#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
ለምን እንደሆነ ባይገባትም ሳታስበው! ሳትጠብቀው ከልቧ ወዳዋለች፣ ጭራው የማይያዝ፤ የማይጠመድ፧ከእጅ የማይገባ ጋማውን እያመስ የሚፈነጭ የዱር ፈረስ ነው የሆነባት።
ይህን እያወቀች የመጨረሻ ውሳኔዋ ላይ መድረሷ እብደት መሰላት፡፡ ገደል ግቢ' ብሎ ቢተዋትስ? “ኡፍ…” በረጅሙ ተነፈሰች፡፡
በወፍራሙ ቅቤ የቀባቸውን ዳቦ ያለርህራሄ ግምጥ አደረገችና
ከትኩሱ ወፍራም ቡና በረጅሙ ፉት አለችበት፡፡ ነፍሷ መለስ አለች፡፡
ከናትናኤል ጋር እንዴት እንደተገናኘች ስታስታውስ፤ ግንኙነታቸው ሲጀመር የነበራት ዓላማና የአሁኑን ስሜቷን ስታስብ ድንቅ ይላታል፡፡
ልታጠምደው ተዘጋጅታ ቀርባ እሷ ራሷ እንዴት ልትጠመድ እንደቻለች ጭራሽ አይገባትም ያደረገችውን ሁሉ የግል ጉዳይ ነው እያለች ራሷን ለማሳመን ብትታገልም ህሊናዋ ሊያርፍ አልቻለም
ቀድማ የዘረጋችውን መረብ ሳትሰበስብ ሌላ መረብ መጣሏ ለራሷም አስፈርቷታል።
ሶስና ባዘጋጀችው የልደት በአሏ ላይ ነበር ከናትናኤል ጋር የተዋወቁት አርፍዶ ነበር የመጣው:: ውስጥ እንደገባ በግራው
ያንጠለጠለ በስጦታ ወረጭት የተጠቀለለውን ለሶስና አቀብሎ ግራ
ጉንጫን ላይ ሳማትና ተያይዘው ወደ ውስጥ ዘለቁ፡፡ ዓይኗ የገባውና
ለይታ ያወቀችው ገና ከበር ነበር። መረቧን ጣለች፡፡ ቀጠን ብሎ ረዘም ያለ ነው ስልክክ ያለ ፊቱ ቅንድቦቹና ሽፋሽፍቶቹ
እንደጎርፍ በአገጩ ዙርያ ፏ ብሎ ግጥም ያለው ጥቁር ጺሙ በሩቅ ሳቧት።
.
“ሶስና እውነቷን ነው አሰበች እርብቃ ደስ የሚል ልጅ ላይ ነው የጣላት እግዜሩ አስጠሊታ ፍጡር ቢሆንም ኖሮ ገብሬልዬ!”
ሶስና ግራ እጁን ይዛ እየጎተተች ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል መሃል ወሰደችው፡፡ በክፍሉ ውስጥ የሚተራመሰው እንግዳ አይትያይም!
ሁሉም በቡድን በቡድን ጨዋታውን ያቀልጠዋል፡፡ ናትናኤል ብዙ የሚያውቀው ሰው ያለው አይመስልም፡፡ ቢሆንም የመደናገር ! ግራ የመጋባት መልክ አልታየበትም፡፡
ሶስና እጁን ይዛ እየጎተተች ኮጓደኞቿ ጋር ስታስተዋውቀው ዞሮ ዞሮ የመመጣው እሷውጋ መሆኑ ታስባትና ፈገግ አለች ርብቃ::
ኬክ ከተቆረሰ ሰኋላ ነበር የተዋወቁት፡፡
“ተዋወቃት:: ርብቃ ትባላለች፡፡ ጓደኛዬ ናት:: ርብቃ አብሬው ነው የምሠራው:: ናትናኤል ይባላል፡፡" አለች ሶስና አሁንም እጁን እየጎተተች አምጥታው፡፡
“ናትናኤል ግርማ፡፡” አላት እጁን ዘርግቶ፣ አስቂኝ ወሬ እንደሰማ ሁሉ ፈገግ ብሎ፡፡ በትክክል የተደረደሩ የሚያማምሩ ትናንሽ ነጫጭ ጥርሶች አሉት፡፡
“ርብቃ ዮሃንስ፡” እጇን ዘረጋችለት፡፡ ጠበት ኣድርጎ ጨበጣት፡፡
ሶስና ድንገት ወደ ጆሮዋ ጠጋ ተጠንቀቂ ታዲያ ዱርዬ ነው” አለችና “በሉ ተጫወቱ::” ብላቸው ከሰው መሃል ተደባልቃ ተሰወረች::
ዱርየው!” ይህ ነበር የምትፈልገው የማስጠንቀቂያ ቃል፡፡ ፈገግ አለች ርብቃ::
“ስምሽን ከዚህ በፊት የማውቀው መሰለኝ አላት ድንገት
“እ በሬድዮ ሰምተኸው ይሆናል ጋዜጠኛ ነኝ::” :
“አ! የአፍሪካ ምጣኔ ሀብት ላይ አላት እጇን ጠበቅ አድርጎ ጨብጦ፡፡
“አዎ፡፡” አለች ፈገግ ብላ ብሬድዮ የምታዘጋጀውን ፕሮግራም ስም
ያለስህተት በመጥራቱ ኮራ ብላ፡፡
“በጣም ነው የምጠላው እሱን ፕሮግራም::”
የሰማችውን ማመን አልቻለችም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ድፍረት ሲያጋጥማት የመጀመሪያ ጊዜዋ ነበር፡፡ መልስ አልጠበቀችም እጇን ከእጁ ውስጥ መንጭቃ ማውጣት ፈለገች፡፡ ነገር ግን ትክ ብለው የሚያይዋት ዓይኖቹ አልሰበር፤ አፋታ አልሰጥ አሏት፡፡
'ብሽቅ' አለች በል፡፡
“ትዝ ይለኛል… በአንድ ወቅት የብዙሁን ፓርቲ ስርዓትና የኢኮኖሚ እድገት በአፍሪካ በሜል ርዕስ አንድ ተከታታይ ዝግጅት አቅርበሽ ነበር…መላቅጡ የጠፋው ዝግጅት ነበር።” አላት ናትናኤል፡፡ ርብቃ ንዴቷን ልትቋቋመው አልቻለችም፡፡
“ካልወደድከው ለምን ትከታተለዋለህ ታዲያ?" አለች ደርዝ ባለው ድምፅ፡፡
“ድምፅሽን ስለምወደው ይሆናል...? አለና ድንገት ከት ብሎ ሳቀ፡፡ወዲያው ኮስተር አለና “ስራዬ አፍሪካ አጠቃላይ ሁኔታ ጋር የሚያገናኘኝ ነው። ስለዚህ ወደድኩትም አልወደድኩትም ፕሮግራምሽ እንዲያመልጠኝ አልፈልግም:: በተለይ እንግዶች ጋብዘሽ ቃለ ምልልስ በምታደርጊበት ወቅት፡፡” አለ ከጎናቸው ካሰ ጠረረጴዛ ላይ ከተደረደሩት በመጠጥ ከተሞሉት ብርጭቆዎች ሁለቱን አንስቶ አንዱን እያሳለፈላት፡፡ “የሚሰማኝን በግልፅ በመናገሬ እንዳልተቀየምሽኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡”
“እህእ...” ትከሻዋን ነቀነቀች፡፡ “ግድ የለኝም የፈለከውን ብትቀባጥር
ለማለት
የምታዘጋጂያቸው ፕሮግራሞች እንደተረዳሁት በአመዛኙ ለአፊሪካ ማንሰራራት ዋነኛ ተስፋ አድርገሽ የምትወስጂው በአፍሪካ አገሮች መሀል
ነው:: አገሮች በተናጠል ለሚያደርጉት ጥረት ቦታ የሰጠሽው አይመስለኝም።
ትክክል ነህ እውነቱ መራሪ ቢሆንም ልቀበለው ስለደፈርኩ ነው።አለች ርብቃ ለዘብ ብላ።
“ምንድን ነው እውነቱ?"
“የአፍሪካ አንድ ተስፋ የለሽ መሆናቸው ከገቡበት አዘቅት መቼም ቢሆን ሊወጡ አለመቻላቸው ተስፋ ያላት አንድ አፍሪካ ብቻ መሆኗ ነው እውነቱ::
“አልገባኝም!” አለ ናትናኤል ቅንድቦቹን አጠጋግቶ።
በአጭሩ በኔሬሬ አፍ እንደተባለው የአፍሪካ ነፃነት የሚገኘው በተዋሀደ እንቅስቃሴ ብቻ ነው::”
ጨርሽዋ!” አለ ናትናኤል ፈገግ ብሎ “ኔሪሪ ያለው ያንን ብቻ አይደለም'ኮ፡፡ ውህደቱ ሊጠናከር የሚችለው በኢኮኖሚያዊ መተባበር የግንኙነት መስመሮችን በማሻሻል በመጨረሻም በፖለቲካ ውህደት ነው መሰለኝ ያለው ኔሬሬ፡፡ ለዚህ ደግሞ እያንዳንዱ የአፍሪካ አገር በተናጠል የሚያደርገው ጥረት ዋጋ ሊሠጠው ይገባል፡፡
“የትኛው ይቅደም መሠለኝ ጥያቄው፡፡” አሀች ርብቃ በስሱ የገጠመቻቸውን ከንፈሮቿን አላቃ፡፡
“ከምኑና ከምኑ?" ጠየቃት ናትናኤል።
“ከኢኮኖሚው ትብብርና ከፖለቲካው ውህደት።”
ይህማ ግልፅ ነው:: የፖለቲካ ውህደት በኢኮኖሚና በሌሎችም ትብብሮች ላይ የሚገነባ : ነው፡፡ ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ይቀድማል።”
“እንደ መጽሐፍ ከሆነ ልክ ነህ መሰለኝ፡፡ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬና ትብብር ለፖለቲካ
ውህደት አንድ መሰረት መሆኑ አያጠራጥርም ጥያቄው ግን መፅሐፍ ላይ የተፃፈው ሳይሰራ ሲቀርስ? የፓለቲካ አቋም ልዩነት በራሱ ለኢኮኖሚው ጥንካሬና ለትብብሩም እንቅፋት ሆኖ ሲገኝስ መድሃኒቱ ምን ይሆናል :: የሚለው ነው፡፡ በአፍሪካ የሚታየው ችግር ይህ ይመስለኛል፡፡
አተኩራ ተመለከተችው፡፡ “መልስልኝ እንጂ፡፡” አለች ናትናኤል ያመነታ
ሲመስላት:: .
“ያገባኛል! ይባኛል እርግጥ የፖለቲካ አለመጣጣም…" ናትናኤል እያመነታ ጀመረ፡፡
“አንዱ የአፍሪካ አገር አለመጣጠማቸው
ለወጭ አራዊቶች ቅጥረኛ እየሆነ የጎረቤቶቹኝ ሰላም ሲያውክስ ኢኮኖሚ ሲያደቅስ አልፎ ተርፎ በገዛ አፍሪካውያን ወንድሞቹ ላይ ጦር ሲሰብቅ
መድሐኒቱ ምን ይሆናል?የተማሩ የተመራመሩ ቅምጥል የአፍሪካ ልጆች አፍሪካ ጥቁር አፈር ሲገለማቸውስ? ነጭ አፈር ፍለጋ ሲዘምቱስ? ጋሻ መከታ መኩሪያ መመኪያ መሪዎቻቸውን፣ በአፍሪካ ቦሀቃ የጠለቁትን ሊጥ በስዊዝ ባንክ ካልጋገርነው ሲሉስ? ፖለቲካ መድህኒት መሆኑ ቀርቶ የነአለብላቢት ጭልፊት፣ የነጎርሶ አይጠግቡ፤ የነውጦ አይጠረቁ ጋሻ ጃግሬ አጋፋሪ ሲሆንስ? መድሀኒቱ ምን ይሆናል? መጽሐፉ እንደሚለው ትብብር ይሁን እፈጠጠችበት።
ይገባኛልኮ ችግሮች መኖራቸውማ ያለ ነገር ነው ግን አለ ናትናኤል፡፡
“በማን ጀርባ ላይ እየተጨፈረ ያለ ነገር ነው? ወንድም ወንድሙን እያስማማ ፧ ከነጭ ወል እየተጋባ፤ ወንድም ወንድሙን እየቸበቸብ ከባዕድ ጡጥ

👍3
እየተጣባ፤ አፍሪካ የሁሉ ቅምጥ እንደ ባቢሎን ግንበኞች ሀምሳ ቋንቋ ስታንቆረቁር አሽቃባጮች የባዕድ ልጋግ እየላሱ ከርዳታው ከዳረጎቱ ሲሻሙ፧ ሲስገበገቡ ነገ በዕዳ ማንቁርታቸው ሊፈጠረቅ ነገ ያጠለቁት ቁምጣ ሲበጣጠስ ቦላሌ ውርደት ሊያጠልቁ ፧ ነገ ደንቆሮ ጥቁር ሲባሉ ሬ በገዛ ዛሬ በገዛ ወንድሞቻቸው ላያ ሲያቃጥሩ ነው 'ያለ ነገር ነው' ብለን የምናልፈው?"
“ርብቃ…” አለ ናትናኤል፡፡ “መቼም "አፍሪካዊ ሆኖ የአፍሪካን አንድነት፤ "የአፍሪካውያንን ልምላሜና ዕድገት " የማይመኝ ፣ ያለ ኖሮ አይመስለኝም፡፡ አፍሪካ ብትበለፅግ፤ አፍሪካ ብትለመልም የእያንዳንዳችን ጓዳ የእያንዳንዳችን ጎተራ ሞላ ማለት ነበራ! ይህኮ የሁላችንም ምኞት ነው፡፡”
“ምንድን ነው ምኞት?” ፊቷን አጠቆረችበት፡፡“ወይስ ምኞት በዘር
በሰፈር የተከፋፈለች አፍሪካችንን እንድ ያደርጋት ይሆን? የተራቆተ ገላችንን
ይሸፍንልን፤ በረሃብ የተቆዘረ ሆዳችንን ይሞላልን፤ ወይስ የሸተተ የከረፋ ስማችንን ፍቆ እንደዝንጀሮ መታየት ያድነን ይሆን?”
... “ርብቃ አንጎሌን እያዘቀጥሽው ነው፡፡” አለ ናትናኤል ፈገግ ብሎ፡፡
“አፍሪካዊ የሆነ ሁሉ ቁጭት ሳይስማው ቀርቶ አይምሰልሽ፡፡ ድህነቱ ድንቁርናው ውርደት እስከ አጥንቱ የማይጠዘጥዘው፤ እስከ ጅማቱ
የማይነዝረው ኖሮ አይምሰልሽ፡፡ መውጫው መፍትሄው ጠፍቶት ነው
ማዶ ማዶ የሚያየው፡፡ ይሄ የእኔ ስሜት ብቻ አይምሰልሽ፡፡ የእያንዳንዱ አፍሪካዊ ነው፡፡ ምክንያቱም ድህነት በወረቀት ላይ በሰንጠረዥና በካርታ የተገታ ሳይሆን በየጓዳችን እሽሩሩ ያምንለውና የምናሞላቅቀው ነው:: ምናልባ እኔሰ ጠግቤ አድር ይሆናልግን ወንድሜ ወይ እሀቴ አለዛም ጎረቤቴ ጾሙን እንደሚያድር አውቃለአ፡፡ ኣፍሪካ ውስጥ ነው ያለነው:: በአንድ ጨረቃ ሁላችንም ጠፍተን ማደር እንደምንችል አውቃለሁ፡፡
ታዲያ ጠግቤ የምተኛው እንቅልፍ የሰላም ይመስልሻል? ድህነቴን ተሸክሜው ስኖር ትከሻዬ የማይላጥ ህሊናዬ የማያኮላሽ ይመስልሻል? ጠግቤ
መብላት እሻለሁ ይርበኛል ድህ : ነኝ ጥሩ መልበስ እፈልጋለሁ እራቆታለሁ ቤተሰብ ቢኖረኝ ወንድ ልጄ በስልጣኔ እንዲያድግ እፈልጋልሁ፤ ይደነቁራል አልታደለማ ፡ ሴት ልጄ በእውቀት እንድታብብ አልማለሁ፤ ትሸረመጣለች ታረግዛለች ይህ ነው እጣዬ ፤ አፍሪካዊ ነኝ፡፡ ይሄ
እያቆረጥምም ትያለሽ አያጠዘጥዝም ትያለሽ? ይህ አይተገትግም ትያለሽ? አፍሪካዊ ደንቆሮ ሆኖ ይሆን? ነጮች እንደሚሉት አፍሪካዊ የማይገባው ንፍር ጭንቅላት ሆኖ ይሆን? በልቶ መጸዳዳት ደሆን ዕድሉ?
ቢከፍቱት ሚሸት እበጥ ይሆን አንጎሉ? በስባሳ መረቅ መግል ይህን ሀሞቱ? አይመስለኝም፡፡ አፍሪካ በጊዜዋ የስልጣኔ ጫፍ፡ ነበረችኮ፡፡ የግብፅና
የማሊ፣የጋናና የዚምባብዌ፣ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔዎችኮ ተበድረን ያመጣናቸው አምጡ መልሱ ስንባል የመለስናቸወ : አልነበሩም::የኛው
የራሳችን ጥሪካዊያን ነበሩ። የጥቁር ንጥር ስልጣኔ ነበሩ፡፡ ታዲያ ዛሬ ምን
ነካን? እንዲያ ከሆነ እኛም ሰው ነን “ ማለት ነዋ! - ዛሬም ብንማር የምናውቅ ብንሰራ የምናድግ ነን ማለት ነዋ! :ታዲያ ምን ነካን? ምንድነው እንቅፋቱ? ማነው ጠላታችን ርብቃ? አፍሪካውያን ጠላታቸው ማን እንደሆነ አጥተውት ይመስልሻል? እርዳታ እያሉም ሲያሽቆጠቁጠን፤ ሆ! ሻሞ እያሉም ሲያናክሱን፤ እኔ እሻል እኔ እሻል እወደድ ባይ ኣሽቃባጭ ሲያደርኑን፧ ብድር ብድር እያሉም በዕዳ ሲዘፍቁን፤ ዕዳችሁን ወለዱ እያሉ ሀብታችንን ሲዝቁ፤ ወገባችንን ሲያደቁን፤ ዘር እያቋጠሩ ሶር እያስታጠቁ
እርስ በራስ ሲያናቁሩን፤ መልሰው ' ዲሞክራሲ ላይ ቆማችሁ ተጫናችሁት
ሲሉ፤ ሲዘባበቱብን፤ ማንም ጭቃውን ሊለድፍብን፤ የገብያ ድንጋይ ሲያደርገን የማይቆረቁረኝ ይመስልሻል?”....
💫ይቀጥላል💫

👍2
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ሲንተከተክ የቆየው፤ የብሶት ቋያ የቀቀለው ፤ትኩስ እንባና እልህ እንዴ
እሳተ ገሞራ ገነፈለ፡፡ ከዚያም ኡኡ!! ብሎ እየጮኽ ዋይታውን ማስማት ሲጀምር፤ ከደጅ ተኮልኩሎ ሲጠባበቀው የነበረው ዘመድ አዝማድ በሙሉ ተከታትሎ ወደቤት መግባት ጀመረ፡፡ ስዎች እየተንጋጉ ገቡ፡፡ እሱም ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር መቀላቀሉን ሲያውቅ፤ እጅግ ሆድ ብሶት ማንባቱን
ቀጠለ...
“አመልማል ፍቅሬ፡፡ ትዳሬ፡፡ አመልማልዬ ምነው ጨከንሽ? ምነው ደስታዬን ገፈፍሽው? እንግዳ መቀበሉን ስታውቂ ምነው በኔ ልብሽ ጨከነ? አመልማል አስራ አንድ ዓመት ሙሉ የናፈቀሽ ልቤን
ምነው በሀዘን ጉዳሽው እናቴ? ቤቷ ተጨናነቀች፡፡ እዚያ የገቡት በሙሉ እየመጡ እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ ይላቀሱ ጀመር፡፡ የሚያለቅሱት ለሱ ይሁን ለሟቿ አይታወቅም ነበር፡፡ ደስታም ከልክ በላይ ሲሆን ያስለቅሳልና የሚወዱት
መቶ አለቃ ድንበሩ ሞትን ድል ነስቶ ሲያገኙት ቢያለቅሱ ምን ይፈረዳል? የሱ በህይወት መገኘት በአንድ በኩል ታላቅ ደስታን ሲፈጥር፧ እሱ አለችልኝ ብሎ፤ በጉጉት ተውጦ፧ ሊያገኛት የመጣ
ሚስቱን በሞት ተነጥቆ፣ እንደዚያ አንጀቱ እየተርገፈገፈ አንጀት በሚበላ
አለቃቀስ ልቡ ተሰብሮ ሲያዩት፤ የሚፈጥረው የሀዘን ስሜት ከባድ ነው፡፡
ክፍሏ በመርዶና በትንሳኤ መካከል ዋዠቀች፡፡ ለቅሶው ቀለጠ፡፡ እየሄዱ
እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ፤ እዬዬ ሆነ፡፡ ደስታው ሙሉ ደስታ ባለመሆኑ
መቶ አለቃ ድንበሩ አለቃቀሱ እጅግ የሚያሳዝን፤ ብዙዎችን በእንባ
ያራጨ ነበር፡፡
አትጨክንም ነበር አመልማል በእንግዳ
ጀርባዋን ሰጠችኝ አረገችኝ ባዳ፡፡
ሞትን አሸንፌ ስመጣ በናፍቆት
ሸሸችኝ፤ ራቀችኝ፤ ኧረ ምን በደልኳት?
አመልማል ትዳሬ አመልማል ህይወቴ
እባክሽ ወይ በይኝ፤ አትጨክኝ እናቴ፡፡
አለሽልኝ ብዬ በጉጉት ስመጣ
ምነው ጉድ አረግሽኝ ደስታዬ ቅጥ አጣ፡፡
ፋናዬን ትንሿን አንዱዬ አካሌን
የአጥንታችን ፍላጭ ሁለት ልጆቻችን፡፡
ኧረ የትደረሱ እባክሽ ንገሪኝ
አንዴ በሹክሹክታ ድምፅሽን አሰሚኝ፡፡
ፈጣሪዬ ስማኝ ልንገርህ ብሶቴን
ዐይኖቿን አይቼ የምወዳት ሚስቴን፡፡
ፍቀድልኝ ባክህ ናፍቆቴን ልወጣ
ተከትያት በአካል ጠቅልዬ እስክመጣ፡፡
አመልመል አመልማል
የትዳሬ ዋልታ፡፡
እኔ ድፍት ልበል፤ እኔ ልንገላታ፡፡
መከራና ስቃይ ደቁሰው ገደሉሽ?
አይዞሽ እመጣለሁ፡፡
የህይወትን ሽክም
በምድር ባልረዳሽም፡፡
እዚያ አግዝሻለሁ፡፡
ናፍቆቴን ልወጣ
አልቀርም እመጣለሁ፡፡
የሀዘን እንጉርጉሮ አንጐራጐረላት፡፡
በዚያን ሰዓት በሻምበል ብሩክና በትህትና ሰርግ ላይ ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው፤ እንደ ወላጅ ሆነው፤ የዳሯቸው የረጅም ጊዜ ጐረቤታቸው አዛውንቱ አቶ ብራቱ በተፈጠረው ሁኔታ በደስታ ሰክረው፤
ከአንድ ሌላ ሰው ጋር ሆነው፤ ወደ መገናኛ ወደ ትህትና ቤት በታክሲ
እየገሰገሱ ነበር፡፡
አዲሱን፣ አስደናቂውን፣ ለማመን አስቸጋሪ የሆነውን፣ ታላቅ የምሥራች ይዘው
ትህትና ድንበሩ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በፀሐፊነት ተቀጥራ በማገልገል ላይ የምትገኝ ባለትዳር ስትሆን፤ የአንድ ወንድና፤ የአንዲት ሴት ልጆች እናትም ለመሆን በቅታለች።
በባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሮ በማገልገል ላይ የሚገኘው ዘንካታው ወጣት አንዱዓለም ድንበሩም፤ አንድና ብቸኛ የሆነቸውን፤ እንደ ዓይኑ ብሌን የሚያያት፣ ህይወቷን አሳልፋ የሰጠችለት፤ ታላቅ እህቱን፣ የሚወደውና በቅርቡ የሻለቅነት ማእረግ ያገኘው አማቹ ሻለቃ
ብሩክና፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊያገባት የተዘጋጀው እጮኛው አዜብ ተሾመን፤ ሊጠይቅ፤ የአሥራ አምስት ቀን የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን ወስዶ ከአሰብ ከመጣ አንድ ሣምንት ሆኖት ነበር፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ የሻለቃ ብሩክ አጥር በር ተንኳኳ፡፡
ሠራተኛዋ በሩን ከፈተች፡፡ ሁለት ሰዎች ቆመዋል፡፡አታውቃቸውም፡፡
“ሻለቃ አለ?” ሲሉ ጠየቋት ሽማግሌው።
በዚያን ሰዓት አንዱዓለም፣ ትህትና፣ ሻለቃ ብሩክና ወንድሞቹ ስብስብ ብለው እየተሳሳቁ እየተጨዋወቱ፤ እራት እየበሉ ነበር፡፡
“አሉ” ስትል መልስ ሰጠቻቸው፡፡
“አንድ ጊዜ ጥሪልኝ” አሏት ረጋ ብለው፡፡
ሄዳ ብሩክን ጠርታ መጣች፡፡
“እንዴ አባባ ብራቱ ዛሬ ከየት ተገኙ? ይዝለቁ እንጂ!”
ትከሻቸውን እቅፍ እድርጐ እየሳማቸው፡፡
“እሱን አደርሳለሁ ሻለቃ፡፡ አመጣጤ ለብርቱ ጉዳይ.
ነበር። ሥራ ይዘሃል?”
“ሥራስ ብይዝ ምን ችግር አለው ? ደግሞ ለርስዎ? አሁን ግን
ምንም ሥራ አልያዝኩም፡፡ ይግቡዋ ታዲያ” በእጁ ወደ ቤቱ እንዲገቡ
እየጋበዛቸው፡፡
“ባለቤትህስ አለች?”
“ባለቤቴም ፤ወንድሟም፤ ሁላችንም አለን፡፡ ምነው በደህና?”
“እንግዲያውስ አንድ ጊዜ መጣሁ በላቸውና ተመለስ፡፡ በጣም
ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ እኔ መሆኔን እንዳትነግራቸው፡፡ አይዞህ በደህና
ነው” አሉት፡፡
ሄዶ የሆነ ምክንያት ሰጥቷቸው ወደ ሽማግሌው ተመለሰ፡፡
ከዚያም ሽማግሌው እጁን ያዝ አደረጉት :: ብሩክ ልቡ በኃይል መታ፡፡
“ምን ሊነግሩኝ ይሆን?” በሚል ጭንቀት ተዋጠ፡፡
ደግነቱ መርዶ በምሽት አይነገርም፡፡
“የውልህ ሻለቃ” አሉና የሆነውን፣ የተፈጠረውን ተአምር ይተርኩለት ጀመር።
የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ፣ ሞቷል ተብሎ ተዝካሩ የተበላለት ሰው በህይወት መግባቱን፣ አሁንም ከድሮው ቤቱ የባለቤቱን መርዶ ተረድቶ መቀመጡን፡ እድርተኛው በሙሉ እንዲሰማ መደረጉን ፡
በሹክሹክታ ሲነግሩት፤ ሻለቃ ብሩክ በህልም ዓለም ያለ ዓይነት ስሜት
ተሰምቶት፤ በአድናቆትና በድንጋጤ ተውጦ አፉ እንደተከፈተ ቀረ፡፡
ተአምር! እውነትም ትንግርት! ይህን ምን ይሉታል?!
ከዚያም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ከሽማግሌው ጋር በእርጋታ ተመካከሩ፡፡ በመጨረሻም ሲነጋ በሌሊቱ ሁለቱን ልጆቹን ወደ ድሮ መኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ ከአባታቸው ጋር ለማገናኘት በፈጠሩት ምክንያት ተስማምተው ተሰነባበቱ፡፡ ሻለቃ ብሩክ ከሽማግሌው ጋር ባደረጉት ስምምነት መሠረት
በጠዋቱ ትህትና ከሁለቱ ልጆቿ ጋር አንዱዓለምንም እንደዚሁ ልብሳቸውን እንዲለባብሱ አደረገ፡፡
“አባባ ብራቱ ጠበል እንድንቀምስላቸው በጠዋት ድረሱ ስለአሉን
እንዳይቀየሙን ቶሎ ቶሎ ልበሱ” በማለት አጣድፎ አለባበሳቸውና፤ይዟቸው በታክሲ ወደ ድሮ ሠፈራቸው ጉዞ ጀመሩ፡፡ አባባ ብራቱ ደግሞ በቀጠሮአቸው መሰረት ቤታቸው ሆነው መምጫቸውን እየተጠባበቁ ነው፡፡ ዛሬ የደስታ ቀን ብቻ እንዳልሆነ ሻለቃ በሚገባ አውቆታል፡፡ ዛሬ
ሞቷል ተብሎ የተለቀሰለት አባታቸው አፈሩን አራግፎ የመጣበት ቀን ነው፡፡ አፈር ለብሳ፤ አፈር ሆና፤ የቀረችው እናታቸው ግን ዳግም ላትነሳ ነው የሄደችው፡፡ ሶስቱ ሲገናኙ በዚያን በሚያስገርም ወደር በሌለው
ደሰታቸው መካከል፤ የተለየቻቸው የእናታቸው ናፍቆት እንደ አዲስ
ተቀስቅሶ፤ በእንባ እንደሚራጩላት አውቋል፡፡
ከልክ በላይ ሲሆን፤ ከሀዘን
ደስታም የበለጠ በእንባ ያንፈቀፍቃል። በተለይ ደግሞ እንደ መቶ አለቃ ድንበሩ ያለ የሚወደድ፤ የሚናፈቅ ፤አባት ሞትን አሽንፎ ሲመጣ ድንጋጤው ብቻ በሽታ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው፡፡ዛሬ ትንሳኤና መርዶ እዚያች ግቢ ውስጥ መንገሳቸው የማይቀር ነው፡፡ ሻለቃ ብሩክ ካሜራውን አዘጋጅቶ ይዟል፡፡ ትህትና እና ወንድሟ
የሚሄዱት ወደ ድግስ እንጂ ወደ አባታቸው ዘንድ መሆኑን እንዴት
ጠርጥረውት? የሞተ ሰው ከመቃብር ተነስቶ አቀባበል ሊያደርግላቸው
እየተጠባበቃቸው መሆኑን እንዴት ገምተውት? ጭቃ እያቦኩ፤ ውሃ
እየተራጩ ባደጉባት፡ በፍቅርና በመተሳሰብ የደስታ ጊአዜአቸውን
ባሳለፉባት፤ አልቅሰው የእናታቸውን ተዝካር ባወጡባት፤ በዚያች የድሮ
ቤታቸው ውስጥ በአካል ተገኝቶ በናፍቆት

❤1👍1
ሊቀበላቸው መዘጋጀቱን ፧እንዴት ይጠርጥሩት? እነሱ የሚያውቁት በወዳጃቸው፡ በባለውለታቸውና
በድሮ ጐረቤታቸው በአባባ ብራቱ ቤት ተገኝተው ጸበል፤ ጸዲቅ ሊቀምሱ፤ ሊጨዋወቱ ነው፡፡ ተዘገጃጅተው ለመሄድ ተነሱ......
ጠዋት ላይ መቶ አለቃ ድንበሩ እንዲጽናና፡ እንዲረጋጋ ተደርጐ፤ እህል ውሃ ከቀመሰ በኋላ፤ ልጆቹ ወደሱ እየመጡ እንደሆነ ተነገረው፡፡ ከዚያም በእድርተኞቹና በወዳጅ ዘመዶቹ ተከቦ አይኖቹን በበሩ አጥር ለይ እያንከራተተ በናፍቀት ይጠባበቅ ጀመር። ልጆቹ ከአሁን አሁን መጥተውለት እስከሚስማቸው፣ እስከሚያቅፋቸው፡ አንገታቸው ላይ ተጠምጥሞ እስከሚያነባ ድረስ ተጣድፎና፤ በጉጉት ተውጦ፤ ከአጥሩ በር ላይ አይኖቹን ሳይነቅል መጠባበቁን ቀጠለ፡፡ ትህትና ትህትና...ትንሿ ትህትና... ቆንጅዬዋ ትህትና፣ የሚወዳት ልጁ እንዴት ሆና
ይሆን? ማንን አክላ ይሆን? እንደዚያ የሚንሰፈሰፍላት ትህትና...
አንዱዓለም ትንሹ የአካሉ ክፋይ ጋሻዬ የሚለው ወንድ ልጁ ፣ እንደ አህያ ጡት ሁለት ብቸኛ ልጆቹ፡፡ በድንገት እንደተለያቸው ሲቀር ለዘመናት ናፍቆታቸው ውስጡን ሲቦረቡረው የኖረው፣ ዐይኖቹ ደም እስከሚያለቅሱ ድረስ ያለቀሰላቸው ልጆቹ ተያይዘው ይመጡልሃል ተብሎ ከተነገረው በኋላ፤ እሰከሚያያቸው፤ እስከሚያገኛቸው ፤ ድረስ አላምን አለ፡፡ እንደ ባለቤቱ እንደ አመልማል እነሱም ከድተውት እንዳይሆን ልቡ ፈርቶና በጥርጣሬ ተውጦ መጠባበቁን ቀጠለ... በንግግራቸው መሰረት እነ ሻለቃ ልክ ቤት መድረሳቸውን ሲያውቁ አባባ ብራቱ ከደጅ
ተቀበሏቸውና....
