#አንቺ_እና_እኔ
#አንቺ ፤
“ጠፊ አላፊ ናቸው ጥላቻና ውበት
ግና ግና
ሕያው ሆኖ ኗሪ ምንግዜም ባለበት
ገንዘብ ማይረታው
ሁኔታ ማይፈታው
ሥፍራ ማይቀይረው ዕድሜ ማይጫጫነው
ፅኑ አምድ በዓለም በፍቅር ማመን ነው፡፡”
#እኔ
ስትዪኝ አምኜ
“ገዳሜ ነሽ ብዬ ባንቺ ሥር መንኜ
እንደጥላሽ ሆኜ
ስትሔጅ ስከትልሽ
አልቅስ አልቅስ ሲለኝ ደስ ደስ ሲልሽ
እንደሰው ኖርሽብኝ፤ እንደሰው ኖርኩልሽ፡፡
አንቺ- እንቆልልህ!.. እኔ - ምናውቅልሽ!..
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#አንቺ ፤
“ጠፊ አላፊ ናቸው ጥላቻና ውበት
ግና ግና
ሕያው ሆኖ ኗሪ ምንግዜም ባለበት
ገንዘብ ማይረታው
ሁኔታ ማይፈታው
ሥፍራ ማይቀይረው ዕድሜ ማይጫጫነው
ፅኑ አምድ በዓለም በፍቅር ማመን ነው፡፡”
#እኔ
ስትዪኝ አምኜ
“ገዳሜ ነሽ ብዬ ባንቺ ሥር መንኜ
እንደጥላሽ ሆኜ
ስትሔጅ ስከትልሽ
አልቅስ አልቅስ ሲለኝ ደስ ደስ ሲልሽ
እንደሰው ኖርሽብኝ፤ እንደሰው ኖርኩልሽ፡፡
አንቺ- እንቆልልህ!.. እኔ - ምናውቅልሽ!..
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