አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
502 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እኔ #እምፈልገው

እውነት ለመናገር እኔ ምፈልገው
ካንቺ ጋር መጋባት
ይህን ሀምሌ ፊቴን : ደጋግሞ ማራባት
ከወፎች ጋር መንቃት : በጊዜ ቤት መግባት::
"ምንም ደሃ ቢሆን: ባይኖረውም ሀብት
ከደጃፍ ሲቀመጥ: ደስ ይላል አባት"
ለሚል መናኛ ጥቅስ: ኑሮየ ማይመጥን
ሲሻኝ በየባንኩ: ስፈልግ በሳጥን
የተረፈኝ ገንዘብ
ደጃፍ ላይ ቁጭ ብየ: ድሀ የምታዘብ
ተምሳሌትነቴ የሚዳረስ ባለም
ሞዴል አባወራ ተብየ ምሸለም
አገሬን ማስከበር
ህዝቤን ማስተባበር
የልጅ ልጅ አፍርቼ
በመቶ አመት ሙቼ
ስላሴ መቀበር
ምኞቴ ይህ ነበር::
እውነት ለመናገር እኔ እምፈልገው
ወንደላጤ ኑሮ
በሴቶች መታጀብ : ልክ እንዳውራ ዶሮ
ጊዜ ጥሎኝ ቢሄድ : ቀን ቢገሰግስም
መላው ጭንቅላቴ : ገብስማ ቢለብስም
ላቅማዳም ነው እንጂ: ለትዳር አልደርስም::
ደሞ
ዘር መዝራት እርሜ ነው : ደጋግሜ ባርስም
ባለመኖር ላሉት: ስቃይ አላወርስም
ቢፈልግ ሌላው ህዝብ
ይፈልፍል እንደዝንብ
ይባዛ እንደንጉዳይ
አገር ስራው ያውጣው! ሰው የራሱ ጉዳይ!!
የራሴ ፈጣሪ- ነኝ የራሴ ገዳይ!!
እኔ እምፈልገው...
እኔ እምፈልገው..
እኔ እምፈልገው
-----------
ገንዘብ ቢመዘበር: በገንዘብ ይተካል
እድሜ ለጉልበትሽ : በላቡ ለሚያድር
በውርስ በስጦታ : ግፋ ቢል በብድር::
በቆጠብነው ቁጥር
ጊዜ ነው የሚያጥር
እድሜ ነው የሚያልቀው
የምንፈልገውን በቅጡ ሳናውቀው::
👉በውቀቱ ስዩም
👍1
#እኔ #ወድሻለሁ


እኔ ወድሻለሁ
ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት
እንደዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ
ደርቦ እንደመምታት

እኔ ወድሻለሁ
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሽ እንደመውረስ

እኔ ወድሻለሁ
እንደመቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ
ያንች ልዝብ ሰይጣን፡፡

ከማለዳ ድባብ የተወሰደ
👍3
#እኔ #ላንቺ #ብዬ

ካንበሳ ደቦል ጋር ትግል ገጥሜለሁ

#ነብርን በካልቾ

#ዝሆንን በቡጢ አንከባልያለዉ

አንድ አገር ወጠምሻ ክንዱን አሳብጦ

ሊነካሽ ቢሰለፍ በሰከንድ ዉስጥ ሆኜ ቡጢ ሰንዝሪአለዉ

ጥርሶቹን ማርገፌን አስታዉሰዋለዉ

ብቻ ወ.ዘ.ተ ወ.ዘ.ተ ብዬሽ የነበረዉ
ሰክሬ ነዉ😳

እንደዉ ስታስቢዉ ከአንበሳ ደቦል ጋር
ሊያዉም ላንቺ ብዬ ስታገል የምገኝ

እኔ ታርዛን ነኝ

ማን አባቴ ነኝ

ብዙ ጎርሬአለሁ መቼም ስጋ ለባሽ ትንሽ ከቀመሰ የሚለዉን አያቅም

በይ እዉነቱን ስሚ እድሜዬን በሙሉ ከጠብ የምርቅ ሰው ነኝ

በተቻለኝ አቅም እንኳን ሰዉ ልመታ ነብርን በርግጫ እህ!! ከሩቅ ያየሁ ለታ ሞፋራን ያስንቃል የምሮጠው ሩጫ

አላወቅሽ
ከሁሉም ከሁሉም እኔ የገረመኝ
አንድ አገር ወጠምሻ ክንዱን አሳብጦ
ሊነካሽ ቢሰለፍ በሰከንድ ዉስጥ ሆኜ
ቡጢ ሰንዝሬለዉ ጥርሶቹን ማርገፌ ብዬ የነገርኩሽ እህ!! አይ እኔ..

ምንድን ነዉ እንደዚ ዝም ብሎ መተርተር መለክያ ሲጨበጥ ቲቢት በዝቶ ነዉ ልክ እንደ ህንድ አክተር እኔ ምልሽ

ባረቄ መአበል ልቤን አሳብጄ ጉራዬን ስነዛ
ከቻልሽ አረ ወደዛ
ወይም አረ ትንሽ በዛ

ብሎ እንደመሸሽ ሁሉንም ያመንሽኝ ምን ነክቶሽ ነው ዉዴ

ክሬዚ ነሽ እንዴ
ሰትገርሚ በናትሽ
👍5😁1
#እኔ_ደግሞ …."


ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……

#እኔ_ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።

ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ

#እኔ_ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።

ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።

ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።

ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ

#እኔ_ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።

ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።

በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….