ዛሬ ጸበል ጻዲቁ የተዘጋጀው ከኔ ቤት ሳይሆን እዚህ ከናንተ ቤት ነው!" አሉና የጐረቤታቸውን የእነትህትናን አጥር በር ብርግድ አድርገው ከፈቱት፡፡ የአብራኩን ክፋዮች ዓይናቸውን ለማየት የአስራ
አንድ አመታት ናፍቆቱን ሊወጣ የሚጠባበቀው እንግዳ እዚያ ከሰዎች
መካከል ሆኖ ደጅ ደጁን ሲናፍቅ በሩ ብርግድ ብሎ ተከፈተ፡፡ የሱም ልብ
ከበሩ ጋር አብሮ ተበረገደ..አባባ ቢራቱ ቀድመው ገቡ፡፡ ከዚያም ሻለቃ
ብሩክ ተከተለ፡፡ እንግዳው ልቡ ከቦታዋ ተነቃነቀች፡፡ቀጥሎ...ቀጥሎ አዎን! ! እሷ ናት! እሷ ናት! ! ትህትና ናት!! ትንሿ ልጄ ናት! የኔ ፍቅር ናት!! እናቴ ናት!! አዎን ! አዎን! ደርባባዬ ናት!! እንደ እብድ
አይነት ሆኖ፤ እጆቹን በሰፊው ዘርግቶ፤ እያለቀሰ፤ እየጮኽ፤ ተነሳ... ምን ያደርጋል? ውስጡ በሃዘንና በመከራ ተደቁሶ አቅም አነሰውና ድንቅፍቅፍ ብሎ ሊወድቅ ሲል ሰዎች ተረባርበው ደገፉት፡፡ ከዚያም ራሱን ከደጋፊዎቹ እጅ አላቀቀና “ትህትናዬ... ትሁቴ ልጄ... ህይወቴ
አካሌ... እንዱዓለሜ..! የኔ ጌታ! ጌታዬ! እናታችሁስ የታለች?
አመልማልዬስ የታለች? የታለች? እናታችሁ?! ጥሯትና ተቀበሉኝ!
ልጆቼ! ኑ ሳሙኝ ልጆቼ ኑ ሳሙኝ ...ኑ! ...ኑ! ...ኑ! ወደዚህ” እንባውን
እንደ ጉድ እያጉረፈ እጆቹን እያርገበገበ በሁለመናው ሊያቅፋቸው እያለቀሰ፤ እየሳቀም፣ እየሳቀ ፧ እያለቀሰም፣ እንደ እብድ ዓይነት ሆኖ፤ እየተደነቃቀፈ፧ ወደ ልጆቹ ተንደረደረ... ትህትናም አንዱዓለምም ከፊት ለፊት ወደ እነሱ የሚመጣው ሰው ሞትን ድል ነስቶ የተነሳ፣ በአካል የሚያዩት ሰው፤ እሱ የሚወዱት፤ የሚያፈቅሩት፤ ገና በልጅነታቸው የተለያቸው አባታቸው፣ አለኝታቸው መቶ አለቃ ድንበሩ
መሆኑን፤ ያ እንደ ነፍሱ የሚወዳቸው አባታቸው መሆኑን፤ ያ ገና ናፍቆቱን የተነጠቁትና ትንሿ ልባቸው በሀዘን
የተሰበረችለት፤መመኪያ ፤አለኝታቸው፤ እሱ ራሱ መቶ አለቃ ድንበሩ
ለማወቅ ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር፡፡ ሥጋ ለሥጋ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ስላለው እሱነቱን ለማወቅ እንዴት ሊሳናቸው ይችላል ? ስጋ የራሱ ቋንቋ እንጂ ምን ሌላ ቋንቋ ያስፈልገዋል እግዚኦ! በዚያን አባታቸው መሆኑን ባውቁ ጊዜ ስሜት? የማይታመን ታሪክ! ሊሆን የማይችል አንደሀውልት ደርቀው ከቀሩበት ሳይንቀሳቀሱ፤ እንደምስሶ ከተገተሩበት ቦታ ንቅንቅ ሳይሉ፤ እሱ በሰዎች ተደግፎ እያለቀሰ፣ እየሳቀ ፣እየሳቀ እያለቀሰም ሄዶ እላያቸው ላይ
ተጠመጠመ...
የተፈጥሮ ህግ አቅጣጫዋን ለወጠች? የቀንና የሌሊት መፈራረቅ ህግ ቀረ? ወንዞች ሽቅብ ይፈስ ጀመረ? ፀሐይዋስ በምስራቅ ወጥታ በምዕራብ መጥለቋን አቆመች? መሬት በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከሯ ታበቃና ወንዞች ሽቅብ መፍሰስ ከጀመሩ ብቻ ነው የሞተ ሰው ሊነሳ የሚችለው፡፡
ሁለቱም በጭንቅላታቸው ውስጥ የነጐድጓድ ድምፅ ያስተጋባ መሰላቸው፡፡
ዓይኖቻቸውን ጨፈኑ፡፡ ገለጡ፡፡ ጨፈኑ፡፡ ገለጡ፡፡ ህያው ነው፡፡ ነገሩ ህልም አይደለም፡፡ ከረጅም ዓመታት በፊት ወጥቶ የቀረውና ሞቷል ብለው ተስፋ
የቆረጡበት አባታቸውን በህይወት ማግኘት ማለት ሊቋቋሙት ከሚገባው
በላይ የሚያስደነግጥ ደስታ ነውና፤ ደንግጠው ያለ እንቅስቃሴ እንደ
ሀውልት በቆሙበት ቦታ ላይ፤ እሱ ደርሶ እላያቸው ላይ ሲጠመጠም፣
ከገቡበት ሰመመናዊ የህልም ዓለም ወጥተው፣ ገሀዳዊውን እውነታ ሲረዱ፣ አባታቸውን በአካል ዳብሰው ሲያስተውሉት፣ በተለይ የትህትና
ሁኔታ እጅግ የሚያሳዝን አንጀት የሚበላ ነበር፡፡ በሰመመን ውስጥ ሆነው፤ በሚንቀጠቀጡ እጆቻቸው ይደባብሱት
ጀመር... ህልም ያለመሆኑን፣ ሥጋ የለበሰ አባታቸው መቶ አለቃ ድንበሩ መሆኑን፣
ሲያረጋግጡ፤ አስተቃቀፋቸው፣ አሳሳማቸው፤ በአጠቃላይ ሁኔታቸው
ሁሉ እጅግ ልብ የሚነካና እዚያ የነበሩትን ሁሉ በእንባ ያራጨ ነበር።
ከዚያም አባትና ልጆች ተቃቅፈው እንደ ስስት እንጀራ እርስ በርስ እየተሻሙ፤ አንገት ለአንገት ተቃቅፈው ሲሳሳሙ ከቆዩ በኋላ፤ ሻለቃ የፈራው ነገር ሁሉ ሆነ :: በዚያች ግቢ ውስጥ ተፈጥሮ እንቅስቃሴዋን ለየት አደረገች፡፡ ፀሃይዋ ጥቁር ግርዶሿን ጣለችና ብርሀንዋን ከለከለች፡፡
ነፋሱም አስገመገመና በዚያች ትንሽ ግቢ ውስጥ አዋራውን ወደ ሰማይ አስነሳ!! ለዚህች አስገራሚና ውብ ቀን ላልታደለችው ሚስኪን የሰማይ አሞራ ጭምር በድጋሜ ዋይ! ዋይ! እያለ አለቀሰላት፡፡ አንገት ለአንገት ተቃቅፈው፤ ለዚያች ይህንን የመሰለውን አስደሳች ቀን ለአንድ ቀን እንኳ ለማየት ላልታደለችው ከርታታ፤ እዬዬ ብለው በእንባ ተራጩላት።
ሁለቱ የትህትና ልጆች በቤተሰቡ ለቅሶ ተደናግጠውና በእናታቸው እግር ላይ የሙጥኝ ብለው ተጠምጥመው የለቅሶው ተካፋዮች ሆኑ፡፡ ሳያውቁት
እነሱም የደስታውና የሀዘኑ ተካፋይነታቸውን አሳዩ :: ድንቅ! ነው ፀሐይዋ እንደጠለቀች አልቀረችም! በሌላ በኩል በተራራው አናት ላይ ብርሀኗን ፈንጥቃለች.. አዲስ ህይወት ይመጣል... አዲስ ህይወት ይቀጥላል...ህዝቡ በዋይታና በደስታው መሃል እየዋዠቀ አብሯቸው ወዲያና ወዲህ ሲሯሯጥ፣ ሻለቃ ብሩክ በደስታ ተሞልቶ፤ እንባውን ከፊቱ ላይ አየጠራረገና ካሜራውን ደጋግሞ እየተጫነ ለነገው ትዝታ የዛሬውን እጅግ አስደናቂውንና አስገራሚውን እውነታ መቅረጹን ቀጠለ.........!!!
✨ተፈጸመ ✨
ታሪኩ ይህን ይመስላል አስተያያታችሁ ለሰጣችሁኝ እንዲሁም በንባብ አብራችሁኝ ለነበራችሁ ሁሉ በጣም አመሰግናለው ዛሬም አንብባችሁ ስትጨርሱ የተለመደውን አስተያየት እጠብቃለው በ @atronosebot አድርሱኝ። ሌላው #ሰመመን ድርሰት በቅርቡ መጠናቀቁን ታውቃላቹ በተቻለኝ መጠን ለመመለስ ሞክሪአለሁ ያልመለስኩት ካለም ምስጋናዬ አሁን ይድረሳቹ በጣም አመሰግናለው ከቡዙዎቸለ ግን ልቤን የነካኝ አንድ አስተያየት አለ በድምፅ የተላከልኝ ስለሆነ ሁላችሁም ብትሰሙት ደስ ይለኛል 👇

👍3❤2
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
እርስ በራስ ሲያናቁሩን፤ መልሰው ' ዲሞክራሲ ላይ ቆማችሁ ተጫናችሁት
ሲሉ፤ሲዘባበቱብን፤ ማንም ጭቃውን ሊለድፍብን፤ የገብያ ድንጋይ ሲያደርገን የማይቆረቁረኝ ይመስልሻል?”
ናትናኤል ቀጠለ፡፡
“ርብቃ አፍሪካውያን ጠላታቸው ማን እንደሆነ አጥተውት ይመስልሻል? ማርና ወተት ከአንደበታቸው እያንጠባጠቡ! በጉቦና በምልጃ ማብሰያ ድስት ጥደው ሲያቁላሉን፤ ነጭ አትያቸው፣ ጥቁር አትያቸው፤ ቡራቡሬ ኬክ ገላ ተንቧኬዎች ከእምብርታችን ቆመው ሲቦጠቡጡን፤ የባዕድ አትያቸው የኛ! የኛ አትያቸው የባዕድ ሽለምጥማጥ እስስቶች ከኛው
ዘርፈው ነጭ ሲሆኑብን፡ በ በስልጣን ኮርቻቸው፧ በፖለቲካ ልምጫቸው፤
ሲኮረኩሩን፤ "ቼ"እያሉ ሲጋልቡን ውስጥ እግሯችንን የማያቃጥለን! ውስጥ እጃችን የማይለበልበን ይመስልሻል? መውጫው ስለጠፋብን ነው፡፡ቢያሰምጠን ከአንደበታችን ቢደርስ ዙሪያው ቢጨቀይ ነው ባሻገር ማተኮራችን፤ የቆምንለትን አላማ ኢያየ እንዳለየ እየሰማ እንዳልሰማ መምሰላችን!”
ለአንድ አፍታ አቶክሮ ተመለከታት፡ “ማነሽ? ርብቃ ለምን የዚህ አይነት ርዕስ አንስተሽ ሰላም ታደፈርሻለሽ?
“መድሐኒቱን ንገረኝና ርዕስ እንቀይር።” አለች ርብቃ ፈገግ ብላ፡፡
ፀ
“ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ውድቀት መልሱ ቅንጅት ያለው እንቅስቃሴ መሆኑኮ እርግጥ ነው፡፡ ግን ይህን ቅንጅት እንዴት ልንፈጥረው እንደምንችል አላውቅም:: ይሁን እንጂ ይህን ቅንጅት አንቺ እንደምታስቢው በአንድ ጀንበር መዳፋችን ውስጥ ልናስገባ የምንችለው አይመስለኝም፡፡ ጊዜ...ጊዜ እንላለን
ዲሞክራሲና ጊዜ እንፈልጋለን፡፡ ይበልጥ መማር፤ ይበልጥ ማወቅ አለብን፡፡ አገሮች በተቻላቸው ግንኙነታቸውን ማዳበር
አለባቸው። እርግጥ ለዚህ የጋራ መድረክ ያስፈልጋል? ብቻ ኣይደለም !እገሮች ጥቃቅንና ግዙፍ ቅራኔዎቻቸውንም ማቻቻል ይኖርባቸዋል፡፡ እንዴት አትበይኝ፡፡ አላውቅም። . እውነቱን ንገረኝ ካልሽ በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ ማውራት አልወድም፡፡ምክንያቱም መልስ የማይገኝላቸው በርካታ ጥያቄዎች
ያፋጥጡኛል፡፡ ስለዚሀ ጉዳዩ እንደማይነካኝ ሁሉ ትከሻዬን ነቅንቄ ማለፉን እመርጣለሁ፡፡ እንጃ ብቻ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም፡፡ ወደ አንቺ የሬዲዮ ፕሮግራም የመጣን እንደሆን ደግሞ አሁንም ተረዳድቶ ቅንጅት ባለው መልክ መስራት ነው፡፡ በኔ በኩል አለፍ አለፍ እያልን እየተገናኘን
እንዲህ ብንወያይ መቼም ያቅሜን በማድረግ አልቆጠብም፡፡ ለምሳሌ : ነገ
ማታ እራት ብጋብዝሽና" ፈገግ ኣለ ናትናኤል፡፡
“ሀ..ሀ..” ከት ብላ ሳቀችበት:: “ኮሚክ ነህ”
እንዳለው በማግስቱም ' ባይሆን በሳምንቱ ተገናኝተው እራት ጋበዛት፡፡ ስለምታዘጋጀው የሬድዮ ፕሮግራም ግን ብዙም አልተወያዩም፡፡ሳይታሰብ ሌሎች በርካታ የመወያያ ነጥቦች ተፈጠሩ - አስቸኳይ ጉዳዮች፡፡ከዚያ ወዲያም ቢሮዋ ድረስ ስልክ እየደወለ ቀጠሮ እየያዙ ግንኙነታቸውን ቀጠሉ፡፡ ርብቃ እንዳጠመደችው ? የተረዳው ወዲያው ነበር፡፡ 'መቼ እንደተጠመደች ግን ጭራሽ አታስታውስም፡፡ እርግጥ መጀመሪያ ባየችውም ሰዓት ደስ ብሏታል፡፡ ናትናኤል ዓይን የሚገባ ወንድ ነው:: ግን ዓላማዋ ሌላ ሆኖ ሳለ አሁን የሚሰማት ጥልቅ ስሜት እንዴትና መቼ ሊፈጠርባት
እንደቻል አይገባትም፡፡ እሷ ማመን የማትፈልገውን ያህል እያፈቀረችው
መጥታለች፡፡ እሱን መውደዷ ከአላማዋ ጋር ሊጋጭ ይችላል የሚል ስጋት
ሲያድርባትም እራሷን ለመቆጣጠር አልቻለችም፡፡
የሚጨንቃትና የሚረብሻት ነገር ቢኖር የናትናኤል ግድየለሽነት ነው፡፡ እርግጥ አልጋ ውስጥ የሚወዳደረው የለም፡፡ ግን ሰው አልጋ ውስጥ አይኖርም፡፡ ናትናኤል ደግሞ ከዛ ውጪ የሌላን ፍጡር ወዳጅነትና አርነት የሚሻ ሰው አይመስልም እንዳልተገራ ፈረስ ያንን አሞሌ ይዛ ስታባብለው ይቀርባታል። ጋማህን ልጨብት ስትለው ይደነብራል፡፡ ከሱ ጋር መስማማት ብትችል እንኳን እነሶስናን የማሳመኑ ጥያቄ ቀላል አይደለም፡፡
ከመጨረሻ ውሳኔዋም የደረሰችው ለዚህ ነው::በየትኛውም አቅጣጫ ተጠያቂ ወይም ተወቃሽ አትሆንም፡፡ መቼስ አጋጣሚ ሆኖ ሆነ... ስለዚህም
መጋባታቸውም ምርጫ የሌለው መፍትሄ ሆኖ ተገኘ፡፡ ስለሆነም ያላትን ብቸኛ ምርጫ ወሰደች፡፡ የሁሉንም ወገን አፍ ሊዘጋ ይችላል ብላ ያሰበችውን እርምጃ ነበር የወሰደችው! ናትናኤልንም ጨምሮ፡፡ አለበለዚያ ለጋብቻ ያለውን ጥላቻ ስታጤን....
