አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...የጠዋት ፀሐይ ከመቼውም ይልቅ ፏ ብላ ወጥታለች ።
"እኔንም አንዳንዴ አስታውሱኝ ፤ ስለእኔ ውበት ድምቀትና ሙቀት ተወያዩ ” የምትል ትመስላለች ሆኖም ቀና ብሎ የሚያደንቃት ወይም ከልቡ ሆኖ የሚሞቃት ተማሪ አልነበረም ። ሁሉም በየፊናው ይሯሯጣል ። ዛሬ የጠዋት እንቅልፍ የሚያሸንፈው ተማሪ የለም ፡

ማዕበሉ በግቢው ውስጥ ተነሥቷል ። ተማሪው ከግፊቱ ለመዳን ይተራመሳል " ድምፅ የለሽ ትርምስ ይተራመሳል ።
ወደ ፈተና ሲገቡ የሚያኾ ትጥቅን ለማሟላት ! እርሳስ ላጲስ ማስምሪያ

አንዳንዱ ሶባኤ ገብቶ የከረመ ይመስል ሞግጓል ።ጾም ጸሎት እንደ ጎዳው ሁሉ ትንፋሽ አጥሮታል « አጎንብሶ በአንገት ሰላምታ እየተለዋወጡ መተላለፍ ብቻ የሁሉም ልብ የፍርህት ደወል ይደውላል በጭንቀት ተወጥሮ ይነጥራል ።

የመፈተኛ አዳራሾቹ እንደ መቃብር አፋቸውን ከፍተው ይጠብቃሉ ቀድሞ የሚገባባቸው ተማሪ የለም ።ሁሉ ዙሪያውን ከብቦ የመጨረሻዋን ደወል ይጠባበቃል ።አንዳንዱ የሰዓቱንና የልቡን ትርታ ያነጻጽራል "እነዚህን የሚውጠው ትልቁ ደወል እስኪደወል ድረስ ! ...

የመፈተኛው እዳራሾች አቅራቢያ የሚገኙት ሽንት ቤቶች በወረፋ ተጨናንቀዋል ። የገባው ቶሎ አይወጣም
የሌለውን በግድ ያምጣል ። ከብዙ ምጥ በኋላ ትንሽ ጭርር አርጎ ይወጣል ። ከውጭ ያለው ያልጐመማል ። ይሳደባል ግን እሱም ሲገባ ያው ነው የፈተና ምጥ !

ቤተልሔም እንደ ልማዷ ሽንት ቤቱን አንቃ ይዛለች። በወረፋ ያገኘችውን መጸዳጃ ቤት በቀላሉ ልትለቀው አልፈለገችም ። ባለ በሌለ ኃይሏ እያማጠች ወስጧን ፈተሸችው ።ጠብ ያለ ነገር አልነበረም” ። በሸቀች ። ምናልባት ድንገተኛ አደጋ ተፈጥሮ እንደሆን ለማረጋገጥ የውስጥ ሱሪዋን መረመረች ቀይ ነገር የለም ።

እንግኒህ ታቃለህ ኢየሱስዬ ! ” አለች የውስጥ ሱሪዋን ታጥቃ ቀሚሷን ቁልቁል እየለቀቀች ።

በሩን ከፍታ ስትወጣ የወረፋ ጠባቂቹን ልጃገረዶች ዐይን ማየት አፍራ አንገቷን ሰብራ ያለፈቻቸው ። ከዚያ ቀጥሉ የታያት የማርታ ዘለፋ ነው። ፀባይዋ እንደሆነ ብታውቅም ሳትለክፋት አታልፍም ። “ .
ያንቺ ሽንት ደግሞ ለምን ፖፖ ይዘሽ አትዞሪም ? ወይም የፕላስቲክ ከረጢት
ብታጠልቂ ይሻላል ።

ዛሬሳ አልለክፈቻትም ። ዝም አለቻት ። ልዩ የምጥ ቀን በመሆኑና ችግሩ በእሷም ላይ ስለሚታይ ከትዕግሥት ጋር ውጪ ቆመው እየጠበቋት ነበር።

ይሄ ሁሉ ትጥቅ ምን ይሠራልሻል ? ” አለቻት ትዕግሥት ቤተልሔምን ፡ ይዛላት የቆየችውን የጽሕፈት መሳርያ ስትመለከት

ማን ያውቃል? ለክፉም ለደጉም" አለችና ቤተልሄም እየሣቀች ተቀበለቻት።

ትጥቋ ብዙ ነው ሁለት እርሳሰና አንድ ብዕር ሁለት ላጲስ ፥ አንድ ቀይ አንድ ጥቁር : ሁለት እስክሪፕቶ አንድ የፕላስቲክና አንድ የእንጨት ፥ ሁለት አጫጭር ማስመሪያ . . . ማን ያውቃል ጭንቅላት እምቢ ያለውን ትጥቁ ይመልሰው እንደሆን?

