አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እኔ_እሷና_እሱ


#በሕይወት_እምሻው


#ማስታወቅያ

እንደሚታወቀው አባል ለመጨመር በምናደርገው ማስታወቅያ አትሰልቹ እባካችሁ እኔ በቀን ውስጥ #post የማደርግበትን ሰአት በቻልኩት መጠን ሁሌ ተመሳሳይ #ሰዓት ላይ ለማድረግ እሞክራለው እናንተም ያቺን ሰዓት ለመከታተል እንዲያመቻችሁ ያዙልኝ #ምርጦቼ በተረፈ መልካም #ንባብ
።።።።።።።
አዲስ ፀባይ ካመጣች ሰነባበተች፡፡
ስሙን ለመጥራት ሰበብ መፈለግ እስክታቆም ወደዋለች።
ይሉኝታዋን እንደ ቆሻሻ ልብስ እስክታወልቅ ልቧን ሰጥታዋለች::
ፍቅር ይሉኝታ ያስጥል የለ? ምን ይሉኝ ፍርኀትን ይገፍ የለ?
እህ... እንደሱ፡፡

የጀማመራት ሰሞን፣ “በረከት እኮ... ሂ ኢዝ ሶ ስማርት... እኛ ቢሮ የሚቆይ አይመስለኝም... ማስተርሱን ይጨርስ እንጂ ዩኤን ይጋደሉበታል... እጁን ስመው ነው የሚቀበሉት”

“ባለፈው ከነ በረከት ጋር ሄድንበት ያልኩህ ካፌ ትዝ ይልሃል? እዚያ ውሰደኝ...”

“በረከት እኮ ካለ ቶሞካ ቡና አይጠጣም...እስቲ አንተም የዚህን
የመንደር ቡና ተውና እዛ ጠጣ...”

“እስቲ ይሄን ዲኦ ተቀባው... የዛሬ ወንዶች እኮ ካለዚህ አይቀቡም ... አሽተውማ... ወንዳ ወንድ ሽታ... ደስ አይልም?”
እያለች ነው የጀመረችው።
አብረን ብዙ ቆይተናል፣ ብዙ ነገሬን አስታምማ ነው የምትኖረው፡እወዳታለሁ፣ “ከእሷ የተሸለ ሴት አላገኝም” እያልኩ ተውኳት፡፡ አለ አይደል... ሲጋራ አጨሳለሁ፤ ጫት እቅማለሁ እጠጣለሁ...
ትወቅ አትወቅ አላውቅም እንጂ ሌላ ሴት ጋር ሄጄም ዐውቃለሁ...
ቢሆን እንደ ሌሎች ሴቶች፣ “ተው...” እያለች አተነዘንዘኝም... “ከነምናምኔ ትወደኛለች...” እያልኩ፡፡

የሚያልፍ ነገር ይሆናል. ትረሳዋለች.. ብዬ ተውኳት፡፡ እሷ ግን ባሰባት፡፡ ስሙን በየቦታው ከመሰንቀር ዘልላ፣ በሐሳብ በመንፈሷ ተሸክማው ትገባና ትወጣ ጀመር፡፡

ሳምንታት ሲያልፉ ነገሩ አድጎ ይሰረስረኝ፤ ይገዘግዘኝ ጀመር፡፡ሁለመናዋ ይቀየር ጀመር፡፡

አንዱን እሑድ ምሽት፣ መጽሐፌን ትቼ አስተውላት ነበር፡፡ አብረን
መኖር ከጀመርን ሦስት ዓመታትን ስላለፈን የምሽት - የቀን የአዘቦት ድርጊቷን ቅደም ተከተሉ ሳይዛነፍ ዐውቀዋለሁ፡፡ ሳምሪ ግዴለሽ ሴት ናት፡፡ ጸጉሯን በየሳምንቱ የውበት ሳሎን ሄዳ
የማታቃጥል፣ ልብሷን ተኩሳ የማትለብስ፣ ኩልና ቻፒስቲክ የሜክአፕ ጥግ የሚመስላት፣ አዲስ ልብስና ጫማ በቀጠሮ የማትገዛ ግዴለሽ ሴት ናት፡፡

