▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ብዙ ሴቶች #ማርያም በሚል ስም ይጠራሉ[1]። [ለምሳሌ]👇
〽️ 1፦ "የሙሴ እህት ማርያም"
/ዘጸ 2፥4-8/
▶️ የዚችን #ማርያም ታሪክ #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ ስናይ #ወንድሟ #ሙሴ በወንዝ #ዳር #በተጣለ ጊዜ በእርሱ ላይ የሚሆነውን #ለማወቅ ስትመለከት ወደ ወንዙ የመጣችውን #የፈርኦንን #ልጅ #በጥበብ አነጋግራና #እንድታጠባው የገዛ #እናታቸውን #በሞግዚትነት ስም አገናኝታ ወንድሟ #ሙሴ እንዲያድግ #አስተዋጽኦ ያደረገች ናት። #ሙሴም በዚህ እድልና በእግዚአብሄር #አላማ አድጎ #እስራኤላውያንን #የኤርትራን #ባህር ካሻገራቸው በኋላ #ነብይት ሆና #ሴቶችን #በመዝሙርና #በምስጋና መርታለች {ዘጸ 15፥20}። ከዛ ግን #ማርያም #የሙሴን የበላይነት ካለመውደዷ የተነሳ #ኢትዮጵያዊት #ሚስቱን ምክንያት አድርጋ #አማችው። #እግዚአብሔር ግን #በለምጽ #ቀጣት {ዘኅ 12 ; ዘዳ 24፥9}። በመጨረሻም #እስራኤላውያን ገና በጉዞ ሳሉ #በቃዴስ #በረሃ #ሞተች በዚያው #ተቀበረች። {ዘኅ 20፥1}።
〽️ 2፦ "የዩቴር ልጅ የዕዝራ የልጅ ልጅ ማርያም" {1ዜና 4፥17} ፦
▶️ የዚች #ማርያም ታሪክና ተግባሯ ብዙም አልተጠቀሰም
〽️ 3፦ "የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም" {ሉቃ 1፤ 26-27} ፦
▶️ ሙሉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ታሪኳ <13🌐☑️ ቅድስት ድንግል ማርያም በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ> በሚለው ርእስ ስር ይቀርባል።
〽️ 4፦ "የማርታና የዓላዛር እህት ማርያም" {ዩሐ 11፥1} ፦
▶️ ከኢየሩሳሌም አጠገብ ባለው #ቢታንያ በተባለው #መንደር #ከእህቷ #ማርታና ከወንድሟ #አላአዛር ጋር ትኖር ነበር። አንድ ቀን #ጌታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስም ወደ ቤታቸው ሄዶ ሲጠይቃቸው ይህቺ #ማርያም ወደ እርሱ #ቀርባ ቃሉን #በጽሞና #ስለሰማችና #ስለተማረች #ክርስቶስ አመስግኗታል {ሉቃ 10፤ 39-42}። ወንድሟ #አላአዛርም #ከሙታን በተነሳ ጊዜ #ከጌታ #ኢየሱስ ጋር ብዙ ተነጋግራለች {ዩሐ 11}። ቀድም ብሎም ይቺ #ማርያም #ጌታችን እንደሚሞት አውቃ #በናርዶስ #ሽቶ #እግሩን ቀብታውም ነበር። {ዩሐ 12፤ 1-8}።
〽️ 5፦ "መግደላዊት ማርያም"፦
