አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሴት_እና_የነገር_ቱባ


#በሕይወት_እምሻው


ቁርሳችንን ለኮፍ ለኮፍ አድርገን ለመውጣት እየተጣደፍን ነው ያለ ቅጥ ረፍዶብናል፡፡

“ብርድ ነው ፀሐይ..? እስቲ ውጣና ዕይልኝ!” አልኩት፡፡ “ሹራብ ልልበስ ሸሚዝ?” በሚል ከተመሣቀለው ቁምሣጥን ልብስ ለመምረጥ
እየተጣደፍኩ፡፡

በቁሙ፧ በግማሽ ልብ ቴሌቪዥን እያየ የሚጠብቀኝ ባሌ፣ መልስ አልሰጠኝም፡

“በረከት!” አልኩት እየጮኽኩ፡፡

“ወ.. ይ...” አለና ከሲ ኤን ኤንዋ ዜና አንባቢ ዐይነን አንስቶ እኔ
ላይ አሳረፈ፡፡

“አትሰማኝም እንዴ?”

“አልሰማሁም...ምን አልሽኝ....?”

“ወይ ጉዴ...! ብርድ ነው ፀሐይ... ውጣና ዕይልኝ... ልብስ እንድመርጥ...”

“ወይ ቆንጂት!... ገና አልለበስሽም እንዴ... ቶሎ ቶሎ በይ እንጂ አለኝ እንደ ነገሩ እያየኝ፡፡

“ወየው.... ከላይ ብቻ ነው የቀረኝ... ዕይልኝ ይልቅ....”

ተበሳጭቻለሁ፡፡

በግብር ይውጣ አካሄድ ወጣና መለስ ብሎ፣ “ደመና ነው... ሹራብ
ያዢ!” አለኝ፡፡

ይሄን ጊዜ ! ከሱሪዬ ጋር የሚሄድ ሹራብ ፍለጋ ቁምሳጥኔን ማተራመስ ጀመርኩ፡፡

“እረ ቆንጂት በፈጠረሽ እንውጣ...! ይቺ ዐሥር ደቂቃ ካለፈች
ታውቂያለሽ የታክሲ ሰልፉ መከራ ነው” አለኝ ቴሌቪዥኑን እያጠፋ፡፡

ሹራብ ፍለጋዬን አቆምኩና ዞር ብዬ ዐየሁት፡፡

ደግሞ ልንጨቃጨቅ ነው፡፡

አሁን አሁን ከምንም ነገር በላይ አብዝተን የምናደርገው ነገር፣
መጨቃጨቅ ነው፡፡

ስለ አለባበሴ እንጨቀጨቃሰን፡፡

ስለ ከጓደኞቹ ጋር ማምሸቱ እንጨቃጨቃለን፡፡

ስለ ገንዘብ አያያዜ እንጨቃጨቃለን፡፡

ስለ ልጆቻችን ጠባይ እንጨቃጨቃለን፡፡

ስለ እናቱ እኔን አለመውደድ ጉዳይ እንጨቃጨቃለን፡፡

ስለኔ ታናሽ ወንድም መበላሸት እንጨቃጨቃለን፡፡

ስለምንም ነገር እንጨቃጨቃለን፡፡

ሹራብ ነው የቀረኝ... ታገሰኝ..." ኣልኩት፤ “ዋ ሌላ ነገር ተናገረኝና
ጉድ ይፈላል” በሚል ዓይነት ድምፅ፡፡

ግን ሌላ ነገር ተናገረኝ፡፡

“ስንት ሰዐት እታገስሻለሁ....? ልብስ ለመልበስ አንድ ሰዓት ሊያውም እንዲህ እረፍዶ?”

አሁን በደንብ ልንጨቃጨቅ ነው፡፡

በኔ በረፈደ ሰዐት ላይ ልብስ ለመልበስ መቆየት መነሻነት የተጀመረው ጭቅጭቅ መዳረሻው የት እንደሆነ አላውቅም..
ጭቅጭቃችን የራሱ ቦይ አለው፡፡ ራሱ እየቀደደ የሚፈስበት ቦይ::
ከቀበና ወንዝ ተነስቶ ሜዲትራኒያን የሚገባበት የራሱ ረጅ....ም....ቦይ፡፡

“አንድ ሰዐት አልፈጀብኝም! አታጋንን፤ ማጋነን ስትወድ "አልኩት፣ ሰማያዊውን ሹራቤን አውጥቼ እየለበስኩ፡፡
“እኔው ነኝ አጋናኙ...?” አለኝ ደክሞት ውሎ እንደመጣ ሰው ሶፋው ላይ ተመልሶ እየተቀመጠ፡፡

“ምን ማለት ነው እኔው ነኝ አጋናኙ..? አንቺ ታጋንኛለሽ ለማለት ነው...?” አልኩት ገንፈል ብዬ፡፡

ዝም አለ፡፡

በአሸናፊነት መንፈስ ሹራቤን ለብሼ የቁምሳጥኑ መስታወት ጋር
ሄጄ ከሱሪዬ ጋር ያለውን ቅንጅት አየሁ፡፡

አያምርም፡፡

ሮዙን ሹራብ ባደርግ ይሻለኛል፡፡

ሰማያዊውን ሹራብ አውልቄ አልጋ ላይ ጣልኩና ሮዙን ሹራብ መፈለግ ስጀምር የሆነ ነገር ሲል ሰማሁት፡፡

“ምን አልክ?”

“ምንም አላልኩም ቆንጂት ”
“ለምን ምንም አላልኩም ትላለህ ...? የሆነ ነገር ስትል
አልሰማሁህም አሁን...?” ወደ ሳሎን መጥቼ አፈጠጥኩበት፡፡

“ምንም አላልኩም.... ....... በይ ይልቅ ፤ ትናንት ብፈልገው አጣሁት... የእዚህ ሪሞት አንዱ ባትሪ የት ገባ...? ወድቆ ጠፍቷል” አለኝ፣ መክደኛ የሌለውን የቴሌቪዥናችንን ሪሞት ኮንትሮል
አገላብጦ እያየ፡፡

“ምን እኔን ትጠይቀኛለህ... አንተ ነህ ተሰክተህበት የምትውልበት
ቲቪውን፤ ...ራስህ አትፈልገውም...?” ሹራቤን ፍለጋ እየተመለስኩ መለስኩ፡፡

“እኔ የት እንዳለ ባውቅ አንቺን ምን አስጠየቀኝ?”

“እንጃ! ምናልባት ለሁሉ ነገር ጥፋተኛ የምታደርገው እኔን ስለሆነ”

“ለሁሉ ነገር?”

አዎ! ....ቲቪ ተበላሸ... ቆንጂት ምን አረግሽው...? የቤቱ ግድግዳ
ለቀቀ ፤ ቆንጂት ምን ስትሰሪ እንዲህ ሆነ..? የልጆቹ ፀባይ ተበላሽ
ቆንጂት አንቺ እኮ ነሽ እያቀበጥሻቸው...? አሁን ደግሞ ሚጢጢ ባትሪ ጠፋ እኔኑ ጥፋተኛ...”

ሳላሰበው ሁለመናዬ ሲግል እየተሰማኝ ተናገርኩ፡፡

“በ...ይ ተይው እገዛለሁ... ሆሆ!” ብሎ ሪሞት ኮንትሮሉን ጠረጴዛው ላይ ሲወረውር ተሰማኝ፡፡

ግዛ አንተ ምን አለብህ...! ሽሮ በርበሬ ብዬ የምሣቀቀው እኔ...
አንተማ መዥረጥ አድርገህ ያሻህን ትገዛለህ..." አልኩ።ግለቴ ሳይበርድ፤ ሮዙን ሹራብ እያደረግኩ፡፡

“ታዲያ ከጠፋ ምን አድርግ ትይኛለሽ...? ደሞ ለባትሪ...”

“ደሞ ለዚች እያልክ ነው ገንዘብ የምታባክነው፡፡ ገንዘብ በትንሹ
ካልተቆጠበ ብዙ ይሆናል...?”

“ደሞ አሁን ገንዘብ አባካኝ ሆንኩ..!.”

ድምፁ ይንቀጠቀጣል፡፡ ድምፁ ከተንቀጠቀጠ ተናዷል ማለት ነው፡፡

“አይ ቆጠብክልኝ እንጂ! ቆጠብክልኝ የኔ ጌታ! ይሄ በየማታው የምትጋተው ድራፍት እንኳን ቢደማመር የልጆቹን አስጠኚ የወር ደሞዝ ቀጥ አድርጎ አይችልም....?” አልኩት ድምጼን ከፍ አድርጌ ፤ ወገቤን በነገረኛ ሴት ቄንጥ ይዤ ወደ ሳሎን እየተመለስኩ፡፡

ፊቱ ቀልቷል፡፡

“በየማታው...? እኔ ነኝ በየማታው ድራፍት የምጋተው....? ከቅዳሜ
ውጪ ...ሊያውም ከሁለት ድራፍት በላይ ስጠጣ አይተሸኛል....?
ደሞ ለነገሩስ ለልጆቹ አስጠኚ ይቀጠር ስልሽ... ተወው ፤ ማቲ እየመጣ እንደፈለጋቸው ያስጠናቸዋል' ብለሽ አይደለም የተውነው እንዴ!”

እሱማ ነበር! ....የሚሆን መስሎኝ፡፡ ገንዘብም እንዲቆጠብ ብዬ .. ግን
ምስኪን ወንድሜን በሳምንት ሦስቱ ለሚመጣው እየገላመጥክ
ከቤቴ አራቅከው... አሁን እስቲ ምን አደረገህ ...? ልጆችህን በነጻ ባስጠናልህ...”

አሁን ቅድም እንደ ዋዛ የጣልኩትን የአንገት ልብሴን እየፈለግኩ
ነው፡፡

“ተይ ቆንጂት ግፍ አትናገሪ፡፡ እኔ ነኝ ወንድምሽን ከዚህ ቤት
ያራቅኩት? ራሱ አይደለም፣ ልጆቹ ማቲ ሲጋራ ሲያጨስ እያዩ እንዳይሰላሹ ምከሪው' ስልሽ ሰምቶ እዚህ ቤት አልመጣም ያለው...? እሱ ዱርዬ በሆነው ለልጆቼ ማሰቤ ነው እኔን
የሚያስወቅሰኝ!”

አሁን በማቲ መጣብኝ፡፡ የማቲ ነገር እንደማይሆንልኝ እያወቀ በጠዋቱ በማቲ መጣብኝ፡፡

“በረከት! ማቲ ዱርዬ አልሆነም... ወጣት ነው….. ሊሳሳት ይችላል...
እንደ ታላቅ ወንድም ልትመክረው ሲገባ እንደ እብድ ውሻ ከገዛ እህቱ ቤት አባረርከው... ይሄ ልክ ነው?” አልኩት የአንገት ልብሴን ፍለጋ ትቼ እያየሁት፡፡

“እህ... ተይው... አንቺ ልጄ..... ታክሲው... ይልቅ በናትሽ ለብሰሽ
ጨርሺ አሁን... እንሂድ፡፡” አሁንም ያንን ሪሞት ኮንትሮል እያገላበጠ ያያል፡፡

እንዲህ በነገር እየለበለብከኝ ምኑን ከምኑ አድርጌ ልልበስ.
ስካርፌ ጠፋብኝ” አልኩት ቀዝቀዝ ብዬ፡፡

“ራስሽ በጀመርሽው ነገር መልሰሽ እኔን... ይልቅ አሁን ጨረስሽ..
እንውጣ?” አለኝ ቦርሳውን እንስቶ እያነገተ፤

“ምነው ስታየኝ ያልጨረስኩ እመስላለሁ....?”

ያለ እቅዱ ነገረኛ ድምፄ ተመለሰ፡፡

“ደሞ ይሄ ምን ማለት ነው?”
“የለበስኩ አልመሰልኩም?... ለነገሩ ስታየኝ አይደል የምታውቀው በጠዋት
ቲቪ ላይ እያፈጠጠክ... ሦስተኛ ጡት አብቅዬ ባድርም እስከ ሁለት ወር የሚታይህ አይመስለኝም”

ሣቀ፡፡

እኔ ግን አልሣቅኩም፡፡ እየተጨቃጨቅን ሲስቅ ያናድደኛል።

“ሶስተኛ ጡት...? ምን?” አለኝ አሁንም እየሣቀ፡፡
👍1
#ገንዘብ_መሆን_የተሳነው_ዕውቀት


#በሕይወት_እምሻው

ከታናሽ ወንድሜ ጋር በዲግሪ ፕሮግራም ተምሮ የተመረቀውን ዳንኤል፣ የኮብልስቶን ሥራን ሲያስተባብር አገኘሁት፡፡

ሻይ ይዘን፤ ስለ የተማሩ ኮብልስቶን ጠራቢና ደርዳሪዎች፤ ተብሎ...
ተብሎ... የተተወውን ክርክር እንደ አዲስ ቀሰቀስነው፡፡

ዳንኤል ፣ “ሥራ አጥተን ቤት ቁጭ ከምንል ገንዘብ እስካገኘን
ብንሠራ ምናለ?” ብሎ ነገሩን ሥራ ከመናቅና ካለመናቅ ጋር አጣብቆት ብዙ ሞገተኝ፡፡

“ሥራ ገንዘብ ማግኛ ነው ፤ ይሄ ደግሞ ገንዘብ ይከፍላል፤ ኀጢአቱ ምንድነው?” ብሎ ተከራከረኝ፡፡

ዳንኤል ልክ ነው፡፡ ድህነት መለዮ ልብሳችን በሆነበት ሀገር ገንዘብ
የሚያስገኝ ነገር ሁሉ እንደ ስኬት እንደሚቆጠር ግልጽ ነው፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ እህል ይሆናል፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ ቤት ኪራይ ይከፍላል፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ የታክሲ ይሆናል፡፡

ያን ያህል ቀላል ነው፤ ይገባኛል፡፡ የእኔ ችግር ከአጠቃላይ ክስረቱ ጋር ነው፡፡ የእኔ ችግር እነዚህ ልጆች ለዓመታት "ሲማሩና ሲመራመሩ" ከርመው፤ ያልተማረና ያልተመራመረ ሰው
በሚችለው ሥራ ላይ መሰማራታቸው... የእነዚያን ሰዎች የሥራ ዕድል ከማጣበባቸው ነው፡፡ ለእኔ ይሄ ክስረት ነው።

ሰለዚህ የመንግሥት ሚዲያዎቻችን፣ እነዚህ ልጆች የምርቃት ሱፋቸውን አውልቀው በሥራ ቱታ ድንጋይ ሲፈልጡ መዋላቸውን እንደ ታላቅ ስኬት ሲያቀርቡት አይገባኝም።

“በሥራ ክቡር ነው!” መልካም አባባል፤ ልሽቀታችንን ሲደብቁት ደስ አይለኝም፡፡ ችግሬ ከልጆቹ መሥራት አይደለም፡፡ ከነገሩ አቀራረብና አረዳድ ነው፡፡

ሥራቸው ልጆቹን ሊያሳፍር ባይገባም፤ እንደ ሀገር ግን ሊያኮራን የሚገባ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ልጆቹ ዲግሪ ለማግኘት ብዙ ከፍለዋል፡፡ ሀገሪቷም ካላት ትንሽ ሀብት ብዙ ከፍላለች፡፡

...እና በረጅሙ ስናስበው፣ ዛሬን በልተው ቢያድሩም የትምህርት ሥርዓታችን ክስረት ባንዲራዎች ናቸው፡፡

ዛሬ ትምህርት ላይ ላሉ፣ ማበረታቻ ሳይሆኑ ማስጠንቀቂያ ናቸው፡፡

ያልተማረ ሰው ሊሠራ የሚችለውን ሥራ ተምረው ስለሚሠሩ፣በልተው ቢያድሩም ለሀገር ውድቀቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን፣ ይህ የእነሱ ጥፋት አይደለም፡፡ መብላት አለባቸው፡፡ መኖር አለባቸው፡፡

ስለዚህ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ዕውቀት ልንሰጣቸው ስላልቻልን ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ጉልበታቸውን ተጠቀሙ:: በዚህ ደግሞ ልናፍር እንጂ ልንኩራራ የሚገባ አይመስለኝም፡፡

💫አለቀ💫

ምን ትላላችሁ የቻናሌ ተከታታዎች ይሄ ጉዳይ የሚመለከታችሁም ልትኖሩ ትችላላችሁ እስቲ ሃሳባቹህን አድርሱን

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
ጀርመናዊው ጉተ መሰለኝ፣ “ለልጆቻችን መስጠት ያለብን መሠረታዊ ነገሮች ሁለት ናቸው ፤ ሥርና ክንፎች” ያለው:: ሥሩ ማንነታቸውን፤ ክንፎቹ ደግሞ ትልቅ የመሆን ህልማቸውን የሚወክሉ ይመስለኛል።

የዛራ እና ቻንድራ ፊት የታተመበት ልጆቻችን የሚማሩበትን ደብተር ሳይ ነው ይህ ትዝ ያለኝ፡፡ የሚማሩበት ደብተራቸው
እንኳን፣ በህንድ እና ቱርክ የፍቅር ታሪክ እንዲነሆልሉ እንጂ ፤
በባዕድ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ስምና ገድል እንዲፈዙ እንጂ፤ “እኔ ማነኝ?” ብለው እንዲጠይቁ የማያደርጋቸውን ልጆች ለማሳደግ እየባዘንን መሆኑን ሳስብ ነው ጉተ ትዝ ያለኝ፡፡

"ምን መሆን እፈልጋለሁ? ምንስ መሆን እችላለሁ?" ብለው መጠየቅ እና ማሰብ የማይችሉ ተማሪዎችን በመፍጠር ላይ ታች እያልን ነው፡፡

አዎ.. . እንዲህ እንደዋዛ ....

በየቤቱ እና በየትምህርት ቤቱ፣ ሥር የሌላቸውን ዛፎች እየተከልን ነው። መብረር የማይችሉ ወፎችን እያረባን ነው።

#በሕይወት_እምሻው

💫ጨረስኩ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ሀገሬ_ኀምሳ_እግር_ናት

የሀገሬ ወንዝ ዋናው ካነገባሩ ሲዘረዘር በንዴት እበግናለሁ።ፉት እንለው፣ ለቅለቅ እንልበት ውሃ ፍለጋ ከከተማ እስከ ገጠር
የምንማስነውን እኛን አስቤ ብግን እላለሁ፡፡

የሀገሬ ቀንድ ከብት ቁጥር፣ ከአፍሪካ አንደኛ” ተብሎ ሲጠራ በንዴት እንተከተካለሁ፡፡ ወተት እየተራጨን በማደግ ፈንታ የላም ወተት የዋልያ ወተት ይመስል ብርቅ የሆነብንን እኛን አስቤ ትክን እላለሁ፡፡

የሀገሬን ስፋት ሳስብ እናደዳለሁ፡፡ የእኔ የምንለው ክብሪት ሣጥን ታክል ቦታ አጥተን በየፊውዳሉ ቤት በጭሰኝነት የልጅነት ሀብታችንን ለምንገብረው እኛ ተቆርቁሬ፣ በንዴት እንገረገባለሁ፡፡

ይሄ ሁሉ እያላት ለእኛ ያልተረፈችው ሀገሬ፣ ሀብት እያላት ድሃ ናት፡፡ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

ያ..... ሁሉ...... እግር እያለው ዘልአለም እንደሚድኸው ቆሞ እንደማያውቀው ኀምሳ እግር፡፡

ከምትድህበት አንስቶ በኀምሳውም እግሯ የሚያቆማት ጎበዝ እስክታገኝ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

#በሕይወት_እምሻው
#ገዳዬ_ገዳዬ


#በሕይወት_እምሻው

ፀሐያቸው ጠልቃ በሰው ሀገር መሽቶብኝ ነበር፡፡ ጨልሟል የተለመደውን አውቶብሴን ተሳፈርኩበ።

አዲስ ነገር የለውም፡ ሁሌም የምጠብቀው ያ ሁሌም በጠበቅኩት
ሰዐት የሚመጣው የማይዛነፍ የዕለት ውሎዬን የሚደመድመው አውቶብስ ነው።

እንደተቀመጥኩ፣ ሰንደቅ የሚያሰቅል ቁመት ያለው! ውብም፤ሎጋም ኢትዮጵያዊ ወንበር ሲፈልግ አየሁት።

አውቶብሱ ውስጥ ብዙ ክፍት ወንበሮች ነበሩ፡፡ ወደ መስኮቴ ዞርኩ
እና ጸሎት ብጤ አደረግኩ፡፡ ብታውቁኝ ለዚህ ዓይነት ነገር ጸሎትን ያህል ነገር የማባክን ሰው አይደለሁም ግን... ጸለይኩ፡፡

ጸሎቴ ተሰማ መሰለኝ እጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ፡፡

ከዚያ ምን ሆነ?

“ሃ...ይ..." አለኝ፡፡ ዝም ብሎ ሃይ አልነበረም፡፡ ይሄ..አንድ ሃ' እና ስድስት 'ይ ያለው ሃይን ታውቁታላችሁ? እሱ ነው! እንደሱ ነው ሃይ ያለኝ፡፡

ዞር ብዬ ሌላ ትንሽ ጸሎት አደረስኩ፡፡

ፈጣሪ በትንሽ ፀሎት ይሄን መለሎ አጠገቤ አምጥቶ ስላስቀመጠልኝ፣ አስቀምጦም እንዲህ ያለውን ሃይ እንዲለኝ ምላስ እና ከንፈሩን ስላቀናጀልኝ ሌላ ፀሎት አደረስኩ።

አስቡት..የመጀመርያው ጸሎቴ ሳይሰማ ኖሮ ይሄ አማላይ ይሄ ሳያነጣጥር ገዳይ አጠገቤ ይቀመጥ ተቀምጦስ ሰላም ይለኝ ነበር....?

እንዳልኳችሁ አውቶብስ ተሳፍሬ ዐይነ ግቡ ሰው በተሳፈረ ቁጥር፣
ወንበር በፈለገ ቁጥር እንዲህ አይነት ጸሎት የምጸልይ አይነት ሴት
አይደለሁም፡፡

የፈለግኩትን ሰው ለማግኘት ቃላትን የማሰናዳ፣

የከንፈር ቀለሜን የማደምቅ፣

ዐይኖቼን የማስለመልም፣

ጡቶቼን ከካኔተራዬ ገፍትሬ የማወጣ፣

መቀመጫዬን ያለ አቅሙ የማንቀጠቅጥ ሴትም አይደለሁም፡፡

ሴት ነኝ፡፡

ልቤን በልቡ ይቀይረኛል በሚል ተስፋ ወንድኝን በጭኖቼ ክፍተት የማስገባ አለመማረክ የሰለቸኝ ለድርያ እንጂ ለትዳር አለመፈለግ ያቆሰለኝ የትርጉም አልባ አጫጭር ግኑኝነቶች ርዝመት ያታከተኝ ሴት ነኝ

ምክንያቱም ጭርሱን መራመድ ተሳነኝ፡፡


ልድገመው፡፡ የትርጉም አልባ አጫጭር ግንኙነቶች ርዘመት ያታከተኝ ሴት ነኝ።

አልፎ ሂያጆቹን ትቼ ስለዚህ ልጅ ብቻ የማወራችሁ ለዚህ ነው፡፡

ለምን እንደሆነ ባላውቅም በልኬ ተሰፍቶ እዚህ አውቶብስ ውስጥ የተጣለ መሰለኝ፡፡ ያልዳነ ቁስሌን የሚያክመኝ ሰው እሱ መሰለኝ፡፡
..የበደሌ ካሳ በሚያምር ልጅ መልክ ተሠርቶ የተበረከተልኝም መሰለኝ፡፡

መሰለኝ እንግዲህ...

አውቶብስ ላይ ከተዋወቅን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲደውልልኝ
ያንኑ ባለ አንድ ሃ' እና ባለ ስድስት 'ይ' “ሃይ' አለኝ፡፡

በተቀመጥኩበት አቁነጠነጠኝ፡፡ እንደ ሆነ ነገር ሠራኝ፡፡ ፈተነኝ...ይሄ ልጅ ክፉኛ ፈተነኝ፡፡

በሚቀጥለው ቀን አንዱ ፓርክ ተቀጣጥረን ቁጭ ብሎ እየጠበቀኝ
ነበር፡፡

ጀርባውን ሳየው የሆነ ነገሬ እንደ ጧፍ ይቀልጥ ጀመር፡፡

የቀለጠው...