#እኔ_ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።

የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።

እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!

🔘አሌክስ አብርሃም 🔘
#እኔ_አንዳንዴ_ስሰጥ

ኑሮ ለገረፈው ፤ በችግር አለንጋ
በረሃብ ጠውልጎ፤ እጁን ለዘረጋ
በመከራ ስለት፤ ጎኑን ለተወጋ
ለዚህ ብሶተኛ፤
ለዚህ ጉዳተኛ፤
ጥቂት ልመፀውት፤ ከኪሴ እገባለሁ
ከብሮች መካከል፤ብሮች አወጣለሁ
አምስት ብርአውጥቼ፤ልሰጠው እልና
እኒህ አምስት ብሮች፤ ይበዙብኝና
አራቱን ለመስጠት፤ጥቂት ሳሰላስል
'ለእኔ አይበዛብኝም ለእሱ ይበዛል' ስል
ሶሥት ብር ለመስጠት፤ውሳኔ ደርሼ
'ጎዶሎ አይሰጥም፤ እልና መልሼ
በሁለት ብሮች ላይ፤ፍርዴን እሰጣለሁ
ፍርዴን ግን መልሼ፤ እከልሰዋለሁ
ሁለት ብር ከምሰጥ፤ ለመንገድ ልመና፤
አንዳንድ እንካፈል፤ ብዬ እወስንና
'አንድ ብር ብሰጠው፤ለዚህ ብሶኛ
ሆላ ቢጠጣበቸፈት፤ እያልኩ አስብና
ያችን አንድ ብርም፤ ኪሴ እከታታለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ!" ብዬው እሄዳለው
#እኔ_ግን ....

አውቃለሁ ታውቂያለሽ
ለኔ አትገቢኝም
በውበት ካንቺ ጋር
አልወዳደርም
አውቃለሁ ታውቂያለሽ
ላንቺስ አልገባ
ተንሰፍስፈውልሽ
ባለሀብቶች ሁላ
አውቃለሁ ታውቂያለሽ
አላገኝሽ ከቶ
ከኔ የተሻለ
አገር ምድሩን ሞልቶ
አውቃለሁ ታውቂያለሽ
እንደማትፈልጊኝ
ወይ ዝና ወይ ክብር
ምንም ስለሌለኝ
ይህን ግን አታውቂም
አውቃለሁ ግን እኔ
በእውነት ያፈቀርኩሽ
ብቸኛው ሰው ሆኜ
እንደምናፍቅሽ
ለህይወት ዘመኔ
አውቃለሁ ግን እኔ፡፡
#ሮዛ


#ክፍል_ሀያ(🔞)


#እኔ_ እና_ኢህአዴግ

ስለ ሚጡ እንድጽፍ የሆንኩት ትላንት ማታ 3፡15 ላይ በኤድናሞል ሲኒማ ያየሁት ፊልም ነው፡፡ ፊልሙን ያየነው ከራኪ ጋር ሲሆን እኔ ፔሬድ ላይ ስለነበርኩ ቢዝነስ አልሄድኩም፡፡ ራኪ በበኩሏ ገና ለገና ከምሳ ደውላ ነው
ዛሪ ማታ ስራ እንደማትገባ ያወጀችው፡፡ ምነው ምን ሆንሽ ስላት «ባክሽን እምሴን ማስደብደብ ሰለቸኝ። ባግዳድ እንኳ እንደኔ እምስ አልተደበደበችም፡፡ ዛሬ የዓመት እረፍት ልወጣ ነው አለችኝ"
ራኪ የድሬዳዋ ልጅ በመሆኗ ቃላት አትመርጥም፡፡ በአነጋገሯ ታስደነግጠኛለች፡፡ በስልክ እንደዛ ስትልኝ
ታከሲ ውስጥ ነበርኩ፡፡ ሁሉም ተሳፋሪ በስልከ ያለችኝን የሰማ ስለመሰለኝ ተሸማቅቄ ልሞት። ግን ደግሞ ግልጽነቷ፣ ነጻነቷ እና ለምንም ነገር ኬረዳሽ መሆኗ ያስቀናኛል፡፡

ማታ ተያይዘን ፊልም ገባን፡፡ "In Time" የሚባል ፊልም ነው ያየነው፡፡ የፊልሙ ጸሀፊ እና ዳይሪክተር በዚህ ፊልም
ለአለም ህዝብ ሊያስተላልፉ የፈለጉት ጠንካራ መልእከት እንዳለ አሰብኩኝ፡፡ አንዳንዴ ሲነሳብኝ እንደ ሸሌ ሳይሆን እንደ ፈላስፋ አስባለሁ፡፡ ይህ ፊልም ራኪን በዱካክ ሊገድላት ነበር፡፡ ለኔ
ግን ትልቅ ግንዛቤ ሰጥቶኝ ነው ያለፈው፡፡ በዚህ የጥድፊያ ዓለም በእርጋታና በስከነት ይህንን ፊልም የተመለከተ ሊተላለፍ የተፈለገውን ቁልፍ መልእከት በደንብ ይረዳል።

