አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዛሬ_ቀኑ_ምንድነው?


#በሕይወት_እምሻው

ተንበርክኬ ነበር፡፡
በዚያ የጥቅምት ውርጭ፣ ከምሽቱ አራት ሰዐት ተኩል ላይ ከሰማይ በላይ እሪታዬን እያቀለጥኩ፣ቀዝቃዛው አስፋልት ላይ ተንበርክኬ ነበር፡፡ በብርድ በሚንገጫገጨ ጥርሶቼ መሃከል እጮኻለሁ፡፡ ጉሮሮዬ የተሰነጠቀ፣ ደረቴ የተተረተረ እስኪመስለኝ ድረስ እጮኻለሁ፡፡

በኋላ ሲነግሩኝ አደጋው ቦታ አምቡላንስ ደርሶ ልጄን አፋፍሶ እስኪወስደው ድረስ እንዲሁ ስጮኽ ነበር፡፡

ሆስፒታል ስንደርስ በጥድፊያ ልጄን በባለጎማ አልጋ እየገፉ ሌላ
ክፍል ወስደውት አላስገባም አሉኝ፡፡

አትገቢም አሉኝ፡፡

መድኀኒት፣ መድኀኒት የሚለው ኮሪደር ላይ ቆሜ ቀረሁ፡፡ በነጭ ካፖርት ውስጥ ወዲህ ወዲያ የሚራራጡ ሐኪሞች፡፡ ሰማያዊ ለብሰው እዚህም እዚያም የሚሉ ነርሶች፡፡ በየወንበሩ ላይ
አንገታቸውን ደፍተው፣ ጥርሳቸውን እያኘኩ የተቀመጡ ሰዎች፡፡
በአንቅልፍ የናወዙ አስታማሚዎች፡፡ አዲስ አደጋ ይዘው እየጮኹና እያለቀሱ ወደ “ ኢመርጀንሲ” ክፍል የሚበርሩ
አትገቡም እያሉ የሚከላከሉ ነርሶች፡፡ ሐኪሞች፡፡

በቆምኩበት የሆነውን ለማሰብ ሞከርኩ፡፡

እየሣቀ ነበር፡፡ እንቅልፌ መጣ ምናምን ብሎኝ፣ “አንተ እኮ ከእንግዲህ ትንሽ ልጅ አይደለህም... እስከ አምስት ሰዐት መቆየት አትችልም እንዴ...? ዳይፐር እንደገና መግዛት ልጀመር እንዴ?”
ስለው እየሣቀ ነበር፡፡ ያቺ ከአባቱ የወረሳት ዲምፕሉ ፣ ያቺ ፍቅፍቅ እያለ የሚስቃት ሣቁ፣ የግራ መጠምዘዣውን ይዤ ብቅ ከማለቴ በልጄ በኩል ጠርምሶት የገባው መኪና ላንድክሩዘር ነበር። ደማቅና የሚያጥበረብረው መብራቱ ፂርርርርርርር... ጩኸቴ፡፡ ግውውውውውው! ጭለማ፤ የልጄ የሲቃ ጩኸት፤ ጨለማ፡፡ በስሱ የሚሰማኝ የሰዎች ኡኡታ፤ ከአጥንቴ የተለየ
የመሰለኝ ሥጋዬ፤ ድንጋጤዬ፤ ጩኸቴ፤ ጨለማ፡፡ ደማቅ የሰዎች ጩኸት፣ በስመ አብዎች፡፡ አንገቴ ሲዞር፣ ከሶኬቱ ወጥቶ እንደ ጨርቅ የተንጠለጠለው የልጄ እጅ ከጆሮው የሚጎርፈው የደም ጅረት፤ ጩኸቴ፡፡ ተርፈዋል ብለህ ነው? በስመአብ! በስመአብ... ኧረ ለፖሊስ ደውሉ፡፡ ኧረ አምቡላንስ ጥሩ፡፡ በስመ አብ.... የሚሉ ድርብርብ ጩኸቶች፡፡ የሚያለቅሱ ሰዎች፡፡
ከዚያ እንደ ጨርቅ ጎትተው ሲያወጡኝ።
እኔን አወጡኝ፡፡ ደህና ናት፡፡ ተአምር ነው፡፡ ልጁ ግን ተጎድቷል፡፡
ምንም ሳትሆን ወጣች ምናምን ሲሉ ይሰማኛል፡፡
ልጄስ...? ልጄስ...? ልጄን...! ብዬ ስጮኽ ትዝ ይለኛል፡፡
የተከደነ ዐይኖቹ፡፡ ደም የለበሰው ግማሽ ፊቱ፡፡ ደም የተነገከረው
ደረቱ፡፡ ለብቻው የተንጠለጠለው ቀኝ እጁ፡፡ ልጄ!

አትግቢ ወዳሉኝ ዝግ ክፍል ስሮጥ ከወንድ የሚጠነክሩ ሁለት
ነርሶች ጠፍንገው ያዙኝ፡፡

“ልጄን...! ልጄን ልየው?” እያልኩ ሳለቅስ ከለከሉኝ፡፡

“እዚህ መጠበቅ አለብሽ. ሰርጀሪ ገብቷል፡፡ እዚህ ጠብቂ...”
አሉኝ፡፡ በብዙ ሰዎች የተሞላው መስኮት አልባ ስፊ ኮሪደር ውስጥ ተዉኝ፡፡ አብዛኛዎቹ ሰዎች ከብረት የተሠሩ የማይመቹ ወንበሮች ላይ ቁጭ ብለዋል፡፡ ግማሾቹ አቧራ፣ በአቧራ በሆነው ነጭ ወለል ላይ በግዴለሽነት ተዘርፍጠዋል፡፡ የመድኀኒትና የሰዉ ሽታ ተቀላቅሎ፣ የልጄ ምስል ተደምሮ ወደ ላይ አለኝ፡፡

እንደምንም መለስኩት፡፡

አንዲት ሴት ሁኔታዬን ዐይታ ይሁን መቀመጥ ሰልችቷት፣ በ “ነይ
እዚህ ተቀመጪ” እጆቿን ስታንቀሳቅስ፣ በድን አካሌን ይዤ
ከብረት ወንበሩ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ፡፡ ከዚህ ቦታ፣ ከዚህ ሁኔታ ራሴን ብነጥል፤ ይሄን አስቀያሚ ቦታና ሁኔታ፣ ደመና ሆኜ ትንን ብዬ ብለየው ፤ ከጥቅምት ውርጭ
ጋር ተቀላቅዬ በረዶ ሠርቼ
ብተወው ምናለ? ከዚህ ሌላ የትም ቦታ ብሆን፣ ከዚህ ውጪ ምንም ነገር ቢደርስብኝ ምን ነበር?

“ልጄ..!”

እንደገና መጮኽ ጀመርኩ፡፡
ወንበሯን የለቀቀችልኝ ሴት ትከሻዬን ያዝ አድርጋ፣ “አታልቅሺ..ጸልዪ... ጸልዪ....” አለችኝ፡፡

ደመና ሆኖ መትነን የለም፡፡ በረዶ ሆኖ ከአየር መቀላቀል ፤ ሌላ ቦታ፣ ሌላ ሁኔታ ላይ መሆን እንደማልችል ዐውቃ መሰለኝ፡፡

“ጸልዩ....”

ለቅሶዬን ወደ ቀስታ እህህታ አውርጄ አካባቢዬን ቃኘሁ፡፡ እንደኔ በዝምታ የሚያለቅሱ፣ ንፍጥ የሚናፈጡ፣ እንባ የሚጠርጉ፣ እርስ በእርስ የሚጽናኑና የሚጸልዩ ብዙ ሰዎችን ዐየሁ፡፡

በእንባ የራሱ ዐይኖቼን ጨፈንኩ፡፡ ወዲያው ደግሞ ገለጥኳቸው፡፡
በሩ ጋር አንዷ ነርስ ከፖሊሶች ጋር ስታወራ ተመለከትኩ፡፡ በረጅሙ
ተነፈስኩ፡፡ በአየር ፈንታ እሳት ያስገባሁ ያህል ውስጤ ተቃጠለ፡፡ ውስጤ ነደደ፡፡

“ጸልዪ..” አለችኝ፡፡ አሁንም አጠገቤ የቆመችው ሴት፡፡

ከወንበሬ ተንሸራትቼ ወለሉ ላይ ተንበረከኩ፡፡

አንገቴን አቀረቀርኩ፡፡

ዐይኖቼን ጨፈንኩ፡፡

እጆቼን በእንባ የበሰበሰ ፊቴ ላይ አደረግኩ።
ከጸለይኩ ዕሥራ አምስት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ለቀብር ካልሆነ፣
ለዝክር ወይ ለበዓል ቤተ ክርስትያን ከረገጥኩ ብዙ ዓመታት ሄደው
መጥተዋል፡፡ ከእናቴ ሞት በኋላ፤ የቱ ቀን ሚካኤል፣ የቱ ቀን ተክልዬ እንደሆነ አስቤ አላውቅም።

እና ምን ተብሎ ነው የሚፀለየው? አባታችን ሆይ ግማሹ ከጠፋብኝ ሰንብቷል ምንድነው የምለው? አባቴ
ሆይ... በሰማይ የምትኖር...? ዐይኖቼን ገልጬ ሴቲቱን ዐየኋት፡፡ እርጂኝ ዓይነት ዓየኋት

“ዝም ብለሸ ጸልዪ....” አለችኝ፡፡

እጸልያለሁ፡፡ መጀመሪያ ይሄን ሁሉ ጊዜ ስላልጸለይኩ፣ እግዜርን ስለተውኩ ይቅርታ እላለሁ ስለሃጥያቴ ሁሉ ይቅርታ እጠይቀዋለሁ፡፡ ከዚያ ግን... ከዚያ ግን፣ ልጄን ተውልኝ... ልጄን
አትውሰድብኝ እለዋለሁ.....

እንደሚባለው ምሕረቱ የበዛ ሩህሩህ ከሆነ፣ ልጄን እንዲያድንልኝ እማጸነዋለሁ፡፡

እያለቀስኩ መሬቱን መሳም ጀመርኩ፡፡

እየጮኹ... እያጉረመረምኩ መጸለይ ጀመርኩ፡፡

“አምላኬ ሆይ.... ልጄን ተውልኝ... ልጁን አድንልኝ.... እጾማለሁ፡፡አስቀድሳለሁ፡፡ እጸልያለሁ፡፡ብቻ ልጄን ተውልኝ አድንልኝ.... ዐርብ እሮብ እጾማለሁ፡፡ ዐብይ ጾምን እጾማለሁ። ደሃ በስምህ አበላለሁ፡፡ አስቀድሳለሁ... አንተ ግን ልጄን ተውልኝ...አምላኬ እባክህ ልጄን አድንልኝ....
እግዚአብሄር ሆይ.... ልጄን ካዳንክ ባሪያህ እሆናለሁ፡፡እንደፈቃድክ እሆናለሁ፡፡ ያልከኝን አደርጋለሁ......”

አልኩና ቀና ብዬ በእንባማ ዐይኖቼ አሁንም ቆማ የምታየኝን ሴት ዐየኋት፡፡

ዛሬ ምንድነው?” አልኩ በጎርናና ድምፅ፡፡

“እ?” አለችኝ፣ ደንገጥ ብላ፡፡

ዛሬ...ቀኑ ምንድነው?”

"አስራ ዘጠኝ ገብሬል ነው"

እንደገና መሬት ላይ ተደፋሁ፡፡ ከንፈሮቼ በእንባዬ ታጥበው ጨው ጨው ይሉኛል፡፡

“ገብርኤልዬ... የኔ ገብርኤል... ልጄን አድንልኝና በዓመት ቁልቢ አልቀርም፡፡ በየወሩ ሱቄን ዘግቼ አከብርሃለሁ፡፡ እዘክርሃለሁ፡፡መልአኩ ገብርኤል ልጄን አድንልኝ...አድንልኝ...”ሴቲቱ ጎትታ አነሳችኝ፡፡ ቆምን፡፡

“ይበቃል... በቃ በቃ...” ከእምባዋ እንደምትታገል፣ በእንባ
በተሸፈኑትና እንደ እሳት በሚያቃጥሉኝ ዐይኖቼ ዐየሁ፡፡ ልክ እንደ ቅርብ ዘመዴ አቅፌያት አለቀስኩ፡፡

“በቃ... በቃ.... አይዞሽ...” አለችኝ፡፡
ብዙ ደቂቃዎች አለፉ፡፡

ነርሶቹ ምነው ጠፉ? ዶክተሩስ ለምን ዝም አለኝ? አዲስ ለቅሶ ጀመርኩ።
ሴቲቱ ታባብለኛለች፡፡
የስለት ቃሌን ለገብርኤል እደግማለሁ፣ መሬት እንበረከካለሁ፤
እቆማለሁ፤ ወደ በሩ እሄዳለሁ፤ ነርሶቹን ስለልጄ እጠይቃለሁ፤ጠብቂ እባላለሁ፤ አለቅሳለሁ፤ እቀመጣለሁ፤ እነሳለሁ፤ ተምበርክኬ ለገብርኤል እሳላለሁ፡፡ነፋስ ያስፈልገኛል፡፡ነፋስ.ነፋስ ያስፈልገኛል፡፡ ወጥቼም እንዳልወጣ ሐኪሞቹ መጥተው ቢያጡኝስ? እዚያ ኮሪደር ላይ
ተቀምጩ ትንፋሽ አጥሮኝ የልጄን
👍2