ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አይተህ_ማረኝ


ወንጀሉ ቢበዛው...ሰው ነብሱን ሲዳኘው
በፀፀት ታኝኮ...መሀረኝ ለሚለው...
ከማስረጃ በላይ....
ልብ ነው የሚያየው....
ቢልም ...መፅሀፉ
ሀጥያቱን ሲቆጥር...እንደው በግርድፉ
ከደጀ ሰላሙ...አልያ ከበራፉ
ህሊና ሲሰቀል...ልክ እንደ #መርገፉ
እንባ መርጨት በቀር....
የጎደፈ ገላ...ማረኝም ለማለት...ይታሰራል አፉ ።

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh


@getem
@getem