#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
ግንቦት 12 ፣ ከለሊቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ
ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ
ብሬንትውድ ፥ ሎስ አንጀለስ ውስጥ
ሎስ አንጀለስ ውስጥ ግንቦት ላይ ሲዘንብ አላስታውስም። አሁን ላይ ግን
በስሱ የሚዘንበው የግንቦት ዝናብ ክንዴ ላይ እየተንከባለለ ሲወርድ ገረመኝ::
ምናልባትም ይሄ በህይወቴ ለመጨረሻ ጊዜ የምገረመው ግርምት ይሆናል፡፡
ደግሞ ቢገርመኝስ? በዚያ ላይ ደግሞ እኔ ከአሁን በኋላ ድንገተኛ ነገርን
ማስተናገድ አልችልም። እንዲያውም ትንግርት የሚባል ነገር ያስጠላኛል፡፡
የቤቴ ጀርባው ለሽ ያለ ሳር የበቀለበት መሬት ሲሆን፣ የቆምኩት ደግሞ ባለፈው ፀደይ ባለቤቴ በአደጋ ከመሞቱ ከወር በፊት በተከለው የሞንጕል ዛፍ አጠገብ ነው። ባለቤቴ የሞተው በአደጋ ነው የሚለውን ነገር ማሰብ ማቆም አለብኝ፡፡ ለምን? ካላችሁኝ ደግሞ ባለቤቴ የሞተው ቀኑ ስለደረሰ ነው ብዬ ስለማላምን ነው። በ405ኛ ጎዳና ምሽት ላይ በጣም የሚወደውን 'ቴስላ' መኪናውን ሲያሽከረክር ነበር እንግዲህ መኪናው ሙሉ በሙሉ ነድዳ እሱም ከነህይወቱ ተቃጥሎ የሞተው። ይሄ ደግሞ ለእኔ ህይወት መዘበራረቅ የመጀመሪያው መጥፎ መነሻ ነበር። ከዚያ በኋላ ነበር እንግዲህ ብዙ ነገሮችን ማወቅ የጀመርኩት፡፡
በእጄ የጨበጥኩት 9 ሚ.ሜ ሉገር ሽጉጤ ልክ የመጫወቻ ሽጉጥ፣
ትንሽ እና ምንም ጉዳት የማያደርስ ይመስላል። የሆነ የጆሮ ጉትቻ ወይንም
የሀር የአንገት ልብስ እንደሸጠልኝ አይነት ሽጉጥ የሸጠልኝ ሰው “ ይህቺ ሽጉጥ ለሴት የተሰራች እና የምትመች ቆንጆ ሽጉጥ ናት” ነበር ያለኝ። ባለቤቴ ደግሞ በመኪና አደጋ ተቃጥሎ ከሞተ በኋላ የሆነ ቀን ላይ ብዙ የእንቅልፍ ክኒኒዎችን በመዋጥ ራሴን የማጥፋት ሙከራ አድርጌያለሁ። ያ የመጀመሪያ ራሴን የማጥፋት ሙከራዬ ግን አልተሳካልኝም ነበር። የፅዳት ሰራተኛዬ ሪታ ደርሳ ለፖሊስ በመደወል ሆስፒታል ተወስጄ ህይወቴ
ሊተርፍ ችሏል፡፡ አሁን ግን ይህቺ የመጫወቻ ሽጉጥ የምትመስለው ትንሿ
ሽጉጤ በደንብ አድርጋ ስራዋን እንደምትሰራ እና ነፍሴን ከስጋዬ
እንደምትነጥለው እተማመናለሁ።
ምንም እንኳን ሥራዬ ሳይኮሎጂስት በመሆኑ የተነሳ ሞትን የሚፈሩ ቆጥሬ የማልጨርሳቸው ታካሚዎቼን በየጊዜው ብመለከትም ቅሉ እኔ በግሌ ሞትን አልፈራም፡፡ ሞትን የማስበው የሆነ የማይታይ እና የሰዎችን እዕምሮ
እንደሚቆጣጠር ጉልበተኛ ነገር ነው:: አሁን ላደርገው ያቀድኩት ነገር ደግሞ
ይህን ጉልበተኛ ነገር በራሴ መንገድ መቆጣጠር ነው። በራስህ መንገድ ይህቺን ዓለም ተሰናብቶ መሄድን የመሰለ ድልቅቅ ያለ አሟሟት አለ?
