#ገዳዬ_ገዳዬ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
ፀሐያቸው ጠልቃ በሰው ሀገር መሽቶብኝ ነበር፡፡ ጨልሟል የተለመደውን አውቶብሴን ተሳፈርኩበ።
አዲስ ነገር የለውም፡ ሁሌም የምጠብቀው ያ ሁሌም በጠበቅኩት
ሰዐት የሚመጣው የማይዛነፍ የዕለት ውሎዬን የሚደመድመው አውቶብስ ነው።
እንደተቀመጥኩ፣ ሰንደቅ የሚያሰቅል ቁመት ያለው! ውብም፤ሎጋም ኢትዮጵያዊ ወንበር ሲፈልግ አየሁት።
አውቶብሱ ውስጥ ብዙ ክፍት ወንበሮች ነበሩ፡፡ ወደ መስኮቴ ዞርኩ
እና ጸሎት ብጤ አደረግኩ፡፡ ብታውቁኝ ለዚህ ዓይነት ነገር ጸሎትን ያህል ነገር የማባክን ሰው አይደለሁም ግን... ጸለይኩ፡፡
ጸሎቴ ተሰማ መሰለኝ እጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ፡፡
ከዚያ ምን ሆነ?
“ሃ...ይ..." አለኝ፡፡ ዝም ብሎ ሃይ አልነበረም፡፡ ይሄ..አንድ ሃ' እና ስድስት 'ይ ያለው ሃይን ታውቁታላችሁ? እሱ ነው! እንደሱ ነው ሃይ ያለኝ፡፡
ዞር ብዬ ሌላ ትንሽ ጸሎት አደረስኩ፡፡
ፈጣሪ በትንሽ ፀሎት ይሄን መለሎ አጠገቤ አምጥቶ ስላስቀመጠልኝ፣ አስቀምጦም እንዲህ ያለውን ሃይ እንዲለኝ ምላስ እና ከንፈሩን ስላቀናጀልኝ ሌላ ፀሎት አደረስኩ።
አስቡት..የመጀመርያው ጸሎቴ ሳይሰማ ኖሮ ይሄ አማላይ ይሄ ሳያነጣጥር ገዳይ አጠገቤ ይቀመጥ ተቀምጦስ ሰላም ይለኝ ነበር....?
እንዳልኳችሁ አውቶብስ ተሳፍሬ ዐይነ ግቡ ሰው በተሳፈረ ቁጥር፣
ወንበር በፈለገ ቁጥር እንዲህ አይነት ጸሎት የምጸልይ አይነት ሴት
አይደለሁም፡፡
የፈለግኩትን ሰው ለማግኘት ቃላትን የማሰናዳ፣
የከንፈር ቀለሜን የማደምቅ፣
ዐይኖቼን የማስለመልም፣
ጡቶቼን ከካኔተራዬ ገፍትሬ የማወጣ፣
መቀመጫዬን ያለ አቅሙ የማንቀጠቅጥ ሴትም አይደለሁም፡፡
ሴት ነኝ፡፡
ልቤን በልቡ ይቀይረኛል በሚል ተስፋ ወንድኝን በጭኖቼ ክፍተት የማስገባ አለመማረክ የሰለቸኝ ለድርያ እንጂ ለትዳር አለመፈለግ ያቆሰለኝ የትርጉም አልባ አጫጭር ግኑኝነቶች ርዝመት ያታከተኝ ሴት ነኝ
ምክንያቱም ጭርሱን መራመድ ተሳነኝ፡፡
ልድገመው፡፡ የትርጉም አልባ አጫጭር ግንኙነቶች ርዘመት ያታከተኝ ሴት ነኝ።
አልፎ ሂያጆቹን ትቼ ስለዚህ ልጅ ብቻ የማወራችሁ ለዚህ ነው፡፡
ለምን እንደሆነ ባላውቅም በልኬ ተሰፍቶ እዚህ አውቶብስ ውስጥ የተጣለ መሰለኝ፡፡ ያልዳነ ቁስሌን የሚያክመኝ ሰው እሱ መሰለኝ፡፡
..የበደሌ ካሳ በሚያምር ልጅ መልክ ተሠርቶ የተበረከተልኝም መሰለኝ፡፡
መሰለኝ እንግዲህ...
