ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
👆👆👆👆👆
ከላይ የቀጠለ

እናንተ ምድራዊ ሰው እንጂ መላእክ እሆን ዘንድ እኔ ማነኝ? እያሉ የሚያቃጥል የትዕትናን እንባ ከዐይኖቻቸው ይፈስ ነበር ። “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ” 1ጴጥ 5÷ 5 እንደተባለ ይህንን ይህን የትዕትና ሥራ ሲከተል ትዕትናው ፀጋውን አብዝታለት ያኔ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ሥላሴን በአንድነት ሦስትነቱ በማመስኑ ተደንቆ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲህ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለው ብሎ የመረቀው የአባቱ ምርቃት ደርሳለት ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከፀሐይ ይልቅ ወደ ምታበራ ሀገር አደረሰው ።

#አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ አባታችንም ደግሞ እንደነርሱ ያዘ በምድር ብቻ ያይደለ በሰማያዊ መቅደስ ጭምር ገብቶ ከሱራፌል ጋር ሱራፊ ሆኖ ክንፉን ከክንፋቸው ገጥሞ ምስጋናው ከምስጋናቸው አንድ ሆኖ በወርቁን ማዕጥንት ይሰልስ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ ራእይ 5፥8 የቅዱስ ጳውሎስን ነገሩን ትምህርቱን የተከተለ ብጹህ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ወደ ሰማይ በመመንጠቅም ተከተለው፡፡ በመከራው መስሎታልና በክብሩ መሰለው “ ወደ ገነት ተነጠቀ ሰውም ሊናገረው የማይገባወን የማይነገረውንም ቃል ሰማ ተብሎ እንደ ተጻፈ 2ቆሮ 12÷4 ስለዚህ በገድሉ መጻሕፍ እንዲ ሲል ሰማነው "ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከሃያ አራቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር በአንንድነት አጠንኩ ምስጋዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደ ልብሳቸው ሆነ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት" ገ/ተ ሃይማኖት ዘአርብ 43÷ 29

#የሐዲሱ_ሱራፊ_የአባታች_የቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት እረድኤትና በረከታቸው በአገራችን በኢትዮጵያና በሕዝበ ክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ጸንቶ ይኑር ! በወርቅ ጥናውም ዘወትር እያጠነ መዓዛ ክርስቶስን የምንሸት እውነተኛ ክርስቲያኖች አድርጎ የመንግሥቱ ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን ያድርገን ለዘላለሙ አሜን!


............. ይቆየን............


ኀዳር 24/2013ዓ.ም