ይህንን የመሰለ የደልቃቃ አሟሟትን ደግሞ ማንም ዕድለኛ ያልሆነ ሰው
ሊሞተው አይችልም፡፡ በእኔ የተነሳ ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በተለይ ዛሬ ማታ ደግሞ አንድ ተጨማሪ የዋህ እና ጨዋ የሆነ፣ ለእኔ ደንታ ያለው እና የሚያስብልኝ፣ እኔም የማስብለት ሰው በእኔ ምክንያት ሊሞት ችሏል።
በዚህ አይነት በእኔ የተነሳ በየጊዜው ሰዎች ለእኔ መሞታቸው መቀጠል
የለበትም። ስለሆነም እኔው እራሴ በእኔ ምክንያት ሰዎች እንዳይሞቱ ራሴን
በማጥፋት እራሴ አስቆመዋለሁ።
ዝናቡ በጣም መዝነቡን ቀጥሏል። በዝናቡ የራሰው እና ሽጉጡን የጨበትኩበት እጄም እንዳያንሸራትተው እና ሽጉጡን አጥብቄ ለመያዝ
እንዲመቸኝም እጄን በለበስኩት ጅንስ ሱሪ ላይ ጠረግኩት። አሁን ምንም
አይነት ስህተት መፈፀም አይኖርብኝም። የሽጉጤን አፈሙዝ አገጩ ስር
ደቀንኩት እና ዞር ብዬ እኔና ዶውግ አብረን የገነባነውን ቤት ተመለከትኩት።
ነጭ ቀለም በተቀባው እና በምስራቃዊው ስቴት የሰራነው ቤታችን ዋናው የመኝታ ክፍል ባልኮኒ አለው። ፊቱንም ወደ ውቅያኖስ ያዞረ ስለሆነ ደስ የሚል ዕይታን እያየን ፍቅራችንን የምንቀጭበት ክፍላችን ነበር። ይገርማል አሁን በመጥፎ ህልም ውስጥ በምዳክርበት ጊዜ ሳይሆን ያኔ ከእሱ ጋር በነበርኩበት እና ጥሩ ህልም ስናስብ በነበርንበት ጊዜ ላይ ነበር እንግዲህ ይህንን ቤታችንን ያሰራነው። አይኔን ጨፍኜም የእነዚህን ሰዎች ፊት አንድ በአንድ በውስጤ መመልከት ጀመርኩኝ፡፡
በጣም የምወዳቸውን ዶውግ እና አኔ ልወዳቸው ከሚገባኝ ሉው ጋር አብረን እንዝለቅ ወይም አንዝለቅ እርግጠኛ አይደለሁም። በህይወቴ የማይገኙት እና የተውኳቸው፦ ሊዛ፣ ትሬይ፣ ዴሪክ ስለሞታችሁ እጅግ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ይቅርታችሁን እሻለሁ። የመጨረሻው ሀሳቤ ደግሞ እጅግ በጣም ስለምጠላው ሰው ነበር። ማን እንደሆንክ ደግሞ ታውቀዋለህ። ዘላለም በሲኦል እሳት ተጠበስ!