አውቶብስ ላይ ከተዋወቅን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲደውልልኝ
ያንኑ ባለ አንድ ሃ' እና ባለ ስድስት 'ይ' “ሃይ' አለኝ፡፡
በተቀመጥኩበት አቁነጠነጠኝ፡፡ እንደ ሆነ ነገር ሠራኝ፡፡ ፈተነኝ...ይሄ ልጅ ክፉኛ ፈተነኝ፡፡
በሚቀጥለው ቀን አንዱ ፓርክ ተቀጣጥረን ቁጭ ብሎ እየጠበቀኝ
ነበር፡፡
ጀርባውን ሳየው የሆነ ነገሬ እንደ ጧፍ ይቀልጥ ጀመር፡፡
የቀለጠው...
ይመስለኛል እግሮቼን እንዲሄዱ የሚያደርገው ጡንቻዬ ነው።
ይመስለኛል አጥንቴ ነው ይመስለኛል ሁለተናዬ ነው።
ምክንያቱም ጭርሱን መራመድ ተሳነኝ።
ቀልጬ ከማለቄ በፊት ድንቅፍቅፍ እርምጃዬን ሰምቶ መሰለኝ ወደኔ መጣ።
ፀሐይ ከሰማይ ወርዳ፣ እግር አውጥታ ወደኔ ትመጣ ይመስል የመቅለጥ ፍርሀቴ ይበልጥ ጨመረ፡፡
“የትኛው አካሌ ቀድሞ አመድ ይሆን፣ ይሆን?” እያልኩ ቆሜ ቀረሁ።
አጠገቤ ሲደርስ አውቶብሱ ላይ ያላየሁትን አዲስ ፈገግታ ፊቱ ላይ ተመለከትኩ።
ሚዛኔ ተመለሰ። እግሮቼ በረቱ።
እንጃ ብቻ...ፈገግ ያሉ ዐይኖቹ ውስጥ የለመድኩት ነገር ሁሉ ታየኝ።
ፊቱ ላይ አራት ኪሎ ታየኝ የድል ሃውልት።በተርታ ያሉት ጭማቂ ቤቶች ከጀርባ ያሉት ሻይ ቤቶች ቁልጭ ብለው ታዩኝ።
ፊቱ ላይ ኢትዮጵያ ታየችኝ፡፡
ፈገግታው በሰከንዶች ውስጥ አከመኝ። ሚዛኔ ሲመለስ ተሰማኝ እግሮቼ እንሂድ አሉኝ፡፡ እጄን ያዘኝ እና መራመድ ጀመርን፡፡
እየሄድን....እጄን ስለያዘኝ ብቻ ማንም የማይነካኝ ክፉ የማያገኘኝ መሰለኝ።
ሁሉ ሰው ስሜን የሚያውቀው፣ሁሉ የሚወደኝ ስፍራ
ሃገሬ.... ኢትዮጵያ የሄድኩ መሰለኝ፡፡
አለ አይደል... በአያያዙ ውስጥ የሀገሬን መንገድ ያገኘሁ ያህል ተሰማኝ።
በዙሪያችን ያሉ ሰዎች “ምን እንደሆንኩ ዐውቀው ይሆን?” ብዬ ዞር ዞር ብዬ አየኋቸው።
"ገዳይ ሰውነት ካለው መለሎ ጋር ሆኜ ላለመሞት እየታገልኩ እንደሆነ አስተውለው ይሆን?" ብዬ ዙርያየን ቃኘው።
ቀጥሎ ምን ሆነ?
