ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#አራቱ_ወንጌላዊያን_በወንጌል_ላይ_ስለ_ጌታችን_ትንሳኤ_የጻፉት_ድርጊቶች_እና_ትዕይንቶች_እርስ_በእርሳቸው_ይጋጫሉ?

አራቱ ወንጌላዊያን ከየራሳቸው የትኩረት አቅጣጫ በዕለተ ትንሳኤ የተከናወኑትን ድርጊቶች እና የተፈጸሙትን ትዕይንቶች እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ እንደገለጠላቸው የሚፈልጉት ነገር ላይ ብቻ የትኩረታቸውን ማዕከል በማድረግ ጽፈዋል።

#ማቴዎስ
👉 በሰንበት ሲነጋ ማርያም መግደላዊት እና ሁለተኛይቱ ማርያም መጡ ይላል። ማቴ 28:1
👉 ሲደርሱም መልአክ ከሰማይ ወርዶ ድንጋዩን እንዳንከባለለና ትንሳኤውንም አብስሮ ለደቀመዛሙርቱ ሄደው እንዲነግሩ አዘዛቸው። ማቴ 28–2—8
👉 በመንገድ ሲሄዱም ክርስቶስን እንዳገኙትና እንደሰገዱለት ይናገራል። ማቴ 28:9

#ማርቆስ
👉 ሰንበት ካለፈ በዋላ ሰሎሜ፣ መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብ እናት ማርያም ሽቶ ገዝተው ሊቀቡት መምጣታቸውን ይናገራል። ማር 16:1–2
👉 ከሳምንቱ በፊተኛው (እሁድ) ቀን እጅግ ማልደው ፀሀይ ከወጣ በኋላ መጥተው መልአኩ አብስሯቸው ሄደው ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሯቸው አዘዛቸው። ማር 16:3–8
👉ከዛም በኋላ ለማርያም መግደላዊት ብቻ እንደታያት ይናገራል። ማር 16:9

#ሉቃስ
👉በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ሽቶ ይዘው ማርያም መግደላዊት፣ ዮሐና፣ የያዕቆብ እናት ማርያም እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ማልደው እንደመጡና መቃብሩም ጋር ሁለት መላእክት እንዳዩ ጽፏል። ሉቃ 24:1–8

#ዮሐንስ
👉መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን እሁድ እንደመጣች የመቃብሩን ባዶ መሆን አይታ ለሐዋርያው ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለዮሐንስ ሄዳ መናገሯን እነርሱም መጥተው እንዳረጋገጡ ይናገራል። ዮሐ 20:1–10
👉 ማርያም መግደላዊት ግን የጌታን ሥጋ ወስደውታል ብላ እያለቀሰች እዛው እንደቆየች እና ሁለት መላእክት እንዳየች ጌታ ራሱም ተገልጦ እንዳነጋገራት አትንኪኝ እንዳላት ይናገራል። ዮሐ 20:11–17

ከላይ የተጻፉትን ስንመለከት እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ይመስላሉ ነገር ግን በፍጹም ግጭት የለባቸውም። በአንድ ቀን እንዴት እንዲህ የተለያየ ሁኔታ ሊፈጠር ቻለ የሚያስብል ይመስላል። ነገር ግን ፍጹም ስህተት የሌለው ነው። እያንዳንዱ ከተፈጸመው ነገር የተወሰነውን ወስደው በአገላለጽ አለያይተው ጻፉት እንጂ። ለምሳሌ ሁለት ሰዎች እግር ኳስ ለማየት ስታዲየም ቢገቡ አንዱ ሜዳ ላይ ስለተደረገው ጨዋታ ቢዘግብ ሌላው ደግሞ ስለ ደጋፊውና ስለ ስታዲየሙ ድባብ ቢናገር ሁለቱ ተጋጭተዋል ማለት አይደለም። አራቱ ወንጌላዊያንም ስለጌታችን ትንሳኤ ሲተርኩ ከተለያየ የትኩረት አቅጣጫ አንድ ነገር ላይ ማዕከል አድርገው ዘገቡት። እንዴት እንደሆነ እንመልከት እስኪ:

#የሰዎቹን_አካሄድ_በተመለከተ

👉ቅዱስ ማቴዎስ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም አለ። ይህ ማለት ወደ መቃብሩ ሌሎች ሰዎች አልመጡም ማለት አይደለም። እነርሱ "ብቻቸውን" መጡ ብሎ አልተናገረምና።

👉ቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ማቴዎስ ያልጠቀሳትን ሰሎሜን ጨመራት።

👉ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ በአጠቃላይ ወደ መቃብሩ የመጡትን ሴቶች ጠቀሳቸው።

👉የዮሐንስ ወንጌል ደግሞ ማርያም መግደላዊት ከሁሉም ቀድማ (በጭለማ) መምጣቷን ይናገራል።

#ስለተከሰቱት_ትዕይንቶች

👉የቅዱስ ማቴዎስን ዘገባ ስንመለከት መልአኩ ድንጋዩን አንከባሎ ሲቀመጥ ሴቶቹ ተመልክተዋል። ከዛም መልአኩ የመቃብሩን ባዶ መሆን ካዩ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲያበስሩ ነገራቸው። በታዘዙት መሰረት ሄደው ለደቀመዛሙርቱ ሲያበስሩ ዮሐንስ እና ጴጥሮስ መጥተው አረጋግጠው ሄደዋል። ቅዱስ ማቴዎስ ግን መቃብሩን ደቀ መዛሙርቱ መተው ማረጋገጣቸውን ሳይናገር አልፎታል።
በመልአኩ ብስራት ሴቶቹ ለደቀመዛሙርቱ ሊያበስሩ ሲሄዱ በመንገድ ጌታችንን አይተው እንደሰገዱለት ተጽፏል። ይህን ስንመለከት ደግሞ ዮሐንስ ማርያም መግደላዊትን ጌታችን እንዳናገራትና አትንኪኝ እንዳላት የተጻፈውን ሳይገልጥ ሴቶቹ ጌታን እንዳገኙት ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ንገሯቸው ሚለውን ብቻ ጽፏል። ይህ ማለት ግን ሌሎች ድርጊቶች አልተፈጸሙም ማለት አይደለም።

👉ቅዱስ ማርቆስ መልአኩ ድንጋዩን ማንከባለሉን ሳይገልጥ መቃብሩን መልአኩ እንዳሳያቸው እና ሄደው ትንሳኤውን እንዲያበስሩ እንዲሁም ጌታ መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት መታየቱን ገለጸ።

👉ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ መልአኩ ድንጋዩን ማንከባለሉን ሴቶቹንም መላእክቱ እንዳናገሯቸው ሄደውም እንዲያበስሩ እንደነገሯቸው ጻፈ። ደቀ መዛሙርቱም በሴቶቹ ብስራት መጥተው ማረጋገጣቸውን ቅዱስ ጴጥሮስ ብሎ ቅዱስ ዮሐንስን ሳይጠቅስ ጽፏል። ቅዱስ ጴጥሮስ ብቻውን ነው የሄደው ማለት ግን አይደለም። ምክኒያቱም "ጴጥሮስ ብቻ" አይልምና።

👉ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሌሎቹ ሴቶች ዘግይተው የመጡ ቢሆንም ቀድማ የመጣቸው ግን ማርያም መግደላዊት ስለነበር ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም መግደላዊት መጣች ብሎ ተናገረ። ይህ ማለት ከእርሷ በኋላ ሌሎቹ ሴቶች አልመጡም ማለት አይደለም። የድንጋዩን መፈንቀል የመቃብሩን ባዶ መሆን ሄዳ ለደቀ መዛሙርቱ (ለጴጥሮስ እና ለዮሐንስ) ተናገረች። እነርሱም መተው አረጋግጠው ሄዱ። እርሷ ግን እዛው እያለቀሰች ቆየች መላእክቱም ስለ ምን እንደምታለቅስ ጠየቋት ጌታችንንም አገኘችው። አትንኪኝ አላት። ከሁሉም ቀድማ ትንሳኤውን አየች።

