አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትልቅ_ደረጃ


#በሕይወት_እምሻው


ከንጋቱ ዐሥራ ሁለት ሰዐት ገደማ... ትራስጌዬ አጠገብ ያለው
ኮመዲኖ ላይ የተቀመጠው ስልኬ ሲርገበገብ ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡
ጥዝዝ... ጥዝዝዝ... ጥዝዝዝዝ....

ተደናብሬ መብራቱን አበራሁ፡፡ ማነው በዚህ ሰዐት የሚደውልልኝ? ስልኩን ከተቀመጠበት አንስቼ ደዋዩን ዐየሁ፡፡ አባዬ ነው፡፡ ስዐቱን ዐየሁ 12፡08

አባዬ በዚህ ሰዐት የሚደውልልኝ ምን ሆኖ ነው? ሁለመናዬ ተናወጠ፡፡ ስልኩን ደግፈው የያዙት ጣቶቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ መቼም በደህናው በዚህ ሰዐት አይደውል! መርዶ ሊነግረኝ መሆን አለበት::
የምሳሳላት ብቸኛ እህቴ የዐይኔ ብሌኔ፣ ኤደንዬ ምን ሆችብኝ? ሳሚ ይሆን? ታዳጊ ወንድሜ ሳሚዬን ምን አገኘብኝ?

እማዬ የሞተች ጊዜም እንዲሁ፣ በዚህ ሰዐት ደውለው ነው፣“ህመሟ ብሶባታል እና ድረስባት” ብለው የጠሩኝ፡፡ አንጀቴ ብጥስ ብሎ፣ አንጎሌ መሞቷን እየነገረኝ፣ ልቤ ግን እውነትም አሟት ይሆናል አይዞህ ብሎ እየደለለኝ ታክሲ ላይ እንደ መንፈቅ ልጅ እየተነፋረቅኩ የደረስኩት፡፡ ያደግኩበት ቤት ደጃችን ላይ ስደርስ፣
ነጠላ ያዘቀዘቁ ሴቶች፣ ወዲህ ወዲያ የሚሉ ካፖርት የደረቡ የሰፈር ሽማግሌዎች፣እዚህም እዚያም የሚሯሯጡ ጎረምሶች ሳይ ነው፣ቁርጤን አውቄ ኮረት ላይ ተንበርክኬ ስሟን እየጠራሁ የጮህኩት፡፡ዛሬ ደግሞ አባዬ በዚህ ሰዐት የሚደውልልኝ፣ ማን ሞተ ሊለኝ ነው?

አነሳሁት፡፡

“ሄሎ አባዬ...” አልኩ፣ ቃላቱን ለማውጣት እየታገልኩ፡፡

“ሄሎ ወንድወሰን... እንዴት አደርክ?”

“ደህና ነኝ እኔ... ምነው ሰላም አይደላችሁም እንዴ?”

“ሰላም ነን... እንዲሁ ፈልጌህ ነው...”

ኡፍፍፍ! ሳምባዬ ይዞት የነበረውን አየር በሙሉ ኡ....ፍ ብዬ አወጣሁት፡፡ ያፏጨሁ መሰለኝ፡፡ የእፎይታ ጩኸት፡፡
እጆቼ መንቀጥቀጥ፣ ራሴ የራሱ ልብ እንዳለው ሁሉ ድው ድው ማለቱን
አቆመ።

“እ... ምነው ታዲያ በዚህ ሌሊት ደወልክልኝ?” አልኩ ድምፄ ወደ
መደበኛው ሁኔታ እየተመለሰ፡፡
“ያው ያንተ ነገር... ከረፈደ ስልክ አታነሳም... ሥራ ሳትወጣ ልደውል ብዬ ነው.... አስቸኳይ ስለሆነ”

“ቢሆንም በዚህ ሰዐት መደወል አልነበረብህም... እኔ እኮ ከአንድ ሰዐት በፊት ከቤት አልወጣም... በጣም አስደነገጥከኝ...”

“አይ! ምን ያስደነግጥሃል?”

“መርዶ ቢሆንስ...?”

“የምን መርዶ...?”

“ምን ዐውቃለሁ እኔ? በዚህ ሰዐት ለመርዶ ካልሆነ ይደወላል...?”

“እስቲ አሁን እሱን ተወውና የደወልኩበትን አዳምጠኝማ!”
የአባዬ ድምፅ ጎላ፤ ቆጣ ካለ፣ ቶሎ የማደርገው ነገር ዝም ማለት ነው፡፡
ዝም አልኩ፡፡

ሄሎ?”

“አቤት አባዬ”

“እየሰማኸኝ ነው?”

“አዎ... እየሰማሁ ነው...”

“እንግዲህ መስከረም አይደል...” ብሎ ጀመረ፡፡ ቅድም ከፍ እና ቆፍጠን ያለው ድምፁ በድንገት እንስ... ቶሎ ኩምሽሽ አለብኝ፡፡

አባዬ ድምፁ የሚያንሰው የማይፈልገውን ነገር ለመናገር ሲገደድ ነው፡፡ አባዬ ግርማ ሞገሳም ድምፁ የሚኮሰምነው ገንዘብ ሊጠይቀኝ ሲል ነው፡፡ አባዬ ገንዘብ ከጠየቀኝ ደግሞ፣ ያሉትን አማራጮች ሁሉ አሟጥጦ ጨርሷል ማለት ነው፡፡ ኩሩ ነውና መሄጃ ካላጣ፣
መሸሸጊያ ካልጠፋበት ፤ እኔን ገንዘብ አይጠይቅም፡፡

ያ ከየት አምጥቶ እንደሆነ ባላውቅም ሳያቋርጥ የሚጥለው ዕቁብ አልደረሰለትም፡፡ ከጓደኞቹ አንድም ሊያበድረው የሚችል ሰው የለም፡፡ በአራጣም ቢሆን ገንዘብ የሚሰጠው አላገኘም፡፡
ይሄንን ሁሉ ደረጃ አልፎ ነው እኔን ገንዘብ የሚጠይቀኝ፡፡ ጅንኑ አባቴ ልጁን ገንዘብ ሲጠይቅ ፤ እንኳን ድምፁ፣ ሰውነቱ ያንሳል፡፡ ያ ጎምላላነቱ ጠፍቶ አንገቱና ቅስሙ ይሰበራል፡፡

“ስንት ብር ፈልገህ ነው አባዬ?” አልኩ፣ ቀላሉን እንዲያደርግልኝ በመመኘት

ጠይቆኝ አልችልም ማለት እሱ እኔን ለመጠየቅ ከሚሸማቀቀው
በላይ ያሸማቅቀኛል፡፡ አብሶ እማዬ ከሞተች በሁዋላ የሴት መላ ጠፍቶ
ቤታችን ዘመም እንዳለ ዐውቃለሁ።
እማዬ ስራ የሚያመጣ ሥራ ሠርታ አትወቅ እንጂ፣ ባንንደላቀቅ እንኳን እሷ
እያለች ሲቸግረን አላውቅም፡፡ ያንን ከውጪ ማጋደል የጀመረ ሰርቪስ፣ ላይ ላዩን አሳድሳ አከራይታ፤ የአባዬን ትንሽ ደሞዝ እስከ ወር መጨረሻ ለጥጣ፣ ፤ በዚህ በኩል ዕቁብ ገብታ፤ በዚያ በኩል
በሴት ማኅበር ድግስ ላይ ጨርቅ ምናምን አትርፋ ሸጣ፤ ትንሽዋን
አብዝታ፣ ጥቂቷን አባዝታ፤ ከኑሯችን በላይ አንቀበራ ታኖረን ነበር፡፡

ትልቅ ደረጃ እንድንደርስ ለራሷ በሁለት ዓመት አንድ ጫማ እየገዛች፣ እስካሁን ሊገባኝ በማይችል ሁኔታ ሦስት ልጆቿን የግል ትምህርት ቤት ታስተምረን ነበር፡፡
ሥራ በያዝኩ በሁለት ዓመቴ እናቴን ሞት መነተፈኝ፡፡ አባዬም ጡረታ ወጣ፡፡ ይከራይ የነበረው ቤትም፣ አባዬ አመል ስላጣ ረግቶ የሚቀመጥበት ሰው ጠፍቶ፤ ከሚከራይበት የማይከራይበት ጊዜ
ይበዛ ነበር፡፡ እማዬ ከሞተች ወዲህ ለአባቴና ለወንድምና እህቴ ኑሮ
ቀላል እንዳልሆነ ይሰማኛል፡፡ አንድ ሁለቴ የሞት ሞቱን ጠይቆኝ፣
የእህቴንና የወንድሜን የግል ትምህርት ቤት ክፍያ አግዤው ነበር፡፡አባዬ ያቅሙን እየታገለ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ግን ከወር ወር ኪሱን የሚሞላ ገቢ የሌለው ጡረተኛ ሽማግሌ ነው፡፡

