#የይቅርታ_ልክ ፩
#አንቺ፤
በፍቅር ገለሽኝ ገንዘሽ ቀብረሽኝ
አፈር አልብሰሽኝ ሔደሻል ትተሽኝ።
ነፍሴ ፤
በፈጣሪዋ ዘንድ
አትሙት ያላላት የተሰጣት ክብር
ዳግም ነፍስ ዘርታ
ሞትሽን ድል ነሳች ወጣች ከመቃብር፡፡
#እኔ፣
ከጥልቁ ጉድጓድ በነፃነት ወጣህ-
ያለሽበት ድረስ ልፈልግሽ መጣሁ፡፡
እኔ እንደአንቺ አይደለህ
ስለፍቅር ብዬ ይቅር ብዬሻለሁ፡፡
ልቤንም አፅድቼ
እጆቼን ዘርግቼ
እንደድሮ ላቅፍሽ መንገድ ጀምሬያለሁ፡፡
አደራ ፍቅርዬ
ደመ ነብስሽ ነግሮሽ
ድንገት ቀና ብለሽ ስትመለከቺ
ከርቀት ብታዪኝ ስመጣ ወደ አንቺ ፤
ሙት መንፈስ መስዬሽ እንዳ ደነግጪ
ይኸውልሽ ካላመንሽ ቆይ እጅሽን አምጪ
ደረቴ ሥር አርገሽ
የልብ አመታቴን ከልብሽ አድምጪ
መላው አካላቴን
ዳብሰሽ በጣቶችሽ ዳሰሽ አረጋግጪ፡፡
እኔው እራሴ ነኝ!
ያጠፋሁት ካለ
ለሠራሁት ስህተት ፍቅሬ ይቅር በይኝ
ይቅርታ ቢስ ከሆንሽ
በይ እንደለመድሽው ካሰኘሽ ግደዪኝ፡፡
እሞትልሻለሁ!
እንዳንቺ አይደለሁም በፈጣሪ አምናለሁ።
ሞትሽን ድል ነስቼ ዳግም እነሳለሁ።
ሺ ጊዜ ብትገዪኝ
እልፍ አዕላፍ ጊዜ ይቅር እልሻለሁ ፤
ምክንያቱም ፍቅሬ
በንፁህ ልቦና እኔ አፈቅርሻለሁ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#አንቺ፤
በፍቅር ገለሽኝ ገንዘሽ ቀብረሽኝ
አፈር አልብሰሽኝ ሔደሻል ትተሽኝ።
ነፍሴ ፤
በፈጣሪዋ ዘንድ
አትሙት ያላላት የተሰጣት ክብር
ዳግም ነፍስ ዘርታ
ሞትሽን ድል ነሳች ወጣች ከመቃብር፡፡
#እኔ፣
ከጥልቁ ጉድጓድ በነፃነት ወጣህ-
ያለሽበት ድረስ ልፈልግሽ መጣሁ፡፡
እኔ እንደአንቺ አይደለህ
ስለፍቅር ብዬ ይቅር ብዬሻለሁ፡፡
ልቤንም አፅድቼ
እጆቼን ዘርግቼ
እንደድሮ ላቅፍሽ መንገድ ጀምሬያለሁ፡፡
አደራ ፍቅርዬ
ደመ ነብስሽ ነግሮሽ
ድንገት ቀና ብለሽ ስትመለከቺ
ከርቀት ብታዪኝ ስመጣ ወደ አንቺ ፤
ሙት መንፈስ መስዬሽ እንዳ ደነግጪ
ይኸውልሽ ካላመንሽ ቆይ እጅሽን አምጪ
ደረቴ ሥር አርገሽ
የልብ አመታቴን ከልብሽ አድምጪ
መላው አካላቴን
ዳብሰሽ በጣቶችሽ ዳሰሽ አረጋግጪ፡፡
እኔው እራሴ ነኝ!
ያጠፋሁት ካለ
ለሠራሁት ስህተት ፍቅሬ ይቅር በይኝ
ይቅርታ ቢስ ከሆንሽ
በይ እንደለመድሽው ካሰኘሽ ግደዪኝ፡፡
እሞትልሻለሁ!
እንዳንቺ አይደለሁም በፈጣሪ አምናለሁ።
ሞትሽን ድል ነስቼ ዳግም እነሳለሁ።
ሺ ጊዜ ብትገዪኝ
እልፍ አዕላፍ ጊዜ ይቅር እልሻለሁ ፤
ምክንያቱም ፍቅሬ
በንፁህ ልቦና እኔ አፈቅርሻለሁ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