ያን ማታ ስታደርግ ያየሁት ነገር፣ እንግዳ የሆነብኝ ለዚህ ነው፡፡
በመተኛትና በመቀመጥ መሃል ሆኜ መጽሐፍ የማነብበት አልጋ ጫፍ ላይ ዕይቼ የማላውቀውን፣ ቄንጠኛና ውድ የሚመስል ፓንት ከመሳዩ ጡት መያዣ ጋር ዘርግታ፣ ልክ ቢለበስ ምን
እንደሚመስል በሚያሳይ ሁኔታ ለረጅም ደቂቃዎች ታየዋለች፡፡ ከዚያ ደግሞ ሁለቱንም ታነሳና፣ ጡት መያዣውን ባደረገችው አሮጌ
የሌሊት ካናቴራ ላይ ደርባ፤ ፓንቱን ደግሞ በተግባቢው ቦታ ላይ፣በሁለት እጆቿ ደገፍ አድርጋ መስታወት ታያለች፡፡
“አዲስ ነው አይደል ይሄ ነገር....?” አልኳት፣ ትኩረቷን ለመስበር፡፡

“እ...?” አለች፣ ፓንቱን ወደ አልጋው ጥላ፣ ከነጡት መያዣዋ ወደ
እኔ እየዞረች፡፡

“ፓንቱና ጡት መያዣው... አዲስ ነው ወይ..?” ራሴን ደገምኩ፡፡

“እ... አዎ... ያምራል አይደል?”

“አዎ... ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ስታደርጊ ዐይቼሽ አላውቅም...
ነይ እስቲ...” አልኳት፣ መጽሐፌን ወደ አንደኛው የአልጋው ጥግ ወርውሬ ቀኝ እጄን ዘርግቼ... መጣች፡፡

“ለኔ ነው...?” ፈገግ ብዬ ጠየቅኩ፡፡

“ሃ.ሃ... ታዲያ ለማን ይሆናል...?” እጆቼን ይዛ መለሰች፡፡

“ልበሺውና ልየዋ...”

“አይ... ለነገ ነው ... ማታ ታየዋለህ ...”

ተስፈንጥራ ወደ ቁምሳጥኑ ሄዳ ልብሶቿን አለቅጥ ማተራመስ ጀመረች፡፡

“ምነው...? ምን ሆንሽ...?” አልኩ፣

ባካሄዷ ድንገተኝነት ተገርሜ፡፡
“አይ... ለነገ ልብስ ልምረጥ... ጠዋት መተራመስ አልፈልግም...”

ነገ ስለምትለብሰው ልብስ ስትጨነቅ ዐይቻት አላውቅም፡፡ ጠዋት
ላይ፣ እጇ የገባውን ልብስ አድርጋ፤ እንደነገሩ ሆና እንደምትወጣ
ነው የማውቀው፡፡

ለአፍታ የረሳሁት ጥርጣሬ ሆዴ ውስጥ ተገላበጠ፡፡

ያ ሁሉ ግዴለሽነትዋ የት ገባ? ያልፋል ያልኩት ተባራሪ ስሜቷ መቼ ሥር ሰድዶ ባሕርይዋን መቀየር ጋር ደረሰ? ያን ቀን ነገር እያላመጥኩ አድሬ ነጋልኝ፡፡

ሲነጋ፣ ከጠዋቱ አንድ ሰዐት አልፎ በታክሲ አናገኝም ጭንቀት ተሰቅፌ፣ ቶሎ እንውጣ እያልኩ እማጸናታለሁ፡፡

“ረፈደ ሳምሪ... ቶሎ በይ...”

“በናትህ ልብሴ ሁሉ አስጠላኝ...”

“ትላንት መረጥኩ አላልሽም?”

“አዎ ግን አስጠላኝ...”

“ያ ስኩዌር ስኩዌሩ ሱሪሽ አሪፍ አይደል? እሱን ልበሺ ሳምሪ...”

“አንተ ደግሞ... እሱ በጣም ሰፊ ነው...”
“ሰፊ ልብስ የምትወጂ መስሎኝ?”

“እወድ ነበር አዎ... ግን ሰፊ ልብስ ይበልጥ ያወፍርሻል ብሎኛል..

ማለቴ ብለውኛል... ጓደኞቼ”

ተንተባተበች፡፡ ሲጋራ ልለኩስ በረንዳ ወጣሁ፡፡

የሁለት ሲጋራ ዕድሜ ጠበቅኳት፡፡ አልወጣችም፡፡ በጥልቅ ተነፈስኩና ወደቤት ገባሁ፡፡

"ሳምሪ!”

“ጨርሻለሁ!”