▶️ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ሰባት #አጋንንት ከእርሷ ካወጣላት ቡኃላ ታገለግለው ነበር {ሉቃ 8፥2 , ማር 15፥40}። ይህቺ #ሴት ለክርስቶስ #መሰቀልና #መነሳት #ምስክር ነበረች {ማቴ 27፤፦55 ፣ 56 ፣ 61, ማር 15፤ 40-47 ፣ ዩሐ 19፤25 ፣ ማቲ 28፤ 1-10 ፣ ማር 16፤ 1-8፣ ሉቃ 24፤10}። #ከትንሳኤውም ቡሀላ #በአትክልት ቦታ ለብቻዋ #ክርስቶስን #ካየችውና #ካነጋገረችው ቡሀላ የመጀመሪያዋ #ትንሳኤውን #መስካሪ ሆናለች {ዩሐ 20፤ 1-18}።
〽️ 6፦ "የቀለዩጳ ሚስት ማርያም "፤
▶️ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ #ከመስቀሉ #አጠገብ ቆማ ነበር {ዩሐ 19፤25}።
〽️ 7፦ "የማርቆስ እናት ማርያም"፤
▶️ ሐዋሪያት ተሰብስበው በቤቷ #ይጸልዩና #ይመካከሩ ነበር {ሐዋ 12፥12}።
እንደምናየው #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ #ብቻ #ማርያም ተብለው የሚጠሩ #ሰባት #ሴቶች አሉ። #እስራኤላውያንም #ለልጆቻቸው #ስም ሲያወጡም ሆነ #ለራሳቸው የሆነ #ስያሜ #ሲመርጡ ከልዩ #የሕይወት #ታሪካቸው ጋር #የተያያዘውን ነው።
አንዳንዶች በተለይ " #ማርያም" የሚለውን ስም #የጌታችን #የኢየሱስ #ክርስቶስን #እናት ብቻ #ማእከል አድርገው በሚገርም ሁኔታ #ተርጉመው #ሌላ #ትምህርት ለዛውም #ከእግዚአብሄር #ብቸኛ የማዳን #ተግባር ጋር #የሚጋጭ አርገው እንዲህ ተርጉመውታል።👇👇
🔆 1ኛ ትርጉም፦
" #ማርያም" ማለት " #ፍጽምት" ማለት ነው። መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን #ንጽሐ ሥጋ #ንጽሐ ነፍስ #በድንጋሌ ሥጋ #በድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና።
🔆 2ኛ ትርጉም፦
" #ማርያም" ማለት #ጸጋ #ወሀብት(ጸጋና ሀብት) ማለት ነው። #ለእናት #ለአባቷ #ጸጋ ሆና ተሰጣለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁሉ #ጸጋ ሆና #ተሰጥታለች።
🔆 3ኛ ትርጉም፦
" #ማርያም" ማለት #መርሕ #ለመንግሥተ ሰማያት(የመንግሥተ ሰማያት መሪ) ማለት ነው። ምዕመናንን መርታ #ገነት #መንግስተ #ሰማያት አግብታለችና።
🔆 4ኛ ትርጉም፦
"ማርያም" ማለት #ልዕልት ማለት ነው። #መትሕተ ፈጣሪ #መልዕልተ ፍጡራን(ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) ይሏታልና።
🔆 5ኛ ትርጉም፦
ተላአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ {#የእግዚአብሄርና #የህዝብ #ተላኪ ማለት ነው።[2]