በፊልሙ እንደተተረከው ሕጻናት ከእናቶቻቸው ማሕጸን ወጥተው ይቺን ምድር ሲቀላቀሉ በምድር የሚቆዩበት
እድሚ ከክርናቸው ግርጌና ከመዳፋቸው አናት ላይ ተጽፎ ነው፡፡ የዚህች አገር ነዋሪ
ማንኛውንም ነገር ሲገዛ እንደገዛው ነገር ዋጋ ከእድሜው ላይ ይቀነሳል፡፡ገንዘቡ እድሜው ነው ፡፡ታክስና የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ከእድሜው ላይ ይቀነስበታል፡ማንኛውንም ስራ ሲሰራ ደግሞ እድሜ እንደ ደሞዝ ይጨመርለታል፡፡ ያማረውን ነገር ሁሉ ከገዛ እድሜው ያጥራል፤ ሕይወቱ በአጭሩ ይቀጫል፡፡ በፊልሙ ላይ ጥቂት እድሜ የቀራቸው ነዋሪዎች ርሃብና ችጋር እያሰቃያቸው ላለመሞት ሲሉ (ማምሻም እድሜ ነው" እንዲሉ) ምግብ አይገዙም፤ ለመሞት በርካታ አመታት የቀራቸውን ሰዎች ከእድሜያቸው የፈቀዱትን ያህል ቻርጅ እንዲያደርጉላቸው ይማጸናሉ፡፡ ልክ እኛ አገር በደም እጥረት ተቸግረው በከፍተኛ ሕመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ደም በበጎ ፈቃድ የሚለግስ ሰው እንዳለ ሁሉ በፊልሙ ምናባዊ አለምም ሞት አፋፍ ላይ ለተጠጉ ሰዎች ከእድሜው ቀንሶ የሚለግስ ሰው እንዳለ ሁሉ በፊልሙ ምናባዊ አለምም ሞት አፋፋ ላይ ለተጠጉ ሰዎች ከእድሜው ቀንሶ የሚለግስ ሰው አለ...

የፊልሙም አጠቃላይ ጭብጥ ይኸው ነው፡፡ ሰዎች በእድሜያቸው ላይ ይህ ነው የሚባል ስልጣን የላቸውም
እኛ ባናውቀውም የሆነ እድሜ ተቆንጥሮ ተሰጥቶናል፡፡ ወደድንም ጠላንም ጊዜያችን ሲደርስ ይሂችን ምድር እንሰናበታታለን። ተንኮል ክፋት ለመስራት ብዙም ጊዜ የላትም አድሜያችን፡፡life is too short to be mean! ስለዚህ እድሜያችን መጉደሏ ላይቀር ስለሌላው እንኑር የሚል መልእከት ነው ያለው ፊልሙን ያየው ሰው የተለያየ ትርጉም ሊሰጠው ይችላል። እኔ ግን የስራዬ ጸባይ ነው መሰለኝ የፊልሙ ጭብጥ አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር አያይዤ ለማሰብ ሞከርኩ፡፡ አሁን በመላው አለም በስፋት ከተንሰራፋው የሆዳምነት እና የገንዘብ ፍቅር ጋር ነው ያያዝኩት። በፊልሙ ላይ እንደተመለከትኩት
ህልውናውን ለማቆየትና ሕይወት ለመቆየት የረባ ስልጣን የላቸውም፡፡ የእድሜያቸው ባርያ ሆነዋል እያንዳንዷን ድርጊታቸውን የሚያሰላስሉት ከእድሜያቸው አንጻር ነው፡፡ እድሚ ገንዘብ ስለሆነ ያን ቢያደርጉ አይገርምም፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ባለንበት አለም ሰው የገንዘብ እና የቁስ ተገዥ ሆኗል፡፡ እኔ ሸሌ የሆንኩት ወሲብ እርካታ ስለሚሰጠኝ እይደለም፡፡ የምፈልገውን ገንዘብ አግኝቼ ህይወቴን ለማቆየት ነው፡፡ ይህ የዘመናችን ዋና መገለጫ ነው። የዚህ ዘመን ሰው አብዛናውን ጊዜውንጉልበቱና እውቀቱን ሁለቱን ነገሮች ለማሟላት ያጠፋል፡፡ በርግጥ ከየትኛውም ዘመን በላይ ሁለቱ ነገሮች እጅግ አስፈላጊ የሆኑበት ጊዜ እርከን ላይ ደርሰናል፡፡ ገንዘብንም ቁሳቁስንም የፈጠረው ሰው ቢሆንም እድሜ ለካፒታሊዝም ስርአት
የሰው ልጅ ለፈጠራቸው ሁለት ነገሮች ባርያ ሆኗል፤ ልክ በፊልሙ ላይ የቀረቡት ሰዎች ለእድሚያቸው ባርያ እንደሆኑት ማለት ነው።

ፊልሙን የወደድኩበት ምክንያት እንደ አብዛኞቹ የአገራችን ተልካሻ ፈልሞች ሰሪዎች ጥልቅ ሀሳብ እና ፍልስፍና የሌለው ፊልም አይደለም፡፡ የኛ ፊልም ሰሪዎች ኮሜዲ እያሉ የሚጃጃሉት ነገር ያበግነኛል።ኮሜዲ ብለው ቢያስቁን እኮ አንድ ነገር ነው፡፡ ጫት ቤት የሚወሩ ቀልዶች እንኳ በወጉ ቢሰበሰቡ የተሻለ ያስቃሉ፡፡ በመጃጃል ሰውን ለማሳቅ መሞከር ግን ቋቅ ይላል፡፤ ሁልጊዜ የአገር ውስጥ ፈልም አለያም ብዬ እገዘትና ከአንዱ ሌላው ይሻላል በሚል እንዲሁም በጓደኞቼ በነራኪ ግፊት አያለሁ፡ አብዛኛዎቹ በተንጋደደ እንግሊዘኛ፣ በስድብና በተረብ ሕዝቡን እያሳቁ ፊልም ሰራን ሲሉ አፍርባቸዋለሁ፡፡ ኑሯችን ትራዴጂ ፊልማችን ኮሜዲ" የተባለው እውነት ነው፡፡እን ራኪ ኮሌጅ ስለበጠሰሽ የፈረንጅ ፊልም ካልሆነ
አላይም እያልሽ አካበድሽ ይሉኛል ብዬ ነው እንጂ በአገሬ ቋንቋ የተሰራ ፊልም ከማይ ኡዝቤኪስታን ወይ የታጃኪስታን ወይ የአፍጋኒስታን ፈልም ብመለከት እመርጣለሁ። አረ እንደውም ድምጽ አልባ ፊልም የተሻለ ያግዘናናኛል፡፡

