አትሮኖስ
279K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አንድ


#በሜሪ_ፈለቀ

ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች "የለውጥ ኩርባ" አለችው አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ ወይ ድርጊቱ የሚቀየርበት።ወደ አዲስ ምእራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት።

=========================
“ማታ ከማን ጋር ባድር ደስ ይልሃል?” ወሬዋ እንዲያምርላት እና የወሬው አካል እንደሆንኩ እንዲሰማኝ (አብዛኛውን ጊዜ አይደለሁም::) ስትፈልግ ጥያቄ ታስመስለዋለች እንጂ ከእኒ መልስ ጠብቃ አታውቅም፡፡ ዝም ብላ ነው የምታወራው የምታወራልኝን ነገር መስማቴን ብቻ ካረጋገጠች ያለእረፍት
ትለፈልፋለች። እራሷ ትጠይቃለች። እራሷው ትመልሳለች።

"ከፍቃዱ ጋር!"

“ፍቃዱ ማን ነው?” ስላት በእርሷ ላይ እንዲሰማኝ የምትፈልገው የባለቤትነት ስሜት የተሰማኝ መስሏት ነው መሰለኝ ደስ ተሰኝታ ወሬዋን አድምቃ ቀጠለች። የማይገባኝ ባህርይዋ ይሄ ነው፡፡
በእርሷ ላይ ባለመብት እንድሆን ትፈልጋለች። ሌላ ሰው አየብኝ፣
ነካብኝ ኸረ አሰበብኝ ብዬ ሁሉ ዘራፍ! ብል ደስ ይላታል፡፡

“አርቲስቱ ነዋ! መጀመሪያ ስንሳሳም ነበር። በቃ ሲስመኝ ሲስመኝ...
ሊስመኝ ቆየና ምን ብናደርግ ጥሩ ነው?” እንዲህ ብዙ ጊዜ ያለማሰሪያ የምትበትነው ፀጉሯ እየተርገበገበ እና በእጆቿ አየሩን እየቀዘፈች እየተቅጠበጠች ስታወራ መላ ሰውነቷ
ከመወራጨቱ የተነሳ ልትበር የምታኮበኩብ ነው የምትመስለኝ።

“ምንም ብታደርጉ ጥሩ አይደለም፡፡” አልኳት ከአፏ ቀልቤ፡፡

“ጅል!” አለች። ከፍቃዱ ጋር ስትሰራ ያደረችውን የድሪያ ወሬዋን ስላናጠብኩባት በሽቃ፡፡ እንደዚህ ስትለኝ እንደሚያስጠላኝ ታውቃለች። ግን አትተውም። በበሽቀች ሰዓት ሁሉ “ጅል
ትለኛለች። የምጠላው ደግሞ ጅል መባል ብልጥ ከመባል ጋር ተነፃፅሮ ውድቀት ስለሆነብኝ አይደለም፡፡ ብቸኛው ምክንያቴ እናቴ ትለኝ ስለነበረ ነው። እናቴ የምትለኝ የነበረውን ነገር ሁሉ እጠላዋለሁ (እናቴ ውዳሴ ከአፉ አይወጣም እንጂ ውዳሴም ቢሆን ከስድቦቿ እንደአንዱ የሚሆንብኝ ይመስለኛል።)ምክንያቱም ከመገለፅ በላይ እጠላታለሁ።

ሴት ከብዙ አርጩሜና ከትንሽ ሰውነት የተሰራች ፍጥረት ትመስለኛለች፡፡ መግረፊያንና ሴትን ምን አገናኛቸው? ወለላ! ወለላን እናትህ ስለሚሉኝ እናቴ ናት እላለሁ። ከልቤ ግን ወለላን
ምኔም ባልላት ደስ ይለኛል፡፡

“የአባትህ ልጅ! ጅል የጅል ዘር!” የሚለው ስድቧ ገላዬ ላይ ከሚያርፈው ዱላዋ እኩል በቀን ለመዓት ጊዜ የምሰማው ነው፡፡ የአባቴ ካልሆነ የማን ልጅ ልሆን ነበር? ሲመስለኝ አባቴ እኔን
እንደሚመስል ስታወራ ሰምቻለሁ፡፡ ያን ማለቷ ይሆን? ወይስ አባቴ ጅል ነበር? እናቴን ጨምሮ ጅል የሚሉኝ ሁሉ የማይገባኝ ነገራቸው አለመዋሸቴን፣ አለማስመሰሌን፣ ያልመሰለኝን
አለማድረጌን፣ ለሚጠይቁኝ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ መመለሴን፣
ተንኮል አለማወቄን እና እነርሱ ብልጠት የሚሉትን ነገር ለመልመድ ራሴን አለማጣቴን ለምን ጅልነት እንደሚሉት ነው::
በተቃራኒው አፈቀላጤነትን፣ ያልሆኑትን መስሎ መታየትን፣መዋሽትን፣ ተንኮለኛነትን... እንደ ብልጥነት መቁጠራቸው ምነኛ አስተሳሰብ ይሆን?

ረድኤት አዳሯን እየነገረችኝ ከማታው የተረፈ ቡረቃዋ እንዳለቀቃት ነው የተሰማኝ፡፡ እኔ ግን ከልቤ ነበር፡፡ ፍቅረኛው ከሌላ ወንድ ጋር ያውም በዝና፣ በገንዘብ፣ በውበት እንደውም በቁመትም ጭምር ከሚበልጠው ታዋቂ አርቲስት ጋር ያሳለፈችውን የአዳር ተረክ ስትነግረው ጥሩ ነው' የሚል ፍቅረኛ
ይኖር ይሆን? በእርግጥ የኔ ፍቅረኛ ከፍቃዱ ጋር የባለገችው በህልሟ ነው፡፡ ቢሆንም 'ጥሩ አይደለም፡፡ አብሯት ማደሩን ከነገረችኝ ሰውዬ ጋር ራሴን ማነፃፀር የጀመርኩበት ምክንያት
ውሉ አልገባኝም፡፡ ህልሟን ባሰብኩ ቁጥር የሚረብሸኝ የትኛው እንደሆነ መነጠል አቃተኝ፡፡ እርሷ የሌላ ሰው መሆኗ ወይስ ሌላኛው ሰው እንደሚበልጠኝ ማሰቤ? ራሴን ከሌላ ሰው ጋር አነፃፅሬ ማወቄን እንጃ! ለንፅፅር የምቀርብ ስለመሆኔም እንጃ እኔ
በቃ ስህተት ነኛ! ስህተት ስሜ ነው ፣
መገለጫዬ ፣ ማንነቴ! ወለላ ልጇ መሆኔን እንኳን ለመናገር የምታፍርብኝ እናቴ ነበረች፣ ሰፈር ብዙ ሰው አያውቀኝም::
ቢያውቀኝም በስሜ ማንም አይጠራኝም እሷኑ ይለጥፉብኛል።የ'ወለላ ልጅ':: ትምህርት ቤት ስታስመዘግበኝ አፏን ሳያዳልጣት

“ስሙ ማን ነው?” ስትባል::
“ስህተት ወለላ” ብላ ነው ያስመዘገበችኝ፡፡ በህይወቴ ውስጥ
ትልቁን ስህተት ማስመዝገቧ አልገባትም፡፡ እሷ ከራሷ ውጪ
ለማንስ ግድ አላት? እኔ ለሷ ከዛ ያለፈ አልነበርኩም ስህተቷ ነኝ፡፡ ታዲያ ስህተት በምን ስሌት ለንፅፅር ይቀርባል?

የረድኤትን ህልም እያደረ ሳስበው በውን ብትባልግ ሳይሻል አይቀርም ነበር፡፡ ምክንያቱም ፍቅረኛዬ ይሄን ህልሟን ከነገረችኝ በኋላ ባህርይዋ የተቀየረ እየመሰለኝ መጣ፡፡ ቤት መዋል
የማትወደው ፍቅረኛዬ ስራ እየቀረች መተኛት ስትጀምር በህልሟ ያደረገችው ድሪያ እየወሰወሳት ልትደጋግም እየመሰለኝ ማሰብ ማቆም አቃተኝ። አጠገቤ ተኝታ በእንቅልፍ ልቧ ድምፅ
ባስማች ቁጥር ከፍቃዱ ጋር እየተላፋች እየመሰለኝ በቅናት ተብሰከሰኩ፡፡ 'አትተኚ አይባል? ህልም አታልሚ አይባል?
ህልሟን ጠላሁት፡፡ የማልጋፋው ባላጋራ ሆነብኝ፡፡ አንድ ዕለት በውድቅት ለሊት በውል ያልሰማሁትን ነገር ስታጉተመትም
ነቃሁ፡፡

“ረዲዬ.... ረዲ....”

“በስመአብ ወ ወልድ! ምነው?” አለችኝ ብርግግ ብላ ከእንቅልፏ እየባነነች።

“ምነው ፍቅሬ ከፈቃዱ ጋር እንትን እያደረግሽ ነበር እንዴ?”ስላት መብራቱን አብርታ ካፈጠጠች በኋላ “ጂላጅል! ከፈቃዱ ጋር አይደለም ከአለሙ ጋር ነው::” አለችኝ፡፡

“አለሙ ደግሞ ማነው? እሱም አርቲስት ነው?”

“እንከፍ! ኸረ ምን ዓይነቱን ነው የጣለብኝ?” ብላ እየተቆናጠረች
ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች።

እሷ ህልሟን ካቆመችበት ለመቀጠል ይመስለኛል እንቅልፍ ጥሏት ስትወራጭ፣ ስታንኮራፋ እንቅልፍ አጥቼ እሰማታለሁ፡፡
ወለላ ደብድባኝ ስታበቃ ምንም የሚጎዳኝ ነገር እንዳላደረገች ተኝታ እንደምታንኮራፋው አልያም እያንጎራጎረች እንደምትኳኳለው።ወለላ እኔን ከመግረፍ በሚተርፋት ጊዜ የኔን
አባት ሳይጨምር እኔ የማውቃቸውን አምስት ባሎች አግብታ ፈታለች፡፡ አባቴን ጨምሮ ሁሉም ባሎቿ ጥለዋት ለመሄዳቸው ምክንያት እኔ እንደሆንኩ ትነግረኛለች፡፡ ምን እንደሚያገናኘው
ዛሬም ድረስ አይገባኝም፡፡ እሷ እንዳለችኝ አባቴ ማርገዟን ስትነግረው ጥሏት ስለሄደ እሺ ብዬ ገፊነቴን ልቀበልላት፡፡
ከአምስቱ ስንተኛው መሆኑን የማላስታውስው አንድም ዓመት
አብሯት ከኖረ በኋላ “አንቺ እኮ ልጅ እንዳለሽ እንኳን ያወቅኩት ካገባሁሽ በኋላ ነው:: ድብቅ ነሽ” ሲላት ሰምቻለሁ፡፡ ይሁን ለዚህኛውም ምክንያት ልሁናት፡፡ ከመታመሟ በፊት ለመጨረሻ
ጊዜ ያገባችው ባሏም ድሮ ሰራተኛዋ የነበረች ሴት ወልዳኝ ጥላባት ሄዳ እሷ እያሳደገችኝ እንደሆነ እንደነገረችው ሳላውቅ እናቴ መሆኗን ስነግረው መጨቃጨቃቸው ትዝ ይለኛል፡፡
ይሁንላት ለዚህኛውም ሰበብ ልሁናት፡ እራሷ ላጠፋችው ጥፋት፣ ባሎቿ ላጠፉት ጥፋት፣ ራሴም ላጠፋሁት ጥፋት
የምቀጠቀጠው እኔ ነኝ፡፡ እንደውም የማላውቃቸውን እና አብሬያቸው እንድጫወት የማትፈቅድልኝን የሰፈራችንን ልጆች ጥፋትም እኔ ሳልሆን እቀራለሁ የምቀጠቀጠው? የሰፈሩ እናቶች በሙሉ ቅጣታቸውን ሳይሰጧት ይቀራሉ?

ከረድኤት አጠገብ ተጋድሜ ሊነጋ ገደማ አንድ መላ መጣልኝ፡፡ 'እሾህን በእሾህ!!”

“መሌ በህልምህ ከሴት ጋር አድረህ ታውቃለህ? ማለቴ እንትን አድርገህ?” አልኩት መላኩን ሱቄ በር ላይ ከተሰበሰቡት
👍51🥰1
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ሁለት


#በሜሪ_ፈለቀ

“እኔንጃ!! ትዝ አይለኝም ግን አጥፍቼ ነው።”

“ወላዲተ=አምላክ!!!!:: ቆይ በምንድነው እንዲህ የመታችህ?”

“እኔንጃ በጫማዋ ሹል መሰለኝ፡፡” እያየኋት ድርቅ ብላለች።

“ምነው አንቺ አትገረፊም እንዴ?”

“ወላዲተ አምላክ!!!! ሰው እንዴት እንዲህ አድርጎ ልጁን ይመታል? አንተ እኮ ትልቅ ሆነሃል!!”

ምን እንዳለችኝ በትክክል የገባኝ ከዛን ዕለት በኋላ ጠዋት ጠዋት ከሰፈራችን የሚያስወጣው መታጠፊያ ላይ መኪናቸው ቆማ እየጠበቀችኝ ትምህርት ቤት አብረን መሄድ ከጀመርን በኋላ
ነበር፡፡ ትምህርት ቤት ደርሰን ስትወርድ አባቷ እንዴት ነበር ያደረጓት? የአንደኛውን እጃቸወሁን ጣቶች ፀጉሮቿ መሃል
እንደማበጠሪያ ሰክተው ወደራሳቸው አስጠጓት፡፡ እንደተለመደ ነገር እንደትክክል ሁሉ ነበር የሚያደርጉት፡፡ ከጉንጭዋ ይልቅ ለአንገቷ የቀረበ ቦታ ላይ ሳሟት። ለኔ ግን የመሰለኝ እንደዛ
አይደለም፡፡ በጆሮዋ የሆነ መለኮታዊ ልሳን ያወሩላት፣በከንፈራቸው ወደሳሟት ቦታ አንዳች ልገልፀው የማልችለው
ዓይነት ምትሃተኛ ነገር እንዳስተላለፉላት፣ በጣቶቻቸው በሆነ ትስስር እንዳሰሯት
እንደዛ ነገር፡፡ መልሳ ጉንጫቸውን
ሳመቻቸው ልበል? በየጠዋቱ ይሄን ትዕይንት ማየት ልክ የሆነ ሌላ ዓለም መኖሩን ነገረኝ፡፡ የምፈራው፣ ያልኖርኩበት እና የማላውቀው የሆነ በሰው ልጆች መሃል ያለ መሳሳብ መኖሩን ነገረኝ፡፡ ወለላ ገረፈችኝ፡፡ ረድኤት ማን ናት? ለምንስ ት/ቤት ያደርሱሃል? ምን አሉህ? ወለላ ሴሰኛ ናት አሉህ? ወለላ ምን
አድርጋው ነው አባትህ ጥሏት የሄደው አሉህ? የማላስታውሰው ጥያቄ እየጠየቀችኝ ደበደበችኝ፡፡ ይሄን ግርፊያ
የሚለየው እንባዬ አልወጣ አለኝ፡፡ አልለመንኳትም፡፡ ፀጥ!ጭጭ ብዬ ተመታሁላት፡፡ አልታገልኳትም፡፡ መምታቷን አቁማ አየችኝ፡፡

“ምን ሆነሃል?”

“ምን ሆንኩ?”

“ምን ይዘጋሃል? ምን አስበህ ነው?” ዝም አልኳት፡፡ ያ የመጨረሻ ዱላዋ ነበር፡፡ “ምን ትጠላለህ?' በሉኝ ወለላን ቀጥለህ
ምን ትጠላለህ?” በሉኝ ወለላን ከዛ በተረፈህ ጥላቻ ምን ትጠላለህ?' በሉኝ ወለላን!!

በሚቀጥለው ቀን የአጥሩ በር ተንኳኳ፡ ረድኤት ነበረች፡፡ለሰላምታ እጄን ዘረጋሁላት፡፡ እጄን ጨብጣ ወደራሷ
አስጠጋችኝና ጉንጬን ሳመችኝ፡፡ አዎ ጉንጬን በከንፈሯ ነካችው። እርጥበቷ ጉንጩ ላይ ታትሞ የቀረ መሰለኝ፡፡

“ለምንድነው ትምህርት ቤት የቀረኸው?”

“ከዛሬ በኋላ ት/ቤት አልመጣም!!”

“እንዴ ለምን?”

“አንቺ ምን አገባሽ? የሚበጀውን ራሱ አውቋል፡፡ ምን ቤት ነኝ ነው?” ወለላ ናት ከየት መጣች ሳልላት አጠገቤ ደርሳ
የመለሰችላት፡፡

“ደሞ ስሚ ሁለተኛ ደጄ ድርሽ ብትዪ ውርድ ከራሴ” አለቻት ቀጥላ፡፡

ረድኤት መልስ ሳትሰጣት ጊቢያችንን ለቃ ወጣች። እኔም ት/ቤት ቀረሁ፡፡ ወለላ ለረድኤት አባት ስሞታ ስለተናገረችባት እቤትም መጥታ አታውቅም፡፡ መንገድ ብታየኝም በርቀት በግንባሯ ሰላም
ብላኝ ታልፋለች እንጂ አትጠጋኝም፡፡ ወለላን ትፈራታለች፡፡ወለላ ደግሞ የኔ ጥላ ናት፡፡ ከዚህ በኋላ ረድኤትን በቅርበት
ያየኋት የዩንቨርስቲ ተማሪ ከሆነች በኋላ አባቷ የሞቱ ጊዜ ነበር፡፡ ስታለቅስ በህይወቴ ከፍተኛውን ሀዘን ያዘንኩበት ቀን ይመስለኛል፡፡ አሳዘነችኝ፡፡ ከዓመታት በፊት በጆሮዋ ሹክ ያሏት የመሰለኝ የመለኮታዊ ቃል ትዝ አለኝ፡፡ ከሰው መሃል ስታየኝ ሮጣ መታ ተጠመጠመችብኝ
ምን ማለቷ እንደሆነ ገብቶኛል አባቷን እያስታወሰችኝ ነው።ሰዎች ቃል ሳይለዋወጡ የሚለዋወጡት ስሜት እንዳለ ገብቶኛል፡፡ ወደራሴ
አስጠግቼ መልሼ አቀፍኳት። ምን እንደተረዳችኝ ባይገባኝም ያለቃል እኔ የነገርኳት “አባትሽ ላንቺ ምን ማለት እንደሆኑ ይገባኛል፡፡ የሀዘንሽ ጥልቀት ተሰምቶኛል የሚለውን ነበር፡፡
ከረድኤት አባት ሞት በኋላ ብዙም ባልራቀ ጊዜ ወለላ ልትቆጣጠራቸው ባልቻለቻቸው ሱሶቿ ምክንያት ማገገሚያ
ገባች፡፡ ከዚያ ቀናት ቀደም ብሎ የምንኖርበትን ቤት ካርታ ሰጠችኝ፡፡በራሷ ስም ነው ያለው ያጠረቀመችውንም በዛ ያለ ገንዘብ ሰጠችኝ (ሱቅ የከፈትኩት በዚያ ብር ነው፡፡)

ወለላ ማገገሚያ ከገባች በኋላ ረድኤት እንደልቧ ቤቴ መመላለስ ጀምራለች፡፡ በሆነ ትምህርት ተመርቃ ስራ እየፈለገች ነበር።አንድ የሆነ ቀን እቤት ተቀምጬ እያለሁ መጣች። ዝም ብላ አጠገቤ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠች። እጄን ከጭኔ ላይ አንስታ እንደማሸት ነገር እንደመዳበስ አደረገችው፡፡ ዝም ብዬ አየኋት።

“ለምን እንደምወድህ ታውቃለህ?”

“አይደለም ምክንያቱን እንደምትወጂኝም አላውቅም፡፡” ስላት አናደድኳት መሰለኝ ተበሳጨችብኝ፡፡ የሚቀጥለውን ለመናገር
ጊዜ ወሰደች፡፡ ከልቤ ነው ያልኳት በማንም ስለመወደድም ማንንም ስለመውደድ ግድ ሰጥቶኝም አስቤም አላውቅም፡፡

“እወድሃለሁ!! የምወድህ ደግሞ ልብህ ስለሚያምር ነው፡፡”

“ልብህ ስለሚያምር?”

“አዎን ብዙ እውነትና ትንሽ ጥላቻ የተሸከመ ንፁህ ልብ ነው ያለህ!”

“ጥላቻ የሚያምር ነገር መሆኑን አላውቅም፡፡ ጥላቻን የተሸከመ
ልብ ንፁህ መባሉም አይገባኝም፡፡” አልኳት።

“አያምርም፡፡ አዎን ጥላቻ አያምርም፡፡ አየህ እውነትህን? ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ... አንዱ ይኖርበታል፡፡ ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባህሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎን ካልተገለጠ በስተቀር ንፁህ ፣ ቅን እና ፍፁም
እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ አንተ እንደዛ አይደለህም፡፡የተሰማህንና የሆንከውን ብቻ ነው የምትኖረው፡፡ የኖርከው
ህይወት የፈጠረብህን ጥላቻና ሽሽት አትደብቀውም፡፡ ያ ደግሞ እንድትድን ያደርግሃል፡፡ አንተ ክፉ ልብ የለህም፡፡ ማንንም መጉዳት አስበህ አትጎዳም፡፡”

ያወራችው ብዙው አልገባኝም፡፡ ከዚህም በላይ ብዙ ነገር አውርታለች፡፡ ከወሬዋ ይልቅ እጄን እየዳበሰችው ያለችው የእጇ
ድብሻ ደስ ብሎኛል፡፡ ረዣዥም የእጇን ጣቶች በትኩረት እያየሁ የምታወራውን ሙሉ በሙሉ አልሰማኋትም፡፡ ተጠጋችኝ
መሰለኝ፡፡ በየትኛው ቅፅበት ከንፈሯ ከንፈሬ ላይ እንዳረፈ አላውቅም፡፡ መሳም ብቻ አይደለም የሳመችኝ : አንድ የሆነ ነገር አድርጋኛለች፡፡ ከገለፃ በላይ የሆነ ምትሃተኛ ነገር፣ ደም የሚመላለስበት አካሌ ብቻ ሳይሆን ፀጉርና ጥፍሬ እንኳን
የሚሰማው ዓይነት ምትሃት!በደነዘዝኩበት ጥላኝ ወጣች፡፡

ከዚያ ቀን በኋላ ግን ውስጤ አንድ የሆነ አዲስ ነገር ተፈጥሯል።
ወለላ ማገገሚያ መግባቷን ሳውቅም ልጠይቃት አልሄድኩም።እንደውም እንደማትመለስ እርግጠኛ እንደሆንኩ ሁሉ ወይም ባትመለስ ምኞቴ እንዲሰምር እየፈለግኩ ተነስቼ የወለላን የግል ንብረቶች መበርበር ጀመርኩ፡፡ምን እንደምፈልግ እንኳን በትክክል ሳላውቅ የሆነ ነገር እፈልጋለሁ። ያን ማድረጌ ረድኤት ያለችኝን በልቤ ያለች ትንሽዬ ጥላቻ ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት
ይሆን? በየዕለቱ እያነበበች የምታለቅስባቸውን ደብዳቤዎቿን
ይዛቸው መሄዷን ስገነዘብ ለአፍታም ቢሆን ማን እንደሚፅፍላት የማወቅ ጉጉት አደረብኝ፡፡ በካርቶን ያጠረቀመቻቸው ብዙ ፖስታዎች ናቸው:: እስከቅርብ ዓመታት በየወሩ ፖስታ ቤት
እየሄደች አንድ አዲስ ፖስታ ይዛ ትመጣለች፡፡ አንብባ ስትጨርስ
ከቀደሙት ጋር ብትቀላቅለውም ሁሌም ብቻዋን ስትሆን ከምትቆልፍበት መሳቢያ ውስጥ እያወጣች ደጋግማ ታነባቸዋለች። አባቴ ይሆን? ወይ ከባሎቿ አንዱ? አልያም ከተለያየ ሰው የሚላክ ይሆናል። ብቻ ቅጥ ያጣ ራስ ወዳድነቷን ዘልቆ በልቧ ቦታ ያገኘ ሰው መሆን አለበት ምናልባት የበደለችው ሰው አልያም ደብዳቤውን መፃፍ ያቆመው ሞቶ
መሆን አለበት።
👍5
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ሶስት


#በሜሪ_ፈለቀ

ትለኛለች።እውነቱን ሳወራት ይከፋታል። አኮረፈች። ጥላኝ ግን አልሄደችም።

"አንተጋ ልደር?” አለችኝ፡፡“

“ደስ ይለኛል!” አልኳት እንድትሄድ አልፈለግኩም፡፡

“የት እተኛለሁ?”

