አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳይወለድ_ሞተ


#በሕይወት_እምሻው

ከሌሊቱ ሰባት ሰዐት ገደማ፡፡
ተኝቼ ነበር፡፡ ሕመም አልነበረኝም፡፡ ያው ከተለመደው ማቅለሽለሽ
ያስጠነቀቀኝ ፤ ለዚህ ልብ ስብራት ያዘጋጀኝ ሕመም.አልነበረኝም፡፡

ብቻ ስደማ ተሰማኝ፡፡.... ቀስም፣ ቶሎ ቶሎም የሌሊት ልብሴ ላይ፣
አንሶላው ላይ ስደማ ተሰማኝ፡፡

ተደናብሬ የራስጌ መብራቱን አበራሁት፡፡

ልብሴም፣ አንሶላውም ደም በደም ሆኗል፡፡

“ሶልዬ...ሶልዬ ተነሳ!” ብዬ ጮህኩ አጠገቤ የተኛው ባሌ አልሰማኝም፡፡

“ሶል... ሶል..... በማርያም ተነሳ!” የፈሰሰ ደሜን እያየሁ መነሳት
ፈርቼ ደግሜ በጩኸት ጠራሁት፡፡

“ምነው...? ምን ሆንሽ...?” አለኝ ተፈናጥሮ እየተነሳ፡፡

“...እየደማሁ ነው...ምን ሆኜ ነው...? ደም በደም ሆኛለሁ...
ሶልዬ... ወይኔ ጉዴ ሶልዬ... ወይኔ ጉዴ እየደማሁ ነው...”
።።።።
ከሰአታት በኋላ...."ተጠርጎ ወቷል።አሁን ለጤናሽ የማያሳስብ ነገር የለውም አለኝ ሐኪም ቤት ውስጥ ወዲህ ወድያ ሲያደርጉኝ

ማሬ... እንደዚህ አትሁኚ... ያው... ማድረግ ነበረባቸው ማለት
ላንቺ ጤና... ወደ ፊት ሌላ ልጅ.... ሌላ ልጅ እንድንወልድ...”

እጄን የያዘው እጁ ይንቀጠቀጣል፡፡ ወደ ዐይኖቹ መሄድ የሚፈልገውን እንባ በአፉ አስገድዶ እየዋጠ፤ በአፍንጫው ሰንጎ
እያስቀረ ሊያጽናናኝ ይሞክራል፡፡

“ልጄን እንደ ቆሻሻ ጠረጉት... ሶልዬ ልጄ እኮ ነው.. ስም አለው
እኮ... ስም አውጥቼ ነበር እኮ... ልጄ እኮ ነው!”
“አንቺ ልጅ... በቃ ዝም በይ! መዐት አትጥሪ... ዋናው ያንቺ
መትረፍ ነው” አለች እናቴ በሩን ከፍታ እየገባች፡፡

ተርፌያለሁ እንዴ...?

“አንተም ከሷ አትሻልም..... ሂድ አሁን ክፈሉ ምናምን እያሉ
ነው ... ዛሬውኑ ትወጣለች ብሎኛል ዶክተሩ፡፡”

የለመደችውን የሴቶች የማርያም ማኅበር ድግስ የምታሰናዳ ነው
የምትመስለው። ምስር የምትለቅም፣ ጎመን የምትከትፍ፣ ሽንኩርት
የምትልጥ፤ እንደተለመደው ሥራ እየሠራች ነው፡፡ መሆን ያለበትን
እያደረገች ነው፡፡

እናቴ የስሜት ሳይሆን የሚና ሰው ናት፡፡ ጎረቤት ሲሞት ከማልቀስ
በፊት ገናዥ የምትጠራ፣ ሰው አዳልጦት ሲወድቅ፣ “እኔን!” ሳትል
የምታነሳ፤ ሕፃን ሲያለቅስ፣ “እሹሩሩ” ሳትል ዝም የምታሰኝ ዓይነት
ሰው ናት፡፡

ስሜት ሩቋ ነው ለርሷ፡፡ የርሷ ሥራ ነገሮችን ቦታ ቦታ ማስያዝ
ነው፡፡ እናቴ ነገር በማስተካከል ተሰተካካይ የላትም፡፡ ስሜት ግን
እንደ ሰማይ ሩቋ ነው፡፡

ይሄን እያወቅኩ፣ “እማ...” አልኳት፡፡ የለበስኩትን ብርድ ልብስ
ታሰናዳለች፡፡

"እመት...”

