ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ኤልሳቤጥ በጸነሰች #በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል #ልጅ #የመውለድ #መልእክት ይዞ ወደ እሷ መጣ። በዚህ ጊዜ #መልእክቱ የመጣው #በገሊላ አውራጃ ከምትገኝ #በናዝሬት ከተማ ለምትኖርና ስሟ #ማርያም ለምትባል #ድንግል ልጃገረድ ነበር። #ማርያም #ከይሁዳ ነገድ #ከዳዊት ትውልድ የሆነች #አይሁዳዊት #ድንግል ነበረች (ኢሳ 7፥14)። #በናዝሬት ከተማ #በአናጺነት ሙያ ለሚተዳደር #ዮሴፍ ለተባለ #ሰው የታጨች ስትሆን (ማቴ 13፥55) ሁለቱም ድሆች ነበሩ (ሉቃ 2፥24 ፣ ዘሌ 12፥8)።

▶️ ከሉቃስ ወንጌል #ምዕራፍ 1፤ 26-33 #የቅዱስ ገብርኤልን #ሰላምታ በደንብ ስንመለከተው #ማርያም ለጊዜው #እንደፈራችና #ግራ እንደተጋባች ያስረዳል። <<ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው>> አላት። #መልአኩ #ሠላምታ ሊሥጣት የመጣው ለምንድን ነው?? #ጸጋ የሞላባትስ በምን #መንገድ ነው? #እግዚአብሔር #ከእሷ ጋር የሆነውስ #እንዴት ነው??..

▶️ የማርያም #ምላሽ #በእግዚአብሄር ፊት #ትሁትና #እውነተኛ እንደነበረ ያሳያል። ከቶውንም #ከመልአክ ጋር እንደምትነጋገርና #ከሰማይ ልዩ #ጸጋዎችን እንደምታገኝ አልጠበቀችም። #የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #የሉቃስ ወንጌል #አንድምታው እንደሚለው <<ማርያም #የኢሳያስን #ትንቢት የሆነውን ኢሳ 7፥14 ስታነብ ያቺን #ሴት ምነው እኔ #በሆንኩ አላለችም። እንደውም ምነው #ከጊዜዋ ደርሼ #ወጥቼ #ወርጄ አገልግያት በማለት #ታስብ እንደነበር ይገልጻል[1]። እንዲህ አይነት #ሁኔታዎች እንዲፈጸምላት የሚያደርግ #ምንም የተለየ ነገር አልነበራትም። አንዳንድ የስነ መለኮት #አስተማሪዎችም እንደሚናገሩት <<ማርያም #ከሌሎች አይሁዳውያን #ሴቶችና #ልጃገረዶች #የተለየች ብትሆን ኖሮ <<መልካም እንግዲህ #ጊዜው #ደርሷል! እስከአሁንም #ስጠብቀው ቆይቻለሁ! ትል ነበር። ነገር ግን #በፍጹም አላለችም[2]!!! ሁሉ ነገር ለእሷ #አዲስና #አስደናቂ #ዱብእዳ ስለነበረ ግራ #ተጋብታለች#ፈርታለች#ደንግጣለችም <<ይህ እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው?>> በማለትም አስባለች። #ቅዱስ ገብርኤልም #አትፍሪ በማለት #የማረጋጋት ተግባር ሲያከናውን ይታያል።

▶️ ከዚያም #መልአኩ ገብርኤል #መልካሙን #ዜና ያበሰራት #ኢየሱስን (አዳኝ፣ መድኃኒት) ማቲ 1፥21 ብላ የምትሰይመውን #መሲህ እንደምትወልድ ነበር። በመቀጠልም #መልአኩ የኢየሱስን #አምላክነትና #ሰብአዊነት አስረግጦ በመንገር #የምትወልደው #ልጅ ታላቅ እንደሆነና እንደሚሆን እንጂ በእርሷ ታላቅነት ላይ አላተኮረም {ሉቃ 1፥31}።

▶️ የሚወለደው ህጻን(ኢየሱስ) #ንጉስ ሆኖ #የዳዊትን #ዙፋን በመውረስ #ለዘላለም በእስራኤል ላይ #ይነግሳል#እግዚአብሔር #ከዳዊት ጋር የገባውን #ቃል #ኪዳን (2ኛሳሙ 7) እና ለእስራኤል #ህዝብ የሰጠውን #የመንግስት የተስፋ #ቃሎች #እያመለከተ ነበር {ኢሳ 9፤1-7፣ 11-12 ፣ 61 ፣ 66፣ ኤር 33}።
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ #ሴቶች ሰፊ ስፍራ #ከወንዶች #እኩል ተሰጥቷአቸው #እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው እናነባለን። በተለይ #በአዲስ ኪዳን #የእግዚአብሄር ቃል በግልጽ <<አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።>> {ገላ 3፥28} ይላል። እንዲሁም <<እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።>> {ሮሜ 2፥11}፣ <<በአይሁዳዊና…
▶️ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉት #ሀሳቦች በሙሉ #የተፈለሰፉት #ማርያም <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> እንደሆነች #መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚናገር በማሰብ ሲሆን ከላይ እንደተገለጸው #ከእግዚአብሄር #ቀጥላ #ሁለተኛ #አምልኮት የሚቀርብላት ሆናለች። ነገር ግን #መልአኩ #ገብርኤልም#ኤልሳቤጥም የተናገሩት አንድ አይነት ቃል <<ከሴቶች በላይ፣ ከፍጡራን ሁሉ በላይ>> ሳይሆን <<ከሴቶች #መካከል>> የሚለውን እንደሆነ #መጽሀፍ ቅዱስን የሚያነብ ሰው ሁሉ የሚያገኘው #እውነት ነው{ሉቃ 1፥ 28፣ 42}።

<<መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።>> {ሉቃ 1፥28}

<<በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።>> {ሉቃ 1፥42}

▶️ ይህ #ቃል #የማርያምን #የበላይነትና የተለየ #ማንነትን ወይም #ትርጉምን በጭራሽ አይሰጥም። ሌለው ነገር ደግሞ #ክርስቶስን #መውለዷ <ከፍጡራን በላይ> አያደርጋትም። ምክንያቱም ደግሞ #ክርስቶስ በእርሷ #በኩል መጣ እንጂ እሷ #ክርስቶስን አልመጣችውም። እንዲያውም #ማርያም በእርሷ የሆነው ሁሉ #ያስገርማትና #ያስደንቃት ነበር እንጂ #በማንነቷ ድምር #ውጤት ያገኘችው #ሽልማት አልነበረም።

▶️ እግዚአብሔር በብዙ #ሰዎችና #መላእክት በተፈጥሮ #ግኡዛንን እንኳ ሳይቀር #በድንቅ #ስራው #በሚገርም #ተአምሩ እንደተጠቀመባቸው ስናይ አድራጊው #ኃያልና #ግሩም መሆኑን #ሃሳቡንም #እንደወደደ እንደሚያደርግ ያሳየናል እንጂ የተጠቀመበት #እቃ ወይም #ፍጡር #ታላቅና #ከሁሉ #በላይ መሆኑን በፍጹም #አያመለክትም {ሉቃ 2፥20}።

▶️ በድንግልና #መውለድ ደግሞ በራሱ <ከፍጡራን በላይ> አያረግም ምክንያቱም #ከእሷ የሆነ #ምንም ነገር የለምና። #በድንግልና ገብቶ #በድንግልና #መውጣት የሚያስገርመው #የክርስቶስ #ማንነት ይረቃል እንጂ የባለድንግልናው #ባለቤት በፍጹም አያስደንቅም። #ድንግልና ለማንኛዋም #ሴት #ከእግዚአብሄር የተሰጣት የተፈጥሮ #ስጦታ ነው። ይልቁንም #በተዘጋ በር #ገብቶ #በተዘጋ በር የወጣው #ኢየሱስ ክርስቶስ ግን #ከተፈጥሮ #ህግ ውጭ የሚንቀሳቀሰው እርሱ #ማነው? #ያስብላል#ያስገርማል#ያስደንቃል#ያስመሰግናል#ያሰግዳል