▶️ ምስለ ፍቁር ወልዳ ተብሎ የተሰየመው #ሥዕል "አንዲት ሴት ('ማርያም') ልዩ #ሐምራዊ_መጎናጸፊያ ለብሳ በአንድ #ረዘም ያለ #ወንበር ላይ ተቀምጣና #በግራ እጇ ልጇን ('ኢየሱስን') ታቅፋ በቀኝ ትከሻዋ በኩል #ክንፉን ወደላይ #የዘረጋ #ሰው የሚመስል ('መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል')፣ በግራ ትከሻዋም በኩል እንደዚሁ #ክንፉን ወደላይ #የዘረጋ #ሰው የሚመስል ('መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል') ሆነው እነዚህ 'መላእክት' በአንዳንድ ቦታ ላይ #ሰይፍ አንዳንድ ጊዜም #አበባ አንዳንድ ጊዜም የ "ቸ" ቅርጽ ያለው #በትር አንዳንዴም #ጦር ይዘው የሚሳለው #ሥዕል ነው።
▶️ ይህ #ሥዕል በተለይ #በኢትዮጵያ በብዙ #አዋልድ_መጽሐፍት ውስጥና #በፖስተር #መልክ ተስሎ #በየገዳማቱና #አድባራቱ እንዲሁም በየገበያ ቦታ በተለያየ መጠን ይገኛል። ይህን #ሥዕል ለመጀመሪያ ጊዜ #በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም /ወሎ -- አንባሰል/ ውስጥ ያለው "ጤፉት" እና "ተአምረ ማርያም" የተባሉት መጽሐፍት <<ወንጌላዊው ሉቃስ ስሏታል[1]>> ብለው ከሚናገሩት በቀር ከእሱ ውጭ ብዙ #መረጃ የለም። ያለው #መረጃ ቢበዛ #ትውፊት ወይም ሰው እርስ በእርሱ የሚያወራው የተለመደ #ወሬ ብቻ ነው።
▶️ እነዚህ #መጻሕፍት የሚናገሩለት #ስዕል #በኢትዮጵያ ዋና #መዲና በሆነችው #በአዲስ_አበባ ከተማ "ብሔራዊ ሙዝየም" ውስጥ በቁፋሮ ተገኘ ተብሎ የሚጎበኘው #ስዕል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ይህም #የአሳሳል_ጥበብና ሰዓሊው የተጠቀመባቸው #መሳሪያዎች ሲታዩ #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ገደማ የነበረ #ሰዓሊ እንደሆነ ያታመናል። ይህ ከሆነ ደግሞ #በወንጌላዊው ሉቃስና በዚህ #ስዕል መካከል #የ1,500 ዘመናት #ርቀት ስለሚኖር #ሉቃስ ሳላት የሚባለው #አፈ_ታሪክ ውሃ ይበላዋል። ይልቁንም #በገዳሙ #ታሪክ መሰረት "እፀ መስቀሉን" #በግሸን_ደብረ_ከርቤ_ገዳም አምጥቶ ሲሰጥ "የመጽሐፈ ጤፉት" እና "የተአምረ ማርያም መጽሐፍ" አብሮ በመስጠቱና የመጻሕፍቱ #ጸሐፊ #አጼ_ዘርዓ_ያዕቆብ በመሆኑ በሁለቱም #መጽሐፍት ውስጥ "ሉቃስን ማን መርማሪ ይመጣበታል እኛ ያልነውን የሚቀበል ሰው መች ይታጣል" በሚል በጊዜው #በድፍረት አስገብቶ ጽፎት እንደሚሆን #መገመት ይቻላል።
▶️ የካቶሊኩ #መጽሐፍ ግን የ "እመ አምላክ ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ሳለ የሚነገርለት ቅዱስ ሉቃስ መሆኑን ማረጋገጫና ማስረጃ የለንም" ብሏል[2]።
▶️ የቤተ ክርስቲያን #ታሪክ ፀሐፊ የሆኑት #ሉሌ_መልአኩም "ሉቃስ ስሎታል ብለው ብዙዎች ይተርካሉ" ብለው #በአፈ_ታሪክ ብቻ እንጂ #ምንጭ እንዳጡለት ገልፀዋል[3]።
▶️ በመሰረቱ #ወንጌላዊው_ሉቃስ #የህክምና_ባለሙያ እንጅ #ሰዓሊ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም {ቆላ 4፥14}። ፈጽሞ #የስዕል ጊዜ እንኳን የነበረው #ሰው አልነበረም።
