ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን #ታቦቱ ይቀመጥበት የነበረውን #ቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ #ቤተመቅደስ ስትለው ቀጥሎ ያለውን ክፍል #ቅድስት #ሦስተኛውን ክፍል ደግሞ #ቅኔ ማህሌት ትለዋለች። በዚህም መሠረት ማርያም #ከ3 ዓመት ዕድሜዋ ጀምሮ #በቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን እንደኖረች #ተአምረ #ማርያም ሲገልጽ <<ልጃቸውን #ማርያምን #በንጽህና ሲያሳድጉ 3 ዓመት በተፈጸመ ጊዜ #ሐና ባሏን #ኢያቄምን ወንድሜ ሆይ ልጃችንን ለቤተ እግዚአብሔር #ብጽአት አድርገን እንስጥ #ልጃችን ቤተ #እግዚአብሔርን #እንድታገለግል ነው እንጂ በዚህ #ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው። #ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ #ሐና በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው። ለመንገድ የሚሆነውን #ስንቅና ለቤተ #እግዚአብሔር የሚሆነውንም #መባዕ ሁሉ አዘጋጅ። #ቤተሰቦቻቸውንና #ባልንጀሮቻቸውን #ዘመዶቻቸውንም ሁሉ ጠራ። ልጃቸውንም ይዘው ሄደው ወደ #ቤተ መቅደስ አስገቧት። ካህናት #በቤተ #መቅደስም ያሉ ሁሉ በሰሙ ጊዜ እነሱም ለመቀበል ወጥተው መንፈሳዊ #ሰላምታ ሰጡአቸው። #ኢያቄምና ሚስቱን #ሐናን ልጃቸውንም #ማርያምን አመሰግነዋቸው #በአንብሮተ-እድ (እጅ በመጫን) ፈጽመው ባረኳቸው። እግዚአብሔርም ሃዘናችሁን #በእውነት ተቀብሏችኋል። #ቸር በምትሆን በዚች ልጅም ደስ አሰኝቷችኋል አሏቸው። #እመቤታችንም ለእግዚአብሄር #ለእናትነት የተመረጥሽ #ንዑድ #ክብርት ሆይ #ፍቅር ይገባሻል አሏት። ታቅፈው ይዘው #በታህሳስ 3 ቀን #በእግዚአብሄር #ፍቅር ወደ #ቤተ መቅደስ አስገቧት[1]>>።

▶️ ቅዳሴ ማርያም ንባቡና አንድምታው እንዲሁም #የወንጌል አንድምታው <<ካህናቱ ወደ #ቤተ #መቅደስ (ቅድስተ ቅዱሳን) ከማስገባታቸው በፊት #የምግቧ ነገር እንዳሳሰባቸው ይገልጽና #ፋኑኤል የሚባል #መልአክ #ሰማያዊ #መጠጥና #ምግብን አምጥቶ ለብቻዋ ሲመግባት አይተው <<የምግቧስ ነገር ከተያዘልን #ከሰው ጋር ምን ያጋፋታል>> ብለው #ከቤተ መቅደስ (ቅድስተ ቅዱሳን) ውስጥ አስገብተዋት 12 #ዓመት በዚያ ውስጥ #እንደኖረች ይገልጻሉ[2]።
<<እርሷም #ከቤተ መቅደስ (ቅድስተ-ቅዱሳን) ውስጥ #በመንፈስ ቅዱስ ሞግዚትነት ገብታ ወንበሯን ዘርግታ #ከደናግለ እስራኤል የተካፈለችውን #ወርቅና #ሐር እያስማማች ስትፈትል #በአምሳለ አረጋዊ (በሽማግሌ) መልክ ገብርኤል መልአክ መጥቶ ትጸንሻለሽ ብሎ እንዳበሰራት የቅዳሴ ማርያም አንድምታው ይነግረናል[3]። እንዲሁም በቤተክርስቲያኗ #ትውፊትና #ትምህርት መሰረት ከማርያም ጀርባ #መንጦላኢተ - ቤተመቅደስ (የቤተመቅደስ መጋረጃ) እና ከፊት ለፊቷ #የቅዱሳት መጽሐፍት ማንበቢያ #አትሮንስ (Pulpit) የሚታየውና መልአኩ #ገብርኤል በብርሃን ተከቦ #ሲያበስራት የሚያሳየው #ስዕል እርሷ #በቤተመቅደስ ውስጥ እንደኖረችና በዚያ ውስጥ #ክርስቶስን የምትወልድ መሆኗን የተበሰረችበት መሆኑን የሚገልጽ #ስዕል ነው።

ይህንንም #ታሪክ መሠረት ተደርጎ <<ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመታቦት ዘግንቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ፤ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቁ ባሕርይ ዘየኅቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ ውስተ #ቤተ መቅደስ - አምላክን የወለደሽ እመቤታችን #ድንግል ማርያም ሆይ #ከማይነቅዝ #እንጨት #የተቀረጸ ዋጋው እጅግ ብዙ የሆነና በከበረ #ወርቅ እንደተለበጠና እንዳማረ #ታቦት #በቤተ መቅደስ ኖርሽ>> እየተባለ ይዜማል[4]።

▶️ እንዲሁም <<አማናዊት #ታቦት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም[5] #ንጽሕተ ንጹሐን #ቅድስተ ቅዱሳን በመሆኗ #በንጽሕና #በድንግልና ጸንታ #በቤተመቅደስ ኖራለች>> ተብሎአል[6]። እንዲሁም #ቤተመቅደስ መኖሯም #በማህሌተ ጽጌ መጽሐፍ #በግጥምና #በዜማ <<የኅዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክመትና አመ ቤተመቅደስ ቦእኪ እንዝትጠብዊ ሐሊበ ሐና ወያስተፌሥሐኒ ካዕብ ትእምርተ ልሕቀትኪ በቅድስና ምስለ አብያጽሁ ከመአብ እንዘ ይሴሲየኪ መና ፋኑኤል ጽጌነድ ዘይከይድ ደመና - ማርያም የሃናን ወተት እየጠባሽ ወደ #ቤተመቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ #ድህነት (ብቸኝነት) ያሳዝነኛል፡ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ #ደመናን የሚረግጥ #የእሳት አበባ #ፋኑኤል ከጓደኞቹ #መላእክት ጋር መናን የመገበሽ #በንጽሕና የማደግሽ #ተአምር ደስ ያሰኛል[7]>> ይላል።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ "ተአምረ ማርያም" 2፤ 27-30፤ 3ኛ ዕትም፤ ገጽ 18፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1989 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ "ቅዳሴ ማርያም" ንባቡና አንድምታው 5፥15፣ 44 ገጽ 120፣ 123. ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1983 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ ወንጌል ቅዱስ ንባቡና አንድምታው፤ የሉቃስ ወንጌል 1፥27፥ ማብራሪያ ገጽ 265፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1997 ዓ.ም።

[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ "ቅዳሴ ማርያም" ንባቡና አንድምታው 5፥44 ገጽ 125፣ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1983 ዓ.ም።

📚፤ አንቀጸ ብርሃን ትርጓሜው፤ ገጽ 411።

📚፤ አንዱአለም ዳግማዊ (መምህር)፤ "ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት"፤ ብራና ማተሚያ ድርጅት፤ አ.አ፥ ገጽ 178።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ "ተአምረ ኢየሱስ" 3ኛ ተአምር ቁ.2፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ ገጽ 14፤ 1994 ዓ.ም።

[4] 📚፤ አንቀጸ ብርሃን ትርጓሜው፤ ገጽ 404።

📚፤ አንዱአለም ዳግማዊ (መምህር)፤ "ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት"፥ ገጽ 276 ብራና ማተሚያ ድርጅት፤ አ.አ፥ ሚያዚያ 1998 ዓ.ም።

