አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
503 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እኔ #እምፈልገው

እውነት ለመናገር እኔ ምፈልገው
ካንቺ ጋር መጋባት
ይህን ሀምሌ ፊቴን : ደጋግሞ ማራባት
ከወፎች ጋር መንቃት : በጊዜ ቤት መግባት::
"ምንም ደሃ ቢሆን: ባይኖረውም ሀብት
ከደጃፍ ሲቀመጥ: ደስ ይላል አባት"
ለሚል መናኛ ጥቅስ: ኑሮየ ማይመጥን
ሲሻኝ በየባንኩ: ስፈልግ በሳጥን
የተረፈኝ ገንዘብ
ደጃፍ ላይ ቁጭ ብየ: ድሀ የምታዘብ
ተምሳሌትነቴ የሚዳረስ ባለም
ሞዴል አባወራ ተብየ ምሸለም
አገሬን ማስከበር
ህዝቤን ማስተባበር
የልጅ ልጅ አፍርቼ
በመቶ አመት ሙቼ
ስላሴ መቀበር
ምኞቴ ይህ ነበር::
እውነት ለመናገር እኔ እምፈልገው
ወንደላጤ ኑሮ
በሴቶች መታጀብ : ልክ እንዳውራ ዶሮ
ጊዜ ጥሎኝ ቢሄድ : ቀን ቢገሰግስም
መላው ጭንቅላቴ : ገብስማ ቢለብስም
ላቅማዳም ነው እንጂ: ለትዳር አልደርስም::
ደሞ
ዘር መዝራት እርሜ ነው : ደጋግሜ ባርስም
ባለመኖር ላሉት: ስቃይ አላወርስም
ቢፈልግ ሌላው ህዝብ
ይፈልፍል እንደዝንብ
ይባዛ እንደንጉዳይ
አገር ስራው ያውጣው! ሰው የራሱ ጉዳይ!!
የራሴ ፈጣሪ- ነኝ የራሴ ገዳይ!!
እኔ እምፈልገው...
እኔ እምፈልገው..
እኔ እምፈልገው
-----------
ገንዘብ ቢመዘበር: በገንዘብ ይተካል
እድሜ ለጉልበትሽ : በላቡ ለሚያድር
በውርስ በስጦታ : ግፋ ቢል በብድር::
በቆጠብነው ቁጥር
ጊዜ ነው የሚያጥር
እድሜ ነው የሚያልቀው
የምንፈልገውን በቅጡ ሳናውቀው::
👉በውቀቱ ስዩም
👍1