#የበረሐ_ገነት
ጥልቍ ዕፍኝ ዋሻ ፣ በቍጥቋጦ አብቦ
ዕርጥቡ ፣ ለምለሙ፤ የሚያሽት ተንቦ።
. . ስውር . .
...ጥምር . .
. . ዘብ ጠበቂ . . .
የመቅደስ ከለላ ፣
የዕልፍኝ እፍታ ፣
የመንፈስ እርካታ፣
የሐሤት ከፍታ።
የሐሩሩ ገነት ፣ ወበቅ የፍም ጭብጥ
ከነዲድ በረሐ ፣ በዕጥፍ የሚበልጥ
የተፈጥሮ ቅኔ . . .
ከመንገደኛ እግሮች ፣ ላዕላይ 'ሚቀመጥ።
በግለት መደሰት ፣ በእሳት መቀባት
የዋሻው፣ የጫካ ፤ የጋራነት ቅባት።
የተረት ፍጻሜ በዳቦ መታበስ
ዋሻውን ባ'ፈ ሙዝ ፣ በካፊያ ማረስረስ።
ኦና ቤትዋ ደርሶ ፣ በዕንጥሻ አስነጥሶ
ክልልን መማስ ነው ፤ ኬላ ድንበር ጥሶ።
እነሆ ከዋሻው .
ቆሞ እያስቀደሰ ፤
በዕንፋሎት ራሰ!
ከበረሓው ገነት በ'ሳቱ ተቀባ
የመንፈስን መባእ ከሙዳይ አስገባ።
ልክ እንደ መናፍስት በእሳት ተጠምቆ
ምንነት ለወጠ ፣ አብቦና ጸድቆ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
ጥልቍ ዕፍኝ ዋሻ ፣ በቍጥቋጦ አብቦ
ዕርጥቡ ፣ ለምለሙ፤ የሚያሽት ተንቦ።
. . ስውር . .
...ጥምር . .
. . ዘብ ጠበቂ . . .
የመቅደስ ከለላ ፣
የዕልፍኝ እፍታ ፣
የመንፈስ እርካታ፣
የሐሤት ከፍታ።
የሐሩሩ ገነት ፣ ወበቅ የፍም ጭብጥ
ከነዲድ በረሐ ፣ በዕጥፍ የሚበልጥ
የተፈጥሮ ቅኔ . . .
ከመንገደኛ እግሮች ፣ ላዕላይ 'ሚቀመጥ።
በግለት መደሰት ፣ በእሳት መቀባት
የዋሻው፣ የጫካ ፤ የጋራነት ቅባት።
የተረት ፍጻሜ በዳቦ መታበስ
ዋሻውን ባ'ፈ ሙዝ ፣ በካፊያ ማረስረስ።
ኦና ቤትዋ ደርሶ ፣ በዕንጥሻ አስነጥሶ
ክልልን መማስ ነው ፤ ኬላ ድንበር ጥሶ።
እነሆ ከዋሻው .
ቆሞ እያስቀደሰ ፤
በዕንፋሎት ራሰ!
ከበረሓው ገነት በ'ሳቱ ተቀባ
የመንፈስን መባእ ከሙዳይ አስገባ።
ልክ እንደ መናፍስት በእሳት ተጠምቆ
ምንነት ለወጠ ፣ አብቦና ጸድቆ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