ይመስለኛል እግሮቼን እንዲሄዱ የሚያደርገው ጡንቻዬ ነው።
ይመስለኛል አጥንቴ ነው ይመስለኛል ሁለተናዬ ነው።

ምክንያቱም ጭርሱን መራመድ ተሳነኝ።

ቀልጬ ከማለቄ በፊት ድንቅፍቅፍ እርምጃዬን ሰምቶ መሰለኝ ወደኔ መጣ።

ፀሐይ ከሰማይ ወርዳ፣ እግር አውጥታ ወደኔ ትመጣ ይመስል የመቅለጥ ፍርሀቴ ይበልጥ ጨመረ፡፡

“የትኛው አካሌ ቀድሞ አመድ ይሆን፣ ይሆን?” እያልኩ ቆሜ ቀረሁ።

አጠገቤ ሲደርስ አውቶብሱ ላይ ያላየሁትን አዲስ ፈገግታ ፊቱ ላይ ተመለከትኩ።

ሚዛኔ ተመለሰ። እግሮቼ በረቱ።

እንጃ ብቻ...ፈገግ ያሉ ዐይኖቹ ውስጥ የለመድኩት ነገር ሁሉ ታየኝ።

ፊቱ ላይ አራት ኪሎ ታየኝ የድል ሃውልት።በተርታ ያሉት ጭማቂ ቤቶች ከጀርባ ያሉት ሻይ ቤቶች ቁልጭ ብለው ታዩኝ።

ፊቱ ላይ ኢትዮጵያ ታየችኝ፡፡

ፈገግታው በሰከንዶች ውስጥ አከመኝ። ሚዛኔ ሲመለስ ተሰማኝ እግሮቼ እንሂድ አሉኝ፡፡ እጄን ያዘኝ እና መራመድ ጀመርን፡፡

እየሄድን....እጄን ስለያዘኝ ብቻ ማንም የማይነካኝ ክፉ የማያገኘኝ መሰለኝ።

ሁሉ ሰው ስሜን የሚያውቀው፣ሁሉ የሚወደኝ ስፍራ
ሃገሬ.... ኢትዮጵያ የሄድኩ መሰለኝ፡፡

አለ አይደል... በአያያዙ ውስጥ የሀገሬን መንገድ ያገኘሁ ያህል ተሰማኝ።

በዙሪያችን ያሉ ሰዎች “ምን እንደሆንኩ ዐውቀው ይሆን?” ብዬ ዞር ዞር ብዬ አየኋቸው።

"ገዳይ ሰውነት ካለው መለሎ ጋር ሆኜ ላለመሞት እየታገልኩ እንደሆነ አስተውለው ይሆን?" ብዬ ዙርያየን ቃኘው።

ቀጥሎ ምን ሆነ?

እልፍ አእላፍ ማታዎች ስንፃፃፍና በስልክ ስናወራ ከረምን።

ተጻጻፍን፡፡ ፎቶ ተላላክን፡፡ አወራን፡፡
ተጻጻፍን፡፡ ፎቶ ተላላክን፡፡ አወራን፡፡
ተጻጻፍን። ፎቶ ተላላክን፡፡ አወራን፡፡
ከዚያ እንደገና ተገናኘን፡፡

እመኑኝ፡፡ በሰው ሃገር ሆናችሁ የወንዛችሁን ልጅ- ያውም እንዲህ
ያለውን ስታገኙ ፈገግታው ሀገራችሁ ነው፡፡

ለዚያ ይሆናል ከፈገግታው መላቀቅ ያቃተኝ፡፡
ለዚያ ይሆናል ዐይኑን ዐይቼ መጥገብ የተሳነኝ፡፡
ዐይኑ ውስጥ ወደ ሃገሬ የሚወስደኝ መንገድ አለ፡፡
ምን ብዬ ላስረዳችሁ እንጂ ...አባቴ ይሙት... እጄን እያያዙ ውስጥ ማንነቴ ሁሉ አለ።

በተገናኘን ምሽት ያን ጃንሜዳን የሚያስንቅ ደረቱን ወለል አድርጎ
የሚያሳይ ጠበቅም -ሳሳም ያለ ሹራብ ለብሶ ነበር።

ወይ ደረቱ! አቤት ደረቱ! ስለ ደረቱ ዐሥር ግጥም በዐሥር ደቂቃ ልፅፍ እችላለሁ። ግን የወሬው አላማ እሱ አይደለም።

እጅ ተያይዘን አብረን ስንራመድ፣ ስንሥቅ፣ ፈገግ ስንል፣ ደረቱ ላይ
ስጋደም፣ ደረቱ ላይ ሲያጋድመኝ፣ በአማርኛ ስናወራ መሸና የሀበሻ
ቤት ሄደን የሀበሻ ቡና በሀበሻ ወግ ጠጣን፡፡

“ቡና እወዳለሁ፡፡” አለኝ፡፡

እኔ ለቡና እስከዚህም ነኝ፣ ግን እሺ ብዬ ጠጣሁ፡፡ ቶና አይደለሃ በረካ አይደለም፡፡

ያን ምሽት ከአቦል ልጅ ጋር ነኝና አምስት ስኒ አቦል ቡና ጠጣሁ።
ስኳር በጨመርኩ ቁጥር፣ “ስኳር ቡናውን ይገድለዋል... ቡና ያለስኳር ነው መጠጣት ያለበት...ሞክሪው፡፡” ሲለኝ፣ ስኳሩን በእሱ ተክቼ ስንት ስኒ ቡና ያለ ስኳር ጠጣሁ?

ስንቱን ስኒ ቡና ባዶውን ሳይመረኝ አንቃረርኩ?

ተለይቼው፣ ቤቴ ገብቼ ከዚህ ቀደም ስለማላዘወትረው ቡና - በተለይ ስለ አቦል ቡና ጀመርኩ። በባዶ ቡና ፍቅር ተንገበገብኩ።

በሚቀጥለው እስካገኘው፣ ያለ ልማዴ በየቀኑ ስለ እሱ እያሰበኩ ስኳር የሌለው ወፍራም ቡና ማፍላት መጠጣት ጀመርኩ

ከዚያስ?

ከነዚያ ምሽቶች በኋላ በድንገት ስልኬን መመለስ፣ ለመልእክቶቼ
መልስ መስጠት አቆመ፡፡ የት ገባ? አላውቅም፡፡ ብቻ…. ብቻ ጠፋብኝ።

እደውላለሁ- አያነሳም፡፡

እጽፋለሁ አይመለስም፡፡

ዐሥራ ሦስት ቀናት አለፉ፡፡

ዐሥራ ሦስት እሱን-አልባ ቀናት ኖርኩ፡፡

ዐሥራ አራተኛው ቀን...

ያ ልጅ... ፈገግታውን፣ እጅ አያያዙን፣ ሳንቃ ደረቱን ይዞብኝ ሲጠፋ...

ያ ልጅ... የሀገሬን መንገድ፣ ኢትዮጵያዬን ይዞብኝ ሲሰወር...

..በላይ በላዩ ባዶውን እጠጣው የነበረው አቦል ቡና በመዐት ማንኪያ ስኳር እንኳን ይመረኝ ጀመር፡፡ ቀረ.. ቀረ.. ቀረ..

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ሕልሜ_እልም...


#በሕይወት_እምሻው

ትላንት በሕልሜ እንዲህ ዐየሁ...

ሕዝባችን...

ሰንሰለቱን በጥሶ፣ የእግር ብረቱን አውልቆ ጥሎ፣ ከእስራቱ ሲፈታ ዐየሁ፡፡

የዘረኝነት ቅጥር ግቢ ፈርሶ፣ የጠባብነት በሮች በእሳት ጋይተው....

ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ፤ ተሰብስበው፤ ከፍ ያለው የክብር ቦታ ተሰጥቷቸው ከንጉስ ማዕድ ሲመገቡ ዐየሁ፡፡

ደግሞም...

በሕዝቡ ላይ መዐት ሲወርድ እያየ የማይታገስ፣

ስለደኅንነታችን የሚቆረቆር፣

ስለኑሯችን ጭንቅ-ጥብብ የሚል፣

የሀገሩን መጥፋት መቋቋም የማይችል፤ ንጉሥ ሲኖረን ዐየሁ፡፡

የተሸረበውን ክፉ ሤራ የሚሽር፣

የተበጠበጠውን በታኝ መድሃኒት የሚያረክስ መሪ ኖሮን ተመለከትኩ፡፡

ሸረኞቹስ?

ሽረኞችማ....

ሽረኞችማ... በማሱት ጉድጓድ ራሳቸው ዘው ሲሉበት፤ ባስቀመጡት
ወጥመድ መልሰው ሲያዙበት፤ በወጠኑት ተንኮል ሲጠመዱ ዐየሁ፡፡

“ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም” ያሉ፤ በሠራዊታቸው የታበዩ ፤
አንገታቸውን ሲደፉ ፈፅሞ ሲያፍሩ ተመለከትኩ።

ከተሞቻቸው ተገለባብጠው ፤ ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ ተደቁሰው;
እንደ ሽክላ እቃ ደቅቀው ፤ መታሰቢያቸው ሁሉ ተደምስሶ ዐየሁ፡፡

ተግሣጽን የጠሉ፣ መታረምን የናቁ.....
እነዚያ... ባለ ክፉ ልቦች፣
እነዚያ ባለ ሐሰተኛ ምላሶች፣
እነዚያ ባለ ትዕቢተኛ ዐይኖች፣

አሉ አይደል...? እነዚያ ...ባለ ለክፋት የሚሮጡ እግሮች?

እነሱ ሁሉ፣ አንዳቸውም ሳይቀሩ

የመንገዳቸውን ፍሬ ሲበሉ የዕቅዳቸውን ውጤት ሲጠግቡ ተመለከትኩ።

ደግሞ እንደገና...

የመከራ ዘመናችን በአሽዋ ላይ ተጽፎ፣

የመፋቀር ዘመናችን ግን በአለት ላይ ተቀርጾ ዐየሁ፡፡

በእጅጋየሁ ሽባባው ምኞት፣

“የሸዋ አባት ልጁን ለትግሬ እየስጠ...
የሐረር ነጋዴ ወለጋ እየሸጠ” ተመለከትኩ

ብርሃኑ እየጎላ የሚሄድ የማለዳ ውጋጋን በሀገሬ ላይ ዐየሁ፡፡

ፀሐይ በምሥራቅ ብቻ ሳይሆን በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምዕራብ ስትወጣ፣

የኢትዮጵያ ሕፃናት ከዳር እስከዳር በስኳር ኮረብታዎች ላይ እየተንሸራተቱ ሲቦርቁ

ጎተራዎች ተትረፍርፈው ገበሬዎች በቲማቲም-ለጨዋታ ሲፈነካከቱ
ዐየሁ፡፡

የመንቀል ጊዜ በመትከል፣

የመሞት ጊዜ በመፈወስ፣

የመበጥበጥ ጊዜ በመስከን፣

የመቅደድ ጊዜ በመስፋት ጊዜ ሲተካ ተመለከትኩ፡፡

የተቀዳደድነው ሁሉ በአረንጓዴ💚፣ ቢጫ💛 ፣ ቀይ❤️ ክር መልሰን ስንሰፋ ዐየሁ፡፡

ከሁሉ በላይ ግን...

የባህር አሸዋን፣ የዝናብ ጠብታን፣ የዘለዓለምነት ቀኖችን ያህል
ፍቅር ዳር እስከዳር ስንካፈል የባሕርን ጥልቀት፣ የሰማይን ምጥቀት የምድርን ስፋት ያህል መውደድን ስንጋራ አየሁ።

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ውዶቼ። 🙏
👍2
#ጸዲ


#በሕይወት_እምሻው

ሰው ሁሉ፣ “ጸዲና ሙሌማ ይጋባሉ፡፡ ተጋብተው አራት ልጅ ይወልዳሉ፡፡ አብረው ያረጃሉ፡፡ ተለያይተው መኖር ስለማይችሉ አንዳቸው ከሞቱ፣ በነጋታው ሌላኛቸው ይከተላሉ፡፡” የምንባል
ዓይነት ነበርን፡፡ እኔና ጸዲ ይኸው ከተለያየን ሁለት ወራት ሞላን፡፡
መጀመሪያ መለያየታችንን መቀበል እምቢ አልኩ፡፡ (ለመንኳት፡፡አስለመንኳት፡፡ አስገዘትኳት፡፡ አብረን በነበርን ጊዜ ቅር የሚላትን፣የሚያበሳጫትን ሁሉ ተውኩ፡፡ የሚያስደስታትን ሁሉ አደረግኩ፡፡
እንደ... በሌሊት ተነስቼ ሥራዋ ድረስ መሸኘት፡፡ ቅዳሜ ቅዳሜ
ጓደኞቼን ትቼ ከእሷ ጋር ስንዘላዘል መዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን
ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ማንበብ፡፡ መጸሐፍ ቅዱስን
በየቦታው መጥቀስ፡፡ በየቀኑ ማስቀደስ፡ የማትወዳቸው ሰዎች
እንዳይደውሉልኝ ስልክ ቁጥሬን መቀየር፡፡ የስልኬን ፓስወርድ መስጠት፡፡ የፌስቡክ ፓስወርዴን የእሷን ስምና ስልክ ማድረግ፡፡
መጠጣት ማቆም፡፡ ማጨስ ማቆም፡፡ መቃም ማቆም፡፡ ከእሷ ጋር
ባልተገናኘ ሁኔታ ደስ የሚለኝን ሁሉ መተው፡፡ በአጠቃላይ በእሷ
ብቻ መደሰት፡፡ በእሷ ፈቃድ ብቻ መላወስ፡፡ በእሷ ቀልድ ብቻ
መሣቅ፡፡ በእሷ ዛቢያ ብቻ መሽከርከር፡፡)
ግን አልሆነም፡፡
ጥላኝ ሄደች፡፡
ከዚያ ደግሞ አያዝኑ አስተዛዘን አዘንኩ፡፡
(ቢጃማ አድርጎ ለቀናት ከቤት ያለመውጣት ዓይነት ሐዘን፡ መጠጥ
ውስጥ የመደበቅ ሐዘን፤ በመጠጥ ብዛት ተገፍቶ በወጣ እንባ የመነፋረቅ ሐዘን፡፡ ለእሷ ብዬ የተውኳቸውን ሱሶች ውስጥ ዳግም የመዘፈቅ ሐዘን፡፡ ሰውን ሁሉ የመጥላት ሐዘን፡፡ የምግብ ፍላጎትን
የገደለ ሐዘን፡፡)

ከተለያዩ ይሞታሉ ቢሉንም፣ ይሄው ሁለታችንም አልሞትንም፡፡
አሁን ደግሞ፣ ከዚያ ሁሉ ልመናና ምልጃ በኋላ፣ ከዚያ ሁሉ መሰባበርና መበጣጠስ በኋላ.... እዚህ ጥላው የሄደችው ቤት ውስጥ
ብቻዬን ቁጭ ብዬ ደህና ደህና ነገሯን ሳይሆን ውስጥ ውስጡን
ያስጠሉኝ ስለነበሩ ነገሮቿ አስባለሁ፡፡
ጓደኛዬ ክብሮም ያዘዘልኝ መድኀኒት ነው፡፡
ክብሮም ስለመለያየት ብዙ ያውቃል፡፡ ብዙዎቹ ገርልፍሬንዶቹ
አንድም ልደት አብረውት አክብረው አያውቁም፡፡ እንቁጣጣሽ ላይ
ጀምረው የጥቅምት እሽት ሳይበላ ይቀየራሉ፡፡ ለቅበላ ተዋውቀው
ሁዳዴ ጦም መሀል ይለያያሉ፡፡ ስለዚህ የወደዳትን የመራቅ፣
የመለየት ጥበብን ቀቅሎ በልቶታልና መከረኝ፡፡
....
ምን ብሎ መከረኝ?

“የጓደኝነቴን ልምከርህ፡፡ አትደውልላት፡፡ አታስባት፡፡ ብታስባት
እንኳን አብራችሁ እያላችሁ ያስጠሉህ የነበሩትን ነገሮች ብቻ
አስብ፡፡ መጥፎ መጥፎውን ብቻ... ገባህ? ለምሳሌ፣ ምኗ ይደብርህ
ነበር? ምኗ ያስጠላህ ነበር? ባትነግራትም ምኗ ያናድድህ ነበር...?”
እያለ ፀዲን ከፊተኛው ሕይወቴ የማባረርበትን ጥበብ አቀበለኝ፡፡
ስለዚህ አሁን እዚህ ቁጭ ብዬ አብረን ባለን ጊዜ ቅር፣ ሲዘልም
ቅፍፍ ይሉኝ የነበሩ ባህሪዎቿን፣ ሁኔታዎቿን፣ ግሳንግስ ጓዞቿን፣
ማሰብ ጀምሬያለሁ፡፡

....አለ አይደል... እንደዛ የቺቺኒያ ሴት አዳሪ የሚያስመስላት ክምር
አስጠሊታ ሂውማን ሄሯ:: ምግብ ስታላምጥ በነጠላ ጫማ የምትሮጥ እስከሚመስል ጧ ጧ እያደረገች የምታስጮኸው ነገር፡፡ ታይት ስትለብስ ሦስተኛ እግር ሊያስገባ የሚችል ክፍተት
የሚተዉት ቀጫጫ ብራኬት እግሮቿ፡፡ ምላሷ ላይ ያሉት መዐት ጥቁር ጠቃጠቆዎች፡፡

(ክብሮም እውነቱን ነው.... ይሄ ነገር ሳይሠራ አይቀርም
...
እንደ... ሸራተን በወሰድኳት ቁጥር ብርቅ እየሰራባት የሚያስጠጣኝ፣ የሚያሳፍረኝ ገጠሬነቷ፡፡ ነዝናዛ እናቷ፡፡ ቆንጆ ግን
ነገረኛ እህቷ፡፡ አንድም ቀን ጥሞኝ የማያውቅ ሽሮዋ፡፡ ሆዳም
ጓደኞቿ፡፡ እንግሊዝኛ አለመቻሏ፡፡እንግሊዘኛ ባለሠቻሏ ፊልም
ባየን ቁጥር፣ ምን አላት...? ምን አለው...? ምንድን ናቸው...?
ምኗ ነው? እያለች መጨቅጨቋ፡፡

(ክብሮም ጥሩ ጓደኛዬ ነው፡፡ መድኀኒቱም ፍቱን ነው፡፡)

ከዲፕሎማ ያልዘለለው የትምህርት ደረጃዋ፡፡ ምን ብር ብታፈስበት፣
ሰው ፊት የሚያስቀርብ ልብስ መርጣ መግዛት አለመቻሏ፡፡ ስስማት
የምታሰማው ደስ የማይል እህ.....፣ ፍቅር ስንሠራ እስቲ ከላይ ሁኚ ስላት፣ “ሂድዛ... ሴተኛ አዳሪ አረግከኝ እንዴ...!” የምትለው ፋራነቷ፡፡ አታጭስ ማለቷ፡፡ አትጠጣ ማለቷ፡፡ አትቃም ማለቷ፡፡
በመሸ ቁጥር ስልኬን መበርበሯ፡፡ የሴት ጓደኛ እንዳይኖረኝ በስልት
መከልከሏ፡፡ (ምን ሆኜ ነበር እወዳት የነበረው?)

ለእነዚያ የማያልፍላቸው አመዳም ቤተሰቦቿ፣ ገንዘቤን ሳታባራ
መበተኗ፡፡ ሚጢጢ ደሞዟ ለቀጫጫ እግሯ ከሚሆን ሉሽን በላይ
ምንም ነገር መግዛት አለመቻሏ፡፡ ለመዝናናት ከገዳም ውጪ አለመምረጧ
ደህና ሬስቶራንት ስወስዳት፣በሹካና በቢላ
እንደመብላት ስቴክ እንደ ዐጥንት አንስታ መጋጧ፡፡ ስልክ ሲደወልላት በሄሎ” ፋንታ “ሃሉ” ማለቷ፡፡

(ክብሮም አስማተኛ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ከደም ሥሬ የወጣች፣ ከቤቴ
የተነነች፣ ከሕይወቴ የጠፋች... ላትመለስ የተባረረች መሰለኝ...)
በደስታ እየተንተንተከተከ ለክብሮም ደወዬ ቢራ ካልጋበዝኩህ ሞቼ እገኛለው አልኩት።እየፈነደቀ እሺ አለኝ።
ተነሳሁና ልብስ ልቀይር ወደ ቁምሳጥኑ ሄድኩ።
ከፈትኩት፡፡ ከትርምሱ መሀል ጸዲ ከዕድሜህ ጋር አይሄድም
አትልበሰው ብላ ከልክላኝ የተውኩትን መበታተን የጀመረ ጂንስ ሱሪ
ጎርጉሬ ሳወጣ የረሳችውን ልብሷን አገኘሁት፡፡

ነጭ ረጅም ብዙ ቀያይ አበቦች የፈሰሱበት ቀሚሷ፡፡ ታይላንድ ስሄድ
ምን ላምጣልሽ ስላት ለቤተክርስትያን የሚሆን ረጅም ቀሚስ ብላኝ
ያመጣሁላት ቀሚሷ፡፡ ቤተክርስትያን ስትሄድ የምታዘወትረው ቀሚሷ፡፡ ከቤተክርስትያን መልስ ቡና ስታፈላልኝ የምትለብሰው
ቀሚሷ፡፡ ይሄን ቀሚስ ለብሳ፣ ቤቱን በዚያ ውብ ሣቋና ግሩም ቡናዋ
የምታደምቀው ነገር ትዝ አለኝ፡፡
ይሄን ቀሚስ ለብሳ፣ የማይጣፍጥ ሽሮዋን ካልበላህ ብላ ፊቴን
በፍቅር እየዳበሰች፣ ዐይኖቼን እየሳመች የምታባብለኝ ውል አለኝ፡፡
ይሄን ቀሚስ ለብሳ ውላ፣ ማታ ልንተኛ ስል፣ ራሷ መክፈት እየቻለች፣ ና ዚፑን ክፈትልኝ ብላ ለአልጋ ላይ ድግስ ሰበብ
የምትፈጥረው ነገር ትውስ አለኝ፡፡
ረስታው ነው? እጆቼ ያለፈቃዴ አነሱት፡፡
አሽተትኩት፡፡

ጸዲ ጸዲን ይላል፡፡

ደግሜ አሽተትኩት፡፡

ሳልሰርግ ያገባኋትን፣ ሳልፈልግ ያጣኋትን የዋኋን ፀዲን፣ ፍቅሬን ፍቅሬን ይላል፡፡
ቀሚሱን እንደያዝኩ፣ ቁምሳጥኑ አጠገብ ቆሜ እንደ ሕፃን ንፍርቅ
ብዬ አለቀስኩ፡፡

ጸዲ... አንቺ ጸዲ...!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
👍2
#ሳይወለድ_ሞተ


#በሕይወት_እምሻው

ከሌሊቱ ሰባት ሰዐት ገደማ፡፡
ተኝቼ ነበር፡፡ ሕመም አልነበረኝም፡፡ ያው ከተለመደው ማቅለሽለሽ
ያስጠነቀቀኝ ፤ ለዚህ ልብ ስብራት ያዘጋጀኝ ሕመም.አልነበረኝም፡፡

ብቻ ስደማ ተሰማኝ፡፡.... ቀስም፣ ቶሎ ቶሎም የሌሊት ልብሴ ላይ፣
አንሶላው ላይ ስደማ ተሰማኝ፡፡

ተደናብሬ የራስጌ መብራቱን አበራሁት፡፡

ልብሴም፣ አንሶላውም ደም በደም ሆኗል፡፡

“ሶልዬ...ሶልዬ ተነሳ!” ብዬ ጮህኩ አጠገቤ የተኛው ባሌ አልሰማኝም፡፡

“ሶል... ሶል..... በማርያም ተነሳ!” የፈሰሰ ደሜን እያየሁ መነሳት
ፈርቼ ደግሜ በጩኸት ጠራሁት፡፡

“ምነው...? ምን ሆንሽ...?” አለኝ ተፈናጥሮ እየተነሳ፡፡

“...እየደማሁ ነው...ምን ሆኜ ነው...? ደም በደም ሆኛለሁ...
ሶልዬ... ወይኔ ጉዴ ሶልዬ... ወይኔ ጉዴ እየደማሁ ነው...”
።።።።
ከሰአታት በኋላ...."ተጠርጎ ወቷል።አሁን ለጤናሽ የማያሳስብ ነገር የለውም አለኝ ሐኪም ቤት ውስጥ ወዲህ ወድያ ሲያደርጉኝ

ማሬ... እንደዚህ አትሁኚ... ያው... ማድረግ ነበረባቸው ማለት
ላንቺ ጤና... ወደ ፊት ሌላ ልጅ.... ሌላ ልጅ እንድንወልድ...”

እጄን የያዘው እጁ ይንቀጠቀጣል፡፡ ወደ ዐይኖቹ መሄድ የሚፈልገውን እንባ በአፉ አስገድዶ እየዋጠ፤ በአፍንጫው ሰንጎ
እያስቀረ ሊያጽናናኝ ይሞክራል፡፡

“ልጄን እንደ ቆሻሻ ጠረጉት... ሶልዬ ልጄ እኮ ነው.. ስም አለው
እኮ... ስም አውጥቼ ነበር እኮ... ልጄ እኮ ነው!”
“አንቺ ልጅ... በቃ ዝም በይ! መዐት አትጥሪ... ዋናው ያንቺ
መትረፍ ነው” አለች እናቴ በሩን ከፍታ እየገባች፡፡

ተርፌያለሁ እንዴ...?

“አንተም ከሷ አትሻልም..... ሂድ አሁን ክፈሉ ምናምን እያሉ
ነው ... ዛሬውኑ ትወጣለች ብሎኛል ዶክተሩ፡፡”

የለመደችውን የሴቶች የማርያም ማኅበር ድግስ የምታሰናዳ ነው
የምትመስለው። ምስር የምትለቅም፣ ጎመን የምትከትፍ፣ ሽንኩርት
የምትልጥ፤ እንደተለመደው ሥራ እየሠራች ነው፡፡ መሆን ያለበትን
እያደረገች ነው፡፡

እናቴ የስሜት ሳይሆን የሚና ሰው ናት፡፡ ጎረቤት ሲሞት ከማልቀስ
በፊት ገናዥ የምትጠራ፣ ሰው አዳልጦት ሲወድቅ፣ “እኔን!” ሳትል
የምታነሳ፤ ሕፃን ሲያለቅስ፣ “እሹሩሩ” ሳትል ዝም የምታሰኝ ዓይነት
ሰው ናት፡፡

ስሜት ሩቋ ነው ለርሷ፡፡ የርሷ ሥራ ነገሮችን ቦታ ቦታ ማስያዝ
ነው፡፡ እናቴ ነገር በማስተካከል ተሰተካካይ የላትም፡፡ ስሜት ግን
እንደ ሰማይ ሩቋ ነው፡፡

ይሄን እያወቅኩ፣ “እማ...” አልኳት፡፡ የለበስኩትን ብርድ ልብስ
ታሰናዳለች፡፡

"እመት...”

