ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.84K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ሮሜ 8÷34 " #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡" #ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና…


ስለዚህም ክፍሉን ስናየው እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? ብሎ ጠየቀ ።ምን ብሎ
መለሰ? << #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው>>ብሎ ነው የመለሰው ።ይህ ማለት
ከሳሹ ማነው? #እግዚአብሔር ነው ማለት አይደለም ።ምክንያቱም #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ራሱ #አይከሳቸውምና በተመሳሳይም
<< #የሚኮንንስ ማነው?
>ብሎ ጠየቀ ምን ብሎ መለሰ? የሞተው ይልቁንም #ከሙታን የተነሣው #በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ #ስለ እኛ #የሚማልደው #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው
ብሎ ነው የመለሰው ።
<< #የሚኮንንስ ማነው?>>
የምትለዋን ጥያቄ ስንመለከት #የሚኮንን ከምትለው ቀጥሎ <#ስ> ፊደል
መግባቷ አንድን ነገር በተመለከተ #በዚያው ጉዳይ ላይ #በድጋሜ የተጠየቀ መሆኑን ያመለክታል። #የእግዚአብሔርን #ምርጦች በተመለከተ " #ማን #ይከሳቸዋል?"ብሎ ጠይቆ ነበርና "" #የሚኮንንስ #ማነው"" ብሎ #በድጋሜ ይጠይቃል ።ይህ ማለት #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #ማን #ይከሳቸዋል?
#እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #ማን #ይኮንናቸዋል?ማለት ነው ወይም ደግሞ
<< #እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል ? #የሚኮንናቸውስ ማነው?
>>ማለት ነው።
ወይም
<< #የእግዚአብሔርን ምርጦች ማን #ይከሳቸዋል?
ማንስ #ይኮንናቸዋል? >>ማለት ነው ።
ለምሳሌ ፦
<< #የአስቴር እኅት #ስሟ #ማነው? #የእናቷስ?>>
ብየ ብጠይቅ ምን እያልኩ ነው? < #የአስቴር እኅት ስሟ ማነው? #የእስቴር እናት ስሟ #ማነው?> ማለት ነው ።
< #ስ> ፊደል አስቴርን በተመለከተ #በድጋሜ #የተጠየቀ መሆኑን ያመለክታል ።

ስለዚህ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል ብሎ ጠይቆ #የሚኮንንስ
#ማነው? ማለቱ የእግዚአብሔርን ምርጦች #የሚኮንናቸው ማነው? ማለቱ ነው።
ደግሜ ልበለው
"< #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? ማንስ
#ይኮንናቸዋል?> ማለት ነው ።


እስኪ #በ1938 ዕትም የተጻፈውን ቃል ተመልከቱ ፦
<<እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች የሚነቅላቸው ማነው #እሱ #ካጸደቀ ማነው #የሚኮንን? >>
ይላል ።እንግዲህ ተመልከቱ ፦ ።<<እሱ #ካጸደቀ ማነው #የሚኮንን?>>የሚለውን
በደንብ አስምሩበት ።
አንድምታ ተርጓሚዎችም ፦
<< #ለእመ ለሊሁ #ያጸድቅ #መኑ #ዘይኮንን ፤ " #እሱ #ቢያጸድቅ #ማን #ይኮንናል?>> ብለውታል።
#እግዚአብሔር #ያጸደቀውን ማን #ይኮንናል? ማለት እንደሆነ
ልትረዱ ይገባል። #የሚኮንንስ ማነው የሚለው #ጥያቄ #እግዚአብሔር #መርጦ
#ያጸደቃቸውን ማን #ይኮንናቸዋል ማለት ነው ።ይህን አስቡበት!!

" #ቅዱስ #ዮሐንስ #አፈወርቅም" ሲተረጉም እንዲህ ብሏል ፦
<< #እግዚአብሔር #ዘውዱን #አቀዳጅቶናል #የሚኮንነን #ማነው? #ክርስቶስ
#ሞቶልናልና #መሞት ብቻ አይደለም #ከዚህም በኋላ #ስለ #እኛ #ስለሚማልድ #ማን #ይኮንነናል>
በማለት ተርጉሞታል።
📖/፤ ሐመር መጽሔት ሐምሌ 2007፥ ገጽ10።

#እንግዲህ #ቃሉን እንዴት እንደተገነዘቡት አስተውሉ!! ክርስቶስ
#ሞቶልናልና ማነው #የሚኮንነን? ክርስቶስ #ይማልድልናልና ማነው #የሚኮንነን?
በማለት ነው ያብራራው።
በእርግጥም #መሠረታዊ #ሐሳቡ ይህ ነበር ።
-----
@gedlatnadersanat
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ስለዚህም ክፍሉን ስናየው እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? ብሎ ጠየቀ ።ምን ብሎ መለሰ? << #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው>>ብሎ ነው የመለሰው ።ይህ ማለት ከሳሹ ማነው? #እግዚአብሔር ነው ማለት አይደለም ።ምክንያቱም #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ራሱ #አይከሳቸውምና በተመሳሳይም << #የሚኮንንስ ማነው? >ብሎ ጠየቀ ምን ብሎ መለሰ? የሞተው ይልቁንም #ከሙታን የተነሣው #በእግዚአብሔር…
<< #እግዚአብሔር የመረጣቸውን #የሚከሳቸው ማነው? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር
ነው>> ሮሜ8:33 አለ።

< #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው>> አለ። #እግዚአብሔር #የሚያጸድቀው #እነማንን
ነው? አግዚአብሔር #የሚያጸድቀው እሱ #የመረጣቸውን ነው።
እሱ < #የጠራቸውን እነዚህን #አጸደቃቸው> ሮሜ8:30 እግዚአብሔር #የመረጣቸውን እሱ ራሱ #የሚያጸድቃቸው ከሆነ እንግዲህ በእነዚህ ምርጦች ላይ ክስ ማንሳት የሚችል
ማነው? #ማንም ሊኖር አይችልም
#እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማንም #ሊከሳቸው አይችልም ለምን? ምክንያቱም #እግዚአብሔር #አምላካችን
#የመረጣቸውን #ምርጦቹን #የሚያጸድቅ አምላክ ነውና።
#እርሱ የመረጣቸውን
#ያጸድቃል ።እርሱ መርጦ #ያጸደቃቸውን ማን #ይከሳቸዋል?
<የጠራቸውን እነዚህን አጸደቃቸው> ተብሎ ተጽፏል። እርሱ እንዲህ አድርጎ ያጸደቀውን ማን
#ሊከስ ይችላል? ማንም #ሊከሳቸው አይችልም ።
---
<< #የሚኮንንስ ማነው? #የሞተው ይልቁን ከሙታን የተነሣው #በእግዚአብሔር ቀኝ
ያለው ደግሞም ስለ እኛ #የሚማልደው #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው >>
ከላይ እንዳየነው #ዮሐንስ አፈወርቅ እንደገለጸው
<< #እግዚአብሔር ዘውዱን
አቀዳጅቶናል ማን #ይኮንነናል? #ክርስቶስ ስለሞተልን ደግሞም ከዚህ በኋላ
#ስለሚማልድልን ማን #ይኮንነናል>> ባለበት አገላለጽ ስንመለከተው
#እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #ያጸድቃቸዋል ፣ታዲያ እርሱ መርጦ #ያጸደቃቸውን
#የሚከሳቸው ማነው? #የሚኮንናቸውስ ማነው? ማንም #ሊኮንናቸው አይችልም።
እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #የሚኮንናቸውስ ማነው? ማንም።
እግዚአብሔር #ምርጦቹን #የመረጣቸው በክርስቶስ ነው ።
<< #ቅዱስና #ነውር የሌለን #በፍቅር እንሆን ዘንድ #በክርስቶስ ኢየሱስ
#መረጠን>>ኤፌ1:4
-
ይላል።
ታዲያ እነዚህ የእግዚአብሔር ምርጦች #በክርስቶስ ናቸው።
#በክርስቶስ #ኢየሱስ ላሉት ደግሞ #ኩነኔ የለባቸዎም << #በክርስቶስ #ኢየሱስ #ላሉት አሁን #ኩነኔ የለባቸውም >>ሮሜ8:1
#በክርስቶስ #ኢየሱስ የሆኑት እነዚህ የእግዚአብሔር ምርጦች አሁን #ኩነኔ #የለባቸውም#ኩነኔ #የሌለባቸውን እነዚህን ምርጦች ማን #ይኮንናቸዋል? ማንም
#ሊኮንናቸው አይችልም።
ለምን? ምክንያቱም ለእነርሱ ሲል #የሞተ አለ ፣ለእነርሱ
ሲል #ከሞት የተነሳ አለ ፣ለእነርሱ ሲል #በእግዚአብሔር ቀኝ #የተቀመጠ አለ
፣ ለእነርሱ ሲል #የሚማልድ #ሊቀ #ካህናት አለ እርሱም #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው።
የእግዚአብሔር ምርጦች #ከኩነኔ #ነጻ የመሆናቸው #ማረጋገጫ በክርስቶስ ሞት
#ትንሣኤ#እርገት እና #ምልጃ ነው ።
#እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይኮንናቸዋል? ማንም #አይኮንናቸውም
ምክንያቱም ለእነርሱ ሲል #የሞተ አለ እርሱም #ክርስቶስ ነው።
#ክርስቶስ #ለምርጦቹ ሲል በደላቸውን ተሸክሞ በእንጨት ላይ #ሞቷል#በበደላቸው
የሚመጣባቸው #ፍርድ እሱ #ተሸክሟል #ፍርዱም #በሞቱ ተፈጽሟል ፣ታዲያ
#ክርስቶስ #ኢየሱስ የሞተላቸውን እነዚህን ምርጦች ማነው #የሚኮንን?
ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ #ሞት #ታርቀዋል /ሮሜ5:8/
ታዲያ ማነው #የሚኮንናቸው? ስለእነርሱ #መሞት ብቻ አይደለም ይልቁንም ስለ እነርሱ #ከሞት #ተነሥቷል ፣ለምን #ከሞት ተነሣ? ።
< #እኛን #ስለማጽደቅ #ከሙታን #ተነሣ> /ሮሜ4:24/
ተብሏል።
#ከሞቱ በበለጠ #ትንሣኤው #ከኩነኔ #ለመዳናቸው ትልቅ ዋስትናቸው ነው። እነርሱን #ለማጽደቅ ከሞት #ተነስቷል #በትንሣኤውም #ጸድቀዋል ፣በክርስቶስ
#ትንሣኤ #የጸደቁትን እነዚህን የእግዚአብሔር ምርጦች #ማን #ይኮንናቸዋል?
እነዚህ ምርጦች #ከእግዚአብሔር ጋር #በልጁ #በክርስቶስ #ሞት #ታርቀዋል
ይልቁንም #ከሞት #ተነስቶ ሕያው ሆኖ በመኖሩ በህይወቱ ደግሞ ይድናሉ ፦
< #ከእግዚአብሔር ጋር #በልጁ ሞት #ከታረቅን #ይልቁንም ከታረቅን በኋላ #በሕይወቱ #እንድናለን> /ሮሜ5:11/
#ክርስቶስ ባይነሳ ኖሮ #ጽድቃቸው አይረጋገጥም
ነበረ ኃጢአተኛ ሆነው ይቀሩ ነበር << #ክርስቶስ #ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት
እስከ አሁን ድረሰ #በኃጢአታችሁ #አላችሁ>> /1ኛቆሮ15:17/ #በክርስቶስ ትንሣኤ
ዘለለማዊ #ጽድቅ አግኝተዋል።
#እግዚአብሔር #በልጁ #ትንሣኤ #ያጸደቃቸውን
ምርጦቹን ማን #ይኮንናቸዋል? ማንም። ስለዚህ #የክርስቶስ #ትንሣኤ #ከኩነኔ #የሚድኑበት ማረጋገጫቸው ሆኗልና የእግዚአብሔርን ምርጦች ማንም
#አይኮንናቸውም
#ይህም ብቻ አይደለም #ክርስቶስ ወደ #ሰማይ አርጎ
#በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡም ታላቅ የደኅንነት #ማረጋገጫቸው ነው።
#ክርስቶስ ወደ ሰማይ የወጣው #የሰዎችን ሥጋ #እንደያዘ ነው።
<< #ወደላይ
#በወጣህ ጊዜ ምርኮን ማረክህ>> /ኤፌ4:7/ እንደተባለ ክርስቶስ #በኃጢአት #በሕግ
#በሞት #በሰይጣን እንዲሁም ከማንኛውም ጠላት ሥር የነበረውን #የሰውን ሥጋ
ከጠላት ማርኮ በድል አድራጊነት ይዞት #በሰማያዊ ሥፍራ #በቀኙ ሥጋችንን #ሲያስቀምጠው በእርሱ #በኩል ከሞት በላይ መሆናችን ማንም ዝቅ ሊያደርገው
#በማይችል ከፍታ ላይ #መሆናችን ሲታወቅ በእርግጥም በእንዲህ አይነት ከፍታ
#ከፍ ያደረጋቸውን የእግዚአብሔር ምርጦች ማንም #ሊኮንናቸው አይችልም።
<< #ከክርስቶስ ጋር አስነሳን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ #ስፍራ ከእርሱ ጋር
#አስቀመጠን >> /ኤፌ2:7/ለው
ያለውም ይህን ነው ።
#ስለ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት #ይታይላቸው ዘንድ
ወደ ሰማይ #ገብቷልና #ማንም #ይኮንናቸው ዘንድ አይችልም
/ዕብ9:24/

