#_ት_ዕ_ዝ_ብ_ት
በበግ ቅዬ ጋጣ...
ቀንድ ከሌላቸው ፥ መሀል የተገኘ
ባጋዘን ቅርፅ ራስ ፥ ጌጡ በተቀኘ
የሳጥናኤል ጭፍራ ፥ መችና ተሰኘ ?
ይማስናል እንጂ
ስምሪቱ መሀል ፥ ግርምት እንዳልታዬ
ዘውድ ጫነ ብሎ ፥
የዋህ በግነቱ ፥ መች ከርሞ ጨቀዬ ?
ተቀጥላ ...
ተደራቢ ...
ተለጣፊ ...
የስም ርቢ ...
ምግባረ ቃል ፥ እንጥልጥሎሽ
አሉባልታ....... ስሚስሞሽ
በበግ እምነት ፥ ይታለፋል
ከበጎች ቤት ፥ በበግ መሀል ።
በእኩልነት..
በሁዳድ መስክ ፥ ያለ ከልካይ
ነጭ ፣ ጥቁር ፣ ቦሀና ፣ ቀይ
ግጦሹ #ወጥ' ! ፥ ጥላው ሰማይ
ሆኖ ያድራል ፥ ባንድ ጋጣ
ሆንተብሎ ለትንኮላ
ከበግ ራስ ፥ ቀንድ አይወጣ ።
ነገር ግን ሲጠጋው....
በግ እንኳን አያልፍም ፥ የመላሸቅ ደዌ
ጆሮው ላይ ሲፈጫጭ...ጥል እንደ ሸውሸዌ
ያኔ ...ገራገሩ
ቀለም ፣ ቀንድ ፣ ልሳን ፥ ስላይደል ሽብሩ ፤
አንዴ ጭንቅላቱ ፥ ለጠብ ካዘገመ
ተንደርድሮ ሄዶ
የሚተመትመው ፥ በግ ቢያጣ የቆመ
ዘረ በግ ቢቀን'ን ...ፍቅርን እያለመ
ካገኘው ሲማታ. . .
ይኖራል ራሱን #እ_የ_ቸ_መ_ቸ_መ ።
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abrham_teklu
@getem
@getem
@getem
በበግ ቅዬ ጋጣ...
ቀንድ ከሌላቸው ፥ መሀል የተገኘ
ባጋዘን ቅርፅ ራስ ፥ ጌጡ በተቀኘ
የሳጥናኤል ጭፍራ ፥ መችና ተሰኘ ?
ይማስናል እንጂ
ስምሪቱ መሀል ፥ ግርምት እንዳልታዬ
ዘውድ ጫነ ብሎ ፥
የዋህ በግነቱ ፥ መች ከርሞ ጨቀዬ ?
ተቀጥላ ...
ተደራቢ ...
ተለጣፊ ...
የስም ርቢ ...
ምግባረ ቃል ፥ እንጥልጥሎሽ
አሉባልታ....... ስሚስሞሽ
በበግ እምነት ፥ ይታለፋል
ከበጎች ቤት ፥ በበግ መሀል ።
በእኩልነት..
በሁዳድ መስክ ፥ ያለ ከልካይ
ነጭ ፣ ጥቁር ፣ ቦሀና ፣ ቀይ
ግጦሹ #ወጥ' ! ፥ ጥላው ሰማይ
ሆኖ ያድራል ፥ ባንድ ጋጣ
ሆንተብሎ ለትንኮላ
ከበግ ራስ ፥ ቀንድ አይወጣ ።
ነገር ግን ሲጠጋው....
በግ እንኳን አያልፍም ፥ የመላሸቅ ደዌ
ጆሮው ላይ ሲፈጫጭ...ጥል እንደ ሸውሸዌ
ያኔ ...ገራገሩ
ቀለም ፣ ቀንድ ፣ ልሳን ፥ ስላይደል ሽብሩ ፤
አንዴ ጭንቅላቱ ፥ ለጠብ ካዘገመ
ተንደርድሮ ሄዶ
የሚተመትመው ፥ በግ ቢያጣ የቆመ
ዘረ በግ ቢቀን'ን ...ፍቅርን እያለመ
ካገኘው ሲማታ. . .
ይኖራል ራሱን #እ_የ_ቸ_መ_ቸ_መ ።
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abrham_teklu
@getem
@getem
@getem
👍3