#ሸሌ_ነኝ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
"ነይ እዚህ ጋር ! ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ...ብርድ ልብሱ ላይ ተኚ" ሲለኝ፣ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር።
ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ግዜ መሽኮርመም። ሰው እንጂ ሴት ያልሆኑኩ መስሎኝ፣ ሥጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ።
አንገቴን እንደሰበርኩ ወደ አልጋው ሄድኩ ሲያገኘኝ እሄድ እንደነበረው አይደለም አካሄዴ።ሰበር ሰካ የለውም፣ ዕዩኝ ዕዩኝ የለውም፣ ተገዝቶ ወደ ሚታረድበት ቦታ እንደሚሄድ በግ ነው አካሄዴ።
ገዥዬ የማያውቀኝ፣ ሰው ፊት ልብሴን ሳወልቅ የመጀመርያዬ እንጀሆነ አያውቅም።
ገዥዬ፣ በገንዘብ ተገዝቼ ከወንድ ለመተኛት ስመጣ የመጀመርያዬ እንደሆነ አያውቅም።
ገዥዬ፣ ለዚህ ስራ ድንግል እንደሆንኩ አያውቅም።
ልብሴን ማውለቅ ሳልጀምር እየፈራው፣ "ይቅርታ....መብራቱን ታጠፋው?" አልኩት።
ዞር ብሎ ዐየኝና፣ "ሃሃ...ሃ! ታሾፌያለሽ እንዴ.? ለምንድን ነው የማጠፋው...? አለኝ። ይስቃል።
ፈራሁ ብለው አያምንም። በሰቀቀን ዝም ብዬ ማውለቅ ጀመርኩ። የአልጋው ጫፍ ላይ ኩምትር እንዳልኩ ድንገት እስካሁን መኖሩን ያላወኩት ብርድ አንዘፈዘፈኝ። ሳል ጀመረኝ።
ይሄን ግዜ ሰውየው ዞር ብሎ ዐየኝና ፤ "ምነው.. ብርድ.. ቲቢ.. ምናምን አለብሽ እንዴ?" አለኝ።
"አይ...በርዶኝ ነው...አያመኝም...አሁን በርዶኝ ነው..." ብዬ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባሁ።
"ኖኖ!...ከላይ ሁኚ...አትግቢ..." አለኝ ቶሎ ብሎ ፣ ቀጭን ትዛዝ ነበር።
እምቢ ብዬ መሄድ እንደማልችል ማወቁ አስከፋኝ። እሺ ብዬው ስለመጣሁ እምቢ ብዬ ስለማልሄድ እርግጠኛ መሆኑን ሳውቅ ከፋኝ። ከነሳሌ ከብርድ ልብስ ወጣሁ። መጥቶ አጠገቤ ተኛ። ሰውነቴ በፍርሃት ተንዘፈዘፈ። ነውስጥ ሱሪ ብቻ ሲቀረው ዕርቃኑን ነው።
እግዜር በሚያውቀው፣ ከማላውቀው ሰው ቤት ለማደር መምጣት አልፈለግኩም ነበር።
የማላውቀው ሰው እጁቹን ጭኖቼ መሀል አስገብቶ እንዲፈነጭ አልፈለግኩም ነበር።
የማላውቀው ሰው ጆሮዬን ተጠግቶ እንዲያቃትትብኝ አልፈለግኩም ነበር። ግን ሰውየው አስገድዶ አላመጣኝም። አልደፈረኝም።
ያስገደደኝ ኑሮ ነው።
የደፈረኝ ድህነት ነው።
ሲነጋና ከኔ ጋር ያለውን ጣጣውን ሲጨርስ፣ የሰጠኝን አምስት መቶ አዳዳስ ብሮች እንደያዝኩ በትእዛዝ ያወለኩትን ልብሴን በከፍተኛ ፍጥነት ለበስኩ። ያወለኩት ክብሬ ግን አልጋው ላይ ቀርቷል።
"ቅዳሜ እመጣለሁ....ማን ብዬ ላስጠራሽ ?" አለኝ በተኛበት።
እንድሄድ ፈልጓል። አገልግሎቴ አብቅቷል። አሁን እንደተፋቀ የሞባይል ካርድ ነኝ። አሁን እንደተጫረ የክብሪት ዕንጨት ነኝ። በድጋሚ በጉጉት የሚያየኝ በሚቀጥለው ቅዳሜ መጥቼ እፎይ ማለት ሲያምረው ነው። ስሜን ነግሬው ዞር አልኩና ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ለመሄድ ስዞር፣
"ማነሽ...እ...በሩን በደንብ ዝጊው!" አለኝ፣ አልጋው ላይ ተገላብጦ ጀርባውን እየሰጠኝ። ፊት እንኳን የማይገባኝ ሰው መሆኔን ሲነግረኝ ነው በጀርባው የሚያናግረኝ፣ የሚታወስ ሰም እንደሌለኝ ሲነግረኝ ነው ማነሽ ያለኝ።
ይሄን ሳስብ ተዛባሁ፣ ተዛነፍኩ።
ካለ አጥንት እንደተፈጠረ ሰው ሰውነቴ ለመቆምም ለመሄድም እምቢ እያለ ወደ ታክሲ ተራው ሄድኩ። ተኝቶ የነጋለት ሰው ይተራመሳል።
ታክሲው ውስጥ ገብቼ መስኮቱን ደገፍ አልኩና ያለ እቅድ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። ከዐይኔ ግድብ የሚፈሰው እንባ ጉንጬቼ ላይ የሚያደርቅ ሳይሆን አዋሽ ወንዝ ለመግባት ያልም ይመስል ይንዠቀዠቃል።
ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው የአንገት ልብሴ ላይ ያርፋል።
ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ጃኬቴ ላይ ያርፋል።
ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ሱሬዬ ላይ ያርፋል።
በለቅሶዬ መሃል፣ "አይዞሽ... ሁሉም ያልፋል" የሚል ድምፅ ሰማሁና ዞርኩ። ከእኔ በእድሜ የምታንስ ልጅ ናት።
"ሁሉም ያልፋል" የሚል የታክሲ ጥቅስ አንብባ የምትደለለው ለዚያ ነው። ትንሽ ልጅ ስለሆነች፣ በቂ ስላልኖረች። አንዳንድ ነገሮች እንደኔ ላለው ሰው እንደማያልፍ የሚያስተምራት የህይወት ልምድ ስለሌላት፣ ቀልደኛ!
ዝም ብዬ አየሇትና በእሽታ ጭንቅላቴን ነቅንቄ ተመልሼ ወደ መስኮቱ ዞርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ዛሬ እዚህ ታክሲ ውስጥ እያለቀስኩ ባልተቀመጥኩ፣ ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ለአምስት መቶ ብር አምስት መቶ ቦታ ባልተሰባበርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ እኔ ትርሲት የአቶ ከለላውና የወይዘሮ ሥምረት ሴት ልጅ፣ የብሌን ታላቅ እህት፣ የዳዊት ታናሽ እህት፣ የዳግም ፍቅረኛ ሀኜ በቀረሁ። አሁን ግን ትርሲት ሸለዋ ነኝ።
ሸሌ ነኝ፣ ሸሌ ብቻ።
ይህንን ሰውየው ዐይን ውስጥ ዐይቼዋለሁ። ይሄንን ሰውየው ትእዛዝ ውስጥ ሰምቼዋለሁ። ይህንን ሰውየው፣ "በሩን በደንብ ዝጊው" ንግግር ውስጥ አድምጭዋለሁ።
ሸሌ ነኝ።
ለማንበብ ደቂቃ የሚፈጅ ሥም በመስጠት የ'ኔን ሥራ ቅዱስ ማድረግ አይቻልምና፣ የለም፣ አንቺ እኮ 'በወሲብ ንግድ የተሰማራች ሴት' ነሽ!" ብላችሁ አታፅናኑኝ።
ከዛሬ ጀምሮ ሸሌ ነኝ።
በረሀብ እያዛጋሁ ቤቴ ገባሁና ከሰል አቀጣጠልኩ። ሳልበላ ውሃ ላፈላ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ልታጠብ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ገላዬን ልታጠብ። ሸሌነቴን በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርጌ ልታጠብ።
ውሃው እስኪፈላ፣ ልብሶቼን አውልቄ ከሌሎቹ ልብሶቼ ጋር እንዳይቀላቀሉ በቤቴ አንዷ መአዘን ላይ ሰብስቤ ጣልኳቸው። ብዙ ልብስ የለኝም፤ ግን እነዚህን ልብሶች መልሼ የምለብሳቸው አይመስለኝም።
'ራቁቴን የሰመጠች አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ውሃው እስኪፈላ እየጠበቅኩ ቤቴን ዐየሁት። ለሰው የሚነገር ነገር ስለሌለኝ እንትኑ እዚያ ጋር፣ እትኑ ደግሞ እዛ ጋር አለ ብዬ ላወራችሁ አልፈልግም። በዋጋ ከተሰላ፤ አሁን ያለኝ፣ ዋጋ የከፈልኩበት አምስት መቶ ብር ብቻ ነው። አልጋዬ ላይ የተቀመጠው አምስት መቶ ብር።
ምንአልባት ካልገመታችሁ፣ እንዲህ ያለው ዋጋ ያልከፈልኩበት ብር ለማግኘት ሞክሬ ነበር። ማለቴ ዘልዬ ሸሌ አልሆንኩም። አሳጥሬ ልንገራችሁ። ሁሉንም ሥራ ሰርቻለው። ግን እኔንና እኔን የሚጠብቁ ቤተሰቦቼን ሆድ ፀጥ የሚያደርግ፣ አንገት ቀና የሚያደርግ፣ ደረት አስነፍቶ የሚያስኬድ ሥራ አላገኘሁም።
እውነቴን ነው የምላችሁ፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።
ልድገመው፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።
የሥጋ ለሥጋን ኑሮ የመረጥኩት ሌላ ነገር ሆኜ መኖር ስላልቻልኩ ነው። ለምሳሌ የሆነ ሰሞን የሆነ "ኤን ጂ ኦ" ሸሌ የመሆን አዝማሚያ ያሳየነውንም፣ ገብተው የተንቧቹበትንም ሴቶች ሰበሰበና፣ "ከዚህ አስነዋሪና ቆሻሻ ሥራ ነፃ እናውጣችሁ፣....ያልገባችሁትንም እናድናችሁ" አለን።
"አልጋ አንጣፊ ስለሆነች ከአልጋ ለመውደቅ ቅርብ ነች" ብለው ነው መሰለኝ፣ ፕሮጀክቱ ውስጥ አስገቡኝ። ደስ ብሎኝ ገባሁ። ኤን ጂ ኦው፣ "አማራጭ የገቢ ማግኛ ዘዴዎች" በሚል ለግማሻችን ጥልፍ፣ ለግማሻችን ዳንቴል ስራ አስተምሮ፤ "በሉ እንግዲህ ሂዱና ንፁህ ስራችሁን እየሰራችሁ በብልፅግና ኑሮ" ብሎ አንድ ኮንቴነር ቤት ተከራይቶልን ሄደ።
እኔ ከጥልፎቹ መሀል ነበርኩ። እንደተማርኩት እየጠለፍኩ አዲሱንና ንፁሑን ሥራዬን ነጻ መውጫዬ፣ መልካም እጣ ፈንታዬ፣ የእግዜር ካሳዬ አድርጌ ተቀብዬው ሥራ ጀምሬ ነበር።
ብዙዎቻችሁ፣ " እንዴ ሸሌ የሆነች ወይ ለመሆን ያኮበኮበች ሴት ሁሌም ሸሌ ናት" ብላችሁ እንደምታስቡ አውቃለሁ። "በሚኒ ስከርት መንገድ መቆም የለመደች ሴት፣ በ'እስከ ጉልበት' የሥራ ቀሚስ ቢሮ መቀመጥ አትችልም ብላችሁ እንደምታምኑ ከውቃለሁ።
የራሳችሁ ጉዳይ

👍3❤1

👍94❤10😁1