እግዚአብሔር መርጦ #ያጸደቀንን ማን #ይከሰናል? #ክርስቶስ #ለኃጢአታችን
#የሞተልንን ማን #ይኮንነናል? #ክርስቶስ እኛን #ለማጽደቅ ከሞት ተነስቷል ታዲያ
ማን #ይኮንነናል? ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት #ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ
ገብቷልና ማን #ይኮንነናል? ክርስቶስ #ስለ እኛ #ይማልዳልና ማን ይኮንነናል?

አሜን ሃሌ ሉያ። ማንም

የክፍሉ ዓብይ ሀሳብ ይህ ነው። ይህንን ከተረዳን። ነገ ደግሞ ስለዚህ ጥቅስ የተነሱትንና የተባሉትን የተለያዩ ኑፋቄዎች እንመለከታለን።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
<< #እግዚአብሔር የመረጣቸውን #የሚከሳቸው ማነው? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው>> ሮሜ8:33 አለ። < #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው>> አለ። #እግዚአብሔር #የሚያጸድቀው #እነማንን ነው? አግዚአብሔር #የሚያጸድቀው እሱ #የመረጣቸውን ነው። እሱ < #የጠራቸውን እነዚህን #አጸደቃቸው> ሮሜ8:30 እግዚአብሔር #የመረጣቸውን እሱ ራሱ #የሚያጸድቃቸው ከሆነ እንግዲህ በእነዚህ ምርጦች ላይ ክስ ማንሳት…
🔽▶️

*⃣ #ሮሜ 8፥34 እና #የመናፍቃኑ እርስ በእርስ አለመግባባት፦

‹‹ #የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ #በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› (ሮሜ 8፡34)፡፡

#በልማድ ለያዙት #የተሳሳተ ትምህርት አልመች ያለውና #በምንፍቅና #ጎዳና ላይ ሆነው #የአዳኛችንን #የኢየሱስ ክርስቶስ #የማዳን ግብር የሆነው #የምልጃ ሥራውን ሽምጥጥ አድርገው #በመካድ ላሉት #ሰዎች ይህ #ጥቅስ #ራስ ምታት ሆኖባቸው ይታያል፡፡ ከዚህም የተነሳ #ቤተክርስቲያኗ ይህን ጥቅስ " #የሚፈርድ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም #ከሙታን ተለይቶ የተነሳው፥ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞም " #ስለእኛ #የሚፈርደው" ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" በሚል አስቀምጣዋለች።
📖 2000 እትም 80 አሀዱ መጽሀፍ ቅዱስ
ለዚህም ደግሞ እንደ #ምክንያት የቀረበው " #የሚማልደው የሚለው ከጊዜ ቡሀላ #መናፍቃን #የጨመሩት ነው እንጂ ቀደም ሲል የነበረው #የግእዙ ትርጉም #የሚፈርደው ነው የሚለው" የሚል ነው።" ይህንንም ተከትሎ ብዙዎች የተለያዩ #ምክንያቶችንና ማስተባበያዎችን ለማቅረብ ሞክረዋል። እስኪ #ከብዙዎች አንዳንዶቹን እንያቸው፤