“ርብቃ ከዚህ በፊት የተናገርኩ መሰለኝ፡፡ ጋብቻ ጊዜው ያለፈበት ጥንታዊ ልማድ ነው፤ ጎጂ ባህል::”አላኝ አንድ ቀን እንደቀልድ ለምን እንደማይቡ ስትጠይቀው።
“እና እስከመቼ እንዘዘላዘል ነው የምትለው?” ቆጣ ለማለት ሞከረች፡፡
“የተጋቡ ምን ያደርጉ መሠለሽ? ያው እንደኛው መዘላዘል ነውኮ::
“ናትናኤል እኔ ትዳር ይዤ ልጆች
ወልጄ መኖር ነው የምፈልገው፡፡”
“ታዲያ ለምን ባል አታገቢም?”
“አንተ ባል መሆን አትችልም? አባት መሆን አትችልም?”
“ርብቃ እኔ ወደዚች ጨካኝ ዓለም ምንም የማያውቁ ህፃናትን የሚያመጣ ድፍን ልብ የለኝም ልጅ መውለድ አልፈልግም::”
በመጀመሪያ እንደ ብዙ ወንዶች ነፃነቱን ከመወደድና በትዳር ዓለም የሚገጥመውን ሀላፊነት ከመፍራት የመነጨ ይመስላት ነበር። በኋላ ግን ትዳርን እንደሚጠላ እየተረዳች መጣች፡፡ ታሟኟ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነች፡፡ ነገር ግን በፊርማና በድግስ ከእርሷ ጋርም ሆነ ከሌላ ሴት ጋር መተሳሰር እንደማይፈቅድ እየተገለጸላት መጣ:: ፍቅሯ ፍርሀትና ስጋት እየወሰደ የመጣው ከዚያ በኋላ ነው።
ተጨማሪ ጭንቀት የሚፈጥርባት ደግሞ ከናትናኤል ጋር ያገናኛት ምክንያት ነው፡፡ ይሉኛል እየሶስና? ሁሉም የፈለጉትን ይበሉ፡፡ ወደድኩት ፤ ወደደኝ ተጋባን። በቃ፡፡” ብላ ስታስበው ነገሩ ጭንቅ ጥብብ ያደርጋታል።
ርብቃ ከአልጋዋ ላይ ተነስታ ቁርስ የበላችበትን ትሪ ይዛ ወደ ወጥ ቤት ገባች ትሪውን ማጠብያው ላይ አስቀምጣ መደ መኝታ ቤት ተመለሰች፡፡ ልብሷን ብትቀይር ይሻላል፡፡ ተመላላሻ ቤት አጸጂ ሴት
ከመጡ ማልጎምጎማቸው አይቀርም አቤት ጥድፊያቸው የቤቱን ወለል
ነካ ነካ አድርገው አፀዳሁ ለማለት የተጠሩ ይመስል በተኛችበት አስር ጊዜ
የመኝታ ቤቱን በር እየከፈቱ እየገቡ “ቤቱን ላፀዳ ብዬ..” የሚሉት ፈሊጣቸው ታወሳት:: ቢነገራቸው የማይገባቸው አብግን” ቶሎ ለባብሳ ብትቆይ ይሻላታል፡፡
እላይዋ ላይ የደረበችውን የጠዋት ልብስ አውልቃ አልጋው ግርጌ ወርወር አደረገችውና እራቁቷን ወደ ፊት ራመድ ብላ መስታወቱ ፊት ቆመች::
ፍረደኝ!
እንተ እዚህ ጠብቀኝ ደርሼ እመለሳለሁ አትለን ነገር እድሜዋም አብሯት ያቶሶቱሳል፡፡ ዘልዛላ፡፡ እያንዳንዷ ፀሃይ ወጥታ በጠለቀች ቁጥር አንድ ቀን እንዳረጀች ይሰማታል፡፡ ሰላሳኛ አመቷን ልትቀበለው የቀሯት ሁለት ጥቃቅን ዓመታት ብቻ ናቸው፡፡ ስታስበው
ይዘገንናታል፡፡
እራቁት ገላዋን በመስታወት ውስጥ ተመለከተችው:: ያው የድሮው ይመስላል ጥምጥም ያለ ገላ፤ ቀና፣ ቀጥ ያለ ትከሻ፤ ሸለግ ያለ ሆድ፣ ሞላ ሞላ ያሉ ጭኖች ድንገት ጡቶቿን በሁለት እጆቿ ያዝ አደረገቻቸው፡፡ከወትሮው ይልቅ ለስለስ ያሉ መሰላት፡፡ ምናልባት መስሏት ይሆናል፡፡ ግን ደግሞ ሊሆንም ይችላል፡፡ ወሳኙ ጊዜ ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ
ጭራሹን ይሞቀሙቃሉ፡፡ የገዛ ሃሳቧ አሸማቀቃት፡፡ ጡቶቿን ቶሎ ለቀቅ አደረገችና ቀኝ እጇን ወደታች ሰደደችው፡፡ ዙሪያኑን ዳሰሰችው፡፡ ሆዷ ከፊት ባይገፋም ጎንና ጎኗ ደንደን ያለ መሰላት:: “እስካሁንም አለማስታወቁ ቁመት
ስላሰኝ ነው::” ብላ አሰበች፡
“ግን ትክክል ውሳኔ ነው ያደረኩት” ራሷን ጠየቀች

👍4
፡፡ “የራስሽ ጉዳይ እየነጎርኩሽ በገዛ እጅሽ
ያመጣሽው ነው ቢለኝስ?” ፊቷ ቅጭም አለ፡፡
''የፈለገውን ያህል ግድየለሽ ይሁን፤ ግን ጨካኝ እይደለም ናቲ፡፡ አይጨክንም በፍጹም ብትነግረው ነው የሚሻለው:: አውቃ እሱን ለማጥመድ እንዳደ ረገችው ማወቅ የለበትም፡፡ እሷ እራሷ እንደተደናገጠች እንደሆነች ሆና ነው መቅረብ ያለባት፡፡ ከቻለች ማልቀስ፡፡ አስወርጅው እንደሚላት በፊቱንም አውቃለች:: ይህን ያህል ጊዜ ደብቃ የቆየችውም ለዚህ ብላ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ምኑን ትደብቀዋለች? ውሎ አድሮ ራሱ እዚ ነው ያለሁት ማለቱ አይቀር፤ ያበጠው ይፈንዳ! እሺ ብለ
ከተቀበላትም ተመስገን፡፡ አንጋባም ልጃችንም ዲቃላ ይሁን ካለም.."
“አይልም! በፍጹም አይልም!” አለች ርብቃ ሳይታወቃት ጮሃ፡፡
የመኝታ ቤቱ በር ሲከፈት ደንግጣ ዞረች::
“ሳለነ ቅድስት!» ራቁቷን ሲያይዋት ፊታቸውን ወደኋላ መንጭቀው ተመለሱና የበረገዱትን . መዝጊያ ዘጉት ተመላላሽ ቤት አጽጅዋ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሁለት ቦታዎች ለመሄድ አቅዷል፡፡ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያና በመረጃው መስሪያ ቤት ወስጥ በጸረ ስሰሳ ክፍል ባልደረባ የሆነው ጓደኛው አብርሃም ጋ:: ትናንት ደውሎ ሲያነጋግረው አብርሃም እያቅማማ ነበር ቀጠሮውን የተቀበለው፡፡
"ግን እንጃ ብዙ ሃሣብ ልሰጥህ የምችል አይመስለኝም::” ብሎት ነበር አብርሃም ስለ ላይቤርያዊው አታሼ አንስቶ ናትናኤል ጫፍ ጫፉን ሲነካካለት፡፡
ቆይ! ቆይ አብርሃም ለማንኛውም እንገናኝና የምታውቀው ነገር ካለ ታካፍለኛለህ፡፡ ያም ካልሆነ ችግር የለም፡፡ እ! በነገራችን ላይ ለምን ምሳ አልጋብዝህም?
“ግን አንተ ለምንድነው በነገሩ የተሳብከው? አንድ የውጭ ዜጋ
ጠፋና የውጭ ጉዳይ ምን አገባው?”
“እንዴት? ምን ማለትህ ነው? ያገባዋል እንጂ፡፡ የውጭ ዜጋ ነው በዛም ላይ ዲፕሉማት፡፡”
“ገባኝ ገባኝ፡፡ ነገሩማ በቀጥታ ነው፡ የሚነካችሁ፡፡ ቢሆንም ሁኔታውን ፖሊስ እየተከታተለው ሳይሆን አይቀርም:: የእኛ መሥሪያ ቤትም ቢሆን መቼም እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም:: ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ አያዘናጋም ለማለት ነው:: ስለዚህ ችግሩን ለምን ለባለቤቶቸ
አትተውም? ናትናኤል፡፡ ለማለት የፈለግሁት አንተ የውጭ ጉዳይ ባልደረባ
እንጂ ወንጀል መርማሪ መኮንን አይደለህም ነው፡፡ ተግባባን?”

#የበረሐ_ገነት
ጥልቍ ዕፍኝ ዋሻ ፣ በቍጥቋጦ አብቦ
ዕርጥቡ ፣ ለምለሙ፤ የሚያሽት ተንቦ።
. . ስውር . .
...ጥምር . .
. . ዘብ ጠበቂ . . .
የመቅደስ ከለላ ፣
የዕልፍኝ እፍታ ፣
የመንፈስ እርካታ፣
የሐሤት ከፍታ።
የሐሩሩ ገነት ፣ ወበቅ የፍም ጭብጥ
ከነዲድ በረሐ ፣ በዕጥፍ የሚበልጥ
የተፈጥሮ ቅኔ . . .
ከመንገደኛ እግሮች ፣ ላዕላይ 'ሚቀመጥ።
በግለት መደሰት ፣ በእሳት መቀባት
የዋሻው፣ የጫካ ፤ የጋራነት ቅባት።
የተረት ፍጻሜ በዳቦ መታበስ
ዋሻውን ባ'ፈ ሙዝ ፣ በካፊያ ማረስረስ።
ኦና ቤትዋ ደርሶ ፣ በዕንጥሻ አስነጥሶ
ክልልን መማስ ነው ፤ ኬላ ድንበር ጥሶ።
እነሆ ከዋሻው .
ቆሞ እያስቀደሰ ፤
በዕንፋሎት ራሰ!
ከበረሓው ገነት በ'ሳቱ ተቀባ
የመንፈስን መባእ ከሙዳይ አስገባ።
ልክ እንደ መናፍስት በእሳት ተጠምቆ
ምንነት ለወጠ ፣ አብቦና ጸድቆ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
ጥልቍ ዕፍኝ ዋሻ ፣ በቍጥቋጦ አብቦ
ዕርጥቡ ፣ ለምለሙ፤ የሚያሽት ተንቦ።
. . ስውር . .
...ጥምር . .
. . ዘብ ጠበቂ . . .
የመቅደስ ከለላ ፣
የዕልፍኝ እፍታ ፣
የመንፈስ እርካታ፣
የሐሤት ከፍታ።
የሐሩሩ ገነት ፣ ወበቅ የፍም ጭብጥ
ከነዲድ በረሐ ፣ በዕጥፍ የሚበልጥ
የተፈጥሮ ቅኔ . . .
ከመንገደኛ እግሮች ፣ ላዕላይ 'ሚቀመጥ።
በግለት መደሰት ፣ በእሳት መቀባት
የዋሻው፣ የጫካ ፤ የጋራነት ቅባት።
የተረት ፍጻሜ በዳቦ መታበስ
ዋሻውን ባ'ፈ ሙዝ ፣ በካፊያ ማረስረስ።
ኦና ቤትዋ ደርሶ ፣ በዕንጥሻ አስነጥሶ
ክልልን መማስ ነው ፤ ኬላ ድንበር ጥሶ።
እነሆ ከዋሻው .
ቆሞ እያስቀደሰ ፤
በዕንፋሎት ራሰ!
ከበረሓው ገነት በ'ሳቱ ተቀባ
የመንፈስን መባእ ከሙዳይ አስገባ።
ልክ እንደ መናፍስት በእሳት ተጠምቆ
ምንነት ለወጠ ፣ አብቦና ጸድቆ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#አሜሪካን_ጉዞ
#በሕይወት_እምሻው
እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ፣ አሜሪካ ለመሄድ ሰ...ፍ ማለት
የጀመርኩት በልጅነቴ ለሚከተሉት ነገሮች በተከታታይ ተጋልጬ ስለነበር ነው።
1. 0ሥር ዓመት ሲሆነኝ የዕድሜ እኩያዬ ካሌብ ፣ “ባቡር መንገድ” ተሻግሮ ትልቅ ሕንጻ ከሚሠራበት ቦታ ፣ ትንሽ ስቶኮ ሰርቆና ደብቆ አመጣና ሁላችንንም ሰብስቦ ፣ “እዩ! የአሜሪካን ጭቃ!” አለን ከስንት ወረፋና ልመና በኋላ የአሜሪካ ጭቃውን፤ አስነካኝ ፡ :
ጣቶቹ በፍራሽ ላይ የሚዘሉ መሰለኝ ይደላል ይመቻል።
“የአሜሪካ ጭቃ ይሄ ነው?” አልኩት ፡ :
“አዎ... ዝናብ ሲዘንብ ጭቃቸው ይሄ ነው ... ደስ አይልም?” አh፤ : :
ሲቆይ የኔ እንዳይመስለኝ፤ ፈርቶ ነው መሰለኝ፤ ስቱኮው፣ እየነጠቀኝ ፡ :
''ጭቃው እንኳን እዲህ ያማር ሀገሩ ፣ ምንኛ ግሩም ነው?” ብዬ እያሰብኩና የሃገሬን ከአፈርና ውሃ የተሰራ ''ተራ" ጭቃ በእግሮቼ እያቦካሁ ወደ ቤቴ ዔድኩ ፡ :
2. በዐሥራ ሁለት ዓመቴ አብሮን የሚማረው የአጎኔ ልጅ ጋዲሳ ፣
አሜሪካ ለመሄድ “ፕሮሰስ”መጀመሩ እንደ ከባድ የሃገር ሚስጥር በእናቴ ፣ በእሱ እናት ፣ በአባቴና በእሱ አባት መካከል በሹክሹክታ ሲወራ ጓዳ ሆኜ ባጋጣሚ ሰማሁ : :
“ፕሮሰስ” ቃሏ ባትገባኝም ወሳኝ ነገር መሆኗ ገብቶኛ:
"ደሞ ለማንም እንዳታወሪ... ፕሮሰስ ለሰው ከተወራ ይበላሻል: : ” እናቴ
ናት ቀስ ብላ ያለችው : :
“አር እኔ ፤ ለማ፣ ምን፣ ብዬ አወራለሁ ...? በሚስጥር ያስጀመረችው
ድንግል በምስጢር ታሳካከት እንጂ...” የጋዲሳ እናት እትዬ ወላንሳ : :
“እናንተ፤ ናችሁ መቼም ወሬ አይጎዳም እያችሁ የምታዛመቱት! ዛሬ ሰው
ተንኮለኛ ነው ... አንድ ሰው አፍ ውስጥ ከገባ 'ለምን' ሆነለት ብሎ ለማፋርስ ሌተ ቀን የሚሰራ ብዙ ነው : : ዋ! ነገርኩ እንግዲህ! ይሄ ነገር ከዚች ቤት እንዳይወጣ!” አባቴ ነው : :
ሴቶቹን በቁጣ ሲያይ ኮሎኔል መንግስቱ መድረክ ላይ ቆመው ለሕዝብ ንግግር ሲያደርጉ እንደሚሆኑት ይሠራዋል : :
“ፕሮሰስ” ከባድ ነገር እንደሆነ የገባኝ ያኔ ነው : :
ከጥቂት ሳምንታት በኋካ ፤ እማዬ ፣ የእትዬ ወላንሳ የሴቶች ማኅበር
ድግስ ይዛኝ ሄደች : : ተጨማሪ ሰሃን አምጪ ተብዬ ኩሽና ገብቼ ስመለስና ያለ አቃሟ ትልልቅ ሶፈፋዎችና ሴቶች ይዛ የተጣበበችው ሳሎን በእልልታ በአንድ እግሯ ስትቆም አንድ ሆነ
“አቤት ድንግል ምን ይሳናታል? ድንግል ምን ይሳናታል!