ሌላው #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በድንግልና #ኢየሱስ ክርስቶስን ከወለደች ቡኋላ እንደ #መቅደስ ስርዓት #ግዝረት ለመፈጸም #በስምንተኛው ቀን (የመንጻት ወራቷ በተፈጸመ ጊዜ) ወደ #ቤተመቅደስ በመሄድ #የሙሴን_ህግ ስትፈጽም #የሙሴ_ህግ እንደሚያዘው አንዲት #ሴት ከወለደች ቡኋላ #የመንጻቷ ጊዜ ሲደርስ #ጠቦት (በግ) ይዛ #ስርዓቱን መፈጸም ነበረባት። በመሆኑም #ጠቦት የሚገዛ #ገንዘብ ስላልነበራት በድህነት አቅሟ #ህጉ የሚፈቅድላትን #ሁለት #የእርግብ_ጫጩቶች #ለመስዋት አቅርባለች [ሉቃ 2፥23፣ ዘሌ 12፥8]።
▶️ ማርያም በኖረችበት #ዘመን #የወፍ_ዝርያዎች ዋጋ 5 ሳንቲም ነበር [ማቴ 10፥29]። እነዚህን 2 #ጫጩቶች ማምጣቷ #ህጉ እንደሚል አንዱን #ስለሀጢአቷ ሌላኛው ደግሞ #ለሚቃጠል_መስዋዕት (እግዚአብሔርን ለማምለክ) ነበር [ዘሌ 12፥8]።
እንግዲህ #ማርያም ፈጽሞ #በድህነት ትኖር ከነበረችና #መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ከተናገረ #በስእሉ ላይ የተገለጸችው እጅግ #የከበረ ቤት ውስጥ #በዘመናዊ #ወንበር ላይ፣ #የከበረ #የወርቅ_ፈርጥ ያለባቸው #የሐር_መጎናፀፊያ (ወርቀ ዘቦ)፣ የሚገርም #ሐረጋማ ያሉት #የወርቅ_አክሊሎች #ዘመናውያን #ወይዛዝርት በሚቀቡት #የከንፈር_ቀለም (ሊፕስቲክ) ያሸበረቀችዋ #ሴት እውን #ማርያም ነች ብሎ ለመቀበል #ድፍረቱስ ይኖረን ይሆን?
ደግሞስ #አዋልድ_መጽሐፍት #ማርያም #ክርስቶስን ስትወልድ #የ16 ዓመት ወጣት ነበረች ካሉ #በስዕሉ ላይ የምትታየዋ ሴት #በግምት #ከ35-38 ዓመት የሆናት #ወይዘሮ እና #ከ12 ዓመት በላይ የሚሆነውን #ታዳጊ ወጣት #ታቅፋ የምትታየዋ #ስዕል #እውን #ማርያምንና_ክርስቶስን ይገልጻልን?
▶️ አንዳንድ ጊዜ #በአንዳንድ ቦታ ተስለው የሚገኙት ደግሞ "የማርያምና" የታቀፈችው #ልጅ መልክና #የጸጉር ቀለም #የሐበሻ #ጥቁር_ፀጉርና #አፍሮ ሁለቱም አንገቶቻቸው #ባለንቅሳት የሆኑ አሁን እነዚህ #እስራኤላዊያን የነበሩትን #ማርያምና #ክርስቶስን ይገልጻሉን?
▶️ ሌላኛው "የማርያም ስዕል" ደግሞ #በእንዝርት #ጥጥ_ስትፈትል የሚያሳየውን ብንመለከት ይህ #የቤት_ተግባር #የኢትዮጵያን እናቶች ተግባር ወይስ #የእስራኤላውያን ባህል?
▶️ በመሆኑም ሁሉንም #የማርያምን_ስዕል ደርድረን ብንመለከተው #ሰዓሊው ደስ ያለውን #ቀለምና_ቅርጽ ያሳረፈበት ለእለት ጉርሱ #ለገበያ ያቀረባቸው #ምስሎች ስለሆኑ #አምልኮና_ስግደቱን ትተን #ስዕሎቻችንን #ለቅርስነትና #ለማስተማርያ ብቻ እናውላቸው!
@gedlatnadersanat
(9.6▶️ጥያቄ) ይቀጥላል. . .