አንቺ የዛሬት ፈተና ተሰርቆ ወጥቶአል ሲባል ሰማው“ኮ” አለች ማርታ የቤተልሔምን ዐይን ዐይን እያየች

"የማን? የእናንተ ወይስ የእኛ? ” አለች ቤተልሔም ብዙም ባልተደነቀ ስሜት
“ ኧረ የኛ ? ”
“ ማን ነገረሽ ? ?

“ እሁን አንቺ ሽንት ቤት እንደ ገባሽ አንዲት ልጅ ስታወራ ሰማሁ ። ”

"ውሸት ነው እባክሽ ፈተና በወጣ ቁጥር
የሚወራ ወሬ ነው አለች ቤተልሔም።

“አረ እባክሽ ማን ያውቃል ? ሊሰረቅ ወይም በዘመድ አዝማድ ሊወጣ ይችላል ” አለች ማርታ ከጥርጣሬ ይልቅ እምነት በሞላበት ስሜት ።

“ እንሒድ እባክሽ ማርታ ” ስትል ትዕግሥት አቋረጠቻቸው። እሷና ማርታ የሚፈተኑበት ክፍል ቤተልሄም ከምትፈተንበት ራቅ ይል ነበር።

"ገና ኮ ነው"

“ አምስት ደቂቃ ነው፡ የቀረው ብንሔድ ይሻላል ” አለችና ትእግስት በቆራጥ ስሜት ተነቃነቀች።

“ መልካም ዕድል ! ” እየተባባሉ ተለያዩ ።

ትዕግሥት ከቤተልያም መለየት የፈለገችው በአቅራቢያዋ ያሉት ወንዶች ሲጠቋቁሙባት አይታ ነው። ምክንያቱ ምን እንደሆነ ይገባታል። አቤል አማኑኤል ሆስፒቲል ደርሶ ከተመለሰ ወዲህ የግቢው ወሬ ስለ እሶ እና ስለ እሱ ሆኗል ል ። “ ጎበዙዙን ተማሪ ያሳበደችው ኝ ” ትዕግሥትን" ትእግስትን ለማየት የማይጓጓ ተማሪ አልነበረም። እሷም በአንድ በኩል ይኸንኑ ፈርታ ፥ በሌላ ደግሞ የጥናት ሰሞን በመሆኑ ፥ መኝታ
ክፍሏ ውስጥ መሽጋ ነው የከረመችው ። የግድ ነውና አሁን ብትወጣ የተማሪው ሹክሹክታ የመንፈስ ዕረፍት ነሳት።

ቤተልሄም ከትዕግሥት እንደ ተለየች ሳምሶን ጉልቤውን አገኘችው የመፈተኛ ክፍሉን ለማወቅ አንደ ተጣደፈ ነበር።

“ ወዴት ነው ሩጫው ?” አለችው ። ልብ ብሎ አልተመለከታትም ነበር ። ድምጿን ሲሰማ ልቡ ተረጋጋ ።

“ መፈተኛ ክፍላችንን አይተሻል ? ” አላት ፡ ከቁጣ ባልተለየ ኃያል ድምፅ።

“ አዎ እዚህ 104 ውስጥ ነው ” አለችና በጣቷ አመለከተችው ።

ወደዚያው ቀረብ እንበላ !”

“ እሺ ቆይ መጣሁ” ብላው ባለችበት ቆመች ። “ ሁለተኛው አምላክ” ወደ እሷ ሲመጣ ተመልክታው ነበር ። ።በዛሬው ዕለት በቁም የምትፈልገው ሰው ነው ። እሱን ሳትሳለም ወደ ፈተና አትገባም ። እሱም ምልምሎቹን እየተዟዟረ በማጽናናት ተዋክቧል ።

“ እንደምን አደርክ ? ” አለችው ' አጠገቧ ሲደርስ
“ እግዚአብሔር ይመስገን፡ ደኅና ነኝ ። ”
እንግዲህ ወደ ፈተና መግባቴ ነው ።

“ አይዞሽ ፡ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ይሁን ብሏት ሄደ።

እሷም ይኽንኑ እንዲላት ነበር የፈለገችው የግዜርን የራሱን ድምፅ የሰማች ያህል ተጽናናች ። የፈተና ሰሞን ሁሉ አምላኳ ነው ።በተጠየቀችው ሐይማኖት ሁሉ እሺ
ነው ። ከጀህባውም ፡ ከጴንጤውም፥ ከባሀዪም ከሁሉም ጋር የግዜርን ቃል” ትሰማለች ። አንዱ ካንዱ ጋር ሲያያት
ዐይኑ እንደሚቀላ አልተገነዘበችም ። በእሷ ቤት ለሦስት ኣምልኮት መቆሟን ብልጠትና ዘዴ አርጋዋለች ። አንዱ አምላክ ቢስት ሌላው አይስትም ነው ጥበቧ ። በዚያ ላይ ደግሞ ስድስት ኮርስ ነው የምትፈተነው ። አንዱን ኮርስ በለማ
ላይ ጥላዋለች ። የተቀሩትን አምስት ኮርሶች በአንድ አምላክ ላይ መጣሉ ይከብዳል ። እና ሦስቱ “ አምላኮች”
ተከፋፍለው ቢሸከሙት ? መልማዮቿ ልቧን ከፍተው እንዳያዩባት እንጂ ጥሩ ዘዴ ነው ።

አቤልና እስክንድርም ከአንድ ጥግ ስፍራ ሆነው የመግቢያው ደውል እስኪደወል ድረስ ትርምሱን ይታዘባሉ ለፈተና ጊዜ የሚያደረገው ግርግርና ሽብር በተለይ እስክንድርን ሁልጊዜም ያበሽቀዋል ። ፈተና እንዲህ ተማሪውን የሚያርበደብድ ነገር ከሆነ የዕውቀት መለኪያነቱ ያጠራጥራል እያለ ለብቻው ውስጥ ውስጡን ያሰላስላል ።

አቤል የተማሪውን ዐይን ለመሸሽ የሚገባበት ጉድጓድ እጥቷል ። ተማሪዉ እሱ ላይ ሲጠቋቆቻምበትና ሲንሾካሾኩበት ይመለከታል ከትዕግሥትም ላይ እንዲሁ የማያውቁት ተማሪዎች አቤል ማለት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ነበር የሚጠቋቆሙት አቤልን ያስገረመው ግን በፊት የሚያውቁትም ተማሪዎች እንደ እንግዳ ሆነው እየሰረቁ
መመልከታቸው ነው "

“ፊቴ ላይ ምን ለውጥ ለማየት ፈልገው ነው ? ወይስ ግንባሬ ላይ የሚያነቡት ነገር አለ ?” ሲል እሰበ ። በተማሪዉ
አስተያየት በሽቅ ።

የተማሪው ሹክሹክታና የስርቆት እይታ ራሱ ሳያብዱ ያሳብዳል ። “ጥናት ቢወጥረው " ምን ፈተና ቢያስጨንቀው
እንዲህ ዐይነቱን ወሬ ማነፍነፉ አይቀርም የስነ ልቦና ጥናት በስሎ አቶ ቢልልኝና የመሃበራዊ ሥራ ባልደረቦች ከአቤል ጋር በቀጥታም ሆና በተዘዋዋሪ ግኑኝነት አላቸው ብለው የገመቷቸውን ተማሪዎች
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በአባቷ አድራጎት ስላፈረች መሬት ተከፍታ ብትውጣት በወደደች፡ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ሁላ በተፈጠረው አስከፊ ሁኔታ የአባቷን ጋጠወጥ ባህሪ እሷም ትጋራ ይሆን?› እያለ እያሰበ የሚያፈጥባት መሰላት፡ የሰዉን አይን ማየት ፈራች:

ሄሪ ማርክስ የቀራት እንጥፍጣፊ ክብሯ ሳይገፈፍ ደረሰላት፡ ቀልጠፍ
ብሎ ተነስቶ በማክበር ወምበሯን ያዝ አድርጎላት፣ ሶቶ እንድትይዘው
ክንዱን ሰጥቷት ከመብል ክፍሉ እንድትወጣ አገዛት፧ ያደረገው ነገር ትንሽ
ቢሆንም እሷን ግን ልቧን ነክቷታል።

አባቷ ለዚህ እፍረት ስለዳረጓት በእጅጉ አንገብግቧታል፡፡ ራት ከተበላ በኋላ በመብል ክፍሉ ውስጥ ለሁለት ሰዓት ያክል የሚከብድ ጸጥታ ነግሶ ቆየ፡ የአየሩ ሁኔታ እየተበላሸ ሲመጣ አባባ እና እማማ የቀን ልብሳቸውን
አውልቀው የመኝታ ልብሳቸውን ለበሱ፡
ፔርሲ ‹‹ይቅርታ እንጠይቅ›› አላት ማርጋሬትን ድንገት፡
ፔርሲ ይህን ሲላት ይቅርታ መጠየቁ የበለጠ እፍረት ውስጥ እንደሚጥላቸው ገመተች፡ ‹‹እኔስ ይቅርታ ለመጠየቅ ድፍረቱ የለኝም››
አለችው ወንድሟን፡፡