"የተመቸሽ ቦታ"

የተመቻት ቦታ ከኔጋ አልጋዬ ላይ መተኛት ነበር፡፡ እንደዛ አደረገች፡፡ እንደብዙ ነገር አደረገች፡፡ ልብሶቼን ከላዬ እንዴት ገፋ
ጣለቻቸው? ከመቼው አልጋው ላይ ወደቅን?ከላዬ ነበረች? በየትኛው ቅፅበት ከስሬ አገኘኋት? የማላውቃት የሆነች ልጅ ነበረች፡፡ የደስታ ሲቃዬን ያበዛችው ግን የማላውቃት ባዕድ ነገር የሆነችብኝ፡፡ ከሰውነቴ አጣብቄ እንዳቀፍኳት ነጋ፡፡

“አትሂጂ አብረሽኝ ኑሪ!” አልኳት፡፡

ትወደኛለህ?” ብላ ጠየቀችኝ።

“እኔንጃ!” መለስኩላት።

ከእናቷ ጋር ብዙ ከተነታረከች በኋላ አብራኝ መኖር ጀመረች፡፡ልክ ያልሆነ ነገር ያለው አኗኗር መሆኑ ይገባኛል፡፡ አብራኝ
ልትኖር የወሰነች ቀን ማታ በድጋሚ “ትወደኛለህ ወይ?” ብላ ጠየቀችኝ፡፡ በማላውቀው ምክንያት ይሄ ጥያቄዋ የሚከብድ ነገር አለው፡፡ መውደድ፣ ናፍቆት፣ ፍቅር ዓይነት ላሉ ስሜቶች
እርግጠኛነቴን እንጃ፡፡ ስሜቱ ምን ስለመምሰሉም አላውቅም።

“ስትስሚኝ ደስ ይለኛል፡ ባለፈው ዕለት እንትን ስናደርግም በጣም ነው ደስ ያለኝ።

“አብሮ ለመኖር ይሄ በቂ አይደለም፡፡ ፍቅር ነው ዋናው! እንደወደድከኝ እስኪሰማህ ድረስ አብሬህ እሆናለሁ፡፡ ነገር ግን ምንም አናደርግም፡፡” ያለችው ምን ያህሉ እንደገባኝ አልገባኝም፡፡

“ቆይ አንቺ ስናደርግ ደስ አላለሽም ነበር?”

“ፍቅር የሌለበት ወሲብ ማድረግ አልፈልግም፡፡” የምጠይቃትና
የምትመልስልኝ አልገጣጠም ይለኛል፡፡ እኔ እስከገባኝ ያደረግነው የሁለታችንም ደስታ የነበረበት ነገር ነበር፡፡ ብቻዬን ያደረግኩ፣ደስታው የእኔ ብቻ እንደነበር፣ እርካታው የግሌ ብቻ እንደሆነ እንዲሰማኝ ለምን እንደምታደርግ አይገባኝም፡፡ እንድዋሻት ትፈልጋለች፡፡ ምክንያቱም ራስዋን መዋሸት ስለምትፈልግ።በፍቅር ስም ለፍቅር ብላ ጭኖቿን እንደከፈተችልኝ እንጂ ለስሜትዋና ለደስታዋ ስትል ከማይወዳት ወንድ ጋር እንዳደረገችው በማሰብ ለራሷ ያላትን ግምት ዝቅ ማድረግ አትፈልግም፡፡ ደስታን መፈለግ ክፋቱ አይገባኝም፡፡ ለምን ሌላ ምክንያት ይለጠፍበታል? ለሁለት ወራት እንደዚህ አብረን ከኖርን በኋላ ነበር ህልሟን የነገረችኝ፡፡ ከፈቃዱ ጋር የሰራችውን የህልም ፍቅር!

በመላኩ ምክር ቅደም ተከተል መሰረት ከመተኛቴ በፊት አንዲት ፍቅረኛዬ የምታደንቃትን ታዋቂ ሴት አርቲስት ገላ ለማሰብ ሞከርኩ፡፡ከፍቅረኛዬ ውጪ የማንም ሴት ገላ ሊከሰትልኝ አልቻለም፡፡ ከዛሬ ሁለት ወር በፊት ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ከላዬ ሆና ዛር እንዳለበት ሰው ካበደችው እብደት ውጪ
ምንም ወደ ሀሳቤ ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ በእርግጥ እንዴትስ ማሰብ ይቻለኝ ነበር? ከሷ ውጪ የሴት እርቃን በፊልም እንኳን
ማየቴ ትዝ አይለኝም፡፡ ያየኋቸውን በአንድ የእጅ ጣት የሚቆጠሩ ፊልሞችም እሷው ናት ያሳየችኝ፡፡ ሴቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው የሚያሳይ ቦታ ነበረው? አላስታውስም፡፡

“እ? ተሳካልሽ? ማታ ቺኳ ከች አለች?” አለኝ መላኩ ሱቄን ጠዋት እንደከፈትኩ ለወሬ ቸኩሎ።

“አላለችም ::አንተ ነህ ከች ያልክብኝ!! አልኩት መናደዴን እንዲያውቅ ጥርሴን ነክሼ።ላለመሳቅ እየታገለ።

“ምን ሳደርግ?” አለኝ።

“ብዙውን አላስታውስም፡፡ በጥፊ ስታልሰኝ ነው ከእንቅልፌ የባነንኩት” ስለው እስኪበቃው አገጠጠ፡፡ በህልሜ ረድኤትን የማስቀናቱ ሀሳብ አልተሳካልኝም።

“መነጋገር አለብን!” አልኳት አዋርቻት በማላውቀው ድምፀት፡፡ስታወራ እሰማታለሁ እንጂ ራሴ ርዕስ ፈጥሬ አዋርቻት አላውቅም።

"ዛሬ ወለላን ሄደን መጠየቅ አለብን።" አለችኝ ያልኳትን እንዳልሰማች ሁሉ ርዕስ ቀይራ:: ትናንትና ከሰዓት የወለላ ነፍስ
አባት እቤት ድረስ መጥተው ጉበቷ አደገኛ ደረጃ ላይ ስለደረስ ከማገገሚያ ወጥታ ከፍተኛ ሆስፒታል ከተኛች መክረሟን ከነገሩን ሰዓት ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ፀብ ቀረሽ ንትርክ ላይ ነን፡፡
እኔ እናቴን ላያት አልፈልግም፡፡ እርሷ ደግሞ ምንም ቢሆን እናቴ ስለሆነች የኛ ጥየቃ ይገባታል እያላች ችክ ብላለች። እኔ
ላናግራት የፈለግኩት በየእርምጃዬ ልረሳው ስላልቻልኩት ህልሜ ነበር። ጭቅጭቋ ሊያሳብደኝ ስለደረሰ ቁርስ እንደበላን ሆስፒታል ሄድን፡፡ ወለላ ጉዷ ተጎትቶ የማያልቅ ሴት መሆኗን ባውቅም
ለአፍታ ሽው ባለች ቅፅበት አስቤው የማላውቀው ነገር ገጠመኝ።
የወለላ ልጅ የእኔ ታላቅ ወንድም ሲያስታምማት አገኘሁት፡፡የተፈጠረው ነገር የሆነ የተልወሰወሰ ነገር አለው። መቼ ነው የወለደችው? አላሳደገችውም ማለት ነው? ለነገሩ ተገላገለ ከድብደባ ነው የተረፈው። ያላሳደገችውን እናቱን እንዴት እናቴ ብሎ ይጠራታል? እንዴትስ እያደረ ያስታምማታል? ይሄን
የማስበው የወለላ ልጅ መሆኑን በነገረኝ ቅፅበት ረድኤት እየተውረገረገች ወንድሙ መሆኔን ስትነግረው እርሱም እልፍ እያሰበ በመሰለኝ ሽርፍራፊ የጊዜ ክፍተት ነው። ምክንያቱም እሱም ወንድም እንዳለው አያውቅም። እርሱ ዝም አላለም።የሰማው ነገር ልክ መሆኑን ሲያረጋግጥ እድሜዬን ጠየቀኝ እና
ከራሱ ጋር ማስላት ጀመረ። በስምንት ዓመት እንደሚበልጠኝ ነገረኝ። ስራ እንዳለበት ነግሮን ሲወጣ አንድ ጥያቄ ብቻ ጠየቅኩት።

"ደብዳቤ የምትፅፍላት አንተ ነበርክ?" በመገረም እያስተዋለኝ አለመሆኑን ነግሮኝ ወጣ: ወንድም ማግኘቴ ከመገረም ልቆ የሰጠኝን ስሜት አላወቅኩትም።ወንድሜ ጥሩ ሰው ይመስላል፡፡ወለላን መውደዱን ግን ማመን አልቻልኩም። ረድኤት ከስራ
እስክትመለስ ሱቅ ቆሜ በሀሳብ እዚህ እዚያ ስረግጥ ዋልኩኝ።ዛሬ ሳላናግራት አላድርም እያልኩ ስዝት ውዬ መጣች።

“ጠዋት ስለምን ነበር ልታወራኝ የነበረው?” አለችኝ እራት የበላንበትን ሰሃን እያነሳሳች።

“እየቀናሁ ነው!” አልኳት፡፡

“አልገባኝም!!” አለችኝ የያዘችውን ሰሃን መልሳ እያስቀመጠች።

“አየሁት ካልሽኝ ህልም ውጪ ምንም ማሰብ አልቻልኩም፡፡”ስላት ሳቀች፡፡ ከት ብላ ሳቀች፡፡

“ጅል ነህ! ጅልነትህን ግን እወደዋለሁ፡፡"

“ጅል አትበይኝ! አትበይኝ በቃ!! የኔ ብቻ እንድትሆኚ መፈለግ ጅልነት ነው? ሌላ ሰው እንዳይነካብኝ መሳሳት ጅልነት ነው?
ስራ ውለሽ እስክትመጪ ላይሽ መጓጓቴ ነው ጅልነት? አቅፌሽ እያደርኩ ለራሴ ስሜት ሳይሆን ላንቺ ቃል መጠንቀቄ ጅልነት ነው? የቱ ነው ጅልነት? ከንፈርሽን መናፈቄ ነው ጅልነት?ንገሪኝ ይሄ ጅልነት ነው?” እንደዚህ መናገር መቻሌን ያወቅኩት ዛሬ ነው።

“አይደለም፡፡” አለችኝ እኔ ከምናገርበት የቁጣ ጩኸት ተቃራኒ በሆነ ለስላሳ አንደበት፡፡

“ይሄ ጅልነት አይደለም ፍቅር ነው ማሬ” አለችኝ፡፡ በፈገግታዋ መሃል ዓይኖቿ እንባ ሲያረግዙ አየኋቸው፡፡ ሳማት ሳማት
የሚለኝን ስሜቴን ማቆም አልቻልኩም። ከማድረጌ ቀድሞ ግን ስልኬ ጠራ! ወንድሜ ነው:: ዛሬ ጠዋት አውቆኝ ፍቅር ፍቅር ሊጫወት ከሆነ እየተገረምኩ ዝም ብዬ ስልኩን አየዋለሁ።የማንሳት ጉጉት አልነበረኝም።ረድኤት እንዳነሳው ስትነግረኝ ግን አነሳሁት፡፡ ምንድነው ያለኝ?

"ስህተት እናታችን ሞታለች:: ማለቴ ተገድላለች::"ሲለኝ መሞቷ አልገረመኝም: አላሳዘነኝምም:: አሟሟቷ እንጂ!
ወለላ እኔን ስትቀጠቅጥ እና ባሎች አግብታ ስትፈታ ኖራ......ኖራ......... ኖራ........ የረሳሁላት ከፍተኛ ምግባር አለ፡፡ስትራገም ኖራ ኖራ....... በተጨማሪ ደብዳቤ ስታነብ ኖራ...ኖራ... ለእኔ የማያልቅ ከሚመስል ዘመን በኋላ በሀያ ሁለት ዓመቴ ሞተች፡፡ እሰይ ሞተች!
👍31
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አራት


የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ መጀመርያው የማይታወቅ ክስተት እንኳን ቢሆን ቀጣይ አለው።ከመጀመርያው ወይ ካለፈው የሚያያይዘው አምድ የድር ያህል የቀጠነ ቢሆንም....ሁሌም ከማሃል ቆመህራስህን ስታገኘው መጀመርያውን የምትጠይቀው ለዛ ነው።

=========================
"ከኔና ከሱሶችህ ምረጥ" ስትለኝ ቀኑ ቅዳሜ ነበር።ስልኬን ጆሮዬ ላይ እንደለጠፍኩ ዙሪያዬን ቃኘሁት፡፡ በሱሶቼ ተከብቤያለሁ።(ያሟላሁ ሱሰኛ ነኝ፡፡)

"መቼ?" አልኳት።

"አሁኑኑ!"

"ዛሬ ከሆነ ሱሴን ነገ ከሆነ ግን አንቺን!” መለስኩላት፡፡ዘጋችው።መልሳ እንደማትደውል አውቃለሁ፡፡ ጥፋተኛው ማነው? ራሷን ከቅጠል ጋር፣ ከጭስ ጋር በሚዛን አስቀምጣልኝ ምን ልበላት?
ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው' ዋጋዋን ከሷ በላይ እንዴት ላውቀው እችላለሁ? ስንተኛዬ እንደሆነች የማላስታውሳት ሴቴ ናት።ሴቶቼ እድሌ ሆኖ ነው መሰል ሱሴን ይጠምዱታል። እኔ ደሞ ፀባዬ ሆኖ ሱሰኛ ሴት ቅልሽልሽቴን ታመጣዋለች:: "በማን ላይ ተቀምጠህ ማንን ታማለህ?" ትለኛለች አለቃዬ(ስምረት) እኔ ስምሪት ነው የምላት አትናደድብኝም:: ከጠዋት ይልቅ ለለሊት የቀረበ ሰዓት ላይ ቢሮ ትገባና ተሰይማ ትጠብቀናለች:: ከጠዋት
ይልቅ ለከሰዓት በቀረበ ሰዓት ቢሮ እከስታለሁ፡፡

"እስቲ አንተን የማላባርርበት አንድ ጥሩ ምክንያት ብቻ ንገረኝ" ትለኛለች፡፡

"ያንቺ ደግነት!" እላታለሁ፡፡

"ወደ ስራ!" ብላ የመጨረሻውን ተሰማሪ ታሰማራኛለች ስምሪት።

ሴት ወዳለሁ። “ማን ይጠላል? አልክ የአዳም ዘር? ሃሃሃሃ..የምሬን እኮ ነው። እኔ ወዳቸዋለሁ። ሳስበው ፈጣሪ በምድር ላይ እንደ ሴት ውብና አማላይ አድርጎ ለፈተና የፈጠረው ነገር
መኖሩን እንጃ!! ገና ሳስባቸው ደም ስሬን የሚወጥሩ ፍጥረቶች ናቸው።ኤጭ አሁን ራሱ ደሜ ሞቀ! እነሱ ከሚወዱኝ የበዛ
ይናደዱብኛል!! "ሴት ሳይሆን ስሪያ ነው የምትወደው" ይሉኛል፡፡
“ስሪያው ታዲያ ከወንድ ጋር ነው እንዴ?" እላቸዋለሁ፡፡

በእርግጥ ከሴት ጋር ሱስ ስለማቆም ከማውራት 'አክሱሜን የሚያቆም ወሬ ማውራት እመርጣለሁ፡፡ (የኢትዮጵያን አክሱም እያልኩህ አይደለም።የራሴን አክሱም!) ሴትና ስሪያ ከመውደዴ
የተነሳ እንደውም ሳስበው መቃብሬ ላይ ራሱ አልቤርጎ ሚሰራ ነው የሚመስለኝ።

"አብረኸት ሆነህ የተለየ ደስ የሚል ስሜት የፈጠረችብህ ሴት የለችም?" ትለኛለች ስምሪት ስለሴቶቼ ስናወራ።

"አብሬያት ሆኜ የሚያስጠላ ስሜት የፈጠረችብኝን ሴት አላስታውስም::" እመልስላታለሁ:: እውነቴን ነው፡፡ በእርግጥ ረዥሙ ከሴት ጋር ቆይታዬ ሁለት ወር ነው። አንድም ቀን ያወቅኳትን ሴት ሁለት ወር ከማውቃት እኩል እወዳታለሁ። ስምሪት ደወለች::

"ወዬ?" መልስ የለም።

"ወዬ ስምሪት?" አልኩኝ ደግሜ፡፡ ከትንፋሽ ውጪ የሚሰማኝ ስላልነበር ዘጋሁትና መልሼ ደወልኩ፡፡ ይነሳል ግን መልስ የለም።

በነገራችሁ ላይ ስምሪት በኔ ውስጥ ፆታ አልባ ናት!! የሆነ ከማውቃቸው
ሴቶች የሚለያት እንደ ሴት እንዳላስባት
የሚያደርገኝ ነገር አላት፡፡ ምናልባት የምትለብሰው የፖሊስ ልብስ፣ ምናልባት ሁለት ሰዓት ለፍልፌባት በሁለት ደቂቃ
የምትመልስልኝ ልብ የሚያሳርፍ መልሷ፣ ምናልባት አለቃዬ መሆኗ፣ ምናልባትም ጆሮዬ እስኪጠነዛ ስለ ሴት መዋቢያና ማጌጫ ከሚያወሩኝ ሴቶች ስለምትለይ፣ ምናልባት የምትመርጣቸው ሮክ ሙዚቃዎችና የስለላ ፊልሞች ከብዙ ሴቶች ምርጫ መለየቱ ምናልባት....ምናልባት...በብዙ ምናልባቶች ፆታ አልባ ናት!! ወንድ ጓደኛ ሲኖረኝ ላወራው የምችለውን ቅሽምናዬን ሳወራት በከፊል ፈገግታ ከመስማት ውጪ አትፈረድብኝም።ስለፅድቅና ኀጢኣት አትሰብከኝም። የሚሰለቸኝ ስብከት መሆኑን ታውቃለች፡፡ ይሄ ማህበረሰብ ምኔ ነው? ምን የሰጠኝን ነው ሊቀበለኝ እጁን የሚዘረጋው? የእጁ አሻራ እስኪጠፋ ከሳሙና ጋር እንዳልተዳራ ከተለያየ ሴት ጋር መታየቴ ኀጢኣት መሆኑን ሊነግረኝ ይዳዳዋል፡፡ ያንተ ኀጢኣት የእኔን ኀጢኣት ፅድቅ
አያደርገውም፡፡ ቢሆንም ግን ራስህን በፃዲቅ ሂሳብ አስልተህ እኔን ለመኮነን ትክክለኛው ሜዳ ላይ አይደለህም:: በሀያ ዘጠኝ የእድሜዬ ቁጥር ላይ የተጓዙበት ይመስል የልክ መስመርን ሊያሰምሩልኝ እና ሊመክሩኝ ይፈልጋሉ:: ጥፋት መሆኑን
ሳላውቅ የማጠፋው ጥፋት አለ እና ነው? ችግሩ አንዳንዴ ልክ እንዳልሆነ በልብህ እያወቅክም ታደርገዋለህ።ብትፀፀትም ግን ትደግመዋለህ፡፡ ታዲያ ምኑን ነው የሚመክሩኝ? በዚህ ዘብራቃ ማህበረሰብ ውስጥ ኀጢኣትህን ኀጢአት የሚያደርገው ድርጊቱ ሳይሆን ያደረግከው ድርጊት በግልፅ መሆኑ ነው። ተደብቀህ ካደረግከው ፅድቅህ ይተረካል፡፡

ከስምሪት ጋር ሶስት ዓመት አብረን ሰርተናል፡፡ እሷ መርማሪ ፖሊስ መሆን ህልሟ ነው:: እኔስ? እኔ ደግሞ ቅዠቴ፡፡ እዩልኝ ይሄ ግራ የገባው የጦዘ የኑሮ ስሌት እና አስተዳደር አላሚና ቃዢን በአንድ ያስተዳድራል።ለሶስተኛ ጊዜ መልሼ ደወልኩ።በተኮላተፈ አንደበት እና በተሰባበሩ ፊደላት የመለሰችልኝ ህፃን
ናት። ቀጣጥዬ የተረዳሁት ደግሞ "ስምረት ሞተች” የሚለውን ንግግር ነው። ዘልዬ ብድግ አልኩ።ይሄኛውን ራሴን
አላውቀውም። በምንም ክስተት እንዲህ እደነግጣለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም።

ከርቀት የማውቀው የስምሪት ቤት ለመድረስ ላዳ ታክሲ ያዝኩ፡፡ሆኜ እንደማላውቀው ታክሲ ውስጥ ቁጭ ብድግ ሰራሁ። ሮጬ ቤቱን ሳንኳኳ የከፈተችልኝ ቅድም በስልክ ያዋራችኝ ህፃን ናት።የኦቲዝም ተጠቂ መሆኗን ለመገንዘብ ከአንድ ዕይታ በላይ
አይጠይቅም፡፡ ዘልዬ እየገባሁ ምን መጠየቅ እንዳለብኝ ግራ ስጋባ
በእጂ ምልክት የሻወር ቤቱን አሳየችኝ፡፡ ክፍት ነው:: ስምሪት ወለሉ ላይ እርቃኗን ተዘርራለች:: እርቃኗን ለቄንጥ የተዘረረች
የሚመስል አነጣጠፍ ነው ወለሉ ላይ የተነጠፈችው።ትንፋሿ መኖሩን ካረጋገጥኩ በኋላ ከወለሉ ላይ ተሸክሜ መኝታ ቤቷ አልጋዋ ላይ አስተኛኋት። በደመነፍስ ማድረግ ያለብኝ የመሰለኝ
ቁምሳጥኑን ከፍቼ ያገኘሁትን ልብስ ማውጣት ነበር። በፎጣ ሰውነቷን አደራርቄ ሳበቃ ፓንቷን አለበስኳት:: የሴት ልጅ ፓንት ያወለቅኩበት ጊዜ እንጂ ያለበስኩበት ቀን አልከሰትልህ አለኝ። የሆነ ገለፃ አልባ ነገር እየተሰማኝ ልብሷን አለባበስኳት እና ወዳቆምኩት ታክሲ ተሸክሜያት ሄድኩ። ህፃኗ ድምፅ
የሌለው ለቅሶ እያለቀሰች እየተከተለችኝ እንደሆነ ያወቅኩት ታክሲ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ነው:: ግራ ተጋባሁ:: ይዣት
ልሂድ? ህፃን ናት እንዴት ትቻት እሄዳለሁ? የቤቱን በር ዘግቼው ታክሲው ውስጥ አስገብቻት አብረን መጓዝ ጀመርን።
ስምሪት እግሮቼ ላይ ናት፡፡

"ስምሪት ምንሽ ናት?" ጠየቅኩ ከስምሪት ላይ ዓይኗን ለአፍታ ያልነቀለችውን ህፃን:: በአትኩሮት በጥያቄ አየችኝ፡፡ ፊቷ ተቆጣ።

"ስምረት ምንሽ ናት?" አስተካክዬ ደገምኩ።

አልመለሰችልኝም። ስምሪት ስለራሷ ነግራኝ የምታውቀው ነገር ካለ ማሰብ ጀመርኩ። መርማሪ ፖሊስ መሆን ህልሟ መሆኑን ብቻ! አስቤው አላውቅም:: ጠይቄያት አላውቅም።ስለእኔ
የማልነግራት የለም:: እንዴት ሆንክ? ያ ነገር እንዴት ሆነልህ ያሁኗ ቺክህ እንዴት ናት? ምን ሆነህ ነው ፊትህ ልክ አይደለም? ዓይንህ ቀልቷል ማታ አልተኛህም እንዴ? ማውራት ትፈልጋለህ? የመሳሰሉ ጥያቄዎች ትጠይቀኛለች፡፡ የጠየቀችኝን እመልስላታለሁ። አንዲትም ቀን አንቺስ? ብያት አላውቅም ፊቷ ጠቆረ? ቀላ? አይቼው አላውቅም። እንደመስታወት የሚያብረቀርቅ የፀዳ ቀይ ፊት እንዳላት እንኳን ያስተዋልኩት
ዛሬ ነው:: በእርግጥ ስትናደድ ጉንጫ ሲቀላ ደስ ትለኛለች

“እናቴ ናት" አለችኝ ህፃኗ መጠየቄን የምረሳበት ያህል
👍1
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አምስት


#በሜሪ_ፈለቀ

ውድ አንባብያን ምንም የተቀየረ ድርሰት የለም እስካሁን የቀረቡትም በቀጣይም የሚቀርበውም #የቀላውጦ_ማስመለስ ተከታይ ክፍሎች ናቸው ነገር ግን ሃሳቦች በሙሉ ላያልቁ ይችላሉ እነዲዚ ሲያጋጥም በራሳችሁ እየጨረሳቹ አንዳንድ ታሪኮች ደሪሲው ብቻ አይጨርሳቸውም አመሰግናለው።
=========================

ስምሪት ነቅታ ተንቀሳቀሰች። ዓይኖቿ ስትገልጣቸው ድልህ መስለዋል። በመጠኑ እፎይታ ተሰማኝ። አርሴማ መንቃቷን ስታውቅ ቦረቀች::

"ወደ ቤት መልሰኝ ምንም አልሆንም አንዳንዴ እንዲህ ያደርገኛል" አለችኝ የሆነውን ከነገርኳት በኋላ፡፡

"አንዳንዴ? መታየት አለብሽ?"

“እንቅልፍ ተኚ፣ እረፍት አድርጊ፣ ፈሳሽ ውስጂ” ነው የሚሉኝ" አለች ከእግሮቼ ላይ ለመነሳት እየተነቃቃች። ብዙ
በእንቢታዋ ፀናች፡፡ ሀሳቧን እንድትቀይር
እየነተረኳት ወደ ቤት ተመለስን፡፡ ምንም የማውራት ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ እሷም እቤቷ መቀመጤ ምቾት የሰጣት
አይመስለኝም፡፡ አርሴማ እናቷ ጉያ ተሸጉጣ ቁልጭ ቁልጭ እያለች አንዴ እኔን አንዴ እናቷን ታያለች።

"ደህና ትሆኛለሽ? ልሂድ?" አልኳት፡፡

"አዎን ደህና እሆናለሁ ሂድ!" አለችኝ የመገላገል አይነት ስሜት ባለው ድምፅ።

ከቤቷ ወጥቼ በእግሬ ብዙ መንገድ እየተጓዝኩ ጭንቅላቴ ስለስምሪት የግርታ ቁልል መደርመሱን አላቆመም:: (ይህቺ ሴት ማናት? አላውቃትም ነበር ማለት ነው? ወይም የፖሊስ ልብሷን ስታወልቅ ቁሌታም ትሆናለች?) እንዲህ የማስበው መታጠቢያ ቤቷ ውስጥ ተዘርራ ያየሁት ሰውነቷ አንድ በአንድ ሲታወሰኝ
ነው። መሬቱ ላይ ተዘርራ አልፎ አልፎ የሳሙና አረፋ ሰውነቷ ላይ መኖሩ ሸራ ላይ የተሳለች ስዕል አስመስሏት ነበር። ከፊል ፀጉሯ ወለሉ ላይ ተበትኗል፡፡ ከፊሉ በትከሻዋ አልፎ ደረቷንና የግራ ጡቷን ሸፍኖታል፡፡ (ፀጉሯን ሁሌም ጠቅልላ ነው
የማውቃት ረዥም ፀጉር እንዳላት አስቤ አላውቅም፡፡ ኸረ ፀጉር እንዳላትም ትኩረት ሰጥቼ አይቻት አላውቅም።) የቀኝ እጇ የቀኝ ጡቷን በከፊል ከልሎ ዘንፈል ብሏል፡፡ ጡቶቿ በአንድ ጨረፍታ እይታ ብቻ በጭንቅላት ውስጥ ይሳላሉ፡፡ የግራ እጇ ወለሉ ላይ ተጥሏል።ከጀርባዋ የተጣበቀው ሆዷ እና ከታችኛው አካሏ ጋር ሲተያይ የሌላ ቀጭን ሴት የሚመስል የሰመጠ ወገቧ በአንድ ጎኗ ወለሉን ተደግፈዋል፡፡ እግሮቿ በመጠኑ ገርበብ ብለው ቀኙ አጠፍ ብሎ ግራው ተዘርግቷል። አይቼ አለመገረም ያቃተኝ
ዙሪያውን ተላጭታው ለ'እሙሙዬዋ" የቀረበ ቦታ ላይ ትንሽዬ ሶስት ማዕዘን ቅርፅ የተወችለት ጭገሯ ነው፡፡ ይህቺን ሴት በፍፁም አላውቃትም።

ራሴን ፣እሷን፣ ልጇን፣ እየዛቆሉ የሚኖሩትን ይህ በስባሳ ኑሮ እያሰብኩ ሳይታወቀኝ ብዙ ተጓዝኩ፡፡ረበሸኝ፡፡ ግድ የለኝም፣ ረስቼዋለሁ፣ ተሻግሬዋለሁ ትላንት ልቤን እየጨመደደ ሲፈነቅለኝ ይታወቀኛል። ደጋግሜ አጨስኩ።ራስ ምታት ጀመረኝ፡፡

ያለፈው በሚመጣው ላይ ምንም ጥቀርሻ መተው የለበትም ብዬ ያለፈውን ከኔ አርቄ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር፡፡ ምናልባት አይቻል ይሆናል፡፡ ዛሬ ከተከሰተው ክስተት ምኑ ከኔጋ እንደሚያያዝ አላውቅም።የሰው
ልጅ ሁሉ ከትላንቱ ተጋብቶ ሳይሆን
አይቀርም የሚኖረው። ዛሬው የትላንት ጭማቂ ነዋ!! የዛሬ ግቡ የትናንት ምክንያቱ ነበራ! ከዓመታት በፊት እናቴ ወይ አባቴ ያነቡት እንባ ምክንያቱን እንኳን ሳይቀይር በልጃቸው ጉንጭ
ላይ ሊወርድ ይችላል፡፡ አባቶች በበሉት መራር ፍሬ የልጆች ጥርስ በለዘ አይነት ሆኖብኝ ትላንት ትዝታ ብቻ አለመሆኑ
የገባኝ ዛሬ ነው፡፡ ትናንት ትውልድን እንኳን ጥሶ እንደሚያልፍ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ሀበሻ ሙዚቃው ውስጥ እንኳን ትዝታ ስልት መኖሩ ከትናንት መፋታት አለመፈለጉ ወይ አለመቻሉ ይሆናል፡፡ ስልኬ ጮኸ፡ ስምሪት ናት። ደነገጥኩ።

"ወዬ ምነው? አመመሽ እንዴ?"

“ኸረ ደህና ነኝ። ቅድም ስላልተረጋጋሁ አመሰግናለሁ እንኳን ሳልልህ!”

“አሁን አልሺኝ!" ብያት ስልኬን ዘጋሁት:: ከትናንትናዬ መዘጋጋት ግን አቃተኝ።

እናቴ ሸርሙጣ ነበረች፡፡ ሀገር ያወቃት ሽርሙጣ፡፡ ስለእርሷ ሲወራ የምሰማው የባሎቿን ብዛት እና የወንዶቿን መደራረብ
ነበር፡፡ እኔን እንኳን ከማን እንደወለደችኝ አታውቅም:: ባሏ ነው የሷ ዲቃላ መሆኔን የሚነግረኝ፡፡ እሷም ጋንጩራ የሰፈረባት
ቀን ሂድ ከዚህ ጥፋ! ዲቃላ ትለኛለች ስትሰድበኝ የሌላ ሰው ነውር እንደሆንኩ ሁላ... እናቴ ምንም አትገባኝም:
አንዳንዴ አቅፋኝ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች፡፡ ወዲያው መልሳ ለዓይኗ እቀፋትና ዞር በልልኝ ትለኛለች፡፡ ቆንጆ ናት።ህልም የመሰለች ቆንጆ! ባሏ ደግሞ ጥንቅቅ ያለ ሱሰኛ ነው:: እናቴንና ባሏን በተመለከተ ብዙ ያልጠየቅኳቸው ያልተመለሱልኝ
ጥያቄዎች አሉ። ማወቅም አለማወቅም የሚሰጠኝ ሽራፊ ስሜት አልነበረም፡፡ እናቴ እንዴት አንድ ዘመድ እንኳን አይኖራትም? አላውቅም! የምንኖርበትን ቪላ አወረሱኝ የምትላቸው ቤተቦቿ
እንዴት አንዲት የዘር ትራፊ አይኖራቸውም? ለምን በየቀኑ
ከተለያየ ወንድ ጋር ትሆናለች? ሲያሻት ራሱ ጠባቂ ለሚያስፈልገው ባሏ ትታኝ የት ነው ከርማ የምትመጣው? ባሏስ
ከመስከር ውጪ የሚያደርገው የመልስ
ምት እንዴት አይኖርም? አላውቅም። እነሱ ለኔ ግድ እንደሌላቸው ሁሉ እኔም
ጉድጓድ ቢገቡ ግድ አልነበረኝም፡፡ አብራን በምትሆንባቸው ምሽቶች እሱ ሰክሮ ይገባል። እሷ ተኳኩላ ትወጣለች፡፡ ለቀናት ጥላን የምትጠፋበት ጊዜም የእድሜዬ ግማሽ ያህል ነው።
ለዓመታት ያልነበረችበት ዘመንም ነበረ። የስምንት ዓመት ልጅ ስሆን ጥላን ሄደች:: የት መሆኑን ባሏም አያውቅም፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ስትመለስም የማንንም ጥያቄ ያለመመለስ መብትና እብሪት ነበራት። የሚቀጥለውን አራት ዓመት አብራን ስሆን ብቅ ጥልቅ ማለቷ ቀርቶ ለባሏ ጥላኝ ሄደች።እሷ ኖረችም
ሄደች ለውጡ ምንም ነው። ልጥገብ ወይ ልራብ፣ ልደስተ ወይ ልዘን፣ ልክሳ ወይ ልወፍር፣ ልማር ወይ ሜዳ ልዋል፣
ልታመም ወይ ጤነኛ ልሁን ሁለቱም ግዳቸው አይደለሁም ምናቸውም አልነበርኩም። አብሬያቸው ሆኜ የረሱኝ ይመስላሉ።

በእርግጥ በፍቅር ከመደኅየታችን ውጪ በኑሮ የጎደለ ሽንቁር አላስታውስም።እሷ በማትኖርበት ጊዜም ከምንኖርበት ትልቁ ቤት ጀርባ የሚከራዩ ሰርቪስ ቤቶች በየወሩ ገቢ ስለነበረን አንቸገርም ነበር።

“እናትህ ሸርሙጣ ናት! ወንድ አትጠግብም።ለገንዘብ ብላ አይደለም የምትሸረሙጠው ሽርሙጥና ሱስ ሆኖባት ነው።ይለኛል ባሏ ይዞ ከመጣው ቢራ እየቀዳልኝ:: ጠዋት ግን ገንዘብ
ስትሰጠው አየዋለሁ።ከርሱ ጋር በየቀኑ እየሰከርኩ ማደር ልምዱ ነበር። ይቀዳልኛል፣ ይቀደድልኛል፣ ቀደዳውንም
ቢራውንም እጋታለሁ። አጣጩ እንጂ የማድግ ልጁ አይደለሁምና በየቀኑ የሚግተኝ አልኮል ምን እንደሚጎትትብኝ
ግድ አልነበረውም።እንደባል የሚጫወተው ምንም ካለመኖሩ
የተነሳ ለማመን ምንም ታክል የማይቀረኝን ሀሜት ስለእርሱ
ሳድግ ሰምቻለሁ። እናቴን ያገባት ትሰራ ከነበረችበት ሽርሙጥናዋ አስትቷት እንደነበር እራሱም ሲያወራ ሰምቻለሁ።
ሆቴል ስትሰራ ደንበኛዋ ከነበረ ሰው ጋር በትገባኛለች ፀብ አክሱሙ ከጥቅም ውጪ መሆኑን ሲያሙት በተደጋጋሚ
ሰምቻለሁ። ለወጉ በዓመቱ መጀመሪያ እንድታስመዘግበኝ ተለማምጫት ወይም እርሱን ለምኜው ት/ቤት እገባለሁ።
ዓመቱን ሙሉ እመላለሳለሁ፡፡ ስንተኛ ክፍል እንደሆንኩ አያውቁም። እድሜዬንም ይዘነጉታል። የትምህርት ቤት ስሜን ሁሉ የማስታውሳቸው እኔ ነኝ። የአባቴ ስም የባሏ ስም ነው።

"የማንም ዲቃላ አባት አይደለሁም:: አባትህን ሄደህ ፈልግ::"ይለኛል ከሷ ጋር ሲጣላ፡፡ እኔ ለነሱ የለሁም
👍2
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ስድስት


#በሜሪ_ፈለቀ

ግፈኛዋ እናቴን መሰልሽኝ፡፡ ግን በተለየ ወደድኩሽ፡ ነው የምላት? እንኳን ለርሷ ለራሴ የተደበላለቀ ነገር አለው። ለርሷ
ላስረዳት ቀርቶ ለራሴም አልገባኝም፡፡ እኔም አልገባኝም። ስምሪት ለምን እናቴን አስታወሰችኝ? “ስምረት ሞተች የሚለው
የአርሴማ ጥሪ የፈጠረብኝ ድንጋጤ እንዴት ብሽቅ ለሆነው የአሁኑ ስሜቴ ጎታች ምክንያት ሆነ? በውል ያልለየሁት
ለስምሪት የተሰማኝ ስሜት በምን ስሌት ወደልጅነት ትዝታዬ አሽመጠጠኝ? አላውቅም!! ምናልባት እስከማስታውሰው ለሰው ግድ የሰጠኝ በዚህ ክስተት ስለሆነ? ምናልባት ሰው መሆን ለሰው ማሰብን ያካትት ይሆን? ምናልባት ሰው ሆኜ ይሆን? ምናልባት ሰው በሆንኩ ቅፅበት እንደሰው ግድ ሳይሰጡኝ
ያለፍኳቸውን ክስተቶች ማሰላሰል መጀመሬ ይሆን? አላውቅም!!
ብቻ ምንም ሽራፊ ስሜት አይሰጠኝም ያልኳቸው ስንጣቂ የኑሮ ሰበዞቼን ሳይቀር ሳልፈልግ እያሰብኳቸው ነው።

"እያስጨነቅኩህ ነው?" አለችኝ ስምሪት ደጋግማ የማልወዳትን እናቴን እና የተለየ ስሜት የፈጠረችብኝን ሴት ምን
እንዳመሳሰላቸው ስትጠይቀኝ ቆይታ።

"እናቴን እንደማልወዳት እርግጠኛ እየሆንኩ አይደለም።" መለስኩላት። በእርግጥ የሚሰማኝ የትኛው እንደሆነ
አልለየሁትም። አቅፋኝ ታለቅስ ለነበረችው እናቴ ይሁን ቁብ ለማትሰጠኝ እናቴ የማልለየው ሀዘን ይቦረቡረኛል፡፡ ደግሞ
ተመልሶ የሚያንገሸግሽ ንዴት እና ጥላቻ ይግተለተልብኛል፡፡
ስምሪት ፀጥ አለችኝ፡፡ ዓይኖቿን አጥብባ ስታየኝ ቆየችና።

"ለምን አታረጋግጥም?" አለችኝ፡፡

"ምኑን?"

"ለእናትህ የሚሰማህን ስሜት?"

"እንዴት? በምን?"

“ፈልጋቸዋ!! ፈልገህ አግኛቸው።"

“የት ብዬ? ትሙት? ትኑር? እንኳን ማወቅ
ይከብዳል፡፡ብዙ ዓመት አልፏል።" ይሄን ለሷ ስመልስላት ራሴን ሰማሁት።ጥያቄዬ ልፈልጋት? ወይስ አልፈልጋት? የሚለውን እርከን አልፏል። 'አልፈልጋትም'የሚለውን
ጭራሽ አለማሰቤ አስገረመኝ። እሷም ይህ የገባት መሰለኝ፡፡ ፈጠን ብላ።

"ራስህን ዝግጁ ካደረግክ ፍንጭ የምናጣ አይመስለኝም::" አለችኝ
ዝግጁነቴን ለማረጋገጥ ነው መሰል ከአፌ የሚወጣውን ቃል አፏን ከፍታ እየጠበቀች፡፡ ፀጥ አልኩ። ፀጥ አለችኝ፡፡ እያየኋት እንደሆነ ሲገባት ታቀረቅራለች፡፡ እያየችኝ እንደሆነ ሳውቅ ዓይኖቼን በሌላ አቅጣጫ አርቄ እልካቸዋለሁ።

"ስምሪት?"

"አቤት?"

“እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?" ራሷን በመነቅነቅ እንድቀጥል ተስማማችልኝ፡፡

"ለምንድነው ከሌላ ሰው በተለየ የምትቀርቢኝ? የምትሰሚኝ?
የምታወሪኝ?" የጠበቀችው ሌላ ጥያቄ እንደሆነ ሁሉ ፊቷ ረገበ።

ከአይምሮ ይልቅ ልብ ይማርከኛል፡፡" መልሷ እርግጠኛነት ነበረው፡፡

"ማለት?"

| “ከእውቀት ይልቅ ለቅንነት ዋጋ እሰጣለሁ ማለት ነዋ!! ቅንነት የሌለበት እውቀት በዜሮ ይባዛብኛል፡፡ቅንነት የሞላበት አለማወቅ እንኳን ይገዛኛል። ልብህ ቅን ነው::" ብላኝ ከኔ መልስ
እንደማትጠብቅ ተደላደለች። እሷ በገለፀችኝ ልክ ልበ ቅን መሆኔን እጠራጠራለሁ። ምክንያቱም ቅንነት ይመነዘራል ይመስለኛል፡፡ እኔ ስለራሴ እስከማውቀው ከራሴ ውጪ ለማንም
ግድ ኖሮኝ ለሰዎች ቀና ለማድረግም ሆነ ቀና ለማስብ ተጨንቄ አላውቅም። ማንም ጉዳዬ አይደለም።እሷ ሁሌም እንደዚህ ናት፡፡ ስለእኔ ስታወራ ባለቤቱ እርግጠኛ ከሆንኩት በላይ እርግጠኛ ናት፡፡ ምናልባት እኔ ራሴን ከማዳምጠው በላይ እሷ ስለምታዳምጠኝ ይሆናል። ሁሌም የምትጠቁመኝ ኪሩቤል መድረስ የሚችልበትን ጫፍ እንጂ ሰዎች ወይ እሷ መዳረሻ ብለው የሰቀሉትን ጫፍ አይደለም።

"ስምሪት?" ባልጠራትም እየሰማችኝ እንደሆነ አውቃለሁ።ከእስከዛሬው ሁሉ በተለየ እንድትሰማኝ ፈለግኩ፡፡

"አቤት?"

“ከዛን ቀን በኋላ አንቺን እንደአለቃዬ ወይም እንደጓደኛዬ ማሰብ እየቻልኩ አይደለም።" አልኳት። ከአፌ እስኪወጣ እየጠበቀችው ያለ ንግግር እንደሆነ ሁሉ መገረምም መደንገጥም ሳይታይባት

"አንድ እርምጃ ጠልቀህ ያወቅከኝ ስለመሰለህ ነው?" መልስ
የምትፈልግም አትመስልም።

“ማለት?" አልኳት ያለችው ሳይገባኝ ቀርቶ ሳይሆን የማስረዳት አቅም ከድቶኝ፡፡

"ኪሩ ልብሳቸውን ስትገፍ ያወቅካቸው እንደሚመስሉህ ሴቶች እርቃኔን ስላየኸኝ ገበናዬን የገለብክ አይምሰልህ፡፡"
የምታወራበት ቅላፄ የማላውቀውና ምሬት የተቀላቀለበት ነው፡፡ ምን
እንደምላት እና ለሷና ለማውቃቸው ሴቶች የሚሰማኝን የአንድ ጤፍ ፍሬና የተራራ ያህል የገዘፈ የስሜት ልዩነት ማስረዳት ባለመቻሌ ተናደድኩ።

"እንደዛ አይደለም የተሰማኝ። ውስጤ የቀረውን የገላሽን ምስል ሳስበው አብሬሽ መተኛት አይደለም የሚሰማኝ፡፡ ተሰምቶኝ በማያውቅ መልኩ ከወለሉ ላይ አንስቼሽ አልጋ ላይ ያደረስኩሽ ቅፅበት የእድሜ ዘመኔን ያህል ረዥም እንዲሆን ነው የሚሰማኝ፡፡ ክንዴ ላይ እንዳቀፍኩሽ የተከደኑ ዓይኖችሽን በስስት እያየሁ ዘመኖቼ ቢያልቁ ነው የተሰማኝ፡፡” ይግባት አይግባት እንጃ ከዚህ በላይ ማስረዳት ግን አቃተኝ፡፡ ደቂቃዎችን ትንፋሽ ያጠረኝ እስኪመስለኝ ፀጥ አለች፡፡
ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች "የለውጥ ኩርባ" አለችው።አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ፡ ወይ ድርጊቱ የሚቀየርባት።ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት፡፡ለውጥ ወደ ተሻለ ማደግ ብቻ አይደለምና ኩርባውን ሲታጠፍ
ውድቀትም ሊሆን ይችላል፡፡ ያቺ የለውጥ ኩርባ አንድ የሆነች ኢምንት ክስተት ልትሆን ትችላለች ወይም ዓረፍተ ነገር ወይም አንዲት ቃል ምናልባት አንዲት መሳም ወይም የአንዲት ደቂቃ
መታቀፍ ወይም...

የኔ የለውጥ ኩርባ ያቺ ቀን ነበረች።

"ልክ አይሆንም። እኔና አንተ ከዚህ ቀደም ከነበረን የዘለለ ግንኙነት ሊኖረን አይችልም::" አለችኝ፡፡

"ቅድም 'ከአእምሮ ይልቅ ልብ ይማርከኛል አልሺኝ አይደል?

" እህ... " የምቀጥለውን ለመስማት እየሰገገች።

"ሲገባኝ ሌላ ፍቺው ከስሌት ይልቅ ለስሜት ቅርብ ነኝ ማለትሽ መሰለኝ፡፡ ልክና ስህተቱን በስሌት ልቀምርልሽ አልችልም። ባንቺ ፍቅር ከመውደቅ በላይ ልክ የሆነ ስሜት ተሰምቶኝ እንደማያውቅ ግን ላረጋግጥልሽ፡፡" አልኳት አሁንም ምን ያህል እንተረዳችኝ ባይገባኝም።

"ምናልባት እስክጋደምልህ ይሆናል። ፍላጎትህ እስኪረግብ!"ከአፉ የሚወጣው ቃልም ድምፀትም የሷ አይመስልም:: ጥርሷን እያፏጨች ነው የተናገረችው። በመጀመሪያ ደነገጥኩ፡፡ ስምሪት
እንዲህ ስትናገር ሰምቼ አላውቅም:: በመቀጠል ተናደድኩ።በፍፁም እየተረዳችኝ አልነበረም።በመሰለስ ግን ስለዚህች ሴት የማላውቀው ብዙ ነገር መኖሩን ማሰብ ጀመርኩ፡፡

ስደነግጥ

ለኔ ሳይሆን ለእርሷ ማንነት የማይመጥናት የመሰሉኝን ቃላቶች
በማውራቷ ዓይኖቼን ጎልጎዬ አፈጠጥኩባት።

ስናደድ

“እየገባሁሽ አይደለም።ስለሴክስ እያወራሁ አይደለም። እዚህ ጋር(ልቤን በእጄ ደግፌ) ስለሚሰማኝ ስሜት ነው እየነገርኩሽ የነበረው።" አልኳት በአፏ አልመለሰችልኝም:: ፊቷ ግን ስልችት
አሳየኝ፡፡

ማሰብ ስጀምር

"ማነው?" አልኳት

“ማን?" መለሰችልኝ

እንዲህ እንዲሰማሽ ያደረገሽ?" በረዥሙ ተንፍሳ ፀጥ አለች።


💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ሰባት


#በሜሪ_ፈለቀ

"እንዲህ እንዲሰማሽ ያደረገሽ?"በረዥሙ ተንፍሳ ፀጥ አለች።

"ድብቅ ነሽ።" አልኳት።

"ድብቅ እንኳን አይደለሁም::"

መለሰችልኝ፡፡

"እኔ የማልነግርሽ ክስተትም ስሜትም ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ስላንቺ
አንዲትም ነገር አውርተሽ አታውቂም።"

"ጠይቀኸኝ አታውቅም፡፡ ለራሴ ቦታ አለኝ፡፡ ዋጋ የሌለኝ ሰው ጋ ራሴን የምጥል ርካሽ አይደለሁም::" ያለችው በትክክል ገብቶኝ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበርኩም።

"አቤት? ዋጋ ባልሰጥሽ ኖሮ ስለራሴስ አወራሽ ነበር?"

"ዋጋ ስለሰጠኸኝ ሳይሆን ዋጋ ስለሰጠሁህ ነው ያወራኸኝ፡፡
ከሴቶችህ ብዙዎቹ ስለራሳቸው ነግረውናል፡፡ አንተ ግን ስለራስህ
ለአንዳቸውም ነግረህ አታውቅም። ለምን ይመስልሃል?ልትሰማቸው እንጂ ሊሰሙህ ጊዜያቸውንም ልባቸውንም አልሰጡህም። ወይም እንደዛ አስበሃል።" ከተናገረችው ሁሉ የገባኝ(ቃል በቃል ባትለውም) ልቤን ሰጥቼሃለሁ' ያለችው ነው።

"አሁን ልሰማሽ ዝግጁ ነኝ፡፡ ንገሪኝ! "

"አሁን ሰዓት ሄዷል። ወደ ቢሮ እንመለስ!" አለች በዓይኗ አስተናጋጅ እየፈለገች። ፍቅር የብዙ ነገር ቁልፍ መሆኑ ገባኝ
መሰለኝ፡፡ አስቤ ስለማላውቃቸው ብዙ ነገሮች ማሰብ ጀመርኩ፡፡
ከመለዮዬ ውጪ ምን ስለመልበስ አስቤ የማላውቀው ሰው ራሴን ልብሶች ስሸምት አገኘሁት።ያንተ ተክለ ሰውነት ልብስ ያስጌጣል እንጂ አንተን ልብሱ አያስጌጥህም፡፡ ለምትለብሰው መጠንቀቅ አይጠበቅብህም።"ብላኛለች ስምሪት ከመለዮዬ ሌላ ለብሼ ያየችኝ የመጀመሪያ ቀን፡፡

“ለምን እራቁቴን አታዪኝም?"

"አትባልግ እንግዲህ!"

በሌላ ቀን ለአንዲትም ቀን አስቤው የማላውቀውን ራሴን ቤተክርስቲያን ስፀልይ አገኘሁት፡፡ (በእርግጥ ከፀሎት ይልቅ ለንግግር የቀረበ ነገር ነበር) ፍቅር የሁሉ ነገር ቁልፍ መሆኑ መሰለኝ፡፡ የሁሉንም የህይወት ጥጎች ማጠንጠን ጀመርኩ።እስካሁን አንድ የሆነ ቦታ ላይ የሆነ እድሜዬ ላይ ቆሜ የነበር አይነት ስሜት ነበር የሚሰማኝ፡፡ ገና አሁን በስምሪት ፍቅር መኖርን የጀመርኩ፡፡ በገፋችኝ መጠን ወደርሷ የሚስበኝ ፍቅሯ
ልቤን ከብዶት ይጎትተኝ ጀመረ።ቀናቶች የንስር ክንፍ አውጥተው ይበራሉ እሷ በቻለችው መጠን ትሸሸኛለች እኔ ደግሞ ከምችለው በላይ ወደርሷ እወነጨፋለሁ። የምንገናኝባቸውን እና ልናወራ የምንችልባቸውን አጋጣሚዎች
ትዘጋቸዋለች።

ከነገ ጀምሮ እረፍት ወጣለሁ::" አለችኝ የሆነ ቀን የቀኑ ስራ ማብቂያ ሰዓት ላይ እየወጣን።

"ለምን? ሽሽት ነው?" አልኳት።

የምን ሽሽት? ማረፍ ፈልጌ ነው።" አለችኝ ዓይኖቼን እየሸሸች።ቆምኩኝ ቆመች አየኋት አቀረቀረች የጡቷቿ ጫፎች ደረቴን እስኪነኩት ተጠጋኋት። አልሸሸችኝም።ምንም እንቅስቃሴ አላደረገችም፡፡ ወደ ጆሮዋ ከንፈሮቼን አስጠግቼ “ታውቂያለሽ? ሁሌም አንድ እርምጃ ወደፊት የማያራምደን
የ'ባይሳካስ?” ፍርሃት ነው። እመኚኝ!! እመኚኝና ልብሽን ስጪኝ። አንድ ነገር ቃል እገባልሻለሁ። ልብሽን አልሰብርም
አልኳት። ዓይኗን ገርበብ አድርጋ ነበር የሰማችኝ ከመግለጧ በፊት አየኋት፡፡ ዓይኔ ከንፈሯ ላይ ቀረ። ውጤቱን ማሰብ
አልፈለግኩም።ወይም ምንም ቢሆን ግድ አልነበረኝም።
ከንፈሮቿን ሳምኳቸው። ለምን ያህል ሰከንድ እንደሆነ ባላውቅም
መልሳ ስማኛለች፡፡ እጇ በወገቤ ዙሪያ አልፏል። ይሄን ያሰብኩት ድንገት አቁማ ገፍታኝ ስትቆም እንጂ ስትስመኝ
ከጥፍጥናዋ ውጪ ማወቅ የቻልኩት ነገር አልነበረም።

“ኪሩ? ምንድነው የምታደርገው?" ጮኸችብኝ፡፡ ፈገግ አልኩ። ልቧን ስትሰማው ስማኛለች፡፡ መንገድ ላይ መሆናችን እንኳን አላሳሰባትም ነበር፡፡ አዕምሮዋን ስትሰማው ነው የገፋችኝ።
ባትነግረኝም የማትክደው ስሜት አላት። ፈገግታዬ አበሳጫት። ተናደደች።

"ኪሩ ሁለተኛ እንዲህ ብታደርግ እንጣላለን። የምሬን ነው!!"
አለች ድርጊቴ እንዳናደዳት ለመግለፅ እየጣረች።

"እሺ፡፡ ከዛሬ በኋላ ራስሽ ካልጠየቅሽኝ አላደርገውም::"

"ማለት?"

ኪሩቤል ሳመኝ ብለሽ አፍ አውጥተሽ ካልጠየቅሽኝ አልስምሽም።" አልኳት።

ወገኛ! ኪሩ እኔ አንተ እንደምታውቃቸው አይነት ሴቶች አይደለሁም።" አለች መንገድ እየጀመረች።

"አውቃለሁ!! ከነሱ የሚለይሽ ነገር ባይኖር ከነሱ የተለየ ስሜት
አትሰጪኝም ነበር።" መለስኩላት እርምጃዬን ከርሷ ጋር እያመጣጠንኩ።
'ለምን እኔን? ለምን? ደግሞስ ለምን አሁን? አንተ ማንም ሴት የምትደነግጥልህ ወንድ ነህ!"

"ማንም ሴት ደንግጣልኝ ይሆናል፡፡ ካንቺ ውጪ ያስደነገጠችኝ ሴት የለችም ለውጡ እንዴት አይታይሽም?" አልኳት።

ተለይታኝ ሄደችበልቤ። ተሸክሜያት ወደ ሱሴ ሄድኩ። በቀኖችህ ውስጥ ለምታደርገው ትግል ጥያቄው መሸነፍህ አይደለም።መዋጋትህ እንጂ ምክንያቱም ሳትታገል ሁሌም ውጤቱ የታወቀ ነው። ተሸናፊ ነህ። በትግልህ ውስጥ ውጤቱ ከሁለት አንዱ ነው። ማሸነፍ ወይም መሸነፍ!! ጥያቄው መዋጋትህ ላይሆን ይችላል የተዋጋህለት አላማ እንጂ። እሷ ናት። ምንንም ባልፍላት የሚገባት። እረፍት መውጣቷን ተከትሎ ናፍቆቷን መታገስ ከምችለው በላይ ነበረ። ስልኳ እረፍት ከወጣችበት ቀን ጀምሮ ዝግ ነው።ጭንቅላቴ የሚፈነዳ መሰለኝ፡፡
እቤቷ ላለመሄድ ከቁጥር በላይ ለሆነ ጊዜ አመነታሁኝ።
በስምንተኛው ቀን እሷን ሳላያት ባድር ትንፋሼ ቆሞ የማድር መሰለኝ።ከስራ ወጥቼ እቤቷ ሄድኩ:: በሩን ስትከፍትልኝ ምን እንደምላት፣ምን ለብሳ እንደማገኛት፣ ስታየኝ ምን እንደሚሰማት እያሰብኩ በሩን በስሱ ቆረቆርኩ ደገምኩት።ጨዋታ አቋርጦ እንደከፈተልኝ የሚያስታውቅ ሰው ያላለቀ ሳቁን እየቀጠለ በሩን ከፈተልኝ።

"አቤት?" አለኝ።

ሰምቼዋለሁ ዝም አልኩ፡፡ ደገመልኝ፡፡ ዝምታዬን ደገምኩለት።ስምሪት ከጀርባው ብቅ አለች። ምንም አይነት የፊት ሜክአፕ
ስትጠቀም አይቻት አላውቅም።ተቀባብታ ሌላ ሴት መስላለች፡፡ከከንፈሯ ውጪ ያልደመቀ የለም:: ለፓንትነት የቀረበ ቁምጣ እና ለጡት ማስያዣነት የቀረበ ሹራብ ለብሳለች። ፀጉሯ ቢመሳቀልም ተለቋል።እሱን አየሁት።በሲሊፐር ነው።
እንግድነት አይታይበትም።የከንፈሩ ጠርዝ ላይ አስተዋልኩ። ስምሪት ያስደነገጣት የኔ መምጣት ይሆን ወይም የመጣሁበት ሰዓት አላውቅም ደንግጣለች፡፡

"እንዴ? ኪሩቤል?" እየተንተባተበች ጨበጠችኝ፡፡

ሰውየው ለኔ ማሳወቅ የፈለገው ነገር ያለ መሰለኝ አቅፎ ወደ ራሱ አስጠግቶ ፀጉሯን ሳማት፡፡ እሷ በድርጊቱ ያፈረች መሰለኝ ዓይኔን ሸሸችው።

"ማሬ የስራ ባልደረባዬ ነው።" አለች ለሰውየው።ለኔ ደግሞ "የአርሴማ አባት ነው::" ተጨባበጥን።

“ኦው ፖሊስ ነህ? የሆሊውድ አክተር ነበር የመሰልከኝ፡፡ ሃሃሃ" ሰውየው መቀለዱ ነው።በቡጢ ዱልዱም አፍንጫውን ባጠፋለት ደስ እንደሚለኝ ቢያውቅ፡፡ በዚህ መሃል አርሴማ ዓይኗን እያሻሸች በአባቷና በእናቷ እግር መሃል ብቅ አለች። ስታየኝ ፈገግ ማለቷ ያስታወሰችኝ ስለመሰለኝ ደስ አለኝ። ልስማት
ስጠጋት ግን ሸሸችኝ፡፡

“ይቅርታ በማይሆን ሰዓት መጣሁ መሰለኝ። የስራ ጉዳይ እቤት ድረስ ይዤ መምጣት አልነበረብኝም::" መናገር ስለነበረብኝ አልኩኝ እንጂ እግሬ ከመሬቱ ጋር ያዛመደው ነገር ያለ ይመስል
አልተንቀሳቀስኩም።ሰውየው እንድገባ ጋበዘኝ፡፡ ለአፉ እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ተሰናብቻቸው እግሬን ከተተከለበት አንቀሳቅሼ በመጣሁበት አቅጣጫ መራሁት። አለመታደል ነው #ቀላውጦ_ማስመለስ ትል ነበር እናቴ፡፡ የምፈልገው ስለርሷ አለማስብ ነው። የማደርገው ግን ተቃራኒውን ነው
የጠራችው ሰውየው የስራ ባልደረባዋ መሆኔን እንዲያምናት ብቻ ነው? ድምፅዋ ውስጥ ለምን ፍርሃት ሰማሁ? ለምን ባለቤቴ ነው አላለችኝም የዛን
እለት አርሴማ
👍2
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ስምንት


#በሜሪ_ፈለቀ

ፊቷ አብጧል። የጣት አሻራ ፊቷን ወርሶታል። የላይኛው ከንፈሯ
በአንድ በኩል አብጧል። ከሰዓታት በፊት ያየኋት ውብ ሴት መሆኗን ያስጠረጥራል።

"እሱ ነው?" አልኳት አገኘው ይመስል እጄን ለጡጫ ጨብጬ።በጭንቅላቷ ንቅናቄ አዎን አለችኝ፡፡ ምን ማለት ወይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ፡፡ አቀፍኳት፡፡ ጣቶቿ ላይ ያለውን ብልዝ አይቼ ከጥፊ የዘለለ እንደደበደባት ገባኝ፡፡ እንዳለችኝ አርሴማ አልተኛችም። ጭራሽም እቤት የለችም፡፡ ይዟት
እንደሄደ ነገረችኝ፡፡ የደበደባት እኔ በመምጣቴ ምክንያት መሆኑን
ስትነግረኝ በቁሜ እግሬ ብርክ ያዘው። ምንም ቃል ሳልተነፍስ በሯን ዘግተን ወዳቆምኩት ታክሲ ይዣት ሄድኩ። ምንም ሳንነጋገር አንገቴ ስር እንደተሸጎጠች እቤት ደረስን።ስለሰውየው ልታስረዳኝ መናገር ጀመረች:: በሁኔታዋ ቁስሏን ማባስ መሰለኝ፡፡

"አሁን ምንም መስማት አልፈልግም። ምንም ለኔ ማስረዳት አይጠበቅብሽም። እረዳሻለሁ::" ብያት ትከሻዋን ነካ ሳደርጋት አመማት።

"እዚህጋም መቶሻል?" አልኳት ከልቤ እየተናደድኩ፡፡

"ሰውነቴ እንዳለ ቁስል ነው:: የተረፈ ቦታ የለኝም::" እየተናገረች እኩል አብጦ ሊጨፈን ከደረሰ ዓይኗ እንባዋ ይወርዳል፡፡

"የተለመደ ነው::" አለች ቀጥላ፡፡

አንዳንዴ ፊቷ ላይ ብልዝ አይቼ እንደማውቅ አስታወስኩ፡፡ሁሌም ሰበቧ ወድቃ እንደነበር ነው። ከመተኛቷ በፊት ሰውነቷን ዘና እንዲያደርግላት የሞቀ ውሃ በርዤ አሰናዳሁላት።

“ውሃ አሙቄልሻለሁ።ገላሽን ልጠብሽና የሚበላ ነገር ትቀምሻለሽ።"

"ምንም አልበላም።" መለሰችልኝ። ገላዋን የማጠቤን ሀሳብ እንዳልሰማ ማለፏ ተቃውሞ እንደሌለበት ወስጄው በቀስታ
የለበሰችውን ሹራብ አወለቅኩት፡፡ የጡት ማስያዣ አላሰረችም።ሰውነቷ በላልዟል። የቀበቶ ግርፋት መሆኑን ብጠረጥርም
እንባዋን እንዳላገረሽባት በመስጋቴ ልጠይቃት አልፈለግኩም።

“አሁን እኔጋ ነሽ!! ነፃ ሁኚ!" አልኳት ስትሳቀቅ ስላስተዋልኩ.ልብሷን በሙሉ ስገፈው ሰውነቷ በሙሉ በሰንበር
ተዥጎርጉሯል፡፡ ተጠንቅቄ ገላዋን አጠብኳት፡፡ ለማንም አዝኜ በማላውቀው ልክ አዘንኩላት። እንደምትሰበር ጌጥ አሳሳችኝ።እርቃኗን የአልጋውን ልብስ ገልጬ እንዳስተኛኋት ክንዴ ላይ
እንቅልፍ ወሰዳት:: ባይነጋ፣ ከእንቅልፏ ባትነቃ፣ እንደ ህፃን ክንዴ ላይ እንደተኛች ብናረጅ ፣ የሚያሳሳ ገላዋን እንዳቀፍኩ
የዓለም ፍፃሜ ቢሆን......

በጀርባዬ ተኝቼ አላውቅም።በደረቴ ካልተኛሁ እንቅልፍ አይወስደኝም። ዛሬ እንቅልፍ ስለመተኛት አይደለም ግዴ ዓይኔን ብከድን ስነቃ አጠገቤ የማጣት ነው የመሰለኝ፡፡ፒጃማ ለብሼ ተኝቼ አላውቅም። ይጨንቀኛል። ዛሬ እሷ ምቾት እንድታጣ አልፈለግኩም። እቤቴ ማንም ሴት መጥታ አታውቅም፡፡ ዛሬ
ስምሪትን አቅፊያት ለወትሮዬ ሰያፍ የምሰመርበት አልጋዬ ላይ አብሪያት ተኝቻለሁ። ይሄንን ሁሉ ብታውቅ? እየጠበቅኳት እንደሆነ ነቅታ ብታይ? አሰብኩት። ወዲያው እንዲህ አሰብኩ የሚሰማኝን ስሜት ነው የማደርገው ወይስ እሷን ለማማለል? ሳስበው አብዛኛዎቻችን እኮ ግብዝ ነን፡፡ ለሚሰማን እውነተኛ ስሜት ሳይሆን ሰዎች ለሚሰጡን የውደሳ ምላሽ ቃርሚያ
እናጎበድዳለን፡፡ ጥሩ ስናደርግ እንኳን ግብዝ ነን። ደግ ለመሆን ከምናደርግ ይልቅ በሌሎች ዘንድ ደግ ለመባል ነው ደግነት የምናሳየው ለቅድስና ደግ ከመሆን ይልቅ ለእውቅና ደግ
እንሆናለን። ሀምሳ ብር ስንቸር ቢያንስ ያደረግንላት ሰው እውቅና እንዲቸረን እንፈልጋለን፡፡ አምስት መቶ ሺህ ብር
ስንሰጥ በሬዲዮ እና በቴሌቭዥን እንዲነገርልን እናደርጋለን፡፡አነሰም በዛም ደግነታችን ዓይንና ልብ እንዲስብ እንፈልጋለን፡፡ያደረግኩት ይሄንን መሰለኝ፡፡ ቢያንስ የሚሰማኝን ስሜት እንድታውቅልኝ መመኘት። ተወራጨች። እየቃዠች እንደሆነ ገብቶኛል፡፡ አጥብቄ አቀፍኳት።

"እሽሽ... ... " አልኳት እንደ ህፃን ልጅ። እያማተበች ተነሳች።

"እኔጋ ነሽ!! አለሁ!" አልኳት አልመለሰችልኝም።ሙቀት
እንደሚፈልግ ህፃን ተጣበቀችብኝ፡፡ በእግሮቿ ጭኖቼን ፈልፍላ እግሮቿን እግሮቼ መሃል አስገባቻቸው፣ ጭንቅላቷን አንገቴ ስር ሸጉጣ ከአልጋው ይልቅ ከግማሽ በላይ ሰውነቷ እኔ ላይ
ተኛች። በሁለቱም እጆቼና በሁለቱም እግሮቼ ወደ ራሴ አስጠግቼ አቀፍኳት፡፡ ደስ አለኝ። ለወትሮው እንዲህ መንሰፍሰፍ
የወንድ ልጅ ስሜት አይመስለኝም ነበር፡፡ ለዛሬ እንዳመነችኝ አይደለም የተሰማኝ፡፡ ለሁሌውም ጠብቀኝ ያለችኝ ነው የመሰለኝ እንዴትና ከምን እንደምጠብቃት አላውቅም፡፡በፍፁም እንድትጎዳ እንደማላደርጋት ግን ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ ብዙም ሳትቆይ እንደገና እንቅልፍ ወሰዳት።ከሚደበድባት ሰውጋ
ለምንድነው የምትሆነው? በምንም መልኩ ለማስቆም አቅሙ አላት፡፡ ለምን?

"አንዳንድ ሰዎች አብሮነታቸው ከሚጠቅምህ ይልቅ ይጎዳሃል።
እየጎዱህም ግን ልታጣቸው አትፈልግም።" ትል ነበር እናቴ ብዙ
ጊዜ። እሷ ማውራት የፈለገችው ስለ ባሏ መሆኑን አውቃለሁ።ስምሪት ስለእናቴ ያለችውን አሰብኩ። የት ልትሆን ትችላለች? ምናልባት ገዳም ገብታ? ምናልባት ሌላ ባል አግብታ ሌሎች
ልጆች ወልዳ? ማን ያውቃል ምናልባትም አሁንም ሀብታሞች የሚዝናኑበት ሆቴል እየሸረሞጠች? የነበራትን ገንዘብ ሰጥታኝ፣ቤቷን ጥላልኝ የት ልትሄድ ትችላለች? ምናልባት ራሷን አጥፍታ ቢሆንስ? አንዴ ስለእናቴ መልሼ ደግሞ ስለ ስምሪት ስፈትል ስቋጭ ሽልብ እንዳደረገኝ ነጋ፡፡ ያንን ሁሉ ሰዓት
አለማጨስ የኑሮ ያህል ትግል ነበረው። መንቃቷን አውቃለሁ።መንቃቴን አውቃለች፡፡ ጀርባዬጋ ዞሮ ባቀፈኝ እጇ ጣቶች በቀስታ ትነካኛለች።

"በልጅነቴ ነው ያገባሁት::"አለችኝ ሳትንቀሳቀስ። ወዲያው ግን
ከአንገቴ ዝቅ ብሎ እንባዋ ረጠበኝ፡፡

"የማታለቅሺ ከሆነ ብቻ ነው መስማት የምፈልገው:: ካለዚያ አልፈልግም። እንባሽን ማየት አልችልም::" አልኳት ቀና ብዬ እያየኋት፡፡ የፊቷ እብጠት ጠፍቶ ብልዘቱ ብቻ ቀርቷል፡፡በጭንቅላቷ እንደማታለቅስ ነግራኝ ተመልሳ ደረቴ ላይ
ተጋደመች እና ማውራት ጀመረች። ማውራት ከመጀመሯ በፊት የሆነ አስማት ነገር ሰርታለች:: ደረቴን ሳመችኝ። ስታወራልኝ ቅደም ተከተሉን አልጠበቀችም። አልረበሽኳትም። ብስጭት፣ፀፀት፣ አልፎ አልፎ እንባ እየተፈራረቁባት በስሜት ነው
የምታወራኝ። ፀጉሯን በጣቶቼ እያበጠርኩ ስሰማት የገባኝ ይሄ
ነው።

ያገባችው ሰው ቤተሰብና የሷ ቤተሰቦች በገንዘብ የተጣሉ ፀበኞች
ናቸው:: እርሷ የቤተሰቦቿ ብቸኛ ልጅና ተስፋቸው ነበረች።ቤተሰቦቿ ከጠላታቸው ልጅ ጋር ፍቅር መጀመሯን ሲያውቁ
ከፍቅሯና ከቤተሰቧ እንድትመርጥ ምርጫ ሰጧት። ቆይቶ ስታውቀው የእርሱ ቤተሰቦች ፀበኛቸው
ከማጣታቸው ይልቅ ልጃቸውን ማጣታቸው እንደሚጎዳቸው ያውቁ ስለነበር ልጃቸውን ይደግፉት ነበር። ፍቅሯን መርጣ ከቤቷ ስትወጣ ደግሰው ተቀበሏት። አባቷ ምን ያህል ቆራጥ
መሆናቸውን ብታውቅም እስከመጨረሻው ይከፉብኛል ብላ
አላሰበችም ነበርና በጊዜው ላፈቀረችው ሰው ቤተሰቧን ማጣቷ በጊዜው ላፈቀረችው ሰው ቤተሰቧን ማጣቷ
የሚገባው የመሰላት መስዋዕትነት ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በሜሪ_ፈለቀ