እየተንደፋደፈች ሁሉ ነገሯን አጣብቆ ይዞ፣ ጾታዋን በአንድ ዕይታ ብቻ የሚያረጋግጥ እጅግ ጠባብ ቢጫ ሱሪ ለብሳለች፡፡
ዐይቼው አላውቅም፡፡

ጸጉሯን ሙልጭ አድርጋ አሲዛዋለች፡፡

ይሄንንም አላውቀውም፡፡

ማታ ያየሁት ጡት መያዣዋ ጫፍ ከለበሰችው ነጭ ሹራብ አፈንግጦ ይታያል፡፡ ይሄንንም አልለመድኩትም፡፡

ያለ ቦታዋ የምትወድቅ አንዲት ዘለላ ጸጉር እስክትረብሻት ድረስ፣
ተጨንቃና ተጠባ፣ ያመለጡ ጸጉሮች እንደሌሉ ለማረጋገጥ ጸጉሯን ትሞዥቃለች፡፡ ከኩል ውጪ የማታውቀው ሚስቴ... በሜክአፕ ተዥጎርጉራ የአውሮፓ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊ መስላ መጥታለች፡፡

“ምንድነው ዛሬ እንደዚህ ለየት ያልሽው?” አልኩ፣ ታክሲው መጠበቂያው ጋር ስንደርስ፡፡

“ስብሰባ አለን... እኔ፣ ቃልኪዳንና በረከት፤ ስብሰባ አለን..."

በረከት....!

ጥርሴን እያንገጫገጭኩ ታክሲ ውስጥ ገባሁ፡፡
****
በዚያ ሳምንት ቅዳሜ ጠዋት ለአራተኛ ጊዜ ቃልኪዳንና በረከት ቤታችን እንደሚመጡ ነገረችኝ፡፡

“ያው እንዳልኩህ በረከትም ይመጣል... ስምንት ሰዐት ነው የሚደርሱት... ጥቁር ስንዴ ዳቦ እወዳለሁ ሲል ስለነበር እሱን
ከባልትናው ቤት አዝኜለታለሁ... ማለቴ ቃልም ስለምትወድ...ይዤ እመጣለሁ ... ልጅቷን ቤቱን በጠዋት መጥተሽ አጽጂ ብያት ነበር... የት አባቷ ናት በናትህ?...”

ለስምንት ሰዐት ቀጠሮ፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰዐት ተኩል ላይ ምን እንዲህ እንደሚያደርጋት ዐውቃለሁ፡፡

ድፎ ዳቦው... ጽዳቱ... ለወትሮው ከሰዐት የምትመጣውን ተመላላሽ
ሰራተኛችንን በሌሊት ድረሺ ማለቱ... ከሁለት ቀን በፊት የተጀመረው ባለ ስድስት ወጡ ድግስ...ግልጽ ነበር፡፡

ዳቦውን ይዛ ስትመጣ ሦስት ሰዐት አልፎ፣ ልጅቱም መጥታ ጽዳቱን አጧጡፋ ነበር፡፡

ስምንት ሰዐት ከሩብ ሆነ፡፡
ተሞልጮ የታሰረ ጸጉሯን ዐሥር ጊዜ እየነካካች፣ ጥብቅ ያለ ቀሚሷ
ያወጣውን ሞላላ ቂጧን ሠላሳ ጊዜ በመስታወት እያየች፣ በሜክአፕ
ያበደ ፊቷን መቶ ጊዜ እያስተካከለች፣ በመቁነጥነጥ ስትጠብቅ ቆይታ ስምንት ከሩብ ላይ በራችን ተንኳኳ፡፡

ሚስቴን ሳይነጥቀኝ የወሰደውን፣ ሳይቀማኝ ያገኛትን ሰው ላየው ነው፡፡ ፍቅሬን አጠገቤ እያለች እንቁልልጭ ያደረገብኝን ሰው ልተዋወቀው ነው፡፡

በሩን ከፍታ ቃልኪዳንን (በኔ ግምት ብቻውን መጣ እንዳይባል የገባች ሰበብ ናት) ካቀፈቻት በኋላ
👍5
‹‹አምስተኛዋ እኔ ነኝ፤አላየኸኝም እንዴ? እኔም እኮ ትናንት እዛ ነበርኩ››ፈገግ አለ፡፡

‹‹እኔ እንጃ፡፡ነበርሽ እንዴ? ምን አልባት በጣም ተጠግተሸኝ ተቀምጠሸ ከሆነ ‹ሎንግ ሳይት› በሽታ ስላለብኝ ቅርቤ ያለውን ነገር አጥርቼ ማየት ይቸግረኛል›› ሲል ተረቧን በተረብ መለሰ፡፡ ‹‹አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ነው የቀረህ››

‹‹እንደ እኔ ግን ሴትዮህ አሮጊቷ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ለደቂቃ እንኳን አይኗ ካንተ አይነቀልም፡፡አንተ ስትኮሳተር ፊቷን ታጠወልገዋለች፣ፈገግ ስትል ትገለፍጣለች፡፡ ምራቋን የዋጠች የሠከነች ሚስት እንደሚወጣት እርግጠኛ ነኝ፡፡››