እማዬ ከሞተች ወዲህ ጎጇችን ምሶሶው
ለመወድቅ እንዳዘነበለ ይሰማኛል፡፡

“ያው ሰርቪሱም ባዶውን ከተቀመጠ አራት ወር አለፈው... አራት
ሺህ የሚከራይ ቤት... ደህና ሰው ጠፋ፡፡ ደላሎቹ ጫት የሚበላ፣ ሲጃራ የሚጠጣ ወፈፌ ብቻ ነው የሚያመጡብኝ.. እምቢ ብዬ ደህና ሰው እስኪያገኝ ብዬ ባዶ ከሆነ አራት ወር አለፈ... ጡረታውም የምታውቀው ነው... ከወር እስከ ወር በመከራ ነው የሚያደርሰን...

አንተን ከማስቸግር ብዬ እነ ኤዱንም ከግል ትምህርት ቤት ላወጣቸው አስቤ ነበር... ግን እናታቸው ብትኖር ምን ትለናለች ብዬ ተውኩት... ዐጥንቷስ
አይወጋኝም... ሁሌም ትልቅ ደረጃ
እንድትደርሱላት ራሷን በድላ ለናንተ ትምህርት የሌለ ገንዘባችንን
ስትገፈግፍ ነው የኖረችው..ታዝንብኛለች.. እነሱን ከለመዱት ትምህርት ቤት... ከጓደኞቻቸው ለይቼ የመንግሥት ትምህርት ቤት ባስገባቸው ምን ይሉኛል? እናታችን ስለሌለች ነው ብለው አያቄሙብኝም... የመንግሥት ትምህርት ቤት ትምህርትስ፣ የት ሊያደርሳቸው... አገር ቤት ያለውም መሬት ቢያንስ ቀለብ ላይ ትንሽ ይደጉመን ነበር ዘንድሮ ደግሞ፣ ድርቁም ሰዉም አብረው
ባዶዬን አስቀሩኝ... ጭራሽ ዕዳም ሳያመጡብኝ አይቀሩ እነሱማ...

ሰው መች አለ ዛሬ... .እናትህ ነበረች
ምታወቅበት.. እኔ ምኑን ከምን ላድርገው ልጄ...”

ው...ይ! ጀመረው ደግሞ፡፡ የራሴ ድው ደው ተመልሶ መጣ፡፡

በረጅሙ ተነፈስኩና

“አባዬ....ስንት ብር ነው የፈለግከው...?” አልኩ፡፡

“አንተስ ከየት ታመጣለህ ልጄ.. በዛሬ ኑሮ... እዚህ ኑር ስትባል ለሥራዬ ራቀኝ... ትራንሰፖርቱም ያው ነው... በዚያው ራሴን
ልቻል ብለህ .... እምቢ ብለህ ኪራይ ቤት አለብህ... ኑሮው እሳት ነው ዛሬ... ወይ ሙያ የለህ፤ ውጪ እየተበላ ገንዘብ እንዴት ይያዛል ዛሬ... ቢሆንም ብድር እንኳን የሚሰጠኝ ሰው ባጣ ነው
ወደንተ መምጣቴ ልጄ.... ባይሆን የመጣው ይምጣ እንጂ በዚህ
ወር ያንን መከረኛ ቤት ለዱርዬም ቢሆን አከራይቼ የስድስት ወር አንድ ላይ ተቀብዬ የቀረውን ወጪ እሸፍናለሁ አሁን የቸገረኝ
ምዝገባ ሰኞ ስለሚያልቅ የልጆቹ ትምህርት ቤት ነው... ክፍያ ጨምረዋል ደግሞ ዘንድሮ... ዩኒፎርሙም ሰማይ ደርሷል... መጽሐፉስ ብትል.. ደሞ ከእኛ ግዙ እያሉ አጥፍ በእጥፍ ነው
የሚያስከፍሉት... ብቻ ይሁን ትልቅ ደረጃ እንዲደርሱልን ነው
2