“አሁን... ሐዘን አልቀመጥም... አንቀመጥም?” ለምን እንደዚህ
እንዳልኳት አላውቅም፡፡ ምናልባት ሳያብብ ለረገፈው ልጄ ተገቢ
ለቅሶ እንድታሰናዳልኝ ፈልጌ ይሆናል፡፡ ፍራሽ፣ ዳስ፣ ቀብር ቢጤ፡፡

ሀዘኔ ላይ የ“መስክረናል፤ ሆኗል” ማህተም እንድታረግልኝ ፈልጌ
ይሆናል፡፡

“አንቺ ልጅ ያምሻል አይደል...? ለማን ነው ሀዘን የምንቀመጠው...?” ትራሴን እያስተካከለች፣ ስሜት ዝር ባላለበት
ዐይኖቿ እያየችኝ መለሰች፡፡

“ልጄ እኮ ነው እማ.... ልጄ እኮ ነው የሞተው!”

“ወረደ ነው የሚባለው... ሞተ አይባልም... ልጅ ካልተወለደ ሞተ
አይባልም” ዝንጅብል እየላጠች የምታወራኝ ነው የምትመስለው፡፡
ከምንድነው የተሠራችው?

ወረደ...?” አልኳት።

"አዎ...ይሄ እኮ ብዙ ሴት ያጋጥመዋል... እግዜር ያላለው አይሆንም... ሌላ ትወልጃለሽ ቶሎ..... አይዞሽ" አይዞሽ ስትል እንኳን አይዞሽ ያለች አትመስልም።

“ወረደ ነው የሚባለው ... ሞተ አይባልም፡፡” ማለት ምን ማለት
ነው? ሰው አልሆነም ማለት ነው...? የሰው ክብር የለውም ማለት
ነው...? ልጄ ልጅ አልነበረም ማለት ነው ...? ስላልተወለደ ዕውቅና
የለውም ማለት ነው....? ሐዘን አይደለም...? የልጄ መሞት አሳዛኝ
አይደለም...? የልጄ ሞቱ ጉዳት የለውም...? ከልብ ብቻ የተሠራሁ
ይመሰል ልቤ ሲመታ ብቻ ይሰማኛል፡፡

“እኔ የምልሽ..." አለችኝ ትንሽ ቆይታ፡፡

“እ...” ዐይኔን መክፈት የካ ተራራን ከመውጣት እየከበደኝ ነው፡፡

“ለሰው አውርተሻል እንዴ...?”

ምኑን?

ነፍሰጡር እንደነበርሽ...”

ለሰው አውርቻለሁ እንዴ? ለሰው አላወራሁም ግን ሰዎች አውቀዋል። ያቅለሸልሸኝ ነበር ፊቴ መለወጥ ጀምሮ ነበር። ደስ ብሎኝ ስለነበር ለልብ ወዳጆቼ ነግሬ ነበር። ሰዎች አውቀዋል።

“ዐየሽ...! እኔን አትሰሚም... ሦሰት ወር ሳያልፍ አይወራም... አፍ ጥሩ አይደለም ስልሽ ብትሰሚ ኖሮ..”

ማልቀስ ጀመርኩ፡፡

እውነት ልጄን በአፌ ነው የገደልኩት?

ለሰው በማውራቴ ነው አቅፌ በመሳም ፈንታ ደም አድርጌ ጨርቅ
ላይ ያፈሰስኩት..?

እኔ ነኝ ያጠፋሁት? እኔ ነኝ የገደልኩት?
ለቅሶዬ በበረታበት ባሌ ሲመለስ ከእናቴ ጋር ተጣሉ፡፡ በለቅሶ ደክሜ
ዐይኖቼን ጨፍኜ ነበር ግን ዘጋው የክፍሌ በር ባሻገር ኮሪደሩ ላይ፣

“እንዴት እንዲህ ይሏታል?”

“አንተ ታቀብጣታለህ.... ወንድ ሁን እንጂ” ሲባባሉ ይሰማኛል፡፡
ደከመኝ፡፡ እጅግ ደከመኝ፡፡ ብዙም ሳልቆይ እርጉዝ ሆኜ ገብቼ ባዶ ሆኜ ወጣሁ፡፡ ሁለት ሆኜ ገብቼ ፤ አንድ ሆኜ ወጣሁ፡፡ከአራት ቀን በኋላ ቤቴ ሶፋዬ ላይ ቁጭ ብዬ፣ “አሁን የእኔ ስም
ማነው?” ብዬ ማስብ ጀመርኩ፡፡ ለሁሉም ዓይነት ሰው ስም አለን፡፡

እናቱ እና አባቱ የሞቱበት ልጅ ፣ “የሙት ልጅ” ይባላል፡፡

ባሏን ፈትታ ብቻዋን ያለች ሴት ጋለሞታ ትባላለች፡፡

ወልዳ የሞተባት ሴት፣ “ልጇ የሞተባት እናት” ትባላለች፡፡

እኔ ምንድነው የምባለው?

የኔ ስም ማነው?

የኔ ሐዘን ስሙ ምንድነው? ሰው ስለኔ ሲያወራ ምን ሆነች ብሎ ነው?

ከዚያ ደግሞ ስለልጄ አስባለሁ፡፡ አገሩን ሁሉ ያዳረሰ ስም ለእኔ ልጅ
ስለማይሆን፣ ልጄን ስለማይመጥን ፤ ብዙ ጥናት ሠርቼ፣ ወጥቼ
እና ወርጄ ስም አውጥቼለት ነበር፡፡ ቄሶች አማክሬ፣ አቧራ የለበሱ
መጽሐፍት ከፍቼ፣ ከጥንት ኢትዮጵያውያን ንጉሠ ነገሥታት የስም
ዝርዘር የምመኝለትን አስቤ ስም አውጥቼለት ነበር፡፡ ትንሽ አድጎ
በየጸጉር ቤቱ፣ በየኬክ ቤቱ ስንሄድ ቁንጅናውን ዐይተው፣ በአበባነቱ
ተስበው እንደንብ የሚከቡት ሰዎች በሙሉ ከሳሙት በኋላ ስሙን
ሲጠይቁት እና ሲነግራቸው ሲደነቁ ይታየኝ ነበር፡፡

“እንዴት የተለየ ስም ነው? በስማም!” ሲሉና፣ እኔም እሱም ስንኮራ ይታየኝ ነበር፡፡

አሁን ስሙን ምን አደርገዋለሁ? ሌላ ልጅ ስወልድ የርሱን ስም
አወጣለታለሁ...? ስሙን እቀማዋለሁ...? አላደርገውም፡፡ አይወለድ
እንጂ... አድጎ አትዩት እንጂ እኔ እኮ ልጄን ዐውቀዋለሁ... ልጄን እወደዋለሁ፡፡

እቅዴ ውስጥ ነበር፡፡ ወደፊቴ ውስጥ ነበረ፡፡

ስሙንማ አልቀማውም...

“ማሬ እንዴት ዋልሽ ዛሬ...?” ሶል ከሥራ መግባቱ ነው፡፡

“ደህና....”

“ሕመም አለሽ እንዴ...?”

“እ..እ... የለኝም...የለኝም...”

“ጎሽ... ደህና ሆንሽልኝ” አለና ግንባሬን ሳም አድርጎኝ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡

ብዙ ሳይቆይ አለበት ሆኖ፣ “ልጅቷን ቡና አፍይ በያት... እነ ቅድስት ይመጣሉ” ሲለኝ ተሰማኝ፡፡

ሰውነቴ እንደ ጎማ ተነፈሰ፡፡

“ለምንድ ነው የሚመጡት?” በዚህ ሰሞን ከሰው በላይ የሚያበሳጨኝ ነገር የለም፡፡

“ሊጠይቁሽ ነዋ ሆዴ....” አለኝ፣ ወደ ሳሎን እየተመለሰ፡፡

“ለምን ይጠይቁኛል...? ምን ብለው ይጠይቁኛል...? በቃደህና
አይደለሁ....?”

ነሽ እሱማ... ያው... ጓደኞቻችን አይደሉ.... አትምጡ አይባል

ነበር.... እን

ደዚህ አትሁኚ፡፡” እንደዚህ አትሁኚ
#ቅድስትና_ትዕግስት


#በሕይወት_እምሻው


ቅድስት ልክ ስምንት ሰዐት ከሩብ ሲል ትዕግስት ቤት ደረሰች፡፡
“ውይ ቅድስትዬ....! ምነው እንዲህ ጠቋቆርሽ....? ፀሐይ እንኳን የለ ዛሬ....” አለች፣ትዕግስት አራት ጊዜ ጉንጭዋን ስማት....

“ኧረ ተይኝ ባክሽ... ለእንደኔ ያለ ሰው ከነዚያ ሴቶች ጋር ሦስት ሰዐት ሙሉ ስለ ልብስና ጫማ ማውራት ራሱ፣ ከሰባት ፀሐይ በላይ አያከስልም?" አለች ቅድስት፣ ሶፋው ላይ ዝርፍጥ ብላ እየተቀመጠች....

እናም፣ በተገናኙ ቁጥር የሚያደሩት ተመሳሳይ ወሬያቸው በእንዲህ
ሁኔታ ተጀመረ፡፡

“አይ ለእኔ ነው ስለነሱ የምትነግሪኝ ቅድስትዬ? እኔስ ምናቸው አስመርሮኝ ብረንች(ይቺ ቃል ግር እንዳትላቹ በእንግሊዘኛ ብሬክ ፋስትን ከ ላንች ጋር አዳቅሎ የተፈጠረ ነው በኛ ደሞ ቁምሳ ማለት ነው) መምጣት ተውኩና!”

“ደግ አደረግሽ... እኔ የምለው? ማስተርስ ድረስ የተማሩ ሴቶች ከልብስንና ከወንድ ውጪ ሌላ ነገር ማውራት አለማቻላቸው አያሳዝንም? በጣም ያሳፍራል እኮ!"

“በጣም እንጂ....! ዐሥር ሴት ሚኒስትር ቢሾም ታች ያለነው ሴቶች ትላንት ስለገዛነው ነገ ስለምንገዛው ልንገዛ ፈልገን ስላጣናው ብቻ ምናወራ ከሆነ፣ ይህች ሀገር እንዴት ብላ ቀና ትላለች...? ሲንፏቀቁ መኖር እኮ ነው!"

"ጎሽ...እኔ እኮ አንቺ ጋር መምጣት የምወደው ለዚህ ነው....ተንፈስ ስለምታደርጊኝ... ቁም ነገር ስለምታዋሪኝ እኮ ነው አንቺ ጋር መምጣት ደስ የሚለኝ ቲጂዬ!”

“እኔስ ብትይ....! እሺ..... ዛሬስ ምን ተፈጠረ ታዲያ?”

“ምን አዲስ ነገር ይፈጠራል... ያው ሴሞ ሴሞ ነው...ሃሜት ሃሜት... ወሬ... ሰው ቡጨቃ... እይው የገዛሁትን ልብስ.... ይሄ ሽቶ ደስ አይልም...? እገሊት ጂም ጀመረች... እንትና ዮጋ ጀመረች
ይሄው ነው ቲጂዬ!”

“አይገርምም...ዘለዓለም ያው ናቸው... ዘለዓለም..ማፈሪያዎች!”

“እህስ!...ዛሬ ደግሞ ያቺ ሶሎሜ መጥታ ጭራሽ ስትጠብሰኝ አረፈደች.. ደህና ተገላግለናት ነበር፡፡”

“መጣች እንዴ? ዱባይ ቫኬሽን ላይ ነኝ ምናምን ብላ ስታናፋ አልነበረም እንዴ?”

“እንግዲህ ያ የግፍ ዶላር ቶሎ አልቆ ይሆናላ! ወር ሳይሞላት ተመለሰች!”

“አዬ! ለዚህችው ነው ያ ሁሉ ጉራ! ...ግን አንቺን ምን አርጋ አናደደችሽ ቅድስትዬ?”
“ኧረ... ተይኝ! ገና በሥርዓት እንኳን ሳልቀመጥ እየሮጠች መጥታ ... 'ቶፕሽ ያምራል... እኔ የዛሬ ሁለት ዓመት በአራት መቶ ብር ገዝቼው ነበር... በቢጫው አለኝ... አሁን ግን ፋሽን ስላለፈበት ለሠራተኛዬ ሰጠኋት አትለኝም?”

“አታደርገውም!”

“አደረገችው እንጂ ትግስትዬ!አደረገችው”

“እና አንቺስ ዝም አልሻት?”

“ማ? እኔ ቅድስት እንዲህ ባደባባይ ሰድባኝ ዝም የምላት ይመስልሻል?”

“እና... እና ምናልሻት?”

“የኔ እናት... ተማስሉብሽ ይሆናል... ይሄ ሌተስት ፋሽን ነው... የጣሊያን እቃ ነው! የገዛሁት ደግሞ አንድ ሺህ ስምንት
መቶ ብር ነው አልኳታ!”

“ወይኔ አንቺ.. አንጀት አርስ እኮ ነሽ!”

“ታዲያስ...የሆነች ባላገር..ትላንት ብረንች ማለት አቅቷት፣ብራንች የምትል ሴትዮ፤ አንዴ ዱባይ ሄጄ መጣሁ ብላ
ትላጥብኛለች እንዴ?”

“ሃሃ... አይ ቅድስት!”

“ይልቅ እነሱን ተያቸውና ቲጂዬ የሚበላ ነገር አለሽ? ሁሉም ሰው ዳይት ላይ ነኝ ምናምን ብሎ ደህና ነገር አልበላሁም፡፡”

“ተይ እንጂ...! ዛሬም ዳይት ላይ ናቸው?”

“ታዲያስ! ለተቆራረጠ ሙዝ ሰማንያ ብር ይከፍላሉ. ዳይት ላይ ነኝ... መቀነስ አለብኝ ቅብጥርሶ ይላሉ፡፡ ምናለ ስለአንጎላቸው እንዲህ ቢጨነቁ......?”

“እኮ...! እና ታዲያ ምን ላምጣልሽ?”

“ሥጋ...ቅባት ያለው ነገር ምናምን... አታምጪብኝ! ትንሽ ጨምሬያለሁ ሰሞኑን ደግሞ...”

“ኧረ ተይ! ምንም አልጨመርሽም ቅድስትዬ! እንደውም ሳትከሺ አትቀሪም...”

“አይ ቲጂዬ...ቦዲ ሼፐር አርጌ ነው... ቦርጩን ጥፍንግ አድርጎ ስለያዘልኝ ነው...”

“ፓ! አሪፍ ነገር ነው ባክሽ... የት አገኘሽው? እኔ ፈልጌ ፈልጌ
የሚሆነኝ አጣሁ...” "መድኀኔ ዓለም ሞል ግራውንድ ፍሎር ላይ የሆነ ቤት አለ....
መዓት አላቸው... ዘጠኝ መቶ ብር ነው የገዛሁት... ብዙ አይመችም
ግን ቢያንስ ይሰበስብሻል... አብረን ሄደን ትገዣለሽ ሰሞኑን....”

“እሺ... አስታውሺኝ በቃ...ያስፈልገኛል.... በይ በቃ ሽሮ ላምጣልሽ እንግዲህ....”

"እሺ. ..ቲጂዬ..."

ቅድሰት የቀረበውን ሽሮ መብላት ጀመረች፡፡

“ውይ ቲጂዬ! ሲጣፍጥ ግን ቅቤ ሞጀርሽበት!”

“ሃሃ ... ለዚያ እኮ ነው ሚጣፍጠው...”
“ልቀንስ እያልኩሽ ቅቤ ትግችኛለሽ አይደል... አንቺ ምን አለብሽ?”

“ብዪ ባክሽ... ከልኩ አያልፍም...”

“ምን? ቦርጭ?”

“አዎ...."

“ሃሃሃ!”

“ኧረ ቅድሰትዬ ሳልነግርሽ... ዮጋ እኮ ጀመርኩ ቀጥ አላልኩብሽም ትንሽ?”

“ዮጋ?”

“አዎ...”

“ጎበዝ ነሽ ልጄ... እኔ አንዴ ከሰኒ ጋር ጀምሬ እናቴ... ሁለመናዬ ተላቀቀ፡፡ እሱን ለመጠገን አጥሚት እና መረቅ ስበላልሽ ነው ይሄን ቦርጭ እዚህ ያደረስኩት ቲጂዬ!”

“ሃሃሃ... ቀልድሽ እኮ ደስ ሲለኝ ቅድስትዬ!”

“አሹፊ አንቺ... ይልቅ ማን በጣም እንደከሳ ገምቺ...”

“ማ?

“እሌኒ!”

“እሌኒ እሌኒ? እሌኒ መርሻ?”

“እህ!”

“እንዴ? እንዴት አርጋ ከሳች በናትሽ?”

“ሙግግ ብላ መጣች ዛሬ... በሳምንት ሁለት ኪሎ እየቀነስኩ አሁን ዐሥራ ሁለት ኪሎ ቀንሻለሁ አለችን...”

“ተይ ባክሽ....! ያን ሁሉ ሰውነት እንዴት አድርጋ ናደችው በናትሽ?”

“የሆነ ቲቪ ላይ የሚታይ የዳይት ሾው አለ አሉ... እሱን አይቼ ሄጄ ነው አለችኝ...”

“ምን ቲቪ ላይ? እዚህ አገር?”

“አዎ....”

“እና ሄዳ ምን አደረጉላት?”

“ምግብ መጥነው ይሠሩልሻል አሉ... “በወር አራት ሺህ ብር እከፍልና ምግቤን ይሠሩልኛል... አሽገው ቤቴ ድረስ አምጥተው ይሰጡኛል' አለችኝ...”
“ተይ እንጂ... ምን ቲቪ ነው ልጄ?”

ፋና መሰለኝ...”

“ለነገሩ እኔ እንዲህ ያለ ነገር ብዙም አይመቸኝ... ግን መቼ መቼ
ነው የሚታየው አለችሽ?”

“እንጃ... እሁድ መሰለኝ... ብቻ ምሳ እና እራት ዐሥራ ሁለት መኮረኒ ተቆጥሮ ነው የሚሰጠኝ ብላ አሳቀችኝ!”

“ሃሃሃ... አትይኝም?”

“ሙች!”

“እና ግን አከሳት?”

“በጣም... ምግቡ እህል ቅጠል አይልም፤ ግን ካከሳኝ ምን ቸገረኝ
ምናምን አለችኝ...”

“ይገርማል... አምሮባታል በይኛ!”

“ያው መቼስ... ትንሽ ሙግግ ብላለች፣ ረኀብተኛ ነው የምትመስለው ፤ ግን ቦርጭዋ ጠፍቶላታል፡፡ ለነገሩ ዛሬ ዕድሜ
ለብራዚል “ሂውማን ሄር የማታምር ሴት አለች?”

“ልክ ነሽ እሱስ... ሂውማን ሄር ሴቱን ሁሉ እኩል አደረገው እኮ... ምን ዋጋ አለው... ጸጉር ጭንቅላት አይሆን!”

“እኮ!”

“የሚገርመኝ ግን ብር ኖሯቸው እንኳን ደህናውን አይገዙም እኮ...የኔን ዕይው አሁን ከጣልያን ነው ያስመጣሁት... ይኸው ሁለት ዓመቱ ንቅንቅ አላለም... ከገዛሽ ደህና ነገር ነው... የሚልከሰከስ
ሰው አልወድም እኔ...”.....

ማታ እንጨርሰው

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም። 🙏
👍2
#ቅድስትና_ትዕግስት (መጨረሻው ነው)


#በሕይወት_እምሻው


“እሺ... ሌላስ ምን አዲስ አለ ታዲያ!”

“ዝናሽም በስንት ጊዜዋ ዛሬ መጥታ ነበር!”

“ተይ እንጂ! እንዴት ናት?”

“አረጀችብኝ.... ጉስቁልቁል ብላለች... ያው እሷን ታውቂያታለሽ.በሜካፕ ኀይል ነው እንጂ እኮ ዕድሜዋ ሄዷል..."

“አዎ እሱስ... ምን ሜካፕ ብትለቀለቅ አንገቷ አሳልፎ ይሰጣት የለ...
ያ.. የአውራ ዶሮ ኩልኩልት የመሰለ አንገት..."

“አንቺ ተይ በስማም... ሃሃሃ!”

“ምን ላርግ ብለሽ ነው....? ደግሞ እኮ ሰው መልክ ባይኖረው ፀባይ
አይኖረውም?

ያ...ባሏ እንዴት ችሏት እንደሚኖር ነው የሚገርመኝ

እኔ...”

“ውይ! አልሰማሽም እንዴ?”

“ምኑን?”

“አልጋ ለይተዋል አሉ እኮ...”

“ተይ ተይ!”

“ሙች! ቆዩ እኮ... ለንብረት ብለው ነው የማይፋቱት ሲሉ ነበር..."

“ወይ ጉድ... የተጎሳቆለችው ለዚህ ነው በይኛ...."

“ይሆናል እንግዲህ...”

የሚገርመው ፌስ ቡክ ላይ ይሄን ሰልፊ ስትለጥፍ እኮ ነው የምትውለው....
ደህና ፊት እንዳለው ሰው... ለነገሩ ስልኳ
ሌተስት' ስለሆነ አሪፍ አርጎ ያነሳታል... በዐይን እስክታያት ቆንጆ ትመስላለች

ሃሃሃሃ...ስልክ ብትይ...አንቺ ግን እስካሁን አልቀየርሽም እንዴ
ይሄንን ስልክ? ዓመት አለፈው እኮ!”

“አዝዣለሁ ሆድዬ... ሰሞኑን ከካናዳ ይመጣልኛል."

“አይ ደግ አደረግሽ....!”

ቅድስት ሸሮውን ጥረግ አድርጋ በልታ ጨረሰችና እጆቿን ታጥባ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡

“ሽቶሽ ደስ ይላል ቅድስትዬ...” አለች ትዕግስት፣ እቃውን ቦታ ቦታ
አሲዛ ወደ ሳሎን ተመለሰችና አጠገቧ እየተቀመጠች፡፡

“ውይ... ሽቶሽ ብትይ ሳልነግርሽ... ያቺ ሕሊና ያረገችውን ዛሬ...”

“የእነዚህ ሴቶች ጉድ አያልቅ! እሷ ደግሞ ምናረገች በናትሽ....?”

ዋው... ሽቶሽ ደስ ይላል... ምንድነው ስሙ አትለኝም?”

እና ነገርሻት...?”

ደህና ዴኦዶራንት ተቀብታ የማታውቅ ዝተታም የአራት ሺህ ስድስት መቶ ብር ሽቶ ስትመኝ አይገርምሽም? እኔማ ምን አለብኝ

ከነዋጋው ነገርኳት.... ያ አመዳም ፊቷ የበለጠ አመድ መሰለ ...

ሃሃሃ”

“ሃሂ... በጣም ያሳዝናል ብቻ የእነሱ ነገር... ስንት የሚያስጨንቅ ነገር እያለ.. ሃገር እየታመሰች ወሬያቸው ሽቶ..ቅባት.ልብስ ሃሜት... ወንድ... ያሳዝናል በጣም.... መማር ምን ጥቅም አለው

ግን?”

“ምንም!”

ጥቂት ቆይቶ ቅድስት መሄድ እንዳለባት ተናገረችና ተነሳች፡፡

“በቃ ልሂድ ቲጂዬ! የማታው እራት ላይ አለሽ አይደል?” አለቻት እንደቆመች፡፡

“አለሁ ቅድስትዬ...”

“ዋ እንዳትቀሪ... አንቺ ስለምትመጪ ነው የምመጣው ... ከነዚያ ሴቶች ጋር ትርኪምርኪ ማውራት አልችልም... አደራሽን እንዳትቀሪ”

“አልቀርም ቅድስትዬ...”

“ጎሽ... በይ ልሂድና ልበጃጅ...”

“ምን ልትለብሺ አሰብሽ ዛሬ?”

“የሆነ ጥቁር ሌስ ቀሚስ ገዝቻለሁ... አንቺስ?”

“እኔ እንኳን አልወሰንኩም፡፡”

“ጸጉርሽንስ? አትሠሪም?”

“አይ ፍሪዝ ላረገው ነው ባክሽ...”

ለነገሩ ያንቺ ጸጉር በፍሪዝ ያምራል..."

“ታንኪው ሆዴ... በይ ልሂድ...”

“ቻው የኔ ቆንጆ...

እሙጳ.. እሙጿ፡፡ እሙጳ....

እኔ የምልሽ ቲጂዬ...?”

“ወዬ ቅድስትዬ...."

“አንቺ ጋር ስመጣ እኮ ነው አንጎል ያለኝ አንጎል የሚመስለኝ...”

“እኔስ ብትዩ!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ዛሬ_ቀኑ_ምንድነው?