〽️1፦ ‹‹የጠራው #የግእዙ #የመጽሐፍ ቅዱስ #ኀይለ ቃል ተለውጦና #በዘመናት ሁሉ ለዚህች #ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢሆን #መልካም ዐስበው በማያውቁ ይልቁንም #ፈራርሳ #ቢያይዋት ደስ በሚሰኙ #የክርስቶስን #ፈራጅነት በካዱ #በባሕር ማዶ #ቀሣጪዎች ብዙ ጊዜ #ተሰርዞ #ተቀይሮ ይገኛል›› የሚል #አስተያየት ይሰጣሉ። ለዚህም #በ1938 በፊላደልፊያ የታተመው #መጽሀፍ ቅዱስ፣ #በ1975 #በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ " #ከግእዝ ወደ ዐማርኛ" የተመለሰው ዐዲስ ኪዳን(በግዕዝና በአማርኛ የታተመውን)፣ #በ1953 #በአሥመራ የታተመው ዐዲስ ኪዳን እና #በ1938 የታተመው #የዐማርኛ #ዐዲስ ኪዳን #መጻህፍትን ይጠቅሳሉ።
📖/፤ ሮዳስ ታደሰ (መጋቤ ዐዲስ)፣ ነገረ ክርስቶስ - ክፍል አንድ (የካቲት 2008)፤ ገጽ 479
📖/፤በርሀ ተስፋ መስቀል (መምህር)፣ "አንባቢው ያስተውል" (መቕለ፣2005) ገጽ 33 የግርጌ ማስተወሻ።
📖/፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምዕመናን የቅዱስ እስጢፋኖስ ጉባኤ፤ ፍኖተ ብርሃን(ጥቅምት 1990) ገጽ 51።
( #ደስታ ተክለ ወልድ፤ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት
"ቀሠጠ"፦ #በስውር ከፍሎ ሰረቀ፣ #ወሰደ#ዐበለ
"ቀሣጢ"፦ #የቀሠጠ#የሚቀሥጥ ዐባይ #ሌባ፤ ብሎ ያስቀምጠዋል(ገጽ 1093)። በዚህ ትርጉም መሰረት ጸሀፊው " #ቀሣጢዎች" ሲሉ " #የሰውን ነገር #የሚወስድ#የሚሰርቅ#ሌባ ለማለት መሆኑን ልብ ይሏል።)

▶️ #በዚህ ጽሑፍ መሠረት " #ይማልዳል የሚለው #መናፍቃን #የጨመሩት እንጂ ትክክለኛ #ትርጉም አይደለም፡፡" ነገር ግን ጸሐፊው ማስተዋል የተሣናቸው #ሐዋርያው #ግእዝ #የጽሑፍ ቋንቋ ባልነበረበት ዘመን ይህን #መልእክት #ለሮሜ ሰዎች #የላከ መሆኑን ነው፡፡ ሐሳቡን #ግልጽ ለማድረግ ይህ #መልእክት #ወደ ሮሜ ሰዎች ሲላክ #ግእዝ ለጽሑፍ #የማይመችና #አናባቢ የሌለው #ቋንቋ ነበር፡፡ በዚህም #ምክንያት #ግእዝ #የሮሜን #መልእክት ለማስተናገድ #አቅም #አልነበረውምና #በግእዝ የተጻፈውን #ምንጭ ማድረግ #የተበከለ #ምንጭ እንደ #መጠጣት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ማንም ብልህ አንባቢ #ቀዳሚውን #ምንጭ መፈለግ ግድ ይለዋል።
ግሪኩ እንዲህ ይላል..

τίς ὁ κατακρινῶν ? Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών , μᾶλλον δὲ ἐγερθείς (ἐκ νεκρῶν) ὅς ‹καί› ἐστιν ἐν δεξι το Θεο ὃς καὶ #ἐντυγχάνει(ኢንቲጋኬኖ) ὑπὲρ ἡμῶν /ሮሜ 8፥34/

*⃣" #entugchanó"፦
to chance upon, by impl. confer with, by ext. entreat
Original Word፦
#ἐντυγχάνω
Part of Speech፦
#Verb
Transliteration: #entugchanó
Phonetic Spelling፦
( #en-toong-khan'-o)
Short Definition፦
I meet, encounter, call upon, to chance upon, confer with, to #entract(in favor or against), deal with, make a #petition, make #intercession
📖/፤ STRONGS GREEK DICTIONARY OF THE NEW TESTAMENT፤ pg 29. No.1793)

👉 http://biblehub.com/greek/5241.htm

👉 https://www.biblestudytools.com/lexicons/greek/nas/entugchano.html

ከተለያዩ የግሪክ ቅጂዎችም ስናይ፦ 👇
http://biblehub.com/texts/romans/8-34.htm

Nestle Greek New Testament 1904

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθείς, ὅς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Westcott and Hort 1881

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθεὶς ἐκ νεκρῶν, ὅς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν·

Westcott and Hort / [NA27 variants]

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθεὶς (ἐκ νεκρῶν), ὅς [καί] ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν·

RP Byzantine Majority Text 2005

τίς ὁ κατακρίνων; Χριστὸς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ καὶ ἐγερθείς, ὃς καὶ ἔστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Greek Orthodox Church 1904

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ καὶ ἐγερθείς, ὃς καὶ ἔστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Tischendorf 8th Edition

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθείς, ὃς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Scrivener's Textus Receptus 1894

τίς ὁ κατακρίνων; Χριστὸς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ καὶ ἐγερθείς, ὃς καὶ ἔστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Stephanus Textus Receptus 1550

τίς ὁ κατακρινῶν Χριστὸς ὁ ἀποθανών μᾶλλον δὲ καί ἐγερθείς ὃς καὶ ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

@gedlatnadersanat
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
@gedlatnadersanat


ለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያኗ ራሷ በግርጌ ማስታወሻ " #በግሪኩ #የሚማልደው #ነው #የሚለው" ብላ የጻፈችው። ይህ ከሆነ ደግሞ #የአዲስ ኪዳን በኩረ ጽሁፍ(እናት ቋንቋ) #ግእዙ ሳይሆን #ግሪኩ መሆኑ ግልጽ ነው። #ግእዙን ጨምሮ ሁሉም #የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት #የትርጉም ሥራቸው የተሰራው #ከግሪኩ በመሆኑ የትኛውም የትርጉም ስራ ሲሰራ #ግሪኩ የሚለውን በማለት ግሪኩ የተወውን በመተው መስራቱ #ለእግዚአብሄር ቃል ያለንን ታማኝነት የምናሳይበት ትልቁ መንገድ ነው። #ግሪኩ እንዲህ #አይልም እያሉ ሌላ ነገር መጻፍ #ታማኝ መሆንን አያሳይም።

▶️ ይህ እንዳለ ሆኖ #ጸሀፊው #ከጠቀሱት #መጻሕፍት በፊት " #በዐጼ ሚኒልክ" ጊዜ የታተመው #የ1887 ዕትም #መጽሀፍ ቅዱስ ይህን ጥቅስ እንዴት #አስፍሮት እንዳለ #መመልከቱ መልካም ነው።
" #ማን ነው የሚኮንን? ክርስቶስ የሱስ የሞተ ነውን? ከሙታን እንኳ የተነሣ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ እርሱም #ያስምረናል"

አንባቢው ልብ እንዲል የሚገባው ነገር #ሰዎቹ እያሉ ያሉት " #ከጊዜ ቡሀላ #የታተሙት ናቸው እንጂ #ቀደምት ዕትሞች " #ክርስቶስ ያማልዳል" አይሉም የሚል ሲሆን እነርሱ #የቀደሙ ናቸው ከሚሏቸው #ቀድሞ #ለንባብ የበቃው #መጽሀፍ ግን እነርሱ እንዲልላቸው የሚፈልጉትን ሳይሆን #እውነታውን #አስፍሮት ይገኛል።
#ወንድሞቻችን መፈናፈኛ ሲያጡ " #እናንተ የቀየራቹትን ሳይሆን #አባቶቻችን ቀደም ሲል #በግእዝ ጽፈው ያስቀመጡልንን ነው የምንቀበለው" ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚሁ ደግሞ #በግእዝና #በአማርኛ ተዘጋጅቶ #በትንሣኤ #ማተሚያ ቤት የታተመውን #መጽሀፍ በዋናነት የሚጠቅሱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ #ግእዙን መሠረት አድርጎ ነው #የታተመው #የሚባለውንና #በ2000 ዓ.ም ለንባብ የበቃውን 80 አሀዱ #መጽሀፍ ቅዱስ ያነሳሉ።
#በግእዝና በአማርኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ ምንም እንኳን በአማርኛው
" #የሚፈርድ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም #ከሙታን ተለይቶ የተነሳው፥ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞም " #ስለእኛ #የሚፈርደው" በማለት ቢያስቀምጡትም ግእዙ ራሱ ግን
" #ወመኑ፡ ውእቱ፡ እንከ፡ ዘይትዋቀሦሙ ለኅሩያነ እግዚአብሔር ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ፤ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ኢየሱስ ዘሞተ፡ ወተንሥአ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር #ወይትዋቀሥ #በእንቲአነ" በሚል ነው የሰፈረው።(ሮሜ 8፤ 33-34)
📖/፤ ትንሳኤ ማሳተሚያ ድርጅት ዐዲስ ኪዳን በግእዝና በዓማርኛ (ዐዲስ አበባ፤ 1994) ገጽ 644።

