ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
፨፨፨፨፨፨፨፨ #ሀሎ ፨፨፨፨፨፨፨፨....
#_06_10_2012
.
እድሜ ለ ግራም-ቤል
ሀሎ ብሎ ማውጋት ...ለሰው ላስለመደ ፣
ሰላቢ ፈጠራው
ድምፅ ጭኖ ያልፋል.....እየሸመደደ ።

ካፍ የሚወጣው ቃል ..አንዱም ሳይዛነፍ ፣
ቅላፄ ልሳኑ...ዜማ ምቱ ሳይነጥፍ ፣
መልዕክተ ዲስኩሩም
በመማሰን ደክሞ ..ሆሄ ፣ ቃሉ ሳይረግፍ ፣
እንደ ተቀበለው...ቆጥሮ ያሻግራል ፣
ቀፎ ተለጉሞ
ከባህር ባሻገር ፥ ሰው ሰውን ያወራል ።

በዘመን ዘምኖ ...
አሁን አሁን ደሞ
ራሱ በራሱ ፥ ግራ እስኪጋባ ፣
ከሀሎ ተሻግሮ...
ብዙ መዘውሩ ...ባንድነት ሲገባ ፣
እንደአዳም መሻት...
መተግበሪያው በዝቶ ፥ ክውኑ ሲጋባ ፣
የሰው መወዳጃው....
ሆኖ ቢተለምም ፥ እርምጃው ላጠረ ፣
ሀሎ ብሎ ማሰሰ...
ያሳብ ግንብ ፈጥሮ ፥ ስጋን እያጠረ ፣
የሩቅ መነፀሩ ፥
የቤተሰብ ልምዱን ፥
ተካቦ ማውጋቱን እንዳቀነጨረ ፣
አላየም ....ፈልሳሚው
አዚም እንደሆነን....የሱ የጅ ቀፎ ፣
በስልክ የተጣደ
ከባእድ ያውካካል ....ከዘመድ ተኳርፎ ።
ሳምንቱን በሙሉ
ሰባቱንም ቀናት...ለሊቱን ጨምሮ ፣
ወሬ ይቃርማል
ስሜተ ህዋሱን ...በመሳ ቀስሮ ።

ለምን....?ብሎ ላለም......
በስመ ስልጠና ፥ ሽንገላ ይበጃል ፣
እንቢኝ ላለውም...
ያረጀ ያፈጀ
ወግ አጥባቂ ይሉት ፥ ሾርኒ ይቀዳጃል ፣
በብቻነቱ ዲን ፥ ብቻውን ይፈጃል ።
( #ይህን_ማን_ይወዳል ??? )

ማለፊያ... ነው ... ትልሙ ፣
ማዘኛም ... ነው ... አቅሙ ፣
በክፉ ቀን ሳይቀር ፥ የሰው ልጅ ድኩሙ ፣
ቤቱ ቢዘጋ እንኳ...
ከስልኩ ተተክሎ ...ግዜ አጣ ለደሙ ።

በይነ መረቡ ላይ ፥ ብዙ በመባተል ፣
ያሻውን ጎንጉኖ ፥
ያሻውን በመፍተል ፣
እንዲመቸው አርጎ...
ያሻውን አውርዶ ፥
ያሻውን ይሰቅላል ፣
ሲቀባበል ውሎ ፥ ሲቀባበል ያድራል ።
በዚህ ቀነ ቅኝት....
" #ኦን_ላየን " ያየውን ፥ ሁሉንም ዘይሮ ፣
አዲስ እያወቀ ፥ አሮጌን አባሮ ፣
ለዋል ፈሰስ ሁሉ...
በሚባክን ግዜ ፥
ብዙ ደባል ይዞ....ቧልቱ ይጠረቃል ፣
ይህኔ ሺ ለምዶ....ከየሺው ይርቃል ።

#ይ_ር_ቃ_ል_!!!

#ይ
#ር
#ቃ
#ል_!!!

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abrham_teklu
@getem
@getem
Audio
🍀🌹🍀🥀🍀🌺🍀🍇🍀🍇🍀🍇

💖💖💖... #ሀሎ .....📱📲

🍀🌹🍀🥀🍀🌺🍀🍇🍀🍇🍀🍇

@Abrham_teklu
@getem
@getem
@getem