#በሕይወት_እምሻው

ተንበርክኬ ነበር፡፡
በዚያ የጥቅምት ውርጭ፣ ከምሽቱ አራት ሰዐት ተኩል ላይ ከሰማይ በላይ እሪታዬን እያቀለጥኩ፣ቀዝቃዛው አስፋልት ላይ ተንበርክኬ ነበር፡፡ በብርድ በሚንገጫገጨ ጥርሶቼ መሃከል እጮኻለሁ፡፡ ጉሮሮዬ የተሰነጠቀ፣ ደረቴ የተተረተረ እስኪመስለኝ ድረስ እጮኻለሁ፡፡

በኋላ ሲነግሩኝ አደጋው ቦታ አምቡላንስ ደርሶ ልጄን አፋፍሶ እስኪወስደው ድረስ እንዲሁ ስጮኽ ነበር፡፡

ሆስፒታል ስንደርስ በጥድፊያ ልጄን በባለጎማ አልጋ እየገፉ ሌላ
ክፍል ወስደውት አላስገባም አሉኝ፡፡

አትገቢም አሉኝ፡፡

መድኀኒት፣ መድኀኒት የሚለው ኮሪደር ላይ ቆሜ ቀረሁ፡፡ በነጭ ካፖርት ውስጥ ወዲህ ወዲያ የሚራራጡ ሐኪሞች፡፡ ሰማያዊ ለብሰው እዚህም እዚያም የሚሉ ነርሶች፡፡ በየወንበሩ ላይ
አንገታቸውን ደፍተው፣ ጥርሳቸውን እያኘኩ የተቀመጡ ሰዎች፡፡
በአንቅልፍ የናወዙ አስታማሚዎች፡፡ አዲስ አደጋ ይዘው እየጮኹና እያለቀሱ ወደ “ ኢመርጀንሲ” ክፍል የሚበርሩ
አትገቡም እያሉ የሚከላከሉ ነርሶች፡፡ ሐኪሞች፡፡

በቆምኩበት የሆነውን ለማሰብ ሞከርኩ፡፡

እየሣቀ ነበር፡፡ እንቅልፌ መጣ ምናምን ብሎኝ፣ “አንተ እኮ ከእንግዲህ ትንሽ ልጅ አይደለህም... እስከ አምስት ሰዐት መቆየት አትችልም እንዴ...? ዳይፐር እንደገና መግዛት ልጀመር እንዴ?”
ስለው እየሣቀ ነበር፡፡ ያቺ ከአባቱ የወረሳት ዲምፕሉ ፣ ያቺ ፍቅፍቅ እያለ የሚስቃት ሣቁ፣ የግራ መጠምዘዣውን ይዤ ብቅ ከማለቴ በልጄ በኩል ጠርምሶት የገባው መኪና ላንድክሩዘር ነበር። ደማቅና የሚያጥበረብረው መብራቱ ፂርርርርርርር... ጩኸቴ፡፡ ግውውውውውው! ጭለማ፤ የልጄ የሲቃ ጩኸት፤ ጨለማ፡፡ በስሱ የሚሰማኝ የሰዎች ኡኡታ፤ ከአጥንቴ የተለየ
የመሰለኝ ሥጋዬ፤ ድንጋጤዬ፤ ጩኸቴ፤ ጨለማ፡፡ ደማቅ የሰዎች ጩኸት፣ በስመ አብዎች፡፡ አንገቴ ሲዞር፣ ከሶኬቱ ወጥቶ እንደ ጨርቅ የተንጠለጠለው የልጄ እጅ ከጆሮው የሚጎርፈው የደም ጅረት፤ ጩኸቴ፡፡ ተርፈዋል ብለህ ነው? በስመአብ! በስመአብ... ኧረ ለፖሊስ ደውሉ፡፡ ኧረ አምቡላንስ ጥሩ፡፡ በስመ አብ.... የሚሉ ድርብርብ ጩኸቶች፡፡ የሚያለቅሱ ሰዎች፡፡
ከዚያ እንደ ጨርቅ ጎትተው ሲያወጡኝ።
እኔን አወጡኝ፡፡ ደህና ናት፡፡ ተአምር ነው፡፡ ልጁ ግን ተጎድቷል፡፡
ምንም ሳትሆን ወጣች ምናምን ሲሉ ይሰማኛል፡፡
ልጄስ...? ልጄስ...? ልጄን...! ብዬ ስጮኽ ትዝ ይለኛል፡፡
የተከደነ ዐይኖቹ፡፡ ደም የለበሰው ግማሽ ፊቱ፡፡ ደም የተነገከረው
ደረቱ፡፡ ለብቻው የተንጠለጠለው ቀኝ እጁ፡፡ ልጄ!

አትግቢ ወዳሉኝ ዝግ ክፍል ስሮጥ ከወንድ የሚጠነክሩ ሁለት
ነርሶች ጠፍንገው ያዙኝ፡፡

“ልጄን...! ልጄን ልየው?” እያልኩ ሳለቅስ ከለከሉኝ፡፡

“እዚህ መጠበቅ አለብሽ. ሰርጀሪ ገብቷል፡፡ እዚህ ጠብቂ...”
አሉኝ፡፡ በብዙ ሰዎች የተሞላው መስኮት አልባ ስፊ ኮሪደር ውስጥ ተዉኝ፡፡ አብዛኛዎቹ ሰዎች ከብረት የተሠሩ የማይመቹ ወንበሮች ላይ ቁጭ ብለዋል፡፡ ግማሾቹ አቧራ፣ በአቧራ በሆነው ነጭ ወለል ላይ በግዴለሽነት ተዘርፍጠዋል፡፡ የመድኀኒትና የሰዉ ሽታ ተቀላቅሎ፣ የልጄ ምስል ተደምሮ ወደ ላይ አለኝ፡፡

እንደምንም መለስኩት፡፡

አንዲት ሴት ሁኔታዬን ዐይታ ይሁን መቀመጥ ሰልችቷት፣ በ “ነይ
እዚህ ተቀመጪ” እጆቿን ስታንቀሳቅስ፣ በድን አካሌን ይዤ
ከብረት ወንበሩ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ፡፡ ከዚህ ቦታ፣ ከዚህ ሁኔታ ራሴን ብነጥል፤ ይሄን አስቀያሚ ቦታና ሁኔታ፣ ደመና ሆኜ ትንን ብዬ ብለየው ፤ ከጥቅምት ውርጭ
ጋር ተቀላቅዬ በረዶ ሠርቼ
ብተወው ምናለ? ከዚህ ሌላ የትም ቦታ ብሆን፣ ከዚህ ውጪ ምንም ነገር ቢደርስብኝ ምን ነበር?

“ልጄ..!”

እንደገና መጮኽ ጀመርኩ፡፡
ወንበሯን የለቀቀችልኝ ሴት ትከሻዬን ያዝ አድርጋ፣ “አታልቅሺ..ጸልዪ... ጸልዪ....” አለችኝ፡፡

ደመና ሆኖ መትነን የለም፡፡ በረዶ ሆኖ ከአየር መቀላቀል ፤ ሌላ ቦታ፣ ሌላ ሁኔታ ላይ መሆን እንደማልችል ዐውቃ መሰለኝ፡፡

“ጸልዩ....”

ለቅሶዬን ወደ ቀስታ እህህታ አውርጄ አካባቢዬን ቃኘሁ፡፡ እንደኔ በዝምታ የሚያለቅሱ፣ ንፍጥ የሚናፈጡ፣ እንባ የሚጠርጉ፣ እርስ በእርስ የሚጽናኑና የሚጸልዩ ብዙ ሰዎችን ዐየሁ፡፡

በእንባ የራሱ ዐይኖቼን ጨፈንኩ፡፡ ወዲያው ደግሞ ገለጥኳቸው፡፡
በሩ ጋር አንዷ ነርስ ከፖሊሶች ጋር ስታወራ ተመለከትኩ፡፡ በረጅሙ
ተነፈስኩ፡፡ በአየር ፈንታ እሳት ያስገባሁ ያህል ውስጤ ተቃጠለ፡፡ ውስጤ ነደደ፡፡

“ጸልዪ..” አለችኝ፡፡ አሁንም አጠገቤ የቆመችው ሴት፡፡

ከወንበሬ ተንሸራትቼ ወለሉ ላይ ተንበረከኩ፡፡

አንገቴን አቀረቀርኩ፡፡

ዐይኖቼን ጨፈንኩ፡፡

እጆቼን በእንባ የበሰበሰ ፊቴ ላይ አደረግኩ።
ከጸለይኩ ዕሥራ አምስት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ለቀብር ካልሆነ፣
ለዝክር ወይ ለበዓል ቤተ ክርስትያን ከረገጥኩ ብዙ ዓመታት ሄደው
መጥተዋል፡፡ ከእናቴ ሞት በኋላ፤ የቱ ቀን ሚካኤል፣ የቱ ቀን ተክልዬ እንደሆነ አስቤ አላውቅም።

እና ምን ተብሎ ነው የሚፀለየው? አባታችን ሆይ ግማሹ ከጠፋብኝ ሰንብቷል ምንድነው የምለው? አባቴ
ሆይ... በሰማይ የምትኖር...? ዐይኖቼን ገልጬ ሴቲቱን ዐየኋት፡፡ እርጂኝ ዓይነት ዓየኋት

“ዝም ብለሸ ጸልዪ....” አለችኝ፡፡

እጸልያለሁ፡፡ መጀመሪያ ይሄን ሁሉ ጊዜ ስላልጸለይኩ፣ እግዜርን ስለተውኩ ይቅርታ እላለሁ ስለሃጥያቴ ሁሉ ይቅርታ እጠይቀዋለሁ፡፡ ከዚያ ግን... ከዚያ ግን፣ ልጄን ተውልኝ... ልጄን
አትውሰድብኝ እለዋለሁ.....

እንደሚባለው ምሕረቱ የበዛ ሩህሩህ ከሆነ፣ ልጄን እንዲያድንልኝ እማጸነዋለሁ፡፡

እያለቀስኩ መሬቱን መሳም ጀመርኩ፡፡

እየጮኹ... እያጉረመረምኩ መጸለይ ጀመርኩ፡፡

“አምላኬ ሆይ.... ልጄን ተውልኝ... ልጁን አድንልኝ.... እጾማለሁ፡፡አስቀድሳለሁ፡፡ እጸልያለሁ፡፡ብቻ ልጄን ተውልኝ አድንልኝ.... ዐርብ እሮብ እጾማለሁ፡፡ ዐብይ ጾምን እጾማለሁ። ደሃ በስምህ አበላለሁ፡፡ አስቀድሳለሁ... አንተ ግን ልጄን ተውልኝ...አምላኬ እባክህ ልጄን አድንልኝ....
እግዚአብሄር ሆይ.... ልጄን ካዳንክ ባሪያህ እሆናለሁ፡፡እንደፈቃድክ እሆናለሁ፡፡ ያልከኝን አደርጋለሁ......”

አልኩና ቀና ብዬ በእንባማ ዐይኖቼ አሁንም ቆማ የምታየኝን ሴት ዐየኋት፡፡

ዛሬ ምንድነው?” አልኩ በጎርናና ድምፅ፡፡

“እ?” አለችኝ፣ ደንገጥ ብላ፡፡

“ዛሬ...ቀኑ ምንድነው?”

"አስራ ዘጠኝ ገብሬል ነው"

እንደገና መሬት ላይ ተደፋሁ፡፡ ከንፈሮቼ በእንባዬ ታጥበው ጨው ጨው ይሉኛል፡፡

“ገብርኤልዬ... የኔ ገብርኤል... ልጄን አድንልኝና በዓመት ቁልቢ አልቀርም፡፡ በየወሩ ሱቄን ዘግቼ አከብርሃለሁ፡፡ እዘክርሃለሁ፡፡መልአኩ ገብርኤል ልጄን አድንልኝ...አድንልኝ...”ሴቲቱ ጎትታ አነሳችኝ፡፡ ቆምን፡፡

“ይበቃል... በቃ በቃ...” ከእምባዋ እንደምትታገል፣ በእንባ
በተሸፈኑትና እንደ እሳት በሚያቃጥሉኝ ዐይኖቼ ዐየሁ፡፡ ልክ እንደ ቅርብ ዘመዴ አቅፌያት አለቀስኩ፡፡

“በቃ... በቃ.... አይዞሽ...” አለችኝ፡፡
ብዙ ደቂቃዎች አለፉ፡፡

ነርሶቹ ምነው ጠፉ? ዶክተሩስ ለምን ዝም አለኝ? አዲስ ለቅሶ ጀመርኩ።
ሴቲቱ ታባብለኛለች፡፡
የስለት ቃሌን ለገብርኤል እደግማለሁ፣ መሬት እንበረከካለሁ፤
እቆማለሁ፤ ወደ በሩ እሄዳለሁ፤ ነርሶቹን ስለልጄ እጠይቃለሁ፤ጠብቂ እባላለሁ፤ አለቅሳለሁ፤ እቀመጣለሁ፤ እነሳለሁ፤ ተምበርክኬ ለገብርኤል እሳላለሁ፡፡ነፋስ ያስፈልገኛል፡፡ነፋስ.ነፋስ ያስፈልገኛል፡፡ ወጥቼም እንዳልወጣ ሐኪሞቹ መጥተው ቢያጡኝስ? እዚያ ኮሪደር ላይ
ተቀምጩ ትንፋሽ አጥሮኝ የልጄን
👍2
#የአልጋ_ላይ_ዱካ


#በሕይወት_እምሻው

ትላንት ማታ ክፉ ነገር ተፈጠረ፡፡
መልከ መልካሙና ገራገሩ እጮኛዬ ላይ ማገጥኩበት፡፡

ያች በልጣጣ ጓደኛዬ ትዕግስት ናት፣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የከተተችኝ።
ሁሌም ለሰኔ ሚካኤል ቤቷ ድል ያለ ድግስ ታዘጋጃለች፡፡ የምታውቀውን ሰው ሁሉ ትጋብዛለች፡፡ ከልክ በላይ
ታበላለች፡፡ ከመጠን በላይ ታጠጣለች፡፡ አንድ ውስኪ ለሦስት ሰው እየቀረበ፣ በረዶ አንሷል እየተባለ ውስኪ እንደተፈጠረ በጉሮሮ ሲንቆረቆር፣ ሰዉ ሁሉ ከማያውቀው ሰው እንደ አብሮ አደግ ይሣሣቃል፣ ያሽካካል፡፡ ምስጢር ይጋራል፡፡ ይሟዘዛል፡፡ የትዕግስት
ፓርቲ እንዲህ ነው፡፡ ነጠላ
ሆኖ የመጣን፣ ጥንድ አድርጎ
ይሸኛል፡፡ አይተው ከማያውቁት ሰው አደጋግፎ፤ አስተቃቅፎ፣አልጋ ድረስ ያጓትታል፡፡

ውስኪዋ ውስጥ ትንሽ ቅንዝር ጠብ፣ ብዙ የፍትወት ፍላጎትና የመማገጥ ዓላማ ሙጅር ታደርግበት ይመስል፤ በየዓመቱ የሚወራ የወሲብ ገድል መነሻ ይሆናል፡፡

ለስድስት ዓመታት ይሄንን የተቀበረ የመጠጥ ፈንጂ አልፌ፤ ዘንድሮው ግን ረገጥኩት፡፡
እርግጥ አድርጌ ብ......ው......
አደረግኩት፡፡ አጀማመሩ እንዲህ ነበር፡፡
ጥሬና ጥብሱን ሥጋ፣ ከዚህ በኋላ ለሳምንት አትበሉም የተባልን ያህል ተስገብግበን ጎስረን፣ ጎስረን፣ “እሰቲ አወራርዱት... እስቲ ጥረጉት” እያለች የምታስተናብረውን ትዕግስት እየሰማን፣ ሁለት ጠርሙስ ውስኪያችንን በጉሮሯችን እያንቆረቆርን ስድስት ሆነን
አንድ ጠረጴዛ ላይ ተሰይመናል፡፡

ከለብታ አልፎ ሞቅታ፣ ከሞቅታ አልፎ ስካር ሲጀማምረኝ ትዕግስት
ወደ ጠረጴዛችን መጥታ፣ “አወራርዱት” ባለች ቁጥር፤ የሞት ሞቴን የብርጭቆዬን አፍ በእጆቼ ለመክደን ብሞክርም፣ ልክ ትንኝ እንደምታባርር ሁሌ እጄን ጧ እያደረገች ታስከፍተኝና በውስኪ
ሞልታው ትሄዳለች፡፡

ቺርስ ባሉ ቁጥር እጠጣለሁ፡፡

“አትጨምሪልኝ... በቃኝ” እያልኩ በእጄ ብርጭቆውን ለመዝጋት እሞክራለሁ፡፡

እጄን ጧ አድርጋ፣ ብርጭቆዬን አስከፍታኝ ሞልታው ትሄዳለች፡፡
ቺርስ ባሉ ቁጥር እጠጣለሁ፡፡
እንደገና “አትጨምሪልኝ... በቃኝ” እያልኩ በእጄ ብርጭቆውን ለመዝጋት እሞክራለሁ፡፡

እጄን ጧ አድርጋ፣ ብርጭቆዬን አስከፍታኝ ሞልታው ትሄዳለች፡፡

ይሄ አዙሪት ለዐሥራ ምናምን ጊዜ እንደቆየ ሳሙኤል ከፊቴ ተከሰተ፡፡ ያንን ሰንደቅ የሚያስቅል ቁመቱን፤ የቀይ ዳማ የደስ ደሳም ፊቱን፣ ቦርጭ አልባ ሰውነቱን ይዞ፣ ሳሙኤል ከፊቱ ተከሰተ፡፡ ያውም አንዴ ሁለት፣ አንዴ አራት፣ አንዴ ስድስት
ሆኖ... ሞቅታዬ አብዝቶት፣ ስካሬ አባዝቶት የቀድሞ ፍቅረኛዬ ሳሙኤል ከፊቴ ተከሰተ።

ሲቀመጥ ትዝ አይለኝም፡፡ እጆቼን ሲያሻሸኝ ግን ትዝ ይለኛል፡፡
መጀመሪያ ሲስመኝ ትዝ አይለኝም፡፡ አፌን አፉ ውስጥ ሳገኘው ግን ትዝ ይለኛል።
መኪናው ላይ ስሳፈር አላስታውስም፡፡ አልጋው ውስጥ መግባቴ ግን ውል ይለኛል፡፡ ልብሳችንን ስናወልቅ ትዝ
አይለኝም፡፡ ዕራቁት ሰውነቱን በስሜት ስቧጭር ግን በደንብ ትዝ ይለኛል።

ከንፈር እየተሻማን ስንቃበጥ፣ አንገቴን ሲልስም፣ ሲስምም፤ ኋላም ሴትነቴን በወፍራም ወንድነቱ ሲከድን፣ መሀሉ መሀሉ ጭለማ በገባበት ሁኔታ ትዝ ይለኛል፡፡

ይሄው ነው፡፡

ጠዋት ላይ፣ አልጋው ውስጥ አናት ከሚፈልጥ ራስ ምታት ጋር
ስነቃ፣ ትላልቅ ድፍርስ ዐይኖቹ ተቀበሉኝ፡፡

ራሴን በሁለት እጆቼ ካልደገፍኩ ቷ ብሎ የሚፈነዳ ስለመሰለኝ፣በቀኝም በግራም እጆቼ ጭንቅላቴን ይዤ፣ ከወገቤ በላይ ብድግ አልኩና፣

“ምንድነው ...! ምንድነው ያደረግነው?” ብዬ ጮኽኩ፡፡ ሳሙኤል
ትላልቅ ዐይኖቹን ፊቱ ላይ እያንጎማለለ ሲያየኝ፣ የራሴ ጩኸት ራስ ምታቴን እያባሰው ከወገቤ በታች ዐየሁ፡፡ እንደፈጠረኝ ነኝ፡፡

“ሳሙኤል... እዚሀ እንዴት መጣሁ...? ምንድነው ያደረገገው...?”አልኩ በአንሶላው ተጠቅልዬ ከአልጋው የመሸሽ ያህል እየወጣሁ:ከአልጋው ፈንጠር ብሎ ወጣ፡፡ ቁምጣ ከሚያህል ቡራቡሬ የውስጥ ሱሪ ሌላ ምንም አላደረገም፡፡

“ሆሆሆ! ምንድነው ያደረግነው? ካርታ ስንጫወት ነዋ ያደርነው”አለኝ፣ እየሣቀ፡፡ ጥርስህ ይርገፍ፡፡

ዝም ብዬው ልብሶቼን ፍለጋ ጀመርኩ፡፡

ሮዝ ጡት ማስያዣዬን አልጋው ግርጌ፣ ጥብቅ ያለው ቀይ የድግስ ቀሚሴን ከአልጋው በስተቀኝ መሬት ላይ አግኝቼ፣ በሰማያዊው ለስላሳ አንሶላ እንደተጠመጠምኩ ወደ ማውቀው መታጠቢያ ቤት ገብቼ ፊቴን ሳልታጠብ መስታወቱ ፊት ቆምኩ፡፡

ምንድነው የሠራሁት?

ምን ነካኝ?

እሺ ለብ ይበለኝ፡፡ እሺ ሞቅ ይበለኝ፡፡ እሺ ልስከር፡፡ እሺ እጄን እንዲይዝ ልፍቀድለት፡፡ እሺ ሲስመኝ ልሳመው፡፡ እሺ ትንሽ ልቃበጥ፡፡ ግን ምንስ ያህል ብጠጣ ከትዕግስት ቤት ወጥቼ፣
መኪናው ውስጥ ገብቼ፣ ከብስራተ ገብርኤል ሰሚት ድረስ ንፋስ እየመታኝ መጥቼ፣ እቤቱ ሄጄ፣ መኝታ ቤቱ ገብቼ፣ አልጋው ጋር ሄጄ፣ አልጋው ውስጥ ገብቼ፣ ልብሴን አውልቄ፣ ራቁቴን ሆኜ፣
እጮኛ (ያውም የሰው ጥግ) እያለኝ፤ ከቀድሞ ፍቀረኛዬ ጋር ስዳራ
ማደሬ ልክ ነው?

ለመልአክ ሩብ ጉዳይ በሆነ እጮኛዬ ላይ
መልከስከሴ ግፍ አይደለም?

ቢሰማ አያብድም?

ቢያውቅ ራሱን አያጠፋም?

ፊቴን በቅጡ ሳልታጠብ፣ ከመታጠቢያ ቤቱ ወጥቼ በጥድፊያ ጫማዬን አድርጌ፣ ቦርሳዬን አነገብኩና... “ስሚኝ...” ምናምን...የሚለኝን ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ዘግቼ እግሬ በፈቀደልኝ ፍጥነት
ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ፡፡
የኮንዶሚኒየሙን ደረጃ እየወረድኩ ስልኬን አወጣሁ፡፡
.
ዐሥራ ዘጠኝ ያመለጡኝ ጥሪዎች፡፡ ሰባት የጽሑፍ መልዕክቶች፡፡ከፈትኩት፡፡

ዐሥራ ስድስቱ የእጮኛዬ ጥሪ ነው፡፡ ስማግጥ ያልመለስኳቸው 16
ጥሪዎች፡፡ እርምጃዬን አቁሜ እጄ እየተንቀጠቀጠ መልዕእክቶቹን
ከፈትኳቸው፡፡ ሁሉም ከእሱ ናቸው፡፡

“ማሬ ስልክ አታነሺም” ... “በሰላም ነው...?”... “ኧረ ተጨነቅኩ”...
.
“በደህናሽ ነው?”... “እባክሽ ደውይልኝ... “ትዕግስትም አላነሳ አለችኝ ... “በናትሽ ደውይልኝ” ....

ኮንዶሚኒየሙ ጣራ ላይ ወጥቼ መፈጥፈጥ አማረኝ፡፡

ልደውልለት ግን ጉልበት አጣሁ፡፡ እሱን ትቼ ትዕግስት ጋር ደወልኩ፡፡ በሁለተኛው ዙር ከአራት ጥሪ በኋላ አነሳች፡፡
ሰላምም ሳልላት፣ “አንቺ ማታ ምንድነው የተፈጠረው?” ብዬ ጮኽኩባት፡፡

“እንዴ እኔ ምናባሽ አውቅልሻለሁ... የት ሆነሽ ነው...?” አለችኝ።ድምፅዋ፣ ቤተክርስትያን ሲያስቀድስ አድሮ የመጣ ሰላማዊ ሰው እንጂ፤ አሸሼ ገዳሜ ሲል ያደረ አይመስልም፡፡

“ምን የት ነሽ?” ትይኛለሽ... ሳሚ ጋር ነበርኩ... እንዴት እንዲህ
ዓይነት ነገር ሲደረግ... እዚህ ሲያመጣኝ ዝም ትያለሽ?” አልኩ፣ ቱግ ብዬ እርምጃዬን እያፈጠንኩ፡፡

“እንዴ... ኧረ ቀስ...! አንቺ አይደለሽ ስንት ሆነን ስንለምንሽ፣ ከእሱ በስተቀር ከማንም ጋር አልሄድም እያልሽ፤ እንደ
እባብ ስትጠመጠሚበት ያመሸሽው?” አለችኝ ቆጣ ብላ፡፡

ወሬውን በስልክ መቀጠል ስላልፈለግኩ፣ ቤት መሆኗን አረጋግጬ ራይድ ጠራሁና ስበር ቤቷ ደረስኩ፡፡

በስልክ የጀመረችልኝን አጠናክራ፣ ለያዥ ለገናዥ ማስቸገሬን፤ ያየኝ ሰው ሁሉ ሲሥቅ እንደነበር፤ መጨረሻ ላይ እንደፈለጋት ትሁን ብለው እንደተዉኝ በሚያም ዝርዝር ነገረችኝ፡፡
ያቀረበችልኝን ቁርስ ሳልነካ ሻዩን ብቻ እየማግኩ፣

“ቲጂ...” አልኳት፡፡

“ወይ...” አለች፣ ዐይን ዐይኔን እያየች፡፡
“ደሬ የሚሰማ ይመስልሻል...? ማለቴ ሰው ቢነግረውስ?” አልኳት፡፡

“እ...ህ አይመስለኝም... ደግነቱ እንደዛ ስታብጂ የነበረው አብዛኛው ሰው ከሄደ በኋላ ነው...ማሐቴ ሳሙኤል ካልተናገረ" አለችኝ።

ሳሙኤል ካልተናገረ!

በተቀመጥኩበት መርዶ እንደተረዳ ሰው
1👍1
#ባይተዋር


#በሕይወት_እምሻው


ስናይና ላምሮት በስንት ጊዜያቸው፣ ስንት ጊዜ ለምኗት፣ ስንት ጊዜ ተለማምጧት፣ ስንት "በናትሽ"አባክኖባት፣ ስንት የኔ ቆንጆ ስወድሽ" ፣ “እስቲ አንዳንዴ እንኳን ያለልጆቹ እንደ ድሮው ወጣ ብለን እንዝናና” አዝንቦባት፧ እየጠጡ ሊያመሹ ቦሌ አካባቢ፣ አንዱ በሚደነቁር ሙዚቃ እና በሲጋራ ጢስ የታፈነ ባር ቁጭ ብለዋል፡፡እሱ ቮድካውን ይለጋል፣ እሷ ጣፋጭ ወይኗን ለኮፍ ለኮፍ ታደርጋለች።

እራት በልተው እሱ አራተኛ ደብል ቮድካው ላይ ሲደርስ፣ እሷ ግን
ያቺኑ አንዲት ብርጭቆ ወይን ታባብላለች፡፡ከተጋቡ 12 ዓመታቸው
ነው ፤ ልጆች ስላሏቸው ብዙ አያመሹም፤ እስከ እኩለ ሌሊት፣ እስከ ከሌሊቱ ዐሥር ሰዐት ሲጠጡና ሲደንሱ የማደር፣ የ”ኦቨር ናይት” ጭፈራ ዘመን ለእነሱ ካበቃ ቆይቷል፡፡ ድሮ ቀረ፡፡ ቢያንስ ላምሮት
በምልጃም ቢሆን ከሦስት ሰዐት በላይ አታመሽም፡፡ሁሌም ከሥራ ወደቤት መሄድ፣ ጓደኞቿን እንኳን ቤቷ መቅጠር፣ በጊዜ በጋቢ ተጠቅልላ ቴሌቪዥን ፊት መጎለት የምትወድ ዓይነት ሴት ናት።

“ኡፋፋ.....! ይሄ ሙዚቃ እስከዚህ ከጣራ በላይ መጮህ አለበት? ሰው እንዴት ብሎ ያወራል? ደግሞ የሲጋራው ጭስ... ምኑ ደስ፣እንደሚልህ አላውቅም እንዲህ አይነት ቦታ ማምሸት....? በናትህ ወደቤት እንሂድ...እ?” ብላ ማማረር ከመጀመሯ፣ ፊት ለፊቷ፣ከአንገቱ ብዙ ካልጎደለው የወይን ጠርሙሷ አጠገብ፣ ጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠችው ስልኳ ጮኸ፡፡

ሰናይ ሰዐቱን ዐየ፡፡ ሦስት ሰዐት ከሠላሳ አምስት፡፡

(ማነው በዚህ ሰዐት የሚደውልላት..? ከቤት ነው? ሰራተኛቸው ናት? ልጆቹ ደህና አይደሉም?)

ስልኩን አንስታ፣ “ሄሎ” አለችና ሌላ ቃል ሳታወጣ ዝም ብላ አዳመጣ ዘጋችው።

ሁኔታዋ ግራ ቢያጋባውም ፤ ሰናይ፣
“ማነው በዚህ ሰዐት የሚደውልልሽ?” ብሎ ሚስቱን የሚነዘንዝ፣ አምባጓሮ የሚያስነሳ፣በራሱ የማይተማመን ባል፤ ሚስቱም በዚህ ሰዐት በሚደወል፣
ተገቢ ያልሆነ ግንኙነትና የስልክ
ጥሪ” የምትጠረጠር ሴት ስላልሆነች ምንም አላላትም፡፡

በመሃል ከስልክ ጥሪው ጋር የማይገናኝ አንድ ሁለት አረፍተ ነገር ወሬ ካወሩ በኋላ፣ አምስት ከማይሞላ ደቂቃ በኋላ ስልኳን አንስታ የሆነ ነገር ፃፈች፡፡ ቴክስት መሰለው፡፡

ከዐሥር ደቂቃ በኋላ የሙዚቃውን ጩኸት፣ የወጣቶቹን ጫጫታና
የሲጋራውን ሽታ መቋቋም ስላልቻለች፥ ሰናይ ሂሳቡን ከፍሎ፣ ለአስተናጋጇ ጉርሻ ሰጥቶ፣ ጃኬቱን ደርቦ ወደቤታቸው ሄዱ፡፡

ይሄ የሆነው አርብ ዕለት ነበር፡፡የዚያኑ ዕለተ ማታ ቤት ደርሰው፣ ልብስ ቀይረው አልጋቸው ውስጥ ሲገቡ፣ ሚስቱ በዚያ ሰዐት የተደወለላትን ስልክ አንስታ
ከሄሎ በስተቀር አንዲት ቃል ሳትናገር መዝጋቷ ሆድ ሆዱን እየበላው ነበር።

በነጋታው ቅዳሜ ጠዋት፣ ሁሌም እንደሚያደርገው ሳሎን ላፕቶፕ
ከሳምንት የተረፈ ሥራ ሲሠራ፤ ፒጃማዋን
እንደለበሰች፣ ጠዋት የጠበሰችውን እንቁላል እንቁላል እየሸተተች አጠገቡ መጣችና፣

“ሰናይዬ፣ ይሄ ስልክ ዜንደሩ አልሠራም ብሎ አስቸገረኝ... እስቲ ዕይና አስተካክልልኝ”ብላ፣ ስልኳን አቀበለችው፡፡ ላምሮት የቴክኖሎጂ ነገር የማይሆንላት፣ ለትንሹም ለትልቁም የእሱን እርዳታ የምትጠይቅ ዓይነት ሚስት ናት፡፡ሪሞት ኮንትሮል በትክክል አነጣጥራ ቲቪ መክፈት ሲያቅታት ቢሮ ደውላ፣ “እምቢ
አለኝ…ምን ላድርግ” የምትል ዓይነት
ሚስት።“ባትሪው ላልቶ ይሆናል እስቲ ክፈቺውና ነካ ነካ አድርገሽ እንደገና ሞክሪው”ሲላት በቃ ስትመጣ ዐያለው” ብላ የምትዘጋ ሚስት።
ስልኳን ሰጠችውና ወደ በረንዳ ወጥታ ቀድማ ካዘጋጀችው ባልዲ እየቀዳች አትክልቶቿን ውሃ ማጠጣት ጀመረች፡፡

በራሱም በሚስቱም የማይተማመን ባል፣ ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሞ አርብ ማታ፣ ለአራት ሃያ አምስት ጉዳይ ላይ ለሚስቱ የደወለው ማን እንደሆን ለማጣራት ስልኩን ይበረብር ነበር፡፡ ሰናይ ግን
እንዲህ ያለ ባል ለመሆን ዝግጁ አልነበረም፡፡ እሱ፣ ሚስቱን የሚያፈቅርና የሚያምን፣ በሦስት ልጆች የጸና ጠንካራና ደስተኛ ትዳር ያለው ሰው ነው፡፡ አእምሮው የተረጋጋ፣ መንፈሱ ያረፈ
አባወራ ነው፡፡

አይደለም እንዴ?

ሁለት ደቂቃ ሳይሞላ የስልክ ጥሪዎች ታሪክ የሚጠራቀምበት ቦታ ገብቶ አርብ ማታ የደወለውን ሰው ቁጥር መፈለግ ያዘ፡፡

አርብ፣ ከምሽቱ 3:35 ደቂቃ “ኤ” በሚል
ስም የተመዘገበ የማያውቀው ቁጥር፣

ጥሪው የቆየበት ጊዜ፡ አምስት ሰከንዶች፡፡

እምምምም....!

ጣቶቹን አፍጥኖ ወደ መልእክት ሳጥኗ ገባ፡፡ በዚያው ምሽት፣ ከእሱ ጋር ተቀምጣ፣ ለ “ኤ” የፃፈችውን መልእክት አየ፡፡ ሃይ፣ ፓርቲ ነኝ... ጫጫታ ስለሆነ አይሰማም፡፡ እደውልልሃለሁ” ይላል፡፡

ፓርቲ ነኝ?

ወደ ላይ ሄደና ከዚያ በፊት የጸፈችለትን ማየት ጀመረ፡፡ ሐሙስ ዕለት ማታ የጻፈችውን፣ “ሃሃሃ ... ይገርማል... ትዝታው ሊገልህ ነዋ! “ የሚል አገኘ፡፡

ትዝታው? የምን ትዝታ?

ከዚያ በፊት ኤ የጻፈውን ዐየ፡፡

“ስሚ ቆንጅዬ... ባለፈው ሳምንት ቀኑን ሙሉ ተአምር የሠራንበትን ራሱን ክፍል መልሰው አይሰጡኝም? አይገርምም?” ይላል፡፡

ይሄን ጊዜ ሰናይ ሁለመናው ከዕንጨት እንደተሠራ ሁሉ ይደርቃል፡፡

ከአፉ ምራቅ ይጠፋል፡፡

ዐይኑ ይደፈርሳል፡፡

ሚዛኑ ይዛባል፡፡

ልቡ ልክ ባልሆነ ዘዬ ይመታል፡፡

ጣቶቹ መንቀጥቀጥ ይጀምራሉ፡፡

ሁሉም ጸጉሮቹ መቆም ይጀምራሉ፡፡

ወደ ላይ ይለዋል፡፡ ሽንቱ ይወጥረዋል፡፡

መሬት ላይ ተዘርሮ ቁና ቁና መተንፈስን ይመኛል፡፡

ግን በሚንቀጠቀጡ ጣቶቹ የስልኳን ገጽ ወደ ላይ ይገልጣል። የኤ እና የታማኝ ሚስቱን የቃላት ድሪያዎች ለደቂቃዎች ያነባል።

አንዱ መልእክት ወደሌላው እየመራው፣ አንዱ አንዱን አንብብ እያለው የሚያንፈራፍር የሆድ ሕመም እስኪይዘው ድረስ ብዙ ጉድ አየ፣ ብዙ ጉድ አነበበ፡፡ ማለቂያ የሌለው የብልግና መልእክት ክምር ውስጥ ራሱን አገኘ፡፡

ማንበብ ማቆም ይፈልጋል፡፡ ግን ያቅተዋል፡፡

በእያንዳንዱ መልእክት የሚስቱ ስብእና ይሸራረፍበታል፡፡

በእያንዳንዱ ፣ “ሃይ ፍቅሬ” ቤቱ ይፈራርስበታል፡፡

በእያንዳንዱ፣ “እኔም ናፍቀኸኛል” ዓለሙ ይጠብበታል፡፡

ግን ማንበብ ማቆም ያቅተዋል፡፡

ባገኙት መድረክ ሁሉ ይባልጋሉ፣ ይሞላፈጣሉ፣ ይጨማለቃሉ፡፡ዋትስአፕ፣ ቫይበር፣ ቴሌግራም፡፡ ....ሃያ ባልሞላ ደቂቃ ውስጥ የ12 ዓመት ትዳሩ አፈር ከድሜ ጋጠ፡፡ የሚያፈቅራት ሚስቱ፣
የሦስት ልጆቹ እናት ፤ በሃያ ደቂቃ ዕድሜ፣ የቡና ቤት ሴት፣ ጎዳና ላይ ቆማ ገበያ የምትጠብቅ ሴት አዳሪ ሆነች፡፡ በሃያ ደቂቃ ዕድሜ ሕይወቱ አይሆኑ ሆነ፡፡
የደስታ ኑሮው አፈር ለበሰ፡፡ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ጢምበራው እንደዞረ ሰው ጭ....ው...እንዳለበት፣ እንደተወዛገበ፣ አለሙ እንደጠበበ፣ሁለንተናው
እንደተበጠበጠ፣ ሦስት ልጆቹ ጠባቡ ግቢ ውስጥ ሲጫወቱ ይሰማዋል፡፡ ላምሮት... ይህች የማያውቃት፣ ባይተዋር ሴት፤ አትክልቶቿ አጠገብ በርጩማ ላይ ተቀምጣ ስታያቸው ይታየዋል፡፡
የረፋድ ፀሐይ በረጅሙ መስኮት በኩል ወደቤት ገብታለች፡፡
ምንድነው የሚያደርገው?

ቀጥታ ወደ ኩሽና ሄዶ፣ ከቢላዎች መሃል ትልቁን ቢላ መርጦ እየተምዘገዘገ አጠገቧ ደርሶ አትክልቶቿ ፊት እንደ አትክልት ይከትፋታል?

የኔ አንጀት እንዲህ ነው የተበጠሰው ብሎ፣ በቢላው አንጀቷን በጥሶ
ያሳያታል?

ልጆቿ /ልጆቻቸው ፊት ይገድላታል?

አያደርገውም፡፡

ፊትለፊቱ የተቀመጠውን ትልቅ መስኮት የሚያህል ቴሌቪዥን (ያ ሁሌ እንደ ጨዋ ሴት በጊዜ ቤቷ ተሰብስባ፣ ተጎልታ የምታየውን) ይከሰክሰዋል።
ልብሷን ሁሉ እያወጣ፣ ፀያፍ ስድብ እየተሳደበ... “አንቺ ሸርሙጣ”
ምናምን እያለ በረንዳ ላይ
👍3
#ትልቅ_ደረጃ


#በሕይወት_እምሻው


ከንጋቱ ዐሥራ ሁለት ሰዐት ገደማ... ትራስጌዬ አጠገብ ያለው
ኮመዲኖ ላይ የተቀመጠው ስልኬ ሲርገበገብ ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡
ጥዝዝ... ጥዝዝዝ... ጥዝዝዝዝ....

ተደናብሬ መብራቱን አበራሁ፡፡ ማነው በዚህ ሰዐት የሚደውልልኝ? ስልኩን ከተቀመጠበት አንስቼ ደዋዩን ዐየሁ፡፡ አባዬ ነው፡፡ ስዐቱን ዐየሁ 12፡08

አባዬ በዚህ ሰዐት የሚደውልልኝ ምን ሆኖ ነው? ሁለመናዬ ተናወጠ፡፡ ስልኩን ደግፈው የያዙት ጣቶቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ መቼም በደህናው በዚህ ሰዐት አይደውል! መርዶ ሊነግረኝ መሆን አለበት::
የምሳሳላት ብቸኛ እህቴ የዐይኔ ብሌኔ፣ ኤደንዬ ምን ሆችብኝ? ሳሚ ይሆን? ታዳጊ ወንድሜ ሳሚዬን ምን አገኘብኝ?

እማዬ የሞተች ጊዜም እንዲሁ፣ በዚህ ሰዐት ደውለው ነው፣“ህመሟ ብሶባታል እና ድረስባት” ብለው የጠሩኝ፡፡ አንጀቴ ብጥስ ብሎ፣ አንጎሌ መሞቷን እየነገረኝ፣ ልቤ ግን እውነትም አሟት ይሆናል አይዞህ ብሎ እየደለለኝ ታክሲ ላይ እንደ መንፈቅ ልጅ እየተነፋረቅኩ የደረስኩት፡፡ ያደግኩበት ቤት ደጃችን ላይ ስደርስ፣
ነጠላ ያዘቀዘቁ ሴቶች፣ ወዲህ ወዲያ የሚሉ ካፖርት የደረቡ የሰፈር ሽማግሌዎች፣እዚህም እዚያም የሚሯሯጡ ጎረምሶች ሳይ ነው፣ቁርጤን አውቄ ኮረት ላይ ተንበርክኬ ስሟን እየጠራሁ የጮህኩት፡፡ዛሬ ደግሞ አባዬ በዚህ ሰዐት የሚደውልልኝ፣ ማን ሞተ ሊለኝ ነው?

አነሳሁት፡፡

“ሄሎ አባዬ...” አልኩ፣ ቃላቱን ለማውጣት እየታገልኩ፡፡

“ሄሎ ወንድወሰን... እንዴት አደርክ?”

“ደህና ነኝ እኔ... ምነው ሰላም አይደላችሁም እንዴ?”

“ሰላም ነን... እንዲሁ ፈልጌህ ነው...”

ኡፍፍፍ! ሳምባዬ ይዞት የነበረውን አየር በሙሉ ኡ....ፍ ብዬ አወጣሁት፡፡ ያፏጨሁ መሰለኝ፡፡ የእፎይታ ጩኸት፡፡
እጆቼ መንቀጥቀጥ፣ ራሴ የራሱ ልብ እንዳለው ሁሉ ድው ድው ማለቱን
አቆመ።

“እ... ምነው ታዲያ በዚህ ሌሊት ደወልክልኝ?” አልኩ ድምፄ ወደ
መደበኛው ሁኔታ እየተመለሰ፡፡
“ያው ያንተ ነገር... ከረፈደ ስልክ አታነሳም... ሥራ ሳትወጣ ልደውል ብዬ ነው.... አስቸኳይ ስለሆነ”

“ቢሆንም በዚህ ሰዐት መደወል አልነበረብህም... እኔ እኮ ከአንድ ሰዐት በፊት ከቤት አልወጣም... በጣም አስደነገጥከኝ...”

“አይ! ምን ያስደነግጥሃል?”

“መርዶ ቢሆንስ...?”

“የምን መርዶ...?”

“ምን ዐውቃለሁ እኔ? በዚህ ሰዐት ለመርዶ ካልሆነ ይደወላል...?”

“እስቲ አሁን እሱን ተወውና የደወልኩበትን አዳምጠኝማ!”
የአባዬ ድምፅ ጎላ፤ ቆጣ ካለ፣ ቶሎ የማደርገው ነገር ዝም ማለት ነው፡፡
ዝም አልኩ፡፡

ሄሎ?”

“አቤት አባዬ”

“እየሰማኸኝ ነው?”

“አዎ... እየሰማሁ ነው...”

“እንግዲህ መስከረም አይደል...” ብሎ ጀመረ፡፡ ቅድም ከፍ እና ቆፍጠን ያለው ድምፁ በድንገት እንስ... ቶሎ ኩምሽሽ አለብኝ፡፡

አባዬ ድምፁ የሚያንሰው የማይፈልገውን ነገር ለመናገር ሲገደድ ነው፡፡ አባዬ ግርማ ሞገሳም ድምፁ የሚኮሰምነው ገንዘብ ሊጠይቀኝ ሲል ነው፡፡ አባዬ ገንዘብ ከጠየቀኝ ደግሞ፣ ያሉትን አማራጮች ሁሉ አሟጥጦ ጨርሷል ማለት ነው፡፡ ኩሩ ነውና መሄጃ ካላጣ፣
መሸሸጊያ ካልጠፋበት ፤ እኔን ገንዘብ አይጠይቅም፡፡

ያ ከየት አምጥቶ እንደሆነ ባላውቅም ሳያቋርጥ የሚጥለው ዕቁብ አልደረሰለትም፡፡ ከጓደኞቹ አንድም ሊያበድረው የሚችል ሰው የለም፡፡ በአራጣም ቢሆን ገንዘብ የሚሰጠው አላገኘም፡፡
ይሄንን ሁሉ ደረጃ አልፎ ነው እኔን ገንዘብ የሚጠይቀኝ፡፡ ጅንኑ አባቴ ልጁን ገንዘብ ሲጠይቅ ፤ እንኳን ድምፁ፣ ሰውነቱ ያንሳል፡፡ ያ ጎምላላነቱ ጠፍቶ አንገቱና ቅስሙ ይሰበራል፡፡

“ስንት ብር ፈልገህ ነው አባዬ?” አልኩ፣ ቀላሉን እንዲያደርግልኝ በመመኘት

ጠይቆኝ አልችልም ማለት እሱ እኔን ለመጠየቅ ከሚሸማቀቀው
በላይ ያሸማቅቀኛል፡፡ አብሶ እማዬ ከሞተች በሁዋላ የሴት መላ ጠፍቶ
ቤታችን ዘመም እንዳለ ዐውቃለሁ።
እማዬ ስራ የሚያመጣ ሥራ ሠርታ አትወቅ እንጂ፣ ባንንደላቀቅ እንኳን እሷ
እያለች ሲቸግረን አላውቅም፡፡ ያንን ከውጪ ማጋደል የጀመረ ሰርቪስ፣ ላይ ላዩን አሳድሳ አከራይታ፤ የአባዬን ትንሽ ደሞዝ እስከ ወር መጨረሻ ለጥጣ፣ ፤ በዚህ በኩል ዕቁብ ገብታ፤ በዚያ በኩል
በሴት ማኅበር ድግስ ላይ ጨርቅ ምናምን አትርፋ ሸጣ፤ ትንሽዋን
አብዝታ፣ ጥቂቷን አባዝታ፤ ከኑሯችን በላይ አንቀበራ ታኖረን ነበር፡፡

“ትልቅ ደረጃ እንድንደርስ ለራሷ በሁለት ዓመት አንድ ጫማ እየገዛች፣ እስካሁን ሊገባኝ በማይችል ሁኔታ ሦስት ልጆቿን የግል ትምህርት ቤት ታስተምረን ነበር፡፡
ሥራ በያዝኩ በሁለት ዓመቴ እናቴን ሞት መነተፈኝ፡፡ አባዬም ጡረታ ወጣ፡፡ ይከራይ የነበረው ቤትም፣ አባዬ አመል ስላጣ ረግቶ የሚቀመጥበት ሰው ጠፍቶ፤ ከሚከራይበት የማይከራይበት ጊዜ
ይበዛ ነበር፡፡ እማዬ ከሞተች ወዲህ ለአባቴና ለወንድምና እህቴ ኑሮ
ቀላል እንዳልሆነ ይሰማኛል፡፡ አንድ ሁለቴ የሞት ሞቱን ጠይቆኝ፣
የእህቴንና የወንድሜን የግል ትምህርት ቤት ክፍያ አግዤው ነበር፡፡አባዬ ያቅሙን እየታገለ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ግን ከወር ወር ኪሱን የሚሞላ ገቢ የሌለው ጡረተኛ ሽማግሌ ነው፡፡

እማዬ ከሞተች ወዲህ ጎጇችን ምሶሶው
ለመወድቅ እንዳዘነበለ ይሰማኛል፡፡

“ያው ሰርቪሱም ባዶውን ከተቀመጠ አራት ወር አለፈው... አራት
ሺህ የሚከራይ ቤት... ደህና ሰው ጠፋ፡፡ ደላሎቹ ጫት የሚበላ፣ ሲጃራ የሚጠጣ ወፈፌ ብቻ ነው የሚያመጡብኝ.. እምቢ ብዬ ደህና ሰው እስኪያገኝ ብዬ ባዶ ከሆነ አራት ወር አለፈ... ጡረታውም የምታውቀው ነው... ከወር እስከ ወር በመከራ ነው የሚያደርሰን...

አንተን ከማስቸግር ብዬ እነ ኤዱንም ከግል ትምህርት ቤት ላወጣቸው አስቤ ነበር... ግን እናታቸው ብትኖር ምን ትለናለች ብዬ ተውኩት... ዐጥንቷስ
አይወጋኝም... ሁሌም ትልቅ ደረጃ
እንድትደርሱላት ራሷን በድላ ለናንተ ትምህርት የሌለ ገንዘባችንን
ስትገፈግፍ ነው የኖረችው..ታዝንብኛለች.. እነሱን ከለመዱት ትምህርት ቤት... ከጓደኞቻቸው ለይቼ የመንግሥት ትምህርት ቤት ባስገባቸው ምን ይሉኛል? እናታችን ስለሌለች ነው ብለው አያቄሙብኝም... የመንግሥት ትምህርት ቤት ትምህርትስ፣ የት ሊያደርሳቸው... አገር ቤት ያለውም መሬት ቢያንስ ቀለብ ላይ ትንሽ ይደጉመን ነበር ዘንድሮ ደግሞ፣ ድርቁም ሰዉም አብረው
ባዶዬን አስቀሩኝ... ጭራሽ ዕዳም ሳያመጡብኝ አይቀሩ እነሱማ...

ሰው መች አለ ዛሬ... .እናትህ ነበረች
ምታወቅበት.. እኔ ምኑን ከምን ላድርገው ልጄ...”