“ ቸሩ መድኀኔአለም እኮ ይሰማል... እሱ ሰመሽ! ወላንሳዬ ፈጣሪ ሰማሽ!
በሚሉ ከዚህም ከዚያም በሚመጡ ዓረፍተ ነገሮች ታጅቦ ዕልልታው
ቀለጠ : :
“የጋዲሳ ፕሮሰስ ተሳካ!” ከሚለው የእትዬ ወላንሳና የእማዬ መረጃ የተሰጠ
ምላሽ ነበር : :
የልጅ የአሜሪካ “ፕሮሰስ” መጀመርና መሳካት ከእናት ፣ ከአክስት ፣ብሎም ለቀበሌው ሴቶች ሁኩ እንዲህ ያለ ደስታ እንዳመጣ ባየሁ ጊዜ ፤
“ወይኔ ይህቺ አሜሪካ ምን ዓይነት ግሩም ሀገር ናት? ያላያት ሁሉ ለሚያያት
ዕልል ለሚልባት ሀገር!” እያልኩና በትልቁ ተቆርሶ የተሰጠንን ድፎ ዳቦ እየገመጥኩ ወደ ቤት ተመለስን።
በሳምቱ ቡዔ ነበር : : የደራው ጭፈራ ግን እኛ ቤት ብቻ ነበር ተደጋግሞ የተሰማው ግጥም ደግሞ ይሄ
“እዛ ማዶ አንድ ጀሪካን ፣
እዚህ ማዶ አንድ ጀሪካን ፣
የኔማ ጋዲሳ ሊሄድ ነው አሜሪካን፣ : :
(በነገራኝ፣ ላይ ሀበሻ አሜሪካን ለምን፣ “አመሪካ” ብቻ ማለት እንደማይችል አይገባኝም : : “አሜሪካን ሀገር ለማለት ፣ “አሜሪካን ሀገር” እንላለ3 ፡ : ነው ወይስ እንዲህ ቡሄ ቡሄ ሲመጣ ስሟ ከጀሪካን ፣
ጋር ገጥሞ ሂያጅ ሀገር እየሰማ እንዲወደስባት ነው?
3. ጋዲሳ ወደ አሜሪካ የሚሔድበት ቀን ደረሰ : :
ቀኑ በብዙ ነገሮች የታጨቁ ቢሆንም በተለይ ትዝ የሚለኝ ግን የሚከተለው
ነው : :
ለወትሮው የት ገባህ? የት ወጣህ? የማይባለው ጋዲሳ ፤ለወትሮው ምን
በላህ? ምን፣ ጠጣህ? ተብሎ የማይጠየቀው ጋዲሳ ፤ ለወትሮው አስር
ጊዜ መታቀፍ ቀርቶ ፣ ዞር ተብሎ ታይቶ የማይታወቀው ጋዲሳ ፤ ልክ በድንገት እንደፀነሰች መሀን ሴት ፤ ልክ በምልጃና ምህላ እንደተገኙ የስለት ልጅ ፤ እንክብካቤ በዛበት ፡ :
“ጋዲሳ ሻወር አድርግ አሁን ፤ ... ሰዐት ደረሰ እኮ!” (ጉዞው ከምሽቱ አራት ተኩል ነው : : ይሄን የተባለውን ግን ከጠዋቱ አምስት ሰዐት ከሩብ ላይ : : )
“ጋዴ...! ለምን የዳግምን፣ ሰማያዊ ጃኬት አትወስደውም? ለብርዱ ይሆንሃል በዛ ላይ አዲስ ነው :የዛሬ ሁለት ዓመት ነው ፣ የቀኝ አዝማች ልጅ ትዕግስት ከእንግሊዝ የላከችለት... አንተ ዳግም! ዳግም!
ከጋዲ ያንን ጃኬት ስጠው!”
ዳግም እባ ቀረሽ ኩርፊያ አኩርፎ ፣ “እምቢ! ለምን እሱ አሜሪካ ሊሄድ ነው
... እኔ ምን አለኝ?” ሲል እናቴ ተቆጥታ ፣
“ያን የመሰለ ጃኬት አንተ የት ትለብሰዋለህ? እሱ ለብሶት ቢሄድ ምን አለበት? ብላው ፣ፍቃዱን ሳትጠይቅ ከቁምሳጥን አውጥታ ሰጠችበት ፡ :
“ጋዲሳ... የአውሮፕላን ምግብ ጥሩ አይደለም ሲሉ እሰማለሁ... እራትህን፣
በደንብ ብላ... ሰዐቱ እኮ ደረሰ!” ይህን የተባለው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዐት ተኩል
ላይ ነው : :
የጋዲሳ ዋጋ በአንድ ጊዜ እንዲህ ከፍ ሲል ቁጭ ብዬ አየሁ።
ጋዲሳ ተከበር : : ጋዲሳ ተወደደ: : አሜሪካ ስለሚሄድ ወርቅ እንቁላል
እንደምትጥል ዶሮ እንክብካቤ በዛበት : :
ወደ ዐሥር ሰዐት ገደማ ፣ ጋዲሳ እንደ ታቦት እየረገዱ ከከበቡት ሰዎች መሀል
ብድግ አለና ፣"በቃ እላይ ሰፈር ሄጄ እነቱቱን ቻው ልበላቸው"ሲል
“በቃ እላይ ሰፈር ሄጄ ራሴን ልግደል " ያለ ይመስል ሁሉም ሰው በአንድነት ክው አለ።
እትዬ ወላንሳ እየሮጠች አጠገቡ ሄደችና “አንተ ልጅ ምን ሆነሃል? መናገደኛ ሆነህ በዛሬ ቀን ከቤት ልትወጣ? ሊያውም ትንሽ ሰዐት ሲቀርህ? ” ስትከው ሁሉም ሰው ፤ “አዎ ... በዛሬ ቀን ባትቀዥቀዥ ጥሩ ነው! ”
“አርፈህ ተቀመጥ!”
“ሆ .…. አንድ ነገር ብትሆንስ? ” በማለት አገዟት ፡ :
ከፖሮሰሱ በፊት ጋዲሳ ከሰፈር ጅብ ጋር እየተጋፋ ሌሊት ስምንት ሰዐት ሲገባ አስታውሳለሁ : :
በቡድን የሰፈር ጠብ ውስጥ ፊታውራሪ ሆኖ በየቦታው እየተፈነካከተ ሲመጣ
ዕይቻhሁ : :
ጠጥቶ በየቱቦው ሲወድቅም ተመልክቻhሁ : :
ያኔ ፣ “አንድ ነገር እንዳትሆን.. ቶሎ ግባ... ተጠንቀቅ!” ያለው ሰው አልነበረም።
ነገሩ ገባኝ : :
ጋዲሳ በዛሬ ቀን እንዳይወጣ የተፈለገው ወጥቶ አንድ ነገር እንዳይሆን ወይ እንዳይሞት ሳይሆን ፤ አንድ ነገር ሆኖ ፣ ወይ ሞቶ ከአሜሪካ እንዳይቀር ነበር : :
ልድገመው : :

ስለዚህ የስንት ዘመን ባልንጀሮቹን እነ ቱቱን ሳይሰናበት ቀረ።
እንደ ዓመት በዓል ሲጠበቅ የነበረው የመሄጃ ሰአት ሲደርስና እቃው ሲመዘን ከሚፈቀደው በላይ ሆነ በሚል ትንሽ ግርግር ከተፈጠረ በኋካ ፣ ጎረቤታች፣ ጋሽ አስራት በሚነዳት ላዳ ታክሲ ወደ ቦሌ ለመሄድ ገባ ፡ ከመኪናዋ ውጪ በጠባቧ ግቢ ውስጥ የሚራኮተው ሰው ሁሉ ዐይን አርፎበታል : : ጋዲሳ ፣ በከፊል በተከፈተው የታክሲዎ የመስኮት መስታወት ሁሉንም እንባ ባቀረረ ዐይኖቹ ያያል : :
ይህን ጊዜ ነው የዲሳ ጓዝ ከመጠን በላይ እንደ ከበደ የገባኝ ፡፡ : ትከሻው ላይ የእናቱን ተስፋ ፣ የአክስቱን አደራ ፤ የእኛን 'ወጥተህ አውጣን” ምኞት

👍1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
...አንተ የውጭ ጉዳይ ባልደረባ
እንጂ ወንጀል መርማሪ መኮንን አይደለህም ነው፡፡ ተግባባን?”
አብርሃም እኔ በሰውየው ላይ የተለየ አትኩሮት ኖሮኝ አይደለም::ጉዳዩ በተዘዋዋሪ ከምሠራው ሥራ ጋር ዝምድና አለው ብዬ በማሰብ ብቻ ነወ:: እንዴት አድርጌ ላስረዳህ አየህ ብንገናኝ እኮ
“ጥሩ! ጥሩ!” አሰ አብርሃም ተስፋ በመቁረጥ:: ለማንኛውም ተገናኝተን እንነጋገራለን፡፡”
“ስንት ሰዓት? የት?” ጠየቀ ናትናኤል፡፡
“እሁድ አይደል ነገ? ሙሉ ቀን ነፃ ነኝ።
"ደህና በስድስት ተኩል ላይ ኢትዮጵያ ሆቴል!”
“አ! አ!” ድንገት አብርሃም ቀዝቀዝ አለ ናትናኤል አንዳችን ቤት ብንገናኝ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ባይሆን በኋላ የት እንደምንሄድ እንወስናለን፡፡”
“ግሩም... መጀመሪያ ለዚያ ጉዳይ ስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ሄጄ ሲሰጠኝ የሚችሉትን ሃሳብ እሰበስባለሁ ብያለሁ:: ከዚያ በኋላ እንደጨረስኩ አራት ወይም አምስት ላይ አንተ ቤት መጥቼ አብረን እንወጣለን::”
“ጥሩ፡ እጠብቅሃለሁ፡፡” የአብርሃም አነጋገር የመስማማት ሳይሆን የመሸነፍ ስሜትን የተላበሰ ነበር፡፡
ናትናኤል ከአብርሃም ጋር ከመገናች በፊት ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ሊሰጡት ፈቃደኛ የሚሆኑትን ማንኛውንም መረጃ ለመሰብሰብ ወስኗል:: የገባ ያገለግላል፡፡
ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደሚያስገባው ጠባብ አስፋልት
መንገድ እጥፍ ሲል ከኋላው በተመሳሳይ ፍጥነት ትከተለው የነበረችው ጥቁር 504 ፔጆም ታጠፈች:: ከውስጥ ሁለት ሰዎች ተቀምጠዋል፡፡መሪውን የያዘው ሰው ኢትዮጵያዊ አለመሆኑ መልኩን በማየት በቀላሉ ለማወቅ ይቻላል፡፡ ከሰሃራ በታች ከሚገኙት ጥቁር አፍሪካ አገሮች
ከአንደኛው የመጣ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ መልኩ በጣም ጠቆር ያለ፤አፍንጫው ደፍጣጣና ወፋፍራም ከናፍር አሉት፡፡ የደረበውን ፀጉራም ካፖርት አንገትዬ ወደ ላይ ቀልብሶታል።አይኖቹ ክፉኛ ደፍርሰዎል፡፡ ሌሊቱን በቂ እንቅልፍ ያገኘ አይመስልም፡፡ ሆኖም ቅልጥፍናና እርጋታ በተሞላው እንቅስቃሴ ከፊት ለፊቱ፡ የምትሄደውን ብርማ 131 ፊያት ይከታተላታል::መሪ ያየዘበት እጁ ከመሪው ጋር ወደ ግራ ሲንቀሳቀስ ጥቁር አረንጓዴ ንቅሳት ከእጅ አንጓው በላይ ብቅ አለ፣ የቀንዳም በሬ ምስል፡፡ መኪናዋ ወደ
ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታጠፈች፡፡
አጠገቡ የተቀመጠው ሰው ኢትዮጵያዊ ገጽታ ያለው ነው:: ጠየም ያለና ረዘም ብሎ ቀጠን፤ መጠጥ ያለ ሰውነት ያላው፡፡ ግራ ጉንጩ ከላይ ከዓይኑ ሥር ጀምሮ እስከታች ከንፈሩ ጫፍ የሚደርስ ኣስፈሪ ጠባሳ ተጋድሞበታል። ትናንሽ ዓይኖቹ ባሉበት ጉድጓድ ውስጥ ሆነው ትክ ብለው ሲመለከቱ ከወዲያ ወዲህ ውር ውር ሲሉ ፊቱን የጨካኝ ገጽታ ያላብሱታል፡፡
“እዚሁ ልቁም ወይስ ልለፈው ኮሎኔል?” አለ መሪ የያዘህ ሰው በፈረንሳይኛ፡፡
አልፈኸው ቁም!” አለ ከጎኑ የተቀመጠው ሰው በፈረሳይኛ ቋንቋ ይከታተላት የነበረችው 131 ፊያት ፊት ለፊት ካለው የፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ ስትቆም ሲያያ ፊቱ ላይ የተጋደመውን ጠባሳ ፈተግ አድርጎ፡፡ መኪናዋ እንደቆመች ከጎን ተቀምጦ የነበረው ሰው በሩን ከፍቶ ወረደ
መሪውን የያዘው ሰው ከተቀመጠበት ወንበር ሥር የተገጠመውን መገናኛ ሬዲዩ ተጫነው፡፡
“ሌ ዦሌ፣ ዦሌ.! ቆንጆዎቹ…! ቆንጆዎቹ….!” በፈረንሳይኛ መልዕክት ያስተላልፍ ጀመር፡፡
የስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሕንፃ ጥንታዊ መልክ ያለው ነው፡፡ ሰዓቱ ቢረፍድም የጠዋቱ ቅዝቃዜ ቦታውን ጭል ጭል ለምትለው ለጋ ጸሀይ ላለመልቀቅ የቆረጠ ይመስላል፡፡ ናትናኤል ወደ ግቢው የሚያስገባውን መዝጊያ አልፎ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡
"ወንድም?” አለችው አንድ ወጣት ሴት ዳሌዋን እየተጠጋችው።
ናትናኤል ዞር ብሎ ተመለከታት:: ጥፋት አጥፍታ ጣቢያ ያደረች መሆን አለባት ብሎ አሰበ፡፡
“ሴሽ ይዘሃል? ይቅርታ ሃርድ ሲስጡኝ ነው ያደሩት፡፡” አለችው አንገቷን ወደ ጣቢያው መታ አድርጋ፡፡ ፀጉሯ ግማሽ ጥቁር፣ ሌላው ቀይየቀረው ብርማ ተቀብቷል፡፡ ከአይኗ ላይ በተላጨችው ቅንድቧ ምትክ፣ በቀጭኑ የተሰመረው እርሳስ ክፋኛ ደብዝዞ ያለ ቅንድብ የተፈጠረች አስመስሏታል፡፡ ከገላዋ የሚነሳው ጠረን የምን እንደሆነ ለመረዳት ናትናኤል ተቸረገ፡፡ አለቅጥ ተጠግታው ስለቆመች በተቻለው ብዙ አየር ላለመሳብ ጣረ፡፡
“ይቅርታ በጠዋት ነጀስኩህ አይደል? ሴሽ ይዘሃል?” እጇን ወደፊት ዘርግታ ፈገግ ስትል የሚታዩት ጥርሶቿ ነጫጭ ናቸው፡፡
“ምን?” አለ የምትለው አልገባ ሲለው፡፡
እ...ማለቴ ሲጋራ አለህ?... ጡቶቿን ወደፊት ገፋ . .ዳሌዋን ነቅነቅ
አደረገችለት ይበልጥ ጠጋ ብላው፡፡
ናትናኤል ከደረት ኪሱ ውስጥ ሲጋራ ሲያወጣ ተሽቀዳድማ ከእጁ ላይ ቀማችውና ፓኮውን ጎን መታ መታ አድርጋ እንድ ሲጋራ አውጥታ አፏ ላይ ከሰካች በኋላ “አንድ ሀባ ልጨር?"አለችው በቀኝ አይኗ ጠቀስ አድርጋው።
“ውሰጅ::” አላት ናትናኤል ትዕግሥቱ እየተለጠጠበት፡፡
አንድ ጭማሪ አውጥታ ስታበቃ ሳትጋበዝ ቀልጠፍ ባለ ሁኔታ ኮቱን መለስ አደረገችና የሲጋራውን ፓኮ ከውስጥ በኩል ኪሱ ውስጥ ሸጎጥ አደረገችለት፡፡
“ብድር መሳሽ ያድርገኝ አለችው ፈገግ ብላ አንዳች ሕይወት አጥተው ስልምልም ባሉ ቅንድብ የለሽ አይኖቿ እያባበለች።
“ችግር የለም፡፡” አለ ናትናኤል አልፏት ለመሄድ እየሞከረ።"
“ካዛንችስ ሞቢሉጋ ስርጉት ቤት' ብቅ በል ቆንጆ ሌሊት እናሳልፋለን… አትጥፋ፡” አላችው በቆመችበት ትቷት ሲሄድ
ጀርባውን ቸብ አድርጋ፡፡
“ዘልዛላ ዘልዛላ ሸርሙጣ፡፡” አለ ናትናኤል በልቡ፡፡ ቢሆንም ዞር ብሎ አልተመለከታትም፡፡ ራመድ እያለ ወደ ጣቢያው ህንፃ አመራ፡፡
“እንደምን አደርክ” አለ ናትናኤል ፊቱን በፈገግታ አስውቦ ከጠረጴዛው ኋላ ተቀምጦ በቀኝ እጁ የስልክ እጀታ በግራው ደግሞ የመስክ መገናኛ ራዲዮ ይዞ ሥራ የበዛበት ለመምሰል የሚጥረውን ወጣት የፖሊስ መኮንን፡፡
መኮንኑ በተቻለው መጠን ፊቱን አኮሳትሮ በቀኝ የያዘውን የስልክ እጀታ ወደ ጎን ዞር አድርጎ “ምንድን ነበር?!” አለ እንደማመናጨቅ እየቃጣው፡፡
“ይቅርታ አድርግልኝ አቋረጥኩህ …እባክህ የጣቢያውን ኃላፊ ለማጋገር ፈልጌ ነበር፡፡” በተቻለው ትህትና ተላብሶ ለመቅረብ ሞከረ ናትናኤል፡፡
መኮንኑ በተሸላቸ ሁኔታ በአገጩ በስተቀኝ በኩል ወዳለ በር አመከተው፡፡
ናትናኤል በምሥጋና ራስን አነቃንቆ በስተቀኝ ያለውን በር ሁለቴ ካንኳኳ በኋላ መዝጊያውን ከፍቶ ገባ።
ናትናኤል በሩን ከፍቶ ወደውስጥ እንደገባ ከውጭ ከበሩ ቆም ብሎ ሁኔታውን ይከታተል የነበረ አንድ ሰው ወደ ወጣቱ መኮንን ጠጋ አለ፡፡
“ምንድን ነበር?” ወጣቱ መኮንዮ ያንኑ ቅጭም ያለ ፊቱን ቀና አድርጎ እንግዳውን ገረመመው፡፡
አንግድየው እጁን ወደ ደረት ኪሱ ከተተና አነስተኛ የመታወቂያ ወረቀት አውጥቶ ለአንድ አፍታ ብልጭ አደረገለትና . መልሶ ከኪሱ ከተተው፡፡
“አቤት ጌታዬ!?” አለ ወጣቱ መኮንን በቀኝና በግራው የያዘውን የስልክ እጀታና መገናኛ ሬዲዮኑን በጥድፊያ ፡ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ ከወንበሩ እየተነሳ፡፡
ቁጭ በል እንግዳው የተለየ እርጋታ ይታይበታል፡፡ ፊቱ ላይ ከተጋደመው ጠባሳ ጋር ሲታይ ከእንጨት ተፈልፍሎ የወጣ እንጂ ከደምና ከስጋ የተፈጠረ አይመስልም:: “ምንድን ነው የጠየቀህ?”