ፊልሙን ጨርሰን ስንመጣ ራኪ በዱካክ ሞትኩ እለቸኝ፡፡ ፈልሙ ግን ገብቶሻል" አልኳት? “በይ እሺ ቀጥይ"ትርጉም በስለሺ" አለችኝ፡፡ ሁልጊዜም እንደምናደርገው ካልዲስ በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን ስለ ፈልሙ ማውራት ጀመርን፡፡ “ስለ ምንድነው ግን በደንብ አልገባኝም አለቸኝ ኮስተር ብላ፡፡ " አንቺን
ፈርቼሽ ነው እንጂ አቋርጬ ሁሉ ልወጣ ነበር ።የገባኝን ያህል ነገርኳት፡፡

"ራኪ.. ምን መሰለሽ_እድሜ ዘመናችሁን ሁሉ ገንዘብ፣ ቤት ልብስ፣ መኪና፣ ሞባይል፣ ገለመኔ እያላችሁ የጥድፊያና የውክቢያ ኑሮ አትምሩ፡፡ በስክነትና በእርጋታ እንዲሁም በተመስጦ ካሰላሰላችሁ ውስጣችሁን በደንብ ካደመጣቹ ስጋንም መንፈስንም የሚያረካ ሕይወትን መምራት ትችላላችሁ
የአለም መንግስታትም በካፒታሊዝም የአለምን ሕዝብ ገንዘብና ቁስ አምላኪ ማድረጋችሁ ተገቢ አደለም። ሰው
ለፈጠራቸው ነገሮች ባርያ መሆኑ እጅግ አስነዋሪ ነው፡፡ የአለም ስርአትን ቀይሩት። በከፍተኛ የሞራል ዝቅጠት ውስጥ ነው ያለነው” የሚል መልዕክት ያለው ፊልም ነው አልኳት፡፡

"በስማም እና ፊልም የገባን መስሎኝ ነበር፡፡ ለካንስ Yougo church ነበረ ይዘሸኝ የሄድሽው" ብላ ሳቀች
አትቀልጂ ባከሽ! አሪፍ ፊልም ነው ራኪ ሙች፣ በጣም ነው የመሰጠኝ"
ሮዚ ሙች አንቺ እኮ ሌክቸር ነበር መሆን የነበረብሽ ያለቦታሽ ገብተሸ ነው የኛን ስራ የምትሻሚው »

"ሌክቸር አይባልም ራኪሌክቸረር ነው የሚባለው"

"እንኳን እሰይ…ምንም ይባል ብቻ ለማለት የፈለኩት ገብቶሻል»

"ዛሬ እስኪበቃኝ ተፈላሰፍኩብሽ አይደል ራኪ የኔ ቆንጆ?»

"እንዴ ቀላል! ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ነው ማርያምን…» ቡና አዘዘች፡፡ እኔ የጉንፋን ስሜት ስለተሰማኝ ካልዲስ እስፔሻል” አዘዝኩ፤
ራኪ ለተወሰነ ሰዓት በሀሳብ ከጠፋች በኃላ…

"ሮዚ እንድ ነገር ልጠይቅሽ እንደማትቀየሚኝ ቃል ግቢልኝ…?»

"እንዴ ራኪ... ከመች ጀምሮ ነው ደሞ አንቺን የምቀየመው? Come on! እንደሱ ስትይ አያምርብሽም እሺ!»

"...ምን መሰለሽ! እም…ተይው ባክሽ…ዝምብሎ የሸሌ ወሬ ነው!" ሆዴን
👍41🔥1
#እኔ_ላንቺ_ማለት

ከሬሳዎች መሀል ወድቆ የተገኘ፣
በጣም የረከሰ ሞቱን የተመኘ፣
ሁሉም የጠየፈው ህሊናውን ሽጦ፣
ባዶውን የቀረ መንፈሱ ተሟጦ፣
ተጠሪ የሌለው ትብያ የወደቀ፣
ወኔው እንደከዳው ጉልበቱ የደቀቀ፣
ሳይወለድ ሞቶ ሳይጀምር ያለቀ፣
በጣም ተራ ሰው ነኝ፡
ምንም የማልረባ፣
ላንቺ የማልመጥን ከቁብ የማልገባ፣
...በኔ መጠየቅሽ አካልሽ ተሳቆ፣
ዕርኩስ እንደነካው ውስጥሽ ተሸማቆ፣
እኔን ላለማየት ህይወትሽ ቢርቅም፣

ጠልቼሽ አላውቅም።

🧿 እሱባለው ብዙነሽ… 🧿
#እኔ_እሷና_እሱ


#በሕይወት_እምሻው


#ማስታወቅያ

እንደሚታወቀው አባል ለመጨመር በምናደርገው ማስታወቅያ አትሰልቹ እባካችሁ እኔ በቀን ውስጥ #post የማደርግበትን ሰአት በቻልኩት መጠን ሁሌ ተመሳሳይ #ሰዓት ላይ ለማድረግ እሞክራለው እናንተም ያቺን ሰዓት ለመከታተል እንዲያመቻችሁ ያዙልኝ #ምርጦቼ በተረፈ መልካም #ንባብ
።።።።።።።
አዲስ ፀባይ ካመጣች ሰነባበተች፡፡
ስሙን ለመጥራት ሰበብ መፈለግ እስክታቆም ወደዋለች።
ይሉኝታዋን እንደ ቆሻሻ ልብስ እስክታወልቅ ልቧን ሰጥታዋለች::
ፍቅር ይሉኝታ ያስጥል የለ? ምን ይሉኝ ፍርኀትን ይገፍ የለ?
እህ... እንደሱ፡፡

የጀማመራት ሰሞን፣ “በረከት እኮ... ሂ ኢዝ ሶ ስማርት... እኛ ቢሮ የሚቆይ አይመስለኝም... ማስተርሱን ይጨርስ እንጂ ዩኤን ይጋደሉበታል... እጁን ስመው ነው የሚቀበሉት”

“ባለፈው ከነ በረከት ጋር ሄድንበት ያልኩህ ካፌ ትዝ ይልሃል? እዚያ ውሰደኝ...”

“በረከት እኮ ካለ ቶሞካ ቡና አይጠጣም...እስቲ አንተም የዚህን
የመንደር ቡና ተውና እዛ ጠጣ...”

“እስቲ ይሄን ዲኦ ተቀባው... የዛሬ ወንዶች እኮ ካለዚህ አይቀቡም ... አሽተውማ... ወንዳ ወንድ ሽታ... ደስ አይልም?”
እያለች ነው የጀመረችው።
አብረን ብዙ ቆይተናል፣ ብዙ ነገሬን አስታምማ ነው የምትኖረው፡እወዳታለሁ፣ “ከእሷ የተሸለ ሴት አላገኝም” እያልኩ ተውኳት፡፡ አለ አይደል... ሲጋራ አጨሳለሁ፤ ጫት እቅማለሁ እጠጣለሁ...
ትወቅ አትወቅ አላውቅም እንጂ ሌላ ሴት ጋር ሄጄም ዐውቃለሁ...
ቢሆን እንደ ሌሎች ሴቶች፣ “ተው...” እያለች አተነዘንዘኝም... “ከነምናምኔ ትወደኛለች...” እያልኩ፡፡

የሚያልፍ ነገር ይሆናል. ትረሳዋለች.. ብዬ ተውኳት፡፡ እሷ ግን ባሰባት፡፡ ስሙን በየቦታው ከመሰንቀር ዘልላ፣ በሐሳብ በመንፈሷ ተሸክማው ትገባና ትወጣ ጀመር፡፡

ሳምንታት ሲያልፉ ነገሩ አድጎ ይሰረስረኝ፤ ይገዘግዘኝ ጀመር፡፡ሁለመናዋ ይቀየር ጀመር፡፡

አንዱን እሑድ ምሽት፣ መጽሐፌን ትቼ አስተውላት ነበር፡፡ አብረን
መኖር ከጀመርን ሦስት ዓመታትን ስላለፈን የምሽት - የቀን የአዘቦት ድርጊቷን ቅደም ተከተሉ ሳይዛነፍ ዐውቀዋለሁ፡፡ ሳምሪ ግዴለሽ ሴት ናት፡፡ ጸጉሯን በየሳምንቱ የውበት ሳሎን ሄዳ
የማታቃጥል፣ ልብሷን ተኩሳ የማትለብስ፣ ኩልና ቻፒስቲክ የሜክአፕ ጥግ የሚመስላት፣ አዲስ ልብስና ጫማ በቀጠሮ የማትገዛ ግዴለሽ ሴት ናት፡፡

ያን ማታ ስታደርግ ያየሁት ነገር፣ እንግዳ የሆነብኝ ለዚህ ነው፡፡
በመተኛትና በመቀመጥ መሃል ሆኜ መጽሐፍ የማነብበት አልጋ ጫፍ ላይ ዕይቼ የማላውቀውን፣ ቄንጠኛና ውድ የሚመስል ፓንት ከመሳዩ ጡት መያዣ ጋር ዘርግታ፣ ልክ ቢለበስ ምን
እንደሚመስል በሚያሳይ ሁኔታ ለረጅም ደቂቃዎች ታየዋለች፡፡ ከዚያ ደግሞ ሁለቱንም ታነሳና፣ ጡት መያዣውን ባደረገችው አሮጌ
የሌሊት ካናቴራ ላይ ደርባ፤ ፓንቱን ደግሞ በተግባቢው ቦታ ላይ፣በሁለት እጆቿ ደገፍ አድርጋ መስታወት ታያለች፡፡
“አዲስ ነው አይደል ይሄ ነገር....?” አልኳት፣ ትኩረቷን ለመስበር፡፡

“እ...?” አለች፣ ፓንቱን ወደ አልጋው ጥላ፣ ከነጡት መያዣዋ ወደ
እኔ እየዞረች፡፡

“ፓንቱና ጡት መያዣው... አዲስ ነው ወይ..?” ራሴን ደገምኩ፡፡

“እ... አዎ... ያምራል አይደል?”

“አዎ... ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ስታደርጊ ዐይቼሽ አላውቅም...
ነይ እስቲ...” አልኳት፣ መጽሐፌን ወደ አንደኛው የአልጋው ጥግ ወርውሬ ቀኝ እጄን ዘርግቼ... መጣች፡፡

“ለኔ ነው...?” ፈገግ ብዬ ጠየቅኩ፡፡

“ሃ.ሃ... ታዲያ ለማን ይሆናል...?” እጆቼን ይዛ መለሰች፡፡

“ልበሺውና ልየዋ...”

“አይ... ለነገ ነው ... ማታ ታየዋለህ ...”

ተስፈንጥራ ወደ ቁምሳጥኑ ሄዳ ልብሶቿን አለቅጥ ማተራመስ ጀመረች፡፡

“ምነው...? ምን ሆንሽ...?” አልኩ፣

ባካሄዷ ድንገተኝነት ተገርሜ፡፡
“አይ... ለነገ ልብስ ልምረጥ... ጠዋት መተራመስ አልፈልግም...”

ነገ ስለምትለብሰው ልብስ ስትጨነቅ ዐይቻት አላውቅም፡፡ ጠዋት
ላይ፣ እጇ የገባውን ልብስ አድርጋ፤ እንደነገሩ ሆና እንደምትወጣ
ነው የማውቀው፡፡

ለአፍታ የረሳሁት ጥርጣሬ ሆዴ ውስጥ ተገላበጠ፡፡

ያ ሁሉ ግዴለሽነትዋ የት ገባ? ያልፋል ያልኩት ተባራሪ ስሜቷ መቼ ሥር ሰድዶ ባሕርይዋን መቀየር ጋር ደረሰ? ያን ቀን ነገር እያላመጥኩ አድሬ ነጋልኝ፡፡

ሲነጋ፣ ከጠዋቱ አንድ ሰዐት አልፎ በታክሲ አናገኝም ጭንቀት ተሰቅፌ፣ ቶሎ እንውጣ እያልኩ እማጸናታለሁ፡፡

“ረፈደ ሳምሪ... ቶሎ በይ...”

“በናትህ ልብሴ ሁሉ አስጠላኝ...”

“ትላንት መረጥኩ አላልሽም?”

“አዎ ግን አስጠላኝ...”

“ያ ስኩዌር ስኩዌሩ ሱሪሽ አሪፍ አይደል? እሱን ልበሺ ሳምሪ...”

“አንተ ደግሞ... እሱ በጣም ሰፊ ነው...”
“ሰፊ ልብስ የምትወጂ መስሎኝ?”

“እወድ ነበር አዎ... ግን ሰፊ ልብስ ይበልጥ ያወፍርሻል ብሎኛል..

ማለቴ ብለውኛል... ጓደኞቼ”

ተንተባተበች፡፡ ሲጋራ ልለኩስ በረንዳ ወጣሁ፡፡

የሁለት ሲጋራ ዕድሜ ጠበቅኳት፡፡ አልወጣችም፡፡ በጥልቅ ተነፈስኩና ወደቤት ገባሁ፡፡

"ሳምሪ!”

“ጨርሻለሁ!”

እየተንደፋደፈች ሁሉ ነገሯን አጣብቆ ይዞ፣ ጾታዋን በአንድ ዕይታ ብቻ የሚያረጋግጥ እጅግ ጠባብ ቢጫ ሱሪ ለብሳለች፡፡
ዐይቼው አላውቅም፡፡

ጸጉሯን ሙልጭ አድርጋ አሲዛዋለች፡፡

ይሄንንም አላውቀውም፡፡

ማታ ያየሁት ጡት መያዣዋ ጫፍ ከለበሰችው ነጭ ሹራብ አፈንግጦ ይታያል፡፡ ይሄንንም አልለመድኩትም፡፡

ያለ ቦታዋ የምትወድቅ አንዲት ዘለላ ጸጉር እስክትረብሻት ድረስ፣
ተጨንቃና ተጠባ፣ ያመለጡ ጸጉሮች እንደሌሉ ለማረጋገጥ ጸጉሯን ትሞዥቃለች፡፡ ከኩል ውጪ የማታውቀው ሚስቴ... በሜክአፕ ተዥጎርጉራ የአውሮፓ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊ መስላ መጥታለች፡፡

“ምንድነው ዛሬ እንደዚህ ለየት ያልሽው?” አልኩ፣ ታክሲው መጠበቂያው ጋር ስንደርስ፡፡

“ስብሰባ አለን... እኔ፣ ቃልኪዳንና በረከት፤ ስብሰባ አለን..."

በረከት....!

ጥርሴን እያንገጫገጭኩ ታክሲ ውስጥ ገባሁ፡፡
****
በዚያ ሳምንት ቅዳሜ ጠዋት ለአራተኛ ጊዜ ቃልኪዳንና በረከት ቤታችን እንደሚመጡ ነገረችኝ፡፡

“ያው እንዳልኩህ በረከትም ይመጣል... ስምንት ሰዐት ነው የሚደርሱት... ጥቁር ስንዴ ዳቦ እወዳለሁ ሲል ስለነበር እሱን
ከባልትናው ቤት አዝኜለታለሁ... ማለቴ ቃልም ስለምትወድ...ይዤ እመጣለሁ ... ልጅቷን ቤቱን በጠዋት መጥተሽ አጽጂ ብያት ነበር... የት አባቷ ናት በናትህ?...”