“አሁን... ሐዘን አልቀመጥም... አንቀመጥም?” ለምን እንደዚህ
እንዳልኳት አላውቅም፡፡ ምናልባት ሳያብብ ለረገፈው ልጄ ተገቢ
ለቅሶ እንድታሰናዳልኝ ፈልጌ ይሆናል፡፡ ፍራሽ፣ ዳስ፣ ቀብር ቢጤ፡፡

ሀዘኔ ላይ የ“መስክረናል፤ ሆኗል” ማህተም እንድታረግልኝ ፈልጌ
ይሆናል፡፡

“አንቺ ልጅ ያምሻል አይደል...? ለማን ነው ሀዘን የምንቀመጠው...?” ትራሴን እያስተካከለች፣ ስሜት ዝር ባላለበት
ዐይኖቿ እያየችኝ መለሰች፡፡

“ልጄ እኮ ነው እማ.... ልጄ እኮ ነው የሞተው!”

“ወረደ ነው የሚባለው... ሞተ አይባልም... ልጅ ካልተወለደ ሞተ
አይባልም” ዝንጅብል እየላጠች የምታወራኝ ነው የምትመስለው፡፡
ከምንድነው የተሠራችው?

ወረደ...?” አልኳት።

"አዎ...ይሄ እኮ ብዙ ሴት ያጋጥመዋል... እግዜር ያላለው አይሆንም... ሌላ ትወልጃለሽ ቶሎ..... አይዞሽ" አይዞሽ ስትል እንኳን አይዞሽ ያለች አትመስልም።

“ወረደ ነው የሚባለው ... ሞተ አይባልም፡፡” ማለት ምን ማለት
ነው? ሰው አልሆነም ማለት ነው...? የሰው ክብር የለውም ማለት
ነው...? ልጄ ልጅ አልነበረም ማለት ነው ...? ስላልተወለደ ዕውቅና
የለውም ማለት ነው....? ሐዘን አይደለም...? የልጄ መሞት አሳዛኝ
አይደለም...? የልጄ ሞቱ ጉዳት የለውም...? ከልብ ብቻ የተሠራሁ
ይመሰል ልቤ ሲመታ ብቻ ይሰማኛል፡፡

“እኔ የምልሽ..." አለችኝ ትንሽ ቆይታ፡፡

“እ...” ዐይኔን መክፈት የካ ተራራን ከመውጣት እየከበደኝ ነው፡፡

“ለሰው አውርተሻል እንዴ...?”

ምኑን?

ነፍሰጡር እንደነበርሽ...”

ለሰው አውርቻለሁ እንዴ? ለሰው አላወራሁም ግን ሰዎች አውቀዋል። ያቅለሸልሸኝ ነበር ፊቴ መለወጥ ጀምሮ ነበር። ደስ ብሎኝ ስለነበር ለልብ ወዳጆቼ ነግሬ ነበር። ሰዎች አውቀዋል።

“ዐየሽ...! እኔን አትሰሚም... ሦሰት ወር ሳያልፍ አይወራም... አፍ ጥሩ አይደለም ስልሽ ብትሰሚ ኖሮ..”

ማልቀስ ጀመርኩ፡፡

እውነት ልጄን በአፌ ነው የገደልኩት?

ለሰው በማውራቴ ነው አቅፌ በመሳም ፈንታ ደም አድርጌ ጨርቅ
ላይ ያፈሰስኩት..?

እኔ ነኝ ያጠፋሁት? እኔ ነኝ የገደልኩት?
ለቅሶዬ በበረታበት ባሌ ሲመለስ ከእናቴ ጋር ተጣሉ፡፡ በለቅሶ ደክሜ
ዐይኖቼን ጨፍኜ ነበር ግን ዘጋው የክፍሌ በር ባሻገር ኮሪደሩ ላይ፣

“እንዴት እንዲህ ይሏታል?”

