ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የስሌት #ጋብቻ
#አንቺ
ሽማግሌ አዘጋጅ ብለሽ ተናግረሻል
ምን አለው ይሉኛል ብለሽ ተጨንቀሻል
#እኔ
ከቀየው መርጬ
በቂ ሽማግሌ አዘጋጅቻለሁ
የሌለኝ ነገር
ለራሴ አለኝ ብዬ በቃል ሸምድጃለሁ
#እነሱ
ቤተዘመድ መጥቶ
ምን አለው ለማለት ማልዶ ይሰለፋል
ሽማግሌ ከቦ
ምን አለው ለሚባል
የወላጅ ጥያቄ የሐሰት መልስ ይፅፋል
#ውዴ #አትጨነቂ
ያንቺ ብቻ አይደለም የሀገር ነው ችግሩ
እኛም ቤት ብትመጪ ይሔው ነው ነገሩ
#አምና
የታናሽ እህቴ
የልጅነት ፍቅሯ አመት በአል አስታኮ
በፍቅር መርቀን
ፈቅደን እንድንሰጠው ሽማግሌ ልኮ
#መልስ #ሲጠባበቅ
በዚህ ወገን ሆኜ እኔም ጠይቄያለሁ
ማይደርስብኝ መስሎኝ ምን አለው ብያለሁ
በሴት ወገን ስንሆን የወንዱን ባናውቅም
ምን አለው ተብሎ ሰው አይጠየቅም
ሀቅ ተዟዙሮ
ቦታ ተቀያይሮ
የትናንት ተቀባይ ከነገ ወዲያ ይልካል
በሴቷ ጠይቆ በወንድ ይጠየቃል
ሸፋፍነነው እንጂ
ደፍረን ከጠራነው ነገሩ ያሳስባል
በንግድ አጠያየቅ
ምን አለው አይደለም ስንት አለው ነው ሚባል
ባንክ ቤት ስንት አለው በጥሬው ያኖረው
ስንት መኪና አለው የሚያሽከረክረው
ስንት ካሬ መሬት ካርታ የወጣለት
ስንት ክፍል ቪላ የተንጣለለለት
በልጅ የደም ቀለም የሌለንን ስንስል
ልጅ የምንድር ሳይሆን ገዢ ነው ምንመስል
የመመኘት ቀመር
የማዟዟር ብዜት በዘመን ሲጣፋ
ምን አለው ነው እንጂ
ከዬት አመጣው የሚል ሽማግሌ ጠፋ
#እኔ #ምለው ?
የማካፈል ስሌት ዞሮ የመጣ ‘ለት
ምን ያህል ይዘናል ምን አለው ለማለት
#ይልቅ
እግዚአብሔር አድሎት
በጥላቻ ዘመን የሰው ልጅ ሲፋቀር
አፍቃሪ ልብና
ሁሉም ነገር አለው ከሀብት በስተቀር
ሀቁን እያወቅነው ውጠን ከማባበል
ምን አለውን ትተን ምን የለውም እንበል
=====||=====
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@beppa_19
#ዝክረ_ቫለንቲኖ

በሮማኖች...አገር
ይሄውልሽ #ውዴ...በፊት ድሮ ድሮ
ሴት ሴቱን ሲከተል ፥ በዘቡ ተማሮ
ንጉስ... #ክላውዲዎስ
ለክተት ዘመቻ....
#ልጄን #ሚስቴን...በሚል ስስት እያነቀው
እንዴት ነው ጦረኛ ፥ ላገር የሚወድቀው ?
ብሎ ስለራደ...
ተባእቱን ሁላ.... ከተራክቦ አገደ
አሻፈረኝ ያለ .. #ሰማዕቱ_ቄስም
በንጉሱ ፈቃድ ስለተናደደ
#እስከተቀላበት...ህይወቱ እስካለፈ
በሚስጥር ፥ ስንቱን ጥንድ ፥ አጋብቶት አረፈ
እናም ዛሬ ዛሬ.......ባገርሽ ፣ ባገሬ
ቀይ....ቀዩ #ነገር ......እየተማገደ
ቫለንቲኖን ማሰብ ....ስለተለመደ
ምን ከኔ ባትኖሪ...
የት እንደሆንሽ እንኳን ፥ ባይጠረጠርም
ግራ ጎኔን #ለራት...ለደስታው ባልቀጥርም
እስክትመጪ ድረስ
#በቀይ ደምቄ........ቤቴን አሸብርቄ
አንቺ መናፈቄ
አስቤሽ መዝለቄ
በ ከማን አንሼ...እንዲያው ለነገሩ
ከማላውቀው አገር ፥ የነበሩት አባት ፥ እንዲህ ሲዘከሩ
ለማላውቅሽ አንቺ
#happy_valentine ...
የተባለ ምኞት ፥ ምኑ ላይ ነው #ነውሩ?

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

" #Happy_valentine_my_Love "
( #ባለሽበት_ቦታ)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
1👍1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

👉👉 #ኪያዬ_አይደለሽም 👈👈

ትዝ ይልሻል #ውዴ
ያኔ... ከ 3 ወራት በፊት

እኔና አንቺ ሆነን
በፍቅርም ከንፈን፤
ህይወትን እረስተን፤
ሀዘንን አባረን፤
እየተደሰትን....
ከሰፊው ሰማይ ላይ
በፍቅር ስንበር፤
ከፊት ማለፍ ስንችል፤
ከዃላ አየቀረን፤
እየተጎተትን፤
ደስተኞች ነበርን....
አዎ ውዷ #ህይወቴ
አውቃለሁ ታውቂያለሽ፤
ይህን አትረሽውም፤
ልብ ለልብ ገጥመን፤
የየቅል ህይወት ትተን፣
እኔ ባንቺ ልብ፣
አንቺ በኔ ልብ ስንኖር
ብዙ አስበን ነበር.....
°°°°°°°°°°°
#ህይወቴ.....
አሁን ግን ከፍቶኛል....
ልቤም ሀዘን ሞልቶት
የምር ደብሮኛል....
ከሳቅም ከደስታም
ሀዘን ይቀናኛል....
ውብ ናቸው ባልሻቸው
ሁለቱም አይኖቼ፣
እንባ ተንንቆኛል...
መኖርም ስጀምር...
ከባዶ አስነስቸሽ፤
ከ ዜሮ አስጀምረሽ፤
ያዳንሽኝን ያህል፣
ደግመሽ ገለሽኛል...
አናም ውዴ....
እሱም ሲል #ኪያዬ
እኔም #ህይወቴ አልኩኝ...
ባነባበት መጠን፤
እኔም አነባሁኝ....
በእሱ ተስፍ መቁረጥ፤
እራሴን ከተትኩኝ.....
ሀዘኑ ሲጎዳው፤
እኔም ተጎዳሁኝ....
ተመለሺ ሲላት
እኔ አልተመኘሁም...
ደስታሽ ደስታዬ ነው
የኔ ባትሆኝም.....
°°°°°°°°°
#ኪያዬ ሲላት ግን
.....እኔ አላልኩሽም....
.....ምክንያቹም.....

አንቺ ለኔ...
#ህይወቴ ነሽ እንጂ፤
#ኪያዬ አጀለሽም።

ተፃፈ በ @Mak_bale
#ካነብብሽው_ላንቺ _እንደሆነ_ታቂዋለሽ።
13.6.2012
@getem
@getem
@getem