/የፍርሀት ቅኔ/
ዳግም ግርማ
.
.
እናት ከማጀቱ ጥግ ተኮራምታ
በጭሱ ላይ ፍርሀት ደርባ እንደ ኩታ
ለጉድ ታነባለች ዓለም መጥፋቷ ነው
የሚሉትን ሰምታ...
:
ያቺም ምስኪን እምቡጥ ሮጣ ያልጠገበች
ከትላንት በስቲያ መማር የጀመረች
ፍልቅልቋ እህቴ ዓለም መጥፋቷ ነው
ሸሽገኝ ወንድሜ ብላ ትጣራለች...
;
ወንድ ልጅ ሲያነባ ገለል ብሎ ነው
እያለ ያሣደገኝ አባቴንም ባየው
ውኃ ቋጥሯል ዐይኑ
ሳግ እየታገለው...
ቤቴን ተመለከትኩ በቃ ሁሉም ያው ነው
;
አየሩ ዳምኗል ሊያስፈራራ ይመስል
ጎዳናው ተራቁቷል አንድ ጀግና ናፍቆ
ቢፈራም ሚያስመስል
ሰው ቤቱ ተከቷል ጭጋግ ድባብ ጠፍቶ
የተስፋ ፍሬዋ ዳግም እስኪበሥል
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደው አንዳች ገዶን
በሰው ሚዛን ቆመን ግን ከመረመርናት
ከማጀት የቆመች አንዲት ቁዝም እናት
ከእሥከዛሬው ሚልቅ ምን እንድትሠጣት ነው
ለዓለም ምታዝንላት?
መኖር ያልጀመረች ያችስ ታናሽ ጨቅላ
ለምን ነው ምትጮህ ዓለም ጠፋች ብላ??
ከኑሮ ስንክሣር እልፉን ያነበበ
ያስ ጀግና አባት ሰው
ምን ቀረኝ ብሎ ነው ለዓለም የሚያለቅሠው???
ብሎ ለጠየቀ እንደኔ ላለ ሰው
ይኸ በሀሣቡ የሚመላለሠው
:
እውን ነው ለሠሙ
ሰው ሁሉ ያላለቀ መንገድ አለኝ ቢልም
ከውዱ መለየት ልቡ ባይከጅልም
ሣይፀዱ መወሠድ ውጋት ሆኖ ቢያምም
የመፍራት ምንጬ ግን ሁሌ ወርቁ ይህ ነው
"ምንም ባይሠራ እንኳ ሰው መኖር አይጠግብም!!"
@getem
@getem
ዳግም ግርማ
.
.
እናት ከማጀቱ ጥግ ተኮራምታ
በጭሱ ላይ ፍርሀት ደርባ እንደ ኩታ
ለጉድ ታነባለች ዓለም መጥፋቷ ነው
የሚሉትን ሰምታ...
:
ያቺም ምስኪን እምቡጥ ሮጣ ያልጠገበች
ከትላንት በስቲያ መማር የጀመረች
ፍልቅልቋ እህቴ ዓለም መጥፋቷ ነው
ሸሽገኝ ወንድሜ ብላ ትጣራለች...
;
ወንድ ልጅ ሲያነባ ገለል ብሎ ነው
እያለ ያሣደገኝ አባቴንም ባየው
ውኃ ቋጥሯል ዐይኑ
ሳግ እየታገለው...
ቤቴን ተመለከትኩ በቃ ሁሉም ያው ነው
;
አየሩ ዳምኗል ሊያስፈራራ ይመስል
ጎዳናው ተራቁቷል አንድ ጀግና ናፍቆ
ቢፈራም ሚያስመስል
ሰው ቤቱ ተከቷል ጭጋግ ድባብ ጠፍቶ
የተስፋ ፍሬዋ ዳግም እስኪበሥል
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደው አንዳች ገዶን
በሰው ሚዛን ቆመን ግን ከመረመርናት
ከማጀት የቆመች አንዲት ቁዝም እናት
ከእሥከዛሬው ሚልቅ ምን እንድትሠጣት ነው
ለዓለም ምታዝንላት?
መኖር ያልጀመረች ያችስ ታናሽ ጨቅላ
ለምን ነው ምትጮህ ዓለም ጠፋች ብላ??
ከኑሮ ስንክሣር እልፉን ያነበበ
ያስ ጀግና አባት ሰው
ምን ቀረኝ ብሎ ነው ለዓለም የሚያለቅሠው???
