ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እያስጠቡ_ጥማት


በኮርማ....
በርችት
ከምንቀበለው ፥ የዘመን መባቻ
ባርቲ ቡርቲ ወሬ ፥ በወገን ጥላቻ
እንደ ሀገር ኖሮ ፥ መሞት ለየብቻ
ምን አውቅልሽ በዝቶ.....
ውሎ ማደር ፈርተን ፥ በማጀት ጉልቻ
ቀናችንን ሳናምን
ጠጥተን ሳንረካ ፥ ጎርሰን ሳንጠግብ
ዛሬ ሳያከትም ፥ ለነገ ስናስብ
የሰቀቀን ጉርሻ ፥ ደጋግሞ እያነቀን
የኑሮ ውድነት ፥ በጠኔ እየናጠን
ዝም ባለ ሰፈር ፥ በፍርሀት ተጣብቀን
በጠራራ ፀሀይ
ጨለማ አውሮን ፥ ምርኩዝ ተስፋ እያጣን
በልተን እንዳልበላ ፥ ስጋት እያከሳን
ካዲስ አመት በላይ
ካዲስ ዘመን በላይ ፥ #ሰላም_ነው_የጠማን !!!

እንጂ!!......ባይከበር ...
ወጉ ሁሉስ..... ቢቀር
አሻፈረን ብንል ፥ ዘመን መች ይቆማል ?
ሲሻው የሳት እራት ፥ አልያ ዜና ገድል
የምንከትብበት
ባለ ሶስት መቶ ገፅ ፥ ብራና ያበጃል
እድሜ እየደረበ ፥ እድሜውን ይፈጃል።


" ባለ 365 ገፅ የሰላም ዘመን ይኩንልን "
#መልካም_በዓል

#አብርሀም_ተክሉ

@Getem
@getem