"ማን ጌታዬ” ወጣቱ መኮንን ቀተቀመጠበት እጆቹን በተጠንቀቅ
ከጎንና ከጎን ለጥፎ ከፊቱ ያጎነበሰውን እንግዳ ሽቅብ እየተመለኩ ጠየቀ፡፡
እንግዳው ጭንቅላቱን በስተቀኝ ወዳለው
በር መታ አድርጎ አመለከተው::
“አሁን የገባውን ሰው ነው ጌታዬ?”
“ቀስ ብለህ ተናገር!”

እንግዳው ጥርሱን ገጥሞ ነው የሚናገረው፡፡
የጣቢያውን ኣዛዥ ነው የፈለገው ጌታዬ::”
መኮንኑ እንደተቆጡት ህፃን ጉንጮቹን ተንጠለጠሉ፡፡
እንግድየው ምንም መልስ ሳይሰጠው ፊቱን ወደ ግራ መልሶ ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን የአዲስ አበባን ከተማ ካርታ ያጠና ጀመር፡፡
ናትናኤል ወደ እዛዡ ቢሮ እንደገባ በሩን ዘግቶ ቆመ:: ከጠረጴዛው ኋላ የተቀመጠው ሲቪል የለበሰው ሰው ግን ካቀረቀረበት ቀና አላለም
እህህህ... ጉሮሮውን አፀዳ ናትናኤል፡፡ ሰውየው ለአንድ አፍታ ቀና ብሎ ካየው
በኋላ በግራ እጁ አንድ ወንበር አመለከተውና እንደገና አቀረቀረ፡፡
ናትናኤል በፀጥታ ወደፊት ፡ ተራመደና ኣዛዡ ባመለክተው የእንጨት ወንበር ተቀምጦ በትዕግት መጠባበቅ ያዘ፡፡ የአዛዡ ቢሮ ይቀዘቅዛል፡፡ በጠባብ መስኮት የሚገባው እነስተኛ ብርሃን ሙቀት ለትንሿ ክፍል ህይወት መስጠት የሚበቃ አይመስልም፡፡
የጣቢዋው አዛዥ የጠረጴዛ መሳቢያውን ስቦ ከውስጥ ዕቃ እንደሚፈልግ አይነት ሲጎረጉር “ምን ልርዳህ?” አለ ድንገት ቀና ብሎ ይዞት የነበረውን ብዕር ጠረጴዛ ላይ ጣል እያረግ፡፡
“እ.. ” ናትናኤል እንዴት መጀመር እንዳለበት ግራ ተጋባ፡፡ የደረት
ኪሱ ውስጥ ገባና የገንዘብ ቦርሳውን አወጣ፡፡ ከውስጥ የመሥሪያ ቤቱን
መታወቂያ ወረቀት አውጥቶ ለሰውየው ዘረጋለት:: ሰውየው በቸልታ መታወቂያ ወረቀቱን ተቀብሎ ከተመለከተች በኋላ መልሶ ከጠረጴዛው ላይ ወርወር አደረገለት፡፡ ናትናኤል ቀልጠፍ ብሎ ጀመረ፡፡
“እ…. ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እ..ባለፈው ሰሞን አንድ የውጭ ዜጋ ለጊዜው ተሰውሮ ነበር፡፡ በጊዜው መኪናውን በቆመችበት ያገኟት የዚህ ጣቢያ አባላት ነበሩ፡፡ እና የምትችሉ ከሆነ አንድአንድ ሃሳብ እንድትሰጡኝ ነበር፡፡”
“በጉዳዩ ላይ በውቅቱ ተገቢውን ዘገባ ያቀረብን መስለኝ፡፡”አለ የጣቢያው አዛዥ ቀዝቀዝ ብሎ፡፡
“እ.. ይሆናል! ይሆናል! ግን ሳስቸግርህና እንደው ስለሰውየው ማንኛውንም ዓይነት ሃሳብ ባገኝ መኪናው የተገኘችው መጠጥ ቤቶች በብዛት በሚገኙበት አካባቢ ነበር…ማለቴ ከዚህ ቀደም ሰውየው ወደዚሁ ቦታ ይመጣ እንደሆነ።”
“ወንጀል አልተፈጸመም።” የጣቢያው ኃላፊ ድንገት አቋረጠው መኪናዋ በእኛ ክልል መገኘቷ ግልፅ ነው፡፡ ያንን ደግሞ ወዲያውኑ ለተገቢው አካል አስተሳልፈናል፡፡ ከዚህ ውጪ ምንም የምናውቀው ነገር የለም::”
“ምን መሰለህ…." ናትናኤል ተስፋ ሳይቆርጥ ሁኔታውን ለማስረዳት
ጀመረ፡፡
“ይቅርታ ወንድም!” ድጋሚ አቋረጠው የጣቢያው ኃላፊ ከመቀመጫው እየተነሳ “ምንም ልሰጥህ የምችለው ሃሣብ የለም፡፡”
ናትናኤል ተስፋ ቆረጠ፡፡ ሰውየው ሊረዳው ፈቃደኛ አይደለም::ከዚህ በኋላ አጥብቆ መጨቅጨቅ ምንም የሚጨምረው ነገር አይኖርም፡፡
“አመሰግናለሁ፡፡ ይቅርታ የሥራ ሰዓትህን ስለተሻማሁ፡፡” ንዴቱን ውጦ የአዛዡን ደረቅ እጅ ጨብጦ ከቢሮው ወጣ፡፡
ናትናኤል ከአዛዡ ቢሮ እንደወጣ ከውጭኛው ክፍል ግድግዳ ላይ
የተለጠፈውን የአዲስ አበባ ካርታ ያጠና የነበረው ዕው ቀልጠፍ ባለ ሁኔታ
የአዛዡን ቢሮ በር ከፍቶ ገባ፡፡ ለአንድ አፍታ ከእዛዡ ጋር ተያዩ፡፡ .
የጣቢያው አዛዥ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ፡፡
“ቆንጆዎቹ፡፡” አለ ፊቱ ላይ ጠባሳ ያለው ሰው እንደ ቆርቆሮ በሚንኳኳ ድምፁ፡፡
አዛዡ ኮተሳበው ጠረጴዛ ኪስ ውስጥ የተቀመጠውን ክር የጎረሰውን አነስተኛ የድምጽ መቅጃ መሣሪያ አውቶ አቀበለው። እንግዳው ሰው በጭንቅላቱ ሠላምታ ሰጥቶ ፈጠን ብሎ ወጣ።
ናትናኤል ከአዛዡ ቢሮ ሲወጣ ተበሳጭቶ ነበር። የጣቢያው አዛዥ በበበጎ አመለካከት ሊረዳው አልተቻለውም:: ሁኔታውን በረጋ መንፈስ አስረድቶት ሊረዳው አለመቻሉን ሊነግረው ሲችል እንዲያ እንደ ጠላት በጥርጣሬና በጥላቻ ለምን እንደተመለከተው ሊገባው አልቻለም፡፡ «ደደብ» እለ ንድድ ብሎት፡፡
ክሕንጻው እንደ ወጣ ዝናብ ብን ብን እያለ መውረድ ስለጀመረ ቀልጠፍ ብሎ ወደ መኪናው አመራ፡፡
"ሄይ" መኪናው'ጋ ደርሶ በሩን ሊከፍት ሲል ከኋላው ሲጠራ ተሰማው፡፡ ፊቱን ሲያዞር አያት፡፡ ወደ ጣቢያው ሲገባ ሲጋራ የጠየቀችው ሴት እየውተረገረገች ስትመጣ ተመለከተ፡፡ “ወደ ፒያሳ ነው የምትሄደው? ወደዛ ከሆን የምትሄደው.…?”
አይደለም! ወደዛ አይደለም ይቅርታ፡፡” ናትናኤል ቀልጠፍ ብሉ የመኪናውን በር ከፍቶ ገባና በሩን ሊዘጋ ሲል ተሽቀዳድማ ግራ ትከሻውን ያዝ እድርጋ ተጠጋችው፡፡ :
“ላስቸግርህና የኔ ጌታ ሌላ ሲጋራ ትሰጠኝ?” እነዛኑ ቅንድብ የለሽ
አይኖቿን አስለመለመችለት፡፡ የዝናቡ ማካፋት የተሰማት አትመስልም፡፡.....

#አልተወለድኩም
ወለድኩሽ ብለሽ ከሆነ
ተገላገልኩሽ አምጬ
አትሳሳቺ ሀሰት ነው
ዛሬም ጭንቅሽ ነኝ እንደገና
በህሊናሽ ውስጥ ተቀምጬ
ምንም ብከፈል ከአብራክሽ
በተፈጥሮ ህግ ተገድጄ
እናቴ ምጥ አያበቃም
ተገልፆልኛል ልጅ ወልጄ
ወለድኩሽ ብለሽ ስትይኝ
የምቀበልሽ ካንጀቴ
ስለ እኔ መኖር ስትተይ ---- ስትጨክኚ ነው እናቴ
እንዲያ ደግሞ እንደማይሆን
እንደሌለ ማረፍ ወልዶ
በተግባር አረጋገጥኩት
ከወለድኩ ዓመታት አልፈው
በልጆቼ ምጥ ጭንቄ ከብዶ
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ🔘
ወለድኩሽ ብለሽ ከሆነ
ተገላገልኩሽ አምጬ
አትሳሳቺ ሀሰት ነው
ዛሬም ጭንቅሽ ነኝ እንደገና
በህሊናሽ ውስጥ ተቀምጬ
ምንም ብከፈል ከአብራክሽ
በተፈጥሮ ህግ ተገድጄ
እናቴ ምጥ አያበቃም
ተገልፆልኛል ልጅ ወልጄ
ወለድኩሽ ብለሽ ስትይኝ
የምቀበልሽ ካንጀቴ
ስለ እኔ መኖር ስትተይ ---- ስትጨክኚ ነው እናቴ
እንዲያ ደግሞ እንደማይሆን
እንደሌለ ማረፍ ወልዶ
በተግባር አረጋገጥኩት
ከወለድኩ ዓመታት አልፈው
በልጆቼ ምጥ ጭንቄ ከብዶ
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ🔘
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
ግንቦት 12 ፣ ከለሊቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ
ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ
ብሬንትውድ ፥ ሎስ አንጀለስ ውስጥ
ሎስ አንጀለስ ውስጥ ግንቦት ላይ ሲዘንብ አላስታውስም። አሁን ላይ ግን
በስሱ የሚዘንበው የግንቦት ዝናብ ክንዴ ላይ እየተንከባለለ ሲወርድ ገረመኝ::
ምናልባትም ይሄ በህይወቴ ለመጨረሻ ጊዜ የምገረመው ግርምት ይሆናል፡፡
ደግሞ ቢገርመኝስ? በዚያ ላይ ደግሞ እኔ ከአሁን በኋላ ድንገተኛ ነገርን
ማስተናገድ አልችልም። እንዲያውም ትንግርት የሚባል ነገር ያስጠላኛል፡፡
የቤቴ ጀርባው ለሽ ያለ ሳር የበቀለበት መሬት ሲሆን፣ የቆምኩት ደግሞ ባለፈው ፀደይ ባለቤቴ በአደጋ ከመሞቱ ከወር በፊት በተከለው የሞንጕል ዛፍ አጠገብ ነው። ባለቤቴ የሞተው በአደጋ ነው የሚለውን ነገር ማሰብ ማቆም አለብኝ፡፡ ለምን? ካላችሁኝ ደግሞ ባለቤቴ የሞተው ቀኑ ስለደረሰ ነው ብዬ ስለማላምን ነው። በ405ኛ ጎዳና ምሽት ላይ በጣም የሚወደውን 'ቴስላ' መኪናውን ሲያሽከረክር ነበር እንግዲህ መኪናው ሙሉ በሙሉ ነድዳ እሱም ከነህይወቱ ተቃጥሎ የሞተው። ይሄ ደግሞ ለእኔ ህይወት መዘበራረቅ የመጀመሪያው መጥፎ መነሻ ነበር። ከዚያ በኋላ ነበር እንግዲህ ብዙ ነገሮችን ማወቅ የጀመርኩት፡፡
በእጄ የጨበጥኩት 9 ሚ.ሜ ሉገር ሽጉጤ ልክ የመጫወቻ ሽጉጥ፣
ትንሽ እና ምንም ጉዳት የማያደርስ ይመስላል። የሆነ የጆሮ ጉትቻ ወይንም
የሀር የአንገት ልብስ እንደሸጠልኝ አይነት ሽጉጥ የሸጠልኝ ሰው “ ይህቺ ሽጉጥ ለሴት የተሰራች እና የምትመች ቆንጆ ሽጉጥ ናት” ነበር ያለኝ። ባለቤቴ ደግሞ በመኪና አደጋ ተቃጥሎ ከሞተ በኋላ የሆነ ቀን ላይ ብዙ የእንቅልፍ ክኒኒዎችን በመዋጥ ራሴን የማጥፋት ሙከራ አድርጌያለሁ። ያ የመጀመሪያ ራሴን የማጥፋት ሙከራዬ ግን አልተሳካልኝም ነበር። የፅዳት ሰራተኛዬ ሪታ ደርሳ ለፖሊስ በመደወል ሆስፒታል ተወስጄ ህይወቴ
ሊተርፍ ችሏል፡፡ አሁን ግን ይህቺ የመጫወቻ ሽጉጥ የምትመስለው ትንሿ
ሽጉጤ በደንብ አድርጋ ስራዋን እንደምትሰራ እና ነፍሴን ከስጋዬ
እንደምትነጥለው እተማመናለሁ።
ምንም እንኳን ሥራዬ ሳይኮሎጂስት በመሆኑ የተነሳ ሞትን የሚፈሩ ቆጥሬ የማልጨርሳቸው ታካሚዎቼን በየጊዜው ብመለከትም ቅሉ እኔ በግሌ ሞትን አልፈራም፡፡ ሞትን የማስበው የሆነ የማይታይ እና የሰዎችን እዕምሮ
እንደሚቆጣጠር ጉልበተኛ ነገር ነው:: አሁን ላደርገው ያቀድኩት ነገር ደግሞ
ይህን ጉልበተኛ ነገር በራሴ መንገድ መቆጣጠር ነው። በራስህ መንገድ ይህቺን ዓለም ተሰናብቶ መሄድን የመሰለ ድልቅቅ ያለ አሟሟት አለ?
