#ሕልሜ_እልም...
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
ትላንት በሕልሜ እንዲህ ዐየሁ...
ሕዝባችን...
ሰንሰለቱን በጥሶ፣ የእግር ብረቱን አውልቆ ጥሎ፣ ከእስራቱ ሲፈታ ዐየሁ፡፡
የዘረኝነት ቅጥር ግቢ ፈርሶ፣ የጠባብነት በሮች በእሳት ጋይተው....
ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ፤ ተሰብስበው፤ ከፍ ያለው የክብር ቦታ ተሰጥቷቸው ከንጉስ ማዕድ ሲመገቡ ዐየሁ፡፡
ደግሞም...
በሕዝቡ ላይ መዐት ሲወርድ እያየ የማይታገስ፣
ስለደኅንነታችን የሚቆረቆር፣
ስለኑሯችን ጭንቅ-ጥብብ የሚል፣
የሀገሩን መጥፋት መቋቋም የማይችል፤ ንጉሥ ሲኖረን ዐየሁ፡፡
የተሸረበውን ክፉ ሤራ የሚሽር፣
የተበጠበጠውን በታኝ መድሃኒት የሚያረክስ መሪ ኖሮን ተመለከትኩ፡፡
ሸረኞቹስ?
ሽረኞችማ....
ሽረኞችማ... በማሱት ጉድጓድ ራሳቸው ዘው ሲሉበት፤ ባስቀመጡት
ወጥመድ መልሰው ሲያዙበት፤ በወጠኑት ተንኮል ሲጠመዱ ዐየሁ፡፡
“ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም” ያሉ፤ በሠራዊታቸው የታበዩ ፤
አንገታቸውን ሲደፉ ፈፅሞ ሲያፍሩ ተመለከትኩ።
ከተሞቻቸው ተገለባብጠው ፤ ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ ተደቁሰው;
እንደ ሽክላ እቃ ደቅቀው ፤ መታሰቢያቸው ሁሉ ተደምስሶ ዐየሁ፡፡
ተግሣጽን የጠሉ፣ መታረምን የናቁ.....
እነዚያ... ባለ ክፉ ልቦች፣
እነዚያ ባለ ሐሰተኛ ምላሶች፣
እነዚያ ባለ ትዕቢተኛ ዐይኖች፣
አሉ አይደል...? እነዚያ ...ባለ ለክፋት የሚሮጡ እግሮች?
እነሱ ሁሉ፣ አንዳቸውም ሳይቀሩ
የመንገዳቸውን ፍሬ ሲበሉ የዕቅዳቸውን ውጤት ሲጠግቡ ተመለከትኩ።
ደግሞ እንደገና...
የመከራ ዘመናችን በአሽዋ ላይ ተጽፎ፣
የመፋቀር ዘመናችን ግን በአለት ላይ ተቀርጾ ዐየሁ፡፡
በእጅጋየሁ ሽባባው ምኞት፣
“የሸዋ አባት ልጁን ለትግሬ እየስጠ...
የሐረር ነጋዴ ወለጋ እየሸጠ” ተመለከትኩ
ብርሃኑ እየጎላ የሚሄድ የማለዳ ውጋጋን በሀገሬ ላይ ዐየሁ፡፡
ፀሐይ በምሥራቅ ብቻ ሳይሆን በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምዕራብ ስትወጣ፣
የኢትዮጵያ ሕፃናት ከዳር እስከዳር በስኳር ኮረብታዎች ላይ እየተንሸራተቱ ሲቦርቁ
ጎተራዎች ተትረፍርፈው ገበሬዎች በቲማቲም-ለጨዋታ ሲፈነካከቱ
ዐየሁ፡፡
የመንቀል ጊዜ በመትከል፣
የመሞት ጊዜ በመፈወስ፣
የመበጥበጥ ጊዜ በመስከን፣
የመቅደድ ጊዜ በመስፋት ጊዜ ሲተካ ተመለከትኩ፡፡
የተቀዳደድነው ሁሉ በአረንጓዴ💚፣ ቢጫ💛 ፣ ቀይ❤️ ክር መልሰን ስንሰፋ ዐየሁ፡፡
ከሁሉ በላይ ግን...
የባህር አሸዋን፣ የዝናብ ጠብታን፣ የዘለዓለምነት ቀኖችን ያህል
ፍቅር ዳር እስከዳር ስንካፈል የባሕርን ጥልቀት፣ የሰማይን ምጥቀት የምድርን ስፋት ያህል መውደድን ስንጋራ አየሁ።
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ውዶቼ። 🙏

👍2