[5] 📚፤ አግዛቸው ተፈራ (ዲያቆን)፤ "አልተሳሳትንምን?" 2ተኛ ዕትም፤ ገጽ 85፤ ሶላር ማተሚያ ቤት፥ መስከረም፤ 2010 ዓ.ም፤ አ.አ ኢትዮጵያ።

[6] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ "መጽሐፈ ሰዓታት" ገጽ 148።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ ገጽ 169፥ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1983 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ ውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው፤ ገጽ 194፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ አዲስ አበባ፤ 1983 ዓ.ም።

[7] 📚፤ አስረዳ ባያብል (ሊቀ ጠበብት)፤ "ማህሌተ ጽጌ ትርጓሜ፤ አ.አ፥ ገጽ 79፥ 1998 ዓ.ም።

(7.2▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ ማርያም #በቤተመቅደስ ውስጥ ኖራለች የሚለውን #አባባል ከማየታችን በፊት መልአኩ #ፋኑኤል ማን ነው? የሚለውን ማየቱ #ተገቢ ነው።

▶️ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በርካታ #መላእክት እንዳሉ ቢገለጽም #ስማቸው ግን የተጠቀሱ #ቅዱሳን #መላዕክት #ገብርኤል#ሚካኤል#ሱራፌል#ኪሩቤል ብቻ ናቸው። ሌሎቹ #ስሞቻቸው #በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጠቀሰው በአጋጣሚ ወይም ተረስተው ሳይሆን #የመላእክትን አምልኮ #ሰዎች እንዳይከተሉ #እግዚአብሔር የወሰደው ጥንቃቄ ነበር {ዘዳ 4፤ 19-24}። በስም የተጠቀሱት #ኃያላን መላእክት በየትኛውም #መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክፍል ብናነብ የአገልግሎታቸው #ማእከል #የክርስቶስ #ጌትነት ነበር። #መላእክት በተጠቀሱበት አንቀጽ ሁሉ ሄደን ብናነብ #የኢየሱስ ክርስቶስ #ክብርና #አዳኝነት ለህዝብ ሁሉ ጥቅም እንዲሆንና ለእርሱ #እንደሚሰግዱ #እንደሚዘምሩ #እንደሚያመልኩትም ክብሩን #እንደሚጠብቁ ለማሳየት የተጠቀሱ ናቸው {ሉቃ 1፤ 26-38፣ 2፤ 10-14፣ ማቴ 2፤13፣ 4፥11፣ ራዕ 4፤ 7-11፣ ራዕ 12፤ 7-12}።

▶️ መልአኩ #ፋኑኤል ግን #በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ #ስሙ ባለመጠቀሱ እንዲህ የሚባል #መልአክ አለ ለማለት #መረጃ የለም። ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን #መልአክ መኖሩን በስም የጠቀሰው አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ #በተአምረ ማርያም መጽሐፍና #በ18ኛው ክፍለ ዘመን ያልታወቀ ጸሐፊ ምናልባት #ደብተራ የጻፈው <<ድርሳነ ፋኑኤል>> ከተባለው #አዋልድ #መጽሐፍት ውጪ አይታወቅም።

▶️ በቁሙ የመልአኩ #ፋኑኤል #ተግባር ነበር ተብሎ የተጠቀሰውን #የማርያምን #ሰማያዊ #ህብስት (ምግብ) እና #ሰማያዊ #መጠጥ #ማርያም #ቤተመቅደስ ውስጥ ነበረች እስከተባለችበት 12 ዓመት ሙሉ #በየሰዓቱ #በታማኝነት ማመላለሱን እያንዳንዱ #የቤተመቅደሱን #ታሪክ #በመጽሐፍ ቅዱስ ሲዘገብ #የፋኑኤል ድካም አለመጻፉ ታሪኩን #ተራ ያሰኘዋል። ይልቁንም #እግዚአብሔር አምላክ የፍጥረት ሁሉ #ምግብ #በምድር ላይ አደረገ የሚለው #ለአእምሮ የሚመች ነው {ዘፍ 1፤ 29-31}።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

(7.3▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat