#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
"ልብ አንጠልጥሎ እንደ ጀመረ ፣ ልብ አንጠልጥሎ የሚጨረሰ ድንቅ መፅሐፍ ነው ለሁሉም እንዲደርስ #Share እያደረጋቹ ውድ ቤተሰቦች መልካም ንባብ።
.....ከመኪናዋ ውስጥ ሆና እሱ ከመኪናው ወርዶ ወደ አንድ ሼድ ውስጥ ሲገባ ተመለከተችው ሼዶቹ ውስጥ ያለው መብራት የፋኖስ ስለነበር ከውጭ ሆና ሼድ ውስጥ ምን እንደሚከናወን ለማየት አልቻለችም። ምን ያህል ድፍረት ልቧ ውስጥ እንደገባ ሳይታወቃት ከመኪናዋ ወርዳ ሼዶቹ ወዳሉበት ቦታ አጎንብሳ ሄደች። አንዱ ሼድ አጠገብ ስትደርስ ከፊት ለፊቷ ሁለት ሰዎች
አውቶማቲክ ጠመንጃቸውን ደግነው ጠበቋት፡፡ ቻርሎቴ የመሳሪያዎቹን
አፈሙዞች ስትመለከት “እባካችሁ እንዳትተኩሱ! እባካችሁ እንዳትገድሉኝ!”
ብላ በሀይል ጮኸች። ድምጿን የሰማው ሰውዬም ወደ እሷ ዞሮ የድንጋጤ
እና የንዴት ፊቱን ለአፍታ ካሳያት በኋላ ፈገግ እያለ “ ተዋት!” ብሎ በማስከተል “እኔ እኮ አሳንሼ ገምቼሽ ነበር። ለካ ቀላል ሰው አይደለሽም!” ብሎ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጠፋት።
“እንግዲህ እዚህ ድረስ ከመጣሽ አይቀር የምሰራውን ስራ ላስጎብኝሽ?” አላት። እና የሀብቱ ምንጭ ምን እንደሆነ ያሳያት ጀመር። ኮኬይን! ቻርሎቴ በህይወቷ አንድም ቀን ቀምሳም ሆነ አይታ አታውቅም። ጭራሽ እንዲሁም
ስሙ ሁሉ ያስፈራት ነበር።
በመጀመሪያ ሼድ ውስጥ የደረቁ የኮኬን ቅጠሎች በደንብ ተደርገው ተፈጭተው ከደቃቅ ኖራ ጋር ይደባለቃሉ። በመቀጠልም እየተሽከረከረ ውሀ ከሚረጭ ማሽን (ስፕሪንክለር) በሚወጣው ውሀ የተፈጨ የኮክ ቅጠል እና ኖራ እንዲደርሱ ያደርጋል። በሚቀጥለው ሼድም በመጀመሪያው ትልቅ ማሽን ውስጥ የተቦካውን ኮኬይን የማጣራት፣ የማቃጠል፣ የመደፍጠጥ እና የመንፋትን የመሳሰሉ ውስብስብ ሂደቶችን ያልፍና ከሰልፈሪክ አሲድ ጋር
ይቀላቀላል። ወደሚቀጥለው ክፍል ተወስዶ እንደ ማስቲካ የተጣበቀ ቢጫማ
ፔስት ሆኖ ይወጣል። በመጨረሻም ቢጫው ፔስት ወደሚፀዳበት ክፍል
(ሼድ) ይወሰድና ከሚሟሟ አሞንያ ጋር ተዋህዶ ኮኬይን ሃይድሮ ክሎራይድ
ሆኖ ይወጣል።
ቻርሎቴ እነዚህን ሁሉ ኮኬይን የሚመረትበትን ሂደት ልክ ሳንዲያጎ
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ይሰጥ እንደነበረው ትምህርት ሁሉ በቁምነገር
ስትሰማው ቆይታ ጉብኝቱ አበቃ፡፡
“ደነገጥሽ እንዴ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ እና በማስከተልም “እሺ እንዳየሽው
እንግዲህ እኔ ኮኬን አምራች ወንጀለኛ ነኝ። ከዚህ በኋላ ከእኔ ጋር መሆን
ትፈልጊያለሽ?” አላት የውሸት ሳቅ እየሳቀ። “እኔ ምንጊዜም እፈልግሀለሁ”
ብላ መለሰችለትና ቀና ብላ በስስት አይን ተመለከተችው፡፡ ይህንን ሁኔታዋን
የተመለከተው ሰውዬዋም ወደ እሱ መኪና ወስዶ በሚገርም ሁኔታ ወሰባት፤
እና መኪናዎቻቸውን ከፊት እና ከኋላ አከታትለው እየነዱ ወደ ከተማ
ተመለሱ።
ለጥቂት ቀናት ያህል ሳያገኛት ቢቀር ባለፈው ምሽት ስለተከተለችው
የተዋት መስሏት ስጋት ውስጥ ገብታ ነበር። ዛሬ ቀን ላይ ግን በስልኳ
“ናፍቄሻለሁ” ብሎ የስልክ መልዕክት ላከላት፡፡ መልዕክቱን እንዳየችም እሱ
በዚህ መንገድ ፍቅሩን ገልፆላት ስለማያውቅ ባለፈው ባደረገችው ነገር
እንዳልተቆጣ ገመተች። በዚህም እሷን እንደ ህፃን ብቻ ሳይሆን እንደ እኩያ
ማየት እንደጀመረ እርግጠኛ ሆነች። የስልክ መልዕክቱ ላይ “የሆነ ደስ የሚል
ነገር አሳይሻለሁ!” ብሎ ማታ ላይ የሚገኙበትን ቦታ ካርታ ሊንክ ልኮላት
ስለነበር ዛሬ ማታ እሱ የሚያሳያትን ነገር ለማየት ብላ ቦታው ድረስ ትሄዳለች። ይህንን ነገሯን ፍሬድሪኩ ለምትባለው የስራ ባልደረበዋ ስታጫውታት ግን ስጋትዋን ነበር የገለጠችላት፡፡
“እንዴ ቻርሎቴ እሱ ማታ ላይ ሊያገኝሽ የቀጠረሽ ቦታ እኮ እንኳን በማታ፣ በቀን የማይኬድበት ቦታ ነው። እዚያ ቦታ ላይ ብዙ ሰዎች ተገድለው የሚጣሉበት ቦታ ስለሆነ እኔ ባትሄጂ ነው የምመርጠው::” ብላ ጓደኛዋ ቻርሎቴን ልታሳምናት ብትጥርም ሳይሳካላት ቀረ።
ቻርሎቴ በመኪናዋ ረጅም ርቀት ተጉዛ ፍቅረኛዋ በቀጠራት ቦታ ላይ በሰአቱ የተገኘች ቢሆንም ከዛን ቀን በኋላ ግን ማንም ሰው በአካል አግኝቷት
አያውቅም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“እሺ ሊዛ ያለፈው ሳምንት ሁኔታሽ እንዴት ነበር?” ዶ/ር ኒኪ ሮበርትሰን ጥቁር ፌድ ሌዘር ወንበሯ ላይ ደገፍ ብላ እና በፈገግታ ተሞልታ ሊዛን ጠየቀቻት፡፡
ሊዛ ፍላንገን የሃያ ስምንት ዓመት ሴት ናት። በፊት ላይ ሞዴል የነበረች ስትሆን፣ የቢልየነሩ ዊሊ ባደን ቅምጥም ሆና ለስምንት አመታት ያህል ቆይታለች፡፡
“አሪፍ ነበር” መዳፎቿን እያፋተገች ፈገግ ብላ እና ወደፊት ቀርባ እጅ እንደመንሳት እያለች ነመስቴ! ዊሊ ጋር መሄድ አቁሜያለሁ፤ ስለዚህም አሁን ሁሉ ነገር ቀለል ብሎኛል።” ብላ መለሰችላት፡፡
“በጣም ደስ ይላል” ኒኪ ራሷን ከፍ እና ዝቅ አድርጋ የሚያበረታታ ፈገግታ አሳየቻት። ከውጭ የሚዘንበው ዝናብ የቢሮዋን መስኮት ሲመታው ይሰማታል፡፡ ሊዛ የዛሬው የመጨረሻ ታካሚ ስለሆነች ደስ ብሏታል። ከእሷ ጋር ያላትን የቴራፒ አገልግሎትን ከጨረሰች በኋላ ወደ ቤቷ በፍጥነት ሄዳ የቤቷን መብራት አጥፍታ ለጥ ማለት ነው የፈለገችው።
“ደግሞስ እንዴት አሪፍ አይሆንልኝ፡፡ በተለይ ደግሞ ባለፈው ጊዜ ተገናኝተን ሳለ የመከርሽኝን ምክር ተግባራዊ ማድረጌ በጣም ነው የጠቀመኝ”
ሊዛ ስታወራ በአንዳንድ ቃላቶቿ ላይ አፅንዖት በመስጠት ስለሆነ ገና
አስራዎቹ ውስጥ ያለች ልጃገረድ ያስመስላታል፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ራሷን
ለመገምገም የሚያስችል መፅሀፍ አንብባ እንደጨረሰችና ራሷን በግምገማ
እንዳበቃች መንፈሳዊ ሰው አድርጋ የምትቆጥር ብትሆንም፣ ኒኪ ግን እንደ
ሳይኮሎጂስት እና ውጤታማ ሰው ሊዛ ለራሷ በምትሰጠው ግምት ላይ አስተያየቷን ከመሰንዘር ይልቅ በሽተኞቿ ከመጥፎ ባህሪዎቻቸው ሊላቀቁ
በሚችሉባቸው ቴክኒኮች ላይ በማተኮር ሃላፊነቷን በትጋት እየተወጣች ነበር።
ኒኪ ሊዛን የምታስባት እንደ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ፣ እንደ በቤቷ ውስጥ የሴተኛ አዳሪነት ተግባርን የምታከናውን ሴት፣ እንደ ሸርሙጣ እና እንደ ህፃን ገዳይ ነው።
ሊዛ ፍላንገን የኒኪ ቢሮ ውስጥ ከሚገኘው ምቹ ሶፋ ላይ ለጠጥ እንዳለች የልቧን መናገር ጀመረች። “እሱ ከገዛልኝ አፓርትመንት እኮ ወጣሁኝ” ብላ
በኩራት ስላደረገችው ነገር አሳውቃ በማስከተልም “በቃ አደረግኩት”
አለቻት፡፡
“በቃ እንዴት ደስ የሚል ስሜት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ እዚህ እኔን በደንብ ትረዳኛለች ብዬ በማስባት ሴት ፊት የውስጤን መናገሬ ትልቅ ነፃነት
እንደመጎናፀፍ ነው። ከአፓርትመንቱ የመውጣት ሀሳቤን ለዊሊ ስነግረው
እንደ እብድ ነበር ያረገው:: በጣም ከመናደዱ የተነሳ ሁሉ የሚመታኝ ነበር
የመሰለኝ፡፡ ብታይው እንደ ብራቅ እየጮኸ ቤት ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎቹን ሁሉ ሲሰባብር ነበር።” አለች ሊዛ፡፡ “እንዴ ዛቻ (ማስፈራሪያ) አድርሶብሻል?” ብላ ኒኪ ጠየቀቻት “እንዴ ቀላል አስፈራራኝ መሰለሽ? “አንቺ ይህንን ነገር ማድረግ በፍፁም አትችይም:: ህይወትሽን ነው የማበላሸው:: አንቺ እኮ ንብረቴ ነሽ፡፡ እንዲያውም ከእኔ ውጪ አንቺ ምንም ነገር ነሽ አለኝ። እኔ ግን በእርጋታ “ይኸውልህ ውዴ ልትረዳኝ ይገባል። ይህንን ነገር ለራሴ ነው ማድረግ የፈለግኩት:: እንዴ አሁን እኮ ሃያ ስምንት አመቴ ነው። ልጅ አይደለሁም::”
ሊዛ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ላይ ከ ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ጋር የነበራትን የምክር አገልግሎትን አስታወሰች:: ዶ/ር ኒኪ ለሊዛ ስለምትወስዳቸው የቫይኮዲን ዕፅ ዊሊ የሚያደንቃቸው የአሜሪካ እግር ኳስ

👍3❤2
ተጨዋች የሆኑ ግዙፍ ጥቁር ተጫዋቾችን የወሲብ ፍላጎት እንድታረካ የሚያስገድዳትን ነገር አንስታ አስረድታት ነበር። ማለትም ሊዛ የዊሊ ቅምጥ እስከሆነች ድረስ ከሁለት ዓመት በፊት ቤቨርሊ ሂል ውስጥ በስሟ በገዛላት አፓርትመንት ውስጥ እንዳስቀመጣት እንደ አንድ የግል ንብረቱ እንደሚቆጥራት
እንድታውቅ ያደረገቻት ያን ዕለት ነበር፡፡ ይሄው በሳምንት ውስጥ ውሳኔ ላይ
ደርሳ ዊሊን መተው ችላለች::
ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ሊዛ የምትወስደውን አደንዛዥ ዕፅ መተው እንድትችልም ወደ ማገገሚያ (ሪሀብ) ክሊኒክ ለመግባትም የሚያስችላትን ትልቅ የውስጧን ጥንካሬ እንድታይ ልታደርጋት ችላለች፡፡ ሊዛ ቁጭ ብላ እኔ መልካም ሰው ነኝ አለች ዕፁን መተው እስከቻልኩ ድረስ ዊሊንም
መተው እችላለሁ። አለች በሀሳቧ።
ዊሊ የገዛላትን አፓርትመንት ከፈለገች ትኖርበታለች። ከፈለገች ትሸጠዋለች፡፡ ለሀያ አምስተኛ የልደት በዓል የሰጣትን የአልማዝ የአንገት ሀብልንም ሸጣ ኑሮዋን እንደ አዲስ መጀመሪ ትችላለች፡፡ ደግሞስ ለስምንት አመታት ያህል የቆየውን የቅምጥ እና ውሽማ ግንኙነትን ማቆሟ ምን ያስደንቃል? በዚያ ላይ ከእሱ ያረገዘችውን ፅንስ ስላስወረደችለት ውለታዋ አለበት አይደል? ይህ ባይሆንማ ኖሮ እንደ ሌሎች ሴቶች ልጇን ወልዳ
ለልጇ ተቆራጭ ከቢሊየነር ውሽማዋ መጠየቅ ትችል አልነበረም? ስለዚህ
ሊተዋት እና ምርጫዋን ሊያከብርላት ይገባል፡፡ ደግሞስ ዊሊ ንዴቱ ካለፈለት
በኋላ ምናልባት ጓደኛማቾች ሊሆኑ የሚችሉበት ምክንያት የለም? ብላ ዶ/ር
ኒኪ ሮበርትስ አሰበች፡፡
ከዚህ ቢሮ ውጭ ያለው ህይወቷ ምን ይመስል ይሆን?
ምስጋና ለጎግል ይግባውና ስለ ኒኪ ሮበርትስ መሰረታዊ ነገሮችን ለማወቅ በቅታለች። ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ሀሞንድ ዕድሜዋ ሰላሳ ስምንት እንደሆነ የመጀመሪያ ድግሪዋን በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እንደሰራች እንዲሁም ደግሞ የዶክትሬት ድግሪዋን በUCLA እንደሰራች በተጨማሪም በሮናልድ ሬገን ህክምና ማዕከል ውስጥ በኢንተርንሺፕነት እንደሰራች ከጎግል ፕሮፋይሏ ላይ አንብባ ተረድታለች።
“ምናልባትም እዚያ (የሬገን ህክምና ማዕከል ውስጥ) ይሆን ባሏን እና
የኒውሮ ሰርጅን ሀኪሙን እንዲሁም ደግሞ በአደንዛዥ ዕፅ ምክንያት
የአዕምሮ መረበሽ ሰዎችን ለማከም ስፔሻላይዝድ ያደረገውን ዶ/ር ዶውግ
ሮበርትስ ያገኘችው?' ብላ ሊዛ ታስባለች። ይህንን ግን መጠየቅ አትችልም። ምክንያቱም በአካሚ እና ታካሚ ግንኙነታቸው ውስጥ እንዲህ አይነት
የግለሰቡን (በተለይም የሀኪሙን ግለሰባዊ ህይወትን) የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስቶ መጠየቅ አይቻልም።
ባሏ በአሰቃቂ የመኪና አደጋ የሞተው ሊዛ ቴራፒዋን የጀመረች ጊዜ ላይ
ነበር፡፡ ያኔ አደጋው በደረሰ ሰሞን የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ዶ/ር ዶውግ ሮበርትስ በሎስ አንጀለስ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ጉልህ አስተዋፅኦ ካበረከቱ ዶክተሮች ውስጥ አንደኛው እንደሆነ አትቶ ነበር።
ሊዛ ከፊት ለፊት የተቀመጠችውን ቀጭን ቆንጆ እና ጉብዝናዋን የሚያሳይላት አረንጓዴ አይንን የታደለች ሴት ባሏ የሞተባት መሆኗን ስታስብ ይገርማታል፡፡
'ውይ ስታሳዝን ምስኪንዋ ዶ/ር ሮበርትስ። ሀዘኗን የምታካፍለው የሆነ
ሰውማ ሊኖራት ይገባል' እያለች ሊዛ በሀሳብ ጭልጥ ብላ ነጎደች።
ከዚህ በኋላ ሀዘንዋን ትታ ተደስታ መኖር ይኖርባታል።
“ሊዛ ጊዜው አልቋል።” የቴራፒስቷ ለስለስ ያለው ድምፅዋ ሊዛን ከሀሳቧ
አባነናት። ቀና ብላ የቢሮው ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የግድግዳ ሰአት ተመለከተች።
“እዚህ ስመጣ ጊዜው እንዴት ይሮጣል። ይህን ታዝበሽ ታውቂያለሽ ዶ/ር ሮበርትሰን?”
ኒኪም ፈገግ አለች እና “አንዳንዴ ይሰማኛል” አለች፡፡ ሊዛ ፍላንግም
ለመሄድ አስባ ከሶፋው ላይ ተነሳች፡፡ “ጃኬት ወይንም ረጅም ኮት አላደረግሽም እንዴ? ውጭ እኮ በደንብ እየዘነበ ነው”
“እንዴ እየዘነበ ነው እንዴ?” ብላ ሊዛ መስኮቱን የሚመታውን ዝናብ
አሁን ገና ተመለከተችው።
ሊዛ ለብሳ የወጣችው በጣም አጭር ሚኒስከርት እና ላዩ ላይ የምንፈልገው ፍቅር ብቻ ነው' የሚል ፅሁፍ የተፃፈበት ብጫቂ ቦዲ ነው።ያው መቼስ ሆዷ ቦርጭ ስለሌላት እና እግሯም የሞዴል ስለሆነ አያስጠላባትም፡፡
“እንደዚህ ከወጣሽ አጥንትሽ ድረስ ነው የምትበሰብሽው” አለቻት እና ኒኪ ተነስታ የራሷን ወፍራም ኮት (ጃኬት) ከተሰቀለበት አውርዳ “በይ ይሄንን ማድረግ ትችያለሽ” አለቻት፡፡
“እንዴ አንቺስ?” ብላ ጃኬቱን ለመቀበል እያመነታች ጠየቀቻት ኒኪም ራሷን እየነቀነቀች “እኔ የህንፃው ምድር ቤት ነው መኪናዬን ያቆምኩት።
በአሳንሰር ወደ ታች ስለምወርድ ችግር የለውም። በሚቀጥለው ስትመጭ
ይዘሽልኝ ትመጭያለሽ፡፡” ብላ ስላሳመነቻት ሊዛ ጃኬትዋን ተቀብላ
“ዶ/ር ሮበርትስ በእውነት በጣም ጥሩ እና ለሰው አሳቢ ሰው ነሽ” ብላ እጇን ልካ የቴራፒስቷን ለስላሳ እጅ በወዳጅነት ጨመቀችው በእርግጥም ደግሞ ዶ/ር ሮበርትስን ከሌሎች ቴራፒስቶች የመረጠቻት ለታካሚዎቿ የምታስብ (የምትጨነቅ) በመሆኗ ስለሆነ ነው ፤ እናም ሊዛ ተደሰተች። እንደ እውነቱ ከሆነ ደግሞ ዶክተር ሮበርትስ ለታካሚዎችዋ የምታስብ እና የምትጨነቅ ሀኪም ናት፡፡ ለእኔም ታስብልኛለች እና ደስ ብሎኛል' ብላ እያሰበች ከቢሮ ወጣች፡፡
ሴንቸሪ ሜዲካል ፕላዛ ህንፃ በቆመበት ቦታ ውጭው እርጥበታማ እና ብርዳማ ነው:: ከህንፃው አጠገብ ለሰአታት ያህል ቆሞ ሲጠብቅ የነበረው ግለሰብ እግሩን በጣም እየጠዘጠዘው ነው፡፡ እያንዳንዱ የሚተነፍሰው አየር እንደ ምላጭ ውስጡን እየቆረጠው ነው። እያንዳንዳቸው ከልብሱ አልፈው
ሰውነቱ ላይ የሚያርፉት የዝናብ ጠብታዎች ደግሞ ልክ አሲድ እንዳረፈበት ያህል ነው የሚያቃጥሉት፡፡ በዕፅ ብዛት የነፈዙት ነርቮቹ እንደ ስጋ በእሳት የተበጠሱ ያሉ ያክል ነው የሚሰማው። ለማድረግ ያቀደውን ነገር ከከወነ በኋላ ደግሞ ቀጥሎ የሚጠብቀው ነገር ፍፁም እርካታ ይሆንለታል፡፡ በመሆኑም አሁን የሚሰማውን ስሜት ታግሶ ማሳለፍ እንደሚኖርበት አምኖ ተቀብሎታል።....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍2
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....“የሚገርምህ ነገር” አለቃው አቋረጠው “የካሜሩን መንግሥት
አደጋ መድረሱን ከገለፀልን ከሰባት ሰዓታት በኋላ ነው እዚያው ያሉ የኤምባሲያችን አባላት የደረሱበት፡፡ አደጋው ካሜሩን ውስጥ በምሥጢር ተይዞ ነበር ማለት ነው፡፡”
“አሁን ምን ላይ ነው ያለነው” አለ አሃሮን በተቀመጠበት እየተቁነጠንጠ፡፡
“በበኩላችን ማብራሪያ ጠይቀናል የካሜሩንን መንግሥት::በተጨማሪም የአደጋውን መነሻ የሚያጠና ቡድን ትናትና ሌሊቱን ወደዚያው በሯል፡፡ ሆኖም ዋናው ነጥብ ይህ አይደለም፡፡ አደጋው ሆን ተብሎ የተፈጸመ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም፡፡ ግድያው የሞሮኮው ጠቅላይ ሚኒስትር ከተሰወሩበት ምክንያት ጋር በተዛመደ መልኩ የተቀነባበረ ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም፡፡ ይህ ደግሞ አምባሳደራችን እጅ ገብቶ የነበረው መረጃ በእርግጥም ከፍተኛ ዋጋ ያለው ነበር ማለት ነው፡፡” አለቅየው ከተቀመጠበት ተነስቶ ከጠረጴዛው
ጀርባ ከቦታው ተመልሶ በገዛ ወንበሩ ላይ ተቀመጠና መሳቢያውን ስቦ የታሸገ ፖስታ አወጣ፡፡
“አሃሮን” አለ ፖስታ የያዘበትን እጁን ወደፊት ዘርግቶ “…ከጆሃንስበርግ ባስቸኳይ ያስጠራሁህ ወደ አዲስ አበባ ሂደሀ የዚህን እንቅስቃሴ እናት ሸምቀቆ ውስጥ እንድታስገባልኝ ነው. ይህ ትኬትሆና ፓስፖርት ነው:” የታሸገውን ፖስታ አቀበለው፡፡
የዛኑ ለሊት ከቴልአቪቭ ተነስቶ በአቴንስ አድርጎ አዲስ አበባ ገባ፡፡በፓስፖርቱ ላይ ያለው ስሙ ካሚል ጀማል ጀማያል ይላል፡፡ ዜግነት ሊባኖሳዊ፤ ሥራ ንግድ፡፡
አዲስ ኣበባ ከገባ ሶስተኛ ወሩን ጨርሶ አራተኛውን ሊይዝ የቀሩት ጥቂት ቀናት ናቸው፡፡ ጨለማው ግን አሁንም አልገፈፈለትም:: አዲስ አበባ
እንደደረሰ ቴልአቪቭ ያለው አለቃው በቅድሚያ ባመቻቸለት መሠረት
ከእንግሊዝ ኤም አይ ስድስት ሰዎች ጋር በቅንጅት በመሥራት መረቡን በስፋት ዘረጋ፡፡ መረቡ ውስጥ የገባ የተጠመደ አሳ ግን አልነበረም፡
አሃሮን ሊክደው ያልቻለው ነጥብ አዲስ አበባ ውስጥ ከሞሳድና ከሲ.አይ.ኤ ይልቅ ኤም አይ ስድስት ቀድሞ ምሥጢሩን ማነፍነፍ መጀመሩን ነበር፡፡ ሆኖም እንግሊዞች የመለመሉት ጥቂት ኢትዮጵያውያንን በመሆኑና እነዚህም ከሞላ ጎደል በኢትዮጵያ የስለላ መዋቅር ውስጥ የታቀፉ ለገንዘብ ሲሉ ተደራቢነት ለኤም አይ ስድስት የሚሰሩ በመሆናቸው የመሥክ ሥራ በስፋት ለመሥራት የማያመቹና አመኔታም የማይጣልባቸው ሆነው አገኛቸው፡፡
ይህን ችግር ለማስወገድ አሃሮን ቴልአቪቭ የሚገኙ ኢትዮጵያ ወስጥ ተወልደው ያደጉ ወደ እሥራኤል የተመሰሱ አይሁዶችኝ በብዛት ወደ
አዲስ አበባ አስመጥቶ አሰማራቸው፡፡ይህ አዲስ አበባ ውስጥ በርካታ
ጆሮዎችና ዓይኖች እንዲኖሩት ከመርዳቱም በላይ የእንግሊዝ ኤም አይ
ስድስት ለሚያደርግላት ድጋፍ ወሮታውን ለመመለስ ኣብቅቶታል።
በአዲስ አበባ ውስጥ በአጭር ጊዜ ከእንግሊዞች የተሻለ ሰፊ መረብ
ዘርግቻለሁ ብሎ ቢያምንም የመጀመሪያውን በር የከፈቱት እንግሊዞች ነበሩ፡፡
ሰኔ መጨረሻ ላይ አዲስ አበባ በገባ በሶስተኛ ወር በአዲስ አበባ የኤም አይ ስድስት ቡድን የሚመራው ሮበርት ፋረል ዜናውን አበሰረለት፡፡ፋረል የሰላሳ ስምንት አመት ጎልማሳ ነው፡፡ ፈጣንና ቀልጣፋ ጭንቅላት ስላለው አሃሮን ያከብረዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁት በ1991 ሱማሊያ ወስጥ ሁለቱም የመረጃ ሥራ ሲሰሩ ነበር፡፡
“እርግጠኛ ነህ?” አለ አሃሮን በመቀደሙ የተሰማውን ብሽቀት አምቆ ይዞ፡፡
“ይመስለኛል፡፡” አለ ፋረል በቀኙ የያዘውን የሽሪ ጠርሙስ እየከተፈ:: የተከፈተውን ጠርሙስ በቀኝ ይዞ በእርጋታ ሁለት መለኪያዎች ከመደርደርሪያው ውስጥ አወጣና ለሁለቱም ከቀዳ በኋላ “ለስፔይን ወይን ጠጅ ጠማቂዎች! ብሎ መለኪያውን አነሳ፡፡ “ዓለም ሁሉ የፈረንሣዮችን ወይን ጠጅ ያደንቃል፡፡ ያኔ ልብ ግን ጥንትም ዛሬም ወደፊትም ያለው
ከስፔይን ጠማቂዎች ጋር ነው!” አለ ፈገግ ብሎ፡፡
“ቦብ .. ይቅርታ አድርግልኝና የመጣሁት ለሼሪ ያለህን ታማኝነት ለማረጋገጥ አይደለም!” አለ አሃሮን በስጨት ብሎ “ለማወቅ የምፈልገው በእርግጥ ቀዳዳ ማግኘትህን ነው፡፡”
“አትቸኩል፡፡” እለ ፋረል ፈገግ ብሎ አሃሮንን ያበልጥ ማበሳጨት የፈለገ ይመስል፡፡ “ልጅ ሆኜ አባቴ ሁሌ የሚነግረኝ ተረት ነበር…የስፔይን
ወይን ጠጅ ጠማቂዎች…”
“የፈጣሪ ያለህ!” አሃሮን ተነስቶ ቆመ “…እመነኝ ካሁን በኋላ ስለ ሼሪ ወይ ስላባትህ ልትቀባጥር ብትሞክር…” አለ አሃሮን ቡጢ ጨብጦ፡
“ደህና…ደህና” . አለ ፋረል እየሳቀ ቶሎ ተቀመጠና “ቁጭ ብለህ ብትሰማኝ አይሻልም?” አለ በንዴት ቡጢ ጨብጦ ቁልቁል የሚመለከተውን አሃሮንን እያየ፡፡
“በል ቀጥል ምን ታየኛለህ…ምንድነው አገኘሁት የምትለው?” :
“መረጃ ያለው ሰው ያጠመድኩ ይመስለኛል፡፡” : አለ ፋረል
ለመጀመሪያ ጊዜ ኮስተር ብሎ
“ማነው እሱ?”
“እ..ለጊዜው ማንነቱን አናቆየው…”
“ቦብ! ምሥጢር መደበቅህ ነው?” አለ አሃሮን በስጨት ብሎ
"ዲፕሎማት ነው፡፡” አላ ፋረል ትንሽ ካቅማማ በኋላ፡፡
“ኢትዮጵያዊ?”
“አይደለም.ላይቤሪያዊ ነው፡፡”
“እንዴት መለመልከው. ስለፈጣሪ ብለህ ሁሉን በግልጽ አስረዳኝ::”
ፋረል መለኪያውን አንስቶ ከጨለጠው በኋላ ዝርዝር ነጥብ ውስጥ እንድገባ አታስገድደኝ አልገባም:: ዋናው ነጥብ ሰውየው ሚስጥሩን እንደሚያውቅ ደርሰንበታል፡፡ ከአሁን በኋላ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ እንደማይዘገይ እርግጠኛ ነኝ የፈለግነው ምሥጢር በጃችን ይገባል” አለ ፋረል በተቆራረጠ አረፍተ ነገር፡፡
“በምን መንገድ ልረዳህ እችላለሁ እኔ? አለ አሃሮን መቀደሙ አንጀቱን እየበላው።
“አመሰግንሃለሁ…ግን ለጊዜው እርዳታ አያሻኝም::” አለ ፋረል ዘብነን እያለ በምሥጢሩ ላይ ያለውን ባለቤትነት ለማሳየት እንደፈለገ ሁሉ፡፡
በሣምንቱ ሁኔታዎች ሁሉ ተቀያየሩ ተስፋ
የተጣለበት የላይቤሪያው ዲፕሎማት የገባበት ጠፋ::
“አሃሮን!” አለ ፋረል ፀጉሩን እየነጨ “እርዳታህን እፈልጋለሁ፡፡”ይሄን ሰው የገባበት ገብተን ማግኘት አለብን፡፡ ምሥጢሩን ይዞ ነው የተሰወረው፡፡
የተባለው የላይቤሪያ ዲፕሎማት መጥፋት ሁለቱን የመረጃ ቤቶች
በአዲስ አበባ ውስጥ ይበልጥ አስተሳሰራቸው:: ያላቸውን የሰው ሃይልና
የገንዘብ ብርታት ሁሉንም በቅንጅት ለመጠቀም ዝግጁ ሆነ፡፡ ዲፕሎማቱ
የላይቤሪያው ወታደራዊ አታሼ በፍጥነት በእጃቸው መግባት አለበት፣በፍጥነት፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ልጅቷ የያዘችውን የሲጋራ ፓኮ ቁልቁል ቀደደችና ከውስጥ ባቄላ የምታክል የድምፅ ማስተላለፊያ መሣሪያ አውጥታ ለአሃሮን አቀበለችው፡፡
“በጣም አደገኛ ዘዴ ነው የተጠቀምነው ግን ውስጥ ከገባ በኋላ ሊያጨስ ፓኮውን ቢያወጣ ኖሮ !” አለ አሃሮን፡፡
“ፓኮውን ቀድዶ ውስጡን እስካላየ ድረስ አያገኛትም፡፡ ደግሞ ይህን ይህን እየተሸተትኩ የደባበስኩትኝ ሲጋራ አውጥቶ ከአፉ ከሰካው ሰውየው
ጤነኛ አይደለም ማለት ነው… እስቲ አሽትተው::” አለች እሷን እሷን የሚሽተውን የሲጋራ ፓኮ ወደ አፍንጫው እያስጠጋች፡፡
“ቦብ ምን ያህል እንደሚደሰት አላውቅም።” አለ አሃሮን ፊቱን
ከሲጋራው ፓኮ እያሸሸ፡፡
“ተደሰተም አልተደሰተም ሥራዬን ጨርሻለሁ.… ቃልህን ማክበር አለብህ በሚቀጥለው አውሮፕላን ወደ ቴልአቪቭ መመለስ እፈልጋለሁ፡፡”
“ያንን መወሰን የሚችል አሮን እራሱ ነው፡፡ እኔ ላደርግ የምችለው ነገር ብሶትሽን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡” አለ አሃሮን ዓይኖቹን ከፊት ለፊት ካለው መንገድ ላይ ተክሎ፡፡ “ያንን ደግሞ አድርጌዋለሁ፡፡”
“እንግዲያው ልትረዳኝ ከልቻልክ ከአሮን
ጋር መገናኘት

👍4
እፈልጋለሁ፡፡”
“ሞኝ አትሁኝ፡፡ አንድ ጊዜ አዲስ አበባ ከደረስሽ በኋላ በምንም መንገድ ከአሮን ጋር መገናኘት እንደማትችይ ገና ከቴልአቪቭ ስትነሽ የተገለፀልሽ መሰለኝ፡፡” አለ አሃሮን ዞር ብሎ ተመልክቷት፡፡
ከቴልአቪቭ ስንነሳ የተነገረኝ ሚሽኑ ከአንድ ወር ሰላይ የማይወስድ ስለመሆኑ ነው! አሁን ግን ሁሉተኛ ወሬን ይዣለሁ፡፡
አይገባችሁም እንዴ የሰው ችግር? ስንት ጊዜ ልንገርህ? ሕፃን ልጄ የልብ ቀዶ ጥገና ሊደረግላት ስትዘጋጅ ነው አሮን አቻኩሎ ቶሎ እንደምመለስ አግባብቶ ወዲህ እንድመጣ ያደረገኝ፡፡ ይገባሃል? ሌላው ቢቀር በዚህ ጊዜ ህፃን ልጄን ልንከባከባት እፈልጋለሁ፡፡ የተሰጠኝን ስራ ጨርሻለሁ፡፡”
“እይው” አለ አሃሮን የመኪናውን ፍጥነት ቀንሶ:: “ይቅርታ አድርጊልኝና እኔ ስለህፃን ልጅና ስለሌላው ችግርሽ ሁሉ የማውቀው ነገር የለም፡፡ እኔ የማውቀው ለስራዩ የምጠቀምበት አማርኛ አጣርታ የምትናገር የአዲስ አበባን ጉራንጉር የምታ'ውቅና ቀላል የጦር መሣሪያዎችን ጠንቅቃ ያጠናች ልምድ ያላት የመስክ ሠራታኛ እንድትላክልኝ መጠየቁንና በሳምንት ውስጥ አንቺ መምጣትሽን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሚሽኑ እስካልተጠናቀቀ አለበለዚያም በአንቺ ምትክ ሌላ ሴት እስካልተተካችልኝ ድረስ ላደርግ የምችለው ነገር ቢኖር ችግርሽን በታሁፍ ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ ተግባባን?”
“ለምን ቀስ ብለህ አሮንን ልታግባባልኝ አትሞክርም አንተ?'' ክርክር መግጠሙ እንደማያዋጣት ስትረዳ ለዘብ አለች::
“አላመንሽኝም ማለት ነው ያለፈው ጊዜ ስነግርሽ» አለ አሃሮን በረጅመ ተንፍሶ፡፡ እኔ ራሴ አሮንን በአካል ላገኘው አልችልም
አየሽ…እሱ የኤምባሲያችን አባል ስለሆነ ክትትል ሊደረግባት ይችላል ስለዚህ እኔ ራሴ ትዕዛዝ ደርሶኝ ከቴልአቪቭ ስነሳ የተገለፀልኝ ነገር ኖር አዲስ አበባ
ከደረስኩ በኋላ ከማንኛውም የኤምባሲያችን አባል ጋር መገናኘት
እንደማልችልና ማንኛውንም ግንኙነት በምሥጢር በተዘረጉ አቀባባይ
ወኪሎች አማካኝነት ብቻ እንድፈጽም ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በቀጥታ ላገኛቸው
የምችለው ለዚሁ ጉዳይ አብረውኝ የመጡ ከበታቼ ያሉ ሠራተኞችን ብቻ
ነው:: በቃ። ደግሞ እውነቱን ንገረኝ ካልሽ አሮንም ቢሆን ሊመልስሽ አይችልም። እንድትመለሽ.ፈቃድ ሊሰጥሽ የሚችለው ሰው ያለው እዛው ቴልኣቪቭ ነው፡፡”
"እና የኔ ችግር መቼ ነው የሚፈታው?
"ሚሽኑ ዳር ሲደርስ”
ኣብደሃል እንዴ! ይህ ነገርኮ ለወራት ሊቆይ ይችላል!” በጭንቀት
አፈጠጠችበት።
“በወራት ጊዜ እንቆቅልሹኝ ከፈታነው እድለኞች ነን፡፡ እውነቱን ንገረኝ ካልሽ ቀናት በተቆጠሩ ቁጥር ፍርሃቴ እየጨመረ ነው የመጣው፡፡በተለይ ከሶስት ሣምንታት በፊት ካዛንቺስ ውስጥ በጥይት ቆስሉ የነበረው የሞሮኮ ወታደራዊ አታሼ አምቡላንሱ ደርሶ ሊያተርፈው ሲችል ፀጥታ አስከባሪ ተብለው የመጡ ፖሊሶች ራሳቸው አፍነው ሲገድሉት የእንግሊዝ
ስድስቶች ያነሱትን ፎቶግራፍ ካየሁ ወዲህ እንጂ…እነዚህ አፍሪካውያን
የሚሰሩትን ጠንቅቀው የተረዱት ይመስለኛል፡፡ እያንዳንዱ እርምጃቸው
ማሰሪያ ያለው ነው የሆነብኝ፡፡ እነዚህ ባሪያዎች ፈንቅለው የተነሱ ዕለት
ዓለም ወዮለት!” | ፈገግ አለ፡፡
“አፍሪካውያን ባሪያዎች አይደሉም፡፡” አለች ኮስተር ብላ፡፡
“ኢትዮጵያዊነቱ አገረሽብሽ እንዴ? ” ፈገግ አለ አሃሮን ፊቱን መልሶ እየተመለከታት፡፡
“እየው.… እሥራኤላዊነቴ ጥያቄ ውስጥ አይገባም” አፈጠጠችበት፡፡
“ግን ይህ የተወለድኩባትና ያደኩባትን አገር እንድጠላ አያደርገኝም፡፡እውነቱን ንገሪኝ ካልክ ደግሞ ሰላይ ሆኜ ወደ ኢትዮጵያ መመለሴ ያቅለሸልሸኛል፡፡”
“ኡፍ! አንቺ ሴትዮ መኪናውን አገማሽው፡፡” አለ አጠገቧ የተቀመጠው አሃሮን መስኮቱን ዝቅ እያደረገ። ሃሣብ ገባው፡፡ “እስቲ ለማንኛውም ድጋሚ አሳውቀዋለሁ ችግርሽን፡፡”
አሃሮን እውነቱን ሊገልጽላት አልፈለገም፡፡ተለዋጭ የመስክ ሠራተኛ ቢጠይቅ የቴልአቪቭ ቢሮ በሰዓታት ውስጥ እንደሚልክለት ልቡ ያውቀዋል፡፡
ሆኖም ይህችን ልጅ መመለስ አልፈለገም፡፡ ፍጥነቷን ድፍረቷንና የመሣሪያ አጠቃቀም ችሎታዋን እምነት እንዲጥልባት አድርጎታል፡፡ እሷን መልሶ
ምናልባት ብቁ ያልሆነ የመስክ ሠራተኛ ላይ መውደቅ አልፈለገም፡፡ ያለው
ምርጫ በተቻለው ሁኔታው ከእርሱ ቁጥጥር ውጭ እንደሆነ ልጅቷን
ማሳመንና አዲስ አበባ እንድትቆይ ማስገደድ ብቻ ነው፡፡.....
