ ቋጥራ የላከችለት የድግስ ምግብ ከትልቅ ጎድጓዳ ሰሃን ላይ ተቀንሶ ቀርቦለት አልጋው ላይ ደገፍ እንዳለ ይበላል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ድህነት የሚባለው ነገር እንደሳትራት በቤታችን ፈዛዛ አምፖል ዙሪያ ሲበርና ትርኪምርኪው የቤት
እቃ ላይ ሲያርፍ ታየኝ፡፡ ልክ ያጠለቁበትን ጥቁር ጭንብል የማያውቀው ቦታ ወስደው ድንገትም እንዳነሱለት ሰው ነበር የቤታችንን ዙሪያ የቃኘሁት፡፡ እንዳላደግሁለት፣ ዛሬ ገና እንዳየሁት ዓይነት፡፡ እናቴ ታዲያ እንዲህ አለችኝ፣
“ውይ መጣህ እንዴ የምታድር መስሎኝ ደሞ ጉንጭህ ላይ የምን ቀለም ነው?” በመዳፌ ጠረኩት …የሮሐ ሊፕስቲክ ነበር፡፡ ወደ መኝታዬ አልፌ ከነልብሴ አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ዘፍ አልኩና፣ ተንጋልዬ ተኛሁ፡፡ ከሁለቱ ክፍሎች የውስጠኛዋ ላይ የተዘረጋች የሽቦ
አልጋ ናት መኝታዬ፡፡ በሁለቱ ክፍሎች መግቢያ በር ላይ አንዲት ያደፈች የጨርቅ
መጋረጃ ተሰቅላለች፡፡ ዙሪያ ግርግዳው ላይ መጥበሻው፣ ድስቱ፣ የበረት ምጣዱ፣
ሰፌዱ፣ ወደ አንድ ጥግ የተቀመጠ የእንጀራ ሞሰብ፣ ግድግዳው ጋር ተጣብቆ በተሰራው የጣውላ መደርደሪያ ላይ ስኒዎት፣ ጀበና፣ ብርጭቆ ተደርድሯል፡፡ እዚያ ፊት ለፊት
ደግሞ የአባቴ የአናጺነት እቃዎች የታጨቁበት ትልቅ የቆዳ ከረጢት፡፡ እና እዚህ ሁሉ መሀል እኔ …! እኔ ውስጥ አልቅስ አልቅስ የሚል፣ እንደቀመስኩት ቢራ የሚጎመዝዝ ስሜት!!
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

ከግቢው ውስጥ የጥድቄ ለቅሶ የቀላቀለ ጩኸት ይሰማል፡፡ የሆኑ ወንዶች የጎረነነና
የተጣደፈ ድምፅም ይሰማል፤ የሚያወሩት ግን አይሰማም ነበር፡፡ ወዲያው አንዲት አምቡላንስ ሳይነሯን እያሸች መጥታ ልክ ማታ እኔና ሮሐ ቆመንበት በነበረው ቦታ ላይ ስትደርስ ቆመች፣ ሁለት ሠራተኞች ከኋላ ቃሬዛ አውጥተው ወደግቢው በር
ተጠግተው ቆሙ:: ቃሬዛውን ሳይ እንደሐሞት የመረረ ፈሳሽ በአፍና በአፍንጫየ ሊወጣ ሲተናነቀኝ ይሰማኝ ነበር፡፡ አምቡላንሱ መኪና አናት ላይ የሚሽከረከረው ደማቅ ቀይ መብራት፡ ከነጭ ሰሀን ላይ እየጨለፈ አካባቢው ላይ ደም የሚረጭ አንዳች ነገር
ይመስል ነበር፡፡ የመኪናው የፊት መብራት የፈጠረው ረዣዥም የሰዎች ጥላ ወዳቦ
ወዲህ ሲንቀሳቀስ አስፈሪ ሕልም ይመስላል፡፡ ጋሽ ዝናቡ ማሚን አንድ ነገር እንዳደረጋት አልተጠራጠርኩም፡፡

እንዱ ፖሊስ የግቢውን በር እንጓጉቶ አምቡላንስ መጥቷል” ብሎ ጮኸ፡፡ ወዲያው በሩ ተከፍቶ፣ አንድ የሰፈራችን ልጅ በወጠምሻ ከንዶቹ ጋቢ የለበሰ ሰው አንከብክቦ አቅፎ መጣ፡፡ ገና ከላይ ከደረቡላት ጋቢ ወጥቶ የተንጠለጠለ ጸጉሯን ሳይ ብርክ ያዘኝ፡፡ ሳሌም
ነበረች፡፡ ከአንገቷ ጀምሮ በጋቢ ተሸፍናለች፡፡ እየጮኸች እና እጁን እያወራጨት ታለቅሳለች::ቃሬዛ ላይ አስተኝተውና የሚወራጭ እጅና እግሯን ይዘው፣ ወደአምቡላንሱ ይዘዋት ሮጡ፡፡ ወዲያው ጥድቄ ተከትላ ወጣች፡፡ ግቢው በር ላይ ድፍት ብላ በቁሟ ወድቃ ፌቷን እየነጨች ኡኡ ትል ጀመር፡፡

አገር ፍረደኝ: አንዲት ፍሬ ልጅ ጉድ ሠሩኝ ኡኡኡኡ " በጩኸት ብዛት ድምፅዋ
ጎርንኖ በየመሀሉ ሹክሹክታ ይሆናል፡፡ “
ጉድ ሠሩኝ ጉድ ሰሩኝ ይኼ ምን ዕድል
ነው ምን ጭካኔ ነው? ተሰምቶ ያቃል ወይ? በሰው ደርሶ ያውቃል ወይ? ፊቷን
በሁለቱም በኩል ከዓይኖቿ በታች ክፉኛ ተልትላው ይደማል፡፡ የደም እምባ የሚፈስስት ነብር የሚመስለው፡፡ የሰፈሩ ሴቶች አብረዋት ኡኡ ሲሉ፣ ትኩስ ሬሳ የወጣበት ቤት መሰለ፡፡ሰዎች ክንዷን ይዘው ከወደቀችበት ሊያነሷት ሲሞከሩ፣መሬቱ ላይ ተንከባለለች፡፡
ቀሚሷ ተገላልቦ ሰውነቷ ሲጋላጥ፣ እንዲት ሴትዮ ነጠላቸውን ከራሳቸው ትከሻ ላይ ገፈው ሊሸፍኗት ሞከሩ፣ ግን እልሆነላቸውም፡፡ በዛ ያሉ ሰዎች አፋፍሰው እዚያው አምቡላንሱ ውስጥ አስገቧት፡፡ የአምቡላንሱ በር ከመዘጋቱ በፊት ጥድቄ እንዲህ እያለች ትጮህ ነበር
“በሳሌም? በሳሌም?… በሳሌም? በእህትህ መሐሪ በላሌም? እኮ በሳሌም? በእህትህ ጨክነህ መሐሪ ….በሳሌም? በሳሌ.. በሩ ጓ ብሎ ሲዘጋ ድምጿ ቆመ፡፡ ፍዝዝ ብዬ እንደቆምኩ የግቢው በር እንደገና ተከፍቶ ሁለት ፖሊሶች መሐሪን መሃላቸው አድርገው ይዘውት ወጡ፡፡ እጁ በካቴና ወደፊት ታስሮ ነበር፡፡ ክንድና ክንዱን ይዘው እንዳተኝ ሳብ አደረጉት፡፡ እንዳቀረቀረ ፍጥነቱን ጨምሮ፣ ቶሎ ቶሎ ተራመደ፡፡ ማሚ ቀን ለብሳው በዋለችው ቀሚስ ላይ ነጠላ እንደደረበች ተከትላው ከኋላ ከኋላ ትሮጣለች፡፡
ፖሊሶቹ እንደከበቡት ወደ ዋናው መንገድ በሚወስደው ጨለም ያለ ኮረኮች በኩል፣
እያጣደፉ ይዘውት ሄዱ፡፡ ሕዝቡ ግር ብሎ ተከትሎ ወደፖሊስ ጣቢያ ተመመ
በቆምኩበት ከእግሬ ጀምሮ ወደላይ ሰውነቴ እየደነዘዘ ሲሄድ ይታወቀኝ ነበር።
የተሰበሰበው ሰው ይሳደባል፣ ይራገማል፣ ግማሹ ቀን ድግሱ ላይ ሲመርቅ ሲያመሰግን የዋለ ነው፡፡

ግራ ግብት እንዳለኝ፣ አንድ ድምፁ እንደ ጣውላ መሰንጠቂያ ማሽን የሚጮህ ሰው “ይኼም ጓደኛው ነው!” ብሎ ከኋላ ጀርባዬን በከዘራው ጫፍ ወጋ አደረገኝ፡፡
የሚጠዘጥዝ መጠርቆስ ነበር፤ ዞር አልኩና ባለ በሌለ ኃይሌ የከዘራውን ጫፍ ይዠ ወደኔ ሳብኩት፣ እየተንገዳገደ ሲጠጋኝ በጥፊ አቃጠልኩት፡ትልቅ ሰው ነበር፤ ግድ አልሰጠኝም፡፡ የተሰበስቡት ሰዎች እግር ሥር እንደ ትል ጥቅልል ብሎ ወድቆ በህግ አምላክ” እያለ ሲጮህ እዚያው ልረጋግጠው ፈልጌ ነበር፡፡ ከየት እንደመጣች እንጂ፣ እናቴ ክንዴን ይዛ ስትጎትተኝ ወደኋላዬ ተመለስኩ፡፡ እየጎተተችኝ ወደ ቤት ስትገሰግስ
ልክ እንደለማዳ በግ በዝምታ ተከተልኳት፡፡ እቤት ስንደርስ፣ እናቴ ተንጠራርታ ጥብቅ
አድርጋ አቀፈችኝና፣ አለቀሰች፡፡ እኔም እየተነፋረቅሁ መሆኑ የገባኝ፣ እንባዬን
ስትጠርግልኝ ነበር!

“ምንድነው” ይላል አባቴ የእግሩ ወለምታ ስላላስኬደው እዚያው እተኛበት ሆኖ
የሆነውን ለመስማት ጓጉቷል፡፡ “ምንድነው? አትናገሩም እንዴ?”

“ምንም አይደል አንተ ደግሞ ዝም ብለህ ተኛ

ምን እተኛለሁ ...ን ከፍተሸብኝ ሂደሽ፣ ንፋስ ገባ መሰለኝ ይኼው ደህና የተሻለኝን እግሬን እየጠዘጠዘኝ ነው!”

ቆም ብዬ አባቴን እየሁትና “እና ቢጠዘጥዝህ ትሞታለህ”አልኩት

እ...አለ ደንግጦ፡፡

ወደ ውስጥ ገብቼ አልጋ ላይ በፊቴ ተደፍቼ ተኛሁ፡፡ ምንም ነገር አልገባኝም፣ ምንም ነገር አላሰብኩም፡፡ አንድ ነገር ብቻ፣ እግዚአብሔርን መሆነ ሰዓቶቹን ወደኋላ መመለስ! ብዙ አይደለም፣ በቃ
እንድ አምስት ሰዓቶች ብቻ ወደኋላ መመለስ:: እግዚአብሔር ይችን ቢያደርግ ምን ይጎዳል? ምናልባት የሆነ ነገር ከአምስት ሰዓት በፊት ሎተሪ የደረሰው ደሃ፣ መልሶ ወደ ለመደው ድህነት ቢመለስ ነው! ድህነት ወንጀል
አይደል፣ ቢበዛ በድስትና በሰሃን በተከበበች ምኝታ ቤት ቢተኛ ነው …ምናለበት … ይችን ብቻ ይችን ብቻ!! ድንገት ቀን ስበላው የዋልኩት በቅመም ያበደ ቀይ ወጥና አልጫ ሆዴ ውስጥ እንደ ማዕበል ተገለባብጦ፤ ወደ ጉሮሮዬ ሊወነጨፍ፣ ከአልጋዬ። ዘልዬ ተነሳሁ፡፡ ዘግይቼ ነበር፤ ከአልጋዬ ሥር ባለው ላስቲክ በተነጠፈበት ወለል ላይ
ትውከቴን ለቀኩት !

“ልጄን! ልጄን እያለች እናቴ ወደ እኔ ስትሮጥ ይሰማኛል …ቀለል አለኝ !

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

"ልጄን! ልጄን እያለች እናቴ ወደ እኔ
ስትሮጥ ይሰማኛል …ቀለል አለኝ !
።።።።
ለድፍን አንድ ሳምንት ከቤቴ ሳልወጣ አሳለፍኩ፤ ከእሁድ እስከ እሁድ፡፡ ምን እኔ ብቻ፣ ከዚያች ምሽት ጀምሮ እናቴ እንቅልፍ አልነበራትም፣ ለወትሮው ጧት ጧት ሳታዛንፍ የምትስመውን ቤተክርስቲያን ርግፍ አድርጋ ትታ፣ የእኔው ጠባቂ ሆና አብራኝ ታሰረች፡፡ እንኳን ከቤት ርቄ ልሄድ፣ ለሽንት እንኳን ከቤታችን ኋላ ወዳለው መፀዳጃ ቤት ደረስ ብዬ ለመመለስ አታምነኝም፡፡ ተከትላኝ ወጥታ በር ላይ ትቆማለች፡፡ ተጨንቃ ነበር፡፡
እውነት ነበራት ደግሞ፤ ድፍን ከተማው ሌላ ወሬ አልነበረውም፡፡ “የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛው የአቶ ዝናቡ ልጅ እቤታቸው ያስጠጓትን ምስኪን ሕፃን ልጅ ደፈረ…”

እግዚኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦ! ስምንተኛው ሺ!”

ጎረቤቱ ከላይ እስከታች በአንድ ጊዜ የነመሐሪን ቤተሰቦች ረጋሚ እና ዘላፊ ሆኖ ነበር፡፡
ይኼ ዘለፋ ታዲያ ባለፍ ገደም ወደኔም እንጥፍጣፊው መድረሱ አልቀረም፡፡ ያስገረመኝ የዚህ የጥላቻ ዘመቻ ዋና አራጋቢዎች ሰፈር ውስጥ ትምህርት እምቢ ያላቸው ልጆች መሆናቸው! እነሱም ብሎ ጎበዝ ተማሪም ይላሉ፡፡ መቼም መሐሪ ሲነሳ “እነሱ” ከተባለ
ያው አንዱ እኔው ነኝ፡፡ እስቲ አሁን ጉብዝናችን ላይ ምን ወስዶ አንጠላጠላቸው? በዚህ ሰበብ ጉብዝናችንን ካዱትም አልካዱትም ትምህርት ሚኒስተር መጽዋች ስለሆነ አይደለም አራት ነጥብ የሰጠን፡፡ ምን ያገናኘዋል? ሲያጨበጭቡልን እየተበሳጩ ነበር እንዴ ሰፈራችንን አስጠራችሁት ያሉት፣ ሰበብ አግኝተው እንደ ኦሪት መስዋዕት ከሰፈር አውጥተው ሊያቃጥሉን ነበር እንዴ? ግን ከተፈጠረው ነገር ይልቅ፣ የተበለጡትን መከረኛ ትምህርት እያነሱ፣ መሐሪንም እኔንም ሲያንቋሽሹ ነበር ውለው የሚያድሩት፡፡
አብሯቸው የኖረ የበታችነት እና የመብለጥ ስሜት፣ ሳሌም የምትባል መርፌ ስትወጋው እንደባሉን እየተነፈሰ ነበር ፡፡

አባባ እንደ ማንኛውም ቀን ፣ምንም እንዳልተፈጠረ፣ በነጠላ እራፊ የተጠመጠመ እግሩን በተደራረበ ትራስ ላይ አሳርፎ፣ (አስር ጊዜ ትራሱን አስተካክልልኝ እያለ)ስለእቁብ
ሲያወራ ይውላል፡፡ ይኼ ነገሩ ትንሽ ቢያሳዝነኝም፣ ከእናቴ ጭንቀት ይልቅ የእርሱ ግድ የለሽነት የተሻለ ያረጋጋኝ ስለነበር፣ ብዙውን ጊዜ የማሳልፈው ከአባባ ጋ በማውራት ነበር፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን የሆነ ነገር እንዲለኝ ፈልጌ ነበር፡፡ ቢያንስ አይዞህ እንዲለኝ፡፡
አይዞህ ብቻ፡፡ ምንም ቢያወራ ነገሬ ብዬ ከማልሰማው አባባ፣ አንድ ቃል ናፈቀኝ፡፡
አባትነት ልጅ በመውለድ ብቻ የሚመጣ ነገር እንዳልሆነ የገባኝ ያኔ ነው እየወደድኩት ውስጤ ያዝን ነበር፡፡ ነፍሱ ውስጥ እኔ የለሁም እላለሁ፡፡ ሩቅ
ሐገር ተፈጽሞ በዜና ቢሰማ እንኳን ስሜትን የሚረብሽ ነገር እዚህ አፍንጫው ሥር፣ ያውም ከወንድምም በሚቀርብ የልጁ ጓደኛ ተፈጽሞ ፣ ጎረቤቱ ሁሉ እየዛተና እየፎከረ - “ድሮውንም አንገት
ደፊ” በሚል ገደምዳሞሽ አሽሙር፣ በሌለሁበት እኔንም ጨምሮ እየቀጣኝ ምንም ስሜት ያልሰጠው አባት፣ እንዴት ዓይነት ተፈጥሮ ቢኖረው ነው!? እያልኩ እገረማለሁ፡፡

ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የእናቴን ጭንቀት ትንሽ እንኳ ቢካፈላት፣ ሌት ተቀን ልጇን ሊነጥቋት እንደከበቧት አራስ ነብር፣ ቁጣና ስጋት ከቧት ስትንቆራጠጥ፡ ኮሽ ባለ ቁጥር ብርክ ሲይዛትና፣ በበር ሽንቁር ወደውጭ እያጨነቆረች ስትመለከት፣ እይዞሽ ቢላት ምናለበት፣ እያልኩ አስባለሁ፡፡ ተኚ እኔ አለሁ ለምን አይላትም? እልናገረውም ግን
አስባለሁ፡፡ ምንም ይሁን አባት፣ ፈርጣማ ክንድ ባይኖረው እንኳ፣ ተስፋና ማጽናናት
እንዴት ይነጥፍበታል፡፡ “እንድ ሰው የልጄን ስም ያነሳና፣ ውርድ ከራሴ፣ እሱ ምን
ያርጋችሁ? እዚህ እንደ እንሽላሊት በየጥጋጥጉ እየሄዳችሁ የምታሽሟጥጡት” ቢል ምን
ይሆናል አንድ ቤት የምንኖር ሳይሆን፣ ታክሲ ፌርማታ ላይ ድንገት ተገናኝተን፣ ታክሲ እስከሚመጣ የምንጠብቅ መንገደኞች የሆንን እስኪመስለኝ ምንም የምንጋራው ስሜት አልነበረም፡፡ ቸልተኛ ነበር፤ እሽ ይሁን፡ ቸልተኝነቱን ትንሽ ወደ ምክር ቢለውጠው እና አይደል፤ አትስማቸው '' ችላ ብሎ ማለፍ ነው" ቢል፡፡

ገና እቤት መዋል በጀመርኩ በሦስተኛው ቀን፡ እናቴን እንዲህ እላት፡፡ “በመንደሩ ያለው ሰው የዝናቡ ልጅ ብቻ ነው እንዴ?…ይውጣና ኮመንደሩ ልጆች ጋር ንፋስ ተቀብሎ ይምጣ፤ እንግዲህ አንዴ የሆነው ሁኗል፡ የፈሰሰ ውሃ እይታፈስ!”፡፡ እንዴ የሆነው ሁኗል ማለት ምን ማለት ነው? እንዳትደግመው እንጂ የሆነው ሆኗል ነበር የሚመስለው አነጋገሩ፡፡ ከዚያ በፊት ችላ ብየው፣ አልያም ሳላስተውለው ቆይቼ የገረመኝ ነገር ደግሞ፣አባቴ መሐሪን በስሙ ጠርቶትም ሆነ ጓደኛህ” ብሎ አያቅም፡፡ “የዝናቡ ልጅ” ነው የሚለው፡፡ ለነገሩ አባባ፣ መሐሪን ብቻ ሳይሆን፣ ሕፃንም ይሁን ወጣት በስም
አይጠራም፡፡ የእከሌ ልጅ ነው የሚለው፡፡ ሴቶችን ሳይቀር “ይች የእከሌ ሚስት” ነው የሚለው፡፡

ይኼው አሁንም “የዝናቡ ልጅ ብቻ ነው ወይ በመንደሩ ያለው? ይለኛል፡፡እና በመንደሩ ማን አለ? …ከመሐሪ ሌላ ማን አለ? …መሐሪ ከሰፈር ልጆች እንዱ አልነበረምኮ መሐሪ ጓደኛ ብቻ አልነበረምኮ ከመኖር ብዛት የራሳችንን ቋንቋ የፈጠርን፣ ሁለት ሰዎች ውስጥ የተቀመጠች አንዲት ውብ ነፍስ የተጋራን ፍጥረቶች ነበርን፡፡ ቃል ሳንተነፍስ
ልባችን ውስጥ ያለውን ሐሳብ በአንድ የዓይን ጥቅሻ የምንካፈል፡፡ ትንሽ ዓለሜ
የቆመችው፣ ሁለት ምሰሶዎች ላይ ነበር፡፡ አንዱ እኔ ራሴ፣ አንዱ መሐሪ! ግማሽ እኔ እስር ቤት ውስጥ ነኝ ሚዛኗን ስታ እየተንገዳገደች ያለች ሚጢጢ ዓለሜን፣ ወደፊት መራመዱ ቢቀር፣ ቀጥ ብላ እንድትቆም እየታገልኩ ነበር፡፡ ለድጋፍ እጁን የሚሰጥ ሰው እንጂ፣ ግዴለም በአንድ እግርህ ውጣና፣ ሌላ እግር ፈልግ የሚል ሰው አልነበረም ፍላጎቴ! “ከሰፈር ልጆች ጋር ነፋስ ተቀበል” ይለኛል፡፡ እንኳን አብሬው ነፋስ የምቀበለው የሰፈር ልጅ፣ በመንደሩ ውስጥ ነፋስ አለ ወይ?… መንደሩስ ራሱ አለወይ … እቤቴ ቁጭ
ያልኩት (ምን ቁጭ ያልኩት የተደበኩት) እንደ ሕፃን ልጅ የራሴን ዓይን ስጨፍን
ከዓለም ሁሉ የተደበቅሁ መስሎ እየተሰማኝ፣ ለአፍታም ቢሆን እፎይታ ስለሚሰማኝ ነበር፡፡ በሆነው ሁሉ ከማፈሬ ብዛት የሰው ዓይን ፈርቼ ነበር፡፡
መሐሪ ሁለት ቀን ፖሊስ ጣቢያ ቆይቶ በሦስተኛው ቀን ፍርድ ቤት ቀረበ ተባለ፡፡ የዚያኑ ቀን ከሰዓት በኋላ፣ ወደ ትልቁ ማረሚያ ቤት እንደተወሰደ ሰማሁ፡፡ ይኼን ሲነግሩኝ፣ ያ አሮጌ የብረት በር እየተንሳጠጠ ከኋለው ሲከረቸምበት ታየኝ፡፡ ውስጤ ሂድ ሂድ ይለኛል፡፡ከስንት ዓመታት በፊት ያየሁት ማረሚያ ቤት ሲታወሰኝ፣ዘገነነኝ፡፡ የማቅለሽለሽ
ስሜትም ተሰማኝ፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ዝም ብሎ የማቅለሽለሽ ስሜት ቶሎ ቶሎ
ይሰማኛል፡፡ሳምንቱን ሙሉ እንደ ነፍሰጡር ምግብ ሲሸተኝ፣ ጧት ስነሳ ያቅለሸልሽኝ ነበር፡፡

ግንኮ እስከ ዛሬ ብዙ ነገር ይስተካከል ይሆናል” ብዬ እራሴን ለማጽናናት ሞከርኩ፡፡ለምሳሌ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ዘመናዊ የመዋኛ ገንዳ ተሠርቶ ሊሆን ይችላል (መሐሪ ዋኝቶ አያውቅም እንጂ ዋና ይወዳል፡፡ ስናድግ እቤቱ የመዋኛ ገንዳ ሊያስገባ ሐሳብ ነበረው) ምናልባት ምሳቸው በባልዲ የተቀዳ ወጥ ሳይሆን፣ ነጫጭ ልብስ በለበሱ ጠረጴዛዎች ላይ፣ በቆንጆ አስተናጋጆች በሸክላ ሰሀን የሚቀርብ ብዙ ዓይነት ምግብ ሊሆን ይችላል፡፡ በቅመም ያበደ ሻይም ከምሳ በኋላ ይቀርብላቸው ይሆናል። (መሐሪ
ከምሳ በኋላ እንደዚያ ዓይነት ሻይ ይወዳል) ከዚህ ሁሉ
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_አራት


#በአሌክስ_አብርሃም

“ወረተኛ ሁሉ! ያሳደግሽውን ልጅ እንደ ድመት ልትበይ አሰፍስፈሻል ና ውርርርር ድመት ሁሉ እያለ ይጮኻል፡፡ ጮኸ ብሎ ይጣራል አብርሃም …አይዞህ! እናስፈታዋለን! ድመት ሁሉ! ውርርርርር …የነገ ዶክተር ….የነገ ኢንጅነር …የነገ ጠቅላይ ሚንስትር ልትበይ አሰፍስፈሻል! …ውርርርርርር …ልጆቻችን ናቸው! …ውርርር! ደፋሪም ተደፋሪም ልጆቻችን ናቸው! ለሁለቱም ማልቀስ ነበር የሚበጀን ሁልጊዜ ማታ ጋሽ አዳሙን እጠብቅ ነበር፡፡ የተመሰከረለት ሰካራም ቢሆንም ቅሉ፣ በእውነት፣ እንደ ደግ አባት
የጨለማ ንግግሩ ይናፍቀኝ ነበር፡፡

ቤት ውስጥ በተቀመጥኩ ልክ በሳምንቱ፣ እሁድ ቀን እዚያ ታች ሰፈር የሚኖሩ ሁልጊዜ ከእናቴ ጋር ቤተክርስቲያን የሚገናኙ ሴትዮ፣ አንድም እናቴን ቤተክርስቲያ ስላላገኟት ለመጠየቅ፣ እግረመንገዳቸውንም አባባን ተሻለህ ወይ ለማለት፣ ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ
እቤታችን ጎራ አሉ፡፡ ገና እንደገቡ እኔን ሲያዩ አንተ አብርሃም እንዲያው ምን
ይሻላችኋል” ብለው አለፍ አሉና ተቀመጡ፡፡ ቡና ተፈልቶ ስለነበር (አቦል ረግጠውማ አይሄዱም) ተብለው ቁጭ አሉ፡፡ቡና እየጠጡ ያው የዚያን ሰሞኑን ወሬ ሲያወሩ ድንገት እናቱን ያየ ሰው ያች ቆንጆ ናት ወይ ያስብላል፣ ባንዴ አመዱን ነስንሶባታል አሉ፡፡ ጆሮዬ ቆመ፤ ስለመሐሪ እናት ስለማሚ ነበር የሚያውሩት፡፡

“ምን ታርግ፣ ይኼ መዓት እንኳን እሷን …" እናቴ ሳትጨርስ ተወችው፡፡

ትላንት ለልጁ ስንቅ ልታደርስ ወደ እስር ቤት ስትሄድ፣ እዚህ ኮረኮቹ ላይ ወደ
ፈረንጆቹ ቤት መገንጣያዋ ጋ፣ የተደበቁ ልጆች ድንጋይ ወርውረው መቷት አሉ፡፡

“ውይ ውይ ውይ የሚመታ ይምታቸው እቴ፣ ሰይጣኖች! እሷ ምናረገች፡፡ ሰው ቀና ብላ የማታይ ሴት፣ ምናረገች ይላሉ እሰቲ አሁን፣ ተጎዳች… ምኗን መቷት?” አለች እናቴ፡፡እንባ ተናንቋት ደረቷን እየደቃች ነበር፡፡

እንጃ ምኗን እንዳገኟት ምን እንደገፋኝ እንጃ ከተቀመጥኩበት ጥግ ተነስቼ በእናቴና በሴትዮዋ መሀል የተዘረጋውን ረከቦት ዘልዬ ወደነመሐሪ ቤት ከነፍኩ፡፡ የቆምኩት የግቢያቸው በር ላይ ስደርስ ነበር፡፡ በሩን ሳንኳካ ፊት ለፊት መንገዱን ተሻግሮ ያለ ግቢ በር ገርበብ ብሎ ተከፈተና፣ መዓዛ የምትባለው የጎረቤት ልጅ ብቅ ብላ አይታኝ፣ መገዱን ተሻግሮ እስኪሰማኝ ኤጭ!” ብላ በሩን ወርውራ ዘጋችው! መዓዛ እኔን አይታ
ኤጭ አለች፡ህ! …እኔና መሐሪን ባየች ቁጥር፣ ቀሚሷን እንደ ሰላም ባንዲራ
እያውለበለበች በዓይኗ ከሁለት አንዳችሁ ተኙኝ እያለች ስትማጸን የኖረች ከንቱ ናት!
ከንቱ ብቻ አልነበረችም፣ ደደብም ጭምር ነበረች፡፡ እኔ የሠራሁላት የቤት ሥራና
አሳይሜት ብቻ ቢቆጠር፣ ከሷ የበለጠ የሷን ትምህርት ተማርኩላት ያስብል ነበር፡፡ደደብ ብቻም አልነበረችም፡፡ ዓይናውጣ። ነገርም ነበረች፡፡ መሐሪን የቤት ሥራ ሥራልኝ ብላ እቤታቸው ሄዳ ልትስመው ሞክራ፡ ገፈታትሮ አስወጥቷት፡ እየሮጠ እኔ ጋ መጥቶ ነግሮኝነበር፡፡አሯሯጡ ራሱ ነፍሱን የሚያድ እንጅ ከንፈር የተቃጣባትን አይመስልም ነበር
ሁሉም የተናቀውን ያህል ሰበብ ፈልጎ ሊንቅ ሲያደባ የኖረ ነበር እንዴ? ውስጤ ተቆጣ ይኼ ሕዝብ ወንጀል አይጸየፍም እንዲያውም የጠላቸውን እና ቀን
የሚጠብቅላቸውን ሰዎች ማጥቂያ በረከት አድርጎ ነው የሚመለከተው።

“ማነው?” አለች ማሚ፡፡ ለዘመናት ሲጸልይ ቆይቶ፣ ፈጣሪ ከሰማይ ድምፁን እንዳሰማው አማኝ፡ ድምጿ ተአምር ነበር የሆነብኝ፡፡

"እኔ ነኝ ማሚ"

በሩን በፍጥነት ከፍታ፣ ሁለት እጆቿን እንደ ከንፍ እንደዘረጋች ተንደርድራ አቀፈችኝና፡
ደረቷ ላይ ለጥፋኝ ማልቀስ ጀመረች ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ፡፡ ከማጥበቋ ብዛት የተነሳ ደረቷ ላይ ያለችው የወርቅ ሐብል ማጫወቻ ጉንጨን የበሳችው እስኪመስለኝ እየወጋችኝ ነበር፡፡ የማደርገው ነገር ግራ ገብቶኝ፣ ደረቷ ላይ ተለጥፌ ዝም አልኩ፡፡ ወጥ ወጥ
ትሽታለች:: ትንሽ አቅፋኝ እንደቆየች፣

“የኔ ነገር፣ ና ግባ ና አለችና መልሼ እንዳልሄድ የፈራች ይመስል በአንድ እጇ
እንባዋን እየጠረገች፣ በሌላኛው እጇ እጄን ይዛ እየጎተተች ወደ ውስጥ መራችኝ፡፡
“ግቢው፣ ቤቱ አዲስ ሆነብኝ፡፡ብዙ ዓመት ቆይቼ የመጣሁ ያህል አዲስ ሆነብኝ፡፡ ዛፎቹን እንደ ሰው እያቀፍኩ ብስማቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ በረንዳ ላይ የተቀመጠውን የጋሽ ዝናቡን ተወዛዋዥ ወንበር፣ እንደ ሰው ስላም ልለው ዳዳኝ፡፡ ከዚህ ግቢ ለአንድ ሳምንት የቀረሁበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ ጭር ብሏል፡፡

የመጠየቂያው ስዓት እንዳይረፍድብኝ ብዬ ወጥ እየሠራሁ ስሯሯጥ ቤቱንም
እላዘጋጀሁት እለች፡፡ እስረኛ መጠየቂያው ስዓት ማለት አልፈለገችም፡፡ ሳሎን ባለው
ሶፋ ላይ፣ በርከት ያሉ የመሐሪ ልብሶች እዚያና እዚህ ተዝረክርከዋል፡፡ የተወሰኑት
በሥርዓት ታጥፈው በአንድ ጎን ተቀምጠዋል፡፡ ቅያሬ ልብስ ልትወስድ አዘጋጅታቸው ነበር፡፡

ድንጋይ እንደወረወሩብሽ ሰምቼ ነው የመጣሁት አልኩ፡፡ ድንገት ነው ያመለጠኝ፡፡

“ዝምብለው ነው ባክህ ልጆች

ጎዱሽ …

አረ ጠጠር ነው፡፡ እግሬን ጫር አድርጎኝ አለፈ፡፡ ታውቀው የለ፣ የዚህ ሰፈር ውሪዎች ጨዋታቸው ለዛ ቢስ ነው፡፡ እናተም ያው ነበራችሁ፡፡ በየቀኑ ስሞታ ነበር ብላ ለመሳቅ ሞከረች ፡፡ ዓይኔን ወደ እግሯ ላከሁት ነጭ ካልሲ አድርጋለች፡፡ ማሚ በጭራሽ ካልሲ አድርጋ አይቻት አላውቅም! ወደ ማድቤት አብሪያት ሄድኩና፣ ግድግዳውን ተደግፌ
ቆምኩ፡፡ የኤሌክትሪክ ምድጃ ላይ ሁለት ብረት ድስት ጥዳ ወጥ እየሠራች ነበር፡፡
አንዱ ድንች በሥጋ የመሐሪ ቁጥር አንድ ምግብ (ሚስቴ አሪፍ ድንች በሥጋ መሥራት ከቻለች ለምን እንፋታለን ብሎኝ ነበር ..ድሮ ስለ ሚስት ይሁን ስለ ፍች ስናወራ )

ከማሚ ጋር ሳንነጋገር ዘለግ ያሉ
ደቂቃዎች ቆየን፡፡ ወዲያ ወዲህ ስትል በዝምታ እመለከታታለሁ፡፡ማንኪያ ታነሳለች፣ ታስቀምጣለች፣ ማማሰያ ታነሳለች እንዲሁ ወጡን ነካክታ ትመልሰዋለች፡፡ ጸጉሯ በሻሽ ጥፍንግ ብሎ ስለታሰረ ነው መሰል፣ ግንባሯ ወጣ
ብሏል፡፡ውስጤ እንደገና እቀፋት እቀፋት ይለኛል፡፡ፊቷን ኮስተር አድርጋ እንዳቀረቀረች በፍጥነት ነበር ወዲያ ወዲህ የምትለው፡፡ አውቃለሁ ማሚ እንዲህ የምትሆነው፣ እንባ
እየተናነቃት ላለማልቀስ ነው፡፡

ድንገት ከሩቅ በመጣ በሚመስል ድምፅ
“እየተዘጋጀህ ነው?” አለች፡፡

“ለምኑ? አልኩ፡፡

“ዩኒቨርስቲ መሄጃችሁ እየደረሰኮ ነው…ልብውልቅ”

ዝም ተባብለን ቆየንና፣ “መሐሪም እዚያ እተረገመ እስር ቤት የሚቆይ አይመስለኝም፤
አብራችሁ ዩንቨርስቲ መሄዳችሁ አይቀርም፡፡ አላደርስ አለኝ እንጂ ዳቦ ቆሎም በሶም አዘጋጅላችኋለሁ፡፡ ግዴለም ትንሽ ቀን አለ” ብላ ወገቧ ላይ ያሰረችውን ሽርጥ ወደ ላይ ስባ እንባዋን ጠረገች፡፡ ምን እንደምል ጨንቆኝ ዝም ብየ እንደቆምኩ፣ ድንገት የግቢው
በር ተንኳኳ፡፡

አንተ እዚሁ ቆይ" ብላኝ ሄደች፡፡ ተከተልኳት፡፡ እናቴ ነበረች፤ ነጠላዋን እንኳን በወጉ ሳትለብስ አንጠልጥላ ስትከንፍ የደረሰችው። ገና ስታየኝ፣ እጇን ልቧ ላይ አድሮ እንባዋን ዘረገፈችው፡፡
“ምንም ኤልሆነልኝም ዘንድሮ፣ በስንቱ ተጨንቄ ልሙት እኔ፣ ምን አደረኩ ምን
በደልኩ እያለች ማልቀስ ስትጀምር፣ ማሚ አቅፋ አጽናናቻት፡፡ ድንገት ዋናው ጉዳይ
ትዝ ያላቸው ይመስል፣ እኔን ትተውኝ ተቃቅፈው ይኼን ለቅሶ እስኪወጣላቸው
አስነኩት፡፡ መሐሪ ከታሰረ በኋላ የተገናኙት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ አልቅሰው ሲወጣላቸው እንግዲህ እግዜር አመጣው፣ ተይው፣ ተይው” ተባብለው ተያይዘው ወደ ቤት ገቡ፡፡

እናቴ በለቅሶ ድምፅ ዘንድሮ መቼም እንዳትታዘቢኝ” ከማለቷ
👍2
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በአሌክስ_አብርሃም

“…ባልወልዳትም እናት ነኝ ብዬ በነጋታው ሳሌምን ልጠይቅ ሆስፒታል ብሄድ፣ ጥድቄ እንደውሻ አከላፍታ መለሰችኝ፡፡ ያች ምስኪን ናት ወይ ትያለሽ፡፡ ሰው ጉድ እስኪል፣ ምን ቀርቶሽ መጣሽ ብላ ኡኡ አለች፡፡ ውሻ አረገችኝ …ውሻ፡፡ ቀና ብዬ የሰው ዓይን ማየት እስከፈራ አቀርቅሬ ወጣሁ፡፡ ይሁን እናት ናት፣ አላዘንኩም፡፡ በኋላ ስሰማ ሳሌምንም ጥድቄንም ፈረንጆቹ እዚያው ግቢ ወስደው አስጠጓቸው አሉ” እንባዋን ጠራረገችና ቀጠለች፡፡

ዝናቡም ይኼው ሳምንቱን ሙሉ ቃል ሳይተነፍስ፣ ከቤትም ሳይወጣ ጧት እዚች
በረንዳ ላይ እንደተቀመጠ ማታ ገብቶ ይተኛል፡፡ ላናግረውም ብል አይተነፍስም፡፡
መሐሪም በሄድኩ ቁጥር አባባ ደህና ነው ወይ ካጠገቡ አትለዬ እንዳለኝ ነው፡፡
እንደሸማኔ መወርወሪያ ከዚያ ከዚህ ስል እውላለሁ… እንደ እብድ ብቻዬን ማውራት
ሁኗል ሥራዬ …የምያዝ ምጨብጠውን አጥቻለሁ”

ዛሬ ጋሽ ዝናቡ የት ሂዶ ነው ታዲያ?”

“ካለወትሮው ጧት ተነስቶ፣ እስቲ ነጠላ ስጭኝ ቤተከርስቲያን ልሂድ አለኝ

እሰይ እንኳን ሄደ፡፡ እሱ መድኃኒያለም ይስማው አለች እናቴ፡፡ እኔ ግን ገረመኝ፡፡
ጋሼን ሳውቀው ጀምሮ ቤተክርስቲያን ረግጦ የሚያውቀው፣ ሰው ሲሞት ለቀብር ብቻ ነበር፡፡ ማሚ ልብሱንም ምግቡንም በሁለት ፌስታሎች ቆጣጥራ አብረን ወጣን፡፡

አብሬሽ ልሂድ ማሚ” አልኳት፡፡ እናቴ ይሉኝታ ይዟት ዓይኗን ማሳረፊያ አጥታ
ስታንከራትት፣ ማሚ የእናቴ ነገር ገብቷት ይሁን አልያም እውነቷን እንጃ፣ ሌላ ቀን! ዛሬ ቤተሰብ ብቻ ነው …አንድ ሰው ብቻ ነው የሚያስገቡት” ብላ ወደ እናቴ ገፋ አደረገችኝና እየተጣደፈች ሄደች፡፡ ገብቶኛል፣ እንባዋ መጥቷል፡፡ እሷ ወደግራ እኛ ወደቀኝ ስንለያይ ዞር ብዬ ከኋላ ተመለከትኳት፡፡ ያች በተረከዘ ረጅም ጫማና ባጭር ቀሚስ መንሳፈፍ በሚመስል መውረግረግ መንገዱ ላይ የምትነግሥ ሴት፣ አላፊ አግዳሚው ጎንበስ ቀና እያለ ወገቡ እስኪቀነጠስ ለሰላምታ የሚያሸረግድላት ሴት፣ ነጠላዋን ተከናንባና ባለማስሪያ ሸራ ጫማ አድርጋ ከኋላዋ የሚያሳድዳት አንዳች ነገር እንዳለ ሁሉ፣ ከሶምሶማ ባልተናነሰ ርምጃ ትገሰግሳለች፡፡ ብቻዋን፡፡ አንድ ልጇን፣ ጓደኛዋን፣ ሁሉ ነገሯን
ወደታሰረበት ማረሚያ ቤት፡፡

እንዴት ነው አሁን መሐሪን የሚያርሙት? ሁለተኛ ሴት እንዳትደፍር ሊሉት ነው?…ሁለተኛ ይችን ምስኪን እናትህን ትተህ የትም እንዳትሄድ ሊሉት ነው ? ጓደኛህ
ሁሉም ነገር የተደበላለቀበት በአንተ ምክንያት ነው፤ ከአሁን በኋላ ሴት ከመድፈርህ በፊት አማክረው ሊሉት ነው ምን ብለው ነው የሚያርሙት ?ምናለ እግዚአብሔር እኔን ለአንድ ጊዜ እግዚሐርነቱን በከፊል ሊያውሰኝ እና፣ ነገሮችን በአንድ ሳምንት
ወደ ኋላ ብመልሳቸው .እግዚሐርነቴን እውር ላብራበት፣ አልያም ሽባ ልተርትርበት አልልም፣ የሞተም በሰላም ይረፍ፣ እሱን አስነስቼ አላንዘፋዝፍም፡፡ አንዲት ነገር ብቻ ትንሽ ተአምር … ሮሐ ያመጣችውን ውስኪ በተአምር ወደ ውሃ፣ ቢራውንም ወደ አምቦ ውሃ ለመቀየር፡፡ ገድልም ይጻፍልኝ አልል፡፡ እንደው በምስጢር ይችን ተአምር ለማድረግ ብቻ!
።።።።
መሐሪን ሳልጠይቀው ሠላሳ ቀናት ነጎዱ፡፡ ድፍን አንድ ወር፡፡ ሰውን ፈርቼ አልነበረም፡፡ሰው ስለመሐሪ እስኪበቃው አውርቶ ወጥቶለት፣ ችላ ወደማለቱ ነበር፡፡ መሐሪን ራሱን ማየት ፈራሁ፡፡ ፊቱን ማየት ፈራሁ፡፡ የመሐሪን ፊት ማየት ፈራሁ፡፡ በቃ አንድ ቀን በጨመረ ቁጥር ፍርሃቴ በዚያው ልክ እያደገ ዓይኑን ማየት ፈራሁ፡፡ መሐሪን አለመጠየቄ ከቤተሰቦቹም አራቀኝ፡፡ ለምን አልጠየቅኸውም ቢሉኝ ምን እላለሁ? የሚል ፍርሃት፡፡ እናቴ እንኳን ከእኔ ተሽላ “አሁን ተረጋግቷል ሂደን ጠይቀነው እንመለስ” ስትለኝ፣ “አንች
ሂጂ ብያት ቀረሁ፡፡ ደርሳ እክትመለስ በጉጉት ስጠብቃት ቆየሁና፣ ከመጣች በኋላ ስለ መሐሪ ልታወራኝ እስረኛው ብዛቱ ብላ ስትጀምር፣ ትቻት ወደ ውጭ ወጣሁ፡፡
የሆነ ዝግንን የሚል ስሜት ሰውነቴን ወረረኝ፡፡ ማንም ሕመሙን ሊረዳው አይችልም፡፡ እንቁላል እራሱ ላይ
አስቀምጦ በቀጭን ገመድ ላይ እንደሚራመድ ሰው ነበር፣ ትላንቴ
ወድቆ እንዳይንኮታኮት የምታገለው፡፡ በቃ የመሐሪ ነገር “ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን” ሆነ፡፡በዚህ ዝምታ ውስጥ እያለሁ ነበር የተመደብንበት ዩኒቨርስቲ ዝርዝር በጋዜጣ የወጣው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመደብኩ፡፡ ውስጤ የዓመታት ምኞቱ እንደተሳካለት ሰው አልፈነደቀም፡፡ እናቴ ምናለች?

እልልልልልልል … የትም ይሁን፤ ብቻ ከዚህ የተረገመ ሰፈር ሂድልኝ እንዲህ እያለች ታዲያ አቅፋኝ ታለቅሳለች፡፡

ዓይኔ ጋዜጣው ላይ ይንከራተታል፡፡ መሐሪ ጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ አፄ ቴዎድሮስ
ከነሠራዊታቸው መጥተው እኔ መናገሻ ላይ የተመደበውን መሐሪን ፍቱ ብለው እስር ቤቱን ሰባብረው ነፃ ቢያስወጡት በቁሜ ቃዠሁ፡፡ (ያበድኩ እስኪመስለኝ) ሮሐ መቀሌ ተመደበች ሁሉም የመቀሌ ወንድ ዙሪያዋን ከብቦ ከበሮ እየደለቀ ምድራችን ላይ
ምናይነት ቆንጆ መጣችብ(ል)ን እያለ ሲጨፍር ታየኝ፡፡ አንድ ክፍሎም የሚባል የቀድሞ ታጋይ፣ የአሁን ባለስልጣን አግብታ አስራ አንድ ቆንጆ ልጆች ትወልዳለች፡፡ ብርክቲ፣ጸጋ፣ አብረኸት፣ ረዳኢ፣ ሐየሎም፣ወልደሰንበት፣ ገብረእግዚ፣ ጎይሌ፣ አጽብሃ ወላ መለስ
እና አርከበ ትላቸዋለች፡፡ ምንም አይለውጥም፣ የባለሥልጣን ሚስት ብትሆን ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ አትችልም፡፡ እቃዣለሁ፡፡

ዝም ብዬ ተቀምጨ፣ የስንት ሺህ ተማሪ ስም ዝርዝር፣ አንድ በአንድ አንብቤ ጨረስኩ፡፡ ስጨርስ፣ ቆንጆ ልብ ወለድ እንዳነበበ ሰው እንደገና ከላይ ጀምሬ ማንበብ ጀመርኩና ድንገት፣ ከዚህ ሁሉ ሺህ ተማሪ እንዴት መሐሪ ተለይቶ እስር ቤት ገባ?” ብዬ አሰብኩ፡፡
ዓይኖቼን ከድኘ አንዱ ስም ላይ ጣቴን አሳርፌ ዓይኔን ስገልጥ፣ “ገረመው ታደሰ አለበል”ይላል፡፡ እሽ ገረመው ታደሰ አለበል ለምን አንዲት ሕፃን ኤልደፈረም? ምናልባት ገረመው የመሽኛ ዝግጅት አልተደረገልትም ይሆናል፣ ምናልባት ገረመው መጠጥ አልጠጣም ይሆናል፣ ወይም የዚያን ቀን የገረመው ጓደኛ፣ ከገረመው ጋር አድሮ ከዚህ መዓት
ታድጎት ይሆናል፡፡ ወይም ገረመው ገና ውጤት ተቀብሎ ወደ ቤት ሲሮጥ፣ መኪና
ገጭቶት ሞቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሞተ ሰው ምደባ አይመጣም ያለው ማነው? ይኼው ለታሰረስ ሰው እየመጣ አይደል እንዴ …?! እቃዣለሁ፡፡

እንዲህ እያልኩ ሳስብ ነበር፣ አንድ ሕፃን በራችንን አንኳኩቶ ሰው እንደሚፈልገኝ
የነገረኝ፡፡ ሮሐ ነበረች፡፡ መንገድ ዳር ላይ ቁማለች፡፡ መሐሪን ያየሁ ያህል ውስጤ በፍርሃት እየተሸማቀቀ ወደሷ ሄድኩ፡፡ ፈገግ ብላ አቀፈችኝ፡፡ እኔም አቀፍኳት “እንች… “አንተ” ስንባባል ቆይተን ስለ ምደባ ወሬ ጀመርን፡፡

እንኳን ደስ ያለሽ” አልኳት፡፡“እንኳን ደስ ያለህ አንተም ዝም ተባብለን ቆየንና አቀርቅራ መሬት መሬት እያየች…

አብርሽ …መሐሪን መጠየቅ ፈልጌ ነበር… እታካሂደኝም?” አለችኝ፡፡ ውስጤ በደስታ
ሲናወጥ ተሰማኝ፡፡ ለምንም አልነበረም፤ ለመሐሪ በዚህ ሰዓት ከማንም በላይ ሮሐ
ታስፈልገዋለች፡፡ እኔ ራሴ መሐሪን የማየት ድንገተኛ ፍላጎት ውስጤን ሞላው፡፡ በቀጣዩ ቀን ልንሄድ ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡
ብዙ እስረኛ ጠያቂዎች እስረኞች፣ ፊት ለፊት እየተያዩ በመደዳ የተቀመጡበት ከእንጨት ርብራብ የተሠራ የማይመች አግዳሚ ላይ፣ እኔና ሮሐ ተቀምጠን ግርግሩን ስንመለከት፣
እሰረኞች ሮሐን ፍጥጥ ብለው ሲያዩዋት ጨነቀኝ፡፡ ዓይናቸውን አይነቅሉም ነበር::
ከጠያቂዎቻቸው ጋር እያዎሩ፣ ዐይናቸው ሮሐ ላይ ነው፡፡ ያኔ ስለ ጉዳዩ የሰሙና፣
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በአሌክስ_አብርሃም

ድንገት ሮሐ ወደ ፊት ሰገግ ብላ ሹከሹክታ በሚመስል ድምፅ “ለምን መሐሪ …ለምን?” አለችው፡፡ ፊቷ ተቀያይሮ እንደ ቲማቲም ቀልቷል፡፡

“ለምን ምን አላት ምንም ሳይመስለው ፈገግ እንዳለ፡፡

ለምን ሳሌምን.....

ባኮሽ አታካብጅው ያጋጥማል!” አለ ትከሻውን ወደላይ በግዴለሽነት ጎፋ እድርስ፡፡
የመሐሪን ቆዳ ለብሶ የለየለት ወንጀለኛ ከፊታችን የተቀመጠ እስኪመስለኝ ድረስ፣ ፊቱ ላይ ትንሽ እንኳን ጸጸት አልነበረም፡፡ መሐሪ የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ በአንድ ወር በምን ተአምር እንዲህ ዓይነት አስፈሪ ሰው እንደሆነ ሳወጣ ሳወርድ አልገባህ አለኝ፡፡ቢጨንቀኝ፣ ቀጥሎ ምን ይፈጠር ይሆን በሚል ግርምት፣ አንዴ ሮሐን አንዴ መሐሪን ማየት ጀመርኩ፡፡

“ምኑ ነው የሚያጋጥመው ሕፃን'ኮ ናት፣ እናተን አምና የተጠጋች ምስኪን ሕፃን
ትንሽዬ ልጅ…ትንሽ …" ሮሐ የምትለው ጠፍቶባት ፍጥጥ ብላ ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠና ዓይኗ እንባ ሞልቶ ስትመለከተው፣ ምንም በማይነበብበት ፊት ትክ ብሎ እያያት፣

ጠጥቸ ነበር፣ አንች ያመጣሽውን ውስኪ ጠጥቼ ነበር፡፡ በዚያ ላይ ትንሽ አሰሳጭተሸኝ ነበር፡፡ሁለታችሁም አበሳጭታችሁኝ ነበር” ብሎ ወደ እኔም ወደሷም ጠቆመና፣ “…በቃ የሆነው ሆነ…ይኼ አዲስ ነገር አይደለም፡፤ በኔ አልተጀመረም ብሎ ተራ በተራ አየን፡፡
ፈገግታው እስከዚያ ሰዓት ድረስ ሙሉ ለሙሉ አልከሰመም ነበር፡፡
እና ደፈርካት….” ብላ አንባረቀችበት፡፡ ድምፅዋ፣ እንኳን ድንገት የሰማውን፣ እኔም ጉዳዩን እየተከታተልኩ ያለሁትን የሚያስደነብር ነበር፡፡ በዙሪያችን የነበሩት ሁሉ ወደ እኛ ዙረው አዩን፡፡ መሐሪ አቀርቅሮ የእጁን መዳፍ እያገላበጠ ተመለከተና፣ ድንገት ተነስቶ
ቆመ፡፡

“ተቀመጥ አልጨረስንም? አለች ከመጀመሪያው በባሰ ጩኸት! ፖሊሶቹ ወደኛ እየመጡ ነበር፡፡
መሐሪ ልክ እንደሷ ጮሆ “ሁለተኛ እንዳትመጡ እዛው የራሳችሁን ሕይወት ኑሩ አለን፡፡ ግራ ተጋብቼ እንደተቀመጥኩ፣ ሮሐ ዘላ ተነስታ ቲሸርቱን ጨምድዳ አነቀችና፣ ባለ በሌለ ኃይሏ ቱ!” ብላ ምራቋን ፊቱ ላይ ተፋችበት፡፡ ከዚያ በኋላ እንደ እብድ መጮህ ጀመረች፡፡ ግራና ቀኝ የቆሙት ፖሊሶች አንቀው ወደኋላ ሲጎትቷት እካባቢው ድብልቅልቁ ወጣ፡፡
አንተ ደደብ! ምንም የማታውቅ ሕፃን ገድለህ፣ ደረትህን ትነፋለህ! መሃይም …ቱ! እዚህ ልትሸለም የመጣሀ መሰለህ? እስር ቤት የሚያኮራህ አንተ ማንዴላ ነህ? ለነፃነት ስትታገል ታስረህ ነው?…ወንጀለኛ ወንጀለኛ ሁነህ ነው! አንዲት ደሀ ቆሎ ሸጣ ያሳደገቻትን ሕፃን ደፍረህ! ዕድሜ ልክህን እዚህ ትበሰብሳለህ ቆሻሻ ኢዲየት! ልቀቁኝ ይኼን ውሻ ድንገት ጫማዋን ባልተያዘው እጁ አውልቃ ስትወረውር፣ መሐሪ ደረት ላይ አረፈ፡፡ ጥሩ ምት ነበር! ሌላ የሚወረወር ነገር ስትፈልግ፣ አንዱ ፖሊስ ሁለት እጇን አነባብሮ ጠፍንጎ ያዘና፣ እየገፈተረ ከእስረኛ መጠየቂያው ክልል ወደ ውጭ ወሰዳት፡፡ እየጮኸች ነበር
“ቆሻሻ ነህ! ራስሆን ነው የናከው! እብድ! ትንሽ ለቤተሰቦችህ አታዝንም? ውሻ

በተቀመጥኩበት እንደ ጨው አምድ ደርቄ ቀረሁ፡፡ መሐሪ የተወረወረበት ጫማ፣
ያረፈበት ቦታ ላይ ቲሸርቱን ተረጋግቶ አራገፈና፣ ጫማውን አንስቶ “ውሰድላት” ብሎ ሰጠኝ፡፡ ተቀበልኩት፡፡ በተረጋጋ እርምጃ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ ከዓይኔ እስኪሰወር ተመለከትኩት፡፡ ዞር እንኳን አላለም፡፡ ፈጽሞ የማያውቀኝ ሰው ነበር የሚመስለው፡፡ በቃ የእድሜ ልክ ጓደኝነት ይኼው ነው …ጫማውን እንከርፍፌ እንደያዝኩ፣ እግሬን እየጎተትኩ ወደ ሮሐ ሄድኩ፡፡ አራት የሚሆኑ ፖሊሶች ከበዋት በየአፋቸው ይጮሁባታል፡፡ “አንች ያምሻል እንዴ? …የሕግ ታራሚ ልትደበድቢ ነው? ምኗ ጥጋበኛ
ናት! " ድንገት ቁጭ ብላ እራሷን ይዛ እዬዬዋን አስነካችው፡፡ ሌላኛው ፖሊስ ነገረ ሥራው አለቃ የሚመስል በእጁ መገናኛ ሬዲዮ የያዘ፣ ወደኔ በሬዲዮው አንቴና እየጠቆመ
“የጋሽ ግርማ ልጅ ናት አይደል” አለኝ፡፡ እራሴን በአዎንታ ነቀነቅሁ፡፡
“በል ይዘሃት ውጣ፡፡ ተነሽ አንች ውጭ !…” ብሎ ኮስተር አለ፡፡ ልይዛት ስሞከር እጇን መንጭቃ ተነሳችና፣ ጫማዋን አድርጋ ቀድማኝ መንገድ ጀመረች፡፡ ተከትያት ወጣሁ፡፡

ከዋናው በር እንደወጣን በጩኸት “አንድ ወር በሥርዓት እንኳን መተኛት አልቻልኩም በሽተኛ ነው የሆንኩት፣ ልክ አይደለሁም! ራሴን ስረግም ስጸጸት ነው የከረምኩት፡፡ ቢያንስ ትንሽ ጸጸት ፊቱ ላይ የማይ መስሎኝ ነበር፡፡ ራሴን ተጭኜ ይቅር ልለው፣ በዚህ ሰዓት ማንም ከጎኑ የለም ብዬ” ድንገት ወደ እስር ቤት የሚገቡ ስዎች አፍጥጠው እንደ
እብድ ሲመለከቷት ቆም ብላ፣
“ምን ሆናችሁ? ሰው አይታችሁ አታውቁም?” ብላ ስታምባርቅባቸው እንደ እብድ ሸሹን፡፡

"ሮሐ ተረጋጊ"

አታረጋጋኝ ..አልፈልግም፤ ማንም ተረጋጊ ምናምን እንዲለኝ አልፈልግም፡፡ ያሳለፍኩትን ራሴ ነኝ የማውቀው …”

“ይገባኛል…”

አይገባህም?

“ምንድነው የሚገባህ? ዳዲ፣ ሽጉጥ…ሽጉጥ ነው ያወጣብኝ! ለምን እሱን አፈቀርሽ ብሎ፡፡ እንደዛ ስላስፈራራኝ አቆምኩ? አላቆምኩም! ለምን? እወደው ነበራ! ምንድነው ችግሩ? ምንድነው እየሆነ ያለው? ምንም ሊገባኝ አልቻለም! …ምንም!! ታምነኛለህ? አፍ
አውጥቼ ሴክስ እናድርግ ብዬው አውቃለሁ፣ የፈራ መስሎኝ ልብሱን ላስወልቀው ታግዬዋለሁ፡፡ ሴት እንደዛ ታደርጋለች? አታደርግም! ሁሉን ነገሬን ለሱ መስጠት የመጨረሻ ደስታዬ ነበር፡፡ ምን ስለሆነ? ቆንጆ ስለሆነ…ምን ቆንጆ ነው? ጥሙጋ! ሃብታም ስለሆነ?…ምንም! በቃ ስላፈቀርኩት፡፡ ከመሳሳም አልፎ አያውቅም! እንደፈለክ አድርገኝ ብየዋለሁ …ከዚህ ወዲያ ምን ላድርግለት? ለምን ይቀናል? ለምን? እንደሚያፈቅረኝ ይነግረኛል፣ ቆንጆ እንደሆንኩ ይነግረኛል፡፡ አንችን ካላየሁ፣ ነፍሴ መንፈሴ ሲለኝ ነው የኖረው፡፡ የፈለገ ቢጠጣ በርሚል ሙሉ ቢጠጣ …ምን ሁኖ ነው አንዲት ሕፃን….በሽተኛ ነው! …በሽተኛ አስተዳደጉም ምኑም በሽተኛ በራሱ
የማይተማመን ስቱፒድ ያ እኔም በሽተኛ ነኝ በዚህ ዕድሜው መጸዳጃ ቤት ለመሄድ
እንኳን አባቱን የሚያስፈቅድ ልጅ፣ ጤነኛ አለመሆኑን እንዴት አላውቅም !በራሱ ቤት በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ የሚኖር በሽተኛ ቱ.. ጮሃ ጮሃ ሲወጣላት ትከሻዬ ላይ ተደፍታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰችና፣ እኔ ምንም አላልኩትም የዛን ቀን ምሽት በእኔ
ምክንያት የሆነ እየመሰለኝ በጭንቀት ልሞት ነው. ያንን ውስኪ ማምጣቴ፣ በየቀኑ በየቀኑ ይጸጽተኛል” አለችና ማልቀስ ቀጠለች፡፡
“የዚያን ቀን ምሽት ነበርኩኮ እኔ ምስክር ነኝ …ሁሉም ነገር፣ የራሱ ችግር ነው፤ አንድም ነገር አላጠፋሽም፡፡ እመኝኝ፣ ላፅናናሽ እይደለም እንዲህ የምለው! ምንም ያጠፋሽው ነገር የለም፡፡ ራስሸን የምትወቅሽበት ምንም ምክንያት የለም! ውሸቱን ነው የቀባጠረው፤ የራሱ
ችግር ነው፣ የራሱ!” ከልቤ ነበር እንዲህ ያልኳት! ንግግሬ አጽናንቷት ይሁን፣ አልያም ለቅሶዋን ጨርሳ የዚያን ቀን እንባዋን ጠራርጋ ወደቤቷ ሄደች፡፡

ልቤ በመሐሪ ማዘኑን ትቶ “የራሱ ጉዳይ!” የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሶ ነበር፡፡
እግዚአብሔር የመሆን ፍላጎቴን ትቼ እንዲያውም ቀሪ ዘመኔን ሁሉ እንደ ሰይጣን በሰዎች ሁሉ ላይ ከፉ ለመሆን ተመኘሁ፡፡ ሰው የሚባል ፍጥረት ተለቃቅሞ ሲኦል ቢወረወር ሲያንሰው ነው፡፡ ሰበበኛ ሁሉ፡፡ መሐሪ ሳሌም ላይ ላደረገው ነገር ሁሉ እኔና ሮሐን መውቀሱ፣ ውስጤን ቢያቃጥለውም፣ በዚህ ጉዳይ በቃ አያገባኝም ብልም፣ ሳሌም ግን ትናፍቀኝ ነበር፡፡ የእውነት ትናፍቀኛለች፡፡ ሳቋ ይናፍቀኛል፣ ከእናቷ እቅፍ
ጀምሮ በዓይናችንና በነፍሳችን እቅፍ
👍4😁1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በአሌክስ_አብርሃም

አንዴ በሕይወት ውስጥ እያወቅናቸው ሰዎች ከናካቴው መስራት እና፣ከሕይወታችን ማስወጣት አንችልም። ሌላው ሁሉ ቢቀረሸ እንደ ሸረሪት ድር የቀጠነች ንፋስ የሚወዘውዛት የትዝታ ክር በመካከላችን ትኖራለች።

ጥሩም ይሁን መጥፎ ትዝታዬን በልቤ እንደተሸከምኩ ወደ ተመደብኩበት ዩኒቨርስቲ ተጓዝኩ፡፡ ያለፈ ታሪኬ ሁሉ በየአጋጣሚው እየመጣ ቢረብሸኝም የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ ነገሮችን ወደኋላ እንድተዋቸውና በብዙ አዳዲስ ጓደኞች ተከብቤ አዲስ ሕይወት እንድጀምር አድርጎኝ ነበር፡፡ ሕይወቴ በማስታወስና በመርሳት መካከል የቆመች ነበረች፡፡
እጠናለሁ፡፡ብዙ ብዙ ነገር አጠናለሁ፤ ያጠናሁትን ላለመርሳት እታገላለሁ፡፡ በትምህርት ዓለም አለመርሳት ነበር ሰው የመሆን መሠረቱ፡፡ በተለይም በኔዋ አገር የትምህርት ዋጋው አዲስ ነገር ከመፍጠር በላይ፣ የሸመደዱትን አለመርሳት ነበር፡፡ በዚያው ልክ ያለፈ
ታሪኬን ለመርሳት እታገላለሁ፤ ሕይወት ውስጥ ወደፊት የመቀጠል መሠረቱ መርሳት ነበር፡፡ግን ደግሞ ልንረሳ ከምንሞከረው ትላንታችን ለይቶልን እንዳንርቅ፣የሚያስተሳስሩን ቀጫጭን ክሮች አይጠፉም፡፡ ሮሐ አንዷ ክር ነበረች፡፡ ሁለታችንም ዩኒቨርስቲ ከገባን
በኋላ፣ ቶሎ ቶሎ እንደዋወል ነበር፡፡በአምስት ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ ከመደዋወል በአካል እስከ መገናኘት እንደ ሮሐ የምቀርበው ሰው አልነበረም፡፡ በየጊዜው ስንደዋወል አብዛኛው ወሬያችን ስለየቀኑ ውሏችን ነበር፡፡ ብዙ እናወራለን፣ ሳቅ ለመፍጠር እንታገላለን፡፡

ዩኒቨርስቲ ተጋባሁ በወራት ውስጥ፣ መሐሪ የአስራ ስድስት ዓመት እስር እንደተፈረደበት ሰማሁ፡፡ ተውኩት፣ ረሳሁት፣ ያልኩት የመሐሪ ነገር አንጀቴን አንሰፍስፎት፣ የዚያን ቀን ምሽት ብቻዬን የሆነ ዛፍ ሥር ተቀምጨ አለቀስኩ፡፡ ያዘንኩት አንድ ወንጀል በሠራ ሰው
ላይ ስለተፈረደ ፍርድ አይደለም፣ እኔ እንደጓደኛ፣ ማሚና ጋሽ ዝናቡ ብዙ ዋጋ
ከፍሎ እንዳሳደገ ወላጅ፣ ሮሐ እንደፍቅረኛ፣ አገር እንደ አገር አንድ እንደላባ የሳሳ ንጹህ ነፍስ በአንድ ምሽት አጣን፡፡ ትልቅ ተስፋ፣ ያውም ተስፋውን እውን ከሚያደርግበት አቅም የነበረው ልጅ፣ አሥር ደቂቃ ባልሞላ ስሕተት ከገጸ ምድር ጠፋ፡፡ የመሐሪ ትንንሽ እጆች፣ ፍርሃቱ፣ ከልጆች ጋር ስንጣላ እንኳን፣ በፍርሃት እኔ ሥር መጥቶ ሽጉጥ የሚለው
ነገር፣ ሁሉም ነገር በየተራ እየታወሰኝ …አለቀስኩ:ማልቀስ ብቻ ሳይሆን፣ ብጮህ፣ኡኡ! ማለት አማረኝ፡፡

እዚያው እንደተቀመጥኩ ለሮሐ ደወልኩላት፡፡ በጋራ ለተነጠቅነው ፍቅር ቢያንስ ስሜት እንጋራለን ብዬ፡፡ቀድማኝ ሰምታ ነበር፡፡ ፍልቅልቅ ብላ ያንን ውሻ አስራ ስድስት ዓመት እከናነቡት ሲያንሰው ነው! አለችና በንግግሯ ተበሳጨሁ? ኤልተበሳጨሁም አዘንኩን
አላዘንኩም! ግን ፍቅር የሚባለው ነገር እንዴት ነው ትንሽ እንኳን ቅሪት ሳይተው
እንዲህ ጥርግርግ ብሎ የሚጠፋው? ብዬ ፍቅርን ተጠራጠርኩት፡፡ በዓለም ላይ የነበሩ የሰው ልጅ ሥልጣኔዎች ሁሉ ከምድር ላይ ለደመሰሱ፣ የሆነ ቅሪት ትተዋልኮ፣ ያንን ቅሪት ነው ቅርስ የምንለው፡፡ ስዎች ይህችን ዓለም ሲሰናበቱ፣ ቢያንስ ለሆነ ሰው ልብ
ውስጥ የሆነች ክር ይተዋሉ፣ ወንዞች ሲደርቁ፣ በደረቀ ምድር ላይ የሚተውት ዱካ አለ፡፡በዚያ መልካ ላ ነው ስዎች የሚሻገሩት፡፡ ምንም አሻራ የማይተው ጉዳይ፣ ሲጀመርም የሌላ ነገር ብቻ ነው፡፡ ወይስ የከሸፈ ፍቅር የሚተወው ዳና ጥላቻ ይሆን?

ለዕረፍት ወደ ቤተሰብ ስመለስ፣ ማሚንም ሆነ ጋሽ ዝናቡን ሂጄ አላየኋቸውም፡፡ እናቴ ሂድና ጠይቃቸው ብልግና ነው ብትለኝም፣ እሽ እያልኩ ሳልሄድ ቀረሁ፡፡ ወደ ዩኒቨርስቲ ከተመለስኩ በኋላ፣ አልፎ አልፎ ለማሚ የመደወል ሐሳብ ውል እያለብኝ፣
ስልኬን አንስቼ እንደስሜ ነፍሴ ላይ የታተመውንና መቼም የማልረሳውን የነመሐሪ ቁጥር ከደወልኩ በኋላ፣ ሲጠራ የዘጋሁበት ጊዜ ብዙ ነበር፡፡ ወደኋላዩ ከመዞር ይልቅ፣ ወደፊት ብቻ ለመራመድ ስታገል፣ ከፊቴ የሚያጋጥሙኝ ደማቅ የሕይወት ገጠመኞች ረድተውኝ፣
ትላቴን አደበዘዙት፡፡ ድብዛዜው ከመርሳት የማይተናነስ ነበር፡፡

የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ሆኜ አንድ ቀን እቤት ስልክ ስደውል፣ እናቴ በብዙ መንጠራዘዝና የረዘመ ማለሳለስ (እንዲህ ስትሆን ይጨንቀኛል) አሳዛኝ ነገር ነገረችኝ፡፡

ምን ሁነሻል? አባባ ደህና አይደለም እንዴ?” አልኳት፡፡ ቀስ ብላ ጋሽ ዝናቡ ማረፉንና ቀብር ውለው መግባታቸው እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ መጀመሪያ ጋሽ ዝናቡ አረፈ ማለት፣ሞተ ማለት መሆኑን፣ ልክ ከሌላ ቋንቋ እንደሚተረጎም ለራሴ ተረጎምኩ እና እየፈራሁ
“ጋሽ ዝናሱ ሞተ” ብዬ ጠየቅኋት፡፡

“አዎ ትላንት ማታ አረፈ"

“ምን ሆነ? ታሞ ነበር እንዴ?

"አረ ድንገት ነው።"

በኋላ ቆይቼ ስሰማ፣ ጋሽ ዝናቡ የሞተው ራሱን አጥፍቶ ነበር፡፡ በተለይም መሐሪ
ከተፈረደበት በኋላ፣ አእምሮው ጤነኛ አልነበረም አሉኝ፡፡ብቻውን ያወራል፤ ሥራውንም በአግባቡ መሥራት ስላልቻለ ለጊዜው ጡረታ አስወጥተውት ነበር፡፡ በዳኝነት ተሠይሞ የሚቀርብለትን ፋይል ሁሉ፣ ትልልቅ ወንጀል የሥሩ ወንጀለኞችን ሳይቀር ነፃ ናችሁ እያለ መልቀቅ ጀምሮ ነበር፡፡ አንድም ቀን መሐሪን እስር ቤት ሂዶ አልጠየቅም፡፡
በመጨረሻም ያ ባለ ነጎድጓዳማ ድምፅ፣ጋሽ ዝናቡ ራሱን አጥፍቶ ይችን ዓለም በዝምታ ተሰናበታት፡፡ ውስጤ ተንገበገበ፡፡ ቢያንስ እየሄድኩም ሆነ እየደወልኩ ብጠይቀው፣ትንሽ
መጽናናት ይሆንለት እንደነበር ማን ያውቃል፡፡

"መሐሪ ሰማ ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።

"እሱ ልጅማ ጤናም አይመስለኝ፣ አንዳች ነገር ለከፎታል”

እንዴት?”

“በፖሊስ ታጅቦ አባቱን እንዲቀብር የሰፈሩ ሰው ሁሉ ተሯሩጦ አስፈቅዶ፣ ና ውጣ
አባትህን ቅበር ቢሉት፣ ኤልሄድም አለ አሉ፡፡ በቃ አባቱን ላይቀብር ቀረ፡፡ እወደው
ነበር፡፡ በዚህ ነገር ትንሽ ቅር አለኝ፡፡ አይ ልክ አልሠራም

የዚያን ቀን ሁለት ሦስት ጊዜ ለማሚ ደውዬ ለቅሶ ለመድረስ አስቤ ተውኩት፡፡ ለእረፍት ወደ ቤተስብ ስመለስም፣ አልጠየኳትም፡፡ እሸሽ ነበር፡፡ አጥብቄ እሸሽ ነበር። መሐሪ እኔና ሮሐን እስር ቤት ከወቀሰን በኋላ ውስጤ፣ ትንሽ ይጨናነቅ ነበር፡፡ “የእውነት እኔና ሮሐ ሳሌም ላይ ያ ነገር ለመፈጠሩ ምክንያት ነበርን? እያልኩ አስባለሁ፡፡ ይኼን ነገር አንዳንዴ ለሮሐ ላነሳባት እፈልግና፣ ከአፌ ላይ እመልሰዋለሁ፡፡ ብቻዬን ራሴን ዕውቅስና
ሳጽናና ለዓመታት ኖሬያለሁ፡፡ ማጽናኛዬ ሁልጊዜም እንድ ዓይነት ነው፡፡መሐሪ ደደብ ነው የሚል፡፡ ራሱን ገደለ፣ አንዲት ሕፃን ገደለ፣ ይኼ አልበቃው ብሎ እንዴት እኔን ይወቅሳል?
።።
ሮሐ ከእኔ ቀድማ ነበር የተመረቀችው፡፡ በአካውንቲንግ፡፡ በዚያው በተመረቀችበት
ዓመት አዲስ አበባ መጣች፡፡ አዲስ አበባ በመምጣቷ፣ ከልቤ ተደስቼ ነበር፡፡ ውስጤ በደስታ ሲፍነከነክ በስልክ የገነባነው ጓደኝነት ግዝፈት ያኔ ገባኝ፡፡ ሥራ አልጀመረችም።ሀብታም ዘመዶቿ “ትምህርት ላይ ከርመሽ የምን ወደሥራ መሮጥ ነው” አሉኝ አለች።ያለው ማማሩ፡፡ በየቀኑ እንደዋወላለን (ለነገሩ እሷ ነች የምትደውልልኝ አንዳንዴ ድንገት ግቢ ትመጣለች፡፡ ጓደኞቼ ሁሉ አውቀዋት ነበር፡፡ “መልአክህ መጥታለች
ይሉኛል፡፡ እዚህ ግቢው በር ላይ
አቁመህ ቀክፍያ ብታስጎበኛትኮ፣ በሳምንት ውስጥ በቃ፣ ሚሊየነር ትሆናለህ” ይሉኛል፡፡

"በጣም ጥ፣ ያበደራችሁኝን ሁሉ በዚሁ ይጣጣ፣ አይታችኋታል” ብዬ በራሳቸው ቀልድ ሂሳብ ሠራሁ፡፡ ሮሐ ታዲያ ስትሰማ ስንት አበድረውህ ነው? አለችኝ እየሳቀች “ሦስት ብር

“በሦስት ብር፣ እንኳን እኔ፣ ድንቢጥ አይጎበኝም፣ ጥሩ ነጋዴ
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በአሌክስ_አብርሃም

....አንድ ቅዳሜ ቀን ራት ስንበላ ድንገት “እስካሁን ጓደኛ አልያዝኩም” አለችኝ፡፡

አንች ምንድነሽ ታዲያ”

"ኖ... ሴት ጓደኛ"

“ይቅርታ፣ ወንድ መሆንሽን እላወኩም!”

ለዛ ቢስ …ገብቶሃል እስካሁን ፍቅረኛ ለምን አልያዝዘከም ኮስተር አለች፡፡

"እኔጃ ትከ ብላ አየችኝና፣

“መቼም እየደስከኝ አይደለም፣ አይደል?”

ለምን እደብቅሻለሁ? እኔጃ! በቃ ሙሉ ለሙሉ ትኩረቴ ትምህርት ላይ ነበር፡፡ ብዙም ርሌሽን ሽፕ ላይ ድፍረቱ አልነበረኝም፣ እፈራለሁ፣ በጣም እፈራለሁ፡፡ ወይም እኔጃ አልኳት፡፡ ዝም ብላ ቆየችና፣

እኔን አልጠየከኝም አራት ዓመት ሙሉ በስልክ ስናወራ ለዕረፍት ስንገናኝ አንድም ቀን ጓደኛ ልያዝ አልያዝ ጠይቀኸኝ አታውቅም፣ ምናገባኝ ነው፣ ወይስ አንዱ አንጠልጥሎ ወደዛ በወሰዳት ነው …ምንድነው?”ብላ አንገቷን ሰበር አድርጋ አየችኝ፡፡ ይኼን
አስተያየቷን ስወደው፡፡

አንዳንዴ ልጠይቅሽ አስብና …አለ አይደል

“ከመሐሪ ጋር የነበረንን ነገር የምታስታውሰኝ እየመሰለህ ወይም ምን አስቦ ነው ትለኛለች ብለህ ትፈራለህ?”

እንደዛ ነገር መሰለኝ

“ለማንኛውም ጓደኛ የለኝም … ወንዶችን መቅረብ አልቻልኩም

“ከመሓሪ ጋር በተያያዘ ነው? …”

አላውቅም! ከሆኑ ወንዶች ጋር እቀራረብና፣ ድንገት ዓይናቸውን ማየት ያስጠላኛል።በቃ ውስጤ ምንም የተረጋጋ አልነበረም፤ እረበሻለሁ፡፡ ለረዥም ጊዜ እንቅልፍ በማጣት ተቸግሬ ነበር፡፡ ሕከምና ሁሉ ወስጃለሁ"

ኧረ ባክሽ አልነገርሽኝም

"ለማንም አልተናገርኩም”

እንኳን ማንም መሆኔን ነገርሽኝ”

“ኖ..ብላ እጄን በሁለት እጆቿ አፈፍ አድርጋ ያዘችኝ! የእጆቿ ልስላሴና ሙቀት መቼም አይረሳኝም፡፡እጆቼን እንደያዘችኝ ትከ ብላ እያየችኝ “በእነዚህ አራት ዓመታት በሕይወትሽ ውስጥ የነበረ ብቸኛ ሰው ጥሪ ብባል አንተ ብቻ ነበርክ” ዝም ብዬ እየኋት፤ ለእንደዚህ ዓይነት ወሬዎች ባዕድ ነኝ፡፡ በውስጤ ግን ያለፉትን ዓመታት ተመልሼ ሳስብ፣ እኔም
ከእርሷ ሌላ ከልቤ የምቀርበው ሰው ማስታወስ አልቻልኩም፡፡

“እኔም ከአንች ውጭ የቀረብኩት ሰው አልነበረም ዝም ተባባልን፡፡ እጆቼን
እንደያዘቻቸው ነበር፡፡ በረዥሙ ተንፍሳ እጆቼን ለቀቀችና ቦርሳዋን አንስታ እንሂድ
አለችኝ፡፡

ከተለያየን በኋላ ስለ ሮሐ ሳስብ አመሸሁ፡፡ እንግዳ ነበር ስሜቱ፡፡ የተዘበራረቀ፡፡ እንደ
ማዕበል ውስጤን ያናወጠ ስሜት፡፡ አብሪያት የመሆን ፍላጎት ውስጤን ለጉድ
ይገፋዋል፡፡ ሁለት ሦስት ጊዜ ልደውልላት ስልኬን አንስቼ ተውኩት፡፡ የዚያን ቀን ሌሊት መሐሪን በሕልሜ አየሁት፡፡ ብዙ ጊዜ ሰሕልሜ አይቼው አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ሕልሞቼ አብረን ካሳለፍናቸው ጊዜዎች ኣንዱ ላይ የሚያርፉ ነበሩ፡፡ የዚያን ጊዜው ግን የሚጨቅ
ዓይነት ሕልም ነበር፡፡ መሐሪ ጋር አብረን ታስረን ይመስለኛል፡፡አንነጋገርም፡፡
አንቀሳቀስም፡፡ ፊት ለፊት ተቀምጠን ዝም ብሎ ያየኛል፡፡ በቃ ማየት ብቻ!! ፊቱ ላይ ሳቅ የለ፣ ኩርፊያ የለ ዝም ያለ ፊት!
።።
ሮሐ ጋር ግንኙነታችን በየቀኑ ሆነ፡፡ የዘመዶቿ ቤት ቅርብ ነበር አራት ኪሎ አካባቢ፡፡ብዙ ጊዜ ከዩኒቨርስቲው ፊት ለፊት ያለች ባለ አንድ ፎቅ ካፌ ውስጥ ተቀምጣ ትጠብቀኛለች። እናወራለን፣ እንሳሳቃለን፡፡ እንዴት ፊት ለፊት ከመቀመጥ ጎን ለጎን ወደ መቀመጥ እንደተሸጋገርን ትዝ አይለኝም፡፡ እንዴት እጅ ለእጅ ተያይዞ መንገድ ላይ
መሄድ እንደጀመርን ትዝ አይለኝም፡፡ በሁለት እጆቿ ክንዴን ይዛ፣ ትከሻዬ ላይ እራሷን ጣል ማድረግ የጀመረችው መቼ እንደነበር አላስታውስም፡፡ራሳችንን ወደ ምንም አልገፋነውም፡፡ ከምንም አልከለከልንም፡፡ ልክ የሆነ ባሕር ላይ ያለች ጀልባ ውስጥ ነፍሳችንን እንደ ማስቀመጥ ነበር፡፡ ድንገት ማዕበል ተነስቶ ወደማናውቀው ቦታ
አሽቀንጥሮ ወሰደን፣ ዓይኖቻችንን ስንገልጥ፣ ያበደ ፍቅር ውስጥ ነበርን፡፡

ማዕበሉ የተነሳባትን ቅጽበት ግን አስታውሳለሁ፡፡ አንድ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ቲያትር ልናይ ጎን ለጎን በተቀመጥንበት ጨለማ አዳራሽ ውስጥ ልክ ስማችን የተጠራ ይመስል፣
ሁለታችንም ድንገት ዙረን ተያየን፡፡ የማስታውሰው ዓይኖቼን ስጨፍንና የሮሐ
ከንፈሮች ከንፈሬ ላይ ሲያርፉ ነበር፡፡ ልክ ርችት እንደሚለኮሰው በዚያች ቅጽበት የሆነ ነገር በመሀላችን ተጫረ፡፡ ስማያትን በብዙ ብርሃንና ቀለማት ተጥለቀለቀ ደንግጨ ነበር፡፡ ስንወጣ አልተነጋገርንም ከንዴን ይዛኝ ቀዝምታ ሸኘኋት! ውስጤ ግን በጸጸት እየተጥለቀለቀ ነበር፡፡ ክሕደት ነው አልኩ ለራሴ፡፡ ብዙ ሚሊዮን ሴቶች ባሉባት ዓለም፣ ጊዜ የጣለውን የጓደኛየን ፍቅረኛ መንጠቅ ምን የሚሉት ከፋትና ስግብግብነት ነው? እያልኩ፣ በራሴ አፈርኩ፡፡ ምናልባትም ሳላውቀው ውስጤ ያደገ የበታችነት ስሜት ሳይሆን አይቀርም አልኩ፡፡ መሐሪን በዚህ የበለጥኩ መስሎኝ፡፡ ተብከነከንኩ፣ ግን
በዚያው ምሽት ሮሐ ደውላልኝ ገባህ ስትለኝና ምንም እንዳልተፈጠረ ስናወራ ሁሉም ነገር ከአእምሮዬ ጠፋ፡፡ ድምፅዋን ስሰማ እንቅዥቅዥ የሚያደርገኝ ነገር ነበር፡፡

ሮሐ ስታፈቅር ሁሉን ነገሯን የምትሰጥ ልጅ ነች፡፡ ሁሉ ነገሯን፡፡ ምናልባት ባይሳካስ ብላ የምታስቀረው ነገር የለም፡፡ ካፈቀረችው ሰው ውጭ ህይወት በምድር ላይ ስለመኖሩም ትዝ አይላትም፡፡ በሕይወቷ ውስጥ ምንም የተወሳሰበ ነገር የለም፡፡ የኑሮ ቀመሯ ግልጽ
ነው ካፈቀረች ታፈቅራለች፣ ከጠላች ትጠላለች በቃ ነፍሷ ወዶኝ ነበር፡፡ለምን
ይመስልሃል ጓደኛ ያልያዝኩት? ስለወደድኩህ ነው ስላፈቀርኩህ እወድሃለሁ የእውነት
እወድሃለሁ!" የተሰማትን ቃል በቃል ሳታፍር ትናገራለች፡፡“የዶርም ልጆች ሁሉ
ያውቃሉ፥ ካልተደዋወልን ስነጫነጭባቸው ነበር የምውለው፡፡”

ነፍሷ ያለፈውን ሁሉ ረስቶ እኔ ጋር ነበር .…መሐሪ የሚባል ሰው በምድር ላይ መኖሩን ሁሉ ስለማስታወሷም እንጃ፡፡ እኔ፣ ፍቅሬም ፍርሃትና ጸጸቴም በጥልቅ ዝምታ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከልቤ ባፈቅራትም ጸጸት በየደቂቃው ውስጤ መጫሩ አልቀረም፡፡ ተገናኝተን በተለያየን ቁጥር፣ ያንገበግበኛል፡፡ አብረን ስንቀመጥ የሰው ሚስት ሰርቄ የተገናኘሁ ያህል፣ አካባቢዬ ምቾት አይሰጠኝም፡፡ በዚህ በኩል ኃይለኛ ጸጸት፣ በሌላ በኩል አቅሌን የሚስት ፍቅር እንደ ድፎ ዳቦ ከላይና ከታች የሚንቀለቀል እሳት ውስጥ ነበርኩ፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ ሮሐ ጋር በፍቅር አበድን፡፡ ሲቆይ የኔውም ህሊና ዓይኖቹን ጨፈነ መሰለኝ፣ እኔ ብሽ ቁጭ አልኩ፡፡ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ጠበቡን፤ “…ከአምስት ኪሎ እስከ አራት ኪሎ ያሉት መንገዶች፣ ብዙ የተራመደባችሁ ማነው?” ቢባሉ አንዲት የሳበችውን አየር እንደ አኮረዲዮን ሙዚቃ እድርጋ ወደ ውጭ የምትተነፍስ ውብ ልጅና፣ ከዓመት እስከ ዓመት የማትቀየር ኦሞ ከለር ጅንስ ሱሪ የሚለብስ፣ እንደ ሌባ ዙሪያውን እየተገላመጠ የሚሄድ ልጅ” የሚሉ ይመስለኛል፡፡ መንገዱ ለምዶናል
መንገደኛው ለምዶናል፡፡ አምስት ኪሎ ታከሲ ተራው አጥሩ ሥር የሚቀመጥ የኔ ቢጤ፤ሮሐ በመጣች ቁጥር ምጽዋት አስለምዳው ኖሮ አንድ ቀን “ምነው አረፈድሽ” አላት፡፡ልክ ደመወዙን ይዛ እንዳረፈደችበት ዓይነት፡፡ እዚህ ድረስ መንገዱ የኛ ሆኖ ነበር፡፡

አዲስ አበባ የመቆየቷ ምክንያት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ አትሠራም አትማርም፡፡ ዕድሜ
ለሀብታም ዘመዶቿ፣ ዘና ብላ እየኖረች፣ የመኖሯን ምክንያት ግን እኔን አድርጋ ነበር፡፡የአዲስ እበባ ሕዝብ ቁጥር ስንት ነው ብትባል አንድ” ብላ ወደ እኔ የምትጠቁም ነው የሚመስለኝ፡፡ ደስ ባላት ሰዓት፣ ድንገት ተነስታ ትመጣለች፡፡ ድንገት ስትመጣ፣ ነፍሴ በደስታ የሚያደርጋትን
👍2
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በአሌክስ_አብርሃም

....ማሬ መሽኛኘት የለም… መሐንዲስ ሆንክ አይደል …እስቲ የዚህን ሆቴል ሕንጻ አሠራር እንገምግመው” ብላ እየሳቀች እዚያው ሆቴል አራተኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኝ ክፍል እጄን ይዛ ወሰደችኝ፡፡ ፈጽሞ ባላሰብኩት ቀን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሮሐ ጋር አብረን ያደርነው እንደዚያ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ነበረች፡፡ ለእርሷም የመጀመሪያዋ፡፡ ጧት ፊቷን የሸፈናትን
ሉጫ ጸጉሯን እንደመጋረጃ ከፊቷ ላይ ወደኋላ እየሰበሰበች፣ ሐፍረት በቀላቀለበት ፈገግታ አየችኝና “ባለጌ ነህ እሽ” አለችኝ፡፡ ከዚያ ቀን በኋላ ብልግና ቀን ወጣለት፡፡የአዲስ አበባ አልቤርጎዎች እንደ አዲስ አበባ መንገዶች ሁሉ ዳናችን ታተመባቸው።በጠረናችን ነበራችን ተጻፈባቸው፡፡በፍቅር አብደን ነበር፡፡ስላለፈውም ስለ ወደፊቱም አላወራንም፡፡ማዕበሉ ወደፈለገበት እንዲወስደን ራሳችንን በፍቅር ጀልባ ላይ አስቀምጠን
ተውነው፡፡ በዚህ በኩል እንሂድ ብለን መንገድ ስላልመረጥን፣ የተሳሳተ መንገድ የሚባል ነገር በሕይወታችን አልነበረም፡፡ ምንም መዳረሻ ስላላለምን፣ የደረስንበት ሁሉ ልክ ነበር፡፡ ሮሐ ለፍቅር የተፈጠረች ልጅ ናት፡፡ ዝባዝንኬ ሳታበዛ በማፍቀር ብቻ፡፡የሕይወትን ደስታ ለምርኮ መውሰድ ተሰጥቷታል፡፡ ምርኮኛ ልሁን፣ አብሬያት ልሰለፍ ባይገባኝም፣ ብቸኛ ፍላጎቴ ሁልጊዜ የትም ቦታ አብሪያት መሆን ብቻ ነበር፡፡

ወደ ቤተሰብ ልመለስ ስዘጋጅ፣ ሮሐ አብረን እንሄዳለን ብላ መዘጋጀት ጀመረች፡፡ ከእንደገና የተዳፈነ ፍርሃቴ ሁሉ ተመለሰ፡፡ አንድ ላይ መሄዳችን ቢያንስ ለቤተሰቦቻትን ወሬው ጥሩ አይደለም፣ አንች ቆይተሸ ተመለሽ፣ ከሳምንት በኋላ መምጣት ትችያለሽ
አልኳት፡፡

ትክ ብላ እያየችኝ፣ “የራሱን መንገድ ተከትሎ የሄደ ሰው፣ ስእኔም ሆነ በአንተ ግንኙነት እንዲወስን አልፈልግም፡፡ ወላ ቤተሰብ፣ ወላ የአገሩ ሰው በሙሉ፡፡ ስለራሳችን ራሳችን ብቻ እንወስናለን

“ማለት የፈለኩት …"

“ማለት የፈለከውማ የጓደኛውን ገርል ፍሬንድ ቀማ ይሉኛል ነው፡፡ አይደል? ይበሉህ!አልቀማህም! ሲጀመር እኔ እንደ ኳስ የሚቀባበሉኝ መጫዎቻ አይደለሁም! ከልቤ ስላፈቀርኩህ የእውነት ስለወደድኩህ ነው አብሬህ የሆንኩት! መሐሪ የሚባል ጓደኛ ከአምስት ዓመት በፊት ነበረኝ፡፡ ለአንተም ጓደኛህ ነበር፡፡ አምናው ነፍሷን የሰጠችውን ሴት ቆሻሻ ላይ ሲወረውራት እክብረህ አነሳሃት ስላነሳሃት ሳይሆን፣ ከልቧ ስለወደደችህ
አብራህ ሆነች፣ በቃ! በራስህ ልትኮራ ነው የሚገባህ” የምትናገረው በቁጣ ስለነበር፣
የምላትን ነገር አጣሁ እናም ዝም ብዬ ስመለከታት

እሽ ሁሉም ነገር ይቅር፣ ተወልጀ ወዳደኩበት ከተማ መሄድ አልችልም እንዴ? ብላ ሳቀች፡፡

"አብሪያት ሳቅሁ"

“ግን በአጋጣሚ አውቶብስ ውስጥ ጎን ለጎን ካለ ወንበር ላይ አብሮኝ የተማረ ልጅ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ይኼ መቼም አያስውግር አያሰቅል ወደኔ ጎትቸ አቀፍኳት፡፡ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት፣ የእዉነት አፈቅራታለሁ፡፡ ምናባቴ እንደሚሻለኝ አላውቅም፡፡ ምን
እንደሚጠብቀን ደግሞ እርሷ አታውቅም

ቸኮ ነገር ነሽ”

በአንድ አውቶብስ ያውም የማውቃቸው የከተማችን ነጋዴዎች የታጨቁበት አውቶብስ በተደገፈችኝና በነካችኝ ቁጥር እየተሳቀቅሁ አብረን ተጓዝን፡፡ አዲስ አበባ ቆይቼ ስመለስ ሁልጊዜም ተወልጄ ያደኩባት ከተማ ትጠበኛለች፤ እታፈናለሁ፡፡ ሐሳቤ ከቤተሰቦቼ ጋር የተወሰነ ጊዜ ቆይቼ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስና፣ሥራ ለመፈለግ ነበር ግን ያላሰብኩት ነገር ሆነ፡፡ በትውልድ ከተማዬ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ሥራ አግኝቸ ጀመርኩ፡፡ ሥራዬ
መጀመሪያ አካባቢ አሰልቺ ነበር። የማንንም አጥርና ድንበር ስለካና ጓሮ ለጓሮ ስዞር እውላለሁ፡፡ ያውም ድንበሬ ተገፋ በሚል ነገረኛ እየተዘለፍኩና እየተዛተብኝ፡፡ የአገሬ ሰው ከአገሩ ድንበር የበለጠ፣ ለመኖሪያ ቤቱ ድንበር ልቡ ስስ መሆኑን ያወቅሁት ያኔ ነው፡፡ ለአገሩ የታፈሩ የተፈሩ የሚባሉ ሽማግሌ፣ የቡና ስኒ የማታስቀምጥ መሬት ከድንበሬ ሄደችብኝ ብለው፣ ሰው ካልገደልኩ ሲሉ አይቻለሁ፡፡ እንዲያውም እኔን ዝቅ
ያደረጉ መስሏቸው “ድንበሬን ማወቅ ከፈለከ ይኼን አባይ ሜትርህን ወዲያ ጣልና፣ አባትህን ሂድና ጠይቀው አጥሩን የሠራው እሱ ነው አሉኝ

ቤተሰቦቼ አብሪያቸው በመሆኔ በጣም ደስተኞች ስለነበሩ፣ እዚያው መቆየቴ ብዙም አላስከፋኝም፡፡ ከሮሐ ጋር መጀመሪያ አካባቢ ሰው አዬን አላዬን እያልን (እሷ እንኳን ግድ አልነበራትም ያው እኔው ነኝ አሳቻ ሰዓትና ቦታ፣ እየቆየን ግን ሰውም አውርቶ ሲወጣለት፣ በግልፅ መገናኘት ጀመርን፡፡ ያኔ ከሚተቸን ይልቅ “አይለያችሁ ባዩ ነበር የበዛው! መሐሪ ከነመፈጠሩም ተረስቶ ነበር፡፡ አንድ ሰው ብቻ መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶኝ ነበር ጋሽ አዳሙ የሚባል የሰፈር ሰካራም፡፡ ስለ እኔና ስለ ሮሐ እንዴት እንደሰማ እንጃ፣ ጠምዶ ያዘኝ፡፡ ቀን ላይ ሳይሰክር አግኝቸው ስላም ስለው፣ ዘግቶኝ
አለፈ፡፡ በቃ አኮረፈ፡፡ ማታ ታዲያ በዚያ ሲያልፍ …ልክ በራችን ላይ ቁሞ፣

“ያምባሰል ማር ቆራጭ ይወጣል

በገመድ፣ አደራ ቢሰጡት ይበላል ወይ ዘመድ ብሎ ይጮሃል፡፡ ትንሽ ይሄድና፣ ጅብ እንኳን የጓደኛውን ሚሰት አይነካም፡፡ በርግጥ ጓደኛው ቆስሎ ካገኘው ይበለዋል” ይላል፡፡ ብስጭት እላለሁ ሁል ጊዜ ይችኑን ነው የሚደጋግመው ከእኔ ወጭ እናቴም ሆነች አባባ አይገባቸውም ተራ የሰካራም ልፍለፋ ነበር የሚመስላቸው ።በእርግጥ የእኔ
ቤተሰቦች ከሮሐ ጋር የነበረንን ነገር አያውቁም ነበር፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ፣ አገር ምድሩ ሰምቶ ቤተሰቦቼ አልሰሙም፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ከሮሐ ጋር ለመጋባት ስንወሰን ነው የነገርኳቸው

ላገባ ነው !" አልኳቸው

እልልልልልልል፡ እሰይ እንዲያው ከዛሬ ነገ እነግርሃለሁ ስል እሰይ! " አለች እናቴ
በደስታ፡፡

የጥሩ ሰው ልጅ አገኘህ ?አለ አባባ፡፡

“ታውቋታላችሁ፣ የጋሽ ግርማ ልጅ”
ግርማ የቱ" አለች እናቴ ፊቷ ላይ ያለው ፈገግታ ልከ እንደ አምፑል ባንዴ ድርግም ብሎ ጠፍቶ፡፡

“ሮሐ"

"እኮ ሮሐ የመሐሪ"

"አንቺ ደግሞ የመቼውን ታሪክ ነው የምታወሪው …”

“የመቼስ ቢሆን እታደረግውም!” አለችና ዘላ ተነስታ ጆርዋን በሁለት እጇ ይዛ ወደ
ውስጥ ገባች፡፡እናቴ እንዲህ ስትሆን አይቻት አላውቅም! እንደ ኣንዳች ነገር ተቀያየረች፡፡ ተከትዬት ላሳምናት ብዙ ሞከርኩ፡፡ ወይ ፍንክች! እንዲያውም ሦስት ቀን ሙሉ ዘጋችኝ፡፡

አባባ ምኑም አልገባውም፣ አላስታወሳትም፡፡ ሮሐ በበኩሏ ለቤተሰቦቿ ስትነግራቸው አበዱ፡፡ ስንገናኝ ልክ እንደ አባቷ እየተንጎራደደች ያሉትን ሁሉ እየሳቀች ነገረችኝ “አንች
ለመሆኑ እዚያ ሰፈር የሚያልከሰክስሽ ምንድነው? ያስነኩሽ ነገር አለ? ሌላው ይቅር እንዴት ኅሊናሽ እሽ ይልሻል፣ ጓደኛውን? የዝናቡ ልጅ ከአባቱ ጋር ጠበኞች ነን፡፡
ቢሆንም ሞራል የሚባል ነገር አለ፡፡ እሱስ ምናይነት አንገት የሌለው ሰው፣ ነው ጓደኛው ታስሮ ምናይነት ዘመን ላይ ደረስን ባካችሁ? ሆሆሆሆሆሆሆሆ!”
በዚያ ብንል በዚህ የሁለታችንም ቤተሰቦች ባንገታችን ገመድ ቢገባ ይኼን ቅሌት አንፈቅድም አሉ፡፡ በተለይ እናቴ አታንሱብኝ አለች፡፡ ገና ነገሩን ሳነሳው ልክ እንደ ወባ ያንዘፈዝፉታል፡፡ ነውር የነውር ነውር መታሰቡስ አልውለደው እንጅ መሐሪ ልጄ ነው እስካሁን ልቤ አብሮት ታስሯል ልጀ ! ትላለች በቁጣ፡፡

አንድ ቀን ሮሐ እቤታችን መጣች፡፡ የቤተሰቦቼን ቤት በአንድ በኩል አስፈርሽ ሰፋ አስደርጌ ሰርቸላቸው ስለነበር፣ ልይላችሁ በሚል ሰበብ፣ ፍጥጥ ብላ መጣች፡፡ አሳዘነችኝ፡፡ እኔን ለማግባት እየተለማመጠች ነበር
👍4
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሀያ


#በአሌክስ_አብርሃም

“እጮኻለሁ ተይው አትጎትችው ይምጣ ይደብድበኝ የኔ የአዳሙ ጩኸት
እንዳይመስልሽ እንቅልፍ የነሳው! የራሱ ኅሊና ነው፣የራሱ ኅሊና አፍ ቢዘጋ ኅሊና ዝም እይልም የጅብ አገር ሕግ ባይምር፣ እንዴት ጓደኛ ጓደኛውን እይምርም? እንዴት ነው የሚኖረው እዚች ምድር ላይ? .…ድንበር መለካት ብቻ አደደለም መሐንዲስነት፣
ለራሳችን ስግብግብነትም ድንበር ማበጀት ነው:: ሁሉ ነገር ድንበር እለው፡፡ አቶ መሐንዲስ እኔም መሐንዲስ ነኝ፡፡ ሰው የሞራል ድንበሩን ሲያልፍ፣ እዚያ ነው
ድንበርህ እላለሁ፡፡ በሕግ አምላከ እላለሁ፡፡ በሕግ አምላክ ፍቅር በተዛነፈ መሠረት ላይ ሲቆም፣ ነገ ተንዶ ትውልድ ከመጫኑ በፊት በሕግ አምላክ እላለሁ ” እስኪበቃው ደንፍቶ በጨለማው ውስጥ ድምፁ እየቀነሰ …እየቀነሰ እየቀነስ ሄዶ ሰፈሩ ፀጥ ረጭ አለ፡፡ ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ፡፡
።።።
እናቴ በዚሀ ብላት በዚያ ብላት፣ የማግባቴን ነገር በጭራሽ አታንሳብኝ” አለች፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ጠቅልዩ አዲስ አበባ ገባሁ፡፡ አንድ የግል ሕንጻ ተቋራጭ ድርጅት ውስጥ ጥሩ ሥራ እግኝቼ ነበር፡፡ ሮሐ ከሦስት ወር በኋላ ተከተለችኝ፡፡ ጊዜ አላጠፋንም፤
ጓደኞቻችንን እማኝ አድርገን በፊርማ ተጋባን፡፡ ማታ ጓደኞቻችን ጋር ሰብሰብ ብለን ራት ተገባበዝን፡፡ ታዲያ እቤታችን ስንገባ ሮሐ ሞቅ ብሏት ነበር ልክ እንደ መፈክር እጁን ከፍ አድርጋ፡ የአብርሽ እናትና የኔ ቤተሰቦች ገደል ይግቡ!"ብላ ጮኸች፡፡ እናም አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ትዳርን እንዲህ ጀመርን፡፡