እንደተመለከትነው አራቱም ወንጌላዊያን መጥቀስ የፈለጉትን ነገር ብቻ ጠቅሰው ተናገሩ እንጂ ታሪኩን አላፈለሱትም እርስ በእርሳቸውም አልተጋጩም።

#እስኪ_ሙሉ_ታሪክ_እና_ትዕይንቱን_እንመልከት

ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ጭለማ ሳለ በማለዳ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሥጋ ሽቱ ልትቀባ መጣች። ከእርሷም ተከትለው ሌሎቹ ሴቶች ወደ መቃብሩ መጡ። የጌታ መልአክ ወርዶም ድንጋዩን አንከባለለው። መቃብሩም ባዶ መሆኑን ሴቶቹ ተመለከቱ። መላእክቱም መቃብሩ ባዶ መሆኑን እርሱም መነሳቱን ነገሯቸው ለደቀመዛሙርቱም እንዲነግሯቸው አዘዟቸው። ሴቶቹም ሄደው መቃብሩ ባዶ መሆኑንና ጌታም መነሳቱን ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ነገሯቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስም መጥተው አረጋገጠው ተመለሱ። ከእነርሱ ኋላም ሴቶቹ መጥተው ነበር ማርያም መግደላዊትም ጭምር መቃብር ውስጥ መላእክት ተገልጸው ከሴቶቹ ጋር ሲነጋገሩ ውጪ ደግሞ ለማርያም መግደላዊት ጌታ ተገለጠላት። መነሳቱንም ተጠራጥራ ነበርና አትንኪኝ አላት። ውስጥ የነበሩት ሴቶች የምስራቹን ለማብሰር በመንገድ ሲሄዱ ጌታ ራሱ ተገለጠላቸው። እነርሱም ሰገዱለት። (ለማርያም መግደላዊት ሲታያት ለሁለተኛ ጊዜ ነው።) የሆነውን ለደቀ መዛሙርቱ ነገሯቸው። በዚህ መሰረት አራቱም ወንጌላዊያን የጻፉትን ስንመለከት ምንም ግጭት እንደሌለ መረዳት እንችላለን።

ይቆየን።
በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
"ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ"
#ውዳሴ_ማርያም ዘ አርብ

የውዳሴ ማርያም ጸአፊ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ ቢሆንም ቅሉ ደራሲው ግን መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ በገለጠለት መሠረት ሊቁ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን "ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ " ሲል አራቆ ጽፏል ።

አዎን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መሰላል ነች ። በመሠላል እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እላይ ያለውም ወደታች ይወርድበታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የምድራዊ ሰዎችን ጸሎትና ልመና ወደ ሰማይ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ታደርሳለች ታሳርጋለች የእግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረትን ደግሞ ወደ ሰው ልጆች ታወርዳለት ፣ታመጣለችና አማናዊት መሰላል ነች። ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማህሌተ ጽጌው "አልቦ ጸሎት  ወአልቦ ትንባሌ እንበሌከ ማርያም የዓአርግ ሉዓሌ" ድንግል ማርያም ሆይ ያላንቺ አማላጅነት ወደ ሰማይ የሚያርግ ጸሎትና ልመና የለም"  እንዳለ

ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ስለ ጌታችን ዕርገት ሲናገር እንዲ ይላል "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። " #ሉቃ 24÷50

ዕርገቱም እንደ ኤልያስ በሠረገላ እንደ ሄኖክም በመሰወር እንደ ሕዝራም ሱቱኤል በመላእክት እገዛ የሆነ አይደለም ። ደመና ከዐይናቸው ሰውራ እስክትቀበለው ድረስ ከፍ ከፍ አለ እንጂ አልጠፋባቸውም ሰማይን አተኩረው እስኪመለከቱ ድረስ የሰማይ መላእክትም እንኪገስጾቸው ድረስ በተመስጦ ሆነው ሲያርግ አዮት እንጂ አረቀቀባቸውም በሰው አምሮ በሚረዳና በሚገባ መልኩ በርዕቀት ከነርሱ ተለይቶ ከፍ ከፍ አለ ዐረገ ። " እናንት የገሊላ ሰዎች እንዲህ አተኩራችሁ ወደ ሰማይ የምትመለከቱት ስለምንድነው እንዲሁ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ደግሞ ይመጣልና " #ሐዋ 1÷11

መሰላል ሁለት ትይይዮ የሆኑ ቋሚ ዘንጎች ያሉት ሲሆን በመካከላቸውም በየተወሰነ ርቀቱ በተደረደሩ አግዳሚ ዘንጎች ሁለቱ ትይዮ ዘንጎች የተጋጠሙ ናቸው ::

ሁለቱ ትይዮ የሆኑ ረጃችም ዘንጎች በሁለት ወገን ድንግል መሆኗን (ድንግል በክሌ) ያመሰጥራሉ። አንድም ብሉይና ሐዲስን ሲወክሉ በመካከላቸው ያሉ ርብራብ ዘንጎች ደግሞ የብሉይና የሐዲስ መገናኛው ድልድይ እመቤታችን መሆኟን ያስረዳሉ በቡሉይ መጨረሻ በሐዲስ መጀመሪያ ተገኝታለችን አንድም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ፈራጅ የሆነ ንጉሥ ሰው ሲሆን አምላክ አምላክ ሲሆን ደግሞ ሰው የሆነውን መካከለኛ ትወልደዋለችና። አንድም የጠቡ ግድግዳ የፈረሰባት ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት ነፍስና ሥጋ የታረቁባት የተቀራረቡባት የዕርቅ ሰነድ እመቤታችን ነችና መሰላል የእመቤታችን ምሳሌ ነው።
በመጻሕፍ ቅዱስ ላይም ይህ ነገር የጎላ የተረዳ ነው::..." ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ #እነሆም_መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም_የእግዚአብሔር_መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥# እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ #ዘፍ 28÷10-13

ታድያ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ አንቺ ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ሲል ግን እንደ መሰላል ተረግጧት ወጣ ማለት አይደለም የወጣው ወደ ሰማይ ነው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቁመትም እንደ ሰው ሁሉ ሦስት ክንድ ከስንዝር ብቻ ነው ።

በምሥጢር ሊናገር የፈለገው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ባይነሳ ኖሮ ለመለኮት ወደ ሰማይ ዐረገ የሚልል ነገር ባልተነገረለት ነበር የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ ስላደረገ ውጣ ፣ከፍ ፣ከፍ አለ ዐረገ የሚሉት ነገሮች ተነገረለት ። ቅዱስ ኤፍሬም ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ብቻ ይበል እንጂ ቅሉ እመቤታችንስ ለቃል ከሰማይ ወደ ምድር ለመውረድም መሰላል ሆናዋለች። ድንግል ማርያም ባትኖር ኖሮ ከማን ሰው ይሆን ነበር? መንክር ኦ ዝ ምሥጢር!

እንዲያውም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዕርገቱንና ሰው የመሆኑን ምሥጢር ሲያወዳጁ እንዲ ይላሉ"የቃል ርደት በማኅጸን የሥጋ ዕርገት በአርባ ቀን"

ምን ማለታቸው ነው ቢሉ ለቃል ርደትም ለሥጋ ዕርገትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ መሰላል ሆና ለች ያለ እመቤታችን የቃል ርደት (መውረድ) ሆነ የሥጋ ዕርገት አይታሰብምና ነው።

ክቡር ዳዊትም ይህን የሊቁን ሀሳብ የቅዱስ ኤፍሬምን ሀሳብ ሲደግፍ እንዲ ይላል። “ #በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ #ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።” #መዝ (68) 68፥33 በምሥራቅ በኩል ማለቱ አቅጣጫን ብቻ የሚጠቁም ሳይሆን ከምሥራቅ ፀሐይ እንደሚወጣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምም ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወጣልና እመቤታችን #ምሥራቀ_ምሥራቃት_ሞጻ_ፀሐይ ትባላለችና ፀሐይ ክርስቶስ የወጣባት ምሥራቃዊ መሠላል እርሷ ነች ። መለኮት በሁሉ የመላ ፣ በሁሉ ያለ ነው የሌለበት ቦታ የለም በዚህ አለ በዚያ የለም አይባልለትም # መዝ 138 (139)÷7-10 ነገር ግን የምሥራቅ የእመቤታችንን ሥጋና ነፍስ በመዋሕዱ ግን ከምድር ወደ ሰማይ ሄደ ከፍ ከፍ አለ ዐረገ ተባለለት ። መለኮት ዐረገ እንዲባል ምክንያትቱ ምሥራቁ ሆነችው ።

የነዚህ የዳዊትና የኤፍሬም የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ምን ይረቅ?
__ #ለምን_ዐረገ ? ___
#ትንቢቱን_ለመፈጸም :-"አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ። #መዝ46(47)÷5-6 ነቢዮ ዳዊት ይህን የተናገረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ነው።
#ሥፍራን_ለማዘጋጀት :- መግሥተ ሠማያት ቀድማ ያልተዘጋጀች አሁን ሄዶ የሚያዘጋጃት ሆና ሳይሆን ለእናንተ ለአባቴ ብሩካኖች የተገባች ሆና በመጨረሻው ቀን ተገልጣ እንድትሰጣችሁ የማደርግ እኔ ነኝ አሁን ሄጄ በአባቴ ዕሪና (ትክክል ) በአብ ቀኝ በክብሩ ዙፋን ልቀመጥ ይገባኛል ሲል ነው “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤” #ዮሐንስ 14፥2
#መንፈስ_ቅዱስን_ለመላክ :- “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።” #ዮሐንስ 16፥7

አ.አ ኢትዮጵያ
ሰኔ ፫ቀን / ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
ዐውደ ምሕረት
Photo
“ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።”
#ዮሐንስ 20፥27
| በድጋሚ የተለጠፈ
" #ከምድር_ወደ_ሰማይ_ለማረግ_መሰላል_ሆንሽ "
________
#ውዳሴ_ማርያም ዘ አርብ

የውዳሴ ማርያም ጸሐፊ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ ቢሆንም ቅሉ ደራሲው ግን መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ በገለጠለት መሠረት ሊቁ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን "ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ " ሲል አራቆ ጽፏል ።

አዎን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መሰላል ነች ። በመሠላል እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እላይ ያለውም ወደታች ይወርድበታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የምድራዊ ሰዎችን ጸሎትና ልመና ወደ ሰማይ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ታደርሳለች ታሳርጋለች የእግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረትን ደግሞ ወደ ሰው ልጆች ታወርዳለት ፣ታመጣለችና አማናዊት መሰላል ነች። #ሊቁ_አባ_ጽጌ_ድንግል በማህሌተ ጽጌው "አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ እንበሌከ ማርያም የዓአርግ ሉዓሌ" #ድንግል_ማርያም_ሆይ ያላንቺ አማላጅነት ወደ ሰማይ የሚያርግ ጸሎትና ልመና የለም" እንዳለ

ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ስለ ጌታችን ዕርገት ሲናገር እንዲ ይላል "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። " #ሉቃ 24÷50

ዕርገቱም እንደ ኤልያስ በሠረገላ እንደ ሄኖክም በመሰወር እንደ ሕዝራም ሱቱኤል በመላእክት እገዛ የሆነ አይደለም ። ደመና ከዐይናቸው ሰውራ እስክትቀበለው ድረስ ከፍ ከፍ አለ እንጂ አልጠፋባቸውም። ሰማይን አተኩረው እስኪመለከቱ ድረስ የሰማይ መላእክትም እንኪገስጾቸው ድረስ በተመስጦ ሆነው ሲያርግ አዮት እንጂ አረቀቀባቸውም በሰው አምሮ በሚረዳና በሚገባ መልኩ በርዕቀት ከነርሱ ተለይቶ ከፍ ከፍ እያለ ዐረገ ። "እናትት የገሊላ ሰዎች እንዲህ አትኩራችሁ ወደ ሰማይ የምትመለከቱ ስለምንድነው እንዲሁ ሲሄድ እንዳያችሁ እንዲሁ ደግሞ ይመጣልና" #ሐዋ1÷11

መሰላል ሁለት ትይይዮ የሆኑ ቋሚ ዘንጎች ያሉት ሲሆን በመካከላቸውም በየተወሰነ ርቀቱ በተደረደሩ አግዳሚ ዘንጎች ሁለቱ ትይዮ ዘንጎች የተጋጠሙ ናቸው ::

ሁለቱ ትይዮ የሆኑ ረጃችም ዘንጎች በሁለት ወገን ድንግል መሆኗን (ድንግል በክሌ) ያመሰጥራሉ። አንድም ብሉይና ሐዲስን ሲወክሉ በመካከላቸው ያሉ ርብራብ ዘንጎች ደግሞ የብሉይና የሐዲስ መገናኛው ድልድይ እመቤታችን መሆኟን ያስረዳሉ በቡሉይ መጨረሻ በሐዲስ መጀመሪያ ተገኝታለችን አንድም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ፈራጅ የሆነ ንጉሥ ሰው ሲሆን አምላክ አምላክ ሲሆን ደግሞ ሰው የሆነውን መካከለኛ ትወልደዋለችና። አንድም የጠቡ ግድግዳ የፈረሰባት ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት ነፍስና ሥጋ የታረቁባት የተቀራረቡባት የዕርቅ ሰነድ እመቤታችን ነችና መሰላል የእመቤታችን ምሳሌ ነው።
በመጻሕፍ ቅዱስ ላይም ይህ ነገር የጎላ የተረዳ ነው::..." ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ #እነሆም_መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም_የእግዚአብሔር_መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥# እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ #ዘፍ 28÷10-13

ታድያ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ አንቺ ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ሲል ግን እንደ መሰላል ተረግጧት ወጣ ማለት አይደለም የወጣው ወደ ሰማይ ነው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቁመትም እንደ ሰው ሁሉ ሦስት ክንድ ከስንዝር ብቻ ነው ።

በምሥጢር ሊናገር የፈለገው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ባይነሳ ኖሮ ለመለኮት ወደ ሰማይ ዐረገ የሚልል ነገር ባልተነገረለት ነበር የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ ስላደረገ ውጣ ፣ከፍ ፣ከፍ አለ ዐረገ የሚሉት ነገሮች ተነገረለት ። ቅዱስ ኤፍሬም ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ብቻ ይበል እንጂ ቅሉ እመቤታችንስ ለቃል ከሰማይ ወደ ምድር ለመውረድም መሰላል ሆናዋለች። ድንግል ማርያም ባትኖር ኖሮ ከማን ሰው ይሆን ነበር? መንክር ኦ ዝ ምሥጢር!

እንዲያውም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዕርገቱንና ሰው የመሆኑን ምሥጢር ሲያወዳጁ እንዲ ይላሉ"የቃል ርደት በማኅጸን የሥጋ ዕርገት በአርባ ቀን"

ምን ማለታቸው ነው ቢሉ ለቃል ርደትም ለሥጋ ዕርገትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ መሰላል ሆና ለች ያለ እመቤታችን የቃል ርደት (መውረድ) ሆነ የሥጋ ዕርገት አይታሰብምና ነው።