💫ይቀጥላል💫

👍1
አንድ ነገር ሁሉ፣ብዙ ከመሰለኝ ፣
እርግጠኛ ሁኚ...
ወይን ጠጥቻለሁ፤ሰው እየደለለኝ።
ብዙ ነገር ሁሉ...
አንድ ነው በሚል ቃል ፣ ከዘጋሁት በሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
የሌለኝን ሁሉ ፣ ከፍዬ መስከሬን።
አንድም ነገር ሁሉ...
ሁሉም ነገር ሁሉ ፣ካልኩስ በእግዜር ነወ፧
እርግጠኛ ሁኚ...
ከከተማ ቄስ ጋር ፣ዝክር ቀምቅሜ ነው።
ሕይወት ሁሉም ነገር ፣ባንድ ነገር ሥር ነው፣
እያልኩኝ ከሰማሽ ካየሽው ማምረሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
በፊደሪል ዱላ፣ታጅቤ ማደሬን።
ሁሉም ነገር የለም!
አንድም ነገር የለም ፤ የሚል ቃል ከወጣኝ፣
እርግጠኛ ሁኚ...
ጀማሪ ፈላስፋ ፣ አረቄ እንዳጠጣኝ።
ሁሉም አንድ ነገር ፤ሁሉም ነገር አለው፤
ብዬ ጸጥ ካልኩኝ ፣ ከበቃኝ ክርክር፣
አርግጠኛ ሁኔ...
እንዲህ የምሆነው፣ ባንቺ ቃል ስሰክር።
🔘በኤልያስ ሽታኹን🔘
ከርእስ የለውም የግጥም ስብስብ መድብል
እርግጠኛ ሁኚ...
ወይን ጠጥቻለሁ፤ሰው እየደለለኝ።
ብዙ ነገር ሁሉ...
አንድ ነው በሚል ቃል ፣ ከዘጋሁት በሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
የሌለኝን ሁሉ ፣ ከፍዬ መስከሬን።
አንድም ነገር ሁሉ...
ሁሉም ነገር ሁሉ ፣ካልኩስ በእግዜር ነወ፧
እርግጠኛ ሁኚ...
ከከተማ ቄስ ጋር ፣ዝክር ቀምቅሜ ነው።
ሕይወት ሁሉም ነገር ፣ባንድ ነገር ሥር ነው፣
እያልኩኝ ከሰማሽ ካየሽው ማምረሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
በፊደሪል ዱላ፣ታጅቤ ማደሬን።
ሁሉም ነገር የለም!
አንድም ነገር የለም ፤ የሚል ቃል ከወጣኝ፣
እርግጠኛ ሁኚ...
ጀማሪ ፈላስፋ ፣ አረቄ እንዳጠጣኝ።
ሁሉም አንድ ነገር ፤ሁሉም ነገር አለው፤
ብዬ ጸጥ ካልኩኝ ፣ ከበቃኝ ክርክር፣
አርግጠኛ ሁኔ...
እንዲህ የምሆነው፣ ባንቺ ቃል ስሰክር።
🔘በኤልያስ ሽታኹን🔘
ከርእስ የለውም የግጥም ስብስብ መድብል
👍1
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
፡
፡
...የሴንቸሪ ሲቲ መንገዶች በሙሉ ውር ውር በሚሉ መኪናዎች ቢሞላም የእግረኛ መንገዶቹ ግን ጭር ያሉ ነበሩ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ ሰዎች
በሎስ አንጀለስ በእግራቸው አይሄዱም፤ በተለይ ደግሞ በዝናብ ውስጥ መሄዱ የማይታሰብ ነገር ነው። እርግጥ የሚጠብቃት ሴት አንድ አንዴ
በእግር ትጓዛለች፡፡ “ዛሬስ ምናልባት በእግሯ ወደ ቤቷ መሄድ ብትችልስ?
“በይ ውጭ እኮ ውጭ የት ነው ያለሽው?” እያለ በውስጡ ሲያመላልስ
በድንገት ሴትየዋ ከህንፃው ስትወጣ ልቡ ደነገጠ፡፡ ምክንያቱም አልተዘጋጀም
ነበር፡፡ ልቡ በደንብ እየደለቀም እሷን መመልከት ጀመረ፡፡
ኮቷንም በቀበቶዋ ሸብ አድርጋ እና ራሷን አቀርቅራ በፍጥነት ወደ መንገዱ መሸጋገሪያ የምትሄደውን ሴት እየተመለከተ “እርዱኝ!” እያለ ጮኸ፡፡
በእርግጥ ድምፁ ያን ያክል ይሰማት አይሰማት እርግጠኛ አይደለም።
ቢሆንም ግን ዛሬ ይህቺ ሴት ልትሰማው ይገባል “ኧረ እርዱኝ!” አለ በድጋሚ፡፡
ይሄኔም ሊዛ ፍላንገን ወደ እሱ ዞር አለች ከቆሻሻው መጣያ አጠገብ አንድ ቀጭን ልጅ ይሁን ትልቅ ሰው መሆኑ የማይለይ ሰው አጎንብሶ ቁጢጥ ብሏል፡፡ ወደ እሱ ስትራመድ ስላያትም “እባክሽን 911 ደውይልኝ! ፖሊስ ጥሪልኝ፡፡ የሆነ ሰው በጩቤ ወግቶኛል።” አላት፡፡
እሷም “በእግዚአብሔር ስም” ብላ ስልኳን አወጣች እና እየደወለች ወደ
ልጁ ቀረበች፡፡ “ምን ሆነህ ነው? ደህና ነህ?” ብላ ጠየቀችው። ልጁ አጎንብሶ
ሆዱን በማጠፍ እጁን ሆዱ ላይ አስቀምጦታል፡፡ ኮፍያ ያለው ሹራብ ነው
የለበሰው:: ሹራቡ ላይ የዘነበበት ዝናብም ፊቱን እና ፀጉሩን አርሶታል።
“የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ምን ነበር የፈለጉት?”
“ፖሊስ ይድረስልኝ፡፡” ብላ ሊዛ በማስከተል “ አምቡላንስም ጭምር” አለች እና አናቱን በእጇ እየነካች “አይዞህ እርዳታ እየመጣልን ነው። ምንህን ነው
የተጎዳኸው?” ብላ ጠየቀችው፡፡
ልጁም ፈገግ ብሎ ሲያያት ሊዛ የልጁን ፊት አይታ በጣም ቀፈፋት እና ለማስታወክ ዳዳት ከሹራብ ኮፍያው ሥር ያለው የልጁ ፊት የሰው አይመስልም፡፡ ፊቱ ፍፁም አረንጎዴ ከመሆኑም በላይ አጥንቱ ገጧል። ይባስ
ብሎም ተቆራርጠው የተንጠለጠሉ የበሰበሱ ነገሮች ከፊቱ ተንጠልጥለዋል። ልትጮህ አፍዋን ብትከፍትም አንድም
ሊወጣላት አልቻለም።
911 ላይ የሚያወራት ሰውም “የእኔ እመቤት የት እንዳለሽ ልትነግሪኝ
ትችያለሽ?” ብሎ ጠየቃት። ባለ አረንጎዴው ፊትም በድንጋጤ የተከፈተውን የሊዛን አፍ እየተመለከተ ከሆዱ ስር ስለታም ጩቤ አወጣ እና ሆዷ ላይ ሰመጠጠው። ይሄኔም አየሩን የሚሰነጥቅ የእሪታ ድምፅ ከሊዛ አፍ ሊወጣ በቃ። በድጋሚም ስለቱን ከሆዷ ነቅሎ በጣም በሀይል ሲሰመጥጥባት እጁ ከጩቤው ጋር ተያይዞ ወደ ውስጥ ስለገባ የሆነ የሚሞቅ ርጥበት እጁ ላይ
ተሰማው።
“እባኮትን ያናገሩኝ? ይሰማዎታል? ምንድን ነው የተከሰተው? የት ቦታ
እንደሚገኙ ሊነግሩኝ ይችላሉ?” መሬት ላይ ከእጇ አምልጦ ከወደቀው ስልክ
የሚወጣ የ911 ሰውዬዋ ድምፅ ነው። ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ የX ክላስ
መርሴዲስ መኪና የሌዘር ወንበር ላይ ተለጥጣ የገራጁ በር እስኪከፈት
እየጠበቀች ትገኛለች፡፡ መንገዱ ክፍት ከሆነ በሀያ ደቂቃ ውስጥ ብሬንትውድ
ውስጥ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ትደርሳለች። ምንም እንኳን ረጅም እና
ባዶ የሆነ ህይወት ቤቷ ውስጥ ቢጠብቃትም ቴሌቪዥን በማየት በአንድ
ጠርሙስ አልኮል ባዶ ህይወቷን ትሞላለች:: እንኳን አንድ ምሽት፣ ሁሉ
ነገር ያልፍ አይደል?
ኒኪ መኪና ውስጥ እንዳለች የዛሬው ውሎዋ ላይ ሊዛን በሙሉ ልቧ ስላላደመጠቻት የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷታል። ታካሚዋን ብትወደውም
ሆነ ብትጠላው ስራዋን በአግባቡ ሰርታ ስላልወጣች በእውነትም ቅር ብሏታል። የገራዥ በር በቀስታ መከፈት እንደጀመረ ኒኪ ወደ በሩ ነዳች እና ከህንፃው ወጥታ ወደ ጠባቡ መንገድ ገባች።
ሊዛ የበሩን መከፈት እና መዘጋት ድምፅን እና የመኪና ሞተር ድምፅ ስትሰማ በነበረበት ጊዜ ከሆዷ እና ከደረቷ ደሟ እንደጎርፍ ይወርድ ነበር።
መሮጥም ሆነ መቆም አልቻለችም:: ማድረግ የምትችለው አንድ ነገር ቢኖር
ጉሮሮዋ እስኪሰነጠቅ ድረስ መጮህ ነበር። በስለት የወጋት ሰው በስለቱ
እጇን፣ ጡቷን እና ጭኗን ጭምር ደግሞ ደጋግሞ ይቆራርጣታል። ቶሎ
ሊገድላት አልፈለገም እና ልክ ድመት የያዘችውን አይጥ እያሰቃየች
እንደምትዝናና ሁሉ እሱም የሚያደርገው ያንን ነበር።
የመኪናው ሞተር ድምፅ እየጨመረ መምጣትን ስትሰማ ግን በተስፋ
ተሞልታ ትንፋሿን ሰበሰበች። ከዚያም በህይወቷ ጮሀ የማታውቀውን
ጩኸት ጮኸች። በጩኸቷ መሀል ላይ ደሟ ጉሮሮዋ ውስጥ ሲንተከተክ
ታውቋታል፡፡ አይኗም ተጎልጉሎ የሚወጣ ሁላ መስሏታል።
የመኪናው መብራት ወደ እነርሱ አቅጣጫ አበራ። ይሄኔም የሚወጋት ሰውዬ እሷን የመውጋት ስራውን አቆመ፡፡ የመኪናው ሞተርም ድምፁ ጠፋ።
ሊዛ ዶ/ር ሮበርትሰን አይታኛለች ከዚህ ነፍሰ ገዳይም ታተርፈኛለች ብላ
እረፍት ተሰማት። ነፍሰ ገዳዩም የያዘውን ጩቤ መሬቱ ላይ ጣለው፡፡ የልብ
ምቷ ቀስ እያለ ሲመታ ይሰማታል፡፡ ባለጩቤው ሰው ግን ጥሏት ሊሮጥ
አልቻለም። የመኪናው በርም ሲከፈት አልሰማችም::
ሁለት... አምስት... አስር ሰኮንዶች አለፉ፡፡ ምንም የተከሰተ ነገር ግን አልነበረም፡፡ “እንዴ... ምንድን ነው ነገሩ?”
የመኪናው ሞተር ድምፅ በድጋሚ ተሰማት፡፡ አይሆንም! ጠባቡን መታጠፊያ የመኪናው መብራት አጥለቀለቀው፡፡
“አይሆንም! አይሆንም! እባክሽን ድረሺልኝ! ስለእግዚአብሔር ብለሽ
ድረሺልኝ!!
የኒኪ ብርማ መርሴዲስ መኪና በጎን በኩል አለፋቸው እና ወደ ዋናው
መንገድ ውስጥ ገባ፡፡የበሰበሱ አጥንታማ እጆችም የሊዛ አንገት ላይ ተጠመጠሙ። ከፊት ለፊቷ አብረቅራቂው የገዳይ ጩቤ በእሷ ደም ጨቅይቶ ይታያታል።
ሊዛ “የት ነበር ያቆምነው?” ብሎ ገዳዩ ሰው እየገለፈጠ የተናገራት ንግግር እና አስቀያሚ ሳቁን ለመጨረሻ ጊዜ ነበር የሰማችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታች እንግዳ ማረፊያ ክፍሉ ስለሚጠብቁት ሁለቱ ታጣቂ የግል
ጠባቂዎች እያሰበ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ፈለገ። አልሰራም፡፡ ጥሩ ስሜት አልተሰማውም፡፡ በመቀጠል ደግሞ ቴራፒስቷን ራቁቷን አሰባት። ይሄ
ሳይሻል አይቀርም፡፡ ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ስሜታዊ ሰው ነች ብሎ ያስባል።
ግራጫ አጭር ቀሚሷን ወደ ላይ ገፋ አድርጎ ዳሌዋን... አሰበ። ቦዲዋ
ተከፍቶ... “ኡፍ ደስ የሚል ነገር ነው...
ካርተር ከእኔ ጋር ነህ?” የሚለው ድምፅ ከሀሳቡ አነቃው። ድምፅዋን ሲሰማ ፊቱ ቀላበት፡፡ በመቀጠል ደግሞ ግራ ተጋባ፤ ለጥቆም ኮስተር አለ፡፡ስኬታማ የኢንቨስትመንት ባንከር፣ ወጣት የተማረ እና በጣም ሀብታም ሰው ነው። ሥራ ቦታው እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ሁሉ ካርተር ሰዎችን በትዕዛዝ ቁጭ ብድግ ያስደርጋቸዋል፡፡ የሚፈልገውን ነገርም ሊያሟሉለት የሚራኮቱለት አይነት ሰው ነው። በተለይ ደግሞ ሴቶችን በሙሉ ስልጣን ውስጥ ሆኖ ነው የሚያዛቸው፡፡ አሁን እዚህ ቦታ ላይ ግን ልክ እንደ አንድ
ረባሽ ተማሪ ስሙን ስትጠራው ምቾት አልተሰማውም።
“ትላንት ማታ ምን አየሁ ብለህ እንዳሰብክ ደግመህ ንገረኝ እስቲ” “ሀሳቤ አይደለም! እንዴ እኔ ያየሁትን ነገር አይቼያለሁ። እኔ እብድ አይደለሁም!”
ብሎ ተበሰጫጨ እና ጥቅጥቅ ቡናማ ፀጉሩን ሞነጫጨረው፡፡
“እኔ እንደዛ አላልኩም” ብላ ድምፅዋን በማለስለስ ቀጠለች እና “አንዳንዴ ጤነኛ የሆኑ ሰዎች ሁሉ እንደዚህ አይነት ነገር ሊገጥማቸው ይችላል። እኔ እራሴ አንዳንዴ እንደዚያ

❤1👍1
እሆናለሁ”
“ይሁን እሺ እኔ ግን እንደዚህ አይነት ነገር አልገጠመኝም” አላት እና በውስጡ “በእየሱስ ስም እነዚህ ዲቃላዎች የሆነ ቀን ላይ ያገኙኝ እና በኤሌክትሪክ ሽቦ አንቀው ወይንም ደግሞ የሆነ ቤት ውስጥ አስገብተውኝ ቀጥቅጠው ሊገድሉኝ ይችላሉ ያኔ ይገባቸዋል ፖሊሶቹ ዶ/ር ሮበርትስም እና ሌሎች ያላመኑት ሰዎች ምነው ባዳመጥነው ኖሮ እያሉ ይቆጫሉ።
ኒኪ ወደፊት ዘንበል ብላ ካርተር አየሁት (ገጠመኝ) ብሎ የሚያስባቸውን
ነገሮች እየዘከዘከ ሲያወራት ታዳምጠዋለች ይሄው እሷ ጋር ሊታከም
ከመጣ አንድ አመት አልፎታል ግን ያኔ እሷ ጋ ከመጣበት ቀን ጀምሮ
የሆኑ ወንጀለኞች ሊገድሉት እየተከታተሉት እንደሆነ የሚነግራትን ነገር
ወይንም ፍራቻውን ሊተወው አልቻለም እንዲያውም ሰዎቹ ይገድሉኛል
የሚለው ፍራቻ ያኔ ከነበረበት በላይ እየጨመረበት ነው የሄደው። ምንም
እንኳን እሱ ግድያው ሊፈፀምብኝ ነው ብሎ ቢያምንም እና ቢፈራም የተጨበጠ ማስረጃ ግን ሊያቀርብላት አልቻለም። እንዲያውም ባለፈው ሳምንት በነበራቸው ቆይታ ላይ ታች የሴንትራል ፕላዛ ክፍል ውስጥ የታካሚዎችዋን ቀጠሮ ከእሷ የስራ ሰአት ጋር እንዲጣጣም ቀጠሮ በማስያዝ የሚያግዛትን ትሬድ ሬሞንድ የተባለውን ረዳቷን ለሜክሲኮ ወንጀለኞች
ይሰልላል ብሎ ነግሯታል።
“ትሬይ ሬሞንድን ለምን ጠረጠርከው? ምን ማስረጃ አለህ?” ብላ ዶ/ር ሮበርትስ ብትጠይቀውም እሱ ግን እንደ ሁልጊዜውም ሁሉ በቃ ይታወቀኛል! ውስጤ ይነግረኛል” የሚል መልስን ነበር የመለሰላት።
ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ይህንን ታካሚዋን ለምን ልታድነው እንዳልቻለች ሊገባት አልቻለም ለምን? ብላ ቤቷ ገብታ ስለታካሚዎቿ ራስዋን ስትጠይቅ ምንም አይነት ግልፅ ያለ መልስ አታገኝም። በቃ ከአቅሟ በላይ የሆነ መሸከም የማይቻል ነገር ሆኖ ነው ለራስዋ የሚሰማት።
“ማንም የማይችለው ከአቅም በላይ...።
ይህን ቃል ስታስብ ከባሏ ዶውግ ጋር በዚህ ቃል ዙሪያ ያወሩት ነገር ትዝ አላት። የሆነ ቀን ላይ ምሳ አብረው በሬስቶራንት ውስጥ ሲመገቡ “ይሄ ከአቅም በላይ መሸከም የማንችለው ቃል ምን ማለት ነው?” ብሎ ይጠይቃታል። እሷም ከሙያዋ አንፃር ቃሉን ታካሚዎችዋ እንዴት እንደሚገልፁላት ነግራው ነበር። ታካሚዎችቿ ሀሳባቸው ወይንም
እሳቤያቸውን መቋቋም ሲያቅታቸው እንዲሁም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ
የጭንቀት ስሜትን በውስጣቸው ሲለቅባቸው እንደሚጠቀሙበት አስረድታው በገለፃዋ ደስ ብሎት ነበር ባሏ ዶውግ በአደንዛዥ ዕፅ ምክንያት
ህይወታቸው እና የአንጎላቸው ነርቮች የተቃወሰባቸው ሱሰኞችን የሚያክም
የበጎ አድራጎ አገልግሎት ሰጪ ክሊኒክ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ከፍቶ እየሰራ
ነበር። በክሊኒኩ ውስጥ ለህክምና የሚመጡ መክፈል የማይችሉ የሎስ
አንጀለስ ታካሚዎችን በነፃ እያከመ ፈውስን ይሰጣቸው ነበር። ምንም እንኳን
ለበሽተኞቹ የጠለቀ ሀሳብ የሌለው ቢመስልም እሱ ግን ለሁሉም ታካሚዎቹ
የጠለቀ ሀሳብ ነበረው። ያን ቀን ላይ ምሳቸውን እየተመገቡ በነበሩበት ጊዜ
ላይም እነዚህን መሰል ደሳስ የሚሉ ሀሳቦችን በቁም ነገር ሲወያዩ ነበር
ያሳለፉት።
እሱ እና እሷ ከተጋቡ ሰባት ዓመት፣ ከተዋወቁ ደግሞ ከሀያ አመት
በላይ የቆዩ ቢሆኑም በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ በጣም በቁም
ነገር ተሞልተው በመግባባት እና ስሜትን በሚይዝ መልኩ ስለነበር አብረው
ምሳ የሚበሉባቸው ጊዜያቶችን ደስ በሚል ስሜት ነበር ያሳልፉ የነበረው።
የዚያን ቀን ላይ ምሳቸውን እየበሉ ስለ ቃሉ ምንነት ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ
ባለቤትዋ ዶውግ “ለማንኛውም ስለ ቃሉ ይህን ያህል ካወራን ይበቃል"
አላት እና በፍቅር አይን እየተመለከታት የጠዋት ላይ ውሎሽ እንዴት ነበር
ውዴ? የእርግዝና ምርመራውን አደረግሽ?”
“እስካሁን አላደረግኩም” ብላ አፈር አለች እና በግማሹ የበላችው ምግብ ላይ አቀረቀረች። በመቀጠልም “እስቲ ማታ እሞክራለሁ”
“ለምን አሁን አታደርጊውም?”
“ምናልባት ኔጌቲቭ ቢሆን የከሰአት ስራዬን ተረጋግቼ እንዳልሰራ ሊያደርገኝ ይችላል” አለችው ኒኪ፡፡ ዶውግም እጁን በጠረጴዛው ላይ አሻግሮ እጇን ያዛት እና ጨመቅ ጨመቅ እያደረገ “የኔ ማር ምናልባት እኮ ፖዘቲቭም ሊሆን ይችላል እኮ” አላት፡፡ “እውነት ነው ሊሆን ይችላል”
አለችው ኒኪ በግድ ፈገግ እያለች በውስጧ። በፊት ላይ ለስድስት ጊዜያት
ያህል ሞክሬ ነበር። ያው ወሩ ባለፈ ቁጥር እንቁላሎቼ እያረጁ እና ከጥቅም
ውጭ እየሆኑ ነው የሚመጡት 'የሆነ ክፉ የሆነ አምላክ ከእኛ ቁጥጥር
ውጭ የሆነ አንድ አካል እኛ ወላጆች እንዳንሆን ወስኖብናል መሰለኝ ብላ
አሰበች፡፡
እሷ እና ዶውግ ሁሉም ነገሮች አሏቸው፡፡ ምርጥ ትዳር፣ ሀብት እና በህብረተሰቡ ውስጥ ጥሩ ቦታ፣ የሚቀናበት ስራ (ሞያ) እና ምርጥ የሆኑ የልብ ከጓደኞችህ አሏቸው፡፡ ታዲያ ከዚህ ኑሯቸው ውስጥ የሚጎድላቸው ነገር የራሳቸው የሆኑ ልጆች ብቻ ናቸው፡፡
“አፈቅርሻለው” አላት ዶውግ፡፡
“እኔም አፈቅርሀለሁ” ብላ መለሰችለት፡፡
“ይሆንልናል እሺ። ደግሞም እኮ ብዙ ጊዜያቶች አሉን፡፡”
ይሆናል' ብላ ኒኪ አሰበች። “አዎን ብዙ ጊዜያቶች አሉን፡፡
“ዶ/ር ሮበርትስ” ብሎ ካርተር በርክሌ በንዴት ድምፅ በማስከተልም
“እያዳመጥሺኝ ነው ግን?” ብሎ ጠየቃት።
“አዎን” አለች እና እያዳመጠችው እንደነበር ልታሳውቀው ብላ
የተናገራቸውን ነገሮች ደገመችለት ከረጅም ጊዜ በፊት ከላይ ማዳመጥ
ብላ የሰየመችውን አንዱን የአንጎሏን ክፍል ሌላ ነገር እንዲያስብ እና ትኩረት እንዲያደርግ በማስቻል እና ሌላኛው ክፍል ደግሞ የሰዎችን ወሬ
በደንብ እንዲሰማና እንዲያስታውስ በማድረግ ክህሎት አዳብራለች ይህንን
ነገር ደግሞ ያስለመዳት ዶውግ ነበር፡፡ ግን ለምንድን ነው ሁሉ ነገሮቼ
ከዶውግ ጋር የሚያያዙት?
“አሁን ሰአታችን አብቅቷል፡፡ ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ማሰብ የሚለውን እንቅስቃሴ በማድረግ የዛሬውን የህክምና ጊዜን መዝጋት እንችላለን።” አለችው ሙሉ በሙሉ ነገሩን እየተቆጣጠረች፡፡ በማስከተልም “እባክህን በጫማህ ወለሉን ሙሉ በሙሉ በመርገጥ ትተባበረኝ.”
ታካሚዋ ካርተር ቢሮዋን ለቆ ከወጣ በኋላ እሷም ከቢሮዋ ወጥታ ወደ
ታች በመውረድ ኮሪደር ላይ እየተንጎራደደች ማሰብ ጀመረች፡፡
ረዳቷ እና የቢሮ ማናጀሯ ትሬይ ሞንድ የታካሚዎቿን የቀጠሮ ጊዜያቶችን በማመቻቸት ስራ ተጠምዷል እርግጥ ነው አሁን ላይ እንደ ዛሬ አመቱ ያህል ብዙ ታካሚዎች የሏትም፡፡ አምና ሀያ ደንበኞች (ታካሚዎች) ነበሯት። ዶውግ ባሏ ከሞተ በኋላ ግን ሀዘኗ የሚገባቸው መስሏቸው ይሁን ወይንም ደግሞ እሷ ሀዘን ላይ ስለሆነች በሙሉ አትኩሮት የቴራፒ አገልግሎትን አትሰጠንም ብለው በማሰብ ይሆናል እሷ ጋ መታከማቸውን
ያቋረጡት እና ቋሚ ታካሚዎች ብቻ የቀራት።
እነዚህ አራቱ ታካሚዎችም ቢሆኑ በጣም በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያሉ እና የትም መሄድ የማይችሉ ስለሆኑ ነው፡፡ ካርተር በርክሌይም ሰዎች ሊገድሉኝ እያሳደዱኝ ነው በሚል ፍራቻ ውስጥ የሚዳክር በሳምንት አንድ ጊዜ እሷ ቢሮ እየመጣ ህክምናውን የሚከታተል ሰው ነው
ሊዛ ፍላንገን ግራ የገባት የቢሊየነር ቅምጥ በሳምንት ሁለቴ ህክምናዋን
የምትከታተል ሰው ነች። አኔ ቤታማን ደህንነት የማይሰማት ፕሮፌሽናል
የቫዬሊን ተጫዋች ስትሆን በየቀኑ ወደ ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ቢሮ እየመጣች
ህክምናዋን የምትከታተል ነች እርግጥም ነው በየቀኑ እሷን እያገኘች
የህክምና አገልግሎት ማግኘት መቻሏ በጣም ከባድ ነገር ቢሆንም ይህቺን
በፍርሀት ውስጥ የምትገኘውን ወጣት እምቢ ማለት አልቻለችም። ከዚህም
በላይ ደግሞ በየቀኑ ለዚህች ወጣት መጨነቅ መጀመሯ ለራሷም እያስገረማት ይገኛል።

Forwarded from ያዝ ለቀቅ via @YazLekkBot
"ከንፈር መሞከር ፈልጋለሁ።" አልኩት
"እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?"
"እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።" ከንፈሩን አቀበለኝ።
ወራት ነጎዱ……
"ድንግል መሆን አልፈልግም።" አልኩት....see and read more✏️

👎3
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
“አብርሃም አለ?” አላት የመኪናውን መስኮት ዝቅ አድርጎ፡፡
የግቢውን በር የከፈተችው ሴት መልስ ሳትሰጠው የብረት በሩን ወለል አድርጋ ከፈተችለት፡፡ የአብርሃም ገረዶች መምጫና መሄጃቸው አይታወቅም፡፡ እንደ አሸን ይፈላሉ፤ እንደ ጤዛ ይበናሉ፡፡ ሁሌ አዲስ ፊት፣ ሁሌ አዲስ ገረድ፡፡
ናትናኤል ፈገግ እንዳለ መኪናውን በእርጋታ እያሽከረከረ ወደ ግቢ
ገባ፡፡ ናትናኤል የአብርሃምን ግቢ በተመለከተ ቁጥር የሚታወሰው ካመት
በፊት ቤቱ ሲሰራ የነበረ ኣቧራና ጭቃ ነው፡፡ ያ ሁሉ አልፎ የዛሬውን አረንጓዴ መስከ ሲመለከት ይገርመዋል፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት አብርሃም ቤቱን ለመሥራት ከባንክ ሊበደር ማሰቡን ሲያማክረው ያከላከለው ታሰበው::
“አብርሃም ምን አስቸኮለህ... ገና
ምኑንም ሳትይዘው ቤት መሥራትን ምን አመጣው?” ነበር ያለው፡፡
“ናትናኤል ከአሁን በኋላ'ኮ ህፃናት አያደለንም፡፡ ፈጠነም ዘገየ ቤተሰብ መከተሉ አይቀርም::” አብርሃም ሊያስረዳው ሞከረ::
“ቢሆንም...በኋላ ከፍለህ የማትጨርሰው ዕዳ ውስጥ ከምትገባ ለምን ትንሽ አትታገስም…”
“ሰታግስ ምን ይመጣልኛል…ናትናኤል ከትምህርት ቤት ከተለየንና ሥራ ከጀመርን እንኳን አራት አመታት አለፉን'ኮ... ጊዜው'ኮ ይሄዳል፡፡ አንተ
እራስህ ካልተነቃቃህ ኮ! ነገም ከዛሬ አይለይም:: ዛሬ የከበደሀ ነገም ይከብድሃል፡፡ ዛሬ አልገፋ ያለህ ነገም አልገፋ ይልሃል፡፡ ጨክኖ መግባት ነው
“እንጂ…
ብድር ውስጥ ግባ ብዬ አልመክርህም::” ናትናኤል እስከመጨረሻው በአብርሃም ሃሳብ አልተስማማም ነበር።
አብርሃም በሃሳቡ ጠንክሮ ከባንክ ተበደረ ቤቱን ሠራ:: ቤቱ ካለቀ በኋላ ናትናኤል ከራሱ ስንፍና ጋር እያነፃፀረ አብርሃምን አደነቀው: ዛሬ የመጣበት ትዝታ ይሄ ነበር፡፡
“አብርሃም አለ? ብሎ ጠየቃት ድጋሚ የግቢውን በር ከፍታ ያስገባችውን የቤት ሠራተኛ፤ የመኪናውን በር ከፍቶ እየወረደ፡፡
“አሉ፡፡” አለችው ሁለት እጆቿን እያፍተለተለች፡፡ ከግራ አይኗ በላይ ግማሽ ግንባራን የሸፈነው የሽታ ምልክት ፊቷን አበላሽቶታል፡፡
“ሳጥናኤል!” አለ አብርሃም የቤቱን በር ከፍቶ ወጥቶ ናትናኤልን ሲያይ፡፡ በተማሪነት ዘመናቸው በናትናኤል ሽርና ተንኮል ዘወትር መሳቂያ ይሆን የነበረ አንድ ጓደኛው ናትናኤልን አሻሽሎ ሳጥናኤል ካለው ወዲያ የቅርብ ጓደኞቹ በዚያው ስም ነው የሚጠሩት::
“የስ” አለ ናትናኤል ከአብርሃም ጋር ወደቤት እየገባ፡፡
“ምነው?”
“አዲስ ገረድ! ” አለ ናትናኤል እያሾፈ፡፡
“ተወኝ ባክህ. አሁንስ ራሴን እየተጠራጠርኩት ነው፡፡ ከራሴው ሳይሆን አይቀርም ችግሩ:: ምሥራቅንም ሰለቻት አሁንስ እሷ ታመጣለች እኔ አባርራለሁ። እሷ ታመጣለች እኔ አባርራለሁ..”
“እኔ'ኮ ብዬሃለሁ. ውቃቢህ ገረድ አይወድም!” ናትናኤል ሳቀ፡፡
“አፈር የበላ ውቃቢ ወይ ወጥ አይሠራ. እንጀራ አደጋግር ብቻ ገረድ ያባርራል!”
“ምሥራቅ ደህና ነች ለመሆነ?”
“ደህና ናች!” አለ አብርሃም እንደፀባያቸው ለናትናኤል የበረዶ
አንኳርች የገባበት ለራሱ ደሞ አምቦ ውሃ ጠብ ያለበት ውስኪ ይዞ እየተመለሰ፡፡
“አሁን ነው'ኮ የሄደችው፡፡ጠብቃህ ነበር ይመጣል ብያት፡፡ አብረን ልንነግርህ ነበር ውሳኔያችንን።”
“የምን ውሳኔ?”
“ልንጋባ ነው” .
“ውሸትክን ነው!” አለ ናትናኤል ከተቀመጠበት ወንበር ላይ
ወደፊት ፎቀቅ ብሎ፡፡ “አባቷን አሳመነቻቸውን ወደስ.…”
“ምን ታሳምናቸዋለች… የደረቁ ሽማግሌ፡፡ አታምንም እንዴት እንደጠላኋቸው::”
“እና ምን ይሁን ነው የሚሉት:: ከሆነ በኋላ? ”
“አ.አ. ኣንት ስለማርዟ ነው የምታወራው፡፡ እሳቸውን ስንለማመጥ ልጁ ሊወለድ ነው፡ አስበው እስቲ አራት ወር አለፈው ኮ
ችኮ ሽማግሌ!”
“አትፍረድ አብርሃም…ሰውየው ቅደም ተከተሉ ጠፍቷቸዋል፡፡እንደነሱ ጊዜ ዛሬም እርግዝና ከጋብቻ በኋሳ እየመሰላቸው ነው'ኮ ተደፈርን የሚሉት፡፡ ልጃቸው መሆኗን አትርሳ.”
“እና ምን ላድርግ …ይቅርታ ጠየቅኩ! ሽማግሌ ላክሁ?” አብርሃም
እጆቹን አወናጨፈ፡፡
“ታዲያ ኣባቷ ሳይስማሙ ነው ልትጋቡ የቆረጣችሁት?”
“አሁንማ እሺ አሉ፡፡ ስታስፈራራቸው፤ እምቢ ካልክ ያለሠርግ ቤቱ እገባሁ ስትላቸው ያኔ ጭንቅላታቸው መስራት ጀመረ” አለ ኣብርሃም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ ብሎ “ጥቅምት ላይ ልንጋባ ነው::”
"ተመስገን ነው!” አለ ናትናኤል ወደኋላ ደገፍ ብዙ እየተነፈሰ
“ወንድ ሽማግሌ ናቸው ግን አራት ወር ሙሉ አቃዡህ።” እለ ናትናኤል ፈገግ ብሎ፡፡
“ትላንትኮ ደውዬ እነግረዋለሁ እያልኩ ሳስብ ነው ቀድመህ የደወልከው፡፡ አንተ!” አለ አብርሃም ድንገት ሌላ ትዝ ያለው ነገር እንዳለ . ሁሉ “በነገራችን ላይ በስልክ ውስጥ እንዲያ ተዝናንተህ አታውራ፡፡አፍህን የምይዝበት መንገድ ጠፍቶኝ ነው እንጅ አየህ የኔ አካባቢ… ማለቴ ሥራዬ
ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ ስልክ ጥሩንባ ነው፡፡ ሁሉ ያዳምጠዋል፡፡ ደግሞስ ስለ
ሞንሮቪያው አታሼ የማውቀው ነገር መኖሩን በምን አወቅህ?"
“ዝም ብዬ በግምት ነው፡፡ መቼም ፀረ ስለላ ውስጥ እየሰራህ አንዳንድ ነገር አታጣም፡፡
“ብቻ ለሁለተኛው ስልክ ይዘህ አትዝፈን፡፡”
“ያወራነው'ኮ ምሥጢር አልነበረም:: የሰውየው መሰወር ከማንም የተደበቀ አይደለም፡፡ የጠየኩህ ደግሞ የምታውቀው ነገር እንዳለ ነው፡፡ ይሄ
ደግሞ ተራ ነገር ነው።”
“ናትናኤል ነገሩ እንተ የምታስበውን ያህል ተራ ነገር አይመስለኝም፡፡ ብቻ እስቲ ቀጥል።” አብርህም የሚያውቀውን ከመዘርዘሩ በፊት ጓደኛው የሚለውን መስማት መምረጡ ግልጽ ነበር፡፡
“በቃ ይኸው ነው'ኮ አብርሃም፡፡ ሰውየው እንዴት ተሰወረ? ለምን ተሰወረ? ያንን ያንን ነወ ለማወቅ የምፈልገው:: ማለቴ... የምታውቀው በመሥሪያ ቤታችሁ በኩል የደረሳችሁበት ምሥጢር እንዳለ.… ናትናኤል ጓደኛውን ትኩር ብሎ ተመለከተው::
“ይኽው ነው?” የአብርሃም ድምፅ ማሾፍ የተቀላቀለበት ነበር፡፡
“እየው አብርሃም.. ናትናኤል ነገሩን ከሥር መህረቱ፡ መጀመር እንዳለበት ተረዳ፡፡ “ባለፋት ወራት ከሰላሳ የሚበልጡ ወታደራዊ አታሼዎች ወደየአገሮቻቸው እየተጠሩ ሄደዋል፡ ይሀ በራሱ ያልተለመደ ክስተት ነው፡፡ባለፈው ሳምንት ደግሞ የጊኒና የሞሮኮ ወታደራዊ አታሼዎች ወደየአገሮቻቸው ሄደው በተመለሱ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተገድለው ተገኙ።
የማገርምህ ነገር የሁለቱም : አሟሟት ተመሳሳይ መሆን ነው፡፡ ይህ ደግሞ
ገዳዩ ወይንም ገዳዬቹ ግንኙነት ያላቸው ያስመስለዋል፤ ሊሆንም ይችላል፡፡
ያህ ሀሉ ያነሰ ይመስል ኣሁን ደግሞ የላይቤርያው ኣታሼ . ድንገት
ተሰወረ፡፡”
ስለዚህ ናትናኤል የጠፋ የሰው አገር ሰው ሊያፈላልግ ቤቱን ቆልፎ ወጣ! ለምን?” አብርሃም ጥርጣሬ የወረሰው መሰለ፡፡
“አይደለም!” ናትናኤል በስጨት አለ፡፡ . “የሰውየው መጥፋት አያደለም ያን ያህል ያሳሰበኝ፡፡ ነገር ግን የሰውየው መሰወር ባለፈው ሳምንት ከተገደሉት ሁለት ዲፕሎማቶችና ባለፉት ጥቂት ወራት ከተደረጉት የአፍሪካ አገር ኤምባሲዎች እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አለው ብዬ
ስላመንኩኝ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አብርሃም፡፡ በተለያዩ የአፍሪካ
ባለሥልጣናት ላይ ባለፉት ወራት የደረሱ ኣደጋዎች አጋጣሚዎች ናቸው
ማለት ያከብደኛል፡፡”
ኣብርሃም ከጎኑ ካለ አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ አንስቶ ለናትናኤል አንድ ሲጋራ ከጋበዘው በኋላ ለራሱም አንድ አወጣና በእርጋታ
የለኮሳትን ሲጋራ ሁለቴ ስቦ ናትናኤልን ትኩር ብሎ ተመለከትው፡፡
“ናትናኤል” አለ ድንገት፡፡ “በጣትሀ ልትጠነቁለው የማይገባህን
በክንድህ እያቦካህው ነው::”
'“ምን

ማለትህ ነው?”
ምን እያደረግህ እንደሆነ ኣለቆችህ ያውቃሉ?”
“በደንብ፡፡ እንደውም አለቃዬ ናቸው ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ
አንድ ወረቀት እንዳዘጋጅ የጠየቁኝ፡፡ እንቆቅልሹን እንድፈታው ይፈልጋሉ፡፡”
ፈገግ አላ ኣብርሃም
“ናትናኤል.…እንቆቅልሹን እንኳን አንተ ታከታትለህ የምትፈታው ዓይነት አይመስለኝም::” .
“ለምን?” ናትናኤል አይኖቹን አጥብቦ ጓደኛውን ተመለከተው
“ሰውየው ሞቷል አይደል?”
“አልሞተም፡፡ “ ቢሞት ይቀል ነበር ለሁላችንም። ግን አልሞተም፡፡አለመሞቱም ነው ሁሉን እረፍት የነሳው።” አለ አብርሃም የሲጋራውን ጭስ
ከተናገራቸው ቃላት ጋር እየለቀቀው፡፡
“አልገባኝም::” ናትናኤል ትዕግሥት አጣ::
ናትናኤል በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ስለደረሰ አደጋዎች ለመተንተን በቂ መረጃ የለኝም፡፡ ወደኛው አዲስ አበባ ስንመለስ ደግሞ ቀደም ሲል የተለያዩ የአፍሪካ ኤምባሲዎች ለምን ወታደራዊ አታሼዎቻቸውን ወደየአገሮቻቸው - እንደጠሩ አላውቅም፡፡ ባለፈው ሣምንት ስለሞቱትም የጊኒና የሞሮኮ አታሼዎች ቢሆን ከሬሳዎቻቸው አጠገብ ከተገኙት ቀለሆችና ጥይቶች ከፈጠሩት ቁስል ተነስተን ሁለቱንም ሰዎች የተገደሉበት መሣሪያ በግብጽና በታንዛንያ ውስጥ ከሚሠሩ ሁለት ተዛማጅ ባለ 7.ሚሜ ሽጉጦች የተተኮሱ ናቸው ብለን ስላመንን ግድያዎቹ የተያያዙ ቢመስሉም ምክንያቱ
ለኛም ገና ግልጽ አልሆነልንም፡፡¨ ስለ ላይቤርያው አታሼ ግን መጠነኛ
ዕውቀት አለኝ፡፡ ቢሆንም የምነግርህ ሁሉን እያደለም። የምነግርህም ቢሆን
ላንተ እንጅ ለአለቃህ ለምታቀርበው ሪፖርት ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡”
ናትናኤል በመስማማት እራሱን ነቀነቀ፡፡
“ሰውየው አዲስ አበባ በሚገኘው የላይቤርያ ኤምባሲ እንዲሰራ ተመድቦ ከመጣ ስድስት ዓመት ሆኖታል፡፡”
ናትናኤል በመስማማት ጭንቅላቱን ነቀነነቀለት አብርሃም ቀጠለ፡፡ “እና…ከሶስት አመታት በፊት ነበር ሰውየው የአገሩን ምሥጢር ለእንግሊዝ የስለላ ድርጅት አሳልፎ እንደሚሰጥ
የደረስንበት፡፡በጊዜው የማያስተላልፋቸውን መረጃዎች በመሃል እየጠለፍን እየቀዳን እናስተላልፍ ስለነበርና መረጃዎቹ ፀረ ኢትዮጵያ ገጽታ የሌላቸው መረጃዎች ስለነበሩ በተለይም ስውየው በገዛ አገሩ ሁኔታ ላይ ያተኮረ
ስለነበረ ማስረጃዎች ብቻ እየሰበሰብን የምንጠቀምበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ
በትዕግሥት መጠባበቅን መረጥን፡፡”፣
“እንዴት ደረሳችሁበት?» ናትናኤል ጠየቀ አላስችል ብሎት፡፡
“የቅብብሎሽን ሠንሠለት መስበር ነው ዋናው ነገር አየህ ሰውየው ለጥቅም ሲል በገዛ አገሩ ላይ የሚሰልል ስለሆነ በአገሩ ኤምባሲ ውስጥ ከሚሰሩ የአገሩ ሰዎች
ራሱን መጠበቅ ነበረበት፡፡ ይህ ደግሞ በዙሪያው ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያን ላይ እንዲደገፍ ገፋፍቶታል፡፡” አብርሃም የጨረሰውን ሲጋራ በመተርኮሻው ውስጥ ኣጠፋና ንግግሩን ቀጠለ “እና የስረቀውን
መረጃ ከቀረጥ ነፃ ከሆኑ ሱቆች በሚገዛቸው የውስኪ ጠርሙሶች ውስጥ
እየደበቀ በኤምባሲው ወስጥ በሾፌርነት ለሚያገለግል ኢትዮጵያዊ ያቀብላል። በርካታ ዲፕሎማቶች ሕገወጥ ንግድ መፈጸማቸው የተለመደና ያደባባይ ምስጢር በመሆኑ ለሰውየው ጥሩ ከለላ ነበር።”
“ሾፌሩ ሁኔታውን ኣያውቅም? ” ናትናኤል ጠየቀ
“ለእሱማ ውስኪ ብሎ ነው ጠርሙሶቹን የሚሰጠው፡፡ መረጃ እንደያዘ አይነግረውም:: ግን ሾፌሩ ያውቃል፤ ማወቅ ብቻ ሳይሆን የኛ ሰው ነው፡፡ በሱ በኩል ነበር መረጃዎቹን የምንጠልፈው፡፡”
“እሺ” አለ ናትናኤል በመቀመጫው ላይ ወደፊት ፎቀቅ ብሎ እየተቀመጠ፡፡
“እና ሹፌሩ የውስኪዎቹን ጠርሙሶች በታዘዘው መሠረት ወስዶ ቤላ የመጠጥ ቤት ላላት ሴት ያስረክባል፡፡ እሷ ደግሞ የተለየ ምልክት ያለበትን መረጃ የያዘውን የውስኪ ጠርሙስ ለይታ ታስቀምጥና የእንግሊዝ ስለላ ሰዎች እንደመጡ ታስረክባለች።”
ሴትየዋም ታውቃለች ማለት ነው?”
“ኣሳምራ፡፡ ማወቅ ብቻ አይደለም ከዛም ታልፋለች፡፡ አየህ ሴትየዋ ፈላሻ ነች፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያና እሥራኤል የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን እንዳደሱ በየጊዜው ፈላሾች የኢትዮጵያ አይሁድ እየተባሉ ወደ እሥራኤል እንዲሄዱ ተፈቅዶላቸው ስለነበር እሷም ወደ እስራኤል ሄዳ ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙ ሣትቆይ በአመቷ የእሥራኤል ፓስፖርቷን ይዛ ተመለሰችና ሴላ መጠጥ ቤት ከፍታ ተቀመጠች፡፡ ስለዚህ ከላይቤርያው
ሰላይ የምታገኘውን መረጃ ለእንግሊዙ ኤም አይ ስድስት. ከማሳለፏ በፊት
የእሥራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ ሳያገኘው የሚቀር አይመስለኝም፡፡”
“ታዲያ ምንድን ነበር የምትጠብቁት? ኣትይዙትም ነበር እጅ ከፍንጅ?” ናትናኤል ኮስተር አለ፡፡
“ለምን? ምን አደረገና? አንድን ሰላይ ስለላ ስላካሄደ ብቻ ተንደርድረህ አትይዘውም:: ፡ በመጀመሪያ ደረጃ የሚያስተላልፋቸው መረጃዎች ኢትዮጵያን የሚጠቅሱ አልነበሩም፡፡ እርግጥ አልፎ አልፎ ብቻ አዎ . …ግን ጉዳት የሚያደርሱ አልነበሩም:: ሁለተኛ ነገር ሰውየው
ሳንጠይቀው የሚያጎርፍልንን መረጃ የእሱንም መኖር እንፈልገዋለን፡፡ ኣየህ.
እሱን ማስያዝ ወይም መያዝ ማለት የምትታለብ ላምህን አርደህ መብላት
ማለት ነው ገና ብዙ ልታልባት ስትችል፡፡”
“እሺ በል ቀጥል።" አላ ናትናኤል ሁኔታው ከጠበቀው በላይ እየተወሰሰበበት ሲመጣ ዝም ብሎ ማዳመጡን መርጦ፡፡
“እንዳልኩህ ሁኔታውን መሃል ላይ በሰነቀርነው ሾፌር አማካኝነት
እየተከታተልን ተጠባብቀን፡፡ ታዲያ ባለፈው ወር አታሼው ወደ አገሩ ሲጠራ
ተጋልጦ እንደሆነ ብለን ሰግተን ስለነበር ብዙ ጥያቄዎች ተከተሉ፡፡ አንደኛ
በሰውየው ምትክ ሌላ ሰው ከተተካ የእሱ ጠቃሚነት ሊቀር ሆነ፡፡ በግልጽ
ካስፈራራነው ደግሞ ምናልባት ተመልሶ ቢመጣ እንኳን ለመለመሉት የእንግሊዝ ሰዎች መጋለጡን ስለሚያሳውቅ አሁንም ጠቃሚነቱ ሊደርቅ ነው:: ከዛ ውጣ ውረድና ክርክር በኋላ ሰውየውን ቀርበን ላለማነጋገርና ከተመለሰ ሥራችንን እንደቀድሞው ለመቀጠል አገሩ እንደሄደ ከቀረም ሞኖሮቪያ ባሉ የኛ ሰዎች አማካኝነት ቀርበን ስለፈጸመው ወንጀል
የምናውቅ መሆናችንን ገልጸን ግነኙነታችንን በማስገደድና በማስፈራራትም ቢሆን ለመቀጠል ወሰንን፡፡”.....

❤1
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
...በመጨረሻም አራተኛዋ ታካሚ ላና ግሬይ ናት። ላና ግሬይ በፊት ላይ መጠነኛ ዝነኛ የነበረች የፊልም አክትረስ ብትሆንም መክፈል የሚገባትን ክፍያ አዘግይታ የምትከፍል ወይንም ጭራሽ የማትከፍል ደምበኛዋ (ታካሚዋ) ናት።
ላናን አስመልክቶ ረዳቷ ትሬይ ሬይድሞንድ “ላና እንደ ደንበኛ ልትቆጠር
አትችልም” ይላል። በተለያዩ ጊዜያት ላይ ስለ እሷ ሲያወሩ “ደምበኞች እኮ ይከፍላሉ። ስለዚህ ለእሷ የበጎ አገልግሎትን እየሰጠሻት እንደሆነ አስቢ። በቃ በምክንያታዊነት እየረዳሻት እንዳለሽም ብታስቢ ይሻላል” ይላል፡፡
“ብለህ ነው?” ኒኪ ፈገግ ትልና “እሺ አንተ ደግሞ ለእኔ ምንድነኝ ብለህ እንደምታስብ ብትነግረኝ ደስ ይለኛል” ትለዋለች፡፡ “እኔ?” ይልና ትሬይ ከሳቀ
በኋላ “እኔ ደግሞ ያው በምክንያታዊነት ከምትረጂያቸው ቅዱሳን ጎራ ነው
የምመደበው። ይህም ቢሆን ግን ዶክ እኔን ማባረር አትችይም። በቃ ልክ
እንደ እዳሽ ቁጠሪኝ። እሱ ረዳትዋ፣ ሠራተኛዋ ባይሆን ኖሮ ስራዋን ቀጥ
አድርጋ መስራት የምትችል ሁሉ አይመስላትም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ከሟች
ባሏ ጋር የሚያያዝ ታሪክ ስላለው አንድ አንዴ በእሱ ውስጥ ባሏን የምታስታውስበት ሰው ነው። ዶውግ ትሬይን ከጎዳና ላይ አንስቶ ከአደንዛዥ
ዕፅ ሱሰኝነትም ነፃ አውጥቶት ሰው ያደረገው ልጅ ነው:: ለብዙ ወጣቶች
ለትሬይ ያደረገውን ነገሮች ቢያደርግላቸውም ግን ሟች ትሬይን በጣም የሚወደው ልክ እንደ ልጁ ነበር።
'እኔ ልወልድለት ያልቻልኩት ልጁ ነበር. ብላ አሰበች
ትሬይ ስራውን ጨርሶ ቀና ሲል በጎን በኩል ኒኪን ስለተመለከተም “
ዶክ ወደ ቤት እየሄድሽ ነው?”
“እየሄድኩኝ ነበር የምትፈልገው ነገር አለ ልቆይ?”
“ኧረ የለም!” ብሎ ጠንካራ ነጭ ጥርሱን በፈገግታ ሲያሳያት ጠይም ፊቱ እያበራ “ችግር የለውም ሂጂ” አላት፡፡
“እርግጠኛ ነህ?”
“አዎን እርግጠኛ ነኝ፡፡ የተለየ ነገር ከገጠመኝ እደውልልሻለሁ” አላት፡፡
የቢሮዋን ህንፃ ለቅቃ እንደወጣች ከውጪ የተቀበላት የካሊፎርንያ ሰማያዊ ሰማይ ላይ የወጣው ሀይለኛ አይን የሚያጭበረብር ፀሀይ ተቀበላት።
ፀሀዩ የትላንቱን ዝናብ ለመበቀል ይመስል በጣም ድምቅ ብሎ ነው የወጣው።
ኒኪ ከፀሀይ ይልቅ ዝናብ ትወድ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ሟቹ ባሏን ዶውግ ስለሚያስታውሳት ዝናብ ትጠላለች። አዎን ስለ ባሏ ስታስብ በጣም ከፍተኛ የሆነ የማይለቃት ንዴት ይሰማታል፡፡ አሟሟቱን ስታስብ የሚመጣባት የቴስላ መኪና ጎማዎች በአስፋልቱ ላይ በሀይል ሲሽከረከሩ ነው። በተለይ ደግሞ ከፊት ለፊቱ የሚገኘው የመንገድ መብራት ላይ
ለመቆም የፍሬን ፔዳሉን እየጨፈለቀ መኪናውን ሊያቆመው ሲሞክር እምቢ
ይለዋል። ምናልባት በተስፋ መቁረጥ እና በድንጋጤ ተሞልቶ ጮሆ ይሆን?
የጮኸ ይመስለኛል መቼስ...
እስከዚያች በመኪና አደጋ ህይወቱን እስካጣበት ቀን ድረስ ዶውግ በጣም
ምርጥ፣ ደስተኛ እና የተባረከ የትዳር አጋር ነው ብላ ነበር የምታስበው:: ግን
ያ የተረገመ ቀን በትዳራቸው ላይ ያላት አመለካከት ትክክለኛ እንዳልነበረ
እንድታውቅ አደረጋት፡፡ አስቀያሚውን እና ጥሬ እውነቱንም ለመቀበል በቃች።
አሁን ዶውግ ሞቷል፡፡ እሷም ብቻዋን ናት፡፡ ህይወቷም በማያባሩ ቅዠቶች እና ባልተመለሱ ጥያቄዎች ሁሌም እንደተረበሸ ይገኛል። ከአደጋው
ቀን በፊት ኒኪ አንድን ሰው በጣም ማፍቀር፣ በጣም መናፈቅ እና በጣም
መጥላት እንደሚቻል አስባ አታውቅም ነበር፡፡ ግን አሁን ይሄው ሦስት ስሜቶቿን እያስተናገደች የየቀን ውሎዋን በስርአቱ ለማካሄድ ትጥራለች።
አንድ አንዴ በስራዋ የተሰላቸች ይመስላታል። ያኔ በህይወት ሳለ
እንደሚያክማቸው የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች ሁሉ በጣም ይጨንቃታል።
የዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ስትሆን ደግሞ እነዚህን ልታክማቸው ያልቻለቻቸውን ታካሚዎቿን አንገት ጨምድዳ ልታርገፈግፋቸው ሁሉ
ይዳዳታል።
በቃ እያርገፈገፈቻቸው “ስለፈጣሪ ብላችሁ ከዚህ ስሜት ውጡ!”
“ወደ ኋላ ወደ ፊት እያላችሁ ራሳችሁን አታሳምሙ” ልትላቸው ትፈልጋለች፡፡
ግን ሊዛ ፍላንግስ?' ሊዛ ፍላንግ ከሌሎች ታካሚዎቿ በተሻለ መልኩ ለውጥ እያመጣች መሆኗን እያየች ነው:: ሊዛ ፍላንግ ቢያንስ ለመለወጥ ራሷን በማዘጋጀት ከክላርክ በርክሌ ትለያለች፡፡ ግን እንደ በርክሌይ በጣም ብልህ እና ጎበዝ አይደለችም፡፡ እንዲያውም እሷ የምታስበውን ነገሮች ሁሉ መለየት የማትችል ደነዝ ሴት ናት፡፡ ያም ሆኖ ለለውጥ ተዘጋጅታለች እና ይሄም አንድ ነገር ነው።
ትላንት ማታ ሊዛ ከወጣች በኋላ ኒኪ በሊዛ ቀንታ ነበር፡፡ “እሷ ወጣትና
ቆንጆ እንዲሁም ለወደፊቱ ብሩህ ህይወትም የሚጠብቃት ሴት በመሆኗ
ልቀናባት ይገባልን?' ብላ ራሷን ጠይቃ መልሱን አግኝታዋለች።
መልሱ ደግሞ እሷ ከዚያ አስቀያሚው የበፊት ህይወቷ እርምጃ ለመጀመር መንገዷን ስለጀመረች ነው። በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና ትላንትና ማታ ወደ ቤቷ ለመሄድ ከቢሮዋ በመኪና እየወጣች እያለ ከዚህ የቅናት ስሜት ለመውጣት ለጥቂት ሰከንዶች ያህል የመኪናዋን ሞተር አጥፍታ ጠባቡ መንገድ ላይ ቆማ ነበር፡፡ ራሷን ካረጋጋች በኋላም መኪናዋን
እያሽከረከረች ወደ ቤቷ አመራች፡፡ ቤቷ ደርሳም አንድ ሙሉ ጠርሙስ ወይኗን ጨረሰች (ይሄ አጠጣጧ የሰሞኑ መገለጫዋ ሳይሆን አይቀርም)።
መጠጧን እንደጨረሰች ደግሞ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ከእንቅልፉ ስትነቃ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት ሆኖ ነበር። ለብዙ ሰዓት መተኛቷ ደግሞ ዛሬ ቀኑን በጥሩ ስሜት እንድታሳልፍ አድርጓታል። ይህን ስሜቷን ማምሻው ላይ ክላርክ ቢበርዝባትም እሱን ከሸኘች በኋላ በግድ ራሷን ወደ ቀደመው ጥሩ ስሜት መለሰች እና ወደ ቤቷም ሄደች፡፡
ቤቷ ገብታ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው መኝታ ቤቷ ከማምራቷ በፊት ቴሌቪዥኑን ከፈተች፡፡ የቴሌቭዥኑ ድምፅ ቤት ውስጥ ብቻዋን እንዳልሆነች እንድታስብ ስለሚያደርጋት ቲቪውን ባታየውም ሁሌም ትከፍተው ነበር።መኝታ ቤቷ ገብታ የስራ ልብሷን ቀይራ ቁምጣ እና ስኒከር ጫማዋን አደረገች:: ዛሬ ከውቅያኖሱ ዳርቻ ስትሮጥ ደስታ፣ መልካም ምኞት እና ተስፋን አርግዛ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ቢያንስ የቀን ላይ ደስታዋን ለምሽቱ ጠብቃ ለማቆየት እና ለለውጥ ያህል ነበር ለመሮጥ የፈለገችው።
የሩጫ ልብሷን አድርጋ ወደ ታች እንደወረደች ቴሌቪዥኑ “አንዲት
ዕድሜዋ በሀያዎቹ መጨረሻ ላይ የምትገኝ ሴት 10ኛው ጎዳና ላይ ተጥላ
ተገኘች” ብሎ ነበር የደረሰችው፡፡ እና ድምፁን ጨመረች። “ሟቿ ነጭ ስትሆን በጩቤ ብዙ ቦታ ተወግታ ነው የተገኘችው። ፊቷም እንዳይለይ ሆኖ
በጣም ስለተቆራረጠ የሟቿን ማንነት ማወቅ አልተቻለም። ከመሞቷ በፊት
በጣም ብዙ አካላዊ ስቃዮች እንደደረሱባት የሚያሳዩ ነገሮች በድኗ ላይ ተገኝቷል።” በመቀጠልም የስፓርት ዜና...” ብሎ ቴሌቪዥኑ ወሬውን
ሊቀጥል ኒኪ እዚህ ሀገር ስንት አይነት አሰቃይተው የሚገድሉ ዕብድ ሰዎች
አሉ ብላ አሰበች እና ቲቪዋን አጥፍታ ወደ በሩ አመራች።
ልክ ፀሀይ ሊገባ ሲልም ስልኳ ደጋግሞ በመጮሁ ምክንያት ሩጫዋን አቋርጣ ቁና ቁና እየተነፈሰች ጆሮዋ ላይ የሰካችውን የስልክ መቀበያ በጣቷ
ተጭና ስልኳን አነሳችው::
የደወለው ትሬይ ሬይሞንድ ነበር። ድምፁም እያለቀሰ መሆኑን ያሳብቅበታል “ወይኔ! ወይኔ! ዶ/ር ኒክ፡፡ ሊዛ...” ብሎ ሊቀጥል ሲል ዶ/ር ኒክ “እስቲ ምን ሆነሀል? ተረጋጋ፡፡ አንድ ሁለቴ አየር እየሳብክ አስወጣ አለችው። እውነት ነው ትሬይ ሊዛ ላይ አይኑን እንደጣለ ሊዛን ሲያይ በሚያሳያቸው ነገሮች ይታወቁበታል፡፡

👍2😁1
ትሬይ እሷ እንዳለችው ሁለት ጊዜ አየር በረጅሙ ስቦ አስወጣና “ዶ/ር ኒኪ ሊዛ ፍላገን ሞተች እኮ!” አላት፡፡
“ምንድን ነው የምታወራው?”