ሕይወት ያላትን ሁሉ ሳትሰስት የሰጠችን ወጣት እና ደስተኛ ባለትዳሮች ሁነን ነበር!
በተጋባን በዓመታችን ልጅ ወለድን …. እንደናቱ በጣም ቆንጆ ልጅ … ልጃችንን ዝም ብዬ ሳየው፣ የእኔ ልጅ ሳይሆን የሮሐ ወንድም ይመስለኛል፡፡ በብዙ ጓደኞች ተከበብን በብዙ መልካም ሰዎች …የሕይወት ነፋስ ሁልጊዜም በዙሪያችን የሚነፍሰው ፍቅር እና ደስታ ተሸክሞ ነበር፡፡ ልክ እንደጥሩ ተረት “በደስታና በፍቅር ይኖሩ ጀመር የሚል ፍጻሜ የሚመስል ሕይወት፡፡

ሮሐ ጥሩ አፍቃሪ ብቻ ሳትሆን፣ ተወዳዳሪ የሌላት ሚስት፣ ወደር የሌላት እናትም
ነበረች፡፡ ለዚህም ይመስለኛል፣ ሁልጊዜ ፍቅረኞች የሆንን መስሎ የሚሰማኝ፡፡ ሁልጊዜ ፍቅረኛዬ ነው የምትመስይኝ ስላት፣ “ባንተ ቤት ሮማንቲክ' ሆነህ ሞተሃል ባክህ በሰርግ ስላልተጋባን ነው ትለኛለች፤ ሁልጊዜም ገና አዲስ የተዋወኳት ሴት መስላ እንድትታየኝ በሚያደርገኝ የአሽሙር ፈገግታዋ ታጅባ፡፡ እያዳፉ እዚያና እዚህ ሲያላጋን የነበረው የህይወት ማዕበል ሰፊ እና ውብ ባሕር ላይ በእርጋታ ያንሳፍፈን ጀመረ፡፡
ዓመታት ነጎዱ፡፡ አልፎ አልፎ፣ በጣም አልፎ አልፎ ከባሕር ውስጥ ዘለው ወጥተው መልሰው እንደሚገቡ ትናንሽ ዓሳዎች፣ የመሐሪ ነገር ለቅፅበት ትዝ ይለኝ ነበር፡፡ ከሮሐ ጋር ግን ፈጽሞ አንስተነው አናውቅም፡፡ አንዳንዴ በውስጧ ታስታውሰው ይሆን የሚል
ሐሳብ ውል ይልብኛል፤ እናም በስሱ፣ በጣም በስሉ፣ ልክ እንደነፋሻ አየር የቅናት ስሜት ዳስሶኝ ያልፋል፡፡

ልጅ ከወለድን በኋላ የሮሐ ቤተሰቦች ኩርፊያቸውን ትተው እየመጡ ይጠይቁን ነበር እኛም በየዓመቱ ልጃችንን ይዘን ፋሲካን ከቤተሰብ ጋር ማሳለፍ ጀመርን፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እናቴ ልጄን ስትመለከት አለቀሰች ፡፡ እንግዲህ እናትነቷ ከዛ በላይ ለማኩረፍ አቅም አሳጥቷት ይሁን አልያም ዓይኔን አፍጥጬ ስሄድባት ውጣ የማትለኝ ነገር ሆኖባት፣ ኩርፌያችን በዛው እድሜው አጠረ፡፡ ሮሐ ታዲያ “ለማይረሳ ኩርፊያ ሰርጌን በሉት
ትላለች ፡፡
።።።
ተስፍሽ “ፔሌ' አብሮ አደግ የሰፈራችን ልጅ ነው፡፡ ጎበዝ እግር ኳስ ተጫዋች ስለነበር ነው ፔሌ ያልነው፡፡ ኳስ ከማሳደድ ይልቅ፣ ወንጀለኛ ማሳደድ ዕጣው ሆነና ከዩኒቨርስቲ ስመለስ፣ ፖሊስ ሆኖ አገኘሁት፡፡

ስቴዲየም ስንጠብቅህ በዩት በኩል ዙረህ ፖሊስ ጣቢያ ተገኘህ ?”አልኩት፣

ያው ነውኮ ሜዳው ይለያይ እንጂ እዚህም ያለው ሁለት ቡድን ነው፡፡ ፖሊስ አለ ወንጀለኛ አለ ሃሃሃሃሃ ብሎ ሳቀ፡፡ ማረሚያ ቤት ነው የሚሠራው፡፡ ከሮሐ ጋር በተጋባን በስድስተኛ ዓመታችን፣ ለፋሲካ በዓል ቤተሰብ ለመጠየቅ ሄድን፡፡ መምጣቴን እንደሰማ ተስፍሽ ሰላም ሊለኝ ወደ ቤት መጣ፡፡

በቀጣዩ ቀን ሻይ ቡና ካላልን ብሎኝ፣ ተያይዘን ወጣን፡፡ ተቀምጠን የልጅነታችንን ትዝታ ስናነሳና ስንጥል ቆይተን ስለመሐሪ ተነሳ፡፡ ውስጤ እየፈራ “መሐሪን ታገኘው ነበር?” አልኩት፡፡

“አዎ ያው ተረኛ ስሆን፣ አንዳንዴ ለሰላምታ ያህል እንተያያለን"

እንዴት ነው …” አልኩ፡፡ ለምን ራስህ ሂደህ አትጠይቀውም እንዳይለኝ እየፈራሁ፡፡

ታውቀው የለ ብዙ አያወራም፡፡ የሆነ ሆኖ ደህና ነው …መውጫው እየደረሰ መሰለኝ
አስራ ሁለት ይሁን አስራ ሦስት ዓመት ታሰረኮ ለማይረባ ነገር ….በስማም ጊዜው እንዴት ይከንፋል” አለና ተከዘ፡፡ ድንገት ምስጢር እንደሚያወራ ሰው ግራ ቀኙን አየት አድርጎ፣ ከአንገቱ ወደእኔ ሰገግ አለና …

አብርሽም አለኝ

"እ''

ለማንም ተናግሬ የማላውቀውን አንድ ነገር ልንገርህ ስለገረመኝ ነው። እስር ቤት
ለሦስት ዓመት አካባቢ ሰርቻለሁ በዚህ ሁሉ ዓመት መሐሪን የሚጠይቁት ሁለት ሰዎች ብቻ ነበሩ፡፡ አንድ እንኳን ሌላ ሰው መጥቶ አያውቅም፤ አንዷ ያው እትየ ሮሚ ነች (የመሐሪን እናት ማሚን ማለቱ ነው) አንዷ ማን እንደሆነች ገምት እስቲ

እኔጃ…ፍቅረኛ ምናምን ያዘ እንዴ …? አልኩ እንደማይሆን ባውቅም እንዲያው
ለመገመት ያህል፣

"ሳሌም !!” አለኝ !

“ምን?…ሳሌም !?” የምጠጣው ቡና ሸሚዜ ላይ እስኪረጭ ደነገጥኩ፡፡

ሳሌም የደፈራት ልጅ!”

“ባክህ አትቀልድ”

እናቴ ትሙት!”

እንዴ ምን ነካህ ተስፍሽ? የማይሆን ነገር

“ቢያንስ ለሁለት ዓመት አካባቢ እኔ ራሱ አላወኳትም ነበር! አንተ ራሱ ብታያት
አታውቃትም! ፈጽሞ አታውቃትም፡፡ ሁልጊዜ በየሳምንቱ ሐሙስ ከሰዓት አስር ተኩል ላይ ነው የምትመጣው፡፡ ያ ሰዓት ብዙም ጠያቂ አይበዛበትም ቆይ አንተ ታዲያ እንዴት አወካት ደግሞስ ፈረንጆቹ ውጭ አገር ወሰዷት አልተባለም
እንዴ?”
እኔም የሰማሁት እንደዛ ነበር አላውቅም! ብቻ ባጋጣሚ ነው ያወኩት፡፡ በነገራችን
ላይ የካቶሊክ መነኩሴ ሆናለች፣ እነዚህ ጥቁር ቀሚስ የሚለብሱት ..እዚህ ፈረንጆቹ ግቢ የሚኖሩት የሉም? ልክ እንደነሱ ነው የምትለብሰው፡፡ እዛው እኛ ሰፈር ፈረንጆቹ ግቢ ነውኮ የምትኖረው

እውነትህን ነው…?”

እናቴ ትሙት እያልኩህ”

"እና …”

አላመንከኝም ይገባኛል፣ ግን እሷ ነች ራሷ ማረሚያ ቤት በመጣች ቁጥር መጽሐፍና
የርቀት ትምህርት ሞጁል ነው ይዛ የምትመጣው ምግብ ምናምን ስታመጣ አይቻት አላውቅም! አንድ ቀን እንዲሁ ይች መነኩሴ ይኼን ሁሉ መጽሐፍ ለማነው የምታመጣው ብዬ በኋላኛው በር በኩል ወጣሁ በዚያ በኩል መጠየቂያው ቦታ ይታያል፡፡ እና ወደ እስረኞች መጠየቂያ ስመለከት ከመሐሪ ጋር ተቀምጠው ሲያወሩ አየኋት፡፡ ሥራዬ ብዬ ከዚያ በኋላ ነው መከታተል የጀመርኩት! ወሬ መውደድ ምናምን
ሳይሆን፣ አለ አይደል አብሮህ ያደገ የሰፈር ልጅ ከሆነች መነኩሴ ጋር ስታይ ዝም ብሎ የሚያጓጓ ነገር አለው፡፡ እና ስከታተላቸው በየሳምንቱ ሐሙስ ትጠይቀዋለች?” አለና ቡናውን ፉት አለ፡፡ዝም ብዬ አየሁት፡፡

እንግዲህ አለማመን ትችላለህ፡፡ ግን ልንገርህ፣ የሆነ ቀን ልክ እኔ ተረኛ ሁኜ ስትመጣ፣ መታወቂያዋን ተቀብየ አየሁት፡፡ ሳሌም ይላል፡፡ ሲስተር ሳሌም፡፡ እንግዲህ ግራህን ሲመቱህ ቀኝህን ስጥ የሚለው ትዛዝ ይኼው
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

እስከ ሐሙስ ከቆየህ፣ ለምን ራስህ አታያትም እውነቴን ነው ማረሚያ ቤት መሄጃ ጋ ካሉት ካፌዎች አንዱ በረንዳ ላይ ተቀምጠህ ስትገባ ማየት ትችላለህ”

እኔ ምን ትሰራልኛለች፤ ነገሩ ገርሞኝ ነው እንጂ”

"እሱማ እኔም በውስጤ ለብቻዬ ስገረም ነበር"

የዚያን ቀን እንዲቹ እንደፈጠጥኩ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ሌሊቱን አጋመስኩት፡፡ ለሮሐ አልነገርኳትም፡፡ ልጃችንን ይዛ ቤተሰቦቿ ቤት ነበረች፡፡ እንኳን ለሷ ልነግራት ለራሴም በማመንና ባለማመን መሀል እየወላወልኩ ነበር፡፡ሳሌም እንዴት የደፈራትን መሐሪን ያውም በየሳምንቱ ለዓመታት እየሄደች ትጠይቀዋለች…? ያውም ያንን በደል ይቅር ብላ? እኔ የዓመታት ጓደኝነቴን በዚያች አጋጣሚ አሽቀንጥሬ ጥዬ ይኼው ዓይኑን ካየሁት አስራ
ሦስት ዓመቴ፡፡ ምን እሱን ብቻ እንደ እናት ያሳደገችኝን ማሚን እንኳን እንዴት ነሽ
ብያት አላውቅም፡፡ ወደ ወቀሳ በሚቀርብ ግርምት ስገረም አደርኩ፡፡ መጨረሻ ላይ
የራሷ ጉዳይ ነው … እኔ መነኩሴ አይደለሁም” ብዬ ራሴን አጽናናሁ፡፡
የሳሌምን ዕድሜ በውስጤ አሰላሁት ሃያ አምስት፣ ሲበዛ ሃያ ስድስት ቢሆናት ነው፡፡

ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ፣ ድንገት ሳሌምን የማግኘት ሐሳብ ከውስጤ ገንፍሎ ወጣ፡፡በቀጣዩ ቀን ለሮሐ ጉዳዩን ሳልነግራት፣ እንዲሁ እስከ ቅዳሜ እንድንቆይ ነገርኳት፡፡ሐሙስ ነበር ወደ አዲስ አበባ ልንመለስ ያሰብነው፡፡

ችግር የለውም፣ ቤቢቾ ተመችቶታል፡፡ ዘና ብለህ የምትሠራውን ጨርስ” አለችኝ፡፡
ለምን? እንዴት? እንኳን አላለችኝም፡፡ እንዲህ ናት በቃ፡፡ የነፍሴ ምቾት ሮሐ፡፡ ጨረቃን አውርጄ ልከሰክሳት ነው ብላት፣ ቆይ መሰላል ልያዝልህ ከማለት አትመለስም፡፡

ሐሙስ ቀደም ብዬ ወጥቼ፣ ልክ ተስፍሽ ፔሌ እንደነገረኝ፣ በማረሚያ ቤቱ ዋና በር
በኩል ካሉት ካፍቴሪያዎች አንዱ በረንዳ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ልቤ እንደጉድ ይመታ ነበር፡፡ምን አስፈራኝ…? ምንም ወንጀል አልሠራሁም እያልኩ ለራሴ! ከተቀመጥኩበት ቦታ ሦስት መቶ ሜትር ርቀት ላይ፣ ለአስራሦስት ዓመት ዓይኑን ያላየሁት መሐሪ የሚባል ልጅ አለ፡፡ እንደማግኔት ሞገድ ወደ ውስጥ ሳበኝ ይሰማኛል፡፡ ማን ያውቃል፣ በዚች
ቅጽበት ትከሻውን እየከበደው ይሆናል፡፡ ድንገት ሃሃሃሃ የሚል ሳቅ ሰምቼ ስዞር

ተስፍሽ "ፔሌ" አጠገቤ እንደጅብራ ተገትሯል፡፡ መላ ሰውነቴን እፍረት አጥለቅልቆ፣እፍረት የቀላቀለ ሳቅ አብሬው ሳቅሁ፡፡

እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ” እለ።

"እንዴት አውቅህ ባክህ?”

ፖሊስ እይደለሁ?… ፊትህ ላይ አነበብኩት ወንበር ስቦ መንገዱ እንዲታየው አመቻችቶ እጠገቤ ተቀመጠና ሰዓቱን አየት አድርጎ በሹክሹከታ “አሁን ትመጣለች” ብሎኝ ፈገግ አለ፡፡

እንዲሁ ገርሞኝ ነው …አለ አይደል” አፍሬ ነበር፡፡

“ይገባኛል አብርሽ፣ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፤ እኔም እንዳንተው ነው የተሰማኝ፡፡እንዲያውም እንኳን መጣህ አብሮኝ የሚገረም ሰው አገኘሁ” ብሎ ትከሻዬን በወዳጅነት ቸብ አደረገኝ፡፡

ቡና አዘን እየጠጣን፣ እስረኛ ለመጠየቅ የሚገቡትን፣ ሰዎች ታሪክ ያወጋኝ ጀመር፡፡ “ይች ሴትዮ ባሏ የደርግ ባለሥልጣን ነበር ዕድሜ ልክ ፍርደኛ ነው… ያች በሷ ምክንያት በጩቤ ሰው የገደለ ቦይ ፍሬንዷን ነው የምትጠይቀው፣ ይኼ ባለባርኔጣው ሰውዬ " እያለ የጠያቂ ታሪክ ሲያሸመድደኝ ቆየንና፣ ድንገት በሹክሹክታ “መጣችልህ” አለኝ፡፡
ቢያንስ ከእኛ መቶ ሜትር እርቀት ላይ ረዥም ጥቁር ቀሚስ የለበሰች፣ ራስ ላይ
የሚጠለቅ ነጭ የጸጉር መሸፈኛ ሻሽ ያደረገች ረዘም ባለ ሰንሰለት አንገቷ ላይ የጣውላ መስቀል ያንጠለጠለች ወጣት መነኩሲት በፈጣን ርምጃ በእጄ ከበድ ያለ የጨርቅ ከረጢት አንጠልጥላ ስትመጣ አየሁ፡፡ እየቀረበች ስትመጣ ለአንዴ ነበር የለየኋት፡፡ ፊቷ ትንሽ ውፍረት ጨምሯል፡፡ ቀጥ ብሎ ወርዶ ጫፉ ወደላይ የሚቀሰር አፍንጫዋና ቀይ ፊቷ ግን ጩኾ ሳሌም ነኝ ይላል፡፡ ታጥፋ ወደ ማረሚያ ቤቱ የሚያስገባውን መንገድ ተከትላ ስትሄድ ከኋላዋ ፈዝዠ እያየኋት ነበር፡፡ ውስጤ ርብሽብሽ አለ፡፡ የዚያች ቀን ምሽት፣ እኔ እዚህ የተቀመጥኩት ሰውዬ ጓደኛዬ መሐሪን መጠጥ እንዳይጠጣ
ብከለክለው፣ ያችን ውስኪ ከሮሐ እጅ ሊቀበል ሲያቅማማ “ተው” ብለው፣ ይች ልጅ እንደዚህ ትሆን ነበር ወይ? ሰው መነኩሴም ይሁን ዓለማዊ፣ ምርጫው ከሆነ ችግር አይደለም፡፡ ሌሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ገፍተው ለዚህ ሲያበቁት ግን ያሳዝናል፡፡ እዚህ ጥቁር ቀሚስ ሥር ያለ ቁስለኛ ልብ ላይ የእኔም ስም የተመዘገበበት የጥላቻ መዝገብ ይኖር እንደሆንስ ማን ያውቃል?፡፡ እነሱ አሳስተውኝ ነው፣ ይቅር በይኝ ብሏት ቢሆንስ?፡፡ እኛን ጭዳ አድርጎ በእኛ ስም እጁን ታጥቦ ቢሆን፡
እህ …ዋሸሁ ” አለኝ ተስፍሽ፡፡

"እሷ ነች አይደለችም?"