መሆናቸውን ብታውቅም እስከመጨረሻው ይከፉብኛል ብላ
አላሰበችም ነበርና በጊዜው ላፈቀረችው ሰው ቤተሰቧን ማጣቷ የሚገባው የመሰላት መስዋዕትነት ነበር። ሁሉም ሰላም እና ውብ ነበር። እየቆየ የባሏ ባህሪ መቀየር ጀመረ:: እሷ መርማሪ ፖሊስ
መሆኗን ተከትሎ ቤቷ ብጥብጥ ወረሰው።ዘግይቶ ሲገባት በብዙ
ህገወጥ ንግዶች ላይ እጁ እንዳለበት ጠረጠረች፡፡ ቢሆንም በቂ መረጃ የላትም
ቢሆንም ታፈቅረዋለች፡፡ቢሆንም ካለ እርሱ አንካሳ ናትና በየእለቱ እንደምትበረታባቸው ወንጀለኞች መረጃ
ለማግኘት አልታተረችም።በዚህ ትርምስ ውስጥ አርሴማ መጣች፡፡በመጀመሪያ የአርሴማ መወለድ ነገሮችን ያበረደ
መሰለ። ውጪ ማደሩን ተወ። መደብደቡን አቆመ።ድጋሚ የምታልመው ጥሩ ትዳር ኖራት። አርሴማ እያደገች ጤነኛ
አለመሆኗን ሲያውቅ ከበፊቱ በባሰ ከፋ፡፡

"እሺ እኔ ምን ማድረግ ነበረብኝ? እኔ እግዚአብሄር ነኝ? ልጄ ጤነኛ ብትሆን እኔስ ደስተኛ አልነበርኩም? ምን ማድረግ እችል ነበር?" አለችኝ ቀና ብላ፡፡
አርሴማ ከፍ ስትል ጭራሽ ከቤቱም ወጣ፡፡ በሁለት ሳምንት አንዴ (ትናንት እንዳደረገው) አርብ ከሰዓት መጥቶ አርሴማን ቤተሰቦቹጋ ይዟት ይሄዳል። ለልጁ የሚያስፈልገውን እሱም ሆነ
ቤተሰቡ ከማድረግ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እሷን ከወንድ ጋር ታየሽ፣ ለልጄ መልካም አርአያ እየሆንሽ አይደለም እያለ
መቆጣጠሩን አለፍ ሲልም ትላንት እንዳደረገው መደብደቡን ቀጠለ። ምንም ማድረግ እንዳትችል አርሴማ አበሰረቻት። አርሴማ አባቷን ስታይ ፈንጠዝያ የሚቀሙት አይደለም። እሱ ሄዶ
ከትምህርት ቤት ያመጣት ቀን ስትጫወት ታመሻለች።

ልጄ ጤነኛ ብትሆን እና እንደ ጤነኛ ልጅ በሌላ የምትደሰት ብትሆን እሺ!
እንዴት አንድ የሳቋን ምክንያት
አሁንም ድረስ፡፡ ከእርሱ ጋር የነበራትን ህይወት ከመመለስ ልንጠቃት? ታውቃለህ? ሲደበድበኝ እያየች
አትጠላውም፡፡ አትፈራውም፡፡ እስሩ ገብታ ነው የምትሄደው።አለች ጥልቅ መከፋት ባለው ድምፅ፡፡

ለዓመታት እንዲመለስላት የምትችለውን ስታደርግ ኖራለች።አሁንም ድረስ።ከእርሱ ጋር የነበራትን ህይወት ከመመለስ ውጪ ሌላ አማራጭ አታስብም።

"ዛሬ ወደ ቤት የምትመለሺበት ምክንያት የለሽም።አብረን እንዋል!! ማታ እራት ልጋብዝሽ!" አልኳት ካለችበት ድብርት
እንድትወጣ፡፡ አልመለሰችልኝም፡፡ ቀና ብላ እያየችኝ "የእናትህን ጉዳይ ዛሬ እንድናጣራ አስቤ ነበር፡፡" አለችኝ ድምፅዋ ውስጥ ደስ የማይል ጥርጣሬ አደመጥኩ። አመነታሁ። ለማወቅ ጉጉት
አድሮብኛል። ለዛሬ ግን ከዚህ በላይ አሳዛኝ ነገር ለመስማት ዝግጁ አልነበርኩም።

"ነገ እናድርገው።ነገ ጠዋት። አሁን ምንም መስማት አልፈልግም። አሁን ስትስቂ ማየት ብቻ ነው የምፈልገው::"
አልኳት:: በምንቸገረኝ ትከሻዋን ሰበቀች። የገጠማትን ረስታ ከኔጋር መሆኗን ብቻ እንድታጣጥም ስጣጣር ዋልኩኝ። ቁርስ
ሰርቼ አበላኋት:: ተመልሰን ተኛን። ማታ ስላልተኛሁ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ስነቃ አጠገቤ ሳጣት ጮኬ ተጣራሁ።ምሳ እየሰራች ነበር፡፡ ገብቷታል:ፈ። ሆዷን ይዛ ሳቀችብኝ፡፡ መቃም እንደምፈልግ
ስነግራት ቡና እንደምታፈላልኝ ነገረችኝ፡፡ በየመሃሉ ጭልጥ ትልብኛለች።ሊመሻሽ ገደማ ወጥተን ቀሚስ እና ጫማ
ገዛሁላት፡፡ ለእራት ልንወጣ ቀሚሷን ላብሳ ተኳኩላ ብቅ አለች።ዝም አልኳት።

"አላማረብኝም? እ?" አለችኝ፡፡

"ምንም ተጨማሪ ነገር ሳትጠቀሚ እኮ ውብ ነሽ!" መለስኩላት።

እሱ ግን ሳልኳኳል አስጠላዋለሁ።" አለችኝ ከንፈሯን ወደ አንድ ጎን አጣማ (ቁሌታም ሴት ይወዳል ብላኝ ነበር ጠዋት ስታወራኝ። የወሲብ ፊልሞች ላይ እንደሚታዩት ሴቶች እንድትለብስለት እና የእነርሱን እንቅስቃሴ እንድትኮርጅለት
( እንደሚያደርጋት አክላልኝ ነበር፡፡)

"አሁን ለእኔ ብለሽ ነው የተቀባሽው? ለእኔ ብለሽ ከሆነ አጥፊው
ምክንያቱም እንደዛ ቆንጅዬ ነሽ! ለራስሽ ብለሽ ካደረግሽው ተይው::" ስላት አመነታች፡፡ ከዛም አጠፋችው።

እራት እየበላን እሷ ወይን እኔ ቢራ እየጠጣን እንዲህ ከወጣች
ዓመታት መቆጠራቸውን ከእንባዋ እየታገለች ነገረችኝ። ሁለት ብርጭቆ እንደጠጣች ሞቅ አላት።

"ታውቃለህ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም። ትክክል መሆኑንም እንጃ!" አለችኝ እቤት እንደገባን፡፡

"ምኑ?"

"የሚሰማኝ ስሜት"

"ምንድነው የሚሰማሽ?" ከአፏ የሚወጣው ዓረፍተ ነገር ምንም ቢሆን እኔ ጆሮጋ ሲደርስ “ላንተ ፍቅር የሚል ቢሆን እየተመኘሁ።

“በደለኝነት፣ ኀጢአተኝነት፣ ጥፋተኝነት፣ ከዳተኝነት፣ ክምር ወቀሳ!” ጭንቅላቷን ይዛ ጫማዋን እያንቋቋች ተረማመደች።
ልቤን ሲበርደው ታወቀኝ፡፡

“ለምን? በምን ምክንያት?” የራሴ የማይመስል ድምፅ ነው ያወጣሁት፡፡ እግሬም የዛለብኝ መሰለኝ እና ተቀመጥኩ።

"ታውቃለህ? ድሮ ድሮ የዛሬ ስምንት ዓመት በድብቅ ፍቅር እንደጀመርን አንድ ቀን ከሰፈር አርቆ ይዞኝ ሄደ፡፡ ሁለታችንም
ህይወት እንደምናያቸው የፍቅር ፊልሞች መጨረሻቸው ግጥምጥም ግጥምጥም ብሎ በደስታ ለዘለዓለም ኖሩ የሚሆን
የሚመስለን ወቅት ነበር፡፡ (የወቅቱን ስሜት በትዝታ ልጓም ጎትታ እንደመቦረቅ እያለች) የሆነ ህንድ ፊልም ላይ እንዳየው
የእኔንም የሱንም የግራ እጅ የቀለበት ጣታችንን ጫፍ በምላጭ ቆርጠን አደማነው።ያስቃል አይደል? የሆነ የጅል ቀልድ ነገር ይመስላል? ግን አያስቅም እሺ! የሁለታችንንም የደሙ ጣቶች
አጋጥመን ቃል ገባልኝ፡፡ ቃል ገባሁለት።እሱ የገባልኝን ቃል
የኖረው ሁለት ዓመታት ብቻ ነው:: እኔ እያንዳንዷ ቃሌን ለመጠበቅ ስምንት ዓመታቴ ተቀርጥፈው ተስሉ፡፡ ለሱ ብዬ
ሁሉንም ተውኩ፡፡ ለማንም ወንድ ልቤንም አካሌንም አስደፍሬ
አላውቅም። እስከ ህይወቴ ፍፃሜ በልቤ ከርሱ ሌላ ላይነግስ ምዬለታለኋ? ምን እንደሚሰማኝ ታውቃለህ? ደሙ በደሜ
ውስጥ ያለ (ትኩረቴን ላለማጣቷ እያረጋገጠች) እውነታው
ባይገጣጠምም እኔ ግን እዛው የዛሬ ስምንት ዓመት ላይ ነኝ።"ማውራቷን አቋርጣ ማልቀስ ጀመረች።ሞቅታውም እያገዛት መሆኑ ገብቶኛል።

"ታውቃለህ አይገባህም! እኔን ስትሆን ብቻ ነው የሚገባህ!" አለችኝ፡፡ ፀጥ ብዬ እየሰማኋት ሀሳቤን ከማቡካት ውጪ ምርጫ አልሰጠችኝም።እውነቷን ነው:: አንዳንዴ ከምክንያታዊነት የሚልቅ ስሜት እንዳለ አሰብኩ። በቦታው ስትገኝ ብቻ የሚገባህ! ሲስማህ ብቻ የምታውቀው። እሷ ዓለሟ ትዳሯ ነው። ዓለም ቤቷ ነው። ዓለሟ ልጇ ናት:: ዓለምን እንደማሸነፍ የላቀ ምን ሀሴት አለ? ምንስ ስኬት ይኖራል? ትዳሯን እንደገና ማሸነፍ
እንደገና በሱ ልብ መንገስ፣ ለልጇ የምትወደውን አባቷን መመለስ፣ ዓለሟን የራሷ ማድረግ ነው ምኞትና ልፋቷ!

ሲመስለኝ ያልተረዳችው ነገር አብዛኛው ወንድ ወደድኩሽ ሲል ሊያስመስል ይችላል፡፡ ጠላሁሽ ካለ በቃ ማለቱ እንደሆነ አልገባትም። አርሴማን ሊወስድ ሲመጣ እግረ መንገዱን አብሯት መተኛቱ ከፍቅር ጋር ተዳቅሎባታል። የነሳትን ክብር ጋርዶባታል ፍቅሩን ያልጨረሰ እየመሰላት ልትጨምርለት ትዳክራለች።

“አንዳንዴ እንዲጠላኝ ያደረገው ፖሊስ መሆኔ ነው ብዬ አስብና ራሴን እወቅሳለሁ፡፡ ምናለ እሱ እንደሚፈልገው የቤት እመቤት ብሆን? እላለሁ! ልጄ በየቀኑ የምታየው አባት ይኖራት ነበር::"
ለንፅፅር የምታቀርበው ነገር ሲኖርህ ነው የተሻለ እና የባስ ብለህ ደረጃ የምታወጣው። እሷ ከእርሱ ውጪ የምታውቀው የላትም፡፡በምን ንፅፅር የምትለውጠው ህይወት የተሻለ መሆኑን
ትመዝናለች?

"ታውቃለህ አንዳንዴ እርግፍ አድርጌ ትቼው ቤተሰቦቼን ሄጄ ይቅርታ ልለምናቸው አስቤ አውቃለሁ፡፡ ያሳፍራል አይደል? እሉ ይበልጥብኛል ባልከው ሰው ተክደህ
👍2🥰1😁1
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስር


#በሜሪ_ፈለቀ

አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ ጊዜው በትክክል
መቼ መሆኑን ባላውቅም። በሞቅታ ስለምታወራ ከመስማት ውጪ አፌን አላላቀኩም።

"ታውቃለህ ለሷ ብለህ ምንም ለመስዋት የተዘጋጀህላት ህፃን ልጅህ ምርጫ ቢሰጣት እሱን እንደምትመርጥ ማወቅ
የሚጠዘጥዝ ቁስል ስሜት እንደሚሰጥ? አታውቅም!! ህፃን ናት በሷ እኮ አልፈርድም፡፡ የሚሰማኝን ፍርሃትና ህመም ግን ልታውቀው አትችልም። ስታድግ አባቷን መርጣ ብትሄድስ? ለእርሷ ብዬ የከፈልኩላት ሁሉ ባይገባትስ? አባቷን ስላሳጣኋት ብትወቅሰኝስ? ለነገሩ አንተ የምትሳሳለት ሰው ኖሮህ አያውቅም::" አለችኝ።

ኖሮኝ አያውቅም፡፡ እስከገባኝ ድረስ በአንዲት ክስተት ስለእርሷ
የተገለጠልኝ ስስት ግን የሶስት ዓመት ጥርቅም እንጂ የዛች ቅፅበት ብቻ አልነበረም። ሶስት ዓመት ሙሉ በእያንደንዷ የስራ ቀን የቀኑን መንጋት ያህል ስምሪት የተለመደ ክስተቴ ነበረች፡፡
ቡና አብሪያት ስጠጣ፣ ስትናደድ ጉንጫ ሲቀላ ደስ ስለሚለኝ ሳበሳጫት፣ ለማንም የማላወራውን ስሜቴን ሳወራት፣ እሷ
እንደማውቃቸው ሴቶች አልነበረችም:: አሁን ያን ላስረዳት አልሞከርኩም፡፡ ከብዙ ወሬዋ እና ከ'ታውቃለህ? አታውቅም!በኋላ አልጋው ላይ ተጋድማ ማውራቷን ቀጠለች፡፡ እያወራች እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡ አልቀሰቀስኳትም አጠገቧ ተጋደምኩ።

"እናትህ ማገገሚያ ነው ያሉት::" አለችኝ ጠዋት ቀድማኝ ተነስታ ያበሰለችውን ቁርስ እየበላን፡፡ ዝም አልኩ፡፡ ቀጥላ
በምትጠቀማቸው ሱሶች ምክንያት መግባቷን አከለችልኝ።ደነገጥኩ? አዘንኩ? ላያት እፈልጋለሁ? ስሜቴ ድብልቅልቅ አለ፡፡
ከስምሪት ጋር ከነጋ ከተወሰኑ ቃላት በላይ አልተነጋገርንም። ልቤን ከብዶኛል፡፡ ምንም የማውራት ፍላጎት የለኝም።ብዙ ዝም ካልኩ በኋላ የረባ ቃላት ሳንለዋወጥ ያለዚያ ቀን መኖሩን ወደማላውቀው የግል ማገገሚያ ሆስፒታል ደረስን፡፡ ሳያት ምን እንደምላት አላውቅም። ባታውቀኝስ ? ጭንቅላቷ የተቃወሰ
ቢሆንስ? እንደልጅነቴ ዞር በል ብላ ብትሰድበኝስ? ቆምኩ።የተዘጋጀሁ አልመስል አለኝ፡፡ ስምሪት ገብቷታል፡፡ እየደጋገመች እጄን ትጨምቀኛለች፡፡ እሷም ተጨንቃለች፡፡ አልጋው ላይ
ተጋድማ ሳያት ልጨብጣት? ልቀፋት? ፈገግ ልበል? ላልቅስ?የትኛው ላለሁበት ቦታና ስሜት እንደሚመጥን አላወቅኩትም።ስታየኝ ከአልጋዋ ወርዳ ማምለጥ ብትችል ፈልጋ ነበር፡፡
የለበሰችው ስስ የአልጋ ልብስ ውስጥ ተሸጎጠች፡፡ ስምሪት ቀድማ ሄዳ አቀፈቻት፡፡ ምንም ሳልናገር አጠገቧ ሄጄ ተቀመጥኩ፡፡ሳላገኛት በፊት ብዙ ጥያቄዎች ብትመልስልኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ከእድሜዋ በላይ አርጅታለች። ሰውነቷ ተጎሳቁሏል፡፡ ማለት የቻልኩት ዝም ብቻ ነው።

"ትልቅ ሰው ሆነሃል!" አለችኝ ፊቷን ከኔ አዙራ:: እያለቀሰች እንደሆነ አውቃለሁ። ላባብላት እፈልጋለሁ ግን አላደርገውም። ሳላስበው እጇን ያዝኳት። መልሼ ወዲያውኑ ለቀቅኳት፡፡

የቱንም ያህል ብትጠላኝ አልፈርድብህም። ይገባሃል::" አለችኝ
ፊቷን ደብቃኝ፡፡

“አልጠላሽም:: ባታወሪኝ እንኳን ትንሽ ደቂቃ አጠገብሽ ልሁን፡፡"አልኳት:: ድምፅ አውጥታ እያለቀሰች ፊቷን ወደእኔ መለሰች።ስምሪት አብራት ታነባለች፡፡ የማደርገው ጠፋኝ፡፡
“እያስጨነቅሽኝ ነው። እባክሽ አታልቅሺ፡፡” አልኳት አቅፌ ባባብላት ደስ ይለኛል። የሚሰማኝ ግን እሩቅነት ነው፡፡ እጄን ሰድጄ መለስኩት።በዝምታ ብዙ ካወራን በኋላ ተነሳሁ።

"መጥቼ አይሻለሁ::" አልኳት። ብርግግ ብላ ተቀመጠች፡፡ አንድ እርምጃ ጀርባዬን ሰጥቻት እንደተራመድኩ።

"ባቢሾ?" ብላ ጠራችኝ፡፡ የቤት ስሜ ነበር፡፡ አጠራሯ የፈለገችው ነገር ኖሮ ልትጠይቀኝ የፈራች ይመስላል። ምን ቸግሯት ይሆን ብዬ እያሰብኩ ተጠግቻት "ምነው?" አልኳት፡፡

በጣም እያመነታች እያየችኝ እጇን ወደ ፊቴ እያስጠጋች "አንዴ ልንካህ?" ስትለኝ ጭንቅላቴ በከባድ ነገር የተመታ መሰለኝ፡፡ ያ ስሜት ለዘመናት የያዝኩባትን ቂም የማጠብ አቅም ነበረው።ልጇን ለመንካት ያስፈቀደች እናት ህመም የእኔ እናት ህመም ብቻ ነው።ይሄ ስሜቷ ከጥላቻ ዋልታ ወደ ፍቅር አርያም
የማምጠቅ ምትሃት ነበረው። የዘረጋቻቸውን እጆቿን ሳምኩላት። እናትነት እንዲሰማት ማድረግ ተመኘሁ።

"ልጅሽ እኮ ነኝ! ብትቆነጥጪኝ እንኳን በኔ ላይ ስልጣን አለሽ!” አልኳት በእጁ አንገቴን ፀጉሬን ፊቴን ደባብሳኝ ስታበቃ በቀስታ እጇን ሰበሰበች። ከሆስፒታሉ እንደወጣሁ ብቻዬን መሆን ፈለግኩ፡፡ ስምሪትን ተሰናብቻት ማሰብ እስካቆም ጠጣሁ።በሚቀጥሉትን ቀናት የተለመደው ዓይነት ህይወት ቀጠልኩ።
አዲስ ነገር እናቴን እየሄድኩ አያታለሁ። አንዳንዴ ከስምሪት ጋር እንሄዳለን፡፡ ስላለፈው አናነሳም፡፡ ልጠይቃት የምፈልገው ብዙ ጥያቄ ቢኖርም አጠገቧ ስሆን ዝም ማለትን እመርጣለሁ።
ከስምሪት ጋር ልክ እንደበፊቱ ሆንን፡፡ ምንም እንዳልተፈጠረ፣ሳያት ምንም እንደማይሰማኝ፣ ስታረፍድ እንደማልንቆራጠጥ፡፡

አንድ ቀን ባሏ ሲመጣ ሳትኳኳል እንደጠበቀችው እና አስጠሊታ
መሆኗን ነግሯት ልጁን ይዞ እንደሄደ ነገረችኝ፡፡

በተደጋጋሚ ይሄን በማድረጓ አብረው መተኛት ማቆማቸውን ነገረችኝ፡፡ ከሳምንታት በኋላ እናቴ ከሱሷ ከማገገሟ በባሰ በጉበት በሽታ እየተሰቃየች ስለነበር ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሌላ ሆስፒታል ተዛወረች።መታመሟን ስታውቅ ዘመዶቿጋ ስልክ ደወለች። እስከዛሬ መኖራቸውን እንኳን አስቤ ከማላውቃቸው
ቤተሰቦቼጋ ለመግባባት መሞከር ያልተለመደ ደባሪ ነገር አለው፡፡
የወንድ አያቴን፣ አጎቴንና አክስቴን ተራ በተራ እየመጡ ሲከርሙ ተዋወቅኳቸው። አክስቴ እዚሁ አዲስ አበባ መኖሯን
ማወቄ ገረመኝ፡፡ እንዴት አይጠያየቁም? አጎቴና አያቴ ከክፍለሃገር ነበር የመጡት: የገባኝ ነገር እናቴ ከቤተሰቦቿም ጋር ቢሆን የጠበቀ ግንኙነት ያላት አይመስለኝም:: ልጅ እንዳላት
እንኳን ያወቁኝ አሁን ነው። አልተገረምኩም እንኳን እነርሱ
አብሬያት ኖሬ የማውቀው ልጇ እንኳን ብዙ የማይፈታ እንቆቅልሽ እንዳላት አውቃለሁ፡፡

“አባትህ የምሰራበት የነበረ ሆቴል ያረፈ ቱሪስት ነበር። በጣም ጥሩ ሰው ነው። ፈረንሳዊ ነው:: የምትኖርበትን ቤት የገዛልኝ እሱ ነው።ሀገሩ ሚስትና ልጆች ስለነበሩት ተመልሶ ወደ ሀገሩ
ሄደ፡፡ አድራሻውን አላውቅም፡፡ ልጅ እንዳለው አያውቅም።አንተን ማርገዜን አልነገርኩትም።እሱ ባከበረኝ ልክ ማንም
ወንድ አክብሮኝ አያውቅም።እሱን ነው የምትመስለው::" አለችኝ ብቻዬን ሆስፒታል ያደርኩኝ የሆነ ቀን ማታ። ዝርዝር አድርጋ እንድትነግረኝ ልጠይቃት አስብና ማስታወስ የማትፈልገው
ታሪኳ ከሆነ ብዬ እየፈራሁ እተወዋለሁ። ማወቄ ለእኔ ከሚፈይደው ቁም ነገር ጋር ሳነፃፅረው ማስታወሷ የሚፈጥርባት
ህመም የሚያመዝን እየመሰለኝ አለማወቄን መረጥኩ። ይሄን
የነገረችኝ ጠዋት ለአክስቴና ከእናቴ ስር ለማይጠፋው የነፍስ አባቷ ቀኑን ለቅቄላቸው ወደ ስራ ልገባ እስኪመጡልኝ
እየጠበቅኳቸው ሳለ አንድ መልከ መልካም ወጣት ገራገር የመሰለች ሴት እጅ ጣቶች በጣቶቹ ቆልፎ ሆስፒታል መጣ። እናቴ ስታየው ግራ ተጋባች። የእርሱ ግድ የለሽነት እና የእናቴ
መቁነጥነጥ ሌላ የማላውቀው ታሪክ ክር ጫፍ መሆኑን ነገረኝ። አብራው የነበረችው ገራገር ሴት ወደ እናቴ ተቅለብልባ ሄዳ እየሳመቻት።
"እንዴት ነሽ ወለላ? መታመምሽን አባ ናቸው ትናንት የነገሩን?አሁን ተሻለሽ?" መልስ አትጠብቅም።ወዲያው ወደ ወጣቱ ዘወር ብላ "ና ሳማት እንጂ! ምን እዛጋ ይገትርሃል?" መልስ ሳይሰጣት በተገተረበት መቆሙን አይታ በዓይኗ ማባበልም ቁጣም የቀላቀለው ማጎረጥረጥ ታጉረጠርጣለች፡፡ ወንበር ላይ ያለ ንግግር ተቀመጠ፡፡
👍4
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በሜሪ_ፈለቀ
---------------------------------------------------
ሁሉም የሕይወት ገፅ መጨረሻ ላይኖረው ይችላል ለህይወት መጨረሻ ብሎ ነገር የለም።የአንዱ ቀን መጨረሻ የሌላው ቀን መጀመርያ ነውና።የሰኞ ማለቅ የማክሰኞ መጀመር እንደሆነው የምድር መጠቅለል ለሰማያዊ ህይወት መጀመር እንደሚሆነው....ሌላ ፅንፍ ግን አለው።

=========================

"እናትሽ በጠና ታማለች፡፡ እባክሽ ልታይሽ ትፈልጋላች...ለአራተኛ ጊዜ የተላከልኝ መልዕክት ነው።

“እስካሁን አልሞተችም እንዴ? ለምን ታጓጓኛለች? አንዳችሁ እንኳን ምናለ ሞተች የሚል ብስራት ብታሰሙኝ?"

"በስመ አብ ወ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ!! (ገዳዳ መስቀል በሰራ እጁ እያማተበ) ምነው ልጄ? ምን የሚሉት ጭካኔ ነው? ደግም አይደል! እግዜርም አይወደው::" መልሴ
አንገሽግሾታል። ሀምሳ ዓመት የሚያልፈው ሰውዬ ነው።የወለደችኝ ሴትዮ የነፍስ አባቷ ነው።

"በናትህ ከቤቴ ውጣልኝ!!"
"ምነው ልጄ? እግዜር የሰጠኝን ሹመት ባታከብሪ በእድሜ አባትሽ አልሆንም?" የሚናገረው ቃል የለዘበ ይሁን እንጂ ቀይ
ወጥ የመሰለ ግለታም ዓይኑ እንደተጠየፈኝ ያሳብቅበታል።

እድሜውን ሳይሆን የለበሰውን የቤተ ክህነት ልብስ ባከብር ደስ ባለኝ ግን ለባሹ ልብሱን እንጂ ልብሱ ለባሹን እንዴት ሊያስከብረው ይችላል? ልብሱ ይሄን ከንቱ ሰውዬ እንዴት ክቡር
ሊያደርገው ይችላል? መሆን የነበረበት ልብሱ ተገፎ ለተከበረ ሰው መደረብ ነበር። ያኔ ልብሱም ለባሹም ይከበራሉ።
መጎናፀፊያ አካልን ይሸፍን ይሆናል፤ ምናልባትም የአካል እንከንን የነፍስ ሴሰኝነት ግን በልብስ አይሸፈንም፡፡ ዝቃጭ ምግባር ግን ለቅድስና ሌት ተቀን ለሚታገሉ ልበ ብርቱዎች በተዘጋጀ መደረቢያ አይከለልም። በሱ ቤት እኔ ከእናቴ ጋር የሚስራውን ብልግና አላውቅበትም። የናቴ ውሽማዋ ነው።

ይሄኔ በየመቅደሱ ሰው የዘራውን ያጭዳል' እያለ ይቦጠለቃል፡፡

ሴሰኝነትን እየዘራ መከበርን ለማጨድ ማጭድ ይስላል፡፡ ከንቱ!!
ይሄኔ ስንቶች ስንጥር ለምታክል በደላቸው ንስሃን ሽተው ከፊቱ
ሲመጡ ዋርካ የሚያክል ስድነቱን በብብቱ ሸሽጎ ልባቸው ለንስሃ
እንዲሰበር ዘክሯል። የዘቀጠ!

የእናቴን ጣር ላይ መሆን ሊነግሩኝ እንደመጡት ሶስቱ እሱም እየተፀየፈኝ ቤቴን ለቆ ወጣ፡፡ የመጀመሪያዋ የእናቴ ብቸኛ እህት ነበረች፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ብትኖርም ገጠር እያለሁ በልጅነቴ ለበዓላት ስትመጣ ነበር ያየኋት፡፡ ጠይቃኝም ጠይቄያትም የማንተዋወቅ አክስቴ ናት።

“ምን አገባኝ ታዲያ? ለምን ፍግም አትልም?" ስላት ብታንቀኝ ደስ ባላት።

"ጨካኝ! አረመኔ!" ብላኝ ወጣች። ሳስበው የኔ ዘመዶች ግን የሆነ
የዛገ የማሰቢያ ክፍል ሳይኖራቸው አይቀርም::እንደወለደችኝ ከነእሪታዬ ጥላኝ አሸሼ ገዳሜዋን ልትል ስትሄድ ዞራ ልታየኝ እንኳን የሚራራ አንጀት ያልነበራትን ሴትዮ ጨካኝ! አረመኔ
ያላሏት ዘመዶቼ በወተት ምትክ ክፋት፣ በእናት እቅፍ ፈንታ ጥላቻ፣ በልጅነት ቡረቃ ልዋጭ መገፋትን ሲግቱ ፍቅርና
ጥላቻን ካምታቱበት ልቤ ርህራሄ ይናፍቃሉ፡፡

ሁለተኛው የእናቴ ብቸኛ ወንድም ነበር፡፡ ታላቋ ነው። አጎቴ የቤታቸው አድባር!!

"እንዴት እናትሽ መታመሟን ሰምተሽ ትቀሪያለሽ? ሞታም ቢሆን እኮ ይኸው ነው::" አለኝ በወቀሳ እፍረት የሚያሲዘኝ
መስሎት፡፡

“እሷ ብቻ ትሙት እንጂ ለሞቷ እንኳን አልዘገይም! ደስ እያለኝ መጥቼ እቀብራታለሁ።” ያልኩት አንቀጠቀጠው። ቅንጣት ርህራሄ እንደሌለኝ አስቦ ጥሎኝ ሄደ፡፡

ሶስተኛው አያቴ ነው:: የእናቴ አባት።
........…
"አባባ እኔን ለማናገር ሀገር አቋርጠህ መጥተህ ባላስቀይምህ ደስ
ይለኝ ነበር፡፡ እንዳደርገው እያስገደድከኝ ነው።እናቴ አንድ ሞት አይደለም አስር ሞት ብትሞት አልፀፀትም::" አልኩት::
"እናትሽ በህይወት ሳለች አግኝታሽ ገንዘብ ልትተውልሽ ትፈልጋለች። ካልደረስሽ ለሌላ ሰው ለማውረስ እያሰበች ነው።"

ብሉኝ ከፊቴ ላይ ስሜቴን መበርበር ጀመረ።

"ሃሃሃሃ ጥሩ ነዋ፡፡ በመኖሯ ማንንም ጠቅማ ማወቋን እኔንጃ በሞቷ እንኳን እስኪ ትጥቀም!" ስለው ደነገጠ፡፡

ንብረት ያሳሳታል ብሎ ማሰቡ ገርሞኛል፡፡ ምክንያቱም በኮልኮሌ ስብስብ ሀሴት የምቃርም ሴት አይደለሁም። የጮቤዬ ምንጭ ገንዘብ ቢሆን እንኳን ከዚህ በኋላ ምንም የገቢ ምንጭ ባይኖረኝ እድሜዬን ሙሉ ጮቤ እየረገጥኩ መኖር የምችልበት ሀብት ላለው ሀብታም የሸጠኝ እራሱ አያቴ ነው:: አያቴ ብቸኛው
በህይወቴ የተከሰተ ለጥሩ የተጠጋጋ ክስተት ነው።እናቴ ጥላኝ ስትሄድ የተቀበለኝ እሱ ነው:: ምንም እንኳን የልጁ ልጅ መሆኔን ሳያሳውቀኝ ባድግም፣ ምንም እንኳን ከሚያኖራቸው አገልጋዮች እንደ አንዷ ራሴን እየቆጠርኩ ስኖር
እንደልክ ሁሉ ቢያስችለውም፣ ምንም እንኳን እናቴ ማን እንደሆነች ሊነግረኝ ሳይፈልግ ባድግም፣ለጨለመ ልጅነቴ አንዱ ምክንያት ቢሆንም፣ ምንም እንኳን
በቅጡ ለማያውቀው ሀብታም ነጋዴ ቢሸጠኝም።ከብዙ ክፉ የኑሮዬ ገፅታዎች ውስጥ ደብዛዛው ክፉ እሱ ነው።

አልጋ ቢኖረኝ እንደ ፍጡር ለሊት ነበረኝ፡፡

ቅዠት ባይሆኑብኝ እንቅልፍ ነበረኝ፡፡

ቢያስተኙኝ ብዙ ህልም ነበረኝ።

ለሁሉም ርህራሄ አልባነቴን ብነግራቸውም ሁሉም የማይገባቸው ሀቅ ግን ሴትየዋን አልጠላትም በገፋችኝ ጥግ ወደርሷ የሚያስወነጭፈኝ ስበት አላት፡፡ የማስታውሰው ቅንጣቢ
የእናት የሚመስል ነገር አሳይታኝ አታውቅም፡፡ በክፋቷ ክምር ልጠላት እፍጨረጨራለሁ። ከንቱ መንፈራገጥ ብቻ ይሆንብኝና ለምትሰራው ቅጥ ያጣ ግፏ ምላሽ ከቀናት ንዴት በኋላ
በማልቆጣጠረው የእናት ፍቅር ጥም ሲቃጠል ራሴን አገኘዋለሁ።ብሽቅ እኔ! ልረሳት እመኛለሁ:: አልችልም።
ልጠላት አጥብቄ እፈልጋለሁ። አልችልም:: ልገላገላት እፈልጋለሁ። የሆነ ፍንትው ያለች ፀሃይ በደመቀችበት ማለዳ
ሞቷን የሚያበስረኝ መላዓክ በፈገግታ ታጅቦ "እነሆ እልልልልል የምትይበት ቀን መጥቶልሻል፡፡ እናትሽ በወዳጇ ሳጥናኤል እቅፍ ትገኛለች:: በክፋቷም በፍቅሯም የምትነጂበት ጊዜ አበቃ!" ቢለኝ ያ የተወለድኩበት ቀን የሚሆን ይመስለኛል። እናቴን መፈለግ ትቼ ራሴን የምፈልግ፡፡

በቁሟ አምርራ የምትጠላኝ እናቴ በሞቷ ዋዜማ ላይ ለንሰሃዋ መጫወቻ ጠጠር ልታደርገኝ ልታየኝ ትፈልጋለች፡፡ ኩነኔን
ፈርታ እንጂ እኔ አሳስቤያት አይደለም፡፡ ምናልባት ይቅርታ ልትጠይቀኝ እንኳን ከሆነ (አታደርገውም እንጂ!) ኀጢአቷን በኔ ይቅርታ ልትቀንስ እንጂ የሰበረችውን ልቤን ፍንክትካች ልትገጣጥም አስባ አይደለም፡፡

ከእያንዳንዱ ክፋት ጀርባ መሪር በደል አለ እያልኩ አስባለሁ።ጥያቄው የሚሆነው በደልን ይቅር ያለ በጎነት የለም ወይ? የሚለው ነው አንዳንዴ የወለደችኝን ሴት ሳስባት ለመራራነቷ ምክንያት እያበጀ በሚጃጃል ልቤ ልረዳት እሞክራለሁ።
ምክንያቷን ማወቅ እመኛለሁ። ከዛ ባዝንላት፣ ደሞ ያደረገችኝን
ሁሉ ብረሳላት፣ ደግሞም እድል ብሰጣት... በልፍስፍሱ እኔነቴ
ራሴን ለምወቅስበት መጠን ያህል ጊዜ ሞክሬያለሁ። አንድ እርምጃ ስጠጋት በመቶ ትሸሸኛለች፡፡ ይቅር ባልኳት እጥፍ
በደሏን ትከምርብኛለች፡፡ እንደቆሻሻ እየተፀየፈችኝ እንኳን እቅፏን እናፍቃለሁ። በሚያቆስል ምላሷ እየገሸለጠችኝ እንኳን
ፀጉሬን እየደባበሰች እንድታባብለኝ እቃዣለሁ። ራሴን ሳየው በርሷ የተለከፍኩ ይመስለኛል። የመኖር ትርጉም ቁልፌ በእሷ እናትነት ውስጥ ያለ ይመስለኛል፡፡ ሰውየው(የነፍስ አባቷ) ገስፀውኝ ከቤቴ ከወጡ ከሰዓታት በኋላም ይሄ ቄጤማ ማንነቴ ስለርሷ ማሰብ እንዳቆም
👍4
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በሜሪ_ፈለቀ

"እኔ ገንዘብሽን አልፈልገውም፡፡ ለምትፈልጊው ሰው ስጪው።ለኔ ግን ለጥያቄዎቼ መልስ ስጪኝ፡፡ ያኔ በመጨረሻ የእናትነት ፍቅርሽን ያለስስት እንደቸርሽኝ በልቤ እፅፍልሻለሁ።" አልኳት የተቃጠለ ውስጤን እና የሚለበልብ ትንፋሼን ለመደበቅ በለዘበ
አነጋገር። ከእርሷ ጠብታ ፍቅር እንደማላገኝ ገብቶኛል፡፡ ቢያንስ ግን ጭንቅላቴ ውስጥ የሚርመሰመሱ
ጥያቄዎቼን እንድትመልስልኝ ተስፋ አደረግኩ፡፡ በስልችት ከንፈሯን ወደጎን
ከፈት አድርጋ አሽሟጠጠች።

"አባቴ ማነው? ከማን ነው የወለድሽኝ?"

“ሰይጣን ነው። አባትሽ ጭራቅ ነው::" ተመሳሳይ መልስ ከዚህ በፊትም መልሳልኛለች። ከሰይጣንነቱ፣ ከጭራቅነቱ ያለፈ አታብራራልኝም። የገባኝ ነገር አባቴ ማንም ይሁን ማን
በድሏታል፡፡ በምሬት ትጠላዋለች።

"እሱ ለበደለሽ በደል ለምን እኔን አስከፈልሽኝ? ለምን ከዳሽኝ?
እኔ ምን በበደልኩሽ ነው የበቀል ጅራፍሽን እኔ ላይ ያጮህሽው?"
ድምፄ እየጨመረ ሲሄድ ጥያቄዎቼ የማይረቡ እንደሆኑ ሁሉ ፊቷ በንቀት ሲሸረድደኝ ዘለሽ ተከመሪባት የሚል ስሜት ተፈታተነኝ።

"ለማንም የማይበጁ ጥያቄዎችሽን.. ብላ እስክትጨርስ መታገስ አቅቶኝ አዞረኝ፡፡ አነቅኳት፡፡ የእጄ ፍጥነት ከቁጥጥሬ
ውጪ ነበረ።

"ከቋጥኝ የከበደ በደልሽን ለመቻሌ ቢያንስ መልስ ይገባኛል፡፡መልሺልኝ፡፡ መልሺልኝ አባቴ ማን ነው?" እጆቼ አንገቷ ዙሪያ ሲከሩ የፊቷ ደምስሮች ተወጣጠሩ።
አላውቀውም።" አለችኝ ከእጄ ለማምለጥ እየሞከረች፡፡ እውነቷን
አው ያለችኝ፡፡ እውነቷን መሆኑን ለማወቅ ዓይኗ እና ድምፀቷ በቂ ነበር፡፡ ሴትየዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውስጧ ስታወራ
ሰማኋት። አላውቀውም።በሚለው ቃሏ ውስጥ ምስጢራት እንደታጨቁ ሁሉ በመላው ሰውነቴ ፊደሎቹ ተሰራጩ፡፡ በሩ
ተከፍቶ ሰው ገባ፡፡ ካላወቀችው ሰይጣን ነው የምትለኝ ማንን እንደሆነ ልጠይቃት
ምላሴ ጫፍ ላይ ቃላቶቹ አንገዋልላቸዋለሁ።ለመተንፈስ ስትንፈራገጥ ነው ያደረግኩት የገባኝ ግርግር ተፈጥሮ ሁከት ደራ።ክፍሉ መሀል ተገትሬ ዘመዷቿ የመሰሉኝ ሰዎች ሲጯጯሁ እሰማለሁ እየደነፉብኝም ይመስለኛል ፖሊስ ሊጠሩም ሲንደፋደፉ፡፡
ከደራው ብጥብጥ አይሎ ጆሮዬ በአንድ ድምፅ ተደፍኗል።
አላውቀውም ሌላ ድምፆች የሚሾልኩበት ቀዳዳ የለም።የአክስቴ የስድብ ናዳዎች ሾልከው ሊገቡ ሲገፋፉ በተደፈነው ጆሮዬ የሚሰርጉ ፊደላትን ስገጣጥም ስድብ ወይ እርግማን
መሆኑን እጠረጥራለሁ።እየገፈታተሩ ከተኛችበት ክፍል ሲያስወጡኝም የሚሉትን አልሰማቸውም። በገፈታተሩኝ
ውክቢያ ፍጥነት እየተራመድኩ ከሆስፒታሉ ወጣሁ። መኪናዬን
ያቆምኩበትን ማስታወስ አልቻልኩም።
ቁልፉን በጣቴ እያሽከረከርኩ አራት እርምጃ በማትሞላ ቦታ ደጋግሜ በፈጣን
እርምጃ እመላለሳለሁ።መኪናዬን የቱጋ ነበር ያቆምኩት? ምንም እያሰብኩ አይደለም፡፡ ጭንቅላቴ ውስጥ የመቃብር ቦታ የመሰለ ረጭታ ነው የሚሰማኝ መኪናዬን ትቼ ለምን ታክሲ ተሳፈርኩ? ለታክሲ ነጂው በየትኛው ደቂቃ የቤቴን አድራሻ ነግሬው ነው ደጄ ላይ የጣለኝ? ምንም ቃል መተንፈሴን አላስታውስም።

መኪናሽስ?" ይለኛል ተፈሪ የአጥሩን በር እንደከፈተልኝ በሌባ ጣቴ እያሸከረከርኩት ያለሁትን የመኪና ቁልፍ እና ያመጣኝን
ታክሲ እያፈራረቀ እያየ። አልመለስኩለትም፡፡ የአጥሩ በር ቁልፍ
እጄ ላይ እያለ ለምን መጥሪያ ተጫንኩ? በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ።ልብሴን አውልቄ እዚያና እዚህ ወርውሬ መታጠቢያ ቤት ገባሁ:: በቁሜ ውሃው እላዬ ላይ ሲፈስ ምን ያህል
እንደቆየሁ እንጃ፡፡ ተፈሪ መኝታ ቤት ሲያወራ ይሰማኛል። ምን እንደሚል አልሰማውም፡፡ ለአስራ ስድስት
ዓመት በቆየ ትዳራችን በድምፁ ብቻ ሲፈልገኝ አውቀዋለሁ።በምንም ስሜት ሆነ በየትኛውም ሰዓት ልብሴን አውልቄ ካየኝ እንዲህ ያደርገዋል፡፡ ያን ድምፁን እጠላዋለሁ:: በክረምት የሚጮሁ ብዙ እንቁራሪቶች ፂፂስታ ይመስለኛል። እንደዛ
ሲያወራ ስሰማው ጆሮዬን ይበላኛል። በጣቴ ጆሮዬን ደጋግሜ እኮረኩራለሁ። እላዬ ላይ ሰፍሮ ላቡንና የወንዴ ፈሳሹን
እስካላንጠባጠበ እንደ ቆስለ ውሻ ማላዘኑን አያቆምም።ሙሉ ቀን የመሰለኝን ያህል ሰዓት ከውሃው ስር ቆሜ ብሰነብትም ተፈሪ ማላዘኑን አላቆመም።እየተንጎራደደ መሆኑን ድምፁ
የሚመጣበት አቅጣጫ ያስታውቃል። ፀጉሬና ገላዬ የተሸከመውን ውሃ እያራገፍኩ ወደ መኝታ ቤት መጣሁ። ቆሞ እየቀላወጠ ያየኛል። መጨቃጨቁ ልቤን ዝቅ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው አውቃለሁ፡፡አይተወኝም:: መገላገል ነው አቋራጩ መንገድ፡፡ አልጋው ላይ እየተሳብኩ በጀርባዬ ተጋድሜ እግሬን ከፈትኩለት፡፡

አንዳንዴ ሳስበው እንኳን ትንፋሽ ኖሮኝ እየሰማ ሞቼ እግሬ ተከፍቶ ቢያገኘኝ በድኔ ላይ ሰፍሮ መወዛወዙን የሚያቆም
አይመስለኝም፡፡ እየገለፈጠ ልብሱን አወላልቆ ከላዬ ሆነ። ስልት የሌለው ውዝዋዜ ከቦርጩ እየታገለ ይወዛወዛል፡፡ በኮርኒሱ ላይ አምፓሉን ከምትዞር ትንኝ ጋር ዓይኖቼ አብረዋት ይዞራሉ።
ለአፍታ ዓይኔን ነቅዬ ስመለስ ወደኋላ ተመልሳ ይሁን ዞራ መጥታ በአምፓሉ ዙሪያ ከነበረችበት ወደ ኋላ መጥታ አገኛታለሁ እስካሁን አልጨረሰም ሰውነቴ ላይ የተንጠባጠበው ላቦቱ ሰውነቱና ሰውነቴ ሲነካካ የሲኦል ማስጠንቀቂያ ደወል የሚመስለኝን ድምፅ ይፈጥራል፣ ሰውነቴ በላቡ ሲጠባበቅ ላቡን የቀመስኩት ይመስል አፌን ጨው ጨው ይለኛል ሁሌም እንዲህ ነበርን።እሱ ተወዛዋዥ እኔ የውዝዋዜው መድረክ፡፡ አለቀ! አስራ ስድስት ዓመት። ዛሬ ግን
በተለየ ሰለቸኝ እንዲወርድልኝ ናፈቅኩ፡፡ መልሼ ዓይኖቼን ወደ አምፖሉ እልካለሁ። የምትዞረዋ ትንኝ የለችም:: ዙሯን ጨርሳ ወይም ሰልችቷት ሄዳለች።የእኔም መንገድ እንደትንኟ ይመርለኛል ዙር መዞር ፤ አንድን መንገድ እየደጋገሙ መርገጥ፡፡ ዓለም ራሷ ክብ አይደለች? ኑረትም እንደዛው መሰለኝ። አንድ ዒላማ ላይ መሽከርከር፡፡ ሽክርክሪቱ ያው ቢሆንም ሁሉም ሰው የሚሽከረከርበት መሃለኛ ነጥብ አለው።የታደሉት የሽክርክሪታቸው መሃለኛ ነጥብ ስህተት መሆኑ ሲገባቸው ወይም ሲሰለቻቸው አልያም ተስፋ ሲቆርጡ ዒላማቸውን ይቀይሩትና አዲስ ሽክርክሪት ይጀምራሉ።
ኡፍፍፍፍ እስካሁን አልጨረሰም? ዛሬ ደግሞ የላቦቱ ብዛት!

እናቴን ቀብሬያት ነው የመጣሁት!" ስለው ራሴን ሰማሁት።ውስጤ ወንድነቱ ሲሟሽሽ ተሰማኝ፡፡ አፍጦ እንደ እብድ እያየኝ ከላዬ ላይ ኩምሽሽ ብሎ ወደ ጎኔ ወደቀ።በስመአብ ወወልድ መቼ ሞተች? ለምን አልነገርሽኝም? እንሂድ እንዴት አትይኝም?"የጣር በሚመስል ቀሰስተኛ ድምፅ ጠየቀኝ፡፡

“ቅድም ሞተች፡፡ እናት የለኝም:: ቀብሬያታለሁ።” ስለው ግራ ተጋብቶ በድንዙዝ ስሜት ከተጋደመበት ተነሳ።
"መች ሞታ ነው? ቄሱ የመጡት የእናትሽን ሞት ሊያረዱሽ ነው? የት ነው የተቀበረችው?"

"እኔ ልብ ውስጥ!" ስለው ጤነኛ አልመስልኩትም። ብዙ ጥያቄ አከታትሎ ጠየቀኝ፡፡ አልመለስኩለትም፡፡ ጭራሹኑ ያልሰማሁት ይበልጣል፡፡ አወላልቆ እንደፍየል በጠጥ የበታተነውን ልብሱን
እየሰበሰበ ትቶኝ ወጣ፡፡ለምን ያህል ሰዓት
እንደዛው እንደተጋደምኩ ለማወቅ ብሞክር እሩቅ ሆነብኝ፡፡ አስባለሁ:: ምን
እንደማስብ ውሉን አልይዘውም:: ለራሴ እየደጋገምኩ "እናት የለኝም።አባቴም አይታወቅም::" እላለሁ። ቃሌን አላመንኩትም:: እደጋግማለሁ:: የአባቴን
ማንነት ማወቅ ያለመቻሌ በተወሰነ መልኩ እረፍት መሰለኝ፡፡ ሌላ ፍቅር ፍለጋ
መፋተጉ አቁሳይ ሊሆንብኝ ይችላል:: ፍፁም ሊገባኝ አልቻለም።እናቴ ስላልተቀበለችኝ ዓለም ሁላ ያልተቀበለኝ ርካሽ እንደሆንኩ እየተሰማኝ አንገቴን የምደፋው ለምን ይሆን? የሷ ጥላቻ የዓለም ሁሉ ጥላቻ ሆኖብኝ የተፈጥሮ ሁሉ
👍2
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በሜሪ_ፈለቀ

በእርግጥ እናቴ እሷ መሆኗን እስካወቅኩበት ቀን ድረስ እናትና አባቴ ሞተውብኝ ከሩቅ ሀገር አምጥተው የሚያሳድጉኝ ጥያቄ አልባ
ቀኖች የነበሩኝ ህፃን ነበርኩ:: አባባ የምለው አሳዳጊዬ እግዚአብሔርን በመፍራቱና በደግነቱ ትንሿ ያደግኩባት የገጠር ከተማ ድፍን ነዋሪ የመሰከረለት፣ ሚስቱ የምትኮራበት፣ ልጆቹ የሚመፃደቁበት፣ እኔን ጨምሮ ቤቱ የምንኖር አገልጋዮቹ የምንመካበት ሰው ነበር፡፡ በልጅነቴ ውስጥ ያለው አሳዳጊዬ ይህ ነው፡፡ የልጅነትን ቡረቃ ተሰናብቼ መብሰልና ህልም ማለም ስጀምር ለክብሩ እንጂ ለእኔ ግድ ከሌለው አያቴ ጋር ተዋወቅን፡፡በእርግጥ በቸርነታቸው ከሚያሳድጉኝ መልካም አሳዳጊዎቼን
ላሳዩኝ በጎነት በልቤ የማመሰግን፣ ለውለታቸው ክፍያ በአቅሜ
የማገለግል አገልጋያቸው እንጂ ለጎደለው
የማማርርበት መብትም ሆነ ይገባኛል የምለው አንዳች ያልነበረኝ ትንሽዬ ልጅ ነበርኩ። ቢቆጡኝ፣ ቢሰድቡኝ፣ ቢያንቋሽሹኝ ትምህርት፣ ቢሰድቡኝ ትምህርት እንድማር ሳይፈቅዱልኝ ከማንበብና መፃፍ የዘለለ ባላውቅም፣ እንደልጅ ለመጫወት ባይፈቅዱልኝ
መሄጃ የለሽ ወላጅ አልባ ህፃን ለሚያሳድጉ ደግ አሳዳጊዎቼልክ ነገር መሆኑ ነበር የሚገባኝ፡፡

በአስራ አራት ዓመቴ ገደማ ለአዲስ ዓመት መለወጫ በዓል ሁሉም ቤተሰብ ተሰብስቧል። አክስቴና እሷ ከአዲስ አበባ ነበር የመጡት:: ሴትነቴ ያበበበት ወቅት ነው።የሰፈራችን ጎረምሶች
በአጠገቤ ሲያልፉ ቂጤን ገፍተር፣ ያጎጠጎጠ ጡቴን ቆንጠር እያደረጉ ያሽኮረምሙኛል፡፡ አመሻሹን ከብቶች ከሜዳ ይዤ ስመለስ ችፍ ያለው የሰንሰል ተክል አጠገብ አዳነ ቆሟል። ጎትቶ
ወደራሱ አስጠጋኝ፡፡ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም:: ጡቴን እንዳስነካው ያባብለኛል። ብዙ አላስለምነውም:: ሲነካካኝ ደስ ስለሚለኝ እፈቅድለታለሁ።

"እረፍ አዳነ ቤት ሁሉም አሉ። እየጠበቁኝ ነው ልቀቀኝ" ብዬው ነበር አልሰማኝም። እንደሌላ ቀኑ አላባበለኝም:: ወደ ሰንሰሉ
ውስጥ ይዞኝ ገባ፡፡ ከላዬ የለበስኩትን ልብስ ወደ ላይ ሰብስቦ ጡቴን ሲነካካኝ የምከለክልበት አቅምም ምክንያትም ከዳኝ። ሳሩ ላይ አጋድሞኝ ጡቴን በአፉ ሙሉ እየጎረሰ ሲተፋው እያቃሰትኩ
ነበር። ድንገት አቁሞ ሲበረግግ የጨፈንኳቸውን ዓይኖቼን ገለጥኳቸው።ያየሁትን ደግሜ ላለማየት ዓይኖቼን ጨፈንኳቸው። መልሼ አጮልቄ አየሁ። ከተጋደምኩበት ሆኜ ሳየው ጋሼ (የአባባ ብቸኛ ወንድ ልጅ) ከሰማይ ላይ ተወርውሮ የተንጠለጠለ መስሎ ዓይኑን ጎልጎሎ አፍጥጦብናል። አዳነ ፓንቱ እስኪቀደድ እግሬ አውጪኝ ብሎ ሲሮጥ ጋሼ ማጅራቴን ጨምድዶ ይዞኝ ወደቤት ገባ። በቤቱ ጣራ ስር ያሉትን ሁሉ
በጩኸቱ ስብስቦ እንደ ክፉ ወንጀለኛ ፊትለፊታቸው አቆመኝ፡፡የት እንዳገኘኝ እና ምን ስሰራ እንደነበረ በሚዘገንን ፀያፍ ቃል ለሁሉም ተናግሮ እንዳበቃ ተራ በተራ የምላሳቸውን መርዝ ተፉት። እሷ ምንም አልተናገረችም።ዓይኖቿ ውስጥ የነበረው መፀየፍ ግን ከእነርሱ ስድብ በላይ ህመም ነበረው።የሚያውቁትን ስድብና ቁጣ ሁላ ጨርሰው ፀጥ ሲሉ ወደ ጎዳ ገባሁ።እሷም ሲጋራዋን ልታጨስ ወደ ውጪ ወጣች።ጋሼም ተከተላት።በጎሮ በር አድርጌ ወጣሁ።ልሰማቸው ፈልጌ ባይሆንም ሲጯጯሁ ይሰማኛል። የመደናቆራቸው መንስኤ እኔ መሆኔን ሳውቅ ጆሮዬን ጥዬ መስማት ጀመርኩ፡፡

እንቺ የወረወርሻትን ዲቃላ እድሜ ለአባቴ በይ አሳደግንልሽ፡፡ እሷ ይዛብን የምትመጣውን ዲቃላ ማን ሊሸከምልሽ ነው?ካንቺም ብሶ እንዳለማች ቆጥረሽ ዝም ትያታለሽ? ባንቺ ነው የወጣችው! ገና ቂጧን ሳትጠርግ በየሳሩ ትሸረሙጣለች፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯን እየጠበቅኩ የከፈተችውን እግሯን አልገጥምም።ከፈለግሽ ወስደሽ የምታደርጊውን አድርጊያት:: " ከእውነታው እኩል የመረጣቸው ፀያፍ ቃላት አስደነገጡኝ፡፡ የሰማሁት
እውነት መሆኑን መቀበል አቃተኝ፡፡ እሷ አትመልስለትም።አጎቴ አንዴ እህቱን አንዴ እኔን እየሞለጨ ደቂቃዎች አለፉ፡፡
ደጋግሞ ከተናገረው እሷ እናቴ መሆኗን እና ለእነሱ ጥላኝ እንደሄደች ገባኝ፡፡

"እናቴ አንቺ ነሽ? አባባ አያቴ ነው?" አልኩኝ ተኮራርፈው ሳሎን እንደተቀመጡ ሁሉም ነብር እንዳየ ጥንቸል ዓይናቸው
ተጎልጉሎ ጆሮአቸው ቆመ።የመለሰልኝ የለም፡፡

ውጪ ያወራችሁትን እንዳለ ሰምቻለሁ::" አልኳቸው፡፡

እና የሰማሽ እንደው ምን ይሁን? እኔ እናትሽ አይደለሁም ስትለኝ እናቴ መሆኗን ስሰማ ተንሰራፍቶ የነበረውን
ብልጭታ ደስታ በተነችው:: አጠገቧ ተጠግቼ እጇን ስይዛት መንጭቃ ገፈተረችኝ፡፡ እናቴ መሆኗን ሳላውቅም በፊት ይዣት አውቃለሁ፡፡ እንደዚህ አስጠልቻት አይቻት አላውቅም፡፡ እነ አባባ ጋር የምትመጣው ከስንት
ዓመት አንዴ ቢሆንም የምትለብሳቸው ልብሶች፣ ሲጋራ አጫጫሷ፣ ቁመቷ፣ አካሄዷ...
ባየኋት ቁጥር እንደርሷ መሆን የምመኝላት ነበረች::ስትመጣ እንግዳ ሲመጣ እንደማደርገው እግሯን የማጥባት እኔ ነበርኩ፡፡ ከስንት ዓመት አንዴ ለአዲስ ዘመን መለወጫ ስትመጣ
አዲስ ልብስ እቤት ላለነው ሁሉ ስትገዛ ለእኔም ገዝታልኝ ታውቃለች:: እንደዛ ቀን በጥላቻ አመናጭቃኝ አታውቅም።

በእርግጥ የምትፈልገውን ነገር ልታዝዘኝ ካልሆነ በቀር በፍቅር ወይ በክብርም አናግራኝ ማወቋን አላስታውስም፡፡
በደስታ፣በተስፋ እና ግራ በመጋባት መሃል ዋለልኩ:: በጥያቄ መዓት ተበታተንኩ፡፡ ተራ በተራ አፍ አፌን ብለው አባረሩኝ፡፡
ዓይኗን እንኳን መልሼ ሳላየው ተመልሳ ወደ አዲስ አበባ ሄደች።

ባልገባኝ ምክንያት ከዚያን ቀን በኋላ ከአባባ በቀር ሁሉም ያመናጭቀኝ ጀመር። ለምን የስጋቸው ክፋይ መሆኔ
እንዳሳፈራቸው ግራ ተጋባሁ:: ምንስ ቢሆን ደግሞ የእኔ ጥፋት ምኑ ላይ ነው? ከቀናት በኋላ አባባን እያለቀስኩ እውነቱን
እንዲነግረኝ ጠየቅኩት። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ከሆነ ጎረምሳ ጋር ተጣልታ ከባድ ጉዳት ስላደረሰችበት አስር ወር ተፈርዶባት መታሰሯን ነገረኝ። ማንም የተፈጠረውን አያውቅም፡፡ ሊጠይቋት ሲመላለሱ ማናቸውንም ለማግኘት ፈቃደኛ አልነበረችም። ፍርዷን ጨርሳ ወደ ቤት ስትመለስ መንገድ ላይ ነበር ምጥ የጀመራት:: ማናቸውም ማርገዟን ሳያውቁ እቤት እንደደረሰች ወለደችኝ፡፡ አባቷ ወግ አጥባቂ እና
ክብሩን ወዳድ ስለነበረ ተዋረድኩ ብሎ ያዙዙኝ ልቀቁኝ አለ፡፡
(ይሄን ሲነግረኝ በቁጭት ነበር) አንዲትም ቀን አላደረችም፡፡ለማንም ምንም ሳትል ከነደሜ ጥላኝ ጠፋች:: ከቤተሰቦቿ ጋር
መልሳ ስትገናኝ አድጌ በእግሬ ድክ ድክ እል ነበር። ሁሉም በዲቃላነቴ ደስተኛ ስላልነበሩ እናቴ መሆኗን እንዳላውቅ
የሰጠችው ማስጠንቀቂያ ተስማማቸው:: አብዛኛዎቹ የቤት አገልጋዮች እንደሚጠሩት ከስሜ የማስከትለው የአባባን ስም ነው:: የእኔ መወለድ ሌላ ሴት እንድትሆን እንዳደረጋት አባባ ሲነግረኝ ለቤተሰቡም ሆነ ለእናቴ ክፉ እጣ እንደሆንኩ ደጋገመልኝ እናቴ እኔን ከመውለዷ በፊት ከወንድ ልጁ ይልቅ በራስ መተማመኗ የሚያስተማምነው፣ ጎበዝ ተማሪ ስለነበረች ቤት ተከራይቶላት ከተማ የሚያስተምራት መኩሪያው፣ ትልቅ
ቦታ ትደርስልኛለች ብሎ የሚመካበት የዓይኑ ማረፊያ፣ ማንም ደፋር ቀና ብሎ የማያያት ጉልበተኛ እና ደፋር እንደነበረች
በትካዜ ፊቱ ደብዝዞ አወራኝ፡፡ እኔን ከወለደች በኋላ ጠፍታ ስትመለስ የማያውቋት ሌላ ሴት ሆና መምጣቷን ጨመረልኝ፡፡

"አባባ አባቴ ማን ነው?" አልኩት:: ምናልባት አባቴ ልጁን በፍቅር ክንዱን ሊዘረጋልኝ ይችላል ብዬ እያሰብኩ፡፡

"አናውቀውም:: ከእርሷ ውጪ የሚያውቅ የለም:: ስለአንቺም ሆነ ስለአባትሽ ጥያቄ ሲነሳባት ጣረሞት እንዳየ ሰው
ትንፈራገጣለች::” አለኝ፡፡

አባባ ከነገረኝ ያልተሟላ ታሪክ
👍2
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_አራት


#በሜሪ_ፈለቀ

እኔ ለተበደልኩ ይቅርታ መጠየቅ ግዴታዬ ሆነ፡፡ እናቴስ ልጇን የክዳችኝ ምንም ይሁን ምን ምክንያት ሊኖራት ይችላል ብዬ ላስብ ምናልባትም ክፉ ስለሆነች ነው ብዬም ልመን እንዴት ከቤተሰቤ ሁሉ ለለቅሶዬ ጆሮ የሚሰጥ አንድ አጣለሁ? እዚህኛው የጥያቄ ወለል ላይ ስቆም ነው የሽክርክሪቴ መሀለኛ ነጥብ እሷ መሆኗ የተገለጠልኝ፡፡

የታየኝ ጭላንጭል ብልጭታ እናቴጋ መሄድ ነበር፡፡ እናቴ መሆኗ ባያራራት እንኳን ሴት መሆኗ ለስሜቴ ቅርብ
ያደርጋታል ብዬ አመንኩ፡፡ በግዳጅ ተመልሼ ከገባሁበት የተፈሪ ቤት ጠፍቼ እናቴን ለማግኘት ሻንጣዬን ይዤ ወጣሁ። የህይወቴ ሰንካላ ሽክርክሪት መጀመሪያው ይህ ጉዞዬ መሆኑ የገባኝ
ሰነባብቶ ነበር፡፡ ተደብቄ ከአጎቴ ማስታወሻ ደብተር ላይ የገለበጥኩት የቤቷ ስልክ ቁጥር ላይ ደወልኩ፡፡ የነፃነቴ ቁልፍ፣የምስቅልቅሌ ፍቺ፣ የኑረቴ አዲስ ምዕራፍ፣ ዳግም ውልደቴ እሷ መሆኗን እየቃዠሁ በጉጉት ተሰቅዤ አገኘኋት። ከቅዠቴ ለመንቃት ደቂቃዎች በቂ ነበሩ፡፡ ያገኘችኝ ቦታ ጥላኝ አልሄደችም:: ወደ ቤቷ ወሰደችኝ፡፡ ባሏና የእንጀራ ልጇ መሆናቸውን ከነገረችኝ ወንዶች ጋር የቅብጠት ኑሮ ነበር የምትኖረው። ያላቸው ትስስር ጥብቀት ምን ያህል የተገመደ መሆኑን ባላውቅም አብሯት በሚኖረው የእንጀራ ልጇ ቀናሁ።
ስለእናቴ ልጠይቀው ተመኘሁ። ግን እድሉን አላገኘሁም።በእርግጥ ልጇ መሆኔን ለአንዳቸውም መንገሯን
እጠራጠራለሁ።ልጁ አብሯቸው ቢኖርም ብቸኛ ይመስላል፡፡ቤታቸው ውስጥ ለጊዜው ትኩረት ልሰጠው ያልፈለግኩት የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ ተሰምቶኛል፡፡

ምን ልታደርጊ መጣሽ?" ስትለኝ ፊቷ ላይ የነበረው መሸከክ ቢያስደነግጠኝም ምክንያቴን እስክነግራት ነው
ብዬ ራሴን አበረታሁ። የሆንኩትን ሁሉ ከዓይኔ የሚፈሰውን እንባና የአፍንጫዬን ንፍጥ በእጄ አይበሉባ እየሞዠቅኩ ነገርኳት።

"እና? እከክሽን እያከክሽ ከመኖር አይሻልሽም? ወይስ እድሜ ልክሽን በየአውድማው ከጎረምሳ ጋር እየተላፋሽ መኖር ነው የምትፈልጊው? ዝቀሽ የማትጨርሺው ሀብት ላይ ስለጣለሽ
ልታመሰግኚው ሲገባ አባቴን የምትኮንኚው ምን አድርግ ብለሽ
ነው?" ነበር ለለቅሶዬና ለብሶቴ መልሷ። ከዚህ በላይ ልትሰማኝ አንድ ደቂቃ አላባከነችም። በሚቀጥለው ቀን ተመልሼ ባሌ ያደረጉት ተፈሪጋ ለመሄድ እንድስናዳ ነገረችኝ፡፡

"እርሺው እኔ እስከዛሬ እናትሽ እንዳልነበርኩ ሁሉ ከዚህ በኋላም
እናትሽ ልሆን አልችልም።ሰበብ እየፈለግሽ ልታገኚኝ እንዳትሞክሪ።" የሚል ማስጠንቀቂያ አከለችበት። የተሰማኝ ስሜት አልነበረም።ምክንያቱም ደንዝዣለሁ። ከተቀመጥኩበት
ለመነሳት ሰውነቴ እንደወትሮው የሚታጠፍ የሚዘረጋ እስከማይመስለኝ በድኛለሁ። በጠዋት የቀሰቀሰችኝ የትራንስፖርት ገንዘብ ሰጥታኝ ከቤቷ ልታሰናብተኝ ነበር፡፡ለቀናት የማደርገውን ሁሉ የማደርገው አስቤ አልነበረም።

መላው አካሌ ከጭንቅላቴ ጋር እየተማከረ መንቀሳቀሱን እንጃ፡፡ ራሴን ከተፈሪ ጋር ያለኝን ኑሮ እያለማመድኩት አገኘሁት።ብቸኛው ፍቅርን ሊያሳየኝ የሚሞክር ፍጡር እሱ ነው።እውነቱን ነው ግን? እያልኩ አስባለሁ። ስለ ወለደችኝ ሴት ከማሰብ የላቀ የምሰራው የዛሬም ሆነ የነገ እቅድ ስላልነበረኝ እሱ የሚያቅድልኝን ውሎ እውላለሁ። መኪና መንዳት መማር፣የምግብ አሰራር ስልጠና ሙያ መሰልጠን፣ ከጓደኞቹ ሚስቶች
ጋር ተማክሮ ገዝቶ በሚያመጣልኝ ልብስና ጫማ ራሴን ለእርሱ ማስጌጥ፣ ፀጉሬን መሰራት እንዳለብኝ አሳስቦኝ በወጣ ቀን ጠዋት የራስ ቅሌን ለፀጉር ሰሪዎቹ እጅ መስጠት፣ ሊተኛኝ ፈልጎ ሲያላዝን በጀርባዬ ተጋድሜ እግሮቼን መክፈት፣በስራ ሰበብ ሲወሰልት ያደረ ቀን በጠዋት ገዝቶ የሚመጣው በግ መስራት.....(አይነግረኝም።አውቃለሁ።
እንደማውቅ ያውቃል።መፀፀቱን አያቆምም።መወስለቱንም እንደዛው። ከሌላ ሴት ጋር ማደሩን ማወቄ ግድ አይሰጠኝም ነበር፡፡ ምናልባት ለእርሱ ግድ ስለሌለኝ አልያም ለራሴ ግድ
ስለሌለኝ ወይ ደግሞ በሆነች የሀሳቤ ጥግ ሌላ ሴት ለመፈለጉ ምክንያት የራሴ መበደን መቀበሌ ይሆናል የዓመታት ባሌ ከሌላ ሴት ጋር በማደሩ ለሚሰማው ፀፀት ማስተሰሪያ የበግ ደም ማፍሰሱን መቀበሌ።)

በራሷ ጭንቅላት የምታስብ ሴት መሆኔ ጠፍቶ በተፈሪ ባወጣልኝ የእለት መመሪያ የምንቀሳቀስ ሮቦት ለመሆን የፈጀብኝ
ጥቂት ወራት ነው። ተፈሪ በስራው ምክንያት ከከተማ እስካልወጣ ድረስ ቀላል ግልፅ እና ተመሳሳይ የአስራ ስድስት ዓመት ውሎ...
የሚወደውን ምግብ ማብሰል፣ ሱቅ ወጥቶ የሚያስፈልግ ነገር መገዛዛት፣ እሱ እንድሆንለት የሚፈልጋትን ንፁህና ዘናጭ ሴት ሆኜ መጎለት፣ እላዬ ላይ ራቁቱን
እየተወዛወዘ መቼ ልጅ እንደምወልድለት ሲነዛነዝ መስማት፡፡
በራሴ ጭንቅላት የማደርገው ብቸኛ ነገር ለእናቴ ስልክ እየደወልኩ በስልኩ ሞገድ ድንዛዜን ማጨድ ብቻ ነው:: የተለየ
ነገር ከአፏ እንዲወጣ በመናፈቅ ሳልታክት ደውልላታለሁ።ከሚቆጠሩ ቃላት የዘለለ አታናግረኝም። ለምጠይቃት ጥያቄ
መልስ አትመልስልኝም። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ባሏ ነኝ ያለ ሰውዬ በዚያ ስልክ እንደማላገኛት ነገረኝ፡፡ ደጋግሜ ብደውልም መልሱ ተመሳሳይ ነበር፡፡ የሆነ እለት እንደአበደ ሰው ተነስቼ
ቤቷ ሄድኩ፡፡ ከቤቷ ከወጣች መሰንበቷን ባሏ የነበረው ሰው እየተነጫነጨ ነገረኝ። የት መሆኗን ሊነግረኝ አልፈለገም ከብዙ ወራት በኋላ በተለመደ ውሎዬ መሃከል ያልተለመደ ስልክ ጥሪ አስተናገድኩ፡፡ አባባ ነበረ። ድምፁን ስሰማ እስከዛ ቀን ድረስ ደህንነቴ ወይ ምቾቴ ግድ ሰጥቶት ደውሉልኝ አለማወቁን እረስቼ ናፍቆቴን ገለፅኩለት: የአቧራ ብናኝ ያህል ግድ
አልሰጠውም:: የእናቴ ባል ስለሞተ ለቅሶ እንድደርስ ነገረኝ። ሟች ባሏ ድጋሚ እሷን ለማየት ምክንያት ስለሆነኝ መሞቱ
አስፈነደቀኝ፡፡ ከተፈሪ ጋር ለቅሶ ለመድረስ ሄድን፡፡ ዘመዶቼ ለቅሶውን የነገረኝ አባባን ጨምሮ ማንም ያለመምጣታቸው
አስገረመኝ፡፡ ድንኳኑ ውስጥ ለሟች ባሏ አምርራ ስታለቅስ ሳያት ድፍርስርስ ያለ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ለባሏ ስትነፋረቅ ሳያት
ቅናት አነደደኝ፡፡ ለደንዳና ልቧ የሰጠሁት አንዱ ማስተባበያዬ ፉርሽ ሆነብኝ፡፡ ለአፍታ ተፈጥሮዋ ድንጋይነት እንደሆነ ሳምን መሰንበቴ ተሰረዞ ሌላ ነገር የገባኝ መሰለኝ፡፡ ሴትየዋ ከኔ ውጪ
ላለ ሰው ልቧ ስጋ እና ደም ነው ብዬ አሰብኩ፡፡ የሟች ልጅ ነው ያለችኝ ወጣት በአባቱ ሞት ያዘነ አይመስልም። እንደታዛቢ ለቀስተኛውን ይገረምማል:: አመሻሹን የለቅሶ ግርግር ሲበርድ
ጠብቄ ባገኘኋት ስንጣቂ አጋጣሚ ተጠቅሜ እያቀፍኳት ምን ያህል እንዳዘንኩ የልቧ በራፍ ያስጠጋኛል
ብዬ በተለማመድኳቸው ቃላት ነገርኳት። ለደቂቃ በእውነታ የሌለሁ የምቃዥ መሰለኝ፡፡ መልሳ አቅፋኝ አመሰገነችኝ፡፡ ካገባሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ከተፈሪ ጋር እንደቅርብ ሰው ስለእርሷ እቅፍ
ንዝረት አብራራሁለት:: ከድንኳኑ ይዤው ወጥቼ ስለእኔ የማያውቀውን ታሪክ በደስታ እየፈነደቅኩ ነገርኩት፡፡ በደሜ
የሚንቀለቀለው እሳት የገባው መሰለኝ:: ባይገባውም ግድ አልነበረኝም። እናቴ ባቀፈችኝ በዛች ደቂቃ ዓለም ቀጥ ብላ
የተፈጥሮ ዑደቶች “ሀ” ብለው አዲስ ቀመር መቀመር እንደጀመሩ ነው የተሰማኝ፡፡ ደስታዬ የተጋባበት መሰለ። ወደ ድንኳኑ ስንመለስ ጨለማው ውስጥ የሳቅ ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ፡፡ ምን አስቤ እንደሆነ አላውቅም ተፈሪን በቆመበት ትቼው ወደ ሰማሁት ድምፅ ተራመድኩ፡፡ እናቴ ናት፡፡ ቅድም የነፍስ አባቷ መሆኑን ሲያወሩ ከሰማሁት ሰው ጋር ጨለማው ውስጥ እየተላፉ ይሳሳቃሉ። የነፍስ አባቷ አፉን ድንቅፍ እንኳን አይለው ከሟች በመገላገላቸው የጀመሩትን የድብቅ ፍቅር
👍2
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በሜሪ_ፈለቀ

እባክሽ ተይኝ! ሳይሽ የሚሰማኝ እንደዛ ነው። እርሺኝ፡፡" አለችኝ የእናቷን ለቅሶ አብቅታ ልትመለስ የተነሳች እለት። የምትናገረኝ ሁሉ ለምን ተስፋ እንደማያስቆርጠኝ አይገባኝም።

ከዓመታት በኋላ ስለእርሷ በማሰብ መታተሬን ለማቆም በምታገልበት ወቅት ነው ታማ መተኛቷንና ልታየኝ መፈለጓን
በመልዕክተኛ የላከችብኝ፡፡

አመሻሽ ላይ ታክሲ ተሳፍሬ ሆስፒታሉ ደጅ የሄድኩት የመኪና ማቆሚያው ጋር የተውኩትን መኪና ለመውሰድ ነበር፡፡ ራሴን ያገኘሁት እናቴ የተኛችበት ክፍል ውስጥ ነው።ማንም የለም። ተመልሼ ዓይኗን የማየት ምንም ሀሳብ በጭንቅላቴ አልነበረም፡፡እዛ ስላየችኝ እንዳልተገረመች ሁሉ የተለየ ገፅታ አላሳየችኝም።
ከለመድኩት በተለየ ዓረፍተ ነገር አልነበረም አፏን ያላቀቀችው።

"ደሞ ምን ቀርቶሽ መጣሽ?"

አልመለስኩላትም። እዚህኛው የስሜት ወለል ላይ ቆሜ ለሷ ያለኝ ስሜት ፍቅር ይሁን ጥላቻ ተዳቅሎብኛል፡፡ ምናልባት
እሷን እየወደድኳት በመሰለኝ ጊዜ ሁሉ ራሴን አጥብቄ እየወደድኩ ይሆናል፡፡ በሷ ፍቅር የእኔን የመኖር መሰረት ላመጣል ይሆናል ፍቅሯን የሙጥኝ ያልኩት:: መራርነቷ ቀደምስሬ ትኩስ ደም ሆኖ ሲያግለኝ አካሌ የተወጣጠረ አይነት
ስሜት ተሰማኝ፡፡ ተራራ የሚያክል ምክንያት ቢኖራት እንኳን በዕድሜ ቁጥሯ የሰናፍጭ ታክል ቅንጣት መራር አስተዋፅኦ
ያላበረከትኩ እኔን ለመጥላት እና ቀኖቼን በጥላቻ ለማመሳቀል በቂ እንደማይሆን እያሰብኩ የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ተኝታ ሳያት
"ከእሷ ሰንሰለት ራሴን ነፃ ማውጣት አለብኝ፡፡" አልኩት ራሴን::
ያሰብኩትን ባሰብኩ ቅፅበት እጅና እግሬ ለመተግበር ተዘርግተዋል፡፡ የማደርገውን ነገር ውጤት ለማሰላሰል የተረፈ
ስንዝር ክፍተት ጭንቅላቴ ውስጥ አልተረፈም።ጭንቅላቴ በብስጭት በፈላ ደም ብቻ የተሞላ ይመስለኛል፡፡

ያደረግኩት ነገር ሀጢያት ይሁን ፅድቅ ግድ አልነበረኝም።ፅድቅና ሀጢያትን ከህሊናዬ ውጪ የት ተማርኩት? ህሊናዬ
የቸረኝ ትልቁ ስጦታዬስ_ዘብራቃ ቀኖችን ብቻ አይደል?ላደረግኩት ድርጊት ስም መለጠፍ አላሻኝም:: ብቻ ግን
የሆስፒታሉን ቅጥር ጊቢ ለቅቄ ስወጣ መቼ እንደሳቅኩ የማላስታውሰውን ድምፅ ያለው ሳቅ ሳቅኩ: በመኪናዬ መስኮት
እየገባ ጉንጨን እየዳበሰ እና ፀጉሬን እየገለበ ከሚያባብለኝ ንፋስ
ጋር እየተጫወትኩ እቤት ስደርስ ተፈሪ ሳሎን ተቀምጦ በቴሌቭዥን ተከታታይ የአማርኛ ድራማ እያየ ነበር።
በደመነፍስ ወይም ለእርሱ ብዬ ያደረግኩት ነገር አልነበረም።ልብሴን አወላልቄ ስጨርስ የእርሱን የሚቀጥል እርምጃ አልጠበቅኩም:: ያለማቋረጥ እየፈገግኩ መሆኔ ይታወቀኛል።
በሁኔታዬ ግራ መጋባቱን ሳይደብቅ የራሱን ልብሶች በመግፈፍ አገዘኝ፡፡ ግራ ቢጋባም ልብሴ ወልቆ ካየኝ ምክንያትና ድርጊት ለማሰብ የሚተርፍ ጭንቅላት እንደማይኖረው አውቃለሁ።በራሴው የውዝዋዜ ስልት አብረን ጮቤ ረገጥን፡፡ ሳቃስት ራሴን መስማቴ መልሶ አስፈገገኝ።

"መቼ ነው ልጅ የምንወልደው? ልጆች እንዲኖሩን እፈልጋለሁ::" የተለመደ ውትወታውን ከወንድ ርጭቱ እና
ከረዥሙ ትንፋሹ ጋር ደምሮ ጠየቀኝ።
በፍፁም እናት መሆን አልፈልግም በፍፁም ልጅ አይኖረኝም።" ለመጀመሪያ ጊዜ መለስኩለት ፈ።

ለምን? ለምን? ከኔ መውለድ ነው የማትፈልጊው ?"

"አይደለም።እናት ምን እንደሆነች አላውቅም እናት መሆን የምችል አይመስለኝም:: እናት የማልሆነውን ልጅ ወደዝህች ምድር ማምጣት አልፈልግም::" መልሴ አጥጋቢ ሆኖለት ይሁን ደስታውን ላለመበረዝ ርዕሱን መቀየር ፈለገ፡፡

"የዛሬው ነገር ማለቴ የማላውቃት ሴት የሆንሽበት ሚስጥር ምንድነው?" ሲለኝና የበር መጥሪያው ሲጮህ አንድ ሆነ፡፡

“ነፃነቴን አገኘሁ::" አልኩት ልብሶቼን እየለባበስኩ፡፡የሚቀጥለውን ጥያቄ ከአፉ ላይ አስቀርቶት ልብሱን እንደነገሩ
ደራርቦ በር ሊከፍት ወጣ፡፡

"ወይዘሮ ማህሌት አጥጋቢ በወይዘሮ ወለላ አጥጋቢ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል::" አለ ተፈሪን አጅበውት ወደ ቤት ከዘለቁት ሶስት ፖሊሶች አንደኛው ወደ ፊት ጠጋ ብሎ፡፡

ስህተት መሆን አለበት። በጭራሽ እሷ ሰው አትገድልም:: ከኔ ጋር ነበረች። ስህተት ነው::" ይላል ተፈሪ ተራ በተራ ፖሊሶቹን እያየ:: ወደእኔ ዞሮ ማረጋገጫ ይጠብቃል።

ስህተት አይደለም:: ገድያታለሁ:: እራሴ ነኝ የገደልኳት፡፡ አንቄ ነው የገደልኳት:: ለፖሊስ ደውዬ ያሳወቅኩትም ራሴ ነኝ!"
ካደረግኩት በላይ ፀፀት እንደሌለብኝ እንዲታወቅልኝ የተናገርኩት ነበር፡፡ በመጠኑም እንደ አብሪ ትል ብልጭ እያለ
የጭንቅላቴ ክፍል ከፀፀት ነፃ የተናገርኩት ይመስለኛል።

እጆቼ በብረት ካቴና ተቆልፈው ወደ እስር ቤት እየተወሰድኩ እየተሰማኝ ያለው ወደ ነፃነት ዓለም እየሄድኩ እንደሆነ ነው።
የሰው ልጅ ዓለሙ ያለው ጭንቅላቱ ውስጥ መሆኑ የገባኝ በጭንቅላቴ ማሰብ ስጀምር ነው።ወደ ሚታየው ዓለም ተርጉሞ የሚኖረው በጭንቅላቱ የሰራውን ዓለም መሆን አለበት።ጭንቅላቴ ውስጥ አዲስ የተገነባው ዓለም ነፃነት ያለበት እና
ጥያቄ አልባ ሲሆን የእስር ቤቱ መሬት ከተፈሪ ሶፋ በላይ እንደተመቸኝ አይነት እና በዙሪያዬ የማየው ሁሉ ድሎት ሳለ
በውስጤ ያረጀው ዓለም ጥቀርሻነት ሳቅ ከፊቴ እንዳሸሽብኝ አይነት:: በእርግጥ በሚዳስሰው ዙሪያችን የራሳችንን ዓለም
መገንባት ረዥም ዕድሜን እንደሚፈጅ ሁሉ በጭንቅላታችን ውስጥም ጥቃቅን መሰረቶችን መጣል ሳይቀር የረዥም ጊዜ
ድልዳል ነው:: ገዳይ መሆንም ጭምር!!!! ዳኛው የእስር ዓመቴ ሀያ ዓመት መሆኑን በሞዶሻቸው ጠረጴዛውን በኩርኩም
ነርተው ሲያውጁ በነፃ ያሰናበቱት ወንጀለኛ ገፅታ ነበር ፊቴ ያጋለጠው።የምጓጓለት ቀሪ ኑሮ የለኝምና ነው:: የታሰርኩ ሰሞን ተፈሪ በየእለቱ ይጠይቀኝ ነበር። ሁሉም ሰላም እንደሆነ እና ከወህኒው ጊቢ ማዶ የሚያጓጓኝ የኔ ዓለም እንደሌለ አምኜ እንደደረስ ጎረምሳ በፉጨት ቀኖቼን እየተለማመድኩ ሳለ
ከዓመታት በፊት ያየሁት የእናቴ የእንጀራ ልጅ ከሌላ አንድ ወንድ ጋር እና ሁለት ሴቶች ጋር ሊጎበኘኝ መምጣቱ ከመገረም
በላይ የማይታመን ነገር ሆነብኝ፡ አጠገባቸው ደርሼ ከመቆሜ ከሴቶቹ ጋር ተደጋግፈው በቆሙት አቋቋም ጥንድ ጥንድ መሆናቸው ገባኝ፡፡ ያልገባኝ ምን ሊሰሩ እንደመጡ ነው፡፡....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_ስድስት (የመጨረሻ ክፍል)


#በሜሪ_ፈለቀ

...ሰላም?” አልኩኝ የማውቀው ፊት ላይ አፍጥጬ።ብዙም ደቂቃ አላባከኑም ወንዶቹ ወንድሞቼ መሆናቸውንና ሴቶቹ
ፍቅረኞቻቸው መሆናቸውን ሲነግሩኝ አልጋ ላይ ሆኜ እየቃዠሁ አለመሆኔን ደጋግሜ ራሴን ስጠይቀው:: ለምን ነበር ወንድሜ መሆኑን እንዳውቅ ያልፈለገችው? ይህቺ ሴትዮ በስንቱ ነው
የምትበድለኝ? ስትሞት ጥያቄዬ ሁሉ አብሯት የሞተና ከዚያ በኋላ መቼም የማያስጨንቀኝ መስሎኝ ነበር፡፡ ነገር
ግን በተቃራኒው ሆነ፡፡ ሞታም ይኸው ግራ እያጋባች ታቀውሰኛለች።
ከተለያየ ወንዶች የወለደቻቸው ሁለት
ወንድሞች አሉኝ፡፡ ምናልባት ሌሎችም ይኖሩ ይሆናል፡፡ምክንያቱም እነርሱም እህት እንዳላቸው ያወቁት ስለገደልኳት
ነው። ሴትየዋ ማን ነበረች? ምንስ ነበር ትርፏ?

ብዙ ዓረፍተ ነገሮች ሳያባክኑ የተረዳሁት ለእነርሱም ጥሩ እናት እንዳልነበረች ነው። ከፍቅራቸው ገዝፎ ጥላቻና መከፋታቸው
ይታያል። ክልሱ ወንድሜ (ኪሩቤል) በተሻለ ፍቅር ነበረው። ስለገደልኳትም ማዘኑን አልደበቀኝም። ታላቃቸው ነኝ
ኪሩቤልን በሶስት ዓመት እበልጠዋለሁ። ቅዱስን በአስራ አንድ ዓመት።
እየተቅለበለበች የምታወራው የቅዱስ ፍቅረኛ በምሰማው ነገር እየተሰማኝ የነበረውን ስሜት ውል መያዝ
እንዳልችል ታስፎርሸኛለች፡፡ የራሷንም የእርሱንም ደምራ በሚቅበጠበጠው መላ አካሏ እየታጀበች የምታወራው እርሷ
ናት። አንዲትም ቃል ሳልተነፍስ የመጠየቂያ ሰዓቱ አልቆ ከመግባቴ በፊት ኪሩቤል እግሩ ስር አስቀምጦት የነበረውን ካርቶን እየሰጠኝ ይሄ አንቺ ትፅፊላት የነበሩት ደብዳቤዎች ናቸው። ከአጠገቧ ተለይቷት አያውቅም። ሆስፒታል እንኳን አብረዋት ነበሩ።
ያንቺ መሆኑን ያወቅነው ከሞተች በኋላ
ነው። ለነዚህ ደብዳቤዎች ፍቅር እንደነበራት አውቃለሁ። እያነበበች
ትንሰቀሰቅ ነበር። ምናልባት የምትፈልጊው ከሆነ ብለን ነው።"
አለኝ፡፡ የነገረኝ ነገር እኔ ውስጥ የሚፈጥረውን ውስብስብ ሳይረዳ፡፡

"ከእኔ ከልጇ በላይ አንቺ የምትፅፊላት ደብዳቤ ትርጉም ነበረው።ማን መሆንሽን ሳላውቅ ብዙ ጊዜ ቀንቼብሻለሁ::" አለ እስካሁን ከንግግር የተቆጠበው ቅዱስ፡፡ በስልክ ላገኛት ባለመቻሌ እቤቷ የሄድኩ ጊዜ ባሏ ነበረ የፖስታ አድራሻዋን የስጠኝ፡፡ ታንብበው አታንብበው እንኳን ሳላውቅ በየወሩ እፅፍላት ነበር፡፡ አንዳንዴ
ባታነበው እንኳን የውስጤን እየተነፈስኩ ስለሚመስለኝ መፃፌን አላቆምም ነበር። ስለእርሷ ለመርሳት መሞከር በጀመርኩ ጊዜ ከጥቂት ዓመታት በፊት ነው መፃፌን ያቋረጥኩት፡፡ተሰናብተውኝ ከሄዱ በኋላ ምን ማሰብና የቱን ማመን እንዳለብኝ
ግራ ተጋባሁ። ትወደኝ ነበር? ትጠላኝ ነበር? ትፀፀት ነበር? የትኛው ነበር ልኩ? የምታሳየኝ ጥላቻ ወይስ የደበቀችኝ ፀፀት?ለቀናት በጥቅጥቅ የጥያቄ ጫካ ውስጥ ተቅበዘበዝኩ። ጠፋሁ። መውጫው የማይገኝ ሆኖብኝ ባተትኩ። ማን ነበረች ይህቺ ሴትዮ?

ኪሩቤል አዘውትሮ መምጣቱን በቀጠለ መጠን ስለእርሷ የሚነግረኝ ነገር ሌላ የማላውቀው የእርሷ ገፅታ ነው።ሁሌም
በመጣ ቁጥር በሞቷ እናቱን እንዳሳጣሁት ይወቅሰኝ ስለነበር
በአንዱ ቀን የበደሌን ግዝፈት ልከምርለት አፌን ለማላቀቅ ተገደድኩ፡፡ የረጋ ቀልብ ያላት ፍቅረኛው በእንባዬ ጠብታ ልክ
እንባዋን እያፈሰሰች ስትሰማኝ እርሱ በጭንቀት ሲንቆራጠጥ ቆይቶ ምንም ቃል ሳይተነፍስ ሄደ፡፡ ለወቀሳው የመጨረሻ ቀን ሆነ፡፡ በፍቅረኛው ተገዶ የሚመጣ የሚመስለኝ ቅዱስ አልፎ
አልፎ ቢመጣም እርሷ ታወራለታለች እንጂ በዝምታ ሰዓቱን ጨረሶ ነበር የሚሰናበተኝ። በቃላት ባይናገረውም አምርሮ እንደሚጠላት መደበቅ አይችልም።የሁሉም ዑደት አንድ ጫፍ ላይ ገተረኝ ማናችንም ሴትየዋን አናውቃትም ልናውቃትም አንችልም። እንቆቅልሽ ነበረች:ፈ።ከነእንቆቅልሿ ተቀብራለች።ይሄን እያሰብኩ የእስር ቤት ቀኖቼን ልረሳት እራሴን እመክራለሁ፡፡ ወንድሞቼ እና ፍቅረኞቻቸው ሲመጡ ወጥቼ ሳገኛቸው ስለእነርሱ የሚሰማኝን ስሜት እፈትሻለሁ። በየእለቱ ተፈሪ ሊጎበኘኝ ሲመጣ አግብቶ እንዲወልድ እነግረዋለሁ።የታሰርኩ ሰሞን በየእለቱ፣ ጊዜው ሲገፋፋ በሁለት ቀን፣ ሲዘገይ
በሳምንት፣ ከራርሞ በወር፣ ሰነባብቶ ጭራሹኑ ቀረ።

ከእያንዳንዱ ክፋት ጀርባ መሪር በደል አለ እያልኩ አስባለሁ።ጥያቄው የሚሆነው በደልን ይቅር ያለ በጎነት የለም ወይ?
የሚለው ነው። ኖሮ ያውቅ ይሆናል፡ በደልን ይቅር ለማለት የሚያስችል ትልቅ በጎነት የሚፈጥር ፍቅር የሚጠይቅ
ይመስለኛል። የገባኝ በዛ መጠን በልቤ የተንሰራፋ መልካምነት መፍጠር የሚችል ከተበደልኩት ልቆ የሚገዝፍ ፍቅር የለኝም። እናቴን ልገድልበት የቻልኩበትን ቅፅበት ሳስብ በሰውኛ ምክንያት
ከመግመድ አይሎ ቅፅበታዊ ስሜት መላው አካላችንን የሚያዝበት አጋጣሚ መኖሩን ነው። ከታሰርኩ ከብዙ ወራት
በኋላ ጠየቂ እንደመጣልኝ ፖሊሷ ነገረችኝ፡፡ ከወንድሞቼ አንዳቸው እንደሚሆኑ እያሰብኩ ስወጣ ፖሊሷ የጠቆመችኝ ያለዛሬ አይቼ የማላውቀው ትልቅ ሰውዬ ነው።

"አላውቅህም!" አልኩት እንደሚሰማኝ ሳረጋግጥ፡፡

“እኔን ማወቅሽ አይደለም እዚህ ያመጣኝ ማወቅ የምትፈልጊውን ነገር እኔ ማወቄ ነው።” ያለኝ በትክክል አልገባኝም፡፡

"እኔ ማወቅ የምፈልገው ነገር የለም።" አልኩት ከሚቀጥለው መልሱ በኋላ ትቼው ልሄድ ራሴን እያሰናዳሁ።

"እናትሽን አውቃታለሁ፡፡ እንዴት እንዳረገዘችሽም አውቃለሁ።"
አለ ስሜቴን ከፊቴ ላይ እየበረበረ::
"ማወቅ አልፈልግም። ጥያቄዬን ከእርሷ ጋር አብሬ ገድዬዋለሁ።" ብዬው እየሸሸሁ መሆኔ እየታወቀኝ ጥዬው ለመሄድ ዞርኩ፡፡

"ከማን እንደወለደችሽስ ማወቅ አትፈልጊም?" ቀጥ አልኩ።ምንም ያህል ብታገል አባቴን ለማወቅ የሚላወሰውን ፍላጎቴን መገደብ አቃተኝ። ተመልሼ አጠገቡ ደረስኩ።

"እናትሽን በአንቺ እጅ ተገድላ መሞቷን ስሰማ የነበራችሁን ግንኙነት ማጣራት ጀመርኩ። ላንቺ፣ ለእናትሽ፣ ለራሴ
ማናችንን ነፃ እንደሚያወጣ ባላውቅም እውነቱን ልነግርሽ እንደሚገባ ወሰንኩ።" መጨማደድ የጀመረ ግንባሩን እያኮራመተ ይለጥጣል፡፡ የወሬ ማጀቢያው ትዕግስቴን እየተፈታተነው ነበር፡፡

ቀጥታ መልሱን ንገረኝ አባቴ ማን ነው?"

"እናትሽ እስር ቤት ውስጥ ተደፍራ ነው ያረገዘችሽ፡፡ ቁጥራቸው የማይታወቅ ጠባቂዎች ናቸው የደፈሯት። የማንኛው ልጅ መሆንሽ አይታወቅም፡፡ በወቅቱ እዛ ፖሊስ ነበርኩ፡፡ ስናገኛት ራሷን አታውቅም ነበር፡፡ ለወራት ስትታከም ቆይታ ነው
የዳነችው። ከባድ ስቃይ ብታልፍም የአካል ቁስሏን ድናለች።ከዛን ዕለት በኋላ ክንፏን የተሰበረች ወፍ ሆነች:: ......"

ማውራቱን ቀጥሏል... ጥዬው ገብቻለሁ።

💫ተ..ፈ..ፀ..መ💫

Like 👍 #Share እያደረጋቹ ይሄ ቢያልቅ ሌላ እንጀምራለን ግን የናንተ አስተያየት ወሳኝ ነው ስለ ድርሰቱ ስለ ቻናላችን ምን ይጨመር? ምን ይቀነስ? ያላችሁን አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን። አመሰግናለው🙏
👍5