ክቡር ዳዊትም ይህን የሊቁን ሀሳብ የቅዱስ ኤፍሬምን ሀሳብ ሲደግፍ እንዲ ይላል። “ #በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ #ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።” #መዝ (68) 68፥33 በምሥራቅ በኩል ማለቱ አቅጣጫን ብቻ የሚጠቁም ሳይሆን ከምሥራቅ ፀሐይ እንደሚወጣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምም ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወጣልና እመቤታችን ምሥራቀ ምሥራቃት ሞጻ ፀሐይ ትባላለችና ፀሐይ ክርስቶስ የወጣባት ምሥራቃዊ መሠላል እርሷ ነች ። መለኮት በሁሉ የመላ ፣ በሁሉ ያለ ነው የሌለበት ቦታ የለም በዚህ አለ በዚያ የለም አይባልለትም #መዝ 138(139)÷7-10 ነገር ግን የምሥራቅ የእመቤታችንን ሥጋና ነፍስ በመዋሕዱ ግን ከምድር ወደ ሰማይ ሄደ ከፍ ከፍ አለ ዐረገ ተባለለት ። መለኮት ዐረገ እንዲባል ምክንያትቱ ምሥራቁ ሆነችው ።

የነዚህ የዳዊትና የኤፍሬም የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ምን ይረቅ?
__#ለምን_ዐረገ ? ___
#ትንቢቱን_ለመፈጸም :-"አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ። #መዝ46(47)÷5-6 ነቢዮ ዳዊት ይህን የተናገረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ነው።
#ሥፍራን_ለማዘጋጀት :- መግሥተ ሠማያት ቀድማ ያልተዘጋጀች አሁን ሄዶ የሚያዘጋጃት ሆና ሳይሆን ለእናንተ ለአባቴ ብሩካኖች የተገባች ሆና በመጨረሻው ቀን ተገልጣ እንድትሰጣችሁ የማደርግ እኔ ነኝ አሁን ሄጄ በአባቴ ዕሪና (ትክክል ) በአብ ቀኝ በክብሩ ዙፋን ልቀመጥ ይገባኛል ሲል ነው “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤” #ዮሐንስ 14፥2
#መንፈስ_ቅዱስን_ለመላክ :- “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።” #ዮሐንስ 16፥7

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ ማርያም
ሰኔ ፫/፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
#ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።”(መዝ 8፥2)

#ፍስሐ #ጽዮን የተባለ #ተክለሃይማኖት በተወለደ በሦስተኛው ቀን "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ እግዚአብሔርን አመሰገነ።

#ነቢየ #እግዚአብሔር #ኤርምያስ “በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።” (ኤር 1፥5)እንደተባለ ቅዱስ #ተክለሃይማኖት ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ነቢይ ሆኖ ለእግዚአብሔር ተለየ።

#መልአከ #ብርሃን ቅዱስ #ገብርኤል ስለ ቅዱስ #ዮሐንስ መጥምቅ“በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤”( ሉቃስ 1፥15) እንዳለ #ተክለሃይማኖት ጻድቅ ከዓለምና ከምኞቷ ሁሉ የተለየ ፤ በጌታም ፊት ታላቅ የተባለ ፤ መንፈስ ቅዱስም የሞላበት ነው።ዳግመኛም መልአክ “ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”(ሉቃ 1፥14) እንዳለ በፍስሐ ጽዮን (በጽዮን ደስታ) በ #ተክለሃይማኖት መወለድ ለጊዜው አባቱ ቅዱስ #ጸጋ ዘአብና እናቱ ቅድስት #እግዚእ ኃረያ ተደስተዋል ፤ ለፍጻሜው ግን ጽዮን የተባለች ቅድስት #ቤተክርስቲያን ተደስታለች።

#ቅዱስ #ጳውሎስም ስለ ራሱ “ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም”(ገላ1፥15-16) እንዳለ አባታችን #ተክለሃይማኖት በጸጋ #መንፈስ #ቅዱስ ለስብከተ ወንጌል ገና በማኅፀን ተጠራ።

#ጌታም በወንጌል ስለ እነ #ተክለሃይማኖት እንዲህ አለ “በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ”(ማቴ 19፥12)

#እንኳን አደረሳችሁ!!!

#ታኅሣሥ 26 /2017 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