ይህንን የመሰለ የደልቃቃ አሟሟትን ደግሞ ማንም ዕድለኛ ያልሆነ ሰው
ሊሞተው አይችልም፡፡ በእኔ የተነሳ ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በተለይ ዛሬ ማታ ደግሞ አንድ ተጨማሪ የዋህ እና ጨዋ የሆነ፣ ለእኔ ደንታ ያለው እና የሚያስብልኝ፣ እኔም የማስብለት ሰው በእኔ ምክንያት ሊሞት ችሏል።
በዚህ አይነት በእኔ የተነሳ በየጊዜው ሰዎች ለእኔ መሞታቸው መቀጠል
የለበትም። ስለሆነም እኔው እራሴ በእኔ ምክንያት ሰዎች እንዳይሞቱ ራሴን
በማጥፋት እራሴ አስቆመዋለሁ።
ዝናቡ በጣም መዝነቡን ቀጥሏል። በዝናቡ የራሰው እና ሽጉጡን የጨበትኩበት እጄም እንዳያንሸራትተው እና ሽጉጡን አጥብቄ ለመያዝ
እንዲመቸኝም እጄን በለበስኩት ጅንስ ሱሪ ላይ ጠረግኩት። አሁን ምንም
አይነት ስህተት መፈፀም አይኖርብኝም። የሽጉጤን አፈሙዝ አገጩ ስር
ደቀንኩት እና ዞር ብዬ እኔና ዶውግ አብረን የገነባነውን ቤት ተመለከትኩት።
ነጭ ቀለም በተቀባው እና በምስራቃዊው ስቴት የሰራነው ቤታችን ዋናው የመኝታ ክፍል ባልኮኒ አለው። ፊቱንም ወደ ውቅያኖስ ያዞረ ስለሆነ ደስ የሚል ዕይታን እያየን ፍቅራችንን የምንቀጭበት ክፍላችን ነበር። ይገርማል አሁን በመጥፎ ህልም ውስጥ በምዳክርበት ጊዜ ሳይሆን ያኔ ከእሱ ጋር በነበርኩበት እና ጥሩ ህልም ስናስብ በነበርንበት ጊዜ ላይ ነበር እንግዲህ ይህንን ቤታችንን ያሰራነው። አይኔን ጨፍኜም የእነዚህን ሰዎች ፊት አንድ በአንድ በውስጤ መመልከት ጀመርኩኝ፡፡
በጣም የምወዳቸውን ዶውግ እና አኔ ልወዳቸው ከሚገባኝ ሉው ጋር አብረን እንዝለቅ ወይም አንዝለቅ እርግጠኛ አይደለሁም። በህይወቴ የማይገኙት እና የተውኳቸው፦ ሊዛ፣ ትሬይ፣ ዴሪክ ስለሞታችሁ እጅግ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ይቅርታችሁን እሻለሁ። የመጨረሻው ሀሳቤ ደግሞ እጅግ በጣም ስለምጠላው ሰው ነበር። ማን እንደሆንክ ደግሞ ታውቀዋለህ። ዘላለም በሲኦል እሳት ተጠበስ!
የምሰራው ነገር ትክክል እንዳልሆነ ይሰማኛል። ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡
ከዚህ የተሻለ ስሜቴን የማክምበት መንገድ ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር።
ለማንኛውም ምኞት አንድም ቀን ቢሆን የተበላሸ ነገርን አስተካክሎ አያውቅም እና አማራጭ የለኝም፡፡
#ቻርሎቲ
#ከአስር_አመት_በፊት
ቻርሎቴ ክላንሲ ሞቃታማው የበጋ ነፋስ ገላዋን ሲዳስሰው የሆነ ደስ የሚል ሸንቋጭ የደስታ ስሜት ተሰማት፡ የዚህ ስሜቷ አንደኛው ክፍል ሰውነቷ የወሲብ እርካታን በማግኘቱ የመጣ ነው። ሌላኛው ደግሞ ያልተለመደ እና አደገኛ የሆነ ነገር ውስጥ በመስመጧ ምክንያት የመጣ
ነው።
ቻርሎቴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በሳንዲያጎ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ስትማር ጨዋ እና ሁሌም ከክፍሏ አንደኛ የምትወጣ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበረች። ምናልባትም በት/ቤት ቆይታዋ ጊዜ ሰራች የተባለው ጥፋት ለጓደኛዋ ስለ ጥንታዊቷ ሜክሲኮ ታሪክ የጥናት ወረቀት መስራቷ ብቻ ነበር። ቻርሎቴ ለሀገረ ሜክሲኮ ልዩ ፍቅር አላት። ስለሆነም የሜክሲኮን
ታሪክ፣ ቋንቋቸውን እና ምግባቸውን ጨምራ ትወዳለች፡፡ ለሀገረ ሜክሲኮ
ባላት ፍቅር የተነሳም ነበር እንግዲህ ቤተሰቧን ጎትጉታ በማሳመን ትምህርት
ቤት ሲዘጋ ክረምቱን ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ መስራት የጀመረችው።
ያኔ ለክረምት ወደ ሜክሲኮ ለመሄድ አባቷን ስትጠይቅ “እኔ ደስ አላለኝም ቻርሊ።” አላትና ኮስተር ብሎ ትንሽ አሰበ፡፡ አባቷ ተከር ክላንሲ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኛና የኢጲስቆጶሳል ቤ/ክርስትያን ዲያቆን ነው። ፊቱን እና ሁኔታውን በማየት እሱ ምን ያህል የቤተሰብ ሰው እና ጥሩ አባት እንደሆነ ማንም ማወቅ ይችላል፡፡ ከአፍታ በኋላ በማስከተል “ግን እኮ እዚያ ሀገር ሰዎች ይታገታሉ፡፡ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ቡድኖችም እርስ በእርስ ሲጠፉፉ ነው የሚታዩት፡፡ መቼስ ሜክሲኮ ውስጥ አንገት ቀልቶ ሰዎችን የመግደል ነገርን ሳትሰሚው አትቀሪም፡፡ ብቻ እኔ ደስ አላለኝም!” አላት እና ዝም አለ።
“ልክ ነህ አባዬ” ብላ ቻርሎቴ በመቀጠል “ግን እኮ ከላይ የዘረዘርካቸው ወንጀሎች በመላው ሀገረ ሜክሲኮ ውስጥ አይፈፀምም፡፡ እኔ ወደምሄድበት
ቦታ ደግሞ እነዚህ አይነት ነገሮች የሉም። የምሄደው ኤልሳቫዶር ወይም ደግሞ ወደ ኮሎምቢያ ቢሆን ኖሮ ችግር ሊኖረው ይችል ነበረ። በዚህ ላይ ደግሞ እኔን የሚወስደኝ የአሜሪካን ኤዩ ፔየርስ ኢንተርናሽናል ኤጀንሲ (AAP) በጣም የሚገርሙ የሠራተኛውን ደህንነትን የሚያስጠብቁ ነገሮችን ነው የሚያደርገው፡፡ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት በሠራተኞቹ ላይ አንድም
አደጋ ደርሶባቸው አያውቅም::” ብላ መለሰችለት።
ተከር ክላንሲ ልጁ እሱን ለማሳመን የምታወራውን ነገር በእሷ ኩራት
እየተሰማው ነበር ያደመጣት፡፡ ልጁ ቻርሊ አንድን ነገር በግማሽ ብቻ አይደለም የምትሞግተው። ሁልጊዜም ቢሆን እሷ ሁሉንም እውነታዎችን እና አሀዞችን ጭምር አጥንታ ከጨረሰች እና በደንብ ከተገነዘበች በኋላ ነው ውሳኔዎችን የምትወስነው፡፡

👍9🔥1
በተጨማሪም ልጁ ቻርሊ
ስሜት ያላት ስለሆነችም ለእሷ መጠንቀቄ ግድ ነው ብሎ ያምናል፡፡
ብቻ በመጨረሻ እናቷ ሜሪ ነበረች በአባት እና ልጅ መሀል ገብታ የቻርሊን ወደ ሜክሲኮ መሄድን የደገፈችው፡፡ በዚህ መልኩ ነበር “ሆዴ እኔም እኮ ትንሽ ፈርቻለሁ!” ብላ ባሏ ተከርን እራታቸውን እየበሉ ባሉበት አንድ ምሽት ላይ አወራችው፡፡ በመቀጠልም “እኛ ስለፈራን ብቻ ልጃችንን ማስቀረት አይኖርብንም፡፡ በሚቀጥለው አመት ኮሌጅ መግባቷ አይቀርም አይደል? ያኔ እራሷ አይደለች እንዴ ውሳኔዎችን የምትወስነው? እና ይህንን ነፃ ሆና የወሰነችበት ነገር አሁን ክረምት ላይ እንድታደርግ መፍቀድ
ይኖርብናል።” ስትለው፡-
“እንዴ የኮሌጅ ትምህርቷን የምትማረው እኮ ኦሀዩ ውስጥ ነው” አለና አባቷ ተከር በማስቀጠልም “ኦሀዩ ውስጥ ደግሞ የሰዎችን አንገት እየቆረጡ ግድያ አይፈፅሙም” አላቸው:: ሜሪም ትንሽ ኮስተር አለችና “እንግዲህ ቻርሎቴ ስታወራ እንደሰማሁት ከሆነ ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥም ቢሆን ሰዎች አንገታቸው እየተቀነጠሰ እንደማይገደሉ አውቃለሁ። ይህንን ደግሞ ከኤጀንሲው አንዲት ሴት
አረጋግጫለሁ። ልጃችን ቻርሊ ደግሞ ተመድባ የምትሰራበት ቤት ባለቤቶች
ጠበቃዎች ሲሆኑ ኑሯቸውም በቅንጦት የተሞላ እንደሆነ ታውቋል። እባክህ
ውዴ ተከር ይህቺ ልጅ እስቲ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ፈታ ብላ ትኑርበት” ብላ
ነበር ባልዋን ያሳመነችው።
ከላይ ያለው እሷ ከቤተሰቧ ጋር ያደረገችው ውይይት የተካሄደው እንግዲህ ከሶስት ወራት በፊት ነበር፡፡ እነሆ ሜክሲኮ ከመጣች ሁለት ወራት
አለፉ፡፡ በእነዚህ ሁለት ወራት ታዲያ በጣም ብዙ ነገሮችን አድርጋለች።
በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀሺሽ አጭሳለች፤ ለመጀመሪያ ጊዜ መጠጥ
ጠጥታ ሰክራለች፤ በፍቅረኛዋ ቶድ ላይም ለመጀመሪያ ጊዜ ማግጣለች።
(ለዚያውም ትዳር ካለው ሰው ጋርም ፍቅር ይዟታል)።
በእርግጥም በፍቅር የወደቀችው ከእንክሪቶ ቤተሰብ አባወራ ጋር
አይደለም፡፡ እንዴ ይህንንማ ካደረገች ርካሽ ሆነች ማለት ነው። በዚያ ላይ
ደግሞ ሚስቱን ሲኞራ ኢንክሪቶን በጣም ስለምትወዳት እና ስለምታስብላት
ይህን ማድረግ የምትችልበት አንጀት አይኖራትም፡፡ ታዲያ ይሄም ሲባል ቻርሎቴ የምታደርገው ነገር ትክክል እንደሆነ አምናበታለች ማለትም አይደለም፡፡ አዎን ከባለትዳር ጋር መቅበጥ የመጥፎም መጥፎ ነገር እንደሆነ ድብን አድርጋ ታውቃለች። በጣም የቤተክርስቲያን ሰዎች ከሆኑት ወላጆቿ ቤት ማደጓ ደግሞ የምትሰራው ሥራ ጥፋት እና ሀጢአት መሆኑንም ታምናለች። ቤተሰቧ በወሲብ ዙሪያ ላይ ካለው ሞራል አንፃርም የጥፋተኝነት ስሜት በደምብ ይሰማታል፡፡ እነዚህ ሁሉ የሥርዓት እና የሞራል ነገሮች
ታዲያ ይህ ያፈቀረችው ባለትዳር ሰው አጠገቧ ሲሆን ምንም መስለው አይሰሟትም። ወላ ፍርሀቷ፣ የጥፋተኝነት ስሜቷ፣ ጥንቃቄዎቿ እና የሞራል ዋጋዎቿ ሁሉ ብርር ብለው በአዕምሮዋ መስኮት ሾልከው ይጠፋሉ። በተለይ ደግሞ አልጋ ላይ የሚያደርጋቸው ነገሮች የፈጣሪ ያለህ
በፍፁም ፍንደቃ እና ጥልቅ ስሜት እንድትጥለቀለቅ ያደርጋታል፡፡ ከጓደኛዋ
ቶድ ጋር ከመቶ ጊዜ በላይ ወሲብ የፈፀመች ብትሆንም ከዚህ ሰው ጋር ግን
የምትፈፅመው ወሲብ ፍፁም የተለየ፣ የሚያንቀጠቅጥ ደስታን እና እርካታን
የሚሰጣት ነው፡፡ እናም ሰውዬውን ማምለክ ነው የሚቀራት፡፡
ከባለትዳር ጋር በመማገጧ እና ወሲብ በመፈፀሟ ምክንያት ገነት ትገባ እንደምትችል ብታምንም፣ ከዚህ ሰው ጋር የምታደርገው ወሲብ ግን በምድር
ሳለች በገነት እየኖረች ያለች አይነት ስሜት እንዲሰማት በማድረግ ደስታዋን
በእልልታ እንድትገልፅ የሚያስገድድ ስሜት ይፈጥርባታል። ታዲያ የዚህ
የወሲብ እና የፍቅር አምላኳ ሰውዬ ስም ማን ይባላል? ሽሽሽሽ... ብላ ለራሷ
እየሳቀች የዚህን ጥያቄ መልስ ታልፈዋለች፡፡ ስሙን በራሷም ሆነ በሌሎች
ሰዎች ፊት ጮክ ብላ ልትጠራው አትችልም፡፡ ሁልጊዜም ያበደ ፍቅር
ስርተው ከጨረሱ በኋላ “እኔ እና አንቺ የምናደርገው ነገር ሁሉ በእኔና በአንቺ መሀል የሚቀር ሚስጥር ነው::” ይላት እና በመቀጠልም “የእኔና የአንቺን ግንኙነት ማንም ሰው ማወቅ የለበትም ገባሽ አይደል?” ይላታል።
እርግጥ ነው ቻርሎቴም ብትሆን እሱ የሚነግራት ነገር በደንብ አድርጎ
ይገባታል፡፡ እሱ ባለትዳር እና የራሱ ህይወት ያለው ሰው ነው። በዚያ ላይ
ደግሞ በዕድሜ፣ በልምድም የሚበልጣት ትልቅ ሰው እንደሆነ ታውቃለች።ይህም ቢሆን እሱ የሚሰራቸውን ነገሮች በሙሉ ማወቅ ትፈልጋለች።አብረው ውጭ ትልልቅ ሆቴሎች ውስጥ በሚሆኑባቸው ጊዜያቶች በአሜሪካን ዶላር የታጨቁ ቦርሳዎችን ለፖሊስ አለቃዎች ሲሰጥም ብዙ ጊዜ አይታዋለች። አብረው ሲተኙ “ምንድን ነው የምትሰራው? የምትሰራውን ማወቅ እፈልጋለሁ?” ብላ ስትጠይቀው የሚመልስላት መልስ “ለአንቺ ደህንነት ብዬ እኮ ነው እንጂ እነግርሽ ነበር” የሚል ስለነበረ ተደብቃ እሱ የሚሰራውን ሥራ ለማየት አሰበች።
አንድ ምሽት ላይም የኢንክሪቶ ቤተሰብ እንድትንቀሳቀስበት በሰጧት መኪና በረጅም ርቀት ከኋላ ተከተለችው:: ዋናውን መንገድ አልፎ ከሚገኝ አንድ ኮሮኮንቻማ ቅያስ ውስጥ ሲገባም ተከትላው ገባች። የፊት መብራቷን
አጥፍታ ተከትላው ስለነበር በመንገዱ ጎርባጣ ቦታዎች ላይ መኪናዋ እየነጠረች ስትከተለው ቆይታ የእሱ መኪና ሲቆም እሷም የመኪናዋን ሞተር አጥፍታ አቆመች፡፡ ከመኪናዋ ውስጥ ሆና እሱ ከመኪናው ወርዶ ወደ አንድ ሼድ ውስጥ ሲገባ ተመለከተችው::.....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍4👏1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
ላስቸግርህና የኔ ጌታ ሌላ ሲጋራ ትሰጠኝ? እነዛኑ ቅንድብ የለሽ አይኖቿን አስለሠለመችለት። የዝናቡ ማካፋት የተሰማት አትመስልም። በጣም ተናደደ፡፡ በተለይ ያንን ቁናስ ገላዋን ደፍራ ወደ አፍንጫው ማስጠጋቷ ክፋኛ አበሳጨው፡፡ ፈጠን ብሎ ከደረት ኪሱ ወስጥ ያለውን የሲጋራ ፓኮ አውጥቶ ወረወንረላትና እያናገረችው ሳለች የመኪናውን በር ዘግቶባት ሞተሩን አስነስቶ ወደ መንገድ ገባ፡፡
ልጅቷ በቆመችበት ፈገግ ብላ እጇን አውለበለበችለት:: ከፓኮው ውስጥ አንድ ሲጋራ አውጥታ ለኮሰች:: አንድ ሰማያዊ ቢ.ኤም.ደብሊው ከጀርባዋ መጥታ አጠገቧ ስትቆም የመኪናውን በር ከፍታ ገባች፡፡
ብራቮ" አላት መሪውን የያዘው ሰው ፈገግ ብሎ እየተመለከታት፡፡
“የቀኑን ኃላፊነትሽን ተወጥተሻል፡፡ የቀረው የቦብ ኃላፊነት ነው።” አለ
በዕብራይስጥ ቋንቋ፡፡
ነጭ ቢሆንም በፀሐይ ሀሩር የተቃጠለና የተጠበሰ የሚመስለው ፊቱ ብዙ ውጣ ውረድ ያላፊ ጠምዛዛ መሆንን ያሳያል። ዛሬ አንድ አስፈላጊነቱ ስለሚቀያየር ይህ ነው ተብሎ የሚነገር ቋሚ ስም የለውም። ሆኖም የጦር አውሮፕላን አብራሪነቱን አቁሞ ስለላን ሙያው፤ ሞሳድን ቤቱ ከማድረጉ በፊት አሃሮን አይትን በመባል ነበር የሚታወቀው፡፡ የተወለደውም ያደገውም ከቴልአቪቭ አቅራቢያ የምትገኝ ሆሎን በምትባል ከተማ ነው፡ እናቱን አያውቅም:: የልጅነት አለሙ በአባቱ የተጣበበ ነበር።
አሃሮን አይተን በእሥራኤል አየር ሃይል ውስጥ ማገልግል ጀመረ በኋላ እጅግ ዝነኛ ከሆኑት ጥቂት አብራሪዎች ጋር አብሮ ለመደመር ረጅም ጊዜ አልወሰደሰትም፡፡ የመጀመሪያ ሲሳዩ ኢራቅ ነበረች፡፡ ሰኔ 7 ቀን 1981
ባግዳድ አካባቢ የሚገኝ የኢራቅን የኒውክለር ማመንጫ እንዲደመስሱ
ከተላኩት አውሮፕላኖች የአንዱ አብራሪ ሆኖ ሲመረጥ የ23 ዓመት ወጣት ነበር፡፡ የኢራቅ የኔውክለር ማመንጫ ወደመ፤ የሃሮን ደረት በኒሻን አጌጠ፡፡ በአመቱ ሁለተኛ ሲሳዩ እጁ ገባች ሊባኖስ በእንግሊዝ የነበሩት የእሥራኤል ኣ
አምባሳደር አሮጎብ በመሃል ለንደን በጠራራ ፀሐይ በአሽባሪዎች ጥይት ቆስሉ። ተከትሎም የ1982 አምስተኛ የአረብና የእሥራኤል ጦርነት ተጀመረ፡፡ የእሥራኤል የጦር አውሮፕላኖች የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤጊንን ፉከራ እውን ለማድረግ በሊባኖስ አየር ላይ አጓሩበት፤ ፈነጩበት። ድል በድል የሆነው የእሥራኤል ጦር ሴመለስ የአሮን ደረት ድጋሚ በኒሻን ተሽሞነሞነ፡፡
ገና በወጣትነቱ በሯን ከፍታ ያቀማጠለችው ዕድሉ በዛው ዓመት
ድንገት ፊቷን አዞረችበት፡፡ ከገሊላ ወጣ ብሎ ከሚገኝ የአየር ሃይል ጦር ሰፈር ተነስቶ የልምምድ በረራ እያደረገ ሳለ የያዛት አውሮፕላን ተከሰከሰች፡፡
ረዳቱ ወዲያውኑ ሲሞት አሃሮን ሞተ ከተባለ በኋላ በሐኪሞች ብርታት
ተመልሶ ሰው ሆነ፡፡ ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ከሃኪም ቤት የወጣው ግን
ከአንድ ዓመት ከሶስት ወር በኋላ ነበር። የቀድሞ ሥራውን የመቀጠል ዕድሉን ከጥያቄ ውጪ ሆኖ አገኘው፡፡
ሞሳድ እጆቹን ዘርግቶ ተቀበለው፡፡
በስለላው ድርጅት ውስጥ ሲገባ ባጋጠመው ሁኔታ መንፈሱ የተሰበረ ቢሆንም በውትድርናው ዓለም ውስጥ የነበረውን ዓይነት ዝና መልሶ የተጎናፀፈው ገና ድርጅቱ ውስጥ በገባ በሁለተኛው አመት ነበር፡፡በጥር ወር 1983 በተካሄደው ኦፕሬሽን ሞሴስ በመባል የሚታወቀው እሥራኤል በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በከሰላና በአላታርች የስደተኛ ሠፈሮች ውስጥ የነበሩ በሽህ የሚቆጠሩ ፈላሻዎችን ከፖርት ሱዳን በስተሰሜን 120 ኪሎ ሜትር ርቆ ኲሚገኝ የቀይ ባህር ጠረፍ በስውር ወደ እሥራኤል ባጓጓዘችበት ኦፕሬሽን ውስጥ ያሳየውን ችሎታ የተመለከቱ የሞሳድ ባለሥልጣናት ዓይናቸውን ጣሉበት፡፡
ከዚህ ኦፕሬሽን ሰኋላ አሃሮን በተለይ በአፍሪካ ውስጥ የመረጃ ሥራ ለመሥራት የሚያበቃውን ልዩ ሥልጠና እንዲወስድ ተደርጎ ሥራውን በጥልቀት ቀጠለ፡፡ በሰሜን ከሚገኙ ጥቂት የአፍሪካ አገሮች ውጪ በተቀሩት የአረብ አገሮች ተዘዋውሮ ሰርቷል፡፡ ዛሬ እድሜው በአርባዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ላይ የሚገኘው አሃሮን አብዛኛውን የአዋቂ አለሙን በአፍሪካ ውስጥ በመረጃ ሥራ በመሥራት በማጥፋቱ አፍሪካን በተመለከተ በሞሳድ ውስጥ ተለዋጭ ሊገኝላቸው ከማይችሉት ሁለትና ሶስት ኤክስፐርቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡
ባለፈው ሚያዚያ አጋማሽ ላይ ነበር ከነበረበት ከጆሃንስበርግ ወደ ቴልአቪቭ እንዲመለስ ትዕዛዝ የተላለፈለት፡፡ በዛኑ ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ቴልአቪቭ ተመልሶ በመሃል ከተማ በሚገኘው የሞሳድ
ዋና ጽህፈት ቤት ሪፖርት ሲያደርግ ወዲያውኑ የሩቅ ምሥራቅና የኣፍሪካ
ጉዳይ ኃላፊ ወደሆነው የበላይ ሹም ቢሮ ኣጣደፉት።
“አይተን…” አለ በስልሳዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኘው በሳል የመረጃ ሰው ከተቀመጠበት ተነስቶ ጠረጴዛውን ዞሮ ወጥቶ ከእሃሮን ፊት ለፊት ወንበር ስቦ እየተቀመጠ፡፡ ሰውየው በሞሳድ ቀጭን የሥልጣን ገመድ ላይ ተረማምደው ቆጥ ላይ ለሰፈሩት በጣት የሚቆጠሩ ባለሥልጣናት አንዱ ቢሆንም እያንዳንዱን የበታች ሠራተኛ የሚያቀርበው እንደ ታናሽ ወንድም እንጅ እንደ ታዛዥ የሥራ ባልደረባ አይደለም፡፡ ከከፍተኛ ችሉታው ውጪ ፍቅርንና ከበሬታን ያተረፈለት ነገር ቢኖር ይኸው ነበር። አይተን እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ ለጊዜው ልሰጥህ የምችለው መረጃ አስተኛ ነው።
ያም ቢሆን ከሞላ ጎደል በዚህ ተካቷል።” አለ አነስተኛ ጥራዝ ከጠረጴዛው
ላይ አንስቶ እያቀበለው፡፡ “ይህን ጊዜ ወስደህ አንብበው! አብላላው። በተረፈ
ግን ሁኔታው ግልፅ እንዲሆንልህ ዋና ፍሬ ሃሳቡን እገልጽልሃለሁ፡፡” በሩ ተከፍቶ የአለቃው ፀሐፊ በትሬ ላይ ቡናና ብስኵቶች ይዛላቸው ገባች፡፡አለቅየው ለአንድ አፍታ ወሬውን ገታ። ፀሐፊው ተመልሳ ስትወጣ የቀረበውን ቡናና ብስኩት ችላ ብሎ ንግግሩን ቀጠሉ።
“የአፍሪካ አገሮች በ1994 ላይ ከሱማሊያና ከርዋንዳ የእርስ በርስ
እልቂት በኋላ ካይሮ ውስጥ ተሰብስበው አፍሪካ የራሷን የሠላም አስከባሪ
ግብረሃይል ልታዋቅር የምትችልበትንና በአገሮች ውስጥ ሁከቶች ሲከሰቱ
ያለ ባዕድ ጣልቃ ገብነት ልትፈታቸው የምትችልበትን ሁኔታ አንስተው
እንደተወያዩ ታስታውሳለህ::”
“አዎ ትዝ ይለኛል” አለ አሃሮን፡፡ “ዝርዝር ሪፖርቱን ያዘጋጀሁት እኔው ነኝ። :
· “በጊዜው እንደምስጢር አልያዙትም ነበር፡፡ ነገር : ግን ባለፈው
ወር” ቀጠለ አለቅየው ''አፍሪካን ዲፌንስ የተባለ መጽሄት ከዓመታት በፊት የጻፈውን ጽሁፍ ጠቅሶ በድጋሚ አፍሪካ ይህም ዕቅድ በተግባር እየተረጎመችው መሆኑን ሲጽፍ መላው አፍሪካ አስተባበለ፡፡”
አሃሮን ጭንቅላቱን በመስማማት ነቀነቀ፤ ሁኔታውን እሱም የተከታተለው መሆኑን በሚገልፅ መልክ፡፡
“ለጊዜው ሁኔታው የዚያን ያህል ባያሳስበንም አንድ ተጨባጭ
ነጥብ ላይ ለመድረስ ስንል በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ
የሚገኙ ወታደራዊ ባለሥልጣናትን ቀርበን መረጃ ለማግኘት ሞከርን፡፡
የሚገርምህ ነገር ሶስት ወር ሙሉ በያለበት ብንዳክርም ትንሽ ፍንጭ እንኳን
ለማግኘት ተሳነን። በመጨረሻም ሳይታሰብ ፈረንሳዮች ቀዳዳ እንዳገኙ
ደረስንበት፡፡”
“የት?” እለ አሃሮን ከወንበሩ ላይ ወደፊት ፎቀቅ ብሉ፡፡
“ሞሮኮ ውስጥ” አለ አለቃው የቡና ስኒው ውስጥ ስኳር ጨምሮ እያማሰለ፡፡ “ለጊዜው በተደራቢነት በመለመልናቸው የፈረንሣይ የመረጃ መኮንኖች በኩል ሁኔታውን ስንከታተል ፈሪሣዮች የሞሮኮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደመለመሉ ደረሥንበት፡፡ ይህ በእርግጥ ግሩም ተስፋ ነበር።ሆኖም ከሁለት ሣምንታት ቆይታ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግል ጀልባቸው በሜድትራንያን ላይ ሲዝናኑ ድንገት

የገቡበት ጠፋ፡፡ የተለያዩ ጋዜጦች
የተለያዩ ጽሁፎችን አወጡ፡፡ ግማሾቹ ታፍነዋል አሉ፤ ሌሎች እራሳቸውን
አጥፍተዋል አሉ…”
“እዎ እኔም በርካታ ጽሁፎች አንብቤአለሁ፡፡” አለ አሃሮን ያጋባውን
የቡና ስኒ እያስቀመጠ፡፡
“በዚህ ተደናግጠን እንዳለን የኛው ልጆች ካሜሩን ውስጥ መረጃ ለመሸጥ ፈቃደኝነትን ያሣዩ ሁለት ባለሥልጣናትን አገኙ፡፡ የገንዘቡ መጠን የሚያስደነግጥ ነበር፡፡ ሆኖም ምርጫ ስላልነበረኝ የተጠየቅነውን ሁሉ ከፈልን፡፡ ከመረጃው በፊት ክፍያ መፈጸም ከደንብ ውጪ ቢሆንም ባለሥልጣናቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ስለነበሩና እኛም ጉጉት ላይ ስለነበርን
ገንዘቡን ከፈልን፡፡”
“እና ምስጢሩ ተገኘ?” አለ አሃሮን፡፡
"አዎ፡፡”
“ምንድነው?”
“እሱን ነው እኔም ያልመለስኩት ጥያቄ!” አለ አለቃው፡፡
“እንዴት ?” አለ አሃሮን ምሥጢሩ ከተገኘ በኋላ ዳግመኛ ሊከሰት የቻለው ችግር አልገለጽልህ ብሎት፡፡
“ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ በሁለተኛው ቀን ማለት ከትላንት ወዲያ ረቡዕ ያውንዴ ያለው አምባሳደራችን አንደኛ ፀሃፊውን መልዕክት አሰዞ ወደዚህ ሰደደው:: በላከው መልዕክት ውስጥ ምሥጢሩን ማግኘቱንና እጅግ አደገኛ የሆነ እንቅስቃሴ በመላው አፍሪካ በተቀናጀ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን እናቱም ያለው አዲስ አበባ ውስጥ እንደሆነ ጠቅሶ ዝርዝር መረጃውን በተመለከተ ግን እርሱ እራሱ ይዞት : በማግሥቱ ወደዚህ
እንደሚበር ገለጸልን፡፡” .
“የእርሱ እዚህ ድረስ መምጣት ለምን አስፈለገ? እንደማንኛውም ምሥጢር በዲፕሎማቲክ ቦርሳ ሊልከው ሲችል” አለ : አሃሮን አለቃውን አቋርጦት፡፡
“አላውቅም! ምናልባት ያገኘው ምስጢር ከፍተኛነት ከራሱ ውጪ ማንንም እንዳይተማመን የፍርሃት ሥሜት አሳድሮቦት ይሆናል፡፡”
“እ.. ሺ” አለ አሃሮን መጨረሻው ናፍቆት፡፡
“የአምባሳደራችንን መምጣት ስንጠባበቅ ትላንት ምሽት ላይ የካሜሩን ኢታማዦር ሹምንና የአገሩን አስተዳደር ሚኒስቴር እንዲሁም የኛን አምባሳደር በአንድነት ጭና ትበር የነበረች የጦር ሄሊኮፕተር በአየር ላይ እንዳለች መቃጠሏን የካሜሩን የውጭ ጉዳይ እዚህ ባለው አምባሳደሩ
በኩል አስታቁን፡፡”
“ሊሆን አይችልም!”
“ሆነ።” አለ አለቃው የተቀመጠበት ወንበር ድጋፍ በቡጢ መትቶ፡፡ እጃችን የገባውም ምሥጢር ከሸጡልን ሁለቱ ባለሥለጣኖች ጋር አብሮ በእሣት ጋየ፡፡”
"እስካሁን ወሬውን እንዴት አላገኘሁትም? ማለትም ያውንዴ ጆሮዎች አሉኝ...ደግሞም
“የሚገርምህ ነገር” አለቃው አቋረጠው “የካሜሩን መንግሥት አደጋ መድረሱን ከገለፀልን ከሰባት ሰዓታት በኋላ ነው እዚያው ያሉ የኤምባሲያችን አባላት የደረሱበት፡፡ አደጋው ካሜሩን ውስጥ በምሥጢር ተይዞ ነበር ማለት ነው፡፡”
“አሁን ምን ላይ ነው ያለነው” አለ አሃሮን በተቀመጠበት እየተቁነጠንጠ፡፡.....