አትሮኖስ
286K subscribers
123 photos
3 videos
41 files
585 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አልተወለድኩም

ወለድኩሽ ብለሽ ከሆነ
ተገላገልኩሽ አምጬ
አትሳሳቺ ሀሰት ነው
ዛሬም ጭንቅሽ ነኝ እንደገና
በህሊናሽ ውስጥ ተቀምጬ
ምንም ብከፈል ከአብራክሽ
በተፈጥሮ ህግ ተገድጄ
እናቴ ምጥ አያበቃም
ተገልፆልኛል ልጅ ወልጄ
ወለድኩሽ ብለሽ ስትይኝ
የምቀበልሽ ካንጀቴ
ስለ እኔ መኖር ስትተይ ---- ስትጨክኚ ነው እናቴ
እንዲያ ደግሞ እንደማይሆን
እንደሌለ ማረፍ ወልዶ
በተግባር አረጋገጥኩት
ከወለድኩ ዓመታት አልፈው
በልጆቼ ምጥ ጭንቄ ከብዶ

🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ🔘