“ይገርማል! ራሷ ነች …”

ነገርኩህ …ምንስ ፎር ፖይንት አምጥተን ዩኒቨርስቲ ባንገባ፣ ይች ይችማ አታቅተንም እኔ የምልህ ተስፍሽ፣ ማናገር ብፈልግ ክልክል ይሆን እንዴ? ማለቴ በእምነታቸው ከወንድ ጋር አያወሩም..?

ኦ! ልታወራት ፈለክ …?

“ያው ታውቃለህ እህቴ ማለት ነበረች፡፡ እጃችን ላይ ነው ያደገችው:: ዩ ኖው ቁም
ነገር ባይሆንም እንዲሁ ባናግራት ደስ ይለኛል፡፡ ሰላም ብላት ምናምን፣ እኔጃ፣ ምን ይመስልሃል ችግር አለው?”

እኔጃ!

ስልኳን ማግኘት ግን እችላልሁ መዝገብ ላይ ስለሚመዘገብ ከፈለክ አመጣልሃለሁ

እባክህ ተቸገርልኝ "

ግን ሕጋዊ አይደለም ብሎ ሳቀ፡፡ ማታ እቤት መጣና ቁራጭ ወረቀት እያቀበለኝ
በሹክሹክታ “ሲስተር ሳሌም ማለት አትርሳ” ብሎኝ እየሳቀ ሄደ፡፡

በቀጣዩ ቀን ጧት ወደአራት ሰዓት አካባቢ ደወልኩ፡፡ ስልኩ ይጠራል አይነሳም፡፡
ሁለተ ሞከርኩ፡፡ አይነሳም፡፡ ወደምሳ ሰዓት አካባቢ መልሶ ተደወለልኝ፡፡ በረዥሙ ተንፍሽ አነሳሁና። ሔሎ አልኩ…
“ጤና ይስጥልኝ፣ በዚህ ስልክ ከሁለት ሰዓት በፊት ተደውሎልኝ፣ ሥራ ላይ ስለነበርኩ አላነሳሁም ይቅርታ፣ ማን ልበል?” አለችኝ ረጋ ባላ ጨዋ ድምፅ፡፡ ልቤ ተመንጥቃ ልትወጣ ደርሳ ነበር፡፡

“ አዎ! አዎ! ኢሲስተር ሳሌምን ፈልጌ ነበር” አልኩ እኔም ረጋ ብዬ፡፡

“ ሲስተር ሳሌም ነኝ… ማን ልበል እርስዎን” አንቱ ልበላት እንቺ ልበላት፣ ግራ ገባኝ…

“እኔ እኔ አብርሃም እባላለሁ፡፡ በጣም ቆየ እንጂ እንተዋወቃለን፡፡ እኔጃ እንዴት
መግለፅ እንዳለብኝ …ብቻ የመሐሪ ጓደኛ ነበርኩ፡፡ እንችም ልጅ ሁነሽ ታውቂኝ ነበር፡፡ እንጃ ታስታውሽኝ እንደሆን …” ኤፌ ተሳሰረብኝ፡፡

“አብርሃም ?እንዴት ነህ? እንዴ በሚገባ አስታውስሃለሁ እንጂ! የት ሄደ እያልኩ
ስጠይቅ ነበር? እንዴት ስልኬን አገኘኸው ኡፍፍፍ ቀለል አለኝ፡፡

“ታሪኩ ረዥም ነው …የምኖረው አዲስ አበባ ነው፡፡ አሁን ለሰዓል ከባለቤቴና ከልጄ ጋር መጥቸ ነው፡፡” አልኩ፡፡ ማግባትና መውለዴን የቀባጠርኩት እንድትረጋጋ ብዬ ነበር፡፡

“ እግዚእብሔር ይመሰገን …”ብላ ዝም አለች፡፡

“እንዲያው እንዴት መጠየቅ እንዳለብኝ አላውቅም፣ ግን ከቅዳሜ በፊት በአካል ባገኝሽና አይቸሽ ብመለስ ደስ ይለኝ ነበር፣ ይቻል ይሆን?”

በሚገባ ይቻላል… የምትመጣበትን ቀን ከነገርከኝ ጥበቃዎቹ ጋ የመግቢያ ካርድ
እተውልሃለሁ”

ኦ …ዛሬ ሰዓት ካለሽ፣ ከሰዓት መምጣት እችላለሁ?

አዎ ትችላለህ… እባከህ ና! ከስምንት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዐስር ሰዓት ባለው መምጣት ትችላለህ፣ ስትደርስ ስምህንና ከእኔ ጋር ቀጠሮ እንዳለህ ንገራቸው ውስጤ በደስታ፣በስጋት እና በማላውቀው ስሜት ተናወጠ፡፡ እንዲህ ይቀላል ብዬ አላሰብኩም
👍31
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

ኧረ ለመሆኑ ምንድነው የምላት? “ምን ልታዘዝ? ብትለኝ ምን እላለሁ? በቃ እንዲሁ ላይሽ ነው የመጣሁት እላለኋ፡፡ በፍጥነት ሮሐ ጋ ደርሼ አብረን ምሳ በልተን ወደ ቤት ተመለስኩ፡፡ ያረፈችው ቤተሰቦቿ ጋር ነበር፡፡

የቀጠሮዬ ሰዓት ሲደርስ ለባብሼ ወጣሁ፡፡ እዚያው ሰፈራችን ያለው የፈረንጆች ግቢ” በዋናው በር ዙሬ በትንሽ የመስተዋት መስኮት በኩል ለተቀመጠው የጥበቃ ሠራተኛ ስሜንና ቀጠሮ እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ የተወሰኑ ካርዶች ካገላበጠ በኋላ፣ ፈገግ ብሎ በሩን ከፈተልኝ፡፡ ግቢው እጅግ ሰፊና ውብ ነው፡፡ አትክልቶቹ ያስደምማሉ፡፡ ፀጥታው ሌላ
ሩቅ አገር እንጂ ተወልጄ ያደኩበት ሰፈር አልመስልህ አለኝ፡፡ ሰፈሬ ውስጥ የታጠረ
ገነት፡፡ ጥበቃው አንድ ልጅ እግር ሰራተኛ ጠርቶ “ወደ ሲስተር ሳሌም ቢሮ ውሰዳቸው አለው፡፡ ልጁ እየመራ ወደ አንድ የሚያምር የድሮ ሕንጻ ወሰደኝና፣ የሳሌምን በር ጠቆመኝ፡፡ በሩ ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ “ሲስተር ሳሌም የሚል ወርቃማ ጽሑፍ ተለጥፎበታል፡፡ አንኳኩቼ ስገባ ሳሌምና አንዲት በዕድሜ የገፉ ፈረንጅ መነኩሴ በፈገግታ ተቀበሉኝ፡፡ እርስ በእርሳቸው በማላውቀው ቋንቋ አውሩና፣ ሴትዮዋ ሰላምታ ሰጥተውን እየሳቁ ወጡ፡፡

አብርሃም!” አለች እየሳቀች፡፡ እጂን መጨበጥ እችላለሁ ወይስ እምነታቸው ይከለክል ይሆን? ተንደርድሬ ማቀፍና እንደ ልጅነቷ ወደ ላይ ማንሳት እችላለሁ ወይስ ነው ነው? እያልኩ ግራ ስጋባ እጇን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ፡፡

“ሳሌም ይቅርታ ሲስተር ሳ…

ችግር የለውም ሳሌም በለኝ፡፡ እንዴት ነህ? ሎንግ ታይም' ኡ” አለችኝ ትክ ብላ
አየችኝ፡፡ ምን እንደምናገር ግራ ገብቶኝ እኔም አየኋት፡፡ ከዕድሜዋ በላይ ትልቅ ሰው መስላለች፡፡ የደፋችው የራስ መሸፈኛም እንደሆነ እንደዚያ እንድትመስል ያደረጋት እንጃ፡፡ እንድቀመጥ ጋበዘችኝ፡፡

ምቹው የእንግዳ መቀበያ ወንበር ላይ አረፍ አልኩ፡፡ ቢሮው ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ ነው:: ፊት ለፊቴ ተቀምጣ አንገቷን ሰበር እደረገችና

“ዩኒቨርስቲ መግባትህን ሰምቻለሁ ..ምን ተማርክ?” አለችኝ አወራሯ ረጋ ያለና እጅግ ትሕትና የተሞላበት ነበር፡፡

“ኢንጅነሪግ“

እግዚአብሔር ይመስገን አሁን እየሠራህ ያለኸው በዛው ዙሪያ ነው”

አዎ… አንድ የግል ድርጅት ውስጥ እየሠራሁ ነው፡፡ ይቅርታ እርሰዎ ነው የሚባለው አንች … ድፍረት እንዳይሆንብኝ አላወኩም” ፈገግ አለችና ችግር የለም፣ ዝም ብለህ አውራኝ…ለስላሳ፣ ውሃ አለ፤ ምን ትፈልጋለህ?”

“ውሃ ይሁንልኝ!” ጥግ ላይ ከቆመ ማቀዝቀዣ ለራሷም ለእኔም የታሸገ ውሃ አመጣች

ውሃዩን ተጎነጨሁና “ሁልጊዜ አስብሻለሁ
ወደ ውጭ አገር ሄዳለች የሚባል ነገር ሰምቼ ነበር.....

“እውነት ነው! አምስት ዓመት አካባቢ ጀርመን ነበርኩ” ምን እንደተማረች መጠየቅ ፈለግሁ፣ ግን ፈራሁ፡፡ እንደው ይኼ አስራ ሦስት ዓመት እንዴት አለፈ? እስቲ ንገሪኝ ማለት ፈለግሁ …ብቻ ብዙና የማያቋርጥ ነገር ልጠይቃት ፈልጌ ሁሉንም ነገር ተውኩትና፣ ለቅጽበት ዝም ተባብለን ቆየን፡፡ እንደምንም ራሴን እደፋፍሬ በቀጥታ እንዲህ እልኳት…
“ሳሌም! ምንም ነገር ተመልሼ ላስታውስሽ አልፈልግም ግን ሁልጊዜ እራሴን እንደወቀስኩና እንደተጸጸትኩ ነው፡፡ መቼም ስለኔና መሐሪ ታውቂያለሽ፣ ወንድሜ ማለት ነበር፤ የተፈጠረው ነገር ከተፈጠረ በኋላ፣ ለአሥራ ሦስት ዓመት ዓይኑን አላየሁትም፡፡ አፈርኩ፣ ዓይኑን ለማየት ተሳቀቅሁ! በየቀኑ ሳላስበው ውዬ አላውቅም፡፡ ግን በቃ፣ እንዴት ልበልሽ፣ የዛሬ አሥራ ሦስት ዓመት እንደታሰረ አካባቢ፣ እኔና ሮሐ ልናየው ሂደን የተፈጠረው ነገር ትንሽ የሚያሳፍር ነገር ነበር፣ መሐሪ እኔንም ሮሐንም ለሆነው ነገር ወቀሰን፡፡ የዚያን ቀን ምሽት ሮሐ መጠጥ ይዛ ነበር የመጣችው፣ እኔም
አትጠጣ አላልኩትም

“አውቃለሁ አብርሃም፣ አትጨነቅ፣ ሁሉም ነገር ይገባኛል”

“ታንኪው! ትንሽም ቢሆን ለተፈጠረው ነገር የእኔ ስህተት እለበት ብዬ ነው የማስበው፡፡የዚያን ምሽት እንዳይጠጣ ብከለከለው ኑሮ ወይም አብሬው ባድር ኖሮ ብቻ ብዙ ነገር ያሳቅቀኛል፡፡ ከዚያ በኋላም ብዙ ነገር እጠፋሁ፡፡ ቤተሰቦቹን ሄጄ ኤልጠየኳቸውም ጋሼ ሲያርፍ እንኳን ለቅሶ አልደረስኩም፡፡ በዚያ ላይ ስለ ሮሐ ልነግራት አስቤ አፌ ላይ አድርሼ ተውኩት፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ንስሐ አባቱ ፊት እንደቀረበ ሰው መናዘዝ
ጀመርኩ፡፡ ዝም ብላ ስታዳምጠኝ ቆይታ፣

ራስህን አትውቀስ፣ ማንም ሰው የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ ሕይወት መቼም ያለፈውን ለመቀየር ዕድል አትስጠንም፣ ወደፊት በተስፋ መጓዝ ብቻ ነው፡፡ መሐሪን በየሳምቱ ማረሚያ ቤት እየሄድኩ እጠይቀዋለሁ

ኧረ? እንዳላወቀ ሰው ለመሆን ሞከርኩ፤ ድራማው ተሳክቶልኝም እንደሆን እንጃ!

ዓዎ! በአንዳንድ ምክንያት ሰዎች እንደምጠይቀው እንዲያውቁ አልፈለኩም፡፡ ያው ይገባሃል መቼም፡፡ሁልጊዜ ስለ አንተ ያነሳልኛል፤መሐሪ ኤልተቀየመህም፤ እንደውም የእውነት ናፍቆሃል፣ ቢያይህ ደስ ይለዋል”

እውነት!?”

አንቺ በእምነትሽም ምክንያት ይሁን በተፈጥሮ፣ ነገሮችን የምትቋቋሚ ሆነሽ ይቅር አልሺው፣ ጋሽ ዝናቡ በተከበረበት አገር ተዋርዶ፣ እዝኖ፣ ራሱን ያጠፋው በማን ምክንያት ነው?..በመሐሪ ምክንያት ነው! ..አባቴ ማለት ነበር፣ አብሮ አሳድጎናል ድምጼ እየጨመረና እንባ እየተናነቀኝ ነበር፡፡

ሳሌም ዝም ብላ ስትመለከተኝ ቆዬች “መሐሪን ይቅር አላልኩትም፣ እንጃ ለዚያም የሚበቃ ልብ ያለኝ አይመስለኝም፡፡ መሐሪን የምጠይቀው፣ ከጎኑ የሆንኩት፣ ሌላው ይቅርና በራሴ ምርጫ እዚህ ለመሥራት መርጨ የተመለስኩትና በየቀኑ ከማስታውሰው
ሕመም ጋር እየታገልኩ የምኖረው ደግ ስለሆንኩ ይመስልሃል? ከአንተም ከሮሐም የተለየ መንፈሳዊ ከፍታ ላይ ስላለሁ ይመስልሃልን አይደለም! እውነታው መሐሪ ምንም ወንጀል የሌለበት ንጹህ ልጅ ስለሆነ …ካለ ሥራው ዕድሜ ልኩን በእስር ስለሟቀቀ ነው

“ተይ እንጂ! ምንም ወንጀል የለበትም?” አጉል ሃይማኖተኝነት መሰለኝ ተበሳጨሁ!

“አብርሃም! የዚያን ቀን ምሽት መሐሪ አልደፈረኝም” ፍጥጥ ብዬ እየኋት፡፡

የደፈረኝ ጋሽ ዝናቡ ነው

“ምን? …ምንድነው የምታወሪው ሳሌም”
“እውነቱን ማወቅ ከፈለክ ይኼው ነው! … መሐሪ የደረሰው በደም ተጨማልቄ ሰውዬው አፌን አፍኖ እንዳልናገር ሲዝትብኝ ነበር፡፡ አቅፎኝ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ አብሮኝ ሲያለቅስ፣ እስከዛሬ ዓይኔ ላይ አለ፡፡ ወዴት ሊወስደኝ እንደነበር እንጃ ብቻ ይዞኝ ከዚያ
ክፍል ሲወጣ፣ ኮሪደሩ ላይ ከእናቴ ጋር ተገጣጠሙ፤ እናቴን ሳይ ጮህኩ ኡኡ አልኩ፡፡ ያን ለታ ማታ የለበስኩት ነጭ ቀሚስ ከፊትም ከኋላም በደም ተጨመላልቆ ነበር የሆነው ሆነ”

“እና…"

“እንድም ሰው መሐሪ ደፈረኝ አላልኩም፡፡ መሐሪ ራሱ ነበር ላገኘው ሰው ሁሉ
እንደደፈረኝ ሲያወራ የነበረው:: ለአንተና ሮሐ፡ ፍርድ ቤትም ጭምር አመነ፡፡ ማንም

ሰው አባቱን አልጠረጠረም፡፡ መሐሪ የዚያን ክፉ ሰውዬ ክብር ለመጠበቅ ሲል ከምንም በላይ እናቱ ተሳቅቃ እንዳትሞት፣ እንዳትሰማ፣ ራሱን መስዋዕት አደረገ፡፡ እኔም ተንፍሼ አላውቅም፡፡ ከእኔና ከመሐሪ ቀጥሎ አንተ መስማትህ ነው፡፡ ሰውዬው ሥራው አሳዶት ራሱን አጠፋ መሐሪም ውድ የወጣትነት ዘመኑን በእስር ቤት አሳለፈ፡፡ ከፍ ካልኩ በኋላ
የዚያን ወንጀለኛ ሰውዬ ድርጊት ለመደበቁ ለረዥም ጊዜ አዝኜበት ነበር፡፡ ግን ደግሞ
ማሚ፣ የእኔም እናት ናት፡፡ ውርደቷ ውርደቴ ነው፡፡ መሐሪ ዕድሜውን፣ እኔም የታፈነ በደሌን ለማሚ አዋጥተን ጐዳቷን ለመቀነስ ሞከርን፡፡
👍1