ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አያስታውቅም_ወይ

በከረረ ጥፊ ፥ ጆሮዬ ሲናጋ
በቡጢና ጡጫ ፥ ገላዬ ሲለጋ
በበላዬ ሰፍረሽ ፥ ልክ እንደ ግመሬ
መላወሻ ባጣ ፥ መሬት ተዘርሬ
#ኡ.... #ኡ.....ብዬ ጮኬ
ጎረቤት አውኬ
በሰለለ ድምፄ የተደናገጡ
#ተግተልትለው መጡ
ከወረደው መአት ፥ ከጭን ሰው ሊያወጡ
ከመቅፅበት ግና ፥ ቤታችን ሲደርሱ
ገላዬን አሳፍሮ ፥ገላሽ መገንደሱ
ከበላይሽ ሆኜ ፥ ቢማትሩ ግዜ
#በእግዜር ተዋት አሉኝ
#ማሪው እንደማለት
ተራዱኝ ያልኳቸው ፥ ቦታዬን በማየት
ዳሩ...ምን ያድርጉ
ባይገባቸው እንጂ ፥ ቦታዬና ቦታሽ
ያስታውቅ ነበር ፥ አንቺ እንዳልተመታሽ ።

#ተበላው ( 😔😔😔 )

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
#ውሎ

ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ...
እስኒከር ተጫምታ ...
ቲሸርት በቁምጣ ....አዘንጧት ፈክታ
አጭር ፍሪዝ ፀጉሯን
አለፍ አለፍ... ብላ ብራውን ቀብታ
ቅሪላ ለማልፋት ....ኳስ ሜዳ ተገኝታ
ሹሌ ሲሏት ሹሌ...
ቴዘር ሲሏት ቴዘር
እንዳማራት ውላ ....ባማራት ስታድር
ሲሻትኝ በቴስታ....በደም የምትነክር
#ወንዳ_ወንድ_ሴት_ልጅ....
በሴት ተክለ ገላ...ያባቷ ዘረመል ...ለወንድ ሲያሾራት
የሰፈሯ ወንዶች ....ለጉድ ነው ሲወዷት
ሴት ወንድማቸውን....አይሹም ሊከፋት...
ልክ....እንደ ብርቅዬ....
#ሙድና ወንድነት...ባዲስ ቃና ጣዕም..ከፍቅሯ ሲቀዳ
ሽር ብትን....እንጂ ...
በሰፈር....በሜዳ
በፊቷ ለመቅሸም
መሰገጥ አይቃጣም ...ምርጥዬ እና አራዳ ።

#ሴት...እንዲሁም ሴት ናት....
ከጥንቱ ሲፈጥራት
እሬት...እሬት ያለ ...በኮሶ የታሸ...የሰለቸ ኑሮ
ሳያጩ...ሳይቋጩ......ከመአት ተምሮ
ለሆነች ሽራፊ ለደቂቃ ውሎ
...#ሀይ...#ባይ.....ለማለቱም... ሴት ያገኘ ግዜ
#ስሜቱ_ግልፅ_ነው
እለቱን ላበራ...በእንስቶች ፀጋ… ያለም ድንዛዜ
እናም ይችን ፍጥረት...ስጦታው ሳያንሳት
ዳግም አክሎባት
በወንድ አረማመድ ፥ ከወንዶቹ ጀማ ፥ እግሯ ሲወክላት
ድድ ማስጫው ዙሪያ....ካሉት ወንዶች ጋራ ፥ ባንድነት ስናያት
#በተመስጦ_አይኔ.......
መምጣቷን ወድጄ....አመጣጧን ስታዘብ
ከወንዶቹ ግንባር ....ይህ ነው #የሚነበብ
ሰላም ከማለቷ....
ውሀ የሚጠብሰው፥ አፈ ጮሌው ጀለስ
ምላሱ ይሰንፋል
ቀደም ቀደም ሲል ፥ ሾርኒዋን ፍራቻ ፥ ከማሸሞር ያርፋል
ፀበኛውም ጓዴ....
ይመችሽ እያለ.....ቴስታዋን ይሸሻል
የቀለደች...እንደው...
የከበበው ጀማ " #ዋህ " ብሎ ይፈርሳል
ካራዳነት ሰፈር...
እያመቻመቹ...በጓደኝነት መስክ ...ዘመን ይታረሳል
ልርሳህ...ቢሉት እንኳ..........ይህ መቼ ይረሳል
እድሜ ለሰጠው ሰው ....እንዳጀብ ይወሳል።

በዚህ...በኛ ሰፈር....
ከቤቴ....ፊት ለፊት
የለመድኳት ... #ቆንጆ......
ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ....አርቃኝ ከጎጆ
ከሰፈሬ ወንዶች....ከጀማው ከትሜ
ስትስቅ...ስቄላት
ስትነሳ....ቆሜ
ድፍረት ለለበሰው ...ውበቷ ታምሜ
በለት እየናረ .... ተሸርፎ አልቆ ቅስሜ
አይኖቼን ...አንብባ ፥ መውደዴ እስኪገባት
ካራዶች ጉባኤ....ከድንጋዩ አግዳሚ
የሷ ጋሻ ጃግሬ....የፍቅሯ ታማሚ...
እኖራለሁ እንጂ.....ሰርክ ስከተላት
ወንዳ ወንድ ውቤን ....ፍቅሬን ስመግባት
ደፍሬም...አልደፍር....
አፍሬም...አላፍራት..
ሳፈቅራትኝ ልኑር....እኔን ሳስለምዳት ።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
#ዝክረ_ቫለንቲኖ