“አዎን ዶ/ር አሁን ነው ዜናውን በቲቪ እያየሁ ያለሁት። አንድ ጨካኝ ሰው እሷን በጩቤ ደጋግሞ ወግቶ ከገደላት በኋላ 10ኛው ጎዳና መንገድ ዳር ሬሳዋን ጥሎታል” አላት። ይህንን ነገር ትሬይ እንደነገራትም ጆሮዋ ያቃጭልባት ጀመር። 'ወይ ሊዛ እኔ በእሷ ቀናሁባት? ምንድን ነው ነገሩ?በፍፁም እንደዚህ እንድትሆን አልተመኘሁም' ብላ በሀሳብ ቡዝዝ ስትል
“ዶ/ር እየሰማሽኝ ነው? ዶ/ር” የሚለው የትሬይ ድምፅ ከሀሳቧ አባነናት እና “ትሬይ ነገ ጠዋት እናወራለን” ብላ ስልኩን ዘጋች።
አሁን ነገሮች ሁሉ ሊቀጥሉ ነው። የሌሊት ሌሊት አስፈሪ ቅዥቷም ካቆመበት ሊቀጥል ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ልጅ ዶ/ር ሮበርትሰን ልናናግራት እንፈልጋለን። ዶ/ር ኒኮላ ሮበርትስ።
በጣም ቀላል ጥያቄ ነው የጠየቅንህ አለች ወይስ የለችም?” ትሬይን ጠየቀው። ሁለቱ ፓሊሶች ከትሬይ ሬሞንድ ዴስክ ፊት ለፊት ጎርደድ ጎርደድ እያሉ ነው:: እሱ ጥቁር፣ እነርሱ ደግሞ ነጭ ያውም ፖሊስ
በመሆናቸው ብቻ ወዳጅነት አይኖራቸውም፡፡ በተለይ ደግሞ የሞት ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ ዌስት ሞንት ደቡብ ሎስ አንጀለስ ውስጥ
የዕፅ አዘዋዋሪ የነበረ አንድ ጥቁር እንዴትስ ብሎ ለነጭ ፖሊሶች የወዳጅነት
ስሜት ይኖረዋል፡፡
“ቢሮ ውስጥ ከታካሚዋ ጋር ናት”
ከፖሊሶቹ ውስጥ አጭሩ፣ ወፍራሙ፣ በዕድሜ ትልቅ የሚመስለው እና ነጭ የመሰለ ከንፈር ያለው ፖሊስ ትሬይን በመጥፎ አይን እየተመለከተው እና በአገጩ ወደ ተዘጋው የቢሮ በር እያመለከተ “እኮ እዚህኛው ክፍል
ውስጥ ማለትህ ነው?” አለው፡፡ ሁለቱም ፖሊሶች የፖሊስ የደምብ ልብስ
ካለመልበሳቸውም በላይ የፖሊስ ባጃቸውንም ጭምር ሳያሳዩት አለቃነት
በሚታይበት ድምፅ ነበር የሚያናግሩት።
“አዎን እዚያ ክፍል ውስጥ” ብሎ ትሬይ ሲያረጋግጥላቸው ወፍራሙ ፖሊስ ፈገግ ብሎ ወደ ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ቢሮ በር መራመድ ጀመረ።ይሄኔ ትሬይ “ግን ጌታዬ እሷ ስራ ላይ ስላለች መረበሽ አትፈልግም” አለው።
ወፍራሙ ፖሊስ ግን መራመዱን ስላላቆመ አብሮት የመጣው ተጨማሪ
ፖሊስ የወፍራሙን ትከሻ ይዞ “ተው ሚክ ስራዋን እስክትጨርስ መጠበቅ
እንችላለን።” አለው እና የመጠበቂያ ክፍል ውስጥ ከሚገኙት የጣልያን ሌዘር
ወንበሮች አንደኛው ላይ አረፍ አለ፡፡ ሳይኮሎጂ ቱዴይ' የሚል መፅሄትን
ከጠረጴዛው ላይ አነሳና “የአንድ ቴራፒ ክፍለ ጊዜ 50 ደቂቃ ነው አይደል?
ጥላኝ የሄደችው ሚስቴ ቴራፒ ታደርግ ስለነበር ስታወራ ሰምቼያት ነበር::አለው ረጅሙ ከወፍራሙ ፖሊስ በዕድሜ የሚያንሰው እና መልከመልካሙ ፖሊስ፡፡ “የትኛዋ ሚስትህ ናት ደግሞ?” ብሎ ወፍራሙ ፖሊስ ነጭ ከንፈሩን ለጥጦ ጠየቀው፡፡ “ሁሉም ያው ናቸው፡፡ አስቸጋሪ ስለነበርኩኝ ቴራፒ ጋ ይሄዱ ነበር” ብሎ እያሾፈ መለሰለት፡፡ ወፍራሙም የስራ
ባልደረባው በቀለደው ቀልድ ፈገግ እንኳን ሳይል አንደኛው ወንበር ላይ
ፊቱን አጨፍግጎ ተቀመጠ።
ትሬይ የ ኤሌ.ፒ.ዲ ፖሊሶችን ከልጅነቱ ጀምሮ ሌባ እና ፖሊስ እየተጫወተ ስላደገ በደንብ ነው የሚያውቃቸው። እነርሱ ምን ያህል ዘረኛ እንደሆኑም ያውቃል። ስለሆነም የአርያን ዘር ነው ያለን ብለው ከሚመፃደቁት ናዚዎች እኩል እንደሆኑ ነው የሚያውቀው፡፡ ለዚህም
ይመስላል አንድን ጥቁር ሰው ተኩሰው ከገደሉ በኋላ ነው ጭንቅላታቸውን
ለማሰብ የሚጠቀሙበት፡፡ ምናልባትም እኮ ይህ ዘረኛ ፖሊስ ክንዱ ላይ የናዚ
አርማ የሆነውን ስዋስቲካን ሁሉ ተነቅሶት ሊሆን ይችላል። አጠገቡ ያለው በዕድሜ አነስ ያለ ፖሊስም ቢሆን በግልፅ ጥላቻ እና ንቀቱን አያሳየኝ እንጂ አጥንቱ ድረስ የሚዘልቅ ከፍተኛ ዘረኝነት የተጠናወተው ሊሆን ይችላል። ያም ቢሆን ግን ሥርአት ያለው እና ተግባቢ ነገር ስለሆነ ከዶር ሮበርትስ ብዙ መረጃን ሊያገኝ ይችላል ብሎ ሬይ ግምቱን በራሱ አሰበ፡፡
በሀሳቡም ረካ እና በሳይኮሎጂስት (ስነ አዕምሮ ሀኪም) ዘንድ በመስራቱ የተነሳ ሰዎችን ቶሎ መረዳት መጀመሩን ለራሱ ነገረው።
“ለምን ያህል ጊዜ ትቆያለች?” ብሎ ባለ ነጩ ከንፈር ፖሊስ ግድግዳው ላይ የተሰቀለውን የግድግዳ ሰአት እያየ ትዕግስት አልባ በሆነ እና በቁጣ
ድምፅ ጠየቀው።
“ከአስራ አምስት ደቂቃ በኋላ ትጨርሳለች” አለና ትሬይ ዶ/ር ሮበርትሰን
ስለ ሊዛ ሊጠይቋት እንደመጡ ሲያስብ ደግሞ ስለ ፖሊሶቹ የተሰማው መጥፎ ስሜት አየለበት፡፡ እነዚህ መርማሪ ተብዬ ፖሊሶች የሊዛን ህይወት እያነሱ እየጣሉ ምርመራቸውን እንደጀመሩ ማሰብ ብቻ አስጠላው::
ትሬይ ባደገበት መንደር ውስጥ ከልጅነቱ ጀምሮ ሰዎች በግድያ ህይወታቸውን ሲያጡ እየተመለከተ ነው ያደገው፡፡ በጣም ብዙ ግድያዎችም ሲፈፀሙ ብዙ ጊዜ በአይኑ በብረቱ ተመልክቷል፡፡ እነዚያ ግን ወሮበላዎች እርስ በእርስ በመተኮሳቸው ምክንያት የሚከሰት የከተማው ሀይለኛ የተደራጁ ቡድኖች አንዱ በአንዱ ላይ ሲያምፅ የሚከሰቱ ሞቶች ስለሆኑ የመንደሩ ሰዎች ሊያዝኑ እንደሚችሉ ነገር ግን በጣም ሊደነግጡ
እንደማይችሉ ያውቃል።
እዚህ ግን ግድያዎች ይለያሉ። ሊዛ እሱ በልጅነቱ እንዳደገበት መንደር ውስጥ ያደገችው። እሷ ነጭ እና ሀብታም ብቻ ሳትሆን ቆንጆም ናት። ይህ ደግሞ የአብዛኛዎቹ የነጮች የህይወት ክፍል ነው። በእነዚህ ሀብታም እና ነጭ ሆነው ኑሯቸውን በሚኖሩ ሰዎች መካከል እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ግድያዎች ሲከሰቱ እምብዛም አይስተዋሉም። ዶ/ር ሮበርትሰም ብትሆን የዚህኛው ህይወት አንደኛዋ አካል ናት። ትሬይ ግን አይደለም፤ ያም ቢሆን ግን ባሏ ዶ/ር ዳውግ ከመሞቱ በፊት ወደ እዚህ እነርሱ እየኖሩ እንዳሉት ህይወት በራሱ በዶር ዶውግ ተጋብዞ ነበር። ምን መጋበዝ ብቻ እንዲያውም ዶክተሩ እንደ ልጁ ሁሉ እንደሚያየው ጭምር ያውቃል።
እነዚህ ዲቃላ የሆኑ መርማሪ ፖሊሶች የእነርሱን በጥላቻ የተሞላ አለምን ወደ እዚህ ብሩህ እና ምርጥ ወደ ሆነው የህይወት ክፍል ይዘው መምጣት አይገባቸውም።
የሚጠጣ ነገር ትፈልጋለህ?” ብሎ ትሬይ ትሁቱን እና በዕድሜ አነስ ያለውን ፖሊስ ጠየቀው፡፡
“አመሰግናለሁ ምንም አልፈልግም”
ሎካ ልትሰጠኝ ትችላለህ?” ብሎ ወፍራሙ ጥጋበኛ ፖሊስ ከስልኩ እስክሪን ላይ አይኑን ሳይነቅል እና ቀና ሳይል ትሬይን አዘዘው።ትሬይን በወፍራሙ መርማሪ ትህትና የጎደለው አጠያየቅ በጣም ተናድዶ ሰውነቱ ሽምቅቅ አለበት፡፡ ስለሆነም ኮካ እንደሌለው ሊነግረው እና
እምቢታውን ሊያሳየው ፈለገ፤ ነገር ግን ውስጡ ያለው ደመ ነፍሱ ፖሊሶችን በተለይ ደግሞ ፊት ለፊታቸው ሆነህ አትሳፈጣቸው የሚል ምክርን ለገሰው፡፡
የኒኪ ቢሮ ውስጥ አኔ ባቴማን ከቀሚሷ ሥር የሚገኙትን የሚያማምሩ እግሮቿን በድጋሚ አጣመረች። ኒኪ አኔ ቤታማንን እየተመለከተች በውስጧ ማሰብ ጀመረች፡፡ ሁሉም እንቅስቃሴዋ ሞገስ ያለው፣ የታሰበበት እና የተቀናጀ ነው ብላ አሰበች፡፡ ትላንት ማታ ኒኪ በድጋሚ አኔን በህልሟ አይታት ነበር። “ምርጥ የቫዩሊን ተጫዋች (ሙዚቀኛ) እና የባሌት ዳንሰኛ
ምናልባትም ተመሳሳይ ነገር ሳይስራቸው አይቀርም' ብላ ኒኪ አሰበች። ብቻ
የትኛው ትክክል ይሁን ወይንም አይሁን አኔ ኑሮ በተባለው የህይወት ጎዳና
ላይ ከውስጧ ከሚወጣው ሙዚቃ ጋር በሚጣጣም መልኩ ራሷ በፈጠረችው
የዳንስ አይነት በመደነስ ላይ እንዳለች ይገባታል።
“ያንቺ ታካሚ ነበረች አይደል? ልክ እንደ እኔ ማለት ነው?” ብላ አኔ ኒኪን ጠየቀቻት፡፡
“ስለ እሷ አብራርቼ ልነግርሽ እንደማልችል መቼስ ታውቂያለሽ አይደል?” ብላ ኒኪ

👍3😁1
ጨዋነት በማይታይበት ሁኔታ መለሰችላት፡፡ እንደ ማንኛውም ሰው ሁሉ አኔ የሊዛ ፍላገንን የግድያ ዜና ሪፖርት
ተመልክታለች። ከቴሌቪዥኑ መስኮቶች ስለ ሊዛ ግድያ የቀረቡት ሪፖርቶች
ደግሞ ውስጧን ስለረበሿት ከኒኪ ጋር በጉዳዩ ላይ ማውራት ስለፈለገችም
ነበር ጥያቄውን ያቀረበችው፡፡
“ባትነግሪኝም ችግር የለውም” አለች ጭኗ ላይ አይኗን ተክላ፡፡ በኮሪደሩ
ላይ ለብዙ ጊዜ ስንተላለፍ አስታውሳታለሁ፤ በጣም የምታሳዝን ሴት ናት” “በጣም” አለች ኒኪ፡፡ ሊዛ የመጨረሻው የህክምና ጊዜዋ ላይ ከኒኪ ቢሮ ስትወጣ በጣም በትልቅ ተስፋ ተሞልታ ነበር፡፡ ህይወቷንም በደንብ አድርጋ ለመምራት ቁርጠኛ ሆና ስለነበር ነው ኒኪ በሊዛ ሞት በጣም የተሰማት።
አሁን ሊዛ በህይወት ስለሌለች ኒኪ ልትረዳት አትችልም፡፡ በህይወት
የምትገኘውን አኔን ግን ልትረዳት እንደምትችል ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ
ታምናለች:: በእርግጥም ደግሞ አኔን ቶሎ ቶሎ እያገኘቻት ስለምትመክራት ለውጧን እየታዘበች ነው፡፡ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በጣም ተወዳጅ እና ተደናቂ የቫዩሊን ተጫዋች ነበረች። በሃያ ስድስት ዓመቷ እጅግ በጣም ስኬታማ ሙዚቀኛ ለመሆን በቅታለች፡፡ ስትታይ ህፃን፣ አንድ አንዴም የህፃን ሥራ ብትሠራም ከዕድሜዋ በላይ ነው የኖረችው፡፡ ገና የአስራዎቹን ዕድሜ
ሳትጨርስ በተለያዩ ሀገራት እየዞረች የሙዚቃ ሥራዎችን ያቀረበች ምርጥ
ሙዚቀኛ ናት፡፡ በመጨረሻ በልጅነቷ በጣም ሀብታም፣ ሞገስ የሞላበት እና
በዕድሜ በጣም የሚበልጣትን ሰው አግብታ በትዳር ስትኖር ቆየች።
አኔ ሲያይዋት የምትስብ ሴት ናት፡፡ ትንሽነቷ እና ስሜተ ስስ መሆኗ
ደግሞ ቆንጅዬ አሻንጉሊት ያስመስላታል፡፡ በእጇ ቫዩሊን ካልያዘች በጣም አይን አፋር እና ፈሪ ነገር ናት። ቫዩሊን እጇ ላይ ሲሆን ግን አኔ ፍፁም በሙዚቃው እና በችሎታዋ ተመስጣ ወደ ድንቅ ሴትነት ትለወጣለች።ቸኮሌት በሚመስሉ ቡናማ ውብ አይኖቿ እና እንደ ንፁህ እምነ በረድ
በሚያበራው የሰውነት ቆዳዋ እንዲሁም ደግሞ በችሎታዋ እየተሳቡ ብዙ
ወንዶች የራሳቸው ሊያደርጓት ብዙ ሞክረዋል። ሁሉንም አሸንፎ ሚስቱ
ያደረጋት ግን ባሏ ነበር፡፡ ከተጋቡ በኋላ ደግሞ ወደ ራሱ ትልቅ ቤት (ስቴት) ወሰዳት። በጣም ብዙ ስጦታዎች ልብሶችን፣ አድናቆቶችን እና ከፍተኛ የሆነ ፍላጎቱን ሁሉ ያለገደብ ሰጣት፡፡ እና ከሚወዷት አድናቂዎቿ ለያት። የራሱ ብቻም አደረጋት።
ለማንኛውም አኔ በጣም ቁርጠኛ የሆነ ውሳኔን በመውሰድ እሱን ጥላው ወደ ተወለደችበት ሎስ አንጀለስ ከተማ ጥላው መጣች፡፡ ባሏን ስለማትወደው
አልነበረም፡፡ ግን በቃ ህይወቷ እየጠራ ፋታ ነሳት። የሙዚቃ ጥሪዋንም ተከትላ ወደ ሎስ አንጀለስ ለመመለስ በቃች፡፡ በትዳርዋ መበላሸት ምክንያት በጣም ጭንቀት ውስጥ በመግባትዋም ከጭንቀትዋ ለመዳን ወደ ኒኪ ቢሮ መጣች....

ሶስት የገጠር ሴቶች
(አለምነሽ ፣ ካሳነሽ ፣ አፀዱ፡፡)
.
.
"ዓለም ነሽ ፣
ካሳ ነሽ ፣
አፀዱ" ሚባሉ ፣ ሶስት ባልንጀሮች
በትልቅ መኪና ….
ተጭነው የመጡ ፣ የህዝብ መዝሙሮች
ከገጠር ተነስተው…
ዘመድ ለመጠየቅ ፣ ከተማ ሲወርዱ
የዘመዳቸው ቤት ጠፍቷቸው መንገዱ
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣
ቆሜ እየጠበቅሁሽ ፣
ከከተሜው ጋራ ፣ ኑሮን ተላመዱ፡፡
እያት ዓለምነሽን…
"ንግድ" በምትለው ፣ በሰፊው ጎዳና
"ኑሮ" በምትለው ፣ በትልቅ መኪና
እድሜዋን ስትጭነው ፣
እንጀራ ለመብላት ፣ እንጀራ ሻጭ ሆና፡፡
ሀገር ነች አለምነሽ !