ሰዎቹ " #ይፈርዳል" እንዲልላቸው የሚጠብቁት ቃል " #ወይትዋቀሥ" የሚለውን ነው።
ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
🔽 " #ተዋቀሠ" የሚለውን ቃል ትርጉም " #ተሟገተ#ተከራከረ" እንደሆነ በግልጽ አስቀምጠውታል።
ይህ እንዲህ ሳለ ግን #ሰዎቹ ከመሰረተ ሀሳቡ #ውጭ በሆነ ሁኔታ #ለመተርጎም የተነሳሱበት ምክንያት #ከእግዚአብሄር ቃል ይልቅ #ለፈቃዳቸው ቅድሚያ የሚሰጡ #ሰዎች በመሆናቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
📖/፤ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(አለቃ)፣ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ዐዲስ፣(1948) ገጽ 401።

" #ይከራከል" የሚለው እንዲያውም " #ይማልዳል" ከሚለው በላይ #ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የሚቆም #መካከለኛ መሆኑን #አጠንክሮ ይገልጣል እንጂ #ይፈርዳል ማለትን አያመለክትም፤ #ግእዙን እንኳን የተጠቀምነው #በአገራችን የተለመደ #ጥንታዊ ትርጓሜ ነው በማለት እንጂ #የአዲስ ኪዳን #መጻህፍት ሁሉ በመጀመሪያ በተጻፉበትና ለሁሉም #ትርጓሜዎች መሰረት በሆነው #የግሪክ ቋንቋ በግልጽ #የሚማልደው ተብሎ ተቀምጧል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው #በግሪክ ቋንቋ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም። ይህንን ስለ እኛ #የሚማልደው የሚለውን ቃል « #የሚፈርደው» ብለው የቀየሩ ሰዎች ራሱ በግሪኩ #የሚያማልደው እንደሚል ራሳቸው ይስማማሉ።(ፎቶው ላይ የግርጌ ማስታወሻውን ይመልከቱ)

@gedlatnadersanat
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ብዙ ሴቶች #ማርያም በሚል ስም ይጠራሉ[1]። [ለምሳሌ]👇

〽️ 1፦ "የሙሴ እህት ማርያም"
/ዘጸ 2፥4-8/

▶️ የዚችን #ማርያም ታሪክ #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ ስናይ #ወንድሟ #ሙሴ በወንዝ #ዳር #በተጣለ ጊዜ በእርሱ ላይ የሚሆነውን #ለማወቅ ስትመለከት ወደ ወንዙ የመጣችውን #የፈርኦንን #ልጅ #በጥበብ አነጋግራና #እንድታጠባው የገዛ #እናታቸውን #በሞግዚትነት ስም አገናኝታ ወንድሟ #ሙሴ እንዲያድግ #አስተዋጽኦ ያደረገች ናት። #ሙሴም በዚህ እድልና በእግዚአብሄር #አላማ አድጎ #እስራኤላውያንን #የኤርትራን #ባህር ካሻገራቸው በኋላ #ነብይት ሆና #ሴቶችን #በመዝሙርና #በምስጋና መርታለች {ዘጸ 15፥20}። ከዛ ግን #ማርያም #የሙሴን የበላይነት ካለመውደዷ የተነሳ #ኢትዮጵያዊት #ሚስቱን ምክንያት አድርጋ #አማችው#እግዚአብሔር ግን #በለምጽ #ቀጣት {ዘኅ 12 ; ዘዳ 24፥9}። በመጨረሻም #እስራኤላውያን ገና በጉዞ ሳሉ #በቃዴስ #በረሃ #ሞተች በዚያው #ተቀበረች። {ዘኅ 20፥1}።

〽️ 2፦ "የዩቴር ልጅ የዕዝራ የልጅ ልጅ ማርያም" {1ዜና 4፥17} ፦

▶️ የዚች #ማርያም ታሪክና ተግባሯ ብዙም አልተጠቀሰም

〽️ 3፦ "የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም" {ሉቃ 1፤ 26-27} ፦

▶️ ሙሉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ታሪኳ <13🌐☑️ ቅድስት ድንግል ማርያም በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ> በሚለው ርእስ ስር ይቀርባል።