‹‹እሷን እርሻት ባክሽ፡፡አታያትም ጥርሷ እራሱ እንዴት እንደሚገጥ፡፡››

‹‹ምን ሁኚ ምንም አፈቅርሻለሁ... አልተውሽም ብለሀታል፤እረሳኸው እንዴ?››

‹‹አረሳሁም፡፡ ግን እንዲህ አይነት ትሁን ማለቴ አይደለም፡፡ ቦርጯን እስቲ እይው? ከሠሎሞን እኮ አትተናነስም፡፡››

‹‹ያቺ ቀጫጫዋስ? ዛሬ ደግሞ ከትናንቱ በተቃራኒ ፈነዲሻ ሆናለች፡፡››

‹‹እሷ እንኳን ምንም አትል ግን ማደናገሪያ ትመስለኛለች፡፡ ስሜቴ እንደዛ ነው የሚነግረኝ፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ይህቺ አንባቢዋ ሳትሆን አትቀርም፡፡››

‹‹ትናንት እኮ እሷ ልትሆን አትችልም ብለኸኝ ነበር፡፡ እሷ ብትሆን የራሷን መፅሃፍ በማንበብ ግልፅ የሆነ ምልክት እንዴት ልታሳጥህ ትችላለች?»

‹‹ታዲያ ምን ላድርግ፤እሺ ንገሪኝ የትኛዋ ነች?>>

«ያቺ ቀዮስ?»

ፊቱን አዞረ፡፡ ሠርቃ ስታየው ተመለከታት‹‹አምጪ አበባውን ..…ታፍኜ አልፈነዳ››

ከቦርሳዋ አውጥታ ሠጠችው፡፡ እጁን ወደ ኪሱ ከተተና ቀለበቱ መኖሩን አረጋጠ፡፡ ከመቀመጫው ተነስቶ በተንቀረፈፈ እርምጃ ወደ ልጅቷ አመራ፡፡

‹‹ሠው አለው?›› ከፊት ለፊቷ ወዳለው ወንበር በጣቱ እያመለከተ፡፡

‹‹የለውም... ከዛ አባረረችህ እንዴ?››

ምንም ሳይመልስላት ተቀመጠ፡፡በዛው ቅፅበት በጨረፍታ ሲመለከት ጠይሟ ወጣት መጽሀፏን ዘግታ ከመቀመጫዋ ለቃ ወደ መውጫው ስታመራ ተመለከታት፡፡ በጥርጣሬ ታፍኖ በአይኑ ሸኛት፡፡ አሮጊቷም አምስት እርምጃ በማይሆን ርቀት ከኃላዋ አንገቷን ደፍታ ተከትላታለች፡፡ ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡ አይኑን ሲመልስ ወርቃማ ፀጉሯን በቀጫጭን ጣቶቿ ወደኃላ እየላገች አፍጣ በመገረም ታየው ነበር፡፡

እንደመርበትበት አለና አይኖቹን ከአይኖቿ አሸሸ፡፡

‹‹የያዝከው አበባ ያምራል፤ የሚቀበልህ አጣህ እንዴ?>>

‹‹አበባውን የሚቀበለኝ ሳይሆን ክራይቴሪያውን የሚያሟላ ነው ያጣሁት፡፡››

‹‹ስላላፈቀርክ ነዋ፡፡››

<<እንዴት?>>

‹‹ክራይቴሪያ የሚኖረው እኮ ከፍቅር በፊት ነው፡፡ ካፈቀርክ ግን የክራይቴሪያ ዘረ ማንዘሮች ተጠራርገው እንጦሮጦስ ይገባሉ፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ጉድለቶችን ሁሉ አይቶ የማለፍ ብቃት አለውና፡፡››

‹‹እንደመልክሽ ንግግርሽም ጣፋጭ ነው››

‹‹አመሠግናለሁ፡፡ ግን ያቺን የመሠለች ቆንጆ ብቻዋን አስቀምጠህ እዚህ የመጣኸው ልትጀነጅነኝ እንዳይሆን?››

‹‹ብጀነጅንሽ ምን አለበት?››

‹‹ምንም የለበትም፡፡ ክፋቱ ዛሬ መጀንጀን አላሠኘኝም፤ ለማንኛውም አበባውን ግን እቀበልሀለሁ ፤ልትሠጠኝ ከፈለክ ማለቴ ነው፡፡››

