ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ያልተወለደ ... #ቃል

ከ ደብሬ ቅጥር....
ላርባ ፆም ምህላ...
ነጠላ ለብሼ ...ካንጋፋ ዛፍ ጥላ...
#ሽው....#ሽው....ከሚለው አፀድ
ከሚንቆረቆረው
የወፍ ዜማ ሞገድ...
ስርአተ ቤተስኪያን....አብሮ ተጨምሮ
በታንቡሬ መስኮት ...
ያገልጋይ ጥዑም ቃል...ሰናይ ተንቆርቁሮ
አቤቱ....የሚሉት ቃል
አለወትሮ ከበደኝ...
እማፀነው ዘንዳ
የት ብዬ ጅማሮ ፥ ማሰሪያው ጨነቀኝ።
ይሄንን እሱም ታዝቧል....
የሆዴ #ጉትምትም
ምን ቃል እንዲወጣው ፥ አፌን ይጠብቃል
እኔም ቃሌ #ታንቋል...
የምላሴ ፍሬ ...ወረቴ እንደሆነ ..ልቦናዬ ያውቃል።
መቅሰፍት የሞላውን ፥ የህይወትን ጋሪ እንደተሳፈረ
አለም ሰፊ መስሎት የተደናገረ
ያልጠረጠረ ነው..... የተመነጠረ
ይላል የውስጤ ቃል...
ሺዎች የበላ አፈር ...አዕላፍ ይጠብቃል
ለዛሬው ይመስገን....ለነገ እርሱ ያውቃል

#ምርምረ.... #ፀሎት

የኔና እሷ ፍቅር .....ጣፍጦልን በለዛ
ከንፈር መሳም አልፈን
ጉልቻ ሳንጎልት ፥ #ኮሮላ ሳንገዛ
እድሜ ለቻይናዎች ....የማያነካካ ... #ኮሮና ተነዛ...

#ኮ_ሮ_ና...

#አቤቱ አንድ...
ጥፋትህን መልስ ፥ምድርህን ጠብቃት ፥ ሰው አይለፍ ከንቱ
የእጅ ስራህ ውጤት ...እንዳሸን ቢዋደቅ ፥ ላንተ ነው ፀፀቱ
ብዬ እንዳልማጠን
ሰው ከፍቶ ፥ በሰው ላይ ፥ለሞት ባቃጠረን
የቀናሾች ሴራ .....እርሱን ቢያስገምተን
በሰው ደባ ተንኮን ....ሰዎች ለታመሱ
ምን በወጣው እርሱ !!!
እላለው....

#አቤቱ ...ሁለት
እንግዲህ ካልቀረ ...ተወራራሽ ቫይረስ ፥ አለምን መዞሩ
ወዳጅ እና #ሚስቴ
አትንካኝ ....አትንካኝ......ማለት ሳይጀምሩ
ያለቃዬን አንጀት ....አራርተህ አንድዬ
የአመት እረፍቴን ...ያሁኑን ከቀደም ፥ ባንድነት ጠቅልዬ
ግዜ ሳላጠፋ ፥ ከስራዬ ልውጣ
ቶሎ ቶሎ ምጪ.....ቶሎ ቶሎ ልምጣ...
ብለን ተቀጣጥረን ...
ከአልጋ ሳንወርድ ..ካንሶላ ሳንወጣ
ሲነጋና ሲመሽ....ሳትነካኝ ፣ ሳልነካት...ነቀርሳው አይምጣ!!
ደሞ ውስጤ....ይላል
#ቱ....
ይህን መሰል ፀሎት...እንዲህ ያለ ጥሪ ፥ ያውም ...ለፋሲካ
ከበሽታው ቀድሞ ...
በመላኩ መጅ ነው ...እያገላበጠ ቀድሞ #የሚያስከካ

#ስብሀት_ለአብ

አቤት ውስጤ #ግሙ
አወየው... #ምላሴ
ስፍር የሌለውን
የበደል ስልቻ ፥ በተቸራት ስጋ ፥ ለታቀፈች ነብሴ
አርምሞሽ ነው #ፅድቄ ፥ ዝምታሽ ነው #ዋሴ
ይሄን ፀሎት ብለሽ...
እምነትሽ መንምኖ ፥ በተስፋ ማጣት ውስጥ ፥ ከምትላወሺ
መለመኑ ይቅር...
ቃል ማውጣቱም ይብቃሽ ..... ለዛሬ ለምሺ ።

ብዬ ወደ ቀልቤ ስመለስ...
እራሴን ሳነቃ..
ሰላም ግቡ ተብሎ .....
ምዕመኑ በፊናው ፥ መላወስ ጀመረ
የጨመትኩት ልሳን ፥ ማዕልተ ፀሎቱ ፥ እዲህ ሲል ቋጠረ !!

በሸከፍነው ከንቱነት...ለሚገጥመን ፈተና
ስናውቅም ...ሳናውቅም ...አስቸጋሪ ነን እና
ምዕንተ እግዝዕትነ ማርያም ....እግዚኦ....መሀረና
#እምነት_ሰው_ያቆማል....እንኳንስ ኮሮና

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

#ፀሎት_ወ_ስግደት
.
.
የሰራነው በደል፣
የከሸፈው ገድል፤
በዘመነ ሀዲስ 'ካፀዱ ሲያርቀን፣
ያንቺን ስግደት አይቶ፤
ያንቺን ፀሎት ሰምቶ አምላክ ይታረቀን፡፡
.
.
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

.......ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ'ለተ ስቅለቱ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን፡፡

.
@abiye12


@getem
@getem
@getem