‹‹ባሮን ጋቦንና ፕሮፌሰር ሃርትማን ጋ ሄደን አባታችን ስላሳየው ያልተገባ ባህሪ ይቅርታ ብንጠይቅ ነው የሚሻለው›› አለ ፔርሲ፡
የአባቷን ጥፋት ለማለዘብ ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም ስትል አሰበች፡፡ እሷም ቀለል ይላታል፡፡ ‹‹አባባ ግን ይናደድብናል›› አለች
አበዛው! አብዷል መስለኝ ከዚህ በኀላ አልፈራውም›› አለ ፔርሲ፡

‹‹እሱ ማወቅ የለበትም ቢናደድ ደግሞ ግድ የለኝም፧ አሁንስ
ፔርሲ ከዚህ በኋላ አልፈራውም› ያለው እውነት መሆኑን ማርጋሬት
አላወቀችም: ህጻን ሆኖ አባታቸውን ፈርቷቸው እያለ ‹አልፈራውም› ይል
ነበር፤ አሁን ግን ህጻን አይደለም፡፡

ፔርሲ ከአባታቸው ቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱ ማርጋሬትን አሳስቧታል፡ አባቷ ብቻ ናቸው የፔርሲን
ያልተገባ ባህሪ ሊያርቁ
የሚችሉት፤ ፔርሲ ሸረኝነቱን እንዲተው ካልተደረገ አይቻልም፡፡

‹‹በይ እንጂ! አሁን እንሂድና ይቅርታ እንጠይቃቸው፤ ያሉበትን ቦታ እኔ አውቀዋለሁ›› አለ ፔርሲ፡
ማርጋሬት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈራ ተባ አለች እያለች ነው አባቷ
ያስቀየሟቸው ሰዎችጋ መሄድና ይቅርታ መጠየቅ ከብዷታል፤ የሆነውን
ሁሉ መተውና አርፎ መቀመጥ ነው የሚሻላቸው ቁስላቸውን መነካካቱ
ምንም ፋይዳ የለውም፡ ሆኖም የዘር መድሎን ለመቃወም እጅ ለእጅ
መያያዝ ያስፈልጋል።

በመጨረሻ ማርጋሬት ሰዎቹን ይቅርታ ለመጠየቅ ወሰነች፡ መቼም ጥሎባት ቦቅቧቃ ናት፡ ከዚህ ቀደም ላጠፋችው ጥፋት ፈርታ ይቅርታ ሳትጠይቅ መቅረቷ ሁልጊዜ ይጸጽታታል፡
አይሮፕላኑ በወጀቡ እየተወዛወዘ ቢሆንም የወንበሯን መደገፊያ ጠበቅ
አድርጋ ይዛ ተነሳችና ‹‹እሺ እንሂድ›› አለችው ወንድሟን፡
የአይሮፕላኑ መወዛወዝ በፍርሃት መንቀጥቀጧን ደብቆላታል፡ ሁለቱ
ሰዎች ወዳሉበት ክፍል አመራች፡፡

ጋቦንና ሃርትማን ግምባር ለግምባር ተቀምጠዋል፡ ሃርትማን የሂሳብ መጽሐፍ ላይ በተመስጦ አፍጠዋል፡፡ ጋቦን የሚሰሩትን አጥተው በጉዞው ተሰላችተው ተቀምጠዋል፡ በመጀመሪያ ማርጋሬትንና ፔርሲን ያይዋቸው እሳቸው ናቸው፡ ማርጋሬት አጠገባቸው መጥታ ወምበራቸውን ተንገዳግዳ ስትይዝ አዩና ፊታቸውን አኮሳተሩ።

ማርጋሬት ቶሎ ብላ ‹‹ይቅርታ ለመጠየቅ ነው የመጣነው›› አለች፡
‹‹ደፋር ነሽ!›› አሉ ጋቦን የፈረንሳይኛ ቋንቋ ቅላጼ ባለው እንግሊዝኛ፡
ማርጋሬት እንዲህ ያለ ምላሽ ይገጥመኛል ብላ ባታስብም ጥረቷን
ቀጠለች፡ ‹‹በአባታችን አድራጎት በጣም አዝኛለሁ፤ ወንድሜም እንዲሁ
ለፕሮፌሰር ሃርትማን ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው፡ ይህንንም ከዚህ ቀደም
ነግሬያቸዋለሁ›› አለች፡:

ሃርትማን ንባባቸውን አቋርጠው ይቅርታውን መቀበላቸውን ራሳቸውን
በመነቅነቅ አመለከቱ፡ ጋቦን ግን አሁንም በቁጣ አበያ በሬ እንደመሰሉ ነው
‹‹እንደ እናንተ ላሉ ሰዎች ይቅርታ መጠየቅ ቀላል ነው›› ሲሉ ማርጋሬት
የምታደርገው ጠፍቷት በድንጋጤ መሬት መሬቱን ታያለች፡፡ ‹ምነው
ባልመጣሁ አለች በሆዷ፡ ‹‹ጀርመን ውስጥ እየተደረገ ያለው ነገር በጣም
እንደሚያሳዝናቸው የሚነግሩን ጨዋ ሰዎች ብቻ ናቸው›› ሲሉ ቀጠሉ ‹‹ግን ምን አደረጉልን፤ እናንተስ ምንድነው የምታደርጉልን?›› አሉ ጋቦን፡፡
ማርጋሬት ፊቷ በድንጋጤ በርበሬ መሰለ፡፡ ምን እንደምታደርግ ግራ ግብት አላት።

‹‹ፊሊፕ ዝም በል እንጂ›› አሉ ሃርትማን ለስለስ ባለ አነጋገር ልጆች እኮ ናቸው›› ወደ ማርጋሬትም ዞር አሉና ‹‹ይቅር ብለናል እናመሰግናለን››

‹‹ጌታዬ ተሳሳትን ይሆን?›› ስትል ጠየቀች::

‹‹በፍጹም›› አሉ ሃርትማን ‹‹እንደውም ጥሩ ነው ያደረጋችሁት ይባርክሽ፧ ጓደኛዬ በጣም ስሜቱ ስለተነካ ነው እንዲህ የሆነው፤ በኋላ እንደእኔ ሲገባው ከንዴቱ መለስ ይላል፡››

‹‹እንግዲህ እንሂድ›› አለች ማርጋሬት እንደከፋት፡
ሃርትማን በመስማማት ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ፔርሲም በተራው ‹‹ይቅርታ አድርጉልን›› አለና ከእህቱ ጋር ተያይዘው
ሄዱ፡፡

ወንድምና እህቱ በአይሮፕላኑ ውዝዋዜ እየተንገዳገዱ ወደ ቦታቸው
ተመለሱ፡፡ ዴቭ መኝታቸውን እያነጣጠፈላቸው ነው፡፡ ሄሪ በቦታው የለም፡ ምናልባትም ወደ መታጠቢያ ቤት ሄዶ ይሆናል፡፡ ማርጋሬት ልብስ
ለመለወጥ ቦርሳዋን አንጠልጥላ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደች፡ እናቷ የመኝታ ልብሳቸውን ለብሰው እምር ድምቅ ብለው ከመጸዳጃ ቤት እየወጡ ስለነበር
‹‹ደህና እደሪ የኔ ማር›› ቢሏትም እሷግን ዝግት አድርጋቸው ገባች:
በሴቶች በሞላው መታጠቢያ ቤት ውስጥ የመኝታ ልብሷን ቶሎ ለውጣ ወጣች፡፡ የመኝታ ልብሷ ሌሎቹ ሴቶች ከለበሱት ደመቅመቅ ካሉትና ከሃር ከተሰሩት ልብሶች ጋር ሲነጻጸር ኋላ ቀር መሆኑ ግድ አልሰጣትም፡፡ ባሮን
ጋቦን በኋላ ያሉት እውነት በመሆኑ ይቅርታ መጠየቁ የፈየደው ነገር የለም ለችግሩ ምንም መፍትሄ ሳያመጡ ይቅርታ› ማለት ቀላል ነው።

ወደ ቦታቸው ሲመለሱ እናትና አባቷ መጋረጃቸውን ጋርደው ተኝተዋል፡፡ አባቷ አገር አማን ነው ብለው ያንኮራፋሉ፡፡ ማርጋሬት የእሷ መኝታ እስኪዘጋጅ ቁጭ ብላ ጠበቀች፡፡

ከቤተሰቦቿ ቁጥጥር ነፃ ለመሆን አንድ መንገድ ብቻ ነው ያላት  እነሱን ትታ እየሰራች መኖር አሁን ይህን ለማድረግ ቆርጣለች፡፡ የገንዘብ፣ የስራና የመኖሪያ ቦታ ችግሯን ለመቅረፍ ግን ገና ነች፡፡

ፎየንስ ላይ የተሳፈረችው ዘናጯ ናንሲ አጠገቧ መጥታ ተቀመጠች።
ሴትየዋ የመኝታ ልብስ ነው የለበሰችው፡፡ ‹‹አስተናጋጁ ብራንዲ እንዲያመጣልኝ ፈልጌ ነበር፤ እሱ ግን እረፍት የለውም፧ እዚህ እዚያ ይንከወከዋል
አለች፡ ሲያይዋት ዘና ብላለች፡ ተሳፋሪው እንዲያያት እጇን አውለበለበች
‹‹ለምን ፓርቲ አንጨፍርም፤ ምን ትያለሽ?›› አለቻት ማርጋሬትን፡፡
‹‹ያልሽው ነገር እንግዳ ነው የሆነብኝ›› አለቻት ማርጋሬት፡፡
ናንሲ የመቀመጫ ቀበቷን አጠባበቀች፡ ደስ ደስ ብሏታል። ‹በፒጃማ
ስትሆኚ መከባበር ብሎ ነገር የለም፤ የወዳጅነት ስሜት መስፈን ነው
ያለበት፡፡ ፍራንክ ጎርደን እንኳን ፒጃማው አምሮበታል፡››

ማርጋሬት በመጀመሪያ ስለማን እንደምታወራ  አልገባትም ነበር፡፡
ወዲያው ግን ካፒቴኑና የኤፍ.ቢ.አይ መርማሪው ሲጨቃጨቁ ፔርሲ ሰምቶ
የነገራት ነገር ትዝ አላት
‹‹እስረኛውን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀቻት።
‹‹አዎ››
‹‹አንቺ አትፈሪውም?››
‹‹አይ አልፈራውም፧ ምን ያደርገኛል!››
‹‹ሰዎች ግን ነፍሰ ገዳይ ነው ይሉታል››
👍202
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የኩችሩ መንደር እንደደመቀች ናት:: ብዛት ያላቸው አሣዎች በወጣቶች በጦር ተወጉ ማጅራታቸውን በዱላ ተመቱ በመንጠቆ ተያዙ፤ ሣር በል የሆኑ አራዊት የሜዳ ፍየልና ውድንቢት ታድነው ተገደሉ ፤ ከጫካ ብዛት ያለው ማር ተቆረጠ፤ ቦቆሎና ማሸላ ኦሞ ወንዝ ተወስዶ ተወቃ.. ይበላል ይጠጣል
ይጨፈራል ይመረቃል።

ሉካዬ ሰማይ ላይ ሆኖ ምስሉ እየታዬ ቢሆንም ሶስት ቀን ሙሉ አልመጣም:

“ሎካዬ ለመምጣት ያስባል! ነጩ እባብ ግን “አልመጣም ብሎ አስቸግሮታል ደንቡን ሳናጓድል ሥርዓቱን ብናሟላ ግን ሁለቱም ይመጣሉ" ስላሉ ሽማግሌዎች፣ ሴት ወንዱ ይኳትናል ሰማይ ላይ ላሉት  ለሎካዬና ለነጩ እባብ በደስታ ለመፍጠር።

ኮንችት የሎካዬ የልጅ ልጅ መሆኗን ከሰሙም በኋላ
የመንደሩ ሰው ተስብስቦ ከአያቷ ወንድም ቤት ፊት ለፊት ተቀመጡ" የሉካዬ ፎቶ ጎጆው ላይ እንደተንጠለጠለ ነው። ከሥሩሁሌም ግልገል ፍየል ከካሮ እየመጣ ታርዶ ይቀመጥለታል።

ልጃገረዶች ኮንችትን ወደ ጎጆው ቤት ውስጥ ይዘዋት
ገብተው ውስጥ ሱሪዋንና ጡት ማስያዥዋን ሳይቀር አስወለቋት::ከውጭ ይዘፈናል እልል ይባላል. ልጃገረዶች በአኖና የዱር እጣን አላቁጠው ፀጉሯን ሰውነቷን ቀብተው የፍየል ቆዳ አለበሷት: ከዚያ
ይዛው የመጣችውን ልብሷን በእጅዋ እንድታንጠለጥል ሰጧትና ከቤት ወደተሰበሰበው ህዝብ ይዘዋት ወጡ። እሳት ነዷል.
ይጨፈራል... ሁለት ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፍተው እጅና እጅዋን
ይዘው ልብሷን ወደ እሳቱ አስወረወሯትና እልልታቸውን ሲያስነኩት
የተሰበሰበው ህዝብ እንደገና ፈነጠዘ ዘለለ  አቅራራ.. ጡሩንባ
እልልታ ተኩስ ድብልቅልቅ አለ:

ኮንችት የተረጋጋች አትመስልም። ቆዳዋ ግን አማረባት ጡቶችዋ ቀልተው ቆሙ ለስላሳው ጭኗ... ሁለመናዋ አጓጊ ሆኗል:
ድንጋጤው ስላልለቀቃት ግን ካንገቷ በላይ ውበቷ ቀንሷል።

ሴቱም ወንዱም እየመጣ እጅዋን እየሳመ ደስታውን
እየገለፀላት ወደ ጭፈራው ሲገባ እንደቆዬ ሰው ሰላምታ እየሰጣት
ኩዩጉነቷን አንድነታቸውን እያረጋገጠላት ከሄደ በኋላ ሶራ እየሳቀ ወደ ኮንችት ተጠግቶ አቀፋት: ሽጉጥ አለች ወደ ደረቱ እንደ
እንቦቀቅላ  ህፃን፡ አይቷት እንደማያወቅ ሁሉ በሁለት እጆቹ ጡቶችዋን እንደያዘ ፈገግ ብሎ ቁልቁል አያት: ልትስመው ስትል
የሆነች ሴት መጥታ መነጨቀቻት። የኩዩጉ ሴት ወንድን በአደባባይ
አትስምማ!

“እሺ!” አለች ኮንችት
የሴትዮዋ ግሣፄ ስለገባት።

“ለምን ልብሴን አወለቁ?  ለምንስ እንዳቃጥለው አደረጉ?''አለችው እሏና ሶራ ከእቅፎቻቸው ከተላቀቁ በኋላ

“የአያትሽን ባህል ረድኤት ለማካፈል! ተፈጥሮአዊ ፀጋሽን ለመመለስ ጎረምሶች ፍቅራቸውን እንደ ወለላ ማር እንዲያውጡሽ….
ለማድረግም" አላት ሶራ እየሳቀ
ባለወይሳው ኮንችትን ባህላዊ ልብስ ለብሳ ሲያያት ደስ አለው። ስለዚ ፈገግ ብሎ ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ ቀረባትና

ካርለትን አይተሻታል ወይ? ብለህ ጠይቃት" አለው ሶራን።ሶራ የነገረውን ለኮንችት ሲተረጉምላት ተኩስ ተሰማ ተኩሱ
ተደገመ።

ጎረምሶች እየተሯሯጡ ወደ ኦሞ ወንዝ ሄዱ። ጭፈራው
ግን አልቆመም። ባለወይሳው ከሌላ አካባቢ የመጣች ፀጉረ ረጅም
ልብስ ለባሽ... ሁሉ እሱ የሚያውቃትን ካርለትን ያውቃል ብሎ አምኗል።

“ካርለት! ማነች ካርለት? የአባቷስ ስም? ዜግነቷስ?”
ኮንችት በስም ብቻ አውቃለሁ፤ አላውቅም  ማለት ትክክል
እንዳልሆነ ታውቃለች: በያገሩ ስንት  ካርለት
ዴቪድ... ሊኖር ፥ይችላል። መጀመሪያ ስም  አገር ሥራ የሚኖርበት አድራሻ...
ለማንነት መለያ ይጠቅማል: በተረፈ በደፈናው ይከብዳል።ባለወይሳው ግን “አውቃታለሁ' አለማለቷ አስከፋው:

ምን የማረጋት መሰላት ካርለት ልጃገረድ ናት!
ብታጠፋም አላገባኋት ጥሎሽ መክፈል አልጀመርሁ... እና-
አላዝባት አልቀጣት... ይህን እያወቅች መደበቋ ምን ይሉታል? ብሎ አስቦ አዘነባት በኮንችት:

በኦሞ ወንዝ ዳር ካለው ጫካ የሆኑ ሰዎች ብቅ ሲሉ ህዝቡ ተንጫጫ። ኮንችት ቀና ብላ ታይ የኩዩጉ ጎረምሶች እንግዶችን
እየመሩ ይመጣሉ። ለኩዩጉ መንደር በሩ ኦሞ ወንዝ የበሩ ደወል ተኩስ መሆኑ ኮንችትን እንዳስደነቃት ነው።

እንግዶቹ ሲጠጉ አንዷ ነጭ ናት ሁለት ወንዶችና
አንዲት ሴት አብረዋት አሉ። እነሱ ከነጭዋ አንፃር ጥቁር ናቸው።እንግዶቹ እንደቀረቡ ባለወይሳው ዘወር ብሎ አያቸውና ከመቅፅበት
አይኑን እንደ አውሬ አፍጦ አንገቱን እንደ ሰጎን መዘዘው
ሁለቱ ሴቶች ባለወይሳውን ሲያዩ ፊታቸው በደስታ ፀዳል አበራ ቸኩለው ግን ወደ እሱ አልተጠጉም።
ከዚያ ነጯ እንደቆመች ሌላዋ ሴት ቀረብ አለችና፡-

“አያ ደልቲ!'' አለችው
በሐመርኛ:ጎይ ቲ"

ረጋ ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ ላዩ ላይ ተጠመጠመችበት: እቅፍ አድርጓት ቆየና ለቀቃት:: ነጭዋንም ካርለት" ብሉ አቀፋት፤ እሷም አቀፈችው ...

የኩችሩ መንደር ኗሪ በሁኔታው ተደንቆ ጭፈራውን አቁሞ
ያያል።

ካርለት! አለች ወገቧን ወደኋላ ለጥጣ በአድናቆት አፏን እንደከፈተች ኮንችት።

ኮንችት! ካርለት ኮንችትን ከእግር ጥፍሯ እስከ ፀጉሯ
በአድናቆት እያየቻት ቆየችና

“አገኘሻቸው?" አለቻት

“አዎ ተገናኘን” ብላ ኮንችት ሳቀች ተሳሳቁ ኮንችትና
ካርለት! ህዝቡም አብሯቸው ሳቁ! መንደሯም በሣቅ ሙላት ተጥለቀለቀች

“ኮንችት እንዴት ልታገኛቸው ቻልሽ?''

“..በጀልባ ነበር እኔና ሶራ የምንጓዘው፤ እና ባጋጣሚ እዚህ ደረስን

“ማንም ሳይመራሽ?'

“ባገኘሁት ማፕም ሆነ ካርታ ኩዩጉዎች ለመኖራቸው ፍንጭ የሚሰጥ ምልክት የለም:: አያቴ የስጠኝ የአደራ ምልክቶች ግን እንደ ኮኮብ መርተውኛል ያም ሆኖ ግን ባጋጣሚ ኩዩጉዎችን
የሚፈልገው ሰው ተኩሶ እነሱ ሲመጡ ማየት ባንችልና ተጠራጥረን
አብረን ባንመጣ ልፋቴ መና ሆኖ! ስሜቴ በስለት ቢላዋ ለሁለት ተተርትሮ ወደ መጣሁበት እየቆዘምኩ እመለስ ነበር። አጋጣሚው
ግን ረዳን፤ ተገናኘን:

“እንዴት አገኘሻቸው ታዲያ?

“ደግ ሩህሩህና ተግባቢዎች ናቸው:: ኑሯቸው በኦሞ ደለል ላይ ማሸላ በማብቀል ከጫካ ማር በመቁረጥና አሣ በማጥመድ ነው።
ከብት ፍየል የላቸውም፤ ይህ ደግሞ ከብት በሚያረቡት የአጎራባች
ያስንቃቸዋል:: ቁጥራቸው
ማህበረሰቦች ማነሱ ከብት
ባለማርባታቸው የሚያጠቃቸው ብዙ ነው። ስለዚህ የሚኖሩት
በጠባቂ ሞግዚት ነው"

“በሞግዚት?”

“አዎ ካርለት!  ጥንት ሞግዚታቸው ካሮ ማህበረሰብ ነበር። አሁን
ግን የካሮዎች ኃይል እየደከመ የኒያንጋቶሞች
(ቡሜዎች) ኃይል እየበረታ በመምጣቱ ኩዩጉዎች ወደ ኒያንጋቶሞች በመጠጋት ከአጎራባች ማህበረሰቦች የሚደርስባቸውን ጥቃት
ሞግዚታቸው ኒያንጋቶሞች ይከላከሉላቸዋል።

“ታዲያ ለሃያሉ ሞግዚታቸው ማር እህል  ከሚሰፍሩት ሌላ ልጃገረዶቻቸውን ካለጥሎሽና ካለ አንዳች ክፍያ ኒያንጋቶሞች
በሚስትነት ይሰጣሉ። ኩዩጉዎች ግን ከኒያንጋቶሞች ካሮዎች.. ጋርዐመጋባት አይችሉም ስለሚናቁ።

“ኩዩጉዎች የሌላቸውን የማይመኙ በዚህ ኑሯቸውም ከአቅም በላይ ለሆኑ ነገሮች የማይሰጉና የማይጨነቁ ናቸው። ከሁሉም በላይ ባህላቸውን አክብረው ራሳቸውን ሆነው መኖርን ይመርጣሉ።
የሚገርምሽ በልጅነቱ ከነሱ የተለየው አያቴ እንኳን እንደ
ዘይትና ውሃ ለረጅም ጊዜ ከኖረበት ስልጣኔና ባል ጋር ሳይዋሃድ ነው ወደ መቃብሩ የወረደወ:
👍261👎1🥰1