የምሰራው ነገር ትክክል እንዳልሆነ ይሰማኛል። ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡
ከዚህ የተሻለ ስሜቴን የማክምበት መንገድ ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር።
ለማንኛውም ምኞት አንድም ቀን ቢሆን የተበላሸ ነገርን አስተካክሎ አያውቅም እና አማራጭ የለኝም፡፡
#ቻርሎቲ
#ከአስር_አመት_በፊት
ቻርሎቴ ክላንሲ ሞቃታማው የበጋ ነፋስ ገላዋን ሲዳስሰው የሆነ ደስ የሚል ሸንቋጭ የደስታ ስሜት ተሰማት፡ የዚህ ስሜቷ አንደኛው ክፍል ሰውነቷ የወሲብ እርካታን በማግኘቱ የመጣ ነው። ሌላኛው ደግሞ ያልተለመደ እና አደገኛ የሆነ ነገር ውስጥ በመስመጧ ምክንያት የመጣ
ነው።
ቻርሎቴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በሳንዲያጎ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ስትማር ጨዋ እና ሁሌም ከክፍሏ አንደኛ የምትወጣ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበረች። ምናልባትም በት/ቤት ቆይታዋ ጊዜ ሰራች የተባለው ጥፋት ለጓደኛዋ ስለ ጥንታዊቷ ሜክሲኮ ታሪክ የጥናት ወረቀት መስራቷ ብቻ ነበር። ቻርሎቴ ለሀገረ ሜክሲኮ ልዩ ፍቅር አላት። ስለሆነም የሜክሲኮን
ታሪክ፣ ቋንቋቸውን እና ምግባቸውን ጨምራ ትወዳለች፡፡ ለሀገረ ሜክሲኮ
ባላት ፍቅር የተነሳም ነበር እንግዲህ ቤተሰቧን ጎትጉታ በማሳመን ትምህርት
ቤት ሲዘጋ ክረምቱን ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ መስራት የጀመረችው።
ያኔ ለክረምት ወደ ሜክሲኮ ለመሄድ አባቷን ስትጠይቅ “እኔ ደስ አላለኝም ቻርሊ።” አላትና ኮስተር ብሎ ትንሽ አሰበ፡፡ አባቷ ተከር ክላንሲ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኛና የኢጲስቆጶሳል ቤ/ክርስትያን ዲያቆን ነው። ፊቱን እና ሁኔታውን በማየት እሱ ምን ያህል የቤተሰብ ሰው እና ጥሩ አባት እንደሆነ ማንም ማወቅ ይችላል፡፡ ከአፍታ በኋላ በማስከተል “ግን እኮ እዚያ ሀገር ሰዎች ይታገታሉ፡፡ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ቡድኖችም እርስ በእርስ ሲጠፉፉ ነው የሚታዩት፡፡ መቼስ ሜክሲኮ ውስጥ አንገት ቀልቶ ሰዎችን የመግደል ነገርን ሳትሰሚው አትቀሪም፡፡ ብቻ እኔ ደስ አላለኝም!” አላት እና ዝም አለ።
“ልክ ነህ አባዬ” ብላ ቻርሎቴ በመቀጠል “ግን እኮ ከላይ የዘረዘርካቸው ወንጀሎች በመላው ሀገረ ሜክሲኮ ውስጥ አይፈፀምም፡፡ እኔ ወደምሄድበት
ቦታ ደግሞ እነዚህ አይነት ነገሮች የሉም። የምሄደው ኤልሳቫዶር ወይም ደግሞ ወደ ኮሎምቢያ ቢሆን ኖሮ ችግር ሊኖረው ይችል ነበረ። በዚህ ላይ ደግሞ እኔን የሚወስደኝ የአሜሪካን ኤዩ ፔየርስ ኢንተርናሽናል ኤጀንሲ (AAP) በጣም የሚገርሙ የሠራተኛውን ደህንነትን የሚያስጠብቁ ነገሮችን ነው የሚያደርገው፡፡ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት በሠራተኞቹ ላይ አንድም
አደጋ ደርሶባቸው አያውቅም::” ብላ መለሰችለት።
ተከር ክላንሲ ልጁ እሱን ለማሳመን የምታወራውን ነገር በእሷ ኩራት
እየተሰማው ነበር ያደመጣት፡፡ ልጁ ቻርሊ አንድን ነገር በግማሽ ብቻ አይደለም የምትሞግተው። ሁልጊዜም ቢሆን እሷ ሁሉንም እውነታዎችን እና አሀዞችን ጭምር አጥንታ ከጨረሰች እና በደንብ ከተገነዘበች በኋላ ነው ውሳኔዎችን የምትወስነው፡፡

👍9🔥1