እልፍ አእላፍ ማታዎች ስንፃፃፍና በስልክ ስናወራ ከረምን።
ተጻጻፍን፡፡ ፎቶ ተላላክን፡፡ አወራን፡፡
ተጻጻፍን፡፡ ፎቶ ተላላክን፡፡ አወራን፡፡
ተጻጻፍን። ፎቶ ተላላክን፡፡ አወራን፡፡
ከዚያ እንደገና ተገናኘን፡፡
እመኑኝ፡፡ በሰው ሃገር ሆናችሁ የወንዛችሁን ልጅ- ያውም እንዲህ
ያለውን ስታገኙ ፈገግታው ሀገራችሁ ነው፡፡
ለዚያ ይሆናል ከፈገግታው መላቀቅ ያቃተኝ፡፡
ለዚያ ይሆናል ዐይኑን ዐይቼ መጥገብ የተሳነኝ፡፡
ዐይኑ ውስጥ ወደ ሃገሬ የሚወስደኝ መንገድ አለ፡፡
ምን ብዬ ላስረዳችሁ እንጂ ...አባቴ ይሙት... እጄን እያያዙ ውስጥ ማንነቴ ሁሉ አለ።
በተገናኘን ምሽት ያን ጃንሜዳን የሚያስንቅ ደረቱን ወለል አድርጎ
የሚያሳይ ጠበቅም -ሳሳም ያለ ሹራብ ለብሶ ነበር።
ወይ ደረቱ! አቤት ደረቱ! ስለ ደረቱ ዐሥር ግጥም በዐሥር ደቂቃ ልፅፍ እችላለሁ። ግን የወሬው አላማ እሱ አይደለም።
እጅ ተያይዘን አብረን ስንራመድ፣ ስንሥቅ፣ ፈገግ ስንል፣ ደረቱ ላይ
ስጋደም፣ ደረቱ ላይ ሲያጋድመኝ፣ በአማርኛ ስናወራ መሸና የሀበሻ
ቤት ሄደን የሀበሻ ቡና በሀበሻ ወግ ጠጣን፡፡
“ቡና እወዳለሁ፡፡” አለኝ፡፡
እኔ ለቡና እስከዚህም ነኝ፣ ግን እሺ ብዬ ጠጣሁ፡፡ ቶና አይደለሃ በረካ አይደለም፡፡
ያን ምሽት ከአቦል ልጅ ጋር ነኝና አምስት ስኒ አቦል ቡና ጠጣሁ።
ስኳር በጨመርኩ ቁጥር፣ “ስኳር ቡናውን ይገድለዋል... ቡና ያለስኳር ነው መጠጣት ያለበት...ሞክሪው፡፡” ሲለኝ፣ ስኳሩን በእሱ ተክቼ ስንት ስኒ ቡና ያለ ስኳር ጠጣሁ?
ስንቱን ስኒ ቡና ባዶውን ሳይመረኝ አንቃረርኩ?
ተለይቼው፣ ቤቴ ገብቼ ከዚህ ቀደም ስለማላዘወትረው ቡና - በተለይ ስለ አቦል ቡና ጀመርኩ። በባዶ ቡና ፍቅር ተንገበገብኩ።
በሚቀጥለው እስካገኘው፣ ያለ ልማዴ በየቀኑ ስለ እሱ እያሰበኩ ስኳር የሌለው ወፍራም ቡና ማፍላት መጠጣት ጀመርኩ
ከዚያስ?
ከነዚያ ምሽቶች በኋላ በድንገት ስልኬን መመለስ፣ ለመልእክቶቼ
መልስ መስጠት አቆመ፡፡ የት ገባ? አላውቅም፡፡ ብቻ…. ብቻ ጠፋብኝ።
እደውላለሁ- አያነሳም፡፡
እጽፋለሁ አይመለስም፡፡
ዐሥራ ሦስት ቀናት አለፉ፡፡
ዐሥራ ሦስት እሱን-አልባ ቀናት ኖርኩ፡፡
ዐሥራ አራተኛው ቀን...
ያ ልጅ... ፈገግታውን፣ እጅ አያያዙን፣ ሳንቃ ደረቱን ይዞብኝ ሲጠፋ...
ያ ልጅ... የሀገሬን መንገድ፣ ኢትዮጵያዬን ይዞብኝ ሲሰወር...
..በላይ በላዩ ባዶውን እጠጣው የነበረው አቦል ቡና በመዐት ማንኪያ ስኳር እንኳን ይመረኝ ጀመር፡፡ ቀረ.. ቀረ.. ቀረ..
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍1