ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አጣብቂኝ

የውልህ አንተዬ
የኛ ነገር ሆኖ ፥ ከድጥ ወደ ማጡ
ክርያላይሶ ብለን ፥ ሰግደን ሳንነሳ ፥ ዳሌ ላይ ማፍጠጡ
ነብሰ በላን ውህድ ፥ በጨለማ ተገን ፥ ለሊት የቀየጡ
ነብስ ማር እያሉ...በፀአዳ ልባስ ፥ ወዳንተ ሲመጡ
ግዝትን ተላልፈው ...
እንደ እስጢፋኖስ ፥ በድንጋይ ውርጅብኝ ፥ ሰው የቀጠቀጡ
ሌላ ሌላም ብዙ ...በደልና ጥፋት
እየተላለፍን በየነጋው...ንጋት...
አፈፃዲቅ እኛ...አንተም ባረምሞ
አይተህ እንዳላየህ ....አፍህ ተከርችሞ...
አልፈህ ስታስገባን ....ሳይቆለፍ ደጅህ
እስከ ትላንትና...እጅ በላን በእጅህ ።
ክፋት ተሸክሞም
የሆዳችን...ነገር
በሆድ እንደዋለ...
ጭንቅ ቀን አስማጠን...በሩቅ አስዋዋለ
አፀድህ ርቆ...አዳፋ ነብሳችን...ከቤት ዘግቶ ዋለ
ይህኔ ...... #ጨነቀን
በተራራ በደል...ቤት ውሎ ...ቤት ማደር
መተንፈሻ ቅጥር...ሲጠፋን እንዳገር
ላለፈው እንለምን....ወይስ ለበፊቱ ?
ማረን ነው የሚባል ?
አውጣን ነው ፀሎቱ ?
በንዲህ ያለ ዘመን...በጠፋ ብልሀቱ
ኋላና ፊት ሆነው ፥ ሀጥያት እና ጥፋት ፥ በመሳ ሲመጡ
ካልጋላይ ሳይወርዱ...ከጎጆም ሳይወጡ
በቀን ይጨልማል ፥ በደል ጎርፍ ሰርቶ ፥ ሜዳ ላይ ሲሰምጡ ።
፨፨

#እንዴት_ታረገን_ይሆን ?

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem