ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram


የአገራችን ቅዱሳን እውን መንፈሳዊ ናቸው ??

#በአገራችን ቅዱሳን ተብለው ታቦት ተቀርጾ -ቀን ተሰይሞ -ገድል ተጽፎላቸው ቃል ኪዳን ተቀብለዋል እየተባሉ ከወር እስከወር የሰው ልብ ላይ ነግሰው የአምላክ ገንዘብ የሆነውን ስግደትና ዝማሬ መስዋእትም በጸጋ ስም የሚኮመኩሙ የቡልጋ የትግራይና የጎጃም ተወላጅ የሆኑ አፈጣጠራቸው አኑዋኑዋራቸውና ትምህርታቸው አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያልተሰማ #ክንፍ ያወጡ/#ሰውነታቸው ተበሳስቶ አሳ የሚሾልክበት/ #ከተወለዱ በሶስተኛው ቀን ያማተቡ/#ከተፈጠሩ ምግብ ያልቀመሱ/#ባህር ውስጥ 12 አመት #ምድር ላይ ሰባት አመት በአንድ እግራቸው ቆመው የጸለዩ ይገኙበታል።
የእነዚህ ሰዎች መንፈሳዊነት አጠያያቂ እየሆነ መጥቶአል። መንፈሳዊ ሊሆኑ የማይችሉ ይልቁንም የክርስቶስን ክብር እንዲጋርዱ ሰይጣን የተጠቀመባቸው እንደሆኑ ለዛሬ በ6 ምክንያቶች እንመልከት….

1፦ እድሜአቸው -
#ዘፍ 6-3 “የሰው ዘመኖቹ መቶ ሃያ አመት ይሆናሉ“በማለት የእድሜ ጣራ ተበጅቶአል.
#መዝ 90-10 “የዘመኖቻችንም እድሜ ሰባ ቢበረታም ሰማኒያ ነው“ይላል. እውነትም እንደ አብረሃም፣ ዳዊት፣ ሙሴ ያሉ ታላላቅ አባቶች እንኩዋን ከዚህ አልዘለሉም።
#አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ግን 562 #ክርስቶስ ሰምራ 375 አመት ኖሩ ተብለናል።

2፦ አፈጣጠራቸው፦
#ዘፍ 1-25 እግዚአብሄር ሁሉን እንደወገኑ እንደፈጠረ ይናገራል. ክንፍ ለአእዋፍ ወገን እንጂ ለሰው ወገን ተሰጥቶ አያውቅም። ተክልዬ ግን 6 ክንፍ እንደተሸለሙ በገድላቸው ተጽፎአል። እንደውም አንዳንድ ሸርዳጆች “የምትበላው የላት የምትከናነበው አማራት“ን እየጠቀሱ “እግር የላቸው ክንፍ አማራቸው “ ሲሉ ሰምቻለሁ። ደግሞስ የት በረሩበት?? እግዚአብሄር ግዜአዊ ችግርን ለመቅረፍ ተፈጥሮን አይቀይርም። ቀይሮም አያቅም። ትልቅ የእግዚአብሄር አጀንዳ የተሸከመው ጳውሎስ እንኳን በደማስቆ ሊይዙት ባሉ ግዜ በቅጥሩ ላይ በቅርጫት ወረደ እንጂ ያለፍጥረቱ ክንፍ አልተሰጠውም። ጌታን ራሱ ሊይዙት ሲሉ በመካከላቸው አልፎ ይሄድ ነበር እንጂ ሌላ አካል አልተገጠመለትም ወይም ክንፍ አላበቀለም። ኤልያስ ከኤልዛቤል በተደበቀ ግዜ ክንፍ ባለው ቁራ ስጋ ይመጣለት ነበር እንጂ ክንፍ አልወሰደም።
የአቡየ በህይወት ዘመን እህል አለመቅመስ ተረት ነው።
ጌታ “ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም“ አለ እንጂ ያለምግብ ይኖራል አላለም።
#ጌታም ተርቧል
#ኤልያስም እንዲሁ……ስጋ ያለምግብ መኖር አይችልምና
ሉቃ 7-34 “መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላ የወይን ጠጅም ሳይጠጣ መጥቶ ነበርና። ጋኔን አለበት አላችሁት።“እንዳለው ጋኔን ያለበት ካልሆነ በቀር……ማርያም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን መቀመጫ ሰገራ እንዳይመጣባቸው ደፈነች የሚለውም የሌለ ነው። ሰው ይበላል ይጸዳዳል። ጌታም ሰይጣን በህመም የደፈነውን መቀመጫ ይከፍታል እንጂ አይደፍንም።

3፦ ለሰይጣን ያላቸው ፍቅር-እነዚህ ሰዎች ለሰይጣን አንጀታቸው ስፍስፍ ነው የሚለው። ክርስቶስ ሰምራ መንፈሳዊ ከሆነች #2ቆሮ 6-15 “ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው??“-#ዘፍ 3-15 “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ“የሚለውን በማወቅ ሰይጣንን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ አትሞክርም ነበር።
ተክልዬም “ባህረ አልቅም“ የተባለውን ሰይጣን ከባህር አውጥተው “ክርስቶስ ሐረዬ“(ክርስቶስ የመረጠው) ብለው ስሙን ቀይረው አገልጋይ አያደርጉትም ነበር።
እግዚአብሄር ሰው ቢያጣ እንኳን ሰይጣንን ለአገልግሎት አይመርጥም።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ሰይጣንን ድንጋይ አሸክመው አያሰሩም ነበር።
አቡነ አረጋዊም እንደዛሬው ዳን ቴክኖክራፍት ሊፍት በዘንዶ አቀበት አይወጡም ነበር።
ምናልባት ይህን ክፍል አላነበቡትም ይሆናል ብለን እናልፋቸዋለን.. 👇
የማቴዎስ ወንጌል 25:41

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ #ለሰይጣንና ለመላእክቱ #ወደ #ተዘጋጀ ወደ #ዘላለም #እሳት ከእኔ ሂዱ።
ሲኦል ራሱ የተዘጋጀው ለሰይጣን ነው መንግስተ ሰማያት ለሰይጣን ቦታ የለም።

4፦ በአንድ አካባቢና ግዜ የተወሰኑ ናቸው፦
የእነዚህ ሰዎች አገልግሎት ከቡልጋና ከአክሱም አልወጣም።
#የተክልዬን ዝክር አሻሮ ያሸተተ ይጸድቃል
#በደብረሊባኖስ የተቀበረ ይድናል -…ወዘተ የሚሉ አሻሮና ደብረሊባኖስ የማታወቅበትን አህጉርና አለም ያላማከሉ አግልግሎቶች(Localized) ናቸው።
እንግሊዝ/ናይጀሪያ/ካናዳ ዝክርና አሻሮ አያውቁም። ሌላው በቅርብ አመታት ክንፍ ያላቸው ፣
በአንድ እግራቸው 7 አመት የሚቆሙ -
ሰውነታቸው ተበሳስቶ አሳ የሚሹለከለክበት ቅዱሳን እንዴት የሉም የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

5፦ መንፈሳዊ ውጊያቸው
#2ቆሮ 10-3 “በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤“ እንደሚል ክርስቲያን ስጋና ደም ከሌለው ጠላት ጋር ስለሚዋጋ የጦር እቃው ጦርና ጋሻ አይደለም።
አቡየ ገ/መንፈስ ቅዱስ ግን ዝቋላ ተራራ ላይ ከሰይጣን ጋር በመብረቅ ይዋጉ ነበር።

6፦ ቃል ኪዳናቸው -የእግዚአብሄር የመዳንና የዘላለም ህይወት መንገድ አንድና በግልጽ የተነገረ ነው። እሱም በልጁ በኢየሱስ አምኖ ... ይሁንና የቅዱሳን ቃልኪዳን የሚባለው ኢ-መጽሃፍ ቅዱሳዊ ብቻ ሳይሆን ሰዎች በሃጢአታቸው እንዲሞቱና ሲኦል የሚጨምር የሰይጣን ምክር አለበት። የእከሌን ገድል ያነበበ-ያስነበበ-የተረጎመ እስከ 10 ትውልድ ምሬልሃለሁ የሚል -#በአቡነ አረጋዊ ስም የተማጸነ 15 ትውልድ ምሬለታለሁ የሚል ምንፍቅና ነው።

ወገኖቼ ሆይ ይህንን እውነት ስንናገር እነሱ ግን የእግዚአብሄር ጠላት ሆነው የቅዱሳን ጠላት ይላሉ። እባካችሁ ከዚህ አዚም ውጡና በሙሉ ልባችሁ ንስሀ ገብታቹ እግዚአብሄርን አክብሩ አምልኩ።

#ተሃድሶ ለተረታተረት

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

@gedlatnadersanat @teeod
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
<< #እግዚአብሔር የመረጣቸውን #የሚከሳቸው ማነው? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው>> ሮሜ8:33 አለ። < #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው>> አለ። #እግዚአብሔር #የሚያጸድቀው #እነማንን ነው? አግዚአብሔር #የሚያጸድቀው እሱ #የመረጣቸውን ነው። እሱ < #የጠራቸውን እነዚህን #አጸደቃቸው> ሮሜ8:30 እግዚአብሔር #የመረጣቸውን እሱ ራሱ #የሚያጸድቃቸው ከሆነ እንግዲህ በእነዚህ ምርጦች ላይ ክስ ማንሳት…
🔽▶️

*⃣ #ሮሜ 8፥34 እና #የመናፍቃኑ እርስ በእርስ አለመግባባት፦

‹‹ #የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ #በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› (ሮሜ 8፡34)፡፡

#በልማድ ለያዙት #የተሳሳተ ትምህርት አልመች ያለውና #በምንፍቅና #ጎዳና ላይ ሆነው #የአዳኛችንን #የኢየሱስ ክርስቶስ #የማዳን ግብር የሆነው #የምልጃ ሥራውን ሽምጥጥ አድርገው #በመካድ ላሉት #ሰዎች ይህ #ጥቅስ #ራስ ምታት ሆኖባቸው ይታያል፡፡ ከዚህም የተነሳ #ቤተክርስቲያኗ ይህን ጥቅስ " #የሚፈርድ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም #ከሙታን ተለይቶ የተነሳው፥ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞም " #ስለእኛ #የሚፈርደው" ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" በሚል አስቀምጣዋለች።
📖 2000 እትም 80 አሀዱ መጽሀፍ ቅዱስ
ለዚህም ደግሞ እንደ #ምክንያት የቀረበው " #የሚማልደው የሚለው ከጊዜ ቡሀላ #መናፍቃን #የጨመሩት ነው እንጂ ቀደም ሲል የነበረው #የግእዙ ትርጉም #የሚፈርደው ነው የሚለው" የሚል ነው።" ይህንንም ተከትሎ ብዙዎች የተለያዩ #ምክንያቶችንና ማስተባበያዎችን ለማቅረብ ሞክረዋል። እስኪ #ከብዙዎች አንዳንዶቹን እንያቸው፤

〽️1፦ ‹‹የጠራው #የግእዙ #የመጽሐፍ ቅዱስ #ኀይለ ቃል ተለውጦና #በዘመናት ሁሉ ለዚህች #ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢሆን #መልካም ዐስበው በማያውቁ ይልቁንም #ፈራርሳ #ቢያይዋት ደስ በሚሰኙ #የክርስቶስን #ፈራጅነት በካዱ #በባሕር ማዶ #ቀሣጪዎች ብዙ ጊዜ #ተሰርዞ #ተቀይሮ ይገኛል›› የሚል #አስተያየት ይሰጣሉ። ለዚህም #በ1938 በፊላደልፊያ የታተመው #መጽሀፍ ቅዱስ፣ #በ1975 #በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ " #ከግእዝ ወደ ዐማርኛ" የተመለሰው ዐዲስ ኪዳን(በግዕዝና በአማርኛ የታተመውን)፣ #በ1953 #በአሥመራ የታተመው ዐዲስ ኪዳን እና #በ1938 የታተመው #የዐማርኛ #ዐዲስ ኪዳን #መጻህፍትን ይጠቅሳሉ።
📖/፤ ሮዳስ ታደሰ (መጋቤ ዐዲስ)፣ ነገረ ክርስቶስ - ክፍል አንድ (የካቲት 2008)፤ ገጽ 479
📖/፤በርሀ ተስፋ መስቀል (መምህር)፣ "አንባቢው ያስተውል" (መቕለ፣2005) ገጽ 33 የግርጌ ማስተወሻ።
📖/፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምዕመናን የቅዱስ እስጢፋኖስ ጉባኤ፤ ፍኖተ ብርሃን(ጥቅምት 1990) ገጽ 51።
( #ደስታ ተክለ ወልድ፤ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት
"ቀሠጠ"፦ #በስውር ከፍሎ ሰረቀ፣ #ወሰደ#ዐበለ
"ቀሣጢ"፦ #የቀሠጠ#የሚቀሥጥ ዐባይ #ሌባ፤ ብሎ ያስቀምጠዋል(ገጽ 1093)። በዚህ ትርጉም መሰረት ጸሀፊው " #ቀሣጢዎች" ሲሉ " #የሰውን ነገር #የሚወስድ#የሚሰርቅ#ሌባ ለማለት መሆኑን ልብ ይሏል።)

▶️ #በዚህ ጽሑፍ መሠረት " #ይማልዳል የሚለው #መናፍቃን #የጨመሩት እንጂ ትክክለኛ #ትርጉም አይደለም፡፡" ነገር ግን ጸሐፊው ማስተዋል የተሣናቸው #ሐዋርያው #ግእዝ #የጽሑፍ ቋንቋ ባልነበረበት ዘመን ይህን #መልእክት #ለሮሜ ሰዎች #የላከ መሆኑን ነው፡፡ ሐሳቡን #ግልጽ ለማድረግ ይህ #መልእክት #ወደ ሮሜ ሰዎች ሲላክ #ግእዝ ለጽሑፍ #የማይመችና #አናባቢ የሌለው #ቋንቋ ነበር፡፡ በዚህም #ምክንያት #ግእዝ #የሮሜን #መልእክት ለማስተናገድ #አቅም #አልነበረውምና #በግእዝ የተጻፈውን #ምንጭ ማድረግ #የተበከለ #ምንጭ እንደ #መጠጣት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ማንም ብልህ አንባቢ #ቀዳሚውን #ምንጭ መፈለግ ግድ ይለዋል።
ግሪኩ እንዲህ ይላል..

τίς ὁ κατακρινῶν ? Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών , μᾶλλον δὲ ἐγερθείς (ἐκ νεκρῶν) ὅς ‹καί› ἐστιν ἐν δεξι το Θεο ὃς καὶ #ἐντυγχάνει(ኢንቲጋኬኖ) ὑπὲρ ἡμῶν /ሮሜ 8፥34/

*⃣" #entugchanó"፦
to chance upon, by impl. confer with, by ext. entreat
Original Word፦
#ἐντυγχάνω
Part of Speech፦
#Verb
Transliteration: #entugchanó
Phonetic Spelling፦
( #en-toong-khan'-o)
Short Definition፦
I meet, encounter, call upon, to chance upon, confer with, to #entract(in favor or against), deal with, make a #petition, make #intercession
📖/፤ STRONGS GREEK DICTIONARY OF THE NEW TESTAMENT፤ pg 29. No.1793)

👉 http://biblehub.com/greek/5241.htm

👉 https://www.biblestudytools.com/lexicons/greek/nas/entugchano.html

ከተለያዩ የግሪክ ቅጂዎችም ስናይ፦ 👇
http://biblehub.com/texts/romans/8-34.htm

Nestle Greek New Testament 1904

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθείς, ὅς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Westcott and Hort 1881

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθεὶς ἐκ νεκρῶν, ὅς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν·

Westcott and Hort / [NA27 variants]

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθεὶς (ἐκ νεκρῶν), ὅς [καί] ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν·

RP Byzantine Majority Text 2005

τίς ὁ κατακρίνων; Χριστὸς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ καὶ ἐγερθείς, ὃς καὶ ἔστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Greek Orthodox Church 1904

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ καὶ ἐγερθείς, ὃς καὶ ἔστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Tischendorf 8th Edition

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθείς, ὃς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Scrivener's Textus Receptus 1894

τίς ὁ κατακρίνων; Χριστὸς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ καὶ ἐγερθείς, ὃς καὶ ἔστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

Stephanus Textus Receptus 1550

τίς ὁ κατακρινῶν Χριστὸς ὁ ἀποθανών μᾶλλον δὲ καί ἐγερθείς ὃς καὶ ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ ὃς καὶ #ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

@gedlatnadersanat