አካሄድ ለማያውቅ ፣ ለጠፋበት መንገድ
ሁለት ፍቺ አለው !
እንጀራ ለመብላት ፣ እንጀራ መነገድ፡፡
አንድም ጥያቄ ነው !
እንጀራ ሚሸጥን
‹‹እንጀራህ ምንድን ነው? ›› ፣ ብሎ እንደመጠየቅ
እንጀራ ጋጋሪን ፣
"እንጀራ ይውጣልህ" ፣ ብሎ እንደመመረቅ
ቀላል ስላልሆነ ፣ መልሱ አይታወቅም
አንድም መልስ ይሆናል!
መንገድ ለጠፋበት፣
መድረሻ ነው እንጂ ፣ ሆድ አያስጨንቅም፡፡
//
እያት ካሳነሽን…
"ህይወት" በምትለው ፣ በሰፊው ጎዳና
"ነውር" በምንለው ፣ በትልቅ መኪና
ሀፍረቷን ጫጭና ፣
ሴትነቷን ስትጥል ፣ ሴት አዳሪ ሆና፡፡
ሀገር ነች ካሳነሽ !
አካሄድ ለማያውቅ ፣ ለጠፋበት መንገድ
ብዙ ፍቺ አለው !
ሴት አዳሪ ሆኖ ፣ ወንድ አዳሪን ማብረድ፡፡
አንድም ጥያቄ ነው !
ከአንደኛው በቀር ፣ መልሱ አይታወቅም
አንድም መልስ ይሆናል !
መንገድ ለጠፋበት ፣
መድረሻ ነው እንጂ ፣ ክብር አያስጨንቅም፡፡
//
ተመልከች አፀዱን…
"ሀብት" በምትለው ፣ በሰፊው ጎዳና
ምንጩ ባልታወቀ ፣ በግሏ መኪና
ንቅሳቷ ጠፍቶ ፣
ከተሜ መስላለች ፣ ግጥርናዋን ጭና፡፡
ሀገር ነች አፀዱ !
አካሔድ ለማያውቅ ፣ ለጠፋበት መንገድ
ሁለት ፍቺ አለው !
ሌሎችን ለመምሰል ፤ ከራስ ላይ መሰደድ፡፡
አንድም ጥያቄ ነው ፣ መልሱ ባይሰጥም
አንድም መልስ ይሆናል !
መንገድ ለጠፋበት፣
መድረሻ ነው እንጂ ፣ ማንነት አይበልጥም፡፡
//
ይሄ ሁሉ ሲሆን…
"እመጣለሁ" ብለሽ ፣
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣ ከሰፊው ጎዳና
ይህን ያህል ጊዜ ፣
ጠብቄሽ ጠብቄሽ ፣ አልመጣሽምና
እስክትመጪ ድረስ…
አለም ነሽ ፣
ካሳ ነሽ ፣
እንዲሁም አፀዱን ፣ የጠፋቸው መንገድ
እኔንም ጠፍቶኛል !
መድረሻ የለኝም ፣ ሳላገኝሽ ብሄድ፡፡
ስለዚህ ዘልዓለም ፣
እስክትመጪ ድረስ ፣ እጠብቅሻለሁ
አንቺ ራሷ ሀገር ነሽ !
ቀርተሸ መጠበቄ ፣ ሁለት ፍቺ አለው፡፡
አንድም ጥያቄ ነው ፣ መልሱ ይቸግራል
አንድም መልስ ይሆናል!
ፍቅር የጠፋበት ፣
አለምን ቢያተርፍም ፣ ሁሉንም ይከስራል፡፡
(አለምነሽ ፣ ካሳነሽ ፣ አፀዱ፡፡)
.
.
"ዓለም ነሽ ፣
ካሳ ነሽ ፣
አፀዱ" ሚባሉ ፣ ሶስት ባልንጀሮች
በትልቅ መኪና ….
ተጭነው የመጡ ፣ የህዝብ መዝሙሮች
ከገጠር ተነስተው…
ዘመድ ለመጠየቅ ፣ ከተማ ሲወርዱ
የዘመዳቸው ቤት ጠፍቷቸው መንገዱ
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣
ቆሜ እየጠበቅሁሽ ፣
ከከተሜው ጋራ ፣ ኑሮን ተላመዱ፡፡
እያት ዓለምነሽን…
"ንግድ" በምትለው ፣ በሰፊው ጎዳና
"ኑሮ" በምትለው ፣ በትልቅ መኪና
እድሜዋን ስትጭነው ፣
እንጀራ ለመብላት ፣ እንጀራ ሻጭ ሆና፡፡
ሀገር ነች አለምነሽ !
አካሄድ ለማያውቅ ፣ ለጠፋበት መንገድ
ሁለት ፍቺ አለው !
እንጀራ ለመብላት ፣ እንጀራ መነገድ፡፡
አንድም ጥያቄ ነው !
እንጀራ ሚሸጥን
‹‹እንጀራህ ምንድን ነው? ›› ፣ ብሎ እንደመጠየቅ
እንጀራ ጋጋሪን ፣
"እንጀራ ይውጣልህ" ፣ ብሎ እንደመመረቅ
ቀላል ስላልሆነ ፣ መልሱ አይታወቅም
አንድም መልስ ይሆናል!
መንገድ ለጠፋበት፣
መድረሻ ነው እንጂ ፣ ሆድ አያስጨንቅም፡፡
//
እያት ካሳነሽን…
"ህይወት" በምትለው ፣ በሰፊው ጎዳና
"ነውር" በምንለው ፣ በትልቅ መኪና
ሀፍረቷን ጫጭና ፣
ሴትነቷን ስትጥል ፣ ሴት አዳሪ ሆና፡፡
ሀገር ነች ካሳነሽ !
አካሄድ ለማያውቅ ፣ ለጠፋበት መንገድ
ብዙ ፍቺ አለው !
ሴት አዳሪ ሆኖ ፣ ወንድ አዳሪን ማብረድ፡፡
አንድም ጥያቄ ነው !
ከአንደኛው በቀር ፣ መልሱ አይታወቅም
አንድም መልስ ይሆናል !
መንገድ ለጠፋበት ፣
መድረሻ ነው እንጂ ፣ ክብር አያስጨንቅም፡፡
//
ተመልከች አፀዱን…
"ሀብት" በምትለው ፣ በሰፊው ጎዳና
ምንጩ ባልታወቀ ፣ በግሏ መኪና
ንቅሳቷ ጠፍቶ ፣
ከተሜ መስላለች ፣ ግጥርናዋን ጭና፡፡
ሀገር ነች አፀዱ !
አካሔድ ለማያውቅ ፣ ለጠፋበት መንገድ
ሁለት ፍቺ አለው !
ሌሎችን ለመምሰል ፤ ከራስ ላይ መሰደድ፡፡
አንድም ጥያቄ ነው ፣ መልሱ ባይሰጥም
አንድም መልስ ይሆናል !
መንገድ ለጠፋበት፣
መድረሻ ነው እንጂ ፣ ማንነት አይበልጥም፡፡
//
ይሄ ሁሉ ሲሆን…
"እመጣለሁ" ብለሽ ፣
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣ ከሰፊው ጎዳና
ይህን ያህል ጊዜ ፣
ጠብቄሽ ጠብቄሽ ፣ አልመጣሽምና
እስክትመጪ ድረስ…
አለም ነሽ ፣
ካሳ ነሽ ፣
እንዲሁም አፀዱን ፣ የጠፋቸው መንገድ
እኔንም ጠፍቶኛል !
መድረሻ የለኝም ፣ ሳላገኝሽ ብሄድ፡፡
ስለዚህ ዘልዓለም ፣
እስክትመጪ ድረስ ፣ እጠብቅሻለሁ
አንቺ ራሷ ሀገር ነሽ !
ቀርተሸ መጠበቄ ፣ ሁለት ፍቺ አለው፡፡
አንድም ጥያቄ ነው ፣ መልሱ ይቸግራል
አንድም መልስ ይሆናል!
ፍቅር የጠፋበት ፣
አለምን ቢያተርፍም ፣ ሁሉንም ይከስራል፡፡
#በዝናብ ቅጠሪኝ
አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበርክኬ
ዕንባዬ እንዳይታይ ካንቺ ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ
ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ ሆድሽም አይባባ
ዝናብ የኔን ብሶት ሀዘኔን ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ ዕንባዬን ይጋርደው
በጉንጬ 'ሚፈሰው ዝናብ እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ አይታይሽ
ውዴ፦
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ አልቅሼ
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም 'ናፍቀሽኛል' ብዬ
ሳለቅስ እንዳታዪኝ
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በክረምት ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላቆ ስስቅ እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ ጠብቂኝ።
-------------------------
አንዱዓለም ኪዳኔ
"በዝናብ ቅጠሪኝ"
የግጥም መድብል
አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበርክኬ
ዕንባዬ እንዳይታይ ካንቺ ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ
ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ ሆድሽም አይባባ
ዝናብ የኔን ብሶት ሀዘኔን ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ ዕንባዬን ይጋርደው
በጉንጬ 'ሚፈሰው ዝናብ እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ አይታይሽ
ውዴ፦
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ አልቅሼ
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም 'ናፍቀሽኛል' ብዬ
ሳለቅስ እንዳታዪኝ
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በክረምት ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላቆ ስስቅ እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ ጠብቂኝ።
-------------------------
አንዱዓለም ኪዳኔ
"በዝናብ ቅጠሪኝ"
የግጥም መድብል
#ተራራ_ነፋስ_ማዕበል
ማዕበል ምን አይቶ ? . . .
መፏከር ጀመረ ከቆመ ተራራ
እኩያ የመኾን የስሌት ቅመራ።
የውሃን ባሕርይ መርጋትን ዘንግቶ
ሽቅብ የመቆምን እብሪትን አንግቶ
ምን ሊረባው ቆመ?
ምን መኾን ተመኘ?
(. . . ውሃ ፍስነት ላይ . . . )
ነፋስ ሆዱ ገባ ፣ ነፋስ ውስጡ ኖረ
ተራራን ለማከል ፣ ሽቅብ ተወጠረ።
.......ካ'ለት ተጋጠመ . . .
.......ካ'ለት ተላተመ . .
.......ካ'ለት ተፋለመ . . .
( . . . ነፋስ ምን አስገባው? . . .)
ካልጠፋ ሰገባ ውሃን የመረጠ፤
የረጋን ውሃ ልብ ፣ገብቶ በጠበጠ።
( . . . ነፋስ በምን ገዱ . . . )
ውቅያኖስ የሚያቆም ከጋራ 'ሚያማስል ፤
በየት ተሽሎክሉኮ
ዐቅም አኮብኩቦ
የተኛን ሙት ባሕር ተራራ ሚያስመስል።
እኔም እንደዚኽ ነኝ . .
ሠርክ የምገዳደር ከሊቅ ፣ ከእግዜሩ፤
ለማከል ፣ ለመኾን እንደ ምስለ ፍቅሩ።
( እኮ እንዴት . . .? )
ልቤ ምን ገብቶት ነው? ከፍጥረት ለይቶ
አንችኑ ያስመኘኝ ሆዴ ጽድቅን ሽቶ።
በየትኛው ዕቅሙ ... ? ?
ፍጡር ከፈጣሪው ደርሶ ይፏከራል?
ያንን! ፍጹም ፍቅር ለመስጠት ይጥራል?
ሽቅብ ተቆልሎ ?!
🔘ተስፉሁን ከበደ🔘
ማዕበል ምን አይቶ ? . . .
መፏከር ጀመረ ከቆመ ተራራ
እኩያ የመኾን የስሌት ቅመራ።
የውሃን ባሕርይ መርጋትን ዘንግቶ
ሽቅብ የመቆምን እብሪትን አንግቶ
ምን ሊረባው ቆመ?
ምን መኾን ተመኘ?
(. . . ውሃ ፍስነት ላይ . . . )
ነፋስ ሆዱ ገባ ፣ ነፋስ ውስጡ ኖረ
ተራራን ለማከል ፣ ሽቅብ ተወጠረ።
.......ካ'ለት ተጋጠመ . . .
.......ካ'ለት ተላተመ . .
.......ካ'ለት ተፋለመ . . .
( . . . ነፋስ ምን አስገባው? . . .)
ካልጠፋ ሰገባ ውሃን የመረጠ፤
የረጋን ውሃ ልብ ፣ገብቶ በጠበጠ።
( . . . ነፋስ በምን ገዱ . . . )
ውቅያኖስ የሚያቆም ከጋራ 'ሚያማስል ፤
በየት ተሽሎክሉኮ
ዐቅም አኮብኩቦ
የተኛን ሙት ባሕር ተራራ ሚያስመስል።
እኔም እንደዚኽ ነኝ . .
ሠርክ የምገዳደር ከሊቅ ፣ ከእግዜሩ፤
ለማከል ፣ ለመኾን እንደ ምስለ ፍቅሩ።
( እኮ እንዴት . . .? )
ልቤ ምን ገብቶት ነው? ከፍጥረት ለይቶ
አንችኑ ያስመኘኝ ሆዴ ጽድቅን ሽቶ።
በየትኛው ዕቅሙ ... ? ?
ፍጡር ከፈጣሪው ደርሶ ይፏከራል?
ያንን! ፍጹም ፍቅር ለመስጠት ይጥራል?
ሽቅብ ተቆልሎ ?!
🔘ተስፉሁን ከበደ🔘
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
... ላለፉት ሦስት ወራትም የኒኪ ታካሚ ሆና ቆይታለች። ኒኪ እና አኔም በደንብ ስለተግባቡ ነው መሰል አኔ ለምታደርጋቸው የቀን ተቀን ውሎዋ ሁሉ የቴራፒስቷን ኒኪን ምክር የምትፈልግ የኒኪ ጥገኛ ሆነች።
“መፍራት የለብሽም” አለቻት ኒኪ በማስተዋል፡፡ “ሊዛ ላይ የደረሰው ነገር
በጣም አሰቃቂ ነው። ነገር ግን ከአንቺ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለምና በጣም አጥብቀሽ አታስቢው:: እሷን እዚህ ቢሮ ውስጥ ስላገኘሻት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ማለቴ ሁለታችሁን የሚያስተሳስር ነገር ሊሆን አይችልም።” አለቻት፡፡ “ልክ ነሽ” ብላ ፈገግ አለች እና “እኔ የማይረባ ነገር ነው እያሰብኩኝ ያለሁት። አሞኝ ሳይሆን አልቀርም”
“ሞኝ እንኳን አይደለሽም፡፡ ሞት በጣም አስደንጋጭ ነገር ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ሰዎች ሲገደሉ ይበልጥ ያስደነግጣል፡፡ አሁን አንቺ የራስሽ የሆነ ችግር ውስጥ ነው የምትገኚው እና አትኩሮቶችሽን ሁሉ ችግሮችሽን በሚፈቱ ነገሮች ላይ አድርጊ። ይሄን ነው ልመክርሽ የምችለው።” አለቻት ኒኪ የምክር ጊዜ ሰዓታቸው ማለቁን ለማሳየት ወደ ኮሪደሩ የሚወስደውን በር ከፍታ እየቆመች። ብዙ ታካሚዎቿ የሚሰናበቷት እጇን በመጨበጥ ነው፡፡
አኔ የምትሰናበታት ግን ወደ ኒኪ ተለጥፋ ጥብቅ አድርጋት በማቀፍ ነው፡፡ ይህ አይነቱ መቀራረብ በሀኪም እና በታካሚ መሀከል ሊኖር ባይገባም አኔ እሷን እያቀፈች በየጊዜው የምትሰናበታትን ነገር ግን በሙሉ ልቧ ልታስቆመው አልቻለችም፡፡ እውነት ነው አኔ እሷን እንደ መከታ ማየቷ ያስደስታታል፡፡ ጥሩ ስሜትም እንዲሰማት ያደርጋታል። ምን ይሄ ብቻ ስለ አኔ የሚሰሟት ነገሮች ሁሉ ጥሩ ስሜት ይሰጧት ከጀመሩም ውለው
አድረዋል።
ዛሬ ግን ኒኪ አቅፋ ስትሰናበታት ያ ስሜት አልተሰማትም። ምክንያቱም ሁለት እንግዳ ሰዎች በኮሪደሩ ላይ ወደ እሷ እየመጡ መሆናቸውን በአኔ ትከሻ አሻግራ ስለተመለከተች ነበር፡፡ ካቀፏት የአኔ ክንዶች ራሷን አላቅቃ ኒኪ አኔን ተሰናበተቻት እና ወደ ሁለቱ ሰዎች ዞረች፡፡
“የምረዳችሁ ነገር አለ?” ብላ ጠየቀች፡፡ ይሄኔም ልጅ እግሩ እና መልከመልካሙ ሰው እጁን ለሰላምታ ዘርግቶ እየጨበጣት የ ኤሌ ፒዲ ፖሊስ አባል ነን፡፡ መርማሪ ፖሊስ ሉው ጉድማን እባላለሁ፡፡ ይሄ ባልደረባዬ ደግሞ መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰን ይባላል” ኒኪ ጉድማንን ከጨበጠች በኋላ እጅዋን ወደ ወፍራም እና አጭሩ መርማሪ ለሰላምታ እየዘረጋች
“እዚህ የመጣችሁት ስለ ሊዛ ለመጠየቅ መሰለኝ፡፡ በጣም የሚያሳዝን ነገር
ነው የደረሰባት” ብትልም አጭሩ መርማሪ ለሰላምታ የዘረጋችለትን እጇን
ሳይጨብጥ ቀረ፡፡
በቁጣ ድምፅም “እዚህ አይደለም የምናወራው።” ብሎ ትሬይን በጎሪጥ
እያየ መለሰላት። ኒኪም በሰውዬው ሥርዓት ያጣ መልስ ትንሽ ቅር አላት
በተጨማሪም ይህን ሰው የሆነ ቦታ እንደምታውቀው ገምታለች፡፡ ቦታውን
ግን የት እንደሆነ አሁን ላይ ልታስታውስ አልቻለችም።
ወደ ቢሮዋ ካስገባቻቸው እና እንዲቀመጡ ከጋበዘቻቸው በኋላ በሩን
ዘግታ እሷም ወንበሯ ላይ ቁጭ አለች። የበሩን መዘጋት ተከትሎ ከቢሮዋ
ውስጥ ሆነው ማውራት ሲጀምሩ ትሬይ የስልኩን እጀታ አነሳና ደወለ።
“ፖሊሶቹ እዚህ ናቸው!” ለማልቀስ በሚዳዳ ድምፅ ውስጥ እንደሆነ ነበር፡፡
“በጣም ፈርቻለሁ። ምን እንደማደርግ አላውቅም” አለ።
ከዚያኛው መስመርም የሚመጣ ድምፅ እንዲረጋጋ ከነገረው በኋላ በማስከተልም “አይዞህ ምንም አያቁም፡ ስለዚህ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም፤ በቃ ተረጋግተህ ቁጭ በል” ብሎት ስልኩን ዘጋው፡፡
ቢሮው ውስጥ መርማሪ ፖሊስ ሉድዎ ጉድማን ሊዛን አስመልክቶ ለዶ/ር ኒኪ ሮበርትሰን ለሚያቀርብላት ጥያቄዎች የምትመልሳቸውን መልሶች መርማሪ ሚክ ጆንሰን ባለማመን ስሜት ውስጥ ሆኖ ነው የሚሰማት። በውስጡም 'ይህቺ ሸርሙጣ ፊቴን እንኳን ለማስታወስ ምንም
አይነት ነገር አታሳይም እያለ ኒኪ የምታወራውን ነገር የሚሰማት ጨጓራው
እስኪላጥ ድረስ በከፍተኛ ንዴት ውስጥ ሆኖ ነው።
ከመገደሏ በፊት ሊዛን መቼ እንዳገኘቻት ጉድማን ኒኪን ሲጠይቃት ሞተች የተባለችበት ቀን ላይ እንዳገኘቻት መለሰችለት። በመቀጠልም ያን ቀን
ወይንም ከዚያን በፊት ባሉት የህክምና ጊዜዋ ላይ ሊዛን የሚያስፈራራት
ሰዎች እንዳሉ ነግራት እንደሆነ ጠየቃት። ኒኪም ነግራኝ አታውቅም” አለችው፡፡
ሊዛን አላማ አድርጎ ሊጎዳት የሚችል ሰው እንዳለ ገምታ ታውቅ እንደሆነ ኒኪን ቢጠይቃትም የእሷ መልስ ግን አሁንም “የለም የሚል ነበር” በዚህ አይነት ብዙ ጥያቄዎችን ሲጠይቋት ቆይተው መርማሪ ጉድማን ወደ እሷ አዘንብሎ አይን አይኗን እያያት “ ዶር ሮበርትስ ምናልባት አንቺ ከጎድዋት ሰዎች በስተቀር ሊዛን ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘሻት ሰው ነሽ፡፡
ስለሆነም በደንብ ማወቅ ይገባናል” አላት፡፡
“ይገባኛል” አለች እና ኒኪ በማስከተልም
“ከዚህ በላይ ምን ልጨምርላችሁ እንደምችል አላውቅም። የዚያን ቀኑ የህክምና ጊዜ ቀና ነበር። እንዲያውም ከወንድ ጓደኛዋ ጋር መለያየት በመቻሏ በጣም ተደስታ ነበር” ብላ ልትቀጥል ስትል መርማሪ ጆንሰን ጣልቃ ገብቶ የወንድ ጓደኛ አልሽኝ? ዊሊ ባደንን ማለትሽ ነው?”
ቢሮ ውስጥ ከገቡ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው አሁን ነው። ንግግሩ ውስጥ ደግሞ ንቀት እና ንዴት ይታይበታል። በእርግጥም ደግሞ
ይህቺን የመሰለች ቆንጆ ልጅ (ሊዛ) ከዚያ ቆሻሻ ሽማግሌ ጋር መወዳጆቷን
ማወቁ ነቃ አድርጎታል።
“ግልፅ እንዲሆን የምፈልገው ነገር ምን መሰለሽ? እሷ ፍቅረኛ የሚባል ነገር የላትም። አየሽ እሷ ባለትዳር ከሆነ ሀብታም ሽማግሌ ጋር ለገንዘብ ብላ
እንደምትተኛ ነው የሚታወቀው” አላት፡፡ ጆንሰን ተው በሚል የልምምጥ
አይን የሚመለከተውን ጉድማንን ችላ በማለት እና ኒኪን በሚያስደነግጥ
አገላለፅ “በቃ እሷ እኮ ከፍተኛ ተከፋይ እና በህብረተሰቡ ጥሩ ቦታ የሚሰጣት
ታላቅ ሸርሙጣ ናት። አይመስልሽም?” አላት፡፡
“ከእሱ ጋር ለምን እንደሆነች አላውቅም:: ደግሞም ታካሚዎቼ ላይ የመፍረድ መብት የለኝም::” አለችው ኒኪ የሚፈታተናትን ንዴት ውጣ በእርጋታ። “
ለማንኛውም ያን ቀን ላይ እሷ ዊሊን የመተው ውሳኔዋን አሳውቃኝ በደስታ እና በጥሩ ስሜት ውስጥ ሆና ነበር ቢሮውን ለቃ የወጣችው።” “እሺ ከዚህ ከወጣች በኋላ ልታገኘው የቀጠረችው ሰው እንዳለ
ነግራሽ ነበር? በመኪና ሊወስዳት የመጣ ሰው ነበር?” በንዴት አይን በጎሪጥ እያየ ጠየቃት፡፡ “ኧረ የለም” እንዲያውም ብቻዋን ነው ብዙ ጊዜ በመኪናዋ
የምትመጣው:: ያን ዕለት ግን መኪናዋን ሳትይዝ ነበር የመጣችው።”
ይህንን ሲሰሙ ፖሊሶቹ በአይን ተነጋገሩ እና “ለምን መኪናዋን ይዛ አልመጣችም?”
ኒኪ ራሷን ግራ እና ቀኝ እየነቀነቀች “አይ ይህን እንኳን አላውቅም። ብቻ ያኔ ዝናብ ይዘንብ እንደነበር እናም ደግሞ በእግሯ ወደ ቤት እንደምትመለሰ ስትነግረኝ ጃኬቴን (ኮቴን) አውሼያት እንደነበር
አስታውሳለሁ” አለች፡፡ ይሄኔም ንዴቱን ሁሉ ረስቶ ከተቀመጠበት ቦታ ሆኖ
በግርምት እያያት “ከዚህ ስትወጣ ያንቺን ጃኬት አድርጋ ነበር?”
“አዎን” አለች ኒኪ “ስለኮቱ አይነት በደንብ ልትገልጪልኝ ትችያለሽ? ዶ/ር ሮበርትስ?” ብሎ ለጠየቃት ጥያቄም ስለ ዝናብ ኮቷ ሁኔታ በደንብ አድርጋ ገለፀች፡፡
“በእውነት በጣም ነው የምናመሰግነው። በጣም ጠቃሚ የሆነ መረጃን ነው የነገርሽኝ::” አላት ደስ የሚል እና አትኩሮትን የሚስብ ፈገግታን እየመገባት፡፡ በቃ ሁኔታው ለእሷ ብቻ አትኩሮት በመስጠት እንዲሁም ትንሽ
የማማለል ነገር በታከለበት

👍2❤1🥰1
ሁኔታ ነበር ያናገራት።
በተቃራኒው ደግሞ አብሮት ያለው አጭርና ወፍራሙ ባልደረባው በጣም ቁጡ የማይስብ እንዲሁም ደግሞ ለሰዎች ምንም አይነት ክብር የሌለው አይነት ሆኖ ነው የታያት። ያም ሆኖ ግን ስለ ዝናብ ኮቷ ስታወራ ያዳመጣት በጣም በትኩረት ነበር።ሁለቱ ፖሊሶች ተሰናብተው ከወጡ በኋላ ትሬይ በሩን አንኳኩቶ ወደ ቢሮው ውስጥ ገባ፡፡ “በእውነት ዶክተር አንቺ እንዳትረበሺ ብነግራቸውም ሊሰሙኝ ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ በተለይ ደግሞ አጭሩ ፖሊስ በጣም በሚረብሽ መልኩ ነበር እያመናጨቀ ያናገረኝ:: ይቅርታ ዶክ” አላት። ኒኪም ትከሻው ላይ እጇን ጣል አድርጋ “ችግር የለውም ዶክ። አንተ የምትችለውን ነገሮች ሁሉ አድርገሀል እና አታስብ:: አሁን እንዴት ነህ? ስለ ሊዛ ጥሩ ነገር እንዳለህ አውቃለሁ።”
“አሁን ደህና ነኝ” ብሎ ትንሽ ተንተባተበ እና በመቀጠልም “በእርግጥ በጣም አዝኜያለሁ በጣምም ደንግጫለሁ።”
“እኔም”
“በጣም ቆንጆ ነበረች”
አዎን ቆንጆ ነበረች” ተባብለው ተለያዩ። ትሬይም ወደ ቤቱ ሄደ።
ትሬይ ከሥራ ከወጣ በኋላ ኒኪ ቢሮዋ ውስጥ ቁጭ ብላ ስለ ንዴታመሙ
መርማሪ ፖሊስ ሁኔታ አሰበች እንዴ እሷ እኮ ከሌላ ሴት ባል ጋር የተኛች ሸርሙጣ ናት ያለውን ነገርም አሰበችው።
ኒኪ ንዴትን ከማንም በላይ ትረዳዋለች። በተለይ ደግሞ ከባሏ ዶውግ ሞት በኋላ ይሄው የንዴት ስሜቷ ቋሚ ወዳጅ ሆኖ አብሮሯት አለ።
ከኪሷ ውስጥ ረጅሙ እና መልከመልካሙ የሰጣትን የአድራሻ (ቢዝነስ) ካርድ አውጥታ አየችው። መርማሪ ፖሊስ ሉው ጉድማን ይላል፡፡ ሉውን እንግዲህ ሌላ ጊዜ መቼ ይሆን የማገኛቸው?” ብላም ራሷን ጠየቀች።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሬሳ መርማሪዋ ጄኒ ፎይል የሊዛ ፍላገንን በድን በፕላስቲክ ሸፈነችው እና አትኩሮቷን አጠገቧ ወዳሉት ሁለቱ መርማሪዎች መለሰች። ጄኒ በሀምሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ፀጉሯ አጭርና የሚጥሚጣ ቀለም ያለው፣ አጭር ወፍራም እና ጠንካራ ሰውነት ያላት ፊቷ ላይ አንድም መዋቢያን የማትጠቀም እና ቆንጆ የማትባል ሴት ናት። ያም ቢሆንም ግን ብልህ አስተዋይ ተፈጥሮን የታደለች በጣም ቀልደኛ እና በስራዋ እንከን
የማይገኝባት ምርጥ የሬሳ መርማሪ ሀኪም ናት።
ከእነዚህ ሁሉ የጩቤ ውጊያዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ነው የሊዛ ፍላንገን ህይወት የነጠቀው ነው የምትይን?” አላት ሚክ ጆንሰን፡፡
“አዎን ልቧ ላይ የጩቤ ውግ ነው ህይወቷን ያጠፋው” አለች እና ጄኒ
በመቀጠልም “ሌሎች የጩቤ ውጎች ግን ጥልቀት የሌላቸው ናቸው። አለ አይደል ለማቁሰል ለመጉዳት እንጂ ለመግደል ታስበው የተሰነዘሩ ውጎች አይደሉም” ይህንን የሰማው ሉው ጉድማንም ቅንድቡን በግርምት እያነሳ
“ሰማኒያ ስምንቱም ውጎች?” ብሎ ጠየቃት፡፡
ጄኒም በረጅሙ አየር ከውስጧ እያወጣች “አዎን እንግዲህ” አለችው፡፡ ብዙ ሰዎች ሉው ገድማንን ከባልደረባው አንፃር ይመርጡታል። ምናልባትም ከሚክ ጆንሰን ይልቅ ሉው ጉድማንን የሚመርጡት መልከመልካም እና ለዛ
ያለው ስለሆነ እንደ ሚክ ጆንሰን ግልፍተኛ እና በንዴት የሰው ፊት ስለማይማታ ሊሆንም ይችላል።
በፎይሌ ፊት ግን የመርማሪ ፖሊስ ሉው ጉድማን ለዛ አይታያትም።የኒው ዮርክ ተወላጅ እና የአይሪሽ ደም ስላላት ነው መሰል ሚኪ ጆንሰን ደስ ይላታል። መልከመልካም ባይሆንም እሷ ሚክን ትመርጣለች፡፡ በላብ የራሱት ልብሶቹን፣ የማይመቹ ቀልዶቹን እና የሚመረምራቸውን ሰዎች በቀጥታ
የማያምን አካሄዱን ትወድለታለች። ሁሉም ነገር ስታይል በስታይል በሆነባት ከተማ እና በፖለቲካ ቁማር በሚዘወርበት የፖሊስ ዲፓርትመንት ውስጥ ሚክ ጆንሰን የጠራ ነፋሻ ደስ የሚል አየር ነው መስሎ የሚታያት፡፡
“እና ከመሞቷ በፊት ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባታል?” ብሎ ሚክ ጆንሰንን
ጠየቃት፡፡ በማስከተልም “እንደዚያ ነው እያልሽን ያለሽው አይደል?”
“ልክ ብልሃል እንደዚያ ነው እያልኩኝ ያለሁት፡፡ ተሰቃይታለች፡፡ ከመጠን በላይ እና አካሏ ላይ በሚደርሱባት ተደጋጋሚ የጩቤ ውጎች እንድትሸበር ተደርጋላች። በማስከተልም ወደ ሌላ ቦታ ተወስዳ ተገደለች። በመጨረሻም የቁሻሻ መጣያው አጠገብ ተጣለች” አለችው።
ሦስቱም በፕላስቲክ የተሸፈነውን የሊዛን ፍላገንን ሬሳ እየተመለከቱ ለጥቂት ጊዜ ያህል ዝም ብለው ቆዩ። አሁን በላስቲክ የተሸፈነው ሬሳ በፊት ላይ የቆንጆዋ ሞዴሊስት ሊዛ ፍላንገን አካል እና ህይወትን አጣጥሞ ለመኖር ተስፋን የሰነቀ ነፍስያም የነበረው ቢሆንም ይሄው ያ አካሏ የተቆራረጠ በድን ሆኖ ከፊት ለፊታቸው ይገኛል፡፡
“በነገርሽን ነገር እርግጠኛ ነሽ?” አላት ጉድማን ዝምታቸውን ሰብሮ፡፡
“አዎን ነኝ፡፡”
“ምክንያት...?”
“ከቁስሎቹ አንፃር መለየት ይቻላል። ልቧ ላይ የተወጋው የጩቤ ውግ ከሌሎቹ የመጀመሪያዎቹ ውጎች ከደረሱ ከሰዓታት በኋላ ነው የተከናወነው። ብዙ ጊዜ ስለተወጋች ብዙ ደም ፈስሷት ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግን ልቧ ላይ የደረሰባት የጩቤ ውግን የመሰለ ህይወቷን የሚነጥቅ ነገር አልነበረም።”
ብላ መለሰችላቸው፡፡ “ወሲባዊ ጥቃት አልደረሰባትም?” ጉድማን ጠየቀ፡፡
ጄኒም ራሷን ግራ እና ቀኝ እየወዘወዘች “አልደረስባትም” አለችው::
“ራሷን ለመከላከልስ ምንም አይነት ነገር አላደረገችም?” ብሎ ጆንሰን ጠየቃት፡፡
“መልካም” ብላ ጄኒ የላስቲክ ጓንቷን አውልቃ ፈገግ አለች ቀጥላም በመጀመሪያ ምንም አይነት መፍጨርጨር አላሳየችም ብዬ ነበር
ይህ ደግሞ ይበልጥ የሚያሸብር ነገር ሆነብኝ። በምርመራዬ የመጨረሻ ወቅት
ላይ ከእጇ አንደኛው ጥፍር ውስጥ በጣም ትንሽ ቁራጭ የተፋቀ ቆዳ
(የሰውነት ህዋስ) ለማግኘት ችያለሁ።” አለቻቸው፡፡
ጆንሰንም ግምባሩን ቋጥሮ “ለምን በጣም ትንሽ የቆዳ ፍቅፋቂ? ማለቴ
ህይወቷን ለማትረፍ በምታደርገው መፍጨርጨር ውስጥ ገዳይዋን በጥፍራ
እስከቧጨረችው ድረስ ለምን ትንሽ ቆዳ ብቻ ይገኛል?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“ልክ ነህ ብዙ የቆዳ ፍቅፋቂ ነበር” አለች እና ይበልጥ ፈገግ ካለች በኋላ
“ለዚያም መሰለኝ ጥፍሮቿ ሥር ድረስ የተቆረጡት፧ ጣቶቿም በደንብ
ተደርገው የተፈተጉት። ከሞተች በኋላ ማለቴ ነው”
“በእየሱስ ሥም” አለ ጉድማን ነገሩን ዘግንኖት፡፡
“ግን የሆነ ቦታ ላይ ፍተጋው ፅዳቱ ሳይከናወን በመቅረቱ ዕድለኛ ነን።
አላት ጆንስን “ይመስለኛል። ግን ናሙናው ትንሽ ነው፤ በዚያ ላይ ትንሽ ያልተለመደ የቆዳ ፍቅፋቂ ነው...” ብላ ዝም ስትል ሁለቱም ነገሩን እንድታብራራላቸው ብለው አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር።
የቆዳው ህዋሶቹ የተለዩ ነበሩ። ማለቴ ከሆነ ከበሰበሰ ሥጋ ላይ የተፋቁ
ነው የሆኑብኝ” ይህንን የሰማው ገድማንም በግርምት “ሆነ ነገር ከአንድ
ከሞት ነገር ላይ የተፋቁ ናቸው።” ብላ መለሰች ጄኒ። መርማሪ ጆንሰንም
አይኑን አጥብቦ “ይህቺ ወጣት የተገደለችው በሞተ ሰው ነው የምትይን?
አላት፡፡
“እንደዚያማ አይሆንም። የሞተ ሰው በህይወት ያለ ሰውን ሊገድል አይችልም::” ብላ ጄኒ መስለች፡፡
“እና ምንድነው እያልሽን ያለው?” ብሎ ጉድማን ጠየቀ፡፡
“በሊዛ ጥፍር ውስጥ የተገኙት ህዋሶች ያልተለመዱ ናቸው። በህዋሶቹ
ጥራት ወይንም የብዛታቸው ማነስ ምክንያት ትክክለኛውን ዲ.ኤን.ኤ ማወቅ
አንችልም ብዬ አስባለሁ” አለች።
ሚኪ በቀልድ መልክ ጄኒን ጎኗ ላይ ጎሽማት እና “ምናልባት ነፍሰ ገዳይ ዞምቢ ሊሆን ይችላል። ዞምቢዎች የእውነት ናቸው ማለት ነው?” አላት
እያሾፈ፡፡ ጄኒም ከት ብላ በቀልዱ እየሳቀች “ሚኪ እሱን አንተው በምርመራህ ድረስበት፡፡ ለማንኛውም ልጅቷ ከመሞቷ በፊት የፃፈችልን ነገር
ይሄ ነው። የተለየ ነገር ካለ አሳውቃችኋለሁ

👍3
እንግዲህ ከዚህ በኋላ ያለው ሥራ የእናንተ ነው።” አለቻቸው፡፡
ከሆስፒታሉ ጥግ ላይ ከሚገኝ አንድ ቢሮ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ መርማሪ ፖሊሶች ጄኒ ስለ ነገረቻቸው ነገር እያሰቡ ነው። የሚክ የዞምቢ ጉዳይ የቀልድ መሆኑ እርግጥ ነው። ግን እንዴት የሞተ ሰው ህዋስ በሊዛ ፍላንገን ጥፍር ውስጥ ሊገኝ ቻለ? በነገሩ ላይ አንዳቸው ወሬ መጀመሪያ እንዳለባቸው ያወቀው ጉድማን ሦስት ቦታዎች (ነገሮች) ላይ አትኩሮት ማድረግ ይኖርብናል። ስቃዩ የተከናወነበት ቦታ ግድያው የተከወነበት ቦታን እና ሬሳው የተጣለበት ቦታን” አለው። “ልክ ነው” አለው ጆንሰንም
የመጀመሪያው ላይ አትኩሮት ሰጥተን ምርመራችንን መጀመሩ ሳያዋጣን
አይቀርም” አለው ጉድማን፡፡
በጣም ጥሩ” ብሎ መለስ ጆንሰን፡፡
ሚክ የዚህ ጉጉ ወጣት መርማሪ ባልደረባው ብዙ ነገሮቹ በጣም
ቢያበሳጩትም በብዙ የሚያሳብዱ እና የሚያበሳጩ አጋጣሚዎች ላይ
የሚያሳየውን ስክነት እና መረጋጋት ግን ሳያደንቅለት አያልፍም። መኪናቸው ውስጥ ገብተው ከሆስፒታሉ ሊወጡ ሞተራቸውን እያስነሱ በነበሩበት ጊዜ ላይ ግን ከሆስፒታሉ ወጥታ ወደ እነርሱ እጂን እንደ ዕብድ እያውለበለበች ስትሮጥ አጠገባቸው ደረሰች።
ጆንሰን የመኪናውን መስታወት አውርዶ “ጄኒ ሳትነግሪን የረሳሽው ነገር አለ? ደግሞ ለምንድነው እንደዚህ እየተክለበለብሽ የመጣሽው? የቫንፓየር
የጥርስ ንክሻ ምልክትም አንገቷ ላይ አግኝቻለሁ ልትይን እንዳይሆን ብቻ?”
አላት።
“ሃ! ሃ!” ብላ ትንሽ ሳቀች እና ጄኒ አንድ ወረቀት በጆንሰን እጅ ላይ እያስቀመጠች “ሚክ ዕድለኛ ሳትሆኑ አልቀራችሁም መሰለኝ። የዲ.ኤን.ኤ ምርመራው መልስ አሁን ነው የመጣው። የዞምቢው ሥም ሳይታወቅ አልቀረም” አለችው እና ጥላቸው ወደ ህንፃው ገባች።....