#አራቱ_ወንጌላዊያን_በወንጌል_ላይ_ስለ_ጌታችን_ትንሳኤ_የጻፉት_ድርጊቶች_እና_ትዕይንቶች_እርስ_በእርሳቸው_ይጋጫሉ?
አራቱ ወንጌላዊያን ከየራሳቸው የትኩረት አቅጣጫ በዕለተ ትንሳኤ የተከናወኑትን ድርጊቶች እና የተፈጸሙትን ትዕይንቶች እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ እንደገለጠላቸው የሚፈልጉት ነገር ላይ ብቻ የትኩረታቸውን ማዕከል በማድረግ ጽፈዋል።
#ማቴዎስ
👉 በሰንበት ሲነጋ ማርያም መግደላዊት እና ሁለተኛይቱ ማርያም መጡ ይላል። ማቴ 28:1
👉 ሲደርሱም መልአክ ከሰማይ ወርዶ ድንጋዩን እንዳንከባለለና ትንሳኤውንም አብስሮ ለደቀመዛሙርቱ ሄደው እንዲነግሩ አዘዛቸው። ማቴ 28–2—8
👉 በመንገድ ሲሄዱም ክርስቶስን እንዳገኙትና እንደሰገዱለት ይናገራል። ማቴ 28:9
#ማርቆስ
👉 ሰንበት ካለፈ በዋላ ሰሎሜ፣ መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብ እናት ማርያም ሽቶ ገዝተው ሊቀቡት መምጣታቸውን ይናገራል። ማር 16:1–2
👉 ከሳምንቱ በፊተኛው (እሁድ) ቀን እጅግ ማልደው ፀሀይ ከወጣ በኋላ መጥተው መልአኩ አብስሯቸው ሄደው ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሯቸው አዘዛቸው። ማር 16:3–8
👉ከዛም በኋላ ለማርያም መግደላዊት ብቻ እንደታያት ይናገራል። ማር 16:9
#ሉቃስ
👉በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ሽቶ ይዘው ማርያም መግደላዊት፣ ዮሐና፣ የያዕቆብ እናት ማርያም እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ማልደው እንደመጡና መቃብሩም ጋር ሁለት መላእክት እንዳዩ ጽፏል። ሉቃ 24:1–8
#ዮሐንስ
👉መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን እሁድ እንደመጣች የመቃብሩን ባዶ መሆን አይታ ለሐዋርያው ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለዮሐንስ ሄዳ መናገሯን እነርሱም መጥተው እንዳረጋገጡ ይናገራል። ዮሐ 20:1–10
👉 ማርያም መግደላዊት ግን የጌታን ሥጋ ወስደውታል ብላ እያለቀሰች እዛው እንደቆየች እና ሁለት መላእክት እንዳየች ጌታ ራሱም ተገልጦ እንዳነጋገራት አትንኪኝ እንዳላት ይናገራል። ዮሐ 20:11–17
✝ ከላይ የተጻፉትን ስንመለከት እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ይመስላሉ ነገር ግን በፍጹም ግጭት የለባቸውም። በአንድ ቀን እንዴት እንዲህ የተለያየ ሁኔታ ሊፈጠር ቻለ የሚያስብል ይመስላል። ነገር ግን ፍጹም ስህተት የሌለው ነው። እያንዳንዱ ከተፈጸመው ነገር የተወሰነውን ወስደው በአገላለጽ አለያይተው ጻፉት እንጂ። ለምሳሌ ሁለት ሰዎች እግር ኳስ ለማየት ስታዲየም ቢገቡ አንዱ ሜዳ ላይ ስለተደረገው ጨዋታ ቢዘግብ ሌላው ደግሞ ስለ ደጋፊውና ስለ ስታዲየሙ ድባብ ቢናገር ሁለቱ ተጋጭተዋል ማለት አይደለም። አራቱ ወንጌላዊያንም ስለጌታችን ትንሳኤ ሲተርኩ ከተለያየ የትኩረት አቅጣጫ አንድ ነገር ላይ ማዕከል አድርገው ዘገቡት። እንዴት እንደሆነ እንመልከት እስኪ:
#የሰዎቹን_አካሄድ_በተመለከተ
👉ቅዱስ ማቴዎስ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም አለ። ይህ ማለት ወደ መቃብሩ ሌሎች ሰዎች አልመጡም ማለት አይደለም። እነርሱ "ብቻቸውን" መጡ ብሎ አልተናገረምና።
👉ቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ማቴዎስ ያልጠቀሳትን ሰሎሜን ጨመራት።
👉ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ በአጠቃላይ ወደ መቃብሩ የመጡትን ሴቶች ጠቀሳቸው።
👉የዮሐንስ ወንጌል ደግሞ ማርያም መግደላዊት ከሁሉም ቀድማ (በጭለማ) መምጣቷን ይናገራል።
#ስለተከሰቱት_ትዕይንቶች
👉የቅዱስ ማቴዎስን ዘገባ ስንመለከት መልአኩ ድንጋዩን አንከባሎ ሲቀመጥ ሴቶቹ ተመልክተዋል። ከዛም መልአኩ የመቃብሩን ባዶ መሆን ካዩ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲያበስሩ ነገራቸው። በታዘዙት መሰረት ሄደው ለደቀመዛሙርቱ ሲያበስሩ ዮሐንስ እና ጴጥሮስ መጥተው አረጋግጠው ሄደዋል። ቅዱስ ማቴዎስ ግን መቃብሩን ደቀ መዛሙርቱ መተው ማረጋገጣቸውን ሳይናገር አልፎታል።
በመልአኩ ብስራት ሴቶቹ ለደቀመዛሙርቱ ሊያበስሩ ሲሄዱ በመንገድ ጌታችንን አይተው እንደሰገዱለት ተጽፏል። ይህን ስንመለከት ደግሞ ዮሐንስ ማርያም መግደላዊትን ጌታችን እንዳናገራትና አትንኪኝ እንዳላት የተጻፈውን ሳይገልጥ ሴቶቹ ጌታን እንዳገኙት ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ንገሯቸው ሚለውን ብቻ ጽፏል። ይህ ማለት ግን ሌሎች ድርጊቶች አልተፈጸሙም ማለት አይደለም።
👉ቅዱስ ማርቆስ መልአኩ ድንጋዩን ማንከባለሉን ሳይገልጥ መቃብሩን መልአኩ እንዳሳያቸው እና ሄደው ትንሳኤውን እንዲያበስሩ እንዲሁም ጌታ መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት መታየቱን ገለጸ።
👉ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ መልአኩ ድንጋዩን ማንከባለሉን ሴቶቹንም መላእክቱ እንዳናገሯቸው ሄደውም እንዲያበስሩ እንደነገሯቸው ጻፈ። ደቀ መዛሙርቱም በሴቶቹ ብስራት መጥተው ማረጋገጣቸውን ቅዱስ ጴጥሮስ ብሎ ቅዱስ ዮሐንስን ሳይጠቅስ ጽፏል። ቅዱስ ጴጥሮስ ብቻውን ነው የሄደው ማለት ግን አይደለም። ምክኒያቱም "ጴጥሮስ ብቻ" አይልምና።
👉ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሌሎቹ ሴቶች ዘግይተው የመጡ ቢሆንም ቀድማ የመጣቸው ግን ማርያም መግደላዊት ስለነበር ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም መግደላዊት መጣች ብሎ ተናገረ። ይህ ማለት ከእርሷ በኋላ ሌሎቹ ሴቶች አልመጡም ማለት አይደለም። የድንጋዩን መፈንቀል የመቃብሩን ባዶ መሆን ሄዳ ለደቀ መዛሙርቱ (ለጴጥሮስ እና ለዮሐንስ) ተናገረች። እነርሱም መተው አረጋግጠው ሄዱ። እርሷ ግን እዛው እያለቀሰች ቆየች መላእክቱም ስለ ምን እንደምታለቅስ ጠየቋት ጌታችንንም አገኘችው። አትንኪኝ አላት። ከሁሉም ቀድማ ትንሳኤውን አየች።
✝ እንደተመለከትነው አራቱም ወንጌላዊያን መጥቀስ የፈለጉትን ነገር ብቻ ጠቅሰው ተናገሩ እንጂ ታሪኩን አላፈለሱትም እርስ በእርሳቸውም አልተጋጩም።
#እስኪ_ሙሉ_ታሪክ_እና_ትዕይንቱን_እንመልከት።
ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ጭለማ ሳለ በማለዳ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሥጋ ሽቱ ልትቀባ መጣች። ከእርሷም ተከትለው ሌሎቹ ሴቶች ወደ መቃብሩ መጡ። የጌታ መልአክ ወርዶም ድንጋዩን አንከባለለው። መቃብሩም ባዶ መሆኑን ሴቶቹ ተመለከቱ። መላእክቱም መቃብሩ ባዶ መሆኑን እርሱም መነሳቱን ነገሯቸው ለደቀመዛሙርቱም እንዲነግሯቸው አዘዟቸው። ሴቶቹም ሄደው መቃብሩ ባዶ መሆኑንና ጌታም መነሳቱን ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ነገሯቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስም መጥተው አረጋገጠው ተመለሱ። ከእነርሱ ኋላም ሴቶቹ መጥተው ነበር ማርያም መግደላዊትም ጭምር መቃብር ውስጥ መላእክት ተገልጸው ከሴቶቹ ጋር ሲነጋገሩ ውጪ ደግሞ ለማርያም መግደላዊት ጌታ ተገለጠላት። መነሳቱንም ተጠራጥራ ነበርና አትንኪኝ አላት። ውስጥ የነበሩት ሴቶች የምስራቹን ለማብሰር በመንገድ ሲሄዱ ጌታ ራሱ ተገለጠላቸው። እነርሱም ሰገዱለት። (ለማርያም መግደላዊት ሲታያት ለሁለተኛ ጊዜ ነው።) የሆነውን ለደቀ መዛሙርቱ ነገሯቸው። በዚህ መሰረት አራቱም ወንጌላዊያን የጻፉትን ስንመለከት ምንም ግጭት እንደሌለ መረዳት እንችላለን።
ይቆየን።
በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት
👉 @AwediMeherit