ብሎ ለጠየቀ እንደኔ ላለ ሰው
ይኸ በሀሣቡ የሚመላለሠው
:
እውን ነው ለሠሙ
ሰው ሁሉ ያላለቀ መንገድ አለኝ ቢልም
ከውዱ መለየት ልቡ ባይከጅልም
ሣይፀዱ መወሠድ ውጋት ሆኖ ቢያምም
የመፍራት ምንጬ ግን ሁሌ ወርቁ ይህ ነው
"ምንም ባይሠራ እንኳ ሰው መኖር አይጠግብም!!"
@getem
@getem
#__ቁዝም....
የዘመን መገለጥ ...የጀምበር ወጋግታ
እኩል አይታይም
ለእኩል ስጋ ለባሽ ...እኩል ባንድ ቦታ ።
እያረፋፈደ
የሚገለጥ ሰማይ
ሰው እያጋደመ ፥ ሰው እያፋረደ
ጨክኖ መጨከን የተለማመደ
የቀደመው ነቅቶ ፥ የተኛ እያረደ
ነጋ...ነጋ ...ባዩ
ሽመሉን ወልውሎ ፥ በነጋው ወረደ ።
ወ
ረ
ደ
መአቱ
ክንትው ....አለ ስንቱ
ሺ ዘመን ቢኖሩ ...
ነገ መሰወሩ ያለመገመቱ
የትላንትና እሾ ዛሬም መዋጋቱ
ለነገ ጠባሳ ሽንቁር ማበጀቱ
ክ
ፋ
ቱ
ይገርማል !!!
በንዲህ ያለ ግዜ መላ ቅጡን ባጣ
ፅልመት ያው....ፅልመት ነው
ተገባም ....ተወጣ
ሁሉን ይጋርዳል
ከነጭ ጥርስ ኋላ
የውሸት ቅጥልጥል ፥ በሌት ይገመዳል
እውነት የሚመስል
ተቀፅላ ሀሰት ፥ ሴረኛው ይወልዳል
የተወለደም ዘር
ባድርባይ እንኮኮ ፥ ተንፈላሶ ያድጋል
ቀመሩ ያልገባው
ልቡ የታወረ
ኗሪ እንደ ደረጃው
ለእግሩ ጧፍ ያነዳል
ጉርሱን ቶሎ ጎርሶ ...
ፍንጥቅ ላምባ ደፍኖ ፥ ትልቅ ሌት ይለምዳል
እንዲ ነው ክፉ ቀን
ይሄ ነው ጨለማ
ይህ ነው ሰንካላ እድል
እግር እየነሳ ፥ ክራንቹን የሚያድል
ስጋ የሚያተላ ... ወገን የሚያጋድል
ይህ ነው እርኩስ ወራት
ይህ ነው ብላሽ እድል
ምንም ማለት ማቃት
ምንም ማድረግ መሳን
ብዙ ጉድ ባለበት ... ባሰቡት ያነዳል
ዳሩ ቀን ሲጎድል
ቀን ሲጥል ቀን እንጂ
ከፈጣሪ በቀር ፥ መች ሰው ይማለዳል ?
የት ችሎስ ይፈርዳል !!!
#አብርሀም_ተክሉ
@Getem
@getem
የዘመን መገለጥ ...የጀምበር ወጋግታ
እኩል አይታይም
ለእኩል ስጋ ለባሽ ...እኩል ባንድ ቦታ ።
እያረፋፈደ
የሚገለጥ ሰማይ
ሰው እያጋደመ ፥ ሰው እያፋረደ
ጨክኖ መጨከን የተለማመደ
የቀደመው ነቅቶ ፥ የተኛ እያረደ
ነጋ...ነጋ ...ባዩ
ሽመሉን ወልውሎ ፥ በነጋው ወረደ ።
ወ
ረ
ደ
መአቱ
ክንትው ....አለ ስንቱ
ሺ ዘመን ቢኖሩ ...
ነገ መሰወሩ ያለመገመቱ
የትላንትና እሾ ዛሬም መዋጋቱ
ለነገ ጠባሳ ሽንቁር ማበጀቱ
ክ
ፋ
ቱ
ይገርማል !!!
በንዲህ ያለ ግዜ መላ ቅጡን ባጣ
ፅልመት ያው....ፅልመት ነው
ተገባም ....ተወጣ
ሁሉን ይጋርዳል
ከነጭ ጥርስ ኋላ
የውሸት ቅጥልጥል ፥ በሌት ይገመዳል
እውነት የሚመስል
ተቀፅላ ሀሰት ፥ ሴረኛው ይወልዳል
የተወለደም ዘር
ባድርባይ እንኮኮ ፥ ተንፈላሶ ያድጋል
ቀመሩ ያልገባው
ልቡ የታወረ
ኗሪ እንደ ደረጃው
ለእግሩ ጧፍ ያነዳል
ጉርሱን ቶሎ ጎርሶ ...
ፍንጥቅ ላምባ ደፍኖ ፥ ትልቅ ሌት ይለምዳል
እንዲ ነው ክፉ ቀን
ይሄ ነው ጨለማ
ይህ ነው ሰንካላ እድል
እግር እየነሳ ፥ ክራንቹን የሚያድል
ስጋ የሚያተላ ... ወገን የሚያጋድል
ይህ ነው እርኩስ ወራት
ይህ ነው ብላሽ እድል
ምንም ማለት ማቃት
ምንም ማድረግ መሳን
ብዙ ጉድ ባለበት ... ባሰቡት ያነዳል
ዳሩ ቀን ሲጎድል
ቀን ሲጥል ቀን እንጂ
ከፈጣሪ በቀር ፥ መች ሰው ይማለዳል ?
የት ችሎስ ይፈርዳል !!!
#አብርሀም_ተክሉ
@Getem
@getem
#የራስ_ሃሳብ
.
.
.
ጡት እንዳጣ ህጻን ፣ መራር እንዳጠቡት
እንደተከፋ አንጀት ፣ ከራስ እንዳፋጩት
ሆዷ እንደጮኸ ሴት፣ርሃብ እንደጠናት
ባሏ እንደቀረባት ፣ እንደ ልጅ አልባ እናት
እንደ ወጥመድ አይጥ ፣ እንደ መረብ አሳ
እንደ እረኛ ዋሽንት ፣ እንዳዘለው ገሳ
መውጫ እንዳጣ ትንፋሽ ፣ ውስጤን እንዳመቀ
በ'ምባ ታጥቦ ሆዴ ፣ ላይፈስ በፈለቀ
ቆሻሻው ጸድቶለት ፣ ንጹህ ነገር ቢያጣ
ባር ባር ይለው ጀመር ፣ ወዳጁን እንዳጣ...
ሃገር ምን ይለኛል? ባልተናገረኝ ሰው ባልሰደቡኝ ስድብ
ቁዝም አቅበዝዝዞኝ በሃዘን ድባት ውስጥ ከደስታዬ ሳድብ?
ምንይለኛል ቀየው ባልከፋብኝ ኑሮ ባልተጫነኝ በደል
አይኔ እንባን አርግዞ ለማማጥ ሲታደል ለመውለድ ሲጋደል?
መሃጸነ አፌ እንደ አይኔ ሁሉ ምናለ ቢነጥፍ?
ያረገዘን ሃሳብ በመውለድ እሳቤ ሳይምጥ ከሚለፍፍ?
ፈልቆ ያልፈሰሰ ተምጦ የቀረው የሃሳብ ልጅ ልጄ
ያንተከትከኛል ለሱ ባልኩት እሳት በእንባዬ ምትክ ትኩስ ደሜን ጥጄ
ይተናነቀኛል ህቅ ስቅ እያለ
ወደ ውስጤ ፈሶ ሞልቶ እያጎደለ
ሃሴት ከኔ አርቆ ድባት እያደለ....
አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
የራሴው ሃሳብ ነው ፣ ውስጤን የሚወቅሰው
ቃሌን ማሰልሰሌ ፣ ሆዴን የሚብሰው
አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
ወደፊቴ ያልኩት ፣ ዛሬን የሚያምሰው
ሃሳቤ ቢሰድበኝ ፣ ሽፍን የማለቅሰው
አልበደለኝ በደል አልተናገረኝ ሰው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የራስ ሃሳብ የጭንቅላት
እየኳለ እያቀላት
ልጇን ወልዳ ልጇ በላት
አይመለስ አይገባላት
እንኳን ሰቡ አዘነለት ሃዘን ልቤን
ይቅር በለኝ ያወጋሁህ ክፉ ሃሳቤን
✍Tomi
@getem
@getem
@getem
.
.
.
ጡት እንዳጣ ህጻን ፣ መራር እንዳጠቡት
እንደተከፋ አንጀት ፣ ከራስ እንዳፋጩት
ሆዷ እንደጮኸ ሴት፣ርሃብ እንደጠናት
ባሏ እንደቀረባት ፣ እንደ ልጅ አልባ እናት
እንደ ወጥመድ አይጥ ፣ እንደ መረብ አሳ
እንደ እረኛ ዋሽንት ፣ እንዳዘለው ገሳ
መውጫ እንዳጣ ትንፋሽ ፣ ውስጤን እንዳመቀ
በ'ምባ ታጥቦ ሆዴ ፣ ላይፈስ በፈለቀ
ቆሻሻው ጸድቶለት ፣ ንጹህ ነገር ቢያጣ
ባር ባር ይለው ጀመር ፣ ወዳጁን እንዳጣ...
ሃገር ምን ይለኛል? ባልተናገረኝ ሰው ባልሰደቡኝ ስድብ
ቁዝም አቅበዝዝዞኝ በሃዘን ድባት ውስጥ ከደስታዬ ሳድብ?
ምንይለኛል ቀየው ባልከፋብኝ ኑሮ ባልተጫነኝ በደል
አይኔ እንባን አርግዞ ለማማጥ ሲታደል ለመውለድ ሲጋደል?
መሃጸነ አፌ እንደ አይኔ ሁሉ ምናለ ቢነጥፍ?
ያረገዘን ሃሳብ በመውለድ እሳቤ ሳይምጥ ከሚለፍፍ?
ፈልቆ ያልፈሰሰ ተምጦ የቀረው የሃሳብ ልጅ ልጄ
ያንተከትከኛል ለሱ ባልኩት እሳት በእንባዬ ምትክ ትኩስ ደሜን ጥጄ
ይተናነቀኛል ህቅ ስቅ እያለ
ወደ ውስጤ ፈሶ ሞልቶ እያጎደለ
ሃሴት ከኔ አርቆ ድባት እያደለ....
አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
የራሴው ሃሳብ ነው ፣ ውስጤን የሚወቅሰው
ቃሌን ማሰልሰሌ ፣ ሆዴን የሚብሰው
አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
ወደፊቴ ያልኩት ፣ ዛሬን የሚያምሰው
ሃሳቤ ቢሰድበኝ ፣ ሽፍን የማለቅሰው
አልበደለኝ በደል አልተናገረኝ ሰው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የራስ ሃሳብ የጭንቅላት
እየኳለ እያቀላት
ልጇን ወልዳ ልጇ በላት
አይመለስ አይገባላት
እንኳን ሰቡ አዘነለት ሃዘን ልቤን
ይቅር በለኝ ያወጋሁህ ክፉ ሃሳቤን
✍Tomi
@getem
@getem
@getem
👍1
እርጉም ድብርት ልቤን ሰርጾ፣
በእልፍ ዱካክ ሐዘን ሊግት ...
ንቁ ጅስሜን በ'ሾህ ቀርጾ፤
ጭምት! ፍዝዝ!
ቁዝም! ትክዝ!
አርጎ ሚጥል አካል ነፍሴን ...
በእንባ ለበቅ በአመል ቁጣ፣
ፊትሽ ዳምኖ ያየ ዐይኔ ...
እንደ ሶምሶን ኃይሉን ሲያጣ።
ንጥር ሀሴት ደሜን ሞልቶ፣
በሳቅ ጀንበር ፌሽታ ሊያጭድ ...
ድድር ጥርሴን ፍካት ቀብቶ፤
ፍንትው! ፍንክንክ!
ፍግግ! ፍልቅልቅ!
አርጎ ሚሰድ ጽልመት በሬን ...
በልዝብ ቀልድ በልጅ እብደት፣
ፊትሽ ፈክቶ ያየ ልቤ ...
እንደ ዳንኤል ሲቸር እምነት።
ሀሴት ጎራሽ መፍለቅለቄ
የሚቀየር ... በአዛኝ ፊትሽ!
ድብርት አዛይ መከፋቴ
የሚለወጥ ... በድንቅ ሳቅሽ!
ቢገርምሽ...
ቢደንቅሽ...
ኑረት እርሳስ ፈተና ኩል፣
እንደራሱ ልቤን ሊኩል ...
ጣቱን ቢያረግ ሰበር ሰካ፣
ህይወቴ መልክ የላትም
ባንቺ ገጽ ነው የምትዳምን ...
ባንቺ ገጽ ነው የምትፈካ።
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@paappii
በእልፍ ዱካክ ሐዘን ሊግት ...
ንቁ ጅስሜን በ'ሾህ ቀርጾ፤
ጭምት! ፍዝዝ!
ቁዝም! ትክዝ!
አርጎ ሚጥል አካል ነፍሴን ...
በእንባ ለበቅ በአመል ቁጣ፣
ፊትሽ ዳምኖ ያየ ዐይኔ ...
እንደ ሶምሶን ኃይሉን ሲያጣ።
ንጥር ሀሴት ደሜን ሞልቶ፣
በሳቅ ጀንበር ፌሽታ ሊያጭድ ...
ድድር ጥርሴን ፍካት ቀብቶ፤
ፍንትው! ፍንክንክ!
ፍግግ! ፍልቅልቅ!
አርጎ ሚሰድ ጽልመት በሬን ...
በልዝብ ቀልድ በልጅ እብደት፣
ፊትሽ ፈክቶ ያየ ልቤ ...
እንደ ዳንኤል ሲቸር እምነት።
ሀሴት ጎራሽ መፍለቅለቄ
የሚቀየር ... በአዛኝ ፊትሽ!
ድብርት አዛይ መከፋቴ
የሚለወጥ ... በድንቅ ሳቅሽ!
ቢገርምሽ...
ቢደንቅሽ...
ኑረት እርሳስ ፈተና ኩል፣
እንደራሱ ልቤን ሊኩል ...
ጣቱን ቢያረግ ሰበር ሰካ፣
ህይወቴ መልክ የላትም
ባንቺ ገጽ ነው የምትዳምን ...
ባንቺ ገጽ ነው የምትፈካ።
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@paappii
👍30❤9
#ያልፋል_አይደል?
:
:
:
እየደለብኩ እየሰባው፤
መሸ ነጋ ወጣው ገባው።
እንደዘበት እንደኑረት፤
ሽቅብ ፍስስ የዕድሜ ጅረት።
ያለ ቁዝም ያለ ስጋት፤
አሁን ምሽት አሁን ንጋት።
ልብ ሳይለኝ ሰቀቀኑ፤
እንደወትሮ ጋመ ቀኑ።
፡
፡
ኖርኩኝ፤
ሄድኩኝ፤
የት እንዳለው ሳላስታውስ፤
እንዲው ንጉድ እንዲው ፍስስ።
፡
፡
መጓዜንም አላበቃው፤
እግር ሲያጥረኝ ድንገት ነቃው።
ልቤ ቢናኝ፤
ዞሬ ስቃኝ፤
ተንደረደርኩ ልደላደል፤
ከቦኝ ኖሯል ለካስ ገደል።
፡
፡
እንዴት ገባው እንዴት ልውጣስ፣
ማን ያድነኝ ምን አውቄ፤
የሚያኖረኝ አንዱ ተስፋ፣
« ያልፋል አይደል ? » ሚል ጥያቄ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
:
:
:
እየደለብኩ እየሰባው፤
መሸ ነጋ ወጣው ገባው።
እንደዘበት እንደኑረት፤
ሽቅብ ፍስስ የዕድሜ ጅረት።
ያለ ቁዝም ያለ ስጋት፤
አሁን ምሽት አሁን ንጋት።
ልብ ሳይለኝ ሰቀቀኑ፤
እንደወትሮ ጋመ ቀኑ።
፡
፡
ኖርኩኝ፤
ሄድኩኝ፤
የት እንዳለው ሳላስታውስ፤
እንዲው ንጉድ እንዲው ፍስስ።
፡
፡
መጓዜንም አላበቃው፤
እግር ሲያጥረኝ ድንገት ነቃው።
ልቤ ቢናኝ፤
ዞሬ ስቃኝ፤
ተንደረደርኩ ልደላደል፤
ከቦኝ ኖሯል ለካስ ገደል።
፡
፡
እንዴት ገባው እንዴት ልውጣስ፣
ማን ያድነኝ ምን አውቄ፤
የሚያኖረኝ አንዱ ተስፋ፣
« ያልፋል አይደል ? » ሚል ጥያቄ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
❤56👍23🎉3🔥2