በሮማኖች...አገር
ይሄውልሽ #ውዴ...በፊት ድሮ ድሮ
ሴት ሴቱን ሲከተል ፥ በዘቡ ተማሮ
ንጉስ... #ክላውዲዎስ
ለክተት ዘመቻ....
#ልጄን #ሚስቴን...በሚል ስስት እያነቀው
እንዴት ነው ጦረኛ ፥ ላገር የሚወድቀው ?
ብሎ ስለራደ...
ተባእቱን ሁላ.... ከተራክቦ አገደ
አሻፈረኝ ያለ .. #ሰማዕቱ_ቄስም
በንጉሱ ፈቃድ ስለተናደደ
#እስከተቀላበት...ህይወቱ እስካለፈ
በሚስጥር ፥ ስንቱን ጥንድ ፥ አጋብቶት አረፈ
እናም ዛሬ ዛሬ.......ባገርሽ ፣ ባገሬ
ቀይ....ቀዩ #ነገር ......እየተማገደ
ቫለንቲኖን ማሰብ ....ስለተለመደ
ምን ከኔ ባትኖሪ...
የት እንደሆንሽ እንኳን ፥ ባይጠረጠርም
ግራ ጎኔን #ለራት...ለደስታው ባልቀጥርም
እስክትመጪ ድረስ
#በቀይ ደምቄ........ቤቴን አሸብርቄ
አንቺ መናፈቄ
አስቤሽ መዝለቄ
በ ከማን አንሼ...እንዲያው ለነገሩ
ከማላውቀው አገር ፥ የነበሩት አባት ፥ እንዲህ ሲዘከሩ
ለማላውቅሽ አንቺ
#happy_valentine ...
የተባለ ምኞት ፥ ምኑ ላይ ነው #ነውሩ?

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

" #Happy_valentine_my_Love "
( #ባለሽበት_ቦታ)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
1👍1
#ያልተወለደ ... #ቃል

ከ ደብሬ ቅጥር....
ላርባ ፆም ምህላ...
ነጠላ ለብሼ ...ካንጋፋ ዛፍ ጥላ...
#ሽው....#ሽው....ከሚለው አፀድ
ከሚንቆረቆረው
የወፍ ዜማ ሞገድ...
ስርአተ ቤተስኪያን....አብሮ ተጨምሮ
በታንቡሬ መስኮት ...
ያገልጋይ ጥዑም ቃል...ሰናይ ተንቆርቁሮ
አቤቱ....የሚሉት ቃል
አለወትሮ ከበደኝ...
እማፀነው ዘንዳ
የት ብዬ ጅማሮ ፥ ማሰሪያው ጨነቀኝ።
ይሄንን እሱም ታዝቧል....
የሆዴ #ጉትምትም
ምን ቃል እንዲወጣው ፥ አፌን ይጠብቃል
እኔም ቃሌ #ታንቋል...
የምላሴ ፍሬ ...ወረቴ እንደሆነ ..ልቦናዬ ያውቃል።
መቅሰፍት የሞላውን ፥ የህይወትን ጋሪ እንደተሳፈረ
አለም ሰፊ መስሎት የተደናገረ
ያልጠረጠረ ነው..... የተመነጠረ
ይላል የውስጤ ቃል...
ሺዎች የበላ አፈር ...አዕላፍ ይጠብቃል
ለዛሬው ይመስገን....ለነገ እርሱ ያውቃል

#ምርምረ.... #ፀሎት

የኔና እሷ ፍቅር .....ጣፍጦልን በለዛ
ከንፈር መሳም አልፈን
ጉልቻ ሳንጎልት ፥ #ኮሮላ ሳንገዛ
እድሜ ለቻይናዎች ....የማያነካካ ... #ኮሮና ተነዛ...

#ኮ_ሮ_ና...

#አቤቱ አንድ...
ጥፋትህን መልስ ፥ምድርህን ጠብቃት ፥ ሰው አይለፍ ከንቱ
የእጅ ስራህ ውጤት ...እንዳሸን ቢዋደቅ ፥ ላንተ ነው ፀፀቱ
ብዬ እንዳልማጠን
ሰው ከፍቶ ፥ በሰው ላይ ፥ለሞት ባቃጠረን
የቀናሾች ሴራ .....እርሱን ቢያስገምተን
በሰው ደባ ተንኮን ....ሰዎች ለታመሱ
ምን በወጣው እርሱ !!!
እላለው....