ለስምንት ሰዐት ቀጠሮ፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰዐት ተኩል ላይ ምን እንዲህ እንደሚያደርጋት ዐውቃለሁ፡፡

ድፎ ዳቦው... ጽዳቱ... ለወትሮው ከሰዐት የምትመጣውን ተመላላሽ
ሰራተኛችንን በሌሊት ድረሺ ማለቱ... ከሁለት ቀን በፊት የተጀመረው ባለ ስድስት ወጡ ድግስ...ግልጽ ነበር፡፡

ዳቦውን ይዛ ስትመጣ ሦስት ሰዐት አልፎ፣ ልጅቱም መጥታ ጽዳቱን አጧጡፋ ነበር፡፡

ስምንት ሰዐት ከሩብ ሆነ፡፡
ተሞልጮ የታሰረ ጸጉሯን ዐሥር ጊዜ እየነካካች፣ ጥብቅ ያለ ቀሚሷ
ያወጣውን ሞላላ ቂጧን ሠላሳ ጊዜ በመስታወት እያየች፣ በሜክአፕ
ያበደ ፊቷን መቶ ጊዜ እያስተካከለች፣ በመቁነጥነጥ ስትጠብቅ ቆይታ ስምንት ከሩብ ላይ በራችን ተንኳኳ፡፡

ሚስቴን ሳይነጥቀኝ የወሰደውን፣ ሳይቀማኝ ያገኛትን ሰው ላየው ነው፡፡ ፍቅሬን አጠገቤ እያለች እንቁልልጭ ያደረገብኝን ሰው ልተዋወቀው ነው፡፡

በሩን ከፍታ ቃልኪዳንን (በኔ ግምት ብቻውን መጣ እንዳይባል የገባች ሰበብ ናት) ካቀፈቻት በኋላ
👍5
#የይቅርታ_ልክ

#አንቺ
በፍቅር ገለሽኝ ገንዘሽ ቀብረሽኝ
አፈር አልብሰሽኝ ሔደሻል ትተሽኝ።
ነፍሴ ፤
በፈጣሪዋ ዘንድ
አትሙት ያላላት የተሰጣት ክብር
ዳግም ነፍስ ዘርታ
ሞትሽን ድል ነሳች ወጣች ከመቃብር፡፡
#እኔ
ከጥልቁ ጉድጓድ በነፃነት ወጣህ-
ያለሽበት ድረስ ልፈልግሽ መጣሁ፡፡
እኔ እንደአንቺ አይደለህ
ስለፍቅር ብዬ ይቅር ብዬሻለሁ፡፡
ልቤንም አፅድቼ
እጆቼን ዘርግቼ
እንደድሮ ላቅፍሽ መንገድ ጀምሬያለሁ፡፡
አደራ ፍቅርዬ
ደመ ነብስሽ ነግሮሽ
ድንገት ቀና ብለሽ ስትመለከቺ
ከርቀት ብታዪኝ ስመጣ ወደ አንቺ ፤
ሙት መንፈስ መስዬሽ እንዳ ደነግጪ
ይኸውልሽ ካላመንሽ ቆይ እጅሽን አምጪ
ደረቴ ሥር አርገሽ
የልብ አመታቴን ከልብሽ አድምጪ
መላው አካላቴን
ዳብሰሽ በጣቶችሽ ዳሰሽ አረጋግጪ፡፡
እኔው እራሴ ነኝ!
ያጠፋሁት ካለ
ለሠራሁት ስህተት ፍቅሬ ይቅር በይኝ
ይቅርታ ቢስ ከሆንሽ
በይ እንደለመድሽው ካሰኘሽ ግደዪኝ፡፡
እሞትልሻለሁ!
እንዳንቺ አይደለሁም በፈጣሪ አምናለሁ።
ሞትሽን ድል ነስቼ ዳግም እነሳለሁ።
ሺ ጊዜ ብትገዪኝ
እልፍ አዕላፍ ጊዜ ይቅር እልሻለሁ ፤
ምክንያቱም ፍቅሬ
በንፁህ ልቦና እኔ አፈቅርሻለሁ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#አንቺ_እና_እኔ

#አንቺ
“ጠፊ አላፊ ናቸው ጥላቻና ውበት
ግና ግና
ሕያው ሆኖ ኗሪ ምንግዜም ባለበት
ገንዘብ ማይረታው
ሁኔታ ማይፈታው
ሥፍራ ማይቀይረው ዕድሜ ማይጫጫነው
ፅኑ አምድ በዓለም በፍቅር ማመን ነው፡፡”

#እኔ

ስትዪኝ አምኜ
“ገዳሜ ነሽ ብዬ ባንቺ ሥር መንኜ
እንደጥላሽ ሆኜ
ስትሔጅ ስከትልሽ
አልቅስ አልቅስ ሲለኝ ደስ ደስ ሲልሽ
እንደሰው ኖርሽብኝ፤ እንደሰው ኖርኩልሽ፡፡
አንቺ- እንቆልልህ!.. እኔ - ምናውቅልሽ!..

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#እኔ_እና_አንቺ

ሒሳብ ፣ ስሌት ፣ ቀመር
ስሜት ፣ እውነት ፣ ፍቅር

አንድ እኔ ማንነት . . .
ዜሮ አንቺነትሽን ቆሞ ይጠብቃል
ከዜሮ ማንነት ዕጥፍ ይሠንቃል።

( የት ነሽ ብዙነቴ . . . ?)

