ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ፀሎተ_ግንቦት

ለተቀረው አመት...ደግሞም እስካመቱ
አንድ ሲል ልደታ...ዘጠኝ ሲል ወራቱ
ቅዬው ሲሰበሰብ ...
ላድባር የሚጀ'በት ፥ ሸክፎ ከቤቱ
ዛሬ ያልጠገብ ፥ አይኑና ፣ አንጀቱ
በማጣት ይታሻል...ጓዳና ፣ ማጀቱ
እንዲለን ልማዱ...
ጋን..እጋን ሲጋባ...መብሉ ሲመሰኳ'
ማቲ ሲተራመስ ...ጨዋታው ሲውኳኳ
ቡኑ ሲከታትም ...ጢሱ ሲትጎለጎል
አጥንት ፣ ጉልጥምቱ ...ከሳቱ ሲታጎል
እንኳንስ ያዳም ከርስ...ያሞራው ሲረካ
ይህን የለመደ ...
ለላመት ድረሱ ፥ ብሎ ይመርቃል ፥ ሆድና መለይካ ።
ልማድ መጥፎ ህመም ...
ሲነጠሉ ግዜ .. ትዝታው በሽታ
የቀረ ለት ያማል...
ቀን በቀኑ ሲደርስ ...ክርሚያው በሽውታ
የሰው ልደት እንኳ ፥ ሲኮስስ ይከፋል ፥ እንኳን #ያዛኝታ
እናም .... #እመቤቴ
ልማድሽ እንዳይቀር... #እመ_ብርሀኒቱ
በለትሽ ምህላ ፥ እንዲሽር ፍጥረቱ
እንዳምና እንድንውል ፥ ለቀጣይ ለፊቱ
ጠርገሽ ወድያ ይጣል ...ነቀርሳ ልክፍቱ ።

#የከርሞ_ሰው_ይበለነ_!! 🙏🙏🙏

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)


@Abrham_teklu

@getem
@getem
@getem