አበባ የያዘ እጁን ወደ እሷ ዘረጋ፡፡ተቀበለችው፡፡ ለደቂቃም በፅሞና ተመለከተችው፡፡ እላዩ ላይ የተለጠፈውን ቁራጭ ወረቀት አነበበች፡፡ ‹‹እንቆቅልሽ›› ጮክ ብላ አነበበችው፡፡ በዝግታ ከጎኗ ያስቀመጠችውን ቦርሳ አነሳችና ጭኗ ላይ አስቀምጣ መክፈት ጀመረች፡፡የሁሴንም ልብ አብሮ መከፈት ጀምሯል፡፡እጇን ቦርሳ ውስጥ ከታ ታተረማምሳለች፡፡

‹‹ቀስ ብለሽ ፈልጊው›› አላት ሳያስበው፡፡

ቀና ብላ አየችውና ፈገግ ብላ ወደ ፍለጋዋ ተመለሠች፡፡ እሱም እጁን ወደ ኪሱ ከቶ ቀለበቱን ባለበት ያፍተለትል ጀመር፡፡ዳግመኛ እጇ ከቦርሳዋ ሲወጣ ግን ይዛ የወጣችው የጓጓለትን ሀብል ሳይሆን ቢዝነስ ካርድ ነው፡፡ ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለትና፡፡ ከወንበሯ ተነሳች፡፡ ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ አድርጋ አበባውን በቀኝ እጇ እንደያዘች <<የኔ ማር ዛሬ ሙዴ ስላልሆነ ነው ፤ያው አድራሻዬ፤ ሌላ ቀን ብትደውልልኝ መገናኘት እንችላለን፡፡ እስከዛው አበባህን ውሃ እያጠጣሁ እንከባከባታለሁ›› በማለት ጎንበስ ብላ ጉንጩን ሳመችውና እየተውረገረገች ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ ሁሴን ባለበት ደነዘዘ፡፡ ምንም መናገር አልቻለም፡፡ ምራቁ መረረው፡፡ ትንግርት መጥታ ከጎኑ በመቀመጥ ብታናግረውም አልሠማትም፡፡ትከሻውን እያርገፈገፈች ለማናገር ሙከራዋን ቀጠለች፡፡

‹‹ስማ ነገሮች እኮ አላከተሙም፡፡ ሌላ አንድ እድል እኮ ይቀርሃል፡፡››

‹‹ተይኝ ባክሽ እንዲያውም አንቺ ነሽ›› አንቧረቀባት፡፡

‹‹ደግሞ እኔ ምን አደረግሁ?››

<<አሳሳትሽኛ፡፡ እኔ አሁን ይህቺን ዲቃላ መች አየኋት፡፡ አንቺ ነሽ የጠቆምሽኝ፡፡ ደግሞ አውቀሽ እንድሳሳት ፈልገሽ ነው፡፡››

‹‹እንዴት እንድትሳሳት እፈልጋለሁ?››

‹‹ከእሷ ጋር እንድንገናኝ እንደማትፈልጊ እኮ ከቅድሙ ንግግርሽ ተረድቼያለሁ፡፡ ደግነቱ አሁን ማን እንደሆነች አውቄያታለሁ ነገ ብቻ ይንጋ፡፡ ወደ ኃላ መመለስ አቃተኝ እንጂ ልክ እኔ ወደዚህ ስመጣ ነው እሷ ተበሳጭታ ስትወጣ ያየኋት፡፡››

‹‹እሷ ብቻ እኮ አይደለችም ተበሳጭታ የወጣችው እንዲያውም የእሷን ብስጭት አልተከታተልኩም፡፡ አሮጊቷ ግን አንገቷን ደፍታ ነበር እያዘነች የወጣችው፡፡››

‹‹በቃ ከአሁን በኋላ በራሴ መንገድ መሄድ ነው የምፈልገው ምክርም አልፈልግም፡፡ እንደውም ጥዋት እሸኝሻለሁ፡፡ የመጨረሻውን ፈተና ብቻዬን መጋፈጥ እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ተነሽ ወደ ሆቴላችን እንሂድ..… በጣም መጠጣት አምሮኛል፡፡›› በማለት መቀመጫውን ለቆ ውጪ ወደቆመው መኪና አመራ፡፡ ከኋላው ተከተለችው፡፡ ቀጥታ ያመሩት አልጋ ወደያዙበት ቢሾፍቱ አፋፍ ሆቴል ነበር፡፡

ይቀጥላል

ቀጣዩ ክፍል ማታ #ሁለት #ሰዓት ይለቀቃል እስከዛው በብዛት ዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ጠብቁኝ ቤተሰቦች 😘
 
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍104🥰13🔥65