#አቤቱ ...ሁለት
እንግዲህ ካልቀረ ...ተወራራሽ ቫይረስ ፥ አለምን መዞሩ
ወዳጅ እና #ሚስቴ
አትንካኝ ....አትንካኝ......ማለት ሳይጀምሩ
ያለቃዬን አንጀት ....አራርተህ አንድዬ
የአመት እረፍቴን ...ያሁኑን ከቀደም ፥ ባንድነት ጠቅልዬ
ግዜ ሳላጠፋ ፥ ከስራዬ ልውጣ
ቶሎ ቶሎ ምጪ.....ቶሎ ቶሎ ልምጣ...
ብለን ተቀጣጥረን ...
ከአልጋ ሳንወርድ ..ካንሶላ ሳንወጣ
ሲነጋና ሲመሽ....ሳትነካኝ ፣ ሳልነካት...ነቀርሳው አይምጣ!!
ደሞ ውስጤ....ይላል
#ቱ....
ይህን መሰል ፀሎት...እንዲህ ያለ ጥሪ ፥ ያውም ...ለፋሲካ
ከበሽታው ቀድሞ ...
በመላኩ መጅ ነው ...እያገላበጠ ቀድሞ #የሚያስከካ

#ስብሀት_ለአብ

አቤት ውስጤ #ግሙ
አወየው... #ምላሴ
ስፍር የሌለውን
የበደል ስልቻ ፥ በተቸራት ስጋ ፥ ለታቀፈች ነብሴ
አርምሞሽ ነው #ፅድቄ ፥ ዝምታሽ ነው #ዋሴ
ይሄን ፀሎት ብለሽ...
እምነትሽ መንምኖ ፥ በተስፋ ማጣት ውስጥ ፥ ከምትላወሺ
መለመኑ ይቅር...
ቃል ማውጣቱም ይብቃሽ ..... ለዛሬ ለምሺ ።

ብዬ ወደ ቀልቤ ስመለስ...
እራሴን ሳነቃ..
ሰላም ግቡ ተብሎ .....
ምዕመኑ በፊናው ፥ መላወስ ጀመረ
የጨመትኩት ልሳን ፥ ማዕልተ ፀሎቱ ፥ እዲህ ሲል ቋጠረ !!

በሸከፍነው ከንቱነት...ለሚገጥመን ፈተና
ስናውቅም ...ሳናውቅም ...አስቸጋሪ ነን እና
ምዕንተ እግዝዕትነ ማርያም ....እግዚኦ....መሀረና
#እምነት_ሰው_ያቆማል....እንኳንስ ኮሮና

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
#ወቅታዊ_ስሜት

በፊት.....የሚነደኝ !!
ከሰዎች ለይተሽ ፥ አልፈሽኝ ስትሄጂ...
አሁን የሚያስቀኝ...
ሁሉንም ሰው ዘለሽ ፥ ትሰልሚኝ ዘንዳ ፥ እኔ ካለሁበት ስትረማመጂ
አጃኢብ ነው እቴ...
የኔና አንቺ ነገር....በሽብር...ባማኑ !
ውድሽ እና ውዴ ፥ግራ ዘመም ሆነው ፥ እንደተቃረኑ
ሀሳቤን ሳታውቂ....ሀሳብሽ ሳይገባኝ
ከመምጣትሽ በላይ....አመጣጥሽ ሆኗል ...እኔን የሚያሰጋኝ ።

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
👍1
#አካብዳለሁ_!!

ባገርሽ...ባገሬ
ከታካሚው በላይ...ብዙ ሺህ #ዶክተሮች
የሰው ኮታ እስኪገኝ ፥ እፅ እየቀመሙ
እንደፈላ ችግኝ ፥ እዚም እዛም ሄደው
ባለ #ሀብቶቻችን ፥ የጤና ማእከል ፥ ሰርክ እያቋቋሙ
#መንግስት እየጦረን ፥ እነሱ እያከሙ
ምን አላት #ሁለት_ወር ?
መች ጠፍቶ ቀለቡ...?
ሲሻን ካመት አመት
እግር አሰቅለው
የምንበላው መኖ ፥ #አርሶ አደሮቻችን እያቀራረቡ
#ነጋዴዎቻችን ፥ አንድ ለሚገዛ ፥ አስር ሲመርቁ
#አከራዮቻችን ፥ ቤት ክራይ ሲለቁ
ባህል ቀማሚያን ፥ ማርከሻ ሲፈጥሩ
እልፎች በምህላ ፥ ምህረት ሲጠሩ...
ይህን ሁሉ ድሎት...
ያየና የሰማ ፥ #ቫይረሱ በራሱ..አይመጣም ወደኛ
ተሽከርክረን ውለን .... #ጧ ብለን እንተኛ ።

ደግሞም #ተናፋቂ ...
ከራሳችን አልፈን ፥ አለምን ጠባቂ
ከሰው የተለየን ፥ ሰዎች እንደሆንን ፥ ቀድሞኑ ስታውቂ
ምቾት ላንገላታው ...እንደኔና እንዳቺ ...ለተፍታታ ዜጋ
#ኮሮራ እንዳይዘን ፥ ስለምነው እሱ ፥ ቅንጣት የምንሰጋ ?
ብዬ መደለያ ...ቅንጣ የተስፋ ቃል...ከምኞት ስላጣሁ
ክብደቱ እንዲከብድሽ ... #ለማካበድ_ወጣሁ!!


አይግረምሽ እንግዲ.... #አካበድሁ!!

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
#ዘመንኛ_ዘማች ❤️❤️❤️

በፊት ድሮ....ድሮ..
ከወንዶች ለይቶ ...ሀሞቱ ኮስትሮ...
ድግን መትረየሱን ..
በዝናር ሸልሞ...ከፈፉ ወድሮ
ባላንጣውን ለቅሞ ...በጥይት የቆላ
የዱር የገደሉ...የሀገሬው ጥላ
ሞት አልያ ጡረታ ...እስኪገላግለው
ግዳጁ... ግንባር ነው
ግንባሩን ...አይነሳም...ግንባር ለለመነው
ክብሩ ለሌላንጂ...
በሱ ደም ጠብታ...ለሚንዘባነነው
ብለን #እያመመን ...ስለሱ ሲነሳ
የተገላቢጦሽ
በኔና ባንች አገር...
ቅቤ ጠባሹ ነው ...የሚያገኘው ምሳ
የሞተልሽ እማ....
ሲሞት ኖሮ ኖሮ...
እንደቀደሙቱ ፥ አያገኝም ካሳ
ብንል ስናወጋ.... ከቀናቶች ቀድሞ
#ግዳጅ...
የወቶ አደር...የሚዋደቅ ቆሞ
አልያም የሀክሙ...
መድህን ለሚሆን ፥ ለሚማቅቅ ታሞ
የተተወላቸው ...አርገን ስንሟገት
ግዜ ጨከነና ... #ገደደን_መጓተት

ታዲያ ..ዛሬ...ዛሬ
እኔም ..አንቺም...ሌላው...
መሰንበቻው ጠፍቶን
ጭራቅ መአልት ወርዶ ...አለሙን ሲበላው
ሳልነካሽ መዋሉ ፥ እንዲሆንሽ ገዴ
ጦስ እንዳቶኝብኝ...ሰበብ ለዘመዴ
ግዳጅ ላይ ....ነን #እኛ ...
ወግ ደርሶን ለዜጋ
ቤት መሽቀን ሆኗል..
ስውር ጠላታችን...ከርሞው #የሚናጋ

እናም...ጓዴ....ውዴ ❤️❤️❤️
#ዘግተሽ ተቀመጪ ...
አልያ #ተሸፍነሽ... #ተጣጥበሽ ባግባቡ
እጆችሽ ለመንካት ... #ፊትሽ አካባቢ ሳይርገበገቡ
#ሳትተፋፈጊ...!!
#ሳትጨናነቂ...!!
ከሰው ሳትጠጊ ...ካምላክሽ ሳትርቂ
ምን ቢሳሳ ጎኔ......እንዴት ብትናፍቂ
ለኔም ላንቺ ሆነ
ለተቀረቅ ዜጋ ... #ግዳጁን_ጠብቂ!!!


#ያንቺው.... #ጓድ ❤️❤️❤️

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
#አይተህ_ማረኝ


ወንጀሉ ቢበዛው...ሰው ነብሱን ሲዳኘው
በፀፀት ታኝኮ...መሀረኝ ለሚለው...
ከማስረጃ በላይ....
ልብ ነው የሚያየው....
ቢልም ...መፅሀፉ
ሀጥያቱን ሲቆጥር...እንደው በግርድፉ
ከደጀ ሰላሙ...አልያ ከበራፉ
ህሊና ሲሰቀል...ልክ እንደ #መርገፉ
እንባ መርጨት በቀር....
የጎደፈ ገላ...ማረኝም ለማለት...ይታሰራል አፉ ።

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh


@getem
@getem
#አጣብቂኝ

የውልህ አንተዬ
የኛ ነገር ሆኖ ፥ ከድጥ ወደ ማጡ
ክርያላይሶ ብለን ፥ ሰግደን ሳንነሳ ፥ ዳሌ ላይ ማፍጠጡ
ነብሰ በላን ውህድ ፥ በጨለማ ተገን ፥ ለሊት የቀየጡ
ነብስ ማር እያሉ...በፀአዳ ልባስ ፥ ወዳንተ ሲመጡ
ግዝትን ተላልፈው ...
እንደ እስጢፋኖስ ፥ በድንጋይ ውርጅብኝ ፥ ሰው የቀጠቀጡ
ሌላ ሌላም ብዙ ...በደልና ጥፋት
እየተላለፍን በየነጋው...ንጋት...
አፈፃዲቅ እኛ...አንተም ባረምሞ
አይተህ እንዳላየህ ....አፍህ ተከርችሞ...
አልፈህ ስታስገባን ....ሳይቆለፍ ደጅህ
እስከ ትላንትና...እጅ በላን በእጅህ ።
ክፋት ተሸክሞም
የሆዳችን...ነገር
በሆድ እንደዋለ...
ጭንቅ ቀን አስማጠን...በሩቅ አስዋዋለ
አፀድህ ርቆ...አዳፋ ነብሳችን...ከቤት ዘግቶ ዋለ
ይህኔ ...... #ጨነቀን
በተራራ በደል...ቤት ውሎ ...ቤት ማደር
መተንፈሻ ቅጥር...ሲጠፋን እንዳገር
ላለፈው እንለምን....ወይስ ለበፊቱ ?
ማረን ነው የሚባል ?
አውጣን ነው ፀሎቱ ?
በንዲህ ያለ ዘመን...በጠፋ ብልሀቱ
ኋላና ፊት ሆነው ፥ ሀጥያት እና ጥፋት ፥ በመሳ ሲመጡ
ካልጋላይ ሳይወርዱ...ከጎጆም ሳይወጡ
በቀን ይጨልማል ፥ በደል ጎርፍ ሰርቶ ፥ ሜዳ ላይ ሲሰምጡ ።
፨፨

#እንዴት_ታረገን_ይሆን ?

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
ቀለል አርገሽ እይው...
ዛሬ ቤት መዋሌን ፥ ፈድዬ በሶፋ
ትሰጭኝ አትጪ ፥ ምሰጥሽ ሳይጠፋ !!
እንኳን በረፍት ለት ፥ በዝክረ ላብ ማፍለቅ...ቀነኛ ልፈፋ
ስራ ቦታም ቢሆን
አስነፊ ሳይመጣ ፥ የለም የሚነፋ ።😂😂😂

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
#የስደተኛ_ውሎ

ቢጠበን ጎዳናው ፥ ቢቀጥን መስመሩ
ለፌሽታና ሀዘን
የሰው ልጅን እድሜ ፥ ቀናት ቢወጥሩ
መስሎ ማደር መልካም ፥ ለምዶ ማለፍ ጥሩ
አልጋ እንደሁ ፥ አልጋ ነው ፥ መርጠው ቢሳፈሩ
መጥፎ ሆነ መልካም ፥ ሳይተኙም አያድሩ
ቀን ሰጥቶ ማለፊያ ፥ ቦታ እስኪቀይሩ።

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@getem
@getem
#ፀሎተ_ግንቦት

ለተቀረው አመት...ደግሞም እስካመቱ
አንድ ሲል ልደታ...ዘጠኝ ሲል ወራቱ
ቅዬው ሲሰበሰብ ...
ላድባር የሚጀ'በት ፥ ሸክፎ ከቤቱ
ዛሬ ያልጠገብ ፥ አይኑና ፣ አንጀቱ
በማጣት ይታሻል...ጓዳና ፣ ማጀቱ
እንዲለን ልማዱ...
ጋን..እጋን ሲጋባ...መብሉ ሲመሰኳ'
ማቲ ሲተራመስ ...ጨዋታው ሲውኳኳ
ቡኑ ሲከታትም ...ጢሱ ሲትጎለጎል
አጥንት ፣ ጉልጥምቱ ...ከሳቱ ሲታጎል
እንኳንስ ያዳም ከርስ...ያሞራው ሲረካ
ይህን የለመደ ...
ለላመት ድረሱ ፥ ብሎ ይመርቃል ፥ ሆድና መለይካ ።
ልማድ መጥፎ ህመም ...
ሲነጠሉ ግዜ .. ትዝታው በሽታ
የቀረ ለት ያማል...
ቀን በቀኑ ሲደርስ ...ክርሚያው በሽውታ
የሰው ልደት እንኳ ፥ ሲኮስስ ይከፋል ፥ እንኳን #ያዛኝታ
እናም .... #እመቤቴ
ልማድሽ እንዳይቀር... #እመ_ብርሀኒቱ
በለትሽ ምህላ ፥ እንዲሽር ፍጥረቱ
እንዳምና እንድንውል ፥ ለቀጣይ ለፊቱ
ጠርገሽ ወድያ ይጣል ...ነቀርሳ ልክፍቱ ።

#የከርሞ_ሰው_ይበለነ_!! 🙏🙏🙏

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)


@Abrham_teklu

@getem
@getem
@getem
#መፈንቅለ_አመል
.
ሳይወድ በግዱ.......በወራት ጭካኔ ፣
በልኩ ሰው ጭኖ
አንበሳ ሲጠግብ ፥ አስተውዬ ባይኔ ፣
ባገም ጠቀም ምስጠት....
ድቅን ሲልብኝ ፥ ያለፈ ዘመኔ፣
በመስኮት ተክዬ
ከውስጥ ወደ ደጁ፥በሩቁ ስማትር ፥ ከወደዚህ እኔ
ከወደዛኛው ጥግ
#የተረገመ_ቀን !!
ሁሉ ተቀምጦ...በወንበሩ ስግስግ፣
እንዴት ...እጄን ልላክ ?
እንዴት ኪስ ልሟግግ...?
ይላል ከደጁ ላይ ...ከመቁረጡ አርፎ ፣
የጅ ቢጢፋ እንኳ...
ካንዷ ኮረዳ ጋር...ማሻሸት አትርፎ ፣
በዘንግ አመሀኝቶ ...ዘንጉን አስደግፎ ፣
እስኪሟሟ ድረስ ...የሴት ዳሌ አልፍቶ ፣
በተለይ ሲጨልም...ቻርኔላውን ፈቶ ፣
የለመደው ሁሉ ...
ትኩሳተ ስራው ፣
አንድም ለብስጭት፥ አንድም ለወገራው፣
እያዘዋወረ....ህዝቡን እንዳልገራው ፣
አሁን ላይ ቢቀየር..ሰልፉ ሆኖ ማግኛው ፣
መታፈግ #ቢፀየፍ
ስርዐት ቢከጅል ... #የኮረና ጥላው ፣
ዛሬ...ባሱን ሸሸ... ፤
ዛሬ ...ባሱን #ጠላው
በዚህ #ለውጠ_ልማድ
ከሸገር ....ባሻገር ፥ ቀን ያጋለጠውን እያገላበጠ ፣
እያለፍ ፣ እያለፍ ፥ ኪሱን እያጠጠ ፣
ግፊያውን #ይጋፋል...፣
ሰልፉን #ይሰለፋል...፣
ምን በሩጋ ቢደርስ ... #ምንግዜም_ይተርፋል

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

አዳሜ እና ሄዋኔ..
ሿ..ሿው ከበረንዳ ጀምሯል...

Join_me
👇👇👇
@Abrham_teklu

@getem
@getem
@getem
👍2
፨፨፨፨፨፨፨፨ #ሀሎ ፨፨፨፨፨፨፨፨....
#_06_10_2012
.
እድሜ ለ ግራም-ቤል
ሀሎ ብሎ ማውጋት ...ለሰው ላስለመደ ፣
ሰላቢ ፈጠራው
ድምፅ ጭኖ ያልፋል.....እየሸመደደ ።

ካፍ የሚወጣው ቃል ..አንዱም ሳይዛነፍ ፣
ቅላፄ ልሳኑ...ዜማ ምቱ ሳይነጥፍ ፣
መልዕክተ ዲስኩሩም
በመማሰን ደክሞ ..ሆሄ ፣ ቃሉ ሳይረግፍ ፣
እንደ ተቀበለው...ቆጥሮ ያሻግራል ፣
ቀፎ ተለጉሞ
ከባህር ባሻገር ፥ ሰው ሰውን ያወራል ።

በዘመን ዘምኖ ...
አሁን አሁን ደሞ
ራሱ በራሱ ፥ ግራ እስኪጋባ ፣
ከሀሎ ተሻግሮ...
ብዙ መዘውሩ ...ባንድነት ሲገባ ፣
እንደአዳም መሻት...
መተግበሪያው በዝቶ ፥ ክውኑ ሲጋባ ፣
የሰው መወዳጃው....
ሆኖ ቢተለምም ፥ እርምጃው ላጠረ ፣
ሀሎ ብሎ ማሰሰ...
ያሳብ ግንብ ፈጥሮ ፥ ስጋን እያጠረ ፣
የሩቅ መነፀሩ ፥
የቤተሰብ ልምዱን ፥
ተካቦ ማውጋቱን እንዳቀነጨረ ፣
አላየም ....ፈልሳሚው
አዚም እንደሆነን....የሱ የጅ ቀፎ ፣
በስልክ የተጣደ
ከባእድ ያውካካል ....ከዘመድ ተኳርፎ ።
ሳምንቱን በሙሉ
ሰባቱንም ቀናት...ለሊቱን ጨምሮ ፣
ወሬ ይቃርማል
ስሜተ ህዋሱን ...በመሳ ቀስሮ ።

ለምን....?ብሎ ላለም......
በስመ ስልጠና ፥ ሽንገላ ይበጃል ፣
እንቢኝ ላለውም...
ያረጀ ያፈጀ
ወግ አጥባቂ ይሉት ፥ ሾርኒ ይቀዳጃል ፣
በብቻነቱ ዲን ፥ ብቻውን ይፈጃል ።
( #ይህን_ማን_ይወዳል ??? )

ማለፊያ... ነው ... ትልሙ ፣
ማዘኛም ... ነው ... አቅሙ ፣
በክፉ ቀን ሳይቀር ፥ የሰው ልጅ ድኩሙ ፣
ቤቱ ቢዘጋ እንኳ...
ከስልኩ ተተክሎ ...ግዜ አጣ ለደሙ ።

በይነ መረቡ ላይ ፥ ብዙ በመባተል ፣
ያሻውን ጎንጉኖ ፥
ያሻውን በመፍተል ፣
እንዲመቸው አርጎ...
ያሻውን አውርዶ ፥
ያሻውን ይሰቅላል ፣
ሲቀባበል ውሎ ፥ ሲቀባበል ያድራል ።
በዚህ ቀነ ቅኝት....
" #ኦን_ላየን " ያየውን ፥ ሁሉንም ዘይሮ ፣
አዲስ እያወቀ ፥ አሮጌን አባሮ ፣
ለዋል ፈሰስ ሁሉ...
በሚባክን ግዜ ፥
ብዙ ደባል ይዞ....ቧልቱ ይጠረቃል ፣
ይህኔ ሺ ለምዶ....ከየሺው ይርቃል ።

#ይ_ር_ቃ_ል_!!!

#ይ
#ር
#ቃ
#ል_!!!

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abrham_teklu
@getem
@getem
#_ት_ዕ_ዝ_ብ_ት

በበግ ቅዬ ጋጣ...
ቀንድ ከሌላቸው ፥ መሀል የተገኘ
ባጋዘን ቅርፅ ራስ ፥ ጌጡ በተቀኘ
የሳጥናኤል ጭፍራ ፥ መችና ተሰኘ ?

ይማስናል እንጂ
ስምሪቱ መሀል ፥ ግርምት እንዳልታዬ
ዘውድ ጫነ ብሎ ፥
የዋህ በግነቱ ፥ መች ከርሞ ጨቀዬ ?

ተቀጥላ ...
ተደራቢ ...
ተለጣፊ ...
የስም ርቢ ...
ምግባረ ቃል ፥ እንጥልጥሎሽ
አሉባልታ....... ስሚስሞሽ
በበግ እምነት ፥ ይታለፋል
ከበጎች ቤት ፥ በበግ መሀል ።

በእኩልነት..
በሁዳድ መስክ ፥ ያለ ከልካይ
ነጭ ፣ ጥቁር ፣ ቦሀና ፣ ቀይ
ግጦሹ #ወጥ' ! ፥ ጥላው ሰማይ
ሆኖ ያድራል ፥ ባንድ ጋጣ
ሆንተብሎ ለትንኮላ
ከበግ ራስ ፥ ቀንድ አይወጣ ።

ነገር ግን ሲጠጋው....
በግ እንኳን አያልፍም ፥ የመላሸቅ ደዌ
ጆሮው ላይ ሲፈጫጭ...ጥል እንደ ሸውሸዌ
ያኔ ...ገራገሩ
ቀለም ፣ ቀንድ ፣ ልሳን ፥ ስላይደል ሽብሩ ፤

አንዴ ጭንቅላቱ ፥ ለጠብ ካዘገመ
ተንደርድሮ ሄዶ
የሚተመትመው ፥ በግ ቢያጣ የቆመ
ዘረ በግ ቢቀን'ን ...ፍቅርን እያለመ
ካገኘው ሲማታ. . .
ይኖራል ራሱን #እ_የ_ቸ_መ_ቸ_መ

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abrham_teklu
@getem
@getem
@getem
👍3
#የልቤ....#እምነት_ክህደት_ቃል


የልክ ሚዛኔ ፥ ላንቺ ተሰበረ
ሰው ሲመዝን ኖሮ ፥
በገለባ አለም ፥ ወርቅ አንቺን ሰፈረ
እቱ ለግላጋዋ !!
እንዶድ ፍቅርሽ ደርሶት
ቅምሻን የታደለ ፥ ካዘኔታሽ ጥዋ
እንኳን እኔ ቀርቶ
መውደድ ያልሸተተው ፥
ለበቀል መሀላ ፥ እራሱን የሰዋ
............. ሳጥናኤል ይገራል
ሰውነት ሰው ሲሆን ፥
ካንቺ መዲያ ላሳር ፥ ሰው ማለም ይከብዳል ።

#አየሽ
ልኬት ለሰበረ ፥ የፍቅር ናሙና
ቃል እየቀረፁ ፥ መቀኞ ቢወርዱ
ምላስ ያነክሳል
አልማዝ ባየ ግዜ ፥ ኮምቼ ሲቆልል ፥ ለከረመ ልምዱ
ጨለማ ተዘግቶ ፥ አዘቅት የከረመ
ብርሀን ቢግቱት ፥ አይኑ እንደታመመ
#ያ' ሰውዬሽ....................... ነኝ እኔ
በወገግታው ዳፍንት ፥ ያጣሁሽ ከጎኔ ።
ቀሽም ቃላቶቼ ፥ ቃልኪዳን አድሰው
ለሰበርኩት ልብሽ ፥ ካሳ ባይሆንሽም
በመምጣትሽ ስካር ፥ ደስታን ባላሟሽም
ያዘገየሽ ግዜ ፥ ቀድሞ ቢወስድሽም
ከኔ ለፈቀቀ ፥ ያንቺ ልዕልና
ጎረበጠኝ ብዬ ፥ አንቺን አልወቅስሽም ።

አንዳንዴ ባይገርምሽ
ፅጌሬዳ አበባ ፥ ውበቷ ሳያንሳት
ሳይነኳት የሚደርስ
ያንን ሁሉ እሾህ ፥ ለጉድ ያሸከምካት
በለስ....ሺ ምንተሺ
እሾህ ቆዳ ስፌት ፥ ጣሟን ያለበስካት
ም'ነው .... አልክ እግዜሩ ?
እላለው
ለሰውነት ህመም
መድህኒት የምትሆን ፥ እንዲት እግሯ ልጅህ
ሰርክ ጠዋት ማታ ፥ ሳትለይ ከደጅህ
በቁም ከሞቱ ጎን ፥ በመስክ አውለሀት
እንዳረጀ ቀብር ፥ በሙታን ወረዳ ፥ ሳማ የከበባት
ምንኛ....ብትወዳት ?
ምንኛ...ብታምናት ?
#እላለው !!
ይሄም ውጣ ውረድ ፥ እያብሰከሰከ ሆዴን ቢበላኝም
ንስር ማንነትሽ ፥
መውጫ ቢያጣ ፥ ብዬ አያሳስበኝም ።

#ይልቅ
ኩፍኩፍ ይመስል ፥
ትዝታሽ በግዜ ፥ በዋዛ ባይለቅም
መጣሽ ከማለቴ
ለመለመ ያልኩት ፥ በቅፅበት ቢደርቅም
ሞገስሽን ያዬ ልቤ
ምን እንደሚልሽ አያውቅም።

2012

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abrham_teklu
@getem
@getem
@getem
#እያስጠቡ_ጥማት


በኮርማ....
በርችት
ከምንቀበለው ፥ የዘመን መባቻ
ባርቲ ቡርቲ ወሬ ፥ በወገን ጥላቻ
እንደ ሀገር ኖሮ ፥ መሞት ለየብቻ
ምን አውቅልሽ በዝቶ.....
ውሎ ማደር ፈርተን ፥ በማጀት ጉልቻ
ቀናችንን ሳናምን
ጠጥተን ሳንረካ ፥ ጎርሰን ሳንጠግብ
ዛሬ ሳያከትም ፥ ለነገ ስናስብ
የሰቀቀን ጉርሻ ፥ ደጋግሞ እያነቀን
የኑሮ ውድነት ፥ በጠኔ እየናጠን
ዝም ባለ ሰፈር ፥ በፍርሀት ተጣብቀን
በጠራራ ፀሀይ
ጨለማ አውሮን ፥ ምርኩዝ ተስፋ እያጣን
በልተን እንዳልበላ ፥ ስጋት እያከሳን
ካዲስ አመት በላይ
ካዲስ ዘመን በላይ ፥ #ሰላም_ነው_የጠማን !!!

እንጂ!!......ባይከበር ...
ወጉ ሁሉስ..... ቢቀር
አሻፈረን ብንል ፥ ዘመን መች ይቆማል ?
ሲሻው የሳት እራት ፥ አልያ ዜና ገድል
የምንከትብበት
ባለ ሶስት መቶ ገፅ ፥ ብራና ያበጃል
እድሜ እየደረበ ፥ እድሜውን ይፈጃል።


" ባለ 365 ገፅ የሰላም ዘመን ይኩንልን "
#መልካም_በዓል

#አብርሀም_ተክሉ

@Getem
@getem
#__ቁዝም....

የዘመን መገለጥ ...የጀምበር ወጋግታ
እኩል አይታይም
ለእኩል ስጋ ለባሽ ...እኩል ባንድ ቦታ ።

እያረፋፈደ
የሚገለጥ ሰማይ
ሰው እያጋደመ ፥ ሰው እያፋረደ
ጨክኖ መጨከን የተለማመደ
የቀደመው ነቅቶ ፥ የተኛ እያረደ
ነጋ...ነጋ ...ባዩ
ሽመሉን ወልውሎ ፥ በነጋው ወረደ ።




መአቱ
ክንትው ....አለ ስንቱ
ሺ ዘመን ቢኖሩ ...
ነገ መሰወሩ ያለመገመቱ
የትላንትና እሾ ዛሬም መዋጋቱ
ለነገ ጠባሳ ሽንቁር ማበጀቱ



ይገርማል !!!

በንዲህ ያለ ግዜ መላ ቅጡን ባጣ
ፅልመት ያው....ፅልመት ነው
ተገባም ....ተወጣ
ሁሉን ይጋርዳል
ከነጭ ጥርስ ኋላ
የውሸት ቅጥልጥል ፥ በሌት ይገመዳል
እውነት የሚመስል
ተቀፅላ ሀሰት ፥ ሴረኛው ይወልዳል
የተወለደም ዘር
ባድርባይ እንኮኮ ፥ ተንፈላሶ ያድጋል
ቀመሩ ያልገባው
ልቡ የታወረ
ኗሪ እንደ ደረጃው
ለእግሩ ጧፍ ያነዳል
ጉርሱን ቶሎ ጎርሶ ...
ፍንጥቅ ላምባ ደፍኖ ፥ ትልቅ ሌት ይለምዳል
እንዲ ነው ክፉ ቀን
ይሄ ነው ጨለማ
ይህ ነው ሰንካላ እድል
እግር እየነሳ ፥ ክራንቹን የሚያድል
ስጋ የሚያተላ ... ወገን የሚያጋድል
ይህ ነው እርኩስ ወራት
ይህ ነው ብላሽ እድል
ምንም ማለት ማቃት
ምንም ማድረግ መሳን
ብዙ ጉድ ባለበት ... ባሰቡት ያነዳል
ዳሩ ቀን ሲጎድል
ቀን ሲጥል ቀን እንጂ
ከፈጣሪ በቀር ፥ መች ሰው ይማለዳል ?
የት ችሎስ ይፈርዳል !!!

#አብርሀም_ተክሉ

@Getem
@getem
#ከፍ_ዝቅ

ህይወት ዥዋ-ዥዌ
ኋላና ፊት ሆኖ ፥ በዝቶ መንቀላዎዝ
በመመላለስ ነው
በጀንበር የሚ'ጦዝ ።

ሞተው እስከሚያርፉ ፥ እስኪገላገሉ
በልቶ በማራገፍ
መኖር ይቀጥላል... ሲሰፍሩ ሲጎሉ !!

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
👍233