ዕወቂኝ ልወቅሽ ፤ በድንቅ ሕገ ሐሳብ
0ጥልቂኝ፣ ታጠቂኝ ፤ በመዋሐድ ሒሳብ።
ዜሮ ነሽ አንድ ነኝ ፤
በዕብሮነት መንገድ
ነይ አብረን እንገኝ።

የሕይወት ውብ እውነት ፣ የሙሉነት ምስጢር
አንድ ከዜሮ ጋር ፣ ሲቆም ሲሰባጠር።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍31
#እኔ

እመስላችሁ ዘንድ አትሹ
እመስላችሁ ዘንድ አትትጉ

እኔ ...
እንደ ስሜቴ አዜማለሁ
እንደ እምነቴ አረግዳለሁ
በራሴ ምህዋር እዞራለሁ
በራሴ ጅረት እፈሳለሁ፡፡

የራሴን ዘውድ እደፋለሁ |
የራሴን መስቀል እሸከማለሁ
የራሴን ንፍጥ እጠርጋለሁ
የራሴን ቁስል አካለሁ:: :

እመስላችሁ ዘንድ አትሹ
እመስላችሁ ዘንድ አትትጉ

እኔ . . .
የታላቋ ነብስ መሪ ነኝ
የክቡር ህይወቴ ሹፌር፡፡

የማንም ፈረስ መሆን አልሻም
የማንም ጋሪ መሆን አልፈቅድም
የማንም ፊትአውራሪ አይደለሁም
የማንም ሰልፈኛ አልሆንም:: ..

እመስላችሁ ዘንድ አትሹ
እመስላችሁ ዘንድ አትትጉ
የልባችን ትርታ
የነብሳችን ሲቃ
አንድ አይደለምና
መንገዳችን ለየቅል ነው::

ትመስሉኝ ዘንድ አልሻም
ትመስሉኝ ዘንድ አልተጋም
እመስላችሁ ዘንድ አትሹ
እመስላችሁ ዘንድ አትትጉ፡፡

🔘መንግስቱ በስር🔘
#እኔ_ላንቺ

"ምርኩዝና ባላ ምሶሶም አይሻ
ሁሉን ይሸከማል ያ'ፍቃሪ ትከሻ"

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍94
#እኔ_እና_ቤቴ

‘ቤቴ’ የኪራይ ናት፡
ከወር ደመወዜ፣ በወር ምታስከፍል፤
እኔ’ ስደተኛ፡
በገዛ ሀገሬ፣ ‘ለገዛ ወገኔ’፣ ለቤት የምከፍል፤
ይኸው በኑሯችን፡
‘ቤቴ’ን አላምናትም፣ እርሷም አታምነኝም፣
አብረን እንኑር እንጂ፡
‹በየኔ ነው ስሜት›፣ ከቶ አንገናኝም፡፡
በእርሷ አልፈርድባትም፡
ድሮስ ስደተኛን፣ ማን አምኖ ያኖራል?
በእኔም አትፍረዱ፡
የራስ ያልሆነን ቤት፣ ማን አምኖ ይኖራል?
ይህን እናውቃለን፡
ፈጽሞ እንደማንችል፣ መኖር ተለያይቶ፣
እንዴትስ ይኖራል?
ቤት ሰው አልባ ሆኖ፣ ሰውም መኖሪያ አጥቶ፤
ዘመናችን ይህ ነው፡
አብረው እየኖሩ፣ አለመተማመን…
ቆይ ግን ምን ነክቶናል?
መለያየት ማንችል፣ አብሮነት ያመመን?

🎴መላኩ አላምረው🎴

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍25👏1
#እኔ_ላንቺ_ማለት

ከሬሳዎች መሀል ወድቆ የተገኘ፣
በጣም የረከሰ ሞቱን የተመኘ፣
ሁሉም የጠየፈው ህሊናውን ሽጦ፣
ባዶውን የቀረ መንፈሱ ተሟጦ፣
ተጠሪ የሌለው ትብያ የወደቀ፣
ወኔው እንደከዳው ጉልበቱ የደቀቀ፣
ሳይወለድ ሞቶ ሳይጀምር ያለቀ፣
በጣም ተራ ሰው ነኝ፡
ምንም የማልረባ፣
ላንቺ የማልመጥን ከቁብ የማልገባ፣
...በኔ መጠየቅሽ አካልሽ ተሳቆ፣
ዕርኩስ እንደነካው ውስጥሽ ተሸማቆ፣
እኔን ላለማየት ህይወትሽ ቢርቅም፣
....ጠልቼሽ አላውቅም።

🎴እሱባለው ብዙነሽ…🎴

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍22🥰6👏4
#እኔ_ጠላሻለሁ

እንደ ጫማ ሽታ

ልክ እንደ በሽታ

ጌታ በባርያው ላይ እንደ ሚበረታ

#እኔ_ጠላሻለሁ

እንደ ረጅም መንገድ

ለሀብታም እንደ መስገድ

ከጠጡ በኋላ እንደ መንገዳገድ

#እኔ_ጠላሻለሁ

ገንዘብ እንደ ማጣት

ዳገት እንደ መውጣት

ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት

#እኔ_ጠላሻለሁ

ልክ እንደ መልከስከስ

እምነት እንደ ማርከስ

ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ

እኔ ጠላሻለሁ . . . (ወዘተ )

አሁን ግን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል ጠላሁሽ ያበዛሁ #ወድጄሽ ነው መሰል፡፡

🔘እዮብ🔘
30👍27😁10👏4
#እኔ
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም

#እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ

#እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)

#እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3215🔥3