〽️ 4፦ "የማርታና የዓላዛር እህት ማርያም" {ዩሐ 11፥1} ፦

▶️ ከኢየሩሳሌም አጠገብ ባለው #ቢታንያ በተባለው #መንደር #ከእህቷ #ማርታና ከወንድሟ #አላአዛር ጋር ትኖር ነበር። አንድ ቀን #ጌታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስም ወደ ቤታቸው ሄዶ ሲጠይቃቸው ይህቺ #ማርያም ወደ እርሱ #ቀርባ ቃሉን #በጽሞና #ስለሰማችና #ስለተማረች #ክርስቶስ አመስግኗታል {ሉቃ 10፤ 39-42}። ወንድሟ #አላአዛርም #ከሙታን በተነሳ ጊዜ #ከጌታ #ኢየሱስ ጋር ብዙ ተነጋግራለች {ዩሐ 11}። ቀድም ብሎም ይቺ #ማርያም #ጌታችን እንደሚሞት አውቃ #በናርዶስ #ሽቶ #እግሩን ቀብታውም ነበር። {ዩሐ 12፤ 1-8}።

〽️ 5፦ "መግደላዊት ማርያም"፦

▶️ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ሰባት #አጋንንት ከእርሷ ካወጣላት ቡኃላ ታገለግለው ነበር {ሉቃ 8፥2 , ማር 15፥40}። ይህቺ #ሴት ለክርስቶስ #መሰቀልና #መነሳት #ምስክር ነበረች {ማቴ 27፤፦55 ፣ 56 ፣ 61, ማር 15፤ 40-47 ፣ ዩሐ 19፤25 ፣ ማቲ 28፤ 1-10 ፣ ማር 16፤ 1-8፣ ሉቃ 24፤10}። #ከትንሳኤውም ቡሀላ #በአትክልት ቦታ ለብቻዋ #ክርስቶስን #ካየችውና #ካነጋገረችው ቡሀላ የመጀመሪያዋ #ትንሳኤውን #መስካሪ ሆናለች {ዩሐ 20፤ 1-18}።

〽️ 6፦ "የቀለዩጳ ሚስት ማርያም "፤

▶️ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ #ከመስቀሉ #አጠገብ ቆማ ነበር {ዩሐ 19፤25}።

〽️ 7፦ "የማርቆስ እናት ማርያም"፤

▶️ ሐዋሪያት ተሰብስበው በቤቷ #ይጸልዩና #ይመካከሩ ነበር {ሐዋ 12፥12}።

እንደምናየው #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ #ብቻ #ማርያም ተብለው የሚጠሩ #ሰባት #ሴቶች አሉ። #እስራኤላውያንም #ለልጆቻቸው #ስም ሲያወጡም ሆነ #ለራሳቸው የሆነ #ስያሜ #ሲመርጡ ከልዩ #የሕይወት #ታሪካቸው ጋር #የተያያዘውን ነው።
አንዳንዶች በተለይ " #ማርያም" የሚለውን ስም #የጌታችን #የኢየሱስ #ክርስቶስን #እናት ብቻ #ማእከል አድርገው በሚገርም ሁኔታ #ተርጉመው #ሌላ #ትምህርት ለዛውም #ከእግዚአብሄር #ብቸኛ የማዳን #ተግባር ጋር #የሚጋጭ አርገው እንዲህ ተርጉመውታል።👇👇

🔆 1ኛ ትርጉም፦

" #ማርያም" ማለት " #ፍጽምት" ማለት ነው። መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን #ንጽሐ ሥጋ #ንጽሐ ነፍስ #በድንጋሌ ሥጋ #በድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና።

🔆 2ኛ ትርጉም፦

" #ማርያም" ማለት #ጸጋ #ወሀብት(ጸጋና ሀብት) ማለት ነው። #ለእናት #ለአባቷ #ጸጋ ሆና ተሰጣለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁሉ #ጸጋ ሆና #ተሰጥታለች

🔆 3ኛ ትርጉም፦

" #ማርያም" ማለት #መርሕ #ለመንግሥተ ሰማያት(የመንግሥተ ሰማያት መሪ) ማለት ነው። ምዕመናንን መርታ #ገነት #መንግስተ #ሰማያት አግብታለችና።

🔆 4ኛ ትርጉም፦

"ማርያም" ማለት #ልዕልት ማለት ነው። #መትሕተ ፈጣሪ #መልዕልተ ፍጡራን(ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) ይሏታልና።

🔆 5ኛ ትርጉም፦

ተላአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ {#የእግዚአብሄርና #የህዝብ #ተላኪ ማለት ነው።[2]