ው...ይ! ጀመረው ደግሞ፡፡ የራሴ ድው ደው ተመልሶ መጣ፡፡

በረጅሙ ተነፈስኩና

“አባዬ....ስንት ብር ነው የፈለግከው...?” አልኩ፡፡

“አንተስ ከየት ታመጣለህ ልጄ.. በዛሬ ኑሮ... እዚህ ኑር ስትባል ለሥራዬ ራቀኝ... ትራንሰፖርቱም ያው ነው... በዚያው ራሴን
ልቻል ብለህ .... እምቢ ብለህ ኪራይ ቤት አለብህ... ኑሮው እሳት ነው ዛሬ... ወይ ሙያ የለህ፤ ውጪ እየተበላ ገንዘብ እንዴት ይያዛል ዛሬ... ቢሆንም ብድር እንኳን የሚሰጠኝ ሰው ባጣ ነው
ወደንተ መምጣቴ ልጄ.... ባይሆን የመጣው ይምጣ እንጂ በዚህ
ወር ያንን መከረኛ ቤት ለዱርዬም ቢሆን አከራይቼ የስድስት ወር አንድ ላይ ተቀብዬ የቀረውን ወጪ እሸፍናለሁ አሁን የቸገረኝ
ምዝገባ ሰኞ ስለሚያልቅ የልጆቹ ትምህርት ቤት ነው... ክፍያ ጨምረዋል ደግሞ ዘንድሮ... ዩኒፎርሙም ሰማይ ደርሷል... መጽሐፉስ ብትል.. ደሞ ከእኛ ግዙ እያሉ አጥፍ በእጥፍ ነው
የሚያስከፍሉት... ብቻ ይሁን ትልቅ ደረጃ እንዲደርሱልን ነው
1
#እኔ_እሷና_እሱ


#በሕይወት_እምሻው


#ማስታወቅያ

እንደሚታወቀው አባል ለመጨመር በምናደርገው ማስታወቅያ አትሰልቹ እባካችሁ እኔ በቀን ውስጥ #post የማደርግበትን ሰአት በቻልኩት መጠን ሁሌ ተመሳሳይ #ሰዓት ላይ ለማድረግ እሞክራለው እናንተም ያቺን ሰዓት ለመከታተል እንዲያመቻችሁ ያዙልኝ #ምርጦቼ በተረፈ መልካም #ንባብ
።።።።።።።
አዲስ ፀባይ ካመጣች ሰነባበተች፡፡
ስሙን ለመጥራት ሰበብ መፈለግ እስክታቆም ወደዋለች።
ይሉኝታዋን እንደ ቆሻሻ ልብስ እስክታወልቅ ልቧን ሰጥታዋለች::
ፍቅር ይሉኝታ ያስጥል የለ? ምን ይሉኝ ፍርኀትን ይገፍ የለ?
እህ... እንደሱ፡፡

የጀማመራት ሰሞን፣ “በረከት እኮ... ሂ ኢዝ ሶ ስማርት... እኛ ቢሮ የሚቆይ አይመስለኝም... ማስተርሱን ይጨርስ እንጂ ዩኤን ይጋደሉበታል... እጁን ስመው ነው የሚቀበሉት”

“ባለፈው ከነ በረከት ጋር ሄድንበት ያልኩህ ካፌ ትዝ ይልሃል? እዚያ ውሰደኝ...”

“በረከት እኮ ካለ ቶሞካ ቡና አይጠጣም...እስቲ አንተም የዚህን
የመንደር ቡና ተውና እዛ ጠጣ...”

“እስቲ ይሄን ዲኦ ተቀባው... የዛሬ ወንዶች እኮ ካለዚህ አይቀቡም ... አሽተውማ... ወንዳ ወንድ ሽታ... ደስ አይልም?”
እያለች ነው የጀመረችው።
አብረን ብዙ ቆይተናል፣ ብዙ ነገሬን አስታምማ ነው የምትኖረው፡እወዳታለሁ፣ “ከእሷ የተሸለ ሴት አላገኝም” እያልኩ ተውኳት፡፡ አለ አይደል... ሲጋራ አጨሳለሁ፤ ጫት እቅማለሁ እጠጣለሁ...
ትወቅ አትወቅ አላውቅም እንጂ ሌላ ሴት ጋር ሄጄም ዐውቃለሁ...
ቢሆን እንደ ሌሎች ሴቶች፣ “ተው...” እያለች አተነዘንዘኝም... “ከነምናምኔ ትወደኛለች...” እያልኩ፡፡

የሚያልፍ ነገር ይሆናል. ትረሳዋለች.. ብዬ ተውኳት፡፡ እሷ ግን ባሰባት፡፡ ስሙን በየቦታው ከመሰንቀር ዘልላ፣ በሐሳብ በመንፈሷ ተሸክማው ትገባና ትወጣ ጀመር፡፡

ሳምንታት ሲያልፉ ነገሩ አድጎ ይሰረስረኝ፤ ይገዘግዘኝ ጀመር፡፡ሁለመናዋ ይቀየር ጀመር፡፡

አንዱን እሑድ ምሽት፣ መጽሐፌን ትቼ አስተውላት ነበር፡፡ አብረን
መኖር ከጀመርን ሦስት ዓመታትን ስላለፈን የምሽት - የቀን የአዘቦት ድርጊቷን ቅደም ተከተሉ ሳይዛነፍ ዐውቀዋለሁ፡፡ ሳምሪ ግዴለሽ ሴት ናት፡፡ ጸጉሯን በየሳምንቱ የውበት ሳሎን ሄዳ
የማታቃጥል፣ ልብሷን ተኩሳ የማትለብስ፣ ኩልና ቻፒስቲክ የሜክአፕ ጥግ የሚመስላት፣ አዲስ ልብስና ጫማ በቀጠሮ የማትገዛ ግዴለሽ ሴት ናት፡፡

ያን ማታ ስታደርግ ያየሁት ነገር፣ እንግዳ የሆነብኝ ለዚህ ነው፡፡
በመተኛትና በመቀመጥ መሃል ሆኜ መጽሐፍ የማነብበት አልጋ ጫፍ ላይ ዕይቼ የማላውቀውን፣ ቄንጠኛና ውድ የሚመስል ፓንት ከመሳዩ ጡት መያዣ ጋር ዘርግታ፣ ልክ ቢለበስ ምን
እንደሚመስል በሚያሳይ ሁኔታ ለረጅም ደቂቃዎች ታየዋለች፡፡ ከዚያ ደግሞ ሁለቱንም ታነሳና፣ ጡት መያዣውን ባደረገችው አሮጌ
የሌሊት ካናቴራ ላይ ደርባ፤ ፓንቱን ደግሞ በተግባቢው ቦታ ላይ፣በሁለት እጆቿ ደገፍ አድርጋ መስታወት ታያለች፡፡
“አዲስ ነው አይደል ይሄ ነገር....?” አልኳት፣ ትኩረቷን ለመስበር፡፡

“እ...?” አለች፣ ፓንቱን ወደ አልጋው ጥላ፣ ከነጡት መያዣዋ ወደ
እኔ እየዞረች፡፡

“ፓንቱና ጡት መያዣው... አዲስ ነው ወይ..?” ራሴን ደገምኩ፡፡

“እ... አዎ... ያምራል አይደል?”

“አዎ... ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ስታደርጊ ዐይቼሽ አላውቅም...
ነይ እስቲ...” አልኳት፣ መጽሐፌን ወደ አንደኛው የአልጋው ጥግ ወርውሬ ቀኝ እጄን ዘርግቼ... መጣች፡፡

“ለኔ ነው...?” ፈገግ ብዬ ጠየቅኩ፡፡

“ሃ.ሃ... ታዲያ ለማን ይሆናል...?” እጆቼን ይዛ መለሰች፡፡

“ልበሺውና ልየዋ...”

“አይ... ለነገ ነው ... ማታ ታየዋለህ ...”

ተስፈንጥራ ወደ ቁምሳጥኑ ሄዳ ልብሶቿን አለቅጥ ማተራመስ ጀመረች፡፡

“ምነው...? ምን ሆንሽ...?” አልኩ፣

ባካሄዷ ድንገተኝነት ተገርሜ፡፡
“አይ... ለነገ ልብስ ልምረጥ... ጠዋት መተራመስ አልፈልግም...”

ነገ ስለምትለብሰው ልብስ ስትጨነቅ ዐይቻት አላውቅም፡፡ ጠዋት
ላይ፣ እጇ የገባውን ልብስ አድርጋ፤ እንደነገሩ ሆና እንደምትወጣ
ነው የማውቀው፡፡

ለአፍታ የረሳሁት ጥርጣሬ ሆዴ ውስጥ ተገላበጠ፡፡

ያ ሁሉ ግዴለሽነትዋ የት ገባ? ያልፋል ያልኩት ተባራሪ ስሜቷ መቼ ሥር ሰድዶ ባሕርይዋን መቀየር ጋር ደረሰ? ያን ቀን ነገር እያላመጥኩ አድሬ ነጋልኝ፡፡

ሲነጋ፣ ከጠዋቱ አንድ ሰዐት አልፎ በታክሲ አናገኝም ጭንቀት ተሰቅፌ፣ ቶሎ እንውጣ እያልኩ እማጸናታለሁ፡፡

“ረፈደ ሳምሪ... ቶሎ በይ...”

“በናትህ ልብሴ ሁሉ አስጠላኝ...”

“ትላንት መረጥኩ አላልሽም?”

“አዎ ግን አስጠላኝ...”

“ያ ስኩዌር ስኩዌሩ ሱሪሽ አሪፍ አይደል? እሱን ልበሺ ሳምሪ...”

“አንተ ደግሞ... እሱ በጣም ሰፊ ነው...”
“ሰፊ ልብስ የምትወጂ መስሎኝ?”

“እወድ ነበር አዎ... ግን ሰፊ ልብስ ይበልጥ ያወፍርሻል ብሎኛል..

ማለቴ ብለውኛል... ጓደኞቼ”

ተንተባተበች፡፡ ሲጋራ ልለኩስ በረንዳ ወጣሁ፡፡

የሁለት ሲጋራ ዕድሜ ጠበቅኳት፡፡ አልወጣችም፡፡ በጥልቅ ተነፈስኩና ወደቤት ገባሁ፡፡

"ሳምሪ!”

“ጨርሻለሁ!”

እየተንደፋደፈች ሁሉ ነገሯን አጣብቆ ይዞ፣ ጾታዋን በአንድ ዕይታ ብቻ የሚያረጋግጥ እጅግ ጠባብ ቢጫ ሱሪ ለብሳለች፡፡
ዐይቼው አላውቅም፡፡

ጸጉሯን ሙልጭ አድርጋ አሲዛዋለች፡፡

ይሄንንም አላውቀውም፡፡

ማታ ያየሁት ጡት መያዣዋ ጫፍ ከለበሰችው ነጭ ሹራብ አፈንግጦ ይታያል፡፡ ይሄንንም አልለመድኩትም፡፡

ያለ ቦታዋ የምትወድቅ አንዲት ዘለላ ጸጉር እስክትረብሻት ድረስ፣
ተጨንቃና ተጠባ፣ ያመለጡ ጸጉሮች እንደሌሉ ለማረጋገጥ ጸጉሯን ትሞዥቃለች፡፡ ከኩል ውጪ የማታውቀው ሚስቴ... በሜክአፕ ተዥጎርጉራ የአውሮፓ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊ መስላ መጥታለች፡፡

“ምንድነው ዛሬ እንደዚህ ለየት ያልሽው?” አልኩ፣ ታክሲው መጠበቂያው ጋር ስንደርስ፡፡

“ስብሰባ አለን... እኔ፣ ቃልኪዳንና በረከት፤ ስብሰባ አለን..."

በረከት....!

ጥርሴን እያንገጫገጭኩ ታክሲ ውስጥ ገባሁ፡፡
****
በዚያ ሳምንት ቅዳሜ ጠዋት ለአራተኛ ጊዜ ቃልኪዳንና በረከት ቤታችን እንደሚመጡ ነገረችኝ፡፡

“ያው እንዳልኩህ በረከትም ይመጣል... ስምንት ሰዐት ነው የሚደርሱት... ጥቁር ስንዴ ዳቦ እወዳለሁ ሲል ስለነበር እሱን
ከባልትናው ቤት አዝኜለታለሁ... ማለቴ ቃልም ስለምትወድ...ይዤ እመጣለሁ ... ልጅቷን ቤቱን በጠዋት መጥተሽ አጽጂ ብያት ነበር... የት አባቷ ናት በናትህ?...”

ለስምንት ሰዐት ቀጠሮ፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰዐት ተኩል ላይ ምን እንዲህ እንደሚያደርጋት ዐውቃለሁ፡፡

ድፎ ዳቦው... ጽዳቱ... ለወትሮው ከሰዐት የምትመጣውን ተመላላሽ
ሰራተኛችንን በሌሊት ድረሺ ማለቱ... ከሁለት ቀን በፊት የተጀመረው ባለ ስድስት ወጡ ድግስ...ግልጽ ነበር፡፡

ዳቦውን ይዛ ስትመጣ ሦስት ሰዐት አልፎ፣ ልጅቱም መጥታ ጽዳቱን አጧጡፋ ነበር፡፡

ስምንት ሰዐት ከሩብ ሆነ፡፡
ተሞልጮ የታሰረ ጸጉሯን ዐሥር ጊዜ እየነካካች፣ ጥብቅ ያለ ቀሚሷ
ያወጣውን ሞላላ ቂጧን ሠላሳ ጊዜ በመስታወት እያየች፣ በሜክአፕ
ያበደ ፊቷን መቶ ጊዜ እያስተካከለች፣ በመቁነጥነጥ ስትጠብቅ ቆይታ ስምንት ከሩብ ላይ በራችን ተንኳኳ፡፡

ሚስቴን ሳይነጥቀኝ የወሰደውን፣ ሳይቀማኝ ያገኛትን ሰው ላየው ነው፡፡ ፍቅሬን አጠገቤ እያለች እንቁልልጭ ያደረገብኝን ሰው ልተዋወቀው ነው፡፡

በሩን ከፍታ ቃልኪዳንን (በኔ ግምት ብቻውን መጣ እንዳይባል የገባች ሰበብ ናት) ካቀፈቻት በኋላ
👍5
#ባርቾ
:
:
#በሕይወት_እምሻው

በ12 ዓመቴ...ስቅስቅ ብዬ» አልቅሼ ስጨርስ ፣ በለቅሶ ይባስ የጠቋቆረ ጥቁር ፊቴን በቀኝ እጄ አይበሉባ እያሻሸሁ ወደ ቤት ስገባ ፣ እማዬን በር ላይ አገኘኋት: :

“ምን፣ ሆንሽ ባርቾ? ... ምነው?”

“ምንም! ” አልኳት ፡ : የደረሰብኝ ነገር ደግሞ ማውራቱ ይበልጥ የሚ ያስለቅሰኝ መስኰ ስለተሰማኝ : :

“ምን... ምንም ትይኛለሽ? ስታለቅሺ አልነበርም?” እማማ ተቆጣች ፡ :

“ትምህርት፥ ቤት ...” አልኩ አልቅሼ የጨረስኩት የመሰኝ እንባዬ እንደ
አዲስ ዐይኔ ውስጥ ሲሞላ እየተሰማኝ ፡ :

“ምን ሆንሽ .. ? ከማን ጋር ተጣካሽ?”

“አማርኛ አስተማሪ ... ቲቸር ስንሻው ...”

“ገረፈሽ ...? ጎሽ! የቤት ሥራ ሳትሰሪ ሄደሽ ገርፎሽ ነው አይደለም?

ደግ አደረገ፡”

“አይደለም አረ... እኔ የቤት ስራዬን ሰርቻለሁ ...”

አህስ... ስትርብሺ ዐይቶሽ ነው አይደለም? እያስተማረ ስቶረብሺ? ነይ
እንዲውም እኔም እጨምርልሻለሁ!” አለች እማዬ ቱግ እያለች ፡ :
አሁን ቀበቶ ፍለጋ ወደ ጎዳ ስትገባ ዐየሁና ጮክ ብዬ፣ አይደለም
እማዬ... እግዚአብሔርን፣... የገና ድራማ አትሠሪም ብሎኝ ነው አልኳት ፣ ስር ስሯ እየተከተልኳት።
ቀበቶውን፣ መፈለጓን ትታ ዞር ብላ አየችኝና ፣ “የገና ምን... ምን አትይም
ብሎኝ ነው? ” ብላ ጠየቀችኝ : :

“የገና ድራማ አትሰሪም ብሎኝ ነው እማዬ” አልኳት : :
ምንድነው ደግሞ የገና ድራማ?”
ባለፈው... ለገና በዓል የክርስቶስ፣ መወለድ በድራማ ትሰራላኝሁ ተብለናል ብዬ ከብሩኬ ጋር ሳጠና አልነበረም እማዬ?”

"ያ ... ሁሉንም በቃሌ መያዝ አለብኝ ስትይው የነበረው ነው እሱ? ”
“አዎ... እማዬ: :
“ታዲያ ፈቅዶልሽ አይደለም እንዴ አጥኚ የተባልሽው?”
“አዎ... እማዬ” አልኳት ፣ እንባዬ ሲመለስ እየተሰማኝ : :
“እና ታዲያ ምንድነው አትሰሪም ያለሽ አሁን?”
“አትሰሪም አትሰሪም አይደለም እኮ ያለኝ ” አልኩ ለቅሶዬን ጀምሬ : :
“ልጅቷ ያማታል እንዴ ...? ምንድነው የምትቀባጥሪው? አትሰሪም አለኝ
አላልሽም አሁን?” አለች እማዬ ቁጣዋ ተመልሶ : :
እኔ የፈለኩት እመቤቴ ማርያምን፣ ሆኜ መስራት ነበር ፡ : ሳጠና የነበረው እኮ የእመቤቴ ማርያምን፣ ነው ... እሱ ግን...

“እሱ ግን…? ምን አለሽ ታድያ ? ”
“እሱ ግን ቲቸሮች ሁኑ ተነጋግረንበት ነበር : :አንቺ በደንብ ብታጠኚውም ጥቁር ስለሆንሽ ማርያምን፣ ሆነሽ መስራት አትችይም : :
ሩት ናት ማርያምን የምትሆነው አለ” ብዬ ለቅሶዬን በነጻነት አድምቄ ጀመርኩት ፡ :

እማዬ ካሁን አሁን ተሰምቷት መጥታ እቅፍ ታደርገኝና ፣ እምባዬን ታብሰውና ፣
የሚይረባ! የኔ ልጅ ናት ማርያምን፤ ሆና የማትሰራው?
ነገውኑ ከአባትሽ ጋር ሄደን ለዲሪክተሩ ነገርነ ነው የምናስባርረው... አይዞሽ
ልጄ” ትለኛለች ብዬ ስጠብቅ ፣

“እውነቱን ነዋ! እስቲ የእመቤቴን ምስል
ዕይው! ምኗ ነው ከቶ አንቺን የሚመስል? አስተማሪሽ የሚልሽን፣ ስሚ ! ልክ ነው!” ብላ፤ ወደ ኩሽና ገባች: :

የዛን ዕለት እመቤቴ ማርያምን፣ ሆኜ ለመጫወት የነበረኝን ጉጉት ባጭር
የቀጩትን “ቲቸሮቼን፡” ፣ ድራማውን፤ በማጥናት ከእሷ 0ሥር እጅ
ብሻልም ቀይና ሰልካካ ስለሆነች ብቻ ማርያምን ሁኚ ተብላ የተመረጠችውን፣
ሩትን፣ ካልጠፋ ቕላት ጥቁር አድርጎ የፈጠረኝን፣ ፈጣሪንም በአንድነት
አማረርኩ ፡ :

ምሽት ላይ ፤ እኔ ፣ ትልቋ እና ቀይዋ እህቴ ፣ ቀዩ ወንድሜ ፣ ጠይሙ አባቴና በጣም ቀይዋ እናቴ ተሰብስበን ቴሌቪዥን እናያለን። ለነገሩ ቴሌቪዥኑን የሚያዩት እነሱ እንጂ እኔ የማየው እነሱንና ቅላታቸውን፣ ነው : : እያየኋቸው እናደሚከተለው አሰባለሁ ፣

...እስቲ አሁን በእመቤቴ ፣ እኔ ከየት መጥቼ ጠቆርኩ? አባቴ ጠይም
ነው ፤ እናቴ በጣም ቀይ ናት ፡ : ሁለቱ ሲቀላቀሉ እንደ እህቴ ስህንና እንደ ወንድሜ ብሩክ ቀይ ሰው ባይፈጥሩ እንኳን እንደኔ ጠቋራ ሰው መፍጠር ነበረባቸው? የእህቴስ ይሁን፡ : ሴት ናት : : በዛ ላይ ታላቄ ናት ፡ ይሁንላት ትቅላ ፤ ግን አሁን እኔ ከምጠቁር ወንድሜ ቢጠቁር ምናለበት እስቲ…? ደግሞ እኮ እኔ ብቻ አይደለሁም : :ሁሉም ሰው የሚለው ነገር
ነው : : እማዬ ሁል ጊዜ ብሩክንና እኔን ይዛን ወጣ ስትል ፣
አይ ወይዘሮ ኤልሳቤጥ! ሴቷን ልጅ አጥቁረሽ ቅላትሽን፣ ሁኩ ወንዱ ልጅ
ላይ አባከንሽው! መልክ ለወንድ ልጅ ምን ያደርጋል አሁን? አሄሄ!” ይላሉ

እኔ እንዲህና እንዲያ ሳስብ ቴሌቪዢኑ ላይ ጓድ መንግስቱ ሐይለማርያም
የዛንቢያውን፣ ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንዳን፤ ሲቀበሉ የሚያሳይ ምስል መጣ ፡ :

መንግስቱ ኃይለማርያም ቴሌቪዥን ላይ ፣ በመጣ ቁጥር የሚቀልዱብኝ ቀልድ
እስኪጅምር ጠበቅኩ ፤ “መንጌ እኮ አባትሽ ነው” ሊሉኝ ነው ።ጠበቅኳቸው።

እህቴ ቀደመችና ፣ ይሄውልሽ ሜሮን አጎትሽ አባትሽን ለመጠይቅ አዲስ
አበባ መጣ!” ሁኩም ሣቁ።

እኔ ግን ነጭ መሃረብ እያርገበገበ ከአውሮፕላን የሚወርደውን፣ “አጎቴ፣” ኬኔት ካውንዳን እየያየሁ እግዚአብሔር ከነነጭ መሃረቡ በአውሎ ንፋስ ጥ...ር...ግ አድርጎ ወደ መጣበት ቢመልሰው እቸተመኘሁ ከእንባዬ ተናነቅሁ : : ደግሞ በዚህ ጥቁርቱ ላይ ነጭ መዓርብ የሚይዘው አማረብኝ ብሎ ነው? ...ወይስ ከሩቅ እንዲታይ? አንጀቴን
አሳረረው : :

“ዕያት ... ዕያት ... በሸቀች! በሸቀች” ይላሉ እየተቀባበሉ።

“አትናደጂ! ይባስ ያጠቁርሻል” አለ
ብሩክ ፣ አጠገቤ መጥቶ እየሣቅ ።

የማርያም አጃቢ ሆኜ የገናውን ድራማ በሰራሁ በሁለት ሳምንቴ አስራ ሶስት
ዓመት ሞላኝ : : ሁሌም ለልደቴ እንደምናደርገው ድፎ ዳቦ ዳቦና
ሻማ ፣ ከተወሰኑ የለስላሳ ጠርሙሶች ጋር ይዘን የልደት ፎቶ ልንነሳ ከእማዬ ፣ አባዬ ፣ ስህንና ብሩክ ጋር አስረስ ፎቶ ቤት ሄድን ጋሽ አስርስ ይወደኛል ፤ “ኮረሪማ!” ይለኛል ገና ከሩቅ ሲያየኝ : :
“ኮረሪማ አረጀሽ በቃ! ትልቅ ሰው ... ትልቅ ኮረሪማ” አለኝ፤ ገና ከመግባታችን። ሣቅኹ ።መጣና እቅፍ አድርጎ ከሳመኝ በኋላ ለፎቶው መዘጋጀት ጀመርኩ።

ጋሽ አስርስ ሁሉን ነገር አሰናድቶ ለማንፀሳት ሲያነጣጥር አባቴ ጮክ አለና

“አስረስ ፣ ይህን መጋረጃ ቀይረው እንጂ ” አለው።
“የቱን? ” አለ ጋሽ አስረስ ፣ ካሜራው፣ ከእነ አንትገ ማንጠልጠያው፥
ከፊቱ ወደ ደረቱ፥ እየመለሰ ።
“ከኋላዋ ያለውን ጥቁር መጋርጃ!” አለ አባቴ : :
ኋላ ላይ ሻማው ፣ ጥርሷና ሚሪንዳው ብቻ ይወጣልህና ጉድ እንዳትሆን!” ሲለው ፤ ይወደኝ የመሰለኝ፤ ጋሽ አስረስ ከቀያዮቹ ቤተሰቦቼ ጋር ተደርቦ ሲስቅ ጠላሁት : :
።።።።።
በሃያ ሁለት ዓመቴ...
እንዲህ እንዲህ ሲብስ ሲብስ ፣ “ባርቾ እኮ ጭንቅላት ባይኖራት ጉዷ ነበር!
“አንቺ፤ ግን ሀበሻ ነሽ? ጋና እኮ ነው የምትመስይው!”
.
:
ሲሻል ደግሞ ፣ ብትቀላ ቆንጆ ነበረች፡ : እየተባልኩ፣ በቀያይ ቤተሰቦቼና ዘመዶቼ እየተቀለደብኝ ኖርኩ ፡ : በሃያ ሁለት ዓመቴም የትወና ጥበብ ተምሬ ጨርስኩና የጊዜውን የፊልም ሥራ በርከት ለመቋደስ ብዙ ቦታ ተመዝግቤ መፈተን ጀመርኩ። ከኮሌጅ ሰቅዬ
ነበር የተመረቕኩት ፣ ግን ደህና የፊልምም የቲያትርም የትወና ሥራ ማግኘት አልቻልኩም : : “በጣም አሪፍ ነው ፡ ፡ እናደውልልሻለን። ይሉኝና አይደውሉም።
ሌሎቹ ደግሞ ፣ ለትወና ሥራ አመልክቼ ፣ “ፐ! አንቺ በጣም ጎበዝ ተዋናይ ነሽ... ለምን፣ ማስተማር አትሞክሪም? ” ይሉኝና ያሰናብቱኛል። ነገሩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግልጥልጥ ያለልኝ ፤ ታሪኩንና ስክሪፕቱ
👍1👏1
#አሜሪካን_ጉዞ

#በሕይወት_እምሻው

እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ፣ አሜሪካ ለመሄድ ሰ...ፍ ማለት
የጀመርኩት በልጅነቴ ለሚከተሉት ነገሮች በተከታታይ ተጋልጬ ስለነበር ነው።

1. 0ሥር ዓመት ሲሆነኝ የዕድሜ እኩያዬ ካሌብ ፣ “ባቡር መንገድ” ተሻግሮ ትልቅ ሕንጻ ከሚሠራበት ቦታ ፣ ትንሽ ስቶኮ ሰርቆና ደብቆ አመጣና ሁላችንንም ሰብስቦ ፣ “እዩ! የአሜሪካን ጭቃ!” አለን ከስንት ወረፋና ልመና በኋላ የአሜሪካ ጭቃውን፤ አስነካኝ ፡ :
ጣቶቹ በፍራሽ ላይ የሚዘሉ መሰለኝ ይደላል ይመቻል።
“የአሜሪካ ጭቃ ይሄ ነው?” አልኩት ፡ :
“አዎ... ዝናብ ሲዘንብ ጭቃቸው ይሄ ነው ... ደስ አይልም?” አh፤ : :
ሲቆይ የኔ እንዳይመስለኝ፤ ፈርቶ ነው መሰለኝ፤ ስቱኮው፣ እየነጠቀኝ ፡ :
''ጭቃው እንኳን እዲህ ያማር ሀገሩ ፣ ምንኛ ግሩም ነው?” ብዬ እያሰብኩና የሃገሬን ከአፈርና ውሃ የተሰራ ''ተራ" ጭቃ በእግሮቼ እያቦካሁ ወደ ቤቴ ዔድኩ ፡ :

2. በዐሥራ ሁለት ዓመቴ አብሮን የሚማረው የአጎኔ ልጅ ጋዲሳ ፣
አሜሪካ ለመሄድ “ፕሮሰስ”መጀመሩ እንደ ከባድ የሃገር ሚስጥር በእናቴ ፣ በእሱ እናት ፣ በአባቴና በእሱ አባት መካከል በሹክሹክታ ሲወራ ጓዳ ሆኜ ባጋጣሚ ሰማሁ : :
“ፕሮሰስ” ቃሏ ባትገባኝም ወሳኝ ነገር መሆኗ ገብቶኛ:
"ደሞ ለማንም እንዳታወሪ... ፕሮሰስ ለሰው ከተወራ ይበላሻል: : ” እናቴ
ናት ቀስ ብላ ያለችው : :
“አር እኔ ፤ ለማ፣ ምን፣ ብዬ አወራለሁ ...? በሚስጥር ያስጀመረችው
ድንግል በምስጢር ታሳካከት እንጂ...” የጋዲሳ እናት እትዬ ወላንሳ : :
“እናንተ፤ ናችሁ መቼም ወሬ አይጎዳም እያችሁ የምታዛመቱት! ዛሬ ሰው
ተንኮለኛ ነው ... አንድ ሰው አፍ ውስጥ ከገባ 'ለምን' ሆነለት ብሎ ለማፋርስ ሌተ ቀን የሚሰራ ብዙ ነው : : ዋ! ነገርኩ እንግዲህ! ይሄ ነገር ከዚች ቤት እንዳይወጣ!” አባቴ ነው : :
ሴቶቹን በቁጣ ሲያይ ኮሎኔል መንግስቱ መድረክ ላይ ቆመው ለሕዝብ ንግግር ሲያደርጉ እንደሚሆኑት ይሠራዋል : :
“ፕሮሰስ” ከባድ ነገር እንደሆነ የገባኝ ያኔ ነው : :

ከጥቂት ሳምንታት በኋካ ፤ እማዬ ፣ የእትዬ ወላንሳ የሴቶች ማኅበር
ድግስ ይዛኝ ሄደች : : ተጨማሪ ሰሃን አምጪ ተብዬ ኩሽና ገብቼ ስመለስና ያለ አቃሟ ትልልቅ ሶፈፋዎችና ሴቶች ይዛ የተጣበበችው ሳሎን በእልልታ በአንድ እግሯ ስትቆም አንድ ሆነ

“አቤት ድንግል ምን ይሳናታል? ድንግል ምን ይሳናታል!

“ ቸሩ መድኀኔአለም እኮ ይሰማል... እሱ ሰመሽ! ወላንሳዬ ፈጣሪ ሰማሽ!
በሚሉ ከዚህም ከዚያም በሚመጡ ዓረፍተ ነገሮች ታጅቦ ዕልልታው
ቀለጠ : :
“የጋዲሳ ፕሮሰስ ተሳካ!” ከሚለው የእትዬ ወላንሳና የእማዬ መረጃ የተሰጠ
ምላሽ ነበር : :
የልጅ የአሜሪካ “ፕሮሰስ” መጀመርና መሳካት ከእናት ፣ ከአክስት ፣ብሎም ለቀበሌው ሴቶች ሁኩ እንዲህ ያለ ደስታ እንዳመጣ ባየሁ ጊዜ ፤
“ወይኔ ይህቺ አሜሪካ ምን ዓይነት ግሩም ሀገር ናት? ያላያት ሁሉ ለሚያያት
ዕልል ለሚልባት ሀገር!” እያልኩና በትልቁ ተቆርሶ የተሰጠንን ድፎ ዳቦ እየገመጥኩ ወደ ቤት ተመለስን።

በሳምቱ ቡዔ ነበር : : የደራው ጭፈራ ግን እኛ ቤት ብቻ ነበር ተደጋግሞ የተሰማው ግጥም ደግሞ ይሄ

“እዛ ማዶ አንድ ጀሪካን ፣
እዚህ ማዶ አንድ ጀሪካን ፣
የኔማ ጋዲሳ ሊሄድ ነው አሜሪካን፣ : :

(በነገራኝ፣ ላይ ሀበሻ አሜሪካን ለምን፣ “አመሪካ” ብቻ ማለት እንደማይችል አይገባኝም : : “አሜሪካን ሀገር ለማለት ፣ “አሜሪካን ሀገር” እንላለ3 ፡ : ነው ወይስ እንዲህ ቡሄ ቡሄ ሲመጣ ስሟ ከጀሪካን ፣
ጋር ገጥሞ ሂያጅ ሀገር እየሰማ እንዲወደስባት ነው?

3. ጋዲሳ ወደ አሜሪካ የሚሔድበት ቀን ደረሰ : :
ቀኑ በብዙ ነገሮች የታጨቁ ቢሆንም በተለይ ትዝ የሚለኝ ግን የሚከተለው
ነው : :

ለወትሮው የት ገባህ? የት ወጣህ? የማይባለው ጋዲሳ ፤ለወትሮው ምን
በላህ? ምን፣ ጠጣህ? ተብሎ የማይጠየቀው ጋዲሳ ፤ ለወትሮው አስር
ጊዜ መታቀፍ ቀርቶ ፣ ዞር ተብሎ ታይቶ የማይታወቀው ጋዲሳ ፤ ልክ በድንገት እንደፀነሰች መሀን ሴት ፤ ልክ በምልጃና ምህላ እንደተገኙ የስለት ልጅ ፤ እንክብካቤ በዛበት ፡ :
“ጋዲሳ ሻወር አድርግ አሁን ፤ ... ሰዐት ደረሰ እኮ!” (ጉዞው ከምሽቱ አራት ተኩል ነው : : ይሄን የተባለውን ግን ከጠዋቱ አምስት ሰዐት ከሩብ ላይ : : )
“ጋዴ...! ለምን የዳግምን፣ ሰማያዊ ጃኬት አትወስደውም? ለብርዱ ይሆንሃል በዛ ላይ አዲስ ነው :የዛሬ ሁለት ዓመት ነው ፣ የቀኝ አዝማች ልጅ ትዕግስት ከእንግሊዝ የላከችለት... አንተ ዳግም! ዳግም!
ከጋዲ ያንን ጃኬት ስጠው!”
ዳግም እባ ቀረሽ ኩርፊያ አኩርፎ ፣ “እምቢ! ለምን እሱ አሜሪካ ሊሄድ ነው
... እኔ ምን አለኝ?” ሲል እናቴ ተቆጥታ ፣
“ያን የመሰለ ጃኬት አንተ የት ትለብሰዋለህ? እሱ ለብሶት ቢሄድ ምን አለበት? ብላው ፣ፍቃዱን ሳትጠይቅ ከቁምሳጥን አውጥታ ሰጠችበት ፡ :
“ጋዲሳ... የአውሮፕላን ምግብ ጥሩ አይደለም ሲሉ እሰማለሁ... እራትህን፣
በደንብ ብላ... ሰዐቱ እኮ ደረሰ!” ይህን የተባለው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዐት ተኩል
ላይ ነው : :

የጋዲሳ ዋጋ በአንድ ጊዜ እንዲህ ከፍ ሲል ቁጭ ብዬ አየሁ።
ጋዲሳ ተከበር : : ጋዲሳ ተወደደ: : አሜሪካ ስለሚሄድ ወርቅ እንቁላል
እንደምትጥል ዶሮ እንክብካቤ በዛበት : :

ወደ ዐሥር ሰዐት ገደማ ፣ ጋዲሳ እንደ ታቦት እየረገዱ ከከበቡት ሰዎች መሀል
ብድግ አለና ፣"በቃ እላይ ሰፈር ሄጄ እነቱቱን ቻው ልበላቸው"ሲል
“በቃ እላይ ሰፈር ሄጄ ራሴን ልግደል " ያለ ይመስል ሁሉም ሰው በአንድነት ክው አለ።
እትዬ ወላንሳ እየሮጠች አጠገቡ ሄደችና “አንተ ልጅ ምን ሆነሃል? መናገደኛ ሆነህ በዛሬ ቀን ከቤት ልትወጣ? ሊያውም ትንሽ ሰዐት ሲቀርህ? ” ስትከው ሁሉም ሰው ፤ “አዎ ... በዛሬ ቀን ባትቀዥቀዥ ጥሩ ነው! ”
“አርፈህ ተቀመጥ!”
“ሆ .…. አንድ ነገር ብትሆንስ? ” በማለት አገዟት ፡ :

ከፖሮሰሱ በፊት ጋዲሳ ከሰፈር ጅብ ጋር እየተጋፋ ሌሊት ስምንት ሰዐት ሲገባ አስታውሳለሁ : :

በቡድን የሰፈር ጠብ ውስጥ ፊታውራሪ ሆኖ በየቦታው እየተፈነካከተ ሲመጣ
ዕይቻhሁ : :

ጠጥቶ በየቱቦው ሲወድቅም ተመልክቻhሁ : :

ያኔ ፣ “አንድ ነገር እንዳትሆን.. ቶሎ ግባ... ተጠንቀቅ!” ያለው ሰው አልነበረም።
ነገሩ ገባኝ : :
ጋዲሳ በዛሬ ቀን እንዳይወጣ የተፈለገው ወጥቶ አንድ ነገር እንዳይሆን ወይ እንዳይሞት ሳይሆን ፤ አንድ ነገር ሆኖ ፣ ወይ ሞቶ ከአሜሪካ እንዳይቀር ነበር : :

ልድገመው : :
ጋዲሳ በዛሬ ቀን እንዳይወጣ የተፈለገው ወጥቶ አንድ ነገር እንዳይሆን ወይ እንዳይሞት ሳይሆን ፤ አንድ ነገር ሆኖ ፣ ወይ ሞቶ ከአሜሪካ እንዳይቀር ነበር : :
ስለዚህ የስንት ዘመን ባልንጀሮቹን እነ ቱቱን ሳይሰናበት ቀረ።

እንደ ዓመት በዓል ሲጠበቅ የነበረው የመሄጃ ሰአት ሲደርስና እቃው ሲመዘን ከሚፈቀደው በላይ ሆነ በሚል ትንሽ ግርግር ከተፈጠረ በኋካ ፣ ጎረቤታች፣ ጋሽ አስራት በሚነዳት ላዳ ታክሲ ወደ ቦሌ ለመሄድ ገባ ፡ ከመኪናዋ ውጪ በጠባቧ ግቢ ውስጥ የሚራኮተው ሰው ሁሉ ዐይን አርፎበታል : : ጋዲሳ ፣ በከፊል በተከፈተው የታክሲዎ የመስኮት መስታወት ሁሉንም እንባ ባቀረረ ዐይኖቹ ያያል : :
ይህን ጊዜ ነው የዲሳ ጓዝ ከመጠን በላይ እንደ ከበደ የገባኝ ፡፡ : ትከሻው ላይ የእናቱን ተስፋ ፣ የአክስቱን አደራ ፤ የእኛን 'ወጥተህ አውጣን” ምኞት
👍1
#አባሮሽ


#በሕይወት_እምሻው


አብረን ያየን ሰው ሁሉ “አፈስሽ አፈስሽ” እያለ ያወራል፡፡
ቆንጀ ፣ ሎጋ፣ ረጋ ያለና ዝምተኛ ነው፡፡ የወንድ ልጅ አማላይነት
የተሠራው ከእነዚህ ተንኮለኛ ንጥረ ነገሮች አይደል?
በፍቅር መውደቅ ከገደል እንደመውደቅ ያማል? በፍቅር መያዝ
እንደ ተስቦ ያማቅቃል?
አዎ፡፡ ቢሆንም እያመመኝ እወደዋለሁ፡፡ እየማቀቅኩ አፈቅረዋለሁ፡፡
እኔ እወደዋለሁ ፤ እሱ ግን እንደ ሁሉም ሰው በግብረ ሥጋ ሳይሆን
ከመላእክት ተዳቅሎ እንደተፈጠረ ይለጠጥብኛል፡፡ ይንበላጠጥብኛል፡፡
ቢሆንም ስሜቴ ለእርሱ ባሪያ ነው፡፡ ሲያወድሰኝ ብቻ የማብብ -
ሲኮንነኝ የምጠወልግ ፤ ሲመለከተኝ የማምር - ፊቱን ሲያዞርብኝ
የማስቀይም፤ እስከሚመስለኝ ድረስ እወደዋለሁ፡፡
ይሄን ዐውቃለሁ፤ ፍቅሬ አቅብጦታል፡፡ መውደዴ አቀማጥሎታል፡፡
ብዙ ጊዜ ደህና ስንጫወት እንውልና በድንገት ያኮርፈኛል፡፡
ይኮፈሳል፡፡ ዐይኔን ማየት ይጠላል፡፡ ያን ጊዜ ሁሉ ነገር
ይዞርብኛል፡፡ ሣቄ ይከስማል። የልቤ ሱረቃ በሐዘን አታሞ ይተካል፡፡
ይገርመኛል፡፡ በስሜቴ ላይ እንዲህ እንዲሰለጥን ከመፍቀዴ በፊት ፤
እሱን ከማግኘቴ በፊት፤ በምን ነበር የምቀው? በምንስ ነበር የምደሰተው?

“ምን ሆንክብኝ?” እለዋለሁ፡፡ ልክ እንደዚያ ሲሠራው::
“ምንም አልሆንኩም.. ተይኝ ላንብብበት።” ለዚህች ለዚህች ጊዜ
ተዘጋጅታ የምትቀመጥ፣ መዥረጥ አድርጎ የሚያወጣት .
የዘወትር መልሱ ናት፡፡

"ኤሊ..."

“እ...” (ከልቡ ሳይሆን)

“ሻይ በጦስኝ ላፍሳልህ?”

(ሻይ በጦስኝ ስለሚወድ)

“አልፈልግም”

“ፍሬንድስን ልክፈትልህ?” (ፍሬንድስን አይቶ ስለማይጠግብ)
“አላሰኘኝም”

“ቶሎ ሃያ ሁለት ሄጄ የፀሐይን ሽሮ ይዤልህ ልምጣ?” (ከትግሬ ሽሮ ሌላ በዓለም ላይ ደህና ምግብ ያለ ስለማይመስለው)

“አልራበኝም...”

“እሺ ምንድነው ምትፈልገው?»

“ተይኝ ላንብብበት...”

ይሄኔ ነው፣ የአዳም ረታን አንዱን መጽሐፍ አውጥቶ ጥሎኝ
የሚሄደው፡፡ ይሄኔ ነው፣ የራሱን ክብ ዓለም ፈጥሮ  አንዱን መጽሐፍ አውጥቶ ጥሎኝ አፈናጥሮ የሚያስወጣኝ።ያን ጊዜ ማውራት መቀጠሌ ለሬሳ መድኀኒት ከመስጠት እንደማይለይ ስለማውቅ ጥዬው ለመሄድ እሰናዳለሁ፡፡
መጽሐፉ ላይ  ተተክሎ  አንዴ የላዘዘ ፈገግታ ሲያሳይ፣ አንዴ ጮህ ብሎ ሲስቅ
ከዚያ እንደማልቀስ ሲሠራው፤ በእሱ ስሜት ላይ
በሠለጠነው ብቸኛው ሰው አዳም ረታ እቀናለሁ፡፡ አንዳንዴም የምወደውን ልጅ ስለነጠቀኝ እያልጎመጎምኩ በልቤ እረግመዋለሁ፡፡
“ብዕርህ ይንጠፍ... እጅህን ቁርጥማት ይዘዝበት...” ዓይነት ነገር፡፡
“ልሄድ ነው ቻው” እለዋለሁ፣ ጫማዬን አጥልቄ ስጨርስ፡፡
እሺ... ቻው...” ይለኛል ቦግ ቦግ ያሉ ዐይኖቹን ከመጽሐፉ
ሳይለይ፡፡ ስሜቱን ከአዳም ረታ ገጸ ባሕርያት ሳያላቅቅ፡፡
ያን ጊዜ ከእንባዬ እየታገልኩ ወደ ቤቴ!
             ።።።።።።።።።
ስምንት ወር አብረን ስንወጣ፤ “ስንተኛ ስንነሳ” ፤ ስንገባ፣ ስንወጣ
ብረት አሎሎ ልቡን አልፈታልኝም፡፡ ስለ አለፈ ሕይወቱ አይነግረኝም፡፡ ስለወደፊቱ አያወራኝም፡፡ ከቤተሰብ - ጓደኛ
አያስተዋውቀኝም፡፡
እየቆየ የትርፍ ሰዓት ሥራው መሆኔ ሲገለጽልኝ፣ ጭምቷ ልጅ
ላብድ ደረስኩ፡፡ ተዉኩት ስል እያገረሽ በሚያስቸግረኝ አስቀያሚ
ፍቅሩ ብሸነፍም ቁርጤን ማወቅ እንዳለብኝ አመንኩ፡፡

አንዱን ቅዳሜ ስገሰግስ ቤቱ ደረስኩ። ከሰዐት ዘጠኝ ሰዐት ቢሆንም፣
አብዝቶ የሚለብሰውን፣ እህቱ ከካናዳ የላከችለትን ፒጃማ አድርጎ
ሶፋው ላይ ተጋደም ያነባል፡፡ ማንን? ያንን በየዓመቱ መጽሐፍ የሚያመርተውን አዳም ረታ፡፡
“ስማ ኤልያስ...? እኔ እንደዚህ መቀጠል አልችልም... ማውራት
አለብን...” አልኩ፣ ቦርሳዬን አንዱ ሶፋ ላይ ወርውሬ አጠገቡ
እየተቀመጥኩ፡፡

.
“እ... ?” አለኝ፣ መጸሐፉን ሳይዘጋ ቀና ብሎ እያየኝ፡፡
“ኣመልህ ሊገባኝ አልቻለም... እኔ እወድሃለሁ... ግን የማትወደኝ
ከሆነ... ማለቴ ልብህን የማትሰጠኝ ከሆነ...”

ሳልጨርስ አቋረጠኝ፡፡

“ምንድነው የምትፈልጊው?” ተናዶም በማይለወጠው እርጋታና ግዴለሽነቱ ጠየቀኝ፡፡

.
መጽሐፉን ዘጋ፡፡ ጉዳዩ “ሲሪየስ"  ነው!

“እኔ?”

“አዎ አንቺ...! ምንድነው የምትፈልጊው?”

ምንድነው የምፈልገው? እንዴትስ ብዬ ነው የምጠይቀው...?

ከአንጀቱ - እንዲህ በትኩረት እያየኝ ይጠይቀኛል ብዬ አስቤ
ስለማላውቅ፣ እያሰብኩ ያንን ውብ ፊቱን አየሁት፡፡
ጢሙ እንደምወደው አድጓል፡፡ ጠጉሩ ጨብረር ብሏል፡፡ መከረኛ
ቢጃማው እጅጌና አንገቱ ጋር መንችኳል፡፡
ብም ብሎ ያየኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ይሄን ያህል ጊዜ ሰጥቶ አያየኝም፡፡

አንሶላ መሀል ገብተን ወንድና ሴት . ድርና ማግ ስንሆን እንኳን፣
እያስበው ዐይኖቹን በዐይኖቼ ስይዘው፣ ዐይኖቹ ላይ ትኩረትና ፍቅር
አላይም፡፡ አንዳንዴ እንደውም ውስጤ መቆየት የሰለቸው... ገላዬ
ውስጥ ዘለዓለም የከረመ ያህል፣ የታከተው የሚመስል ነገር ዐይኖቹ
ላይ አነባለሁ፡፡

እንዲህ ዐይቶኝ አያውቅም፡፡

በማውራት ይሄን ያልተለመደ ክስተት ላቋርጥና ላበላሽ ስላልፈለግኩ፣ ካለሁበት ሶፋ እየተሳብኩ ተጠጋሁት፡ ማየቱን ቀጥሏል፡፡ ደርሼ አንገቴን አንገቱ ውስጥ ቀብሬ በጥልቀት
አሽተትኩት፡፡ ጦስኝ ጦስኝ ይላል፡፡ የምወደው ልጅ በጦስኝ፡፡ልቤ እንደሰም ሲቀልጥ፣ መንፈሴ በስሜት ማዕበል ሲታመስ እንኳን፤ የማወራው የማስበው ነገር ከአንጎሌ ሲተን...

“እህስ ምንድነው የምትፈልጊው?” አለኝ፣ ከአንገቱ ውስጥ በእጁ ጎትቶ እያወጣኝ፡፡

“ምንም...”

“ምንም አትፈልጊም?”

“ኤሊ... እንድትወደኝ... እንድትወደኝ ነው የምፈልገው:: ይከብዳል?” ወደ ኣንገቱ ሥር ተመልሼ ልወሽቅ ስል፣ አሁንም
መልሶ አወጣኝና በእነዚያ አሸባሪ ዐይኖቹ እያየኝ..

“መች ጠላሁሽ...?” አለኝ፡፡

"እንደማትጠላኝ ዐውቃለሁ... ግን አንድ ቀን እወድሻለሁ ብለኸኝ አታውቅም፡፡ እ... ከመሬት ተነስተህ ታኮርፈኛለህ:
ታበሻቅጠኛለህ."

“ምንድነው የምትፈልጊው? በሥርዓት ቁጭ ብለን ይሄን ነገር
እንቋጨው...” አለኝ፡፡ ለስብሰባ እንደተቀመጠ ሰው መጽሐፉን
እንደተከፈተ ሶፋው ላይ አስቀምጦ፤ እጆቹን አጣምሮ፡፡ .

ቀና ብዬ ተቀመጥኩ፡፡


“ልብህን... ልብህን ነው የምፈልገው፡፡”

እጆቹን አመሳቀለና ሣቀ፡፡

ተበሳጨሁ፡፡

“ያስቃል?”

“ሃሃ... አዎ... እዚህ መጽሐፍ ላይ ያለው... አንዱ የአዳም ካራክተር' ምን አለ መሰለሽ... ልቤን ለሴት ከምስጥ ለጎረቤት ድመት ብሰጥ ይሻለኛል...”
ዝም ብዬ ዐየሁት፡፡

“ምን ታይኛለሽ... ካ'ንጀቴ እኮ ነው እውነቴን ነው፡፡”

አሁንም ዝም ብዬ ዐየሁት...

ጨረስን? ወደ መጽሐፌ ልመለስ?”

እየቀለድክ አይመስለኝም።

አልኩ፣ | በተቀመጥኩበት እየተቁነጠነጥኩ፡፡

“አይደለም አልኩሽ እኮ...”

“የአንድ ሥራ ፈት ደራሲ ተረት ተረት እና ቅዥት እያነበብክ
የእኛን ሕይወት ማበላሸት አለብህ?”
“አዳም ስለማይገባሽ አልፈርድብሽም...”
“እሱን ተወው... ዝባዝንኬ አይገባኝም... ድመት ምናምን...ሰውየው የሚያወራውን አያውቀው ... ግን አንተ ምነው ለልብህ
እንደዚህ ሣሣህ? ልብህን ስጥተኸው የጎዳህ ሰው ነበር እንዴ?”
እየተቁለጨለጭኩ ተጠየቅኩት፡፡
ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆየና...

“ለምን ጦስኝ ሻይ አታፈይልኝም?

ጠዋት የጠጣሁ ነኝ” አለኝ፣

መጽሐፉን እያነሳ..

“ለምን አትመልስልኝም...?

ለምንድነው
እንደዚህ ፍቅርን የምትፈራው?”

“በናትሽ ሻዩን... እያዛጋኝ ነው...”
የምናብ ደጁ ሊዘጋብኝ ነው። ለዛሬ
👍6011👏2😁1
#የአልጋ_ላይ_ዱካ


#በሕይወት_እምሻው

ትላንት ማታ ክፉ ነገር ተፈጠረ፡፡
መልከ መልካሙና ገራገሩ እጮኛዬ ላይ ማገጥኩበት፡፡

ያች በልጣጣ ጓደኛዬ ትዕግስት ናት፣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የከተተችኝ።
ሁሌም ለሰኔ ሚካኤል ቤቷ ድል ያለ ድግስ ታዘጋጃለች፡፡ የምታውቀውን ሰው ሁሉ ትጋብዛለች፡፡ ከልክ በላይ
ታበላለች፡፡ ከመጠን በላይ ታጠጣለች፡፡ አንድ ውስኪ ለሦስት ሰው እየቀረበ፣ በረዶ አንሷል እየተባለ ውስኪ እንደተፈጠረ በጉሮሮ ሲንቆረቆር፣ ሰዉ ሁሉ ከማያውቀው ሰው እንደ አብሮ አደግ ይሣሣቃል፣ ያሽካካል፡፡ ምስጢር ይጋራል፡፡ ይሟዘዛል፡፡ የትዕግስት
ፓርቲ  እንዲህ ነው፡፡ ነጠላ
ሆኖ የመጣን፣ ጥንድ አድርጎ
ይሸኛል፡፡ አይተው ከማያውቁት ሰው አደጋግፎ፤ አስተቃቅፎ፣አልጋ ድረስ ያጓትታል፡፡

ውስኪዋ ውስጥ ትንሽ ቅንዝር ጠብ፣ ብዙ የፍትወት ፍላጎትና የመማገጥ ዓላማ ሙጅር ታደርግበት ይመስል፤ በየዓመቱ የሚወራ የወሲብ ገድል መነሻ ይሆናል፡፡

ለስድስት ዓመታት ይሄንን የተቀበረ የመጠጥ ፈንጂ አልፌ፤ ዘንድሮው ግን ረገጥኩት፡፡
እርግጥ አድርጌ ብ......ው......
አደረግኩት፡፡ አጀማመሩ እንዲህ ነበር፡፡
ጥሬና ጥብሱን ሥጋ፣ ከዚህ በኋላ ለሳምንት አትበሉም የተባልን ያህል ተስገብግበን ጎስረን፣ ጎስረን፣ “እሰቲ አወራርዱት... እስቲ ጥረጉት” እያለች የምታስተናብረውን ትዕግስት እየሰማን፣ ሁለት ጠርሙስ ውስኪያችንን በጉሮሯችን እያንቆረቆርን ስድስት ሆነን
አንድ ጠረጴዛ ላይ ተሰይመናል፡፡

ከለብታ አልፎ ሞቅታ፣ ከሞቅታ አልፎ ስካር ሲጀማምረኝ ትዕግስት
ወደ ጠረጴዛችን መጥታ፣ “አወራርዱት” ባለች ቁጥር፤ የሞት ሞቴን የብርጭቆዬን አፍ በእጆቼ ለመክደን ብሞክርም፣ ልክ ትንኝ እንደምታባርር ሁሌ እጄን ጧ እያደረገች ታስከፍተኝና በውስኪ
ሞልታው ትሄዳለች፡፡

ቺርስ ባሉ ቁጥር እጠጣለሁ፡፡

“አትጨምሪልኝ... በቃኝ” እያልኩ በእጄ ብርጭቆውን ለመዝጋት እሞክራለሁ፡፡

እጄን ጧ አድርጋ፣ ብርጭቆዬን አስከፍታኝ ሞልታው ትሄዳለች፡፡
ቺርስ ባሉ ቁጥር እጠጣለሁ፡፡
እንደገና “አትጨምሪልኝ... በቃኝ” እያልኩ በእጄ ብርጭቆውን ለመዝጋት እሞክራለሁ፡፡

እጄን ጧ አድርጋ፣ ብርጭቆዬን አስከፍታኝ ሞልታው ትሄዳለች፡፡

ይሄ አዙሪት ለዐሥራ ምናምን ጊዜ እንደቆየ ሳሙኤል ከፊቴ ተከሰተ፡፡ ያንን ሰንደቅ የሚያስቅል ቁመቱን፤ የቀይ ዳማ የደስ ደሳም ፊቱን፣ ቦርጭ አልባ ሰውነቱን ይዞ፣ ሳሙኤል ከፊቱ ተከሰተ፡፡ ያውም አንዴ ሁለት፣ አንዴ አራት፣ አንዴ ስድስት
ሆኖ... ሞቅታዬ አብዝቶት፣ ስካሬ አባዝቶት የቀድሞ ፍቅረኛዬ ሳሙኤል ከፊቴ ተከሰተ።

ሲቀመጥ ትዝ አይለኝም፡፡ እጆቼን ሲያሻሸኝ ግን ትዝ ይለኛል፡፡
መጀመሪያ ሲስመኝ ትዝ አይለኝም፡፡ አፌን አፉ ውስጥ ሳገኘው ግን ትዝ ይለኛል።
መኪናው ላይ ስሳፈር አላስታውስም፡፡ አልጋው ውስጥ መግባቴ ግን ውል ይለኛል፡፡ ልብሳችንን ስናወልቅ ትዝ
አይለኝም፡፡ ዕራቁት ሰውነቱን በስሜት ስቧጭር ግን በደንብ ትዝ ይለኛል።

ከንፈር እየተሻማን ስንቃበጥ፣ አንገቴን ሲልስም፣ ሲስምም፤ ኋላም ሴትነቴን በወፍራም ወንድነቱ ሲከድን፣ መሀሉ መሀሉ ጭለማ በገባበት ሁኔታ ትዝ ይለኛል፡፡

ይሄው ነው፡፡

ጠዋት ላይ፣ አልጋው ውስጥ አናት ከሚፈልጥ ራስ ምታት ጋር
ስነቃ፣ ትላልቅ ድፍርስ ዐይኖቹ ተቀበሉኝ፡፡

ራሴን በሁለት እጆቼ ካልደገፍኩ ቷ ብሎ የሚፈነዳ ስለመሰለኝ፣በቀኝም በግራም እጆቼ ጭንቅላቴን ይዤ፣ ከወገቤ በላይ ብድግ አልኩና፣

“ምንድነው ...! ምንድነው ያደረግነው?” ብዬ ጮኽኩ፡፡ ሳሙኤል
ትላልቅ ዐይኖቹን ፊቱ ላይ እያንጎማለለ ሲያየኝ፣ የራሴ ጩኸት ራስ ምታቴን እያባሰው ከወገቤ በታች ዐየሁ፡፡ እንደፈጠረኝ ነኝ፡፡

“ሳሙኤል... እዚሀ እንዴት መጣሁ...? ምንድነው ያደረገገው...?”አልኩ በአንሶላው ተጠቅልዬ ከአልጋው የመሸሽ ያህል እየወጣሁ:ከአልጋው ፈንጠር ብሎ ወጣ፡፡ ቁምጣ ከሚያህል ቡራቡሬ የውስጥ ሱሪ ሌላ ምንም አላደረገም፡፡

“ሆሆሆ! ምንድነው ያደረግነው? ካርታ ስንጫወት ነዋ ያደርነው”አለኝ፣ እየሣቀ፡፡ ጥርስህ ይርገፍ፡፡

ዝም ብዬው ልብሶቼን ፍለጋ ጀመርኩ፡፡

ሮዝ ጡት ማስያዣዬን አልጋው ግርጌ፣ ጥብቅ ያለው ቀይ የድግስ ቀሚሴን ከአልጋው በስተቀኝ መሬት ላይ አግኝቼ፣ በሰማያዊው ለስላሳ አንሶላ እንደተጠመጠምኩ ወደ ማውቀው መታጠቢያ ቤት ገብቼ ፊቴን ሳልታጠብ መስታወቱ ፊት ቆምኩ፡፡

ምንድነው የሠራሁት?

ምን ነካኝ?

እሺ ለብ ይበለኝ፡፡ እሺ ሞቅ ይበለኝ፡፡ እሺ ልስከር፡፡ እሺ እጄን እንዲይዝ ልፍቀድለት፡፡ እሺ ሲስመኝ ልሳመው፡፡ እሺ ትንሽ ልቃበጥ፡፡ ግን ምንስ ያህል ብጠጣ ከትዕግስት ቤት ወጥቼ፣
መኪናው ውስጥ ገብቼ፣ ከብስራተ ገብርኤል ሰሚት ድረስ ንፋስ እየመታኝ መጥቼ፣ እቤቱ ሄጄ፣ መኝታ ቤቱ ገብቼ፣ አልጋው ጋር ሄጄ፣ አልጋው ውስጥ ገብቼ፣ ልብሴን አውልቄ፣ ራቁቴን ሆኜ፣
እጮኛ (ያውም የሰው ጥግ) እያለኝ፤ ከቀድሞ ፍቀረኛዬ ጋር ስዳራ
ማደሬ ልክ ነው?

ለመልአክ ሩብ ጉዳይ በሆነ እጮኛዬ ላይ
መልከስከሴ ግፍ አይደለም?

ቢሰማ አያብድም?

ቢያውቅ ራሱን አያጠፋም?

ፊቴን በቅጡ ሳልታጠብ፣ ከመታጠቢያ ቤቱ ወጥቼ በጥድፊያ ጫማዬን አድርጌ፣ ቦርሳዬን አነገብኩና... “ስሚኝ...” ምናምን...የሚለኝን ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ዘግቼ እግሬ በፈቀደልኝ ፍጥነት
ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ፡፡
የኮንዶሚኒየሙን ደረጃ እየወረድኩ ስልኬን አወጣሁ፡፡
.
ዐሥራ ዘጠኝ ያመለጡኝ ጥሪዎች፡፡ ሰባት የጽሑፍ መልዕክቶች፡፡ከፈትኩት፡፡

ዐሥራ ስድስቱ የእጮኛዬ ጥሪ ነው፡፡ ስማግጥ ያልመለስኳቸው 16
ጥሪዎች፡፡ እርምጃዬን አቁሜ እጄ እየተንቀጠቀጠ መልዕእክቶቹን
ከፈትኳቸው፡፡ ሁሉም ከእሱ ናቸው፡፡

“ማሬ ስልክ አታነሺም” ... “በሰላም ነው...?”... “ኧረ ተጨነቅኩ”...
.
“በደህናሽ ነው?”... “እባክሽ ደውይልኝ... “ትዕግስትም አላነሳ አለችኝ ... “በናትሽ ደውይልኝ” ....

ኮንዶሚኒየሙ ጣራ ላይ ወጥቼ መፈጥፈጥ አማረኝ፡፡

ልደውልለት ግን ጉልበት አጣሁ፡፡ እሱን ትቼ ትዕግስት ጋር ደወልኩ፡፡ በሁለተኛው ዙር ከአራት ጥሪ በኋላ አነሳች፡፡
ሰላምም ሳልላት፣ “አንቺ ማታ ምንድነው የተፈጠረው?” ብዬ ጮኽኩባት፡፡

“እንዴ እኔ ምናባሽ አውቅልሻለሁ... የት ሆነሽ ነው...?” አለችኝ።ድምፅዋ፣ ቤተክርስትያን ሲያስቀድስ አድሮ የመጣ ሰላማዊ ሰው እንጂ፤ አሸሼ ገዳሜ ሲል ያደረ አይመስልም፡፡

“ምን የት ነሽ?” ትይኛለሽ... ሳሚ ጋር ነበርኩ... እንዴት እንዲህ
ዓይነት ነገር ሲደረግ... እዚህ ሲያመጣኝ ዝም ትያለሽ?” አልኩ፣ ቱግ ብዬ እርምጃዬን እያፈጠንኩ፡፡

“እንዴ... ኧረ ቀስ...! አንቺ አይደለሽ ስንት ሆነን ስንለምንሽ፣ ከእሱ በስተቀር ከማንም ጋር አልሄድም እያልሽ፤ እንደ
እባብ ስትጠመጠሚበት ያመሸሽው?” አለችኝ ቆጣ ብላ፡፡

ወሬውን በስልክ መቀጠል ስላልፈለግኩ፣ ቤት መሆኗን አረጋግጬ ራይድ ጠራሁና ስበር ቤቷ ደረስኩ፡፡

በስልክ የጀመረችልኝን አጠናክራ፣ ለያዥ ለገናዥ ማስቸገሬን፤ ያየኝ ሰው ሁሉ ሲሥቅ እንደነበር፤ መጨረሻ ላይ እንደፈለጋት ትሁን ብለው እንደተዉኝ በሚያም ዝርዝር ነገረችኝ፡፡
ያቀረበችልኝን ቁርስ ሳልነካ ሻዩን ብቻ እየማግኩ፣

“ቲጂ...” አልኳት፡፡

“ወይ...” አለች፣ ዐይን ዐይኔን እያየች፡፡
“ደሬ የሚሰማ ይመስልሻል...? ማለቴ ሰው ቢነግረውስ?” አልኳት፡፡

“እ...ህ አይመስለኝም... ደግነቱ እንደዛ ስታብጂ የነበረው አብዛኛው ሰው ከሄደ በኋላ ነው...ማሐቴ ሳሙኤል ካልተናገረ" አለችኝ።

ሳሙኤል ካልተናገረ!

በተቀመጥኩበት መርዶ እንደተረዳ ሰው
👍706😱3🔥2👏1
#ሸሌ_ነኝ


#በሕይወት_እምሻው

"ነይ እዚህ ጋር ! ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ...ብርድ ልብሱ ላይ ተኚ" ሲለኝ፣ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር።

ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ግዜ መሽኮርመም። ሰው እንጂ ሴት ያልሆኑኩ  መስሎኝ፣ ሥጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ።

አንገቴን እንደሰበርኩ ወደ አልጋው ሄድኩ    ሲያገኘኝ እሄድ እንደነበረው አይደለም አካሄዴ።ሰበር ሰካ የለውም፣ ዕዩኝ ዕዩኝ የለውም፣ ተገዝቶ ወደ ሚታረድበት ቦታ እንደሚሄድ በግ ነው አካሄዴ።

ገዥዬ የማያውቀኝ፣ ሰው ፊት ልብሴን ሳወልቅ የመጀመርያዬ እንጀሆነ አያውቅም።

ገዥዬ፣ በገንዘብ ተገዝቼ ከወንድ ለመተኛት ስመጣ የመጀመርያዬ እንደሆነ አያውቅም።

ገዥዬ፣ ለዚህ ስራ ድንግል እንደሆንኩ አያውቅም።

ልብሴን ማውለቅ ሳልጀምር እየፈራው፣ "ይቅርታ....መብራቱን ታጠፋው?" አልኩት።

ዞር ብሎ ዐየኝና፣ "ሃሃ...ሃ! ታሾፌያለሽ እንዴ.? ለምንድን ነው የማጠፋው...? አለኝ። ይስቃል።
ፈራሁ ብለው አያምንም። በሰቀቀን ዝም ብዬ ማውለቅ ጀመርኩ። የአልጋው ጫፍ ላይ ኩምትር እንዳልኩ ድንገት እስካሁን መኖሩን ያላወኩት ብርድ አንዘፈዘፈኝ። ሳል ጀመረኝ።

ይሄን ግዜ ሰውየው ዞር ብሎ ዐየኝና ፤ "ምነው.. ብርድ.. ቲቢ.. ምናምን አለብሽ እንዴ?" አለኝ።

"አይ...በርዶኝ ነው...አያመኝም...አሁን በርዶኝ ነው..." ብዬ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባሁ።

"ኖኖ!...ከላይ ሁኚ...አትግቢ..." አለኝ ቶሎ ብሎ ፣ ቀጭን ትዛዝ ነበር።

እምቢ ብዬ መሄድ እንደማልችል ማወቁ አስከፋኝ። እሺ ብዬው ስለመጣሁ እምቢ ብዬ ስለማልሄድ እርግጠኛ መሆኑን ሳውቅ ከፋኝ። ከነሳሌ ከብርድ ልብስ ወጣሁ። መጥቶ አጠገቤ ተኛ። ሰውነቴ በፍርሃት ተንዘፈዘፈ። ነውስጥ ሱሪ ብቻ ሲቀረው ዕርቃኑን ነው።

እግዜር በሚያውቀው፣ ከማላውቀው ሰው ቤት ለማደር መምጣት አልፈለግኩም ነበር።

የማላውቀው ሰው እጁቹን ጭኖቼ መሀል  አስገብቶ እንዲፈነጭ አልፈለግኩም ነበር።

የማላውቀው ሰው ጆሮዬን ተጠግቶ እንዲያቃትትብኝ አልፈለግኩም ነበር። ግን ሰውየው አስገድዶ አላመጣኝም። አልደፈረኝም።

ያስገደደኝ ኑሮ ነው።

የደፈረኝ ድህነት ነው።

ሲነጋና ከኔ ጋር ያለውን ጣጣውን ሲጨርስ፣ የሰጠኝን አምስት መቶ አዳዳስ ብሮች እንደያዝኩ በትእዛዝ ያወለኩትን ልብሴን በከፍተኛ ፍጥነት ለበስኩ። ያወለኩት ክብሬ ግን አልጋው ላይ ቀርቷል።

"ቅዳሜ እመጣለሁ....ማን ብዬ ላስጠራሽ ?" አለኝ በተኛበት።

እንድሄድ ፈልጓል። አገልግሎቴ አብቅቷል። አሁን እንደተፋቀ የሞባይል ካርድ ነኝ። አሁን እንደተጫረ የክብሪት ዕንጨት ነኝ። በድጋሚ በጉጉት የሚያየኝ በሚቀጥለው ቅዳሜ መጥቼ እፎይ ማለት ሲያምረው ነው። ስሜን ነግሬው ዞር አልኩና ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ለመሄድ ስዞር፣

"ማነሽ...እ...በሩን በደንብ ዝጊው!" አለኝ፣ አልጋው ላይ ተገላብጦ ጀርባውን እየሰጠኝ። ፊት እንኳን የማይገባኝ ሰው መሆኔን ሲነግረኝ ነው በጀርባው የሚያናግረኝ፣ የሚታወስ ሰም እንደሌለኝ ሲነግረኝ ነው ማነሽ ያለኝ።

ይሄን ሳስብ ተዛባሁ፣ ተዛነፍኩ።

ካለ አጥንት እንደተፈጠረ ሰው ሰውነቴ ለመቆምም ለመሄድም እምቢ እያለ ወደ  ታክሲ ተራው ሄድኩ። ተኝቶ የነጋለት ሰው ይተራመሳል።

ታክሲው ውስጥ ገብቼ መስኮቱን ደገፍ አልኩና ያለ እቅድ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። ከዐይኔ ግድብ የሚፈሰው እንባ ጉንጬቼ ላይ የሚያደርቅ ሳይሆን አዋሽ  ወንዝ ለመግባት ያልም ይመስል ይንዠቀዠቃል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው የአንገት  ልብሴ ላይ ያርፋል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ጃኬቴ ላይ ያርፋል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ሱሬዬ ላይ ያርፋል።

በለቅሶዬ መሃል፣ "አይዞሽ... ሁሉም ያልፋል" የሚል ድምፅ ሰማሁና ዞርኩ። ከእኔ በእድሜ የምታንስ ልጅ ናት።

"ሁሉም ያልፋል" የሚል የታክሲ ጥቅስ አንብባ የምትደለለው ለዚያ ነው። ትንሽ ልጅ ስለሆነች፣ በቂ ስላልኖረች። አንዳንድ ነገሮች እንደኔ ላለው ሰው እንደማያልፍ የሚያስተምራት የህይወት ልምድ ስለሌላት፣ ቀልደኛ!

ዝም ብዬ አየሇትና በእሽታ ጭንቅላቴን ነቅንቄ ተመልሼ ወደ መስኮቱ ዞርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ዛሬ እዚህ ታክሲ ውስጥ እያለቀስኩ ባልተቀመጥኩ፣ ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ለአምስት መቶ ብር አምስት መቶ ቦታ ባልተሰባበርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ እኔ ትርሲት የአቶ ከለላውና የወይዘሮ ሥምረት ሴት ልጅ፣ የብሌን ታላቅ እህት፣ የዳዊት ታናሽ እህት፣ የዳግም ፍቅረኛ ሀኜ በቀረሁ። አሁን ግን ትርሲት ሸለዋ ነኝ።

ሸሌ ነኝ፣ ሸሌ ብቻ።

ይህንን ሰውየው ዐይን ውስጥ ዐይቼዋለሁ። ይሄንን ሰውየው ትእዛዝ ውስጥ ሰምቼዋለሁ። ይህንን ሰውየው፣ "በሩን በደንብ ዝጊው" ንግግር ውስጥ አድምጭዋለሁ።

ሸሌ ነኝ።

ለማንበብ ደቂቃ የሚፈጅ ሥም በመስጠት የ'ኔን ሥራ ቅዱስ ማድረግ አይቻልምና፣ የለም፣ አንቺ እኮ 'በወሲብ ንግድ የተሰማራች ሴት' ነሽ!" ብላችሁ አታፅናኑኝ።

ከዛሬ ጀምሮ ሸሌ ነኝ።

በረሀብ እያዛጋሁ ቤቴ ገባሁና ከሰል አቀጣጠልኩ። ሳልበላ ውሃ ላፈላ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ልታጠብ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ገላዬን ልታጠብ። ሸሌነቴን በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርጌ ልታጠብ።

ውሃው እስኪፈላ፣ ልብሶቼን አውልቄ ከሌሎቹ ልብሶቼ ጋር እንዳይቀላቀሉ በቤቴ አንዷ መአዘን ላይ ሰብስቤ ጣልኳቸው። ብዙ ልብስ የለኝም፤ ግን እነዚህን ልብሶች መልሼ የምለብሳቸው አይመስለኝም።

'ራቁቴን የሰመጠች አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ውሃው እስኪፈላ እየጠበቅኩ ቤቴን ዐየሁት። ለሰው የሚነገር ነገር ስለሌለኝ እንትኑ እዚያ ጋር፣ እትኑ ደግሞ እዛ ጋር አለ ብዬ ላወራችሁ አልፈልግም። በዋጋ ከተሰላ፤ አሁን ያለኝ፣ ዋጋ የከፈልኩበት አምስት መቶ ብር ብቻ ነው። አልጋዬ ላይ የተቀመጠው አምስት መቶ ብር።

ምንአልባት ካልገመታችሁ፣ እንዲህ ያለው ዋጋ ያልከፈልኩበት ብር ለማግኘት ሞክሬ ነበር። ማለቴ ዘልዬ ሸሌ አልሆንኩም። አሳጥሬ ልንገራችሁ። ሁሉንም ሥራ ሰርቻለው። ግን እኔንና እኔን የሚጠብቁ ቤተሰቦቼን ሆድ ፀጥ የሚያደርግ፣ አንገት ቀና የሚያደርግ፣ ደረት አስነፍቶ የሚያስኬድ ሥራ አላገኘሁም።

እውነቴን ነው የምላችሁ፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።

ልድገመው፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።

የሥጋ ለሥጋን ኑሮ የመረጥኩት ሌላ ነገር ሆኜ መኖር ስላልቻልኩ ነው። ለምሳሌ የሆነ ሰሞን የሆነ "ኤን ጂ ኦ" ሸሌ የመሆን አዝማሚያ ያሳየነውንም፣ ገብተው የተንቧቹበትንም ሴቶች ሰበሰበና፣ "ከዚህ አስነዋሪና ቆሻሻ ሥራ ነፃ እናውጣችሁ፣....ያልገባችሁትንም እናድናችሁ" አለን።

"አልጋ አንጣፊ ስለሆነች ከአልጋ ለመውደቅ ቅርብ ነች" ብለው ነው መሰለኝ፣ ፕሮጀክቱ ውስጥ አስገቡኝ። ደስ ብሎኝ ገባሁ። ኤን ጂ ኦው፣ "አማራጭ የገቢ ማግኛ ዘዴዎች" በሚል ለግማሻችን ጥልፍ፣ ለግማሻችን ዳንቴል ስራ አስተምሮ፤ "በሉ እንግዲህ ሂዱና ንፁህ ስራችሁን እየሰራችሁ በብልፅግና ኑሮ" ብሎ አንድ ኮንቴነር ቤት ተከራይቶልን ሄደ።

እኔ ከጥልፎቹ መሀል ነበርኩ። እንደተማርኩት እየጠለፍኩ አዲሱንና ንፁሑን ሥራዬን ነጻ መውጫዬ፣ መልካም እጣ ፈንታዬ፣ የእግዜር ካሳዬ አድርጌ ተቀብዬው ሥራ ጀምሬ ነበር።

ብዙዎቻችሁ፣ " እንዴ ሸሌ የሆነች ወይ ለመሆን ያኮበኮበች ሴት ሁሌም ሸሌ ናት" ብላችሁ እንደምታስቡ አውቃለሁ። "በሚኒ ስከርት መንገድ መቆም የለመደች ሴት፣ በ'እስከ ጉልበት' የሥራ ቀሚስ ቢሮ መቀመጥ አትችልም ብላችሁ እንደምታምኑ ከውቃለሁ።
👍9410😁1