“አንተ ታቀብጣታለህ.... ወንድ ሁን እንጂ” ሲባባሉ ይሰማኛል፡፡
ደከመኝ፡፡ እጅግ ደከመኝ፡፡ ብዙም ሳልቆይ እርጉዝ ሆኜ ገብቼ ባዶ ሆኜ ወጣሁ፡፡ ሁለት ሆኜ ገብቼ ፤ አንድ ሆኜ ወጣሁ፡፡ከአራት ቀን በኋላ ቤቴ ሶፋዬ ላይ ቁጭ ብዬ፣ “አሁን የእኔ ስም
ማነው?” ብዬ ማስብ ጀመርኩ፡፡ ለሁሉም ዓይነት ሰው ስም አለን፡፡

እናቱ እና አባቱ የሞቱበት ልጅ ፣ “የሙት ልጅ” ይባላል፡፡

ባሏን ፈትታ ብቻዋን ያለች ሴት ጋለሞታ ትባላለች፡፡

ወልዳ የሞተባት ሴት፣ “ልጇ የሞተባት እናት” ትባላለች፡፡

እኔ ምንድነው የምባለው?

የኔ ስም ማነው?

የኔ ሐዘን ስሙ ምንድነው? ሰው ስለኔ ሲያወራ ምን ሆነች ብሎ ነው?

ከዚያ ደግሞ ስለልጄ አስባለሁ፡፡ አገሩን ሁሉ ያዳረሰ ስም ለእኔ ልጅ
ስለማይሆን፣ ልጄን ስለማይመጥን ፤ ብዙ ጥናት ሠርቼ፣ ወጥቼ
እና ወርጄ ስም አውጥቼለት ነበር፡፡ ቄሶች አማክሬ፣ አቧራ የለበሱ
መጽሐፍት ከፍቼ፣ ከጥንት ኢትዮጵያውያን ንጉሠ ነገሥታት የስም
ዝርዘር የምመኝለትን አስቤ ስም አውጥቼለት ነበር፡፡ ትንሽ አድጎ
በየጸጉር ቤቱ፣ በየኬክ ቤቱ ስንሄድ ቁንጅናውን ዐይተው፣ በአበባነቱ
ተስበው እንደንብ የሚከቡት ሰዎች በሙሉ ከሳሙት በኋላ ስሙን
ሲጠይቁት እና ሲነግራቸው ሲደነቁ ይታየኝ ነበር፡፡

“እንዴት የተለየ ስም ነው? በስማም!” ሲሉና፣ እኔም እሱም ስንኮራ ይታየኝ ነበር፡፡

አሁን ስሙን ምን አደርገዋለሁ? ሌላ ልጅ ስወልድ የርሱን ስም
አወጣለታለሁ...? ስሙን እቀማዋለሁ...? አላደርገውም፡፡ አይወለድ
እንጂ... አድጎ አትዩት እንጂ እኔ እኮ ልጄን ዐውቀዋለሁ... ልጄን እወደዋለሁ፡፡

እቅዴ ውስጥ ነበር፡፡ ወደፊቴ ውስጥ ነበረ፡፡

ስሙንማ አልቀማውም...

“ማሬ እንዴት ዋልሽ ዛሬ...?” ሶል ከሥራ መግባቱ ነው፡፡

“ደህና....”

“ሕመም አለሽ እንዴ...?”

“እ..እ... የለኝም...የለኝም...”

“ጎሽ... ደህና ሆንሽልኝ” አለና ግንባሬን ሳም አድርጎኝ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡

ብዙ ሳይቆይ አለበት ሆኖ፣ “ልጅቷን ቡና አፍይ በያት... እነ ቅድስት ይመጣሉ” ሲለኝ ተሰማኝ፡፡

ሰውነቴ እንደ ጎማ ተነፈሰ፡፡

“ለምንድ ነው የሚመጡት?” በዚህ ሰሞን ከሰው በላይ የሚያበሳጨኝ ነገር የለም፡፡

“ሊጠይቁሽ ነዋ ሆዴ....” አለኝ፣ ወደ ሳሎን እየተመለሰ፡፡

“ለምን ይጠይቁኛል...? ምን ብለው ይጠይቁኛል...? በቃደህና
አይደለሁ....?”

ነሽ እሱማ... ያው... ጓደኞቻችን አይደሉ.... አትምጡ አይባል

ነበር.... እን

ደዚህ አትሁኚ፡፡” እንደዚህ አትሁኚ