አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ገንዘብ_መሆን_የተሳነው_ዕውቀት


#በሕይወት_እምሻው

ከታናሽ ወንድሜ ጋር በዲግሪ ፕሮግራም ተምሮ የተመረቀውን ዳንኤል፣ የኮብልስቶን ሥራን ሲያስተባብር አገኘሁት፡፡

ሻይ ይዘን፤ ስለ የተማሩ ኮብልስቶን ጠራቢና ደርዳሪዎች፤ ተብሎ...
ተብሎ... የተተወውን ክርክር እንደ አዲስ ቀሰቀስነው፡፡

ዳንኤል ፣ “ሥራ አጥተን ቤት ቁጭ ከምንል ገንዘብ እስካገኘን
ብንሠራ ምናለ?” ብሎ ነገሩን ሥራ ከመናቅና ካለመናቅ ጋር አጣብቆት ብዙ ሞገተኝ፡፡

“ሥራ ገንዘብ ማግኛ ነው ፤ ይሄ ደግሞ ገንዘብ ይከፍላል፤ ኀጢአቱ ምንድነው?” ብሎ ተከራከረኝ፡፡

ዳንኤል ልክ ነው፡፡ ድህነት መለዮ ልብሳችን በሆነበት ሀገር ገንዘብ
የሚያስገኝ ነገር ሁሉ እንደ ስኬት እንደሚቆጠር ግልጽ ነው፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ እህል ይሆናል፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ ቤት ኪራይ ይከፍላል፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ የታክሲ ይሆናል፡፡

ያን ያህል ቀላል ነው፤ ይገባኛል፡፡ የእኔ ችግር ከአጠቃላይ ክስረቱ ጋር ነው፡፡ የእኔ ችግር እነዚህ ልጆች ለዓመታት "ሲማሩና ሲመራመሩ" ከርመው፤ ያልተማረና ያልተመራመረ ሰው
በሚችለው ሥራ ላይ መሰማራታቸው... የእነዚያን ሰዎች የሥራ ዕድል ከማጣበባቸው ነው፡፡ ለእኔ ይሄ ክስረት ነው።

ሰለዚህ የመንግሥት ሚዲያዎቻችን፣ እነዚህ ልጆች የምርቃት ሱፋቸውን አውልቀው በሥራ ቱታ ድንጋይ ሲፈልጡ መዋላቸውን እንደ ታላቅ ስኬት ሲያቀርቡት አይገባኝም።

“በሥራ ክቡር ነው!” መልካም አባባል፤ ልሽቀታችንን ሲደብቁት ደስ አይለኝም፡፡ ችግሬ ከልጆቹ መሥራት አይደለም፡፡ ከነገሩ አቀራረብና አረዳድ ነው፡፡

ሥራቸው ልጆቹን ሊያሳፍር ባይገባም፤ እንደ ሀገር ግን ሊያኮራን የሚገባ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ልጆቹ ዲግሪ ለማግኘት ብዙ ከፍለዋል፡፡ ሀገሪቷም ካላት ትንሽ ሀብት ብዙ ከፍላለች፡፡

...እና በረጅሙ ስናስበው፣ ዛሬን በልተው ቢያድሩም የትምህርት ሥርዓታችን ክስረት ባንዲራዎች ናቸው፡፡

ዛሬ ትምህርት ላይ ላሉ፣ ማበረታቻ ሳይሆኑ ማስጠንቀቂያ ናቸው፡፡

ያልተማረ ሰው ሊሠራ የሚችለውን ሥራ ተምረው ስለሚሠሩ፣በልተው ቢያድሩም ለሀገር ውድቀቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን፣ ይህ የእነሱ ጥፋት አይደለም፡፡ መብላት አለባቸው፡፡ መኖር አለባቸው፡፡

ስለዚህ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ዕውቀት ልንሰጣቸው ስላልቻልን ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ጉልበታቸውን ተጠቀሙ:: በዚህ ደግሞ ልናፍር እንጂ ልንኩራራ የሚገባ አይመስለኝም፡፡

💫አለቀ💫

ምን ትላላችሁ የቻናሌ ተከታታዎች ይሄ ጉዳይ የሚመለከታችሁም ልትኖሩ ትችላላችሁ እስቲ ሃሳባቹህን አድርሱን

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