ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አካብዳለሁ_!!

ባገርሽ...ባገሬ
ከታካሚው በላይ...ብዙ ሺህ #ዶክተሮች
የሰው ኮታ እስኪገኝ ፥ እፅ እየቀመሙ
እንደፈላ ችግኝ ፥ እዚም እዛም ሄደው
ባለ #ሀብቶቻችን ፥ የጤና ማእከል ፥ ሰርክ እያቋቋሙ
#መንግስት እየጦረን ፥ እነሱ እያከሙ
ምን አላት #ሁለት_ወር ?
መች ጠፍቶ ቀለቡ...?
ሲሻን ካመት አመት
እግር አሰቅለው
የምንበላው መኖ ፥ #አርሶ አደሮቻችን እያቀራረቡ
#ነጋዴዎቻችን ፥ አንድ ለሚገዛ ፥ አስር ሲመርቁ
#አከራዮቻችን ፥ ቤት ክራይ ሲለቁ
ባህል ቀማሚያን ፥ ማርከሻ ሲፈጥሩ
እልፎች በምህላ ፥ ምህረት ሲጠሩ...
ይህን ሁሉ ድሎት...
ያየና የሰማ ፥ #ቫይረሱ በራሱ..አይመጣም ወደኛ
ተሽከርክረን ውለን .... #ጧ ብለን እንተኛ ።

ደግሞም #ተናፋቂ ...
ከራሳችን አልፈን ፥ አለምን ጠባቂ
ከሰው የተለየን ፥ ሰዎች እንደሆንን ፥ ቀድሞኑ ስታውቂ
ምቾት ላንገላታው ...እንደኔና እንዳቺ ...ለተፍታታ ዜጋ
#ኮሮራ እንዳይዘን ፥ ስለምነው እሱ ፥ ቅንጣት የምንሰጋ ?
ብዬ መደለያ ...ቅንጣ የተስፋ ቃል...ከምኞት ስላጣሁ
ክብደቱ እንዲከብድሽ ... #ለማካበድ_ወጣሁ!!


አይግረምሽ እንግዲ.... #አካበድሁ!!

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem